Muhammed Computer Technology (MCT)
38.1K subscribers
527 photos
7 videos
254 files
910 links
🔴አድራሻ:-
✅ ስ.ቁ: 0929273364
✅ ዌብሳይት www.mctplc.com
✅ቴሌግራም አካውንት: https://t.me/mctplc
✅ email: mct16plc@gmail.com
✅ ቲክቶክ አካውንት tiktok.com/@mctplc
Download Telegram
የተማሪዎችን ውጤት ለምሳሌ A,B,C,D and F በማለት ግሬድ Computer ላይ በ Microsoft Excel መስራት
የተማሪዎችን ውጤት በ Grading system መስራት እንዴት እንችላለን? Student Mark (Grading System) መታየት ያለበት ቪዲዮ
👇👇👇ይመልከቱት👇👇👇
https://youtu.be/j7FOjQ9YaoE
https://youtu.be/j7FOjQ9YaoE
https://youtu.be/j7FOjQ9YaoE
https://youtu.be/j7FOjQ9YaoE
https://youtu.be/j7FOjQ9YaoE
👍40❤10👎4🔥1
ለተመራቂ ተማሪዎች
ሪሰርች ስትሰሩ ከዚህ በታች የጠቀስኳቸው ከከበዷችሁ ነገ በምርጥ አቀራረብ ቪዲዮ ይዥላችሁ ቀርባለሁ!
✅ Automatic References
✅ Automatic List of tables
✅ Automatic List of figures
✅ Citation እንዴት እንሰራለን?
በምርጥ አቀራረብ በYouTube ተዘጋጅቶ ለእይታ ዝግጁ ነው ከታች ያለውን ሊንክ በመጫን መመልከትና መማር ትችላላችሁ!
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
https://youtu.be/VujbubSHkZs

ከዚህ በታች የዘረዘርኳቸው
✔️ Automatic Tables of Content.
✔️ Page Break እንዴት እንሰራለን? ለሚለው ከታች ያለውን ሊንክ በመጫን ይመልከቱ
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
https://youtu.be/aB-z5uKq75U
~><~~~~
የYouTube ቻናሉን Subscribe በማድረግ ምርጥ ምርጥ ትምህርቶችን ይማሩ!
የ YouTube ቻናል ሊንክ
👇👇👇
https://www.youtube.com/channel/UCZBIP6PqUdmmagdTjbyp_AQ
👍33🥰5😁2
💻 ኮምፒውተር ላይ በአማርኛ እንዴት እንደሚፃፍ ያውቃሉ?ሲጽፉስ ምን ያህል ይፈጥናሉ?
=========================

■ ጠቃሚ መረጃ ነው!! ላልደረሰው ያዳርሱ አሁኑኑ ሼር ያድርጉት፡፡

❖መጀመሪያ ከላይ የለቀቅንላችሁን Software ያወረዱ እና install ያድርጉት ከዛም አማርኛ መፃፍ ስትፈልጉ power ge'ez status phonetic Unicode Mode (ፎ) ላይ ያድርጉት በ English መፃፍ ስትፈልጉ ደግሞ power ge'ez status English Mode (ኢ) ላይ አድርጉት ከዛም የሚከተሉትን ኣጭር መግላጫ በትክክል ይመልከቱ።
⁉️ ሶፍትዌሩን ለማግኘት ከፈለጋችሁ ከቴግራም ቻናሌ ማግኘት ትችላላችሁ
👇👇👇👇👇👇👇👇👇 https://t.me/MuhammedComputerTechnology
◕ሀ➭H_ሁ➭Hu_ሂ➭Hi_ሃ➭Ha_ሄ➭Hy_ህ➭He_ሆ➭Ho

◕ለ➭L_ሉ➭Lu_ሊ➭Li_ላ➭La_ሌ➭Ly_ል➭Le_ሎ➭Lo

❖ሐ➭Shift+h_ሑ➭Shift+hu_ሒ➭Shift+hi_ሓ➭Shift+ha_ሔ➭Shift+hy_ሕ➭Shift+he_ሖ➭Shift+ho

◕መ➭M_ሙ➭Mu_ሚ➭Mi_ማ➭Ma_ሜ➭My_ም➭Me_ሞ➭Mo

❖ሠ➭Shift+s_ሡ➭Shift+su_ሢ➭Shift+si_ሣ➭Shift+sa_ሤ➭Shift+sy_ሥ➭Shift+se_ሦ➭Shift+so

◕ረ➭R_ሩ➭Ru_ሪ➭Ri_ራ➭Ra_ሬ➭Ry_ር➭Re_ሮ➭Ro

◕ሰ➭S_ሱ➭Su_ሲ➭Si_ሳ➭Sa_ሴ➭Sy_ስ➭Se_ሶ➭So

❖ሸ➭Shift+s_ሹ➭Shift+su_ሺ➭Shift+si_ሻ➭Shift+sa_ሼ➭Shift+sy_ሽ➭Shift+se ሾ➭Shift+so

◕ቀ፡➭Q ቁ፡➭Qu ቂ፡➭Qi ቃ፡➭Qa ቄ፡➭Qy ቅ፡➭Qe ቆ፡➭Qo

◕በ፡➭B ቡ፡➭Bu ቢ፡➭Bi ባ፡➭Ba ቤ፡➭By ብ፡➭Be ቦ፡➭Bo

◕ተ፡➭T ቱ፡➭Tu ቲ፡➭Ti ታ፡➭Ta ቴ፡➭Ty ት፡➭Te ቶ፡➭To

◕ ቸ፡➭C ቹ፡➭Cu ቺ፡➭Ci ቻ፡➭Ca ቼ፡➭Cy ች፡➭Ce ቾ፡➭Co

◕ነ፡➭N ኑ፡➭Nu ኒ፡➭Ni ና፡➭Na ኔ፡➭Ny ን፡➭Ne ኖ፡➭No

❏ኘ፡➭Shift +n ኙ፡➭Shift +nu ኚ➭Shift+ni ኛ፡➭Shift +na ኜ፡➭Shift +ny ኝ፡➭Shift + ne ኞ፡➭Shift +no

◕ከ፡➭Ka ኩ፡➭Ku ኪ፡➭Ki ካ፡➭Ka ኬ፡➭Ky ክ፡➭Ke ኮ፡➭Ko

❖ ኸ ☛capslock + Shift + h
ኹ ☛capslock + Shift + hu
ኺ ☛capslock + Shift + hi
ኻ ☛Capslock + Shift + ha
ኼ ☛Capslock + Shift + hy
ኽ ☛Capslock + Shift + he
ኾ ☛Capslock + Shift + ho

❏ኀ፡➭ Capslock + H ኁ፡➭ Capslock + HU ኂ፡➭Capslock + HI ኃ፡➭Capslock + HA ኄ፡➭Capslock + HY ኅ፡➭Capslock + HE ኆ፡➭Capslock + HO

❏አ፡➭Capslock X ኡ፡➭Xu ኢ፡➭Xi ኣ፡➭Xa ኤ፡➭Xy እ፡➭Xe ኦ፡➭XoDe

❖ዐ፡➭Shift +x ዑ፡➭Shift +xu ዒ➭Shift +xi ዓ፡➭Shift +xa ዔ➭Shift +xy ዕ፡➭Shift +xe ዖ➭Shift +xo

✪ወ፡➭W ዉ፡➭Wu ዊ፡➭Wi ዋ፡➭Wa ዌ፡➭Wy ው፡➭We ዎ፡➭wo

✪ዘ፡➭Z ዙ፡➭Zu ዚ፡➭Zi ዛ፡➭Za ዜ፡➭Zy ዝ፡➭Ze ዞ፡➭Zo

❏ዠ፡➭Shift + Z ዡ፡➭Shift + Zu ዢ፡➭Shift + Zi ዣ፡➭Shift +Zaዤ፡➭Shift + Zy ዥ፡➭Shift +Ze ዦ፡➭Shift + Zo

✪ፈ፡➭F ፉ➭Fu ፊ፡➭Fi ፋ፡➭Fa ፌ፡➭Fy ፍ፡➭Fe ፎ፡➭Fo

✪ ፐ፡➭P ፑ፡➭Pu ፒ፡➭Pi ፓ፡➭Pa ፔ፡➭Py ፕ፡➭Pe ፖ፡➭Po

✪ገ፡➭G ጉ፡➭Gu ጊ፡➭Gi ጋ፡➭Ga ጌ፡➭Gy ግ፡➭Ge ጎ፡➭Go

✪ደ፡➭D ዱ፡➭Du ዲ፡➭Di ዳ፡➭Da ዴ፡➭Dy ድ፡➭ዶ፡Do

❏ጠ፡➭Shift + t ጡ፡➭Shift + tu ጢ፡➭Shift + ti ጣ፡➭Shift+ta ጤ፡➭Shift + ty ጥ፡➭Shift + te ጦ፡➭Shift + to

❏ጨ፡➭Shift +c ጩ፡➭Shift +cu ጪ፡➭Shift +ci ጫ፡➭Shift+caጬ፡➭Shift +cy ጭ፡➭Shift +ce ጮ: ➭Shift +co

❏ጸ፡➭Capslock + t ጹ፡➭Capslock + tu ጺ፡➭Capslock + ti ጻ፡➭Capslock + ta ጼ፡➭Capslock + ty ጽ፡➭Capslock + t ጾ፡➭Capslock + to

❖ ፀ➭☞Capslock+Shift+t
ፁ➭☞Capslock+Shift+tu
ፂ➭☞Capslock + Shift + ti
ፃ➭☞Capslock + Shift + t
ፄ➭☞Capslock + Shift + ty
ፅ➭☞Capslock + Shift + te
ፆ➭☞Capslock + Shift + to

✪ጀ፡➭J ጁ፡➭Gu ጂ፡➭Ji ጃ፡➭Ga ጄ፡➭Gy ጅ፡➭Ge ጆ፡➭Jo

✪ቨ፡➭V ቩ፡➭Vu ቪ፡➭Vi ቫ፡➭Va ቬ፡➭Vy ቭ፡➭Ve ቮ፡➭Vo
▁▁▁▁▁▁▁▁▁▁

ቋ➭Capslock+qwa ቧ➭Capslock+bwa
ቷ➭Capslock+twa
ኟ➭Capslock +Shift+nwa
ቿ➭Capslock+cwa ሟ➭Capslock+mwa
ቷ➭Capslock+twa ጓ➭Capslock gwa
ፏ➭Capslock+fwa ሯ➭Capslock +rwa ዷ➭Capslock+dwa ቯ➭Capslock+vwa ኋ➭Capslock+hwa ዟ➭Capslock+zwa ዧ➭Capslock+Shif+zwa
ኗ➭Capslock+nwa ሏ➭Capslock+lwa
ኳ➭Capslock+kwa ሷ➭Capslock+swa
ጇ➭Capslock+jwa ጧ➭Capslock+twa

♨️የተቸገሩ ሰዎችን በጣም ይጠቅማቸዋል አሁኑኑ ሼር ያድርጉ፡፡
━━━━━━ ⊙ ━━━━━━
👍155❤35👏8🥰5🔥4👎2🎉2🤔1
የፌስቡክ ገጼ 120,000 ቤተሰብ ደርሰናል!
አመሰግናለሁ!
ፔጁን like ያድርጉ!
👇👇👇open👇👇👇
https://www.facebook.com/mameamin.6te.net/
👍69👏16❤8🥰8
🤦🤦🤦 አዳ ቲዩብ 🤦🤦🤦🤦
💻📱 ከዚህ በታች ስለ Autocad 2022 አዲሱ ቨርዥን ቲቶሮችን ይዞላችሁ ቀርቧል

✅ New features of autocad 2022
https://youtu.be/15-Sx-k1VAA

✅ Autocad 2022 classic Workspace Settings
https://youtu.be/2_pdccXhDQc

✅How to draw 2Dand 3D drawing by autocad 2022
https://youtu.be/0wu7nxm_uJY

#Subscribe the channel
ቻናሌን ሰብስክራይብ በማድርግ ድጋፋችሁን አይለየኝ

https://www.youtube.com/channel/UClXEt7DFjKVSb_m03DvXSPg?sub_confirmation=1
👍27
♎️ Plagiarism Checker X 8.0.3.0

#PlagiarismChecker ይፈልጋሉ?
👇👇👇ይግቡ👇👇👇
https://t.me/researchRC/179
❤8👍7
የሥራ ቃለ መጠይቅ / Interview/

ክፍል 1

የክረምት መዳረሻዎች እና ወራቶች ላይ ዩኒቨርሲቲዎች እና ኮሌጆች የተማረ የሰው ኃይል ለሕዝብ የሚያስረክቡበት ነው። በመሆኑም አብዛኞቹ ተቋማት ከዚህ ወር ጀምሮ የቅጥር ቃለ መጠይቅ ያካሂዳሉ። ዘመኑ የውድድር መንፈስ የተጠናወተው ነውና ራስን ማዘጋጀት የብልህ ሰው መለያ ነው።

በሥራ ቃለ መጠይቅ /Interview/ ላይ በብዛት የሚጠይቁ ጥያቄዎች እንደሚከተለው ቀርበዋል። እነሱም:-

1ኛ. ራስዎን ያስተዋውቁን?

(Please introduce yourself to know who you are?)

ይህ ጥያቄ ቀላል ቢመስልም፤ ብዙዎች ገና ከጅምሩ ስህተት የሚሰሩበት ነው። ብዙዎች የሕይወት ታሪካቸውን ያወራሉ። የጥያቄው አይን ግን በሥራ (በትምህርት) ሕይወት ላይ ስለቆያችሁበት ማንነት፣ የት/ት ደረጃ፣ የስራ ልምድ ካላችሁ ስለ ልምዳችሁ፣ ስላስመዘገባችሁት እና ስለ ሰራችሁት ጥሩ ሥራዎች፣ ጀማሪ ተቀጣሪ ከሆናችሁ ደግሞ በዩኒቨርሲቲ ቆይታችሁ ስለ ነበራችሁ መልካም እንቅስቃሴዎች ወይም ስለ ሰራችሁት የመመረቂያ ጥናት (Research) ወይም ፕሮጀክት በመዘርዘር እራሳችሁን ማስተዋወቅ ነው። በንግግራችሁ ወቅት ለጠያቂው የመጀመሪያ ምርጫው እንድትሆኑ ጠቃሚ ነገሮች ላይ ትኩረት አድርጉ። የዘር ሀረግ እየቆጠሩ፣ በትውልድ ቦታ እየከለላችሁ ጥያቄውን እንዳትወድቁ ተጠንቀቁ። ለዚያውም በዚህች ጎጠኛ ዓለም ላይ ተሳታፊ ሆኖ ጎጥ መቁጠር ተገቢ አይደለም።

2ኛ. ስለዚህ የሥራ ማስታወቂያ እንዴት መረጃ አገኙ?
 
(How did you got an information about this vacancy?)

ይኸም በተደጋጋሚ ይጠየቃል። የዚህ ጥያቄ ዓላማው ድርጅቱን ምን ያክል እንደምትወዱትና እንደምትፈልጉት ለማወቅም ጭምር ነው። በመሆኑም መልሳችሁ "የድርጅቱን ድረገጽ እከታተል ስለነበር ከዛ ላይ አገኘው"፣ "ከጋዜጣ ላይ"፣ "ከማስታወቂያ ቦርድ ላይ" በማለት በትክክል መልሱ። ለመልሶቻችሁ ውበት ብላችሁ የሌለ ነገር ከጠቀሳችሁ ውሸታም ያስብላችኋል።

3ኛ. ሾለ መስሪያ ቤታችን ምን ያውቃሉ? 

(Have any knowhow about this organization?)

ለቃለ መጠይቅ ፈተና ከመቅረባችሁ በፊት ስለ መስሪያ ቤቱ የምስረታ ዘመን፣ ተልዕኮውን (Mission)፣ አላማውን እና ስፋቱን (Scope and Objective)፣ ራዕዩን (Vision)፣ የምርት ውጤት (Final Output) አስቀድመው ለማወቅ እና እርሰዎ ለአላማው መሳካት የሚያደርጉትነ አስተዋጽኦ ለማካተት ይሞክሩ። ይህንን መረጃ ከድረገጽ እና ከተለጠፉ ታፔላዎች ማግኘት ይቻላል። ለዚህ ጥያቄ ተገቢውን ምላሽ መስጠት ለሥራው ትኩረት መስጠትን ያመለክታል።

4ኛ. ለምን እዚህ መቀጠር ፈለጉ? 

(Why did you want to be employee in this company?)

በምንም ምክንያት "ሼል ዕድል ስለፈጠረልኝ፣ ደሞዝተኛ ለመሆን፣ ሼል ላለማጣት" á‹¨áˆšáˆ‰ ነገሮችን እንዳትመልሱ። በምትኩ አግባብነት ያላቸውን መልሶች ለምሳሌ ያህል ቀርበዋል። እነሱም:-

~ "በመስሪያ ቤቱ ባሉት ዘርፍ/ዘርፎች ላይ ብሳተፍ ትልቅ አስተዋፅኦ እንደማበረክት ስላመንኩኝ"

~ "መስሪያ ቤቱ የላቀ እንቅስቃሴዎችን እያስመዘገበ በመሆኑ እኔም የበኩሌን ድርሻ በመወጣት ሀገሬን እና መስሪያ ቤቱን ማሳደግ ስለምፈልግ፡፡"

~ መስሪያ ቤት የሚሰጠውን አገልግሎት በመጥቀስ "እንደዚህ ያለ አገልግሎት የሚሰጡ ቦታዎች ላይ መሆን ታላቅ እርካታን ስለሚሰጠኝ።" ብለው መልሱ።

5ኛ. ለመስሪያ ቤቱ ምን አይነት አስተዋጽኦ አደርጋለሁ ብለው ያምናሉ?

(If you will be employed, what role do you believe that you may pay for company?)

በመስሪያ ቤቱ የምሰራ ከሆንኩ፤ በቡድን እንቅስቃሴ ውስጥ የቡድን አንድነትን ማጠናከር (Team Work)፣ የክህሎት ማጎልበቻ ሥልጠናዎችን ማመቻቸት (Skill Building Trainings)፣ የሥራ ልውውጥ ማድረግ (Experience Sharing)፣ አዳዲስ ጥናቶችን ከመደበኛ ሥራዬ ጎን ለጎን በመስራት (Researches and Projects)፣ ደንበኞችን በአክብሮት እና በተገቢው ሁኔታ ማስተናገድ (Respect and Legality for customers) እና መሰል ነገሮችን በማድረግ ለመስሪያ ቤቱ እድገት ጉልህ አስተዋጽኦ እንደምታበረክቱ ተናገሩ። 

6ኛ. ጠንካራ ጎኖዎ ምን ምንድናቸው?

(What are your strength?)

የምትፈልጉትን ምኞት ሳይሆን እውነተኛ ጥንካሬዎቻችሁን መስክሩ። ከምትወዳደሩበት የሥራ መደብ ጋር ተያያዥነት ያላቸውን ሙያዊ ጥንካሬዎችዎን ብታስቀድሙ የተሻለ ነው ፡፡

7ኛ. የዚህን ድርጅት ራዕይ እና ተልእኮ ያውቃሉ?

(What are vision and missions of this organization?)

ይህን ጥያቄ ለመመለስ አስቀድሞ መዘጋጀት ይጠበቅባችኋል። እየተወዳደራችሁበት ያለውን የድርጅቱን ራዕይ፣ ዓላማ እና ተልእኮ አስቀድማችሁ በሚገባ ማወቅ አለባችሁ። ይህንን መረጃ በድርጅቱ ድረገጽ፣ በተሰቀሉ ባነሮች ላይ፣ በታተሙ በራሪ ወረቀቶች ላይ፣ በድርጅቱ የውስጥ ግድግዳዎች ላይ ስለሚገኙ ፈጽሞ ሳታውቁ እንዳትገቡ ይመከራል። ምንም መረጃ ባታገኙ እንኳን ገና ራዕይ እና ተልዕኮ ያልረቀቀላቸው ሊሆኑ ስለሚችሉ በራስዎ ከመመለስ ይልቅ የቅርብ ሰዎችን አፈላልጎ መጠየቅ ተገቢ ነው።

8ኛ. ስለ ድርጅቱ ምን ምን ያውቃሉ?

(What knowhows do you have about this organization?)

እያንዳንዱ ድርጊት የራሱ የሆነ ታሪክ አለው። ይህም ጥያቄ ድርጅቱን ለማወቅ እና የድርጅቱ ሰራተኛ ለመሆን ካላችሁ ጉጉት አንጻር ምን ያክል እንደተጓዛችሁ የሚያመላክት ስለሆነ ሰፋ ያለ መረጃዎችን በማሰባሰብ ምላሽ መስጠት ተገቢ ነው። ለዚህ መልስ ለመስጠት ቢያንስ መቼ እንደተመሰረተ፣ ማን እንደመሰረተው (ባለቤቱ ማን እንደሆነ)፣ የት እና በምን ያክል መነሻ ገንዘብ (Capital) እንደተመሰረተ፣ ስንት ቅርንጫፎች እንዳሉት፣ ዋና መስሪያ ቤቱ የት እንደሆነ፣ ምን ምን አይነት አገልግሎቶች እንደሚሰጥ፣ ምን ያክል የገንዘብ ሃብት እንዳለው፣ ምን ያክል ሰራተኞች እንዳሉት፣ ምን አይነት የእድገት ፍጥነት እንዳለው እና የመሳሰሉትን ማወቅ ይኖርባችኋል። እነዚህን ካወቃችሁ የድርጅቱን ማንነት መግለጽ ትችላላችሁ ማለት ነው።

9ኛ. በአንድ መስሪያ ቤት ውስጥ ሊኖሩ የሚገባቸው መርሆች እና እሴቶች ምን ምን ናቸው?

(What are values and principles expected from one organization?)

በአብዛኛው እነዚህ ነገሮች፤ ለሁሉም ድርጅቶች ተቀራራቢ የሆነ ይዘት ቢኖራቸውም እንደ ድርጅቱ ባህርይ እና ይዘት ሊለያዩ ሾለ ሚችሉ በራሱ በድርጅቱ ውስጥ ያሉትን እሴቶች እና መርሆች አፈላልጎ ማወቅ ተገቢ ነው። 
ከእነዚህም ውስጥ ሃቀኝነት (Integrity)፣ የደንበኞች እርካታ (Customer Satisfaction)፣ የሰራተኞች እርካታ (Employees Satisfaction)፣ ታማኝነት (Honesty)፣ የቡድን ወይም የኅብረት ሼል (Team Work)፣ የህዝብን አደራ መወጣት (Public Trust)፣ ትህትና (Humility)፣ ፈገግተኛ መሆን (Simplicity)፣ አንድነት (Unity)፣ ደስተኛነት (Happiness)፣ ነጻነት (Freedom)፣ ግልጸኝነት (Articulate)፣ ፍቅር á‹‹áŠ“ ዋናዎቹ ናቸው።
👍86🥰2👏2❤1
የሥራ ቃለ መጠይቅ / Interview/
ከላይ የቀጠለ 👆👆👆ይመልከቱ👆👆👆
# 10ኛ. ድክመቶችዎ ምን ምን ናቸው? [what are your weaknesses?]
...
ለሁሉም ሰው ድክመቶች ቢኖሩበትም ቅሉ በሥራ ቃለ መጠይቅ ወቅት እኒህ እኒህ ድክመቶች አሉብኝ ብሎ መናገር አይመከርም። ይልቁን "የሚታይ ድክመት አለብኝ ብዬ አላምንም ለዚህም ማስረጃ የሚሆነኝ እኔ ባለብኝ ድክመት ምክንያት ነገሮች ተበላሽተውበኝ አለማወቃቸው አንዱ ማሳያዬ ነው" ብሎ መመለስ ተገቢ ይሆናል፡፡
...
# 11ኛ. በሙያዎ ያስመዘገቡት ስኬት ምንድነው? [what role do you have payed before with your profession?]
...
አሁን ሊቀጠሩበት ባለው የሙያ ዘርፍ ቀደም ብለው ያስመዘገቡትን ውጤት ይናገሩ። የሠሩትን ነገር መናገር።
+++++++++++++++×
++. . ለተመራቂ ተማሪዎች
++. # የቃለመጠይቅ መረጃ [Interview]
------ ------------------
የተማሩትን ት/ት በተመለከተ
...
# 1ኛ。የተማሩበትን የትምህርት ክፍል ባጭሩ ያብራሩል![ለምሳሌ የተማሩት CoTM ትምህርት ክፍል ከሆነ፦ What do you mean by construction, technology and management?]
...
በዚህ ጥያቄ ላይ ለማወቅ የተፈለገው ነገር የት/ት ክፍሉን ስም አይደለም። ይልቁንም ስለትምህርት ክፍሉ ጠቃሚነት፣ ከጊዜ ጥራት እና ኢኮኖሚ አንጻር የሚፈይዳቸውን ሃገራዊ አስተዋጽኦዎች [cost, time and quality]፣ ከሃብት አጠቃቀም አንጻር የሚያበረክታቸውን ዋጋዎች [manpower, material, equipment, natural resourses management]፣ የማህበረሰብን ችግር ከመፍታት አንጻር ያለውን ቦታ [solving role to community problem]፣ ከተማሯቸው የትምህርት አይነቶች ጋር በማዛመድ አጠር እና ግልጽ በሆነ መልኩ ለማስረዳት ይሞክሩ።
....
# 2ኛ。እርስዎ በተማሩት ትምህርት ያገኙት የብቃት ክህሎቶች ምን ምን ናቸው? [what are your professional skills?]ያለዎትን
....
ለዚህ ጥያቄ ደግሞ ችሎታ በክፍል በክፍል ለማስረዳት መቻል አለብዎት። ለምሳሌ፦
. # የኮምፒውተር_ሥራ_ብቃት [computer skill]፦ የሚችሏቸውንና የተማሯቸውን ሶፍትዌሮችን {autocad, microsoft project planner, peachtree, archicad, ...} እና ማይችሮሶፍቶች {microsoft word, micrososf excel, microsoft powerpoint...} etc
. # ሙያዊ_የሥነዘዴ_ብቃት [Technical skill]፦ የዋጋ ትንበያ {cost estimation}፣ የገበያ ዳሰሳ {market analaysis}፣ የጊዜ ሰሌዳ እና የዕቅድ ሥራ {scheduling and planning}፣ .... etc
. # የሥራ_አመራር_ብቃት [Managemental skills]፦ የቡድን ሥራ {team and group working}፣ሰራተኞችን ማበረታት {motivation}፣ የመሪነት ክህሎት {Leadership}፣ የቁጥጥርና ክትትል ክህሎት {monitoring and controling skill}.... etc
. # ሥነ_ጥበባዊ_ወይም_ሳይንሳዊ_ክህሎት [Scientific skills]፦ ጥናታዊ ምርምሮችን ማከናወን {research}፣ የቴክኖሎጂ ግኝቶች ላይ መሳተፍ {investigation for technological issues}፣ አዳዲስ የቴክኖሎጂ ውጤቶችን መጠቀም {trying to use new technology outputs}.... etc
. # ሌሎችም
....
# 3ኛ。ማህበረሰቡን በምን በምን ተጨማሪ ሥራዎች አገለግላለሁ ብለው አስበዋል? [what do you planned to serve the community out of your employeed job?]
....
ይህ ጥያቄ ከሚቀጠሩበት የሙያ ቦታ ወጣ ያለ ሃሳብ ያለዎት ትጉህ ሠራተኛ መሆንዎን ለማወቅ ነው። ለምሳሌ የሚወዳደሩት ለመምህርነት፣ ለቢሮ ሠራተኛነት፣ ለባንክ መኮንንነት ከሆነ፣ ጥያቄው ከዚህ ወጣ ያለ ሃሳብ ስለመኖሩ ለማወቅ ያተኮረ ነው። ስለሆነም ከእነዚህ ሥራዎች ዉጪ የተለያዩ ጥናታዊ ዳሰሳዎችን በማቅረብ {by implementing research for company and local problems፣ ማህበራዊ አገልግሎቶችን በመስጠት {community servoce provision}፣ ሙያዊ ሥልጠናዎችን በማዘጋጀት {giving profesional trainings for community}...etc ብለው ቢመልሱ የተሻለ ነው።
....
ሌሎች መረጃዎችን ለማግኘት # Like_Page
መልካም ዕድል!!!
የፌስቡክ ገጼ 120,000 ቤተሰብ ደርሰናል!
አመሰግናለሁ!
ፔጁን like ያድርጉ!
👇👇👇open👇👇👇
https://www.facebook.com/mameamin.6te.net/
👍70❤17🥰2🤮2
በቻናሉ በሚለቀቁ መረጃዎች ምን ያክል እረክተዋል?
Anonymous Poll
93%
ጥሩ ነው በርታ!👍
6%
መካከለኛ ነው
1%
አልተመቸኝም 👎
👍232❤42👏28🔥5👎1
ፍላሽ ዲስክ ከኮምፒውተራችን ጋር ተጠቅመን ከጨረስን በኋላ eject ማድረጋችን ምንድን ነው ጥቅሙ? አስበውት ያውቃሉ እስኪ ሀሳባችሁን አጋሩኝ?
✅ ፍላሽ፣ External Hard Disk፣ እንዲሁም CD/DVD ከኮምፒውተራችን ሰክተን ተጠቅመን ስንጨርስ በቀጥታ የሚታየን ነገር ቢኖር በቶሎ ፍላሹን፣ External Hard Disk መልቀል ወይም CD/DVD ከሆነ ደግሞ ሲዲው እንዲወጣ መጫን ነው።
✅ ነገር ግን አብዛኛዎቻችን ፍላሼ፣ External ሀርዲ ዲስኬ፣ የምጠቀምበት ሲዲ አልሰራልኝ አለ? ኮራፕት አደረገብኝ፣ ፍላሽ ዲስኬ Write Protected ሆነብኝ፣ ፍላሽ ዲስኬ ከነጭራሹ ከኮምፒውተሬ ጋ ብሰካው እይሰራም፣ ፍላሽ ዲስኬን ከኮምፒውተሩ ጋ ስሰካው ድምጽ ያሰማኛ ግን My computer ጋ ስሄድ የለም የሚል በብዛት የሚነሳ ጥያቄ ነው። ለዚህ ሁሉ ችግር ተጠያቂዎቹ እኛው ነን።
✅ቅድመ ጥንቃቄ ማድረግ አለባችሁ።
በመጀመሪያ ደረጃ ፍላሽ ዲስክ፣ External ሀርድ ዲስክ፣ ሲዲ/ዲቪዲ ወደ ኮምፒውተር ስብሰካና ስናስገባ ኮምፕዩተሩ Read/ Write process ያደርጋል። ይህ ማለት ስራ እየሰራ ነው ማለት ነው።
✅ ፍላሽ ዲስክ፣ External ሀርድ ዲስክ፣ ሲዲ/ዲቪዲ ወደ ኮምፒውተር ሰክተንና አስገብተን ፋይል ለምሳሌ ከኮምፒውተር ወደ ፍላሽ፣ ከፍላሽ ወደ ኮምፒውተር, ከExternal Hard Disk ወደ ኮምፒውተር .......... መረጃ ስናገላብጥ አሁን ሁሉም ስራ ላይ ናቸው ማለት ነው። ስለሆነም መረጃ እያላላክን ሳለ ከተሰካበት ብንነቅለው። ከገባበት ብባወጣው። ስራውን ሳይጨርስ አቋረጥነው ማለት ነው። በዚህ አጋጣሚ የመበላሸት አጋጣሚው በጣም ሰፊ ነው በተለይ ደግሞ ለExternal Hard Diskና CD/DVD እንዲሁም ፍላሽ ዲስኮች።
✅ ፍላሽ ዲስክ፣ External ሀርድ ዲስክ፣ ሲዲ/ዲቪዲ ከኮምፒውተር ጋ ተሰክተው እያለ ዝም ብለን የምነቅለው ከሆነ ይህም የመበላሽት አጋጣሚው በጣም ሰፊ ነው።
✅ ስለሆነም ማንኛውንም ከኮምፒውተር ጋ የሚሰኩ Storage Device በጥንቃቄ በሚከተለው ፕሮሰስ ፍላሽ ዲስክ፣ External ሀርድ ዲስክ፣ ሲዲ/ዲቪዲ ከኮምፒውተራችን ሳንነቅለው በፊት Eject ማድረግ አለባችሁ።
✅ Start -> All Program -> Computer or This PC -> ወደ ፍላሻችን ወይም External Hard Disk..... በመሄድ Right click በማድረግ Eject የሚለውን ይጫኑ። ከዛም ቢያንስ ለ5 ሰከንድ ይጠብቁ በቅድሚያ ግን ከፍላሽ ዲሳክችን....... የተከፈተ ማንኛውንም ፕሮግራም መዝጋት አስፈላጊ ነው።
ምስሉን ይመልከቱ!⁉️
✅ Eject ጥቅም ከኮምፒውተር ጋ የተሰካን ማንኛውንም ነገር ግንኙነቱን ያቋርጣል ማለት ነው። እንደገና ግንኙነቱ እንዲቀጥል ከፈለጋችሁ እንደአዲስ በመንቀል መሰካት ያስፈልጋል።
✅ይህ ተግባር የሁልጊዜ ስራችንና ተግባራችን ይሁን።
✅ ከተመቻችሁ ለሌሎች ሰዎች እንዲደርሳቸው #ሼር ይደረግ!
✅ ለፔጁ አዲስ የሆናችሁ ሰዎች #Like #shear ይደረግ።
👍101👏15🔥7
Telegra ካርድ እየበላ አስቸግሮታል?
ካርድ የሚጨርስበት ምክኒያት የተላኩልን message በራሱ ግዜ dawnload ስለሚያደርግባችሁ ስለሆነ የሚከተለውን ይሞክሩት
ቴግራማችሁ ላይ ትገቡና በግራ በኩል ከላይ ሶስት መስመሩን ትጫኑና settings የሚለውን ትፈልጉና ትጫናላችህ ከዛ ብዙ አማራጭ ያመጣ ከሱ ዉስጥ data and storage የሚለውን ትጫናላችሁ እዛ ዉስጥ authomatic media dawnload የሚል አለ ቀጥሎ ከሱ ታች when using mobile data የሚለውን ትጫናላችሁ እዛ ውስጥ
photos
voice message
videos
file
music
Gif
የሚሉትን ሁሉንም የራይት ምልክት(checkbox) ያለበትን ታጠፋላችሁ
ከዛ በኋለ በራሱ ግዜ ፎቶም ይሁን ሌሎችንም ዳውንሎድ አያደርግም
እንደተመቻችሁ ተስፋ አደርጋለሁ ይህን ማረጃ ለሌሎችም እንዲደርስ #Share አድርጉላቸው
ፔጁንም Like አድርጉ አስተያትም መጻፍ ይቻላል
👍149❤24👏21
ስልኮ ላይ ያሉ ስልክ # ቁጥሮች (contacts)
#ቢጠፋስ ብለው ይሰጋሉ ስልክ ቁጥሮች ከሲም ካርዶ ወይም ሰልኮ በተጨማሪ በኢሜል በማስቀመጥ ስልኮ
ሲጠፈ ፣ ሲበላሽ፣ በቫይረስ ሲጠቃ ከሚገጥሞት የመረጃ መጥፋት መካላከል እንችላለን።
ከዚህም በተጨማሪ አዲስ ሲም ብንገዛ የስልክ ቁጥሮችን አንድ በአንድ ሴቭ በማድረግ
ከኢሜላችን ጋር በማገናኘት በአንዴ ወደ ስልካችን ማምጣት ያስችለናል። ለዚህም የሚከተለውን ስቴፕ ይመልከቱ።
1,"የስልኮን menu button መጫን ከዛም “Settings.”
2,“Accounts and sync.” መጫን
3,“Add account” button መጫን
4,“Google.” የሚለው አማራጭ መጫን
5“Next” button መጫን
የGmail login መረጃ በማስገባት “Sign in” በመጫን (ይህ ግን ከዚ በፊት አካውን ከነበሮት ነው Gmail አካውን ት ከሌሎዎት “Create” button የሚለው መጫን
ከዛ አስፈላጊውን መረጃ በማስገባት አካውን መፍጠር።
“Sign in” button ስንጫን ስልካችን Gmail ላይ ያሉት የስልክ ቁጥር መረጃዎችን ያወርዳል።
“Sync Contacts/Sync now” አማራጭ መጫን
“Finish” button መጫን ከላይ ያሉትን ስቴፖች በመከተል የስልክ ቁጥሮን ማስቀመጥ ይችላሉ።
┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈
👍124❤25👎4🔥3🥰2
✳️ Operating System (OS) #ምንድነው ? #ጥቅሙስ?
✅ Operating System በእኛ በተጠቃሚዎች እና #በኮምፒውተሩ ሀርድዌር መካከል እንደገፅታ የሚያገለግል ሶፍትዌር ነው ።

✅ ማንኛውም ኮምፒውተር እንደ Chrome, Microsoft office, Game እና የተለያዩ አፕልኬሽኖችን ለማጫወት (ለመጠቀም) ግዴታ ቢያንስ አንድ #Operating System ያስፈልገዋል ።

✅ Operating System በዋነኝነት የሚያስፈልገን እኛ ከኮምፒውተሩ ጋር ለመግባባት ምንም አይነት ቋንቋ ሳያስፈልገን በቀላሉ #ኮምፒውተሩን እንድንረዳ ያግዘናል ።

✅ ማንኛውም ተጠቃሚ የትኛውንም ኮምፒውተር ሆነ #ስልክ ያለ Operating System መጠቀም በፍፁም አይችልም ።
👍38❤1
🔰ፕረዘንቴሽን የማቅረብ ጥበብ ለተማሪዎች
*⃣ፕረዘንት ለማድረግ ምን ብለን እንጀምር ❓
ዳስተር /Eraser ከተቀመጠበት ለማንሳት ረጋ ብላችሁ እየተረዳመዳችሁ Hello my classmates ፡
Hello dear our ......(Subject) teacher;
ዳስተሩን አንስታችሁ ቦርድ እያጠፋችሁ ንግግራችሁን ሳታቋርጡ ቀጥሉ
Here we are going to see about ..........(your lesson topic)
e.g Here we are going to see about philosophy .....ቦርድ ላይ ቀን ካልተፃፈ ፃፉ ...about philosopy ስትሉ ቦርድ ላይ ከድምፃችሁ እኩል ፅፋችሁ ጨርሱ

ወደ ተማሪዎቹ ዞር ብላችሁ

So if you are ready ,let's began.Philosophy means ....

So here we go.Philosophy means.... የሚል skeleton ተጠቅማችሁ ወደ ፕረዘንቴሽናችሁ መግባት

🔰ፕረዘንቴሽ ስናቀርብ ማድረግ ያለብን ነገሮች!

1⃣ ሰዓት አጠቃቀም

❓የተሰጣችሁን ሰዓት በዓግባብ ካልተጠቀማችሁበት ማለት የምትፈልጉትን ሃሳብ ሳትናገሩ ወደመቀመጫችሁ ትሸኛላችሁ!ስለዚህ ጊዜ ለመቆጠብ ፦


1)አንድ ነገር እየደጋገማችሁ ለማስረዳት አትሞክሩ።

2) ለተማሪዎች ኖት ለመፃፍ አትሂዱ!ኖት ከመፃፍ ይልቅ ትናንት ባሳየኋችሁ ምሳሌ መሰረት draft ያደረጋችሁትን Outline በBullet & numbering ቦርዱን አሸብርቁት!

3) ጊዜ ለመቆጠብ ከፈለጋችሁ በምታወሯቸው ቃል ማህል እንደ ባለስልጣን ' እእእ...' እያላችሁ ንግግር አታቆርፍዱ! ሳዓት ያልቃል ፤ ንግግራችሁ ይደብራል ፤ ነጥባችሁንም ያስጎምዳል!

2⃣ ቦታ አጠቃቀም

ሙሉ ቦታ ለመጠቀም ብላችሁ እንደ Dance chirography መድረኩን አትፈንጩበት!

ከመድረኩ ቀኝ ረድፍ ላይ መቆም ካለባችሁ ቆሙ ፤ በግራ መልኩ መሆን ካለባችሁ እንደዛው አክት አርጉ!ዘና በሉና

❗️Warning : calculation ከሆነ ቦርድ ላይ የምትሰሩት ተማሪዎችን ሳትከልሉ ፤ ራሳችሁን ከቦርዱ ወደ ዳር ገለል አርጋችሁ ማቀጣጠል ይኖርባችኋል!

❗️THINK 'BOUT DIS : ቦታ አጠቃቀም ላይ ጎበዝ ካልሆናችሁ የመድረኩ ማህከል ላይ ሁኑ!በግራም በቀኝም ፤ በማህልም ረድፍ ያሉ ተማሪዎች ትኩረታችሁን አይነፍጓችሁም!

3⃣የሰውነት እንቅስቃሴ አጠቃቀም!

ጥናቶች እንደሚያሳዩት ''በቃል ለቃል ምልልስ'' ጊዜ የሰውነት እንቅስቃሴዎች ሃሳባችንን በ 30% ጭማሪ ቀላል እና ግልፅ ያረጉታል።ስለዚህ የሰውነት እንቅስቃሴያችሁ እንደሚከተለው ይሁን!

✅ የእጅ እንቅስቃሴ አጠቃቀም

1)እጃችሁን ከጭንቃላታችሁ በላይ አታወራጩ!...የሚመለከታችሁ ሰው ይደክመዋል)

2) ነገሮችን በተለመዱ የእጅ መልክቶችን ለመግለፅ ሞክሩ!...ለምሳሌ

መሮጥ ከሆኑ ቃሉ እነ ሃይሌ ገ/ስላሴ ሲረጡ እጃቸውን እይደሚያረጉት ማሳየት ...

3) እጃችሁን ኪሳችሁ አታርጉ!...የጋጣወጥ ባህሪ አላችሁ ተብሎ ይታሰባልና

4) እያወራችሁ ሳለ እጃችሁን አትፈትጉ። የእጃችሁን ጣቶች ለማንቋቋት አትሞክሩ!እንደዛ ስታረጉ ሰው አይኑቹን እጃችሁ ላይ ያረጋል!ያኔ ድንብርብራችሁ ይወጣል!

5) አደራ እየፃፋችሁ የምትሳሳቱት ነገር ካያችሁ በእጃችሁ አታጥፉ!ምምህሩ እና ተማሪዎቹ ለናንተ ያላቸው ቦታ ይቀንሳል!ለምን አንድ ፊደል አትሆንም ከተሳሳተች በዳስተር አጥፉ!

✅ የእግር እንቅስቃሴ አጠቃቀም!

1).በተለይ ሴቶች 😡ጭነታችሁን በአንድ እግራችሁ ላይ አታርጉ!ቆፈጠን በሉ! የተመጣጠነ አረማመድ ይኑራችሁ!ላንዴ እንኳን ዘንበል የሚል አቋቋም እንዳይኖራችሁ!

✅ የጭንቅላት እንቅስቃሴ አጠቃቀም

1) ይሄ እንኳን ብዙ አይጠፋችሁም ፤ ራስ በመነቅነቅ የሚደረግ እንቅስቃሴ ነው!

4⃣የአቀራረብ ዘዴ

1). ተማሪዉን የሚያሳትፍ ከባቢ ፍጠሩ!

ለተማሪዎች ስታስረዱ ጥያቄ ጠይቋቸው ፣ መልሳቸውንም እየሰማችሁ የተነቃቃ audience ያዙ!መምህሩ አሪፌ እንቅስቃሴ ሲያይ ደስ ይለዋል!

2).ፕረዘንቴሽን ማቅረብ ከጀመራችሁበት second አንስቶ ለ አንዴ እንኳን ወደ መምህሩ እንዳታዩ!

አንዳንድ ደግ መምህር አለ ልክ ዞር ብላችሁ ስታዩት ራሱን እየነቀነቀ ልክ መሆናችሁን እየነገረ የሚያበረታታችሁ!

ሌሎች ግን መስመር ሊያስቷችሁ ነው ሚፈልጉት!በዛላይ አስረዱ የተባላችሁት ተማሪዎችን እንጂ መምህሩን አይደለም!

3.) ፕረዘንት ስታረጉ ልክ እንደመምህሩ ማድረግ ያለባችሁ ነገሮች አርጉ!
የሚረብሽ ካለ ከክፍል አሶጡ ፤ የሚንጫጫ ካለ ተቆጡ!

4.)የተለየ ፈፈግታ ወይም መሽኮርመም አታሳዩ!ሙዳችሁ ይጠፋባችኋልና

5.) ሁሉንም ተማሪ በዓይ ለመጎብኘት ሞክሩ!ይህ ካልተመቻችሁ !ደስ በሚል ሁኔታ ትምህርቱን በመከታተል ላይ ያሉ ቀና ተማሪዎችን መርጣችሁ ከነሱ ጋር የአይን ንግግር አርጉ!

...........Done !

❓ለመሆኑ Presentation ላይ ልዩ ቄንጦች ምንድናቸው?
የሚከተሉትን ቄንጦቾ ስትጠቀሙ በእርግጥ ክላሱ ሁሉ እናንተን ለማየት ይናፍቃል!
❗️Warning ፡ አንዳንድ ቄንጥ የማይወድ ወግ አጥባቂ መምህር አለ!ቦታ ለይታችሁ ተጠቀሙ ቄንጦቹ ፦

🔰 እያስተማራችሁ እያለ በእጃችሁ የያዛችሁትን ረጅም chalk ከዳሯ ላይ በጣታችሁ ሽርፍ በማድረግ ሽራፊዋን ወደ ምድር በንቀት መወርወር ....😎

🔰 ኮት ነገር አጥልቃችሁ ከነበር አሁን በንግግር ላይ ሳላቹ ኮታችሁን አውልቃችሁ ....chair lay ጣል ማረግ😎😎

🔰የሆነ diagram አንስታችሁ እያወራችሁ ከቦርዱ ራቅ በሉና ...ድንገት ከፍ ባለ ድምፅ ....ተመልአቱ እዛ መሃል ያለውን ነገር ብላችሁ እጃችሁን መሰንዘር.... ህዝቤ ከዛን ሰፍ 😎

🔰የኮት ቁልፍ መፍታት (በተለይ ሳንቃ ደረት ላላችሁ ወንዶች)

ገልፃ እያረጋችሁ ጀነን ባለ መልኩ የኮት ቁልፍ ቀስ ብላችሁ ፈታ ማረግ

❌አንዳንድ ተማሪ ቄንጥ ናቸው ብሎ የሚያስባቸው ነገር ግን ስግጥና የሆኑ ቄንጦች በ presentstion

🚫 አንገት ማሸሻት.......


🚫 ፀጉር በአንድ ጣት ማከክ....


❤️ልብ በሉ : አንዳንድ ተማሪ አለ present እያረጋችሁ ጥያቄ ጠይቆ ግራ ሊያጋባችሁ ሚፈልግ !ስለዚህ ማንም ተማሪ ቢሆን ጥያቄ ለመጠየቅ እጁን ካወጣ ስጨርስ መልስልሃለው በሉት!በኋላ ላይ ወላ ሊረሳው ይችላል!

❤️ልብ በሉ: Present አርጋችሁ ከጨረሳችሁ በኋላ ከተማሪዎች እንዲሁም ከመምህሩ ጥያቄ ይነሳባችኋል!ይህን ጊዜ ተማሪዎች እንዲሳተፉ እድል መስጠት ብልጥነት ነው!

👨‍💻This is all about!
©በቀሰም Academy ተዘጋጅቶ የቀረበ ::
👍128❤18🥰6👏5🔥4😁2
እንዴት ኢሜል #Email አካውንት እንከፍታለን?
✅እንደነገርኳችሁ Email account ለመክፈት መጀመሪያ Google Account መክፈት አለብን።

✅Gmail website ሲገቡ ወደ Google sign up page ይወሰዶታል።

✅መሰረታዊ መረጃዎች name, birth date, gender,እና location እንድታስገቡ ይጠዪቃችኋል።

✅ለሚከቱትፍ email address ስም መስጠት ዪጠበቅባችኋል።

አካዉንቱን ለመክፈት ከታች ያሉትን እስቴፖች ዪከተኩ።

👇👇👇👇👇👇
1⃣የሚወዱtን አሳሽ #browser (Google Chrome, Opera mini, Firefox ,PHX browser ወይም ሌላ) ይክፈቱና www.gmail.com ብለው ይጻፉ

2⃣ከዛ #Create Account የሚለውን ዪጫኑ

3⃣ #Sign Up form ሲመጣላችሁ የሚጠዪቃችሁን #information (First Name ,Last Name, Username እና Password) አስገብታችሁ #Next የሚለውን ተጫኑ

4⃣ከዛ የስልክ ቁጥራችሁን አስገቡ እና አካውንታችሁን #Verify አድርጉ።

👉ስልክ ቁጥራችሁን አስገብታችሁ #Next የሚለውን ስትጫኑ ስልክ ቁጥራችሁ ላይ የማረጋግጫ ኮድ (Verification Code ) በ SMS Google ይልክላች ሗል

5⃣ የተላከላችሁን የማረጋገጫ ኮድ ያሲገቡ እና #Verify የሚልውን ዪጫኑ

6⃣ከዛ #Personal Information ማስገቢያ #form ዪመጣላችኋል ከዛ #Name, Birth day እና Gender አስገብታችሁ #Next የሚለውን ይጫኑ።

7⃣ Privacy and Terms የሚል ሲመጣ I agree የሚልውን ዪጫኑ

8⃣አሁን በሚገባ አካውንታችሁን ፈጥራችኋል🤷‍♀።

አስኪ #Share እና #Like በማድረግ አበረታቱን💪።

ያወቁትን ማሳወቅ መልካምነት ነዉ።
ለጓደኞቻችሁ #Share ↪️ አድርጉ
ስለተከታተሉን እናመሠግናለን🙏
👍68❤3👎3🥰1
F1 – F12 ቁልፎች አገልግሎት
በኮምፒውተራችን ኪይቦርደ ከላይ ተደርድረው የምናገኛቸው ከF1 – F12 ያሉ ቁልፎችን Function Key እንላቸዋለን፡፡ በዋናነትም ከሌሎች ቁልፎች ጋር በማጣመር እንደ አቋራጭ እንጠቀምባቸዋለን፡፡ እንኘህ ቁልፎች እንደ ምንጠቀመው የ ኦፐሬቲንግ ሲስተም እና ሶፍትዌሮች አገልግሎታቸው ይለያያል፡፡: በዛሬው ቱቶሪያላችንም የተወሰኑትን እናያለን፡፡ 
F1  ብዙ ጊዜ የምንጠቀመው እርዳታ ስንሻ ነው፡፡ በአብዛኛው ሶፍትዌሮች F1 ስንጫን የ Help መስኮትን ይከፍቱልናል፡፡ ማይክሮሶፍት ወርድ ላይ ካለን Start እና F1 መጫን የ Microsoft Online Help ይከፍታል፡፡ 
 F2  የተመረጠን አይከን፤ፋይል ወይንም አቃፊ ስም ለመቀየር F2 መጫን ይቻላል፡፡ ማይክሮሶፍት ወርድ ላይ ካለን Alt + Ctrl + F2 መጫን የ Open መስኮትን ይከፍታል፡፡፡ 
F3 á‹´áˆľáŠ­á‰śá• ላይ ካን ስንጫን የፍላገ መስኮት ይከፈታል፡፡ ማይክሮሶፍት ወርድ ላይ ካለን ቃልን መርጠን Shift + F3 መጫን የተመረጠው ቃል ውስት የሚገኙ ፊደላትን አንድላይ ካፒታል ወይን ስሞል ወይንም የመጀመሪያውን ፊደል ካፒታል ያደርግልናል፡፡ 
F4 áŠ áˆáŠ•áˆ ማይክሮሶፍት ወርድ ላይ ካለን F4 መጫን ለመጨረሻ ጊዜ የተገበርነውን ይደግምልናን፡፡ ለምሳሌ አበበ ብለን ብንጽፍ እና F4 ብናጫን በ የምትባለውን ፊደለ በድጋሚ ይጽፍልናል፡፡Alt + F4 መጫን አክቲቭ የሆነውን መስኮት ይዘጋልናል፡፡ Ctrl + F4 ስንጫን ደግሞ አክቲቭ ከሆነው መሰኮት ውስጥ አክቲቭ የሆነውን ታብ ይዘጋልናል፡፡ ለዚህ ጥሩ ምሳሌ የሚሆነው በ ብራውሰራችን ከአንደ በላይ ታብ ከከፈትን Ctrl + F4 ስንጫን ያለንበትን ታብ ብቻ ይዘጋልናለን ነገር ግን Alt + F4 ብንጫን ሙሉ በሙሉ ብራውሰሩን ይዘጋብና ማት ነው፡፡ 
F5 አሁን ገበያ ላይ ባሉት አብዛኛዎ ብራውሰሮች ላይ F5 መጫን Refresh ያደርገልና፡፡ ማይክሮሶፈት ወርድ ላይ የ Find መስኮትን ይከፍትልናል፡፡ ማክሮሶፍት ፓወር ፖይንት ላይ ደግሞ Slideshow ያስጀምርልና፡፡ 
F6 á‰ áŠ á‰Ľá‹›áŠ›á‹ ብራውሰሮች ላይ F6 ስንጫን የማውሳችን አቅጣጫ መጠቆሚያ(cursor) ወደ አድራሻ መጻፊያው ይወስድልና፡፡ ከአንድ በላይ የማይከሮሶፍት ወርድ ከከፈትን Ctrl + Shift + F6 መጫን ወደቀጣዩ የማይክሮሶፍት መስኮትያሸጋግረናል፡፡ 
F7 ማይክሮሶፍት ወረድ ላይ Shift + F7 መጫን የ Thesaurus መስኮትን ይከፍትልናል የሚያገለግለውም ሰፔሊንግ፤ ፍቺ እና ሰዋሰው ለማስተካከል ነው፡፡ 
F8 áŠŽáˆá’á‹á‰°áˆŤá‰˝áŠ• ሲነሳ የ Windows፤ Startup menu ለመግባት የጠቅማል፡፡ 
F10 አክቲቭ የሆነውን ዊንዶው ሜኑ ባርን አክቲቭ ለማድረግ ያስችላል፡፡ Shift + F10 መጨን ራይት ክሊክ እንደማድረግ ይቆጠራል፡፡ 
F11 በአብዛኛዎ ብርውሰሮች ላይ F10 ስንጫን የምንመለከተው መስኮት ሙሉ በሙሉ የኮምውተራችንን ስክሪን ይሞላዋል (Full screen) ፡፡
 F12 áˆ›á‹­áŠ­áˆŽáˆśáá‰ľ ወርድ ላይ የ Save as ማስኮትን ይከፍትልናል፡፡ Ctrl + Shift + F12 ፐሪንት ያዛል፡፡
👍73❤18
SafewayManufacturing_1_1.0.apk
1.5 MB
ምርጥ ዌብሳይትና የዌብሳይት App በተመጣጣኝ ዋጋና በታላቅ ቅናሽ ያሰሩ!
አፕልኬሽኑን በማውረድ ስልኮ ላይ ሸመጫን ይሞክሩት! ይደውሉልን ስልካችንን እፕልኬሽኑን ሲከፍቱት ያገኙታል።
በቅርቡ ሰርተን ያስረከብናቸው ዌብሳይቶችን ይጋበዙልን።
እርስዎም የሚሰሩትን ስራ ሊያቀላጥፍልዎ የሚችል ዌብሳይት ይዘዙን!
ለንግድ፣ ለመንግሥት ተቋማት፣ ለግል ድርጅቶች፣ ለኮሌጆች፣ ለሆቴሎች፣ ለአስመጭና ላኪ ድርጅቶች፣ ለድለላ ስራ፣ ለማንኛውም አገልግሎት ሰጭ ድርጅቶች በቅልጥፍና አገልግሎት ማግኘት ይችላሉ።
☎️ 0929273364 ሙሀመድ ኮምፒውተር ቴክኖሎጂ
1ኛ www.4wcomputers.com
2ኛ www.safeway7.com
3ኛ www.mametechsolution.com
4ኛ www.ethiotechnologys.com
5ኛ www.bournworks.com
👍27🔥5👎3👏1
💻. SQL መማር ይፈልጋሉ
👩‍🎓👩‍🎓 ለጀማሪዎች እሚሆን በአማርኛ የተዘጋጀ ቲቶር ከክፍል 1 እስከ ክፍል 4 በAda Technology Tube ተዘጋጅቶ ቀርቦላችኋል::

✅ SQL Tutorial -full database course for beginner part 1
https://youtu.be/sWel3mrNUAI

✅ SQL Tutorial -full database course for beginner part 2
https://youtu.be/V1OFOxmFXhQ

✅ SQL Tutorial -full database course for beginner part 3
https://youtu.be/NIfYCp3z2jk

✅ SQL Tutorial full database course for beginner part 4
https://youtu.be/VGpOaQJnzLY

ዩትዩብ ቻናሌን ሰብስክራይብ በማድርግ ድጋፋችሁ አይልየኝ ??
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
https://www.youtube.com/channel/UClXEt7DFjKVSb_m03DvXSPg
👍32❤5
#የዛሬው_ምክር
💢የዛሬው ማሳሰቢያ ስልክዎ 📱 ላይ #backup ስለመያዝ ነው፤ ይህም በድንገተኛ ችግሮች ስልክዎ ሊበላሽ ❌ ወይንምሊጠፋ ስለሚችል #backup መያዝ በጣም ጠቃሚ ነው።

✔️ #backup እንዴት መያዝ እንችላለን❓

1.አንዳንድ ስልኮች ላይ #backup መያዣ አፕ ተጭኖ ስለሚመጣ ስልክዎ 📲 ላይ ይፈልጉት፤ አጠቃቀሙ በጣም ቀላል ነው።

2.ስልክዎ 📲 ላይ ከሌለ ከ play store ላይ በማውረድ 📥 ይጠቀሙ።

✔️#ባክአፑን ምን ላይ ብናስቀምጠው 📥 የተሻለ ነው❓

➡️ ከሁሉም በተሻለ online
1. Dropbox
2. MOBILedit
3. Mobogenie
4. Mobisynapse
5. MoboRobo
6. iCloud
7. MEGA
ላይ ማስቀመጥ የተሻለ ነው።
⏺ ከላይ የተጠቀሱትን Apps አንዱን በስልካችሁ በማውረድና Login እንድታደርጉ ይጠይቃችኋል። ስለሆነም እናንተ መጀመሪያ Register ማድረግ ይጠበቅባችኋል። ለምሳሌ Full name, Email, Password እንድታስገቡ ይጠይቃችኋል። ከዛም ይከፍትላችኋል። የፈለጋችሁትን መረጃ ለምሳሌ ሪሰርቾችን፣ ፎቶዎችን.... መጫን ትችላላችሁ። ግን የነጻ Free Storage ከ5-15 GB ነው የሚሰጡት።
➡️Backup ፋይሉን ኮምፒውተርዎ 💻 ላይ ማስቀመጥም ይችላሉ።

➡️ ከላይ 👆 የተጠቀሱትን ለማድረግ ካልቻሉ የመጨረሻ አማራጭዎ ስልክዎ 📲 ውስጥ ያለው ሚሞሪ ካርድ(SD card) ላይ ማስቀመጥ ይችላሉ።

⚠️ነገ የሚሆነው ሰለማይታወቅ አሁኑኑ #backup ይያዙ።
👍77👏5😁3❤1
🔵 አንድሮይድ ስማርት ስልካችንን እንዴት ማሻሻል /update/ ማድረግ ይቻላል?
በስማርት ስልኮች ኦፕሬቲንግ ሲስተም ገበያ ውስጥ አንድሮይድ ቀዳሚውን ስፍራ ይይዛል።
የአንድሮይድ ኦፕሬቲንግ ሲስተም ባለቤት የሆነው ጎግል፥ በየጊዜው በአንድሮይድ ላይ የተለያዩ ማሻሻያዎችን ያደርጋል።
በዚሁ ጊዜም የተሻለ አገልግሎት ለማግኘት የአንድሮይድ ኦፕሬቲንግ ሲስተማችንን ማሻሻል /update/ ማድረግ ይጠበቅብናል።
➚አንድሮይድ ኦፕሬቲንግ ሲስተምን በየጊዜው ለምን ማሻሻል ያስፈልጋል…?
↬የስልካችን የመስራት አቅም እንዲጨምር
↬የስልካችን እድሜምን ለማርዘም
↬አዳዲስ ማሻሻያዎችን ለመጠቀም
↬የሰልካችንን ደህንነት ለመጠበውቅ
↬ስልካችንን ከተለያዩ የቫይረስ ጥቃት ለመከላከል
↬የስልካችን ባትሪ የቆይታ እንድሜን ለማርዘም
➠አንድሮይድ ኦፕሬቲንግ ሲስተም ለማሻሻል /update/ ለማድረግ መከተል ያለብን ቅደም ተከተል..
1. የአንድሮይድ ስልካችን መተግበሪያ ውስጥ በመግባት ሴቲንግስ /Settings/ መክፈት
2. ከሚመጡልን ዝርዝር ውስጥ “About phone” ወይም ሌላ ተመሳሳይ አማራጭ መክፈት
3. ከዛም “System Updates” ወይም “Software Update” የሚል አማራጭ የሚመጣልን ሲሆን፥ እዛ ውስጥ በመግባት ማሻሻል እንችላለን።
4. “System Updates” በምንከፍትበት ጊዜ በርከት ያሉ አማራጮች የሚመጡ ከሆነ “Check for updates now”፣ “Software update check” ወይም ሌሎች ተመሳሳይ አማራጮች ውስጥ በመግባት የስማርት ስልካችን ኦፕሬቲንግ ሲስተምን ማሻሻል /update/ ማድረግ እንችላላን።
ማስጠንቀቂያ፦
❗️በዳታ ብዙ ብር ሊቆርጥብቆት ስለሚችል ይጠንቀቁ በWiFi Update ቢያደርጉት ይመረጣል።
❗️በቅድሚያ ስልክዎትን በበቂ ሁኔታ ቻርጅ ያድርጉ Update እያደረገ ባለበት ሁኔታ ቻርጅ ቢዘጋ ስልኮ አደጋ ውጥ ሊገባ ይችላል።
share በማድረግ ሌሎችንም ያሳውቁ!!
👍91👏10❤3😁1