Muhammed Computer Technology (MCT)
38.1K subscribers
527 photos
7 videos
254 files
910 links
🔴አድራሻ:-
✅ ስ.ቁ: 0929273364
✅ ዌብሳይት www.mctplc.com
✅ቴሌግራም አካውንት: https://t.me/mctplc
✅ email: mct16plc@gmail.com
✅ ቲክቶክ አካውንት tiktok.com/@mctplc
Download Telegram
የእቅድ form.pdf
643.9 KB
የንግድ ሥራ አቅድ

የንግድ ሥራ ዕቅድ፣ ስኬታማ ንግድ ለመጀመር፣ ለመገንባትና ለመምራት በጣም አስፈላጊ ሰነድ ነው፡፡ እንዲሁም አስፈላጊውን ካፒታል ለማሰባሰብ /ለማሳደግ/ እና የኢንቨስተሮችን ፍላጎት ለመሳብ/ለመያዝ/ ውጤታማ መሳሪያ ነው፡፡ የንግድ ሥራ እቅድ የንግዱን ግባችና ዓላማዎች በግልፅና በተጨመቀ መልኩ የሚገልፅና ለእሱም ስኬት የአሰራር ስልቱን የሚያመለክት መሣሪያ ነው፡፡ እንዲሁም የንግድ ሥራ እቅድ ለአምራቾች/አገልግሎት ሰጭዎች ፍላጎት ላላቸው ኢንቨስተሮችና አቅራቢዎች ለንግዱ ግቦች የላቀ የመገናኛ መሣሪያ ነው፡፡
በርካታ የንግድ ሥራዎች በእቅድና በዝግጅት እጥረት ምክንያት ይወድቃሉ፡፡ ስኬታማ ለሆነ ንግድ ሥራ ከዚህ በታች የተዘጋጀው መመሪያ ለአምራቹ/ለአገልግሎት ሰጪው የንግድ እቅድ መረጃ ምን ያህል እንደሚያስፈልግ በበለጠ ለመረዳት ይረዳል፡፡ የመረጃው በዝርዝር መምሪያ ትክክለኛ መሆን፣ ተቋማት፣ ባንኮች፣ ኢንቨስተሮችና አቅራቢዎች ድጋፍ ሲጠይቅ ፈጥኖ ምላሽ ለመስጠት ያመቻል፡፡ በአጠቃላይ አምራቹ/አገልግሎት ሰጭው ራሱ የንግድ እቅድ ለማዘጋጀት ኃላፊነት አለበት፡፡
የንግድ እቅድ ንግዱ ምን እንደሚሰራ፣ እንዴትና የት እንደሚሰራ አና የንግዱ ካፒታል እንዴት እንደሚገነባና እንዴት እንደሚመራ የሚከተሉትን ምዕራፎች ጨምሮ መሰረታዊ ክፍሎቹን ያብራራል፡፡
• ግላዊ መረጃዎች
• ያሉና የሚገዙ የመሥሪያ መሣሪያዎች
• ስራው የሚካሄድበት ህንፃና መሬት
• የዓመታዊ ምርቱ/አገልግሎት እቅድ
• ለዓመት የሚያስፈልጉ ጥሬ እቃዎች
• ዓመታዊ የሽያጭ እቅድ
• ሌሎች ዓመታዊ የስራ ማስኬጃ ወጭዎች
• የዓመታዊ ትርፈና ኪሳራ መግለጫ

በቀጣዮ ፅሁፍ ዕቅድ ለማቀድ የሚረዱ ጠቃሚ ሰነዶችን አቀርብላችሀለዉ።
ድጋፍ ከፈለጉ
+251912688642
በቴሌግራም አካውንት ያግኙን
https://t.me/Research100stock
👍50❤5🥰1👏1
የንግድ ድርጅት ምስረታ አይነቶች

የንግድ ድርጅት አይነቶች

በአደረጃጀታቸውና በአሰራራቸው የተለያዩ የንግድ ድርጅቶች አሉ፡፡ በአጠቃላይ ድርጅቶችን ለትርፈ የተቋቋሙና አትራፊ ያልሆኑ ብለን በሁለት መክፈል እንችላለን፡፡ እንደገናም በግል ባለቤትነት የተያዙ እና የመንግስት ብለን በሁለት መክፈል ይቻላል፡፡ በእኛ ሀገር በመንግስት የተያዙ የንግድ ድርጅቶችን ሳይጨምር ሶስት አይነት የንግድ ድርጅቶች ያሉ ሲሆን እነሱም፡-

፨የግለሰብ
፨ ነጋዴ
፨የንግድ ማህበራትና
፨የኀብረት ሥራ ማህበራት ናቸው፡፡

እነዚህ የንግድ ድርጅቶች እያንዳንዳቸው የተለያየ ባህሪና ውስጣዊ አደረጃጀት ያላቸው ሲሆን የተለያየ ጠቀሜታም አላቸው፡፡ በመሆኑም ማንኛውም ሰው ወደ ንግድ ተግባር ከመግባቱ በፊት ከእነዚህ የንገድ ድርጅት አይነቶች የበለጠ የሚስማማቸውን በመምረጥ ህጋዊ እውቀና ማግኘት ይኖርባቸዋል፡፡ የተሻለ የሚሉትን ለመምረጥ ደግሞ ስለእያንዳንድ የንግድ ድርጅት አይነት በቂ ግንዛቤ ሊኖረን ይገባል፡፡

ከዚህ ቀጥሎ ስለ እነዚህ የንግድ ድርጅቶች በዝርዝር እንመለከታለን፡፡

ጠቃሚ ናቸው ብዬ ያመንኩባቸዉን መረጃዎች አደርሳችኋለሁ እናንተም ጠቃሚ ናቸዉ ብላችሁ ካመናቹባቸዉ ለሌሎች አጋሯቸዉ።

ድጋፍ ከፈለጉ
+251912688642
በቴሌግራም አካውንት ያግኙን
https://t.me/Research100stock
👍52❤8👎1
Model Exam version 3.pdf
594.1 KB
ለኮምፕዩተር ሳይንስ ተማሪዎች በሙሉ፡ ይህንን ጥያቄ መውጫ ፈተና ላይ የማስታውሳቸው ጥያቄ ስለሆነ በደንብ ስሯቸው፡፡ ለቀጣይም ይጠቅማችኋል፡ ሌላ የመውጫ ፈተና ጥያቄ የማስታውሳቸው ካለ ወደ እናንተ እልክላችኋለሁ፡፡ እስከዛ በትዕግስት ይጠብቁን፡፡
Model Exam version 7.pdf
1021.2 KB
ለኮምፕዩተር ሳይንስ ተማሪዎች በሙሉ፡ ይህንን ጥያቄ መውጫ ፈተና ላይ የማስታውሳቸው ጥያቄ ስለሆነ በደንብ ስሯቸው፡፡ ለቀጣይም ይጠቅማችኋል፡ ሌላ የመውጫ ፈተና ጥያቄ የማስታውሳቸው ካለ ወደ እናንተ እልክላችኋለሁ፡፡ እስከዛ በትዕግስት ይጠብቁን፡፡

---Join---

https://t.me/MuhammedComputerTechnology
👍45🔥4👏4❤2
all Exit exam with Ans and Note.zip
12.6 MB
ገራሚ ለኮምፕዩተር ሳይንስ ተማሪዎች በሙሉ፡ ይህንን ጥያቄ መውጫ ፈተና ላይ የማስታውሳቸው ጥያቄ ስለሆነ በደንብ ስሯቸው፡፡ ለቀጣይም ይጠቅማችኋል፡ ሌላ የመውጫ ፈተና ጥያቄ የማስታውሳቸው ካለ ወደ እናንተ እልክላችኋለሁ፡፡ እስከዛ በትዕግስት ይጠብቁን፡፡

---Join---

https://t.me/MuhammedComputerTechnology
👍58❤15😱3
በአጋርፋ ግብርና ኮሌጅ የ Students Information Management System ስልጠና በመስጠት ወደ ተግባር እንዲገባ ማድረግ ችለናል። አንጋፋው አጋርፋ ግብርና ኮሌጅ
የኮሌጁ ዲኖች፣ የትምህርት ክፍል ተጠሪዎች፣ መምህራኖች፣ የሬጅስትራር ሀላፊ፣ የሬጅስትራር ባለሙያዎች፣ ለተማሪዎች ስልጠና በመስጠት የኮሌጁን ነባር ተማሪዎችና አዲስ ተማሪዎችን መረጃ እንዲገባ በማድረግ አሰራር ከማንዋል ወደ ዲጂታላይዝ አሰራ በመቀየር ሲስተሙን ኦንላይን ማድረግ ችለናል። ለዚህም ስልጠናና ተግበራ መሳካት የኮሌጁ ዲን ዶ/ር ጫላ ፈየራ፣ የኮሌጁ የሬጅስትራር ሀላፊ አቶ በቀለ አብዲሳ እንዲሁም የኮሌጁ የማኔጅመንት አባላትን ላመሰግናቸው እወዳለሁ።

በስልጠናውም የኮሌጁ ዲን ዶ/ር ጫላ ፈየራ፣ የኮሌጁ አካዳሚክ ዲን አቶ አብርሀም ተስፉ፣ የሬጅስትራት ሀላፊው አቶ በቀለ አብዲሳ እንዲሁም መመህራን፣ ዲፓርትመንት ሀላፊዎችና ተማሪዎች አሰራሩ ዲጅታል በመሆኑ ደስተኛ መሆናቸውን ገልጸውልኛል። እኔም በነበረኝ ቆይታ ደስተኛ መሆኔን እገልፃለሁ።

በነበረኝ ቆይታ የስልጠናውን በከፊል ፖስት አድርጌላችኋለሁ።

ለበለጠ መረጃ 0923233955 መደወል ይቻላል።
👍28❤10😁1