Muhammed Computer Technology (MCT)
38.1K subscribers
527 photos
7 videos
254 files
910 links
🔴አድራሻ:-
✅ ስ.ቁ: 0929273364
✅ ዌብሳይት www.mctplc.com
✅ቴሌግራም አካውንት: https://t.me/mctplc
✅ email: mct16plc@gmail.com
✅ ቲክቶክ አካውንት tiktok.com/@mctplc
Download Telegram
Students Information Management System (ሬጅስትራር ሲስተም) Registrar System, For College ለኮሌጆች ምርጥ ሲስተም
በቪዲዮ ይመልከቱት!
👇👇👇👇
https://youtu.be/4OYhb8yf-Yw
https://youtu.be/4OYhb8yf-Yw
https://youtu.be/4OYhb8yf-Yw

ሁለቱን ሲስተሞችን መጠቀም የምትፈልጉ 0929273364 ይደውሉ። ወይም በቴሌግራም ሊያገኙኝ ይችላሉ👉👉 @mctplc

ቴሌግራም ቻናል https://t.me/MuhammedComputerTechnology
👍10❤5
የትኛውን ሲስተም ድርጅታችሁ ላይ ተግባራዊ በማድረግ አሰራራችሁን ዲጅታላይዝ ማድረግ ይፈልጋሉ?

💎 Muhammed Computer Technology የሶፍትዌር ልማት ድርጅት የሚከተሉትን ሲስተሞችን ሶፍትዌሮችን በማበልጸግ ለተለያዩ ድርጅቶች ተግባራዊ እያደረገ ይገኛል።

✅ የሰው ሀብት መረጃ አስተዳደር ስርአት Human Resource Information Management System
💎 የምንኛውንም ድርጅት የሰው ሀብት መረጃ የምናስተዳድርበት

✅ የንብረት መረጃ አስተዳደር ስርአት Property Information Management System
💎 የማንኛውንም ድርጅት ንብረት የምናስተዳድርበት

✅የከተማ መሬት መረጃ አስተዳደር ስርአት Urban Land  Information Management System
💎 ለከተማ ማዘጋጃ ቤቶች መረጃቸውን የሚያስተዳድሩበት

✅ የተማሪዎች መረጃ አስተዳደር ስርአት Students   Information Management System
💎 ለኮሌጆች የማስተርስ፣ የዲግሪና የቴክኒክና ሙያ ኮሌጆች የተማሪዎች መረጃን የምናስተዳድርበት

💎 እንዲሁም የተለያዩ ድረገጾችን እንዲሰራላችሁ ይፈልጋሉ?

✅ ጊዜው የዲጅታል የቴክኖሎጂ ነው፡፡
ህልምዎን እውን የሚያደርጉ ሲስተሞችን, ድረ-ገጾችን (ዌብሳይቶችን) ለማሰራት  ይደውሉ። አሰራርዎን ዘመናዊ ያድርጉ!

🔴አድራሻ:-
✅ ስ.ቁ: 0929273364
✅ ዌብሳይት www.mctplc.com
✅ቴሌግራም አካውንት: https://t.me/mctplc
✅ በቴሌግራም ቻናል: https://t.me/MuhammedComputerTechnology
✅ email: mct16plc@gmail.com
✅ Facebook:- https://m.facebook.com/MuhammedComputerTechnology/
✅ ቲክቶክ አካውንት tiktok.com/@mctplc
✅ የYouTube ቻናልን ሰብስካራይብ በማድረግ ወቅታዊ የቴክኖሎጂ መረጃን ያግኙ!
👇👇👇Subscribe👇👇👇
https://youtube.com/@muhammedcomputertechnology
የተቋምዎን  መረጃን ዲጅታላይዝ እናድርግልዎ ስንል በደስታ ነው!
👍24❤9
Window 7 installation steps.pdf
654.3 KB
windows 7,8,10 installation Guide
ዊንዶውስ 7,8,10 ኮምፒውተር ለመጫን ይህንን PDF ይመልከቱ
✅ በቴሌግራም ቻናል: https://t.me/MuhammedComputerTechnology
https://t.me/MuhammedComputerTechnology
👍41❤12
windows11_installation_MuhammedComputetTechnology.pdf
1.9 MB
windows 11installation Guide
ዊንዶውስ 11 ኮምፒውተር ለመጫን ይህንን PDF ይመልከቱ
✅ በቴሌግራም ቻናል: https://t.me/MuhammedComputerTechnology
https://t.me/MuhammedComputerTechnology
👍38😁3❤2
✅ ምርጥ የሪሰርች የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ።   

❓ትምህርት እየተማሩ ነው? ወይም ለመማር አስበዋል?
❓ጥናትና ምርምር(Research) እየሰሩ ነው?
❓ስለ Research እውቀትዎን ማሳደግ ይፈልጋሉ?
❓ስለ SPSS, Stata, matlab ማውቅ ይፈልጋሉ?
✅በአማርኛ ና በእንግሊዝኛ በግልጽና ቀላል አገላለጽ ስለ Research ጽንሳ ሀሳብ ጀምሮ ጽሑፎችን ያገኛሉ።
👇👇👇👇👇👇👇
https://t.me/star_research_consultancy https://t.me/star_research_consultancy https://t.me/star_research_consultancy
👆👆👆👆👆👆👆👆
👍15❤2
አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ-Artificial Intelligence
🔷 መግቢያ
አሁን በአለንበት ዘመን የኢንተርኔት ቴክኖሎጂ ዓለምን ከጥግ እስከ ጥግ እያዳረሰ፤ ዕውቀትን እና መረጃን የማሰራጨት እና የማጋራት ባህል በከፍተኛ ደረጃ እየጨመረ ነው፡፡ በመሆኑም በውስብስብነቱ እና በአስቸጋሪነቱ ምክንያት በብዙ የሳይንስ ምሁራን ዘንድ ሳይደፈር ለዘመናት በአዝጋሚ የእድገት ደረጃ ላይ የቆየውን “አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ” ቴክኖሎጂን በፍጥነት እያሳደገው ይገኛል፡፡ ዕውቀት ከአንዱ የዓለም ክፍል ወደሌላኛው የዓለም ክፍል በፍጥነት እና በብዛት መሰራጨቱ፤ ችግሮችን በጋራ አቅርቦ የመፍታት እና የመማማር ባህል መዳበሩ፤ በተለያዩ የአለም ክፍሎች የሚገኙ አፍቅሮተ-ቴክኖሎጂ ያላቸው ወጣቶች (Tech geeks) በብዛት መሳተፋቸው፤ ለዘርፉ በከፍተኛ ደረጃ ማደግ እንደ ምክንያትነት የሚጠቀሱ ናቸው፡፡
በዚህ ዘርፍ ለሰው ልጅ የሚጠቅሙ አያሌ ግኝቶች በስራ ላይ ውለዋል፡፡ከነዚህም ውስጥ ከባድ እና አሰልቺ የሆኑ ተደጋጋሚ ስራዎችን በፍጥነት እና ያለምንም ስህተት የሚያከናውኑ ግዙፍ የፋብሪካ ሮቦቶችን፤ እጅግ ሰፊ ከሆነ የዕውቀት ውቅያኖስ ውስጥ ተፈላጊውን መረጃ በአጭር ጊዜ እና በከፍተኛ ፍጥነት የሚያቀርቡ ሶፍትዌሮችን፤ያለምንም አሽከርካሪ ራሳቸውን ችለው የሚንቀሳቀሱ መኪናዎችን.. ወዘተ መጥቀስ ይቻላል፡፡
አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ እና ሮቦቲክስ ምን እና ምን ናቸው
አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ማመዛዘንን (ምክኒያታዊነትን)፣ ዕውቀትን፣ ዕቅድን፣ መማርን እና ቋንቋን በፅንሰ-ሀሳብ ደረጃ ሚስጥራቸውን መፍታት እና በሳይንሳዊ ሂደት መተንተን ነው፡፡ የሰው ልጅ አነኚህን ክህሎቶች የሚያዳብረው በተጠናና በተቀመረ መልኩ ሳይሆን በተፈጥሮ የህይወት ዑደት ውስጥ ነው፡፡ በተፈጥሮአዊ ልምምድ የሚዳብሩትን እነዚህን ክህሎቶች በቀመር እና በሳይንሳዊ ጥናት ለመተንተን መሞከር ግን እጅግ ፈታኝ ተግባር ነው፡፡ አንድ ህፃን ልጅ እየተኮላተፈ አማርኛ ሲናገር፤ ከዛም በአጭር ጊዜ ቋንቋውን ሲያቀላጥፈው ማየት ለብዙዎቻችን አስገራሚ አይሆንም፡፡ ሆኖም ይህንን የክህሎት ሒደት በሳይንሳዊ ትንተና ፈትቶ እና ተመሳሳይ ባህሪያትን ለማሽኖች ወይም ለሶፍትዌሮች አላብሶ ማላበስ መቻል ግን ከፍተኛ ስኬት ነው፡፡ አንዳንዴም እንዲህ ያለው ተግባር የፈጣሪን ሚና እንደመተካት ሊቆጠር ይችላል፡፡ቢሆንም ብዙ ወጣቶችን ወደዚህ ዘርፍ እንዲሳቡ ያደረጋቸው ዋነኛ ምክንያት ይህ የዘርፉ ውስብስብነት የፈጠረው ተግዳሮትን የመፍታት እልህ እና ተፈጥሮን አስመስሎ እና ተንትኖ የማቅረብ ረሀብ ነው፡፡
በሌላ በኩል ሮቦቲክስ የሜካኒካል ምህነድስና፣ ኤሌክትሮኒክ ምህንድስና፣ እና የኮምፒውተር ሳይንስ ቅርንጫፍ ሲሆን፤ የአርቴፊሻል ኢንተለጀንስን ዕውቀት በከፍተኛ ደረጃ በግብዓትነት በመጠቀም የሚንቀሳቀሱ፣ እንደሰው አመዛዝነው ውሳኔ የሚሰጡ፣ ሰውን ተክተው አልያም ከሰውልጅ ጎን ለጎን ሆነው የተለያዩ ተግባራትን የሚከውኑ ሜካኒካዊ እና ኤሌክትሮኒካዊ ሮቦቶችን የሚያጠና ዘርፍ ነው፡፡ ዘርፉ ቁስ አካላዊ ሮቦቶችን ብቻ ሳይሆን መረጃን የሚያቀነባብሩ ብልህ የኮምቲውተር ሲስተሞችንም ያጠቃልላል፡፡
አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ስለ ማመዛዘን (ምክኒያታዊነት)፣ ዕውቀት፣ ዕቅድ፣ መማር እና ቋንቋ ፅንሰ-ሀሳባዊ ምንነት በሳይንሳዊ ትንታኔ ሲያቀርብ፤ ሮቦቲክስ ደግሞ ከአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ያገኘውን የውስብስብ ፅንሰ-ሀሳቦች ምንነት እና ሌሎች ተጓዳኝ የምህንድስና ዕውቀት በመጨመር ለተለያዩ ጥቅም የሚውሉ ሮቦቶችን ይሰራል፡፡
🔷 ታሪክዊ ሂደት
ግኡዛንን እንደሚያስቡ እና ባለአዕምሮ ፉጡራን አድርጎ መስራት ጥንት የግሪክ፣ የግብፅ፣ እና ሌሎችም ጥንታዊ ገናና የሰውልጅ ስልጣኔ ታሪክ ውስጥ ጉልህ ስፍራ ነበራቸው፡፡ በተለይ በግሪክ እና ግብፅ ጥንታዊ ስልጣኔ ውስጥ ለጣኦት አምልኮ የሚውሉ የሚንቀሳቀሱ ግኡዝ አካላትን መስራት የተለመደ ነበር፡፡ እነዚህ የሰው ልጅ ፍላጎቶች የተለያዩ መልኮችን ይዘው እና አድገው እስከ 2ኛው የዓለም ጦርነት ድረስ በመዝለቅ፤ አሁን ላለንበት የዲጂታል ቴክኖሎጂ እና አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ምዕራፍ ወሳኝ መሰረት የጣለውን ‹‹የአለን ቱሪንግ››ን የምርምር ውጤት ወልደዋል፡፡
ከአመታት በኃላ፣ እ.ኤ.አ በ1956 በዶረቱሙን ኮሌጅ ግቢ በተደረገው ኮንፍረንስ የተመሰረተው የአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ጥናት፤ በኮንፍራንሱ ተሳታፊዎች እና በተማሪዎቻቸው አማካኝነት ለብዙ አስርታት የመስኩ ብቸኛ ተዋናይ ሆነው ቆይተዋል፡፡ ተማሪዎቹ በወቅቱ ለብዙዎች አስገራሚ ሊባሉ የሚችሉ ‹‹ምጡቅ›› የኮምፒውተር ፕሮግራሞችን በመስራት ለእይታ አቅርበው ነበር፡፡ ቼዝ ተጫወተው የሚያሸንፉ፤ አልጄብራን እንዲሁም የሎጂክ ቴረም ጥያቄዎችን የሚፈቱ እና እንግሊዘኛ የሚናገሩ የኮምፒውተር ፕሮግራሞች ተማሪዎቹ ይሰሯቸው ከነበሩት ውስጥ ተጠቃሽ ናቸው፡፡ ከ1960 ጀምሮ የዚህ ምርምር የገቢ ምንጭ የአሜሪካ መከላከያ ተቋም ስለነበረ በ1974 የገንዘብ ድጋፉ በመቋረጡ የዘርፉም እድገት በከፍተኛ ሁኔታ ቀንሶ ነበር፡፡ ይሁን እንጂ በ1980 መጀመሪያ አካባቢ በተለያዩ የሙያ ዘርፎች የባለሙያ ትንታኔ የመስጠት ችሎታ የነበረው
‹‹የኤክስፐርት ሲስተም›› ከፍተኛ ተቀባይነት በማግኘቱ ዘርፉ እንደገና አንሰራራ፡፡ በዚህም ምክንያት የዘርፉ ጠቅላላ ገቢ እስከ 1ቢሊዮን ዶላር ደርሶ ነበር፡፡ ይሁን እንጂ እንደገና በ1987 አካባቢ ከሊስፕ ኮምፒውተር ገበያ ማጣት ጋር ተያይዞ ገበያው በመቀዛቀዙ ሁለተኛውን እና ረጅሙን የድብርት(Depression) ጊዜ አሳልፏል፡፡ ከዛም ከ1990ዎቹ ጊዜ እስከ 21ኛው ክፍለ ዘመን መጀመሪያዎቹ ድረስ ድምፁን አጥፍቶም ቢሆን ከፍተኛ ስራ ሰርቷል፡፡
በ1997 ‹‹ዲፕ ብሉ›› የተባለው የኮምፒውተር ቼዝ ተጫዋች በወቅቱ በቼዝ ጨዋታ ሻምፒዬን የነበረውን ጌሪ ካስፓሮቭን በማሸነፍ አለምን ጉድ አሰኝቶ አልፏል፡፡ በ2011 የIBM ስሪት የሆነው ዋትሰን የተባለው የኮምፒወተር ሮቦት በ ጆፓራዳይ የቴሌቭዥን የጥያቄ እና መልስ ሾው ላይ በመሳተፍ ብራድ ሩተር እና ጆን ክኒንስ የተባሉትን የጥያቄና መልስ ውድድር ቻምፒዎኖቹን በከፍተኛ የነጥብ ልዩነት አሸንፏቸዋል፡፡
🔷 የአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ትግበራ በተለያዩ ዘርፎች ውስጥ
አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ በህክምና፣ ህግ፣ ሮቦቲክስ፣ ሪሞት ሴንሲንግ፣ ትራንስፖርት ዘርፎች ላይ ተግባራዊ የሆነ ቢሆንም፤ አንዴ ለገበያ ከቀረበ እና በሰፊው ጥቅም ላይ ከዋለ፤ አሰራሩም ከታወቀ በኃላ ግን ‹‹ብልህ›› መሆኑ ያከትምለታል ብለው ብዙዎች ይከራከራሉ፡፡ በዚህም ምክንያት በብዙ ሺህ የኢንደስትሪ ማሽኖች ላይ ተገጥመው የሚገኙ ቢሆኑም ለረጅም ጊዜ ለብልህነታቸው ይህ ነው የሚባል እውቅና ሲሰጣቸው አይሰተዋልም፡፡
🔷 በህክምና እና ጤና ተቋማት
የተለያዩ የህክምና ተቋማት የውስጥ አስተዳደራዊ አሰራራቸውን ለማቀላጠፍም ሆነ ሳይንሳዊ መረጃዎችን ለህክምና ባለሙያች ለመለገስ አርቴፊሻል ኢንተለጀንስን እይተጠቀሙ ይገኛሉ፡፡ የአስተኝቶ ማከም ቀጠሮዎችን በማመቻቸት ሆነ የባለሙያዎችን የስራ ፈረቃ ፕሮግራም በማውጣት ላቅ ያለ አስተዳደራዊ ጥቅም ይሰጣሉ፡፡ በተጨማሪም በኮምፒውተር የታገዘ ምስል በማንሳት እንደ ካንሰር ያሉ ችግሮችን ለባለሙያዎች በመጠቆም፤ እጅግ ብዙ ከሆኑ የሜዲካል ዕውቀቶች ውስጥ ተፈላጊውን መረጃ አስሶ ለባለሙያው በመስጠት ሙያዊ አበርክቶ ያደርጋሉ፡፡
👍21❤2😁1
🔷 በከባድ ኢንደስትሪዎች
ለሰው ልጅ እጅግ አደገኛ በሆኑ፣ ድግግሞሽ በሚበዛባቸው አድካሚ የከባድ ኢንደስትሪ ስራዎች ውስጥ የአርቴፊሻል ኢንተለጀንስን ዕውቀት የሚጠቀሙት ሮቦቶች የማይተካ ሚና ይጫወታሉ፡፡ ስለሆነም የሰው ልጆችን ከአደጋ ይታደጋሉ፣ ስህተት ስለማይሰሩ እና ስለማይደክማቸው ከፍተኛ ውጤት ያስመዘግባሉ፡፡ በአሁኑ ወቅት በመኪና ምርት፣ በማዕድን ማውጣት ስራ እና ትላልቅ የፋብሪካ ማሽኖችን በሚያመርቱ ኢንደስትሪዎች ውስጥ ከፍተኛ አገልግሎት በመስጠት ላይ ናቸው፡፡
🔷 በትራንስፖርት
ሹፌር አልባ መኪኖች ራሳቸውን በራሳቸው የሚያንቀሳቅሱ፤ የተሰጣቸውን ትእዛዝ ተቀብለው ሰውንም ሆነ ዕቃ የተፈለገው ቦታ የሚያደርሱ፤ ተሰሳስተው አልያም ደክሟቸው በቸልተኝነት አደጋን የማያደርሱ መኪኖች የአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ የምርምርና ዕውቀት ውጤቶች ናቸው፡፡ ምንም እንኳን በአሁኑ ጊዜ በስፋት ለጥቅም ባይውሉም በGoogleX ፕሮጀክት በመሰራት ላይ ያለው አሽከርካሪ አልባ መኪና ተጠቃሽ ነው፡፡ ይህ መኪና ‹‹ጉግል ሹፌር›› የሚባል ሶፍትዌር የተገጠመለት ሲሆን የአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ዕውቀትን ተግባራዊ በማድረግ የተሰራ ሶፍትዌር ነው፡፡ መኪናው በአሁኑ ወቅት በሙከራ ላይ ይገኛል፡፡
የሥነ ምግባር እና የፍልስፍና ጥያቄዎች
አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ በተወሰነ ደረጃም ቢሆን የሰው ልጅ አስተሳሰብ፣ ባህሪ እና ጠባይ ለማሽኖች የሚያላብስ የሳይንስ ዘርፍ እንደሆኑ መጠን፤ ከዚህ ጋር ተያይዞ በዛ ያሉ የሞራል፣ የስነምግባር እና የፍልስፍና ጥያቄዎችን ማስነሳቱ አልቀረም፡፡ ከፍልስፍና ጥያቄዎቹም ውስጥ ከዚህ በታች የተዘረዘሩት ሶስቱ በዋነኛነት ተጠቃሽ ናቸው፡-
1. ማሽኖች የሰው ልጅ ሊፈታቸው የሚችላቸውን ችግሮ በሙሉ የመፍታተት አቅም ይኖራቸዋልን? ወይስ ማሽኖችን ‹‹ሰው›› የማድረግ ጥረት ገደብ አለው?
2. የአርቴፊሻል ኢንተለጀንስን ባህሪያት የተላበሱ ማሽኖች አደገኛ ሊሆኑ ይችላሉን? በስነ-ስርአት እና ወግ ባለው መልኩ ጥቅም ላይ እንዲውሉ፤ ብሎም በምንም አይነት መልኩ ከቁጥጥር ውጭ የሆነ ባህሪ እንዳይላበሱ ማድረግ ይቻላልን?
3. ማሽኖችን ልክ እንደ ሰው ባለአእመሮ እና ባለህሊና ማድረግ ይቻላልን? እንደ ሰው ልጆችስ መብት ይኖራቸዋል? አውቀው እና በራሳቸው ተነሳሽነት ተንቀሳቅሰው በሰው ልጅ ላይ ጉዳት ማድረስ ይችላሉን?
ከላይ በተነሱት ጥያቄዎች ዙርያ የተለያዩ ሙሁራን የየራሳቸውን ፅሁፍ እያቀረቡ በንድፈ-ሀሳብ ደረጃ የተከራከሩ ሲሆን፤ ጥያቄዎቹ ምላሽ ሊያገኙ የሚችሉት በጊዜ ሒደት ብቻ ነው፡፡ በዚህም ምክንያት የተለያየ ጥግ ይዘው ጥያቄዎቹን ለመመለስ የሞከሩም ሆኑ የሚሞክሩ ምሁራን ትክክለኛነታቸው የሚረጋገጠው በዘርፉ የተፈጥሮ እድገት ሂደት ውስጥ ብቻ ይሆናል ማለት ነው፡፡ እዚህ ጋር ሳይጠቀስ የማይታለፈው አንደኛው ጥያቄ ከሞራል ጋር የተገናኘው ነው፡፡ የሰው ልጆች ከአደጉበት ባህል፣ ከኖሩበት ዘመን ጋር በማቆራኘት ስለ ሞራል ምንነት ትርጓሜ ሲሰጡ ይታያል፡፡ በዚህም የተነሳ በተለያዩ የህይወት ውሳኔዎቻቸው ላይ ይህ የሞራል ግንዛቤ የራሱን አስተዋፅኦ ያሳድራል፡፡ ሞራል የጊዜ እና የባህል ተፅዕኖ ስለሚበዛበት አንድ ወጥ የሆነ ሞራላዊ ምንነት ለማሽኖች እንዲላበሱ የሚደረገውን ምርምር በዛው ልክ ወጥ ያልሆነ እና ውስብስብ እንዲሆን አድርጎታል፡፡ ይሁን እንጂ ከላይ በተነሱት ፅንሰ-ሀሳባዊ የፍልስፍና ጥያቄዎች ዙርያ የሚደረጉት ምሁራዊ ክርክሮች እና ትንታኔዎች አሁንም ድረስ እንደቀጠሉ ናቸው፡፡
ከሞራል እና ስነ-ምግባር ጋራ የሚነሱ ጥያቄዎች እና በምሁራን የሚሰጡ ትንታኔዎች አከራካሪ፣ መሳጭ እና የሰውን ልጅ የወደፊት እጣ ፈንታ የሚወስኑ ስለሚሆኑ፤ በቀጣይ በዚህ ድረ-ገፅ የተለያዪ ፅሁፎችን በትንታኔ መልክ ለማቅረብ ይሞከራል፡፡
🔷 ማጠቃለያ
ብልህ እና እንደ ሰው ልጅ የሚያስቡ ቁስ አካላትን ለመፍጠር የሚደረገው ሳይንሳዊ ምርምር እና ዕውቀት ወደፊት የሰውን ልጅ የአኗኗር ስልት በከፍተኛ ሁኔታ እንደሚቀይር የማያጠራጥር ነው፡፡ አደጋን የሚቀንሱ፣ ጤንነትን የሚያሻሻሉ፣ ከፍተኛ ምርትን የሚያስገኙ፣ ወዘተ ጥቅሞችን እየሰጡ የሚገኙ እና ወደፊትም በላቀ ጥራት እና ውስብስብነት የሰውን ልጅ ህይወት የሚያቀሉ የአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ውጤቶች በዚህ አጭር ዕሁፍ ለመዳሰስ መሞከር ‹‹አባይን በጭልፋ›› እንደ መዝገን ይሆንብኛል፡፡
በዚህ ዘርፍ አያሌ እና ተነግረው የማያልቁ ግኝቶች፣ በምርምር ላይ ያሉ ዕውቀት፣ በዘርፉ ላይ የተነሱ እና የሚነሱ ጥያቄዎች፣ ወዘተ በመረጃነት ይገኛሉ፡፡በመሆኑም በዚህ ድረ-ገፅ ከዘርፉ ጋር ተያያዥ እና ጠቃሚ ናቸው የምንላቸውን ዜናዎች፣ አርቲክሎች(መጣጥፎች)፣ ፖድካስቶችን የምናቀርብ ሲሆን፤ የዘርፉን ውስብስብ ዕውቀትና ልምድ የሚያንፀባርቁ የምሁራን ክርክሮችን ጭምር በየጊዜው በቀላል አገላለፅ ለማቅረብ እንሞክራለን፡፡
👍30❤4
የትኛውን ሲስተም ድርጅታችሁ ላይ ተግባራዊ በማድረግ አሰራራችሁን ዲጅታላይዝ ማድረግ ይፈልጋሉ?

💎 Muhammed Computer Technology የሶፍትዌር ልማት ድርጅት የሚከተሉትን ሲስተሞችን ሶፍትዌሮችን በማበልጸግ ለተለያዩ ድርጅቶች ተግባራዊ እያደረገ ይገኛል።

✅ የሰው ሀብት መረጃ አስተዳደር ስርአት Human Resource Information Management System
💎 የምንኛውንም ድርጅት የሰው ሀብት መረጃ የምናስተዳድርበት

✅ የንብረት መረጃ አስተዳደር ስርአት Property  Information Management System
💎 የማንኛውንም ድርጅት ንብረት የምናስተዳድርበት

✅የከተማ  መሬት መረጃ አስተዳደር ስርአት Urban Land  Information Management System
💎 ለከተማ ማዘጋጃ ቤቶች መረጃቸውን የሚያስተዳድሩበት

✅ የተማሪዎች መረጃ አስተዳደር ስርአት Students   Information Management System
💎 ለኮሌጆች የማስተርስ፣ የዲግሪና የቴክኒክና ሙያ ኮሌጆች የተማሪዎች መረጃን የምናስተዳድርበት

💎 እንዲሁም የተለያዩ ድረገጾችን እንዲሰራላችሁ ይፈልጋሉ?

✅ ጊዜው የዲጅታል የቴክኖሎጂ ነው፡፡
ህልምዎን እውን የሚያደርጉ ሲስተሞችን, ድረ-ገጾችን (ዌብሳይቶችን) ለማሰራት  ይደውሉ። አሰራርዎን ዘመናዊ ያድርጉ!

🔴አድራሻ:-
✅ ስ.ቁ: 0929273364
✅ ዌብሳይት www.mctplc.com
✅ቴሌግራም አካውንት: https://t.me/mctplc
✅ በቴሌግራም ቻናል: https://t.me/MuhammedComputerTechnology
✅ email: mct16plc@gmail.com
✅ Facebook:- https://m.facebook.com/MuhammedComputerTechnology/
✅ ቲክቶክ አካውንት tiktok.com/@mctplc
✅ የYouTube ቻናልን ሰብስካራይብ በማድረግ ወቅታዊ የቴክኖሎጂ መረጃን ያግኙ!
👇👇👇Subscribe👇👇👇
https://youtube.com/@muhammedcomputertechnology
የተቋምዎን  መረጃን ዲጅታላይዝ እናድርግልዎ ስንል በደስታ ነው!
👍30👏4👎1🔥1
#SD_CARD  
የዘመናችን አስደናቂ ፈጠራዎች ከሆኑት መካከል ስለ #ሜሞሪ_ካርድ ወይም SD(Secure Digital) CARD በጥቂቱ:

◽ ይህች SD(Secure Digital) Card የምንላት መሳሪያ ኤሌክትሮኒክ የመረጃ #ማከማቻ ስትሆን ዲጅታል ኢንፎርሜሽኖችን ለማስቀመጥ ወይም Store ለማድረግ ያገለግላል፡፡ ይቺ ዳታ ማከማቻ በዲጅታል ካሜራዎች፣ በተንቀሳቃሽ ስልኮች፣ በላፕቶፖችና በኮንፒውተሮች፣ በታብሌቶች ፣በmp3 ማጫዋቻዎችና በቪድዮ ጌም ኮንስሎች ትገኛለች፡፡

◽️ የሚሞሪ ካርድ #በመጀመሪያ ወደ አለም ብቅ ያለው በፈረንጆቹ አቆጣጠር በ1995 ሲሆን ይሄውም PC Card (PCMAIA) የሚል ስያሜ ነበራቸው፡፡ እነዚህ የመጀመሪያዎቹ ሚሞሪዎች አሁን በስፋት ተሰራጭተው ከሚገኙ ሚሞሪዎች በመጠን ከፍ ያሉ ሲሆን መረጃ የመያዝ አቅማቸውም በጣም አነስተኛ ነበር፡፡

◽️ በአሁኑ ወቅት እነዚህ ቀደምት ሚሞሪዎች በስፋት እያገለገሉ ያሉት በእንዱስትሪያል አፕልኬሽኖችና እንደ ሞደም ያሉ ኤሌክትሪካል ዲቫይሶችን ለማገናኘት ብቻ ነው፡፡ አብዛሃኞቹ ሚሞሪ ካርዶች መረጃዎችን እንደገና መላልሶ ማጥፋትና መጫን የሚያስችሉ ሲሆን መረጃዎችንም የሚይዙት ያለምንም ፓዎር ነው፡፡

◽️ ከአመታት በኋላ መሻሻሎችን በማሳየት የተላየዩ ሚሞሪዎች ገበያውን መቀላቀል ጀመሩ በተለይ ከመጀመሪያዎቹ PC Card በመጠን አነስ ያሉና መረጃ የመያዝ አቀማቸው ከፍ ያሉ በመሆናቸው ተቀባይነት ለማገኘት ብዙ ጊዜ አልፈጀባቸውም፡፡ ከነዚህም ውስጥም Compact Flash, Smart Media, እና Miniature Card ይገኝበታል፡፡

◽️ በ2001 (እ.ኤ.አ) Smart Media ሚሞሪ ካርድ 50% የዲጅታል ካሜራ ገበያውን ተቆጣጥሮ ነበር፡፡ Compact Flash, የተባለው የሚሞሪ ካርድ አይነት ደግሞ በአብዛኛው የፕሮፌሽናል ዲጅታል ካሜራዎች ላይ ነግሶ ነበር፡፡ እነዚህ የሚሞሪ ካርድ አይነቶች ተፈላጊነታቸው ጥያቄ ውስጥ የገባው በ2010 (እ.ኤ.አ) Micro SD ሚሞሪ ካርዶች መምጣታቸውን ተከትሎ ሲሆን በብዙ የሞባይል ብራንዶች ላይ እና ታብሌቶች ላይ በመገጠም ተፈላጊነታቸው በጣም ሊንር ችሏል፡፡

◽️ እስከ 2010 (እ.ኤ.አ) የሶኒ ካምፓኒ ለምርቶቹ ሚሞሪ እስቲክን ብቻ ይጠቀም ነበር በተመሳሳይ ታዋቂው የዲጅታል ካሜራዎች አምራች Olympus ኩባንያ sd CARD ብቻ የሚጠቀሙ ካሜራዎችን ያመርት የነበረ ሲሆን በኋላ ላይ ግን ሶኒም ሆነ ኦሎምፐስ በምርቶቻቸው ላይ SD MEMORY CARD እንደተጨማሪ የሚያስገቡ ካሜራዎችን ማምረት ግድ ብሏቸዋል፡፡

◽️ አሁን ላይ በብዛት የምንጠቀምባቸው Micro SD ሚሞሪ ካርድ 1.4 mm ቲክነስ ያላቸው ሲሆን በቅርቡ ይፋ በተደረገው መረጃ መሰረት እስከ 1 TB ወይም 1000 GB መረጃን የመሸከም አቅም እንዲኖራቸው ተደርጎ ለመስራት ተችሏል፡፡ ልብ በሉ የመጀመሪያዎቹ ሚሞሪ ካርዶች መረጃ የመሸከም አቅም 32 MB ነበረ ይህ ማለት ከ30 ፎቶዎች በላይ የመያዝ አቅሙ ያልነበረው ነው፡፡ ለ25 አመታት የፍላሽ ስቶሬጅ (Flash Storage) ገበያውን እየመራ ያለው San የተባለው እውቅ ካንፓኒ አሁን ላይ ባለው ቴክኖሎጂ 128 GB SDXC Memory Card (1.4 mm) ማምረቱን ያስታወቀ ሲሆን መረጃን በስሌት ለማስርዳት ያህል አዲሱ ሜሞሪ፡-
🔳16 ሰዓት HD ቪድዮዎች
🔊7500 ሙዚቃዎችን
🔲3200 ፎቶዎችን
🔽 ከ125 በላይ አፕልኬሽኖችንም በዛች ጉደኛ SDXC ሚሞሪ ካርድ (1.4mm) ከላይ የተጠቀሱትን ሚዲያ ፋይሎች በሙሉ በአንድ ላይ ማስቀመጥ ተችሏል ይለናል፡፡
ከወደዱት ለወዳጅዎ #ያጋሩ!
👍35❤6
ኮምፒውተርዎን ፈጣን የሚያደርጉ 10 ዘዴዎች

1. ትላልቅ መጠን ያላቸውን ፎቶዎች ዎልፔፐር አይጠቀሙ፡፡
2. ሁሌም ኮምፒዩተሩ ከፍቶ ሳይጨርስ አፕሊኬሽን ለመክፈትም ሆነ ለመነካካት አይሞክሩ፡፡
3. አፕሊኬሽን ከዘጉ በሁዋላ ዴስክቶፑን ሪፍሬሽ ያድርጉ፤ ይህም ራም ሜሞሪን ነፃ ያደርጋል፡፡
4. የማይጠቀሙበት ሶፍትዌር ካለ ከኮምፒውተሩ ይሰርዙ (አን-ኢንስታል) ያድርጉት)፡፡
5. ዴስክቶፕ ላይ ፋይል አያስቀምጡ፤ ሾርትከትም መብዛት የለበትም፡፡
6. ኮምፒዩተሩ ሲከፈት በራሳቸው የሚከፈቱ ለምሳሌ: ስካይፕ አይነት አፕሊኬሽኖች ካሉ disable ያድርጉ
7. Recycle binን ሁሌም ባዶ ያድርጉ::
8. ሀርድ ዲስኩን ሁለት ፓርቲሽን ይፍጠሩለት፡፡
9. ብዙ ሶፍትዌሮችን ባንዴ አይክፈቱ::
10. ኮምፒውተርዎን update ያድርጉ!
👍48❤5
ኮምፒውተራችን ክራሽ ወይም የሚዘጋበት የሚያደርገበት ዋና ዋና ምክንያቶች ምንድን ናቸው?


1⃣ የሀርድዌር መቃረን

ለ Windows ክራሽ የማድረግ ዋነኛው ምክንያት የ Hardware áˆ˜á‰ƒáˆ¨áŠ• ነው፡፡እያንዳንዱ Hardware áŠ­ááˆŽá‰˝ ለመግባባት IRQ(interrupt request channel) ያስፈልጋቸዋል፡፡ እነዚህ IRQ ለየሀርድዌሩ የተለዩ ወይም የተነጠሉ መሆን አለባቸው፡፡

ለምሳሌ አንድ ፕሪንተር IRQ 7 ሲኖረው ኪቦርድ ደግሞ IRQ 1፡፡እያንዳንዱ ሀርድዌር የራሱ የሆን IRQ ለመያዝ ጥረት ያደርጋል፡፡ ግን ብዙ የሀርድዌር እቃዎች ስንጠቀም ወይም የሀርድዌሩ ሶፍትዌር በስርዓት ካልተጫነ ሁለት ሀርድዌሮች ተመሳሳይ IRQ ሊጋሩ ይችላሉ፡፡ በዚህም ሰዓት ሁለት የሀርድዌር ዕቃዎች በተመሳሳይ ሰዓት ለመጠቀም ስንሞክር ክራሽ ሊከሰት ይችላል፡፡ 


2⃣ የተበላሸ ራም

ራም Ram (random-access memory) ችግሮች ዋናው የብሉ እስክሪን áŠŚá ዴዝ (blue screen of death) ዋና መንስኤ ሲሆን የሚያሳየው áˆ˜áˆáŠĽáŠ­á‰ľ ፋታል ኤክሰብሽን ኢረር( Fatal Exception Error) á‹¨áˆšáˆ ነው፡፡

ፋታል ኢረር የሚነግረን አሳሳቢ የሀርድዌር ችግር አለ ማለት ነው፡፡ አንዳንዴ የሀርድዌር ክፍል ስለተጎዳ መቀየር እንዳለበት ይናገራል፡፡ በራም የሚመጡ ችግሮች ብዙ ግዜ የራሙ ከኮምፒዉተሩ ጋር ሳይጣጣም ሲቀር ነው፡፡ ይህም ማለት ለኮምፒዉተር የራም ስሎት ጋር ሳይመጣጠን ሲቀር ፤ የራሱ ያልሆነ ሞዴል ስንጠቀም እና የተለያየ አይነት ራም በአንድ Computer á‹áˆľáŒĽ ስንጠቀም ነው፡፡ለምሳሌ 70ns ለይ 60ns ራም ስንጠቀም ኮምፒተሩን ፍጥነት ይቀንሳል፡፡ይሄ ደግሞ ራሙን ከአቅሙ በላይ ይጫነዋል በዚህ ግዜ window ክራሽ ያደርጋል፡፡


3⃣ባዬስ ሴቲንግ


እያንዳንዱ ማዘር ቦርድ ሲመረት የራሱ የሆነ የተለያዩ ቺፕሴት ሴቲንግ አብሮት ይጫናል፡፡ እነዚህን ሴቲንግ ለመጠቀም በኮምፒውተራችን ኪቦርድ ላይ F2 ወይም F10 (እንደ ኮምፒዉተሩ ይለያያል) ኮምፒዉተሩ ስንከፍት ከጥቂት ሰከንድ በኻላ በመንካት ሴቲንጉን አክሰስ ማድረግ ይቻላል፡፡

ነገር ግን አንዴ ባዮስ ዉስጥ ከገባን ከፍተኛ ጥንቃቄ ማድረግ አለብን፡፡ ማንኛውንም ሴቲንግ ከመቀየራችን በፊት ፎቶ ወይም ወረቀት áˆˆá‹­ ሴቲንጎቹን ማኖር አንድ ያበላሸነው ነገር ካለ በቀላሉ መቀየር ያስችለናል፡፡ብዙን ግዜ የባዮስ ችግር የራም ላተንሲ ችግር ነው፡፡

የድሮ ኮምፒዉተር ራም áˆ‹á‰°áŠ•áˆ˛ 3 ሲሆን የቅርብ ግዜ ራሞች ደግሞ ላተንሲ 2 ናቸው፡፡ ይሄንን ሴቲንግ በምንቀይርበት ጊዜ ኮምፒዉተሩ ክራሽ ያደርጋል ወይም ፍሪዝ ይሆናል፡፡


4⃣ቫይረስ


ቫይረሶች የኮምፒዉተር ፕሮግራም ሲሆኑ እራሳችውን በማብዝት ወይም ኮምፒዉተር ፋይሎች ላይ በማጣበቅ ከፍተኛ ጉዳት ሊያደርሱ ይችላሉ፡፡ 

ቫይረሶች የትእዛዞች ስብስብ ሆኖ እራሱን በሌላ የኮምፒዉተር ፕሮግራም ያጣብቃሉ(ብዙ ግዜ ኦፕሬቲንግ ሲስተሙን)፡፡ áŠŽáˆá’á‹‰á‰°áˆŤá‰˝áŠ• ውስጥ ቫይረስ ሲያጠቃ የኦፕሬቲንግ ሲስተሙን ፋይል የመቀየር ሀይል ስላለው ኮምፒዉተሩን ክራሽ ወይም ፍሪዚ ሊያረግ ይችላል፡፡


5⃣ከፍተኛ ሙቀት

በኮምፒዉተራችን ዉስጥ ካሉ ሀርድዌሮች በጣም አስፈላጊው እና ዋናው ሲፒዩ ነው፡፡ ሲፒዩ በኤሌትሪክ ሃይል የሚሰራ ሲሆን ካለው ውስብስብ የትራዚስተር ብዛት አማካኝነት የሚፈጥረው ከፍተኛ ሙቀት ሲፒዩን ሊያበላሸው ወይም ከጥቅም ውጪ ሊያደርገው ይችላል፡፡


ሲፒዩ ብዙ ጊዜ ከማቀዝቀዣ ቬንትሌተር áŠ¨áŠŽáˆá’á‹‰á‰°áˆŤá‰˝áŠ• አንድ ላይ ይመጣል፡፡ áŠĽáŠá‹šáˆ… ቬንትሌተር ከተበላሹ ወይም ሲፒዩ ካረጀ የኮምፒዉተራችን ሲፒዩ መጋል ይጀምራል፡፡ ይህ ደግሞ በኮምፒዉተራችን ላይ የከርንል ኢረር ያስከትላል፡፡


ይሄ ችግር ብዙ ጊዜ የሚታየው በኦቩር ክሎኪንግ ጊዜ ነው፡፡ ይህ ማለት ሲፒዩን ከሚገባው በላይ በማሰራት ወይም ከፍተኛ ፍጥነት እንዲገባ በማድረግ ነው፡፡ሲፒዩ በጣም ሲግል ኮምፒዉተራችን ሳናስበው እራሱን ይዘጋል ወይም ክራሽ ያደርጋል፡፡

6️⃣ ዊንዶውስ አፕዴትስ

የኮምፒውተራችን ኦፕሬቲንግ ሲስተም አፕዴት በሚያደርግበት ጊዜ ባልተፈለገ ሰአት ወይም ዊንዶው አፕዴት አድርጎ ሳይጠናቀቅ በኤሌክትሪክ ሀይል መቆራረጥ ምክንያት አፕዴት ሳይጨርስ በሚቋረጥበት ምክንያት ኮምፒውተራችን ላይ ችግር ሊፈጥር ይችላል።
👍60❤4👏3
ስልካችሁ ኦሪጅናል ነው ወይስ ፎርጅድ እራስዎ ማረጋገጥ ይችላሉ።
✅ ዌብሳይት ጥቆማ ይዤላኋለሁ

💎 http://www.imei.info

እዚህ  ዌብሳይት ውስጥ በመግባት የስልክዎን IMEI no (*#06#) ያስገቡና የሚመጣልዎ #መረጃ ስለራስዎ ስልክ  ከሆነ ስልኩ ኦርጅናል ነው፤ የሌላ #ስልክ ከሆነ ግን

✔️አሁን ላይ በተለይ በብዛት የሚስተዋለው አዲስም ሆነ ያገለገሉ የሚገዟቸው #ስልኮች (አንዳንድ ከስልክ ቤቶች የሚገዟቸውንም ይጨምራል) የሚሸጡልዎ IMEI number በመቀየር ነው ይህም #ስልክዎ ለጊዜው ቢሰራም ከዋናው ስልክ ጥራቱ የወረደ ነው። (RAM, internal storage, camera qualityው እንዲሁም የአገልግሎት ጊዜው ከኦርጅናሉ ስልክ ይቀንሳል)

✔️ስለዚህም ቼክ ሲያደርጉ የሌላ ስልክ መረጃ ከመጣልዎ ስልኩን ከመግዛት ይቆጥቡ።
#MCT

✅ Facebook:- https://m.facebook.com/MuhammedComputerTechnology/
✅ ቲክቶክ አካውንት tiktok.com/@mctplc
✅ የYouTube ቻናልን ሰብስካራይብ በማድረግ ወቅታዊ የቴክኖሎጂ መረጃን ያግኙ!
👇👇👇Subscribe👇👇👇
https://youtube.com/@muhammedcomputertechnology
የተቋምዎን  መረጃን ዲጅታላይዝ እናድርግልዎ ስንል በደስታ ነው!
👍53❤5👏1
የቻግኒ ከተማ አስተዳደር ማዘጋጃ ቤት የከተማ መሬት መረጃ አስተዳደር ስርዓት (Urban land Information Management System, ULIMS) ሶፍትዌር በቻግኒ ከተማ አስተዳደር ከተማና መሰረተ ልማት ጽ/ቤት ስልጠና መጀመራችን ይታወቃል በመሆኑም አሁን ላይ ፋይሉ በካይዘን ፍልስፍና በመታገዝ እየተደራጀ ሲሆን ስራውን በዲጅታል ቴክኖሎጂ በመታገዝ ወደ ሲስተም የማስገባት ስራ ተጀምሯል። በቅርቡ በማጠናቀቅ በይፋ እናስመርቃለን።

✅ ጊዜው የዲጅታል የቴክኖሎጂ ነው፡፡
ህልምዎን እውን የሚያደርጉ ሲስተሞችን, ድረ-ገጾችን (ዌብሳይቶችን) ለማሰራት  ይደውሉ። አሰራርዎን ዘመናዊ ያድርጉ!

🔴አድራሻ:-
✅ ስ.ቁ: 0929273364
✅ ዌብሳይት www.mctplc.com
✅ቴሌግራም አካውንት: https://t.me/mctplc
✅ በቴሌግራም ቻናል: https://t.me/MuhammedComputerTechnology
✅ email: mct16plc@gmail.com
✅ Facebook:- https://m.facebook.com/MuhammedComputerTechnology/
✅ ቲክቶክ አካውንት tiktok.com/@mctplc
✅ የYouTube ቻናልን ሰብስካራይብ በማድረግ ወቅታዊ የቴክኖሎጂ መረጃን ያግኙ!
👇👇👇Subscribe👇👇👇
https://youtube.com/@muhammedcomputertechnology
የተቋምዎን  መረጃን ዲጅታላይዝ እናድርግልዎ ስንል በደስታ ነው!
❤10👍7👏3