Muhammed Computer Technology (MCT)
38K subscribers
527 photos
7 videos
254 files
910 links
🔴አድራሻ:-
✅ ስ.ቁ: 0929273364
✅ ዌብሳይት www.mctplc.com
✅ቴሌግራም አካውንት: https://t.me/mctplc
✅ email: mct16plc@gmail.com
✅ ቲክቶክ አካውንት tiktok.com/@mctplc
Download Telegram
በወረቀት ያለን ጽሁፍ ወደ Soft copy በሰከንድ መቀየር Image To Text Convert From Hard copy to Soft copy easily በቀላሉ!
👇👇👇👇👇👇👇👇👇
https://youtu.be/82v-xzREk4Y
https://youtu.be/82v-xzREk4Y
https://youtu.be/82v-xzREk4Y
https://youtu.be/82v-xzREk4Y
https://youtu.be/82v-xzREk4Y
👍1
ለመሆኑ የአማዞን መስራች ማን ነዉ። እንዴትስ ተመሰረተ??👇👇

🛒amazon (አማዞን)

⚛ በጃኑዋሪ 12 1964 ዓ.ም. ነዉ ሜክሲኮ በተባለች የአሜሪካ ክፍለ ግዛት ዉስጥ የተወለደዉ ጄፍ ቤዞስ ገና በወጣትነቱ ነበር ለኮምፒዉተር ፍቅር ያደረበት። ከዚህም የተነሳ የወላጆቹን የመኪና ማቆሚያ ጋራዥ በመዉሰድ የራሱ የኮምፒዉተር ቤተ-ሙከራ አደረገዉ። የ2ተኛ ደረጃ ትምህርቱን በከፍተኛ ዉጤት ከተመረቀ በኋላ በታዋቂዉ የፕሪንስተን ዩኒቨርስቲ የመጀመሪያ ድግሪዉን በኮምፒዉተር ሳይንስና ኤሬክትሪካል ኢንጅነሪንግ በ1986 ዓ.ም. በከፍተኛ ማዕረግ ተመርቋል። በርካታ የሥራ መቀጠር እድሎችን ያገኘዉ ጄፍ በዞስ በኒዉዮርክ ከተማ በከፍተኛ ደሞዝና ኃላፊነት ተቀጥሮ መሥራት ጀመረ። ምንም እንኳን ተቀጥሮ የሚሰራበት ስራ ከፍተኛ ደመወዝ የሚያስገኝለትና ስልጣንንም ያቀናጀዉ ቢሆንም፣ ሥራዉን ከአራት አመት በኋላ ለቆ በመዉጣት ዛሬ በኢንተርኔት ዘርፍ ታላቅ ስኬት የተቀናጀዉን አማዞንን ለማቋቋም ተነሳ። በወቅቱ ገና አዲስ የነበረዉን ኢ-ኮሜርስን ለማካሄድ ምርጥ ስራዉን የመልቀቅ እርምጃዉ እብድ ቢመስልም የፈጠራ ባለሙያዎች ባህርይ አንድን ነገር ለመሞከር መድፈርና ዉድቀትን አለመፍራት በጄፍ ቤዞስ ዉስጥም ጎልቶ ታይቷል። በ1994 ዓ.ም. ኒዉዮርክን ለቆ ኑሮዉን በሲያትል ከተማ በማድረግ የመጀመሪያዉን የመፅሀፍ መገበያያ ድረ-ገፅ ይፍ አደረገ። የመኖርያ ቤቱን የመኪና ጋራዥ የኮምፒዉተር ተቋሙ፣ መኝታ ቤቶቹንም ቢሮ በማድረግ ከጥቂት ሠራተኞች ጋር ስራዉን ጀመረ። 300 ያክል ዘመድ ወዳጆቹን ለሙከራ ወደ ስራዉ የመገበያያ ድረ-ገፅ በመጋበዝ አነስተኛ ክፍያን እየተቀበለ መፅሃፍትን በኢንተርኔት ላይ መሸጥ የተጀመረዉ ስራ በጁላይ 1995 ዓ.ም. "amazon.com" በሚል ስም ለተጠቃሚ ክፍት አደረገ። ቤዞስ አማዞን የሚለዉን ስም ያወጣዉ በሁለት ምክንያቶች ነበር። የመጀመሪያዉ የአማዞንን ጫካ በመወከል በርካታ መፅሃፍት የሚገኙበት ግዙፍ የኢንተርኔት መደብር መሆኑን ለማሳየት ሲሆን፣ ሁለተኛዉ ደግሞ በወቅቱ ድረ-ገጾች በፊደል ቅደም ተከተል ይደረደሩ ስለነበር በቀላሉ ለሰዎችበድረ-ገጾች ማሰሻ ላይ እንዲታይ ታስቦ ነበር። የአማዞን መለያ አርማ በሶስት የመሻሻል ሂደት ዉስጥ ያለፈ ሲሆን፣ በ2000 ዓ.ም. የተደረገዉ መሻሻል ዛሬ ድረስ የምናቀዉን መልክ ሰጥቶታል። በዚህ የመለያ አርማ ላይ ያለዉ ከፍ "A" ተነስቶ "Z" ጋር የሚደርስ ቀስት ሁሉንም ነገር በአማዞን ላይ ማግኘት እንደሚቻል ለማሳየት ነዉ።

♈️ ድረ-ገጹ ተወዳጅነትን ያተረፈዉ ወድያዉኑ ነበር። በ60 ቀናት ዉስጥ ያለምንም ማስታወቂያ በበርካታ የአሜሪካ ግዛቶች እና ከ45 በላይ አገራት ዉስጥ የሚነኙ ደንበኞች ዋጋዉ ከ$20 ሺህ በላይ የሚያወጣ የመፅሃፍ ግዢን ፈጸሙ። በ1997 ዓ.ም. አማዞን አክስዮኑን ለህዝብ መሸጥ ጀመረ። ጄፍ ቤዞስ በድረ-ገጹ ላይ የሚሸጠዉን እቃ ከመፅሃፍት ባለፈ መልኩ በማሳደግ ሲዲዎቹንና ፊልሞችን አካቶ መሸጥ ጀመረ። ቀጥሎም የህጻናት አሻንጉሊቶችን፣ ልብሶችንና የኤሌክትሮኒክ እቃዎችንና በርካታ ምርቶችን መሸጡን ቀጠለ። በወቅቱ ተከስቶ በነበረዉ የኢንተርኔት ኢኮኖሚ ቀዉስ "dot com crisis" ብዙ ኩባንያዎችን ከገበያ ዉጪ ቢያደርጋቸዉም አማዞን ግን ትርፍማነቱን ቀጥሎ በ1995 ዓ.ም. ከአካሄደዉ የ500 ሺህ ዶላር ሽያጭ በጥቂት ዓመት ዉስጥ ቁጥሩ እጅግ ጨምሮ ወደ ሚሊየኖች ገባ። አማዞን በ2007 ዓ.ም. የመፅሃፍት ነባራዊ እዉነታ የሚቀይር ፈጠራ አስተዋወቀ። ኪንድል የዲጂታል መፅሃፍ ማንበቢያ "e-reader" በመፍጠር የታተሙ መፅሃፍትን ከመግዛት በተጨማሪ አንባቢዎች ዲጂታል መፅሃፍትን በኪንድል ገዝቶ በማዉረድ እንዲጠቀሙ አስቻለ። በ2011 ዓ.ም. ኪንድል ፍየር የተባለዉን ታብሌትም ይፍ አድርጎ የገበያ ፉክክርን ተቀላቀለ። ኩባንያዉ በመላዉ ዓለም በርካታ ቢሮዎች፣ የመረጃ ተቋማት (datacenters) እና ከ150 ሺህ በላይ ሰራተኞች አሉት። በሰከንድ እስከ 500 የግዢ ትዕዛዞችን ማስተናገድ የሚችለዉ አማዞን በመላዉ አለም ከ244 ሚሊየን በላይ ቋሚ ደንበኞች እንዳሉት ይነገራል። በአሁኑ ሰዓት በአመት በአማካኝ ወደ $130 ቢሊየን በላይ ሽያጭ ያከናዉናል። ጄፍ ቤዞሶ ከ$110 ቢሊየን በላይ በማካበት በአጠቃላይ የሰዉ ልጅ ታሪክ ዉስጥ ትልቁ ባለጸጋ ሊሆን በቅቷል። ከ1990ዎቹ ጀምሮ በዓለም ላይ አንደኛ ባለጸጋ የሆነዉን ቢል ጌትስ ለመጀመሪያ ጊዜ በሃብት በመብለጥ የዓለማችን 1ኛ ባለጸጋ መሆን የቻለዉም በ2017 አጋማሽ ላይ ነበር። የባለጸግነቱ እርከን በየጊዜው ቢቀያየርም በፎርብስ ዘገባ መሠረት ጄፍ ቤዞስ በሰዉ ልጅ ታሪክ ዉስጥ ቁንጮ የዓለማችን ባለጸጋ ሊሆን በቅቷል።

🔜
⏺ የYouTube channel Subscribe በማድረግ ጥሩ ጥሩ ትምህርታዊ ቪዲዮችን ይከታተሉ።
የ YouTube ቻናል ሊንክ 👇👇👇
https://www.youtube.com/channel/UCZBIP6PqUdmmagdTjbyp_AQ
👍2❤1👏1
♦️ለምን ከብርሃን ፍጥነት በላይ መጓዝ አይቻልም?

▪️አንስታይን በዚሁ የአንጻራዊ ዕይታ ጥናቱ ላይ የብርሃን ፍጥነት የአጽናፈ አለም የፍጥነት ወሰን እንደሆነ አብራርቷል። ከብርሃን ፍጥነት በላይ መጓዝ የማይታሰብና የፊዚክስ ህግን እና ሌሎች መሠረታዊ ህጎችን የሚጥስ ነዉ። ከብርሃን ፍጥነት በላይ መጓዝ ማለት ሽጉጥን ሳንተኩስ ጥይቱ ዒላማዉን መታ ማለት ነዉ። ብርሃን በሰከንድ 300 ሺህ ኪሎ ሜትር ይጓዛል።

በጠፈር ዉስጥ የሚገኝ ቁስ አካል "Higgs field" በተሰኘ ሚስጥራዊ ይዘት ዉስጥ ይንቀሳቀሳል። የተለያዩ ቁስ አካላት ከ"Higgs field" ጋር በሚያደርጉት ጥምረት የተነሳ ክብደታቸዉን "mass" ያገኛሉ። ከ"Higgs field" በተለያየ የጥንካሬ ደረጃ እና መጠን የሚፈጥሩት ጥምረትም ቁሶች የተለያየ አይነት ክብደት እንዲኖራቸዉ ያደርጋል። ብርሃን ግን ፎቶን "Photon" ከሚባሉ ቅንጣቶች "Particler" ስለተፈጠረ ክብደት የለዉም።

ክብደት ያላቸዉ ቁስ አካላት ሁሉ ምንም አይነት ፍጥነት እንዲያገኙ የሆነ ልዩ ሃይል ያስፈልጋቸዋል። የአንድን አካል ፍጥነት ወደ ብርሃን ፍጥነት እንዲቀርብ ለማድረግ ደግሞ እጅግ ከፍተኛ የሆነ ሃይል መስጠት ያስፈልጋል። ምክንያቱም ፍጥነት በጨመረ ቁጥር የአንድ ቁስ ክብደትም ስለሚጨምር ነዉ። ይህ ከፍጥነት የተነሳ የሚፈጠር የክብደት መጨመር አስገራሚ እዉነታ፣ አንድ እጅግ ኢምንት የሆነች እና ለዓይን እንኳን የማትታይ ቁስን በብርሃን ፍጥነት ለማስኬድ ልክ የለሽ ሃይል እንዲያስፈልግ ያስገድዳል። ምክንያቱም ይህች እጅግ ትንሽ የሆነች ነገር በዚህ ፍጥነት ለመሄድ ስትሻ ክብደቷ ገዝፎ ያልተወሰነና በጣም ትልቅ ስለሚሆን ነዉ። በዚህ አጽናፈ ዓለም ላይ አንድን ኢምንት ቁስ እንኳን በብርሃን ፍጥነት እንድትጓዝ ማድረግ ከባድ ከሆነ፣ የገዘፈን ነገር በዚህ ፍጥነት እንዲጓዝ ማድረግ ምን ያህል ከባድ እንደሆነ ማሰብ ይቻላል።
👍1
ጎግል ዶክስ(Google Docs) ምንድን ነው? ምንስ ለማድረግ ነው የሚጠቅመን?እንደትስ ነው መጠቀም የምንችለው?

ጎግል ዶክስ(Google Docs) ምንድን ነው?
how to user Google Docs
ጎግል ዶክስ(Google Docs) ማለት ነፃ የሆነ የመስመር ላይ(online) ፕሮግራም ሲሆን ተጠቃምሆችን
ልክ እንደ ማይክሮሶፍት ኦፍስ(microsoft office) ማይክሮሶፍት ወርድ(microsoft word) ፣ ኤክስል(microsoft excel) እና ፓወር ፖይንት(microsoft powerpoint) የመሳሰሉ ፕሮግራሞችን ማዘጋጀት ያስችላል።
ምንስ ለማድረግ ነው የሚጠቅመን?
የተለያዩ ዶክመንቶችን መስቀል(upload) እና ማውረድ(download) ያስችላል
ዶክመንቶችን በአማርኛ መፃፍ ያስችላል
በቀላሉ ዶክመንቶችን ማጋራት(share) ማድረግ ያስችላል
አንድን ዶክመነት በአንድ ግዜ ለብዙ ሰው ሆኖ መስራት ያስችላል
በወርድ ኮክመንት የተፃፉ ዶክመንቶችን ማንበብ እና መፃፍ ያስችላል
ዶክመንቶችን (save) ማድረግ አያስፈልግም እራሱ ያድርገዋል
እንደትስ ነው መጠቀም የምንችለው?
ጎግል ዶክስ(Google Docs) ለመጠቀም በሁለት አይነት መንገድ መግባት ይቻላል።
1. ጅሜል አካውንት(gmail) በመጠቀም
2. በቀጥታ https://docs.google.com መግባት ይቻላል
ጅሜል አካውንት(gmail) ተጠቅሞ ለመገግባት
1. መጀመሪያ የጎግል አካውንት(gmail) በመጠቀም ይግቡ
2. በጅሜል አካውንት ከገቡ በኋላ
በቀኝ በኩል ጥግ ላይ የአራት ማዘን ምልክት ይጫኑ
Docs የሚለውን ይምረጡ (ካላገኙት more የሚለውን ይጫኑ) አሁንም ካላኙት even more የሚለውን ይምረጡት

በቀጥታ https://docs.google.com መግባት ይቻላል
1. ቀጥታ ያለ ጅሜል መግባት ከፈለጉ ይህን URL https://docs.google.com ፅፈው ከገቡ በኋላ
የጅሜልን የመጠቀሚያ ስም(username) እና የይለፍ ቃል(password) ካስገቡ በኋላ

please click image for better view
1. የሚጠቀሙበትን ዶክመንት ዓይነትለመምረጥ ይህን ምልክት ይጫኑ
1. ወርድ(microsoft word) ከሆነ የሚፈልጉት Docs ኤክስል(microsoft excel) ከሆነ የሚፈልጉት Spread በመጨረሻም ፓወር ፖይንት(microsoft powerpoint) ከሆነ የሚፈልጉት Slides የሚለውን ይምረጡት።
የተለያዩ ቀድመው በተዘጋጁ ዶክመንቶች መጠቀም ያቻላል
ወርድ/Docs(Microsoft word) ተምፕሌት(Templates)
1. Blank
2. Resume
3. Report
4. Letters
5. Essay
6. Class notes
7. Lesson plan
8. project proposal
9. Meeting notes
ኤክስል/Spread(microsoft excel) ተምፕሌት(Templates)
1. Blank
2. To-do list
3. Annual budget
4. Monthly budget
5. Calendar
6. Schedule
7. Travel Planner
8. Wedding Planner
9. Invoice
10. Weekly time sheet
11. Expense report
12. Purchase order
13. Attendance
14. Grade book
ፓወር ፖይንት/Slides (microsoft powerpoint) ተምፕሌት(Templates)
1. Blank
2. Pitch
3. Photo album
4. Wedding
5. Lesson plan
6. Book report
7. Status report
8. Case Study
9. Consulting proposal
10. Professional profile
11. Employee certificate
12. General Presentation
13. Photo Album
14. Recipe book
15. Profolio
16. Lookbook
17. party invite
⏺ የYouTube channel Subscribe በማድረግ ጥሩ ጥሩ ትምህርታዊ ቪዲዮችን ይከታተሉ።
የ YouTube ቻናል ሊንክ 👇👇👇
https://www.youtube.com/channel/UCZBIP6PqUdmmagdTjbyp_AQ
👍7😁1
አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ-Artificial Intelligence
🔷 መግቢያ
አሁን በአለንበት ዘመን የኢንተርኔት ቴክኖሎጂ ዓለምን ከጥግ እስከ ጥግ እያዳረሰ፤ ዕውቀትን እና መረጃን የማሰራጨት እና የማጋራት ባህል በከፍተኛ ደረጃ እየጨመረ ነው፡፡ በመሆኑም በውስብስብነቱ እና በአስቸጋሪነቱ ምክንያት በብዙ የሳይንስ ምሁራን ዘንድ ሳይደፈር ለዘመናት በአዝጋሚ የእድገት ደረጃ ላይ የቆየውን “አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ” ቴክኖሎጂን በፍጥነት እያሳደገው ይገኛል፡፡ ዕውቀት ከአንዱ የዓለም ክፍል ወደሌላኛው የዓለም ክፍል በፍጥነት እና በብዛት መሰራጨቱ፤ ችግሮችን በጋራ አቅርቦ የመፍታት እና የመማማር ባህል መዳበሩ፤ በተለያዩ የአለም ክፍሎች የሚገኙ አፍቅሮተ-ቴክኖሎጂ ያላቸው ወጣቶች (Tech geeks) በብዛት መሳተፋቸው፤ ለዘርፉ በከፍተኛ ደረጃ ማደግ እንደ ምክንያትነት የሚጠቀሱ ናቸው፡፡
በዚህ ዘርፍ ለሰው ልጅ የሚጠቅሙ አያሌ ግኝቶች በስራ ላይ ውለዋል፡፡ከነዚህም ውስጥ ከባድ እና አሰልቺ የሆኑ ተደጋጋሚ ስራዎችን በፍጥነት እና ያለምንም ስህተት የሚያከናውኑ ግዙፍ የፋብሪካ ሮቦቶችን፤ እጅግ ሰፊ ከሆነ የዕውቀት ውቅያኖስ ውስጥ ተፈላጊውን መረጃ በአጭር ጊዜ እና በከፍተኛ ፍጥነት የሚያቀርቡ ሶፍትዌሮችን፤ያለምንም አሽከርካሪ ራሳቸውን ችለው የሚንቀሳቀሱ መኪናዎችን.. ወዘተ መጥቀስ ይቻላል፡፡
አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ እና ሮቦቲክስ ምን እና ምን ናቸው
አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ማመዛዘንን (ምክኒያታዊነትን)፣ ዕውቀትን፣ ዕቅድን፣ መማርን እና ቋንቋን በፅንሰ-ሀሳብ ደረጃ ሚስጥራቸውን መፍታት እና በሳይንሳዊ ሂደት መተንተን ነው፡፡ የሰው ልጅ አነኚህን ክህሎቶች የሚያዳብረው በተጠናና በተቀመረ መልኩ ሳይሆን በተፈጥሮ የህይወት ዑደት ውስጥ ነው፡፡ በተፈጥሮአዊ ልምምድ የሚዳብሩትን እነዚህን ክህሎቶች በቀመር እና በሳይንሳዊ ጥናት ለመተንተን መሞከር ግን እጅግ ፈታኝ ተግባር ነው፡፡ አንድ ህፃን ልጅ እየተኮላተፈ አማርኛ ሲናገር፤ ከዛም በአጭር ጊዜ ቋንቋውን ሲያቀላጥፈው ማየት ለብዙዎቻችን አስገራሚ አይሆንም፡፡ ሆኖም ይህንን የክህሎት ሒደት በሳይንሳዊ ትንተና ፈትቶ እና ተመሳሳይ ባህሪያትን ለማሽኖች ወይም ለሶፍትዌሮች አላብሶ ማላበስ መቻል ግን ከፍተኛ ስኬት ነው፡፡ አንዳንዴም እንዲህ ያለው ተግባር የፈጣሪን ሚና እንደመተካት ሊቆጠር ይችላል፡፡ቢሆንም ብዙ ወጣቶችን ወደዚህ ዘርፍ እንዲሳቡ ያደረጋቸው ዋነኛ ምክንያት ይህ የዘርፉ ውስብስብነት የፈጠረው ተግዳሮትን የመፍታት እልህ እና ተፈጥሮን አስመስሎ እና ተንትኖ የማቅረብ ረሀብ ነው፡፡
በሌላ በኩል ሮቦቲክስ የሜካኒካል ምህነድስና፣ ኤሌክትሮኒክ ምህንድስና፣ እና የኮምፒውተር ሳይንስ ቅርንጫፍ ሲሆን፤ የአርቴፊሻል ኢንተለጀንስን ዕውቀት በከፍተኛ ደረጃ በግብዓትነት በመጠቀም የሚንቀሳቀሱ፣ እንደሰው አመዛዝነው ውሳኔ የሚሰጡ፣ ሰውን ተክተው አልያም ከሰውልጅ ጎን ለጎን ሆነው የተለያዩ ተግባራትን የሚከውኑ ሜካኒካዊ እና ኤሌክትሮኒካዊ ሮቦቶችን የሚያጠና ዘርፍ ነው፡፡ ዘርፉ ቁስ አካላዊ ሮቦቶችን ብቻ ሳይሆን መረጃን የሚያቀነባብሩ ብልህ የኮምቲውተር ሲስተሞችንም ያጠቃልላል፡፡
አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ስለ ማመዛዘን (ምክኒያታዊነት)፣ ዕውቀት፣ ዕቅድ፣ መማር እና ቋንቋ ፅንሰ-ሀሳባዊ ምንነት በሳይንሳዊ ትንታኔ ሲያቀርብ፤ ሮቦቲክስ ደግሞ ከአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ያገኘውን የውስብስብ ፅንሰ-ሀሳቦች ምንነት እና ሌሎች ተጓዳኝ የምህንድስና ዕውቀት በመጨመር ለተለያዩ ጥቅም የሚውሉ ሮቦቶችን ይሰራል፡፡
🔷 ታሪክዊ ሂደት
ግኡዛንን እንደሚያስቡ እና ባለአዕምሮ ፉጡራን አድርጎ መስራት ጥንት የግሪክ፣ የግብፅ፣ እና ሌሎችም ጥንታዊ ገናና የሰውልጅ ስልጣኔ ታሪክ ውስጥ ጉልህ ስፍራ ነበራቸው፡፡ በተለይ በግሪክ እና ግብፅ ጥንታዊ ስልጣኔ ውስጥ ለጣኦት አምልኮ የሚውሉ የሚንቀሳቀሱ ግኡዝ አካላትን መስራት የተለመደ ነበር፡፡ እነዚህ የሰው ልጅ ፍላጎቶች የተለያዩ መልኮችን ይዘው እና አድገው እስከ 2ኛው የዓለም ጦርነት ድረስ በመዝለቅ፤ አሁን ላለንበት የዲጂታል ቴክኖሎጂ እና አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ምዕራፍ ወሳኝ መሰረት የጣለውን ‹‹የአለን ቱሪንግ››ን የምርምር ውጤት ወልደዋል፡፡
ከአመታት በኃላ፣ እ.ኤ.አ በ1956 በዶረቱሙን ኮሌጅ ግቢ በተደረገው ኮንፍረንስ የተመሰረተው የአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ጥናት፤ በኮንፍራንሱ ተሳታፊዎች እና በተማሪዎቻቸው አማካኝነት ለብዙ አስርታት የመስኩ ብቸኛ ተዋናይ ሆነው ቆይተዋል፡፡ ተማሪዎቹ በወቅቱ ለብዙዎች አስገራሚ ሊባሉ የሚችሉ ‹‹ምጡቅ›› የኮምፒውተር ፕሮግራሞችን በመስራት ለእይታ አቅርበው ነበር፡፡ ቼዝ ተጫወተው የሚያሸንፉ፤ አልጄብራን እንዲሁም የሎጂክ ቴረም ጥያቄዎችን የሚፈቱ እና እንግሊዘኛ የሚናገሩ የኮምፒውተር ፕሮግራሞች ተማሪዎቹ ይሰሯቸው ከነበሩት ውስጥ ተጠቃሽ ናቸው፡፡ ከ1960 ጀምሮ የዚህ ምርምር የገቢ ምንጭ የአሜሪካ መከላከያ ተቋም ስለነበረ በ1974 የገንዘብ ድጋፉ በመቋረጡ የዘርፉም እድገት በከፍተኛ ሁኔታ ቀንሶ ነበር፡፡ ይሁን እንጂ በ1980 መጀመሪያ አካባቢ በተለያዩ የሙያ ዘርፎች የባለሙያ ትንታኔ የመስጠት ችሎታ የነበረው
‹‹የኤክስፐርት ሲስተም›› ከፍተኛ ተቀባይነት በማግኘቱ ዘርፉ እንደገና አንሰራራ፡፡ በዚህም ምክንያት የዘርፉ ጠቅላላ ገቢ እስከ 1ቢሊዮን ዶላር ደርሶ ነበር፡፡ ይሁን እንጂ እንደገና በ1987 አካባቢ ከሊስፕ ኮምፒውተር ገበያ ማጣት ጋር ተያይዞ ገበያው በመቀዛቀዙ ሁለተኛውን እና ረጅሙን የድብርት(Depression) ጊዜ አሳልፏል፡፡ ከዛም ከ1990ዎቹ ጊዜ እስከ 21ኛው ክፍለ ዘመን መጀመሪያዎቹ ድረስ ድምፁን አጥፍቶም ቢሆን ከፍተኛ ስራ ሰርቷል፡፡
በ1997 ‹‹ዲፕ ብሉ›› የተባለው የኮምፒውተር ቼዝ ተጫዋች በወቅቱ በቼዝ ጨዋታ ሻምፒዬን የነበረውን ጌሪ ካስፓሮቭን በማሸነፍ አለምን ጉድ አሰኝቶ አልፏል፡፡ በ2011 የIBM ስሪት የሆነው ዋትሰን የተባለው የኮምፒወተር ሮቦት በ ጆፓራዳይ የቴሌቭዥን የጥያቄ እና መልስ ሾው ላይ በመሳተፍ ብራድ ሩተር እና ጆን ክኒንስ የተባሉትን የጥያቄና መልስ ውድድር ቻምፒዎኖቹን በከፍተኛ የነጥብ ልዩነት አሸንፏቸዋል፡፡
🔷 የአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ትግበራ በተለያዩ ዘርፎች ውስጥ
አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ በህክምና፣ ህግ፣ ሮቦቲክስ፣ ሪሞት ሴንሲንግ፣ ትራንስፖርት ዘርፎች ላይ ተግባራዊ የሆነ ቢሆንም፤ አንዴ ለገበያ ከቀረበ እና በሰፊው ጥቅም ላይ ከዋለ፤ አሰራሩም ከታወቀ በኃላ ግን ‹‹ብልህ›› መሆኑ ያከትምለታል ብለው ብዙዎች ይከራከራሉ፡፡ በዚህም ምክንያት በብዙ ሺህ የኢንደስትሪ ማሽኖች ላይ ተገጥመው የሚገኙ ቢሆኑም ለረጅም ጊዜ ለብልህነታቸው ይህ ነው የሚባል እውቅና ሲሰጣቸው አይሰተዋልም፡፡
🔷 በህክምና እና ጤና ተቋማት
የተለያዩ የህክምና ተቋማት የውስጥ አስተዳደራዊ አሰራራቸውን ለማቀላጠፍም ሆነ ሳይንሳዊ መረጃዎችን ለህክምና ባለሙያች ለመለገስ አርቴፊሻል ኢንተለጀንስን እይተጠቀሙ ይገኛሉ፡፡ የአስተኝቶ ማከም ቀጠሮዎችን በማመቻቸት ሆነ የባለሙያዎችን የስራ ፈረቃ ፕሮግራም በማውጣት ላቅ ያለ አስተዳደራዊ ጥቅም ይሰጣሉ፡፡ በተጨማሪም በኮምፒውተር የታገዘ ምስል በማንሳት እንደ ካንሰር ያሉ ችግሮችን ለባለሙያዎች በመጠቆም፤ እጅግ ብዙ ከሆኑ የሜዲካል ዕውቀቶች ውስጥ ተፈላጊውን መረጃ አስሶ ለባለሙያው በመስጠት ሙያዊ አበርክቶ ያደርጋሉ፡፡
የቀጠለ........ በቅድሚያ ከላይ ያለውን ያንብቡ...
አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ-Artificial Intelligence
🔷 በከባድ ኢንደስትሪዎች
ለሰው ልጅ እጅግ አደገኛ በሆኑ፣ ድግግሞሽ በሚበዛባቸው አድካሚ የከባድ ኢንደስትሪ ስራዎች ውስጥ የአርቴፊሻል ኢንተለጀንስን ዕውቀት የሚጠቀሙት ሮቦቶች የማይተካ ሚና ይጫወታሉ፡፡ ስለሆነም የሰው ልጆችን ከአደጋ ይታደጋሉ፣ ስህተት ስለማይሰሩ እና ስለማይደክማቸው ከፍተኛ ውጤት ያስመዘግባሉ፡፡ በአሁኑ ወቅት በመኪና ምርት፣ በማዕድን ማውጣት ስራ እና ትላልቅ የፋብሪካ ማሽኖችን በሚያመርቱ ኢንደስትሪዎች ውስጥ ከፍተኛ አገልግሎት በመስጠት ላይ ናቸው፡፡
🔷 በትራንስፖርት
ሹፌር አልባ መኪኖች ራሳቸውን በራሳቸው የሚያንቀሳቅሱ፤ የተሰጣቸውን ትእዛዝ ተቀብለው ሰውንም ሆነ ዕቃ የተፈለገው ቦታ የሚያደርሱ፤ ተሰሳስተው አልያም ደክሟቸው በቸልተኝነት አደጋን የማያደርሱ መኪኖች የአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ የምርምርና ዕውቀት ውጤቶች ናቸው፡፡ ምንም እንኳን በአሁኑ ጊዜ በስፋት ለጥቅም ባይውሉም በGoogleX ፕሮጀክት በመሰራት ላይ ያለው አሽከርካሪ አልባ መኪና ተጠቃሽ ነው፡፡ ይህ መኪና ‹‹ጉግል ሹፌር›› የሚባል ሶፍትዌር የተገጠመለት ሲሆን የአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ዕውቀትን ተግባራዊ በማድረግ የተሰራ ሶፍትዌር ነው፡፡ መኪናው በአሁኑ ወቅት በሙከራ ላይ ይገኛል፡፡
የሥነ ምግባር እና የፍልስፍና ጥያቄዎች
አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ በተወሰነ ደረጃም ቢሆን የሰው ልጅ አስተሳሰብ፣ ባህሪ እና ጠባይ ለማሽኖች የሚያላብስ የሳይንስ ዘርፍ እንደሆኑ መጠን፤ ከዚህ ጋር ተያይዞ በዛ ያሉ የሞራል፣ የስነምግባር እና የፍልስፍና ጥያቄዎችን ማስነሳቱ አልቀረም፡፡ ከፍልስፍና ጥያቄዎቹም ውስጥ ከዚህ በታች የተዘረዘሩት ሶስቱ በዋነኛነት ተጠቃሽ ናቸው፡-
1. ማሽኖች የሰው ልጅ ሊፈታቸው የሚችላቸውን ችግሮ በሙሉ የመፍታተት አቅም ይኖራቸዋልን? ወይስ ማሽኖችን ‹‹ሰው›› የማድረግ ጥረት ገደብ አለው?
2. የአርቴፊሻል ኢንተለጀንስን ባህሪያት የተላበሱ ማሽኖች አደገኛ ሊሆኑ ይችላሉን? በስነ-ስርአት እና ወግ ባለው መልኩ ጥቅም ላይ እንዲውሉ፤ ብሎም በምንም አይነት መልኩ ከቁጥጥር ውጭ የሆነ ባህሪ እንዳይላበሱ ማድረግ ይቻላልን?
3. ማሽኖችን ልክ እንደ ሰው ባለአእመሮ እና ባለህሊና ማድረግ ይቻላልን? እንደ ሰው ልጆችስ መብት ይኖራቸዋል? አውቀው እና በራሳቸው ተነሳሽነት ተንቀሳቅሰው በሰው ልጅ ላይ ጉዳት ማድረስ ይችላሉን?
ከላይ በተነሱት ጥያቄዎች ዙርያ የተለያዩ ሙሁራን የየራሳቸውን ፅሁፍ እያቀረቡ በንድፈ-ሀሳብ ደረጃ የተከራከሩ ሲሆን፤ ጥያቄዎቹ ምላሽ ሊያገኙ የሚችሉት በጊዜ ሒደት ብቻ ነው፡፡ በዚህም ምክንያት የተለያየ ጥግ ይዘው ጥያቄዎቹን ለመመለስ የሞከሩም ሆኑ የሚሞክሩ ምሁራን ትክክለኛነታቸው የሚረጋገጠው በዘርፉ የተፈጥሮ እድገት ሂደት ውስጥ ብቻ ይሆናል ማለት ነው፡፡ እዚህ ጋር ሳይጠቀስ የማይታለፈው አንደኛው ጥያቄ ከሞራል ጋር የተገናኘው ነው፡፡ የሰው ልጆች ከአደጉበት ባህል፣ ከኖሩበት ዘመን ጋር በማቆራኘት ስለ ሞራል ምንነት ትርጓሜ ሲሰጡ ይታያል፡፡ በዚህም የተነሳ በተለያዩ የህይወት ውሳኔዎቻቸው ላይ ይህ የሞራል ግንዛቤ የራሱን አስተዋፅኦ ያሳድራል፡፡ ሞራል የጊዜ እና የባህል ተፅዕኖ ስለሚበዛበት አንድ ወጥ የሆነ ሞራላዊ ምንነት ለማሽኖች እንዲላበሱ የሚደረገውን ምርምር በዛው ልክ ወጥ ያልሆነ እና ውስብስብ እንዲሆን አድርጎታል፡፡ ይሁን እንጂ ከላይ በተነሱት ፅንሰ-ሀሳባዊ የፍልስፍና ጥያቄዎች ዙርያ የሚደረጉት ምሁራዊ ክርክሮች እና ትንታኔዎች አሁንም ድረስ እንደቀጠሉ ናቸው፡፡
ከሞራል እና ስነ-ምግባር ጋራ የሚነሱ ጥያቄዎች እና በምሁራን የሚሰጡ ትንታኔዎች አከራካሪ፣ መሳጭ እና የሰውን ልጅ የወደፊት እጣ ፈንታ የሚወስኑ ስለሚሆኑ፤ በቀጣይ በዚህ ድረ-ገፅ የተለያዪ ፅሁፎችን በትንታኔ መልክ ለማቅረብ ይሞከራል፡፡
🔷 ማጠቃለያ
ብልህ እና እንደ ሰው ልጅ የሚያስቡ ቁስ አካላትን ለመፍጠር የሚደረገው ሳይንሳዊ ምርምር እና ዕውቀት ወደፊት የሰውን ልጅ የአኗኗር ስልት በከፍተኛ ሁኔታ እንደሚቀይር የማያጠራጥር ነው፡፡ አደጋን የሚቀንሱ፣ ጤንነትን የሚያሻሻሉ፣ ከፍተኛ ምርትን የሚያስገኙ፣ ወዘተ ጥቅሞችን እየሰጡ የሚገኙ እና ወደፊትም በላቀ ጥራት እና ውስብስብነት የሰውን ልጅ ህይወት የሚያቀሉ የአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ውጤቶች በዚህ አጭር ዕሁፍ ለመዳሰስ መሞከር ‹‹አባይን በጭልፋ›› እንደ መዝገን ይሆንብኛል፡፡
በዚህ ዘርፍ አያሌ እና ተነግረው የማያልቁ ግኝቶች፣ በምርምር ላይ ያሉ ዕውቀት፣ በዘርፉ ላይ የተነሱ እና የሚነሱ ጥያቄዎች፣ ወዘተ በመረጃነት ይገኛሉ፡፡በመሆኑም በዚህ ድረ-ገፅ ከዘርፉ ጋር ተያያዥ እና ጠቃሚ ናቸው የምንላቸውን ዜናዎች፣ አርቲክሎች(መጣጥፎች)፣ ፖድካስቶችን የምናቀርብ ሲሆን፤ የዘርፉን ውስብስብ ዕውቀትና ልምድ የሚያንፀባርቁ የምሁራን ክርክሮችን ጭምር በየጊዜው በቀላል አገላለፅ ለማቅረብ እንሞክራለን፡፡
👍2
በኮምፒውተር Videos Editing የሰርግ, የምረቃ, የልደት, የቤተሰብ,ፎቶዎችንና ቪዲዮችን ለማቀናበር የሚያስችል ምርጥ ቪዲዮ ካታች ያላውን ሊንክ በመጫን ይመልከቱ።
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
https://youtu.be/-hlhERSvULI

ሶፍትዌሩን ቴሌግራም ላይ ማግኘት ይችላሉ
ቴሌግራም ቻናሌ
https://t.me/MuhammedComputerTechnology/1273
👍1
የበይነ - መረብ ንግድ (Online Business)

ይህን ቻናል ከጀመርን ጀምሮ፤ በቢዝነስ ዙርያ ብዙ ምክረ - ሃሳቦችን እያጋራን ሰንብተናል። አብዛኛው ተደራሲም (የቻናላችን ቤተሰቦች) በመረጃዎቹ እየተጠቀሙ እና እየተማሩ መሆኑን በውስጥ መስመር እና በሃሳብ መስጫ (Comment Box) ሲያጋሩን ነበር። የተለያዩ ጥያቄዎች እየተጠየቁ ምላሽ በተናጠል ስንሰጥ ነበር።

ነገር ግን ከአብዛኛው ቤተሰብ፤ አንድ ተመሳሳይ ጥያቄ በተደጋጋሚ በየጊዜው ሲነሳልን አስተዋልን፤ እሱም "Online Business እንዴት መስራት እንችላለን? በትርፍ ሰዓታችን ኢንተርኔትን በመጠቀም እና በመስራት እንዴት ገቢ ማግኘት እንችላለን?" የሚል ነው።

ይህ ጥያቄ መልኩን እየቀያየረ ረጅም ጊዜ ሲጠየቅ የነበር ቢሆንም በስራ መደራረብ እና ተገቢውን መልስ ለመስጠት ደግሞ ጥናትም ማድረግ ያስፈልግ ስለነበር በጊዜው ማቅረብ አልቻልንም። ለዚህም ከልብ ይቅርታ እንጠይቃለን። ዛሬ በተቻለን አቅም ከኢትዮጵያ ገበያ እና አኗኗር ጋር የተስማማ የበይነ መረብ ንግድ (Online Business ) እንዴት መስራት እንደሚቻል እና በዛም ተጨማሪ ገቢን እንዴት መፍጠር እንደምንችል ለማየት እንሞክራለን።

🖥🖥🖥

ያለንበት ዘመን፤ የዲጂታል ዘመን ስለመሆኑ ምንም የሚያሻማ ጉዳይ አይደለም። አብዛኛውን የሕይወታችንን ክፍል የበይነ - መረቡ (Internet ) ዓለም ጥገኛ እየሆነ ነው። ይህንንም የቫል ኖህ ሃራሪ የተባለ ጸሐፊ " 21 Lessons for the 21st century " በሚል መጽሐፉ በጥሩ ገልጾታል። ከትምህርት እስከ ስራ፣ ከንግድ እስከ ትዳር፣ ከስብሰባ እስከ ስርዓተ ዓምልኮ፣ ከጉርብትና እስከ የዓለም ጦርነት (Cyber War)፤ ሁሉም ነገር በበይነ - መረብ (Internet) ሆኗል።

ታዲያ "በፍየል ዘመን በግ መሆን ለመታረድ ነው" እንዳሉት አንድ አባት፤ በዚህ በዲጅታል ዘመን እኛም ከጊዜው ጋር እኩል ካልተራመድን ወዳቂ ነን። እናም ከጊዜው ጋር እኩል ከምንሄድባቸው ጉዳዮች አንዱ አብዛኛውን የሕይወታችንን ክፍል የምናሳልፍበትን "ስራ" ዲጂታላይዝ በማድረግ ነው። ስራችንን፣ ንግዳችንን ዲጂታላይዝ ማድረግ እና አዲስ ስራዎችን በበይነ - መረቡ አማካኝነት መስራት ለነገ የማይባል ጉዳይ ነው።

📡 ታክሲ ⚰ በ Uber (Ride) ተተካ

📡 ሆቴል ⚰በ AirBnB ተተካ

📡 ሱቅ እና ሱፐርማርኬቶች ⚰ በ Amazon፣ Alibaba፣ በእኛም ሀገር ጅምር ላይ ያሉ እየተኩት ነው።

📡 የአዳራሽ ኪራዮች ⚰ በ Zoom ተተኩ

📡 ሲኒማ ⚰ በ Netflix፣ Amazonprime፣ ሶደሬቲዩብ ተተኩ

📡 ጥሬ ገንዘብ ⚰ በ ክሪፕቶከረንሲ ተተካ

📡 ምግብ ቤቶች ⚰ በ Online ሬስቶራንቶች (Pizza Hut እና ዴሊቨሪ አዲስ) እየተተኩ ነው።

እንደዚህ ብዙ መዘርዘር ይቻላል። በይነ - መረቡ እየገዘፈ እና Dominate እያረገ ነው።

እሺ ጥሩ! የበይነ - መረብን (Internet) አስፈላጊነት ተረዳሁ። ተጽእኖውንም አየሁ። ታዲያ እንዴት ነው የበይነ - መረብ ንግድ (Online Business) መጀመር የምችለው? ምን አይነትስ የ Online Business ነው ገቢ ሊያስገኝልኝ የሚችለው?

መልካም!

የበይነ - መረብ ንግድ ውስጥ ከመግባት ወይም ለመግባት ከማሰብ በፊት በመጀመሪያ የንግድን ጽንሰ ሃሳብ (Concept) መረዳት ያስፈልጋል። ንግድን (Business) በአጭሩ ስናሰቅምጠው ወይንም ቢዝነስ የሚወለደው ከሁለት ቅርጫቶች ነው።

ንግድ

💡 ያለን የኖረን ችግር ፈልገን፣ አጥንተን መጠገን ወይም መቅረፍ (We find a problem and we fix it)

💡 ያለ የሚታይ እጥረትን መሙላት (We find a shortage or demand and fill it)

በአለም ላይ የምናያቸው ከትልልቅ እስከ አነስተኛ ቢዝነሶች መነሻቸው (Motive) ከዚህ አይወጣም።

💡 አንደኛው ላይ ፦ ህብረተሰቡ ( consumer) በጣም የሚያስፈልገው ቁሳቁስ ወይም አገልግሎት የሌለ ከሆነ፤ አልያም ደሞ ያ ህብረተሰብ አገልግሎቱ ወይም ቁሱ ኖሮት ነገር ግን ጊዜ እና ጉልበት የሚፈጅበት ከሆነ ፦ አንድ ሰው ይህን ጉድለት በፈጠራ በመታገዝ ወደ ቢዝነስ መቀየር ይችላል ማለት ነው።

ለምሳሌ፦ የታክሲ አገልግሎት ለዘመናት የኖረ ሆኖ ሳለ ለተገልጋዩ ግን እንደልብ አልነበረም። ስለዚህ አንተርፕረነሮች የታክሲን ስራ አዘምነው (ከዚ በፊት ያልተሞከረ) ፣ ለተገልጋዩ በሩ ድረስ የሚመጣለት አገልግሎት ፈጠሩ። አሁን ያ ፈጠራ በዓለም ላይ ቢልየን ዶላሮችን እያንቀሳቀሰ ነው። ይህን ሲስተም (uber፣ Ride) የፈጠሩት ሰዎች አንድም ታክሲ የላቸውም። ነገር ግን መቶ ሺዎች መኪኖችን ያንቀሳቅሳሉ። በፈጠራ !

ሌላ ምሳሌ ለመጥቀስ፦ በሀገራችን የመኪኖች የካርበን ልቀት በጣም እየጨመረ መጥቷል። በዚህም አየሩ በጣም ከመበከሉ የተነሳ በተለይ ጠዋት እና ማታ ላይ ጉም ሰርቶ ከባቢ አየር ላይ ተንሳፎ ይታያል። ሰዎች ንጹህ አየር መተንፈስ እያቃታቸው ነው። ስለዚህ ለዚህ ፨ችግር፨ አንድ ፈጠራ (Innovation) አንድ ሰው ቢሰራ፡ ማለትም ከባቢ አየር ላይ ያለውን ካርበን (CO2) እየሳበ (suck) የሚያጣራ እና ካርበኑን የሚያጠራቅም አነስተኛ ሳጥን ቢያዘጋጅ፤ ይችንም ሳጥን በየ ስልክ እንጨቱ በየመንገድ ዳር ላይ ቢሰቅላት። ይህን በማድረግም አንድም የተበከለ አየር የማጣራት አገልግሎት ለህብረተሰቡ ይሰጣል፤ ሁለተኛ በሳጥኗ ውስጥ የሚጠራቀመውን ካርበን (CO2) በመሸጥ ተጨማሪ ገቢ ያገኝበታል። ይህን ማድረግ የሚችል ሰው በቀላሉ ቢዝነስ አቋቋመ (someone founded a business) እንላለን፤ ምርቱንም ከግለሰብ እስከ ሃገር ሊገዙት ይችላሉ። (⭕️ይህ የጸሐፊው የፈጠራ ሃሳብ ነው።)

(ጥያቄ፦ በነገራችን ላይ አየር ላይ የሚንሳፈፈው ካርቦንዳይኦክሳይድ (CO2) በብዙ ዶላሮች እንደሚሸጥ ታውቃላችሁ? )

💡ሁለተኛው ደሞ በህብረተሰቡ ውስጥ ያለን ከፍተኛ ፍላጎት (demand) ለይቶ አይቶ ያን ፍላጎት በማሟላት ገቢ ማግኘት ነው። ለዚህ ቀላል ምሳሌ በእኛ ሃገር ያለው የትራንስፖርት እጥረት ነው። የትራንስፖርት አገልግሎት በማቅረብ ቢዝነስ መጀመር። ሌላው የምግብ ፍጆታ እንደ ዘይትና ስኳር። ከፍተኛ demand አለ። ይህንንም ስራውን አጥንቶ መስራት ራሱን የቻለ ቢዝነስ ውስጥ ይከታል።

፨፨፨፨

ንግድ (business) የፍላጎት እና አቅርቦት (demand and supply) ጉዳይ ነው። የንግድ እስትንፋሱ እነዚህ ሁለቱ ናቸው። ከሁለቱ አንዱ ከሌለ ቢዝነስ የለም! ቆም ብላችሁ በአካባቢያችሁ ወይም በሃገታችን ያለውን ፍላጎት (demand) እስቲ አስተውሉት። የስራ ፈጠራ የሚጀምረው ከዛ ነው።

ሰው ምን ይፈልጋል?

ምን ተቸግሯል?

ከዛ ለነዚህ ጥያቆዎች መልስ ፈልጉላቸው። ያ ለነዚህ ጥያቄዎች የምታገኙት መልስ ነው እንግዲህ ቢዝነስ የሚሆነው፤ እናንተንም አንተርፕረነር የሚያደርጋችሁ።

ŠFekadu_G21

ይቀጥላል......
ይቀጥል?
👍4
የበይነ - መረብ ንግድ (Online Business)

ክፍል 2 (ከትላንቱ የቀጠለ)

አሁን ወደ ተነሳንበት የበይነ - መረብ ንግድ (Online Business) እንመለስ። ከላይ ባብራራነው ጽንሰ ሃሳብ መሰረት የበይነ - መረብ ንግድ መጀመር እና ሌላ የገቢ ምንጭ መፍጠር ይቻላል። ነገር ግን ከዘልማዳዊው "ያበላል ወይስ አያበላም" አይነት ያልተጨበጠ ጥያቄ መውጣት እና መጠነኛ የገበያ ጥናት ማድረግ ያስፈልጋል።

፨ ምን ይፈለጋል? ህብረተሰቡ በጣም የሚፈልገው እና የጎደለው ነገር ምንድነው?

ይህ ጥያቄ የትኛው ቢዝነስ ትርፋማ እንደሆነ በራሱ ጠቋሚ ነው። ይህን ጥያቄ ስትጠይቁ መልሱ፦

፨ ወይ ያ ህብረተሰቡ የሚፈልገው ነገር ጭራሽ የለም፤ አልተፈጠረም።

፨ ወይንም አለ፤ ነገር ግን ከፍተኛ እጥረት አለበት።

ስለሆነም በነዚህ ስሌት መነሻነት አንድ ሰው ወይ ፈጣሪ (Innovator) ይሆናል። አልያም ያለን የጎደለን ነገር በማቅረብ በቀላሉ ወደ ንግዱ ይገባል ማለት ነው።

ወደ Online business ስትገቡም በዚህ ጥያቄ መነሻነት ቢሆን መልካም ነው። መታወቅ ያለበት ነገር ቢኖር የግል ስራን መጀመር ቀላል እንዳልሆነ ነው። ቢዝነስ ሲባል ባጠቃላይ እስኪጠነክር እና እውቅናን አትርፎ ደንበኞችን እስኪይዝ ድረስ ውጣ ውረዶች አሉት ። የበይነ መረብ ንግድም ከዚህ አይለይም። ገበያው ላይ ሰርጎ ለመግባት የሚወስደው ጊዜ እና ትእግስት አለ። ይህን ከተረዳን እና ከተስማማን Online biz ለመስራት ( እንደ ስራው አይነት) የሚያስፈልጉ ቁሳቁስ አሉ። ስማርት ስልክ፣ ኢንተርኔት፣ ኮምፒውተር ፣ ካሜራ እና መሰል ኤሌክትሮኒክስ የሚያስፈልጉ ሲሆን ስማርት ስልክ እና ኢንተርኔት መሰረታዊ እቃዎች ናቸው።

እነዚህን ቁሳቁስ በመጠቀም ልንሰራቸው የምንችላቸው የonline biz አይነቶች በብዛት አሉ። በውጩ አለም በዚህ መንገድ በጣም ብዙ የሚሰሩ ስራዎች ያሉ ሲሆን ወደኛ አገር ስንመጣ ግን በመንግስታዊ ህጎች መጥበቅ፣ አዳዲስ ፈጠራዎች ባለመኖራቸው እና የኢንተርኔት ተደራሽነቱም አናሳ በመሆኑ በበይነ መረቡ (online) ላይ የሚሰሩ ስራዎች ውስን ናቸው። የተወሰኑት እና ከእኛ ሀገር ህግና ገበያ ጋር የሚሄዱትን ከዚ ቀጥሎ ለማየት እንሞክራለን።

1⃣ Youtube ፕሮግራሞች ማዘጋጀት

ይሄ በጣም ቀላል እና አለም ላይ በጣም ብዙ ሰዎች እየተጠቀሙበት ያለ አንድ የገቢ ምንጭ ነው። ሙሉ ስራው አለቃ እና አዛዥ ሳይኖርባችሁ በራሳችሁ ተነሳሽነት እና ፈጠራ ብቻ የምትሰሩት ስራ ነው። ዩቱብ አዘጋጅ ለመሆን ደሞ የሞባይል ስልካችሁ ካሜራና ኢንተርኔት በቂ ናቸው። በዚህ መነሳት እና ወደተሻለ ጥራት ማደግ ይቻላል። ነገር ግን ከስራችሁ ተጠቃሚ እና ትርፋማ ለመሆን የምታዘጋጇቸው ቪድዮዎች የሰውን ቀልብ የሚገዙና የሚወደዱ መሆን አለባቸው። ምክንያቱም ትርፋችሁ እና ገቢያችሁ የሚወሰነው ስራዎቻችሁን በሚያይላችሁ የሰው ብዛት ስለሆነ።

አሁንም ከላይ እንደጠቀስነው በዚህም ስራ ትርፋማ ለመሆን "ሰው ምን ይፈልጋል?" የሚለው ጥያቄ ወሳኝ ነው። በዚህ መሰረት በየእለቱም ሆነ በየሳምንቱ ቪድዮዎችን በማዘጋጀትና በመልቀቅ አንድ የገቢ ምንጭ ማግኛት ይቻላል። የአከፋፈል ሁኔታውን፣ መጠኑን እና ትርፉን google በማድረግ ማወቅ ትችላላችሁ። ወይንም በዚህ ቻናላችን ወደፊት እንዳስሰው ይሆናል።

ጥቆማ፦

⏺ ኦንላይን ትምህርቶችን በዩቱብ ማዘጋጀት (እንደ ጊታር ማሰልጠን፣ የ 8ኛ እና 12ኛ ክፍል ተፈታኞችን ማብቃት ወይ ገለጻ ማድረግ፣ ኤሌክትሮኒክስ ጥገና በቀላል አማርኛ፣ ቤት አጠጋገን እና ቀለም አቀባብ) ወዘተ...ህብረተሰቡ ራሱን ሊረዳባቸው እና ሊያሻሽልባቸው የሚችሉ እውቀቶችን ማካፈል፤ ማቅረብ፤


ማሳሰቢያ፦ በተቻለ መጠን የጥላቻ ንግግሮችን እና ፖለቲካ አፍራሽ ነገሮች በመጠቀም ገቢ ለማግኘት አንጣር!!! ሃገር አፍርሶ ህዝብ አጋጭቶ የሚመጣ ገቢ ገደል መግቢያ ነው!

2⃣ Online ሱቆች

እነዚህ አሁን ላይ እኛ ሃገር በጣም በብዛት እየተሰራበት ይገኛል። ብዙ ተቋማት እና ግለሰቦች በfacebook እና በቴሌግራም ግብይት መፈጸም ከጀመሩ ሰነባብቷል። እናንተም የራሳችሁ ቻናል እና facebook page በማዘጋጀት የራሳችሁ Online business ሊኖራችሁ እና ልትሰሩ ትችላላችሁ። ነገር ግን አሁንም " What's the demand in the market" ብሎ መጠየቅ ተገቢ ነው። ምንም ነገር ውስጥ ዘው ብሎ መግባት ሩቅ መንገድ አያስኬድም። ብዙ ኦንላይ ቢዝነስ አለ፤ ታድያ እንዴት መስራት እችላለሁ? ስራው ተይዟል ካላችሁ እነዚህ ቢዝነሶች ገበያውን ሰብረው የገቡበት መንገድ ትምህርት ይሆነናል፦

📶 ሼባ ሰአቶች እና ጌጣጌጦች። የራሱን መልክ ፣ ስም እና ፈጠራ ይዞ ስለመጣ ከነበሩት እጅግ ብዙ ንግዶች ጎልቶ ወጥቷል።

📶 ጦማር መጻህፍት አቅራቢ። መጻህፍትን ( የጠፉትን ሳይቀር ) ለገዢዎች ቤታቸው ድረስ የሚያደርስ

📶 TIKVAH-Ethiopia። በጣም ብዙ የዜና እና የሚድያ ተቋማት ስራው ላይ ቆይተውበት እያለ ይህ የቴሌግራም ቻናል ግን አቀራረቡን በመቀየር እና በመርህ በመሄድ ስኬታማ ሆኗል።

ŠFekadu_G21

ይቀጥላል...
👍6
የበይነ - መረብ ንግድ (Online Business)

ክፍል 3 (ከትላንቱ የቀጠለና የመጨረሻ ክፍል)

3️⃣ የግል ቴሌግራም ቻናል

ቴሌግራም በተለይ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ መሪነቱን እየወሰደ ነው። ብዙ ሰዎች ለብዙ ስራ ቀዳሚ ምርጫቸው እያደረጉት ነው። ስለሆነም የግል ቴሌግራም ቻናል በመክፈት እና ተፈላጊ እና ተወዳጅ ነገሮችን በመልቀቅ ብዙ ተከታይ ማፍራት። ከዛም በቻናላችሁ ላይ ማስታወቂያ ተከፍሏችሁ በመስራት፣ የፕሪምየም (ልዩ ዝግጅቶች) በማዘጋጀት በክፍያ ማስተላለፍ፣ Podcast በማዘጋጀት እና በክፍያ ለአባላቶች ማቅረብ፣ የራሳችሁ የሆነን ፈጠራ (ስእሎች፣ የአርት ስራዎች፣ የመስታወት እና ብርጭቆ ላይ ህትመቶች...) በመሸጥ ወዘተ አይነት ዘዴዎችን በመጠቀም ገቢ ማግኘት ይቻላል።

4️⃣ App እና Website ግንባታ

እነዚህ ስራዎች በርግጥ ትምህርት እና ልምድ ይጠይቃሉ። በዚህ የሰለጠነ ሰው ከቋሚ ስራው ጎን ለጎን ለግለሰቦችም ሆነ ለተቋማት በቅናሽ ዋጋ ድረገጾችን በመገንባት ተጨማሪ ገቢ ማግኘት ይችላል።

ከዚህ በፊት ያልተሰሩ እና ለህብረተሰቡ ጠቀሜታ የሚሰጡ App Develop በማድረግም ከባድ ትርፍ (ምናልባትም ሕይወትን የሚቀይር) ማግኘት ይችላል። ለዚህ አንድ ቀላል ማሳያ

☑️ በቅርቡ የእቁብ App Develop ያደረገችው ወጣት የስራ ፈጠራ ባለቤት

☑️ Ride

☑️ Afrotie የኦንላይን ግብይት App


⏺ ማጠቃለያ

ከላይ መግቢያው ላይ እንደጠቀስኩት በእኛ ሃገር በተለያዩ ሰንሰለታማ ምክንያቶች የበይነ - መረብ ንግድ መሄድ ያለበትን ርቀት አልሄደም። ምቹ ሁኔታዎች ብዙም ስላልተፈጠሩለት። ይህም ወደ ኦንላይን ቢዝነስ ለመግባት ላሰበ ሰው አንድ ተግዳሮት ነው።

በርግጥ በውስጥ መስመር ሲመጡልን ከነበሩ "Online Business" እንዴት እንጀምር የሚሉ ጥያቄዎች አብዛኞቹ የፈለጉት እንደ ቅጥር አይነት ስራን ይመስለኛል። የጥያቄዎቹ ስሜት እንደዛ ነው። የሆነም ስራ ኦንላይን መስራት፤ ከዛ ለእሱ ክፍያ መቀበል። ትክክል ነው። ይህ አሰራር በውጩ አለም በስፋት እየተሰራበት ነው። እኛ ሃገር ግን እንደዚህ አይነት ስራዎች ባደረኩት መጠነኛ ፍለጋ አላጋጠሙኝም። በርግጥ አንዳንድ እንደ መረጃ መሰብሰብ (Surveying) አይነት ስራዎች አልፎ አልፎ ከትምህርት እና የምርምር ተቋማት አካባቢ ይታያሉ። ሆኖም እነሱም ወቅታዊ ስራዎች ስለሆነ አያዛልቁም ወይም ቋሚ የገቢ ምንጭ አይሆኑም። One Time Job ናቸው። ስለሆነም ብቸኛው እና የሚያዋጣው አማራች የራስን የኦንላይን ቢዝነስ መመስረት እና የሚያስፈልገውን ጥረት አድርጎ ገበያው ላይ ዘልቆ በመግባት ስራውን መስራት አንዱ መፍትሄ ነው ብዬ አምናለሁ።

መልካም ስራ እና እድል!

ŠFekadu_G21
👍3❤1
app-debug-5.apk
3.7 MB
ሰሞኑን የተሰሩ ዌብሳይቶች ከነ አፕልኬሽን እርሶም በቅናሽ ዋጋ ያሰሩ!
1ኛ 4wcomputers ይባላል ይህ የግል የኮምፒውተር(ላፕቶፕና ደስክቶፕ) ሽያጭ እንዲሁም የኮምፒውተር አክሰሰሪዎችን የሚሽጥ ነው ስለሆነም በጥሩ ሁኔታ ዌብሳይቱን ሰርተንለታል እናስረክባለን አፑን ወደ ስልክዎ በመጫን ወይም ከታች ያለውን ሊንክ በመጫን መመልከት ይችላሉ!
www.4wcomputers.com
ለግል፣ ለመንግሥት ድርጅቶች ዌብሳይቶችን ማሰራት ለምትፈልጉ በቅናሽ ዋጋ ያሰሩ online አድርገን እንሰጥዎታለን በቴሌግራም ( @ma100me) ልታገኙኝ ትችላላችሁ።
ከዚህ በታች ያለው የቴሌግራም ቻናል ስለኮምፒውተር ቴክኖሎጂ ጥያቄ አጥቸ ሰዎች የሚፈተኑበት ቻናል ነው። እስከዛሬ ድረስ 100 ጥያቄዎች ያሉ ሲሆኑ በመግባት እራሳችሁን ፈትኑ እወቁ! መልሱን ወዲያውኑ ታውቃላችሁ! ወደፊት ጥሩ ጥያቄወችን እያዘጋጀሁ እለቅላችኋለሁ

👇👇ይግቡ ሊንኩ ከታች ያለውን ይጫኑ👇👇👇
@mame_tech_QA
@mame_tech_QA
@mame_tech_QA
@mame_tech_QA
ምርጥ የቴክኖሎጂ የዩቱቭ ቻናል ገባ በሉ እውቀት ታገኛላችሁ!
https://www.youtube.com/channel/UC7itLSzJdbzZQv8XrSHN_EQ
👍1
🗯 ሮቦቶች እና የተሰማሩበት የስራ ዘርፍ

◼️ ሮቦቶች በተለያዩ ሰዎች እይታ የተለያየ መልክ ይዘዉ ኖረዋል። ሮቦት የሚለዉ ስም "robota" ከሚለዉ የቼክ ቋንቋ የመጣ ቃል ሲሆን፣ ትርጉሙም የግዳጅ ሠራተኛ ወይም አገልጋይ ማለት ነዉ። ሮቦቶች ልክ እንደ ሰማቸዉ ትርጉም ሳይታክቱ እና ደከመኝ ሳይሉ ስራቸዉን የሚያከናዉኑ የሰዉ ልጆች አጋዥ ናቸዉ። ለአንዳንድ የሰዉ ልጆች ረዳት እንደሆኑ ተደርገዉ የሚታዩት ሮቦቶች በሌሎች ሠዎች ዓይን ደግሞ ከስማቸዉ አፈንግጠዉ ወደፊት የሰዉ ልጆችን ሊተኩ፣ ሊቆጣጠሩና ሊገዙም የሚችሉ አደገኛ ሰዉ-ሰራሽ ማሽኖች እንደሆኑ ተደርገዉም ይታያሉ። በዓለም ዙርያ በተለያዩ ዘርፎች፣ በተለይም በኢንዱስትሪዉ ሥራ ላይ የተሰማሩ በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ ሮቦቶች በርካታ አገልግሎት እየሠጡ ይገኛሉ። ከእነዚህ ዉስጥ ጥቃቶቹን እንመልከት፦

1. ወተት አላቢዉ ሮቦት፦ እኛ በተለምዶዉ ከምናዉቀዉ በሰዉ እጅ ከሚከናወነዉ የላም ወተት አስተላለብ ሌላ ሮቦቶች ይህንን ተግባር እጅግ በተቀላጠፈ ሁኔታ እንደሚያከናዉኑ ታዉቃላቹህ? "Robotic Milking" ወይንም "Automatic Milking System" -- AMS" በመባል የሚታወቀዉ አሰራር ያለምንም የሰዉ ጣልቃ ገብነት በተቀላጠፈ ሁኔታ በኮምፒዉተር ትዕዛዝ የሚታገዙ ሮቦቶች ከላም ላይ ወተትን የማለቡን ተግባር ይፈጽማሉ። የመሣሪየዉ ዋጋ ከ140 እስከ 200 ሺህ ዶላር ያወጣል።

2.📍የሮቦት ፖሊስ

▪️በማሽን የታገዘ ግድያ መፈጸም አዲስ ነገር አደለም። ጠመንጃ፣ ታንክ፣ የጦር አዉሮፕላን እና የመሳሰሉት በሰዉ ቢታገዙም ይህንኑ ሲፈጽሙ የቆዩ ማሽኖች ናቸዉ። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ደግሞ ሰዉ አልባ ድሮኖች የሚፈለገዉ ቦታ ድረስ በመሄድ ጥቃት እንዲሰነዝሩ እየተደረገ ይገኛል። ሮቦቶች ቦምብ ለማምከን፣ ወንጀለኛን አድኖ ለመያዝ እና ለመሳሰሉት ከፍተኛ ጥቅም የወንጀል መከላከል ስራዎች የአሜሪካ የፖሊስ ሀይልን ማገዝ ከጀመሩም ሰነባብተዋል። ነገር ግን በ2006 ዓ.ም. የሆነዉ ለየት ያለ ነገር ነበር። በአሜሪካ ሀገር በጥቁሮች ላይ በሚፈጸም ተከታታይ የፖሊስ ግድያ ተበሳጭቶ በዳላስ ቴክሳስ ዉስጥ አምስት ፖሊሶችን የገደለዉን ጥቁር አሜሪነበር ስናይፐር (የሮቦቱ ስም) አድኖ በመግደል ሮቦት ለመጀመሪያ ጊዜ በወንጀል መከላከል ግድያ ላይ ቀጥተኛ ተሳታፊ ሆኗል። ሮቦቱ የሚፈነዳ ገዳይ መሳሪያን በመሸከም ነበር ስናይፐሩ ወደተሸሸገበት ቦታ በመሄድ ግድያዉን የፈጸመዉ። ይህ ስናይፐር ተጨማሪ ሰዎችን ከመግደሉ በፊት ለማስቆም ያለዉ ብቸኛ አማራጭ ይኸዉ እንደነበር የተናገሩት ባለስልጣናት፣ ሰዉን ወደእርሱ ልኮ በቁጥጥር ስር ለማዋል ወይንም በሰዉ እጅ ለመግደል ፍጹም አደገኛ ሁኔታ እንደነበርም ገልጸዋል። ምክንያቱም ደግሞ ስናይፐሩ ከዚህ ቀደም የሚሊቴሪ ስልጠና የወሠደ በመሆኑ እና አንዲሁም ግድያ ይፈጽም የነበረበት ቦታ እርሱን በቁጥጥር ለማዋል ፈጽሞ የማይመች ስለነበረ ነዉ። በሚሊቴሪ ስራ ላይ የዋለ የሮቦት አሰራር በአሜሪካ የፖሊስ ሃይል ዉስጥ ተሰማርቶ ሰዉን በመግደል ተግባር ላይ መዋሉ አከራካሪ ሆኖ ሰንብቷል። ወደፊት ይህ ቴክኖሎጂ ከመስመር የወጣ አሠራር ዉስጥ ሊገባ እንደሚችልም አመልካች ሁኔታን ፈጥሯል። በአንጻሩ ሮቦቶች ከባድ በሆነ ሁኔታ ዉስጥ አልፈዉ የነፍስ ማዳን ስራ ላይ ተሰማርተዉ ከፍተኛ ጥቅም እየሰጡም ይገኛሉ። በ2001 ዓ.ም. ኒዉ ዮርክ ከተማ ላይ በአሸባሪዎች ጥቄት በተፈጸመበት ከወደሙት የዓለም የንግድ ማዕከል ህንፃዎች ዉስጥ ከፍተኛ ሙቀት ካለዉ ብረታ ብረትና ከሲሚንቶ ፍርስራሽ በታች የተረፉ ሰዎችን ለመፈለግ በርካታ ሮቦቶች ተሠማርተዉ ነበር።

3. ሮቦት ዘበኛ

"Knightscope" የተባለ ተንቀሳቃሽ ሮቦት በትምህርት ቤቶች፣ በንግድ ስፍራዎች፣ በህዝብ መናፈሻዎች፣ በቢሮ ህንፃዎችና በመሳሰሉ ስፍራዎች ላይ የጥበቃ ስራን ለማከናወን በስራ ላይ ዉሏል። የሮቦቱ አምራቾች እንደገለጹት ለዚህ ፈጠራ የተነሳሱበት በዲሴምበር 14 2012 ዓ.ም. በአሜሪካኗ የከነቲከት (Connecticut) ግዛት በሚገኝ ሳንዲ ሁክ የተባለ 1ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ዉስጥ በአንድ ነፍሰ ገዳይ አማካኝነት የተከሰተ አሰቃቂ የሆነ የህጻናት እልቂት ነዉ። የሮቦቱ ፈጣሪዎች እንዲህ ያለዉን አደጋ እንዳይከሰት የቅድመ መከላከል በማድረግ ይህ ጠባቂ ሮቦት ትልቅ አስተዋጽዎ እንደሚኖረዉ ተናግረዋል። 1.5 ሜትር ርዝመትና 136 ኪሎ ግራም ክብደት ያለዉ ይህ ሮቦት በላዉ ላይ በተገጠሙለት የቪድዮ ካሜራ፣ ሙቀትን በመለካት እንቅስቃሴን መለየት በሚችል ቴክኖሎጂ፣ ራዳር፣ ጨረር፣ ማይክሮፎንና የአየር ብክለት መለኪያ ቴክኖሎጂዎችን በመጠቀም ጥበቃን ማከናወንና የወንጀል እንቅስቃሴዎችን መከታተል ይቻላል። አስጊ ሁኔታን ካስተዋለ ወዲያዉኑ ለፖሊስ መጠቆም የሚችልበት ፈጣን የመገናኛ ቴክኖሎጂም ተካቶለታል።

4. ሮቦት ሼፍ

"Moley" ይባላል። በዓለም ላይ የመጀመሪያዉ የሮቦት ሼፍ ነዉ። ሁለት እጆች ያሉት ይህ ሮቦት ከሙሉ አዉቶማቲክ የምግብ ማደራጃና ማብሰያ ጋር አብሮ የሚመጣ ሲሆን እጆቹ ከጣሪያ የሚወርዱና የሰዉ ልጅ እጅ የሚሰራዉን ተግባር ማከናወን የሚችሉ ናቸዉ። በሚያስደንቅ ሁኔታ የሰዉ እጅ አይነት እንቅስቃሴ ያለዉ ይህ ሞሊ የሮቦት ሼፍ የምግብ ግብዓቶችን ከመምረጥ፣ ከመመጠን ወይም ከመለካት፣ ከመክተፍ፣ ከማማሰል፣ ማብሰያ እቃዎችን አንስቶ የሚገባቸዉ ቦታ ከማስቀመጥ አንስቶ አብስሎ እስኪጨርስ ማብሰያዉን እስከ ማጽዳት ድረስ አስገራሚ የማብሰል ክንዉን ያካሂዳል።

ማብሰል በራሱ የሚወደድ ተግባር ቢሆንም፣ በስራና የዕለት ተዕለት ጉዞ ዉስጥ የተጠመዱ ሰዎች ወደፊት በማብሰል ይጠፍ የነበረዉ ሰዓታቸዉን ከሚወዱት ሰዉ ጋር በመጫወት ወይንም ሌሎች ነገሮችን በማከናወን ሊያሳልፉ ይችላሉ። ይህንን ሮቦት በ "touch screen" እንዲሁም በስልክ ላይ በሚጫን "app" መቆጣጠር ይቻላል። የሮቦት እጁን መጠቀም በማያስፈልግ ጊዜ ወደ ጣሪያዉ እንዲሰበሰብ አድርጎ ማብሰያ ቦታዉን ለሰዉ ጥቅም ማዋል ይቻላል። ይህ ቴክኖሎጂ የሙከራ ጊዜዉን አጠናቆ በጥቂት ዓመታት ዉስጥ ለተጠቃሚዎች እንደሚቀርብ ታዉቋል።


5. ሮቦት የፍርማሲ ሰራተኛ

ከላይ እንደተጠቀሰዉ በካሊፎርኒያ የዩንቨርስቲ ሆስፒቴል ዉስጥ የሚገኝ መድሀኒት ቤት ዉስጥ አገልግሎት መስጠት የጀመረዉ ሮቦት የመጀመሪያዉ በመስኩ በፍርማሲ የተሰማራ ሮቦት ቢሆንም፣ ይህ አሰራር ወደፋት በስፍት ሊቀጥል እንደሚችል አመልካች ሁኔታ እየታየ ነዉ። እንግሊዝ ሀገር በሚገኝ ሆስፒታል ዉስጥ የሚገኝ ልላ መድሀኒት ቤትም ሰዉን ተክቶ የፍርማሲ ስራ የሚሰራ ሮቦት ተግባራዊ ሆኗል። መድሃኒቶች ከመደርደሪያቸዉ ወስዶ ለደንበኞች ማቀበል የሚችል እጆች የተገጠሙለት ሮቦት ይህንን ተግባር በጥቂት ሴኮንዶች ዉስጥ ያከናዉናል።

6. አረጋዉያን አጫዋቹና ረዳቱ ሮቦት?

በጃፓን ዉስጥ የአረጋዉያን ቁጥር ከፍተኛ ነዉ። 20 በመቶዉ የጃፓን ህዝብ እድሜዉ ከ65 ዓመት በላይ ሲሆን፣ ወጣቱ ህብረተሰብ ደግሞ ከማነሱ ባሻገር ህይወቱ እጅጉን የተጨናነቀ ዓይነት ስለሆነ ከአረጋዉያን ጋር የሚያጠፋዉ ጊዜ የለዉም። ይህንን ችግር ለማቃለል የሚችል የሙከራ የሮቦት ቴክኖሎጂ በዚችዉ ሀገር ተፈጥሮ በስራ ላይ ዉሏል። ፈጠራዉን በስራ ላይ ያዋለዉ የአረጋዉያን መጦሪያ ተቋም ቴክኖሎጂዉ ደንበኞቹን ለማገልገል አስቸዋጽዎ እያደረገ እንደሚገኝ ገልጿል። ሌላ አይነት የአረጋዉየን አጋዥ ሮቦት ደግሞ ምግብንና ዉሃን በማቀበል በብራትን በማብራትና በማጥፋት እንዲሁም ቤትን በማጽዳት አረጋዉያንን
👍6
....የቀጠለ ......
ቅድሚያ ከላይ ያለውን ክፍል ያንብቡ(ሮቦቶች እና የተሰማሩበት የስራ ዘርፍ)

የሚያገለግል ሲሆን፣ ወደፊት ይህ አሰራር በተለያዩ ሀገራት በሰፊዉ ተግባራዊ እንደሚሆን ይጠበቃል።

⚔ገዳይ ተዋጊ ሮቦቶች

ሰዉ-ሰራሽ ክህሎት እና የሮቦቲክ አሰራር የተገጠመላቸዉ ቴክኖሎጂዎች በጦርነት ዘርፍ ከገቡ ሰነባበተ። ለዚህም ጥሩ ምሳሌ የሚሆነዉ የድሮን ቴክኖሎጂ ነዉ። ፓይለቱ በሺህ ኪሎሜትሮች ርቆ ድሮኑን በሪሞት ኮንትሮል በመቆጣጠር የሚፈለገዉን ኢላማ መቶ የጠላትን ግዛት መደምሰስና ሰዉን መግደል ይችላል። የወደፊቱ ስጋት ደግሞ ከዚህ ባለፈ መልኩ የሮቦት ወታደሮች "humanoid robots" ቢፈጥሩስ የሚል ነዉ። እንደዚህ ያለዉ ፈጠራ ህያዉ ከሆነ የጦርነት መልክ ከዚህ በፊት ሆኖ በማያዉቅ ሁኔታ እስከ ወዲያኛዉ ሊቀየር ይችላል። አቅም የሌላቸዉ ሀገራት የሰዉ ወታደር ሲያሰልፉ ኃያላኑ በሮቦት ወታደሮቻቸዉ የሚዋጓቸዉ ከሆነ ጦርነት አዲስና አስፈሪ መልክ ይይዛል ማለት ነዉ። ጦርነት መቼም ቢሆን በጎገጽታ ኖሮት አያዉቅም፣ ወደፊትም አይኖረዉም! ይሁንና መከሰቱ በማይቀር ወቅት ግን ይብዛም ይነስም ዓለም ዓቀፍ መተዳደሪያና ደንብ አለዉ። ለዚህ ነዉ እንደ ኒኩሊየር ቦንብ ያለ ጅምላ ጨራሽ መሳሪያ አልያም ደግሞ የኬሚካልና ባዮሎጂካል መሳሪያን በጦርነት ላይ መጠቀም አይቻልም የሚል ስምምነት በዓለም አቀፍ ደረጃ ተተግብሮ የሚገኘዉ። ታድያ ወደፊት ሮቦት ወታደሮች ቢሰሩ እገዳ ይጣልባቸዉ ይሆን? ኢላን መስክን ጨምሮ ሌሎች ታዋቂ ግለሰቦች ገዳይ ሮቦቶች ፈጽሞ እንዳይሰሩ ካሁኑ ጠንካራ እገዳ መጣል አለበት ሲሉ የተባበሩት መንግስታት ይህን ጉዳይ በህግ ደረጃ እንዲያስፈጽም ዋና ኃላፊነትን ወስዶ መስራት አለበት ብለዋል።

የስራ አጥነት ስጋት፣ "ከእኛ ብቃት አልፈዉ እና ትዕዛዝ መቀበል አቁመዉ ይቆጣጠሩን ይሆን?" የሚል ፍርሃትና ሌሎች በርካታ የጎንዮሽ ስጋቶች እንዳሉ ሆነዉ የሮቦቶች በጎ ገጽታ ደግሞ የሚካድ አደለም።

"እኛዉ የፈጠርናቸዉ ሮቦቶች ይገዙን ይሆን?" ተብሎ በሚሰጋበት ወቅትም የሰዉ ልጅ አዲስ ነገርን የማወቅ ጉጉቱ ከምድር አልፎ ኅዋ ድረስ በመሄድ ጭራሽ አይቶ የማያዉቀዉን የአጽናፈ ዓለም ክፍል የማየት ፍለጎቱን ፈጽሞ አላቋረጠም። ምናልባትም የሰዉ ልጅ ወደፊት ለምርምር ብቻ ሳይሆን ለቱሪዝም እና ለጫጉ ሽርሽር ከዉብ ደሴቶች ባለፈ ጉዞዉን ወደ ጠፈር ያደርግ ይሆን?

🗣አንድ ጥያቄ ልጠይቃቹ

- እኛዉ የፈጠርናቸዉ ሮቦቶች ይገዙን ይሆን?
👍4❤1
የ 7፣8፣9፣10፣11፣12 teacher guide ና ሌሎች ወሳኝ ትምህርታዊ ነገሮችን የምታገኙበት ቻናል ይቀላቀላሉ👇
ያሉትትን መፅሐፍ ሚያገኙበት channal ከታች ያለውን link አንዴ ይንኩ 💯ያስደስቶታል::! ያረጋግጡ ገብተው:::+::::
👇👇👇👇👇👇👇👇
👇👇👇👇👇👇
Join @EthiopiaDigitalLibrary
Join @EthiopiaDigitalLibrary
Join @EthiopiaDigitalLibrary
Join @EthiopiaDigitalLibrary
Join @EthiopiaDigitalLibrary
Join @EthiopiaDigitalLibrary
👍1😁1
ፕሮግራሚንግ መማር ለምትፈልጉና ፕሮግራመር ለመሆን ለመሆን የሚያስችሉ ምርጥ ዌብሳይቶች
Sites to practice programming and solve challenges to improve programming skills

1️⃣ https://edabit.com
2️⃣ https://codeforces.com
3️⃣ https://www.codechef.com
4️⃣ https://leetcode.com
5️⃣ https://www.codewars.com
6️⃣ http://www.pythonchallenge.com
7️⃣ https://coderbyte.com
8️⃣ https://www.codingame.com/start
9️⃣ https://www.freecodecamp.org/learn
👍3❤2
❤1
ሞባይል ጥገና ክፍል 1.pdf
1.9 MB
ክፍል 1 - የሞባይል ሃርድዌር ጥገና መሳሪያዎችና አጠቃቀማቸው
Click to join👇👇👇👇
❀✤┈┈┈••✦✦••┈┈┈✤❀
➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖
🍁 Join : @EthiopiaDigitalLibrary
🍁 Join : @EthiopiaDigitalLibrary
➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖
❀✤┈┈┈••✦✦••┈┈┈✤❀
👍5