Muhammed Computer Technology (MCT)
37.7K subscribers
528 photos
7 videos
254 files
913 links
🔴አድራሻ:-
✅ ስ.ቁ: 0929273364
✅ ዌብሳይት www.mctplc.com
✅ቴሌግራም አካውንት: https://t.me/mctplc
✅ email: mct16plc@gmail.com
✅ ቲክቶክ አካውንት tiktok.com/@mctplc
Download Telegram
ንግድ ላይ ተሰማርተዋል?
E-Commerce ዌብሳይት በርግጠኝነት ያስፈልግዎታል!

በአሁኑ ሰአት ሁሉም ነገር አሰራራችን በሙሉ ዲጅታላይዝ እየሆነ መጥቷል።
መሸጥና መግዛት በኢንተርኔት አማካኝነት እየሆነ መጥቷል ለዚህም እርስዎ ማንኛውንም የሽያጭና የግዥ ስርአትዎን በ E-Commerce ዌብሳይት አማካኝነት መሸጥ መለወጥና በየትኛውም የሀገራችን ክፍል ተደራሽ መሆን ይጠበቅብዎታል። እርስዎን በዲጅታል አለም ታዋቂ መሆን ይጠበቅብዎታል።
ስለሆነም
✅ የኤሌክትሮኒክስ ሽያጭ
✅ የኮንስትራክሽን እቃዎች
✅ የድለላ ስራዎች
✅ የሆቴሎች
✅ ለመንግስትና ለግል ኮሌጆች
✅ በተጨማሪም እርስዎ በሚያስፈልግዎ መስክ
በተመጣጣኝ ዋጋ ስለምንሰራ በታላቅ ደስታ ነው። እርሶም እራዎን ቀልጣፋና ዘመናዊ ያድርጉ!

✅ ለማንኛውም ኮምፒውተራይዝድ ስራ እናማክራለን!

Muhammed Computer Technology(MCT)
ቴሌግራም አድራሽ @ma2323me
☎️ 0929273364
👍62🖕4🔥3❤2😁2👏1
ላፕቶፕ ስንገዛ ማወቅ እና ማየት ያለብን ወሳኝ ነጥቦች
1 የመሳሪያ ስርዓት (Operating system)

2 የስክሪን መጠን (Screen Size)

3 ሲፒዩ(CPU)

4 ራም(RAM)

5 የሃርድ ድራይቭ አይነት (Hard Drive Type)

6 የምስል ጥራት (Image Quality)

7 የባትሪ ቆይታ (Battery Life)

8 ብራንድ (Brand)
ኮርi3 ኮርi5 ኮርi7 ምንድናቸው?
በሃገራችን ገበያ አሁን አሁን በርከት ያሉ የላፕቶፕ እና
የኮምፒውተር ሱቆች እየታዩ ይገኛሉ፡፡ለገቢያም የተለያዩ
የላፕቶፕ አይነቶች.በተለያየ ይዘት ይገኛሉ፡፡ እንዚህን
የተለያየ ይዘት ያላቸውን የላፕቶፕ አይነቶች ለመግዛት በዋናነት
መታየት ያለበትን ከዚህ በታች በዝርዝር ተቀምጠዋል፡፡

1. የመሳሪያ ስርዓት (platform) Windows, Mac and Linux
ለአጠቃቀም ምቹ እንደሆነ የሚነገርለት Windows የብዙ ሰዎች
ምርጫ ነው፡፡ቀላል፣ ምቹ እና ተለዋዋጭ ነው፤ በዋጋም ደረጃ
ጥሩ የሚባል ነው፡፡ ማክ( Mac) የአፕል ድርጅት ምርት ሲሆን ለዲዛይን
ተመራጭ የሆነ ፕላትፎረም ነው፡፡ለደህንነትም ከWindows እንደሚሻል ይነገርለታል፡፡

2. የስክሪን መጠን ወደ ግዢ ከመግባታችን በፊት የምንገዛው ላፕቶፕ ከቦታ
ወደ ቦታ ይዘን ለመንቀሳቀስ (portable) ምቹ መሆኑን ማረጋገጥ
ያስፈልጋል፡፡ ላፕቶፖች እንደየስክሪን መጠናቸው የተከፋፈሉ ናቸው፡፡
• 11 to 12 inches(27.94cm-30.48cm) ፡በጣም
ቀጭን እና ቀላሉ የስክሪን ሳይዝ ነው፡፡ ከ1.1ኪሎ እስከ1.5ኪሎ
ይመዝናል፡፡
• 13 to 14 inches (33.02cm- 35.56cm) ፡ይህ የስክርን
ሳይዝ ያለቸው ላፕቶፖች በጣም ተመጣጣኝ portability
ያላቸው እና በላፕቶፕ ተጠቃሚዎች ተመራጭ ናቸው፡፡
• 15 inches(38.1cm): እውቁ የላፕቶፕ የስክሪን
ሳይዝ ሲሆን፤ተለቅ ያለ የስክሪን ሳይዝ ከፈለጉ ይህንን እንዲገዙ
እንመክራለን ፡፡
• 17 to 18 inches (43.18cm- 45.72cm)፡
ላፕቶፖን ይዘው የማይንቀሳቀሱ ከሆነ እና ትልቅ የስክሪን ሳይዝ
ከፈለጉ ይህንን ይግዙ፡፡ ለጌመሮች እና ትልልቅ የሶፈተዌር
ዲዛይን ለሚያደርጉ ሰዎች ተመራጭ የሆነ የላፕቶፕ አይነት ነው፡፡

3. ሲፒዩ(CPU)
የኮምፒዉተር አይምሮ በመባል የሚታወቀው ሲፒዩ
(CPU), ላፕቶፕ ለመግዛት ሁላችንም ማየት ያለብን ዝርዝር ነው፡፡
• AMD A series or Intel Core i3 / i5: በየቀኑ
ለምንጠቀማቸው ስራዎች የሚሆኑ የሲፒዩ አይነቶች
ሲሆኑ Corei5 ለሶፈትዌር ዴቨሎፕመንት እና አነስተኛ የዲዛይን
ስራዎችን ለምሳሌ እንደ Photoshop, Archicad, AutoCadን
የመሳሰሉ በጥሩ ሁኔታ እንድንሰራ ይጠቅሙናል፡፡
በተጨማሪም ግራፊክስ ካርድ ያለውና የሌለው በማለትም ይለያያሉ፡፡
ግራፊክስ ካርድ ያለቸው የተሻለ የዲዛይን እና አኒሜሽን ስራዎችን
ያከናውኑልናል፡፡ በዋጋውም ተመጣጣኝ ነው፡፡
• Intel Core i7፡ በጣም አስደማሚ የጌም እና
የዲዛይን እንዲሁም ልዩ የሆኑ የኮምፒውተር ስራችን ለምሳሌ አንደ
ሜትሮሎጂ፤ውስብስብ ስሌቶችን እንድንሰራ የሚረዳን
የላፐቶፕ አይነት ነው፡፡

4 .ራም(RAM): ለፍጥነት 4ጂቢ እና ከዛ በላይ የሆነ
RAM እንዲጠቀሙ እንመክሮታለን፡፡ ዋጋቸው አነስ ያሉ
ላፕቶፖች በ2ጂቢ ይመጣሉ፡፡ የዲዛይን ስራዎችን እና የሶፈትዌር
ዴቨሎፕመንት ስራዎችን ለመስራት 8ጂቢ ራም እና ከዚያ
በላይ ያለው ላፕቶፕ ቢገዙ ይመረጣል፡፡

5. የሃርድ ድራይቭ አይነት፡ ሁለት አይነት የሃርድ ድራይቭ
አይነቶች ያሉ( HDDrive እና SSDrive) ሲሆን
በሃገራችን ያልተለመደው SSDrive ከHDDrive የተሻለ የፍጥነት
አቅም እና ድራይቩ ላይ ያለውን ዳታ በፍጥነት መድረስ እና
መገልበጥ (copy)ያስችለናል፡፡
6 .የምስል ጥራት፡ የተሻለ ጥራት የተሻለ ምስል
እንድናገኝ ይረዳናል፡፡ 1366 x 768 ጥሩ የሚባል የምስል ጥራት
ያለው ሲሆን ከዚህ የተሻለ ወጪ በማውጣት 1920 x 1080
የተሻለ ምስል ማግኘት እንችላለን፡፡Full HD 1080P በመባልም
ይታወቃል፡፡

7 .የባትሪ ቆይታ፡ አብዛኛው ሃገር ውስጥ የሚገቡት
የላፕቶፕ አይነቶች 4 ሰዓታት የሚቆዩ ሲሆን ከ6-8 ሰዓታትም
የሚቆዩ ኦርጅናል ላፕቶፖች አሉ፡፡

8 . ብራንድ፡ የተላያዩ የላፕቶፕ ብራንዶች ባሉበት ገቢያ
የተኛውን መግዛት እንዳለብን አስቀድመን ማወቅ አለብን
👍113❤10👏4👎2🥰1
Muhammed Computer Technology (MCT) pinned «ንግድ ላይ ተሰማርተዋል? E-Commerce ዌብሳይት በርግጠኝነት ያስፈልግዎታል! በአሁኑ ሰአት ሁሉም ነገር አሰራራችን በሙሉ ዲጅታላይዝ እየሆነ መጥቷል። መሸጥና መግዛት በኢንተርኔት አማካኝነት እየሆነ መጥቷል ለዚህም እርስዎ ማንኛውንም የሽያጭና የግዥ ስርአትዎን በ E-Commerce ዌብሳይት አማካኝነት መሸጥ መለወጥና በየትኛውም የሀገራችን ክፍል ተደራሽ መሆን ይጠበቅብዎታል። እርስዎን በዲጅታል አለም…»
✅ ምርጥ የኮምፒውተር ሳይንስ ትምህርት መጽሀፎችን በPDF
✅ አዲሱን የመደበኛ ትምህርት ስርአተ ትምህርት(Curriculum) የተዘጋጀው መጽሀፍ በPDF ቴሌግራም ቻናላችን ማግኘት ይችላሉ!
👇👇👇Join👇👇👇
https://t.me/EthiopiaDigitalLibrary
https://t.me/EthiopiaDigitalLibrary
https://t.me/EthiopiaDigitalLibrary
👍26👏5🥰1
ፌስቡክዎ መጠለፉን ለማወቅና ከጠለፋ እራስዎን ያውጡ!
1. Setting and Privacy ይግቡ
2. Setting ይንኩ
3. Security
4. Security and login
5. Where you are logged in ከዚህ ውስጥ በምን ሞባይል ወይም ኮምፒውተር፣ የት ቦታና ሀገር፣ በምን ብራውዘር፣ ወይም አፕልኬሽን፣ መቼ ቀን ከዚህ በፊት እንደከፈታችሁት ያሳያችኋል። ነገር ግን ደግሞ Active now በሚል በአረንጓዴ የተጻፈው አሁን የከፈታችሁበትን ይነግራችኋል። ከዚህ በታች የተዘረዘረውን Session ስትመለከቱ የናንተ ካልሆነና የሚያጠራጥር ከሆነ ከታች ላይ Logout All Sessions የሚለውን በመጫን Logout የሚለውን በመጫን እራስዎን ከጠላፋ ማውጣት ይኖርብዎታል።
የተጠለፈ መሆኑ ከተጠራጥሩ በፍጥነት Password መቀየር ይኖርብዎታል።
ከአምስተኛው ተራ ቁጥር በመቀጠል ካለው Step Where you are logged in በታች Login ከሚለው በታች Change password የሚለውን በመጫን current password እና New password በማስገባት Save Changes የሚለውን ይጫኑ።

✅ በተጨማሪም Two factor Authentication On ቢያደርጉት ጥሩ ነው። ይህ On መሆኑ ምንም እንኳን የፊስቡክ አካውንትዎን Password ሰው ቢያውቅብዎ በስልካችሁ የሚላከውን Security code እስካላወቁ ድረስ መክፈትና መጠቀም አይችሉም። ስለዚህ On በማድረግ እንድትጠቀሙ እመክራለሁ። በፈለጋችሁ ሰአት Off ማድረግ የምትችሁ ይሆናል!

እራስዎን ከጠላፊዎች ይከላከሉ!
👍77❤9👏2
ሰላም እንዴት ናችሁ ውድ የ #Muhammed Computer Technology የ Facebook Page ተከታታዮች በጥሩ አቀራረብ ቪዲዮዎችን እየሰራሁ ለእናንተ ለእይታ እያቀረብኩ ነው። (ኢንተርኔት ማግኘት ለምትችሉ ብቻ)
ስለዚህ ቻናሉ ላይ በመግባት #Subscribe በማድረግ የቻናሉ ዘመድ እንዲሆኑ ግብዣየ ነው። ከዚህ በፊት የለቀቅኳቸውን #Videos ዝርዝር እንደሚመለከተው አቅርቤላችኋለሁ! የ #YouTube ለቻናሉ አዲስ ከሆናችሁ #subscribe ማድረግ እንዳትረሱ!
⚠️Subscribe ስታደርጉ የምንለቃቸው ፕሮግራሞች ወዲያው ይደርሷችኋል።
⚠️ ቴክኖሎጂን ከ"ሀ" ለምትጀምሩ ሰዎች በቀላሉ ብዙ ነገር ታውቃላችሁ።
⚠️መሰረታዊ ነገር ለምታውቁም በደንብ ይረዳችኋል።
⚠️በተጨማሪም ይበልጥ እንድሰራ ድጋፍ ትሆኑኛላችሁ።
ከዚህ በፊት ያመለጡአችሁ አዳዲስ ቪድዩዎቾ ለማየት ሊንኩን ተጫኑት
~\|/~~
✅
የእርሶ የሞባይል Original or Fake እንዴት እርግጠኛ ነዎት? ኦርጅናል ና ፎርጅድ መሆኑን እንዴት ማወቅ እንችላለን? በ IMEI ቁጥር ብቻ!
መታየት ያለበት ጠቃሚ ቪዲዮ
👇👇👇👇👇
https://youtu.be/U58gbQ8RXRY

✅ሰለ አንድ ኮምፒውተር (Laptop) ሙሉ መረጃ(System Information) እንዴት ማወቅ እንችላለን? ኮምፒውተር ለመግዛት ካሰቡ ይህ ቪዲዮ ይጠቅማችኋል!
👇👇👇👇👇👇👇👇

https://youtu.be/EKhKqrbv7Z0
የተማሪዎችን ውጤት ለምሳሌ A,B,C,D and F በማለት ግሬድ Computer ላይ በ Microsoft Excel መስራት
የተማሪዎችን ውጤት በ Grading system መስራት እንዴት እንችላለን? Student Mark (Grading System) መታየት ያለበት ቪዲዮ
👇👇👇👇👇👇

https://youtu.be/j7FOjQ9YaoE

✅ ምንም አይነት ሶፍትዌር ሳንጠቀም ኮምፒውተር ላይ አማርኛ እንዴት እንጽፋለን? How to Write Amharic without any Software
ጠቃሚ ቪዲዮ ይመልከቱት
👇👇👇👇👇👇👇👇👇

https://youtu.be/2geXm9IE8UY

✅ ላፕቶፓችንን ከቴሌቪዥን ጋር እንዴት አድርገን ማገናኘት እንችላለን? How to Connect Laptop and Television(TV)
👇👇👇ይመልከቱት👇👇👇👇
https://youtu.be/IWBUvdT9nqE

✅ ሪሰርች ስትሰሩ ከዚህ በታች የጠቀስኳቸው ከከበዷችሁ ነገ በምርጥ አቀራረብ ቪዲዮ ይዥላችሁ ቀርቤያለሁ!
✅ Automatic References
✅ Automatic List of tables
✅ Automatic List of figures
✅ Citation
በምርጥ አቀራረብ በYouTube ተዘጋጅቶ ለእይታ ዝግጁ ነው ከታች ያለውን ሊንክ በመጫን መመልከትና መማር ትችላላችሁ!

https://youtu.be/VujbubSHkZs

ከዚህ በታች የዘረዘርኳቸው
✔️ Automatic Tables of Content.
✔️ Page Break እንዴት እንሰራለን? ለሚለው ከታች ያለውን ሊንክ በመጫን ይመልከቱ

https://youtu.be/aB-z5uKq75U

✅ ፌስቡካችሁ መጠለፉን ለማወቅ፣ ፌስቡካችንን ከጠለፋ ማውጣት፣ የተጠለፈበትን ቦታ ለማወቅ፣ በስልካችን ገብተን የጠለፈብንን ሰው እንዳይጠቀምበት Logout መዝጋት
ሊንኩን በመጫን በማየት ይቻላል 👇👇👇
https://youtu.be/azdo0eTD4XY

✅ Delete Format የተደረገ ሜሞሪ፣ ፍላሽ፣ ኮምፒውተር ሀርድዲሰክ ፋይል እንዴት መመለስ እንችላልን HOW TO RECOVER DELRTED DATA Amharic👇👇👇

https://youtu.be/G8HQeWaIUKY

✅ 50 GB በነጻ! ሜሞሪ ሞላብኝ መረጃየ ይጠፋብኛል ብሎ መጨነቅ ቀረ 50GB Free storage በነጻ መረጃችሁን ያስቀምጡ! Amharic(በአማርኛ)
👇👇👇

https://youtu.be/V0Hq7k92XGY

✅ Mail Merge ተጠቅመን ብዙ ደብዳቤዎች በአንድ ጊዜ መስራት እንዴት እንችላለን? ማታየት ያለበት ቪዲዮ
👇👇👇👇👇👇

https://youtu.be/ov6pLgt_x-4

✅ ኢሜይል በሞባይል እንዴት መላክ እንችላለን? በአማርኛ How to send email using Mobile Phone Amharic
👇👇

https://youtu.be/s1JcnGOcWeg

✅ ከኮምፒወተር ላይ ያለ ፋይሎችን እንዳይክፍትብንና Delete እንዳይድርግብን በኮምፒውተር፣ በፍላሽ፣ በHard Disk ያሉ ፋይሎችን መደበቅና
👇👇👇

https://youtu.be/4IdgIEE675s

✅ ለተመራቂ ተማሪዎች ፓወርፖይንት (PowerPoint) ማዘጋጀት እንዴት እንችላለን? ለተመራቂ ተማሪዎች How to prepare PowerPoint Presentation? ከታች ያለው ሊንክ በማየት መጠቀም ትችላላችሁ
👇👇👇👇👇👇

https://youtu.be/oNv5u8Ru-3Q

✅ እንዴት የኮምፒተር Usersና (Password) በCMD መስበር አንችላለን How to Crack Computer Password? 👇👇

https://youtu.be/9BHgunGi2vc
✅ ፔሮል በማይክሮሶፍት ኤክሴል MS-Excel እንዴት መስራት አንችላለን ክፍል 2 Payroll Part 2
👇👇👇👇

https://youtu.be/AsQhn_ua3Cg

✅ ፔሮል በማይክሮሶፍት ኤክሴል MS-Excel መስራት አንችላለን? ክፍል -1 How to make payroll using Microsoft Excel in amharic
👇👇👇👇👇

https://youtu.be/rNcfrxbTyxo

✅ ለስራ ቅጥር CV በኢሜል መላክ ለተቸገራችሁ ወንድምና እህቶች በስልካችን ኢሜይል እንዴት መላክ እንደምንችል የሚያሳይ ቪዲዮ ምርጥ መፍትሔ ይሆናል ብየ አስባለሁ።
ከታች ያለውን ሊንክ በመጫን ይሞክሩት
👇👇👇👇👇👇

https://youtu.be/s1JcnGOcWeg
✅ ኮምፕዩተር ፎርማት በፍላሸ ዲሰከ ለማድረግ ፍላሹን እንዴት ቡቴብል ማድረግ እንችላለን! How to Create a Bootable USB Flash Drive👇👇👇

https://youtu.be/bLCoN7LFhvA

✅ በቫይረስ የተጠቃን ፍላሽ እንዴት ቫይረሱን ማጥፋት እንችላለን?
👇👇👇

https://youtu.be/FGNbefApawM

✅ ፕሪንተር ኮምፒውተራችን ፕሪንት እንዲያደርግ እንፈልጋለን ስለሆነም እንዴት ማስተዋወቅ እንደሚቻል
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇

https://youtu.be/guHu5hK-hNE

✅ ኮምፒውተራችንን እንዴት #Format አድርገን Window መጫን እንችላለን?
~በቪዲዮ ለመመልከት ከታች ያለው ሊንክ ይጠቀሙ
በWi
ndows 10 ኮምፒውተር ፍርማት ማድረግ እንዴት እንችላለን? ወይም የኮምፒውተር ዊንዶስ እንዴት መቀየር እንችላለን?
👇👇👇~~~
https://youtu.be/32GFG78SBC0

✅ እንዴት አድርገን በስልካችን ኢሜይል መክፈት እንችላለን? How can we create Email Using Mobile Phone
👇👇👇

https://youtu.be/N-aoXuQRCXc
👍79❤8🔥3👏3😁3👎1🥰1
✅ 15GB ነፃ Storage እንዲሁም ወደ Google Drive ፋይል መጫንና ከ ወደ ሌላሰው በኢሜይል(Email) እንዴት መላክ እንችላለን ፋይል ማስቀመጥ ይቻላል?
👇👇👇

https://youtu.be/HEvXJo8E3k0

#Subscribe በማድረግ ምርጥና ወቅታዊ የቴክኖሎጂ ትምህርቶችን ይከታተሉ!
በነዚህ አድራሻዎቼ ያልገባዎት ነገር ካለ ወይንም ግር ያሎትን ነገር ካለምንም ስጋት ፈታ ብለው መጠየቅ ይችላሉ። 🔻Follow me🔻
✏️Facebook:
https://m.facebook.com/mameamin.6te.net
ቴሌግራም https://t.me/MuhammedComputerTechnology
👍45❤6😁4👎1
የኮምፒውተራይዝድ ሬጅስትራር ሲስተም
ወደ ትግበራ ስራ ገብተናል 7 ኮሌጆችን ተጠቃሚ ሁነዋል! አሁንም ስራ ላይ ነኝ!
ስራው ተግባራዊ የሆነበት ቦታ
1ኛ በአማራ ክልል እንጅባራ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ
2ኛ በአማራ ክልል ቲሊሊ ቴክኒክና ሙያ ኮሌጅ
3ኛ በአማራ ክልል ቻግኒ ቴክኒክና ሙያ ኮሌጅ
4ኛ በአማራ ክልል ዳንግላ ቴክኒክና ሙያ ኮሌጅ
5ኛ በአማራ ክልል አንክሻ ቴክኒክና ሙያ ኮሌጅ
6ኛ በአማራ ክልል አዲስቅዳም ቴክኒክና ሙያ ኮሌጅ
7ኛ በደቡብ ክልል ወራቤ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ
ስራውን የትኛውም የሀገራችን ክፍል ላሉ የግልና የመንግስት ኮሌጆች ለማግኘት ከፈለጉ በተመጣጣኝ ክፍያ መውሰድ የሚቻል መሆኑን እገልጻለሁ።
ስለሆነም አሰራራችንን ዲጅታላይዝ በማድረግ ስራችንን ፈጣን፣ ቀልጣፍ፣ ምቹና ቀላል እናድርግ!
ስ.ቁ 0929273364
👍113❤12🔥9👏4
ትግበራ ዙር ሁለት!
የሬጅስትራር ሲስተሙ በደብረብርሃን ፖሊ ቴክኒክና ኮሌጅና በሰሜን ሸዋ ዞን ላሉ 9 ቴክኒክና ሙያ ኮሌጆች እንዲጠቀሙበት ስልጠና በመስጠት ወደ ተግባር ተገብቷል።

በስልጠናው ከ34 የኮሌጅ ም/ዲኖች፣ የሬጅስትራር ሀላፊና ባለሙያዎች እንዲሁም የICT መምህራን በስልጠናው ተሳትፈዋል።

እስካሁን ድረስ በአማራ ክልል ለ2 ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅና ለ14 ቴክኒክና ሙያ ኮሌጆች በጠቅላላ ለ16 ተቋማት እየተጠቀሙበት ነው።

ሲስተሙ አሁን ላይ ተጨማሪ Features የተካተቱበት ሲሆን ሲስተሙ እያደገና በኮሌጆች ውስጥ ያለውን አሰራር ሙሉ በሙሉ ዲጅታል ለማድረግ ስራውን በጥራትና በጥሩ ሁኔታ እየሄደ ይገኛል።

በቅርብ ቀን የሌሎች ተቋማትን ችግር የሚቀርፍ የዲጅታል አሰራር ይፋ የሚሆንና ወደ ተግባር የምንገባ ይሆናል።

በየተቋማችሁ የተሰራውን የዲጅታል ስርዓት ስለተጠቀማችሁና አሰራራችሁ ዲጅታል ለማድረግ ለሄዳችሁበት ርቀት በጣም ጥሩና የሚመሰገን ተግባር ስለሆነ ሁላችሁንም ላመሰግናችሁ እወዳለሁ!

በ0929273364 ልታገኙኝ ትችላላችሁ!
Telegram
👇👇👇
@ma2323me
👍23❤2
🔆ዛሬ ጠቃሚ #የመጽሐፍ 📚 ድረ ገጾችን ልጠቁማችሁ👇👇👇

1⃣. http://gen.lib.rus.ec/
ይህ👆 ድረ-ገጽ ማንኛው አይነት መፅሀፍ ማውረድ የሚያስችሎት
ሲሆን በሚሊዮን የሚቆጠር መፅሀፎች አሉት በዉስጡ
ከሚግኙ መፅሀፎች መካከል👉 #የትምህርት መፅሀፎች፤ #የሳይኮሎጂ መፅሀፎች፤
#ፍልስፍና መፅሀፎች ፤ #የታሪክ መፅሀፎች ይገኙበታል፡፡

2⃣. http://sci-hub.org/
ይህ👆 ድህረ-ገጽ ከ64 ሚሊዮን በላይ #የጥናት ወረቀት
የሚገኝ ሰለሆነ በቀላሉ ማዉረድ ይቻለሉ ፡፡

✔️በዚህ👆 ድረ- ገጽ የተለያዩ መጻፎች በተለያ ምርጫ እና አይነት ያገኛሉ።

3⃣. https://bookboon.com/
ይህ👆 ድረገጽ ማንኛው አይነት የነጻ መጻፍ የሚያገኝበት
ሲሆን በየትኛዉም የክፍል ደረጃ 👨‍🎓 ላሉ #ተማሪዎች አንዲዉም
በማንኛው የስራ ሁኔታ ላይ ላሉ ሰዎች ጠቃሚ ድርገጽ ነው፡፡

4⃣. http://bookzz.org/
#ቡክዚ 👆 አለማችን ለይ ትልቅ የመጻሀፍ #ላይብረሪ ያለው ሲሆን በአማካኝ 2.6 #ሚሊዮን መጻሀፍ በ ድረገጹ ይገኛል።

5⃣. www.allitebooks.com/
ይህ 👆 ድረገጽ ብዙ የቴክኖሎጂ #መጽሀፍት ያሉት ሲሆን የፕሮግራሚንግ፤ ግራፊክስ ፤ የኮምፒተር አጠቃቀም እና
የተለዩ የትምህርት መጻሃፎች📚 ያገኛሉ፡፡
👍62❤6👏3👎2👌1
DV ያለ ፓስፖርትና ፖስፖርት የለው ሰው እንዴት መሙላት እንደምንችል በምርጥ አቀራረብ በቪዲዮ ይዠላችሁ ቀርብልያለሁ የ YouTube ቻናል ሰብስክራይቭ ያድርጉ!
👇👇👇ቪዲዮውን ይመልከቱ👇👇👇
https://youtu.be/qT1Q3FatMt0
https://youtu.be/qT1Q3FatMt0
https://youtu.be/qT1Q3FatMt0
https://youtu.be/qT1Q3FatMt0
👍65❤1
💻 ኮምፒውተራችሁን በምትከፍቱት እና በምትጠቀሙበት ሰአት እየተንቀራፈፈ አማሯችዋል😨?

እንግዲያውስ ፍጥነቱን ሊጨምሩ የሚችሉ ነገሮችን እናያለን🤔።

✔1. Power option
Start menu ላይ power option ብላቹ ፈልጉ ከሚመጣላቹ window ውስጥ high performance የሚለውን ምረጡ

✔2.Disable unwanted start up programs

ይሄ ኮምፒዩተራችንን በምንከፍትበት ጊዜ ያለ እኛ ፍቃድ ፕሮግራሞችን እየከፈተ ፍጥነቱን ከሚቀንሱ ነገሮች አንዱ ነው። ይሄን ለመከላከል

Task manager ላይ መግባት (ይሄን ለማግኘት start menu ላይ right click አድርጎ ማግኘት ይቻላል አልያም Ctrl Alt እና delete የሚለውን አንድ ላይ መጫን) ከሚመጣው window ውስጥ start up ላይ በማድረግ የማትፈልጉትን ፕሮግራሞች disable ማድረግ።

እዚህ ጋር impact የሚለው high ከሆነ disable ባታረጉ ይመረጣል።

✔3.Defragment and optimize drive Start menu search bar ላይ defragment ብሎ መፈለግ
Window ሲመጣላቹ የምትፈልጉትን driver መርጣቹ optimize ማድረግ

✔4. Delete unnecessary temporary file Start menu ላይ right click አድርጎ run የሚለውን መምረጥ አልያም window key እና R ን ከ ኪቦርዳችን ላይ አንድ ላይ መጫን
%temp% ብሎ ጽፎ enter መጫን የሚመጣላቹ folder ላይ ያሉ ፋይሎችንctrl + A ተጭነን ሁሉንም ሲመርጥልን ማጥፋት
ድጋሚ run ቦክሱን ከፍታቹ temp ብሎ መጻፍ ከሚመጣላቹ folder ውስጥ ያሉ ፋይሎችን ሁሉ ማጥፋት አሁንም ለ ሶስተኛ ጊዜ run ቦክስ ላይ prefetch ብሎ መጻፍ የሚመጣላቹ folder ውስጥ የሚገኙ ፋይሎችን ማጥፋት።

እነዚህን የምናጠፋበት ምክንያት ጊዜያዊ እና space የያዙ ፋይሎች ስለሆኑ ነው። ምንም አይነት ችግር አያመጡም።

✔5. Clean up Memory
This pc ውስጥ ገብታቹ የምፈልጉት local ዲስክ ላይ right click በማድረግ property መምረጥ Disk clean up የምትለውን icon click ማድረግ
የሚመጣውን የ warning box ok ማድረግ እዚህ ጋ recycle bin ውስጥ ያሉ ፋይሎች ሳይቀሩ ነው የሚጠፉት

✔6. Reduce run time service
Run box ከፍታቹ msconfig ብሎ መጻፍ ቀጥሎ ከሚመጣው window service የሚለውን መጫን በመቀጠል hide all microsoft service የሚለውን tick ማድረግ በመቀጠል disable የምትለዋን icon click ማድረግ

✔7. Registry tweaks
Run box መክፈት(window key + R) regedit ብሎ መጻፍ
Hkey -current user Control panel Mouse Mouse hover time valueን ወደ 10 መቀየር
እዛው folder ላይ desktop መምረጥ Menu show delay
Valueን ወደ 10 መቀየር

✔8. visual effects
Start menu ላይ System ብሎ መፈለግ Advanced system setting መምረጥ
Advance ውስጥ በመግባት setting መምረጥ Adjust for best performance መምረጥ
ቀጥሎ የምትፈልጉት ነገር ካለ ቲክ በማድረግ መምረጥ በመጨረሻም ከላይ ያሉትን ከጨረስን በኋላ ኮምፒዩተራችንን Restart ማድረግ
👍125😁7🔥5🥰5❤4👏1🕊1
💻 ኮምፒውተር ላይ በአማርኛ እንዴት እንደሚፃፍ ያውቃሉ?ሲጽፉስ ምን ያህል ይፈጥናሉ?
=========================

■ ጠቃሚ መረጃ ነው!! ላልደረሰው ያዳርሱ አሁኑኑ ሼር ያድርጉት፡፡

❖መጀመሪያ ከላይ የለቀቅንላችሁን መጀመሪያ Ge'ez 10 Software ያወረዱ እና install ያድርጉት ከዛም አማርኛ መፃፍ ስትፈልጉ power ge'ez status phonetic Unicode Mode (ፎ) ላይ ያድርጉት በ English መፃፍ ስትፈልጉ ደግሞ power ge'ez status English Mode (ኢ) ላይ አድርጉት ከዛም የሚከተሉትን ኣጭር መግላጫ በትክክል ይመልከቱ።
⁉️ ሶፍትዌሩን ለማግኘት ከፈለጋችሁ ከቴግራም ቻናሌ ማግኘት ትችላላችሁ
👇👇👇👇👇👇👇👇👇 https://t.me/MuhammedComputerTechnology
◕ሀ➭H_ሁ➭Hu_ሂ➭Hi_ሃ➭Ha_ሄ➭Hy_ህ➭He_ሆ➭Ho

◕ለ➭L_ሉ➭Lu_ሊ➭Li_ላ➭La_ሌ➭Ly_ል➭Le_ሎ➭Lo

❖ሐ➭Shift+h_ሑ➭Shift+hu_ሒ➭Shift+hi_ሓ➭Shift+ha_ሔ➭Shift+hy_ሕ➭Shift+he_ሖ➭Shift+ho

◕መ➭M_ሙ➭Mu_ሚ➭Mi_ማ➭Ma_ሜ➭My_ም➭Me_ሞ➭Mo

❖ሠ➭Shift+s_ሡ➭Shift+su_ሢ➭Shift+si_ሣ➭Shift+sa_ሤ➭Shift+sy_ሥ➭Shift+se_ሦ➭Shift+so

◕ረ➭R_ሩ➭Ru_ሪ➭Ri_ራ➭Ra_ሬ➭Ry_ር➭Re_ሮ➭Ro

◕ሰ➭S_ሱ➭Su_ሲ➭Si_ሳ➭Sa_ሴ➭Sy_ስ➭Se_ሶ➭So

❖ሸ➭Shift+s_ሹ➭Shift+su_ሺ➭Shift+si_ሻ➭Shift+sa_ሼ➭Shift+sy_ሽ➭Shift+se ሾ➭Shift+so

◕ቀ፡➭Q ቁ፡➭Qu ቂ፡➭Qi ቃ፡➭Qa ቄ፡➭Qy ቅ፡➭Qe ቆ፡➭Qo

◕በ፡➭B ቡ፡➭Bu ቢ፡➭Bi ባ፡➭Ba ቤ፡➭By ብ፡➭Be ቦ፡➭Bo

◕ተ፡➭T ቱ፡➭Tu ቲ፡➭Ti ታ፡➭Ta ቴ፡➭Ty ት፡➭Te ቶ፡➭To

◕ ቸ፡➭C ቹ፡➭Cu ቺ፡➭Ci ቻ፡➭Ca ቼ፡➭Cy ች፡➭Ce ቾ፡➭Co

◕ነ፡➭N ኑ፡➭Nu ኒ፡➭Ni ና፡➭Na ኔ፡➭Ny ን፡➭Ne ኖ፡➭No

❏ኘ፡➭Shift +n ኙ፡➭Shift +nu ኚ➭Shift+ni ኛ፡➭Shift +na ኜ፡➭Shift +ny ኝ፡➭Shift + ne ኞ፡➭Shift +no

◕ከ፡➭Ka ኩ፡➭Ku ኪ፡➭Ki ካ፡➭Ka ኬ፡➭Ky ክ፡➭Ke ኮ፡➭Ko

❖ ኸ ☛capslock + Shift + h
ኹ ☛capslock + Shift + hu
ኺ ☛capslock + Shift + hi
ኻ ☛Capslock + Shift + ha
ኼ ☛Capslock + Shift + hy
ኽ ☛Capslock + Shift + he
ኾ ☛Capslock + Shift + ho

❏ኀ፡➭ Capslock + H ኁ፡➭ Capslock + HU ኂ፡➭Capslock + HI ኃ፡➭Capslock + HA ኄ፡➭Capslock + HY ኅ፡➭Capslock + HE ኆ፡➭Capslock + HO

❏አ፡➭Capslock X ኡ፡➭Xu ኢ፡➭Xi ኣ፡➭Xa ኤ፡➭Xy እ፡➭Xe ኦ፡➭XoDe

❖ዐ፡➭Shift +x ዑ፡➭Shift +xu ዒ➭Shift +xi ዓ፡➭Shift +xa ዔ➭Shift +xy ዕ፡➭Shift +xe ዖ➭Shift +xo

✪ወ፡➭W ዉ፡➭Wu ዊ፡➭Wi ዋ፡➭Wa ዌ፡➭Wy ው፡➭We ዎ፡➭wo

✪ዘ፡➭Z ዙ፡➭Zu ዚ፡➭Zi ዛ፡➭Za ዜ፡➭Zy ዝ፡➭Ze ዞ፡➭Zo

❏ዠ፡➭Shift + Z ዡ፡➭Shift + Zu ዢ፡➭Shift + Zi ዣ፡➭Shift +Zaዤ፡➭Shift + Zy ዥ፡➭Shift +Ze ዦ፡➭Shift + Zo

✪ፈ፡➭F ፉ➭Fu ፊ፡➭Fi ፋ፡➭Fa ፌ፡➭Fy ፍ፡➭Fe ፎ፡➭Fo

✪ ፐ፡➭P ፑ፡➭Pu ፒ፡➭Pi ፓ፡➭Pa ፔ፡➭Py ፕ፡➭Pe ፖ፡➭Po

✪ገ፡➭G ጉ፡➭Gu ጊ፡➭Gi ጋ፡➭Ga ጌ፡➭Gy ግ፡➭Ge ጎ፡➭Go

✪ደ፡➭D ዱ፡➭Du ዲ፡➭Di ዳ፡➭Da ዴ፡➭Dy ድ፡➭ዶ፡Do

❏ጠ፡➭Shift + t ጡ፡➭Shift + tu ጢ፡➭Shift + ti ጣ፡➭Shift+ta ጤ፡➭Shift + ty ጥ፡➭Shift + te ጦ፡➭Shift + to

❏ጨ፡➭Shift +c ጩ፡➭Shift +cu ጪ፡➭Shift +ci ጫ፡➭Shift+caጬ፡➭Shift +cy ጭ፡➭Shift +ce ጮ: ➭Shift +co

❏ጸ፡➭Capslock + t ጹ፡➭Capslock + tu ጺ፡➭Capslock + ti ጻ፡➭Capslock + ta ጼ፡➭Capslock + ty ጽ፡➭Capslock + t ጾ፡➭Capslock + to

❖ ፀ➭☞Capslock+Shift+t
ፁ➭☞Capslock+Shift+tu
ፂ➭☞Capslock + Shift + ti
ፃ➭☞Capslock + Shift + t
ፄ➭☞Capslock + Shift + ty
ፅ➭☞Capslock + Shift + te
ፆ➭☞Capslock + Shift + to

✪ጀ፡➭J ጁ፡➭Gu ጂ፡➭Ji ጃ፡➭Ga ጄ፡➭Gy ጅ፡➭Ge ጆ፡➭Jo

✪ቨ፡➭V ቩ፡➭Vu ቪ፡➭Vi ቫ፡➭Va ቬ፡➭Vy ቭ፡➭Ve ቮ፡➭Vo
▁▁▁▁▁▁▁▁▁▁

ቋ➭Capslock+qwa ቧ➭Capslock+bwa
ቷ➭Capslock+twa
ኟ➭Capslock +Shift+nwa
ቿ➭Capslock+cwa ሟ➭Capslock+mwa
ቷ➭Capslock+twa ጓ➭Capslock gwa
ፏ➭Capslock+fwa ሯ➭Capslock +rwa ዷ➭Capslock+dwa ቯ➭Capslock+vwa ኋ➭Capslock+hwa ዟ➭Capslock+zwa ዧ➭Capslock+Shif+zwa
ኗ➭Capslock+nwa ሏ➭Capslock+lwa
ኳ➭Capslock+kwa ሷ➭Capslock+swa
ጇ➭Capslock+jwa ጧ➭Capslock+twa

♨️የተቸገሩ ሰዎችን በጣም ይጠቅማቸዋል አሁኑኑ ሼር ያድርጉ፡፡
━━━━━━ ⊙ ━━━━━━

🗣➹share &Join Us
👇🏾👇🏾👇🏾
እንዲሁም ከዚህ በፊት የለቀቅኳቸውን ቪዲዮዎችን ብትከታተሉ ምርጥ እውቀትን ልታገኙ ትችላላችሁ
አሁንም የቴሌግራምና የYouTube ቻናሌን Subscribe በማድረግ ድጋፋችሁን አሳዩኝ።
✅✅✅#ያወቁትን ማሳወቅ ብልህነት ነው!✅✅✅

የ YouTube ቻናል ሊንክ 👇👇👇
https://www.youtube.com/channel/UCZBIP6PqUdmmagdTjbyp_AQ

ቴሌግራም ቻናል
👇👇👇👇👇👇 https://t.me/MuhammedComputerTechnology
👍93👏9🔥5❤3🥰2😁1
ጎግል ፕሌይ ስቶር ብልሽት ለማስተካከል

✅ Google Play Store በአብዛኛዎቹ የAndroid ዘመናዊ ስልኮች ላይ ተጭኖ የሚመጣ ሲሆን በሆነ ምክንያት በዲቫይሱ(ስልክ ወይም ታብሌት) ላይ መሥራት ሊያቆም ሊያጋጥም ይችላል፡፡

✅ በዚህም ምክንያት በዲቫይሱ ላይ የተጫኑ ሶፍትዌሮችን የቅርብ ግዜ ማድረግ፣ ሶፍትዌሮችን ዳውንሎድ አድርገን መጫን እና አንድሮይድ ኦፕሬቲንግ ሲስተሙን የቅርብ ግዜ ማድረግ አንችልም፡፡

✅ Google Play መደብር በእርስዎ ዲቫይስ ላይ የማይሰራ ከሆነ ችግሩን ለመፍታት አንዳንድ መንገዶችን እጠቁማለሁ

1. የዲቫይሱን ቀን እና ሰዓት ቅንብር(ሴቲንግ) ያስተካክሉ
የተሳሳተ ቀን እና የጊዜ ገደብ ሲኖርዎት የGoogle አገልጋዮች ከአሳሽዎ ጋር ማመሳሰል ችግሮች ያጋጥማቸዋል ለማሰተካከል ወደ ሲስተም ሴቲንግ በመሄድ «ቀን እና ሰዓት» ማስተካከል ይጠበቅብዎታል፡፡
“Automatic date & time” and “Automatic time zone” እንዲሰራ ክፍት ያድርጉ ወይም ማኑዋሊ ቀን እና ሰዓት ያስተካክሉ፡፡

2. ጎግል ፕሌይ ስቶር ከዚህ በፊት ይዞት የነበረውን ዳታ ማጽዳት
በጎግል ፕሌይ ስቶር ላይ ከዚህ በፊት ተጠቅመናቸው የነበረው ሶፍትዌሮች ዝርዝ ይዞ ይቀመጣል(Cached data) ይሄ በምንፈልገው ጊዜ በፍጥነት ለመክፈት ኢንተርኔት ግንኙነቱ ፍጥነት ባይኖረውም ይረዳናል ነገር ግን Cached data አንዳንድ ጊዜ በPlay Store ላይ ችግር ይፈጥራል፡፡

✅ በGoogle Play ላይ Cached data ለማጽዳት እነዚህን ደረጃዎች ይከተሉ:
ደረጃ # 1: ሲስተም ሴቲንግ
ደረጃ # 2: አፕስ (Apps)
ደረጃ # 3: Google Play Store ይክፈቱ
ደረጃ # 4: ስቶሬጂ በመክፈት “CLEAR CACHE“.

3. የቅርብ ግዜ የሆነ ጎግል ፕሌይ ስቶር መጫን
በየጊዜው ሶፍትዌሮችን የሚሰሩ ዴቨሎፐሮች ለሰሩት ሶፍትዌር የቅርብ ግዜ ማድረጊያ አብዴተር የሚለቁ ሲሆን በዚህ የቅር ማድረጊያ ላይ የተለያዩ ችግሮች ለመፍታት የሚያስችል ይካተታል፡፡.
በተመሳሳይ መልኩ Google የ Play ስቶር አብዴተር በየጊዜው የሚያወጣ ሲሆን እንደሚኖሩበት አገር የሚለቀቀው አብዴት ሊዘገይ ይችላል በቀጥታ የቅርብ ማድረጊያውን(APK ፋይል) ማግኘት ከቸኮሉ APKMirror በማለት ኢንተርኔት መጠቀሚያ ብሮውዘር ላይ ፈልገው ማውረድ ይችላሉ፡፡

4. ጎግል ፕሌይ ስቶር ወደነበረበት የመጀመሪያው ቨርዥን መመለስ
አንዳንዴ የቅርብ ጊዜ የተደረገ የጎግል ፕሌይ ስቶር ስሪት በርካታ ችግሮችን ሊያመጣ ይችላል ስለሆንም አብዴት የተደረገው በማጥፋት ዲቫይሱን ስንገዛ የነበረውን(factory version ) ጊዜ መመለስ፡፡ እነዚህን ደረጃዎች በመከተል እናጥፋ:
ደረጃ # 1: ሲስተም ሴቲንግ
ደረጃ # 2: አፕስ (Apps)
ደረጃ # 3: Google Play Store ይክፈቱ
ደረጃ # 4: “Uninstall Updates”

5. ጎግል ፕሌይ ሰርቪስ መስራቱን ማረጋገጥ
Google Play Services ዋናው ተግባራት የGoogle አገልግሎቶች የሆኑትን Google Play ስቶር፣ ጎግል ማፕ፣ ጎግል ፕላስ ወዘተ አገልግሎቶች አውቶማቲካሊ ግንኙነት እንዲያደርጉ እና አብዴት የሚያደርግ የሚረዳ በመሆኑ እንደ ተጨማሪ መፍትሄ በመውሰድ Google Play Services መስራቱን ያረጋግጡ፡፡

6. ጎግል ፕሌይ ስቶርን ዘግቶ መክፈት
ይህ በአብዛኛው ተጠቃሚዎች የሚተገበሩበት የተለመደ ዘዴ ነው፡፡ ማድረግ ያለብዎት ነገር Google Play Storeን በመዝጋት እንደገና ማስጀመር( ለሌሎች አፕ ይሰራል) ችግሩን ሊፈታው ይችላል
ደረጃ # 1: ሲስተም ሴቲንግ
ደረጃ # 2: አፕስ (Apps)
ደረጃ # 3: Google Play Store ይክፈቱ
ደረጃ # 4: “Force Stop” የሚለውን በመጠቀም መዝጋት እና እንደገና ይክፈቱ

7. ዲቫይሱን አጥፍቶ ማብራት
ዲቫይሱን አጥፍቶ ማብራት ተመራጭ መፍትሄ ሲሆን ብዙውን ግዜ ይሰራል ምክንያቱም ስማርትፎን ስልኮች አጥፍተን ዳግም ማስጀመር በዲቫይሱ ላይ ያሉትን አፕ ያረጋጋል፡፡ በተቻለ መጠን አንድ አፕ ከወትሮው የተለየ ተግባር ካመጣ ዳግም አጥፍተን ስናስጀምር የተሻለ አፈጻጸም እና ችግሩን መፍታት ይችላል፡፡

8. ዲቫይሱን አንድሮድ ኦፕሬቲንግ ሲስተም ዳግም ማስጀመር
ከላይ በጠቀስኩት መፍትሄ ምንም የማይሰራ ከሆነ ዲቫይሱን ፋብሪካ ዳግም ማስጀመር (hard reset) ማድረግ በዚህ ሂደት በዲቫይሱ ላይ ያሉትን ዳታ፣ የተጫኑ አፕሊኬሽን ሶፍትዌር እንደዚሁም የተጠቃሚውን አካውንት የመሳሰሉትን ሁሉ ያጠፋል፡፡
በርካታ ችግሮች በዲቫይሱ ላይ ካልገጠመዎት በስተቀር የፋብሪካ ዳግም ማስጀመር (hard reset) ባትጠቀሙ እመርጣለሁ ዳግም ለማስጀመር ከወሰኑ ሚሞሪው ያውጡ መጠባበቂያ መውሰድዎን አይርሱ፡፡

ይሄን ችግር ለመፍታት ሊያግዝ የሚችል የተሻለ መፍትሄዎች ካለዎት አስተያየትዎን ይስጡን እንዲሁም ለ ጉዋደኞቹዎ ያካፍሉ
https://t.me/MuhammedComputerTechnology
👍66👏6❤5
በኢትዮጵያ የፔሮል ሲስተም በምርጥ አቀራረብ በማይክሮ ሶፍት ኢክስኤል ክፍል እንድንና ሁለትን በትክክል ይመልከቱት
✅ ፔሮል በማይክሮሶፍት ኤክሴል MS-Excel መስራት አንችላለን? ክፍል -1
👇👇👇👇👇

https://youtu.be/rNcfrxbTyxo

✅ ፔሮል በማይክሮሶፍት ኤክሴል MS-Excel እንዴት መስራት አንችላለን ክፍል 2 Payroll Part 2
👇👇👇👇

https://youtu.be/AsQhn_ua3Cg
👍46❤6😁1
*The most important words*
1.*PAN* - permanent account number.
2. *PDF* - portable document format.
3. *SIM* - Subscriber Identity Module.
4. *ATM* - Automated Teller machine.
5. *IFSC* - Indian Financial System Code.
6. *FSSAI(Fssai)* - Food Safety & Standards Authority of India.
7. *Wi-Fi* - Wireless fidelity.
8. *GOOGLE* - Global Organization Of Oriented Group Language Of Earth.
9. *YAHOO* - Yet Another Hierarchical Officious Oracle.
10. *WINDOW* - Wide Interactive Network
Development for Office work Solution.
11. *COMPUTER* - Common Oriented Machine. Particularly United and used under Technical and Educational Research.
12. *VIRUS* - Vital Information Resources Under Siege.
13. *UMTS* - Universal Mobile Telecommunications System.
14. *AMOLED* - Active-matrix organic light-emitting diode.
15. *OLED* - Organic light-emitting diode.
16. *IMEI* - International Mobile Equipment Identity.
17. *ESN* - Electronic Serial Number.
18. *UPS* - Uninterruptible power supply.
19. *HDMI* - High -Definition Multimedia
Interface.
20. *VPN* - Virtual private network.
21. *APN* - Access Point Name.
22. *LED* - Light emitting diode.
23. *DLNA* - Digital Living Network Alliance.
24. *RAM* - Random access memory.
25. *ROM* - Read only memory.
26. *VGA* - Video Graphics Array.
27. *QVGA* - Quarter Video Graphics Array.
28. *WVGA* - Wide video graphics array.
29. *WXGA* - Widescreen Extended Graphics Array.
30. *USB* - Universal serial Bus.
👍78❤10👏6😁2
​Are you looking for programming trainings?

Strongly encourage you to check out
TOFI TECHNOLOGIES PLC. (TT)

I think you need to look for a place where you can get some hands on training on the software they use and how it works and more likely to be successful in the workplace. 

Also, make sure you have a
good understanding of the business and the industry before you get started

📌 programming course.
course will include the following topics:


📚Frontend with javascript, html, css and bootstrap (4 months training)
📚Java for Android studio (4 months training)

📚 Backend with Nodejs, Express and Mysql (3 months training)
📚 basic cyber security (1 month training)

contact 📨

web:- https://tofitech.net
telegram:-  tofitechno.t.me
phone number:- +251902077707

📍 adress
Ayer tena peniel tower 3rd floor
👍24👏4
ከF1 እስከ F12 ያሉ #የዊንዶውስ
ቁልፎች አገልግሎት

የኮምፒውተር ኪቦርዳችን ላይ ከላይ የሚገኙትን (F1-F12) በተኖች ጥቅማቸውን ያውቁ ኖሯል?

ካላወቃችሁ አትጨነቁ፡፡ ዛሬ የተወሰነ ጥቅማቸውን እናሳያችኋለን፡፡ እነዚህን የኪይቦርድ በተኖች ከዚህ በፊት ድምፅ ለመጨመር እንዲሁም የብርሃን መጠን ለማስተካከል ተጥቀምውባቸው ይሆናል፡፡ ነገር ግን ጥቅማቸው ከዚህ ከፍ ያለ ነው:: ሁሉም ኮምፒውተር በሚያስብል ሁኔታ እነዚህን በተኖች ይዞ ነው የሚመጣው፡፡ እና ምንም ማስተካከል ሳያስፈልግ መጠቀም እንችላለን፡፡ ነገር ግን አንዳንድ ኮምፒውተሮች ላይ እነዚህን በተኖች ለመጠቀም FN የሚለውን በተን በቅድሚያ መንካት አለብን::

ከF1 እስከ F12 ያሉትን በተኖች ጥቅም አንድ በአንድ ከስር ዘርዝረናል .... ሼር በማድረግ ከራስዎ አልፈው ለሌሎችም ይትረፉ፡፡

🏷 በኮምፒውተራችን ኪይቦርድ ከላይ ተደርድረው
የምናገኛቸው ከF1 – F12 ያሉ ቁልፎችን Function
Key እንላቸዋለን፡፡
በዋናነትም ከሌሎች #ቁልፎች ጋር
በማጣመር እንደ አቋራጭ እንጠቀምባቸዋለን፡፡ እንኘህ
ቁልፎች እንደ ምንጠቀመው የ ኦፐሬቲንግ ሲስተም እና
ሶፍትዌሮች አገልግሎታቸው ይለያያል፡፡: በዛሬው
ቱቶሪያላችንም የተወሰኑትን እናያለን፡፡

◽️F1
ብዙ ጊዜ የምንጠቀመው እርዳታ ስንሻ ነው፡፡ በአብዛኛው
ሶፍትዌሮች F1 ስንጫን #የ Help መስኮትን ይከፍቱልናል፡፡
ማይክሮሶፍት ወርድ ላይ ካለን Start እና F1 መጫን የ
Microsoft Online Help ይከፍታል፡፡
◽️F2
#የተመረጠን አይከን፤ፋይል ወይንም አቃፊ ስም ለመቀየር
F2 መጫን ይቻላል፡፡ ማይክሮሶፍት ወርድ ላይ ካለን Alt
+ Ctrl + F2 መጫን #የ Open መስኮትን ይከፍታል፡፡፡
◽️F3
ዴስክቶፕ ላይ ካን ስንጫን የፍላገ መስኮት ይከፈታል፡፡
ማይክሮሶፍት ወርድ ላይ ካለን ቃልን መርጠን Shift +
F3 መጫን #የተመረጠው ቃል ውስት የሚገኙ ፊደላትን
አንድላይ ካፒታል ወይን ስሞል ወይንም የመጀመሪያውን
ፊደል ካፒታል ያደርግልናል፡፡
◽️F4
አሁንም ማይክሮሶፍት ወርድ ላይ ካለን F4 #መጫን
ለመጨረሻ ጊዜ የተገበርነውን ይደግምልናን፡፡ ለምሳሌ
አበበ ብለን ብንጽፍ እና F4 ብናጫን በ የምትባለውን
ፊደለ በድጋሚ ይጽፍልናል፡፡ Alt + F4 መጫን አክቲቭ
#የሆነውን መስኮት ይዘጋልናል፡፡ Ctrl + F4 ስንጫን
ደግሞ አክቲቭ ከሆነው መሰኮት ውስጥ አክቲቭ የሆነውን
ታብ ይዘጋልናል፡፡ ለዚህ ጥሩ ምሳሌ የሚሆነው በ
ብራውሰራችን ከአንደ በላይ ታብ ከከፈትን Ctrl + F4
ስንጫን ያለንበትን ታብ ብቻ ይዘጋልናለን ነገር ግን Alt +
F4 ብንጫን ሙሉ በሙሉ ብራውሰሩን ይዘጋብና ማት
ነው፡፡
◽️F5
አሁን ገበያ ላይ ባሉት አብዛኛዎ ብራውሰሮች ላይ F5
መጫን # Refresh ያደርገልና፡፡ ማይክሮሶፈት ወርድ ላይ የ
Find መስኮትን ይከፍትልናል፡፡ ማክሮሶፍት ፓወር ፖይንት
ላይ ደግሞ Slideshow ያስጀምርልና፡፡
◽️F6
በአብዛኛው ብራውሰሮች ላይ F6 ስንጫን የማውሳችን
አቅጣጫ መጠቆሚያ #(cursor) ወደ አድራሻ መጻፊያው
ይወስድልና፡፡ ከአንድ በላይ የማይከሮሶፍት ወርድ
ከከፈትን Ctrl + Shift + F6 መጫን #ወደቀጣዩ
የማይክሮሶፍት መስኮትያሸጋግረናል፡፡
◽️F7
ማይክሮሶፍት ወረድ ላይ Shift + F7 መጫን የ
#Thesaurus መስኮትን ይከፍትልናል የሚያገለግለውም
ሰፔሊንግ፤ ፍቺ እና ሰዋሰው ለማስተካከል ነው፡፡
◽️F8
ኮምፒውተራችን ሲነሳ የ Windows፤ #Startup menu
ለመግባት የጠቅማል፡፡
◽️F9
በዊንዶውስ ላይ ጥቅም የለውም ነገር ግን
በማይክሮሶፍት ኦፍስ እንጠቀምበታለን
#Ctrl + F9= እንዲህ አይነት ባዶ ቦታ ለማስገባት { }
ወይም የመረጥነው ቃል በዚህ ዉስጥ { } ለማስገባት
CTRL + SHIFT + F9 ሊንክ የነበረውን ሊንኩ
ለማጥፋት
◽️F10
አክቲቭ የሆነውን ዊንዶው ሜኑ ባርን አክቲቭ ለማድረግ
ያስችላል፡፡ Shift + F10 መጨን #ራይት ክሊክ
እንደማድረግ ይቆጠራል፡፡
◽️F11
በአብዛኛዎ ብርውሰሮች ላይ F10 ስንጫን
የምንመለከተው መስኮት ሙሉ በሙሉ የኮምውተራችንን
ስክሪን ይሞላዋል # (Fullscreen) ፡፡
◽️F12
ማይክሮሶፍት ወርድ ላይ #የ Save as ማስኮትን
ይከፍትልናል፡፡ Ctrl + Shift + F12 ፐሪንት ያዛል፡፡
👍65🎉3😁2❤1
ኮምፒውተርዎን ፈጣን የሚያደርጉ 10 ዘዴዎች

1. ትላልቅ መጠን ያላቸውን ፎቶዎች ዎልፔፐር አይጠቀሙ፡፡
2. ሁሌም ኮምፒዩተሩ ከፍቶ ሳይጨርስ አፕሊኬሽን ለመክፈትም ሆነ ለመነካካት አይሞክሩ፡፡
3. አፕሊኬሽን ከዘጉ በሁዋላ ዴስክቶፑን ሪፍሬሽ ያድርጉ፤ ይህም ራም ሜሞሪን ነፃ ያደርጋል፡፡
4. የማይጠቀሙበት ሶፍትዌር ካለ ከኮምፒውተሩ ይሰርዙ (አን-ኢንስታል) ያድርጉት)፡፡
5. ዴስክቶፕ ላይ ፋይል አያስቀምጡ፤ ሾርትከትም መብዛት የለበትም፡፡
6. ኮምፒዩተሩ ሲከፈት በራሳቸው የሚከፈቱ ለምሳሌ: ስካይፕ አይነት አፕሊኬሽኖች ካሉ disable ያድርጉ
7. Recycle binን ሁሌም ባዶ ያድርጉ::
8. ሀርድ ዲስኩን ሁለት ፓርቲሽን ይፍጠሩለት፡፡
9. ብዙ ሶፍትዌሮችን ባንዴ አይክፈቱ::
10. ኮምፒውተርዎን update ያድርጉ!
👍68👏7
✅🔸የዓለማችንን መልክ የቀየሩት 20ዎቹ የምንግዜም ታላላቅ ኢኖቬሽኖች
========================
▫️በሰው ልጆች ረዥም የህይወት ጉዞ ውስጥ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚና እንዲ በቀላሉ የሚገለፅ ጉዳይ አይደለም፡፡ ሰዎች ወደዚች ምድር ከመጡ አንስቶ አካላዊውን ዓለም ለመግራት የሚያስችሉ የተለያዩ ፈጠራዎችንና የኢኖቬሽን ውጤቶች ያለማቋረጥ ሲተገብሩ ቆይተዋል፡፡ እነዚህ መሳሪያዎች አለም አሁን ያላትን መልክ ያጎናፀፏት እና የቀጣዩንም ትውልድ እጣ ፋንታ በበጎም ይሁን በክፉ የመወሰን አቅማቸው በእጅጉ የተጠበቀ ነው፡፡ አለማችን እስካሁን ያየቻቸውን የኢኖቬሽን ውጤቶች ለሰው ልጆች ከሰጡት ግልጋሎት እና በታሪክ ውስጥ ካላቸው የገዘፈ ተጽዕኖ አንፃር የሚከተሉት ኢኖቬሽኖች ከምንግዜም ታላላቆቹ መካከል ይገኙበታል፡፡ በዘመን ቅደም ተከተል እንመልከታቸው፡

▫️1. እሳት (FIRE) - ስለእሳት ስናነሳ ብዙዎች የሚከራከሩበት ጉዳይ ቢኖር እሳት ተፈለሰፈ ከሚባል ይልቅ ተገኝቷል የሚለው ሃሳብ እጅግ ተስማሚ መሆኑን ነው፡፡ ቀደምት የሰው ዘሮች እሳትን እንዴት መፍጠር እና መቆጣጠር እንደሚችሉ ከማወቃቸው በፊት የእሳትን አደጋዎች በየአጋጣሚው ተመልክተው ሊሆን ይችላል፡፡ ነገር ግን የእሳትን ምንነት ከተረዱና የሚሰጣቸውን ጥቅም ካወቁ በኋላ እሳትን እንደ አንድ ትልቅ መገልገያ መጠቀም ጀምረዋል፡፡ አንዳንድ የአርኪዎሎጂ አጥኝዎች እሳት ጥቅም ላይ የዋለው ከ2 ሚሊዮን አመት በፊት ነው ሲሉ ሌሎች ደግሞ 125 ሺ አመታት እንዳስቆጠረ ይገልፃሉ፡፡ ይህ ክርክር ምንም ተባለ ምንም በሰው ልጆች ታሪክ ታላቅ ግኝት የሆነው እሳት ሰዎች ራሳቸውን ከተለያዩ ነገሮች እንዲከላከሉ እና ማብሰል የሚባለውን ትልቅ ክህሎት እንዲረዱ ያስቻል አስገራሚ ግኝት ነው፡፡

▫️2. ተሽከርካሪ ጎማ (WHEEL) - ይህ ፈጠራ የተገኘው በ3500 ዓመተ ዓለም (B.C) በሜሶፖታሚያ የስልጣኔ ዘመን ነበር፡፡ የሜሶፖታሚያ ህዝቦች ይህንን አስገራሚ ፈጠራ የሸክላ ቁሳቁሶችን ለማበጃጀት ሲጠቀሙበት የቆየ ቢሆንም ከሶስትና አራት መቶ አመታት በኋላ ፈጠራው ለሰረገላ ማሽከርከሪያ ጥቅም ላይ ከዋለ በኋላ የመሳሪያው ተፅዕኖ እጅግ እየናኘ ሄዷል፡፡ ተሽከርካሪ ጎማ ለሰው ልጆች የመጓጓዣ እና የንድግ ስርዓት መፈጠር ትልቅ ሚና ያለው ግኝት ነው፡፡

▫️3. ኦፕቲካል ሌንሶች (OPTICAL LENSES) - የሰዎችን የእይታ አቅም ይበልጥ ለመጨመር እንደ ኦፕቲካል ሌንሶች ያሉ አስገራሚ ግኝቶች እጅግ ወሳኝ ነበሩ፡፡ ረዥም የፈጠራ ሂደት የነበራቸው እነዚህ ግኝቶች በጥንቱ የግብፅ እና የሜሶፖታሚያ የስልጣኔ ዘመን እንደበለፀጉ የሚታመን ሲሆን ከግሪክ የተገኙት የብርሃን ንድፈ ሃሳቦች ደግሞ ለግኝቱ እውን መሆን ትልቅ ሚና ነበራቸው፡፡ ኦፕቲካል ሌንሶች እንደቴሊቭዥን፣ ፎቶግራፍ እና ፊልም ያሉ ትልልቅ የሚዲያ ቴክኖሎጂዎች እንዲፈጠሩ መንገድ የጠረጉም ናቸው፡፡

▫️4. ኮምፓስ (COMPASS) - ይህ እንቅስቃሴን ለመምራት የተዘየደው የቴክኖሎጂ ግኝት የሰው ልጆችን የአሰሳ ጥበብና አቅም ወደ አዲስ ምዕራፍ በመወሰድ ተተኪ የማይገኝለት አስገራሚ ግኝት ነው፡፡ የመጀሪያዎቹ ኮምፓሶች በተፈጥሮ የመግነጢሳዊ ይዘት ባላቸው የማዕድን ቁራጮች ወይም (lodestone) አማካኝነት የተሰሩ ሲሆን፤ ከክርስቶስ ልደት በፊት በ 300 እና 200 አመተ አለም አካባቢ በቻይና እንደተሰሩም ይነገራል፡፡

▫️5. ወረቀት (PAPER) - በ100 ዓመተ አለም አካባቢ በቻይና የተፈለሰፈው ይህ ግኘት የሰው ልጆችን የፅህፈት እና ሃሳብን የማጋራት ልምድ በእጅጉ የቀየረ እንደሆነ ይነገርለታል፡፡ ከዚህ ጊዜ በፊት በግብፅ እና በሜክሲኮ የስልጣኔ ዘመናት የተፈለሰፉት እንደ ፓፒረስና አሜት ያሉ የመፃፊያ ቁሶች ለወረቅት መፈጠር አስተዋፅዖ ቢኖራቸውም በቻይና የነበረው ግኝት ግን አሁን ላለው የወረቀት ቴክሎጂ ትልቅ መሰረት የጣለ ነው፡፡
▫️6. ባሩድ (GUNPOWDER) - ከተለያዩ የኬሚካል ንጥረ ነገሮች ተቀይጦ የሚሰራው ይህ ተቀጣጣይ ፈንጂ በ9ኛው ክፍለ ዘመን በቻይና እንደተፈለሰፈ የሚነገር ሲሆን ለዘመናዊው የጦር ቴክኖሎጂ መስፋፋትም ፈር ቀዳጅ የሚባል ነው፡፡ ይህ ግኘት በሰው ልጆች የውጊያ ታሪክ ውስጥ ትልቅ ተፅዕኖ ያሳደረ መሆኑም ይነገርለታል፡፡

▫️7. ማተሚያ (PRINTING PRESS) - እንደአውሮፓውያኑ በ1439 በጀርመናዊው ዮሃንስ ጉተንበርግ የተፈጠረው ይህ መሳሪያ ለሰው ልጆች የአዲስ ህይወት መጀመሪያ ዘመን ተደርጎ በብዙዎች ይወሰዳል፡፡ ይህ አስገራሚ ቴክኖሎጂ በሰዎች እጅ እየተፃፈ የሚሰራጨውን አድካሚ የፅህፈት ስርዓት በሜካናይዝድ ማሽን በመተካት የእውቀት አድማስ በሰዎች ዘንድ በቀላሉ እንዲሰፋፋ እና የሃይማኖት አስተምህሮዎች በአለም ላይ በፍጥነት እንዲናኙ ያስቻለ አስገራሚ ግኘት ነው፡፡

▫️8. ኤሌክትሪክ (ELECTRICITY) - የኤሌክትሪክ ፈጠራ ብዙ ብሩህ አዕምሮዎች ለሺህና ከዚያ በላይ አመታት አስተዋፅዖ ያደረጉበት እፁብ ድንቅ የሆነ የቴክኖሎጂ ግኝት ነው፡፡ በ18ኛው ክፍለ ዘመን የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ቤንጃሚን ፍራንክሊን ስለኤሌክትሪክ የነበረውን የአለም መረዳት አንድ እርምጃ ያራመደ የመሪነት አበርክቶት እንደነበረው የሚገለፅ ሲሆን በምርምር ዘርፍ ደረጃ ለመስኩ የሰጠው ሁለንተናዊ ትኩረት የቴክኖሎጂውን እድገት በእጅጉ አፋጥኖታል፡፡ ከዚህ ሂደት በማስከተል በ1879 የቶማስ ኤዲሰን የብርሃን አምፖል መፈጠር የኤሌክትሪክ ቴክኖሎጂ ይበልጥ ወደሰዎች እንዲቀርብ ያስቻለ ክስተት ነው፡፡ ይህ የምንግዜም ታላቅ ፈጠራ የሰው ልጆችን የህይወት መንገድ እስከወዲያኘው የቀየረ ግሩም ቴክኖሎጂ ነው፡፡

▫️9. የእንፋሎት ሞተር (STEAM ENGINE) - በስኮትላንዳዊው የፈጠራ ባለሙያ ጀምስ ዋት ከ1763 እስከ 1775 ተሰራ የሚባለው የእንፋሎት ሞተር ሌላኛው ለሰው ልጆች ትልቅ መሰረት የጣለ አስደናቂ የፈጠራ ውጤት ነው፡፡ ይህ የቴክኖሎጂ ግኝት በጊዜው ለነበሩት ባቡሮች፣ መርከቦች እና በጠቅላለው ለኢንዱስትሪው አብዮት ዋና የሃይል ምንጭ በመሆን ተከትሎ ለመጣው የሰው ልጅ አብርሆት ታላቅ ውለታ ያደረገ አስገራሚ ፈጠራ ነው፡፡

▫️10. የነዳጅ ሞተር (INTERNAL COMBUSTION ENGINE) - በ19ኛው ክፍለዘመን የተዋወቀው ይህ የቴክኖሎጂ ፈጠራ በመጀመሪያ በቤልጄሚያዊው ኢንጅነር ኢትየን ሌኖየር (በ1859) የተፈጠረ ሲሆን ከጥቂት አመታት በኋላ በጀርመናዊው ኒኮላስ ኦቶ ይበልጥ ሊሻሻል ችሏል፡፡ ይህ አስገራሚ ፈጠራ የኬሚካል ኢነርጂን ወደ ሜካኒካል ኢነርጂ በመቀየር ቀድሞ የእንፋሎት ሞተር ሲሰጥ የነበረውን ግልጋሎት በተሻለ ሁኔታ በመተካት ለዘመናዊ መኪናዎችና አውሮፕላኖች ማገልገል የቻለ አስገራሚ ፈጠራ ነው፡፡

▫️11. ስልክ (TELEPHONE) - የስኮትላንድ ተወላጁ አሌግዛንደር ግርሃም ቤል በሰው ልጆች የመገናኛ ጥበብ ውስጥ ትልቅ አብዮት የፈጠረውን የስልክ ቴክኖሎጂ በራሱ ስም ያስመዘገበ ታላቅ የፈጠራ ባለሙያ ቢሆንም ከሱ ቀደምና እሱ በነበረበት ዘመንም ብዙ የፈጠራ ባለሙያዎች ለቴክኖለጂው ማበብ የራሳቸውን አሻራ ጥለዋል፡፡ አሌግዛንደር ግርሃም ቤል አንደአውሮፓውያኑ በ1876 በኤሌክተሪክ ስልክ የመጀመሪያውን ፓትንት ካገኘ በኋላ የሰው ልጆች እርስ በእርስ የመገናኘት ልምድ እስወዲያኛው ተቀይሯል፡፡
👍38👏1😁1