Muhammed Computer Technology (MCT)
38.1K subscribers
527 photos
7 videos
254 files
910 links
🔴አድራሻ:-
✅ ስ.ቁ: 0929273364
✅ ዌብሳይት www.mctplc.com
✅ቴሌግራም አካውንት: https://t.me/mctplc
✅ email: mct16plc@gmail.com
✅ ቲክቶክ አካውንት tiktok.com/@mctplc
Download Telegram
Truecaller-gold-v12 premium-unlocked.apk
89 MB
✅ ከ ኖርማሉ truecaller በጣም ይለያል ምክንያቱም ይሄ ፕሪሚየሙ ስለሆነ በውስጡ ብዙ አዳዲስ features አለው ተጠቀሙበት።
https://t.me/MuhammedComputerTechnology
👍13🤯1
ሰላም! ዛሬ ስለ computer አፃፃፍ ትንሽ እንማማር ።
ኮምፒውተር ላይ በአማርኛ እንዴት እንደሚፃፍ ያውቃሉ?ሲጽፉስ ምን ያህል ይፈጥናሉ?
=========================
❖መጀመሪያ Ge'ez 10 Software ያወረዱ እና install ያድርጉት ከዛም አማርኛ መፃፍ ስትፈልጉ power ge'ez status phonetic Unicode Mode (ፎ) ላይ ያድርጉት በ English መፃፍ ስትፈልጉ ደግሞ power ge'ez status English Mode (ኢ) ላይ አድርጉት ከዛም የሚከተሉትን ኣጭር መግላጫ በትክክል ይመልከቱ።
◕ሀ➭H_ሁ➭Hu_ሂ➭Hi_ሃ➭Ha_ሄ➭Hy_ህ➭He_ሆ➭Ho
◕ለ➭L_ሉ➭Lu_ሊ➭Li_ላ➭La_ሌ➭Ly_ል➭Le_ሎ➭Lo
❖ሐ➭Shift+h_ሑ➭Shift+hu_ሒ➭Shift+hi_ሓ➭Shift+ha_ሔ➭Shift+hy_ሕ➭Shift+he_ሖ➭Shift+ho
መ➭M_ሙ➭Mu_ሚ➭Mi_ማ➭Ma_ሜ➭My_ም➭Me_ሞ➭Mo
❖ሠ➭Shift+s_ሡ➭Shift+su_ሢ➭Shift+si_ሣ➭Shift+sa_ሤ
➭Shift+sy_ሥ➭Shift+se_ሦ➭Shift+so
◕ረ➭R_ሩ➭Ru_ሪ➭Ri_ራ➭Ra_ሬ➭Ry_ር➭Re_ሮ➭Ro
◕ሰ➭S_ሱ➭Su_ሲ➭Si_ሳ➭Sa_ሴ➭Sy_ስ➭Se_ሶ➭So
❖ሸ➭Shift+s_ሹ➭Shift+su_ሺ➭Shift+si_ሻ➭Shift+sa_ሼ
➭Shift+sy_ሽ➭Shift+se ሾ➭Shift+so
◕ቀ፡➭Q ቁ፡➭Qu ቂ፡➭Qi ቃ፡➭Qa ቄ፡➭Qy ቅ፡➭Qe ቆ፡➭Qo
◕በ፡➭B ቡ፡➭Bu ቢ፡➭Bi ባ፡➭Ba ቤ፡➭By ብ፡➭Be ቦ፡➭Bo
◕ተ፡➭T ቱ፡➭Tu ቲ፡➭Ti ታ፡➭Ta ቴ፡➭Ty ት፡➭Te ቶ፡➭To
◕ ቸ፡➭C ቹ፡➭Cu ቺ፡➭Ci ቻ፡➭Ca ቼ፡➭Cy ች፡➭Ce ቾ፡➭Co
◕ነ፡➭N ኑ፡➭Nu ኒ፡➭Ni ና፡➭Na ኔ፡➭Ny ን፡➭Ne ኖ፡➭No
❏ኘ፡➭Shift +n ኙ፡➭Shift +nu ኚ➭Shift+ni ኛ፡➭Shift +na ኜ፡➭Shift +ny ኝ፡➭Shift + ne ኞ፡➭Shift +no
◕ከ፡➭Ka ኩ፡➭Ku ኪ፡➭Ki ካ፡➭Ka ኬ፡➭Ky ክ፡➭Ke ኮ፡➭Ko
❖ ኸ ☛capslock + Shift + h
ኹ ☛capslock + Shift + hu
ኺ ☛capslock + Shift + hi
ኻ ☛Capslock + Shift + ha
ኼ ☛Capslock + Shift + hy
ኽ ☛Capslock + Shift + he
ኾ ☛Capslock + Shift + ho
❏ኀ፡➭ Capslock + H ኁ፡➭ Capslock + HU ኂ፡➭Capslock + HI ኃ፡➭Capslock + HA ኄ፡➭Capslock + HY ኅ፡➭Capslock + HE ኆ፡➭Capslock + HO
❏አ፡➭Capslock X ኡ፡➭Xu ኢ፡➭Xi ኣ፡➭Xa ኤ፡➭Xy እ፡➭Xe ኦ፡➭XoDe
❖ዐ፡➭Shift +x ዑ፡➭Shift +xu ዒ➭Shift +xi ዓ፡➭Shift +xa ዔ➭Shift +xy ዕ፡➭Shift +xe ዖ➭Shift +xo
✪ወ፡➭W ዉ፡➭Wu ዊ፡➭Wi ዋ፡➭Wa ዌ፡➭Wy ው፡➭We ዎ፡➭wo
✪ዘ፡➭Z ዙ፡➭Zu ዚ፡➭Zi ዛ፡➭Za ዜ፡➭Zy ዝ፡➭Ze ዞ፡➭Zo
❏ዠ፡➭Shift + Z ዡ፡➭Shift + Zu ዢ፡➭Shift + Zi ዣ፡➭Shift +Zaዤ፡➭Shift + Zy ዥ፡➭Shift +Ze ዦ፡➭Shift + Zo
✪ፈ፡➭F ፉ➭Fu ፊ፡➭Fi ፋ፡➭Fa ፌ፡➭Fy ፍ፡➭Fe ፎ፡➭Fo
✪ ፐ፡➭P ፑ፡➭Pu ፒ፡➭Pi ፓ፡➭Pa ፔ፡➭Py ፕ፡➭Pe ፖ፡➭Po
✪ገ፡➭G ጉ፡➭Gu ጊ፡➭Gi ጋ፡➭Ga ጌ፡➭Gy ግ፡➭Ge ጎ፡➭Go
✪ደ፡➭D ዱ፡➭Du ዲ፡➭Di ዳ፡➭Da ዴ፡➭Dy ድ፡➭ዶ፡Do
❏ጠ፡➭Shift + t ጡ፡➭Shift + tu ጢ፡➭Shift + ti ጣ፡➭Shift+ta ጤ፡➭Shift + ty ጥ፡➭Shift + te ጦ፡➭Shift + to
❏ጨ፡➭Shift +c ጩ፡➭Shift +cu ጪ፡➭Shift +ci ጫ፡➭Shift+caጬ፡➭Shift +cy ጭ፡➭Shift +ce ጮ: ➭Shift +co
❏ጸ፡➭Capslock + t ጹ፡➭Capslock + tu ጺ፡➭Capslock + ti ጻ፡➭Capslock + ta ጼ፡➭Capslock + ty ጽ፡➭Capslock + t ጾ፡➭Capslock + to
❖ ፀ➭☞Capslock+Shift+t
ፁ➭☞Capslock+Shift+tu
ፂ➭☞Capslock + Shift + ti
ፃ➭☞Capslock + Shift + t
ፄ➭☞Capslock + Shift + ty
ፅ➭☞Capslock + Shift + te
ፆ➭☞Capslock + Shift + to
✪ጀ፡➭J ጁ፡➭Gu ጂ፡➭Ji ጃ፡➭Ga ጄ፡➭Gy ጅ፡➭Ge ጆ፡➭Jo
✪ቨ፡➭V ቩ፡➭Vu ቪ፡➭Vi ቫ፡➭Va ቬ፡➭Vy ቭ፡➭Ve ቮ፡➭Vo
ቋ➭Capslock+qwa ቧ➭Capslock+bwa
ቷ➭Capslock+twa
ኟ➭Capslock +Shift+nwa
ቿ➭Capslock+cwa
ሟ➭Capslock+mwa
ቷ➭Capslock+twa
ጓ➭Capslock gwa
ፏ➭Capslock+fwa
ሯ➭Capslock +rwa
ዷ➭Capslock+dwa
ቯ➭Capslock+vwa
ኋ➭Capslock+hwa
ዟ➭Capslock+zwa
ዧ➭Capslock+Shif+zwa
ኗ➭Capslock+nwa
ሏ➭Capslock+lwa
ኳ➭Capslock+kwa
ሷ➭Capslock+swa
ጇ➭Capslock+jwa
ጧ➭Capslock+twa
======================================
#የተማሩትን_ማስተማር #ያወቁትን_ማሳወቅ #ብልህነት ነው
#ለሰው መልካሙን እንጅ መጥፎውን አትመኝ
#ስለኮምፒውተር ያለዎትን እውቀት ያጎለብታሉ
ይህ የኔ የፌስቡክ ገጽ ነው ስለሆነም ፔጄን ላይ ጠቃሚና ወቅታዊ መረጃዎች ያገኛሉ
👇👇👇👇

https://www.facebook.com/MuhammedComputerTechnology

ስለዚህ ፔጁን #ላይክ #ሼር በማድረግ ለሌሎች እህት ወንድሞች ጓደኞቻችሁ እንዲደርስ ያድርጉ
#በይበልጥ_ስለኮምፒውተር_ይማራሉ
#ፔጄን_like_share_ያድርጉ_መረጃ_እንዲደርሳችሁ
👍35❤9👏3🙏3😁1
አዲስ Smart ሞባይል ስልክ ሲገዙ ማገናዘብ የሚገባዎ 13 ነገሮች እነማን ናቸው?

መግዛት ያሰቡት smart ሞባይል ስልክ iPhone ወይም Samsung ወይም ሌላ ሊሆን ይችላል።ማንኛውም smart ሞባይል ስልክ ሲገዙ ስልኩ ቀጥሎ የተዘረዘሩትን 13 መመዘኛዎች ማሟላቱን ማረጋገጥ ያስፈልጋል።
1~ ፕሮሰሰር(Processor)
ብዙ ግዜ ጌም የሚጫወቱ ከሆነ፣ቪድዮ የሚያዩ ከሆነ ወይም የቪድዮ ኤዲቲንግ የሚሰሩ ከሆነ የስልኩ ፕሮሰሰር Qualcom Snapdragon(652/820/821) ቢሆን ይመረጣል።ለመካከለኛ ተጠቃሚ ፕሮሰሰሩ MedaTek ከሆነ በቂ ነው።
2 ~ ካሜራ
ፎቶ የማንሳት ልምድ ያለው ሰው የስልኩ ካሜራ 13mp(Megapixels) በላይ መሆኑን ማረጋገጥ ያስፈልጋል።ለመካከለኛ ተጠቃሚ ግን 8mp በቂ ነው።
3 ~ ባትሪ
ብዙ ሰዓት ቪድዮ ለሚያይ፣ጌም ለሚጫወት ሰው ባትሪው 3500mAh(Miliamp Hour) በላይ መሆኑን ማረጋገጥ ያስፈልጋል። ለመካከለኛ ተጠቃሚ 3000mAh በቂ ነው።
4 ~ ኦፐሬቲንግ ሲስተም(OS)
የተለያዩ ኦፐሬቲንግ ሲስተም(OS) ቨርዥኖች አሉ።ለምሳሌ samsung galaxy ስልኮች ኪትካት፣ሎሊፓፕ፣ማርሽሜሎ...ወዘተ የተባሉ ቨርዥኖች አሉ። ስለዚህ latest ቨርዥን መምረጥ ይመከራል።
5 ~ Storage
ስልኩ በቂ የማጠራቀሚያ አቅም ቢኖረው ይመረጣል። 16GB/32GB/64GB..ከነዚህ ውስጥ መምረጥ ነው። ስልኩ ኤክስተርናል ሜሞሪ(microSD card) የሚቀበል መሆን አለበት።
6 ~ Headphone Jack
HeadPhone 3.5mm audio
jack ቢሆን ይመረጣል።
7 RAM ከተቻለ ከ4GB በላይ ቢሆን ጥሩ ነው ነገርግን ለመካከለኛ ተጠቃሚ 2GB በቂ ነው
8 USB File transfer USB 2.0 በአሁኑ ጊዜ ያለ ስለሆነ ይህ ፖርት ያለው ቢሆ ይነረጣል , USB 3.0 ቢሆን ጥሩ ነው.
9 Physical Size በኢንች ለናንተ የሚቸውንም መምረጥ አለባችሁ በተለይ ለአያያዝ ምቹ መሆኑን አረጋግጡ።
10 የሚቀበለው የሲም ካርድ አይነት መለየት።
11 Display: 6.5 inches በጣም ምርጥ ነው ለአያያዝ ምቹ ነው።
12 Resolution 1080 x 2400 pixels ቢሆን ይመከራል
13 Data 4G LTE ለመጠቀም ያመች ዘንድ 4G Support የሚያደርግ ቢሆን ይመረጣል

ምሳሌ ከታች ያለውን Specification ተመልከቱ።
Dimensions: 75.8 x 164 x 8.9 mm
Weight : 205 g
SoC: MediaTek Helio P35 (MT6765)
CPU : 4x 2.3 GHz ARM Cortex-A53, 4x 1.8 GHz ARM Cortex-A53, Cores : 8
GPU : PowerVR GE8320, 680 MHz
RAM : 3 GB, 4 GB, 6 GB
Storage : 32 GB, 64 GB, 128 GB
Memory cards : microSD, microSDHC, microSDXC
Display : 6.5 in, TFT, 720 x 1560 pixels, 24 bit
Battery : 5000 mAh, Li-Ion
OS: Android 10
Camera : 8000 x 6000 pixels, 1920 x 1080 pixels, 30 fps
SIM card : Nano-SIM
Wi-Fi : a, b, g, n, n 5GHz, ac, Dual band, Wi-Fi Hotspot, Wi-Fi Direct
USB: 2.0, Micro USB
Bluetooth: 5.0
Positioning: GPS, A-GPS, GLONASS, BeiDou
👍17❤9🤔1
www.gewanetvt.edu.et_1_1.0.apk
1.2 MB
ይህ App የGewane Agricultural TVET College ዌብሳይትን የMCT Software Development Group በማበልጸግ ወደ ስራ አስገብቷል!
👇👇👇ይጋበዙ👇👇👇
www.gewanetvt.edu.et
ማሰራት ከፈለጉ ይደውሉ
#0929273364
Muhammed Computer Technology (MCT)
❤1
✴️ ኮምፒዩተራችንን በ schedule እንዴት መዝጋት እንችላለን?

🎈አንዳንዴ ትልቅ መጠን ያለውን ፋይል እንዲያወርድ አዘነው አልያም ትልቅ ሶፍትዌር install እያደረግን ከተወሰነ ሰአት በኻላ ኮምፒዩተራችን እንዲዘጋ እንፈልግ ይሆናል።

ለምሳሌ ማታ ላይ የሆነ ፋይል ብናዝ እና ከ ሁለት ሰአት በኻላ ፋይሉን አውርዶ ቢጨርስ ከዛ በኻላ እስኪነጋ ሳንዘጋው ብንተወው ለኮምፒዩተር ጤንነት አይመከርም።

🎈ይሄን ችግር ለመቅረፍ ኪይቦርዳችን ላይ የ window + R አንድ ላይ ስንጫን ከሚመጣልን መስኮት ላይ የሚከተለውን ኮማንድ እንጽፋለን።
shutdown –s –t number

🎈Number ቦታ ላይ የምንፈልገውን ሰከንድ እንጽፍለታለን።

🎈ለምሳሌ:-  shutdown –s –t 3600 ብለን enter ብንለው ከ 1 ሰአት በኻላ ኮምፒተራችን በራሱ ይዘጋል ማለት ነው።

🎈 ሌላው ሀሳባችንን ብንቀይር እና ያዘዝነውን ለማጥፋት ብንፈልግ window + R ተጭነን የሚከተለውን ኮማንድ እንጽፋለን።
shutdown –a

🏳️ ከላይ ያለው በዋነኛነት ለ window 10 የሚሰራ ሲሆን በሌሎች window OS ላይም ሊሰራ ይችላል።
════❁✿❁ ═══════
👍11
በኢትዮጵያ ትልቁ የዲጅታል ቤተ-መጽሀፍት!
ሼር አርጉላቸው

📌Join and share 👇👇👇

➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖
✦Join➬ @EthiopiaDigitalLibrary
✦Join➬ @EthiopiaDigitalLibrary
➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖
👍2
iNSTALL Ge'ez 10.exe
3.8 MB
❖መጀመሪያ ይህን Software Computet ላይ install ያድርጉት!

✅ ከዛም አማርኛ መፃፍ ስትፈልጉ power ge'ez status phonetic Unicode Mode (ፎ) ላይ ያድርጉት

✅በ English መፃፍ ስትፈልጉ ደግሞ power ge'ez status English Mode (ኢ) ላይ አድርጉት።
━━━━━━ ⊙
👍16❤1
IBM SPSS Statistics 26.0.iso
1 GB
💖 IBM SPSS Statistics 26.0
untuk 32 + 64 bits

IBM® SPSS® Statistics is the world’s leading statistical software used to solve business and research problems by means of ad-hoc analysis, hypothesis testing, and predictive analytics. Organizations use IBM SPSS Statistics to understand data, analyze trends, forecast and plan to validate assumptions and drive accurate conclusions.
👇👇👇Join👇👇👇
https://t.me/researchRC
https://t.me/researchRC
https://t.me/researchRC
https://t.me/researchRC
👍6❤1👎1
ከዚህ በፊት የለቀቅኳቸውን #Videos ዝርዝር እንደሚመለከተው አቅርቤላችኋለሁ! የ #YouTube ለቻናሉ አዲስ ከሆናችሁ #subscribe ማድረግ እንዳትረሱ!
ከዚህ በፊት ያመለጡአችሁ አዳዲስ ቪድዩዎቾ ለማየት ሊንኩን ተጫኑት
👇👇👇
ሪሰርች ስትሰሩ ከዚህ በታች የጠቀስኳቸው ከከበዷችሁ ነገ በምርጥ አቀራረብ ቪዲዮ ይዥላችሁ ቀርቤያለሁ!
✅ Automatic References
✅ Automatic List of tables
✅ Automatic List of figures
✅ Citation
በምርጥ አቀራረብ በYouTube ተዘጋጅቶ ለእይታ ዝግጁ ነው ከታች ያለውን ሊንክ በመጫን መመልከትና መማር ትችላላችሁ!

https://youtu.be/VujbubSHkZs

ከዚህ በታች የዘረዘርኳቸው
✔️ Automatic Tables of Content.
✔️ Page Break እንዴት እንሰራለን? ለሚለው ከታች ያለውን ሊንክ በመጫን ይመልከቱ

https://youtu.be/aB-z5uKq75U
✅ ስልክ ለመጥለፍ፣ መጠለፉን ለማወቅ፣ ከጠለፋ ስልካችንን ማውጣት፣ ስልካችን እንዳይጠለፍ ማድረግ እንዴት እንችላለን?
ሊንኩን በመጫን ማየት ይቻላል
https://youtu.be/-z9ciu-7rAo

✅ ፌስቡካችሁ መጠለፉን ለማወቅ፣ ፌስቡካችንን ከጠለፋ ማውጣት፣ የተጠለፈበትን ቦታ ለማወቅ፣ በስልካችን ገብተን የጠለፈብንን ሰው እንዳይጠቀምበት Logout መዝጋት
ሊንኩን በመጫን በማየት ይቻላል 👇👇👇
https://youtu.be/azdo0eTD4XY

✅ Delete Format የተደረገ ሜሞሪ፣ ፍላሽ፣ ኮምፒውተር ሀርድዲሰክ ፋይል እንዴት መመለስ እንችላልን HOW TO RECOVER DELRTED DATA Amharic👇👇👇

https://youtu.be/G8HQeWaIUKY

✅ 50 GB በነጻ! ሜሞሪ ሞላብኝ መረጃየ ይጠፋብኛል ብሎ መጨነቅ ቀረ 50GB Free storage በነጻ መረጃችሁን ያስቀምጡ! Amharic(በአማርኛ)
👇👇👇

https://youtu.be/V0Hq7k92XGY

✅ ኢሜይል በሞባይል እንዴት መላክ እንችላለን? በአማርኛ How to send email using Mobile Phone Amharic
👇👇

https://youtu.be/s1JcnGOcWeg

✅ ከኮምፒወተር ላይ ያለ ፋይሎችን እንዳይክፍትብንና Delete እንዳይድርግብን በኮምፒውተር፣ በፍላሽ፣ በHard Disk ያሉ ፋይሎችን መደበቅና
👇👇👇

https://youtu.be/4IdgIEE675s

✅ እንዴት የኮምፒተር Usersና (Password) በCMD መስበር አንችላለን How to Crack Computer Password? 👇👇

https://youtu.be/9BHgunGi2vc
✅ ፔሮል በማይክሮሶፍት ኤክሴል MS-Excel እንዴት መስራት አንችላለን ክፍል 2 Payroll Part 2
👇👇👇👇

https://youtu.be/AsQhn_ua3Cg

✅ ፔሮል በማይክሮሶፍት ኤክሴል MS-Excel መስራት አንችላለን? ክፍል -1 How to make payroll using Microsoft Excel in amharic
👇👇👇👇👇

https://youtu.be/rNcfrxbTyxo

✅ ኮምፕዩተር ፎርማት በፍላሸ ዲሰከ ለማድረግ ፍላሹን እንዴት ቡቴብል ማድረግ እንችላለን! How to Create a Bootable USB Flash Drive👇👇👇

https://youtu.be/bLCoN7LFhvA

✅ በቫይረስ የተጠቃን ፍላሽ እንዴት ቫይረሱን ማጥፋት እንችላለን?
👇👇👇

https://youtu.be/FGNbefApawM

✅ እንዴት አድርገን በስልካችን ኢሜይል መክፈት እንችላለን? How can we create Email Using Mobile Phone
👇👇👇

https://youtu.be/N-aoXuQRCXc

✅ 15GB ነፃ Storage እንዲሁም ወደ Google Drive ፋይል መጫንና ከ ወደ ሌላሰው በኢሜይል(Email) እንዴት መላክ እንችላለን ፋይል ማስቀመጥ ይቻላል?
👇👇👇

https://youtu.be/HEvXJo8E3k0
ወሳኝ MS Office Word Formulas ብዙዎቻችን የማናውቃቸው ስራን የሚያቀሉ ፎርሙላዎች
👇👇👇ይመልከቱት👇👇👇
https://youtu.be/qmU_wvTF980
#Subscribe በማድረግ ምርጥና ወቅታዊ የቴክኖሎጂ ትምህርቶችን ይከታተሉ!
በነዚህ አድራሻዎቼ ያልገባዎት ነገር ካለ ወይንም ግር ያሎትን ነገር ካለምንም ስጋት ፈታ ብለው መጠየቅ ይችላሉ። 🔻Follow me🔻
ቴሌግራም https://t.me/MuhammedComputerTechnology
👍17❤6🔥1🤔1
BExANet IT Solution PLC (ቤክሳኔት አይቲ ሶሊሽን) በኢትዮጵያ የቴክኖሎጂ ባለሙያዎች የተቋቋመ ድርጅት ነው።
ይህ ድርጅት የሀገራችን የዲጅታል ቴክኖሎጂን ለማዘመንና ሀገራችንን ከውጩ አለም ጋር በዲጅታል ቴክኖሎጂ ማህበረሰባችን ስራውንና አሰራሩን ቀላል፣ ቀልጣፋና ምቹ እንዲሆንለት በማሰብ የተቋቋመ ድርጅት ነው።
ስለሆነም ቤክሳኔት አሁን ላይ በሀገራችን ጠቃሚ የሆኑ የዲጅታል ቴክኖሎጂ ስራዎችን በተለያዩ ዘርፎች ማለትም በትምህርት፣ በጤና፣ በገንዘብ፣ በሰው ሀብት ልማት፣ና በተለያዩ የሀገራችን መስሪያቤቶች ችግር የሆኑትን ኋላቀር አሰራሮችን በመንቀስና ለችግሮቹ መፍትሄ የሚሆኑትን ቀላልና ቀልጣፋ የዲጅታል ሲስተሞችን በመስራት ወደ ገበያ እያቀረበና የተጠቃሚዎችንም ቁጥር በማብዛት ስራዎቹን ተደራሽ በማድረግ ላይ ይገኛል።

በመሆኑም ከቤክሳኔት ጋር በጋራ ለመስራት የምትፈልጉ እንዲሁም ከቤክሳኔት የተሰሩ የዲጅታል ቴክኖሎጂዎችን ለእናንተ ተቋም ተጠቃሚ እንድትሆኑ ሲል በታላቅ ግብዣ ነው።
"Empowering Digital Excellence !"

የምሰጣቸው አገልግሎቶች!
✅ Software Developement
🔶 SystenSystem
🔶 Web development
🔶 Customization
🔶 Integration
🔶 Data migration
🔶 API Developement
🔶 BackUp configuration
🔶 Vichel GPS Tracking

✅ Network & infrastructure
🔶 Installing new network
🔶 Configuring core network
🔶 SetUp security Monitoring tool
🔶 Network scaleUp
🔶 Performance Troubleshooting
🔶 Network Design
🔶 Security Cammera

✅ Training & Consultancy
🔶 ICT Training
🔶 Research & Proposal
🔶 Expertise Advisory
🔶 Risk Analysis

✅ AI & Machine Learning
🔶 Expert System
🔶 Robotics
🔶 Data Science
🔶 Data Analysis
🔶 Data Insight & Analytics
🔶 Data Engineering

ሀገር በቀል የዲጅታል ቴክኖሎጂ ድርጅት!
ቤክሳኔትን! የፌስቡክ ገጹን #Like በማድረግ የገጹ ወዳጅ ይሁኑ!


አድራሻ:-
ዌብሳይት https://bexanet.com/

Facebook:- https://www.facebook.com/profile.php?id=100090537960178&mibextid=ZbWKwL
👍6❤2😁1
ዋና ዋና የሳይበር ጥቃት አይነቶች

✅ መረጃ ጠላፊዎች የግለሰቦችን ኮምፒውተር፣ የስልክ፣ የባንክ ካርድ እና ማንኛውንም በይነመረብ ላይ ያኖሩትን መረጃ በርብረው ሊመነትፉ ይችላሉ።

✅ የሳይበር ጥቃት በግለሰብ ደረጃ ሲፈጸም ጉዳቱ እጅግ አስደንጋጭ ባይሆንም ችግሩ በአገር ደረጃ መዋቅራዊ ጉዳትን ያስከትላል ተብሏል።

✅ የሳይበር ጥቃቶች በተለያዩ የማጥቂያ መንገዶች የሚፈጸሙ ሲሆን÷ በሳይበር ምህዳሩ በስፋት ከተለመዱ ከሳይበር ጥቃት አይነቶች ውስጥ የአገልግሎት መቋረጥ፣ የዲፌስምነት ጥቃት፣ የማልዌር ጥቃት፣ ስፓምናየፌሺንግ ጥቃቶች ናቸው፡፡

✅ የአገልግሎት መቋረጥ ይህ የሳይበር ጥቃት አይነት የሲስተሞችን አቅም ባልተፈለገ ሁኔታ በማጨናነቅ ህጋዊ ተጠቃሚው አገልግሎት እንዳያገኝ ማድረግ ነው፡፡

✅ የዲፌስምነት ጥቃት ( መልክን የመቀየር ጥቃት ) ሆን ተብሎ እና ሳይጠበቅ ጣልቃ በመግባት መደበኛ የኮምፒውተር ተግባርን የሚያውክ የጥቃት አይነት ነው።

✅ የማልዌር ጥቃት የተጠቂውን ድረ- ገጽ በሀሰተኛ ሰነዶች በመቀየር የሚፈጸም የጥቃት አይነት ሲሆን÷ ስፓም (Spam): ደግሞ ብዛት ያለው እና የአጥፊነት ተልዕኮ ያላቸው ኢሜሎችን በመላክ የሚፈጸም የጥቃት አይነት ነው ተብሏል፡፡

✅ የፊሺንግ ጥቃት የሚባለው የሳይበር ጥቃት የተለያዩ የማታለያ እና የማዘናጊያ ዘዴዎችን በመጠቀም አጭበርባሪዎች ከተጠቃሚዎች ሚስጥራዊ የሆኑ መረጃዎችን ለመመዝበር የሚደረግ የማህበራዊ ምህንድስና ጥቃት ነው።
👍6❤3
አምስቱን የፈጠራ ሂደቶች ያውቋቸዋል?
================
የመፍጠር አቅማችንን የሚያሳድጉትን እነዚህ አምስት ነጥቦች ይመልከቷቸው

አዲስ ነገር ስለመፍጠር ወይም ስለመስራት ሲነሳ ምንም የመፍጠር ሙድ ውስጥ አይደለሁም፣ ዛሬስ መፍጠር ተስኖኛል፣ ሌሎች ከእኔ በላይ የመፍጠር ፀጋ አላቸው የሚሉ ተደጋጋሚ ምክንያቶች ከብዙዎች ይሰማል፡፡ ይሁን እንጂ መፍጠር የሚለው ጉዳይ ከዚህ የላቀ እይታ እና ትንታኔ የሚያስፈልገው ፅንሰ ሃሳብ ነው፡፡ ፈጠራ እንደብዙዎች እምነት ዝም ብሎ የሚከሰት ወይም የሚሆን ነገር ሳይሆን ከነበረው አሰራር ጋር አዲስ ሃሳብ በማገናኘት የሚከናወን የአዕምሮ ቅንብር ወይም የመረዳት ሂደት ነው፡፡

ሁላችንም በዕለት ተዕለት ህይወታችን እና የኑሮ እንቅስቀሴያችን ላይ አዲስ የፈጠራ መፍትሄና ውሳኔ የሚስፈልገው ጉዳይ አጋጥሞን ይሆናል፡፡ ለዚያም ጉዳይ የራሳችንን የፈጠራ ውሳኔ አሳልፈን በጎም ይሁን መጥፎ ውጤትን በፀጋ ተቀብለናል፡፡ መፍጠር ሁላችንም ውስጥ የሚገኝ ፀጋ እንደመሆኑ መጠን በተለያዩ መንገዶች ልናበለፅገውና ለእናሳድገው እንችላለን፡፡

ከዚህ ጋር ተያይዞ ከብዙ አስርት አመታት በፊት በጀምስ ዌብ ያንግ የተደረሰው አምስቱ የፈጠራ ቴክኒኮች የሚለው እይታ በዓለማችን ለተፈጠሩ አዳዲስ ሃሳቦች ትልቅ አስተዋፆኦ እንደነበረው ብዙዎች ይጠቅሳሉ፡፡ በተለይም የመፍጠር ሂደትን (creative process) በማብራራት በኩል የቢዝነስ ሰዎች፣ የገበያ ስትራቴጂስቶች እና ሌሎች ባለሙያዎች እስካሁን ድረስ እንደሚጠቀሙበት ይነገራል፡፡

እንደ ጀምስ ዌብ ያንግ ትንታኔ ከሆነ የመፍጠር ሂደት የሚባለው ነገር፤ አንድ ቀድሞ የነበረ ሃሳብ ላይ ወይም እይታ ላይ አዲስ ግንኙነት የመፍጠር ስራ ነው፡፡ ብዙዎቻችን እንደምናስበው ፈጣሪ መሆን ወይም ፈጠራ ከአዲስ ሃሳብ ጋር መምጣት ብቻ ሳይሆን፤ በዙሪያችን ካሉ እና ከነበሩ ሃሳቦች ጋር ሌሎች ሃሳቦችን ማቆራኘትና ማስተሳሰር ነው፡፡ ይህም በመሆኑ በእያንዳንዳችን ውስጥ የተሟላ የመፍጠር አቅም ይገኛል፡፡ ታዲያ አንዳንዶች በፍጥነት የመፍጠር አቅም ኖሯቸው የሌሎች ደግሞ ዘገምተኛ ከሆነ በቀጥታ የሚያያዘው ከላይ የተጠቀሱትን አምስቱን የፈጠራ ሂደቶች በሚገባ ካለማካሄድ ሊሆን ይችላል፡፡

5ቱ የፈጠራ ሂደቶች የሚከተሉት ናቸው፡፡

1. Preparation Stage

ሃሰብ ከየትም ሊመጣ ይችላል፡፡ ነገር ግን አብዛኛውን ጊዜ ሃሳብ የሚፈጠረው ከፍጀታ ነው፡፡ በዙ ነገር ላይ በመሳተፍ ጊዜያችንን የምናውል ከሆነ አዳዲስ ሃሳቦች ወደኛ ሊጎርፉ ይችላሉ፡፡ በመሆኑም በዚህ የመጀመሪያ ሂደት ልናደርግ የምንችለው አያሌ መረጃዎችን መሰብሰብና ሃሳቦች ሊያድጉ የሚችሉበትን ጥሩ ከባቢ ማዘጋጀት ነው፡፡ ፈጠራ የተፅዕኖ፣ የመቅዳት እና በዚያ ላይ ደግሞ የራስን ትርጉም የመስጠት ሂደት በመሆኑ ለአዳዲስ ልምዶች እና እይታዎች ራስን ዝግጁ ማድረግ የመጀመሪያው መንገድ ነው፡፡

2. Incubation Stage

በዚህ ሂደት ልናደርግ የምንችለው ከብዙ ቦታ ያሰባሰብናቸውን መረጃዎች እና ሃሳቦች በተለያየ እይታና መነፅር በመመልከት ወደ እንድ የሚመጡበትን ሁኔታ መፍጠር ነው፡፡ የመጀመሪያው ሂደት ራስን ብዙ ቦታዎች በማሳተፍ ከነገሮች ጋር ለመተዋወቅ መሞከር እንደመሆኑ መጠን በሁተኛው ሂደት ደግሞ ሰፊ ጊዜ በመስጠት እነዚህን ጉዳዮች ለማስተሳሰር እና ለማቀናበር የሚሞከርበት ነው፡፡ የኢንኩቤሽን ስቴጅ በረዘመ የማሰላሰል ሂደት ውስጥ የሚያልፍ በመሆኑና ረዥም ጊዜያትን በመውሰዱ የሚሰራ በመሆኑ አንዳንድ ጊዜ ሌሎች ስራዎችን እየሰራን በንቃት ወይም (consciously) ልናከናውነው እንችላለን፡፡ ይህ ሂደት ከሶስተኛው የፈጠራ ሂደት እስከሚደርስ ድረስ የሃሳቦች ህብር የሚፋጩበት እና ለውሳኔም የሚያንደረድረን ነው፡፡
3. Illumination Stage

ረዥም ጊዜ ከሚወስደው የኢንኩቤሽን ስቴጅ በኋላ የምናገኘው ይህ ሶስተኛ ሂደት የeureka ወይም የውጤት ደረጃ ይባላል፡፡ ብዙ የተለያዩ ሃሳቦችና ምልከታዎች ከተተነተኑ በኋላ አንድ ቅርፅ ወይም መልክ ይዘው የሚቀርቡበት ደረጃ ነው፡፡ የኢሉሚኔሽን ስቴጅ ቀድሞ ከነበረው ደረጃ አንፃር እጅግ በፈጠነ እና ባለተጠበቀ ሁኔታ የሚከናወን ሲሆን፤ ይህም የሚሆንበት ምክንያት በኢንኩቤሽን ስቴጅ የሚደረጉት ረዥም የሃሳብ መብላላቶች ወደ አንድ ውጤት መተው ፊት ለፊት በመታየታቸው ነው፡፡

4. Evaluation Stage

ይህ ስቴጅ የምክኒያዊነት ደረጃ ይባላል፡፡ ሶስቱን የመፍጠር ሂደቶች ጨርሰን ስንመጣ ስላረቀቅነው አዲስ ሃሳብ ራሳችንን የምንጠይቅበት ደረጃ ማለት ነው፡፡ በዚህ ሂደት ሃሳባችንን የሚፈትሹ አያሌ ጥያቄዎች ይነሳሉ፡፡ ለምሳሌ ስለሃሳቡ ረቢነት፣ ከዚህ በፊት ስለመሰራቱ፣ አንዳች ለውጥ የሚያስፈልገው ከሆነ እና ከኛ በላይ ያሉ ሰዎች ስለሃሳቡ የሚኖራቸው ግምት የሚሉ የተለያዩ ጥያቄዎች እንዲነሱ ያስፈልጋል፡፡ ይህ ሂደት ከራሳችን ጋር ትግል የምናደርግበት እና ታማኝነታችንን የምንለካበት ደረጃ እንደመሆኑ መጠን የሃሳቡን ክፍተት እና ጉድለት በሚገባ እንድንመለከት እድል ይሰጠናል፡፡ የኢቫሉዌሽን ስቴጅ ለብዙ የፈጠራ ሰዎች የስኬትም ሆነ የውድቀት ቁልፍ በመሆኑ አብዛኛውን ጊዜ የሃሳባችንን ነፀብራቅ በጥንቃቄ መፈተሽ ግድ ይላል፡፡

5. Elaboration (interpretation) Stage

በጀምስ ዌብ ያንግ የፈጠራ ሂደት ውስጥ የመጨረሻው ደረጃ ይህ ስቴጅ ነው፡፡ ኢላቦሬሽን ስቴጅ በአራቱ የመፍጠር ሂደቶች ሲብላላ የቆየውን አዲስ ሃሳብ ለትግበራ የምናዘጋጅበት እና ወደ መሬት የምናወርድበት የመጨረሻው ደረጃ ነው፡፡ ይህ ሂደት ብዙዎቹ የፈጠራ ሰዎች የሚለዩበት ከመሆኑም ባለፈ አያሌ የፈጠራ ሰዎች አምጠው የወለዱትን ሀሳብ መተግበር ተስኗቸው የሚወድቁበትም ወሳኝ ስቴጅ ነው፡፡ ጀምስ ዌብ ያንግ ይህን የፈጠራ ሂደት በአጭሩ ሲገልፀው የቶማስ ኤዲሰንን ታዋቂ ጥቅስ ይጠቀማል “1 percent inspiration and 99 percent perspiration.” በፈጠራ ሂደት ውስጥ 99 በመቶ አቅማችን ሊውል የሚገባው በፈጠርነው አዲስ ሃሳብ ላይ ነው እንጂ ለፈጠራችን መነሻ በሆነው አንድ ፐርሰንት ላይ መሆን የለበትም፡፡
ምንጭ፡ Ideapod እና James Taylor
👍17❤4
✳️ የሞባይል ባንኪንግ ሲጠቀሙ ሊያደርጓቸው የሚገቡ ጥንቃቄዎች

🚩የሞባይል ባንኪንግ የባንክ አገልግሎቶችን ወደ ባንኮች ቅርንጫፍ መሄድ ሳያስፈልግ በተንቀሳቃሽ ስልኮች አማካኝነት ብቻ የባንክ አገልግሎቶችን ማለትም ገንዘብ መላክ እና መቀበል እንዲሁም የተለያዩ ክፍያዎችን ለመፈፀም የሚያስችል ቴክኖሎጂ ነው፡፡

🚩የሞባይል ባንኪንግ አገልግሎት የተጠቃሚዎችን ድካም ከመቀነስ ጋር በተያያዘ አገልግሎቱን ተመራጭና ቀላል ያደርገዋል፤ ታዲያ ይህ አገልግሎት የቴክኖሎጂ ውጤት ከመሆኑ ጋር ተያይዞ ተጓዳኝ የመረጃ መረብ ጥቃት ተጋላጭነት አያጣውም፡፡

🚩ተጠቃሚዎች አገልግሎቱን ሲጠቀሙ የሚከተሉትን ጉዳዮች ሊያውቋቸው እና ጥንቃቄ ሊያደርጉባቸው ይገባል ሲል የኢንፎርሜሽን መረብ ደኅንነት አስተዳደር ይመክራል፡፡

➊. የተረጋገጡና ትክክለኛ የሞባይል ባንኪንግ መተግበሪያዎችን (application) ከተረጋገጡ ምንጮች አውርዶ መጠቀም፦ የሞባይል ባንኪንግ መተግበሪያዎች ትክክለኛ በባንኩ እውቅና ያላቸው መሆኑንና የሚገኙትም በትክክለኛው የመተግበሪያ ቋት ማለትም ለአንድሮይድ የመተግበሪያ ቋት ወይም ለአይ.ኦ.ኤስ ኦፕሬቲንግ ሲስተም በማውረድ መጠቀም ተገቢ ነዉ፡፡

➋. በስልኮች ላይ ያሉ ሌሎች መተግበሪያዎች ፍቃዶችን ማጥናት፡- በስልክዎ ላይ የሚገኙ ሌሎች መተግበሪያዎች የሚጠይቋቸውን ግንኙነቶች (አክሰስ) ልብ ይበሉ፡፡
መተግበሪያዎች ለአገልግሎቶቻቸው ከሚያስፈልጋቸው የሞባይል መረጃ ዉጪ ሌሎች መረጃዎች እንዲዳረሱ እንዳይፈቅዱ፡፡

➌. አፕሊኬሽኖችን /መተግበሪያዎችን ማዘመን፡- በስልኮች ላይ የሚገኙ የባንኪንግ መጠቀሚያ መተግበሪያዎችን ወቅቱን ጠብቀዉ ያዘምኑ፡፡
መተግበሪያዎች ላይ ለስርቆት የሚዳርጋቸው ክፍተቶች ሲገኙ በየወቅቱ ማዘመኛ ስለሚለቀቅላቸው የደህንነት ክፍተቶቹን ለመድፈንና የባንክ ሂሳብዎን ደህንነት ለማስጠበቅ በየጊዜው ያዘምኗቸው፡፡

➍. የሞባይል ስልክ ኦፕሬቲንግ ሲስተምን ማዘመን፡- የስልክዎን ደህንነት ክፍተት ለመሙላት በየጊዜው ክፍተት መሙያና ማሻሻያ እድሳቶች ስለሚለቀቁ በየወቅቱ እየተከታተሉ ያዘምኗቸው፡፡

➎. ከህዝብ መገልገያ ዋይፋይ ይልቅ የሞባይል ዳታ ይጠቀሙ፡- የሞባይል ባንኪንግ አገልግሎቶችን በሞባይልዎ ለመጠቀም ለህዝብ መገልገያ የቀረቡ ነፃ ዋይፋዮችን ከመጠቀም ይልቅ የሞባይል ዳታዎችን ይጠቀሙ፡፡

➏. ዘርፈ-ብዙ የደህንነት ማስጠበቂያ የይለፍ-ቃሎችን ይጠቀሙ፦ ሞባይል ስልክዎን በአሻራ፣ ፊት ማንበብያ (ፌስ ሪኮግኒሽን)፣ ፓተርን፣ ፓስወርድ እና ፓስ ኮድ የመሳሰሉትን በመጠቀም ስልክዎን ይቆልፉ፡፡

➐. በማህበራዊ ሚዲያ የሚለቋቸውን ግላዊ መረጃዎች ይገድቡ፡- በማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ የሚለቀቁ መረጃዎች የተገደቡ ሊሆኑ ይገባል፡፡

➑. ፀረ-ቫይረስ (ማልዌር) ይጠቀሙ

➒. የሞባይል ስልክዎን አካላዊ ደህንነት ያስጠብቁ

➓. የባንክ ሂሳብዎን ዘወትር ይከታተሉ፡- በተጨማሪ ተገቢውን ሁሉ ጥናቃቄ ካደረጉ በኋላም ስለ ባንክ አካውንትዎ የሚደርሱ ማንቂያዎችን (notifications) በአግባቡ መከታተል እንዲሁም በየጊዜው ስለ አካውንትዎ ሁናቴ (ስታተስ) መከታተል እና የማያውቁት የሂሳብ ለውጥ ካለ በአፋጣኝ ለባንክዎ ያሳውቁ፡፡
👍12❤2
💥የ ደህንነት ካሜራ ፣አደገኛ አጥር (fence ) ማስገጠም አስበዋል።
እነሆ መፍትሄው እኛ ጋር አለ 👇
ለ ሁሉም ቦታ የሚሆን
☞ : ለመኖሪያ ቤት
☞ : ለድርጅት
☞ : ለሱቅ
☞ : ለፋርማሲ
☞ : ለሆቴል
☞ : ለሱፐር ማርኬት
☞ : ለፋብሪካ
☞ : ለሌሎችም
ደህንነትዎን ከ መቼውም ጊዜ በላይ አስተማማኝ ያድርጉ
እጅግ ዘመናዊ ቴክኖሎጂ የተካተተባቸው ከ የተኛውም ቦታ ሆነው በቀጥታ በስልክዎ 24 ሰዓት ይከታተሉ ።
በ አነስተኛ ዋጋ ንብረትዎን እና አካባቢዎን ይጠብቁ።
ባለ 2 ካሜራ=23000
¶ 4 ቻነል ዲቪአር ሪከርደር
¶ 2 ካሜራ HD
Âś 2 ባለ 20 ሜትር ካሜራ ኬብል 

ባለ 4 ካሜራ=29500
¶ 4 ቻነል ዲቪአር ሪከርደር
¶ 4 ካሜራ HD
Âś 4 ባለ 20 ሜትር ካሜራ ኬብል 

ባለ 6 ካሜራ=39500
¶ 8 ቻነል ዲቪአር ሪከርደር
¶ 6 ካሜራ HD
Âś 6 ባለ 20 ሜትር ካሜራ ኬብል 

ባለ 8 ካሜራ=42000
¶ 8 ቻነል ዲቪአር ሪከርደር
¶ 8 ካሜራ HD
¶ 8 ባለ 20 ሜትር ካሜራ ኬብል
¶ባለ 16 ካሜራ
16 ቻናል ቪዲዮ ሪከርደር
16ባለ 20 ሜትር ኦሪጂናል የካሜራ ኬብሎች ከነ አክሰሰሪያቸው
ባለ 16 ካሜራ 78,000 ብር
Hard Disk 500GB  =2500
Servilliance HD 1TB =6000
Servilliance HD 2TB=7500
Installation 1000 per camera

ከ ተሟላ የ ሀርድ ዲሰክ አቅርቦትና ገጠማ ጋር። ያሉባት ድሪስ መጥተን እንገጥሞታለን
#secured your life & your Bussiness
#Enjoy by technolodgy

Contact us now👇👇👇👇
#0945358175
#0703453596
#0919217468
https://t.me/stareld1212
👍13