Muhammed Computer Technology (MCT)
38.3K subscribers
496 photos
7 videos
229 files
839 links
🔴አድራሻ:-
ስ.ቁ: 0929273364
ዌብሳይት www.mctplc.com
ቴሌግራም አካውንት: https://t.me/mctplc
email: mct16plc@gmail.com
ቲክቶክ አካውንት tiktok.com/@mctplc
Download Telegram
የት/ት ፍኖተ ካርታ የሚጀምሩ የመጀመሪያ ደረጃ ከ1ኛ-6ኛ ክፍል የክ/ጊዜ ብዛት::
====================
😁አንድ ክ/ጊዜ 40 ደቂቃ አለው፡፡
😁በቀን 6 ክ/ጊዜ
😁በሳምንት 30 ክ/ጊዜ
😁የት/ት ሰዓት ከጥዋቱ 2:15-6:30 የጥዋት ሸፍት ከ6:45-11:00 የከሠዓት ሸፍት ሆኖ 15 ደቂቃ ዕረፍት አለው፡፡
😁የት/ት ሠዓት በየሸፍቱ 4ሰዓት ነው፡፡
😁በየት/ት አይነቱ የክ/ጊዜ ብዛት:-
====================
😁1ኛ= የአፍ መፍቻ ቋንቋ የሳምንት ክ/ጊዜ ብዛት 4 ፣የሳምንት የት/ት ሠዓት 2 ሰዓት ከ40 ደቂቃ እና የዓመቱ ሰዓት 104 ሰዓት ነው፡፡
😁2ኛ= አገር አቀፍ ቋንቋ ክ/ጊዜ 3፣ በሳምንት 2ሠዓት እና በአመት78 ሠዓት አለው፡፡
😁3ኛ= እንግሊዘኛ የሳምንት ክ/ጊዜ 4 ፣ የሳምቱ ሠዓት 2ሰዓት ከ40ደቂቃ እና የአመቱ 104 ሰዓት አለው፡፡
😁4ኛ= ሂሳብ በሳምንት5 ክ/ጊዜ በሳምንት 3ሰዓት ከ20ደቂቃ እና በዓመት130ሰዓት አለው፡፡
😁5ኛ= አካባቢ ሳይንስ በሳምንት 5 ክ/ጊዜ፤ በሳምንት 3ሰዓት ከ20ደቂቃ እና በዓመት 130 ሰዓት አለው፡፡
😁6ኛ= የግብረገብ ት/ት በሳምንት 3 ክ/ጊዜ፣ በሳምንት 2ሰዓት እና በዓመት 78ሰዓት አለው፡፡
😁7ኛ= የሙያ ት/ት በሳምን 3 ክ/ጊዜ ፣ በሳምንት 2ሰዓት እና በዓመት 78ሰዓት አለው፡፡
😁8ኛ= የሰውነት ማጎልመሻ ት/ት በሳምንት 3ክ/ጊዜ፣ በሳምንት 2ሰዓት እና በዓመት 78ሰዓት አለው፡፡
😁በአጠቃላይ በሳምንት 30 ክ/ጊዜ ወይም 20 ሰዓት እና በዓመት 780 ሰዓት አለው:: ስለሆነም የት/ት አመታዊ እቅድ በዚህ ስሌት መሠረት ይዘጋጀል፡፡
😁መልካም የት/ት ዘመን!!!
👍41
የኮምፒዉተራችን storage space ሲሞላብን እንዴት ማስለቀቅ እንችላለን
የኮምፒዉተርዎ storage space ሞልቶበት ተቸግረዋል፡፡ እንግዲያዉስ የሚከተሉትን ምክሮች ይከተሉ
1. ለብዙዎች እፎይታን የሰጠ መፍትሔ ሲሆን የኮምፒዉተራችንን ስቶሬጅ የሞሉብንን የተለያዩ ፋይሎች በማጥፋት ብዙ ትርፍ storage space እንዲኖረን ያስችለናል፡፡ ኮምፒዉተራችን ላይ የማንጠቀምባቸዉ እና የማይጠቅሙን ጊዜያዊ ፋይሎችን (temporary files) በማጥፋት ኮምፒዉተራችን ላይ ብዙ ቦታ እንዲኖረን ያስችለናል፡፡
Delete unnecessary temporary file
Start menu ላይ right click አድርጎ run የሚለውን መምረጥ አልያም window key እና R ን ከ ኪቦርዳችን ላይ አንድ ላይ መጫን
%temp% ብሎ ጽፎ enter መጫን
የሚመጣላቹ folder ላይ ያሉ ፋይሎችንctrl + A ተጭነን ሁሉንም ሲመርጥልን ማጥፋት
ድጋሚ run ቦክሱን ከፍታቹ temp ብሎ መጻፍ ከሚመጣላቹ folder ውስጥ ያሉ ፋይሎችን ሁሉ ማጥፋት
አሁንም ለ ሶስተኛ ጊዜ run ቦክስ ላይ prefetch ብሎ መጻፍ የሚመጣላቹ folder ውስጥ የሚገኙ ፋይሎችን ማጥፋት።
እነዚህን የምናጠፋበት ምክንያት ጊዜያዊ እና space የያዙ ፋይሎች ስለሆኑ ነው። ምንም አይነት ችግር አያመጡም።
2. የማንጠቀምባቸዉን ፕሮግራሞች Uninstall ማድረግ
አብዛኞቹ ኮምፒዉተር ተጠቃሚዎች የኮምፒዉተራቸዉን ቦታ የሚያጣብባቸዉ የጫኗቸዉ ሶፍትዌሮች እና ጌሞች ናቸዉ፡፡ የማንጠቀምባቸዉን ሶፍትዌሮች Uninstall በማድረግ ቦታ መቆጠብ እንችላለን፡፡ ከኮምፒዉተሮ ላይ የማይፈልጉትን ሶፍትዌር ለማጥፋት የሚከተሉትን ቅደምተከተሎች ይከተሉ፡-
1. Start -> Control Panel -> Uninstall a program
2. ብዙ ቦታ የያዘዉን ሶፍትዌር ለማወቅ በ size ቅደም ተከተል ይደርድሯቸዉ፡፡
3. ማጥፋት የፈለጉትን ሶፍትዌር መርጠዉ Uninstall የሚለዉን ይጫኑ፡፡
3. የተደጋገሙ ፋይሎችን ያጥፉ
ዊንዶዉስ በራሱ የተደገሙ ፋይሎችን ለይቶ የሚያጠፋ ሲስተም የለዉም ስለዚህ ይህንን ስራ የሚሰሩ ሶፍትዌሮችን መጫን ይኖርብናል፡፡ ይህንን የሚያደርጉ የተለያዩ ሶፍትዌሮች አሉ፡፡ ከነዚህም ዉስጥ Duplicate Sweeper አንዱ ነዉ፡፡ Duplicate Sweeper ኮምፒዉተራችን ላይ ያሉ የተደጋገሙ ፋይሎችን scan አድርጎ ያቀርብልናል፡፡ እኛም ከዘ ዉስጥ የተደገሙ መሆናቸዉን እያረጋገጥን ማጥፋት እንችላለን፡፡
4. ጊዜያዊ ፋይሎች (Temporary Files)
በ Windows Disk Cleanup አማካኝነት ጊዜያዊ ፋይሎችን እንዴት ማጥፋት እንደምንችል አይተናል፡፡ ነገርግን Windows Disk Cleanup ሊያገኛቸዉ የማይችሉ እንደ browser ያሉ የጫንናቸዉ ሶፍትዌሮች የፈጠሩትን ጊዜያዊ ፋይሎች ለማጥፋት የሚያስችለን ሌላ መንገድ Google Chrome ን እንደ ምሳሌ በመዉሰድ እናያለን፡፡
1. Google Chrome ን ይክፈቱ
2. settings menu ይክፈቱ
3. More tools የሚለዉን ይምረጡ
4.Clear Browsing data የሚለዉ ዉስጥ በመግባት ማጥፋት የሚፈልጉትን ጊዜያዊ ፋይል
መርጠዉ ያጥፉ
5. Recycle Bin ዉስጥ ያሉ ፋይሎችን ያጥፉ
ከኮምፒዉተራችን ላይ ያጠፋናቸዉ ፋይሎች permanently delete ካላደረግናቸዉ መልሰን ብንፈልጋቸዉ ማግኘት እንድንችል Recycle Bin ዉስጥ ይቀመጣሉ፡፡ ከላይ ባሉት መንገዶች ያጠፋናቸዉ ፋይሎችም Recycle Bin ዉስጥ ሊቀመጡ ይችላሉ፡፡ እነዚህ Recycle Bin ያሉ ፋይሎች ግን ከኮምፒዉተራችን ላይ የያዙትን storage space እንደያዙ ነዉ የሚቆዩት፡፡ ስለዚህ storage space ለማስለቀቅ እነዚህን የማንፈልጋቸዉ ፋይሎች ከRecycle Bin ዉስጥ ማጥፋት ይኖርብናል፡፡
➤➤➤➤➤➤➤➤➤➤➤➤➤➤➤➤
ይህ መረጃ ጠቃሚ እንደሆነ ተስፋ አደርጋለሁ!
አመሰግናለሁ!
➤➤➤➤➤➤➤➤➤➤➤➤➤➤➤➤
👍8😁2
የት/ት ፍኖተ ካርታ የሚጀምሩ መካከለኛ የመጀመሪያ ደረጃ ከ7ኛ-8ኛ ክፍል የክ/ጊዜ ብዛት::
====================
😁አንድ ክ/ጊዜ 40 ደቂቃ አለው፡፡
😁በቀን 6 ክ/ጊዜ
😁በሳምንት 30 ክ/ጊዜ
😁የት/ት ሰዓት ከጥዋቱ 2:15-6:30 የጥዋት ሸፍት ከ6:45-11:00 የከሠዓት
ሸፍት ሆኖ 15 ደቂቃ ዕረፍት አለው፡፡
😁የት/ት ሠዓት በየሸፍቱ 4ሰዓት ነው፡፡
በየት/ት አይነቱ የክ/ጊዜ ብዛት:-
====================
😁1ኛ= የአፍ መፍቻ ቋንቋ የሳምንት ክ/ጊዜ ብዛት 2 ፣የሳምንት የት/ት ሠዓት 1 ሰዓት ከ20 ደቂቃ እና የዓመቱ ሰዓት 52 ሰዓት ነው፡፡
😁2ኛ= አገር አቀፍ ቋንቋ ክ/ጊዜ 2፣ በሳምንት 1ሠዓት ከ20 ደቂቃ እና በአመት52 ሠዓት አለው፡፡
😁3ኛ= እንግሊዘኛ የሳምንት ክ/ጊዜ 4 ፣ የሳምቱ ሠዓት 2ሰዓት ከ40ደቂቃ እና የአመቱ 104 ሰዓት አለው፡፡
😁4ኛ= ሂሳብ በሳምንት4 ክ/ጊዜ በሳምንት 2ሰዓት ከ40ደቂቃ እና በዓመት104ሰዓት አለው፡፡
😁5ኛ= አጠቃላይ ሳይንስ በሳምንት 4 ክ/ጊዜ፤ በሳምንት 2ሰዓት ከ40ደቂቃ እና በዓመት 104 ሰዓት አለው፡፡
😁6ኛ= የህብረተሰብ ት/ት በሳምንት 3 ክ/ጊዜ፣ በሳምንት 2ሰዓት እና በዓመት 78ሰዓት አለው፡፡
😁7ኛ= የስነ-ዜጋ ት/ት በሳምን 3 ክ/ጊዜ ፣ በሳምንት 2ሰዓት እና በዓመት 78ሰዓት አለው፡፡
😁8ኛ= የጥበብ ስራ ት/ት በሳምንት 2 ክ/ጊዜ፣ በሳምንት 1ሰዓት ከ20 ደቂቃ እና በዓመት 52ሰዓት አለው፡፡
😁9ኛ=የአይቲ ት/ት በሳምንት 2ክ/ጊዜ በሳምንት 1ሰዓት ከ20ደቂቃ እና በዓመት 52 ሰዓት አለው፡፡
😁10ኛ=የሰውነት ማጎልመሻ በሳምንት 2ክ/ጊዜ (1ሰዓት ከ20ደቂቃ) እና በዓመት 52 ሰዓት አለው፡፡
😁11ኛ=የሙያ(የእጅ) ስራ በሳምንት 2 ክ/ጊዜ (1ሰዓት ከ20 ደቂቃ) እና በዓመት 52 ሰዓት አለው፡፡
😁በአጠቃላይ በሳምንት 30 ክ/ጊዜ ወይም 20 ሰዓት እና በዓመት 780 ሰዓት አለው:: ስለሆነም የት/ት አመታዊ እቅድ በዚህ ስሌት መሠረት ይዘጋጀል፡፡
መልካም የት/ት ዘመን!!!
👍1
የት/ት ፍኖተ ካርታ የሚጀምሩ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤቶች (ከ9ኛ-10ኛ ክፍል) የክ/ጊዜ ብዛት::
====================
😁አንድ ክ/ጊዜ 40 ደቂቃ አለው፡፡
😁በቀን 6 ክ/ጊዜ
😁በሳምንት 30 ክ/ጊዜ
😁የት/ት ሰዓት ከጥዋቱ 2:15-6:30 የጥዋት ሸፍት ከ6:45-11:00 የከሠዓት ሸፍት ሆኖ 15 ደቂቃ ዕረፍት አለው፡፡
😁የት/ት ሠዓት በየሸፍቱ 4ሰዓት ነው፡፡
*በየት/ት አይነቱ የክ/ጊዜ ብዛት:-
====================
😁1ኛ= የእንግሊዘኛ= የሳምንት ክ/ጊዜ ብዛት 3 ፣የሳምንት የት/ት ሠዓት 3 ሰዓት እና የዓመቱ የት/ት 78 ሰዓት ነው፡፡
😁2ኛ= ሒሳብ =በሳምንት 4 ክ/ጊዜ ( 2ሠዓት ከ40 ደቂቃ) እና በአመት 104 ሠዓት አለው፡፡
😁3ኛ= ባዮሎጂ =በሳምንት 3ክ/ጊዜ (2ሰዓት) እና የአመቱ 78 ሰዓት አለው፡፡
😁4ኛ= ኬሚስትሪ በሳምንት3 ክ/ጊዜ በሳምንት 2ሰዓት እና በዓመት 78 ሰዓት አለው፡፡
😁5ኛ= ፊዚክስ በሳምንት 3 ክ/ጊዜ፤ በሳምንት 2ሰዓት እና በዓመት 78 ሰዓት አለው፡፡
😁6ኛ= ጂኦግራፊ በሳምንት 2 ክ/ጊዜ፣ በሳምንት 1ሰዓት ከ20 ደቂቃ እና በዓመት 52 ሰዓት አለው፡፡
😁7ኛ= ታሪክ ት/ት በሳምን 2 ክ/ጊዜ ፣ በሳምንት 1ሰዓት ከ20 ደቂቃ እና በዓመት 52 ሰዓት አለው፡፡
😁8ኛ= ሲቪክስ በሳምንት 2 ክ/ጊዜ፣ በሳምንት 1ሰዓት ከ20 ደቂቃ እና በዓመት 52ሰዓት አለው፡፡
😁9ኛ=የአይቲ ት/ት በሳምንት 2ክ/ጊዜ በሳምንት 1ሰዓት ከ20ደቂቃ እና በዓመት 52 ሰዓት አለው፡፡
😁10ኛ=ኢኮኖሚክስ በሳምንት 2ክ/ጊዜ (1ሰዓት ከ20ደቂቃ) እና በዓመት 52 ሰዓት አለው፡፡
*ንዑስ ድምር:-
========
የሳምንት ክ/ጊዜ 26 (17ሰዓት ከ20 ደቂቃ) እና በዓመት 676 ሰዓት ይሆናል፡፡
*ተጨማሪ አማራጭየት/ት አይነቶች:-
===================
😁1ኛ=የአፍ መፍቻ ቋንቋ በሳምንት 2ክ/ጊዜ (1ሰዓት ከ20ደቂቃ) እና በዓመት 52 ሰዓትአለው፡፡
2ኛ=አገር አቀፍ ቋንቋ በሳምንት 2ክ/ጊዜ (1ሰዓት ከ20ደቂቃ) እና በዓመት 52 ሰዓት አለው፡፡
😁3ኛ=የውጭ ቋንቋ በሳምንት 2ክ/ጊዜ (1ሰዓት ከ20ደቂቃ)እና 52ሰዓት አለው፡፡
😁4ኛ=የሰውነት ማጎልመሻ በሳምንት 2ክ/ጊዜ (1ሰዓት ከ20ደቂቃ) እና በዓመት 52ሰዓት አለው፡፡
😁5ኛ=የሙያ ት/ት በሳምንት 2ክ/ጊዜ (1ሰዓት ከ20ደቂቃ) እና በዓመት 52 ሰዓት አለው::
ንዑስ ድምር በሳምንት 4ክ/ጊዜ (2ሰዓት ከ40 ደቂቃ)እና በዓመት 104 ሰዓትአለው
*በአጠቃላይ ድምር:-
=========================
በሳምንት 30 ክ/ጊዜ ወይም 20 ሰዓት እና በዓመት 780 ሰዓት አለው:: ስለሆነም የት/ት አመታዊ እቅድ በዚህ ስሌት መሠረት ይዘጋጀል፡፡
😁መልካም የት/ት ዘመን!!!
👍6
የት/ት ፍኖተ ካርታ የሚጀምሩ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤቶች (ከ11ኛ-12ኛ ክፍል) ሶሻል ዲፓርትመንት የክ/ጊዜ ድልድል:
====================
😁አንድ ክ/ጊዜ 45 ደቂቃ አለው፡፡
😁በቀን 7 ክ/ጊዜ
😁በሳምንት 35 ክ/ጊዜ
😁የት/ት ሠዓት በየፈራቃው 4ሰዓት ከ40 ደቂቃ ነው፡፡
😁በየት/ት አይነቱ የክ/ጊዜ ብዛት:-
====================
$ ቋንቋ እና ሶሻል ሳይንስ ት/ት ክፍል!
=====================
😁1ኛ= የእንግሊዘኛ ቋንቋ የሳምንት ክ/ጊዜ ብዛት 4 ፣የሳምንት የት/ት ሠዓት 3 ሰዓት እና የዓመቱ የት/ት 117 ሰዓት ነው፡፡
😁2ኛ= ሒሳብ ክ/ጊዜ 4፣ በሳምንት 3ሠዓት እና በአመት 117 ሠዓት አለው፡፡
😁3ኛ= ጂኦግራፊ የሳምንት ክ/ጊዜ 3 ፣ የሳምቱ ሠዓት 2ሰዓት ከ15 ደቂቃ እና የአመቱ 87 ሰዓት ከ45 ደቂቃ አለው፡፡
😁4ኛ= ኢኮኖሚክስ በሳምንት 3 ክ/ጊዜ፣ በሳምንት 2ሰዓት ከ15 ደቂቃ እና በዓመት 87 ሰዓት ከ45 ደቂቃ አለው፡፡
😁5ኛ= ታሪክ ት/ት በሳምን 3 ክ/ጊዜ ፣ በሳምንት 2ሰዓት ከ15 ደቂቃ እና በዓመት 87 ሰዓት ከ45 ደቂቃ አለው፡፡
😁ኛ6=የአይቲ ት/ት በሳምንት 3ክ/ጊዜ በሳምንት 2ሰዓት ከ15ደቂቃ እና በዓመት 87 ሰዓት ከ45 ደቂቃ አለው፡፡
ቋሚ የት/ት አይነቶች ክ/ጊዜ ብዛት ድምር=20ሲሆን:-
በዚህ ዘርፍ ፊልድ (የሙያ) ተጨማሪ አማራጭ የት/ት አይነቶች:-
===================
😁1ኛ=የአፍ መፍቻ ቋንቋ እና ስነ ጽሑፍ በሳምንት 4ክ/ጊዜ (3ሰዓት ) እና በዓመት 117 ሰዓት አለው፡፡
😁2ኛ=ማህባራዊ ስራ በሳምንት 4ክ/ጊዜ (3 ሰዓት ) እና በዓመት 117 ሰዓት አለው፡፡
😁3ኛ=ስነ ሰብ በሳምንት 4ክ/ጊዜ (4ሰዓት) እና 117ሰዓት አለው፡፡
😁4ኛ=ሰነ-ዜጋ በሳምንት 3ክ/ጊዜ (3ሰዓት) እና በዓመት 117ሰዓት አለው፡፡
የፊልድ ክ/ጊዜ ድምር 15 ክ/ጊዜ ነው፡፡
😁 በአጠቃላይ በሳምንት 35 ክ/ጊዜ ወይም 26ሰዓት ከ15 ደቂቃ እና በዓመት 1023 ሰዓት ከ45 ደቂቃ አለው::
$ ቢዝናስ የት/ት ክፍል የክ/ጊዜ ድልድል:-
==================
😁1ኛ=እንግሊዘኛ በሳምንት 4ከ/ጊዜ (3ሰዓት) እና በዓመት 117ሰዓት ነው፡፡
😁2ኛ=ሒሳብ በሳምንት 4ክ/ጊዜ (3ሰዓት) እና በዓመት 117ሰዓት አለው፡፡
😁3ኛ=ጂኦግራፊ በሳምንት 3ክ /ጊዜ (2ሰዓት:ከ15 ደቂቃ) እና በዓመት 78 ሰዓት ከ45ደቂቃ አለው፡፡
😁4ኛ=ታሪክ በሳምንት 3ክ/ጊዜ (2ሰዓት 15ደቂቃ) እና በዓመት 78ሰዓት ከ45 ደቂቃ አለው፡፡
😁5ኛ=ኢኮኖሚክስ በሳምንት 3ክ/ጊዜ (2ሰዓትከ15 ደቂቃ) እና 78ሰዓት ከ45ደቂቃ አለው፡፡
😁6ኛ=ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ በሳምንት 3ክ/ጊዜ (2ሰዓት ከ15ደቂቃ) እና 78ሰዓት ከ45ደቂቃ አለው፡፡
😁ስለዚህ ቋሚ የት/ት አይነቶች ክ/ጊዜ ብዛት ድምር 20 ነው፡፡
በዚህ ዘርፍ የሙያ ፊልድ ተጨማሪ የት/ት አይነቶች:-
😁1ኛ=አካውንቲንግ እና ፋይናንስ በሳምንት 3ክ/ጊዜ (2ሰዓት ከ15ደቂቃ) እና 78ሰዓት ከ45ደቂቃ አለው::
😁2ኛ=ባንኪንግ እና ኢንሹራንስ በሳምንት 3ክ/ጊዜ (2ሰዓትከ15ደቂቃ) እና 78ሰዓት ከ45ደቂቃ አለው፡፡
😁3ኛ=የቢሮ አስተዳደር በሳምንት 3ክ/ጊዜ (2ሰዓትከ15 ደቂቃ) እና 78ሰዓት ከ45ደቂቃ አለው፡፡
😁4ኛማርኬቲንግ በሳምንት 3ክ/ጊዜ 2ሰዓት ከ15 ደቂቃ እና በዓመት 78 ሰዓት ከ45 ደቂቃ አለው፡፡
😁5ኛ=ሆቴልና ቱሪዝም በሳምንት 3ክ/ጊዜ (2ሰዓት ከ15ደቂቃ) እና 78ሰዓት ከ45 ደቂቃ ሲኖራው በድምሩ የሙያ ዘርፍ 15ክ/ጊዜ ይይዘል::
በአጠቃላይ በሳምንት 35ክ/ጊዜ (26ሰዓትከ15ደቂቃ) እና በዓመት 1023 ሰዓት ከ45ደ ቂቃ አለው፡፡
ስለሆነም የት/ት አመታዊ እቅድ በዚህ ስሌት መሠረት ይዘጋጀል፡፡
😁መልካም የት/ት ዘመን!!!
👍3👏1🤩1
የጥንቃቄ መልእክት ለሞባይል ባንኪንግ ተጠቃሚወች ።
ሼር በማድረግ ማህበረሰባችንን ከዚህ ጥፋት እንታደግ!
አጭበርባሪወች የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሞባይል ባንኪንግ ተጠቃሚ የሆኑ ግለሰቦችን ስልክ ቁጥር በተለያየ መንገድ ካገኙ በኋላ ፤ የባንክ ቁጠባ እድለኞች ሽልማት የደረሳቸው በማስመሰል ሜሴጅ ይልካሉ ፤

በተጨማሪም ወድያውኑ በስልካቸው ደውለው እርስዎ የወሩ የባንካችን እድለኛ ነዎት በመሆኑም በሽልማት የደረሰዎት 300,000 ሺ ብር በአካውንትዎ ገቢ እንዲሆንልዎ መጀመሪያ የሞባይል ባንኪንግ ተጠቃሚ ከሆኑ *889# ብለው ያስገቡ በመቀጠል ስንደውልልዎ የራስዎን ሚስጥር ቁጥር (pin code) ያስገቡ በሚል አጭበርባሪወች እራሳቸው የባንክ ሰራተኛ መስለው ካልኩሌሽኑን በስልክ ይመራሉ ፤

በመቀጠል በግለሰቦች አካውንት ያለውን ገንዘብ በሙሉ ወደ እራሳቸው አካውንት በማዞርና ወዲያውኑ ገቢ ያደረጉትን ገንዘብ በማውጣት እየተሰወሩ ከፍተኛ ዘረፋ እየፈፀሙ ስለሆነ ፤ ማንኛውም ሰው ባንክ እየገባ ትክክለኛነቱን ሳያረጋግጥ በስልክ ጥሪ ብቻ እየተታለለ ገንዘቡን እንዳይበላና ተገቢውን ጥንቃቄ እንዲያደርግ እናሳስባለን ።
!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!
( መረጃውን ያደረሰን የምስራቅ ጎጃም ዞን ፓሊስ መምሪያ የወንጀል መረጃና ክትትል ዋና ክፍል ነው )
እንዲሁም ከዚህ በፊት የለቀቅኳቸውን ቪዲዮዎችን ብትከታተሉ ምርጥ እውቀትን ልታገኙ ትችላላችሁ
አሁንም የቴሌግራምና የYouTube ቻናሌን Subscribe በማድረግ ድጋፋችሁን አሳዩኝ።
#ያወቁትን ማሳወቅ ብልህነት ነው!

የ YouTube ቻናል ሊንክ 👇👇👇
https://www.youtube.com/channel/UCZBIP6PqUdmmagdTjbyp_AQ
👍41🥰1
ፍላሽ ዲስክ ከኮምፒውተራችን ጋር ተጠቅመን ከጨረስን በኋላ eject ማድረጋችን ምንድን ነው ጥቅሙ? አስበውት ያውቃሉ እስኪ ሀሳባችሁን አጋሩኝ?
ፍላሽ፣ External Hard Disk፣ እንዲሁም CD/DVD ከኮምፒውተራችን ሰክተን ተጠቅመን ስንጨርስ በቀጥታ የሚታየን ነገር ቢኖር በቶሎ ፍላሹን፣ External Hard Disk መልቀል ወይም CD/DVD ከሆነ ደግሞ ሲዲው እንዲወጣ መጫን ነው።
ነገር ግን አብዛኛዎቻችን ፍላሼ፣ External ሀርዲ ዲስኬ፣ የምጠቀምበት ሲዲ አልሰራልኝ አለ? ኮራፕት አደረገብኝ፣ ፍላሽ ዲስኬ Write Protected ሆነብኝ፣ ፍላሽ ዲስኬ ከነጭራሹ ከኮምፒውተሬ ጋ ብሰካው እይሰራም፣ ፍላሽ ዲስኬን ከኮምፒውተሩ ጋ ስሰካው ድምጽ ያሰማኛ ግን My computer ጋ ስሄድ የለም የሚል በብዛት የሚነሳ ጥያቄ ነው። ለዚህ ሁሉ ችግር ተጠያቂዎቹ እኛው ነን።
ቅድመ ጥንቃቄ ማድረግ አለባችሁ።
በመጀመሪያ ደረጃ ፍላሽ ዲስክ፣ External ሀርድ ዲስክ፣ ሲዲ/ዲቪዲ ወደ ኮምፒውተር ስብሰካና ስናስገባ ኮምፕዩተሩ Read/ Write process ያደርጋል። ይህ ማለት ስራ እየሰራ ነው ማለት ነው።
ፍላሽ ዲስክ፣ External ሀርድ ዲስክ፣ ሲዲ/ዲቪዲ ወደ ኮምፒውተር ሰክተንና አስገብተን ፋይል ለምሳሌ ከኮምፒውተር ወደ ፍላሽ፣ ከፍላሽ ወደ ኮምፒውተር, ከExternal Hard Disk ወደ ኮምፒውተር .......... መረጃ ስናገላብጥ አሁን ሁሉም ስራ ላይ ናቸው ማለት ነው። ስለሆነም መረጃ እያላላክን ሳለ ከተሰካበት ብንነቅለው። ከገባበት ብባወጣው። ስራውን ሳይጨርስ አቋረጥነው ማለት ነው። በዚህ አጋጣሚ የመበላሸት አጋጣሚው በጣም ሰፊ ነው በተለይ ደግሞ ለExternal Hard Diskና CD/DVD እንዲሁም ፍላሽ ዲስኮች።
ፍላሽ ዲስክ፣ External ሀርድ ዲስክ፣ ሲዲ/ዲቪዲ ከኮምፒውተር ጋ ተሰክተው እያለ ዝም ብለን የምነቅለው ከሆነ ይህም የመበላሽት አጋጣሚው በጣም ሰፊ ነው።
ስለሆነም ማንኛውንም ከኮምፒውተር ጋ የሚሰኩ Storage Device በጥንቃቄ በሚከተለው ፕሮሰስ ፍላሽ ዲስክ፣ External ሀርድ ዲስክ፣ ሲዲ/ዲቪዲ ከኮምፒውተራችን ሳንነቅለው በፊት Eject ማድረግ አለባችሁ።
Start -> All Program -> Computer or This PC -> ወደ ፍላሻችን ወይም External Hard Disk..... በመሄድ Right click በማድረግ Eject የሚለውን ይጫኑ። ከዛም ቢያንስ ለ5 ሰከንድ ይጠብቁ በቅድሚያ ግን ከፍላሽ ዲሳክችን....... የተከፈተ ማንኛውንም ፕሮግራም መዝጋት አስፈላጊ ነው።
ምስሉን ይመልከቱ!⁉️
Eject ጥቅም ከኮምፒውተር ጋ የተሰካን ማንኛውንም ነገር ግንኙነቱን ያቋርጣል ማለት ነው። እንደገና ግንኙነቱ እንዲቀጥል ከፈለጋችሁ እንደአዲስ በመንቀል መሰካት ያስፈልጋል።
ይህ ተግባር የሁልጊዜ ስራችንና ተግባራችን ይሁን።
ከተመቻችሁ ለሌሎች ሰዎች እንዲደርሳቸው #ሼር ይደረግ!
ለፔጁ አዲስ የሆናችሁ ሰዎች #Like #shear ይደረግ።
👍15👏1
#ውድ የ Muhammed Computer Technology የፌስቡክ ገጽ ተከታታዮች። እንደሚታወቀው በፌስቡክና በቴሌግራም ምርጥ አስተማሪ የቴክኖሎጂ መረጃዎችን እያደረስኳችሁ እገኛለሁ።
ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ደግሞ በYouTube ጠቃሚ ትምህርቶችን ለተመልካች እያቀረብኩ እገኛለህ። ስለሆነም በ1 አመት ብቻ #28,000 በላይ #Subscribers ማግኘት የቻለ ተወዳጅ ቻናል ሁኗል ስለሆነም በYouTube በምለቀቃቸው Vedios ጠቃሚና አስተማሪ ሰልሆኑ #Subscribe በማድረግ #ይማሩ #ይወቁ
#በቅንነት ሼር አድርጉልኝ!
ያቀቁትን ማሳወቅ የተማሩትን ማስተማር ብልህነት ነው።
YouTube ቻናል ሊንክ
👇👇👇

https://www.youtube.com/channel/UCZBIP6PqUdmmagdTjbyp_AQ
https://www.youtube.com/channel/UCZBIP6PqUdmmagdTjbyp_AQ
https://www.youtube.com/channel/UCZBIP6PqUdmmagdTjbyp_AQ
👍34🔥3👎2🤔21
የኢሜል password ብንረሳዉስ🙈?
የኢሜል ፓስዋርዳችሁ ከጠፋባችሁ ከዚህ በታች ያሉትን እስቴፖች በመከተል የጠፋባችሁን የኢሜል ፓስዋርድ
አጥፍታችሁ #reset በማድረግ በአዲስ መቀየር ትችላላችሁ ።
👇👇
1⃣ ይከከን ማስፈንጠሪያ

https://accounts.google.com/signin/recovery

ተጭናችሁ ወደ #Google account recovery ፔጅ ግቡ።

2⃣ፖስዋርዱ የጠፋባችሁን ኢሜል አድራሻ (email address) አስገብታችሁ #forget password የሚለዉን በተን ተጫኑ።

3⃣የምታስታዉሱትን የ ኢሜል ፓስዋርድ እንድታስገቡ ይጠይቃችሗል።

እዚህ ላይ ያስታወስችሁትን የጠፋዉን ፖስዋርድ አስገቡ እና #Next የሚለዉን በተን ተጫኑ።

ብትሳሳቱም አትጨነቁ አካዉንታችሁን አይዘገሠዉም።

4⃣ከዛ #Google የሜረጋገጫ #Verification code
ኢሜሉን ስትከፍቱ ባስገባችሁት ስልክ ቁጥር ይልክላችሗል።

በምን ይልካል?

#Text or Call የሚል ሲመጣ የሚፈልጉትን የመቀበያ መንገድ ይምረጡ።

5⃣የተላከላችሁን ባለ 6 #digit የማረጋገጫ ኮድ አስገቡ።

6⃣ከዛ አዲስ ፖስዋርድ እንድታስጋቡ ይጠይቃችሗላ።

የፈለጉትን ፖስዋርድ እና ኮንፌርሜሽን ፓስዋርድ(መጀመሪያ ያስገባችሁትን ደግማችሁ አስገቡ) አስገብታችሁ
#Next የሚለዉን ሲጫኑ የጠፋዉ ፖስዋርድ በአዲስ ፓስወርድ ተቀየረ ማለት ነዉ።
ከተመቻችሁ ሼር
👍16👏1
15GB ነፃ Storage እንዲሁም ወደ Google Drive ፋይል መጫንና ከ ወደ ሌላሰው በኢሜይል(Email) እንዴት መላክ እንችላለን ፋይል ማስቀመጥ ይቻላል?
15GB ነጻ ፋይል ማስቀመጫና ከ25MB በላይ ፋይልን ለሌላ አካል ኢሜይል ማድረግ እንችላለን? ብዙ ግዜ ከ25MB በላይ ኢሜይል ለመላክ እምቢ ላላችሁ ሰዎች መፍትሄው ከዚህ በታ ያለውን ሊንክ በመጫን መመልከት ትችላላችሁ
https://youtu.be/HEvXJo8E3k0
https://youtu.be/HEvXJo8E3k0
👍2😁1
ኮምፒውተር ላይ ማንኛውንም ፍላሽና ኤክስተርናል ሀርድ ዲስክ ሲሰካ እንዳይሰራ ማድረግ
1. የኛን መረጃ ሌላ ሰው ያለእኛ ፈቃድ እንዳይወስድብን ለመዝጋትና
2ኛ. ኮምፒውተራችን ላይ #ፍላሽ ዲስክ በምንሰካበት ጊዜ ብዙ ጊዜ ፍላሽ ዲስኩ በቫይረስ የተጠቃ በሚሆንበት ጊዜ ቫይረሱ በቀጥታ ወደ ኮምፒውተራችን በመግባት ኮምፒውተራችንን ስራ ማስተጎጎል እንዲሁም እስከ ማጥፋት ሊያደርስ ይችላል ስለዚህ ማንኛውንም ፍላሽ ዲስክ ሰዎች ወደ ኮምፒተራችን ከተው እንዳይጠቀሙ ምን ማድረግ አለብን።
👇👇👇ቪዲዮውን ይመልከቱ👇👇👇
https://youtu.be/zqtpTxn4KQs
https://youtu.be/zqtpTxn4KQs
https://youtu.be/zqtpTxn4KQs
https://youtu.be/zqtpTxn4KQs
https://youtu.be/zqtpTxn4KQs
https://youtu.be/zqtpTxn4KQs
👍6
📝 ቢትኮይን ምንድነው? What is Bitcoin?
ቢትኮይን ማለት በቀላል ቋንቋ፤ ዲጂታል+ገንዘብ+መገበያያ በማለት ማጠቃለል ይቻላል።
ይህ መገበያያ በኪሳችን ተሸክመን እንደምንዞረው የብር ኖት ወይም ሳንቲም ሳይሆን 'ኦንላይን' የሚቀመጥ ዲጂታል ገንዘብ ነው።
በቀላሉ በሀገራችን አገላለፅ ሲገለፅ
" በአይን የማይታይ በእጅ የማይዳሰስ ዘመናዊ ገንዘብ ነው "
♻️ ቢትኮይን ከፍተኛ ዋጋ ያለው የብሎክ ቼይን ቴክኖሎጂ ውጤት ነው፡፡
📌 በፈረንጆቹ 2008 satoshi Nakamoto በተባለ ግልሰብ በሰራው የMaths Project የተፈጠረ ምናባዊ (ዲጂታል) የመገበያያ ገንዘብ ነው፡፡
♻️ ይህ አዲስ ዋጋ ያለው ገንዘብ አለም አሁን እየተጠቀመባቸው ካሉ ገንዘቦች ሁሉ በምንዛሬ ከፍተኛ ዋጋ ያለው ዲጂታል ገንዘብ ነው፡፡
🔺የቴኖክሎጂ ባለሙያዎችን እስከ ዛሬ ሲያስጨንቃቸው የነበረው ጉዳይ አንድን እቃ ቅጂው እጃቸው ላይ ሳይኖር ለሌላ ሰው እንዴት ማስተላለፍ ይቻላል? የሚለው ነው፡፡
ለምሳሌ፡ 50 ብርን ለአንድ ሰው በዲጂታል መንገድ ለመላክ ኮፒው ላኪው ጋር አለመቅረቱ ምንም ማረጋገጫ የለም፡፡
🔺ይህ ጉዳይ ክሪፕቶግራፈሮች ለረጅም ጊዜ ሲቸገሩበት የነበረው ጉዳይ ነው፡፡ ክሪፕቶ ከረንሲ ይህንን ችግር የፈታ አዲሱ ቴክሎጂ ነው፡፡
በተለመደው አሰራር የሀገራት የገንዘብ ዝውውር መንግስት እና ባንኮች የሚቆጣጠሩት ነው፡፡
🔺ቢትኮይን የተባለው ገንዘብ ግን ዝውውሩን የሚቆጣጠረው ባለቤቱ ሲሆን የዝውውሩ ህጋዊነት ማረጋገጫ ደግሞ ሁሉም የቢትኮይን ተጠቃሚዎች ናቸው፡፡
ሰዎች በአለም ላይ ካሉ ከሚፈልጉት ሰው ጋር በየትኛውም ቦታ ሆነው ሶስተኛ ወገን ወይም ባንክ ሳያስፈልግ የሚገበያዩበት ቴክኖሎጂ ነው፡፡
⚠️ማንም ሊቆጣጠረው እና ሊያጭበረብረው አይችልም፡፡ መንግስታትም ቢሆኑ፡፡
ቁጥጥሩ በሁሉም ግልሰቦች እጅ ሆኖ በሁሉም የቢትኮይን ረቂቅ ገንዘብ ተጠቃሚ ኮምፒውተሮች ላይ መረጃዎቹ ሰፍረው ይገኛሉ፡፡
ለምሳሌ፡ አንድ ሰው የቢትኮይን ተጠቃሚ ሲሆን ልክ እንደ ጂ-ሜል እና ፌስ ቡክ የመለያ ስም አውጥቶ የሚስጥር ቁልፍ መርጦ መጠቀሚያ ይከፍታል፡፡ የሚስጥር ቁጥሩ በጣም ጠንካራ በመሆኑ የመሰረቅ አደጋ አይገጥመውም፡፡
ከዚያ ከፈለገው ሰው ጋር ቢትኮይን መላላክ ይችላል፡፡
ያ የተላላከው የገንዘብ ዝውውር በአለም ላይ ባሉ ኮምፒውተሮች ቅጂው ይቀመጣል፡፡
እነዚህ ሁለት ሰዎች ቢከዳዱ እንኳ አለም ላይ ባሉ ኮምፒውተሮች ዝውውሩ ተመዝግቦ በቅጂ መልክ ስለሚቀመጥ እውነቱን ማወቅ ይቻላል፡፡
🧩በቀላል ምሳሌ እንየው
ለምሳሌ ፡ አንድ ሰው ጫማ መግዛት ቢፈልግ እና ባንክ ቤት ገንዘብ ለማውጣት ቢሄድ ባንክ ቤቱ ሰውየው በስሙ ገንዘብ መኖርና አለመኖሩን አረጋግጦ ገንዘብ ይሰጠዋል፡፡ ሰውየው ገንዘብ እንዳለውና እንደሌለው የሚያውቀው ባንኩ ብቻ ነው፡፡
እሱን ካረጋገጠ በኋላ ገንዘቡን ይሰጠውና የሚፈልገውን መግዛት ይችላል፡፡
ሰውየው በክፍያ ካርድ ቢሆን መግዛት የሚፈልገው እና ካርዱን ለባለሱቁ ሰጥቶ የጫማ መግዣውን ቢያስቆርጥ፤ ሰውየው ገንዘብ እንዳለውና እንደሌለው የሚቆጣጠረው በተመሳሳይ ሶስተኛ ወገን የሆነው ባንኩ ነው፡፡
📌ክፍል 2 - የቢትኮይን ምንዛሬ
የቢትኮይን ዋጋ unstable ነው በየጊዜው ይጨምራል! የተወሰነ መዋዠቅም ያጋጥመዋል!
♻️ ግንቦት 2010 ላይ የ1 ቢትኮይን ዋጋ 0.01 ዶላር ነበር!
♻️ ይህንን ፅሁፍ በምናዘጋጀበት ጊዜ ደግሞ ዋጋው ወደ 43,531.10 United States Dollar ዶላር (2,018,639.40 Ethiopian Birr ብር) ነው!
♻️ በቀጣይ አመት ደግሞ 1Bitcoin ወደ 100,000 ዶላር እንደሚደርስ ማለትም ወደ 4,637,234.98 ብር እንደሚሆን የዘርፉ ባለሙያዎች እየተነበዩ ይገኛሉ!
💰 በአለም ላይ 21ሚሊዮን Bitcoin ብቻ ነው የተፈጠሩት በአሁን ሰአት 18 ሚሊዮን Bitcoin በሰው እጅ ላይ ገብተዋል የሚቀሩት 3 ሚሊዮን Bitcoin ብቻ ናቸው!
♻️ እነዚህ ቢትኮይኖች ሁሉም ለማለቅ 132 አመት እንዲቆዩ ተደርጎ የተቀመረ ስሌት ነው!
📝 NOTE | ማስታወሻ 📝
🩸Bitcoin Wallet - በአጭሩ ቢትኮይናችን የሚቀመጥበት ካዝና ማለት ነው!
🩸Bitcoin Wallet Address - ማለት ቢትኮይን ለተጠቃሚዎቹ የሚሰጠው የተዘበራረቀ የአካውንት ቁጥር ነው!
(Bitcoin ስንልክም ሆነ ስንቀበል የሚያስፈልገን ቁጥር (ልክ እንደ ባንክ Account ቁጥር) ባለ 34 Digit ወይንም ባለ 36 Digit
🩸Mining - ማለት የሽልማት አይነት ሲሆን በመሳሪያ እንዲሁም ዌብሳይት ላይ የምናገኘው ቢትኮይን በነፃ የምናገኝበት ዘዴ ነው!
🩸Transactions ID - ቢትኮይን ስንልክም ሆነ ስንቀበል የምናገኘው ኮድ ሲሆን ያንን ኮድ ወደ blockchain official web ላይ ስናስገባው ከየትኛው Wallet address ወደ የትኛው bitcoin እየተዘዋወረ እንደሆነ እንዲሁም የተዘዋወረበትን ሰዓት እና Bitcoinu Confirm መሆን አለመሆኑን ማወቅ እንችላለን!
🩸Blockchain - የምንላላከውን Bitcoin መዝግቦ የሚያስቀምጥ System ነው!
ክፍል 3
ከቢትኮይን ጥቅሞች በጥቂቶቹ
🔥 መገበያያ ገንዘብ ነው
🔥 መጭበርበርን ያስወግዳል ሁለት የማይተዋወቁና የማይተማመኑ ሰዎች እንዲተማመኑ ሲስተሙ ይረዳቸዋል
🔥 ገንዘባችንን መንግስት ና ባንክ ጣልቃ ሳይገባ እንደፈለግን ከ አለም ጫፍ እስከ አለም ጫፍ መላክ ፣መላላክ ፣ መገብየት፣ መሸጥ.... እንችላለን
🔥 ለአጠቃቀም በጣም ምቹ ና ቀላል ነው ልክ - ለሰው Message እንደመላክ ነው
🔥 በምንዛሪ/Currency የአለም አገራት አንድ አይነት መገበያያ ገንዘብ እንዲኖራቸው ይረዳል (በቢትኮይን ስለሚገበያዩ)
🔥 ኢንተርኔት ባለበት ሁሉ መጠቀም እንችላለን
🔥 Open source software (የ አለም ህዝብ ሁሉ በነፃ የሚጠቀመው ነው ) (የራሱን powerful ኮሚፒዩተሮችን በመደርደር ቢትኮይን ማግኘት ይችላል)
🔥 አስተማማኝ ነው
🔥 የሌብነት ፣የመጭበርበር፣ የአላስፈላጊ ክፍያ/ወጪ፣ የገንዘብ ዝውውር መዘግየት እና የመሳሰሉትን ችግሮች ያስቀራል.....
እና ሌሎችም ያልጠቀስናቸው
እጅግ ፈርጀ ብዙ ጥቅሞች አሉት....
ከቢትኮይን ጉዳቶች በጥቂቶቹ
🔥 በየጊዜው የምንዛሬ መቀያየር ሊያጋጥመው ይችላል
🔥 ስልካችን Format ቢሆን ፣ የBitcoin አካውንታችን ቢጠፋ ቢትኮይናችንን መልሰን ማግኘት አንችልም
🔥 ምናልባትም Part Of New World Order ሊሆን ይችላል ስለዚህ በሀገራችን ብዙም ተቀባይነት ሊኖረው አይችልም
ማሳሰቢያ: በፌስቡክ፣ በቴሌግራም ብር አጭበርባሪዎች ስላሉ ይጠንቀቁ! ምንም አይነት ብር እንዳያስገቡ! እኔ ለመማር ብቻ ነው ጽሁፉን ያቀረብኩት!
👍8
DV 2023 እንዴት ራሳችን መሙላት እንችላለን?
በጥያቂያቹ መሰረት ዲቪ 2023 ለመሙላት መከተል ያለብንን መንገዶች እነሆ
›በመጀምሪያ ዲቪ መሙላት የምንችለዉ ከ መስከረም 27,2014 በኢትዮጵያ ወይም በፈረንጆች ኦክቶበር ሀሙስ 07/2021 ጀምሮ ህዳር 09/2021 ለሊት 6፡00 ድረስ ብቻ ነው።
DV-2023 Program: Online Registration
DV-2023 Program: The online registration period for the DV-2023 Program begins on Wednesday, October 7, 2021 at 12:00 noon, Eastern Daylight Time (EDT) (GMT-4), and concludes on Tuesday, November 09, 2021 at 12:00 noon, Eastern Standard Time (EST) (GMT-5). Individuals who submit more than one entry during the registration period will be disqualified.
DV-2023 Program Instructions

›የዲቪ ፎርሙን ከመሙላታችን በፊት ማሟላት ያሉብን ነገሮች፦
እያንዳንዱ የ DV አመልካች የትምህርት / የሥራ ልምድ ማሟላት አለበት
ማለትም
በ ፕሮግራሙ መሰረትም-
• ቢያንስ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ወይም ተመጣጣኝ, የ 12 ዓመት ትምህርት
በሚገባ ያጠናቀቀ / ያጠናቀቀች።
ወይም
• ባለፉት አምስት ዓመታት ውስጥ የሁለት አመት የሥራ ልምድ ያለው።
•ጉርድ ፎቶ ግራፍ
በመቀጠልም
www.dvlottery.state.gov በሚለው ዌብ ሳይት መግባት
›ዌብ ሳይቱ ዉስጥ ገብተን Entry ሚለውን በመጫን መቀጠል
በፎቶ መልክ የተቀመጠልንን Authentication code በድጋሚ በመጻፍ ወደ
ፎርም መሙያዉ መግባት።
ፎርም አሞላል
1. Name - ስም - Last/Family Name (የመጨረሻ/የቤተሰብ ስም ወይም
የአያት ስም) ፣ Middle Name- (የመካከለኛ ስም ወይም የአባት ስም) ፣
First Name (የመጀመሪያ ስም ወይም የእርሶን ስም) በፓስፖርትዎ ላይ
ያለውን ስም ሳያሳስቱ በእንግሊዝኛ መጻፍ።
2. Gender - ፆታ - ወንድ (Male) ወይም ሴት(Female) መምረጥ።
3. Birth date - የልደት ቀን - መጀመሪያ Month (ወር) ፣ Day (ቀን) ፣ Year
( ዓመት) በፈረንጆች አቆጣጠር በተሰጠው ቦታ መጻፍ።.
4. City Where You Where Born - የተወለዱበትን ከተማ.
5. Country Where You Were Born - የተወለዱበትን ሀገር
6. Country of Eligibility for the DV Program - ለ DV መርኃ-ግብር
ብቁ የሆነ ሀገር ማለትም yes ሚለዉ ላይ በመተው ማለፍ
7. Entrant Photograph - የመግቢያ ፎቶግራፍ ማስገባት
- የቅርብ ጊዜ ጉርድ ፎቶግራፍ -ፎቶ ግራፉ በደንብ የሚታይ ልኬቱ 600ፒክስል
* በ600 ፒክስል የሆነ መጠኑ ከ 240 ኪሎባይት የማይበልጥ ከለር ፎቶ ግራፍ
፣JPEG Format መሆን አለበት።
8. Mailing Address - የፖስታ መላኪያ አድራሻ መሙላት
9. Country Where You Live Today - አሁን የምንኖርበትን ሀገር መምረጥ
10. Phone Number - ስልክ ቁጥር ማስገባት ለኢትዮጲያ +251 ብለን
በመጀመር ስልካችንን ማስገባት / አለማስገባትም ይቻላል
11. E-mail Address - የ ኢሜል አድራሻንን ማስገባት
12. What is the highest level of education you have achieved,
as of today?
የትምህርት ደረጃችንን መምረጥ
13. What is your current marital status?- በአሁን ሰአት ያለን የትዳር
ሁኔታ መምረጥ
14 . Number of Children - የልጅ ብዛት በቁጥር መጻፍ
እያንዳንዱ የተወለዱ ሕጻናት እንዲሁም የማደጎ ልጆች፣ የእንጀራ ልጆች
በእርስዎ ፎርም ውስጥ እያንዳንዱ ያላገቡ ህጻናት, ምንም እንኳን ልጅዎ
ከእርስዎ ጋር አብረው ባይኖሩም መሞላት አለባቸዉ።
»በመጨረሻም continue በማለት Confirmation Number ያለበትን
ወረቀት ፕሪንት በማድረግ ማስቀመጥ እና በ Confirmation Number ን
DV-2023 ሲወጣ ማየት እንችላለን።
DV-2023 Submission Confirmation : Entry success
በዚ መሰረት ፎርሙን በመሙላት እድላችሁን መሞከር ትችላላችሁ ፔጃችንም
መልካም እድል ይመኝላቹሀል
ይሄን መረጃ ለወዳጆ ሼር በማድረግ ማስተላለፍ ትችላላችሁ
👍13
SafewayManufacturing_1_1.0.apk
1.5 MB
ምርጥ ዌብሳይትና የዌብሳይት App በተመጣጣኝ ዋጋና በታላቅ ቅናሽ ያሰሩ!
አፕልኬሽኑን በማውረድ ስልኮ ላይ ሸመጫን ይሞክሩት! ይደውሉልን ስልካችንን እፕልኬሽኑን ሲከፍቱት ያገኙታል።
በቅርቡ ሰርተን ያስረከብናቸው ዌብሳይቶችን ይጋበዙልን።
እርስዎም የሚሰሩትን ስራ ሊያቀላጥፍልዎ የሚችል ዌብሳይት ይዘዙን!
ለንግድ፣ ለመንግሥት ተቋማት፣ ለግል ድርጅቶች፣ ለኮሌጆች፣ ለሆቴሎች፣ ለአስመጭና ላኪ ድርጅቶች፣ ለድለላ ስራ፣ ለማንኛውም አገልግሎት ሰጭ ድርጅቶች በቅልጥፍና አገልግሎት ማግኘት ይችላሉ።
☎️ 0929273364 ሙሀመድ ኮምፒውተር ቴክኖሎጂ
1ኛ www.4wcomputers.com
2ኛ www.safeway7.com
3ኛ www.mametechsolution.com
4ኛ www.ethiotechnologys.com
5ኛ www.bournworks.com
👍31
ይህ Muhammed Computer Technology የፌስቡክ ገጽ ነው። አሁን ላይ 114,000 በላይ ተከታይ ያለው ፔጅ ነው። ስለሆነም እርሶም ፔጁን like በማድረግ ቴክኖሎጂ አዘል መረጃዎችንና ትምህርቶችን ይከታተሉ።
👇👇👇ሊንኩ ይህ ነው👇👇👇
https://m.facebook.com/mameamin.6te.net
👍2
ምናባዊ እውነታ (VIRTUAL REALITY) ምንድን ነው?
ምናባዊ እውነታ ( VR ) ከእውነተኛው ዓለም ጋር ተመሳሳይ ወይም ሙሉ ለሙሉ ሊመሳሰል የሚችል የማስመሰል ተሞክሮ ነው። የቨርችዋል አተገባበር ትግበራዎች መዝናኛን (ለምሳሌ ጨዋታ ) እና የትምህርት ዓላማዎችን (ለምሳሌ የህክምና ወይም የውትድርና ስልጠናን) ሊያካትቱ ይችላሉ ። በአሁኑ ጊዜ መደበኛ ምናባዊ የእውነታ ስርዓቶች ምናባዊ የእውነታ ማዳመጫዎችን ወይም በብዙዎች የታሰበ አካባቢን በመጠቀም እውነተኛ ምስሎችን ፣ ድምጾችን እና ሌሎች የተጠቃሚዎችን አካላዊ ስሜት በሚያንፀባርቁ አካባቢዎች ውስጥ ለማስመሰል ይሞክራሉ። አንድ ሰው ምናባዊ የእውነተኛ መሣሪያዎችን የሚጠቀም ሰው ሰው ሰራሽ የሆነውን ዓለም ለመመልከት ፣ በውስጡ ለመንቀሳቀስ እና ከምናባዊ ባህሪዎች ወይም ዕቃዎች ጋር ለመግባባት ይችላል ፡፡ውጤቱ በተለምዶ ከዓይኖቹ ፊት ለፊት ትንሽ ማያ ገጽ ካለው የራስ-ተጭኖ ማሳያ ጋር በ VR የጆሮ ማዳመጫዎች የተፈጠረ ነው ፣ ግን በተጨማሪ ብዙ ትላልቅ ማያ ገጾች ባሉት ልዩ ንድፍ ክፍሎች ሊፈጠሩ ይችላሉ ፡፡ የምናባዊ እውነታ በተለምዶ auditory እና ቪዲዮ ግብረመልሶችን ያካተተ ነው
ምናባዊ እውነታ እንደ ቪዲዮ ጨዋታ እና 3D ሲኒማ ያሉ በመዝናኛ መተግበሪያዎች ውስጥ በብዛት ጥቅም ላይ ይውላል ። የሸማቾች ምናባዊ የእውነት ራስጌዎች በመጀመሪያ በ 1990 ዎቹ አጋማሽ በቪዲዮ ጨዋታ ኩባንያዎች ተለቀቁ ፡፡ እ.ኤ.አ. ከ 2010 ዎቹ ጀምሮ ፣ የሚቀጥለው የንግድ ጅምር ራእዮች አዲስ በሆነው የመተግበሪያ ልማት ማዕቀፍ ላይ በመመሥረት በኦካውስ (ራይተር) ፣ በ HTC (Vive) እና በ Sony (በ PlayStation VR) ተለቅቀዋል ፡፡ 3d ሲኒማ ለስፖርታዊ ዝግጅቶች ፣ ለስነ-ጥበባት ፣ ለሙዚቃ ቪዲዮች እና ለአጫጭር ፊልሞች ጥቅም ላይ ውሏል ፡፡ እ.ኤ.አ. ከ 2015 ጀምሮ ፣ ሮለር ገ andዎች እና ጭብጥ መናፈሻዎች የእይታ ውጤቶችን ከአስቂኝ ግብረመልስ ጋር ለማዛመድ ምናባዊ እውነታ አካተዋል። በሕክምና ውስጥ ፣ በባለሙያዎች ቁጥጥር ስር የተመሰሉ የ VR የቀዶ ጥገና አካባቢዎች ሰልጣኞች በሚከሰቱበት ጊዜ ስህተቶችን እንዲገነዘቡ እና እንዲያስተካክሉ በማስቻል ውጤታማ እና ተደጋጋሚ ስልጠና በአነስተኛ ወጪ ሊሰጡ ይችላሉ ፡፡ ከ 2000 ዎቹ ዓመታት ጀምሮ እውነተኛው አካላዊ በአካላዊ ተሃድሶ ውስጥ ጥቅም ላይ ውሏል ፡፡ ምንም እንኳን ብዙ ጥናቶች የተካሄዱ ቢሆንም ጥሩ እና ውጤታማ መሣሪያ ከሌላቸው የመልሶ ማቋቋም ዘዴዎች ጋር ሲነፃፀር ጥሩ የጥራት ማስረጃ የፓርኪንሰን በሽታን ለመያዝ ይጎድለዋል ፡፡ በተመሳሳይ መልኩ የተጠናቀቀው ለየትኛውም የፓቶሎጂ በሽታ የመስተዋት ሕክምና ውጤታማነት ላይ የ 2018 ግምገማ ፡፡ የ VR ን ማስመሰል የማስፋፋት እና በኒውትሮቲካል እና ኦቲዝም ዲስኦርደር ዲስኦርደር ዲስኦርደር ግለሰቦች መካከል ባለ ሁለት-ልኬት አምሳያ ላይ የሰጡትን ልዩነት የገለጸ ሌላ ጥናት ተደረገ VR ለሥራ ቦታ የሥራ ደህንነት እና የጤና ዓላማዎች ፣ ለትምህርታዊ ዓላማዎች እና ለስልጠና ዓላማዎች እውነተኛ የሥራ ቦታዎችን ማስመሰል ይችላል ፡፡ ተማሪዎቹ ውድቀትን በእውነተኛ-ዓለም የሚያስከትለውን ውጤት ሳያገኙ ችሎታቸውን እንዲያዳብሩበት ምናባዊ አካባቢን ለማቅረብ ሊያገለግል ይችላል ፡፡ በአንደኛ ደረጃ ትምህርት ፣ ወታደራዊ ፣ የጠፈር ተመራማሪዎች ላይ ስልጠና ፣ የበረራ አስመሳይዎች ፣የማዕድን ስልጠና ፣ የሥነ-ሕንፃ ንድፍ ፣ ጥቅም ላይ ውሏል እና ጥናት ተደርጓል። የአሽከርካሪ ስልጠና እና የድልድይ ፍተሻ። አስማጭ የ VR ምህንድስና ስርዓቶች መሐንዲሶች ከማንኛውም አካላዊ ፕሮቶኮሎች ከመገኘታቸው በፊት ምናባዊ ምስሎችን እንዲመለከቱ ያስችላቸዋል። ወጪን በሚቀንሱበት ጊዜ በወታደራዊ አገልግሎት እና በጤና እንክብካቤ ስልጠና ላይ የእውነተኛነት እድሎችን እንደሚያቀርቡ ተገለፀ ፡፡ በተጨማሪም በስልጠና ወቅት ያወጡትን የጦር መሳሪያ መጠን በመቀነስ ወታደራዊ ሥልጠና ወጪዎችን እንደሚቀንስ ታውቋል ፡፡
1👍1
DV ያለ ፓስፖርትና ፖስፖርት የለው ሰው እንዴት መሙላት እንደምንችል በምርጥ አቀራረብ በቪዲዮ ይዠላችሁ ስለማቀርብ የ YouTube ቻናል ሰብስክራይቭ ያድርጉ!
ሀሳብ አስተያየት ካላችሁ ጻፉልኝ!
የ YouTube ቻናል ሊንክ 👇👇👇
https://www.youtube.com/channel/UCZBIP6PqUdmmagdTjbyp_AQ
https://www.youtube.com/channel/UCZBIP6PqUdmmagdTjbyp_AQ
https://www.youtube.com/channel/UCZBIP6PqUdmmagdTjbyp_AQ
https://www.youtube.com/channel/UCZBIP6PqUdmmagdTjbyp_AQ
👍1
የኢትዮጵያ የዩኒቨርስቲዎች ድረገፆች ( website )
አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ www.aau.edu.et
መቀሌ ዩኒቨርስቲ www.mu.edu.et
አዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርስቲ www.astu.edu.et
አክሱም ዩኒቨርስቲ www.axu.edu.et
አምቦ ዩኒቨርስቲ www.ambou.edu.et
አርባ ምንጭ ዩኒቨርስቲ www.amu.edu.et
ባህር ዳር ዩኒቨርስቲ www.bdu.edu.et
ደብረ ብርሃን ዩኒቨርስቲ www.dbu.edu.et
ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርስቲ www.dmu.edu.et
ዲላ ዩኒቨርሰቲ www.du.edu.et
ጎንደር ዩኒቨርስቲ www.gu.edu.et
ጂማ ዩኒቨርስቲ www.ju.edu.et
ሃረማያ ዩኒቨርስቲ www.haramaya.edu.et
ሃዋሳ ዩኒቨርስቲ www.hu.edu.et
ወላይታ ሶዶ ዩኒቨርስቲ www.wsu.edu.et
ወለጋ ዩኒቨርስቲ www.wu.edu.et
ድሬ ዳዋ ዩኒቨርስቲ www.ddu.edu.et
ወሎ ዩኒቨርስቲ www.wou.edu.et
ጅጅጋ ዩኒቨርስቲ www.jgu.edu.et
መዲ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ www.mwu.edu.et
ሚዛን ቲፒ ዩኒቨርሲቲ www.mtu.edu.et
ሰመራ ዩኒቨርሲቲ www.su.edu.et
ኮተቤ ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ www.kuc.edu.et
አአ ሾል. & ቴክ ዩኒቨርሲቲ www.aastu.edu.et
አዲግራት ዩኒቨርሲቲ www.adu.edu.et
አሶሳ ዩኒቨርሲቲ www.asu.edu.et
ቡሌ ሁራ ዩኒቨርስቲ www.bhu.edu.et
ደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ www.dbtu.edu.et
መቱ ዩኒቨርሲቲ www.mtu.edu.et
ዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ www.wcu.edu.et
ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ www.wku.edu.et
ወልድያ ዩኒቨርሲቲ www.wdu.edu.et
አርሲ ዩኒቨርሲቲ www.aru.edu.et
ጋምቤላ ዩኒቨርሲቲ www.gmu.edu.et
ኦዳ ቡልቱም ዩኒቨርሲቲ www.obu.edu.et
የት/ት ፍኖተ ካርታ በሁለተኛ ደረጃ ት/ቤቶች ከ11ኛ-12ኛ ክፍል ናቹራል ሳይንስ ዲፓርትመንት የሚሰጡ የት/ት አይነቶች::
====================
😁አንድ ክ/ጊዜ 45 ደቂቃ አለው፡፡
😁በቀን 7 ክ/ጊዜ
😁በሳምንት 35 ክ/ጊዜ
😁የት/ት ሠዓት በየፈረቃው 4ሰዓት ከ40 ደቂቃ ነው፡፡
====================
😁ቋሚ (7ቱ) የት/ት አይነቶች እና የክ/ጊዜ ብዛት:-
====================
😁1ኛ= የእንግሊዘኛ ቋንቋ የሳምንት ክ/ጊዜ ብዛት 4 ፣የሳምንት የት/ት ሠዓት 3 ሰዓት እና የዓመቱ የት/ት 117 ሰዓት ነው፡፡
😁2ኛ= ሒሳብ ክ/ጊዜ 4፣ በሳምንት 3ሠዓት እና በአመት 117 ሠዓት አለው፡፡
😁3ኛ= ባዮሎጂ የሳምንት ክ/ጊዜ 3 ፣ የሳምቱ ሠዓት 2ሰዓት ከ15 ደቂቃ እና የአመቱ 87 ሰዓት ከ45 ደቂቃ አለው፡፡
😁4ኛ= ኬሚስትሪ በሳምንት3 ክ/ጊዜ በሳምንት 2ሰዓት ከ15 ደቂቃ እና በዓመት 87ሰዓት ከ45 ደቂቃ አለው፡፡
😁5ኛ= ፊዚክስ በሳምንት 3 ክ/ጊዜ፤ በሳምንት 2ሰዓት ከ15 ደቂቃ እና በዓመት 87 ሰዓት ከ45 ደቂቃ አለው፡፡
😁6ኛ= አይቲ በሳምንት 3 ክ/ጊዜ፣ በሳምንት 2ሰዓት ከ15 ደቂቃ እና በዓመት 87 ሰዓት ከ45 ደቂቃ አለው፡፡
😁7ኛ= ግብርና ት/ት በሳምን 3 ክ/ጊዜ ፣ በሳምንት 3ሰዓት ከ15 ደቂቃ እና በዓመት 87 ሰዓት ከ45 ደቂቃ አለው፡፡
አጠቃላይ የዋና የት/ት አይነቶች የሳምንት ክ/ጊዜ ብዛት 23 (17ሰዓት ከ20 ደቂቃ) እና በዓመት 676 ሰዓት ይሆናል፡፡
😁ተጨማሪ አማራጭ 5ቱ የሙያ ፊልዶችና በስሩ የሚገኙ የት/ት አይነቶች:-
===================
#አምራች(ማኑፋክቸሪግ) ፊልድ የመረጡ ተማሪዎች፡፡
====================
😁1ኛ= ብረተብረት ስራ
😁2ኛ=ጥገና(አውቶ) ስራ
😁3ኛ=የጨርቃጨርቅና የቆዳ ስራ
😁4ኛ=የእንጨት ስራ ናቸው፡:
===============
#ኮንስትራክሽን ፊልድ የመረጡ ተማሪዎች:-
===============
😁1ኛ=ኤሌክትሪክ ሲቲ
😁2ኛ=ቧንቧ ስራ
😁3ኛ=አናፂነት
😁4ኛ=የቀለም ቅብ ስራ ናቸው::
==================
#አይሲቲ ፊለድ የመረጡ ተማሪዎች:-
==================
😁1ኛ=አይቲ
😁2ኛ=የኮምፒዩየተር ጥገና እና ኔትወርክ
😁3=ዌብሳይት ዲዛይን
😁4ኛ=ኮምፒዩተር ንድፈ ዲዛይን ናቸው::
=====================
#ግብርና የመረጡ ተማሪዎች:-
=====================
😁1ኛ=ሰብል ማምረትና አስተዳደር
😁2ኛ=የእስሳት እርባታና አስተዳደር
😁3ኛ=የተፈጥሮ ሀብት አስተዳደር
😁4ኛ= የግብርና ቴክኖሎጂ ናቸው::
=================
ጤና ሳይንስ የመረጡ ተማሪዎች:-
=================
😁1ኛ=የግልና የማህበረሰብ ጤና እና የበሽታኛ አያያዝ::
😁2ኛ=የምግብና የማዕድ ጥናት
😁3ኛ=የህፃናት እንክብካቤና ደህንነት
😁4ኛ= ጤናማ ተዋልዶ ናቸው:: ስለሆነም እያንዳንዳቸው የሙያ የት/ት አይነቶች በሳምንት 3ክ/ጊዜ (3ሰዓት ከ15ደቂቃ) እና በዓመት 87 ሰዓት ከ45 ደቂቃ አለው፡፡
😁 በአጠቃላይ የቋሚና የሙያ የት/ት አይነቶች በሳምንት 35 ክ/ጊዜ ወይም 26 ሰዓት ከ15 ደቂቃ እና በዓመት 1023 ሰዓት ከ45 ደቂቃ አለው:: ሰለሆነም የት/ት እቅዱ በዚህ ስሌት መሠረት የሚዘጋጅ ይሆናል፡፡
መልካም አዲሱ የት/ት ፍኖተ ካርታ!
👍8