Muhammed Computer Technology (MCT)
38.1K subscribers
527 photos
7 videos
254 files
910 links
🔴አድራሻ:-
✅ ስ.ቁ: 0929273364
✅ ዌብሳይት www.mctplc.com
✅ቴሌግራም አካውንት: https://t.me/mctplc
✅ email: mct16plc@gmail.com
✅ ቲክቶክ አካውንት tiktok.com/@mctplc
Download Telegram
ስልካቹን Factory rest ከማድረጋቹ በፊት ማድረግ ያለባችሁ ነገር

ስልኩ የራሳቹ ከሆነ እና የራሳቹን Email አድሬስ ያስገባቹበት ከሆነ rest ካደረጋቹት በሁዋላ ስትጠቀሙበት የነበረውን email እንድታስገቡ ስለሚጠይቃቹ password እና email መርሳት የለባቹም ::


ነገር ግን ከሰው ላይ ገዝታቹት ከሆነ እና የገባበትን email ካላወቃቹት ግን ፓተርኑን ወይም የስልኩን ፓስወርድ የምታውቁት ከሆነ ይህንን ነገር ማጥፋት አለባቹ

መጀመሪያ ላይ Setting
👇
About Phone
👇
Software information
👇
Build Number የሚለውን ሶስት ግዜ ስትነኩት
👇
Developer Option ON ይሆናል

ከዛ ወደ setting ትመለሱና developer option ገብታቹ
OME Unlock የሚለውን ታበሩትና ከዛ FactoryRest ማድረግ ትችላላቹ ምንም Email አይጠይቃቹም ማለት ነው።

ወይም factory reset ከማድረጋችሁ በፊት
Setting👉account👉remove Google acount
👍85❤25🥰3
ለተመራቂ ተማሪዎች
ሪሰርች ስትሰሩ ከዚህ በታች የጠቀስኳቸው ከከበዷችሁ በምርጥ አቀራረብ ቪዲዮ ይዥላችሁ ቀርቤያለሁ!
✅ Automatic References
✅ Automatic List of tables
✅ Automatic List of figures
✅ Citation እንዴት እንሰራለን?
በምርጥ አቀራረብ በYouTube ተዘጋጅቶ ለእይታ ዝግጁ ነው ከታች ያለውን ሊንክ በመጫን መመልከትና መማር ትችላላችሁ!

https://youtu.be/VujbubSHkZs

ከዚህ በታች የዘረዘርኳቸው
✔️ Automatic Tables of Content.
✔️ Page Break እንዴት እንሰራለን? ለሚለው ከታች ያለውን ሊንክ በመጫን ይመልከቱ

https://youtu.be/aB-z5uKq75U
~><~~~~
የYouTube ቻናሉን Subscribe በማድረግ ምርጥ ምርጥ ትምህርቶችን ይማሩ!
👍89❤14👏7🥰3😁2
ቢትኮይን በኢትዮጵያ

#Ethiopia | ‹‹ኢትዮጵያ ውስጥ በርካታ ሰዎች የቢትኮይን ተጠቃሚ መሆናቸው በጥናት ታውቋል›› አቶ ዮናስ ማሞ፣ በፋይናንስ ደኅንነት አገልግሎት የፋይናንስ ወንጀሎች ትንተና ኃላፊ

ከኢትዮጵያ አኳያ ትኩረት ተሰጥቶት እየተሠራበትና ክትትሎች የሚደረግበት የመጀመሪያውን ክሪፕቶ ከረንሲ ዓይነት ቢትኮይን ነው፡፡

ከዚህ ጋር ተያይዞ ክሪፕቶ ከረንሲ የራሱ የሆነ መገለጫዎች ያሉት ሲሆን፣

የመጀመሪያው ‹‹ዲሴንትራላይዝድ›› (ማዕከላዊ ያልሆነ) ስለሆነ ማንም ሰው አይቆጣጠረውም፡፡

በዓለም የፋይናንስ ሥርዓት ውስጥ ባንኮች የራሳቸው የሆነ ‹‹ሴንትራላይዝድ›› (ማዕከላዊ) የሆነ ዳታ ቤዝ አላቸው፡፡ ቨርቹዋል ከረንሲ ዲሴንትራላይዝድ ስለሆነ በተለያዩ ኮምፒዩተሮች ላይ ተበታትኖ ይገኛል፡፡ ስለዚህ እያንዳንዱ የግብይት እንቅስቃሴ በተለያዩ ኮምፒዩተሮች ላይ በተመሳሳይ መረጃ ተበትኖ ይገኛል፡፡

ሁለተኛ የመገበያያው አጠቃላይ አቅርቦት 21 ሚሊዮን ብቻ ነው፡፡

ለምሳሌ ኢትዮጵያም ሆነች አሜሪካ ገንዘብ ሲያጥራቸው ገንዘብ ያትማሉ፣ ገደብ የለውም፡፡ ነገር ግን ሳቶሺ ኮሞቶ የቢትኮይን ፕሮቶኮል ላይ እንደተገለጸው፣ አጠቃላይ የመገበያያው መጠን 21 ሚሊዮን ብቻ ነው፡፡ ለግለሰቦች ተሸጦ ደግሞ የሚያልቀው 2140 መጠን ድረስ ነው፡፡

ይህ የቢትኮይን መጠን በተለያየ መንገድ ለግለሰቦች እንዲደርስ ይደረግና እሱ ብቻ እየተንቀሳቀሰ በዲጂታል መንገድ እንዲቀጥል ይሆናል፡፡

ዓላማቸውም መንግሥት የማይቆጣጠረው፣ ግለሰቦች ወይም ማንም የማይታወቅ ሰው የመሠረተውና የሚመራው ማድረግ ነው፡፡ አከፋፈቱ ላይ ግለሰቦች ራሳቸውን ኮምፒዩተር ወይም ላፕቶፕ ተጠቅመው የሚከፍቱት ነው፡፡

በተለምዶ በባንኮች ሥርዓት ውስጥ የሚገኘውንና ኬዋይሲ (ኖዊንግ ዩር ከስተመር) በሚባል ዓለም አቀፍ አሠራር የሚገኘውን እያንዳንዱ ባንክ ገንዘብ የሚያንቀሳቅስለትን ደንበኛ መረጃ የሚሞላው ፎርም ይገኛል፡፡

ወደ ክሪፕቶ ሲመጣ ግን በኢንተርኔት አማካይነት የሚከፈት ስለሆነ ማንም ተቆጣጣሪ አካል የለውም፡፡

ኢትዮጵያ ውስጥ ምን ያህል ይህን የመገበያያ ዓይነት ይዞ የሚገኝ ሰው አለ? ቢባል፣ በብሔራዊ ባንክም ሆነ በሌሎች አካላት መረጃው የለም፡፡

Via ሪፖርተር
👍71❤12😁4🔥3🥰2😢1
✅ አሁናዊ የቴክኖሎጅ(#Technological) ቪዲዮዎችን
✅ የኦላይን ቢዝነስ (#online #business) ቪዲዮዎችን
✅ የሶፍትዌር ቲቶር ቪዲዮዎችን
👉🏻 ሲቪል ኢንጂነሪንግ ሶፍትዌር (#civil #engineering #software)
👉🏻 ፎቶ ሾፕ ሶፍትዌር( #photo #shop #software)
👉🏻 የአኒሜሸን ቪዲዎ ሶፍትዌር (#Adobe #Character #Animator )
👉 #SQL ሶፍትዌር
✅ የማይክሮ ሶፍት ኦፊስ (#Microsoft #office) ቪዲዮዎችን
✅ የተለያዩ የኮምቲውተር(#computer) መርጃ ቪዲዮዎችን
✅ የተለያዩ የስልክ (#phone) መርጃ ቪዲዮዎችን
👌እንዲሁም የተለያዩ አስተማሪ እና አዝናኝ ቪዲዮዎችን ያገኛሉ።
ከርስዎ እሚጠበቀው ቻናላችንን ሰብስክራይብ #subscribe በማድርግ እና የድወል ምልክቷን በመጫን ቤተሰብ መሆን ነው።

👁️👁️መልካምነት ለራስ ነው!!!👁️👁️

👇👇👇👇👇👇👇👇

https://www.youtube.com/channel/UClXEt7DFjKVSb_m03DvXSPg?sub_confirmation=1
https://www.youtube.com/channel/UClXEt7DFjKVSb_m03DvXSPg?sub_confirmation=1
👍46😁4🔥2👏2👎1
በቅናሽ ኮምፒውተር ይፈልጋሉ?
ZAN የኮምፒውተር የሽያጭ ማእከል
👍👍👍በቅናሽ የሚያገኑበት
🔶 ኦሪጅናል ላፕቶፕ ኮምፒውተር
🔶 ኦሪጅናል ዴስክቶፕ ኮምፒውተር
🔶 ኦሪጅናል ባትሪ
🔶 ኦሪጅናል ቻርጀር
የፈለጉትን በአዲስና በመጠኑ ያገለገሉ እቃዎችን በቅናሽ ዋጋ ማግኘት ይችላሉ!
አድራሻ:- አዲስ አበባ, መገናኛ, ዘፍመሽ ፕላዛ, 3ኛ ፎቅ, 322 ቁጥር
ይደውሉ! Mobile 0923479869
በቴሌግራም ቻናላችን በመግባት እቃዎቻችንን ማግኘት ይችላሉ!.
👇👇👇Join👇👇👇
https://t.me/zanlaptop
https://t.me/zanlaptop
https://t.me/zanlaptop
👍34❤3🥰3
✴️ ኮምፒውተራችን እንዴት በቀላሉ ከፕሪንተር ጋር ማስተዋወቅ እንችላለን

🔆 ኮምፒውተራችንን ከፕሪንተር ጋር ለማስተዋወቅ የሚጠቅሙ ብዙ ሶፍትዌሮች እንዳሉ ይታወቃል እንዲሁም ተመሳሳይ  wifi በመጠቀምም በዋየርለስ ወይም ያለ ኬብል ፕሪንተራችንን ከኮምፒውተራችን ጋርም ማስተዋወቅ እንችላለን።
🔆 እኔ ግን ዛሬ ይዤላችሁ የቀረብኩት ያለምንም wifi እና software ኮምፒውተራችንን ከፕሪንተር ጋር እንዴት ማስተዋወቅ እንደምንችል ነው።
🔆 ኮምፒውተራችንን እንዴት ከፕሪንተራችን ጋር ማስተዋወቅ እንችላለን።
1⃣ control panel ውስጥ በመግባት device printer እንመርጣለን ወይም start ን በመንካት search box ላይ device and printer ብለን እንፅፋለን።
ኮምፒውተራችንን ከፕሪንተር ጋር ማያያዙን እንዳንረሳ።
2⃣ በመቀጠል add printerን  እንመርጣለን ።search እስኪጨርስ እንጠብቃለን።
3⃣ add alocal printer የሚለውን መርጠን next እንለዋለን።
4⃣ በመቀጠል ፕሪንተራችንን ያያዝነው በኬብ ስለሆነ ከሚመጣልን ምርጫ የመጀመሪያውን USB portን እንመርጣለን።next እንለዋለን
5⃣ አሁን ከሚመጡልን ዝርዝሮች ውስጥ የፕሪንተራችንን ስም በመፈለግ መርጠን next ቀጥሎም next እንለዋለን።
6⃣ በመጨረሻም print a test page የሚል ይመጣልናል click አርገን test እናደርግና finish ብለን እንጨርሳለን።
ለወዳጆ ያጋሩ
👍73❤8👏4
❖ ዩቲዩብን እንዴት የገቢ ምንጭ ማድረግ ይችላሉ?
▄▄▄▄▄▄▄▄▄▄▄▄▄▄▄

❑ ዩቲዩብ ለብዙዎቻችን ተንቀሳቃሽ ምስሎችን በነፃ የምንኮመኩምበት ድረ-ገፅ ነው።

ነገር ግን ዩቲዩብ ከዚህም አልፎ ለብዙዎች የገቢ ምንጭ መሆን ከጀመረ ሰነባብቷል፤ ታዋቂነት ከማትረፍም በላይ ሚሊዬነር መሆን የቻሉ ጥቂት አይደሉም።

አብዛኛው ተጠቃሚ በነፃ ከሚመለከተው ተንቀሳቃሽ ምስል እንዴት ገቢ ሊገኝ ይችላል? የሚለው ግን የብዙዎች ጥያቄ ነው። እነሆ አምስት መንገዶች...

①• ማስታወቂያዎች
╤╤╤╤╤╤╤╤╤

❑ የመጀመሪያው ዩቲዩብን የገቢ ምንጭ ማድረጊያው መንገድ ማስታወቂያ ነው። አንድ ምስል ከመመልከትዎ በፊት የሚመጣው ማስታወቂያ ለዩቲዩበኞች አንደኛው የገቢ ምንጫቸው ነው።

አንድ ሺህ ተጠቃሚዎች ማስታወቂያውን በተመለከቱ ቁጥር ጉግል ለዩቲዩበኛው ከ1 ዶላር 5 ዶላር ድረስ ሊከፍል ይችላል።

ነገር ግን ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ዩቲዩብ 50 በመቶውን ገቢ መውሰድ በመጀመሩ ምክንያት ከማስታወቂያ የሚገኘው ገቢ እጅግ ቀንሷል።

እርስዎ አንድ ምስል ዩቲዩብ ላይ ሰቅለው የእርስዎን ምስል ለማየት የሚመጡ አንድ ሚሊዮን ሰዎች ማስታወቂያውን ከተመለከቱ ከ1ሺህ ጀምሮ እስከ 5ሺህ ዶላር ሊያገኙ ይችላሉ ማለት ነው።

②• ለሚከፍሉ/ለሚለግሱ ማሳየት
╤╤╤╤╤╤╤╤╤╤

❑ ዩቲየበኞች ሰው ብዙም የማያውቀው የገንዘብ መሰብሰቢያ መንገድ በመጠቀምም ገቢ ያገኛሉ።

ታዋቂው እንግሊዛዊ ዩቲዩበኛ ኢቫን ኤዲንገር እንደሚናገረው "በይነ-መረብን በመጠቀም ሳንቲም ማሰባሰብ የሚቻልበት መንገድ እንደሆነ አስቡት" ይላል።

"ተጠቃሚዎች ቪዲዎችን ተመልክተው ከወደዷቸው ከ1 ዶላር ጀምሮ በወር እርዳታ እንዲለግሱ የሚያደርግ ሂደት ነው" ሲል ይተንትናል።

አንዳንድ ዩቲዩበኞች መሰል ሂደት ያለውን ጥቅም በመረዳት እርዳታ የሚለግሱ ተጠቃሚዎች ብቻ ምስሎቹን የሚመለከቱበት ድረ-ገፅ ይዘረጋሉ።

③• ተያያዥ ድረ-ገፆች
╤╤╤╤╤╤╤╤

❑ ይህ መላ በተለይ ፋሽንና የመዋቢያ ውጤቶችን በተመለከተ ተንቀሳቃሽ ምስል ሰርተው ዩቲዩብ ላይ ለሚሰቅሉ በጣም ተመራጭ ነው።

ለምሳሌ ዩቲዩበኞቹ አንድ የመዋቢያ ውጤት የሆነ የምርት ዓይነትን ጥቅምና ጉዳት ከተነተኑ በኋላ ያንን ምርት መሸመት የሚፈልጉ ሰዎች ተያይዞ በተቀመጠው ድረ-ገፅ አማካይነት ምርት መግዛት እንደሚችሉ ይጠቁማሉ።

በዚህ መንገድም የመዋቢያ ምርቱን ከሚሸጠው ድርጅት ጋር ባላቸው ስምምነት መሠረት ጥቅም ያገኛሉ ማለት ነው።

④• ምርት ጥቆማ
╤╤╤╤╤╤╤

❑ ፖስተሮች፣ ቲሸርት እንዲሁም የተንቀሳቃሽ ስልክ አካላት ዩቲዩበኞች ገቢ የሚያገኙባቸው ሌሎች መላዎች ናቸው።

ለምሳሌ አንዲት ዩቲዩበኛ በድረ-ገፁ በምታስተላልፈው መልዕክት ላይ አንድን ምርት የሚጠቁም ቲሸርት ለብሳ ወይም ስልክ ይዛ ብትታይ ይህ ማለት ተዘዋዋሪ ምርት ማስተዋወቅ በመሆኑ ሌላ የገቢ ምንጭ ሆኖ ያገልግላል።

የምርት ምልክት (ብራንድ) ነገር በዚህ ብቻ የሚያበቃ አይደለም።

⑤• የምርት ምልክት (ብራንድ) ማስታወቂያ
╤╤╤╤╤╤╤╤╤╤╤╤

❑ ኤዲንገር እንደሚናገረው የምርት ምልክት ለዩቲዩበኞች ዋነኛ የገቢ ማግኛ መላ ነው።

ብዙ ጊዜ ኩባንያዎችና አምራቾች ብዙ ተከታይ ባላቸው ዩቲዩበኞች አማካይነት ምርቶቻቸውን ያስተዋውቃሉ፤ ለዚህም በርካታ ገንዘብ ይከፍላሉ።

"ሉክ የተባለ ባልንጀራዬ ከአንድ የአሜሪካ ኩባንያ ጋር የ26 ሺህ ዶላር ስምምነት እንደተፈራረመ አውቃለሁ" ይላል ኤዲንገር።

ብዙ ተከታይ (ሰብስክራይበር) ያላቸው ዩቲዩበኞች ከላይ በተጠቀሱት መንገዶች የትየለሌ ትርፍ ሊያገኙ ይችላሉ፤ እያተረፉም ይገኛሉ።
══════❁✿❁ ══════
ŠTechtalkwithsolo
👍76❤9🔥3
#የፌስቡክ አካውንታችን የምንሰረቅባቸው ምክንያቶች??
የፌስቡክ ተጠቃሚዎች የፌስቡክ አካውንታቸው ከሁለተኛ ወገን ወይም ከሰራቂዎች ለመጠበቅ የሚያስችሉ ብዙ መንገዶች ያሉ ሲሆን ይህንንም ለማድረግ የፌስቡክ ተቋም ብዙ አማራጮችን ለተጠቃሚዎች አቅርቧል፡፡
የፌስቡክ አካውንታችንን ከሁለተኛ ወገን ወይም ከጠላፊዎች ለመከላከል መውሰድ የሚገባንን ጥንቃቄ ከመመልከታችን በፊት የፌስቡክ አካውንታችን በቀላሉ በጠላፊዎች እጅ እንዲወድቅ የሚያደርጉንን ተግባራቶች እና ድክመቶች ከዚህ በታች እንመለከታለን
የፌስቡክ አካውንታችን በቀላሉ የሚሰረቁበት ምክንያቶች
1. ለፌስቡክ አካውንታችን መግቢያ ቀላል የሆነ የይለፍ ቃል ወይም ፓስዎርድ ማስቀመጥ
የብዙ ሰዎች የፌስቡክ አካውንታቸው በቀላሉ በጠላፊዎች እንዲወሰድ የሚያደርገው ባለማወቅ እና በመዘናጋት በቀላሉ ሊታወቁ እና ሊገመቱ የሚችሉ የይለፍ ቃል ወይም ፓስወርድ መጠቀማቸው ዋነኛነው ነው፡፡
ለምሳሌ ያህልም የፌስቡክ አካውንት ስሙን ለይለፍ ቃልም መጠቀም›፣ የግል ስማቸውን ወይም የአባት ስማቸውን ወይም የሚታወቁበትን ሌላ ስም መጠቀም፣ ቀላል ቁጥሮችን መጠቀም( 123456.፣ 987654.፣1112223
344፣ በቀላሉ የሚታወቁ ቃላቶችን መጠቀም (Love,Happy,Good, etc…)፣ስልክ ቁጥርን ለፓስወርድ መጠቀም ወዘተ….
እነዚህን መሰል ፓስወርድ መጠቀም በቀላሉ ሊታወቁ እና በጠላፊዎች አካውንታችን እንዲሰረቅ የሚያደግ ዋናኛ ምክንያት ነው፡፡
2. በውስጥ መስመር የሚላኩ ምንነታቸው ያልታወቁ ሊንኮችን ለመክፈት መሞከር
በርካታ የፌስቡክ ተጠቃሚያን ከማያውቁትም ሰው ይሁን ከሚያውቁት ሰው በፌስቡክ የውስጥ መስመር የሚላክላቸውን ምንነቱ ያልታወቀ ሊንክ ለመክፈት መሞከራቸው አካውንታቸው በቀላሉ በጠላፊዎች እጅ እንዲወድቅ ያደርገዋል፡፡ በውስጥ መስመር ብቻ ሳይሆን የተለያዩ አላስፈላጊ ምስል እና ቪዲዬዎችን የያዙ ጠላፊዎች በሚለቁት ሊንኮች በፌስቡክ ሲሰራጩ እነሱን ለመክፈት ሊንኩን ሲጫኑ በቀላሉ አካውንታቸው በጠላፊዎች እጅ ይገባል፡፡ በተለይም ሊንኩን ተጭነን ለመክፈት ስንሞከር በድጋሚ የይለፍ ቃላችንን ወይንም ፓስወርዳችንን እንድናስገባ ከተጠየቅን እና ካስገባን በቀላሉ አካውንታችን በጠላፊዎች እጅ የመግባቱ እድል ሰፊ ይሆናል፡፡
3. የይለፍ ቃል ወይንም ፓስወርድን ለረጅም ጊዜ ሳይቀይሩ መቆየት
ብዙ የፌስቡክ ተጠቃሚዎች የይለፍ ቃላቸውን ምናልባትም አካውንቱን ከከፈቱበት ቀን ጀምሮ ላይቀይሩት ይችላሉ፡፡ የይለፍ ቃልን በየጊዜው ለጥንቃቄ አለመቀያየር በጠላፊዎች አካውንታችንን ለመስረቅ ለሚያደርጉት ሙከራ እገዛ ያደርግላቸዋል፡፡ የይለፍ ቃሉ ስለማይቀየር ከተደጋጋሚ ሙከራ ቡኋላ ለፌስቡክ አካውንታችን ያስገባነውን የይለፍ ቃል ሊደርሱበት ይችላሉ ፡፡
4 የፌስቡክ አካውንት የከፈቱበትን ኢሜል አድራሻ ለሁሉም እንዲታይ ማድረግ ወይም ሁሉም የሚያውቀውን አድራሻ መጠቀም
የፌስቡክ አካውንት ለመክፈት ያወጣነውን የኢሜል አድራሻ ለሁሉም ሰው እንዲታይ (visible to All) ካደረግነውን የኛን አካውንት ለመስረቅ ለሚፈልጉ ጠላፊዎች የኢሜል አድራሻንን በመጠቀም ኢሜላችንን በመስረቅ በቀላሉ የፌስቡክ አካውንታችንን እንዲጠልፉ ያግዛቸዋል፡፡
የኢሜል አድራሻችንን ብቻ ከፌስቡክ ላይ እንዳይታይ ማድረግ በራሱ የስርቆት አደጋውን ቢቀንሰውም ሁሉም ሰው የሚያውቀውን፣ለተለያዩ አገልግሎቶች የምንጠቀማቸውን የኢሜል አድራሻ ለፌስቡክ አካውንትም የምንጠቀመው ከሆነ በቀላሉ በጠላፊዎች ሊታወቅ እና አካውንታችንን ለመስረቅ ለሚያደርጉት ሙከራ ሊያግዛቸው ይችላል፡፡
በተወሰነ መልኩ ብዙዎቻችን አካውንቶቻችን እንዲሰረቁ እድሉን የሚያመቻቹትን ምክንያቶች ከላይ ለማስረዳት ሞክሬያለው፡፡ ምክንያቶቹ እነዚህ ብቻ ናቸው ማለት ሳይሆን ሌሎችም በርካታ ምክንያቶች መኖራቸው ከግንዛቤ ውስጥ ሊገባ ይገባል፡፡
የችግሩን ምክንያቶች ከተረዳን አሁን ደግሞ መፍትሄዎቹን እና ልንወስዳቸው የሚገቡ ጥንቃቄዎችን እንመልከት

የፌስቡክ አካውንታችን ከጠላፊዎች ለመጠበቅ የሚረዱ ጥንቃቄዎች እና መፍትሄዎች
1. ጠንካራ የይለፍ ቃል ወይንም ፓስዎርድ ለፌስቡክ አካውንታችን መጠቀም
በቀላሉ ሊገመቱ የማይችሉ ቢያንስ ከ8 ያላነሱ ረዘም ያሉ የተለያዩ ፊደላት፣ቁጥሮች እና ምልክቶችን አጣምረው የያዙ የይለፍ ቃል ወይም ፓስዎርድ መጠቀም የፌስቡክ አካውንታችን ከጠላፊዎች በቀላሉ እንዳይሰረቅ ይረዳናል፡፡
ለምሳሌ next285$@1፣ @85ads#26
ይህን ረጅም እና ድብልቅ ፓስወርድ መጠቀማችን ጠላፊዎች የአካውንታችንን የይለፍ ቃል ለመገመት ስለሚከብዳቸው በቀላሉ ሊሰርቁብን አይቻላቸውም፡፡
2. በተወሰነ ጊዜያት ልዩነት የይለፍ ቃላችንን መቀየር
የይለፍ ቃላችንን በየጊዜው መቀያየራችን የኛን አካውንት ለመስረቅ ሙከራ እያደረገ የነበረ ጠላፊ ካለ የይለፍ ቃላችንን በቀየርን ቁጥር ሲያደርገው የነበረው ሙከራ ሁሉ ከንቱ እየሆነ እንዲቀር ያደርገዋል፡፡ የምንቀይረው አዲሱ የይለፍ ቃል ወይንም ፓስወርድ ቀድሞ ከነበረው ፓስዎርድ ጋር ተቀራራቢ ባይሆን ይመረጣል፡፡ የቀይርነው የይለፍቃል እንዳይረሳን ወይንም እንዳይጠፋብን ፅፎ ማስቀመጡ ተመራጭ ነው፡፡
3. የፌስቡክ አካውንት ለመክፈት የምንጠቀምበት የኢሜል አድራሻ ድብቅ ማድረግ
በቀላሉ ኢሜላችን በጠላፊዎች እንዳይታወቅ ለማድረግ ከፌስቡክ ገፃችን ላይ የኢሜል አድራሻችን በማንም እንዳይታይ መደበቁ አስፈላጊ ነው፡፡ ይህንንም ለማድረግም የሚከተለውን መተግበር ያስፈልጋል
Edit Profile >Contact and Basic Info> email address ከሚለው ጎን Edit የሚለውን መጫን> 'Only Me የሚለውን መምረጥ
ኢሜል አድራሻችን ከኛ ውጪ በማንም እንዳይታይ ካደረግነው ቡሃላም ለጥንቃቄ ለፌስቡክ የምንጠቀምበትን ኢሜል አድራሻ ለሌላ አገልግሎት ባንጠቀም የተሻለ ነው፡፡ በሌሎች ሰዎች የሚታወቅ የኢሜል አድራሻ ምናልባት በጠላፊዎች እጅ ሊገባብን ስለሚችል ማንም የማያውቀው፣ለሌላ አገልግሎት የማንጠቀምበት ፣ፌስቡክ ብቻ ለመጠቀም አገልግሎት ላይ የሚለው ኢሜል አድራሻ ቢኖረን የተሻለ ነው፡፡
በተጨማሪም ለፌስቡክ የምንጠቀምበት የኢሜል አድራሻ ከፌስቡክ ስማችን ጋር የማይመሳሰል ቢሆን ተመራጭ ነው፡፡ ለምሳሌ የፌስቡክ አካውንቴ Abu dawd Osman ሆኖ የኢሜል አድራሻዬም abudawdosman@..... ከሆነ በጠላፊዎች በቀላሊ ሊገመት እና ሊታወቅ ይችላል፡፡
4. የኢሜል እና የፌስቡክ የይለፍ ቃል ወይም ፓስዎርዳችን ተመሳሳይ አለማድረግ
የኢሜል እና የፌስቡክ አድራሻችን የይለፍ ቃሉ የተለያየ ከሆነ የፌስቡክ አካውንታችንን ባጋጣሚ በጠላፊዎች እጅ ቢገባ የኢሜል አድራሻው እስካልተቀየረ ድረስ በኢሜል አድራሻችን አማካኝነት አካውንታችንን ለማስመለስ እድል ይኖረናል፡፡በተጨማሪም ተመሳሳይ የይለፍቃል የሚሆን ከሆነ የፌስቡክ አካውንታችንን ከሰረቁብን በቀላሉ የኢሜል አድራሻችንንም ሊነጥቁን ያስችላቸዋል፡፡
5. ለፌስቡክ አካውንታችን ተጨማሪ የኢሜል አድራሻ ማድረግ
ፌስቡክ ከአንድ በላይ የኢሜል አድራሻ እንዲኖረን የሚፈቅድ ሲሆን ባጋጣሚ አካውንታችን መክፈት ብንቸገር ወይም ቢሰረቅብን አካውንታችንን ዳግም ልናገኝበት የምንችልበትን ኮድ የሚልክበት ተጨማሪ ኤሜል አድራሻ መጨመሩ ጠቃሚ ነው፡፡
ክፍል 1
👍51
ከክፍል 1 የቀጠለ.......
ይህን ለማድረግ General Account Settings የሚለው ውስጥ በመግባት Contact በሚለው ስር Primary Contact እና Add another email or mobile number የሚል ይመጣልናል፡፡ Add another email የሚለውን በመጫን የምንፈልገውን ሁለተኛ ኢሜል አድራሻ እናሰገባለን፡፡ የኛ አድራሻ መሆኑን ለማረጋገጥም በመጀመሪያው የኢሜል አድራሻችን የማረጋገጫ ኮድ ይልክልናል፡፡ እሱን ኤሜል ከፍተን የኛ መሆኑን ካረጋገጥን ቡሃላ ለመጠባበቂያነት ያስገባነው አዲሱ ኤሜል በሙሉነት የኛ አድራሻ ሆኖ አገልግሎት መስጠት ይጀምራል ማለት ነው፡፡
6. ምንነቱ የማይታወቅ ሊንክ አለመክፈት
በውስጥ በኩልም ይሁን ፖስት የተደረገ ምንነቱ ያልታወቀን ሊንክ ለመክፈት መሞከር አደጋ ስለሚኖረው አካውንታችንን ከጠላፊዎች ለመጠበቅ በውስጥ በኩል የሚላክልን ሊንክ ካለ ምንነቱን ሳናረጋገጥ ለመክፈት መሞከር የለብንም፡፡
የፌስቡክ አካውንት ጠላፈዎች የሰዎችን አካውንት በቀላሉ ለመጥለፍ የሚጠቀሙበት ዘዴ አንዱ Phishing ይባላል፡፡ ይህ ዘዴ ከፌስቡክ ድረ ገፅ ጋር ተመሳሳይ እና ተቀራራቢ የሆነ ይዘት ያለው ሊንክ በማዘጋጀት ለመስረቅ ወደታሰበው ሰው የሚላክ ሊንክ ነው፡፡ አንድ ሰው ባለማወቅ ይህን ሊንክ ሲጫን ወደ ፌስቡክ ለመግባት አድራሻ እና የይለፍ ቃል የሚጠይቅበትን የትክክለኛውን የፌስቡክ ድረ ገፅ መግቢያ የተመሳሰለ ገፅ የሚከፍት ሲሆን ትክክለኛው የፌስቡክ ድረ ገፅ መስሎን የፌስቡክ አድራሻችንን እና የይለፍ ቃላችንን ስናስገባ በቀላሉ ዘራፊው የአካውንታችንን አድራሻ እና የይለፍ ቃል በቀላሉ ማወቅ ያስችለዋል፡፡ በዚህም አካውንታችንን በጠላፊዎች እንነጠቃለን፡፡ ከዚህ ዘረፋ ለመጠንቀቅ ምንነቱ የማናውቀውን ሊንክ መክፈት የለብንም፡፡
7. ፌስቡክ ለመጠቀም ስንገባ ትክክለኛው የፌስቡክ ድረ ገፅ መሆኑን ማረጋገጥ
ወደ ፌስቡክ ለመጠቀም ስንገባ ትክክለኛው የፌስቡክ ድረገፅ መሆኑን ማረጋገጥ ይኖርብናል፡፡ ይህን ማድረጋችን ተመሳስለው በጠላፊዎች በተሰሩ ሊንኮች ተሸውደን አካውንታችን በዘራፈዎች እጅ እንዳገባ ለጥንቃቄ ይረዳል፡፡
8. የይለፍ ቃል እንድናስገባ ለሚጠይቀን ነገር ሁሉ አለማስገባት
በትክክለኛው የፌስቡክ ድረ ገፅ ከገባን ቡሃላ ባለማወቅ የነካነው ሊንክ ካለ ወይንም ተልኮልን ለመክፈት ከሞከርን እና ፌስቡክ መጠቀማችንን ለመቀጠል እንደ አዲስ የፌስቡክ አድራሻችንን እና የይለፍ ቃል ወይንም ፓስወርዳችንን እንድናስገባ ከተጠየቅን በፍፁም ማስገባት አይኖርብንም፡፡ የፌስቡክ አካውንት ጠላፊዎች የአካውንታችንን የይለፍ ቃል ለመስረቅ እንዲረዳቸው ያዘጋጁት ወጥመድ ሊሆን ስለሚችል የይለፍቃላችንን እንድናስገባ የሚጠይቀን ሊንክ ከከፈትን በፍፁም ማስገባት አይኖርብንም፡፡ ምክንያቱም ሊንኩ ከላይ የተጠቀሰው በPhishing ዘዴ የተዘጋጀ ሊንክ ሊሆን ይችላልና፡፡
9. ፌስቡክ ተጠቅመን ስንጨርስ Log Out ብሎ መውጣት
ብዙ ጊዜ በስልካችን ስንጠቀም አልያ በኮምፒውተራችን የከፈትነውን ፌስቡክ Log Out ሳንለው እንዲሁ ዘግተን የምንወጣበት ጊዜ በርካታ ነው፡፡ Log Out ሳንል መውጣታችን ለአካውት ጠላፊዎች ምቹ ሁኔታን ይፈጥርላቸዋል፡፡ፌስቡካችንን ሳንዘጋው ወጥተን የግል ሞባይላችንን ሌሎች ሰዎች ካገኙት በቀላሉ አካውንታችንን መውሰድ ይችላሉ፡፡ በተለይ የህዝብ ኢንተርኔት መገልገያ ቦታዎች ላይ ስንጠቀም የይለፍ ቃላችንን Save አለማድረጉን ማረጋገጥ ይኖርብናል፡፡ ጨርሰን ስንወጣም በትክክል Log Out ማለታችንን ማረጋገጥ ተገቢ ነው፡፡ ይህ ካልሆነ እኛ ስንጠቀምበት ከነበረው ኮምፒውተር ጋር በኔትወርክ የተሳሰሩ ኮምፒውተሮች ላይ ሲጠቀም የነበረ ጠላፊ በቀላሉ አካውንታችንን ሊሰርቅብን ይችላል፡፡
10. በፌስቡክ ለጥንቃቄ የተዘጋጀልንን የጥንቃቄ ዘዴዎች መጠቀም
ሀ. Login Notifications፡- ይህ ዘዴ ከሌላ በኩል የፌስቡክ አካውንታችን ከተከፈተ ፌስቡክ ለኛ የሚያሳውቅበት አንዱ መንገድ ነው፡፡ ይህን የምናገኘው Security Settings የሚለው ክፍል ውስጥ በመጀመሪያ ረድፍ ላይ ነው፡፡
Login Alerts የሚለውን ምርጫ ስንጫን Get notifications እና Don't get notifications የሚል ምርጫ ይኖራል፡፡ እኛ Get notifications የሚለውን በመምረጥ ከኛ ውጪ ከሌላ በኩል አካውንታችን ሲከፈት የማሳወቂያ መልዕክት እንዲደርሰን ማድረግ ይቻላል፡፡
ለ. Require Login Approvals :- ይህ ዘዴ እኛ ክምንጠቀምበት ውጪ በሌላ አካል ወይም ብራውዘር የፌስቡክ አካውንታችን ለመክፈት ሙከራ ሲደረግ የማረጋገጫ የይለፍ ቃል እንዲጠይቅ ማስቻያ ዘዴ ነው፡፡ ማንም ሰው የፌስቡክ አካውንታችንን የይለፍ ቃል አውቆ አካውንታችንን ለመክፈት ሙከራ ካደረገ ይህን ዘዴ አገልግሎት ላይ ካዋልነው አካውንቱን ለመክፍ ግዴታ የኛን ፈቃድ ፌስቡክ የሚጠይቅ በመሆኑ የፌስቡክ አድራሻችንን ከጠላፊዎች መጠበቅ ያስችለናል፡፡
ይህን ዘዴ አገልግሎት ላይ ለማዋል Security Settings የሚለው ውስጥ በመግባት ሁለተኛ ረድፍ ላይ የሚገኘውን Login Approvals የሚለውን ምርጫ በመጫን Enable እናደርገዋለን፡፡ ይህን ስናደርግ በሞባይል ቁጥራችንን የስልክ መልዕክት መላኪያን ጨምሮ ሌላ 4 አማራጮች ያመጣልናል፡፡ ከነዚህ አራት አመራጮች ውስጥ የፈለግነውን በመምረጥ አገልግሎቱን ማስጀመር እንችላለን፡፡
በተለይ Text Message (SMS) የሚለው አማራጭ ማንም ሰው አካውንታችንን ለመክፈት ከሞከረ በሌላ በኩል አካውንታችንን ለመክፈት እየሞከረ ያለ አካል መኖሩን በማሳወቅ የኛን ፈቃድ በስልክ ቁጥራችን አማካኝነት ፌስቡክ SMS) በመላክ ፈቃዳችንን እንድንሰጠው አልያ እንድንጠነቀቅ ያስታውቀናል፡፡ በዚህም ለመስረቅ የሞከረው ጠላፊ አካውንታችንን ሳይሰርቀን በፊት ሊሰርቀን እየሞከረ መሆኑን ማወቅ ስለሚያስችለን ለመክፈት የሞከረውን ፈቃድ በመከልከል እንዲሁም የፌስቡክ አካውንት የይለፍ ቃላችንንም ቶሎ በመቀየር ከመዘረፍ መትረፍ እንችላል፡፡
ሐ. App Passwords :- ይህ ዘዴ ፌስቡክ ለመጠቀም የምንጠቀምበት አፕልኬሽን የራሱ የሆነ መግቢያ ኮድ እንዲኖረው ማድረጊያ ዘዴ ነው፡፡
ማንም ሰው የኛን አካውንት ለመክፈት ሲሞክር ይህን እኛ ብቻ የምናውቀውን ኮድ ካላስገባ በስተቀር መክፈት አይችልም፡፡
ይህን ዘዴም ለመጠቀም ከላይ እንደተጠቀሱት ዘዴዎች Security Settings የሚለው ውስጥ በመግባት ሶስተኛ ረድፍ ላይ App Passwords የሚለውን ማግኘት ይቻላል፡፡ በመቀጠልም እሱን ስንጫን Generate app passwords የሚል ምርጫ ያመጣልናል፡፡ ይህን በመጫን የምንጠቀምበትን የፌስቡክ አፕሊኬሽን ኮድ ማስገባት እንችላለን፡፡ ይህን ካደረግን ማንም ሰው የኛን አካውንት የይለፍ ቃል አውቆት ለመክፈት ቢሞክር እንኳን ይህን ኮድ ካላስገባ በስተቀር አካውንታችን አይከፈትለትም፡፡
መ. Your Trusted Contacts፡- ይህ ዘዴ ደግሞ የፌስቡክ አካውንታችን ቢሰረቅ አልያ ለመክፈት ብንቸገር ሊረዱን የሚችሉ 3 የፌስቡክ ጓደኞቻችንን ስም በማስመዝገብ አካውንታችንን ከስርቆት ለማስመለስ አልያ ከገጠመን ችግር ለመውጣት የምንጠቀምበት ዘዴ ነው፡፡
👍39❤5🔥1👏1
ከክፍል 2 የቀጠለ ........
ለምሳሌ የፌስቡክ አካውንታችን ቢሰረቅ ወይንም መክፈት ብንቸገር ለነዚህ ቀድመን አካውንታቸውን ላስመዘገብናቸው ሶስት ሰዎች ፌስቡክ መልዕክት በመላክ ለነሱ የተላከውን ኮድ ለኛ በመስጠት አካውንታችን ዳግም ለመመለስ የምንችልበት ዘዴ ነው፡፡
ይህን የምናገኘው አሁንም እዛው Security Settings ውስጥ ሲሆን ከተዘረዘሩት ውስጥ Your Trusted Contacts የሚለውን በመጫን Choose trusted contacts. የሚለውን በመምረጥ ሶስት የምናምናቸውን የፌስቡክ ጓደኞቻችንን ስም መርጠን በማስገባት አገልግሎት ላይ ማዋል ይቻላል፡፡
ረ. Where You're Logged In ይህ ዘዴ ደግሞ እኛ ፌስቡክ ለመጠቀም የገባንበትን ብራውዘር (Browser) ስም፣ ሰአት፣እና ቦታ የሚነግረን ሲሆን እኛ ከምናውቀው ውጪ ከሌላ በኩል ተከፍቶ ከሆነ ወይም በሌላ በኩል እኛ ሳናውቅ የሚጠቀም ሰው ካለ ይህን ምርጫ ከፍተን በማየት ማወቅ ያስችለናል፡፡
ፌስቡካችንን ለመጠበቅ ይህን አማራጭ ዘወትር በመክፈት ሌላ አካል ሌላ ቦታ አካውንታችን ከፍቶብን እንደሆነ ማረጋገጥ ይቻላል፡፡
ይህንንም አማራጭ Security Settings ውስጥ Where You're Logged In በሚል እናገኘዋለን፡፡ Where You're Logged In የሚለውን ስንጫን እየተጠቀምንበት ያለውን ብራውሰር ይነገረናል፡፡ምናልባትም ከሌላ በኩል ተከፍቶ ከሆነም የተገባበትን ብራውሰር (Browser) ፣ከነቦታው እና ሰአቱ ያስውቀናል፡፡ ለጥንቃቄ ሁሌም ፌስቡክ ተጠቅመንስንጨርሽ ይህን ምርጫ በመክፈት End Activity የሚለውን በመጫን ማፅዳት ይገባል፡፡
ከላይ የተዘረዘሩት መንገዶች የፌስቡክ አካውንታችንን ከጠላፊች ለመታደግ የሚረዱ ዘዴዎች ሲሆኑ በአላህ ፈቃድ የብዙሃኑን የጠላፊዎች ሙከራ ማክሸፍ ያስችላሉ፡፡
©(አቡ ዳውድ ኡስማን)
👍39🥰2
በፍላሽ ዲስካችን የተደበቀን መረጃ እንዴት አድርገን ማውጣት እንችላለን?
Steps: -
1. ፍላሽ ዲስካችሁን ከኮምፒውተራችን ይሰኩ
2. የፍላሽ ዲስኩን letter እይ ለምሳሌ . E ሊሆን ይችላል
3. ኮማንድ ፕሮምፑትን(CMD) ይክፈቱ
5.  CMD/ Command prompt / ከከፈተልን
6. ምሳሌ የፍላሽ Letter E ከሆነ E: ብላችሁ ጽፋችሁ ኢንተርን ይጫኑ ከዛም ወደ ፍላሽ ዲስኩ (E) ይገባል ማለት ነው።
7. ከዛም ይህንን ይጻፉ attrib -s -h /s /d *.*
ከዛ  Enter ይጫኑ በእያንዳንዱ Space(ክፍተት) አለ ለምሳሌ attrib ክፍተት -s ክፍተት -h ክፍተት /s ክፍተት /s ክፍተት *.* በቃ
👍79👏16❤9🔥1
የኮምፒውተራችን እድሜ pc manufacturing date ስንት እንደሆነ ለማወቅ
1. System information በመጠቀም
📌 Search bar ላይ System information ብላችሁ ጻፉ
📌 ክሊክ ስትሉት ከሚመጡት ዝርዝር አማራጮች BIOS Version/date ላይ ኮምፒተሩ የተገጣጠመበትን ቀን ታገኛላችሁ
2. CMD በመጠቀም
📌 አሁንም Search bar ላይ CMD ብላችሁ ጻፉ
📌 open CMD
📌 CMD ሲከፍት systeminfo.exe ወይም systeminfo ብላችሁ ጻፉና ENTER በሉት ከሚመጡት ዝርዝር አማራጮች BIOS Version ላይ ኮምፒተሩ የተገጣጠመበትን ቀን ታገኛላችሁ::
👍46🔥4
የሜሞሪ ስቶሬጅ መለኪያ ከትንሽ
ወደ ትልቅ መጠን በቅደም ተከተል!
8 ቢትስ ↔1 ባይት
1024 ባይት 1 ኪሎ ባይት
1024 ኪሎ ባይት↔ 1ሜጋ ባይት
1024 ሜጋ ባይት 1 ጊጋ ባይት
1024 ጊጋ ባይት↪1 ቴራ ባይት
1024 ቴራ ባይት 1 ፔታ ባይት
1024 ፔታ ባይት↔ 1 ኤክዛ ባይት
1024 ኤክዛ ባይት↪1 ዜታ ባይት
1024 ዜታ ባይት 1 ዮታ ባይት
1024 ዮታ ባይት↪1 ቦርኖቶ ባይት
1024 ቦርኖቶ ባይት 1 ጂኦፕ ባይት
ጂኦፕ ባይት ትልቁ የሜሞሪ ስቶሬጅ መመዘኛ ነው
👍52❤8🔥4
ኮምፒውተርዎ የትኛው ትውልድ እንደሆነ ያውቃሉ?
👍23❤4
በዊንዶውስ 11/10/8/7 ላይ ከሆኑ የኢንቴል ፕሮሰሰርዎ የትኛው ትውልድ እንደሆነ ማወቅ በጣም ቀላል ነው።
🔻🔻🔻🔻ከላይ ያለውን ምስል ይመልከቱ!🔻🔻🔻🔻
የኢንቴል ሲፒዩ ያለበትን ትውልድ የሞዴል ቁጥሩን በመመልከት መለየት ይችላሉ።

የእርስዎ ፒሲ ኢንቴል ሲፒዩ ያለበትን ትውልድ መለየት በጣም ቀላል ነው።
ይህንን እንዴት ማየት እንደሚቻል እነሆ።

Step 1፡ á‰ áŠĽáˆ­áˆľá‹Ž ዊንዶውስ 10 ፒሲ፣ በዴስክቶፕ ላይ ባለው This PC/ Computer Icon ላይ Right Click ያድርጉ እና ከዚያ Properties Click ያድርጉ።

Step 2፡  እዚህ ከታች በምስሉ ላይ እንደምትመለከቱት፣ በስርዓት ክፍሉ ውስጥ፣ Windows 10 የእርስዎን ፕሮሰሰር ሞዴል ቁጥር ያሳያል።
ኢንቴል ሲፒዩ ሞዴል ቁጥሩ i5-5300U የሚለው ሲስተም ፕሮሰሰር ነው።


የኢንቴል ኮር ፕሮሰሰር፣ በትውልድ ምርጥ በሚል በደረጃ የተቀመጡ፡-
📌 8ኛ ትውልድ፣ ከ2017 እስከ 2019 ተለቋል።
📌 9ኛ ትውልድ፣ ከ2018 እስከ 2019 ተለቋል።
📌 10ኛ ትውልድ፣ ከ2019 እስከ 2020 ተለቋል።
📌 11ኛ ትውልድ፣ ከ2020 እስከ 2021 ተለቋል።
✅ ዋና ቅጥያ ትርጉሞች፡-
C፡ የዴስክቶፕ ፕሮሰሰር ከከፍተኛ ደረጃ ግራፊክስ ጋር
F፡ ከፍተኛ ፕሮፎርማንስ ያለው ፕሮሰሰር ከተለየ ግራፊክስ ካርዶች ጋር ጥቅም ላይ የዋለ (ለምሳሌ ለጌም)
H: ከፍተኛ ፕሮፎርማንስ ግራፊክስ
K: ከመጠን በላይ ለመጨረስ ተከፍቷል።
M፡ ሞባይል
Q፡ ባለአራት ኮር
R፡ የዴስክቶፕ ፕሮሰሰር፣ BGA1364 (ሞባይል) ፓኬጅ፣ ባለከፍተኛ ደረጃ ግራፊክስ
S፡ ፕሮፎርማንስ የተመቻቸ ላይፍስታይል
T፡ ለምርጥ የዴስክቶፕ ማስላት በሃይል የተመቻቸ
U: ለላፕቶፕ ውጤታማነት እጅግ በጣም ዝቅተኛ ኃይል
X: ለከፍተኛ የዴስክቶፕ ፕሮፎርማንስ እጅግ በጣም የተከፈተ
Y: በጣም ዝቅተኛ ኃይል

በዚህ የሞዴል ቁጥር፣ ከሰረዙ በኋላ ያለው የመጀመሪያው ቁጥር (አስታውስ፣ ከሰረዙ በኋላ) የሲፒዩ ጀኔሬሽን(ትውልድ) ያመለክታል።
ስለዚህ፣ በዚህ አጋጣሚ፣ የእኔ ሲፒዩ የ5ኛው ትውልድ ነው።
ለምሳሌ፣ የእርስዎ ሲፒዩ ሞዴል ቁጥር i5-5300U ከሆነ፣ የ3ኛው ትውልድ ነው።
የመጀመሪያው ቁጥር ሊሆን የሚችለው 3, 4, 5, 6, 7, 8, 9, 10, ወይም 11 ነው ሊሆን የሚችለው።

ምሳሌ እንመለከታለን!
📌 IntelÂŽ Core™ Processor i7-10710U Processor 10ኛ ትውልድ ነው áˆáŠ­áŠ•á‹Ťá‰ąáˆ 10 á‹¨á‰°á‹˜áˆ¨á‹˜áˆ¨á‹ ከ i7 በኋላ ነው።
📌 IntelÂŽ Core™ Processor i9-9900 á•ሎሰሰር 9ኛ ትውልድ ነው áˆáŠ­áŠ•á‹Ťá‰ąáˆ 9 á‹¨á‰°á‹˜áˆ¨á‹˜áˆ¨á‹ ከ i9 በኋላ ነው።
📌 IntelÂŽ Core™ Processor i7-9850H Processor 9ኛ ትውልድ ነው áˆáŠ­áŠ•á‹Ťá‰ąáˆ 9 á‹¨á‰°á‹˜áˆ¨á‹˜áˆ¨á‹ ከ i7 በኋላ ነው።
📌 Intel® Core™ Processor i5-8600 ፕሮሰሰር 8ኛ ትውልድ ነው ምክንያቱም ቁጥሩ 8 የተዘረዘረው i5 በኋላ ነው።
📌 Intel® Core™ Processor i3-7350K ፕሮሰሰር 7ኛ ትውልድ ነው ምክንያቱም ቁጥር 7 የተዘረዘረው ከ i3 በኋላ ነው።
📌 Intel® Core™ Processor i5-6400T ፕሮሰሰር 6ኛ ትውልድ ነው ምክንያቱም ቁጥሩ 6 የተዘረዘረው i5 በኋላ ነው።
👍65❤9🥰3🤩2🔥1
👁️👁️👁️ አዳ ቲዩብ 👁️👁️👁️
🌐🌐 ከዚህ በታች የ wifi password ማወቂያ የተለያዩ መንገዶችን ይዞልችሁ ቀርቧል።
✅ Wifi password በኮምፒውተር CMD በመጠቀም ማወቅ።
✅ WiFi password በኮምፒውተር control panel በጥቅም ማወቅ።
✅ Wifi password በቀላሉ በስልካችን ማወቅ።
🙏 Wifi password በኮምፒውተር CMD በመጠቀም ማወቅ።
https://youtu.be/AHhn2OLGw9c
🙏 Wifi password በቀላሉ በስልካችን ማወቅ።
https://youtu.be/TnvSkhDiX30
🙏 WiFi password በኮምፒውተር control panel በጥቅም ማወቅ።
https://youtu.be/UzHnsmVDKZU
👍56😁4🔥1
Research SPSS ሶፍትዌሮች ይፈልጋሉ?
ሊንኩን በመጫን ማውረድ ይችላሉ!
SPSS Software
👇👇👇👇
https://t.me/researchRC/68
SPSD cracker
👇👇👇👇
https://t.me/researchRC/69
👍60👎6❤4
ይህንን ላፕቶፕ ይግዙ!
Dell intel core i5
Generation-7th
Storage -1000gb
👇👇👇Join👇👇👇
https://t.me/zanlaptop
https://t.me/zanlaptop
https://t.me/zanlaptop
Ram-4gb ddr4
Inch-15.6
Battery 🔋 5hr
Status dubai used
Address megnagna zefmesh shopping center 3rd floor 322
#ዋጋ 22,500

📞ስ.ቁ #0923479869

One year full warranty
በቅናሽ ኮምፒውተር ይፈልጋሉ?
ZAN የኮምፒውተር የሽያጭ ማእከል
👍👍👍በቅናሽ የሚያገኑበት
🔶 ኦሪጅናል ላፕቶፕ ኮምፒውተር
🔶 ኦሪጅናል ዴስክቶፕ ኮምፒውተር
🔶 ኦሪጅናል ባትሪ
🔶 ኦሪጅናል ቻርጀር
የፈለጉትን በአዲስና በመጠኑ ያገለገሉ እቃዎችን በቅናሽ ዋጋ ማግኘት ይችላሉ!
አድራሻ:- አዲስ አበባ, መገናኛ, ዘፍመሽ ፕላዛ, 3ኛ ፎቅ, 322 ቁጥር
ይደውሉ! Mobile #0923479869
በቴሌግራም ቻናላችን በመግባት እቃዎቻችንን ማግኘት ይችላሉ!.
👇👇👇Join👇👇👇
https://t.me/zanlaptop
https://t.me/zanlaptop
https://t.me/zanlaptop
👍37👎5
የተማሪዎችን ውጤት ለምሳሌ A,B,C,D and F በማለት ግሬድ Computer ላይ በ Microsoft Excel መስራት
የተማሪዎችን ውጤት በ Grading system መስራት እንዴት እንችላለን? Student Mark (Grading System) መታየት ያለበት ቪዲዮ
👇👇👇ይመልከቱት👇👇👇
https://youtu.be/j7FOjQ9YaoE
https://youtu.be/j7FOjQ9YaoE
https://youtu.be/j7FOjQ9YaoE
https://youtu.be/j7FOjQ9YaoE
https://youtu.be/j7FOjQ9YaoE
👍40❤10👎4🔥1
ለተመራቂ ተማሪዎች
ሪሰርች ስትሰሩ ከዚህ በታች የጠቀስኳቸው ከከበዷችሁ ነገ በምርጥ አቀራረብ ቪዲዮ ይዥላችሁ ቀርባለሁ!
✅ Automatic References
✅ Automatic List of tables
✅ Automatic List of figures
✅ Citation እንዴት እንሰራለን?
በምርጥ አቀራረብ በYouTube ተዘጋጅቶ ለእይታ ዝግጁ ነው ከታች ያለውን ሊንክ በመጫን መመልከትና መማር ትችላላችሁ!
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
https://youtu.be/VujbubSHkZs

ከዚህ በታች የዘረዘርኳቸው
✔️ Automatic Tables of Content.
✔️ Page Break እንዴት እንሰራለን? ለሚለው ከታች ያለውን ሊንክ በመጫን ይመልከቱ
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
https://youtu.be/aB-z5uKq75U
~><~~~~
የYouTube ቻናሉን Subscribe በማድረግ ምርጥ ምርጥ ትምህርቶችን ይማሩ!
የ YouTube ቻናል ሊንክ
👇👇👇
https://www.youtube.com/channel/UCZBIP6PqUdmmagdTjbyp_AQ
👍33🥰5😁2
💻 ኮምፒውተር ላይ በአማርኛ እንዴት እንደሚፃፍ ያውቃሉ?ሲጽፉስ ምን ያህል ይፈጥናሉ?
=========================

■ ጠቃሚ መረጃ ነው!! ላልደረሰው ያዳርሱ አሁኑኑ ሼር ያድርጉት፡፡

❖መጀመሪያ ከላይ የለቀቅንላችሁን Software ያወረዱ እና install ያድርጉት ከዛም አማርኛ መፃፍ ስትፈልጉ power ge'ez status phonetic Unicode Mode (ፎ) ላይ ያድርጉት በ English መፃፍ ስትፈልጉ ደግሞ power ge'ez status English Mode (ኢ) ላይ አድርጉት ከዛም የሚከተሉትን ኣጭር መግላጫ በትክክል ይመልከቱ።
⁉️ ሶፍትዌሩን ለማግኘት ከፈለጋችሁ ከቴግራም ቻናሌ ማግኘት ትችላላችሁ
👇👇👇👇👇👇👇👇👇 https://t.me/MuhammedComputerTechnology
◕ሀ➭H_ሁ➭Hu_ሂ➭Hi_ሃ➭Ha_ሄ➭Hy_ህ➭He_ሆ➭Ho

◕ለ➭L_ሉ➭Lu_ሊ➭Li_ላ➭La_ሌ➭Ly_ል➭Le_ሎ➭Lo

❖ሐ➭Shift+h_ሑ➭Shift+hu_ሒ➭Shift+hi_ሓ➭Shift+ha_ሔ➭Shift+hy_ሕ➭Shift+he_ሖ➭Shift+ho

◕መ➭M_ሙ➭Mu_ሚ➭Mi_ማ➭Ma_ሜ➭My_ም➭Me_ሞ➭Mo

❖ሠ➭Shift+s_ሡ➭Shift+su_ሢ➭Shift+si_ሣ➭Shift+sa_ሤ➭Shift+sy_ሥ➭Shift+se_ሦ➭Shift+so

◕ረ➭R_ሩ➭Ru_ሪ➭Ri_ራ➭Ra_ሬ➭Ry_ር➭Re_ሮ➭Ro

◕ሰ➭S_ሱ➭Su_ሲ➭Si_ሳ➭Sa_ሴ➭Sy_ስ➭Se_ሶ➭So

❖ሸ➭Shift+s_ሹ➭Shift+su_ሺ➭Shift+si_ሻ➭Shift+sa_ሼ➭Shift+sy_ሽ➭Shift+se ሾ➭Shift+so

◕ቀ፡➭Q ቁ፡➭Qu ቂ፡➭Qi ቃ፡➭Qa ቄ፡➭Qy ቅ፡➭Qe ቆ፡➭Qo

◕በ፡➭B ቡ፡➭Bu ቢ፡➭Bi ባ፡➭Ba ቤ፡➭By ብ፡➭Be ቦ፡➭Bo

◕ተ፡➭T ቱ፡➭Tu ቲ፡➭Ti ታ፡➭Ta ቴ፡➭Ty ት፡➭Te ቶ፡➭To

◕ ቸ፡➭C ቹ፡➭Cu ቺ፡➭Ci ቻ፡➭Ca ቼ፡➭Cy ች፡➭Ce ቾ፡➭Co

◕ነ፡➭N ኑ፡➭Nu ኒ፡➭Ni ና፡➭Na ኔ፡➭Ny ን፡➭Ne ኖ፡➭No

❏ኘ፡➭Shift +n ኙ፡➭Shift +nu ኚ➭Shift+ni ኛ፡➭Shift +na ኜ፡➭Shift +ny ኝ፡➭Shift + ne ኞ፡➭Shift +no

◕ከ፡➭Ka ኩ፡➭Ku ኪ፡➭Ki ካ፡➭Ka ኬ፡➭Ky ክ፡➭Ke ኮ፡➭Ko

❖ ኸ ☛capslock + Shift + h
ኹ ☛capslock + Shift + hu
ኺ ☛capslock + Shift + hi
ኻ ☛Capslock + Shift + ha
ኼ ☛Capslock + Shift + hy
ኽ ☛Capslock + Shift + he
ኾ ☛Capslock + Shift + ho

❏ኀ፡➭ Capslock + H ኁ፡➭ Capslock + HU ኂ፡➭Capslock + HI ኃ፡➭Capslock + HA ኄ፡➭Capslock + HY ኅ፡➭Capslock + HE ኆ፡➭Capslock + HO

❏አ፡➭Capslock X ኡ፡➭Xu ኢ፡➭Xi ኣ፡➭Xa ኤ፡➭Xy እ፡➭Xe ኦ፡➭XoDe

❖ዐ፡➭Shift +x ዑ፡➭Shift +xu ዒ➭Shift +xi ዓ፡➭Shift +xa ዔ➭Shift +xy ዕ፡➭Shift +xe ዖ➭Shift +xo

✪ወ፡➭W ዉ፡➭Wu ዊ፡➭Wi ዋ፡➭Wa ዌ፡➭Wy ው፡➭We ዎ፡➭wo

✪ዘ፡➭Z ዙ፡➭Zu ዚ፡➭Zi ዛ፡➭Za ዜ፡➭Zy ዝ፡➭Ze ዞ፡➭Zo

❏ዠ፡➭Shift + Z ዡ፡➭Shift + Zu ዢ፡➭Shift + Zi ዣ፡➭Shift +Zaዤ፡➭Shift + Zy ዥ፡➭Shift +Ze ዦ፡➭Shift + Zo

✪ፈ፡➭F ፉ➭Fu ፊ፡➭Fi ፋ፡➭Fa ፌ፡➭Fy ፍ፡➭Fe ፎ፡➭Fo

✪ ፐ፡➭P ፑ፡➭Pu ፒ፡➭Pi ፓ፡➭Pa ፔ፡➭Py ፕ፡➭Pe ፖ፡➭Po

✪ገ፡➭G ጉ፡➭Gu ጊ፡➭Gi ጋ፡➭Ga ጌ፡➭Gy ግ፡➭Ge ጎ፡➭Go

✪ደ፡➭D ዱ፡➭Du ዲ፡➭Di ዳ፡➭Da ዴ፡➭Dy ድ፡➭ዶ፡Do

❏ጠ፡➭Shift + t ጡ፡➭Shift + tu ጢ፡➭Shift + ti ጣ፡➭Shift+ta ጤ፡➭Shift + ty ጥ፡➭Shift + te ጦ፡➭Shift + to

❏ጨ፡➭Shift +c ጩ፡➭Shift +cu ጪ፡➭Shift +ci ጫ፡➭Shift+caጬ፡➭Shift +cy ጭ፡➭Shift +ce ጮ: ➭Shift +co

❏ጸ፡➭Capslock + t ጹ፡➭Capslock + tu ጺ፡➭Capslock + ti ጻ፡➭Capslock + ta ጼ፡➭Capslock + ty ጽ፡➭Capslock + t ጾ፡➭Capslock + to

❖ ፀ➭☞Capslock+Shift+t
ፁ➭☞Capslock+Shift+tu
ፂ➭☞Capslock + Shift + ti
ፃ➭☞Capslock + Shift + t
ፄ➭☞Capslock + Shift + ty
ፅ➭☞Capslock + Shift + te
ፆ➭☞Capslock + Shift + to

✪ጀ፡➭J ጁ፡➭Gu ጂ፡➭Ji ጃ፡➭Ga ጄ፡➭Gy ጅ፡➭Ge ጆ፡➭Jo

✪ቨ፡➭V ቩ፡➭Vu ቪ፡➭Vi ቫ፡➭Va ቬ፡➭Vy ቭ፡➭Ve ቮ፡➭Vo
▁▁▁▁▁▁▁▁▁▁

ቋ➭Capslock+qwa ቧ➭Capslock+bwa
ቷ➭Capslock+twa
ኟ➭Capslock +Shift+nwa
ቿ➭Capslock+cwa ሟ➭Capslock+mwa
ቷ➭Capslock+twa ጓ➭Capslock gwa
ፏ➭Capslock+fwa ሯ➭Capslock +rwa ዷ➭Capslock+dwa ቯ➭Capslock+vwa ኋ➭Capslock+hwa ዟ➭Capslock+zwa ዧ➭Capslock+Shif+zwa
ኗ➭Capslock+nwa ሏ➭Capslock+lwa
ኳ➭Capslock+kwa ሷ➭Capslock+swa
ጇ➭Capslock+jwa ጧ➭Capslock+twa

♨️የተቸገሩ ሰዎችን በጣም ይጠቅማቸዋል አሁኑኑ ሼር ያድርጉ፡፡
━━━━━━ ⊙ ━━━━━━
👍155❤35👏8🥰5🔥4👎2🎉2🤔1