Muhammed Computer Technology (MCT)
38K subscribers
527 photos
7 videos
254 files
910 links
🔴አድራሻ:-
✅ ስ.ቁ: 0929273364
✅ ዌብሳይት www.mctplc.com
✅ቴሌግራም አካውንት: https://t.me/mctplc
✅ email: mct16plc@gmail.com
✅ ቲክቶክ አካውንት tiktok.com/@mctplc
Download Telegram
Opera mini ኢንተርኔት ሲጠቀሙ ኮኔክሽኑ በጣም
ቀርፋፋ ሆኖ ተቸግረዋል? እንዴት
በopera mini ላይ የኢንተርኔት ፍጥነቱን መጨመር እንችላለን የሚለውን
እናያለን። ከታች
የተጠቀሱትን 9 እስቴፓች በመከተል ፈጣን ኢንተርኔት በopera mini ላይ
መጠቀም
ይችላሉ።

step1. በመጀመሪያ Opera miniውን ይክፈቱ።
step2. በመቀጠልም Address Bar ውስጥ ገብተው www.
የሚለውን ያጥፉ።

step3. ከዛም Address Bar ውስጥ opera:config ብለው ይፃፉ።
step4. ከዛም Power Settings ይመጣሎታል።

step5. የመጀመሪያውን Option "Large placeholders for
images" የሚለውን YES
ከሆነ NO አድርጉት።

step6. ከዚያም ሁለተኛውን Option "Fit text to screen" የሚለውን
YES ከነበረ NO
ያድርጉት።

step7. በመቀጠልም ሶስተኛውን Option 'Loading timeout'
የሚለውን 20
ያድርጉት።

step8. ከዛም Save የሚለውን በመጫን ይጨርሱ።
step9. ከዛም Operaዎትን ዘግተው እንደገና መልሰው በመክፈት ፈጣን
የሆነውን
ኢንተርኔት ይጠቀሙ።
ከተመቾት ለወዳጆት ያጋሩ
❤1
💢HDMI Cable ማለት ምን ማለት ነው?

✅ HDMI cable ማለት ከስሙ እንደምንረዳው #Cable/ገመድ ነገር ሲሆን እንደ አንዳንድ #ኬብሎች ምስልና ድምፅ ከአንድ የ Electronics Device ወደ ሌላ ለማስተላለፍ ይረዳል። ነገር ግን ለየት የሚያደርገው በጣም #ከፍተኛ😱 በሆነ ምስል ጥራት(HD QUALITY) ለማየት ይረዳል።

✅ይህንንም ኬብል የምንጠቀመው ከ(Receiver, Laptop, DVD, Ps3, CPU, PSP)...ወደ ተለያዩ ምስልና ድምፅ ሊያወጡልን ወደሚችሉ መሳሪያዎች (TV🖥, Projector, monitor) ለማስተላለፍ ነው።

📌 አጠቃቀሙ እንደሚከተለው ነው፡ ⬇️

✅ያላችሁ TV🖥 HD መሆን አለበት ወይም በሌላ አገላለፅ የ HDMI መቀበያ #Port ያለውና #Flat የሆነ መሆን አለበት።

✅ያላችሁ ሪሲቨር #HD መሆን አለበት።ነገር ግን አንዳነድ ሪሲቨሮች HD ሳይሆኑ‼️ እንደ TVው HDMI መቀበያ #Port ያላቸው ሊሆኑ ይችላሉ።

✅በቅድሚያ #ኬብሉን በሪሲቨሩና በTvው🖥 ላይ በአግባቡ ይሰኩ።

✅በTvው🖥 ላይ #INPUT ወይም #Source የሚለውን በመጫን የሰካችሁበትን Port (HDMI1, HDMI2..) ምረጡ።

✅በምስሉ ላይ #ብዙ👌 የሚባል የጥራት ልዩነት ታያላችሁ። ያን ያህል ያልተጋነነ የምስል ጥራት ለውጥ ካለያችሁ ግን #በሪሲቨሩ ላይ Video Resolution/ የጥራቱን መጠን በመጨመር ወደ 1080i ድረስ አድርጋችሁ የተሻለ👏 ነገር ማግኘት ትችላላቹ።👍
👍3
ሰሞኑን የተሰሩ ዌብሳይቶች እርሶም በቅናሽ ዋጋ ያሰሩ!
1ኛ 4wcomputers ይባላል ይህ የግል የኮምፒውተር(ላፕቶፕና ደስክቶፕ) ሽያጭ እንዲሁም የኮምፒውተር አክሰሰሪዎችን የሚሽጥ ነው ስለሆነም በጥሩ ሁኔታ ዌብሳይቱን ሰርተንለታል ከታች ያለውን ሊንክ በመጫን መመልከት ይችላሉ!
www.4wcomputers.com
2ኛ Ethio Technology ይባላል ይህ ዌብሳይት ስለቴክኖሎጅ መረጃዎችን የሚያቀርብልን ሲሆን በተጨማሪም Online ሽያጭ ሊያሰራ የሚችል ዌብሳይት ነው። ከታች ያለውን ሊንክ በመጫን መመልክት ይችላሉ!
www.ethiotechnologys.com
3ኛ mame tech solution ይባላል ይህ ዌብሳይት እኛ በፌስቡክ፣ ቴሌግራምና ዩቱብ በተጨማሪ በዚህ ዌብሳት አገልግሎት እየሰሁ እገኛለሁ ስለሆነም ከታች ያለውን የዌብሳይት አድራሻ በመጠቀም ይማሩ መረጃ ያግኙ!
www.mametechsolution.com
ለግል፣ ለመንግሥት ድርጅቶች ዌብሳይቶችን ማሰራት ለምትፈልጉ በቴሌግራም ( @ma100me) ልታገኙኝ ትችላላችሁ።
👍1
app-debug-5.apk
3.7 MB
ሰሞኑን የተሰሩ ዌብሳይቶች ከነ አፕልኬሽን እርሶም በቅናሽ ዋጋ ያሰሩ!
1ኛ 4wcomputers ይባላል ይህ የግል የኮምፒውተር(ላፕቶፕና ደስክቶፕ) ሽያጭ እንዲሁም የኮምፒውተር አክሰሰሪዎችን የሚሽጥ ነው ስለሆነም በጥሩ ሁኔታ ዌብሳይቱን ሰርተንለታል እናስረክባለን አፑን ወደ ስልክዎ በመጫን ወይም ከታች ያለውን ሊንክ በመጫን መመልከት ይችላሉ!
www.4wcomputers.com
ለግል፣ ለመንግሥት ድርጅቶች ዌብሳይቶችን ማሰራት ለምትፈልጉ በቅናሽ ዋጋ ያሰሩ online አድርገን እንሰጥዎታለን በቴሌግራም ( @ma100me) ልታገኙኝ ትችላላችሁ።
👍2
Ethio Technology ይባላል ይህ ዌብሳይት ስለቴክኖሎጅ መረጃዎችን የሚያቀርብልን ሲሆን በተጨማሪም Online ሽያጭ ሊያሰራ የሚችል ዌብሳይት ነው። ከታች ያለውን ሊንክ በመጫን መመልክት ይችላሉ!
www.ethiotechnologys.com
​​📌ቀለል ባለ መንገድ ኮምፒውተርን ወይንም☛ላፕቶፕን ፍላሽ ዲስክ ተጠቅመን አዲስ ኦፐሬቲንግ ሲስተም እንዴት መጫን እንደምንችል ነው።

🔸🔸ማዘጋጀት ያለብን ነገሮች🔸🔸

1. 4 ጂቢ ወይንም ከዛ በላይ የሆነ ፍላሽ ዲስክ

2. Rufus የተሰኘ Software

3. መጫን የምንፈልገውን በ ISO format የተዘጋጀ ዊንዶውስ ኦፐሬቲንግ
ሲስተም( WINDOWS XP 7,8,8.1 or 10) ስንገዛ ወይም ስናወርድ እንደዛ መሆኑን ማረጋገጥ አለብን።

4. ይሄን ስራ የምንሰራበት ላፕቶፕ

🔹🔹አስራሩ እንዴት ነው?🔹🔹

▪️Rufus የሚባለው ፕሮግራም አሉ ከሚባሉ ለዚ ስራ የሚያገለግሉ ቀለል ያለ እና ፈጣን ስለሆነ ለዛሬ በሱ እንዴት እንደምንሰራ እናያለን:-

▪️ያዘጋጀነውን 4ጂቢ ፍላሽ ዲስክ ኮምፒተራችን ላይ እንሰካለን።▪️

1.ፕሮግራሙን ዳውንሎድ ካረግን በኀላ መጫን ሳያስፈልገን ራይት ክሊክ አርገን ራን አስ አድሚንስትሬተር
ብለን እንከፍተዋለን ከዛ አብዴት ሲጠይቅ no እንመርጣለን።

2.ፕሮግራሙ ከተከፈተ በኅላ ፍላሽ ዲስኩን ዲቫይስ የሚለው ሜኑ ተጭነን እንመርጠዋለን።

3.ከዛ iso image የሚለው ቦታ ሄደን ቅድም ይዘጋጀነውን የዊንዶውስ ሶፍት ኮፒ አስገብተን ድራይቭ ሌተሩን እንመርጣለን።

✏️ ይህን ስናደርግ ፕሮግራሙ ራሱ ሁሉን ነገር አውቶማቲካሊ ስለሚያዘጋጅ ሌላ የምናስተካክለው ነገር የለም ማለት ነው።

4. ከዛ start የሚለውን በተን ስንጫን ፍላሽ ላይ ያለ ማንኛውም ዳታ ይጠፋል ብሎ ማስጠንቀቂያ ይሰጠናል
የምንፈልግው ፍይል ፍላሽ ላይ ካለ ባክአፕ ማድረግ አለብን።
እሱን ካረጋገጥን በኅላ ok እንለዋለን።

5. በስተመጨረሻ ፕሮግራሙ የዊንዶውን ሴትአፕ ወደ ፍላሽ ዲስኩ ኮፒ በማድረግ ስራውን መስራት ይጀምራል።

✏️ ፕሮግራሙ ኮፒ አድርጎ ሲጨርስ
close የሚለውን በተን ክሊክ መጫን የምንፈልገው ኮምፒተር ላይ ወስደን እንጠቀማለን።

🔸🔸በUSB ኮምፒውተሮን እንዴት ፎርማት ማረግ ይችላሉ🔸🔸

1.ኮምፒውትሮን turn off ያርጉ

2.ቅድም ከላይ ያዘጋጀነውን USB ፍላሽ አስገብትው turn on ያድርጉ።

3.F2 ወይም F12 ን (እንደ ኮምፒውተሩ ሞዴል ይለያያል) ይጫኑ እና ቀጣይ ትዕዛዙን ይከተሉ።

4." install windows " የሚለው ሲመጣልዎ የሚፈልጉትን ቋንቋ እና ሌሎች ዝርዝሮችን ይሙሉ ከዛም next ን ክሊክ ያድርጉ።

5."Please read the license terms" የሚለው ሲመጣልዎ
"I accept the license terms" የሚለውን ክሊክ ያርጉ

6."Which type of installation do you want?" ሲልዎት Custom የሚለውን ይምረጡ።

7."Where do you want to install Windows?" የሚለው ፔጅ ላይ "Drive options" የሚለውን ክሊክ

8.ፎርማት ማድረግ የሚፈልጉትን "partition" ይምረጡና "format" ላይ ክሊክ ያድርጉ

9.ፎርማት አድርገው ሲጨርሱ "next" ላይ ክሊክ ያድርጉ

10. ከዛ በመቀጠል ትዕዛዙን (instruction ) በመከተል window install ያድርጉ።
═══════════════

╚═════📌Share📌════╝
👍7❤2
ሀርድ ዲስክ ምንድን ነው? Hard_Disk
ሀርድ ዲስክ መረጃን ለማስቀመጥ ሁለተኛው ማግኔታዊ የመዝገብ አካል ነው:: ሀርድ ዲስክ ክብ ቅርፅ ካለው የብረት አካል የተሰራ ሲሆን በላዩ ላይ መረጃን ማግኔታዊ በሆነ መልኩ እንዲያግዝ # Metal_oxide በሚባል ንጥረ ነገር ተቀብትዋል:: ከዚህም በተጨማሪ ከብረት በተሰራ አነስተኛ ሳጥን ውስጥ የተሸነፈ ሲሆን ለመፃፍና ለማንበብ የሚረዳው ራስ (Read\write heads) በውስጡ ይገኛል::
.
የሀርድ ድራይቭ የውስጠኛው አካል ነጣጥሎ ለማውጣት አዳጋች ነው:: በአብዛኛውን ግዜ በሲስተም ዩኒት ውስጥ እንደ አንድ ክፍል ሆኖ ስለሚገኝ ችግር ወይም ብልሽት ቢገጥም እና የሀርድ ዲስኩን የአቅም ብቃት ለማሳደግ በሚፈለግበት ወቅት ብቻ ሲስተም ዩኒቱን በመክፈት ለማውጣት ይቻላል::
.
የሀርድ ዲስኩ የመረጃ ማስቀመጫ ጠፍጣፋ ክብ የብረት ክፍል በደቂቃ ከ7200 ፍጥነት በመሽከርከሩ መረጃው እንዲቀመጥ ወይም እንዲነበብ ያደርጋል:: መረጃውን ከዲስኩ ላይ በሚያነብበት ወቅት በማንበብያው ጫፍ በመጠቀም መረጃውን በመፈለግ ወደ # ሜሞሪ ያስተላልፋል:: መረጃን ለማስቀመጥ በሚያስፈልግበት ወቅትም እንዲሁ መረጃው ከጊዜያዊ ማስታወሻ ወይም ሜሞሪ አካል ማግኔታዊ በሆነ መልኩ ወደ ሀርድ ዲስኩ ላይ ይመዘግበዋል:: መረጃ ለማንበብ እና ለመፃፍ የሚያገለግለው ራስ በዲስኩ አካል ላይ በመሆን ነብዙ ሺህ ትራክና ሴክተር ላይ መረጃን ይዘግባል:: አንድ ለግል ጥቅም የሚውል ኮምፒዩተር መረጃ የመሸከሙ አቅም ከ1ቢሊዮን እስከ 10 ቢሊየን ካራክተር መሸከም ይችላል::
⏺ የYouTube channel Subscribe በማድረግ ጥሩ ጥሩ ትምህርታዊ ቪዲዮችን ይከታተሉ።
የ YouTube ቻናል ሊንክ 👇👇👇
https://www.youtube.com/channel/UCZBIP6PqUdmmagdTjbyp_AQ
👍1
የነገሮች ኢንተርኔት (The Internet Of Things)

🔸ኢንተርኔት በተለምዶ እንደሚታወቀዉ ኮምፒዉተሮች ብቻ እርስ በእርሳቸዉ ተገናኝተዉ የሚሰሩበት አሠራር ታሪክ እየሆነ ነዉ ቢባል ማጋነን አይሆንም። በ1984 ዓ.ም. ከኢንተርኔት ጋር የተያያዙ ኮምፒዉተሮች 1 ሺህ ብቻ ነበር። ይህ ቁጥር በ1992 ዓ.ም. ወደ 1 ሚሊዮን ማደግ የቻለ ሲሆን በ2006 ዓ.ም. ደግሞ 600 ሚሊዮን መድረስ ችሏል። እድገቱ በሚያስገርም ሁኔታ ጨምሮ በ2008 ዓ.ም. 1 ቢሊዮን የደረሰ ሲሆን፣ እስከ 2014 ዓ.ም. ያለዉ መረጃ እንደሚጠቁመው ደግሞ ከ15 ቢሊዮን በላይ የኤሌክትሮኒክ ቁሶች ከኢንተርኔት ጋር ተገናኝተዋል።

የነገሮች ኢንተርኔት (The Internet Of Things - IoT) የሚባለዉ ክስተት በዛሬ ጊዜ ከኢንተርኔት ጋር ያልተገናኘ ቁስ የሌለ አስመስሎታል። የነገሮች ኢንተርኔት (IoT) ማለት በኤሌክትሮኒክስ፣ በጂ.ፒ.ኤስ (GPS)፣ በአነፍናፊ ቁሶች (Seasors)፣ እንዲሁም በሶፍትዌር በመታገዝና የኢንተርኔት ቴክኖሎጂን በመጠቀም እጅግ በርካታ ቁሶች ጠቃሚ መረጃዎችን እንዲሰበስቡ የሚያደርግ ቴክኖሎጂ ነዉ። እነዚህን መረጃዎች ለዕለት ተዕለት ኑሯችን በምንጠቀምባቸዉ እንደ ኮምፒዉተር፣ ስልክ፣ ቤት፣ መኪና፣ ፍርጅ፣ ቴሌቪዥን፣ ምድጃ፣ አየር ማቀዝቀዣ፣ የሙዚቃ ማጫወቻ፣ ካሜራ፣ የአየር መቆጣጠሪያ፣ መነጽር፣ ጫማ፣ የስፖርት እቃ፣ የህክምና ቁስ፣ የቢሮ ቁስ፣ የመዝናኛ ቁስ፣ ሰዓት፣ የልብስ ማጠቢያ፣ የቡና ማፍያ፣ ማብሪያ ማጥፊያ፣ አምፖል ባሉ ብዙና የተለያዩ የኤሌክትሮኒክስ ቁሶች አማካኝነት በማስተላለፍ እርስ በርሳቸዉ ወይም ማዕከላዊ ከሆነ የኮምፒዉተር መረጃ ቋት (database) ጋር በኢንተርኔት አማካኝነት ተገናኝተዉ በመለዋወጥ ሰፊ አገልግሎትን እንዲሰጡ እየተደረገ ይገኛል።

ከየትኛዉም ቦታ ሆነን የቤታችንን የአየር ሙቀት በእጅ ስልካችን መቆጣጠር፣ መብራት ሳናጠፋ ረስተን ብንወጣ ስልካችንን በመጠቀም ማጥፍት፣ ቤታችን እንዲገባ የምንፈልገዉ ሰዉ ቢኖር ከየትም ሆነን በራችንን መክፈት፣ ብርሃን ከመስጠት አልፈዉ የዋይፋይ አገልግሎት የሚሰጡ የመንገድ መብራቶች፣ እንደ ድልድይ፣ ግድብ፣ ህንጻ፣ ያሉ መሠረተ ልማቶች እክል ሲገጥማቸዉ በተገጠመላቸዉ "sensor" እና የኢንተርኔት ቴክኖሎጂ አማካኝነት በራሳቸዉ ለተቋማቱ ማሳወቅ የሚችሉ አሠራሮች የነገሮች ኢንተርኔት (IoT) ከሚሰጣቸዉ አዲስ አይነት አገልግሎቶች እጀግ ጥቂቶቹ ናቸዉ።
👍3
✳️ እስከ 100 GB + ነፃ online ማንኛውም File ማስቀመጪያ ምርጥ ሳይቶች

▫️Sign up at Ozibox.com to get 100GB of free storage.

▫️Sign up at SurDoc.com to get 100GB of free storage.

▫️Sign up at Shared.com to get 100GB of free storage.

▫️Sign up at Adrive.com to get 50GB of free storage

▫️Sign up at Mega.co.nz to get 50GB of free storage.

▫️Sign up at Hubic.com to get 25GB of free storage.

▫️Sign up at Firedrive.com to get 20GB of free storage.

▫️Sign up at Onedrive.live.com to get 15GB of free storage.

▫️Sign up at Copy.com to get 15GB of free storage.

▫️Sign up at Mediafire.com to get 10GB of free storage. (40GB more available with other activities)

▫️Sign up at Pcloud.com to get 10GB of free storage (10GB more available with other activities)

▫️Sign up at Box.com to get 10GB of free storage.
👍1
ምን አይነት የኮምፒውተር ሶፍትዌሮችን ይፈልጋሉ? ኮሜንት ያድርጉልኝ! በተጨማሪም በዌብሳይቴ በመግባት ምርጥ ሶፍትዌሮችን ማግኘት ይችላሉ!
👇👇👇ይጫኑ👇👇👇
www.mametechsolution.com
🔥1
በወረቀት ያለን ጽሁፍ ወደ Soft copy በሰከንድ መቀየር Image To Text Convert From Hard copy to Soft copy easily በቀላሉ!
👇👇👇👇👇👇👇👇👇
https://youtu.be/82v-xzREk4Y
https://youtu.be/82v-xzREk4Y
https://youtu.be/82v-xzREk4Y
https://youtu.be/82v-xzREk4Y
https://youtu.be/82v-xzREk4Y
👍1
ለመሆኑ የአማዞን መስራች ማን ነዉ። እንዴትስ ተመሰረተ??👇👇

🛒amazon (አማዞን)

⚛ በጃኑዋሪ 12 1964 ዓ.ም. ነዉ ሜክሲኮ በተባለች የአሜሪካ ክፍለ ግዛት ዉስጥ የተወለደዉ ጄፍ ቤዞስ ገና በወጣትነቱ ነበር ለኮምፒዉተር ፍቅር ያደረበት። ከዚህም የተነሳ የወላጆቹን የመኪና ማቆሚያ ጋራዥ በመዉሰድ የራሱ የኮምፒዉተር ቤተ-ሙከራ አደረገዉ። የ2ተኛ ደረጃ ትምህርቱን በከፍተኛ ዉጤት ከተመረቀ በኋላ በታዋቂዉ የፕሪንስተን ዩኒቨርስቲ የመጀመሪያ ድግሪዉን በኮምፒዉተር ሳይንስና ኤሬክትሪካል ኢንጅነሪንግ በ1986 ዓ.ም. በከፍተኛ ማዕረግ ተመርቋል። በርካታ የሥራ መቀጠር እድሎችን ያገኘዉ ጄፍ በዞስ በኒዉዮርክ ከተማ በከፍተኛ ደሞዝና ኃላፊነት ተቀጥሮ መሥራት ጀመረ። ምንም እንኳን ተቀጥሮ የሚሰራበት ስራ ከፍተኛ ደመወዝ የሚያስገኝለትና ስልጣንንም ያቀናጀዉ ቢሆንም፣ ሥራዉን ከአራት አመት በኋላ ለቆ በመዉጣት ዛሬ በኢንተርኔት ዘርፍ ታላቅ ስኬት የተቀናጀዉን አማዞንን ለማቋቋም ተነሳ። በወቅቱ ገና አዲስ የነበረዉን ኢ-ኮሜርስን ለማካሄድ ምርጥ ስራዉን የመልቀቅ እርምጃዉ እብድ ቢመስልም የፈጠራ ባለሙያዎች ባህርይ አንድን ነገር ለመሞከር መድፈርና ዉድቀትን አለመፍራት በጄፍ ቤዞስ ዉስጥም ጎልቶ ታይቷል። በ1994 ዓ.ም. ኒዉዮርክን ለቆ ኑሮዉን በሲያትል ከተማ በማድረግ የመጀመሪያዉን የመፅሀፍ መገበያያ ድረ-ገፅ ይፍ አደረገ። የመኖርያ ቤቱን የመኪና ጋራዥ የኮምፒዉተር ተቋሙ፣ መኝታ ቤቶቹንም ቢሮ በማድረግ ከጥቂት ሠራተኞች ጋር ስራዉን ጀመረ። 300 ያክል ዘመድ ወዳጆቹን ለሙከራ ወደ ስራዉ የመገበያያ ድረ-ገፅ በመጋበዝ አነስተኛ ክፍያን እየተቀበለ መፅሃፍትን በኢንተርኔት ላይ መሸጥ የተጀመረዉ ስራ በጁላይ 1995 ዓ.ም. "amazon.com" በሚል ስም ለተጠቃሚ ክፍት አደረገ። ቤዞስ አማዞን የሚለዉን ስም ያወጣዉ በሁለት ምክንያቶች ነበር። የመጀመሪያዉ የአማዞንን ጫካ በመወከል በርካታ መፅሃፍት የሚገኙበት ግዙፍ የኢንተርኔት መደብር መሆኑን ለማሳየት ሲሆን፣ ሁለተኛዉ ደግሞ በወቅቱ ድረ-ገጾች በፊደል ቅደም ተከተል ይደረደሩ ስለነበር በቀላሉ ለሰዎችበድረ-ገጾች ማሰሻ ላይ እንዲታይ ታስቦ ነበር። የአማዞን መለያ አርማ በሶስት የመሻሻል ሂደት ዉስጥ ያለፈ ሲሆን፣ በ2000 ዓ.ም. የተደረገዉ መሻሻል ዛሬ ድረስ የምናቀዉን መልክ ሰጥቶታል። በዚህ የመለያ አርማ ላይ ያለዉ ከፍ "A" ተነስቶ "Z" ጋር የሚደርስ ቀስት ሁሉንም ነገር በአማዞን ላይ ማግኘት እንደሚቻል ለማሳየት ነዉ።

♈️ ድረ-ገጹ ተወዳጅነትን ያተረፈዉ ወድያዉኑ ነበር። በ60 ቀናት ዉስጥ ያለምንም ማስታወቂያ በበርካታ የአሜሪካ ግዛቶች እና ከ45 በላይ አገራት ዉስጥ የሚነኙ ደንበኞች ዋጋዉ ከ$20 ሺህ በላይ የሚያወጣ የመፅሃፍ ግዢን ፈጸሙ። በ1997 ዓ.ም. አማዞን አክስዮኑን ለህዝብ መሸጥ ጀመረ። ጄፍ ቤዞስ በድረ-ገጹ ላይ የሚሸጠዉን እቃ ከመፅሃፍት ባለፈ መልኩ በማሳደግ ሲዲዎቹንና ፊልሞችን አካቶ መሸጥ ጀመረ። ቀጥሎም የህጻናት አሻንጉሊቶችን፣ ልብሶችንና የኤሌክትሮኒክ እቃዎችንና በርካታ ምርቶችን መሸጡን ቀጠለ። በወቅቱ ተከስቶ በነበረዉ የኢንተርኔት ኢኮኖሚ ቀዉስ "dot com crisis" ብዙ ኩባንያዎችን ከገበያ ዉጪ ቢያደርጋቸዉም አማዞን ግን ትርፍማነቱን ቀጥሎ በ1995 ዓ.ም. ከአካሄደዉ የ500 ሺህ ዶላር ሽያጭ በጥቂት ዓመት ዉስጥ ቁጥሩ እጅግ ጨምሮ ወደ ሚሊየኖች ገባ። አማዞን በ2007 ዓ.ም. የመፅሃፍት ነባራዊ እዉነታ የሚቀይር ፈጠራ አስተዋወቀ። ኪንድል የዲጂታል መፅሃፍ ማንበቢያ "e-reader" በመፍጠር የታተሙ መፅሃፍትን ከመግዛት በተጨማሪ አንባቢዎች ዲጂታል መፅሃፍትን በኪንድል ገዝቶ በማዉረድ እንዲጠቀሙ አስቻለ። በ2011 ዓ.ም. ኪንድል ፍየር የተባለዉን ታብሌትም ይፍ አድርጎ የገበያ ፉክክርን ተቀላቀለ። ኩባንያዉ በመላዉ ዓለም በርካታ ቢሮዎች፣ የመረጃ ተቋማት (datacenters) እና ከ150 ሺህ በላይ ሰራተኞች አሉት። በሰከንድ እስከ 500 የግዢ ትዕዛዞችን ማስተናገድ የሚችለዉ አማዞን በመላዉ አለም ከ244 ሚሊየን በላይ ቋሚ ደንበኞች እንዳሉት ይነገራል። በአሁኑ ሰዓት በአመት በአማካኝ ወደ $130 ቢሊየን በላይ ሽያጭ ያከናዉናል። ጄፍ ቤዞሶ ከ$110 ቢሊየን በላይ በማካበት በአጠቃላይ የሰዉ ልጅ ታሪክ ዉስጥ ትልቁ ባለጸጋ ሊሆን በቅቷል። ከ1990ዎቹ ጀምሮ በዓለም ላይ አንደኛ ባለጸጋ የሆነዉን ቢል ጌትስ ለመጀመሪያ ጊዜ በሃብት በመብለጥ የዓለማችን 1ኛ ባለጸጋ መሆን የቻለዉም በ2017 አጋማሽ ላይ ነበር። የባለጸግነቱ እርከን በየጊዜው ቢቀያየርም በፎርብስ ዘገባ መሠረት ጄፍ ቤዞስ በሰዉ ልጅ ታሪክ ዉስጥ ቁንጮ የዓለማችን ባለጸጋ ሊሆን በቅቷል።

🔜
⏺ የYouTube channel Subscribe በማድረግ ጥሩ ጥሩ ትምህርታዊ ቪዲዮችን ይከታተሉ።
የ YouTube ቻናል ሊንክ 👇👇👇
https://www.youtube.com/channel/UCZBIP6PqUdmmagdTjbyp_AQ
👍2❤1👏1
♦️ለምን ከብርሃን ፍጥነት በላይ መጓዝ አይቻልም?

▪️አንስታይን በዚሁ የአንጻራዊ ዕይታ ጥናቱ ላይ የብርሃን ፍጥነት የአጽናፈ አለም የፍጥነት ወሰን እንደሆነ አብራርቷል። ከብርሃን ፍጥነት በላይ መጓዝ የማይታሰብና የፊዚክስ ህግን እና ሌሎች መሠረታዊ ህጎችን የሚጥስ ነዉ። ከብርሃን ፍጥነት በላይ መጓዝ ማለት ሽጉጥን ሳንተኩስ ጥይቱ ዒላማዉን መታ ማለት ነዉ። ብርሃን በሰከንድ 300 ሺህ ኪሎ ሜትር ይጓዛል።

በጠፈር ዉስጥ የሚገኝ ቁስ አካል "Higgs field" በተሰኘ ሚስጥራዊ ይዘት ዉስጥ ይንቀሳቀሳል። የተለያዩ ቁስ አካላት ከ"Higgs field" ጋር በሚያደርጉት ጥምረት የተነሳ ክብደታቸዉን "mass" ያገኛሉ። ከ"Higgs field" በተለያየ የጥንካሬ ደረጃ እና መጠን የሚፈጥሩት ጥምረትም ቁሶች የተለያየ አይነት ክብደት እንዲኖራቸዉ ያደርጋል። ብርሃን ግን ፎቶን "Photon" ከሚባሉ ቅንጣቶች "Particler" ስለተፈጠረ ክብደት የለዉም።

ክብደት ያላቸዉ ቁስ አካላት ሁሉ ምንም አይነት ፍጥነት እንዲያገኙ የሆነ ልዩ ሃይል ያስፈልጋቸዋል። የአንድን አካል ፍጥነት ወደ ብርሃን ፍጥነት እንዲቀርብ ለማድረግ ደግሞ እጅግ ከፍተኛ የሆነ ሃይል መስጠት ያስፈልጋል። ምክንያቱም ፍጥነት በጨመረ ቁጥር የአንድ ቁስ ክብደትም ስለሚጨምር ነዉ። ይህ ከፍጥነት የተነሳ የሚፈጠር የክብደት መጨመር አስገራሚ እዉነታ፣ አንድ እጅግ ኢምንት የሆነች እና ለዓይን እንኳን የማትታይ ቁስን በብርሃን ፍጥነት ለማስኬድ ልክ የለሽ ሃይል እንዲያስፈልግ ያስገድዳል። ምክንያቱም ይህች እጅግ ትንሽ የሆነች ነገር በዚህ ፍጥነት ለመሄድ ስትሻ ክብደቷ ገዝፎ ያልተወሰነና በጣም ትልቅ ስለሚሆን ነዉ። በዚህ አጽናፈ ዓለም ላይ አንድን ኢምንት ቁስ እንኳን በብርሃን ፍጥነት እንድትጓዝ ማድረግ ከባድ ከሆነ፣ የገዘፈን ነገር በዚህ ፍጥነት እንዲጓዝ ማድረግ ምን ያህል ከባድ እንደሆነ ማሰብ ይቻላል።
👍1
ጎግል ዶክስ(Google Docs) ምንድን ነው? ምንስ ለማድረግ ነው የሚጠቅመን?እንደትስ ነው መጠቀም የምንችለው?

ጎግል ዶክስ(Google Docs) ምንድን ነው?
how to user Google Docs
ጎግል ዶክስ(Google Docs) ማለት ነፃ የሆነ የመስመር ላይ(online) ፕሮግራም ሲሆን ተጠቃምሆችን
ልክ እንደ ማይክሮሶፍት ኦፍስ(microsoft office) ማይክሮሶፍት ወርድ(microsoft word) ፣ ኤክስል(microsoft excel) እና ፓወር ፖይንት(microsoft powerpoint) የመሳሰሉ ፕሮግራሞችን ማዘጋጀት ያስችላል።
ምንስ ለማድረግ ነው የሚጠቅመን?
የተለያዩ ዶክመንቶችን መስቀል(upload) እና ማውረድ(download) ያስችላል
ዶክመንቶችን በአማርኛ መፃፍ ያስችላል
በቀላሉ ዶክመንቶችን ማጋራት(share) ማድረግ ያስችላል
አንድን ዶክመነት በአንድ ግዜ ለብዙ ሰው ሆኖ መስራት ያስችላል
በወርድ ኮክመንት የተፃፉ ዶክመንቶችን ማንበብ እና መፃፍ ያስችላል
ዶክመንቶችን (save) ማድረግ አያስፈልግም እራሱ ያድርገዋል
እንደትስ ነው መጠቀም የምንችለው?
ጎግል ዶክስ(Google Docs) ለመጠቀም በሁለት አይነት መንገድ መግባት ይቻላል።
1. ጅሜል አካውንት(gmail) በመጠቀም
2. በቀጥታ https://docs.google.com መግባት ይቻላል
ጅሜል አካውንት(gmail) ተጠቅሞ ለመገግባት
1. መጀመሪያ የጎግል አካውንት(gmail) በመጠቀም ይግቡ
2. በጅሜል አካውንት ከገቡ በኋላ
በቀኝ በኩል ጥግ ላይ የአራት ማዘን ምልክት ይጫኑ
Docs የሚለውን ይምረጡ (ካላገኙት more የሚለውን ይጫኑ) አሁንም ካላኙት even more የሚለውን ይምረጡት

በቀጥታ https://docs.google.com መግባት ይቻላል
1. ቀጥታ ያለ ጅሜል መግባት ከፈለጉ ይህን URL https://docs.google.com ፅፈው ከገቡ በኋላ
የጅሜልን የመጠቀሚያ ስም(username) እና የይለፍ ቃል(password) ካስገቡ በኋላ

please click image for better view
1. የሚጠቀሙበትን ዶክመንት ዓይነትለመምረጥ ይህን ምልክት ይጫኑ
1. ወርድ(microsoft word) ከሆነ የሚፈልጉት Docs ኤክስል(microsoft excel) ከሆነ የሚፈልጉት Spread በመጨረሻም ፓወር ፖይንት(microsoft powerpoint) ከሆነ የሚፈልጉት Slides የሚለውን ይምረጡት።
የተለያዩ ቀድመው በተዘጋጁ ዶክመንቶች መጠቀም ያቻላል
ወርድ/Docs(Microsoft word) ተምፕሌት(Templates)
1. Blank
2. Resume
3. Report
4. Letters
5. Essay
6. Class notes
7. Lesson plan
8. project proposal
9. Meeting notes
ኤክስል/Spread(microsoft excel) ተምፕሌት(Templates)
1. Blank
2. To-do list
3. Annual budget
4. Monthly budget
5. Calendar
6. Schedule
7. Travel Planner
8. Wedding Planner
9. Invoice
10. Weekly time sheet
11. Expense report
12. Purchase order
13. Attendance
14. Grade book
ፓወር ፖይንት/Slides (microsoft powerpoint) ተምፕሌት(Templates)
1. Blank
2. Pitch
3. Photo album
4. Wedding
5. Lesson plan
6. Book report
7. Status report
8. Case Study
9. Consulting proposal
10. Professional profile
11. Employee certificate
12. General Presentation
13. Photo Album
14. Recipe book
15. Profolio
16. Lookbook
17. party invite
⏺ የYouTube channel Subscribe በማድረግ ጥሩ ጥሩ ትምህርታዊ ቪዲዮችን ይከታተሉ።
የ YouTube ቻናል ሊንክ 👇👇👇
https://www.youtube.com/channel/UCZBIP6PqUdmmagdTjbyp_AQ
👍7😁1
አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ-Artificial Intelligence
🔷 መግቢያ
አሁን በአለንበት ዘመን የኢንተርኔት ቴክኖሎጂ ዓለምን ከጥግ እስከ ጥግ እያዳረሰ፤ ዕውቀትን እና መረጃን የማሰራጨት እና የማጋራት ባህል በከፍተኛ ደረጃ እየጨመረ ነው፡፡ በመሆኑም በውስብስብነቱ እና በአስቸጋሪነቱ ምክንያት በብዙ የሳይንስ ምሁራን ዘንድ ሳይደፈር ለዘመናት በአዝጋሚ የእድገት ደረጃ ላይ የቆየውን “አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ” ቴክኖሎጂን በፍጥነት እያሳደገው ይገኛል፡፡ ዕውቀት ከአንዱ የዓለም ክፍል ወደሌላኛው የዓለም ክፍል በፍጥነት እና በብዛት መሰራጨቱ፤ ችግሮችን በጋራ አቅርቦ የመፍታት እና የመማማር ባህል መዳበሩ፤ በተለያዩ የአለም ክፍሎች የሚገኙ አፍቅሮተ-ቴክኖሎጂ ያላቸው ወጣቶች (Tech geeks) በብዛት መሳተፋቸው፤ ለዘርፉ በከፍተኛ ደረጃ ማደግ እንደ ምክንያትነት የሚጠቀሱ ናቸው፡፡
በዚህ ዘርፍ ለሰው ልጅ የሚጠቅሙ አያሌ ግኝቶች በስራ ላይ ውለዋል፡፡ከነዚህም ውስጥ ከባድ እና አሰልቺ የሆኑ ተደጋጋሚ ስራዎችን በፍጥነት እና ያለምንም ስህተት የሚያከናውኑ ግዙፍ የፋብሪካ ሮቦቶችን፤ እጅግ ሰፊ ከሆነ የዕውቀት ውቅያኖስ ውስጥ ተፈላጊውን መረጃ በአጭር ጊዜ እና በከፍተኛ ፍጥነት የሚያቀርቡ ሶፍትዌሮችን፤ያለምንም አሽከርካሪ ራሳቸውን ችለው የሚንቀሳቀሱ መኪናዎችን.. ወዘተ መጥቀስ ይቻላል፡፡
አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ እና ሮቦቲክስ ምን እና ምን ናቸው
አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ማመዛዘንን (ምክኒያታዊነትን)፣ ዕውቀትን፣ ዕቅድን፣ መማርን እና ቋንቋን በፅንሰ-ሀሳብ ደረጃ ሚስጥራቸውን መፍታት እና በሳይንሳዊ ሂደት መተንተን ነው፡፡ የሰው ልጅ አነኚህን ክህሎቶች የሚያዳብረው በተጠናና በተቀመረ መልኩ ሳይሆን በተፈጥሮ የህይወት ዑደት ውስጥ ነው፡፡ በተፈጥሮአዊ ልምምድ የሚዳብሩትን እነዚህን ክህሎቶች በቀመር እና በሳይንሳዊ ጥናት ለመተንተን መሞከር ግን እጅግ ፈታኝ ተግባር ነው፡፡ አንድ ህፃን ልጅ እየተኮላተፈ አማርኛ ሲናገር፤ ከዛም በአጭር ጊዜ ቋንቋውን ሲያቀላጥፈው ማየት ለብዙዎቻችን አስገራሚ አይሆንም፡፡ ሆኖም ይህንን የክህሎት ሒደት በሳይንሳዊ ትንተና ፈትቶ እና ተመሳሳይ ባህሪያትን ለማሽኖች ወይም ለሶፍትዌሮች አላብሶ ማላበስ መቻል ግን ከፍተኛ ስኬት ነው፡፡ አንዳንዴም እንዲህ ያለው ተግባር የፈጣሪን ሚና እንደመተካት ሊቆጠር ይችላል፡፡ቢሆንም ብዙ ወጣቶችን ወደዚህ ዘርፍ እንዲሳቡ ያደረጋቸው ዋነኛ ምክንያት ይህ የዘርፉ ውስብስብነት የፈጠረው ተግዳሮትን የመፍታት እልህ እና ተፈጥሮን አስመስሎ እና ተንትኖ የማቅረብ ረሀብ ነው፡፡
በሌላ በኩል ሮቦቲክስ የሜካኒካል ምህነድስና፣ ኤሌክትሮኒክ ምህንድስና፣ እና የኮምፒውተር ሳይንስ ቅርንጫፍ ሲሆን፤ የአርቴፊሻል ኢንተለጀንስን ዕውቀት በከፍተኛ ደረጃ በግብዓትነት በመጠቀም የሚንቀሳቀሱ፣ እንደሰው አመዛዝነው ውሳኔ የሚሰጡ፣ ሰውን ተክተው አልያም ከሰውልጅ ጎን ለጎን ሆነው የተለያዩ ተግባራትን የሚከውኑ ሜካኒካዊ እና ኤሌክትሮኒካዊ ሮቦቶችን የሚያጠና ዘርፍ ነው፡፡ ዘርፉ ቁስ አካላዊ ሮቦቶችን ብቻ ሳይሆን መረጃን የሚያቀነባብሩ ብልህ የኮምቲውተር ሲስተሞችንም ያጠቃልላል፡፡
አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ስለ ማመዛዘን (ምክኒያታዊነት)፣ ዕውቀት፣ ዕቅድ፣ መማር እና ቋንቋ ፅንሰ-ሀሳባዊ ምንነት በሳይንሳዊ ትንታኔ ሲያቀርብ፤ ሮቦቲክስ ደግሞ ከአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ያገኘውን የውስብስብ ፅንሰ-ሀሳቦች ምንነት እና ሌሎች ተጓዳኝ የምህንድስና ዕውቀት በመጨመር ለተለያዩ ጥቅም የሚውሉ ሮቦቶችን ይሰራል፡፡
🔷 ታሪክዊ ሂደት
ግኡዛንን እንደሚያስቡ እና ባለአዕምሮ ፉጡራን አድርጎ መስራት ጥንት የግሪክ፣ የግብፅ፣ እና ሌሎችም ጥንታዊ ገናና የሰውልጅ ስልጣኔ ታሪክ ውስጥ ጉልህ ስፍራ ነበራቸው፡፡ በተለይ በግሪክ እና ግብፅ ጥንታዊ ስልጣኔ ውስጥ ለጣኦት አምልኮ የሚውሉ የሚንቀሳቀሱ ግኡዝ አካላትን መስራት የተለመደ ነበር፡፡ እነዚህ የሰው ልጅ ፍላጎቶች የተለያዩ መልኮችን ይዘው እና አድገው እስከ 2ኛው የዓለም ጦርነት ድረስ በመዝለቅ፤ አሁን ላለንበት የዲጂታል ቴክኖሎጂ እና አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ምዕራፍ ወሳኝ መሰረት የጣለውን ‹‹የአለን ቱሪንግ››ን የምርምር ውጤት ወልደዋል፡፡
ከአመታት በኃላ፣ እ.ኤ.አ በ1956 በዶረቱሙን ኮሌጅ ግቢ በተደረገው ኮንፍረንስ የተመሰረተው የአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ጥናት፤ በኮንፍራንሱ ተሳታፊዎች እና በተማሪዎቻቸው አማካኝነት ለብዙ አስርታት የመስኩ ብቸኛ ተዋናይ ሆነው ቆይተዋል፡፡ ተማሪዎቹ በወቅቱ ለብዙዎች አስገራሚ ሊባሉ የሚችሉ ‹‹ምጡቅ›› የኮምፒውተር ፕሮግራሞችን በመስራት ለእይታ አቅርበው ነበር፡፡ ቼዝ ተጫወተው የሚያሸንፉ፤ አልጄብራን እንዲሁም የሎጂክ ቴረም ጥያቄዎችን የሚፈቱ እና እንግሊዘኛ የሚናገሩ የኮምፒውተር ፕሮግራሞች ተማሪዎቹ ይሰሯቸው ከነበሩት ውስጥ ተጠቃሽ ናቸው፡፡ ከ1960 ጀምሮ የዚህ ምርምር የገቢ ምንጭ የአሜሪካ መከላከያ ተቋም ስለነበረ በ1974 የገንዘብ ድጋፉ በመቋረጡ የዘርፉም እድገት በከፍተኛ ሁኔታ ቀንሶ ነበር፡፡ ይሁን እንጂ በ1980 መጀመሪያ አካባቢ በተለያዩ የሙያ ዘርፎች የባለሙያ ትንታኔ የመስጠት ችሎታ የነበረው
‹‹የኤክስፐርት ሲስተም›› ከፍተኛ ተቀባይነት በማግኘቱ ዘርፉ እንደገና አንሰራራ፡፡ በዚህም ምክንያት የዘርፉ ጠቅላላ ገቢ እስከ 1ቢሊዮን ዶላር ደርሶ ነበር፡፡ ይሁን እንጂ እንደገና በ1987 አካባቢ ከሊስፕ ኮምፒውተር ገበያ ማጣት ጋር ተያይዞ ገበያው በመቀዛቀዙ ሁለተኛውን እና ረጅሙን የድብርት(Depression) ጊዜ አሳልፏል፡፡ ከዛም ከ1990ዎቹ ጊዜ እስከ 21ኛው ክፍለ ዘመን መጀመሪያዎቹ ድረስ ድምፁን አጥፍቶም ቢሆን ከፍተኛ ስራ ሰርቷል፡፡
በ1997 ‹‹ዲፕ ብሉ›› የተባለው የኮምፒውተር ቼዝ ተጫዋች በወቅቱ በቼዝ ጨዋታ ሻምፒዬን የነበረውን ጌሪ ካስፓሮቭን በማሸነፍ አለምን ጉድ አሰኝቶ አልፏል፡፡ በ2011 የIBM ስሪት የሆነው ዋትሰን የተባለው የኮምፒወተር ሮቦት በ ጆፓራዳይ የቴሌቭዥን የጥያቄ እና መልስ ሾው ላይ በመሳተፍ ብራድ ሩተር እና ጆን ክኒንስ የተባሉትን የጥያቄና መልስ ውድድር ቻምፒዎኖቹን በከፍተኛ የነጥብ ልዩነት አሸንፏቸዋል፡፡
🔷 የአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ትግበራ በተለያዩ ዘርፎች ውስጥ
አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ በህክምና፣ ህግ፣ ሮቦቲክስ፣ ሪሞት ሴንሲንግ፣ ትራንስፖርት ዘርፎች ላይ ተግባራዊ የሆነ ቢሆንም፤ አንዴ ለገበያ ከቀረበ እና በሰፊው ጥቅም ላይ ከዋለ፤ አሰራሩም ከታወቀ በኃላ ግን ‹‹ብልህ›› መሆኑ ያከትምለታል ብለው ብዙዎች ይከራከራሉ፡፡ በዚህም ምክንያት በብዙ ሺህ የኢንደስትሪ ማሽኖች ላይ ተገጥመው የሚገኙ ቢሆኑም ለረጅም ጊዜ ለብልህነታቸው ይህ ነው የሚባል እውቅና ሲሰጣቸው አይሰተዋልም፡፡
🔷 በህክምና እና ጤና ተቋማት
የተለያዩ የህክምና ተቋማት የውስጥ አስተዳደራዊ አሰራራቸውን ለማቀላጠፍም ሆነ ሳይንሳዊ መረጃዎችን ለህክምና ባለሙያች ለመለገስ አርቴፊሻል ኢንተለጀንስን እይተጠቀሙ ይገኛሉ፡፡ የአስተኝቶ ማከም ቀጠሮዎችን በማመቻቸት ሆነ የባለሙያዎችን የስራ ፈረቃ ፕሮግራም በማውጣት ላቅ ያለ አስተዳደራዊ ጥቅም ይሰጣሉ፡፡ በተጨማሪም በኮምፒውተር የታገዘ ምስል በማንሳት እንደ ካንሰር ያሉ ችግሮችን ለባለሙያዎች በመጠቆም፤ እጅግ ብዙ ከሆኑ የሜዲካል ዕውቀቶች ውስጥ ተፈላጊውን መረጃ አስሶ ለባለሙያው በመስጠት ሙያዊ አበርክቶ ያደርጋሉ፡፡
የቀጠለ........ በቅድሚያ ከላይ ያለውን ያንብቡ...
አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ-Artificial Intelligence
🔷 በከባድ ኢንደስትሪዎች
ለሰው ልጅ እጅግ አደገኛ በሆኑ፣ ድግግሞሽ በሚበዛባቸው አድካሚ የከባድ ኢንደስትሪ ስራዎች ውስጥ የአርቴፊሻል ኢንተለጀንስን ዕውቀት የሚጠቀሙት ሮቦቶች የማይተካ ሚና ይጫወታሉ፡፡ ስለሆነም የሰው ልጆችን ከአደጋ ይታደጋሉ፣ ስህተት ስለማይሰሩ እና ስለማይደክማቸው ከፍተኛ ውጤት ያስመዘግባሉ፡፡ በአሁኑ ወቅት በመኪና ምርት፣ በማዕድን ማውጣት ስራ እና ትላልቅ የፋብሪካ ማሽኖችን በሚያመርቱ ኢንደስትሪዎች ውስጥ ከፍተኛ አገልግሎት በመስጠት ላይ ናቸው፡፡
🔷 በትራንስፖርት
ሹፌር አልባ መኪኖች ራሳቸውን በራሳቸው የሚያንቀሳቅሱ፤ የተሰጣቸውን ትእዛዝ ተቀብለው ሰውንም ሆነ ዕቃ የተፈለገው ቦታ የሚያደርሱ፤ ተሰሳስተው አልያም ደክሟቸው በቸልተኝነት አደጋን የማያደርሱ መኪኖች የአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ የምርምርና ዕውቀት ውጤቶች ናቸው፡፡ ምንም እንኳን በአሁኑ ጊዜ በስፋት ለጥቅም ባይውሉም በGoogleX ፕሮጀክት በመሰራት ላይ ያለው አሽከርካሪ አልባ መኪና ተጠቃሽ ነው፡፡ ይህ መኪና ‹‹ጉግል ሹፌር›› የሚባል ሶፍትዌር የተገጠመለት ሲሆን የአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ዕውቀትን ተግባራዊ በማድረግ የተሰራ ሶፍትዌር ነው፡፡ መኪናው በአሁኑ ወቅት በሙከራ ላይ ይገኛል፡፡
የሥነ ምግባር እና የፍልስፍና ጥያቄዎች
አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ በተወሰነ ደረጃም ቢሆን የሰው ልጅ አስተሳሰብ፣ ባህሪ እና ጠባይ ለማሽኖች የሚያላብስ የሳይንስ ዘርፍ እንደሆኑ መጠን፤ ከዚህ ጋር ተያይዞ በዛ ያሉ የሞራል፣ የስነምግባር እና የፍልስፍና ጥያቄዎችን ማስነሳቱ አልቀረም፡፡ ከፍልስፍና ጥያቄዎቹም ውስጥ ከዚህ በታች የተዘረዘሩት ሶስቱ በዋነኛነት ተጠቃሽ ናቸው፡-
1. ማሽኖች የሰው ልጅ ሊፈታቸው የሚችላቸውን ችግሮ በሙሉ የመፍታተት አቅም ይኖራቸዋልን? ወይስ ማሽኖችን ‹‹ሰው›› የማድረግ ጥረት ገደብ አለው?
2. የአርቴፊሻል ኢንተለጀንስን ባህሪያት የተላበሱ ማሽኖች አደገኛ ሊሆኑ ይችላሉን? በስነ-ስርአት እና ወግ ባለው መልኩ ጥቅም ላይ እንዲውሉ፤ ብሎም በምንም አይነት መልኩ ከቁጥጥር ውጭ የሆነ ባህሪ እንዳይላበሱ ማድረግ ይቻላልን?
3. ማሽኖችን ልክ እንደ ሰው ባለአእመሮ እና ባለህሊና ማድረግ ይቻላልን? እንደ ሰው ልጆችስ መብት ይኖራቸዋል? አውቀው እና በራሳቸው ተነሳሽነት ተንቀሳቅሰው በሰው ልጅ ላይ ጉዳት ማድረስ ይችላሉን?
ከላይ በተነሱት ጥያቄዎች ዙርያ የተለያዩ ሙሁራን የየራሳቸውን ፅሁፍ እያቀረቡ በንድፈ-ሀሳብ ደረጃ የተከራከሩ ሲሆን፤ ጥያቄዎቹ ምላሽ ሊያገኙ የሚችሉት በጊዜ ሒደት ብቻ ነው፡፡ በዚህም ምክንያት የተለያየ ጥግ ይዘው ጥያቄዎቹን ለመመለስ የሞከሩም ሆኑ የሚሞክሩ ምሁራን ትክክለኛነታቸው የሚረጋገጠው በዘርፉ የተፈጥሮ እድገት ሂደት ውስጥ ብቻ ይሆናል ማለት ነው፡፡ እዚህ ጋር ሳይጠቀስ የማይታለፈው አንደኛው ጥያቄ ከሞራል ጋር የተገናኘው ነው፡፡ የሰው ልጆች ከአደጉበት ባህል፣ ከኖሩበት ዘመን ጋር በማቆራኘት ስለ ሞራል ምንነት ትርጓሜ ሲሰጡ ይታያል፡፡ በዚህም የተነሳ በተለያዩ የህይወት ውሳኔዎቻቸው ላይ ይህ የሞራል ግንዛቤ የራሱን አስተዋፅኦ ያሳድራል፡፡ ሞራል የጊዜ እና የባህል ተፅዕኖ ስለሚበዛበት አንድ ወጥ የሆነ ሞራላዊ ምንነት ለማሽኖች እንዲላበሱ የሚደረገውን ምርምር በዛው ልክ ወጥ ያልሆነ እና ውስብስብ እንዲሆን አድርጎታል፡፡ ይሁን እንጂ ከላይ በተነሱት ፅንሰ-ሀሳባዊ የፍልስፍና ጥያቄዎች ዙርያ የሚደረጉት ምሁራዊ ክርክሮች እና ትንታኔዎች አሁንም ድረስ እንደቀጠሉ ናቸው፡፡
ከሞራል እና ስነ-ምግባር ጋራ የሚነሱ ጥያቄዎች እና በምሁራን የሚሰጡ ትንታኔዎች አከራካሪ፣ መሳጭ እና የሰውን ልጅ የወደፊት እጣ ፈንታ የሚወስኑ ስለሚሆኑ፤ በቀጣይ በዚህ ድረ-ገፅ የተለያዪ ፅሁፎችን በትንታኔ መልክ ለማቅረብ ይሞከራል፡፡
🔷 ማጠቃለያ
ብልህ እና እንደ ሰው ልጅ የሚያስቡ ቁስ አካላትን ለመፍጠር የሚደረገው ሳይንሳዊ ምርምር እና ዕውቀት ወደፊት የሰውን ልጅ የአኗኗር ስልት በከፍተኛ ሁኔታ እንደሚቀይር የማያጠራጥር ነው፡፡ አደጋን የሚቀንሱ፣ ጤንነትን የሚያሻሻሉ፣ ከፍተኛ ምርትን የሚያስገኙ፣ ወዘተ ጥቅሞችን እየሰጡ የሚገኙ እና ወደፊትም በላቀ ጥራት እና ውስብስብነት የሰውን ልጅ ህይወት የሚያቀሉ የአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ውጤቶች በዚህ አጭር ዕሁፍ ለመዳሰስ መሞከር ‹‹አባይን በጭልፋ›› እንደ መዝገን ይሆንብኛል፡፡
በዚህ ዘርፍ አያሌ እና ተነግረው የማያልቁ ግኝቶች፣ በምርምር ላይ ያሉ ዕውቀት፣ በዘርፉ ላይ የተነሱ እና የሚነሱ ጥያቄዎች፣ ወዘተ በመረጃነት ይገኛሉ፡፡በመሆኑም በዚህ ድረ-ገፅ ከዘርፉ ጋር ተያያዥ እና ጠቃሚ ናቸው የምንላቸውን ዜናዎች፣ አርቲክሎች(መጣጥፎች)፣ ፖድካስቶችን የምናቀርብ ሲሆን፤ የዘርፉን ውስብስብ ዕውቀትና ልምድ የሚያንፀባርቁ የምሁራን ክርክሮችን ጭምር በየጊዜው በቀላል አገላለፅ ለማቅረብ እንሞክራለን፡፡
👍2
በኮምፒውተር Videos Editing የሰርግ, የምረቃ, የልደት, የቤተሰብ,ፎቶዎችንና ቪዲዮችን ለማቀናበር የሚያስችል ምርጥ ቪዲዮ ካታች ያላውን ሊንክ በመጫን ይመልከቱ።
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
https://youtu.be/-hlhERSvULI

ሶፍትዌሩን ቴሌግራም ላይ ማግኘት ይችላሉ
ቴሌግራም ቻናሌ
https://t.me/MuhammedComputerTechnology/1273
👍1
የበይነ - መረብ ንግድ (Online Business)

ይህን ቻናል ከጀመርን ጀምሮ፤ በቢዝነስ ዙርያ ብዙ ምክረ - ሃሳቦችን እያጋራን ሰንብተናል። አብዛኛው ተደራሲም (የቻናላችን ቤተሰቦች) በመረጃዎቹ እየተጠቀሙ እና እየተማሩ መሆኑን በውስጥ መስመር እና በሃሳብ መስጫ (Comment Box) ሲያጋሩን ነበር። የተለያዩ ጥያቄዎች እየተጠየቁ ምላሽ በተናጠል ስንሰጥ ነበር።

ነገር ግን ከአብዛኛው ቤተሰብ፤ አንድ ተመሳሳይ ጥያቄ በተደጋጋሚ በየጊዜው ሲነሳልን አስተዋልን፤ እሱም "Online Business እንዴት መስራት እንችላለን? በትርፍ ሰዓታችን ኢንተርኔትን በመጠቀም እና በመስራት እንዴት ገቢ ማግኘት እንችላለን?" የሚል ነው።

ይህ ጥያቄ መልኩን እየቀያየረ ረጅም ጊዜ ሲጠየቅ የነበር ቢሆንም በስራ መደራረብ እና ተገቢውን መልስ ለመስጠት ደግሞ ጥናትም ማድረግ ያስፈልግ ስለነበር በጊዜው ማቅረብ አልቻልንም። ለዚህም ከልብ ይቅርታ እንጠይቃለን። ዛሬ በተቻለን አቅም ከኢትዮጵያ ገበያ እና አኗኗር ጋር የተስማማ የበይነ መረብ ንግድ (Online Business ) እንዴት መስራት እንደሚቻል እና በዛም ተጨማሪ ገቢን እንዴት መፍጠር እንደምንችል ለማየት እንሞክራለን።

🖥🖥🖥

ያለንበት ዘመን፤ የዲጂታል ዘመን ስለመሆኑ ምንም የሚያሻማ ጉዳይ አይደለም። አብዛኛውን የሕይወታችንን ክፍል የበይነ - መረቡ (Internet ) ዓለም ጥገኛ እየሆነ ነው። ይህንንም የቫል ኖህ ሃራሪ የተባለ ጸሐፊ " 21 Lessons for the 21st century " በሚል መጽሐፉ በጥሩ ገልጾታል። ከትምህርት እስከ ስራ፣ ከንግድ እስከ ትዳር፣ ከስብሰባ እስከ ስርዓተ ዓምልኮ፣ ከጉርብትና እስከ የዓለም ጦርነት (Cyber War)፤ ሁሉም ነገር በበይነ - መረብ (Internet) ሆኗል።

ታዲያ "በፍየል ዘመን በግ መሆን ለመታረድ ነው" እንዳሉት አንድ አባት፤ በዚህ በዲጅታል ዘመን እኛም ከጊዜው ጋር እኩል ካልተራመድን ወዳቂ ነን። እናም ከጊዜው ጋር እኩል ከምንሄድባቸው ጉዳዮች አንዱ አብዛኛውን የሕይወታችንን ክፍል የምናሳልፍበትን "ስራ" ዲጂታላይዝ በማድረግ ነው። ስራችንን፣ ንግዳችንን ዲጂታላይዝ ማድረግ እና አዲስ ስራዎችን በበይነ - መረቡ አማካኝነት መስራት ለነገ የማይባል ጉዳይ ነው።

📡 ታክሲ ⚰ በ Uber (Ride) ተተካ

📡 ሆቴል ⚰በ AirBnB ተተካ

📡 ሱቅ እና ሱፐርማርኬቶች ⚰ በ Amazon፣ Alibaba፣ በእኛም ሀገር ጅምር ላይ ያሉ እየተኩት ነው።

📡 የአዳራሽ ኪራዮች ⚰ በ Zoom ተተኩ

📡 ሲኒማ ⚰ በ Netflix፣ Amazonprime፣ ሶደሬቲዩብ ተተኩ

📡 ጥሬ ገንዘብ ⚰ በ ክሪፕቶከረንሲ ተተካ

📡 ምግብ ቤቶች ⚰ በ Online ሬስቶራንቶች (Pizza Hut እና ዴሊቨሪ አዲስ) እየተተኩ ነው።

እንደዚህ ብዙ መዘርዘር ይቻላል። በይነ - መረቡ እየገዘፈ እና Dominate እያረገ ነው።

እሺ ጥሩ! የበይነ - መረብን (Internet) አስፈላጊነት ተረዳሁ። ተጽእኖውንም አየሁ። ታዲያ እንዴት ነው የበይነ - መረብ ንግድ (Online Business) መጀመር የምችለው? ምን አይነትስ የ Online Business ነው ገቢ ሊያስገኝልኝ የሚችለው?

መልካም!

የበይነ - መረብ ንግድ ውስጥ ከመግባት ወይም ለመግባት ከማሰብ በፊት በመጀመሪያ የንግድን ጽንሰ ሃሳብ (Concept) መረዳት ያስፈልጋል። ንግድን (Business) በአጭሩ ስናሰቅምጠው ወይንም ቢዝነስ የሚወለደው ከሁለት ቅርጫቶች ነው።

ንግድ

💡 ያለን የኖረን ችግር ፈልገን፣ አጥንተን መጠገን ወይም መቅረፍ (We find a problem and we fix it)

💡 ያለ የሚታይ እጥረትን መሙላት (We find a shortage or demand and fill it)

በአለም ላይ የምናያቸው ከትልልቅ እስከ አነስተኛ ቢዝነሶች መነሻቸው (Motive) ከዚህ አይወጣም።

💡 አንደኛው ላይ ፦ ህብረተሰቡ ( consumer) በጣም የሚያስፈልገው ቁሳቁስ ወይም አገልግሎት የሌለ ከሆነ፤ አልያም ደሞ ያ ህብረተሰብ አገልግሎቱ ወይም ቁሱ ኖሮት ነገር ግን ጊዜ እና ጉልበት የሚፈጅበት ከሆነ ፦ አንድ ሰው ይህን ጉድለት በፈጠራ በመታገዝ ወደ ቢዝነስ መቀየር ይችላል ማለት ነው።

ለምሳሌ፦ የታክሲ አገልግሎት ለዘመናት የኖረ ሆኖ ሳለ ለተገልጋዩ ግን እንደልብ አልነበረም። ስለዚህ አንተርፕረነሮች የታክሲን ስራ አዘምነው (ከዚ በፊት ያልተሞከረ) ፣ ለተገልጋዩ በሩ ድረስ የሚመጣለት አገልግሎት ፈጠሩ። አሁን ያ ፈጠራ በዓለም ላይ ቢልየን ዶላሮችን እያንቀሳቀሰ ነው። ይህን ሲስተም (uber፣ Ride) የፈጠሩት ሰዎች አንድም ታክሲ የላቸውም። ነገር ግን መቶ ሺዎች መኪኖችን ያንቀሳቅሳሉ። በፈጠራ !

ሌላ ምሳሌ ለመጥቀስ፦ በሀገራችን የመኪኖች የካርበን ልቀት በጣም እየጨመረ መጥቷል። በዚህም አየሩ በጣም ከመበከሉ የተነሳ በተለይ ጠዋት እና ማታ ላይ ጉም ሰርቶ ከባቢ አየር ላይ ተንሳፎ ይታያል። ሰዎች ንጹህ አየር መተንፈስ እያቃታቸው ነው። ስለዚህ ለዚህ ፨ችግር፨ አንድ ፈጠራ (Innovation) አንድ ሰው ቢሰራ፡ ማለትም ከባቢ አየር ላይ ያለውን ካርበን (CO2) እየሳበ (suck) የሚያጣራ እና ካርበኑን የሚያጠራቅም አነስተኛ ሳጥን ቢያዘጋጅ፤ ይችንም ሳጥን በየ ስልክ እንጨቱ በየመንገድ ዳር ላይ ቢሰቅላት። ይህን በማድረግም አንድም የተበከለ አየር የማጣራት አገልግሎት ለህብረተሰቡ ይሰጣል፤ ሁለተኛ በሳጥኗ ውስጥ የሚጠራቀመውን ካርበን (CO2) በመሸጥ ተጨማሪ ገቢ ያገኝበታል። ይህን ማድረግ የሚችል ሰው በቀላሉ ቢዝነስ አቋቋመ (someone founded a business) እንላለን፤ ምርቱንም ከግለሰብ እስከ ሃገር ሊገዙት ይችላሉ። (⭕️ይህ የጸሐፊው የፈጠራ ሃሳብ ነው።)

(ጥያቄ፦ በነገራችን ላይ አየር ላይ የሚንሳፈፈው ካርቦንዳይኦክሳይድ (CO2) በብዙ ዶላሮች እንደሚሸጥ ታውቃላችሁ? )

💡ሁለተኛው ደሞ በህብረተሰቡ ውስጥ ያለን ከፍተኛ ፍላጎት (demand) ለይቶ አይቶ ያን ፍላጎት በማሟላት ገቢ ማግኘት ነው። ለዚህ ቀላል ምሳሌ በእኛ ሃገር ያለው የትራንስፖርት እጥረት ነው። የትራንስፖርት አገልግሎት በማቅረብ ቢዝነስ መጀመር። ሌላው የምግብ ፍጆታ እንደ ዘይትና ስኳር። ከፍተኛ demand አለ። ይህንንም ስራውን አጥንቶ መስራት ራሱን የቻለ ቢዝነስ ውስጥ ይከታል።

፨፨፨፨

ንግድ (business) የፍላጎት እና አቅርቦት (demand and supply) ጉዳይ ነው። የንግድ እስትንፋሱ እነዚህ ሁለቱ ናቸው። ከሁለቱ አንዱ ከሌለ ቢዝነስ የለም! ቆም ብላችሁ በአካባቢያችሁ ወይም በሃገታችን ያለውን ፍላጎት (demand) እስቲ አስተውሉት። የስራ ፈጠራ የሚጀምረው ከዛ ነው።

ሰው ምን ይፈልጋል?

ምን ተቸግሯል?

ከዛ ለነዚህ ጥያቆዎች መልስ ፈልጉላቸው። ያ ለነዚህ ጥያቄዎች የምታገኙት መልስ ነው እንግዲህ ቢዝነስ የሚሆነው፤ እናንተንም አንተርፕረነር የሚያደርጋችሁ።

ŠFekadu_G21

ይቀጥላል......
ይቀጥል?
👍4
የበይነ - መረብ ንግድ (Online Business)

ክፍል 2 (ከትላንቱ የቀጠለ)

አሁን ወደ ተነሳንበት የበይነ - መረብ ንግድ (Online Business) እንመለስ። ከላይ ባብራራነው ጽንሰ ሃሳብ መሰረት የበይነ - መረብ ንግድ መጀመር እና ሌላ የገቢ ምንጭ መፍጠር ይቻላል። ነገር ግን ከዘልማዳዊው "ያበላል ወይስ አያበላም" አይነት ያልተጨበጠ ጥያቄ መውጣት እና መጠነኛ የገበያ ጥናት ማድረግ ያስፈልጋል።

፨ ምን ይፈለጋል? ህብረተሰቡ በጣም የሚፈልገው እና የጎደለው ነገር ምንድነው?

ይህ ጥያቄ የትኛው ቢዝነስ ትርፋማ እንደሆነ በራሱ ጠቋሚ ነው። ይህን ጥያቄ ስትጠይቁ መልሱ፦

፨ ወይ ያ ህብረተሰቡ የሚፈልገው ነገር ጭራሽ የለም፤ አልተፈጠረም።

፨ ወይንም አለ፤ ነገር ግን ከፍተኛ እጥረት አለበት።

ስለሆነም በነዚህ ስሌት መነሻነት አንድ ሰው ወይ ፈጣሪ (Innovator) ይሆናል። አልያም ያለን የጎደለን ነገር በማቅረብ በቀላሉ ወደ ንግዱ ይገባል ማለት ነው።

ወደ Online business ስትገቡም በዚህ ጥያቄ መነሻነት ቢሆን መልካም ነው። መታወቅ ያለበት ነገር ቢኖር የግል ስራን መጀመር ቀላል እንዳልሆነ ነው። ቢዝነስ ሲባል ባጠቃላይ እስኪጠነክር እና እውቅናን አትርፎ ደንበኞችን እስኪይዝ ድረስ ውጣ ውረዶች አሉት ። የበይነ መረብ ንግድም ከዚህ አይለይም። ገበያው ላይ ሰርጎ ለመግባት የሚወስደው ጊዜ እና ትእግስት አለ። ይህን ከተረዳን እና ከተስማማን Online biz ለመስራት ( እንደ ስራው አይነት) የሚያስፈልጉ ቁሳቁስ አሉ። ስማርት ስልክ፣ ኢንተርኔት፣ ኮምፒውተር ፣ ካሜራ እና መሰል ኤሌክትሮኒክስ የሚያስፈልጉ ሲሆን ስማርት ስልክ እና ኢንተርኔት መሰረታዊ እቃዎች ናቸው።

እነዚህን ቁሳቁስ በመጠቀም ልንሰራቸው የምንችላቸው የonline biz አይነቶች በብዛት አሉ። በውጩ አለም በዚህ መንገድ በጣም ብዙ የሚሰሩ ስራዎች ያሉ ሲሆን ወደኛ አገር ስንመጣ ግን በመንግስታዊ ህጎች መጥበቅ፣ አዳዲስ ፈጠራዎች ባለመኖራቸው እና የኢንተርኔት ተደራሽነቱም አናሳ በመሆኑ በበይነ መረቡ (online) ላይ የሚሰሩ ስራዎች ውስን ናቸው። የተወሰኑት እና ከእኛ ሀገር ህግና ገበያ ጋር የሚሄዱትን ከዚ ቀጥሎ ለማየት እንሞክራለን።

1⃣ Youtube ፕሮግራሞች ማዘጋጀት

ይሄ በጣም ቀላል እና አለም ላይ በጣም ብዙ ሰዎች እየተጠቀሙበት ያለ አንድ የገቢ ምንጭ ነው። ሙሉ ስራው አለቃ እና አዛዥ ሳይኖርባችሁ በራሳችሁ ተነሳሽነት እና ፈጠራ ብቻ የምትሰሩት ስራ ነው። ዩቱብ አዘጋጅ ለመሆን ደሞ የሞባይል ስልካችሁ ካሜራና ኢንተርኔት በቂ ናቸው። በዚህ መነሳት እና ወደተሻለ ጥራት ማደግ ይቻላል። ነገር ግን ከስራችሁ ተጠቃሚ እና ትርፋማ ለመሆን የምታዘጋጇቸው ቪድዮዎች የሰውን ቀልብ የሚገዙና የሚወደዱ መሆን አለባቸው። ምክንያቱም ትርፋችሁ እና ገቢያችሁ የሚወሰነው ስራዎቻችሁን በሚያይላችሁ የሰው ብዛት ስለሆነ።

አሁንም ከላይ እንደጠቀስነው በዚህም ስራ ትርፋማ ለመሆን "ሰው ምን ይፈልጋል?" የሚለው ጥያቄ ወሳኝ ነው። በዚህ መሰረት በየእለቱም ሆነ በየሳምንቱ ቪድዮዎችን በማዘጋጀትና በመልቀቅ አንድ የገቢ ምንጭ ማግኛት ይቻላል። የአከፋፈል ሁኔታውን፣ መጠኑን እና ትርፉን google በማድረግ ማወቅ ትችላላችሁ። ወይንም በዚህ ቻናላችን ወደፊት እንዳስሰው ይሆናል።

ጥቆማ፦

⏺ ኦንላይን ትምህርቶችን በዩቱብ ማዘጋጀት (እንደ ጊታር ማሰልጠን፣ የ 8ኛ እና 12ኛ ክፍል ተፈታኞችን ማብቃት ወይ ገለጻ ማድረግ፣ ኤሌክትሮኒክስ ጥገና በቀላል አማርኛ፣ ቤት አጠጋገን እና ቀለም አቀባብ) ወዘተ...ህብረተሰቡ ራሱን ሊረዳባቸው እና ሊያሻሽልባቸው የሚችሉ እውቀቶችን ማካፈል፤ ማቅረብ፤


ማሳሰቢያ፦ በተቻለ መጠን የጥላቻ ንግግሮችን እና ፖለቲካ አፍራሽ ነገሮች በመጠቀም ገቢ ለማግኘት አንጣር!!! ሃገር አፍርሶ ህዝብ አጋጭቶ የሚመጣ ገቢ ገደል መግቢያ ነው!

2⃣ Online ሱቆች

እነዚህ አሁን ላይ እኛ ሃገር በጣም በብዛት እየተሰራበት ይገኛል። ብዙ ተቋማት እና ግለሰቦች በfacebook እና በቴሌግራም ግብይት መፈጸም ከጀመሩ ሰነባብቷል። እናንተም የራሳችሁ ቻናል እና facebook page በማዘጋጀት የራሳችሁ Online business ሊኖራችሁ እና ልትሰሩ ትችላላችሁ። ነገር ግን አሁንም " What's the demand in the market" ብሎ መጠየቅ ተገቢ ነው። ምንም ነገር ውስጥ ዘው ብሎ መግባት ሩቅ መንገድ አያስኬድም። ብዙ ኦንላይ ቢዝነስ አለ፤ ታድያ እንዴት መስራት እችላለሁ? ስራው ተይዟል ካላችሁ እነዚህ ቢዝነሶች ገበያውን ሰብረው የገቡበት መንገድ ትምህርት ይሆነናል፦

📶 ሼባ ሰአቶች እና ጌጣጌጦች። የራሱን መልክ ፣ ስም እና ፈጠራ ይዞ ስለመጣ ከነበሩት እጅግ ብዙ ንግዶች ጎልቶ ወጥቷል።

📶 ጦማር መጻህፍት አቅራቢ። መጻህፍትን ( የጠፉትን ሳይቀር ) ለገዢዎች ቤታቸው ድረስ የሚያደርስ

📶 TIKVAH-Ethiopia። በጣም ብዙ የዜና እና የሚድያ ተቋማት ስራው ላይ ቆይተውበት እያለ ይህ የቴሌግራም ቻናል ግን አቀራረቡን በመቀየር እና በመርህ በመሄድ ስኬታማ ሆኗል።

ŠFekadu_G21

ይቀጥላል...
👍6
የበይነ - መረብ ንግድ (Online Business)

ክፍል 3 (ከትላንቱ የቀጠለና የመጨረሻ ክፍል)

3️⃣ የግል ቴሌግራም ቻናል

ቴሌግራም በተለይ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ መሪነቱን እየወሰደ ነው። ብዙ ሰዎች ለብዙ ስራ ቀዳሚ ምርጫቸው እያደረጉት ነው። ስለሆነም የግል ቴሌግራም ቻናል በመክፈት እና ተፈላጊ እና ተወዳጅ ነገሮችን በመልቀቅ ብዙ ተከታይ ማፍራት። ከዛም በቻናላችሁ ላይ ማስታወቂያ ተከፍሏችሁ በመስራት፣ የፕሪምየም (ልዩ ዝግጅቶች) በማዘጋጀት በክፍያ ማስተላለፍ፣ Podcast በማዘጋጀት እና በክፍያ ለአባላቶች ማቅረብ፣ የራሳችሁ የሆነን ፈጠራ (ስእሎች፣ የአርት ስራዎች፣ የመስታወት እና ብርጭቆ ላይ ህትመቶች...) በመሸጥ ወዘተ አይነት ዘዴዎችን በመጠቀም ገቢ ማግኘት ይቻላል።

4️⃣ App እና Website ግንባታ

እነዚህ ስራዎች በርግጥ ትምህርት እና ልምድ ይጠይቃሉ። በዚህ የሰለጠነ ሰው ከቋሚ ስራው ጎን ለጎን ለግለሰቦችም ሆነ ለተቋማት በቅናሽ ዋጋ ድረገጾችን በመገንባት ተጨማሪ ገቢ ማግኘት ይችላል።

ከዚህ በፊት ያልተሰሩ እና ለህብረተሰቡ ጠቀሜታ የሚሰጡ App Develop በማድረግም ከባድ ትርፍ (ምናልባትም ሕይወትን የሚቀይር) ማግኘት ይችላል። ለዚህ አንድ ቀላል ማሳያ

☑️ በቅርቡ የእቁብ App Develop ያደረገችው ወጣት የስራ ፈጠራ ባለቤት

☑️ Ride

☑️ Afrotie የኦንላይን ግብይት App


⏺ ማጠቃለያ

ከላይ መግቢያው ላይ እንደጠቀስኩት በእኛ ሃገር በተለያዩ ሰንሰለታማ ምክንያቶች የበይነ - መረብ ንግድ መሄድ ያለበትን ርቀት አልሄደም። ምቹ ሁኔታዎች ብዙም ስላልተፈጠሩለት። ይህም ወደ ኦንላይን ቢዝነስ ለመግባት ላሰበ ሰው አንድ ተግዳሮት ነው።

በርግጥ በውስጥ መስመር ሲመጡልን ከነበሩ "Online Business" እንዴት እንጀምር የሚሉ ጥያቄዎች አብዛኞቹ የፈለጉት እንደ ቅጥር አይነት ስራን ይመስለኛል። የጥያቄዎቹ ስሜት እንደዛ ነው። የሆነም ስራ ኦንላይን መስራት፤ ከዛ ለእሱ ክፍያ መቀበል። ትክክል ነው። ይህ አሰራር በውጩ አለም በስፋት እየተሰራበት ነው። እኛ ሃገር ግን እንደዚህ አይነት ስራዎች ባደረኩት መጠነኛ ፍለጋ አላጋጠሙኝም። በርግጥ አንዳንድ እንደ መረጃ መሰብሰብ (Surveying) አይነት ስራዎች አልፎ አልፎ ከትምህርት እና የምርምር ተቋማት አካባቢ ይታያሉ። ሆኖም እነሱም ወቅታዊ ስራዎች ስለሆነ አያዛልቁም ወይም ቋሚ የገቢ ምንጭ አይሆኑም። One Time Job ናቸው። ስለሆነም ብቸኛው እና የሚያዋጣው አማራች የራስን የኦንላይን ቢዝነስ መመስረት እና የሚያስፈልገውን ጥረት አድርጎ ገበያው ላይ ዘልቆ በመግባት ስራውን መስራት አንዱ መፍትሄ ነው ብዬ አምናለሁ።

መልካም ስራ እና እድል!

ŠFekadu_G21
👍3❤1