Muhammed Computer Technology (MCT)
37.4K subscribers
530 photos
7 videos
254 files
916 links
🔴አድራሻ:-
ስ.ቁ: 0929273364
ዌብሳይት www.mctplc.com
ቴሌግራም አካውንት: https://t.me/mctplc
email: mct16plc@gmail.com
ቲክቶክ አካውንት tiktok.com/@mctplc
Download Telegram
Muhammed Computer Technology (MCT) pinned «አዲስ ዜና ይህ አዲስ የከፈትኩት የቴሌግራም ግሩፕ ነው እስካሁን እኔ የምለቃቸውን መረጃዎችን ብቻ ነበር የምትከታተሉት ግን ደግሞ ሁላችንም ሀሳባችንን የምንገልጽበት የምንወያይበት እውቀት ሼር የምንደራረግበት ግሩፕ ያስፈልገናል የሚል ሀሳብ ስላሰብኩ ይህንን ግሩፕ እንድትቀላቀሉ እጋብዛችኋለሁ። በዚህ የቴሌግራም ግሩፕ የተለያዩ ስለኮምፒውተር እንዲሁም ስለቴክኖሎጅ የሚነሱ ጥያቄዎችን የምንጠያየቅበት እና ጥያቄውን…»
ወደ መማሪያ ግሩፓችን አሁኑኑ ይቀላቀሉ
https://t.me/joinchat/KPglFhgByUl5eskmbeIsbA
ይህንን ሊንክ ቢያንስ ለ 10 ይጋብዙኝ በተረፈ እኔ መደረግ ያለበትነረ ቅድመ ሁኔታ እያዘጋጀሁ ነው ትምህርቱን ከመሰረታዊ የኮምፒውተር እውቀት ጀምሮ C++ C# JAVA PHP HTML CSS JAVASCRIPT SQL DATABASE MYSQL DATABASE...... ሌሎች ስለ ሞባይል አዳዲስ የማናውቃቸውን ነገሮች እንማርበታለን በደንብ ግሩፓችን መጠናከርና ወደ ትምህት እንገባለን
ኮምፒውተርዎን ፈጣን የሚያደርጉ 10 ዘዴዎች
1. ትላልቅ መጠን ያላቸውን ፎቶዎች ዎልፔፐር አይጠቀሙ፡፡
2. ሁሌም ኮምፒዩተሩ ከፍቶ ሳይጨርስ አፕሊኬሽን ለመክፈትም ሆነ ለመነካካት አይሞክሩ፡፡
3. አፕሊኬሽን ከዘጉ በሁዋላ ዴስክቶፑን ሪፍሬሽ ያድርጉ፤ ይህም ራም ሜሞሪን ነፃ ያደርጋል፡፡
4. የማይጠቀሙበት ሶፍትዌር ካለ ከኮምፒውተሩ ይሰርዙ (አን-ኢንስታል) ያድርጉት)፡፡
5. ዴስክቶፕ ላይ ፋይል አያስቀምጡ፤ ሾርትከትም መብዛት የለበትም፡፡
6. ኮምፒዩተሩ ሲከፈት በራሳቸው የሚከፈቱ ለምሳሌ: ስካይፕ አይነት አፕሊኬሽኖች ካሉ disable ያድርጉ
7. Recycle binን ሁሌም ባዶ ያድርጉ::
8. ሀርድ ዲስኩን ሁለት ፓርቲሽን ይፍጠሩለት፡፡
9. ብዙ ሶፍትዌሮችን ባንዴ አይክፈቱ::
10. Temp ውስጥ ያሉትን ፋይሎች በሙሉ ያጥፉ temp ለማግኘት የስታርት ምልክት(ኪቦርድ ላይ) እና R በአንድ ላይ ይጫኑ ከዛም RUN ይመጣላችኋል ከዛም %temp% ብለው OK ይጫኑ የሚመጣው ፎልደር ውስጥ ያለውን ፋይል ያጥፉት
ይህ መረጃ ለእርስዎ ጠቃሚ እንደነበረ ተስፋ አደርጋለሁ።
አመሰግናለሁ!
ስለኮምፒውተርና ቴክኖሎጅ ያለዎትን እውቀት ያሳድጉ ወደ ትምህርታዊ የቴሌግራም ግሩፕ በዚህ ሊንክ ይቀላቀላሉ https://t.me/joinchat/KPglFhgByUl5eskmbeIsbA
በቴሌግራሜ ቻናል ምርጥ ምርጥ ስለኮምፒውተር የምለቃቸውን መረጃዎችን ለመከታተል እንዲያመችዎ ይህንን ይጫኑ https://t.me/MuhammedComputerTechnology በቴሌግራም መከታተል ትችላላችሁ
በተጨማሪም በፌስቡክ ገፄ https://m.facebook.com/mameamin.6te.net ይህንን ሊንክ በመጫን ፔጁን like በማድረግ በፍጥነት መረጃ እንዲደርሳችሁ
ሼር ማድረጋችሁን አትርሱ
የፌስቡክ ፔጁን Like & share ያድርጉ
#ፔጄን_ላይክ ማድረግዎን አይርሱ
👍1
www.mameamin.6te.net ይህ የግሌ ዌብሳይት ነው ስለሆነም ጥሩ መረጃን በዚጅ ዌብሳይት ማግኘት ትችላላችሁ።
የግብፅ የአስዋን ግድብ እውነታዎች!!!
---------------
የጠቅላላ እወቀት ደረጃዎን ያሳድጉ ።
አወቆ መገኘት ብልህነት ነው።
አንብበው ለሌሎች ሼር ያድርጉ።
ግብጻውያን ‹‹የአስዋን ግድብ›› ያለፈው ክፍለ ዘመን ብርቱ
የድካማቸው ውጤት እና በታሪክ የመዘገቡት የሚኮሩበት
እና የሚመኩበት አንጡራ ሃብታቸው እንደሆነ ይናገራሉ፡፡
....
ግድቡ የተገነባው ከ1952 የግብጽ አብዮት በኋላ ነው፡፡
ግድቡ 111 ሜትር ከፍታና 3.8 ኪሎሜትር ርዝመት
አለው፡፡ 10 ቢሊየን kilowatt-hours በየአመቱ
የማመንጨት አቅም ያለው ሲሆን የግብጽ ሌሊቶች ከዚህ
በሚመነጭ የብርሃን ጎርፍ እየተጥለቀለቁ ከተሞቻቸው
ከቀን ጸሐይ ይልቅ በምሽት መብራቶች ያብረቀርቃሉ፡፡
...
ለዚህ የብርሃን ጎርፍ ማመንጫ ለግድቡ የተገጠሙት 12
ተርባይኖች ያለእንቅልፍ ይሽከረከራሉ፡፡ ልብ አድርግ 95
ፐርሰንት የግብጽ ህዝብ የሚኖረው የናይል ወንዝን ተከትሎ
20 ኪሎ ሜትር እንኳን ሳይርቅ ነው፡፡
...
ግድቡ በ1.2 ቢሊየን ዶላር ወጪ የተገነባ ሲሆን በወቅቱ
ምእራባውያን በማኩረፋቸው ገንዘቡ በቀጥታ የተገኘው
ከታላቋ ሶቭየት ህብረት ነበር (እነ አሜሪካ ለምን እንዳኮረፉ
በዚሁ ጽሁፍ መጨረሻ ላይ ታገኘዋለህ)፡፡
...
ግድቡ 33 ሺህ ስድሰት መቶ ስኩዌር ኪሎሜትር የሚሆን የምድር ስፋትን ለሚያዳርስ የመስኖ ልማት በቀጥታ ውሃ ያቀርባል፡፡
የግድቡን ሥራ በ1960 እ.ኤ.አ ያስጀመሩት ፕሬዝዳንት
ገማል አብድል ናስር ሲሆኑ የተጠናቀቀው በአስር አመት
ጊዜ ውስጥ ነው፡፡
...
የአስዋን ግድብ መገንባት በሱዳን እና በግብጽ መካከል እጅግ ማራኪ የሆነው የናስር ሐይቅ እንዲፈጠር አስችሏል፡፡ እንዲሁም የኑቢያ ሐውልቶች ጉዳት እንዳይደርስባቸውም ተከላክሏል፡፡
...
የግድቡ ዋናና እጅግ ቀዳሚ የሆነው ዓላማ እኛን ተሰናብቶ
እየጋለበ የሚሄደውን የአባይን (ናይል) ወንዝ እና
የሚያደርሰውን ጥፋት ለማስታገስ ብሎም ዓመቱን ሙሉ
በመላ የግብጽ ምድር ላይ ለሚከናወነው መስኖ ተኮር
የግብርና ልማት የተመጣጠነ የውሃ ፍሰት እንዲፈጠር
ለማድረግ ነው፡፡
...
ግድቡ የግብጽን የከርሰ ምድር ውሃ እንዲጨምርም
አስችሏል፡፡ ከግድቡ የሚመነጨው ከፍተኛ መጠን ያለው
የኤሌክትሪክ ኃይል በምድሪቱ ላሉ በርካታ ፋብሪካዎች
ለአፍታ የማይቋረጥ ጉልበት ሆኗቸዋል፡፡
...
ፖለቲካዊ አንድምታ ያለው የአስዋን ግድብ ያገሪቱ ህዝብ
በድህነት እንዳይናወጥ ያደረገ ሲሆን በበርካታ ኢኮኖሚያዊ
እንቅስቃሴዎቹ የግብጽን ወጣቶች የኢኮኖሚ ጥማት
የመለሰ ሲሆን የተፈጠሩ በርካታ የሥራ እድሎች የተረጋጋ
እና የተሻለ ህይወት እንዲመሩ አስችሏቸዋል፡፡(ልብ አድርግ
ኢትዮጵያ ውስጥ ተመርቀው ስድስት እና ሰባት አመት ስራ
ያላገኙ ወገኖች አሉህ)፡፡
...
በግድቡ ዙሪያ የተመጠኑ እውነታዎች
--------
1. ከ1970-1990ዎቹ እ.ኤ.አ ባሉት ጊዜያት የምስራቅ እና
የምእራብ አፍሪካ ሀገራት በድርቅ እና በረሃብ ሲናወጡ
እድሜ ለአስዋን ግድብ ግብጽ ያ ክፉ ቀን ጨረፍታውም
አልነካት፡፡(ይህንን የሚሉት እነሱ ናቸው)፤
...
2. ይህ ግድብ ‹‹አስዋን ሃይ ዳም›› በመባል የሚታወቅ
ሲሆን የመጀመሪያው ግድብ ‹አስዋን ሎው ዳም› በ1898
በእንግሊዞች ተጀምሮ በ1902 የተጠናቀቀው ነው፤
...
3. የግድቡ ሥራ በእንግሊዞች ታቅዶ በራሺያዎች ተሰርቷል፤
...
4. 90 ሺህ ኑቢያዎች ከመኖሪያ ስፍራቸው በ45
ኪሎሜትር እንዲርቁ ተደርገዋል፤
...
5. ግድቡ ሲገነባ አስር አመት ወስዶበታል (በወቅቱ
ቴክኖሎጂ)፤
...
6. በ1912 አድሪያን ዳኒኖስ የተባለ የግሪክ መሃንዲስ
ተመሳሳይ ግድብ ለመስራት ሃሳብ አቅርቦ የነበር ሲሆን
በወቅቱ የነበረው ንጉስ ፋሩቅ ሃሳቡን አልተቀበለውም፡፡
ይህንነ ለማድረግ የበረታው ፕ/ት ገማል አብድል ናስር
ነው፤
...
7. ግድቡ በዓመት 10042 ጊጋዋት የኤሊክትሪክ ሃይል
ያመነጫል፡፡
..
እነሱ ይህን ሁሉ ትሩፋት ከአባይ ወንዝ አግኝተው 70
ፐርሰንት በጨለማ ለሚማቅቀው እና በኩበት ጪስ
ለሚጨናበሰው (ያውም የውሃው ባለቤት ሆኖ፣ ያውም
በማይጎዳቸው መልክ ለመጠቀም እየተነገራቸው)
ለኢትዮጵያ ህዝብ ቅንጣት ታህል ርህራሄ አለማሳየታቸው
ይቀፋል፡፡
...
አስደማሚው ነገር ግድቡ ሊሰራ በታሰበበት ወቅት
ምእራባውያን በተለይ አሜሪካና እንግሊዝ በቀዝቃዛው
ጦርነት (የጂኦፖለቲካል ቀውስ) ውስጥ ከራሽያ ጋር
ሲነታረኩ በነበረበት ወቅት ገማል አብድል ናስር ላቀረቡት
ሃሳብ ስላልተገዛ የግድቡን መገንቢያ ገንዘብ ሲከለክሉት
በቼኮዝሎቫኪያ በኩል ተራምዶ ከራሽያ ጋር በመደራደር በ
2% ወለድ 1.2 ቢሊየን ዶላር ማግኘቱ ሲታወስ ነው፡፡ ያኔ
አሜሪካ ቆሽቷ እርር ብሎ ነበር፡፡ (ከላይ እንዳልኩህ
እነአሜሪካ ያኮረፉት በዚህ ነው)፡፡
...
ግድቡ ግብጾችን ጎዳቸው ከተባለ በቀንድ አውጣ ሸክም
የሚመጣው <ስኪስቶሶሚያሲስ> የተባለው ፓራሳይት
የሚያስከትለው ብለድ ኢንፌክሽን ብቻ ነው፡፡ ለዚህም ኪኒኒ
እየዋጡ ነው፡፡ መድሃኒቱን ደግሞ ያገኘላቸው ጅጅጋ
የተወለደው የሀገርህ ልጅ ዶክተር አክሊሉ ለማ ነው፡፡
የበሽታው ሌላ ስም ቢልሃርዚያ ነውና፡፡
...
ሲጠቃለል፡- ውሃው የበረሃው ሙቀት ከሚበላው እኛጋ
መቆየቱ ጠቃሚ እንደሆነ በ1950ዎቹ የነገራቸው
የእንግሊዙ መሃንዲስ ሃሮልድ ኤድዊን ነው፡፡ እንዲሁም
የህዳሴው ግድብ በናስር ሃይቅ እና በናይል ወንዝ
የሚከማቸውን ደለል በመቀነስ እጅግ እንደሚጠቅማቸው
ቢነገራቸውም ለማዳመጥ የፈለጉ አይመስልም፡፡
via social medias
አዲስ ዜና ይህ አዲስ የከፈትኩት የቴሌግራም ግሩፕ ነው እስካሁን እኔ የምለቃቸውን መረጃዎችን ብቻ ነበር የምትከታተሉት ግን ደግሞ ሁላችንም ሀሳባችንን የምንገልጽበት https://t.me/joinchat/KPglFhgByUl5eskmbeIsbA
የምንወያይበት እውቀት ሼር የምንደራረግበት ግሩፕ ያስፈልገናል የሚል ሀሳብ ስላሰብኩ ይህንን ግሩፕ እንድትቀላቀሉ እጋብዛችኋለሁ።
በዚህ የቴሌግራም ግሩፕ የተለያዩ ስለኮምፒውተር እንዲሁም ስለቴክኖሎጅ የሚነሱ ጥያቄዎችን የምንጠያየቅበት እና ጥያቄውን እርስ በእርሳችን የምንመልስበት እንዲሁም ስለኮምፒውተር ያለንን እውቀት የምናዳብርበት ግሩፕ ነው። ወደ ቴሌግራማችን ሌሎች እንዲቀላቀሉ ይጋብዙ ይህንን ሊንክ በመጫን መቀላቀል እንዲሁም ምርጥ ምርጥ ሀሳባችሁን እውቀታችሁን እንከፋፈልበት
https://t.me/joinchat/KPglFhgByUl5eskmbeIsbA
🤔1
ካሜራ ከመግዛት በፊት ማየት ያለብን ነጥቦች
አፔቸር(aperture)
በኦፕቲክስ አፔቸር (optics aperture)ማለት ብርሃን የሚጓዝበት ቀዳዳ ወይም ፎቶ ሌንስ ቀዳዳ ሲሆን ቀዳዳው በተለያየ መጠን ብርሃን ማስገባት የሚችል ብቃት አለው። የብርሃን ምጣኔው የሚቆጣጠረው አፈሙዝ ስፋት ሲኖረው ለፎቶ በሚመጥን የብርሃን ምጣኔ በመፍቀድ የፎቶውን የብርሃን ተጋላጭነት (exposure) ይቆጣጠራል። አፔቸር የሚለካው በኤፍስቶፕ(f/
stops) ሲሆን ከ 1.4 እስክ 16 ድረስ ነው። ኤፍስቶፕ ባነሰ ቁጥር ፎቶው ድምቀት ይኖርዋል በተቃራኒው ቁጥሩ በጨመረ ግዜ የፎቶው ድምቀት ወይም ብርሃን መጠን ይቀንሳል።
ISO
አፔቸር በካሜራችን ውሰጥ የሚገባውን የብርሃን መጠን መቆጣጠሪያ ሲሆን አይሶ ደግሞ የፎቶውን መጨለም እና መብራት ይቆጣጠራል። ይህ ማለት የካሜራው ሴንሰር ምንያህል ብርሀን ማስቀመጥ ይችላል ማለት ነው። የአይሶ ቁጥር በጨመረ ቁጥር የፎቶ ግራፉ ድምቀት እየጨመረ ይመጣል በተቃራኒው የአይሶ ቁጥር ሲያንስ ፎቶግራፉ የመጨለም ባህሪ ያሳያል። በዚህ ምክንያት አይሶ ለማታ ፎቶዎች ወይም በቂብርሃን በሌለበት ወቅት ጥሩ ፎቶግራፍ እድናነሳ ይረዳል። አሁን ያሉት ካሜራዎች ISO ሃይላቸው ከፍተኛ በመሆኑ የተነሳ በትንሽ ብርሀን ማለትም በትንሽ የሻማ ብርሀን ከፍተኛ የፎቶግራፍ ጥራት ማንሳት ተችሏል። ትንሽ ISO ማለት ሴንሰሩ ትንሽ ብርሀን የመያዝ አቅም አለው ማለት ሲሆን ትልቅ ISO ማለት ሴንሰሩ ትልቅ ብርሀን የመያዝ አቅም አለው ማለት ነው ። አሁን ያሉ ካሜራዎች ከ100 እስከ 3000 በላይ ISO መጠን አላቸው።
ካሜራ ሸተር (Camera Shutter)
በያንዳንዱ ካሜራዎች ውስጥ የተለያዩ ክፍሎች ሲኖር ከዛ ውስጥ አንዱ ሌንስ ይባላል። ሌንስ (መስታያት ካሜራ) ካሜራ ውስጥ ያለ አካል ሲሆን ብርሃንን በማተኮር ወይም የመበተን ስራን ይሰራል።ሸተር ካሜራ ውስጥ የሚገኘ ሲሆን በካሜራ ሴንሰሩ ፊትለፊት የሚገኝ መጋረጃ መሰል ነው። ይህ መጋረጃው ካሜራው ፎቶ ሲያነሳ ይከፈታል። ካሜራው ፎቶ በሚያነሳበት ግዜ ሸተሩ በደንብ በመከፈት የተቻለውን የብርሀን መጠን በማስገባት ካሜራ ሴንሰር በማሳረፍ ፎቶ ለመፍጠር በቂ ብርሃን ካገኘ በሁሃላ ሸተሩ ይዘጋል።ሸተር ስፖድ ማለት የካሜራው ሸተር የሚከፍት የግዜ ርዝመት ማለት ነው። ይህ ማለት የካሜራ ሴንሰሩ በምን ያህል ግዜ ውስጥ የካሜራ ሴንሰር ለብርሃን ይጋለጣል ማለት ነው። ወይም ካሜራው ፎቶ ለማንሳት የሚወስድበት ግዜ ማለት ነው።
ረዥም ሸተር ስፒድ በምንጠቀምበት ግዜ ሴንሰሩ ለከፍተኛ ብርሃን ይጋለጣል በዚህ ግዜ ፎቶው ደብዛዛ ይሆናል። ረዥም ሸተር ስፒድ ባለግዜ ተንቀሳቃሽ ነገሮች በፎቶ ላይ ደብዛዛ ይሆናሉ።ብዙ ግዜ በመኪና ማስታወቂያ ለይ የመኪናው ፍጥነት እዳለው ለማስመሰል እንጠቀማለን። አጭር ሸተር ስፒድ ተጠቀምን ማለት ደግሞ ሴንሰሩ ለተወሰነ ግዜ ብቻ ለብርሃን ተጋለጠ ማለት ሲሆን ይህ ማለት ቅዝፈታዊ ፎቶዎች ማንሳት ይቻላል። ሸተር ስፒድ ትንሽ ከሆነ የፎቶግራፍ የመደብዘዝ ሁኔታ ይቀንሳል። ለምሳሌ በፍጥነት የሚያለፍ እቃን በ1/30 ሰከንድ እና በ1/200 ሰከንድ ፎቶ ብናነሳ 1/30 ሰከንድ ፎቶግራፍ ደብዘዝ ያለ ሲሆን 1/200 ሰከንድ ደግሞ ቀጥያለ ወይም ያልደበዘዘ ፎቶ ይወጣወል።
ሜጋፒክስል
ሜጋፒክስል ማለት የሚሊዮን ፒክስል ጥርቅም ነው። ፒክስል ደግሞ የዲጂታል ምስል የሚገኘ አካል ሲሆን የምስሉ አነስተኛ መለኪያ ነው። ፒክስልን እንደ ነጥም ማሰብ ይቻላል። ነጥብ ተሰብስበው መስመር እንደሚሰሩ ሁሉ ፒክስል ተሰባስቦ ደግሞ ምስል ይሰራሉ ግን እደ ነጥብ አይቆጠሩም ማለት አደለም። የሜጋፒክስሉ ቁጥር ብዛት የአንድ ምስል ልቀት(resolutions) ይወስናል እና ተጨማሪ ሜጋፒክስሎች ያለው ዲጂታል ምስል ተጨማሪ ልቀት አለው ማለት ነው።በዲጂታል ፎቶግራፍ ላይ ከፍተኛ ልቀት መኖሩ ጠቃሚ ነው። ይህም ካሜራ የበለጠ ምስሎችን ለመፍጠር ብዙ ፒክሴሎችን እንደሚጠቀም ይህም የበለጠ ትክክለኛ ምስል ለመፍጠር ይረዳል። የካሜራ ሴንሰሮች ፒክስል ተብለው የሚጠሩ ብርሃን ተቀባዮች በውስጡ ይዞል።እያንዳንዳቸው እነዚህ ተቀባይም የብርሃኑን በመለካት ይመዘግባሉ። አንድ ሴንሰር እነዚህን አይነት ተቀባዮች በሚሊየን አይነት ይኖሩታል። ስለዚህ ሚሊየን ተቀባዮች ሜጋ ፒክስል ተብለው ይጠራሉ።
ብዙ ፒክስል አለ ማለት የፎቶግራፍ ጥራት ይጨምረዋል ማለት ላይሆን ይችላል። ለምሳሌ ገበያ ላይ ያሉ ስልኮች እስከ 25 ሜጋፒክስል ድረስ ሲኖሩ የሳምሰንግ እና አይፎን ስልኮች ለምን ከ13 ሜጋፒክስል ሆነው እንዴት በጥራት ይበልጣሉ? ይህነን ለመመለስ ከላያ የተጻፉትን የካሜራ ባህራት ማየት ትሩ ነው። በነዚህ ስልኮች በላቀ መልኩ ይተገበራሉ በተጨማሪም የፎቶግራፍ ጥራቱ በሜጋፒክስሉ ብቻ ሳይሆን በሴንሰሩ የቁመት መጠን ይወሰናል። ለምሳሌ ካሜራው 30 ሜጋፒክስል ሆኖ ፒክስል ሴንሰሩ ትንሽ ከሆነ የ20 ሜጋፒክስሉ ትልቅ ሴንሰር ያለው የላቀ ጥራት አለው ማለት ነው። ስለዚህ ስልክ ወይም ካሜራ በምንገዛበት ግዜ ሜጋፒክስሉ ለይ ብቻ ትኩረት አለማረግ ተገቢ ነው።
ብዙ #መማር የሚፈልጉ ሰዎች ስላሉ እባክዎ #ሼር ያድርጉት...
#የተማሩትን_ማስተማር #ያወቁትን_ማሳወቅ #ብልህነት ነው
#ለሰው መልካሙን እንጅ መጥፎውን አትመኝ
ስለኮምፒውተርና ቴክኖሎጅ ያለዎትን እውቀት ያሳድጉ በተጨማሪም በቴሌግራሜ ቻናል ምርጥ ምርጥ ስለኮምፒውተር የምለቃቸውን መረጃዎችን ለመከታተል እንዲያመችዎ ይህንን ይጫኑ https://t.me/
MuhammedComputerTechnology በቴሌግራም መከታተል ትችላላችሁ
ሼር ማድረጋችሁን አትርሱ በፍጥነት መረጃ እንዲደርሳችሁ
Like & share this page
#ሼር_ያድርጉ
#ፔጄን_ላይክ ማድረግዎን አይርሱ
👍1
#የሀያላን_አገር_መሪዎች_ፈጣሪን_ተማጸኑ ..
ጣሊያን ዛሬም ደግሞ 793 ዜጎቿን አጥታለች፡፡
በ4ቀን ውስጥ ብቻ ከ'3000 በላይ ዜጎቿ
ይህችን አለም የተሰናበቱባት የጣሊያኑ ጠ/ሚ/ር ኮንቴ እንባ እየተናነቃቸው የሚከተለውን ብለዋል፡፡
=============••••••••••••••••••===========
"ወረርሽኙን መቆጣጠር አልቻልንም። በአካልና በአእምሮ
እየሞትን ነው። ከዚህ በኋላ ምን ማድረግ እንደምንችል
አላውቅም። በምድር ላይ አለ የተባለ መፍትሄ አልቀረንም።
አሁን የቀረን ወደ ሰማይ ብቻ ነው።"
==============••••••••••••••••••===========
የኢጣልያ ጠቅላይ ሚኒስተር ...ኮንቴ
ያአሏህ ማረን ያረሂሙ
ሰላም ሰላም ወንድም እህቶች እንዴት ናችሁ ይሄው ዛሬ ቀኑ ደርሶ ክላስ ልንጀምር ነው
ስለዚህ የምንማራቸውን course outline ከዚህ በታች እዘረዝራቸዋለሁ
1 የኮምፒውተር መግቢያ
2 የኮምፒውተር ታሪካዊ አመጣጥና እድገት
3 የኮምፒውተር አይነቶች
4 የኮምፒውተር ሃርድዌር አካላት
5 የኮምፒውተር ሶፍትዌር
6 የኮምፒውተር የመረጃ መቀበያ አካላት input devices
7 የኮምፒውተር ውጤት መግለጫ መሳሪያዎች output devices
8 ማዘርቦርድ mother board
9 central processing unit CPU
10 መረጃ ማስቀመጫ መሳሪያዎች data storage device
ከላይ 10 የዘረዘርኳቸውን አንድ በአንድ እናያለን ማለት ነው ይሄንን ከጨረስን ወደ አድቫንስድ እንሄዳለን
ይህንን በሁለቱም ቋንቋ የተዘጋጄ ነው በአማርኛ እና በ እንግሊዝኛ ይቀርባል። ስለዚህ እንድትከታቱኝ በአክብሮት እጠይቃለሁ።
በነገራችን ላይ በዚህ ግሩፕ 3 አይነት ሰዎች አሉ ብዙም ስለኮምፒውተር እውቀት የማይኖራቸው(እንደዚህ ስላችሁ ቅር እንዳይላችሁ) መካከለኛ እንዲሁም ከፍተኛ ስለኮምፒውተር እውቀት ያላቸው አሉ። ከተሳሳትኩ እንድታርሙኝ ስል በትህትና እጠይቃለሁ። ስለዚህ ሀሳብ አስተያየት ስጡኝ
https://t.me/joinchat/KPglFhgByUl5eskmbeIsbA
በዚህ ግሩፕ ይቀላቀሉ
እንዳያመልጣችሁ
ዛሬ የማሳያችሁ እንዴት  "Window Key + R" በአንድ ላይ ስንጫን  Run Window ይመጣልናል ከዛም ከዚህ በታች ያሉትን አቋራጭ ቁልፎችን በመጻፍ ስለኮምፒውተራችን መረጃ ማግኜትና ኮምፒውተራችንን መቆጣጠር እንችላለን
1) Compmgmt.msc 👉Computer management    
2) devmgmt.msc  👉Device manager
3) diskmgmt.msc 👉Disk management
4) dfrg.msc 👉Disk defragevent
5) vwr.msc 👉Event viewe
6) rfsmgmt.msc 👉Shared folder
7) sgpedit.msc 👉Group policies  
8) lusrmgr.msc 👉Local user and groups
9) perfmon.msc 👉Performance monitor
10) services.msc  👉Various Services
11) msconfig 👉System Configuration Utility
12) regedit 👉Registry Editor
13) msinfo32 👉System Information 14) winver 👉Shows current version of windows
15) mailto: 👉Opens default email client
16) cmd 👉Opens command prompt
17) perfmon.msc 👉Performance monitor
18) rsop.msc 👉Resultant set of policies
19) secpol.msc 👉Local security setting
20) swin.ini 👉Windows loading information
21) shutdown /s 👉Shutdown
22) shutdown /r  👉Restart
23) shutdown /h  👉Hibernate
25) የተሰማችሁን ሀሳብ comment box ላይ ጻፉልኝ
26) ሼር ያድርጉት
ይህ መረጃ ለእርስዎ ጠቃሚ እንደነበረ ተስፋ አደርጋለሁ።
አመሰግናለሁ!
ስለኮምፒውተርና ቴክኖሎጅ ያለዎትን እውቀት ያሳድጉ በቴሌግራሜ ቻናል ምርጥ ምርጥ ስለኮምፒውተር የምለቃቸውን መረጃዎችን ለመከታተል እንዲያመችዎ ይህንን ይጫኑ https://t.me/MuhammedComputerTechnology በቴሌግራም መከታተል ትችላላችሁ
በተጨማሪም በፌስቡክ ገፄ https://m.facebook.com/mameamin.6te.net ይህንን ሊንክ በመጫን ፔጁን like በማድረግ በፍጥነት መረጃ እንዲደርሳችሁ
ሼር ማድረጋችሁን አትርሱ
የፌስቡክ ፔጁን Like & share ያድርጉ
#ፔጄን_ላይክ ማድረግዎን አይርሱ
👏1
Muhammed Computer Technology (MCT) pinned «ዛሬ የማሳያችሁ እንዴት  "Window Key + R" በአንድ ላይ ስንጫን  Run Window ይመጣልናል ከዛም ከዚህ በታች ያሉትን አቋራጭ ቁልፎችን በመጻፍ ስለኮምፒውተራችን መረጃ ማግኜትና ኮምፒውተራችንን መቆጣጠር እንችላለን 1) Compmgmt.msc 👉Computer management     2) devmgmt.msc  👉Device manager 3) diskmgmt.msc 👉Disk management 4) dfrg.msc…»
የኮሮና መከላከያና መረጃ ጥሪ ማዕከላት፦
በአገር ደረጃ ፡ 8335
የትግራይ ክልል፦ 6244
የአማራ ክልል፦ 6982
የኦሮሚያ ክልል፦ 6955
የደቡብ ክልል፦ 6599
ድሬዳዋ ከተማ፦ 6407
በስፔን የሟቾች ቁጥር 2 ሺህ አልፏል ዛሬ 434 ሞቶባታል
በጣልያን ዛሬም 602 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ ሞተዋል
አሜሪካ ዛሬ ብቻ 7,295 አዲስ ተጠቂዎችን አግኝታለች
ደቡብ አፍሪካ ዛሬ ብቻ 128 አዲስ ኬዝ አግኝታለት
ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም ስለ ቫይረሱ ስርጭት ያሉት አለ
በኒውዮርክ ዛሬ ብቻ +5,085 አዲስ ኬዝ አግኝታለች
ከቫይረሱ ማገገም የቻሉትም 100 ሺህ አልፈዋል
ቻይና ላይ የቫይረሱ ስርጭት በቁጥጥራቸው ስር ያደረጉት ይመስላል። ዛሬ የተመዘገበው አዲስ ኬዝ 39 ብቻ ሲሆን በአሳሳቢ ሁኔታ ላይ ከሚገኙት 1,749 ሰዎች ውስጥ ዛሬ 9 ሞተውባታል።
በደቡብ አፍሪካ 24 ሰዓት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ 128 ሰዎች ይፕትፕገኙ ሲሆን በጠቅላላው 402 ኬዝ በማስተናገድ ከአፍሪካ ቀዳሚዋ ሀገር ሆናለች።
የዓለም ጤና ድርጅት ዳይሬክተር ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም የኮሮና ቫይረስ ፈጣ የኮነ ስርጭትን እንዲህ ሲሉ ገልፀዋል።
" በኮሮናቫይረስ የተያዘው የመጀመሪያው ሰው ሪፖርት ከተደረገ በኋላ፤ የመጀመሪያዎቹ 100 ሺህ ሰዎች በቫይረሱ ለመያዝ 67 ቀናት ወስደዋል። ቀጣዮቹ 100 ሺህ ሰዎች የተያዙት በ11 ቀናት ውስጥ ሲሆን ፤ ሦስተኛ 100 ሺህ ሰዎች የተያዙት ግን በ4 ቀናት ውስጥ ነው” በማለት የቫይረሱን አስደንጋጭ የስርጭት ፍጥነት አመላክተዋል። via- BBC አማርኛ
ዩናይትድ ስቴትስ አሜሪካ ገና 24 ሰዓት ሳይሞላ 7,796 አዲስ ኬዝ ያስተናገደች ሲሆን 79 ሰዎችም ሞተውባታል። በጠቅላላው በሀገሪቱ የተመዘገበው ኬዝ 41,342 ሲሆን የሟቾች ቁጥርም ወደ 498 ከፍ ብሏል።
ስፔን ከጣልያን ቀጥሎ በርካታ ሰዎቿን እያጣች ያለች ሀገር ስትሆን ዛሬም 435 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ ኬዝ ሕይወታቸውን አጥተዋል። በሀገሪቱ የተመዘገበው ጠቅላላ የሟቾች ቁጥርም 2,207 ደርሷል። ስፔን በአለማችን በርላታ የኮሮና ቫይረስ ኬዝ ያለባት 4ኛ ሀገርም ነች (33,089 ሰው ተጠቅቷል)
በቫይረሱ የሚያዘው የሰው ቁጥር በከፍተኛ ፍጥነት እየጨመረ ቢሆንም መልካም የሚባለው ዜና አገግመው ከሆስፒታል የሚወጡት ሰዎችም የዛኑ ያክል በርከት ብሏል። አሁን ላይ በመላው አለም 101,069 ሰዎች ከቫይረሱ ማገገማቸው ሪፖርት ተደርጓል።
የፌደራል የመንግስት ሰራተኞች ከነገ ጀምሮ ተጨማሪ ውሳኔ እስከሚተላለፍ ስራቸውን በቤታቸው ሆነው እንዲያከናውኑ ተወሰነ
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 15፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ሚኒስትሮች ምክር ቤት የኮቪድ19 ገደብ የለሽ ስርጭት ሊያስከትል የሚችለውን ማኅበራዊ፣ ፖለቲካዊ እና ኢኮኖሚያዊ ውዥንብር ለመከላከል የሚወሰዱ እርምጃዎችን በተመለከተ አስቸኳይ ስብሰባ አካሂዷል።
ምክር ቤቱ በአስቸኳይ ስብሰባው የፌደራል የመንግስት ሰራተኞች ከነገ መጋቢት 16 ጀምሮ ተጨማሪ ውሳኔ እስከሚተላለፍ ስራቸውን በቤታቸው ሆነው እንዲያከናውኑ ውሳኔ አሳልፏል።