Muhammed Computer Technology (MCT)
38.1K subscribers
527 photos
7 videos
254 files
910 links
🔴አድራሻ:-
ስ.ቁ: 0929273364
ዌብሳይት www.mctplc.com
ቴሌግራም አካውንት: https://t.me/mctplc
email: mct16plc@gmail.com
ቲክቶክ አካውንት tiktok.com/@mctplc
Download Telegram
በአጋርፋ ግብርና ኮሌጅ የ Students Information Management System ስልጠና በመስጠት ወደ ተግባር እንዲገባ ማድረግ ችለናል። አንጋፋው አጋርፋ ግብርና ኮሌጅ
የኮሌጁ ዲኖች፣ የትምህርት ክፍል ተጠሪዎች፣ መምህራኖች፣ የሬጅስትራር ሀላፊ፣ የሬጅስትራር ባለሙያዎች፣ ለተማሪዎች ስልጠና በመስጠት የኮሌጁን ነባር ተማሪዎችና አዲስ ተማሪዎችን መረጃ እንዲገባ በማድረግ አሰራር ከማንዋል ወደ ዲጂታላይዝ አሰራ በመቀየር ሲስተሙን ኦንላይን ማድረግ ችለናል። ለዚህም ስልጠናና ተግበራ መሳካት የኮሌጁ ዲን ዶ/ር ጫላ ፈየራ፣ የኮሌጁ የሬጅስትራር ሀላፊ አቶ በቀለ አብዲሳ እንዲሁም የኮሌጁ የማኔጅመንት አባላትን ላመሰግናቸው እወዳለሁ።

በስልጠናውም የኮሌጁ ዲን ዶ/ር ጫላ ፈየራ፣ የኮሌጁ አካዳሚክ ዲን አቶ አብርሀም ተስፉ፣ የሬጅስትራት ሀላፊው አቶ በቀለ አብዲሳ እንዲሁም መመህራን፣ ዲፓርትመንት ሀላፊዎችና ተማሪዎች አሰራሩ ዲጅታል በመሆኑ ደስተኛ መሆናቸውን ገልጸውልኛል። እኔም በነበረኝ ቆይታ ደስተኛ መሆኔን እገልፃለሁ።

በነበረኝ ቆይታ የስልጠናውን በከፊል ፖስት አድርጌላችኋለሁ።

ለበለጠ መረጃ 0923233955 መደወል ይቻላል።
👍2810😁1
YouTube ላይ ቪዲዮ ዳውንሎድ ማድረግ
ከ YouTube ላይ ቪዲዮችን ዳውንሎድ ለማድረግ የሚያገለግሉ ብዙ ሶፍትዌሮች ኢንተርኔት ላይ ይገኛሉ፡፡ አንዳዳቹን በነፃ ሌሎቹን ደግሞ በክፍያ ነው ዳውንሎደ የሚደረጉት፡፡ ቪዲዮችን ዳውንሎድ ከማድረጋችን በፊት ዳውንሎድ የምናደርግበትን ሶፍትዌር እራሱ ዳውንሎድ ማድረግ ወይንም ከሌላ ኮምፒውተር ላይ ኮፒ ማድረግ ይኖርብናል፡፡
ዳውንሎድ ማድረግ ወይንም ማውረድ ማለት ምን ማለት ነው?
ማንኛውንም አይነት ፋይል (ቪዲዮ፤ድምጽ፤ጽሁፍ፤ስእል ….) ከኢንተርኔት ላይ ወደ ኮምፒውተራችን ኮፒ የምነዳርገበት መንገድ ዳውንሎድ ይባላል፡፡ ምሳሌ፡ ከ YouTube ላይ ቪዲዮ ስናወርድ/ዳውንሎድ ስናደርግ ቪዲዮውን ከ ዌብሳይት ላይ ወደ ኮምፒውተረችን ኮፒ አደረግን ማለት ነው በተመሳሳይ መጽሀፍት፤ፊልሞች ወይንም ጌሞችን ከኢንተርኔት ላይ ወደ ኮምፒውተራችን ኮፒ ስናደርግ ዳውንሎደ አደረግን ማለት ነው፡፡
ከ YouTube ላይ ቪዲዮችን ለማውረድ/ዳውንሎደ ለማድረግ ተጨማሪ ለዳውንሎድ ማድረጊያ ተብለው የተዘጋጁ ሶፍተትዌሮች ያስፈልጉናል፡፡ ከ ለማውረድ ከሚያገለግሉ ሶፈትዌሮች መከካል Internet Download Manager (IDM) በብዙዎች ዘንድ ተመራጭ ነው። ግን እሱ ብቻ ነው ዳውንሎደ ማድረጊያ ማለት አይደለም፡፡ በዛሬው ቱቶሪያላችን ከ ደውንሎደ መማድረጊያ ሶፍትዌሮች ሶስቱን እናያለን፡፡
Internet Download Manager (IDM)
በብዙዎች ዘንድ ተመራጭ እና ተወዳጅ ነው ፡፡ከቪዲዮ ባሻገር የተለያዩ የፋይል አይነቶችን ዳውንሎድ ማድረግ ይችላል፡፡ ነፃ ሶፍትዌር አይደለም ፡፡ይህን ሶፍትዌር የሚያመርተው ድርጅት ሶፍትዌሩን ለ 30 ቀን የሙከራ ጊዜ ይሰጠናል ከተባለው ቀን በኋላ ከተመቸን እንድንገዛ ካልተመቸን ደግሞ ከኮምፒውተራችን እንድናሰስወግደው አድርጎ ነው የሚሰራው፡፡እንደ ሶፍትዌሩ አምራች ከሆነ ኮምፒውተራችን ላይ ከተጫነ ከ 30 ቀን በላይ አያገለግለንም ማለት ነው፡፡ በእኛ ሀገር ሁኔታ በኢንተርኔት አማካኝነት መገበያየት ስለማንችል ያለን አማራጭ ሶፍትዌረን ለ 30 ቀን ተጠቅመን ማስወገድ ወይንም ሶፍትዌሩን ክራክ በማድረግ የአግልግሎት ጊዜውን ማስቀጠል ነው፡፡እዚህ ጋር ክራክ ማድረግ ማለት ሶፍትዌሩን ሳንገዛው አንደ ገዛነው ማድረግ ማለት ነው፡፡
የ IDM አጫጫን
1. መጀመሪያ IDM ዳውንሎድ ያድርጉ (IDM የሚለውን ክሊክ በማድረግ ዳውንሎድ ያድርጉ)
2. ብራውሰራችንን እንዝጋ
3. ዚፕ ፈይሉን ይክፈቱት ከዛም ኤክስትራክት የድርጉት
4. Setup የሚለውን አቃፊይክፈቱ
5. idman615 የሚለውን እንደገና ይክፈቱ
6. Accept ሚለውን ይምረጡ
7. ኢንስታሌሽኑ አስኪያልቅ ድረስ Next የሚለውን መጫን
* ክራክ እንዴት እንደምናደርግ Installation የሚለውን በመክፈት ማንበብ ይቻላል
ዳውንሎድ አደራረግ
የተለያዩ አይነት ፋይሎችን ማውረድ እንደሚችል ጠቅሰናል እንደ ምሳሌ ግን የምናየው ቪዲዮ ፋይሎችን እንዴት እንደምናወርድ ነው፡፡
1. YouTubeን እንከፍታለን
2. የምንፈልገውን የቪዲዮ ስም በመፈለጊያ ሳጥን ውስጥ እንፃፍለት ቀጥሎም Search ውይንም ኢንተርን መጫን
3. ከሚመጡት የቪዲዮ ዝርዝሮች መካከል የምንፈልገው ላይ ክሊክ በማድረግ መክፈት
4. ቪዲዮው ሎድ አድርጎ መጫወት ሲጀምር ከቪዲዮው ማጫወቻ ሳጥን ከላይ በቀኝ በኩል Download video የሚል ይመጣልናል ቀጥሎም የምንፈልገውን የፋይል አይነት በመምረጥ Start now ማለት ነው
5. ዳወነንሎድ አደርጎ እስኪጨርስ እንደ ፋይሉ መጠን እና እንደ ኢንተርኔቱ ፍጥነት ጊዜ ይወስዳል
6. ዳውንሎደ አድርጎ ሲጨርስም መጨረሱን ይገልጽልናል
7. እኛ ካልቀየርነው በስተቀር ዳውንሎድ የሚያደርጋቸውን ፋይሎች በ Downloads ፎልደር ውስጥ ነው የሚያስቀምጠው ፤ ለጊዜው ዳውነሎደ ያደረግነው ቪዲዮ ስለሆነ ዳውንሎደ የደረግነውን ፋይል የምናገኘው Downloads ---> Videos የሚለው ፈልደር ውስጥ ይሆናል ማለት ነው፡፡
Free Download Manager (FDM)
FDM እንደ IDM ዳውንሎደ ለማድረጊያ ሶፍትዌር ነው፡፡ በነፃ ደውንሎድ የሚደረግ ሲሆን እስከፈለግነው ጊዜ ድረስ ክራክ ማድረግ ሳያስፈልገን የምንጠቀምበት ሶፍትወዌር ነው፡፡
FDM ከ IDM የሚለየው በነፃ የሚገኝ መሆኑ እና በተጨማሪ የ ቶረንት ፋይሎችን ማውረድ መቻሉ ነው፡፡
FDMን ከ www.freedownloadmanager.com ላይ በቀጥታ በመግባት Download የሚለውን ታብ በመጫን የምንፍልገውን ቨርሽን ዳውንሎድ ማድረግ እንችላለን፡፡ ዳውንሎደ አድርገን ከጨረስን በኋላ ከላይ ለ IDM በተጠቀምነው መንገድ በተመሳሳይ ሁኔታ ኢንስታል ማድረግ፡፡ ኢንስታል አድርገን ከጨረስን በኋላ ልክ እንደ IDM፤ YouTube በመክፈት የምፈልገውን ቪዲዮ ከከፈጥን በኋላ ከቪዲዮ ላይ በግራ ጠርዝ በኩል Download የሚል ያመጣልናል እሱን ክሊክ በማድረግ ዳውነሎዱን ማስጀመር፡፡፡ ዳውንሎድ አድርጎ ሲጨርስ በተመሳሳይ መልኩ ዳውኖዳችንን መጨረሱን ይገልጽልናል፡፡
XiloSoft YouTube Downloader
ይሄኛው ሶፍትዌር ስራው YouTube ብቻ ቪዲዮችን ዳውንሎደ ማድረግ ነው፡፡ በነፃ ዳውንሎድ የሚደረግ ሲሆን ከተጫና በኋላ እንደ ቀደምቶቹ ቨዲዮችን በብራውሰራችን ፈልገን ሳይሆን የምናወርደው በራሱ በሶፍትወሩ በመጠቀም ነው፡፡
XiloSoft YouTube Downloader (ክሊክ ያድርጉት ) ዳውንሎደ በማድረግ ከላይ በተጠቀሱት መንገድ ኢንታል ማድረግ፡፡ ዴስክቶፓችን ላይ የተፈጠረውን XiloSoft YouTube Downloader ሾርትከት መክፈት ወይንም በተለመደው አካሄድ All Programs በመግባት መክፈት የቻላል ፡፡ ቀጥሎም ሶፍተዌሩ ውስጥ በሚገኘው የመፈለጊየ ሳጥን ውስጥ የምንፈልገውን ቪዲዮ ስም በመፃፍ ቪዲዮችን መፈለግ፡፡ የምንፈልገውን ቪዲዮ መርጠን ማጫወት ስንጀምር ከለያ ሜኑ ባር ላይ ከተዘረዘሩት ምልክቶች መካከል መጀመሪያ ላይ የሚገኘውን የወደታች ቀስት መጫን ቅስቱን ስንጫን በቀጥታ ዳውንሎድ ማድረግ ይጀምራል ማለት ነው፡፡ የዳውንሎዳችንን ሁኔታ ለማየት በግራ በኩል ከተዘረዘሩት ሜኑዎች ውስጥ Downloads የሚለውን በመጫን ምን ላይ እንደ ደረሰ ማወቅ ይቻላል ሲጨርም መጨረሱን ይነግረናል፡፡ በተጨማሪ አንዱ ዳውነሎድ ሳያልቅ ሌሎችን ማሰጀመርም ይቻላል
👍8013🥰6👏5🔥1
ቴሌግራም ላይ ሀክ እንዳትደረጉ ማድረግ ያለባችሁ maximum security እና privacy level

1. Device Passcode ተጠቀሙ። ማንኛውም ሰው ስልካችሁን አንስቶ የተላላካችሁትን ሚሴጅ እንዳያይ ወይም ቴሌግራም የሚልከውን የሚስጠር ቁጥር እንዳያገኝ እናንተ ብቻ የምታውቁት የሚስጢር ቁጥር ይኑራችሁ።
ይህን ለማስተካካል
Settings - privacy and security - passcode

2. 2-step verification ተጠቀሙ።
2-step verification የማይጠቀም ሰዉ ሀክ የመደረግ እድሉ ከፍተኛ ነው።
Settings - privacy and security - 2-step verification ላይ በመግባት on አድርጉት።
ምናልባት ሀክ ብትደረጉ አካውንታችሁን መልሳችሁ ለማግኘት recovery email መሙላት አለባችሁ።

3. ከ2 በላይ device ላይ አትጠቀሙ። Login ያደረገችሁበት device በጨመረ ቁጥር ሀክ የመደረግ እድላችሁ ይጨምራል።
ስለዚህ privacy and security -device ላይ ግቡና የተዘረዘሩት ዲቫይሶችን terminate secc ቀንሷቸው።

4. በDesktop ስትጠቀሙ official የDesktop ሶፍትዌሩን ተጠቀሙ እንጂ web ላይ አትጠቀሙ።

5. ከofficial የtelegram አፕሊኬሽኖች ውጪ ሰዉ በላከላችሁ Link ላይ login ለማድረግ አትሞክሩ።

6. የቴሌግራም ኮንታክታችሁን ለሰዎች ስትሰጡ username ወይም የአካውንታችሁን qr-code Share አድርጉ እንጂ ስልክ ቁጥር አትስጡ።

7. ለማታቁትና ለማታምኑት ሰዉ ፎቷችሁን፣ የድምፅ መልዕክት እንዲሁም ሌሎች ሚስጢራዊ የሆኑ መጃዎችን በፍፁም መላክ የለባችሁም። የግድ መላክ ካለባችሁም በsecret message ወይም self destruct ( የተላከለት ሰው ካያቸው በኋላ የሚጠፉ) ሚሴጆችን ላኩ።

8. የስልካችሁ status bar ላይ notification እንዳይታይ off አድርጉት።

9. በመጨረሻም የPrivacy settings ላይ በዚህ መልኩ አስተካክሉ።
Phone number - Nobody
Last seen & online - My contacts
Profile photos - My contacts
Forwarded message - Nobody
Calls - My contacts
Group & channels - My contacts

የ YouTube ቻናል ሊንክ 👇👇👇
https://www.youtube.com/channel/UCZBIP6PqUdmmagdTjbyp_AQ

ቴሌግራም ቻናል
👇👇👇👇👇👇 https://t.me/MuhammedComputerTechnology
👍638🤔3👏2👎1
Telegra ካርድ እየበላ አስቸግሮታል?
ካርድ የሚጨርስበት ምክኒያት የተላኩልን message በራሱ ግዜ dawnload ስለሚያደርግባችሁ ስለሆነ የሚከተለውን ይሞክሩት
ቴግራማችሁ ላይ ትገቡና በግራ በኩል ከላይ ሶስት መስመሩን ትጫኑና  settings  የሚለውን ትፈልጉና ትጫናላችህ ከዛ ብዙ አማራጭ ያመጣ ከሱ ዉስጥ data and storage የሚለውን ትጫናላችሁ እዛ ዉስጥ authomatic media dawnload የሚል አለ ቀጥሎ ከሱ ታች when using mobile data የሚለውን ትጫናላችሁ እዛ ውስጥ
photos
voice message
videos
file
music
Gif
የሚሉትን ሁሉንም የራይት ምልክት(checkbox) ያለበትን ታጠፋላችሁ
ከዛ በኋለ በራሱ ግዜ ፎቶም ይሁን ሌሎችንም ዳውንሎድ አያደርግም
እንደተመቻችሁ ተስፋ አደርጋለሁ ይህን ማረጃ ለሌሎችም እንዲደርስ #Share አድርጉላቸው
ፔጁንም Like አድርጉ አስተያትም መጻፍ ይቻላል
👍11816👏7🔥2
ከF1 እስከ F12 ያሉ #የኪቦርድ ቁልፎች አገልግሎት

🏷 በኮምፒውተራችን ኪይቦርድ ከላይ ተደርድረው
የምናገኛቸው ከF1 – F12 ያሉ ቁልፎችን Function
Key እንላቸዋለን፡፡
በዋናነትም ከሌሎች #ቁልፎች ጋር
በማጣመር እንደ አቋራጭ እንጠቀምባቸዋለን፡፡ እንኘህ
ቁልፎች እንደ ምንጠቀመው የ ኦፐሬቲንግ ሲስተም እና
ሶፍትዌሮች አገልግሎታቸው ይለያያል፡፡: በዛሬው
ቱቶሪያላችንም የተወሰኑትን እናያለን፡፡

◽️F1
ብዙ ጊዜ የምንጠቀመው እርዳታ ስንሻ ነው፡፡ በአብዛኛው
ሶፍትዌሮች F1 ስንጫን #የ Help መስኮትን ይከፍቱልናል፡፡
ማይክሮሶፍት ወርድ ላይ ካለን Start እና F1 መጫን የ
Microsoft Online Help ይከፍታል፡፡
◽️F2
#የተመረጠን አይከን፤ፋይል ወይንም አቃፊ ስም ለመቀየር
F2 መጫን ይቻላል፡፡ ማይክሮሶፍት ወርድ ላይ ካለን Alt
+ Ctrl + F2 መጫን #የ Open መስኮትን ይከፍታል፡፡፡
◽️F3
ዴስክቶፕ ላይ ካን ስንጫን የፍላገ መስኮት ይከፈታል፡፡
ማይክሮሶፍት ወርድ ላይ ካለን ቃልን መርጠን Shift +
F3 መጫን #የተመረጠው ቃል ውስት የሚገኙ ፊደላትን
አንድላይ ካፒታል ወይን ስሞል ወይንም የመጀመሪያውን
ፊደል ካፒታል ያደርግልናል፡፡
◽️F4
አሁንም ማይክሮሶፍት ወርድ ላይ ካለን F4 #መጫን
ለመጨረሻ ጊዜ የተገበርነውን ይደግምልናን፡፡ ለምሳሌ
አበበ ብለን ብንጽፍ እና F4 ብናጫን በ የምትባለውን
ፊደለ በድጋሚ ይጽፍልናል፡፡ Alt + F4 መጫን አክቲቭ
#የሆነውን መስኮት ይዘጋልናል፡፡ Ctrl + F4 ስንጫን
ደግሞ አክቲቭ ከሆነው መሰኮት ውስጥ አክቲቭ የሆነውን
ታብ ይዘጋልናል፡፡ ለዚህ ጥሩ ምሳሌ የሚሆነው በ
ብራውሰራችን ከአንደ በላይ ታብ ከከፈትን Ctrl + F4
ስንጫን ያለንበትን ታብ ብቻ ይዘጋልናለን ነገር ግን Alt +
F4 ብንጫን ሙሉ በሙሉ ብራውሰሩን ይዘጋብና ማት
ነው፡፡
◽️F5
አሁን ገበያ ላይ ባሉት አብዛኛዎ ብራውሰሮች ላይ F5
መጫን # Refresh ያደርገልና፡፡ ማይክሮሶፈት ወርድ ላይ የ
Find መስኮትን ይከፍትልናል፡፡ ማክሮሶፍት ፓወር ፖይንት
ላይ ደግሞ Slideshow ያስጀምርልና፡፡
◽️F6
በአብዛኛው ብራውሰሮች ላይ F6 ስንጫን የማውሳችን
አቅጣጫ መጠቆሚያ #(cursor) ወደ አድራሻ መጻፊያው
ይወስድልና፡፡ ከአንድ በላይ የማይከሮሶፍት ወርድ
ከከፈትን Ctrl + Shift + F6 መጫን #ወደቀጣዩ
የማይክሮሶፍት መስኮትያሸጋግረናል፡፡
◽️F7
ማይክሮሶፍት ወረድ ላይ Shift + F7 መጫን የ
#Thesaurus መስኮትን ይከፍትልናል የሚያገለግለውም
ሰፔሊንግ፤ ፍቺ እና ሰዋሰው ለማስተካከል ነው፡፡
◽️F8
ኮምፒውተራችን ሲነሳ የ Windows፤ #Startup menu
ለመግባት የጠቅማል፡፡
◽️F9
በዊንዶውስ ላይ ጥቅም የለውም ነገር ግን
በማይክሮሶፍት ኦፍስ እንጠቀምበታለን
#Ctrl + F9= እንዲህ አይነት ባዶ ቦታ ለማስገባት { }
ወይም የመረጥነው ቃል በዚህ ዉስጥ { } ለማስገባት
CTRL + SHIFT + F9 ሊንክ የነበረውን ሊንኩ
ለማጥፋት
◽️F10
አክቲቭ የሆነውን ዊንዶው ሜኑ ባርን አክቲቭ ለማድረግ
ያስችላል፡፡ Shift + F10 መጨን #ራይት ክሊክ
እንደማድረግ ይቆጠራል፡፡
◽️F11
በአብዛኛዎ ብርውሰሮች ላይ F10 ስንጫን
የምንመለከተው መስኮት ሙሉ በሙሉ የኮምውተራችንን
ስክሪን ይሞላዋል # (Fullscreen) ፡፡
◽️F12
ማይክሮሶፍት ወርድ ላይ #የ Save as ማስኮትን
ይከፍትልናል፡፡ Ctrl + Shift + F12 ፐሪንት ያዛል፡፡
ስሞኑን የለቀቅኳቸው ጥሩና አስተማሪ ቪዲዮዎች አሉ እነሱን እንድታዪቸው ግብዣየ ነው። በተጨማሪም አዳዲስ ቪዲዮችን እየሰራሁ ስለሆነ #Subscribe በማድረግ ምርጥ ምርጥ ትምህርታዊ ቪዲዮዎችን ይከታተሉ!
#ያወቁትን ማሳወቅ ብልህነት ነው!
የ YouTube ቻናል ሊንክ 👇👇👇
https://www.youtube.com/channel/UCZBIP6PqUdmmagdTjbyp_AQ
👍8822👎3
የጥናትና ምርምር (Research) መሰረታዊ ዋና ዋና ክፍሎች ምንድን ናቸው?
👇👇ይመልከቱት በምርጥ አቀራረብ የተዘጋጀ!👇👇
https://youtu.be/4BEcKNFqguM
https://youtu.be/4BEcKNFqguM
https://youtu.be/4BEcKNFqguM
https://youtu.be/4BEcKNFqguM
እነዚህ 16 ነጥቦች ልብ ይበሉ!

የጥናት/ሪሰርች ይዘት፣ ስፋትና ጥልቀት ሊለያይ ይችላል፡፡
ተጨባጭ ችግርን ለመፍታት ይሁን የተደበቀ ምስጢርን ፈልፍለን ለማግኘት ወይንም ከዚሁ ለተለየ ዓላማ ጥናት ሊታቀድና ሊከናወን ይችላል፡፡
በዚሁ መሰረት አንድ ጥናት/ሪሰርች ሲዘጋጅ ከዚህ በታች የተመለከቱትን ብዙዎች ዘንድ የተለመዱ ዋና ዋና ይዘቶችን ሊያካትት ይችላል፡፡
👇👇ይመልከቱት በምርጥ አቀራረብ የተዘጋጀ!👇👇
https://youtu.be/4BEcKNFqguM
https://youtu.be/4BEcKNFqguM
https://youtu.be/4BEcKNFqguM
https://youtu.be/4BEcKNFqguM
👍4511
ከዚህ በታች ያለው የቴሌግራም ቻናል ስለኮምፒውተር ቴክኖሎጂ ጥያቄ አጥቸ ሰዎች የሚፈተኑበት ቻናል ነው። እስከዛሬ ድረስ 50 ጥያቄዎች ያሉ ሲሆኑ በመግባት እራሳችሁን ፈትኑ እወቁ! መልሱን ወዲያውኑ ታውቃላችሁ! ወደፊት ጥሩ ጥያቄወችን እያዘጋጀሁ እለቅላችኋለሁ

👇👇ይግቡ ሊንኩ ከታች ያለውን ይጫኑ👇👇👇
https://t.me/mame_tech_QA
👍366
pdf-to-word_full417.exe
10.1 MB
ከPDF ወደ Word በቀላሉ መቀየር የሚያስችል የኮምፒውተር ሶፍትዌር

ለ ጓደኞቻችሁ ሼር አርጉላቸው 👇👇

📌Join and share 👇👇👇


✦Join➬ https://t.me/MuhammedComputerTechnology
✦Join➬ https://t.me/MuhammedComputerTechnology
👍7711👎4👏4