Muhammed Computer Technology (MCT)
38.1K subscribers
527 photos
7 videos
254 files
910 links
🔴አድራሻ:-
✅ ስ.ቁ: 0929273364
✅ ዌብሳይት www.mctplc.com
✅ቴሌግራም አካውንት: https://t.me/mctplc
✅ email: mct16plc@gmail.com
✅ ቲክቶክ አካውንት tiktok.com/@mctplc
Download Telegram
ዋና ዋና የሳይበር ጥቃት አይነቶች

✅ መረጃ ጠላፊዎች የግለሰቦችን ኮምፒውተር፣ የስልክ፣ የባንክ ካርድ እና ማንኛውንም በይነመረብ ላይ ያኖሩትን መረጃ በርብረው ሊመነትፉ ይችላሉ።

✅ የሳይበር ጥቃት በግለሰብ ደረጃ ሲፈጸም ጉዳቱ እጅግ አስደንጋጭ ባይሆንም ችግሩ በአገር ደረጃ መዋቅራዊ ጉዳትን ያስከትላል ተብሏል።

✅ የሳይበር ጥቃቶች በተለያዩ የማጥቂያ መንገዶች የሚፈጸሙ ሲሆን÷ በሳይበር ምህዳሩ በስፋት ከተለመዱ ከሳይበር ጥቃት አይነቶች ውስጥ የአገልግሎት መቋረጥ፣ የዲፌስምነት ጥቃት፣ የማልዌር ጥቃት፣ ስፓምናየፌሺንግ ጥቃቶች ናቸው፡፡

✅ የአገልግሎት መቋረጥ ይህ የሳይበር ጥቃት አይነት የሲስተሞችን አቅም ባልተፈለገ ሁኔታ በማጨናነቅ ህጋዊ ተጠቃሚው አገልግሎት እንዳያገኝ ማድረግ ነው፡፡

✅ የዲፌስምነት ጥቃት ( መልክን የመቀየር ጥቃት ) ሆን ተብሎ እና ሳይጠበቅ ጣልቃ በመግባት መደበኛ የኮምፒውተር ተግባርን የሚያውክ የጥቃት አይነት ነው።

✅ የማልዌር ጥቃት የተጠቂውን ድረ- ገጽ በሀሰተኛ ሰነዶች በመቀየር የሚፈጸም የጥቃት አይነት ሲሆን÷ ስፓም (Spam): ደግሞ ብዛት ያለው እና የአጥፊነት ተልዕኮ ያላቸው ኢሜሎችን በመላክ የሚፈጸም የጥቃት አይነት ነው ተብሏል፡፡

✅ የፊሺንግ ጥቃት የሚባለው የሳይበር ጥቃት የተለያዩ የማታለያ እና የማዘናጊያ ዘዴዎችን በመጠቀም አጭበርባሪዎች ከተጠቃሚዎች ሚስጥራዊ የሆኑ መረጃዎችን ለመመዝበር የሚደረግ የማህበራዊ ምህንድስና ጥቃት ነው።
👍6❤3
አምስቱን የፈጠራ ሂደቶች ያውቋቸዋል?
================
የመፍጠር አቅማችንን የሚያሳድጉትን እነዚህ አምስት ነጥቦች ይመልከቷቸው

አዲስ ነገር ስለመፍጠር ወይም ስለመስራት ሲነሳ ምንም የመፍጠር ሙድ ውስጥ አይደለሁም፣ ዛሬስ መፍጠር ተስኖኛል፣ ሌሎች ከእኔ በላይ የመፍጠር ፀጋ አላቸው የሚሉ ተደጋጋሚ ምክንያቶች ከብዙዎች ይሰማል፡፡ ይሁን እንጂ መፍጠር የሚለው ጉዳይ ከዚህ የላቀ እይታ እና ትንታኔ የሚያስፈልገው ፅንሰ ሃሳብ ነው፡፡ ፈጠራ እንደብዙዎች እምነት ዝም ብሎ የሚከሰት ወይም የሚሆን ነገር ሳይሆን ከነበረው አሰራር ጋር አዲስ ሃሳብ በማገናኘት የሚከናወን የአዕምሮ ቅንብር ወይም የመረዳት ሂደት ነው፡፡

ሁላችንም በዕለት ተዕለት ህይወታችን እና የኑሮ እንቅስቀሴያችን ላይ አዲስ የፈጠራ መፍትሄና ውሳኔ የሚስፈልገው ጉዳይ አጋጥሞን ይሆናል፡፡ ለዚያም ጉዳይ የራሳችንን የፈጠራ ውሳኔ አሳልፈን በጎም ይሁን መጥፎ ውጤትን በፀጋ ተቀብለናል፡፡ መፍጠር ሁላችንም ውስጥ የሚገኝ ፀጋ እንደመሆኑ መጠን በተለያዩ መንገዶች ልናበለፅገውና ለእናሳድገው እንችላለን፡፡

ከዚህ ጋር ተያይዞ ከብዙ አስርት አመታት በፊት በጀምስ ዌብ ያንግ የተደረሰው አምስቱ የፈጠራ ቴክኒኮች የሚለው እይታ በዓለማችን ለተፈጠሩ አዳዲስ ሃሳቦች ትልቅ አስተዋፆኦ እንደነበረው ብዙዎች ይጠቅሳሉ፡፡ በተለይም የመፍጠር ሂደትን (creative process) በማብራራት በኩል የቢዝነስ ሰዎች፣ የገበያ ስትራቴጂስቶች እና ሌሎች ባለሙያዎች እስካሁን ድረስ እንደሚጠቀሙበት ይነገራል፡፡

እንደ ጀምስ ዌብ ያንግ ትንታኔ ከሆነ የመፍጠር ሂደት የሚባለው ነገር፤ አንድ ቀድሞ የነበረ ሃሳብ ላይ ወይም እይታ ላይ አዲስ ግንኙነት የመፍጠር ስራ ነው፡፡ ብዙዎቻችን እንደምናስበው ፈጣሪ መሆን ወይም ፈጠራ ከአዲስ ሃሳብ ጋር መምጣት ብቻ ሳይሆን፤ በዙሪያችን ካሉ እና ከነበሩ ሃሳቦች ጋር ሌሎች ሃሳቦችን ማቆራኘትና ማስተሳሰር ነው፡፡ ይህም በመሆኑ በእያንዳንዳችን ውስጥ የተሟላ የመፍጠር አቅም ይገኛል፡፡ ታዲያ አንዳንዶች በፍጥነት የመፍጠር አቅም ኖሯቸው የሌሎች ደግሞ ዘገምተኛ ከሆነ በቀጥታ የሚያያዘው ከላይ የተጠቀሱትን አምስቱን የፈጠራ ሂደቶች በሚገባ ካለማካሄድ ሊሆን ይችላል፡፡

5ቱ የፈጠራ ሂደቶች የሚከተሉት ናቸው፡፡

1. Preparation Stage

ሃሰብ ከየትም ሊመጣ ይችላል፡፡ ነገር ግን አብዛኛውን ጊዜ ሃሳብ የሚፈጠረው ከፍጀታ ነው፡፡ በዙ ነገር ላይ በመሳተፍ ጊዜያችንን የምናውል ከሆነ አዳዲስ ሃሳቦች ወደኛ ሊጎርፉ ይችላሉ፡፡ በመሆኑም በዚህ የመጀመሪያ ሂደት ልናደርግ የምንችለው አያሌ መረጃዎችን መሰብሰብና ሃሳቦች ሊያድጉ የሚችሉበትን ጥሩ ከባቢ ማዘጋጀት ነው፡፡ ፈጠራ የተፅዕኖ፣ የመቅዳት እና በዚያ ላይ ደግሞ የራስን ትርጉም የመስጠት ሂደት በመሆኑ ለአዳዲስ ልምዶች እና እይታዎች ራስን ዝግጁ ማድረግ የመጀመሪያው መንገድ ነው፡፡

2. Incubation Stage

በዚህ ሂደት ልናደርግ የምንችለው ከብዙ ቦታ ያሰባሰብናቸውን መረጃዎች እና ሃሳቦች በተለያየ እይታና መነፅር በመመልከት ወደ እንድ የሚመጡበትን ሁኔታ መፍጠር ነው፡፡ የመጀመሪያው ሂደት ራስን ብዙ ቦታዎች በማሳተፍ ከነገሮች ጋር ለመተዋወቅ መሞከር እንደመሆኑ መጠን በሁተኛው ሂደት ደግሞ ሰፊ ጊዜ በመስጠት እነዚህን ጉዳዮች ለማስተሳሰር እና ለማቀናበር የሚሞከርበት ነው፡፡ የኢንኩቤሽን ስቴጅ በረዘመ የማሰላሰል ሂደት ውስጥ የሚያልፍ በመሆኑና ረዥም ጊዜያትን በመውሰዱ የሚሰራ በመሆኑ አንዳንድ ጊዜ ሌሎች ስራዎችን እየሰራን በንቃት ወይም (consciously) ልናከናውነው እንችላለን፡፡ ይህ ሂደት ከሶስተኛው የፈጠራ ሂደት እስከሚደርስ ድረስ የሃሳቦች ህብር የሚፋጩበት እና ለውሳኔም የሚያንደረድረን ነው፡፡
3. Illumination Stage

ረዥም ጊዜ ከሚወስደው የኢንኩቤሽን ስቴጅ በኋላ የምናገኘው ይህ ሶስተኛ ሂደት የeureka ወይም የውጤት ደረጃ ይባላል፡፡ ብዙ የተለያዩ ሃሳቦችና ምልከታዎች ከተተነተኑ በኋላ አንድ ቅርፅ ወይም መልክ ይዘው የሚቀርቡበት ደረጃ ነው፡፡ የኢሉሚኔሽን ስቴጅ ቀድሞ ከነበረው ደረጃ አንፃር እጅግ በፈጠነ እና ባለተጠበቀ ሁኔታ የሚከናወን ሲሆን፤ ይህም የሚሆንበት ምክንያት በኢንኩቤሽን ስቴጅ የሚደረጉት ረዥም የሃሳብ መብላላቶች ወደ አንድ ውጤት መተው ፊት ለፊት በመታየታቸው ነው፡፡

4. Evaluation Stage

ይህ ስቴጅ የምክኒያዊነት ደረጃ ይባላል፡፡ ሶስቱን የመፍጠር ሂደቶች ጨርሰን ስንመጣ ስላረቀቅነው አዲስ ሃሳብ ራሳችንን የምንጠይቅበት ደረጃ ማለት ነው፡፡ በዚህ ሂደት ሃሳባችንን የሚፈትሹ አያሌ ጥያቄዎች ይነሳሉ፡፡ ለምሳሌ ስለሃሳቡ ረቢነት፣ ከዚህ በፊት ስለመሰራቱ፣ አንዳች ለውጥ የሚያስፈልገው ከሆነ እና ከኛ በላይ ያሉ ሰዎች ስለሃሳቡ የሚኖራቸው ግምት የሚሉ የተለያዩ ጥያቄዎች እንዲነሱ ያስፈልጋል፡፡ ይህ ሂደት ከራሳችን ጋር ትግል የምናደርግበት እና ታማኝነታችንን የምንለካበት ደረጃ እንደመሆኑ መጠን የሃሳቡን ክፍተት እና ጉድለት በሚገባ እንድንመለከት እድል ይሰጠናል፡፡ የኢቫሉዌሽን ስቴጅ ለብዙ የፈጠራ ሰዎች የስኬትም ሆነ የውድቀት ቁልፍ በመሆኑ አብዛኛውን ጊዜ የሃሳባችንን ነፀብራቅ በጥንቃቄ መፈተሽ ግድ ይላል፡፡

5. Elaboration (interpretation) Stage

በጀምስ ዌብ ያንግ የፈጠራ ሂደት ውስጥ የመጨረሻው ደረጃ ይህ ስቴጅ ነው፡፡ ኢላቦሬሽን ስቴጅ በአራቱ የመፍጠር ሂደቶች ሲብላላ የቆየውን አዲስ ሃሳብ ለትግበራ የምናዘጋጅበት እና ወደ መሬት የምናወርድበት የመጨረሻው ደረጃ ነው፡፡ ይህ ሂደት ብዙዎቹ የፈጠራ ሰዎች የሚለዩበት ከመሆኑም ባለፈ አያሌ የፈጠራ ሰዎች አምጠው የወለዱትን ሀሳብ መተግበር ተስኗቸው የሚወድቁበትም ወሳኝ ስቴጅ ነው፡፡ ጀምስ ዌብ ያንግ ይህን የፈጠራ ሂደት በአጭሩ ሲገልፀው የቶማስ ኤዲሰንን ታዋቂ ጥቅስ ይጠቀማል “1 percent inspiration and 99 percent perspiration.” በፈጠራ ሂደት ውስጥ 99 በመቶ አቅማችን ሊውል የሚገባው በፈጠርነው አዲስ ሃሳብ ላይ ነው እንጂ ለፈጠራችን መነሻ በሆነው አንድ ፐርሰንት ላይ መሆን የለበትም፡፡
ምንጭ፡ Ideapod እና James Taylor
👍17❤4
✳️ የሞባይል ባንኪንግ ሲጠቀሙ ሊያደርጓቸው የሚገቡ ጥንቃቄዎች

🚩የሞባይል ባንኪንግ የባንክ አገልግሎቶችን ወደ ባንኮች ቅርንጫፍ መሄድ ሳያስፈልግ በተንቀሳቃሽ ስልኮች አማካኝነት ብቻ የባንክ አገልግሎቶችን ማለትም ገንዘብ መላክ እና መቀበል እንዲሁም የተለያዩ ክፍያዎችን ለመፈፀም የሚያስችል ቴክኖሎጂ ነው፡፡

🚩የሞባይል ባንኪንግ አገልግሎት የተጠቃሚዎችን ድካም ከመቀነስ ጋር በተያያዘ አገልግሎቱን ተመራጭና ቀላል ያደርገዋል፤ ታዲያ ይህ አገልግሎት የቴክኖሎጂ ውጤት ከመሆኑ ጋር ተያይዞ ተጓዳኝ የመረጃ መረብ ጥቃት ተጋላጭነት አያጣውም፡፡

🚩ተጠቃሚዎች አገልግሎቱን ሲጠቀሙ የሚከተሉትን ጉዳዮች ሊያውቋቸው እና ጥንቃቄ ሊያደርጉባቸው ይገባል ሲል የኢንፎርሜሽን መረብ ደኅንነት አስተዳደር ይመክራል፡፡

➊. የተረጋገጡና ትክክለኛ የሞባይል ባንኪንግ መተግበሪያዎችን (application) ከተረጋገጡ ምንጮች አውርዶ መጠቀም፦ የሞባይል ባንኪንግ መተግበሪያዎች ትክክለኛ በባንኩ እውቅና ያላቸው መሆኑንና የሚገኙትም በትክክለኛው የመተግበሪያ ቋት ማለትም ለአንድሮይድ የመተግበሪያ ቋት ወይም ለአይ.ኦ.ኤስ ኦፕሬቲንግ ሲስተም በማውረድ መጠቀም ተገቢ ነዉ፡፡

➋. በስልኮች ላይ ያሉ ሌሎች መተግበሪያዎች ፍቃዶችን ማጥናት፡- በስልክዎ ላይ የሚገኙ ሌሎች መተግበሪያዎች የሚጠይቋቸውን ግንኙነቶች (አክሰስ) ልብ ይበሉ፡፡
መተግበሪያዎች ለአገልግሎቶቻቸው ከሚያስፈልጋቸው የሞባይል መረጃ ዉጪ ሌሎች መረጃዎች እንዲዳረሱ እንዳይፈቅዱ፡፡

➌. አፕሊኬሽኖችን /መተግበሪያዎችን ማዘመን፡- በስልኮች ላይ የሚገኙ የባንኪንግ መጠቀሚያ መተግበሪያዎችን ወቅቱን ጠብቀዉ ያዘምኑ፡፡
መተግበሪያዎች ላይ ለስርቆት የሚዳርጋቸው ክፍተቶች ሲገኙ በየወቅቱ ማዘመኛ ስለሚለቀቅላቸው የደህንነት ክፍተቶቹን ለመድፈንና የባንክ ሂሳብዎን ደህንነት ለማስጠበቅ በየጊዜው ያዘምኗቸው፡፡

➍. የሞባይል ስልክ ኦፕሬቲንግ ሲስተምን ማዘመን፡- የስልክዎን ደህንነት ክፍተት ለመሙላት በየጊዜው ክፍተት መሙያና ማሻሻያ እድሳቶች ስለሚለቀቁ በየወቅቱ እየተከታተሉ ያዘምኗቸው፡፡

➎. ከህዝብ መገልገያ ዋይፋይ ይልቅ የሞባይል ዳታ ይጠቀሙ፡- የሞባይል ባንኪንግ አገልግሎቶችን በሞባይልዎ ለመጠቀም ለህዝብ መገልገያ የቀረቡ ነፃ ዋይፋዮችን ከመጠቀም ይልቅ የሞባይል ዳታዎችን ይጠቀሙ፡፡

➏. ዘርፈ-ብዙ የደህንነት ማስጠበቂያ የይለፍ-ቃሎችን ይጠቀሙ፦ ሞባይል ስልክዎን በአሻራ፣ ፊት ማንበብያ (ፌስ ሪኮግኒሽን)፣ ፓተርን፣ ፓስወርድ እና ፓስ ኮድ የመሳሰሉትን በመጠቀም ስልክዎን ይቆልፉ፡፡

➐. በማህበራዊ ሚዲያ የሚለቋቸውን ግላዊ መረጃዎች ይገድቡ፡- በማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ የሚለቀቁ መረጃዎች የተገደቡ ሊሆኑ ይገባል፡፡

➑. ፀረ-ቫይረስ (ማልዌር) ይጠቀሙ

➒. የሞባይል ስልክዎን አካላዊ ደህንነት ያስጠብቁ

➓. የባንክ ሂሳብዎን ዘወትር ይከታተሉ፡- በተጨማሪ ተገቢውን ሁሉ ጥናቃቄ ካደረጉ በኋላም ስለ ባንክ አካውንትዎ የሚደርሱ ማንቂያዎችን (notifications) በአግባቡ መከታተል እንዲሁም በየጊዜው ስለ አካውንትዎ ሁናቴ (ስታተስ) መከታተል እና የማያውቁት የሂሳብ ለውጥ ካለ በአፋጣኝ ለባንክዎ ያሳውቁ፡፡
👍12❤2
💥የ ደህንነት ካሜራ ፣አደገኛ አጥር (fence ) ማስገጠም አስበዋል።
እነሆ መፍትሄው እኛ ጋር አለ 👇
ለ ሁሉም ቦታ የሚሆን
☞ : ለመኖሪያ ቤት
☞ : ለድርጅት
☞ : ለሱቅ
☞ : ለፋርማሲ
☞ : ለሆቴል
☞ : ለሱፐር ማርኬት
☞ : ለፋብሪካ
☞ : ለሌሎችም
ደህንነትዎን ከ መቼውም ጊዜ በላይ አስተማማኝ ያድርጉ
እጅግ ዘመናዊ ቴክኖሎጂ የተካተተባቸው ከ የተኛውም ቦታ ሆነው በቀጥታ በስልክዎ 24 ሰዓት ይከታተሉ ።
በ አነስተኛ ዋጋ ንብረትዎን እና አካባቢዎን ይጠብቁ።
ባለ 2 ካሜራ=23000
¶ 4 ቻነል ዲቪአር ሪከርደር
¶ 2 ካሜራ HD
Âś 2 ባለ 20 ሜትር ካሜራ ኬብል 

ባለ 4 ካሜራ=29500
¶ 4 ቻነል ዲቪአር ሪከርደር
¶ 4 ካሜራ HD
Âś 4 ባለ 20 ሜትር ካሜራ ኬብል 

ባለ 6 ካሜራ=39500
¶ 8 ቻነል ዲቪአር ሪከርደር
¶ 6 ካሜራ HD
Âś 6 ባለ 20 ሜትር ካሜራ ኬብል 

ባለ 8 ካሜራ=42000
¶ 8 ቻነል ዲቪአር ሪከርደር
¶ 8 ካሜራ HD
¶ 8 ባለ 20 ሜትር ካሜራ ኬብል
¶ባለ 16 ካሜራ
16 ቻናል ቪዲዮ ሪከርደር
16ባለ 20 ሜትር ኦሪጂናል የካሜራ ኬብሎች ከነ አክሰሰሪያቸው
ባለ 16 ካሜራ 78,000 ብር
Hard Disk 500GB  =2500
Servilliance HD 1TB =6000
Servilliance HD 2TB=7500
Installation 1000 per camera

ከ ተሟላ የ ሀርድ ዲሰክ አቅርቦትና ገጠማ ጋር። ያሉባት ድሪስ መጥተን እንገጥሞታለን
#secured your life & your Bussiness
#Enjoy by technolodgy

Contact us now👇👇👇👇
#0945358175
#0703453596
#0919217468
https://t.me/stareld1212
👍13
ቤክሳኔትን ይጎብኙ!
www.bexanet.com
👍2
የደሞዝ አሰራር እንዴት ማዘጋጀት እንችላለን? ክፍል -1
ከታች ያለውን ሊንክ በመጫን ይመልከቱት!
👇👇👇👇
https://youtu.be/rNcfrxbTyxo


የደሞዝ አሰራር እንዴት ማዘጋጀት እንችላለን? ክፍል -2
ከታች ያለውን ሊንክ በመጫን ይመልከቱት!
👇👇👇👇
https://youtu.be/AsQhn_ua3Cg
👍10
የተማሪዎችን ውጤት በ Grading system መስራት እንዴት እንችላለን? Student Mark (Grading System)
ከታች ያለውን ሊንክ በመጫን ይመልከቱት!
👇👇👇
https://youtu.be/j7FOjQ9YaoE
👍4❤1🥰1
የቤክሳኔትን የYouTube ቻናልን ሰብስካራይብ በማድረግ ወቅታዊ የቴክኖሎጂ መረጃን ያግኙ!
👇👇👇Subscribe👇👇👇
https://youtube.com/@bexanetitsolutionplc

አድራሻ:-
ዌብሳይት https://bexanet.com/

Facebook:- https://www.facebook.com/profile.php?id=100090537960178&mibextid=ZbWKwL
👍2🔥2
✅ላፕቶፓችን ላይ ያለውን ኢንተርኔት እንዴት ያለምንም ሶፍት ዌር በሞባይላችን
መጠቀም እንችላለን?✅
➡️1. cmdን በአንሜኒስትሬተር ያሩጡት (right click በማድረግ run as
administrator የሚለውን መጫን)
➡️2. ላፕቶፓችን ኔትዎርክ ሼር ለማድረግ ብቁ መሆኑን ለማረጋገጥ: netsh
wlan show drivers የሚለውን ጽፎ ከሚመጣልን ዝርዝር ውስጥ Hosted
network supported :Yes ይህ ከመጣ ላፕቶፓችን ይችላል ማለት ነው
➡️3. በመቀጠል ይህንን ኮማንድ ማስገባት: netsh wlan set
hostednetwork mode=allow ssid=Hotspotname
key=password
ማሳሰቢያ: SSID የሚለውን በፈለግነው ስም መቀየር እንችላለን: KEY የሚለው
የዋይ ፋይ ፓስዎርዳችን ስለሆነ የምንፈልገውን መስጠት እንችላለን
➡️4. በመቀጠል የኔት ዎርክ አዳፕተራችንን በመክፈት እና እሱላይ right click
በማድረግ : Allow other network users to connect through this
computer's internet connection የሚለውን እንመርጥያ ከስር ካለው
ሊስት ውስጥ የፈጠርነውን የዋየርለስ ኔትዎርክ እንመርጥለታለን::ከዛም
OK በለን እንወጣለን
➡️5. በመጭረሻ ወደ CMD ተመልሰን:
ለማስጀመር netsh wlan start hostednetwork የሚለውን ኮማንድ
እናስገባለን ለማቆም netsh wlan stop hostednetwork የሚለውን እናስገባለን
➡️6. አሁን ሞባይላችንን wifi ከፍትን SSID ላይ ያስገባነውን የኔትዎርክ ስም
መርጠን ለሚለው KEY ላይ ያስገባነውን በመስጠት መጠቀም መጀመር እንችላለን።
👍15❤4
cutting point.pdf
4.5 MB
የሀገር አቀፉ የቴክኒክና ሙያ ኮሌጅ የመግቢያ ነጥብ ይፋ ሁኗል።

የ2015 የቴክኒክና ሙያ ኮሌጅ የመግቢያ የመቁረጫ ነጥብ ይፋ ሁኗል።

በ2015 ወደ ቴክኒክና ሙያ ኮሌጆች ይገባሉ ተብሎ ታሳቢ የተደረገ ቂጥር
✅ በአገር አቀፍ ደረጃ የ12ኛ ክፍል አገር አቀፍ መልቀቂያ ፈተና ላይ የተቀመጡ 890,741 ተማሪዎችን መነሻ ማድረግ የተቻለ ሲሆን
✅ ከተፈታኞች መካከል 50% ያመጠ ተማሪዎች 29,999 ብቻ ናቸው ሌሎች 869,611 ተማሪዎች ወደ ከፍተኛ ትምህርት ለመግባት አልቻሉም
✅ 100,000 ተማሪዎች በቀጣ አመት ዩኒቨርስቲ ለመግባት የአቅም ማሻሻያ ስልጠና እንዲያገኙ እድል ተሰጥቷቸዋል
✅ በመሆኑም በአገር አቀፍ ፈተና ከተፈተኑት መካከል 760,832 ተማሪዎች ምንም አይነት የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የመግባት እድል የላቸውም
✅ ከዚህ በፊት በነበረው ልምድ ማለትም የዩኒቨርስቲ መግቢያ ያላመጡ ተማሪዎች 20%(152,166) ተማሪዎች በፖሊስ ኮሌጆች፣ በመከላከያና በሌሎች የትምህርት ተቋማት የሚገቡ ይሆናል
✅ በአጠቃላይ ከላይ የተጠቀሱትን እድሎችን ያላገኙ 608,666 ተማሪዎች ወደ ቴክኒክና ሙያ ኮሌጆች ገብተው ይሰለጥና ተብለው ይታመናል
👍1👎1
Electronic Medical Record ሲስተም ምንድን ነው?

✅ አሁን ላይ በሁሉም ተቋማት ላይ ያለው የመረጃ አያያዝ ስርአታችን የወረቀት አሰራር ሲሆን በተለይ በጤና ተቋማት ላይ ያለው የመረጃ አያያዝ ስርአት አሰራራቸውን የዲጅታል ቴክኖሎጂና መጠቀም አስፈላጊ ነው።

🔴 የዲጅታል ቴክኖሎጂ በመጠቀማቸው ምንድን ነው ጥቅሙ?

✅ አሰራርን ማዘምውን ሲሆን አሁን ላይ ከሚተገበረው የወረቀት አሰራር የሚስተናገዱ ባለጉዳዮችን በፍጥነት እንዲስተናገዱ ያደርጋቸዋል።

✅ በየአመቱ የሙወጣው እንደየ ተቋሙ ሁኔታ በሚሊዮኖች፣ በመቶ ሽህዎች የሚቆጠር የስቴሽነሪ(የወረቀት፣ እስክብሪቶ፣ የህትመት፣ የክላሴርና የደረሰኞችን ወዘተ...) ወጭዎችን ሙሉ በሙሉ ማጥፋት የሚያስችል ነው።

✅ መረጃችንን ከአደጋዎች ነጻ ማድረግ ሲሆን በአንድ የጤና ተቋም ውስጥ የእሳት፣ የጎርፍና አንድንድ የሰው ሰራሽ አደጋዎችን ለመከላከል ያስችላል።

✅ የደንበኞች እርካታ በከፍተኛ ሁኔታን መጨመር የሚያስችል ሲሆን ለምሳሌ አንድ ታካሚ መጥቶ ወደ ህክምና ክፍል ለመግባትና ለመታከም ቢፈልግ የህክምና ማስረጃዎች(History) በወረቀት ገና ከካርድ ክፍል ተፈልጎ፣ መረጃውን በትክክል ቢገኝም ምን ያክል ግዜ እንደሚወስድ ግልጽ ነው። በዲጅታሉ አሰራር ግን አንድ ታካሚ ለህክምና ሲመጣ በተፈለገው ሰአት መረጃውን በሰከንዶች በማግኘት እንዲታከም ማድረግ ይቻላል።

✅ አንድ ታካሚ ለመታከም ቢፈልግ በዲጅታሉ አሰራሩ ከምርመራ ክፍል፣ ከላብራቶሪ ክፍል፣ ከክፍያ ክፍል፣ ከተለያዩ የምርመራ ክፍሎች ጋር በማስተሳሰር ደንበኞች በቀላሉ የሚገልጉትን አገልግሎት አግኝተው እንዲመለሱ ማድረግ ያስችላል።

✅ የደንበኞች የክፍያ ስርአትን በተደራጀ ሁኔታ በቀለሉ የሚከፍሉበትን ሁኔታ በመፍጠር ክፍያውን በቀላሉ እንዲከፍሉ ያደርጋቸዋል።

✅ በጤና ተቋማት መስተናገድ ያለባቸውን ደንበኞችን በብዙ እጥፍ ማስተናገድ ያስችላል።

✅ ደንበኞች በጤና ተቋማት ላይ በመስተንግዶ ችግር ምክንያት የሚያብክኑት ግዜ ሙሉበሙሉ ማጥፋት ይቻላል።

✅ ደንበኞች በቀጠሮ ግዜያቸው መሰረት እንዲስተናገዱ ያደርጋቸዋል።

✅ ደንበኞች ከሚያወጡት አላስፈላጊ ወጭዎች መዳን ይችላሉ።

🔴 Electronic Medical Record ሲስተም በብዙ ተቋማቶች ላይ ተግባራዊ የተደረገ ሲሆን ከ4 አመታት በላይ በመጠቀም ወጤታማ ስራና አሰራርን ተግብረው ተቋማቸውን ዘመናዊነትን አላብሰዋል።

✅ በአጠቃላይ የአንድን የጤና ተቋምን የሚያዘምን የዲጅታል ቴክኖሎጂ በመጠቀም አሰራራቸውንና ስራቸውን ፈጣን፣ ቀልጣፋ፣ ምቹና ተስማሚ በማድረግ የደንበኞችን እርካታ እንዲጨርም በማድርግ የተቋሙን የስራ አፈጻጸም መጨመር ያስችላል።

✅ በመሆኑም በኢትዮጵያውያን የተመሰረተው የቤክሳኔት (BExANet) ይህንን የዲጅታል ቴክኖሎጂ በማበልጸግ በሀገራችን ላሉ የጤና ተቋማት እንዲጠቀሙበት በታላቅ ግብዣ ነው።

✅ BExANet (ቤክሳኔት) ከዚህ በተጨማሪም በብዙ ሴክተሮች ችግሮችን በመለየት በሀገራችን ያለውን አለም የደረሰበትን የዲጅታል ቴክኖሎጂን አጠቃቀም ሀገራችንና ማህበረሰባችን እንዲጠቀሙበት በማድረግ ስራን፣ አሰራርን ቀላል፣ ቀልጣፋና ምቹ እንዲሆን የማድረግን ስራ እየሰራን እንገኛለን።

✅ BExANet የሚያበለጽጋቸውን የዲጅታል ቴክኖሎጂዎን ሁሉም ተቋማት እንዲጠቀምባቸው ታላቅ ግብዣ እናቀርባለን።

✅ ስለ BExANet ትክክለኛ መረጃ ከፈለጋችሁ

🔴አድራሻ:-
✅ ስ.ቁ: #0929273364
✅ Telegram Account @ma1000me
✅ email: bexanetplc@gmail.com
✅ ዌብሳይት https://bexanet.com/
✅ Facebook:- https://www.facebook.com/profile.php?id=100090537960178&mibextid=ZbWKwL

✅ የቤክሳኔትን የYouTube ቻናልን ሰብስካራይብ በማድረግ ወቅታዊ የቴክኖሎጂ መረጃን ያግኙ!
👇👇👇Subscribe👇👇👇
https://youtube.com/@bexanetitsolutionplc
የጤና ተቋምዎን መረጃን ዲጅታላይዝ እናድርግልዎ ስንል በደስታ ነው!
👍14❤2👎1
የሰው ሀብት መረጃ አስተዳደር ስርዓት(Human Resource Management Information System) ምንድን ነው?

✅ አለማችን አሁን ላይ የአኗኗር ዘይቤውን ቀላል እንዲሆን ካደረጉት አንዱ የዲጅታል ስርአት ከመጣ በኋላ ቀለል ባለ መልኩ ሰው አኗኗሩን ቀላል እንዲሆንለት አድርጓል።

✅ በእያንዳንዱ የማህበረሰብ፣ የመንግስትና የግል ተቋማት ላይ ብዙ ስራዎች አሰልች፣ አድካሚ፣ ብዙ ገንዘብ፣ ብዙ ግዜ፣ ብዙ የሰው ሀይል የሚጠይቅ ስራና አሰራር ያለበት ሲሆን ይህንን አሰራርና ስራ በቅልጥፍና፣ በታማኝነት፣ ከብዙ ግዜ ወሳጅነት፣ ከብዙ ወጭ የሚገላግለው ዲጅታላይዜሽን ነው።

✅ ለአንድ ተቋም የሰው ሀብት በጣም ወሳኙ አንድት ተቋም ትርፋማ እንዲሆን የሚያደርግ፣ አንድን ተቋም እንዲከስር የሚያደርግ፣ አንድት ተቋም ወደ ላቀ ደረጃ እንዲደርስ የሚያደርግ ውጤታማ የሚያደርግ፣ አንድን ተቋም ህክውና የሚወስነው የተቋሙ የሰው ሀብት አስተዳደር ነው። ተቋሙ ውስጥ ያለው የሰው ሀብት በደንብ ካልተመራ፣ ካልተደራጀ፣ ካልተያዘ ተቋሙ እንዳልነበር ሊሆን ይችላል።

✅ በመሆኑም የአንድ ተቋም የሰው ሀብትን በደንብ በዲጅታል የቁጥጥር ስርአት በመዘርጋት፣ በዲጅታል የሰው ሀብትን መረጃ በመያዝ በአግባቡ ከተመራና በዲጅታል የቁጥጥር ስርአት ውሰጥ በማስገባት ማን በአግባቡ በስራ ገበታው በተቋሙ ውስጥ በመገኘት ስራውን ማከናወኑን፣ የተሰጠውን ተግባር በአግባቡ መስራቱን የምንቆጣጠርበት የሰው ሀብት በሰውና በወረቀት አሰራር ከሆነ በጣም አድካሚ፣ አሰልች የሚሆን ሲሆን ሁሉም ተቋማታ ወደ ዲጅታሉ አለም በማሸጋገር የሰው ሀብት ቁጥጥር ስርአቱን ማዘመንና የሰው ሀብት አያያዝ ስርአታችንን ቀላል፣ ቀልጣፋና ምቹ በማድርገ ስራን መስራት ያስችለናል።

✅ የሰው ሀብት አስተዳደር የመረጃ አስተዳደር ስርአት ማለት አሁን ላይ የመረጃ አያያዝ ስርአቱ ከወረቀት የመረጃ አያያዝ ስርአት ወጣ ባለ መልኩ ቀላልና ቀልጣፋ በሆነ መልኩ የአንድን ተቋም የመረጃ አያያዝ ስርአቱን ዲጅታላይዝ የማድረግ ስርአት ነው።

✅ የአንድ ተቋም የሰው ሀይል መረጃ በቋሚነት ከእሳት፣ ከጎርፍ አደጋዎች ለመከላከል፣ ከመረጃ ስርቆት፣ ከመረጃ መቀደድ፣ ከመረጃ መጥፋት፣ ከመረጃ መጭበርበር ለመከላከል ዋነኛ መፍትሄ የሚሆነው ዲጅታላዜሽን በተቋማችን ስንዘረጋ ይሆናል ማለት ነው።

✅ የተቋም ሰራተኞች የፈለጉትን የግለሰብ መረጃ ቢጠይቅ በቅጽበት ማግኘት የሚያስችል ሲሆን የተቋም ሰራተኞች በአንድ ግዜ የጠየቁትን መረጃ አግኝተው ወቅታዊ መረጃ በማግኘት መስተናገድ ያስችላቸውል።

✅ በአንድ ተቋም የሰራተኞች የቁጥጥር ሰአት መኖር ያለበት ሲሆን ይህንን ለማድረግ በዲጅታል ቢደገፍ በጣም ውጤታማ ማድረግ የሚያስችል ሲሆን ለተቋም ውጤትና ከፍትኛ አስተዋጽኦ ያበረክታል።


✅ በመሆኑም በኢትዮጵያውያን የተመሰረተው የቤክሳኔት (BExANet) ይህንን የዲጅታል ቴክኖሎጂ በማበልጸግ በሀገራችን ላሉ ለሁሉም ተቋማት በሚመጥንና ስታንዳዱን በጠበቀ መልኩ የተዘጋጀ በመሆኑ ማንኛውም የግልም ሆነ የመንግስት የግል እንዲጠቀሙበት በታላቅ ግብዣ ነው።

✅ BExANet (ቤክሳኔት) ከዚህ በተጨማሪም በብዙ ሴክተሮች ችግሮችን በመለየት በሀገራችን ያለውን አለም የደረሰበትን የዲጅታል ቴክኖሎጂን አጠቃቀም ሀገራችንና ማህበረሰባችን እንዲጠቀሙበት በማድረግ ስራን፣ አሰራርን ቀላል፣ ቀልጣፋና ምቹ እንዲሆን የማድረግን ስራ እየሰራን እንገኛለን።

✅ BExANet የሚያበለጽጋቸውን የዲጅታል ቴክኖሎጂዎን ሁሉም ተቋማት እንዲጠቀምባቸው ታላቅ ግብዣ እናቀርባለን።

✅ ስለ BExANet ትክክለኛ መረጃ ከፈለጋችሁ

🔴አድራሻ:-
✅ ስ.ቁ: 0929273364
✅ በቴሌግራም: https://t.me/ma1000me
✅ email: bexanetplc@gmail.com
✅ ዌብሳይት https://bexanet.com/
✅ Facebook:- https://www.facebook.com/profile.php?id=100090537960178&mibextid=ZbWKwL

✅ የቤክሳኔትን የYouTube ቻናልን ሰብስካራይብ በማድረግ ወቅታዊ የቴክኖሎጂ መረጃን ያግኙ!
👇👇👇Subscribe👇👇👇
https://youtube.com/@bexanetitsolutionplc
የጤና ተቋምዎን መረጃን ዲጅታላይዝ እናድርግልዎ ስንል በደስታ ነው!
👍20❤3
እንኳን ለ2015 የትምህርት ዘመን አደረስዎ! በአዲስ የሰልጣኝ ቅበላ አሰራርዎን በማዘመን ይጀምሩ!
የሬጅስትራር ሲስተሙን በ27 ኮሌጆች በ5 ክልሎች በ31 ካምፖሶች ተግባራዊ ተደርጓል
✅ የመንግስት ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ
1 እንጅባራ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ
2 ወልቂጤ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ
3 ወራቤ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ
4 ደብረብርሃን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ
5 አልማዝ በም ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ
6 ታርጫ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ
7 ሚዛን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ
8 አማን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ
9 ቴፒ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ
10 ቦንጋ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ
~~|||~
✅ ከ
ፌደራል ግብርና ቴክኒክና ሙያ ኮሌጅ
11 ገዋኔ ግብርና ቴክኒክና ሙያ ኮሌጅ
12 ሚዛን ግብርና ቴክኒክና ሙያ ኮሌጅ
~~|||~
✅ የግል ኮሌጆች
13 ኮ
ቻ ኪድማስ ቢዝነስና ቴክኖሎጂ ኮሌጅ
14 MA ኮሌጅ አሶሳ፣ ግልገል በለስ፣ ቡለን
~~|||~
✅ የመንግስት ቴክኒክና ሙያ ኮሌጆች
15
ዳንግላ ቴክኒክና ሙያ ኮሌጅ
16 ቲሊሊ ቴክኒክና ሙያ ኮሌጆ
17 ቻግኒ ቴክኒክና ሙያ ኮሌጆ
18 አዲስቅዳም ቴክኒክና ሙያ ኮሌጆ
19 አንከሻ ቴክኒክና ሙያ ኮሌጆ
20 አጣዬ ቴክኒክና ሙያ ኮሌጆ
21 መኮይ ቴክኒክና ሙያ ኮሌጆ
22 ደነባ ቴክኒክና ሙያ ኮሌጆ
23 እነዋሪ ቴክኒክና ሙያ ኮሌጆ
24 አረርቲ ቴክኒክና ሙያ ኮሌጆ
25 ደብረ ሲና ቴክኒክና ሙያ ኮሌጆ
26 ሞላሌ ቴክኒክና ሙያ ኮሌጆ
27 መሀል ሜዳ ቴክኒክና ሙያ ኮሌጆ

በተሳካ ሁኔታ የኮምፒውተራይዝድ ሬጅስትራር ሲስተም  ትግበራን  እንደሀገር ከ27 በላይ የግልና የመንግስት ኮሌጆች ተግባራዊ ተደርጓል እየተጠቀሙበት ነው። በዚህ ተግባራቸው ኮሌጆች አሰራራቸውን ዲጂታላይዝ በማድረግ ውጤታማ በማድረግ ኮሌጆቻቸው የተሞክሮ ማእከል ሁኗል።
በ #0929273364 ይደውሉ!
Telegram 👉👉👉 https://t.me/ma1000me
ኮምፒውተራይዝድ የሬጅስትራር የመረጃ አያያዝ ስርዓቱን

🔰 በሀገራችን 27 ኮሌጆችን በ5 ክልሎች እንዲጠቀሙበት ተደርጓል።

✅✅✅✅በሀገራችን✅✅✅✅
✅ ለ10 ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጆች
✅ ለ2 ፌዴራል ግብርና ቴክኒክና ሙያ ኮሌጅ
✅ ለ2 ግል ኮሌጆች በ4 የተለያዩ ካምፖሶች
✅ ለ13 ቴክኒክና ሙያ ኮሌጆች
💡 በተጨማሪም የCOC መረጃ አደረጃጀትና ምዝገባ የክፍያ ስርአቱን ከሬጅስትራር ጋር በማገናኘት ስለጣኞች የከፈሉትን የክፍያ ስርዓት ከሲስተሙ ጋር የገንዘብ ያዥና የሬጅስትራር ባለሙያዎች ተናብበው እንዲሰሩና የከፈለ ሰልጣኝና ያልከፈለ ስልጣኝ በአንድ ግዜ ማወቅ እንዲያስችለን ተደርጎ ተሰርቷል።
👍17❤4👏2🥰1
ቤክሳኔት ምንድን ነው?
ዌብሳይቱን ይመልከቱ!
www.bexanet.com
👏5👍2
💻 አዲስ ላፕቶፕ ከመግዛት በፊት ሊያገናዝቧቸው የሚገቡ ነገሮች

📝 በዋናነት ሁለት አይነት Laptop አለ!

📌በWindows OS የሚሰራ
📌በMac OS(ለApple ብቻ)
(Kali linux, ubuntu...እራሳችን የምንጭናቸው Custom OS ስለሆኑ ብዛት እነዚ OS ያላቸውን ላፕቶፖች ገበያ ላይ አናገኝም!)

📌በብዛት በWindows OS የሚሰሩ የLaptop ዝርዝር👇
🔺Hp
🔺Dell
🔺Accer
🔺Toshiba
🔺Asus
🔺LG
🔺SONY....ወዘተ

📌በMac OS(ለApple ብቻ)
🚩Macbook Pro
🚩Macbook Air
🚩Macbook Retina

📝 Graphics Card Size
- 2GB, 4GB, 8GB...

📝 Graphics Card Type
- Nividea
- AMD Radeon (ለApple ብቻ)

📝 Screen (በኢንች)
- 13.3'', 15.6'', 17.3''

📝 Intel Processor
- Core i3, Core i5, Core i7, Core i9

📝 HDD
- 250GB, 500GB, 1TB, 2TB, 4TB...

📝 RAM/Random Access Memory
- 4GB, 8GB, 16GB, 32GB, 128GB

📝 Generation
5th, 6th, 7th, 8th

📝 Battery (ባትሪ)
- 10,000 mAh
- 20,000 mAh
- 30,000 mAh

📝 OS (ኦፕሬቲንግ ሲስተም)
- Windows
- Mac/Osx
- Kali linux
- Ubuntu
👍81❤1
ጥናታዊ ጽሁፍ/research ማዘጋጀት ትፈልጋለህ? እነዚህን 15 ነጥቦች ልብ በል።
የጥናት/ሪሰርች ይዘት፣ ስፋትና ጥልቀት ሊለያይ ይችላል፡፡ ተጨባጭ ችግርን ለመፍታት ይሁን የተደበቀ ምስጢርን ፈልፍለን ለማግኘት ወይንም ከዚሁ ለተለየ ዓላማ ጥናት ሊታቀድና ሊከናወን ይችላል፡፡
በዚሁ መሰረት አንድ ጥናት/ሪሰርች ሲዘጋጅ ከዚህ በታች የተመለከቱትን ብዙዎች ዘንድ የተለመዱ ዋና ዋና ይዘቶችን ሊያካትት ይችላል፡፡ ዝርዝሩን ተመልከቱት፤
⏺ የጥናቱ ርዕስ/ Topic
የጥናት ርዕስ ቃላት ጥንቃቄ ይፈልጋል፡፡ ትክክለኛ ስዋሰው፣ ገላጭ ቃላት፣ የጥናቱን ችግር፣ ሥፍራ/ቦታ በተቻለ መጠን በሚስብ ሁኔታ ቢጻፍ ይመረጣል፡፡ ርዕሱን የሚያነብ ሰው የጥናቱን ይዘት በቀላሉ እንዲረዳ ማድረግ ያስፈልጋል፡፡ በዚሁ በፊት ገጽ ላይ ከርዕስ በተጨማሪ፣ የአጥኚው/ዎቹ ሙሉ ሥም፣ ጥናቱ የሚቀርብለት ሠው/ተቋም፣ጥናቱ የተዘጋጀበት ወቅትና ሥፍራ ይጠቀሳሉ፡፡
⏺ ምስጋና/ Acknowledgement
የምሥጋና መልዕክት ግልጽ ነው፡፡ ጥናቱ ተጀምሮ እንዲጠናቀቅ በተለያዩ መልኩ አስተዋጽኦ ያደረጉ ሠዎች የሚመሰገኑበት ክፍል ነው፡፡ ሠው ብቻ ላይመሰገንበትም ይችላል፡፤ ሥፍራዎች፣ ሁኔታዎች፣ ወቅቶችና ሌሎች ጉዳዮች በዚህ ክፍል ሊመሰገኑ ይችላሉ፡፡
⏺ ማውጫ/Table of content
በማውጫ የጥናቱ የተለያዩ አቢይና ንዑስ ክፍሎች የሚገለጽበት ገጽ ይጠቀሳል፡፡
⏺ መግቢያ/ Introduction
በዚህ ክፍል የጥናቱን መነሻ ለአንባቢዎች መረጃ የሚሰጥበት ነው፡፡ መግቢያ መንዛዛት የለበትም፡፡ አንድ ገጽ ይበቃል፡፡ ዞሮ ዞሮ የአንድ ጥናት መግቢያ የአንባቢውን ስሜት የሚቀሰቅስ፣ የጥናቱን ወሰንና አቅጣጫ የሚያመላክት፣ጥናቱን እንዴት እንደሚሰራና የጥናቱን ጭብጥ የሚያሳይ ይዘት እንዲኖረው ተደርጎ ይዘጋጃል፡፡
⏺ የጥናቱ ዓላማ /Objective
የጥናት ዓላማ ከተለያዩ ርዕሶች ጋር ጥልቅ ቁርኝት አለው፡፡ የጥናት ዓላማ፣ ከጥናቱ ችግሮች፣መላ ምቶች መረጃና ውጤት አቀራረብና አተናተን፣ ማጠቃለያና መደምደሚያ ጋር ይተሳሰራል፡፡ የጥናት ርዕሰ ከተመረጠ በኋላ፤ በጉዳዩ ዙሪያ ያሉ ችግሮችን በሚገባ ከተረዳን በኋላ የጥናት ዓላማዎች ይዘጋጃሉ፡፡
የጥናት ዓላማዎች አቢይና ዝርዝር ተብለው ሊቀመጡ ይችላሉ፡፡ ዞሮ ዞሮ ዓላማዎች በጥናቱ የተጠቀሱ ቁልፍ ችግሮችን ወይንም መላምትን መሰረት ተደርገው ይቀረጻሉ፡፡
⏺ Statement_of_the_problem ፦ ይኸኛው ዋና መሠረት ነው። ትክክለኛ ገለጻም ይጠይቃል። “የጥናቱ ርዕስ ለመስራት ያነሳሳህ/ሽ ምን ችግር ኖሮ ነው[what is the problem that initiate you to apply your research over this title?.....]” ለሚል ጥያቄ ተገቢ መልስ የምትሰጡበት የጥናት ሰነድ ክፍል ነው። ለጥናት የተሰማራችሁበትን ችግር ወይም የአንድ ነገር እጥረት ለማስቀመጥ ሞክሩ። ገለጻችሁም "There is lack of/a problem of/ ____" የሚል አይነት ቢሆን መልካም ነው።
⏺ የጥናቱ አስፈላጊነት/ Significance of the study
ጥናት ለተለያየ አገልግሎት ይውላል፡፡ በዚህ ክፍል የዚህን ጥናት ውጤት አስፈላጊነት ግልጽ በሆነ መልኩ በዝርዝር ይቀመጣል፡፡
የጥናቱን ወሰን/ Scope of the study
በዚህ ንዑስ ክፍል የጥናቱ አጠቃላይ ስፋት፣ ርዝመትና ጥልቀት ይገለጻል፡፡ ለምሌ ያህል፣ ጥናቱ የት እንደሚሰራ፣ በእነማን ላይ እንደሚሰራ፣ ጊዜና የመሳሰሉ ወሰኖች በግልጽ ይቀመጣሉ፡፡ ወሰን ያልተበጀለት ጥናት መጀመሪያውንና መጨረሻውን ማወቅ ይቸግራል፡፡
⏺ የጥናቱ ታሳቢ ክፍተቶች/ Limitation
አንድ ጥናት ሲካሄድ ሁሉም ነገር አልጋ ባልጋ ሊሆን አይችልም፡፡ የተለያዩ ክፍተቶች ሊፈጠሩ ይችላሉና በዚህ ክፍል በጥናቱ ወቅት ሊገጥሙን የሚችሉ ችግሮች ይጠቀሳሉ፡፡ ይሁን እንጂ እነዚህ ችግሮች ከአጥኚው አቅም በላይ ሊሆኑ ይገባል እንጂ ሁሉንም ችግር መጥቀስ አይገባም፡፡ ታዲያ በዚህ ክፍል ክፍተቶቹን ለማጥበብ በአጥኚው ሊደረጉ የሚገቡ ጥረቶችም ሊካተቱ ይገባል እንጂ ክፍተቶችን ብቻ ጠቅሶ እጅን አጣጥፎ መቀመጥ አይገባም፡፡
⏺ የጥናቱ ዘዴና አካሄድ/ Methodology of the study
የአንድ ጥናት ዘዴና አካሄድ/ Methodology እንደየ ጥናቱ ጠባይ፣ችግር፣አይነትና ዓላማ የተለያየ ሊሆን ይችላል፡፡ ዘዴና አካሄድ መጥቀስ ማለት በአጭሩ ጥናቱ እንዴት እንደሚሰራ፣ የት እንደሚሰራ፣ የመረጃ መሰብሰቢያ ዘዴ ፣ የመረጃውም መሰብሰቢያ ዘዴ እንዴት አንደተዘጋጀ፤ ምን አይነት ጥናት እንደሆነ፣ የናሙና ይዘት፣ አመራረጥና መጠን (ናሙና ያለው እንደሆነ) ፣ ውጤቱ እንዴት እንደሚተነተን፣ውጤቱ እንዴት እንደሚሰራጭና የመሳሰሉ የጥናቱን አጠቃላይ አሰራርና አካሄድ መግለጽ ማለት ነው፡፡
⏺ የተዛማጅ ፅሁፍ ምልከታ/ Literature Review
በዚህ ክፍል ከዚህ በፊት የተደረጉ ጥናቶችንና ስምምነቶችን የተቀመጡ ንድፈ-ሃሳቦችን በጥልቀት ይመረመራሉ፡፡ ተዛማጅ ጽሁፍ በጥናት ውስጥ በተለያየ መልኩ ማካተት የሚስችል የጥና ጽሁፍ ምልከታ አጻጻፍ አለ፤ ከዚህ ውስጥ የሚስማማንን መርጠን መጠቀም የእኛ ምርጫ ነው፡፡ የተዛማጅ ፅሁፍ ምልከታ ሥራ ሰፊና ጥልቅ ነውና በዚህች አጭር ንዑስ ርዕስ ሁሉን መግለጽ ይከብዳል፡፡
⏺ የጥናት ግኝት አቀራረብ ትንተና/ Data analysis & Interpretation
የአንድ ጥናት ውጤት እንደ ጥናቱ አይነትና የመረጃ ማጠናቀሪያ ሥልት ሁኔታ፣ በተለያየ መልክ ሊቀርብና ሊተነተን ይችላል፡፡ አንድን ጥናት ጥናት የሚያሰኘው አጥኚው የሳይንስና የሎጂክን ስልት በመከተል በግኝቶቹ ላይ የሚደረገው ትንታኔና ትርጉም እንጂ ጥሩ የሆኑ መረጃ ማቅረብ ብቻ ሊሆን አይችልም፡፡
በመሆኑም በግኝት አቀራረብና አተናተን ወቅት አስተያየትን ከተጨባጭ ሁኔታ መለየት፤የጥናቱን ወሰን ማስታወስ እንዲሁም የተሳሳተ ትንታኔና ትርጉም ላለመስጠት ጥንቃቄ ማድረግ ያስፈልጋል፡፡
⏺ ማጠቃለያ/ Conclusion
ጥናቶች የተለያየ ስፋትና ጥልቀት አላቸው፡፡ ታዲያ ይህ ክፍል ከመጀመሪያው እስከ መጨረሻው ያሉ የወቅቱን ሁኔታና ግኝቶች በማጠቃለል አጠር ተደርጎ የሚቀርበት ነው፡፡
⏺ የመፍትሔ ሐሳብ/ Recommendation
በጥናቱ የተለዩ ችግሮችና መንስዔዎቻቸው ከታወቁ በኋላ የመፍተሄ ሃሳቦች በዝርዝር ይቀመጣሉ፡፡ ስለዚህ የመፍተሄ ሃሳቦችን ከማቅረባችን በፊት ችግሮቹን በሚገባ መረዳት ይገባል፡፡
በዚህ ክፍል ሁሉም የመፍሔ ሀሳብ ሊገለጽ አይገባም፡፡ ተጨባጭ ሁኔታን በመረዳት ተግባራዊ ሊሆኑ የሚችሉትን በመለየት በቅደም ተከተል ማቀመጥ ያስፈልጋል፡፡
⏺ አባሪ/ Appendices
በዚህ ክፍል ለጥናቱ የተገለገልንባቸውን ዝርዝር የመረጃ ማጠናቀሪያ ቅጾችና ሌሎች ዝርዝር ግብዓቶች ይቀመጣሉ፡፡
ጥናቱ ለማካሄድ የተጠቀምናቸውን መረጃዎች ማለትም መጠይይቆች፤ የተለያዮ ፕሮግራሞች እና ሌሎች ፎርማቶች ከጥናቱ ጋር ተያይዘው የሚቀርቡበት ነው፡፡
⏺ ማጣቀሻ /Reference
ይህ ክፍል ለጥናቱ የተጠቀምናቸው መረጃዎች የሚገለጽበት ነው፡፡ መረጃዎቹ በማን፣ መቼ፣የት እንደተጻፉ በግልጽ መቀመጥ አለባቸው፡፡ ስምምነት የተደረሰባቸው የተለያዩ ማጣቀሻ አጻጻፍ ስልቶች አስተምህሮዎች አሉና በተፈላጊው ስልት ማጣቀሻን በግልጽ በማስቀመጥ የጥናቱ እውነተኛነት በዚህ ክፍል ይረጋገጣል፡፡
👍110❤15👏7
የቤክሳኔት አይቲ ሶሊሽን ከዚህ ቀደም በተለያዩ መስሪያቤቶች  አሰራሮችን ዘመናዊ ለማድረግ ብዙ የወረቀት አሰራርን በሚያስቀር መልኩ፣ ለመስሪያቤቶች ከብዙ ወጭ፣ እንግልት፣ ልፋት፣ ድካም አሰራራቸውን ዘመናዊ በማድረግ ባለጉዳዮች በአጭር ሰአት ውስጥ የሚፈልጉትን መስተንግዶ በማግኘት እንዲሄዱ በማድረግ፣ የመስተንግዶ የመልካም አስተዳደር ችግር በቀላሉ የሚቀርፍ አሰራርን በመለየት ብዙ ስራዎችን በብዙ ተቋማት ላይ ተግባራዊ ያደረግን ሲሆን በዚህም ብዙ ተቋማቶች ሲስተማችንን በመጠቀም ብዙ ተጠቃሚ ሁነዋል።

አሁን ደግሞ እናንተ በመትሰሩበት መስሪያቤቶች በተለይ ከአሰራር አኳያ ዘመናዊ ቢሆን ብላችሁ የምታስቡትን ሀሳብና መስሪያቤቶችን በተወሰነ መልኩ እንድትገልጹልን እየጠየቅን አሁን በምትሰሩበት መስሪያቤቶች ምንምን ችግር አጋጠማችሁ? የሚለውን ሀሳብ መነሻ በማድረግ አጭር አስተያየት እንድትሰጡን በታላቅ ደስታ ነው።

በመረጡት ሶሻል ሚዲያ ገፆቻችንን ይጎብኙ፤ ይከተሉን!

አድራሻ:-
✅ ስ.ቁ: 0955220055
✅ ቴሌግራም አካውንት: https://t.me/BExANetplc
✅ በቴሌግራም ቻናል: https://t.me/BExANet
✅ email: bexanetplc@gmail.com
✅ ዌብሳይት www.bexanet.com
✅ Facebook:- https://www.facebook.com/profile.php?id=100090537960178&mibextid=ZbWKwL

✅ የቤክሳኔትን የYouTube ቻናልን ሰብስካራይብ በማድረግ ወቅታዊ የቴክኖሎጂ መረጃን ያግኙ!
👇👇👇Subscribe👇👇👇
https://youtube.com/@bexanetitsolutionplc
የተቋምዎን  መረጃን ዲጅታላይዝ እናድርግልዎ ስንል በደስታ ነው!
👍19👎1🔥1
✅ ስኬት👉 ወጥነት👉 ጥንካሬ

✅ ስኬታማ ለመሆን ወጥነት (consistency) ያለዉ ስራን መስራት እንጅ ጥንካሬ (intensity) አለኝ ብለህ ያለፍካቸዉ ደረጃዎች ለድካምህ ምክንያት ይሆኑሀል

✅ በአጭር ጊዜ ዉስጥ ታዋቂ እና ስኬታማ ለመሆን ከመጋጋጥ ትንሿን እና ወጥነት ያለዉን ስራ በመስራት ስኬትህ ላይ ትደርሳለህና አትቸኩል
👍44❤12🔥1