Muhammed Computer Technology (MCT)
37.4K subscribers
530 photos
7 videos
254 files
916 links
🔴አድራሻ:-
✅ ስ.ቁ: 0929273364
✅ ዌብሳይት www.mctplc.com
✅ቴሌግራም አካውንት: https://t.me/mctplc
✅ email: mct16plc@gmail.com
✅ ቲክቶክ አካውንት tiktok.com/@mctplc
Download Telegram
#የኔትዎርክ_የትውስትድ_ፔር_ገመድ_ኬበል_ከለር_ኮዶች!
ትውስትድ ፔር ገመድ ለኔትዎርክ ስንጠቀምበት ኮምፒውተሮችንና ዲቫይሶችን ለማገናኘት ያሉትን ገመዶች ቀለማት በመደርደር በአለም አቀፍ የተሰጠውን የአደራደር ተራ ከ1 እስከ 8 በማስቀመጥ ወደ አርጃ(RJ)45 ዲቫይስ ውስጥ እናስገባለን በመቀጠልም ለኔትዎርክ ዝርጋ ከሚያስፈልጉት ዋናው እቃ ውስጥ ክሊገፐርን በመጠቀም አርጃ(RJ)45 ዲቫይስ እንጨፈልቃለን ይህን ከማድረጋችን በፌት በአለም አቀፍ ደረጃ የተሰጣቸውን የቀለም አደረራደረር አይነት የሚጠቀሙትን መለየት ያስፈልጋል እነዚህን እንደሚከተልው እናያለን፡፡
በቲውስድ ፔር ገመድ ውስጥ ያለው አንሽድድ ቲውስትድ ፔር ገመድ በ568A ና 568B እንከፍለዋለን ይን ገመድ ያሉትን ስምንት(8) ገመዶች ውስጥ ካሉት ቀለማት ከዚህ በታች ባለው መሰረት እንደረድራቸዋለን
በ568B
1. ነጭና ኦሬንጂ (ብርቱካናማ)
2. ኦሬንጂ(ብርቱካናማ)
3. ነጭና አረንጔዴ
4. ስሚያዊ
5. ነጭና ስሚያዊ
6. አረንጔዴ
7. ነጭና ቡናማ
8. ቡናማ ናቸው
በ568A
1. ነጭና አረንጔዴ
2. አረንጔዴ
3. ነጭና ኦሬንጂ (ብርቱካናማ)
4. ስሚያዊ
5. ነጭና ስሚያዊ
6. ኦሬንጂ(ብርቱካናማ)
7. ነጭና ቡናማ
8. ቡናማ ናቸው
ቀጥታ & በማጣመር ዲቫይሶችን ማገናኘት
ኮምፒውተሮችንና ዲቫይሶችን ለማገናኘት ገመዶች ቀለማት በመደርደር በኔትዎርካችን ላይ የምንጠቀማቸውን ዲቫይሶች ስትሬት (ቀጭታ)ና ክሮስኦቨር በማለት እንለያለን
ቀጥታ የምንጠቀመው በሁለቱም(2) ጫፍ ላይ አርጃ (RJ)45 ላይ የምናስገባው ለሚከተሉት ዲቫይሶች ነው
ስዊች ከራውተር ጋር ስናገናኝ
ኮምፒውተር ከስዊች
ኮምፒውተር ከሃብ ጋር ብቻ ናቸው
ይህም ማለት በA ወይም በB አደራደረ ብቻ በሁለቱም ጫፍ በመጠቀም ነው
ክሮስ አቨር(በማጣመር)የምንለው በአንድ ጫፍ
በB በሌላኛው ሳይድ በA በመስራት ስንጠቀም ነው
ይህም አደራደር የሚጠቀሙት የሚከተሉት ዲቫይሶች
ናቸው፡፡
ስዊች ከስዊች
ስዊች ከሃብ
ሀብ ከሃብ
ራውተር ከራውተር
ኮምፒውተር ከኮምፒውተር
ኮምፒውተር ከራውተር ናቸው

ብዙ #መማር የሚፈልጉ ሰዎች ስላሉ እባክዎ #ሼር ያድርጉት...
#የተማሩትን_ማስተማር #ያወቁትን_ማሳወቅ #ብልህነት ነው
#ለሰው መልካሙን እንጅ መጥፎውን አትመኝ🙏
ስለኮምፒውተርና ቴክኖሎጅ ያለዎትን እውቀት ያሳድጉ በተጨማሪም በቴሌግራሜ ቻናል ምርጥ ምርጥ ስለኮምፒውተር የምለቃቸውን መረጃዎችን ለመከታተል እንዲያመችዎ ይህንን ይጫኑ https://t.me/MuhammedComputerTechnology በቴሌግራም መከታተል ትችላላችሁ
ሼር ማድረጋችሁን አትርሱ በፍጥነት መረጃ እንዲደርሳችሁ
Like & share this page
#ሼር_ያድርጉ
#ፔጄን_ላይክ ማድረግዎን አይርሱ
👏2
የመረጃዎቻችን መጠባበቂያ "backups" በምን መልኩ እና ምን ላይ ማስቀመጥ እንችላለን?
በኮምፒውተሮቸችን በተለያየ መልኩ ሊፈጠሩ በሚችሉ ሳይበር ጥቃቶች ፣ በኮምፐውተሩ አካል ላይ በሚደርስ ጉዳቶች እንዲሁም የኮምፒውተሩ ውስጥ የሥርዓት መዛባት አማካኝነት እጅግ አስፈላጊ ምንላቸውን መረጃዎችን ልናጣ እንችላለን፡፡ እነዚህን አደጋዎችን ለመቀነስ መጠባበቂያ መረጃ መያዝ ወሳኝ ነው፡፡ በመሆኑም እነዚህን መረጃዎች ለመያዝ የሚውሉ መገልገያዎችን እንጠቁምዎ፡፡-
- # ፍሎፒ_ዲስክ /Floppy Disk/:- ትንሽና አነስተኛ መጠን ያለው ዲስክ ሲሆን አቅሙም 1.4 MB ነው፡፡ ጠቃሚ መረጃዎችን በፍሎፒ ዲስክ ለመያዝ በርካታ ዲስኮች ያስፈልጉናል፡፡ የድሮ ኮምፒውተሮች በብዛት ፍሎፒ ዲስክ መጠቀሚያ የነበራቸው ሲሆን በአሁኑ ወቅት የሚመረቱ ኮምፒውተሮች አብዛኞቹ አገልግሎቱ የላቸውም፡፡
- # ዚፕ_ድራይቭ /Zip Drive/፡- ዚፕ ድራይቭ በመቶዎች የሚቆጠር MB መጠን ያላቸው ፋይሎችን /data/ የመያዝ አቅም አላቸው፡፡ ዚፕ ድራይቮችን ለመጠቀም የግድ በኮምፒውተራችን ላይ መሰካት /hook up/ ይኖርባቸዋል፡፡
- # ቴፕ_ድራይቭ / Tape Drive/፡- ቴፕ ድራይቭ በመቶዎች የሚቆጠር GB (በሺዎች የሚቆጠር MB) መጠን ያላቸው ፋይሎችን ይይዛል፡፡ ይህም ተጨማሪ ድራይቭ በመሆኑ የግድ በኮምፒውተራችን ላይ መሰካት ይኖርበታል፡፡
- # ሲዲ_በርነር /CD Burner/፡- ሪከርድ የሚያደርጉ ሲዲዎች /CD-Rs/ እስከ 700 MB የሚሆኑ ፋይሎች የመያዝ አቅም አላቸው፡፡ አሁን ላይ የምንጠቀምባቸው አብዛኞቹ ኮምፒውተሮች ሲዲ በርነር /CD Burner/ አላቸው፡፡ አንዳንዶቹም ዲቪዲ በርነር /DVD Burners/ አላቸው፡፡ ዲቪ ዲ አር ኤስ /DVD-Rs/ እስከ 4.7 GB ፋይል የመያዝ አቅም አላቸው፡፡ ስለዚህ በአማራጭ የመጠባበቂያ ፋይል መያዣ ሊያገለግሉ ይችላሉ፡፡
- # ፍላሽ_ድራይቭ /Flash Drive/፣ የ ኤስ ቢ ድራይቭ /USB Drive/ እና ተምብ ድራይቭ /Thumb Drive/፡- ለአንድ ነገር የተለያየ ስያሜ ቢኖርም በኮምፒውተሮቻችን የዩ ኤስ ቢ /USB/ ፋይል መቀበያ በኩል በቀላሉ የሚሰኩ ተነቃይ ድራይቨሮች ናቸው፡፡ እነዚህ ድራይቨሮች ከ10 MB የሚጀምሩ ሲሆን 1 GB፣ 2 GB፣ 4 GB፣ 8 GB፣ 16 GB፣ 32 GB፣ 64 GB … እያሉ አሁን ላይ 4TB ፋይል የመያዝ አቅም ያላቸው ፍላሽ ድራይቮች በገበያ ላይ ይገኛሉ፡፡ ፍላሽ ዲስኮች በቀላሉ በኪስ የሚያዙና ተንቀሳቃሽ ቢሆኑም በቀላሉ ወድቀው ሊጠፉ የሚችሉ በመሆኑ ጥንቃቄ ሊደረግባቸው ይገባል፡፡
- # ኤክስተርናል_ሃርድ_ዲስክ /External hard Drive/:- ኤክስተርናል ሀርድ ድርይቭ በኮምፒውተር ሲስተሞቻችን ውጪ ከፍተኛ መጠን ያላቸው ፋይሎችን የምናስቀምጥበት መሣሪያ ነው፡፡ ይህ መሣሪያ /Drive/ ፋይሎችን ይዞ ከቦታ ወደ ቦታ ለመንቀሳቀስ የሚያስችል እና ከኮምፒውተራችን ጋር በዩ ኤስ ቢ /USB/፣ በፋየርዋየር /Firewire/ ኮኔክሽን ወይም በገመድ አልባ /wirelesely/ ሊገናኝ የሚችል ነው፡፡
- # ታይም_ማሽን /Time Machine/፡- Time Mac ለተጠቃሚዎች አማራጭ የኤክስተርናል ፋይል መጠባበቂያ መያዣ መንገድ ነው፡፡ ይህ መጠባበቂያ መያዣ ዘዴ ለ24 ሰዓት በቀጥታ ፋይሎቻችንን ለማስቀመጥ ያስችላል፡፡ በመሆኑም ፋይሎች ተረስተው ለጉዳት እንዳይጋለጡ ያግዛል፡፡ ታይም ማሽን በመጠባበቂያው የሚይዘው የተመረጡ ፋይሎችን ብቻ ሳይሆን አጠቃላይ ድራይቨሩን ነው፡፡
- # ኔትወርክድ የሆነ የመረጃ ማካማቻ /Networked Attached Storage/:- ይህ ከአንድ በላይ የሆኑ ኮምፒውተሮች በኔትወርክ ተገናኝተው መረጃ የሚቀመጥበት ሥርዓት ሲሆን ይህም በስርዓት የተደረደሩ፣ ያልተደጋገሙ የፋይል ማከማቻ ኮኒቲነሮችን እና በርካታ የዲስክ ድራይቭ አካላትን የያዘ ነው፡፡ ይህም በፍጥነት መረጃ ለማግኘት፣ በቀላሉ መረጃዎችን ለማስተዳደርና ለማስተካከል የሚያስችል ዘዴ ነው፡፡
- # ስውር_የበይነ_መረብ_መረጃ ማከማቻ /Cloud Storage/:- ይህ የፋይል ማከማቻ ዓለም አቀፍ የመረጃ ማከማቻ ሥርዓት ሲሆን በኔትወርክ አማካኝነት በመገናኘት መረጃዎቻችን ክላውድ ተብሎ በሚጠራ የመረጃ መጠባበቂያ ሥርዓት /Cloud Server/ ውስጥ የምናስቀምጥበት መንገድ ነው፡፡ በርካታ የክላውድ ማማቻ ዓይነቶች በበየነ-መረብ ውስጥ የሚገኙ ሲሆን እነዚህም በነጻ ወይም በክፍያ አገልግሎት የሚሰጡ ናቸው፡፡ iCloud፣ Dropbox፣ Google Drive እና OneDrive የታወቁ የመረጃ ማከማቻ መንገዶች ናቸው፡፡ መረጃዎቹ የሚከማቹበት ሥፋራ በመራጃ በለቤቶቹ ቁጥጥር ሥር ባለመሆኑ የመረጃዎቹ ደህንነት አስተማማኝ እንደስጋት ይታያል፡፡
- # ፕሪንት_ማድረግ /Printing/:- ምንም አንኳን መረጃዎቻችን በሶፍት ኮፒ የምናስቀምጠውን የህል የተማቹ ባይሆኑ ኮምፒውተሮቻችን በተለያየ ምክንያት ለቀናት አገልግሎት መስጠት የሚያቆሙበት አጋጣሚ ቢፈጠር ፕሪንት ያደረግናቸው ፋይሎች እጅጉን ይጠቅሙናል፡፡
ብዙ #መማር የሚፈልጉ ሰዎች ስላሉ እባክዎ #ሼር ያድርጉት...
#የተማሩትን_ማስተማር #ያወቁትን_ማሳወቅ #ብልህነት ነው
#ለሰው መልካሙን እንጅ መጥፎውን አትመኝ🙏
ስለኮምፒውተርና ቴክኖሎጅ ያለዎትን እውቀት ያሳድጉ በተጨማሪም በቴሌግራሜ ቻናል ምርጥ ምርጥ ስለኮምፒውተር የምለቃቸውን መረጃዎችን ለመከታተል እንዲያመችዎ ይህንን ይጫኑ https://t.me/MuhammedComputerTechnology በቴሌግራም መከታተል ትችላላችሁ
ሼር ማድረጋችሁን አትርሱ በፍጥነት መረጃ እንዲደርሳችሁ
Like & share this page
#ሼር_ያድርጉ
#ፔጄን_ላይክ ማድረግዎን አይርሱ
👍2
Muhammed Computer Technology (MCT) pinned «የመረጃዎቻችን መጠባበቂያ "backups" በምን መልኩ እና ምን ላይ ማስቀመጥ እንችላለን? በኮምፒውተሮቸችን በተለያየ መልኩ ሊፈጠሩ በሚችሉ ሳይበር ጥቃቶች ፣ በኮምፐውተሩ አካል ላይ በሚደርስ ጉዳቶች እንዲሁም የኮምፒውተሩ ውስጥ የሥርዓት መዛባት አማካኝነት እጅግ አስፈላጊ ምንላቸውን መረጃዎችን ልናጣ እንችላለን፡፡ እነዚህን አደጋዎችን ለመቀነስ መጠባበቂያ መረጃ መያዝ ወሳኝ ነው፡፡ በመሆኑም እነዚህን መረጃዎች…»
#ላፕቶፕ_ስንገዛ_ማወቅ_እና_ማየት_ያለብን_ወሳኝ_ነጥቦች
1 የመሳሪያ ስርዓት (Operating system)
2 የስክሪን መጠን (Screen Size)
3 ሲፒዩ(CPU)
4 ራም(RAM)
5 የሃርድ ድራይቭ አይነት (Hard Drive Type)
6 የምስል ጥራት (Image Quality)
7 የባትሪ ቆይታ (Battery Life)
8 ብራንድ (Brand)
ኮርi3 ኮርi5 ኮርi7 ምንድናቸው?
በሃገራችን ገበያ አሁን አሁን በርከት ያሉ የላፕቶፕ እና
የኮምፒውተር ሱቆች እየታዩ ይገኛሉ፡፡ለገቢያም የተለያዩ
የላፕቶፕ አይነቶች.በተለያየ ይዘት ይገኛሉ፡፡ እንዚህን
የተለያየ
ይዘት ያላቸውን የላፕቶፕ አይነቶች ለመግዛት በዋናነት
መታየት
ያለበትን ከዚህ በታች በዝርዝር ተቀምጠዋል፡፡
1. የመሳሪያ ስርዓት (platform) Windows, Mac and
Linux
ለአጠቃቀም ምቹ እንደሆነ የሚነገርለት Windows የብዙ
ሰዎች
ምርጫ ነው፡፡ቀላል፣ ምቹ እና ተለዋዋጭ ነው፤ በዋጋም
ደረጃ
ጥሩ የሚባል ነው፡፡
ማክ( Mac) የአፕል ድርጅት ምርት ሲሆን ለዲዛይን
ተመራጭ
የሆነ
ፕላትፎረም ነው፡፡ለደህንነትም ከWindows እንደሚሻል
ይነገርለታል፡፡
2. የስክሪን መጠን
ወደ ግዢ ከመግባታችን በፊት የምንገዛው ላፕቶፕ ከቦታ
ወደ
ቦታ ይዘን ለመንቀሳቀስ (portable) ምቹ መሆኑን
ማረጋገጥ
ያስፈልጋል፡፡ ላፕቶፖች እንደየስክሪን መጠናቸው የተከፋፈሉ
ናቸው፡፡
• 11 to 12 inches(27.94cm-30.48cm) ፡በጣም
ቀጭን
እና ቀላሉ የስክሪን ሳይዝ ነው፡፡ ከ1.1ኪሎ እስከ1.5ኪሎ
ይመዝናል፡፡
• 13 to 14 inches (33.02cm- 35.56cm) ፡ይህ
የስክርን
ሳይዝ ያለቸው ላፕቶፖች በጣም ተመጣጣኝ portability
ያላቸው እና በላፕቶፕ ተጠቃሚዎች ተመራጭ ናቸው፡፡
• 15 inches(38.1cm): እውቁ የላፕቶፕ የስክሪን ሳይዝ
ሲሆን፤ተለቅ ያለ የስክሪን ሳይዝ ከፈለጉ ይህንን እንዲገዙ
እንመክራለን ፡፡
• 17 to 18 inches (43.18cm- 45.72cm)፡
ላፕቶፖን
ይዘው የማይንቀሳቀሱ ከሆነ እና ትልቅ የስክሪን ሳይዝ
ከፈለጉ
ይህንን ይግዙ፡፡ ለጌመሮች እና ትልልቅ የሶፈተዌር ዲዛይን
ለሚያደርጉ ሰዎች ተመራጭ የሆነ የላፕቶፕ አይነት ነው፡፡
3. ሲፒዩ(CPU)
የኮምፒዉተር አይምሮ በመባል የሚታወቀው ሲፒዩ(CPU),
ላፕቶፕ ለመግዛት ሁላችንም ማየት ያለብን ዝርዝር ነው፡፡
• AMD A series or Intel Core i3 / i5: በየቀኑ
ለምንጠቀማቸው ስራዎች የሚሆኑ የሲፒዩ አይነቶች ሲሆኑ
Core
i5 ለሶፈትዌር ዴቨሎፕመንት እና አነስተኛ የዲዛይን
ስራዎችን
ለምሳሌ እንደ Photoshop, Archicad, AutoCadን
የመሳሰሉ በጥሩ ሁኔታ እንድንሰራ ይጠቅሙናል፡፡
በተጨማሪም
ግራፊክስ ካርድ ያለውና የሌለው በማለትም ይለያያሉ፡፡
ግራፊክስ
ካርድ ያለቸው የተሻለ የዲዛይን እና አኒሜሽን ስራዎችን
ያከናውኑልናል፡፡ በዋጋውም ተመጣጣኝ ነው፡፡
• Intel Core i7፡ በጣም አስደማሚ የጌም እና የዲዛይን
እንዲሁም ልዩ የሆኑ የኮምፒውተር ስራችን ለምሳሌ አንደ
ሜትሮሎጂ፤ውስብስብ ስሌቶችን እንድንሰራ የሚረዳን
የላፐቶፕ
አይነት ነው፡፡
4 .ራም(RAM): ለፍጥነት 4ጂቢ እና ከዛ በላይ የሆነ
RAM
እንዲጠቀሙ እንመክሮታለን፡፡ ዋጋቸው አነስ ያሉ ላፕቶፖች
በ2ጂቢ ይመጣሉ፡፡ የዲዛይን ስራዎችን እና የሶፈትዌር
ዴቨሎፕመንት ስራዎችን ለመስራት 6ጂቢ ራም እና ከዚያ
በላይ
ያለው ላፕቶፕ ቢገዙ ይመረጣል፡፡
5.የሃርድ ድራይቭ አይነት፡ ሁለት አይነት የሃርድ ድራይቭ
አይነቶች ያሉ( HDDrive እና SSDrive) ሲሆን በሃገራችን
ያልተለመደው SSDrive ከHDDrive የተሻለ የፍጥነት
አቅም
እና ድራይቩ ላይ ያለውን ዳታ በፍጥነት መድረስ እና
መገልበጥ
(copy)ያስችለናል፡፡
6 .የምስል ጥራት፡ የተሻለ ጥራት የተሻለ ምስል እንድናገኝ
ይረዳናል፡፡ 1366 x 768 ጥሩ የሚባል የምስል ጥራት
ያለው
ሲሆን ከዚህ የተሻለ ወጪ በማውጣት 1920 x 1080
የተሻለ
ምስል ማግኘት እንችላለን፡፡Full HD 1080P በመባልም
ይታወቃል፡፡
7 .የባትሪ ቆይታ፡ አብዛኛው ሃገር ውስጥ የሚገቡት
የላፕቶፕ
አይነቶች 4 ሰዓታት የሚቆዩ ሲሆን ከ6-8 ሰዓታትም የሚቆዩ
ኦርጅናል ላፕቶፖች አሉ፡፡
8 . ብራንድ፡ የተላያዩ የላፕቶፕ ብራንዶጭ ባሉበት ገቢያ
የተኛውን መግዛት እንዳለብን አስቀድመን ማወቅ አለብን
ብዙ #መማር የሚፈልጉ ሰዎች ስላሉ እባክዎ #ሼር ያድርጉት...
#የተማሩትን_ማስተማር #ያወቁትን_ማሳወቅ #ብልህነት ነው
#ለሰው መልካሙን እንጅ መጥፎውን አትመኝ🙏
ስለኮምፒውተርና ቴክኖሎጅ ያለዎትን እውቀት ያሳድጉ በተጨማሪም በቴሌግራሜ ቻናል ምርጥ ምርጥ ስለኮምፒውተር የምለቃቸውን መረጃዎችን ለመከታተል እንዲያመችዎ ይህንን ይጫኑ https://t.me/MuhammedComputerTechnology በቴሌግራም መከታተል ትችላላችሁ
ሼር ማድረጋችሁን አትርሱ በፍጥነት መረጃ እንዲደርሳችሁ
Like & share this page
#ሼር_ያድርጉ
#ፔጄን_ላይክ ማድረግዎን አይርሱ
ስልክ network አልሰራ የሚልበት ሁለት አይነት ምከንያቶች ብቻ ናቸዉ ።
1. hardware problem
2. Software problem
የ hardware ችግር መሆኑን ማወቂያ ምልክቶች
no sim-card(sim እያለዉ)
insert sim-card(sim እያለዉ)
no service (sim እያለዉ)
ስልኮ ከላይ የተዘረዘሩትን የሚል ከሆነ የhardware ችግር ስለሆነ ለ ጠጋኝ ማሳየት ግዴታ ነዉ።
የ software ችግር መሆኑን ማወቂያ ምልክቶች
Emergency
network locked
unknown sim
invalid sim
invalid imei
incomplete imei
ስልኮ ከላይ የተዘረዘሩትን የሚል ከሆነ የsoftware ችግር ስለሆነ imei repair በማድረግ ይስተካከላል።
ብዙ #መማር የሚፈልጉ ሰዎች ስላሉ እባክዎ #ሼር ያድርጉት...
#የተማሩትን_ማስተማር #ያወቁትን_ማሳወቅ #ብልህነት ነው
#ለሰው መልካሙን እንጅ መጥፎውን አትመኝ🙏
ስለኮምፒውተርና ቴክኖሎጅ ያለዎትን እውቀት ያሳድጉ በተጨማሪም በቴሌግራሜ ቻናል ምርጥ ምርጥ ስለኮምፒውተር የምለቃቸውን መረጃዎችን ለመከታተል እንዲያመችዎ ይህንን ይጫኑ https://t.me/MuhammedComputerTechnology በቴሌግራም መከታተል ትችላላችሁ
ሼር ማድረጋችሁን አትርሱ በፍጥነት መረጃ እንዲደርሳችሁ
Like & share this page
#ሼር_ያድርጉ
#ፔጄን_ላይክ ማድረግዎን አይርሱ
Muhammed Computer Technology (MCT) pinned «ስልክ network አልሰራ የሚልበት ሁለት አይነት ምከንያቶች ብቻ ናቸዉ ። 1. hardware problem 2. Software problem የ hardware ችግር መሆኑን ማወቂያ ምልክቶች no sim-card(sim እያለዉ) insert sim-card(sim እያለዉ) no service (sim እያለዉ) ስልኮ ከላይ የተዘረዘሩትን የሚል ከሆነ የhardware ችግር ስለሆነ ለ ጠጋኝ ማሳየት ግዴታ ነዉ። የ software…»
የሞባይል ኢንተርኔትን በላፕቶፕ ላይ ለመጠቀም
(በኬብልና ያለኬብል ለማገናኘት)
ክቡራን የፔጃችን ታዳሚዎች… እንዴት አርገን ሞባይላችንን
ከኮምፒውተር ጋር በማገናኘትና የሞባይላችንን የኢንተርኔት ዳታ
ለኮምፒውተራችን መጠቀም እንደምንችል እንደሚከተለው
አቅርበንላችኋል፡፡
❶. የሚከተሉትን steps ማዛነፍ አይፈቀድም
➢step ①
የሞባይሎን ኢንተርኔት ዳታ ያብሩ
➢step ②
ሞባይሎን ከኮምፒተሮ ጋር በUSB cable ያገናኙ
➢step ③
የሞባይሎን setting ይክፈቱ
➢step ④
more በሚለው ይግቡና ከሚመጣሎ አማራጭ tethering and
portable hotspotን ይክፈቱና USB tethering የሚለውን on
ያድርጉ
➢step ⑤
ወደ ኮምፒውተሮ በመመለስ የፈለጉትን browser (chrome,
Firefox or opera) በመጠቀም በኮምፒተሮ ኢንተርኔት ማግኘት
ይችላሉ
-------
❷. other method
Internet sharing የሚል ሴቲንግ ያላቸው ሞባይሎች ያለ ኬብል
መጠቀም ይችላሉ፡፡
•► መጀመሪያ ዳታ ማብራት
•►ከዚያ ኢንተርኔት ሼሪንግ የሚለውን ኦን ማድረግ፤ ከዚያ ሄደው
ላፕሮፕ ላይ ልክ እንደ ዋይ ፋይ የሞባይሎን ዳታ ያገኙታል፡፡
•► ኢንተርኔት ሼሪንግ የሚለው ሴቲንግ ውስጥ የተቀመጠውን
የፓስዋርድ ቁጥር ላፕቶፑ ላይ ማስገባት
•► ከዚያ መጠቀም መጀመር
ነገር ግን በሞባይል ከምታገኙት ኢንተርኔት ይህ ዋጋው ከፍ
ይላል፡፡ የሞባይሎን ካርድ ቶሎ ነው የሚበላው፡፡
⌘ሌላው ማወቅ ያለብዎ ሞባይሎን ነቅለው መልሰው
ከኮምፒውተሮ ጋር ሲያገናኙ ከላይ የተጠቀሱትን steps እንደአዲስ
መከተል ግድ ይላል በርግጥ ይህንን አጠቃቀም ምታውቁ
እንደምትኖሩ አንጠራጠርም፡፡
ብዙ #መማር የሚፈልጉ ሰዎች ስላሉ እባክዎ #ሼር ያድርጉት...
#የተማሩትን_ማስተማር #ያወቁትን_ማሳወቅ #ብልህነት ነው
#ለሰው መልካሙን እንጅ መጥፎውን አትመኝ🙏
ስለኮምፒውተርና ቴክኖሎጅ ያለዎትን እውቀት ያሳድጉ በተጨማሪም በቴሌግራሜ ቻናል ምርጥ ምርጥ ስለኮምፒውተር የምለቃቸውን መረጃዎችን ለመከታተል እንዲያመችዎ ይህንን ይጫኑ https://t.me/MuhammedComputerTechnology በቴሌግራም መከታተል ትችላላችሁ
ሼር ማድረጋችሁን አትርሱ በፍጥነት መረጃ እንዲደርሳችሁ
Like & share this page
#ሼር_ያድርጉ
#ፔጄን_ላይክ ማድረግዎን አይርሱ
Muhammed Computer Technology (MCT) pinned «የሞባይል ኢንተርኔትን በላፕቶፕ ላይ ለመጠቀም (በኬብልና ያለኬብል ለማገናኘት) ክቡራን የፔጃችን ታዳሚዎች… እንዴት አርገን ሞባይላችንን ከኮምፒውተር ጋር በማገናኘትና የሞባይላችንን የኢንተርኔት ዳታ ለኮምፒውተራችን መጠቀም እንደምንችል እንደሚከተለው አቅርበንላችኋል፡፡ ❶. የሚከተሉትን steps ማዛነፍ አይፈቀድም ➢step ① የሞባይሎን ኢንተርኔት ዳታ ያብሩ ➢step ② ሞባይሎን ከኮምፒተሮ ጋር በUSB…»
እራስን የኮምፒውተር ፕሮግራሚግ ወይም ኮዲንግ ችሎታን ማስተማሪያ 8 ጠቃሚ ነጥቦች
እራስን የኮምፒውተር ፕሮግራሚግ ወይም ኮዲንግ ችሎታን ማስተማሪያ 8 ጠቃሚ ነጥቦች
ፕሮግራሚግ በአሁኑ ወቅት በአለማችን ላይ እጅግ በጣም ጠቃሚ እና አዋጪ የሞያ ዘርፍ ነው። እንዲሁም በአለም ላይ እጅግ በጣም ትልቁን ክፍያ ውይም ደሞዝ ከሚከፈልባቸው ዋና ዋና የኮምፒውተር ቴክኖሎጂ የስራ ዘርፎች ግንባር ቀደሙ ነው። ታዲያ የዚህን ሞያ ችሎታ ለመማር እና ችሎታቹን ለማሳደግ የመጀመርያ ጉዟቹን የጅመራቹ ከሆነ እነኚን እጅግ በጣም ጠቃሚ እና በትክክለኛው መንገድ ላይ እንድትጓዙ የሚረዳቹ 8 ነጥቦች ይመልከቱ።
እነኚህ ነጥቦች በዚህ ሞያ ላይ ስኬታማ የሆኑ ግለስቦች ሁሉም በጋራ የሚስማሙበት ነጥቦች ናቸው፤ ታዲያ ይህን ስላቹ ይህ ብቸኛው እካሄድ ነው ለማለት አይደለም ስኬታማ ፕሮግራመር ለመሆን። ነገር ግን በጉዞዋቹ ላይ ሊያጋጥም ከሚችሉ የግራ መጋባት ሁኔታ ወይም ሌሎች የሚያጋጥሙ የአካሄድ ችግሮች አንዳይፈጠርባቹህ ይረዳችኋል ማሌቴ ነው።
ነጥብ 1 መጀመሪያ የኮምፒውተር ፕሮግራሚግ ወይም ኮዲግ መማር ለምን እንዳስፈለጋቹ ለይታቹ እወቁት።
ለምሳሌ፦አላማቹ ለገቢ ምንጭ ተሆነ የኮምፒውተር ፕሮግራሞች የገበያ ሁኔታ ማወቅ አስፈላጊ ነው። ምክንያቱም ገበያው የሚፈልገውን ፕሮግራም ለመለየት እና ትኩረት ሰቶ ለማጥናት። ሌላው ምክንያት ያሚሆነው ደግሞ የእውቀት ደረጃቸውን ለማስፋት ወይም በትምህርት ውስጥ ሆነው የኮምፒውተር ፕሮግራም እና ተመሳሳይ የትምህርት አይነቶችን በተሳካ ሁኔታ ፈተናዎችን ለመስራት።
ነገሩ ይህም ሆነ ያ ዋናው እና በጣም ይህን ከማድረጋቹ በፊት ማወቅ የለባቹ ሁለት ነገሮች አሉ።
አንደኛው ነገር የኮምፒውተር ፕሮግራሚግ ለማወቅ ፍላጎት ሊኖራቹሁ አስፈላጊ ነው። ዝም በላቹ በዚህ ሞያ የሚገኘውን ገቢ ብቻ ለማግኝኘት አስባቹህ ከሆነ ትልቅ ስህተት እየሰራችሁ ነው። ይህ ሞያ የለፍላጎት የሚሰራ ከሆነ ብዙም መጓዝ የማይቻል ነው ምክንያቱም ብዝዎቹ በዚህ ሞያ የሚሰሩ ስራዎች በራስ ተነሻሽነት የሚሰሩ ናቸው።
ሁለትኛው ነገር ደግሞ ሰለ ኮምፒውተሮች በቂ ግንዛቤ ሊኖሮት ይገባል። ለምሳሌ፦የኮምፒውተሮች ዋና ዋና ክፍሎችን፤ እያንዳንዱ ክፍሎች አገልግሎታቸው፤ ክፍሎቹም በምን አይነት መልኩ ስራቸውን እንደሚሰሩ ወይም ምን አይነት ትእዛዞችን በመከተል የተፈለገውን ስራ እንደሚሰሩ የመሳሰሉትን እና ሌሎችንም ዋና ዋና ስለ ኮምፒውተሮች ማውቅ። ይህ ርእስ በደንብ የሚያስተምር መጸሀፍ ለማንበብ ከፈለጋቹ introduction to computer science የሚል መጸሀፍ ፈልጋቹ ማንበብ ትችላላችሁ። በተጨማሪ መሰረታዊ የኮምፒውተር አጠቃቀም ማወቅ ያስፈልጋችኋል።
ነጥብ 2 ትክክለኛውን መማር የምትፈልጉትን የፕሮግራሚግ ቋንቋ አይነት ይምረጡ እና ይወስኑ።
ሁለተኛው ደረጃ የሚሆነው የዚህን ችሎታ የፈለጋችሁበት ምክንያት መሰረት በማድረግ የፕሮግራሚንግ ቋንቋዎችን ለይቶ ማወቅ እና የትኛው የፕሮግራሚግ ቋንቋ ማጥናት እንዳለባቹ ወይም ከየትኛው ቋንቋ ጥናታቹን መጀመር እንዳለባቹ ማወቅ ያስፈልጋችዋል። ይህን ስላቹ በቴክኖሎጂ አለም ውስጥ ለብዙ አላማ እና ለተለያዩ የኮምፒውተር አይነቶች ወይም ደረጃዋች የሚጠቅሙ እጅግ በጣም ብዙ የፕሮግራሚንግ ቋንቋዎች ተፈጥረዋል እንዲሁም ይገኛሉ። ስለዚህ በጣም ጥንቃቄ በተሞላበት ሁኔታ የትኛው ቋንቋ ለየትኛው አገልግሎት እንደሚውል ለዩ፤ ይህን ግዜ ግራ የሚያጋባ እና እራሳቹ የመሰላቹን ከማድረግ ይቆጠቡ፤ በIT ወይም በCOMUPTER SCINECE ዘርፍ የተማሩ በቅርብ የሉ ሰዎችን ይጠይቋቸው፤ ይህን ለማድረግ የማችሉ ከሆነ በኢንተርኔት ይህን ጥያቄ መልስ የሚሰጡ ድረ ገጽ በመመልከት ወይም ስለ ፕሮግራሚንግ ቋንቋ አይነቶች እና ልይነታቸውን የሚያብራራ መጸሀፎችን እና ድረ ገጾችን መመልከት ትችላላቹሁ በቂ ግንዛቤ ለማግኘትም ይሞክሩ። ለግንዛቤ ያህል የሚከተለውን ያንብቡት፦
የተለያዩ ቋንቋዎች የተለያየ አገልግሎት አላቸው። ስለዚህ በአይነት ከፋፍለን ማየት እንችላለን ማለት ነው። የተወሰኑት እነዚህ ናቸው፦
Machine languages — interpreted directly in hardware
Assembly languages — thin wrappers over a corresponding machine language
High-level languages — anything machine-independent
System languages — designed for writing low-level tasks, like memory and process management
Scripting languages — generally extremely high-level and powerful
Visual languages — non-text based
ነጥብ 3 ከቲኒሹ ወይም ቀለል ከሚለው የፕሮግራሚንግ ቋንቋ ይጀምሩ (እና ማጥናት ወይም ማንበብ ከጀመራቹ በኋላ በትእግስት ሳታቋርጡ ለመጨረስ ጥረት አድርጉ )።
እንደ C C++ Python ወይም Ruby ከመሳሰሉት ቀለል ከሚሉት ቋንቋዋች መጀመር የተሻለ ነው።
ነጥብ 4 የመረጣቹሁት የፕሮግራሚግ ቋንቋ መማሪያ መጸሀፍት እና በተግባር የምትለማመዱበት መሳሪያዎችን የዘጋጁ።
ከተለያዩ ድረ ገጾች ላይ የምትፈልጉትን የመማሪያ መሳሪያዎች በነጻ በብዛት ማግኘት ትችላላቹሁ።ከዚህ ድረ ገጽ ብዙ አይነት መጸሀፍትን ያገኛሉ፦
GitHub.com
ነጥብ 5 የጥናት ወቅታቹሁን በሚመች መልኩ በፕሮግራም በስርአቱ የውጡ እና በጽሁፍ የዘጋጁት። የጥናታቹህ ፕሮግራም ቋሚ መሆን አለበት።
ነጥብ 6 በጥናታችሁ ጉዞ ላይ በእያንዳንዱ ከፍሎች ወይም ምእራፎች ላይ የሚገኙትን ጥያቄዎችን እና ልምምዶችን በተገቢው መልኩ ለመስራት ይሞክሩ።
ለመስራት ያዳገታቹሁን ጥያቄ እንዳታልፉት ተስፋ ሳትቆርጡ ለመስራት ጥረት ያድርጉ የበለጠ እና የተሻለ ግንዛቤ ያገኛሉ።
ነጥብ 7 ሌሎች ይህንን የፕሮግራሚንግ ቋንቋ መማር ፍላጎት ላላችው ግለሰቦች እስከ ተማራቹሁት ድረስ ለማስተማር ይሞክሩ። የተማራቹሁትን ለማስታውስ እና ዘላቂ እውቀት እንድታገኙ የግዛቹሀል።
ነጥብ 8 ሌሎች የሰሩትን ትናኒሽ ፕሮግራም ኮዶችን በመፈለግ የፕሮግራሙን እያንዳንዱን ክፍል በመመራመር እንዴት እንደሚሰራ ለመረዳት ይሞክሩ። ኮዱንም በራሳቹ ለማሻሻል ወይም በመቀያየር ይለማመዱ፡፡
ብዙ #መማር የሚፈልጉ ሰዎች ስላሉ እባክዎ #ሼር ያድርጉት...
#የተማሩትን_ማስተማር #ያወቁትን_ማሳወቅ #ብልህነት ነው
#ለሰው መልካሙን እንጅ መጥፎውን አትመኝ
ስለኮምፒውተርና ቴክኖሎጅ ያለዎትን እውቀት ያሳድጉ በተጨማሪም በቴሌግራሜ ቻናል ምርጥ ምርጥ ስለኮምፒውተር የምለቃቸውን መረጃዎችን ለመከታተል እንዲያመችዎ ይህንን ይጫኑ https://t.me/
MuhammedComputerTechnology በቴሌግራም መከታተል ትችላላችሁ
ሼር ማድረጋችሁን አትርሱ በፍጥነት መረጃ እንዲደርሳችሁ
Like & share this page
#ሼር_ያድርጉ
#ፔጄን_ላይክ ማድረግዎን አይርሱ
❤1
Muhammed Computer Technology (MCT) pinned «እራስን የኮምፒውተር ፕሮግራሚግ ወይም ኮዲንግ ችሎታን ማስተማሪያ 8 ጠቃሚ ነጥቦች እራስን የኮምፒውተር ፕሮግራሚግ ወይም ኮዲንግ ችሎታን ማስተማሪያ 8 ጠቃሚ ነጥቦች ፕሮግራሚግ በአሁኑ ወቅት በአለማችን ላይ እጅግ በጣም ጠቃሚ እና አዋጪ የሞያ ዘርፍ ነው። እንዲሁም በአለም ላይ እጅግ በጣም ትልቁን ክፍያ ውይም ደሞዝ ከሚከፈልባቸው ዋና ዋና የኮምፒውተር ቴክኖሎጂ የስራ ዘርፎች ግንባር ቀደሙ ነው። ታዲያ የዚህን…»
የስኬታማ አመራሮች አምስት የዉጤት ሚስጥራዊ ባህሪያት
===============================
ለአንድ ተቋም የላቀ ውጤታማነት ትልቁን ሚና የሚይዘው አመራሩ ነው፡፡
የአመራሩ ጥንካሬ ወይም ድክመት አንድን ትንሽ ተቋም አይደለም አገርን
ያህል ነገር ደካማ ወይም ጠንካራ ሊያደርግ ይችላል፡፡ በተለያዩ ተቋማት
ውስጥ ያሉ አመራሮች የሚመሩት ድርጅት አትራፊም ይሁን ትርፋማ
ያልሆነ እስከ 40 በመቶ ድረስ ውጤታማነቱን የመወሰን አቅም አላቸው፡፡
አመራሩ የበታች ሰራተኞችን ይቀጥራል፣ ያሰራል፡፡ ድርጅቱ ውጤታማ
ባይሆን ተጠያቂው የሚሆነው ስራውን በበላይነት የሚያሰራው ወይም
ደግሞ ስራውን የሚሰሩ ሰዎችን የቀጠረው ነው ሊሆን የሚችለው፡፡
ለዚያም ነው አንድ ድርጅት ሲመሰረት አመራሩ ማነው ተብሎ በቅድሚያ
መለየት ያለበት፡፡
የምንመራው ተቋም የፖለቲካ ፓርቲ ሊሆን ይችላል፣ የእግር ኳስ ክለብ
ሊሆን ይችላል፣ መንግሥታዊ ያልሆነ ድርጅትም እንዲሁ፡፡ በተመሳሳይ
መልኩ አትራፊ የንግድ ድርጅትም ሊሆን ይችላል፡፡ ሁሉም እንደ ተቋም
ግን የተቋቋመበትና ሊያሳኩት የሚፈልጉት ራዕይና ግብ አላቸው፡፡ ተቋምን
ተቋም ከሚያሰኙት አንዱ መለያ ባህሪያቸው ሰርቶ ሊያሳካቸው
የሚፈልጋቸው ግልፅ አላማዎች መኖራቸው ነው፡፡ እነዚህን ዳር
ለማድረስ ነው እንግዲህ የአመራሩ ሚና፡፡
በዓለም አቀፍ ደረጃ የምርጥ አመራር ባህሪያት ምንድን ናቸው?
አንድ አመራር ብቃት የ‹‹BASKET›› ፅንሰ ሃሳብን ያሟላ መሆን
አለበት፡፡ ሁሉም ሰው መሪ መሆን ቢፈልግም መሪ መሆን የሚችሉት ግን
ጥቂቶች ብቻ ናቸው፡፡ መሪ መሆን ችለውም የላቀ ውጤት ማስመዝገብ
የሚችሉት አሁንም ጥቂቶች ናቸው፡፡ የእጅግ ውጤታማ ሰዎች
አመራሮች አንድ መገለጫዎች ‹‹BASKET›› የተባለውን መስፈርት
የሚያሟሉ መሆናቸው ነው፡፡ ‹‹ባስኬት›› ሲባል ቅርጫት ለማለት ተፈልጎ
አይደለም፡፡ ምህፃረ ቃል ነው፡፡
#1. B- Behavior…ባህሪ!
“Leadership is a potent combination of strategy and
behavior. But if you must be without one, be without
strategy”… Norman Skhwarzkopf
እንደሚታወቀው አንድ አመራር ስለሚጠበቅበት የስራ ኃላፊነት ሊወጣው
የሚያስችለው ባህሪ ሊኖረው ይገባል፡፡ አንዳንዱ መሪ እንኳን ለመምራት
ለመመራት የማይሆን ባህሪ ያለው አለ፡፡ እንኳን ሌሎችን ሊመራ ራሱ
መሪ የሚያስፈልገው ሰውም አለ፡፡ የመሪነት ባህሪ ራሱን የቻለ ልዩ ገጽታ
ነው፡፡ ለዚያም ነው ሁሉም ሰው መሪ መሆን የማይችለው፡፡ ለዚያ
ኃላፊነት ዝግጁ የሆነ ባህሪ ሊኖረው ይገባል፡፡ አንድ ሰው በአገራችን
ካለው የሊደርሽፕ ተቋምም ሆነ ሐርቫርድ ዩኒቨርሲቲ ገብቶ ቢማር
የመሪነት ባህሪ ካልታደለው ወይም ደግሞ በውስጡ ካላዳበረው
ውጤታማ መሪ ሊሆን አይችልም፡፡
መኪና ከፈለግንበት ቦታ ሊያደርሰን የሚችለው ጎማ ሲገጠምለት ነው፡፡
አንድ መሪም እንዲሁ የሚመራውን ተቋም ከዳር ማድረስ የሚችለው
ለአመራርነት የሚያበቃ ባህሪ ሲገጠምለት ነው፡፡ ከየትኛውም ተቋም
ውጤት በስተጀርባ የአመራሮችን ባህሪ እናገኛለን፡፡ ጥሩ ውጤት ያላቸው
ከሆነ ጥሩ የአመራር ባህሪ አላቸው ማለት ሲሆን ውጡቱ ደግሞ
ከተጠበቀው በታች ከሆነም ባህሪያቸው የዚያኑ ያህል ሆኗል ማለት
ይቻላል፡፡
አንድ የእግርኳስ አሰልጣኝ ለአሰልጣኝነት የሚሆን ባህሪ ከሌለው ቡድኑ
ውጤት ሊያመጣ አይችልም፡፡ አንድ የፖለቲካ ተቋም /ፓርቲ/ መሪ
ፖለቲካዊ መድረክን ወደ ውጤት ለመቀየር የሚያስችል አፈፃፀም
ከሌለው በተመሳሳይ መልኩ ፓርቲው እንኳን ምርጫ ተወዳድሮ ሊያሸንፍ
አይደለም የራሱን ህልውና ለማስጠበቅ እንኳን ሊሳነው ይችላል፡፡ አንድ
የንግድ ተቋም አመራር ለንግድ አመራርነት የሚያበቃ ባህሪ ከሌለው
ድርጅቱ አትራፊ ሆኖ ሊዘልቅ አይችልም፡፡ ይህ የሚያሳየን የአመራር
ባህሪ እንደየተቋሙ ባህሪ የሚለያይ መሆኑ ነው፡፡
ለዚያም ነው ታክሲ ሲነዳ የነበረ ሹፌር አውቶብሱን መንዳት የሚሳነው፡፡
አውቶብሱን ለመንዳት የሚያስችል ባህሪ ከዳበረ ግን በጥሩ ሁኔታ
መንዳት ይችላል፡፡ አንድ ቦ ለውጤት ያበቃ ባህሪ ለሌላም ሊያበቃ
የሚችል ሲሆን አንድ ቦታ ላይ ተፈትሾ ያልሰራ ባህሪ ደግሞ በሌላ ቦታ
ላይም ሊራ አይችልም፡፡ ሆኖም ለብዙ ተቋማት ውድቀት ትልቁ ምክንያት
ያ ተቋም የሚፈልገውን ልዩ የአመራር ባህሪ ካለመኖር ወይም ደግሞ
ካለማዳበር የሚመነጭ ነው የሚሆነው፡፡ ለዚያም ነው አንዳንዴ
በአመራር ብቃታቸው ሌላ ቦታ ውጤታማ ሆነው በሌላ ድርጅት ላይ
ሲቀጠሩ ድርጅቱን ሊጥሉት የሚችሉት፡፡ ይህም ማለት ባህሪ በየጊዜው
የሚዳብር፣ እንደምንመራው ተቋም ባህሪም በአዲስ መልክ የሚሻሻልና
ውጤትን የሚወስን አንዱ የመሪዎች ወሳኝ ገፅታ መሆኑን ነው፡፡
#2. A Attitude… አመለካከት
“If your actions inspire others to dream more, learn
more, do more and become more, you are a leader”
John Quincy Adams
ይህ የመሪዎች ሌላኛው ውጤት ቀያሪ መገለጫቸው ነው፡፡ የመሪዎች
ገንቢ አመለካት ለገንቢ ውጤት የሚያበቃ ኃይል አለው፡፡ አንድ መሪ
የድርጅቱን ራዕይ የራሱ ራዕይ አድርጎ ከመነሳት ይጀምራል፡፡ አንዳንድ
አመራሮች በአንድ ተቋም ላይ ለመሪነት ሲመረጡ ወይም ደግሞ ሲሾሙ
የድርጅቱን ራዕይ ላያውቁት ወይም ደግሞ ላያምኑበት ከቻሉ ግለሰቡና
ተቋሙ አልተዋወቁምና ከዚህ መሰል አመራር ውጤት መጠበቅ ማለት
ከጠራ ሰማይ ላይ ዝናም ይጥላል ብሎ ጥላ እንደመያዝ ነው
የሚቆጠረው፡፡ እንዲሁም የትኛውም የንግድ ተቋም ስራውን
የሚገዳደሩት ተወዳዳሪ ተቋማት አሉ፡፡ የንግድ ድርጅትን ብንወስድ
ከእነሱ ካልተሻለ ሊጥሉት የሚችሉ ተወዳዳሪዎ አሉት፡፡ በንግድ ውስጥ
ያለው አማራጭ፣ ወይም መምራት አልያም መውጣት ነው፡፡ ከፊት
መሪዎች ውስጥ አንዱ መሆን መቻል አለበት፡፡ የእግርኳስ ክለብንም
ብንወስድ እንዲሁ ነው፡፡ የፖለቲካ ፓርቲም ተፎካካሪዎች አሉት፡፡
በመሆኑም የትኛውም ተቋም በአሸናፊነት መንፈስ የተገነባ አመራር
ያስፈልገዋል፡፡ ተቋሙ ከሌሎች ተሽሎ የሚገኝ ተቋም እንደሆነና እሱም
ያንን በተግባር እውን ማድረግ እንደሚችል የሚያምን፣ ቁርጠኝነቱ
ያለው፣ አመራር ያስፈልጋል፡፡ በአንፃሩ ደግሞ ራሱንና ተቋሙን አሳንሶ
የሚመለከት አመራር እኩል ውጤት ሊያመጣ አይችልም፡፡
እንዲሁም የድርጅቱ ውጤት የእኔ ውጤት ነው፤ የድርጅቱ ውድቀት የእኔ
ውድቀት ነው ብሎ የሚያምን አመራርም ያስፈልጋል፡፡ የትም ቦታ አንድ
መሪ ስራውን ቀይሮ ቢወጣ ለሌላ አመራርነት ሊታጭ የሚችለው ከአሁን
ቀደም በመሪነት ደረጃ ያመጣቸው ውጤቶች ታይተው ነው፡፡ የመሪው
ህልውና በቀጥታ ከተቋሙ ህልውና ጋር ይያያዛል፡፡ ዛሬ ላይ ለውጤት
ያበቃ ባህሪ ነገ ሌላ ቦታ ላይ ይኸው ባህሪ አብሮት ይዘልቃል፡፡
ተቃራኒውም እንዲሁ ነው፡፡ በመሆኑም በአመራርነት ደረጃ ላይ
እስከተቀመጠ ድረስ የተቋሙ ውጤት የእኔ ውጤት ውድቀቱም የእኔ
ውድቀት ነው ብሎ ማመን መቻል ይኖርበታል፡፡ ይህ እንደ መሪ
የሚያስፈልግና ለውጤት የሚያበቃ አመለካከት ነው፡፡
#3. S-skill…ችሎታ
“A man who wants to lead the orchestra must turn his
back on the crowd!” Mad Lucado
መሪነት ራሱን የቻለ ችሎታም ነው፡፡ ከሚመሯቸው በላይ የላቀ ችሎታን
ይጠይቃልና አውቶብስ መንዳት ራሱን የቻለ ችሎታ ነው፡፡ ተቋምን
መሾፈርም እንደዚሁ፡፡ የትኛውን ማርሽ በየትኛው ጊዜ ላይ ወስኖ
መጠቀም እንዳለበት መረዳት የሚችል፤ የትኛውን
👍3
ተተኪ አመራሮችን በኮችንግ፣ በስልጠና
እንዲሁም ከበላይ ካሉ አመራሮች ስር በመሆን እንዲሰሩ በማድረግ
ማብቃት እንችላለን፡፡ በተላዩ የድርጅቱ ክፍሎችና ቅርንጫፎች ውስጥ
በማዟዟር ልዩ ልዩ እውቀትን፣ ልምድንና ችሎታን እንዲያዳብሩ ካደረግን
በኋላ ወደ ላይ ማምጣት እንችላለን፡፡
መንፈሳችን ስለወደዳቸው፣ ደስ ስላለን ወይም ስለመሰለን
የምነቀጥራቸው ወይም ደግሞ የምንተካው ሰዎች መኖር የለበትም፡፡ ደስ
ስላለን ብቻ መኪናችን እንዲነዳልን ቁልፍ ሰጥተን በመኪናው ውስጥ
ተሳፍረን የምንሄድ ስንቶቻችን ነን? አናደርገውም፡፡ ተቋምም እንዲሁ
ነው፡፡
ፍ መንካት
እንዳለበትና እንደሌለበት ማወቅ የሚችል፤ አቅጣጫን የመረዳት ችሎታ፣
የመኪናውን ባህሪ የመረዳትና ማስተካከል የሚችል ችሎታ
ያስፈልገዋል፡፡ አንድ የተቋም አመራርም በተግባር የተፈተሸ ልዩ ልዩ
ችሎታዎች ያስፈልጉታል፡፡ ገንዘብ የማስተዳደር ችሎታ፣ ሰው አስተዳድሮ
የማሰራት ችሎታ፣ ስሜቱን የመቆጣጠር ችሎታ፣ ውጤታማ
ኢንቨስትመንት የማድረግ ችሎታ፣ ተናግሮ የማሳመን ችሎታ፣ የማቀድ
ችሎታ፣ የወደፊቱን የመተንበይ ችሎታ፣ እያለ ይቀጥላል፡፡ አንድ አመራር
ጥሩ ገንቢ አመለካከት ቢኖረው እንኳን ትክክለኛ ችሎታ በሌለበት ሁኔታ
ያለትክክለኛ ትግበራ የሚጠበቀውን ትክክለኛ ውጤት ለማምጣት
ያስቸግረዋል፡፡
#4. K- Knowledge…
“It the blind lead the blind, both shall fall in the
ditch”… Jesus Christ
በእርግጥ ችሎታ የሚዳብረው ከማወቅ ነው፡፡ ለአመራርነት የሚያበቁ
ችሎታዎችን ለማዳበር በቅድሚያ ስለችሎታዎቹ መሰረታዊ እውቀት
ሊኖረው ይገባል፡፡ ሁሉም አይነት እውቀት አይደለም፣ ለትክክለኛ ቦታ
የሚሆን ትክክለኛ እውቀት እንጂ፡፡ ይህ ብቻ አይደለም፣ ስለሚመራው
ተቋምም ውስጣዊና ውጫዊ ሁኔታዎችን ሊያውቅ ይገባል፡፡ እንዲሁም
የሚመራው አንድን የንግድ ተቋም ከሆነ ስለንግድ አሰራር መሰረታዊ
እውቀት ያስፈልገዋል፡፡ ብዙውን ጊዜ በአገራችን የድርጅቱ ባለቤት
ስለሆኑ ብቻ እንጂ መሰረታዊ የንግድ ‹‹ሀሁ›› እውቀት ኖሯቸው
ድርጅታቸውን የሚመሩ ሰዎች ጥቂት ናቸው፡፡
አንድ ሰው የሚመራው የእግርኳስ ክለብን ከሆነ ደግሞ ስለ እግርኳስ
መሰረታዊ እውቀትን ሊጨብጥ ይገባል፡፡ የፖለቲካ ፓርቲም ከሆነም
ስለፖለቲካና አገራዊ አመራር ትክክለኛ እውቀት ያስፈልገዋል፡፡
ምክንያቱም እውቀቱ ችሎታውን ይወስናል፤ ችሎታውን ተግባሩን፡፡
ተግባሩ ደግሞ ባህሪውን ይቀርፃል፡፡ በመጨረሻም የግለሰቡንና
የተቋሙን ውጤት፡፡
ለምሳሌ በአገራችን ያሉ መካከለኛና ከፍተኛ የሚባሉ ኢንተርፕራይዞች
በቀጥታ ለመመራት ያለባቸው በቢዝነስ ሁለተኛ ዲግሪ ባላቸው
ባለሙያዎች ሲሆን ብዙዎቹን ስንመለከት ግን ይህን ሚዛን አያልፉም፡፡
ለዚያም ነው የሚመሯቸው ተቋሞች ወደ ላይና ወደ ታች ሲሉ
የምናያቸው፡፡ በፓርቲም ደረጃ እንዲሁ በፖለቲካል ሳይንስ በቂ ግንዛቤ
ያላቸውን አመራሮች ይጠይቃል፡፡ አለበለዚያ አላዋቂ ሳሚ እንዳይሆን
ራሳችንን መፈተሽ ይገባል፡፡ ለትክክለኛ ተቋምና ለትክክለኛ የአመራር ቦታ
ብቁ የሚያደርግ ትክክለኛ እውቀት!!
#5. E- Experience… ልምድ
“Leadership and (experience) are indispensable to
each other”… John f. Kennedy
ከላይ ያሉት የአመራር ችሎታዎች የሚዳብሩት በልምድ እና በልምምድ
ውስጥ ነው፡፡ እንዲሁም የአመራርነት ባህሪ በራሱ የልምድ ውጤት
ነው፡፡ ከአሁን ቀደም አንድ ሰው ያዳበረው ልምድ ውጤት የማያመጣ
ወይም የውድቀት ከሆነ ባህሪውም ይሄንኑ ነው፡፡ በእርግጥ የአመራር
ችሎታዎቹም ቢሆኑ ውድቀትን የሚያላብሱ ናቸው የሚሆኑት፡፡ በሥራ
ማስታወቂያዎች ላይ ‹‹በዘርፉ ይህን ያህል የሥራ ልምድ›› የሚባለውም
ለዚያ ነው፡፡ የአንድን አመራር ልምድ በቀላሉ ለመረዳት ‹‹ከአሁን ቀደም
ምን ያህል ድርጅቶች አቋቁመህ ወይም መርተህ ለውጤት
አብቅተሃል?›› የሚለው ወሳኝ ጥያቄ ነው፡፡ አንዳንዱ ረጅም ዓመት
የመምራት ልምድ ኖሮት ሊሆን ይችላል፡፡ ዋናው ነገር በቦታው ላይ
መቆየቱ አይደለም፡፡ ድርጅቱን ከየት አንስቶ የት አደረሰው? የገጠሙትስ
ተግዳሮቶች ምን ነበሩ? እንዴትስ በመፍታት ተቋሙን ለውጤት አበቃው?
ነው ጨዋታው፡፡ አመራርነት ስልጣን አይደለም ውጤት እንጂ፡፡ ማዕረግ
አይደለም፡፡ አፈፃፀም እንጂ ረጅም ዓመታት በመምራት መቆየትም
አይደለም ረጅም የሚያስከነዳ ውጤትን ማስጨበጡ ላይ ነው ቁም
ነገሩ፡፡
#6. T- Talent… ልዩ ብቃት
“Your are your master, only you have the master key to
pen the inner locks!”
…Leonardo Davienchi
ይህ የአመራርነት የመጨረሻው ማስተሪ ይሉታል ባለሙያዎች፡፡ መሰጠት
እንደማለት ነው፡፡ ታለንት በተፈጥሮ የተሰጠን ሊሆን ይችላል፡፡
በትምህርትና ልምምድም ወደ ማስተርነት የተቀየረም ሊሆን ይችላል፡፡
ከላይ ያሉት ውጤት ተኮር እውቀቶች፣ ውጤት ተኮር ችሎታዎች፣ ውጤት
ተኮር አመለካከቶች፣ ውጤት ተኮር ልምዶች በየጊዜው በዳበሩ ቁጥር
ግለሰቡ ለዚያ ቦታ የሚኖረው ልቀት ያለው አመራር (Leadership
excellence) ወደ ፍፁም ብቃት ይሸጋገራል፡፡ ውጤታማ አመራርነት
ለግለሰቡ ቋንቋው፣ ተግባሩ፣ መንፈሱ፣ መሆን ሲጀምር ሊደርሺፕ በራሱ
ታለንት ወደ መሆን ተሸጋገረ እንለዋለን፡፡
ለዚህ መሰሉ ሰው ውጤታማ አመራርነትን አውቆት ወይም አስቦበት
ሳይሆን ሳያውቀው ሁሉ የሚተገብረው ነው የሚሆነው (autopilot)፡፡
የሊደርሽፕ ማስተሪ ማለት ይህ ነው፡፡ ይሁን እንጂ በአመዛኙ የምናየው
የትምህርት ማስተርስ እንጂ ውጤትና ለውጥ ሊያመጣ የሚችል ማስተሪ
አይደለም፡፡ ይህ ምናልባት የትምህርት ተቋሞቻችን አንዱ ክፍተት ሊሆን
ይችላል፡፡
ለምሳሌ እኔ ባለፍኩበት የህክምና ሳይንስ ተቋም ማለትም አዲስ አበባ
ዩኒቨርሲቲ እንደ ህክምና ሳይንስ አመለካከታችን በሔታክራተሳዊ
ኤቲክስ፣ እውቀቱ ረጅም ዓመታት የሚፈጅ፣ ከመጀመሪያው ዓመት ጀምሮ
በፍፁም ተግባር ላይ የተንተራሰ፣ ለሶስት ዓመታት ያህል ከሲኒየር
ሐኪሞች ስር በመሆን እንደ ሐኪም ህሙማንን በመመርመርና በማገዝ፣
በተለያዩ ሆስፒታሎች በመዘዋወር ውስጥ ተሞክሮ የተገነባበት በመሆኑ
አንድ የህክምና ዶክተር ከተመረቀ ጀምሮ በየትኛውም ቦታ ላይ
የሚገጥሙትን የስራ ላይ ተግዳሮቶች መወጣት ይችላል፡፡ ድንገተኛ ቀዶ
ህክምና አስፈልጓቸው በገጠሩ በቂ መብራት በሌለበት ሁኔታ ውስጥ
እንኳን ቀዶጥገና አድርገው ህይወት ያተረፉ፣ እንደዚሁም በቀዶ ህክምና
ያዋለዱ ተመራቂ ጓደኞች ነበሩኝ፡፡ በመሆኑም ሁሉም የትምህርት
ተቋማት ከላይ ያሉትን የአመራር ገጽታዎችን በተሞላ መልኩ የገነቡ
ተተኪ ወጣቶችን ለማፍራት የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በተለይ
የህክምና ሳይንስ ኮሌጆችን ተሞክሮ ቢወስዱ የሚል እምነት አለኝ፡፡
እንዲሁም በዓለማችን ታዋቂ ዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ አንዱ ከሆነው
የአሜሪካው ስታንፎርድ ዩኒቨርሲቲ ውስጥ ከሚመረቁ አምስት ሰዎች
ውስጥ አንዱ በአምስት ዓመት ውስጥ ውጤታማ የድርጅት ባለቤት
ሲሆን ከእነዚህ ውስጥ አንዱ ደግሞ አለማቀፍ ኩባንያዎች ውስጥ
የአንዱ አገር ዲቪዥን የበላይ አመራር ሆኖ የመቀጠር እድል አለው፡፡
ይህ የሚያሳየው ዩኒቨርሲቲው የሚያወጣቸው ተማሪዎች
የ‹‹BASKET›› ፅንሰ ሃሳብን በተላበሰ መልኩ ስለሚያስተምሯቸው
ነው፡፡ በነገራችን ላይ የስመ ገናናው ኢሲኤክክስ መስራች ዶ/ር እሌኒ
ገ/መድህን የዚህ ዩኒቨርሲቲ ውጤት ናት፡፡ ዩኒቨርሲቲ በንግድ ሳይንስ
ካስተማራቸው ውስጥ በአሁኑ ወቅት በዓለም ላይ 30 በህይወት ያሉ
ቢሊየነር ነጋዴዎችን ማፍራት የቻለው ከዚህ አንፃር ነው፡፡ እንግዲህ
ቢሊየነሮቹ ይህን ያል ከሆኑ መልቲ ሚሊየነሮቹ ምን ያህል ይሆኑ?
ሚሊየነሮቹስ? እጅግ ብዙ፣ ይህን በእኛ ሀገር ብንፈትሽ ስንቶቹ የንግድ
ሳይንስ ተማሪዎች የት ደርሰዋል? ብለን ማንሳትና ማጥናትም አለብን፡፡
እናም በየትኛውም ተቋማት ውስጥ ለምንቀጥራቸው አመራሮች
እንደመመልመያ መስፈርትም ሆነ መገምገሚያነት እንዲሁም ተተኪ
አመራሮችን ወደ ላይ ለማምጣት የ‹‹B ASKET›› መርህን መከተል
እንችላለን፡፡ በምንመራው ተቋም ውስጥም ልንጠቀምበት እንችላለን፡፡
እንዲሁም በዚህ
Muhammed Computer Technology (MCT) pinned «ተተኪ አመራሮችን በኮችንግ፣ በስልጠና እንዲሁም ከበላይ ካሉ አመራሮች ስር በመሆን እንዲሰሩ በማድረግ ማብቃት እንችላለን፡፡ በተላዩ የድርጅቱ ክፍሎችና ቅርንጫፎች ውስጥ በማዟዟር ልዩ ልዩ እውቀትን፣ ልምድንና ችሎታን እንዲያዳብሩ ካደረግን በኋላ ወደ ላይ ማምጣት እንችላለን፡፡ መንፈሳችን ስለወደዳቸው፣ ደስ ስላለን ወይም ስለመሰለን የምነቀጥራቸው ወይም ደግሞ የምንተካው ሰዎች መኖር የለበትም፡፡ ደስ ስላለን…»