Muhammed Computer Technology (MCT)
38.1K subscribers
527 photos
7 videos
254 files
910 links
🔴አድራሻ:-
✅ ስ.ቁ: 0929273364
✅ ዌብሳይት www.mctplc.com
✅ቴሌግራም አካውንት: https://t.me/mctplc
✅ email: mct16plc@gmail.com
✅ ቲክቶክ አካውንት tiktok.com/@mctplc
Download Telegram
🔵 IDM (Internet Download Manager) Serial Number እየጠየቀ ለተቸገራችሁ፣ ማንኛውንም ፋይል ለማውረድ ስትሞክሩ Couldn't Find Server እያለ ካስቸገራችሁ በሚከተለው መንገድ ማስተካከል ትችላላችሁ

✅ በመጀመሪያ  www.internetdownloadmanager.com/downloads2 ውስጥ በመግባት Latest IDM version ያውርዱና ይጫኑት / Help * Check for updates

✅ በማስከተል ኮምፒውተርዎን ከኢንተርኔት ጋር Disconnect ያድርጉት

✅ በመቀጠልም ከስር ያለውን Fix IDM የሚለውን Zipped File extract አድርገው ውስጡ ላይ የሚገኘውን የ IDM activation.cmd የሚለውን bat file ይክፈቱ

✅ በማስከልም ከተዘረዘሩት ሜኑዎች Reset IDM activation / trial registry የሚለውን ለመምረጥና ፕሮሰሱን ለማስጀመር ኪቦርዳችሁ ላይ '2' ቁጥርን ይጫኑ

✅ ከዛ reset አድርጎ እስከሚጨርስ ድረስ ይጠብቁትና Press any key to exit ሲላችሁ ኪቦርድ ላይ ማንኛውንም ኪይ ይጫኑ

✅  አሁን ኮምፒውተራችሁን ከኢንተርኔት ጋር በማገናኘት ብሮውዘራችንን ከፍተን የምንፈልጋቸውን ፋይሎች ዳውንሎድ በማድረግ ያለሀሳብ IDM ን መጠቀም እንችላለን።
🫶 ይመቻችሁ 👌

🎯 መረጃውን ለወዳጅ ዘመድ ያጋሩ!! መልካም ቀን/ምሽት

➡️ ©muleritsolutions2
👍41❤14
Fix_IDM (2).rar
10.8 MB
🔵 IDM Serial Number እየጠየቀ ላስቸገራችሁ ከላይ በተጠቀሰው መንገድ ማስተካከል ትችላላችሁ

🆕 Lifetime IDM Downloader Active No Need Any Software or Patch 2023

🔅 Features IDM :

😀Lifetime activation with a single bat command

✅ No need for any software or patch

✅ Full-speed downloads and resume interrupted downloads

✅All other features of the premium version of IDM

🔰  Šmuleritsolutions2

ሶፍትዌሩን ቴሌግራም ላይ ማግኘት ይችላሉ
ቴሌግራም ቻናሌ
https://t.me/MuhammedComputerTechnology
👍31❤7
Muhammed Computer Technology (MC) YouTube Channel በአዲስ ዝግጅት የተለያዩ ቪዲዮችን በመስራት ተደራሽ እንሆናለን በYouTube ጠቃሚ ትምህርቶችን ለተመልካች እያቀረብኩ እገኛለህ። #57,100 በላይ #Subscribers ማግኘት የቻለ ተወዳጅ ቻናል ሁኗል ስለሆነም በYouTube በምለቀቃቸው Vedios ጠቃሚና አስተማሪ ሰልሆኑ #Subscribe በማድረግ #ይማሩ #ይወቁ
ያቀቁትን ማሳወቅ የተማሩትን ማስተማር ብልህነት ነው።
YouTube ቻናል ሊንክ
👇👇👇

https://www.youtube.com/channel/UCZBIP6PqUdmmagdTjbyp_AQ
https://www.youtube.com/channel/UCZBIP6PqUdmmagdTjbyp_AQ
https://www.youtube.com/channel/UCZBIP6PqUdmmagdTjbyp_AQ
👍13❤9👏3👎2
❇️ምርምር / Research / ምንድን ነው?❇️

ከጽሑፍ መረጃዎች መገንዘብ እንደሚቻለው ምርመር /Research/ ለሚለው ቃል አንድ ወጥና የማይለዋወጥ ትርጉም አልተገኘለትም፡፡ ምክንያቱም መስኩ ሰፊና በተለያዩ ምሁራን የተለያየ ማብራሪያ ሲሰጥበት የቆየ በመሆኑ ነው፡፡ አንዳንድ ጊዜ በአንዳንድ ምሁራን እጅግ በጣም ቀለለ ያለ ትርጉም ሲሰጠው በሌላ ጊዜና በሌሎች ምሁራን ደግሞ ላቅ ያለና ውስብስብ የሆነ ትርጉም ሰጥተውታል፡፡ ይህ እንዳለ ሆኖ በአጠቃላይ መልኩ ሲታይ ምርምር አዲስ ዕውቀትን ለማግኘትና የተገኘውንም እውቀት እውነተኛነት ለማረጋገጥ ወይም በእለት ተእለት እንቅስቃሴ የሚያጋጥመንን ችግር መፍትሄ ለማበጀት ሲባል ሥርዓት ባለው ሁኔታ የተቀነባበረና ሆን ተብሎ የሚከወን የሰው ልጅ የተግባር
እንቅስቃሴ ነው፡፡

በዚህም መሠረት በምርምሩ ሂደት ውስጥ የችግሩ ምንነት ይለያል፣ ስልት ይቀየሣል፣ይቀነባበራል፣ መረጃ ይሰበሰባል፣ ይገመገማል፣ ይተነተናል፣ ብሎም የተገኘው ውጤት በተቀነባበረ መልክ ይገለፃል፡፡ ከዚህም ሂደት በመነሳት ምርምር ሳይንሳዊ ይዘት አለው ማለት ይቻላል፡፡

❇️የምርምር /Research/ ዓይነቶች❇️

ልዩ ልዩ የምርምር ዓይነቶች አሉ፡፡ ከእነዚህ መካከል ለዚህ ጽሑፍ አስፈላጊ ናቸው የተባሉትንና ዋና ዋናዎቹን በሶስት ከፍሎ ማየት ይቻላል፡፡

1️⃣. ታሪክ ነክ ምርምር / Historical Study/

በዚህ የምርምር ዓይነት ተማራማሪው ያለፈን ታሪክ በማጥናትና በመመዝገብ ዕውቀቱን ያዳብራል፡፡ ይህ ዓይነት ምርምር ሲያዩት ቀላል ይመስላል፡፡ ሆኖም ግን ተማራማሪው የተነሳበትን መላምት ለማረጋገጥ የተለያዩ መረጃዎችን አሰባስቦ ማስረዳት መቻል ይኖርበታል፡፡

📌 ለምሳሌ አንድ ተመራማሪ ስለ ኢትዮጵያ ትምህርት ታሪክ ሲያጠና ለኢትዮጵያ ዘመናዊ ትምህርት መስፋፋት ከንግሥት ዘውዲቱ ይልቅ አጼ ምኒሊክ ከፍ ያለ አስተዋጽኦ አድርገዋል የሚለውን ሃሳብ ይዞ ቢነሳ ሐሳቡ እውነት ወይም ሀሰት መሆኑን በተለያዩ ዘዴዎች መረጃዎችን ሰብስቦ በማገናዘብ አሳማኝ ውሳኔ ላይ መድረስ ይኖርበታል፡፡

2️⃣. ገላጭ ምርምር

ይህ የምርምር ዓይነት የአንድን ሁኔታ ትክክለኛ ገጽታ ለማወቅ ወይም በትክክል ለመግለጽ ሲባል መረጃዎችን ከመጽሐፍትና ከሌሎችም ጥናታዊ የጽሑፍ ምንጮች በማሰባሰብና የምልከታ መረጃዎችን በማጠናቀር ትንተና በማድረግ የሚያጠና ሲሆን ውጤቱን በስድስት ንዑስ ክፍሎች ከፍሎ ማየት ይቻላል፡፡
እነሱም፡-
❇️ ሀ/ ውሱን ጥናት /Case study/
❇️ ለ/ አወዳዳሪ ጥናት /Comparative Study Study/Studies/
❇️ ሐ/ ዕድገት ተኮር ጥናት/developmental
❇️ መ/ ተከታታየነት ያለው ጥናት/follow up studies/
❇️ ሠ/ ተዛምዶን የሚያሳይ ጥናት /correlational/
❇️ ረ/ አሣሽ ጥናት/Survey Study/

ℹ️ 2.1. ውሱን ጥናት /case Study/

ይህ ዓይነቱ ምርምር የአንድን የተወሰነ ሁኔታ የአለፈ ታሪክ ጨምቆ በማጥናት አሁን ላለው ይዘትና ጠባይ በማብራሪያነት መጠቀምን ይመለከታል፡፡
📌 ለምሳሌ ተማራማሪው ስለ አንድ ተማሪ ጠባይ ማጥናት ይፈልጋል እንበል፡፡ ተማሪው በት/ቤቱ አስቸጋሪ
ፀበይ/ባህሪ ቢኖረው የጥናቱ ትኩረት በዚሁ በተማሪው ጠባይ ላይ ይሆናል፡፡ በጥናቱ ሂደት ሊነሳ የሚችለው ዋናው ጥያቄ ይህ ተማሪ ለምን እንዲህ ሆነ የሚለው ነው፡፡

በዚህ መሠረት ሊሰጡ ከሚችሉ መልሶች አጥኚው መላ መምታት ይችላል፡፡ ከመላ ምቶቹ ውስጥ፡-
✅ ከመምህራንና ተማሪዎች፣ የተቀባይነትና ጥሩ አመለካከት በማጣት፣ በትምህርቱ ውጤት ተስፋ በማጣት፣ ከቤተሰቦቹ አያያዝና አስተዳደግ የተነሳና ሌላም ሊሆኑ ይችላሉ፡፡

እንግዲህ የተማራማሪው ተግባር በልዩ ልዩ የምርምር ዘዴዎች ተጠቅሞ በየትኛው ምክንያት ተማሪው ለረብሻ እንደተገፋፋ ማወቅና መንስኤውን ካወቀ በኋላም ልጁ መልካም ጠባይ እንዲኖረው የተጠቀመባቸውን ዘዴዎች የጥናቱና ምርምሩ ውጤት ያደርጋቸዋል፡፡

ℹ️ 2.2. አሣሽ ጥናት / Survey study/

እንደዚህ ዓይነቱ ምርምር ስለአንዳንድ ማህበራዊ ክስተቶች መረጃዎችን አሰባስቦ በመተንተን ስለተጠናው ጉዳይ እውነተኛ ገጽታ መናገር የሚያስችል ነው፡፡
📌 ለምሳሌ ከአንደኛ ደረጃ ትም/ቤቶች ተማሪዎች በየጊዜው እየወጡ የሚቀሩት በምን ምክንያት ነው
በሚል ጥያቄ መነሻ ምርምር ማካሄድ ይቻላል፡፡

ውሱን ጥናት በተወሠነ ጉዳይ ላይ ጠለቅ ያለ ምርምር ማካሄድ ሲሆን አሣሽ ጥናት ደግሞ ሠፋ ባለ ርዕስ ጉዳይ ላይ በማተኮር አጠቃላይ መፍትሔ ለመሻት ነው፡፡

ℹ️ 2.3. አወዳዳሪ ጥናት /Comparative study/

ሁለት ወይም ከሁለት በላይ ሁኔታዎችን ወስዶ ስለእያንዳንዱ ጉዳይ በጥልቀት በማወቅ አንዱ ከሌላው የሚለይበትንና አንድ የሚሆንበትን ሁኔታ በግልጽ ማሳየት የሚቻልበት የምርምር ዓይነት ነው፡፡

📌 ለምሳሌ ለአንደኛ ደረጃ ት/ቤቶች መምህራን ሥልጠና የተሻለው ፕርግራም የቱ ነው በዲግሪ ወይም በዲፕሎማ ለሚለው ጥያቄ ምላሽ ለመስጠት የሁለቱን
ፕሮግራሞች ደካማና ጠንካራ ጎን ለመለየት ከዚህ በፊት በሁለቱም ፕሮግራሞች የሰለጠኑና በሥራ ላይ ያሉትን መምህራን የሥራ ውጤት በጥንቃቄ በመገምገም፣ የተሻለውን ፕሮግራም ማወቅ ያስችላል ማለት ነው፡፡

ℹ️ 2.4. ዕድገት ተኮር ጥናት / Developmental Studies/

ይህ ጥናት በተለያየ የዕድሜ ደረጃ ሕፃናት፣ ወላጆች፣ ተማሪዎች በየእርከኑ የሚያሳዩት የባሕሪይ ለውጥ ወይም የአስተሳሰብና የአእምሮ ዕድገት ለውጥን የማጥናት ሥልት ነው፡፡
ተማሪው በየክፍል ደረጃው በአንድ ወይም ከአንድ በላይ ባሉ የትምህርት ዓይነቶች የሚያስመዘግባቸውን ውጤቶች ተከታትሎ ማጥናትን እንደ ምሳሌ መውሰድ ይቻላል፡፡

ℹ️ 2.5. ተከታታይነት ያለው ጥናት / Follow-up studies/

ይህ ሥልት አንድ የትምህርት መርሃ ግብር ውጤታማ ስለመሆኑ ለአንድ ሙያ የሰለጠኑ ሰዎች በመስክ የሚያሳዩትን ለውጥ ወዘተ የምንገመግምበት ዘዴ ነው፡፡ በአዲሱ የሥርዓተ ትምህርት ትግበራ ወቅት በሙከራ ት/ቤቶች በ1ኛ እና 5ኛ፣ በ2ኛ እና 6ኛ፣ በ3ኛ እና 7ኛ
በ4ኛ እና 8ኛ ክፍሎች ሲካሄዱ የነበሩ ሂደታዊ ግምገማዎች እንደምሳሌ ሊጠቀሱ
ይችላሉ፡፡

ℹ️ 2.6. የተዛምዶ ጥናቶች /correlational studies/

የዚህ ዓይነቱ ሥልት
✳️ 1. ዕድሜ ከአእምሮ ጋር ያለውን ግንኙነት
✳️ 2. የአጠናን ሥልት ከትምህርት ውጤት ጋር ያለውን ዝምድና
✳️ 3. የአንደኛ ደረጃ ትምህርት ውጤት ለ2ኛ ደረጃ ትምህርት የሚኖረውን ዝምድናና
የመሳሰሉትን የምንዳስስበት ዘዴ ነው፡፡

3️⃣. የሙከራ ምርምር /Experimental Study/

ይህ እይነቱ ምርምር አንድን ሁኔታ በሙከራ አረጋግጦ ማየትን የሚመለከት ምርምር ነው፡፡

📌 ለምሳሌ በአፀደ ሕፃናት ፕሮግራም ውስጥ ካለፉና በቀጥታ ከቤታቸው ወደ አንደኛ ክፍል ከገቡ ሕፃናት ሒሣብን፣ አማርኛን፣ ሣይንስን፣ ወይም ሌላ ትምህርት የትኞቹ በይበልጥ እንደሚከታተሉ ሕፃናቱን ለይቶ በጥንቃቄ በመከታተል ማወቅ ይቻላል፡፡
ጥናቱ ተጀምሮ እስኪጠናቀቅ መረጃዎችን በጥንቃቄ መያዙ ለውጤቱ ትክክለኛነት እጅግ በጣም ወሳኝ ነው፡፡

📌 ለምሳሌ ከትምህርት ቤት ውጪ ተጨማሪ እገዛ ማግኘት አለማግኘታቸውን፣ የቤተሰብ ልዩነት አለመኖሩንና የቤተሰብ የኑሮ ሁኔታ ልዩነት ሁሉ መጤን ያለባቸው ነገሮች ናቸው፡፡

ምርጥ የResearch ቻናል።
👇👇👇Join👇👇👇
https://t.me/researchRC
👍33❤9
የቢዝነስ ፕላን (እቅድ) ዝግጅት
✅ የቢዝነስ ፕላን (እቅድ) ምን ማለት ነው?
▪ ማንኛውም አንተርፕራይዝ ሊተገብር ያሰበው የንግድ ስራ ግብና ዓላማ ምን እንደሆነ፣ የስራው ሂደት ምን
እንደሚመስልና እንዴት እንደሚሠራ እንዲሁም እያንዳንዱ ክንውን መቼ እንደሚሰራ የሚያስረዳ ዶኩመንት (ሰነድ) ነው፡፡
▪ የታለመውን ግብ ለመምታት የሚያስችል የአሰራር መመሪያን የያዘ ነው፡፡
▪ የኢንተርፕራይዙን የቢዝነስ /የንግድ ስራ አሰራር ፍኖተ ካርታ ያሳያል፡፡
▪ የኢንተርፕራይዙን የቢዝነስ/የንግድ ስራ ያለውን እድል ለገንዘብ ተቋማትና ባለሀብቶች ሊያስረዳ የሚችል ሰነድ ነው፡፡
▪ የኢንተርፕራይዙን የቢዝነስ/የንግድ ስራ ሊኖረው የሚችለውን ማንኛውንም እድል /ሁኔታ በመዘርዝር የሚታቀድበት በቂ ቅድመ ዝግጅት የሚደረግበት ነው፡፡

✅ የቢዝነስ / የንግድ ስራ ፕላን (እቅድ) ለምን ይዘጋጃል?

▪ የቢዝነስ / የንግድ ስራ ፕላን (እቅድ) በተዘጋጀው ግብና ዓላማ ላይ ትኩረት / አጽንኦት በመስጠት ስራን ለማከናወን ይረዳል፡፡
▪ የገንዘብ አቅምን ከተለያየ ምንጭ ለማግኘት ይረዳል፡፡
▪ ቢዝነሱ/የንግድ ስራው የሚጀመርበትንና ሊመራበት የሚገባውን ስርዓት በማሳየት አቅጣጫ ጠቋሚ ይሆናል፡፡
▪ በተነደፈው የቢዝነስ /የንግድ ስራ ዘርፍ ለመሰማራት ፍላጎት ካላቸው አጋር ድርጅቶች ጋር ግንኙነት ለመፍጠር
ይረዳል፡፡
▪ የተነደፈው የቢዝነስ /የንግድ ስራ የስኬት እድል ያለው መሆኑን ለማሳየት ይጠቅማል፡፡
▪ በኢንተርፕራይዙ ውስጥ ቢዝነሱን /የንግድ ስራውን ለማስተዳደር የሚያስፈልገው በቂ ችሎታ እንዳለ መኖሩንና ለሚመረተው ምርትና አገልግሎት የገበያ እድል መኖሩን ለማረጋገጥ ይጠቅማል፡፡
▪ ስራው ከተጀመረ በኃላ በጊዜ ሂደት ውስጥ በእቅድ ደረጃ የተቀመጠውን ውጤት በተግባር ከሚሆነው ጋር ለማወዳደር የቢዝነስ / የንግድ ስራ ፕላን (እቅድ) እንዴት ይዘጋጃል?
▪ በቢዝነስ / በንግድ ስራ ውስጥ የሚጠየቁ ማንኛውንም ጥያቄዎች በመዘርዘርና ለጥያቄዎቹ መልስ በመስጠት
▪ ከተጠየቁት / ሊጠየቁ ከሚችሉት ጥያቄዎች መካከል ምላሽ ለመስጠት ተጨማሪ መረጃ በማሰባሰብ
▪ አስፈላጊ የሆኑ መረጃዎችን በሙሉ በማሰባሰብ
▪ የተለያዩ አማራጮችን በማወዳደርና የተሻለውን አማራጭ ለመውሰድ በመወሰን።

✅ በቢዝነስ ፕላን (እቅድ) ምን ሊደረግ ይችላል?

▪ የቢዝነስ/ የንግድ ስራ ፕላን (እቅድ) አስቀድሞ ማዘጋጀት ለክትትል ይረዳል፡፡ ይህም ማለት በእቅድ የተያዘውን ስራ ከተከናወነው ስራ ጋር በማነጻጸር ለመገምገም ይጠቅማል፡፡
▪ ከገንዘብ ተቋማት እንዲሁም ፍላጎት ካላቸው አጋር ድርጅቶች ጋር ለሚደረግ ውይይት የመነሻ ሃሳብ ይሆናል፡፡

የቢዝነስ / የንግድ ስራ እቅድ ለጅምላ ንግድ፣ ለችርቻሮ ንግድ፣ አገልግሎት የሚሰጥ የንግድ ድርጀት፣ ምርት
የሚያመርት (አምራች) ድርጅት፣ ማንኛውም የንግድ ድርጅት፣ ለገንዘብ ተቋማትና ለንግድ ዘርፍ ባለቤቶችና ስራ አስኪያጆች ሊዘጋጅ ይችላል፡፡

✅ የቢዝነስ ፕላን (እቅድ) ገጽታ ምን ይመስላል?
▪ የተተየበና በጥራዝ የተቀመጠ፣ በንጽህና የተጠበቀ/የተያዘ፣ ማጠቃለያና እዝል ያለው (ዋናውን እቅድ ላለማስረዘም ማለት ነው)፣ እያንዳንዱ ገጽ የገጽ ቁጥር የተሰጠው፣ በሚመለከተው አባል የተፈረመ መሆን የተገባው ሲሆን የቢዝነስ እቅድ መድብል ብዙ ወይም ጥቂት መሆን የሚወሰነው እንደ ንግዱ የዘርፍ ዓይነት ነው፡፡

✅ የቢዝነስ / የንግድ ስራ ፕላን (እቅድ) ማንን ያካትታል?

▪ የንግድ ዘርፉ ተጠቃሚ የሆኑ ደንበኞችን፣ በዘርፉ የሚሰሩ ተወዳዳሪ ግለሰቦችና ድርጅቶች፣ አቅራቢዎች፣ ተቀጣሪዎች፣ ለገበያ የሚቀርቡ ምርቶች፣ የንግድ ስራው የሚካሄድበት ስፍራ ወይም አድራሻ፣ ለንግዱ ስራ የሚያስፈልገው ቁሳቁስ. ወዘተ
ሙሉ ቢዝነስ ፕላን PDF ማግኘት ከፈለጉ ከላይ ያለውን Amharic version Preparing business plan የሚለውን ይጠቀሙ።
👍30❤19
«የኢትዮጵያ መንግስት ከተባበሩት አረብ ኢምሬት ጋር በመተባበር በቀጣይ 3 አመታት 5ሚሊየን ፕሮግራመሮችን ለማፍራት እቅድ ይዘዋል።
ይህ ስልጠና ሲጠናቀቅ አለም አቀፍ ተቀባይነት ያለው ሰርተፍኬት ያገኛሉ::ትምህርቱ የሚሰጠው በኦን ላይን ሲሆን ከርሰዎ የሚሰፈልገው ሞባይል ወይ ላበቶፕ እና ኢንተርኔት ብቻ ነው ::ትምህርቱን በኢንተርኔት ከቤተዎ ሁነው ይማራሉ::
የሚሰጡ ትምህርቶች:-
1. Android Kotlin Development Fundamentals
2. Data Science Fundamentals
3. Programming Fundamentals

#Code_for_Change: Ethiopia's Path to Innovation and Growth!!
የ5 ሚሊዮን የኢትዮጵያ ኮደርስ ኢኒሼቲቭ ይፋ መደረጉ የሚያስገኘውን ሁለንተናዊ ጥቅሞች በተወሰነ መልኩ በመጠቆም የዚህ እድል ተካፋይ እንሁን።
1. Enhanced Educational Opportunities: ይህ ኢኒሼቲቭ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን በተለይም ወጣቶች ለዘመናዊው ዲጂታል ኢኮኖሚ ወሳኝ ክህሎት እንዲያገኙ ይረዳል።
2. Economic Empowerment፡ በዘርፉ በቂ እውቀት የሚያገኙ ኢትዮጵያውያን ከፍተኛ ክፍያ በሚያስገኙ የቴክኖሎጂና የስራ ፈጠራ ስራዎችን በመጠቀም ገቢያቸውን ለማሳደግና አጠቃላይ ሀገራዊ የኢኮኖሚ እድገትን ለመጨመር ያግዛል።
3. Cultural Exchange and Knowledge Transfer: ከተባበሩት አረብ ኤሚሬቶች ጋር በሚደረገው ሁለንተናዊ ትብብር የባህል ልውውጥንና ምርጥ ተሞክሮዎችን በትምህርትና በቴክኖሎጂ ለመጋራት ያስችላል።
4. Technological Advancements፡ በቴክኖሎጂ የተካኑ በርካታ ግለሰቦችን በማልማት ውጥኑ በኢትዮጵያ ውስጥ ባሉ የተለያዩ ኢንዱስትሪዎች የቴክኖሎጂ ፈጠራን በማስፋፋት ምርታማነትን እና ቅልጥፍናን ያሳድጋል።
5. Job Creation and Workforce Development: ኢኒሼቲቩ በቴክኖሎጂ ዘርፍና በተዘዋዋሪ በተዛማጅ የስራ ዘርፎች የስራ እድል በመፍጠር የስራ አጥነትን ችግር ከማቃለል በተጓዳኝ የሰለጠነ የሰው ሃይል ለመገንባት ያስችላል።
6. Global Competitiveness: ኢትዮጵያ ጠንካራ የቴክኖሎጂ ተሰጥኦ ፑል በማዘጋጀት በአለም አቀፍ የቴክኖሎጂ መልከዓምድር ላይ ተወዳዳሪ ተጫዋች ሆና ዓለም አቀፍ ቢዝነሶችን እንዲሁም ኢንቨስትመንቶችን ለመሳብ ምቹ ሁኔታን ይፈጥራል።
7. Sustainable Development፡ በአጠቃላይ ይህንን ኢኒሼቲቭ ከዘላቂ የልማት ግቦች ጋር በማጣጣም ጥራት ያለው ትምህርትንና ጤናማ የስራ ባህልን በማስተዋወቅ ለኢትዮጵያ የረዥም ጊዜ ብልጽግናና መረጋጋት ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያደርጋል።
The launch of the 5 Million Ethiopian Coders Initiative, in partnership with the UAE, delivers these comprehensive benefits. Empowering Ethiopia’s Future by Cultivating 5 Million Coders.
ለመመዝገብ ይህን ሊንክ ይጠቀሙ
https://ethiocoders.et
👍73❤8👎5
✅ኢንተርኔት_ስንጠቀም_የዳታ_ለመቆጠብ ከስር ያሉትን ዘዴዎች መጠቀም ትችላላቹ
❇️ጠቅላላ_የስልክ_ዳታን_ለመቆጠብ


❶ #setting ይጫኑ
❷ #data_usage ይጫኑ
❸ #option ወይም ... ከላይ እነዚህን ሶስት ነጥብ ይጫኑ
❹ #restrict_background_data ሚለውን ይጫኑ።
አፖች_ላይ_ዳታን_ለመቆጠብ
🔶እነዚህን መንገዶች ተጠቀሙ።


♻️Telegram_ላይ_ዳታን_ለመቆጠብ
❶ #Telegram ይክፈቱ
👇👇👇👇👇
❷ #setting ይጫኑ
👇👇👇👇👇
❸ #data_and_storage ይጫኑ
👇👇👇👇👇
❹ #when_using_mobile_data ይጫኑ
👇👇👇👇👇
❺ ራይት(✔) የተደረጉትን በሙሉ ያጥፉት

#Facebook_Lite_ላይ_ዳታን_ለመቆጠብ
❶ #facebook_lite ይክፈቱ
👇👇👇👇👇
❷ #setting ይጫኑ
👇👇👇👇👇
❸ #Data_Usage ይጫኑ
👇👇👇👇👇
❹ #data_saverን_on ያርጉት

✳️WhatsApp_ላይ_ዳታን_ለመቆጠብ
❶ #whatsappን ይክፈቱ
👇👇👇👇👇
❷ #option ወይም --- ከላይ እነዚህን ሶስት ነጠብጣብ ይጫኑ
👇👇👇👇👇
❸ #settingን ይጫኑ
👇👇👇👇👇
❹ #data_and_storage_usage ን ይጫኑ
👇👇👇👇👇
❺ #whan_using_mobile_data ን ይጫኑ
👇👇👇👇👇
❻ ራይት(✔) የተደረጉትን በሙሉ ያጥፉት

🔰Messenger_ላይ_ዳታን_ለመቆጠብ
❶ #Messenger ን ይክፈቱ
👇👇👇👇👇
❷ #setting ይጫኑ
👇👇👇👇👇
❸ #Data_saver ይጫኑ
👇👇👇👇👇
❹ #data_saverን on ያድርጉ
👍35❤4🤔4
iNSTALL Ge'ez 10.exe
3.8 MB
❖መጀመሪያ ይህን Software Computet ላይ install ያድርጉት!

✅ ከዛም አማርኛ መፃፍ ስትፈልጉ power ge'ez status phonetic Unicode Mode (ፎ) ላይ ያድርጉት

✅በ English መፃፍ ስትፈልጉ ደግሞ power ge'ez status English Mode (ኢ) ላይ አድርጉት።
━━━━━━ ⊙ ━━━━━━

        🗣➹share &Join Us
                 👇🏾👇🏾👇🏾
👍22❤6
💻 ኮምፒውተር ላይ በአማርኛ እንዴት እንደሚፃፍ ያውቃሉ?ሲጽፉስ ምን ያህል ይፈጥናሉ?
=========================

■ ጠቃሚ መረጃ ነው!! ላልደረሰው ያዳርሱ አሁኑኑ ሼር ያድርጉት፡፡

❖መጀመሪያ ከላይ የለቀቅንላችሁን Software ያወረዱ እና install ያድርጉት ከዛም አማርኛ መፃፍ ስትፈልጉ power ge'ez status phonetic Unicode Mode (ፎ) ላይ ያድርጉት በ English መፃፍ ስትፈልጉ ደግሞ power ge'ez status English Mode (ኢ) ላይ አድርጉት ከዛም የሚከተሉትን ኣጭር መግላጫ በትክክል ይመልከቱ።
⁉️ ሶፍትዌሩን ለማግኘት ከፈለጋችሁ ከቴግራም ቻናሌ ማግኘት ትችላላችሁ
👇👇👇👇👇👇👇👇👇 https://t.me/MuhammedComputerTechnology
◕ሀ➭H_ሁ➭Hu_ሂ➭Hi_ሃ➭Ha_ሄ➭Hy_ህ➭He_ሆ➭Ho

◕ለ➭L_ሉ➭Lu_ሊ➭Li_ላ➭La_ሌ➭Ly_ል➭Le_ሎ➭Lo

❖ሐ➭Shift+h_ሑ➭Shift+hu_ሒ➭Shift+hi_ሓ➭Shift+ha_ሔ➭Shift+hy_ሕ➭Shift+he_ሖ➭Shift+ho

◕መ➭M_ሙ➭Mu_ሚ➭Mi_ማ➭Ma_ሜ➭My_ም➭Me_ሞ➭Mo

❖ሠ➭Shift+s_ሡ➭Shift+su_ሢ➭Shift+si_ሣ➭Shift+sa_ሤ➭Shift+sy_ሥ➭Shift+se_ሦ➭Shift+so

◕ረ➭R_ሩ➭Ru_ሪ➭Ri_ራ➭Ra_ሬ➭Ry_ር➭Re_ሮ➭Ro

◕ሰ➭S_ሱ➭Su_ሲ➭Si_ሳ➭Sa_ሴ➭Sy_ስ➭Se_ሶ➭So

❖ሸ➭Shift+s_ሹ➭Shift+su_ሺ➭Shift+si_ሻ➭Shift+sa_ሼ➭Shift+sy_ሽ➭Shift+se ሾ➭Shift+so

◕ቀ፡➭Q ቁ፡➭Qu ቂ፡➭Qi ቃ፡➭Qa ቄ፡➭Qy ቅ፡➭Qe ቆ፡➭Qo

◕በ፡➭B ቡ፡➭Bu ቢ፡➭Bi ባ፡➭Ba ቤ፡➭By ብ፡➭Be ቦ፡➭Bo

◕ተ፡➭T ቱ፡➭Tu ቲ፡➭Ti ታ፡➭Ta ቴ፡➭Ty ት፡➭Te ቶ፡➭To

◕ ቸ፡➭C ቹ፡➭Cu ቺ፡➭Ci ቻ፡➭Ca ቼ፡➭Cy ች፡➭Ce ቾ፡➭Co

◕ነ፡➭N ኑ፡➭Nu ኒ፡➭Ni ና፡➭Na ኔ፡➭Ny ን፡➭Ne ኖ፡➭No

❏ኘ፡➭Shift +n ኙ፡➭Shift +nu ኚ➭Shift+ni ኛ፡➭Shift +na ኜ፡➭Shift +ny ኝ፡➭Shift + ne ኞ፡➭Shift +no

◕ከ፡➭Ka ኩ፡➭Ku ኪ፡➭Ki ካ፡➭Ka ኬ፡➭Ky ክ፡➭Ke ኮ፡➭Ko

❖ ኸ ☛capslock + Shift + h
ኹ ☛capslock + Shift + hu
ኺ ☛capslock + Shift + hi
ኻ ☛Capslock + Shift + ha
ኼ ☛Capslock + Shift + hy
ኽ ☛Capslock + Shift + he
ኾ ☛Capslock + Shift + ho

❏ኀ፡➭ Capslock + H ኁ፡➭ Capslock + HU ኂ፡➭Capslock + HI ኃ፡➭Capslock + HA ኄ፡➭Capslock + HY ኅ፡➭Capslock + HE ኆ፡➭Capslock + HO

❏አ፡➭Capslock X ኡ፡➭Xu ኢ፡➭Xi ኣ፡➭Xa ኤ፡➭Xy እ፡➭Xe ኦ፡➭XoDe

❖ዐ፡➭Shift +x ዑ፡➭Shift +xu ዒ➭Shift +xi ዓ፡➭Shift +xa ዔ➭Shift +xy ዕ፡➭Shift +xe ዖ➭Shift +xo

✪ወ፡➭W ዉ፡➭Wu ዊ፡➭Wi ዋ፡➭Wa ዌ፡➭Wy ው፡➭We ዎ፡➭wo

✪ዘ፡➭Z ዙ፡➭Zu ዚ፡➭Zi ዛ፡➭Za ዜ፡➭Zy ዝ፡➭Ze ዞ፡➭Zo

❏ዠ፡➭Shift + Z ዡ፡➭Shift + Zu ዢ፡➭Shift + Zi ዣ፡➭Shift +Zaዤ፡➭Shift + Zy ዥ፡➭Shift +Ze ዦ፡➭Shift + Zo

✪ፈ፡➭F ፉ➭Fu ፊ፡➭Fi ፋ፡➭Fa ፌ፡➭Fy ፍ፡➭Fe ፎ፡➭Fo

✪ ፐ፡➭P ፑ፡➭Pu ፒ፡➭Pi ፓ፡➭Pa ፔ፡➭Py ፕ፡➭Pe ፖ፡➭Po

✪ገ፡➭G ጉ፡➭Gu ጊ፡➭Gi ጋ፡➭Ga ጌ፡➭Gy ግ፡➭Ge ጎ፡➭Go

✪ደ፡➭D ዱ፡➭Du ዲ፡➭Di ዳ፡➭Da ዴ፡➭Dy ድ፡➭ዶ፡Do

❏ጠ፡➭Shift + t ጡ፡➭Shift + tu ጢ፡➭Shift + ti ጣ፡➭Shift+ta ጤ፡➭Shift + ty ጥ፡➭Shift + te ጦ፡➭Shift + to

❏ጨ፡➭Shift +c ጩ፡➭Shift +cu ጪ፡➭Shift +ci ጫ፡➭Shift+caጬ፡➭Shift +cy ጭ፡➭Shift +ce ጮ: ➭Shift +co

❏ጸ፡➭Capslock + t ጹ፡➭Capslock + tu ጺ፡➭Capslock + ti ጻ፡➭Capslock + ta ጼ፡➭Capslock + ty ጽ፡➭Capslock + t ጾ፡➭Capslock + to

❖ ፀ➭☞Capslock+Shift+t
ፁ➭☞Capslock+Shift+tu
ፂ➭☞Capslock + Shift + ti
ፃ➭☞Capslock + Shift + t
ፄ➭☞Capslock + Shift + ty
ፅ➭☞Capslock + Shift + te
ፆ➭☞Capslock + Shift + to

✪ጀ፡➭J ጁ፡➭Gu ጂ፡➭Ji ጃ፡➭Ga ጄ፡➭Gy ጅ፡➭Ge ጆ፡➭Jo

✪ቨ፡➭V ቩ፡➭Vu ቪ፡➭Vi ቫ፡➭Va ቬ፡➭Vy ቭ፡➭Ve ቮ፡➭Vo
▁▁▁▁▁▁▁▁▁▁

ቋ➭Capslock+qwa ቧ➭Capslock+bwa
ቷ➭Capslock+twa
ኟ➭Capslock +Shift+nwa
ቿ➭Capslock+cwa ሟ➭Capslock+mwa
ቷ➭Capslock+twa ጓ➭Capslock gwa
ፏ➭Capslock+fwa ሯ➭Capslock +rwa ዷ➭Capslock+dwa ቯ➭Capslock+vwa ኋ➭Capslock+hwa ዟ➭Capslock+zwa ዧ➭Capslock+Shif+zwa
ኗ➭Capslock+nwa ሏ➭Capslock+lwa
ኳ➭Capslock+kwa ሷ➭Capslock+swa
ጇ➭Capslock+jwa ጧ➭Capslock+twa

♨️የተቸገሩ ሰዎችን በጣም ይጠቅማቸዋል አሁኑኑ ሼር ያድርጉ፡፡
━━━━━━ ⊙ ━━━━━━
👍92❤19🥰7
ከመረጃ ማሰሻዎች/ browsers/ጋር ተያይዘው ሊፈጠሩ የሚችሉ የመረጃ ምዝበራዎችን እንዴት መከላከል እንችላለን

የበይነ-መረብ አገልግሎትን ለማግኘት በምንፈልግበት ወቅት ኢንተርኔት ኤክስፕሎረር/ Internet Explorer/ ፣ ሳፋሪ /Safari/ ፣ ክሮም/Chrome/ ፣ ፋየርፎክስ /Firefox/ ወይም ኦፔራ (opera) እንጠቀማለን፡፡ እነዚህ የመረጃ ማሰሻዎች ደግሞ በተጠቃሚዎች ሊደርሱ የሚችሉ የመረጃ ስርቆቶችን እና የመረጃ ጥቃቶችን መከላከል የሚያስችል አማራጮችን ተግብረዋል፡፡
የክሮም ተጠቃሚ ከሆኑ “Advanced Settings;” የፋየርፎክስ “Options” menu; ፣ የኢንተርኔት ኤክስፕሎረር “Internet Options” ፣ የሳፋሪ ተጠቃሚዎች ደግሞ “Preferences” አማራጮችን በመጫን የደህንነት ስርዓታቸውን ማስተካከል ይቻላሉ፡፡ በመሆኑም ደህንነቱ የተጠበቀ የመረጃ አሰሳ ለማድረግ ተጠቃሚዎች ሊተገብሯቸው ከሚገቡ የደህንነት አማራጮች ውስጥ፡ የሚከተሉት ይገኙበታል፡-
1. 'በብሮውዘሮቻችን' ውስጥ የተቀመጡልንን አማራጮች በመከተል የግላዊነት እና የደህንነት ቅንብሮችን ማስተካከል
2. የኮምፒውተሮቻችን ደህንነት ደረጃ ከፍ የሚያደርጉ አማራጮችን ተግባራዊ ማድረግ፡፡ ለመረጃ ጥቃት ተጋላጭ የሚያደርጉንን አማራጮች አገልግሎት ማገድ/ Disabling features /
3. የይለፍ-ቃሎችን በመረጃ ማሰሻችን 'ብሮውዘሮች' ላይ አለማስቀመጥ/ Don’t save passwords/ 'ብሮውዘሮች' ላይ የይለፍ-ቃላትን እንዲቀምጡ መፍቀድ ምቹ ሊሆን ይችላል ግን የደህንነት አደጋዎችን ይፈጥራል፡፡
4. በ'ብሮውዘሮች' ላይ የምንተገብራቸውን ተሰኪ /plug-ins/ ሶፍትዌሮችን በጥንቃቄ መምረጥ
5. ብሮውዘሮችን በመደበኛነት ማዘመን፡ የመረጃ ማፈላለጊያዎች እንደ ሌሎች ሶፍትዌሮች ሁሉ መደበኛ ማዘመኛዎች ይቀርቡላቸዋል፡፡ የሚቀርቡ ማዘመኛዎች ለሚፈጠሩ የሶፍትዌር ክፍተቶች መሙያንት ያገለግላሉ፡፡ በመሆኑም ተጠቃሚዎች የሚለቀቁ የደህንነት ማዘመኛዎችን በመደበኛነት መጠቀም ይገባቸዋል፡፡
6. ለተጠቃሚዎች የሚቀርቡ የደህንነት አማራጮችን ማውረድ እና ማዘመን
እነዚህን 'ብሮውዘሮች' በቤትዎ ወይም በመስሪያቤትዎ አላስፈላጊ አደጋዎችን እንዳይፈጥሩ ለመከላከል ከላይ የተቀመጡ አማራጮቸን ተግባራዊ ማድረግዎን ያረጋግጡ ፡፡
👍21❤3🔥1🥰1😍1
በድረ-ገጽ የሚሰጡ  የሰው ሰልሽ አስተውሎት ትምህርቶች ጥቆማ

ሰርተፊኬት ከሚያስገኙ የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ የኦንላይን ትምህርቶች መካከል ጥቂቶቹን እናስተዋውቃችሁ፡፡ አንዳንዶቹ ትምህርቶች በነጻ የቀረቡ ሲሆን ቀሪዎቹ ደግሞ ትምህርቶቹን በነጻ ተከታትለዉ ሰርቲፊኬቱን ለማግኘት ክፍያ የሚጠይቁ ናቸዉ፡፡ በሌላ በኩል ነጻ የሙከራ አማራጭን በጊዜ ገደብ በማመቻቸት ክፍያ የሚጠይቁም ይገኙበታል፡፡

እርስዎም ለዘርፉ ፍላጎት ካለዎት ከዝርዝሮቹ የሚስማማዎትን በመምረጥ ለመጪው ጊዜ የመወዳደሪያ አቅም የሚሆንዎትን እውቀት ይገበዩ ዘንድ ጥቆማችንን እነሆ ብለናል፡፡  

1. AI for Beginners:
https://microsoft.github.io/AI-For-Beginners/

2. Prompt Engineering and Advanced ChatGPT:
https://www.edx.org/learn/computer-programming/edx-advanced-chatgpt

3. CS50's Introduction to Artificial Intelligence:
https://www.edx.org/learn/artificial-intelligence/harvard-university-cs50-s-introduction-to-artificial-intelligence-with-python

4. Machine Learning with Python:
https://www.coursera.org/learn/machine-learning-with-python

5. Artificial Intelligence with Python:
https://www.mygreatlearning.com/academy/learn-for-free/courses/artificial-intelligence-with-python

ለ ጓደኞቻችሁ ሼር አርጉላቸው 👇👇

📌Join and share 👇👇👇

➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖
✦Join➬ https://t.me/MuhammedComputerTechnology
✦Join➬  https://t.me/MuhammedComputerTechnology
➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖
👍46👏6🔥3❤1
ጉዞ ወደ ዲጅታላይዜሽን ታላቅ የዲጅታል ሲሳተም ማስመረቅ ፕሮግራም‼️‼️‼️

✅ በአዘና ከተማ ማዘጋጃ ቤት ዲጅታል የከተማ መሬት መረጃ አስተዳደር ስርአት Urban Land Information Management System (ULIMS) በማበልጸግ ተግባራዊ ማድረግ ችለናል።

✅ በአንድ ከተማ፣ ወረዳ ውስጥ ያለውን የግለሰብ፣ የመንግስት፣ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች የይዞታ ሙሉ መረጃን የሚያዘምን፣ ሁሉንም አሰራር በፊት ሲሰራ ከነበረው የወረቀት አሰራር በመውጣት ደስክቶፕ ኮምፒውተር፣ ላፕቶፕ ኮምፒውተር፣ ሞባይል፣ ታብሌት ሞባይሎችን በመጠቀም የሚያስችል እግጅ ዘመናዊ ወቅቱን የሚመጥን የዲጅታል ቴክኖሎጂን ማስመረቅ ችለናል።

✅ በተጨማሪም የማዘጋጃ ቤቱን ሁሉንም ነባርና አዲስ የባለይዞታዎችን ፋይል መረጃ 100% ሲስተም ወስጥ በመዝገብ ስራቸውን ዘመናዊ ማድረግ ችለናል።

✅ በካይዘን በማደራጅተ የፋይል አደረጃጀቱን ዘመናዊ ማድረግ የተቻለ ሲሆን ይህንን የካይዘን የፋይል አደረጃጀት በጥራት በመስራት የማዘጋጃ ቤቱ ስራ አስኪያጅ አቶ ወንድም ምህረት አነሳሽነት መስራት ተችሏል።

✅ በምረቃ ፕሮግራሙም የአዊ ዞን ብሔረሰብ አስተዳደር አስተዳዳሪ አቶ ቴዎድሮስ እንዳለው፣ የብሔረሰብ ዞን ም/ አስተዳዳሪና የከተማና መሰረተ ልማት መምሪያ ሀላፊ አቶ አይተነው ታዴ እንዲሁም ሌሎች የዞኑ ከፍተኛ አመራሮች፣ የዞኑ የሚገኙ የማዘጋጃ ቤት ስራ አስኪያጅና ቡድን መሪዎች፣ የአየሁ ጓጉሳ ወረዳ አስተዳዳሪ አቶ ገበየሁ በሪሁን አንዲሁም የወረዳው ከፍተኛ አመራሮች የአዘና መሪ ማዘጋጃ ቤት ስራ አስኪያጅ አቶ ወንድም ምህረትና የማዘጋጃ ቤቱ ቡድን መሪዎችና ባለሙያዎች፣ የአዘና ከተማ ማህበረሰቦች በተገኙበት ማስመረቅ ችለናል።
👍14❤6
ጉዞ ወደ ዲጅታላይዜሽን ታላቅ የዲጅታል ሲስተም ማስመረቅ ፕሮግራም‼️‼️‼️

✅ በአዘና ከተማ ማዘጋጃ ቤት ዲጅታል የከተማ መሬት መረጃ አስተዳደር ስርአት Urban Land Information Management System (ULIMS) በማበልጸግ ተግባራዊ ማድረግ ችለናል።

✅ በአንድ ከተማ፣ ወረዳ ውስጥ ያለውን የግለሰብ፣ የመንግስት፣ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች የይዞታ ሙሉ መረጃን የሚያዘምን፣ ሁሉንም አሰራር በፊት ሲሰራ ከነበረው የወረቀት አሰራር በመውጣት ደስክቶፕ ኮምፒውተር፣ ላፕቶፕ ኮምፒውተር፣ ሞባይል፣ ታብሌት ሞባይሎችን በመጠቀም የሚያስችል እግጅ ዘመናዊ ወቅቱን የሚመጥን የዲጅታል ቴክኖሎጂን ማስመረቅ ችለናል።

✅ በተጨማሪም የማዘጋጃ ቤቱን ሁሉንም ነባርና አዲስ የባለይዞታዎችን ፋይል መረጃ 100% ሲስተም ወስጥ በመዝገብ ስራቸውን ዘመናዊ ማድረግ ችለናል።

✅ በካይዘን በማደራጅተ የፋይል አደረጃጀቱን ዘመናዊ ማድረግ የተቻለ ሲሆን ይህንን የካይዘን የፋይል አደረጃጀት በጥራት በመስራት የማዘጋጃ ቤቱ ስራ አስኪያጅ አቶ ወንድም ምህረት አነሳሽነት መስራት ተችሏል።

✅ በምረቃ ፕሮግራሙም የአዊ ዞን ብሔረሰብ አስተዳደር አስተዳዳሪ አቶ ቴዎድሮስ እንዳለው፣ የብሔረሰብ ዞን ም/ አስተዳዳሪና የከተማና መሰረተ ልማት መምሪያ ሀላፊ አቶ አይተነው ታዴ እንዲሁም ሌሎች የዞኑ ከፍተኛ አመራሮች፣ የዞኑ የሚገኙ የማዘጋጃ ቤት ስራ አስኪያጅና ቡድን መሪዎች፣ የአየሁ ጓጉሳ ወረዳ አስተዳዳሪ አቶ ገበየሁ በሪሁን አንዲሁም የወረዳው ከፍተኛ አመራሮች የአዘና መሪ ማዘጋጃ ቤት ስራ አስኪያጅ አቶ ወንድም ምህረትና የማዘጋጃ ቤቱ ቡድን መሪዎችና ባለሙያዎች፣ የአዘና ከተማ ማህበረሰቦች በተገኙበት ማስመረቅ ችለናል።

✅ አቶ ወንድም ምህረት ይህንን የዲጅታል ሲስተም በማዘጋጃ ቤቱ ለመተግበር በሀሳብ አመንጭነት፣ በሲሳተም ስራው ላይ ከፍተኛ ክትትል፣ ደጋፍ፣ ሀሳብ በመስጠት እጅግ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ስላደረገልኝ ከልቤ ላመሰግን እወዳለሁ።

✅ የካይዘን አደርጃጀቱ በጥራት የተሰራ ሲሆን መደበኛ የፋይል ቤት ውስጥ ያለው መረጃና የዲጅታል ሲስተሙ በአንድ አይነት የካይዘንና የሲስተም ፋይል አደረጃጀት ማድረግ ችለናል።

✅ ይህ የዲጅታል ሲስተምና የፋይል ቤት የካይዘን አደረጃጀት እጅግ በጣም ውጤታማ  በመሆኑ ሌሎች ከተማ ማዘጋጃ ቤቶች ላይ ተግባራዊ ለማድረግ ዝግጅታችን አጠናቅቀን በመጠበቅ ላይ ስለሆንን በማንኛው ከተማ ማዘጋጃ ቤቶች ምንም አይነት ወጭ ሳታወጡ ተግባራዊ ለማድረግና ለመጠቀም ፈቃደኛ የሆና ማንኛውም ከተማ በሚከተለው አድራሻ መደወል ይችላሉ።

☎️ 0929273364
ቴሌግራም አድራሻ 👉 @ma1000me
የቴሌግራም ቻናል 👉 https://t.me/MuhammedComputerTechnology
👍28❤6
👍3❤1😁1