Muhammed Computer Technology (MCT)
38.2K subscribers
527 photos
7 videos
254 files
910 links
🔴አድራሻ:-
✅ ስ.ቁ: 0929273364
✅ ዌብሳይት www.mctplc.com
✅ቴሌግራም አካውንት: https://t.me/mctplc
✅ email: mct16plc@gmail.com
✅ ቲክቶክ አካውንት tiktok.com/@mctplc
Download Telegram
ከኮምፒወተር ላይ ያለ ፋይሎችን ሌላ ሰው እንዳይክፍትብንና Delete እንዳይድርግብን በኮምፒውተር፣ በፍላሽ፣ በHard Disk ያሉ ፋይሎችን መደበቅና ማውጣት
👇👇👇ይማሩ ይወቁ👇👇👇

https://youtu.be/4IdgIEE675s
💦💦💦መልካም አዳር 💦💦💦
✅ላፕቶፓችን ላይ ያለውን ኢንተርኔት እንዴት ያለምንም ሶፍት ዌር በሞባይላችን
መጠቀም እንችላለን?✅
➡️1. cmdን በአንሜኒስትሬተር ያሩጡት (right click በማድረግ run as
administrator የሚለውን መጫን)
➡️2. ላፕቶፓችን ኔትዎርክ ሼር ለማድረግ ብቁ መሆኑን ለማረጋገጥ: netsh
wlan show drivers የሚለውን ጽፎ ከሚመጣልን ዝርዝር ውስጥ Hosted
network supported :Yes ይህ ከመጣ ላፕቶፓችን ይችላል ማለት ነው
➡️3. በመቀጠል ይህንን ኮማንድ ማስገባት: netsh wlan set
hostednetwork mode=allow ssid=Hotspotname
key=password
ማሳሰቢያ: SSID የሚለውን በፈለግነው ስም መቀየር እንችላለን: KEY የሚለው
የዋይ ፋይ ፓስዎርዳችን ስለሆነ የምንፈልገውን መስጠት እንችላለን
➡️4. በመቀጠል የኔት ዎርክ አዳፕተራችንን በመክፈት እና እሱላይ right click
በማድረግ : Allow other network users to connect through this
computer's internet connection የሚለውን እንመርጥያ ከስር ካለው
ሊስት ውስጥ የፈጠርነውን የዋየርለስ ኔትዎርክ እንመርጥለታለን::ከዛም
OK በለን እንወጣለን
➡️5. በመጭረሻ ወደ CMD ተመልሰን:
ለማስጀመር netsh wlan start hostednetwork የሚለውን ኮማንድ
እናስገባለን ለማቆም netsh wlan stop hostednetwork የሚለውን እናስገባለን
➡️6. አሁን ሞባይላችንን wifi ከፍትን SSID ላይ ያስገባነውን የኔትዎርክ ስም
መርጠን ለሚለው KEY ላይ ያስገባነውን በመስጠት መጠቀም መጀመር እንችላለን።
👍1
ቻናሉን እንዴት አያችሁት?
anonymous poll

ምርጥ ነው 👍 – 313
👍👍👍👍👍👍👍 97%

አልተመቸኝም 👎 – 9
▫️ 3%

👥 322 people voted so far.
👍2
🌐ዓለም ከኮምፒውተር ጋር ከተዋወቀ በርካታ ዓመታት ቢቆጠሩም የብዙዎች የኢንተርኔት አጠቃቀም መስመርን የሳተ ነው።
===================

✍ ከመረጃ ደህንነት ጋር የተያያዙ የትየለሌ እሮሮዎች በተደጋጋሚ የሚሰሙትም ከአጠቃቀም ስህተቶች ጋር በተያያዘ ነው።

የኢንተርኔት አጠቃቀም ስህተት ለአካላዊ ወይም አእምሯዊ ጉዳት እንደሚያጋልጥ
ተመራማሪዎች ይናገራሉ።

በስፔን የሚገኘው የበይነ-መረብ ደህንነት ተቋም ኢንተርኔት ሰክዩሪቲ ኦፊስ (ኢኤስኦ) በተደጋጋሚ የሚሰሩ ስህተቶችን ይፋ አድርጓል።

ከኮምፒውተር መረጃ መዝባሪዎች ራሳችሁን ለመታደግ ስህተቶቹን ከመፈጸም ተቆጠቡም ብሏል።

#የማይታወቁ_ማስፈንጠሪያዎች

የኮምፒውተር መረጃ መዝባሪዎች ሰዎችን ከሚያጠምዱባቸው መንገዶች አንዱ የተሳሳቱ ማስፈንጠሪያዎች መላክ ነው። ሰዎችን በቀላሉ ማማለል የሚችሉ 'የዋጋ ቅናሽ' ወይም 'በነጻ የሚታደሉ ምርቶች' ማስታወቂያ ይጠቀሳሉ።

ማስፈንጠሪያዎቹ ቫይረስ ወደተሸከሙ ገጾች ስለሚወስዱ የተጠቃሚዎችን የመረጃ ደህንነት አደጋ ውስጥ ይጥላሉ።

ኢኤስኦ "ማስፈንጠሪያዎች ከመከተልዎ በፊት ቆም ብለው ያስቡ" ይላል።

#ያረጁ_ሶፍትዌሮች

በስልክ ወይም በኮምፒውተር የሚጫኑ ሶፍትዌሮች በየግዜው መታደስ አለባቸው። ሳይታደሱ ከቆዩ የኮምፒውተር ወንጀለኞች በየግዜው ለሚሰሯቸው አደገኛ ቫይረሶች ያጋልጣሉ።

#አጠራጣሪ_መተግበሪያዎች

መተግበሪያዎችን (አፕ) ከተለያዩ ድረ ገጾች መጫን ለደህንነት አስጊ ነወ። ትክክለኛ የሚመስሉ
ነገር ግን ለቫይረስ የሚያጋልጡ መተግበሪያዎች ብዙ ናቸው።
ብዙዎችም ያለማወቅ ይጭኗቸዋል።

#ቀላል_የይለፍ_ቃል

የኮምፒውተር መረጃ መዝባሪዎች የተጠቃሚዎችን የግል መረጃ ለመስረቅ የይለፍ ቃላቸውን ይሰብራሉ።

ስለዚህም ኢኤስኦ "ጠንካራ የይለፍ ቃል ይኑራችሁ" ይላል። ምክንያቱም በቀላሉ
የሚገመቱ የይለፍ ቃሎች በርካቶችን ለአደጋ አጋልጠዋል።

#የመረጃ_ቅጂ_አለማስቀመጥ

በኮምፒውተር ወይም በስልክ ላይ ያሚገኙ መረጃዎችን ቅጂ አለማስቀመጥ ሌላው ችግር
ነው። የኮምፒውተር መረጃ መዝባሪዎች የግል መረጃ ካገኙ ለባለቤቱ ለመመለስ ገንዘብ ይጠይቃሉ።

ተጠቃሚዎች የመረጃቸው ቅጂ ካላቸው ግን ከመዝባሪዎች ጋር መደራደር
አያስፈልጋቸውም።
Facebook አካውንት Hack እንዳይደረግ እንዴት ማድረግ እንደምንችል አሳያችኋለሁ😀

✔️መፍትሄውን እነሆ👇👇👇

1⃣.በመጀመሪያም ይህ መሆኑን እና አለመሆኑን ለማረጋገጥ አሁን step by step ተከታተሉኝ
💢Facebook ➡ seting ➡ Security and login ➡ Where you are logged in 👉 ላይ በመግባት በእናንተ አካውንት የገባ ሰው እንዳለና እንደሌለ ማወቅ ያስችላል።

⚠️Note: እራስዎ በሌላ #አፕ ከገቡም ያመጣልዎታል መርጠው መርጠው ነው።

✴️ ከዛም Terminate all other sessions ክሊክ በሉት፤ ይህ ሚጠቅመው በሌላ ስልክ 📱 የእናንተን #አካውንት የሚጠቀም ሰው ካለ remove ያደርገዋል።

2⃣.Security ደግሞ ለማጠናከር Setting ➡ Security and login ➡ Two Factor Authentication ➡ use two factor authentication ➡ ውስጥ በመግባት በስልካችሁ የሚላከውን Code በማስገባት ON ታረጉታላችሁ እሄም የሚጠቅመዉ Passwordachun እራሱ ቢያገኙት Facebookኩ ሚፈልገዉ Password ሳይሆን በስልካችሁ የሚላከዉን Code ነው ሚጠቀመዉ

✴️ ይህ👆 ጠንካራ የሚባለው #የፌስቡክ security new
ፌስቡካችሁ መጠለፉን ለማወቅ፣ ፌስቡካችንን ከጠለፋ ማውጣት፣ የተጠለፈበትን ቦታ ለማወቅ፣ በስልካችን ገብተን የጠለፈብንን ሰው እንዳይጠቀምበት Logout መዝጋት
ሊንኩን በመጫን በማየት ይቻላል
👇👇👇

https://youtu.be/azdo0eTD4XY
❤1
💢ስልካችሁ📱 ላይ የሆነ #አስቸኳይ ነገር ልትሰሩ ፈልጋችሁ ቻርጅ ዘጋባችሁ📵 እንበል፤ ቻርጀር ደግሞ በአካባቢያችሁ የለም።

✅ለዚህ መፍትሄ የሚሆን እንዴት ከሌላ ስልክ📲 ላይ ቻርጅ #ማስተላለፍ እንደምትችሉ አሳያችኋለሁ።
💢ስልካችንን📲 እንዴት ከሌላ ስልክ ላይ ቻርጅ ማድረግ እንችላለን?

#አስፈላጊ ነገሮች⬇️⬇️⬇️

✅ሌላኛው ስልክ
✅OTG
✅data cable

1⃣. አሰራር፦ ኬብሉን #OTG ላይ ይሰኩና በቀላሉ #OTG ያለበትን ጫፍ ቻርጅ ሰጪው ስልክ📲 ላይ ይሰኩት።

2⃣. ሌላኛውን ጫፍ ቻርጅ ማድረግ የሚፈልጉት ስልክ ላይ ይሰኩት።

አለቀ፤ ዳይ ወደ ዘረፋ😎

creditŠ ethiotechs
👍1
#ይነበብ
ውድ የ Muhammed Computer Technology የቴሌግራም ቻናል ተከታታዮች። እንደሚታወቀው በፌስቡክና በቴሌግራም ምርጥ አስተማሪ የቴክኖሎጂ መረጃዎችን እያደረስኳችሁ እገኛለሁ።
ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ደግሞ በYouTube ጠቃሚ ትምህርቶችን ለተመልካች እያቀረብኩ እገኛለህ። ስለሆነም በ4 ወራቶች ብቻ ❤ #5,700 በላይ #Subscribers ማግኘት የቻለ ተወዳጅ ቻናል ሁኗል ስለሆነም በYouTube በምለቀቃቸው Vedios ጠቃሚና አስተማሪ ሰልሆኑ #Subscribe በማድረግ #ይማሩ #ይወቁ
#በቅንነት ሼር አድርጉልኝ!
ያቀቁትን ማሳወቅ የተማሩትን ማስተማር ብልህነት ነው።
YouTube ቻናል ሊንክ
👇👇👇

https://www.youtube.com/channel/UCZBIP6PqUdmmagdTjbyp_AQ
ከሞባይል ወደ ላፕቶፕ እንዲሁም ከ ላፕቶፕ ወደ ሞባይል ፋይል እንዴት መላክ እንችላለን?
How to share File using Bluetooth from mobile to laptop and laptop to Mobile
✅ ዶክመንቶችን
✅ ፎቶዎችን
✅ ኦዲዮ
✅ ቪዲዮዎችን
በፍጥነት እንዴት መላላክ እንደምንችል የሚያሳይ ምርጥ ቪዲዮ።
👇👇👇እንዲመለከቱት ግብዣየ ነው👇👇👇
https://youtu.be/EH8X_p7kYuk
ስለ ላፕቶፖቻችን እናያለን

ላፕቶፕ ከ ዴስክቶፕ ኮምፒውተር ጋር ተመሳሳይ ሲሆኑ ዴስክቶፕ ኮምፒውተሮችን ከ ቦታ ቦታ ይዘናቸው እየተንቀሳቀስን መጠቀም አንችልም ይህን ስል ተንቀሳቃሽ አይደሉም እያልኩ ሳይሆን በቀላሉ ይዘናቸው አንንቀሳቀስም ለማለት ነው ላፕቶፖችን ግን በቀላሉ በቦርሳዎችም ይሁን በጃችን ይዘን መንቀሳቀስ እንችላለን እንዲሁም በትንሽ ቦታ ላይ አስቀምጠን መጠቀም እንችላለን እንዲሁም እንደ ሞባይል ስልኮቻችን ቻርጅ እያደረግን ስለሆነ ምንጠቀመው የመብራት መቆራረጥ ስራችንን አስቸጋሪ አያደርገውም ማለት ነው ስለ ላፕቶፕ ብዙ ማለት ይቻላል ግን እዚህ ላይ ይብቃንን ስለ አጠቃቀማችን እና ጥንቃቄ አወሳሰዳችን እንይ

1⃣ላፕቶፖች ለመያዝ እና ለማንቀሳቀስ ቀላል ስለሆኑ አብዛኛዎቻችን በ እግራችን ላይ አስቀምጠን እንጠቀማለን ነገር ግን በእግራችላ ይ ማስቀመጥና መጠቀም እንደሌለብን ጥናቶች ያሳያሉ ላፕቶፖቾ ስራ በሚሰሩ ሰአት ሙቀት ይፈጠራል ያ ሙቀት እየበዛ በሚሄድ ሰአት ከሙቀቱ ጋር አብሮ የተለያዩ ጨረሮች ይለቀቃሉ ይህም በእግራችን ላይ ጉዳት ያደርሳል ነገሩ እየተደጋገመ ሲመጣ ደግሞ ለከፋ ጉዳት ይዳርገናል በተለይ ነብሰጡሮች በፅንሱ ላይ ከፍ ያለ ጉዳት ስለሚያደርስ ጥንቃቄ መውሰድ አስፈላጊ ነው፡፡
ስለሆነም ላፕቶፖችን ስንጠቀም ከሆዳችን 30cm ራቅ አርገን በጠረጴዛ ላይ አስቀምጠን እንድንጠቀም ይመከራል፡፡

2⃣ ሌላው ደግሞ የባትሪያችንን እድሜ ማስረዘም ሲሆን የላፕቶፕ ባትሪዎች ከ 40 _ 80% ቻርጅ ከተደረጉ በቂ ነው በተለይ 99 98% ሲሉ ብንነቅላቸው እና ሲጨርሱ 1% እንደዚህ ሲቀራቸው ብንሰካቸው ይህን ሬንጅ በመጠበቅ ቻርጅ ብናረግ እድሜያቸውን ማስረዘም እንችላለን ማለት ነው፡፡

3⃣ እንዲሁም ላፕቶፖችን በጨለማ ወይም በቂ ብርሀን በሌለበት ቦታ አለመጠቀም ከ ላፕቶፑ ብርሀን ጋር ተመጣጣኝ ብርሀን ያለበት ቦታ መጠቀም አይናችንን ከህመም መጠበቅ እንችላለን፡፡

4⃣ ላፕቶፓችን አየር እንዲያገኝ ማድረግ እና አካባቢውን ሙቀት እንዳይበዛበት ለማድረግ መሞከር ፀሀይ ላይ አለመጠቀም በአካባቢው መፅሀፍት ምግቦች መጠጣች ወዘተ አለመደርደር ስስ የሆኑ ነገሮች ላይ አለማስቀመጥ ማለት ለምሳሌ አልጋ ላይ አርገን ይህም የላፕቶፑን አየር ማስገቢያውን ቀዳዳዎች ስለሚያፍኑት ለላፕቶፑ ጤንነት ጥሩ አይደለም፡፡

5⃣፡የላፕቶፑን ንፅህና መጠበቅ እና ማፅዳት ቢያንስ በቀላሉ ከላይ ያሉ አቧራዎችን ወዘተ ንፁህ በሆነ ጨርቅ ማፅዳት ከማፅዳታችን በፊት ላፕቶፑን ማጥፋታችንን አለመዘንጋት ከዚህ ባለፈ የላፕቶፑ ኪይቦርድ በምናፀዳበት ወይት በቀላሉ መነቀልና መሰካት ስለሚችል ነቅለን ማፅዳት፡፡ እንዲሁም የ ላፕቶፑ ፋን አየር ለማስገባት በሚስብብት ወቅት የተለያዩ አቧራዎች አብረው ይገባሉ ይህነንን ለማፅዳት ላፕቶተፑን በደንብ እምናውቀውና ፈተን የመግጠም ችሎታው ካለን ፈተን ማፅዳት እንችላለን ካልሆነ ደግሞ በላፕቶፑ አየር ማስገቢያ ቀዳዳዎች ውስጥ ከፍ ያለ አየር በማስገባት ማፅዳት እንችላለን ማለት ነው ፡፡ ያው ላፕቶፕ የራሱ ማፅጃ ያለው ቢሆንም መግዛት ካልቻልን በተቻለ መጠን በንፁህ ስስ ጨርቅ በጥንቃቄ ማፅዳት ተገቢ ነው፡፡ ከብዙ በጥቂቱ ለላፕቶፖቻችን መውሰድ ካሉብን ጥንቃቄዎች ውስጥ የተወሰኑት እነዚህ ናቸው፡፡

ለወዳጆ ሼር በማድረግ ያግዙን እናመሰግናለን
👍1
ምርጥ የResearch ቻናል።

❓ትምህርት እየተማሩ ነው? ወይም ለመማር አስበዋል?
❓ጥናትና ምርምር(Research) እየሰሩ ነው?
❓ስለ Research እውቀትዎን ማሳደግ ይፈልጋሉ?
❓ስለ SPSS ማውቅ ይፈልጋሉ?
⁉️የምንረዶት ጉዳይ አለ?

✅በአማርኛ ና በእንግሊዝኛ በግልጽና ቀላል አገላለጽ ስለ Research ጽንሳ ሀሳብ ጀምሮ ጽሑፎችን ያገኛሉ።

💻በጥናትና ምርምር ዙርያ የማማከር አገልግሎትም እንሰጠለን።
👇👇👇👇👇👇👇
@researchRC
@researchRC
@researchRC
@researchRC
@researchRC
👆👆👆👆👆👆👆👆
iCare_Data_Recovery_Enterprise_Edition_v3_8_2_Software_+_Serial.rar
3.1 MB
ከላይ ያለው ሶፍትዌር icare data recovery ይባላል
ማንኛውንም ፎርማት የተደረገን፣ ድሌት የተደረገን፣ ማንኛውንም computer, Flash Disk, Hard Disk በሙሉ ይመልሳል። እንዴት እንደሚመልስ በቪዲዮ ለመመልከት ለምትፈልጉ ከታች ያለውን ሊንክ በመጫን መመልከት ይችላሉ።
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇

https://youtu.be/G8HQeWaIUKY
https://youtu.be/G8HQeWaIUKY
https://youtu.be/G8HQeWaIUKY


✅ በቴሌግራም ቻናል: https://t.me/MuhammedComputerTechnology
https://t.me/MuhammedComputerTechnology
👍3❤2
📶 ዋይ ፋይ ምንድነው?
✅ Wi-Fi እንዴት ይሰራል?
ይህ ቃል ለአብዛኛው ተጠቃሚ፤ ሞያተኛውንም ሲጨምር አጋጥሞናል ከ ኢንተርኔት ጋር እየተለዋወጠ ሲገባ እናየዋለን፡፡ በሞያችንም ለሰዎች ለማስረዳት ስንሞክር አለመግባባት ይከሰታሉ፡፡ እርግጥ ነው ዋይ ፋይ ኢንተርኔት ለማገኘት ይራዳል ነገርግን በራሱ ኢንተርኔት አይደለም፡፡
✅ምንም እንኳን በአይናችን ባናያቸውም የራዲዮ ሞገዶች ሁሌም መረጃዎችን ተሸክመው በዙሪያችን እንዳሉ ይታወቃል፡፡ ከእነዚህ የሬዲዮ ሞገዶች ጥቂቶቹ የWi-Fi ሲግናሎች ናቸው፡፡ Wi-Fi በሚለው ስም ውስጥ የሚገኙ ሆሄያት እንደ አህጽሮተ ቃል የትኛውንም ነገር የማይወክሉ ሲሆን በመነሻነት አንድ ከፍተኛ መጠን ያለውን መረጃ በአጭር ርቀት ውስጥ የራዲዮ ሞገዶችን በመጠቀም ማስተላለፍ የሚችልን ቁስ በቀላሉ ማስታዎስ እንዲቻል ተብሎ የተሰጠ ስያሜ ነው፡፡

✅ እንደ ብሮድካስት ራዲዮና ተንቀሳቃሽ ስልክ ሲግናሎች ሁሉ የWi-Fi ሲግናልም በ19ኛው መቶ ክፍለ ዘመን መገባደጃ አካባቢ የተገኘ ሳይንሳዊ ፈጠራ ነው፡፡ ኤሌክትሮኖች በሽቦ ውስጥ በሚንቀሳቀሱበት ጊዜ በየተወሰኑ ጊዜያት አቅጣጫዎችን ይቀይራሉ፡፡ በሌላ ሽቦ ላይ የሚገኙ ኤሌክትሮኖች ከእነዚህ አቅጣጫ ከሚቀያይሩ ኤልክትሮኖች ጋር ቴሌፋቲክ በሆነ መንገድ የተያያዙ ስለሆኑ መንቀሳቀስ ይጀምራሉ፡፡ ይህ ግኝት መጀመሪያ የታወቀው በ1887 በሄንሪክ ሄርትዝ ነው፡፡

✅ የሚታይ ብርሃንን የያዙ ኤሌክትሮመግነጢሳዊ ህብሮች ከራዲዮ ሞገዶች የተሻለ ከፍተኛ ፍሪኩየንሲን ያመነጫሉ፡፡ የተለመዱት የኤ ኤም ወይም ኤፍ ኤም ራዲዮ እና የቴሌቪዥን ስርጭቶች መረጃን በተከታታይ ሲግናሎች ወይም በአናሎግ ያደርሳሉ፡፡ Wi-Fi መረጃን የሚያሰራጨው እንደ ያልተያያዙ ዋጋዎች የባይናሪ መረጃ ዜሮዎችና አንዶች በዲጂታል መንገድ ነው፡፡ ይህም የሞባይል ቁሶች ከፍተኛ መጠን ያላቸውን እንደ ቪዲዮ፣ ምስል፣ ድምጽ እና የጽሁፍ መልዕክቶችን በቀላሉ እንዲልኩ ያስችላቸዋል፡፡

✅ አንድን መረጃ በዋይ ፋይ ኦንላይን ላይ ስንፈልግ የዋይ ፋይ ቁሳችን የሬዲዮ ሞገዶችን አልፎ ከዋይ ፋዩ መገኛ ነጥብ ጋር ይናበባል፡፡ ይህም በኢንተርኔት ራውተራችን አንቴና አማካኝነት ነው፡፡ ከዚያም በአካባቢው ባሉ የኢንተርኔት ገመዶች አማካኝነት ጥያቄያችን ወደምንፈልገው የመረጃ ቋት ይተላለፋል፡፡ ሂደቱ ሲያልቅም በመጣበት መንገድ ተመልሶ ይመጣል፡፡

✅ በተለያዩ ኩባንዎች የተሰሩ የዋይ ፋይ ቁሶች 802.11 የተሰኘ ተመሳሳይ ስታንዳርድን ስለሚከተሉ እርስ በርሳቸው መናበብ ይችላሉ፡፡ ይህ ስታንዳርድ ዜሮዎችና አንዶች ራዲዮ ሞገድን በመጠቀም እንዴት እንደተወከሉና ቁሶቹ ራሳቸውን እንዴት እንደሚለዩ የሚወስን ነው፡፡ እነዲሁም ደግሞ ኬሪየር ሴንስ መልቲፕል አክሰስ (CSMA) የተሰኘ እንዴትና መቼ መግባባት እንዳለባቸው የሚወስን አሊጎሪዝም ይከተላሉ፡፡ ይህ አሊጎሪዝም የዋይ ፋይ ቁሶችን ስማርት ያደርጋቸዋል፡፡

✅ አንዳንድ ጊዜ ከዋይ ፋይ ጋር በተያያዘ ችግሮች ይገጥሙናል፡፡ ወይም ከዋይ ፋዩ መገኛ ነጥብ ጋር ለመገናኘት እንቸገራለን ይህም የሚሆነው የራዲዮ ሲግናሎች በርቀት ምክንያ ሲደክሙ ነው፡፡ ለምሳሌ ወፍራም ግድግዳ፣ የብረት መከለያዎች አንዲሁም አኳሪየም የራዲዮ ሞገዶችን ሊያደክማቸው ይችላል፡፡

✅ ዋይ ፋይ ይህ ቃል ለአብዛኛው ተጠቃሚ፤ ሞያተኛውንም ሲጨምር አጋጥሞናል ከ
ኢንተርኔት ጋር እየተለዋወጠ ሲገባ እናየዋለን፡፡ በሞያችንም ለሰዎች ለማስረዳት ስንሞክር አለመግባባት ይከሰታሉ፡፡ እርግጥ ነው ዋይ ፋይ ኢንተርኔት ለማገኘት ይራዳል ነገርግን በራሱ ኢንተርኔት አይደለም፡፡

✅ ዋይ ፋይ ገመድ አልባ የኮምፒውተር ግንኙነት መፍጠሪያ ዘዴ ሲሆን ኢንተርኔትን ጨምሮ የተለያዩ መረጃዎችን፣ ፋይሎችን፣ እንዲሁም እቃዎችን (ፕሪንተር፣ እስካነር) በጋራ እንድንጠቀም ይረዳናል፡፡ ይህ ማለት ደግሞ የባለገመድ ግንኙነት (cable Network) ምትክ መሆኑን ያሳያል፡፡
👍1
SD(Secure Digital) Card ሜሞሪ
የዘመናችን አስደናቂ ፈጠራዎች ከሆኑት መካከል ስለ #ሜሞሪ_ካርድ ወይም SD(Secure Digital) CARD በጥቂቱ:

◽ ይህች SD(Secure Digital) Card የምንላት መሳሪያ ኤሌክትሮኒክ የመረጃ #ማከማቻ ስትሆን ዲጅታል ኢንፎርሜሽኖችን ለማስቀመጥ ወይም Store ለማድረግ ያገለግላል፡፡ ይቺ ዳታ ማከማቻ በዲጅታል ካሜራዎች፣ በተንቀሳቃሽ ስልኮች፣ በላፕቶፖችና በኮንፒውተሮች፣ በታብሌቶች ፣በmp3 ማጫዋቻዎችና በቪድዮ ጌም ኮንስሎች ትገኛለች፡፡

◽️ የሚሞሪ ካርድ #በመጀመሪያ ወደ አለም ብቅ ያለው በፈረንጆቹ አቆጣጠር በ1995 ሲሆን ይሄውም PC Card (PCMAIA) የሚል ስያሜ ነበራቸው፡፡ እነዚህ የመጀመሪያዎቹ ሚሞሪዎች አሁን በስፋት ተሰራጭተው ከሚገኙ ሚሞሪዎች በመጠን ከፍ ያሉ ሲሆን መረጃ የመያዝ አቅማቸውም በጣም አነስተኛ ነበር፡፡

◽️ በአሁኑ ወቅት እነዚህ ቀደምት ሚሞሪዎች በስፋት እያገለገሉ ያሉት በእንዱስትሪያል አፕልኬሽኖችና እንደ ሞደም ያሉ ኤሌክትሪካል ዲቫይሶችን ለማገናኘት ብቻ ነው፡፡ አብዛሃኞቹ ሚሞሪ ካርዶች መረጃዎችን እንደገና መላልሶ ማጥፋትና መጫን የሚያስችሉ ሲሆን መረጃዎችንም የሚይዙት ያለምንም ፓዎር ነው፡፡

◽️ ከአመታት በኋላ መሻሻሎችን በማሳየት የተላየዩ ሚሞሪዎች ገበያውን መቀላቀል ጀመሩ በተለይ ከመጀመሪያዎቹ PC Card በመጠን አነስ ያሉና መረጃ የመያዝ አቀማቸው ከፍ ያሉ በመሆናቸው ተቀባይነት ለማገኘት ብዙ ጊዜ አልፈጀባቸውም፡፡ ከነዚህም ውስጥም Compact Flash, Smart Media, እና Miniature Card ይገኝበታል፡፡

◽️ በ2001 (እ.ኤ.አ) Smart Media ሚሞሪ ካርድ 50% የዲጅታል ካሜራ ገበያውን ተቆጣጥሮ ነበር፡፡ Compact Flash, የተባለው የሚሞሪ ካርድ አይነት ደግሞ በአብዛኛው የፕሮፌሽናል ዲጅታል ካሜራዎች ላይ ነግሶ ነበር፡፡ እነዚህ የሚሞሪ ካርድ አይነቶች ተፈላጊነታቸው ጥያቄ ውስጥ የገባው በ2010 (እ.ኤ.አ) Micro SD ሚሞሪ ካርዶች መምጣታቸውን ተከትሎ ሲሆን በብዙ የሞባይል ብራንዶች ላይ እና ታብሌቶች ላይ በመገጠም ተፈላጊነታቸው በጣም ሊንር ችሏል፡፡

◽️ እስከ 2010 (እ.ኤ.አ) የሶኒ ካምፓኒ ለምርቶቹ ሚሞሪ እስቲክን ብቻ ይጠቀም ነበር በተመሳሳይ ታዋቂው የዲጅታል ካሜራዎች አምራች Olympus ኩባንያ sd CARD ብቻ የሚጠቀሙ ካሜራዎችን ያመርት የነበረ ሲሆን በኋላ ላይ ግን ሶኒም ሆነ ኦሎምፐስ በምርቶቻቸው ላይ SD MEMORY CARD እንደተጨማሪ የሚያስገቡ ካሜራዎችን ማምረት ግድ ብሏቸዋል፡፡

◽️ አሁን ላይ በብዛት የምንጠቀምባቸው Micro SD ሚሞሪ ካርድ 1.4 mm ቲክነስ ያላቸው ሲሆን በቅርቡ ይፋ በተደረገው መረጃ መሰረት እስከ 1 TB ወይም 1000 GB መረጃን የመሸከም አቅም እንዲኖራቸው ተደርጎ ለመስራት ተችሏል፡፡ ልብ በሉ የመጀመሪያዎቹ ሚሞሪ ካርዶች መረጃ የመሸከም አቅም 32 MB ነበረ ይህ ማለት ከ30 ፎቶዎች በላይ የመያዝ አቅሙ ያልነበረው ነው፡፡ ለ25 አመታት የፍላሽ ስቶሬጅ (Flash Storage) ገበያውን እየመራ ያለው San የተባለው እውቅ ካንፓኒ አሁን ላይ ባለው ቴክኖሎጂ 128 GB SDXC Memory Card (1.4 mm) ማምረቱን ያስታወቀ ሲሆን መረጃን በስሌት ለማስርዳት ያህል አዲሱ ሜሞሪ፡-
🔳16 ሰዓት HD ቪድዮዎች
🔊7500 ሙዚቃዎችን
🔲3200 ፎቶዎችን
🔽 ከ125 በላይ አፕልኬሽኖችንም በዛች ጉደኛ SDXC ሚሞሪ ካርድ (1.4mm) ከላይ የተጠቀሱትን ሚዲያ ፋይሎች በሙሉ በአንድ ላይ ማስቀመጥ ተችሏል ይለናል፡፡
ከወደዱት ለወዳጅዎ #ያጋሩ

Read more 👇👇👇
https://en.m.wikipedia.org/wiki/Memory_card
✅ኢንተርኔት_ስንጠቀም_የዳታ_ለመቆጠብ ከስር ያሉትን ዘዴዎች መጠቀም ትችላላቹ
❇️ጠቅላላ_የስልክ_ዳታን_ለመቆጠብ

❶ #setting ይጫኑ
⓶ #connection ይጫኑ
⓷ #data_usage ይጫኑ
⓸ #Data Saver off የነበረውን On አድርጉት።
~~~~~~~\\//~~~~~~~~~~~~
✅ አፖች_ላይ_ዳታን_ለመቆጠብ
እነዚህን መንገዶች ተጠቀሙ።
♻️Telegram_ላይ_ዳታን_ለመቆጠብ
❶ #Telegram ይክፈቱ
👇
❷ #setting ይጫኑ
👇
❸ #data_and_storage ይጫኑ
👇
❹ #when_using_mobile_data ይጫኑ
👇
❺ ራይት(✔) የተደረጉትን በሙሉ ያጥፉት

#Facebook_Lite_ላይ_ዳታን_ለመቆጠብ
❶ #facebook_lite ይክፈቱ
👇
❷ #setting ይጫኑ
👇
❸ #Data_Usage ይጫኑ
👇
❹ #data_saverን_on ያርጉት

✳️WhatsApp_ላይ_ዳታን_ለመቆጠብ
❶ #whatsappን ይክፈቱ
👇
❷ #option ወይም --- ከላይ እነዚህን ሶስት ነጠብጣብ ይጫኑ
👇
❸ #settingን ይጫኑ
👇
❹ #data_and_storage_usage ን ይጫኑ
👇
❺ #whan_using_mobile_data ን ይጫኑ
👇
❻ ራይት(✔) የተደረጉትን በሙሉ ያጥፉት

🔰Messenger_ላይ_ዳታን_ለመቆጠብ
❶ #Messenger ን ይክፈቱ
👇
❷ #setting ይጫኑ
👇
❸ #Data_saver ይጫኑ
👇
❹ #data_saverን on ያርጉት
⏺ በYouTube channel ጥሩ ጥሩ ትምህርታዊ ቪዲዮችን ይከታተሉ።
የ YouTube ቻናል ሊንክ 👇👇👇
https://www.youtube.com/channel/UCZBIP6PqUdmmagdTjbyp_AQ
⏺ በቴሌግራም ቻናሌ ጥሩ ጥሩ ትምህርታ አዘል መረጃዎችን ያግኛሉ 👇👇👇👇👇 https://t.me/MuhammedComputerTechnology
#ይነበብ
ውድ የ Muhammed Computer Technology የቴሌግራም ቻናል ተከታታዮች። እንደሚታወቀው በፌስቡክና በቴሌግራም ምርጥ አስተማሪ የቴክኖሎጂ መረጃዎችን እያደረስኳችሁ እገኛለሁ።
ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ደግሞ በYouTube ጠቃሚ ትምህርቶችን ለተመልካች እያቀረብኩ እገኛለህ። ስለሆነም በ4 ወራቶች ብቻ ❤ #5,900 በላይ #Subscribers ማግኘት የቻለ ተወዳጅ ቻናል ሁኗል ስለሆነም በYouTube በምለቀቃቸው Vedios ጠቃሚና አስተማሪ ሰልሆኑ #Subscribe በማድረግ #ይማሩ #ይወቁ
#በቅንነት ሼር አድርጉልኝ!
ያቀቁትን ማሳወቅ የተማሩትን ማስተማር ብልህነት ነው።
YouTube ቻናል ሊንክ
👇👇👇

https://www.youtube.com/channel/UCZBIP6PqUdmmagdTjbyp_AQ
#ይማሩ #ይወቁ
ፔሮል በማይክሮሶፍት ኤክሴል MS-Excel እንዴት መስራት አንችላለን ክፍል 2 Payroll Part 2
👇👇👇👇

https://youtu.be/AsQhn_ua3Cg

✅ ፔሮል በማይክሮሶፍት ኤክሴል MS-Excel መስራት አንችላለን? ክፍል -1 How to make payroll using Microsoft Excel in amharic
👇👇👇👇👇

https://youtu.be/rNcfrxbTyxo
አንድሮይድ ስማርት ስልካችንን እንዴት ማሻሻል /update/ ማድረግ ይቻላል?
በስማርት ስልኮች ኦፕሬቲንግ ሲስተም ገበያ ውስጥ አንድሮይድ ቀዳሚውን ስፍራ ይይዛል።
የአንድሮይድ ኦፕሬቲንግ ሲስተም ባለቤት የሆነው ጎግል፥ በየጊዜው በአንድሮይድ ላይ የተለያዩ ማሻሻያዎችን ያደርጋል።
በዚሁ ጊዜም የተሻለ አገልግሎት ለማግኘት የአንድሮይድ ኦፕሬቲንግ ሲስተማችንን ማሻሻል /update/ ማድረግ ይጠበቅብናል።
➚አንድሮይድ ኦፕሬቲንግ ሲስተምን በየጊዜው ለምን ማሻሻል ያስፈልጋል…?
↬የስልካችን የመስራት አቅም እንዲጨምር
↬የስልካችን እድሜምን ለማርዘም
↬አዳዲስ ማሻሻያዎችን ለመጠቀም
↬የሰልካችንን ደህንነት ለመጠበውቅ
↬ስልካችንን ከተለያዩ የቫይረስ ጥቃት ለመከላከል
↬የስልካችን ባትሪ የቆይታ እንድሜን ለማርዘም
➠አንድሮይድ ኦፕሬቲንግ ሲስተም ለማሻሻል /update/ ለማድረግ መከተል ያለብን ቅደም ተከተል..
1. የአንድሮይድ ስልካችን መተግበሪያ ውስጥ በመግባት ሴቲንግስ /Settings/ መክፈት
2. ከሚመጡልን ዝርዝር ውስጥ “About phone” ወይም ሌላ ተመሳሳይ አማራጭ መክፈት
3. ከዛም “System Updates” ወይም “Software Update” የሚል አማራጭ የሚመጣልን ሲሆን፥ እዛ ውስጥ በመግባት ማሻሻል እንችላለን።
4. “System Updates” በምንከፍትበት ጊዜ በርከት ያሉ አማራጮች የሚመጡ ከሆነ “Check for updates now”፣ “Software update check” ወይም ሌሎች ተመሳሳይ አማራጮች ውስጥ በመግባት የስማርት ስልካችን ኦፕሬቲንግ ሲስተምን ማሻሻል /update/ ማድረግ እንችላላን።
ማስጠንቀቂያ፦
❗️በዳታ ብዙ ብር ሊቆርጥብቆት ስለሚችል ይጠንቀቁ በWiFi Update ቢያደርጉት ይመረጣል።
❗️በቅድሚያ ስልክዎትን በበቂ ሁኔታ ቻርጅ ያድርጉ Update እያደረገ ባለበት ሁኔታ ቻርጅ ቢዘጋ ስልኮ አደጋ ውጥ ሊገባ ይችላል።
share በማድረግ ሌሎችንም ያሳውቁ!!
⏺ በYouTube channel ጥሩ ጥሩ ትምህርታዊ ቪዲዮችን ይከታተሉ።
የ YouTube ቻናል ሊንክ 👇👇👇
https://www.youtube.com/channel/UCZBIP6PqUdmmagdTjbyp_AQ
❤1
ስልካችሁ ላይ አፕልኬሽን ስትከፍቱ :⬇️
✔This Application Stopped Working‼️
✔Crashing‼️
✔Won’t open‼️
✔Won’t respond‼️
✔Isn’t working properly‼️

እያለ ላስቸገራችሁ መፍትሔ⬇️

➊.Restart እና Update ይሞክሩ፤ እንደዚህ ስታደርጉ በአብዛኛው ጊዜ ይስተካከላል።

🚫ስልካችሁን #Restart አድርጉት።

🚫 Setting➡️ Software Update ውስጥ ገብታችሁ የስልካችሁን📲 Operating System #Update አድርጉ።

🚫 Playstore ላይ ገብታችሁ አፑን #Update አድርጉት።

➋.Update Google Play Services

🚫 ስትከፍቱ #Update አድርጉት ይላችኋል።

❸. አፑን የማትጠቀሙበት ከሆነ Setting ውስጥ ገብታችሁ #Forced_Stop አድርጉት።

🚫 System App ካልሆነ #Uninstall❌ ያድርጉት።

❹. Clear App and Cache ይሞክሩ።

🚫 Setting➡ Manage apps➡ ያስቸገራችሁን አፕ➡Clear Data and Clear Cache.

❺. እኔ እንዳየሁት ከሆነ ከላይ በነገርኳችሁ መፍትሔ 95% ስልኮች📲 ይስተካከላሉ👍 ለተቀሩት ስልኮች #Hard_Reset መሞከር ይቻላል
✅የምፈልገውን #አፕ ከ PlayStore እያገኘሁ አይደለም!

''አብዛኛው ጊዜ #Search አርጌ ስፈልግ አይመጣም''

✅#Update ያላቸው አፕሊኬሽኖች #PlayStore ላይ #ማደስ አልቻልኩም!

✅PlayStore ጭራሹም #Download ማድረግ አቁሟል መሰል እምቢ አለኝ!

❓መሰል የሆኑ ጥያቄዎች በተለያዩ አጋጣሚዎች ይደርሱናል❕

✳️በዚህም ላይ ልዩ የሆነ ጥናት አርገን #ትክክለኛ የሆነ መልስ ይዘን እነሆ ለናንተ ልናካፍላችሁ ወደድን!

🛃አብዛኛው ጊዜ የምንፈልገውን አፕ ከ #PlayStore ላይ ለመጫን ፈልገን ነገር ግን አይመጣልንም! ይህ ችግር የሚፈጠረው የስልካችን #Version ከመተግበሪያው ጋር የማይሄድ ሲሆን ነው! ይህ ጥያቄ ምላሽ ያገኘ ይመስለኛል!

🛃 #Update ያላቸው ነገር ግን #PlayStore ላይ #Update የሚል ነገር አይመጣም! ይሄ ሙሉ ለሙሉ የስልኩ ችግር ነው! ያረጀ ነው አልያም #ሶፍትዌሩ የድሮ ነው! አዳዲስ ነገራቶች መቀበል አይችልም!

🛃 #Download አያረግም ''Waiting For Network'' ብሎ ይቀራል! ይህ ቀለል ያሉ አማራጮችን እንጠቀም
✔️ #PlayStore የምንጠቀምበት #አካውንት (Gmail) መቀየር!
✔️ የስልካችን #Settings (Apk Manager) ውስጥ በመግባት #ClearData ማድረግ!
✔️Google Play Service #Update ማድረግ ቀጥታ #VidMate, #Aptiude, #ApkPure ላይ ታገኙታላችሁ!
✔️ስልክዎን #Restart አርጋችሁ መሞከር!
💠በነዚህ መንገዶች ካልተስተካከለ #ስልክዎን #Restore አርገው ይሞክሩት! ምናልባትም ሙሉ ለሙሉ ይሰራ ይሆናል!
ያለ ፓወር ግእዝ ሶፍትዌር (አፕሊኬሽን) አማርኛ መፃፍ ይቻላል በዴስክቶፕም በላፕቶፕም እንዴት ለሚለዉ
ከታች እስቴፑን ተመልከቱ

በመጀመሪያ
1ኛ ፦start ላይ እንገባለን በመቀጠልም 2ኛ ፦control panel የምለዉን እንነካለን ከዛ ደግሞ
3ኛ ፦ date and language የምለዉን አማራጭ እንነካለን ከዛ
4ኛ ፦change keyboard language የምለዉን እንነካለን በመቀጠልም ብዙ ቋንቋዎች ይመጣሉ ከነዛም
5ኛ ፦ Amhric Ethiopia የምለውን አማራጭ ትመርጣላችሁ ከዛ አማርኛ መፃፍ ትችላላችሁ ።
6ኛ
በጣም ቀላል ነዉ
ደመናን ማዝነብ (cloud seeding)
************************

ደመናን ማዝነብ እየተለመደ የመጣ የሳይንስ ግኝት ነው። ደመና ከመሬት ከፍ ብሎ በሚገኝ ከባቢ ላይ በትነት መልክ የሚገኝ የውኃ ስብስብ ቅንጣት ነው። ይህ በሚሊዮን የሚቆጠር ወደዝናብ ያልተቀየረ ነጠብጣብ/ቅንጣት በንጥረ ነገር ርጭት አማካኝነት ከነጠብጣቡ ከፍ ብሎ እንዲያድግና ወደ መሬት ዝናብ ሆኖ እንዲወርድ ማድረግ ይቻላል። ይህ ነው ደመና ማዝነብ (cloud seeding) የሚባለው።

ደመና ያለበት አካባቢ ላይ በአውሮፕላን የኬሚካል ርጭት ይደረጋል። ንጥረ ነገሩ (ሲልቨር አይወዳይድና ፖታሺየም አይወዳይድ) ተበታትኖ የነበረው ደመና ላይ ሲያርፍ ደመናው እንዲሰበሰብና ወፈር ወዳለ የውኃ እንክብል እንዲቀየር ያደርገዋል። ይህ የውኃ እንክብል በመሬት ስበት አማካኝነት ወደ መሬት እንዲዘነብ ይገደዳል።

የንጥረ ነገር ርጭቱ ሀገራት እንዳላቸው አቅም ከመሬት ወደ ደመናው መርጭትም የሚቻልባቸው ሁኔታዎች አሉ።

በሮኬት መልክ መተኮስ የሚቻል ሲሆን በሰው አልባ አውሮፕላኖችም ርጭት ማድረግ ይቻላል። የተለመደው ግን በአውሮፕላን ከደመናው በላይ አልያም በታች እየበረሩ መርጭት ነው።

ኢትዮጵያ ሰሞኑን የሞከረችው በአውሮፕላን የሚረጨውን ሲሆን ከደመናው ስር በመሆን ንጥረ ነገሩን በአውሮፕላን የሚረጭበት ነው።

የተለያዩ የደመና አይነቶች ሲኖሩ ይህኛው ደመና የሚስብ/የሚነፍስ ንፋስ ስላለው ንጥረ ነገሩ ከስሩ ሲረጭ ከደመናው ጋር ወስዶ ይቀላቅለዋል።

ሁለተኛው አማራጭ ደግሞ ከመሬት ላይ በሚተከል "ግራውንድ ጀነሬተር" አማካኝነት ዝናብ ማዝነብ ሲሆን እዚህ ላይም ኢትዮጵያ ሥራዎችን እየሠራች ነው።

ንጥረ ነገሩን የሚረጭ "ግራውንድ ጄነሬተር" እንጦጦ ላይ ተከላ እያካሄደች ነው። ይህኛው አሠራር ተራራማ ቦታዎች ላይ ተተክሎ ከመሬት ቅርብ ወደ ሆነ ደመና ንጥረ ነገር እንዲረጭ የሚደረግበት ነው። ቁጥጥሩ ደግሞ ከሜትዮሮሎጂ ኤጀንሲ ባለ ማዕከል ላይ ይደረጋል።

ይህንን ሥራ ለመሥራት ኢትዮጵያ የተጠቀመችው ንጥረ ነገር በዋጋው ዝቅተኛ የሆነውን ሶዲየም ክሎራይድ እና ፖታሺየም ክሎራይድ ድብልቅ (ሃይድሮስኮፒክስ) የተሰኘውን ንጥረ ነገር ነው።

ይሄ ቴክኖሎጂ በተፈጥሮ የሚገኝ ደመናም ይፈልጋል። አየር ላይ ደመና ከሌለ ዝናብ ማመንጨት አይቻልም። ቴክኖሎጂው ደመና መፍጠር የሚያስችል አቅም ላይ አልደረሰም።

ይህንን ከደመና ዝናብ የማመንጨት ቴክኖሎጂ እስራኤል፣ ቻይና እና ዩናይትድ ዓረብ ኤምሬትስ በተለያየ መልኩ ይጠቀሙበታል። በርሃማ ቦታዎቻቸውን ማልማትም ችለዋል።

ከሀገራት በተጨማሪ የተለያዩ ተቋማትም ደመናን የማዝነብ ዘዴ እንደሚጠቀሙ ይነገራል።

የሃይድሮ ፓወር ኩባንያዎች በበጋ ወቅት የሚያጋጥመውን የውኃ እጥረት ለመቀነስ፤ የወይን አምራች ድርጅቶች የምርት ብክለት እንዳያጋጥም ለማድረግ፤ እንዲሁም የኢንሹራንስ ኩባንያዎች የሚደርሱ አደጋዎችን ለመቀነስ እንደተጠቀሙበት መረጃዎች ያሳያሉ።

ኢትዮጵያ ይህንን ቴክኖሎጂ ጥቅም ላይ ስታውል ዩናይትድ ዓረብ ኤምሬትስ የተለያዩ ድጋፎን አድርጋላታልች።

የኢትዮጵያ ባለሙያዎችም በሰፊው ተሳትፈውበታል። ከበረራ ጋር በተያያዘም የኢፌዴሪ አየር ኃይል የጥገና ባለሙያዎች እና አብራሪዎች ተሳትፈዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ያስጀመሩት እና የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር የሚመራው ይህ ሥራ የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት፣ የብሔራዊ ሜትዮሮሎጂ ኤጀንሲ፣ የተፋሰስ ባለሥልጣን፣ የሰው ሠራሽ አስተውሎ ማዕከል፣ የቴክኖሎጂ እና ኢኖቬሽን ኢንስቲትዩት፣ የኢንፎርሜን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ፣ የስፔስ ሳይንስ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት እና ከግሉ ዘርፍ ድሮን ላይ የሚሠሩ ቡድኖች ተሳትፈዋል።

ኢትዮጵያ አሁን ዓለም ላይ ያለውን ቴክኖሎጂ መጠቀም ብቻ ሳይሆን መፍጠርንም መማር አለባት የሚሉት የኤኖቬሽናን ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታ አህመዲን መሀመድ (ፒ.ኤች.ዲ) ኢትዮጵያም ይህንን ቴክኖሎጂ በረሃማ ቦታዎችን ለማልማት በሰፊው ጥቅም ላይ ታውለዋለች ብለዋል።

ኢትዮጵያ ከዚህ ቀደም በረሃማና ከፍተኛ የውኃ እጥረት ያለባቸው አካባቢዎችን ለማልማት የሚያስችሉ አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን ወደ ሀገር ውስጥ የማስገባት ሂደት በቅርቡ እንደሚጀመር ይፋ አድርጋ ነበር።
ŠEBC
👍2👏1