Muhammed Computer Technology (MCT)
37.4K subscribers
530 photos
7 videos
254 files
916 links
🔴አድራሻ:-
✅ ስ.ቁ: 0929273364
✅ ዌብሳይት www.mctplc.com
✅ቴሌግራም አካውንት: https://t.me/mctplc
✅ email: mct16plc@gmail.com
✅ ቲክቶክ አካውንት tiktok.com/@mctplc
Download Telegram
እንዴት አድርገን በስልካችን በHTML ካልኩሌተር ማስራት እንችላለን ከዚህ በታች ያለውን ኮድ በመጠቀም እንዴት ካልኩሌተር ማእራት እንደምንችል እንመለከታለን
መጀመሪያ ከgoogle play store HTML Editor እናወርዳለን በመቀጠል ፎቶውን በመመልከት ቅደም ተከተል step በመከተል ከኮምፒውተር በተጨማሪ በስልካችን መጠቀም እንደምንችልና በቀላሉ መማር እንችላለን
<h1>SIMPME HTML CALCULATOR </h1>
<form name="Calculator">
<table border="2" align="center" cellpadding="10" cellspacing="10" bgcolor="999999">
<tr>
<td>
<input type="text" name="Input" Size="30">
<br>
</td>
</tr>
<tr>
<td>
<input type="button" name="one" style="font-size:25px" value=" 1 " OnClick="Calculator.Input.value += '1'">
<input type="button" name="two" style="font-size:25px" value=" 2 " OnCLick="Calculator.Input.value += '2'">
<input type="button" name="three" style="font-size:25px" value=" 3 " OnClick="Calculator.Input.value += '3'">
<input type="button" name="add" style="font-size:25px" value=" + " OnClick="Calculator.Input.value += ' + '">
<br>
<input type="button" name="four" style="font-size:25px" value=" 4 " OnClick="Calculator.Input.value += '4'">
<input type="button" name="five" style="font-size:25px" value=" 5 " OnCLick="Calculator.Input.value += '5'">
<input type="button" name="six" style="font-size:25px" value=" 6 " OnClick="Calculator.Input.value += '6'">
<input type="button" name="minus" style="font-size:25px" value=" - " OnClick="Calculator.Input.value += ' - '">
<br>
<input type="button" name="seven" style="font-size:25px" value=" 7 " OnClick="Calculator.Input.value += '7'">
<input type="button" name="eight" style="font-size:25px" value=" 8 " OnCLick="Calculator.Input.value += '8'">
<input type="button" name="nine" style="font-size:25px" value=" 9 " OnClick="Calculator.Input.value += '9'">
<input type="button" name="mul" style="font-size:25px" value=" * " OnClick="Calculator.Input.value += ' * '">
<br>
<input type="button" name="clear" style="font-size:25px" value=" c " OnClick="Calculator.Input.value = ''">
<input type="button" name="zero" style="font-size:25px" value=" 0 " OnClick="Calculator.Input.value += '0'">
<input type="button" name="DoIt" style="font-size:25px" value=" = " OnClick="Calculator.Input.value = eval(Calculator.Input.value)">
<input type="button" name="div" style="font-size:25px" value=" / " OnClick="Calculator.Input.value += ' / '">
<br>
</td>
</tr>
</table>
</form>
<h2>muhammed Amin</h2>
#የተማሩትን_ማስተማር #ያወቁትን_ማሳወቅ #ብልህነት ነው
#ለሰው መልካሙን እንጅ መጥፎውን አትመኝ🙏
ስለኮምፒውተርና ቴክኖሎጅ ያለዎትን እውቀት ያሳድጉ በተጨማሪም በቴሌግራሜ ቻናል ምርጥ ምርጥ ስለኮምፒውተር የምለቃቸውን መረጃዎችን ለመከታተል እንዲያመችዎ ይህንን ይጫኑ https://t.me/MuhammedComputerTechnology በቴሌግራም መከታተል ትችላላችሁ
ሼር ማድረጋችሁን አትርሱ በፍጥነት መረጃ እንዲደርሳችሁ
Like & share this page
#ሼር_ያድርጉ
#ፔጄን_ላይክ ማድረግዎን አይርሱ
👍3
Muhammed Computer Technology (MCT) pinned «እንዴት አድርገን በስልካችን በHTML ካልኩሌተር ማስራት እንችላለን ከዚህ በታች ያለውን ኮድ በመጠቀም እንዴት ካልኩሌተር ማእራት እንደምንችል እንመለከታለን መጀመሪያ ከgoogle play store HTML Editor እናወርዳለን በመቀጠል ፎቶውን በመመልከት ቅደም ተከተል step በመከተል ከኮምፒውተር በተጨማሪ በስልካችን መጠቀም እንደምንችልና በቀላሉ መማር እንችላለን <h1>SIMPME HTML CALCULATOR…»
የኮምፒውተር ቫይረስ ሰለባ መሆንዎን እንዴት ማወቅ ይችላሉ
1 ድንገተኛ የሆነ የአገልግሎት መቋረጥ፡ ከዚህ ቀደም ድንገተኛ የሆነ የአገልግሎት መቆራረጥ አጋጥሞዎት በተደጋጋሚ ሰማያዊ ቀለም ያለው ገጽታ የሚያሳይ ከሆነ ኮምፒውተርዎ አደጋ ላይ መውደቁን ጠቋሚ ነው፡፡
2. የኮምፒውተር ስርዓት ማዝገም /Slow System/፡ በሲስተምዎ ላይ ብዙ ቦታ የማይፈልጉ መተግበሪያዎችን(applications)ሳይጠቀሙ የኮምፒውተር ስርዓቱ ዝግ ማለት የኮምፒውተርዎ ስርዓት በቫይረስ መጠቃትን ሊያመለክት ይችላል።
3. ከልክ ያለፈ የሃርድ ድራይቭ እንቅስቃሴ( 3. Excessive Hard Drive Activity) ምንም እንኳን ኮምፒተርዎ ስራ እየሰራ ባይሆንም ጥቂት የማይባሉ የሃርድ ድራይቭ እንቅስቃሴን ካስተዋሉ ይህ ምናልባትም በቫይረስ ስለመጠቃትዎ የማስጠንቀቂያ ምልክት ሊሆን ይችላል፡፡
4. ያልተለመዱ የዊንዶው ምልክቶች ሲስተዋሉ፡ ኮምፒውተርዎን በሚከፍቱበት ወቅት እንግዳ የሆኑ ነገሮች ብቅ ካሉ እና በተለይ በኮምፒተርዎ ላይ የተለያዩ ድራይቭዎች /drive/ ከጠፉ ችግር መፈጠሩን አመላካች ነው፡፡
5. የተለዩ መልእክቶች፡ በተለያዩ መልእክቶች ወደ እርስዎ የመልእክት መለዋወጫዎች ሲገቡ እና ፋይሎችን በሚከፍቱበት ጊዜ ካልተከፈተ የተፈጠረ ችግር አለ ማለት ነው፡፡
6. መጥፎ የፕሮግራም እንቅስቃሴ፡- ፕሮግራሞችዎ ከጠፉ ፣ ከተበላሹ ፣ ወይም ያለ እርስዎ ፍቃድ እራሳቸውን በራሳቸው መክፈት ከጀመሩ ፣ እንዲሁም ያለ እርስዎ ትእዛዝ ኢንተርኔት ለመድረስ እየሞከረ መሆኑን የሚገልጽ ማሳሰቢያ ከደረሰዎ ይህም የቫይረስ ሰለባ መሆንዎን ጠቋሚ ነው፡፡
7. የዘፈቀደ አውታረ-መረብ እንቅስቃሴ /Random Network Activity/ ምንም ጉልህ የሆኑ ፕሮግራሞችን ወደስራ ሳያስገቡ አልያም ከፍተኛ የበይነ-መረብ ዳታን በማይጠቀሙበት ጊዜ የእርስዎ ራውተር በቋሚነት ብልጭ ድርግም የሚል ምልክት የሚያሳይ ከሆነ ፣ የሆነ ችግር መፈጠሩን አመላካች ነው፡፡
8. የተሳሳቱ የኢሜይል መልእክቶች፡- እርስዎ ለማንም ኢ-ሜይል ባይልኩም ከእርስዎ የኢሜይል አድራሻ ለእርስዎ ኢ-ሜይል መልእክት ከደረስዎ የእርስዎ ስርዓተ ኮምፒውተር ተጥሷል (ወይም የኢ-ሜይል የይለፍ ቃልዎ እንደተሰረቀ የሚያሳይ ጠንካራ ማስረጃ ነው)
9. የአይፒ አደራሻዎ በበይነመረብ ፕሮቶኮል አድራሻ በጥቁር መዝገብ ከተቀመጠ/Blacklisted IP Address/ የእርስዎ የአይፒ አድራሻ በጥቁር መዝገብ መያዙን የሚገልጽ ማስታወቂያ ከደረሰዎት ኮምፒተርዎ በጥሩ ሁኔታ ላይ አለመሆኑን የሚያሳይ ምልክት፡፡
10. ያልተጠበቀ የፀረ-ቫይረስ አገልግሎት መቆም፡- ብዙ ተንኮል-አዘል ሶፍትዌር /malware/ ፕሮግራሞች ፀረ-ቫይረስ አገልግሎት የማስተጓጎል ወይም ከጥቅም ውጪ የማድረግ ተልእኮ በመያዝ የተቀየሱ ናቸው፡፡ ስለሆነም የፀረ-ቫይረስ ስርዓትዎ በድንገት የማይሠራ ከሆነ የኮምፒውተር ስርዓቱ ትልቅ ችግር ላይ መውደቁን የሚያሳይ በመሆኑ የመፍትሄ እርምጃዎችን መውሰድ የግድ ይላል፡፡
#የተማሩትን_ማስተማር #ያወቁትን_ማሳወቅ #ብልህነት ነው
#ለሰው መልካሙን እንጅ መጥፎውን አትመኝ🙏
ስለኮምፒውተርና ቴክኖሎጅ ያለዎትን እውቀት ያሳድጉ በተጨማሪም በቴሌግራሜ ቻናል ምርጥ ምርጥ ስለኮምፒውተር የምለቃቸውን መረጃዎችን ለመከታተል እንዲያመችዎ ይህንን ይጫኑ https://t.me/MuhammedComputerTechnology በቴሌግራም መከታተል ትችላላችሁ
በፌስቡክ ገጻችን https://m.facebook.com/mameamin.6te.net
ሼር ማድረጋችሁን አትርሱ በፍጥነት መረጃ እንዲደርሳችሁ
Like & share this page
#ሼር_ያድርጉ
#ፔጄን_ላይክ ማድረግዎን አይርሱ
Muhammed Computer Technology (MCT) pinned «የኮምፒውተር ቫይረስ ሰለባ መሆንዎን እንዴት ማወቅ ይችላሉ 1 ድንገተኛ የሆነ የአገልግሎት መቋረጥ፡ ከዚህ ቀደም ድንገተኛ የሆነ የአገልግሎት መቆራረጥ አጋጥሞዎት በተደጋጋሚ ሰማያዊ ቀለም ያለው ገጽታ የሚያሳይ ከሆነ ኮምፒውተርዎ አደጋ ላይ መውደቁን ጠቋሚ ነው፡፡ 2. የኮምፒውተር ስርዓት ማዝገም /Slow System/፡ በሲስተምዎ ላይ ብዙ ቦታ የማይፈልጉ መተግበሪያዎችን(applications)ሳይጠቀሙ የኮምፒውተር…»
በኮምፒውተራችሁ ላይ ቢጫ ፎልደር ማየት ሰልችቶችሁል?
የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ተከታዮች በየቤታችሁ፣ በስራ ቦታ፣ በት/ቤ እንደሁም በተለያዮ ቦታዎች የምትጠቀሙበት ኮምፒውተር ሁሉንም ፎልደሮች የሚያሳያችሁ በዲፎልት በቢጫ ከለር በመሆኑ የምትፈልጉትን ፋይል በፍጥነት ላለማግኘት ስንተቻችሁን አበሳጭቶችሁል? ሁሌ አንድ አይነት ከለር ማየት ሰልችቶችሁል? ማክሮሶፍት ዊንዶ የምንጠቀምባቸውን በሁሉም ቨርዥን ኦፕሬቲንግ ሲስተም ላይ የምንተቀምባቸውን ፎልደሮች በዲፎልት በቢጫ ከለር ብቻ የሚሰጠን ሲሆን ፎልደሮችን እንደሚመቸን እና እንደሚቀለን አድርገን ፋይሎቻችን የምናስቀምጠበት ፎልደሮች በኮምፒውተሩ ዴስክቶፕ፣ ዶክመንት፣ በሲ እና ዲ ላይ ላሉት በቀለሉ በመስጠት እንዲያስችለን በሶስተኛ ወገን የተሰራ ነፃ ሶፍትዌር አለ
1. ሶፍትዌሩን ዳውንሎድ አድረገን እንጫን http://www.softorino.co
m/foldercolorizer/how-to-use/
2. ከለር ለመቀየር የምንፈልገው ፎልደር ላይ ራይት ክሊክ
3. Colorizer የሚለውን እንምረጥ እና በሱ ትይዮ ከሚሰጠን የተለያዮ ከለሮች ለመረጥነው ፎልደር እንምረጥ
4. ኮምፒውተሩን ሪፍሬሽ እናድርግ በዚህ ጊዜ የመረጥነው ከለር ፎልደሩን ይቀይራል
ማስታወሻ
• የቀየርነውን ፎልደር ከለር በፊት ወደነበረበት መመለስ እንችላለን
የተቀየረው ፎልደር ላይ ራይት ክሊክ - colorizer - ሪስቶር ኦሪጂናል ከለር የሚለውን እንምረጥ
Share your knowledge free for millions ያለዎትን እና ያገኙትን እውቀት በነፃ ለሚሊዎኖች ያካፍሉ/ያድርሱ

#የተማሩትን_ማስተማር #ያወቁትን_ማሳወቅ #ብልህነት ነው
#ለሰው መልካሙን እንጅ መጥፎውን አትመኝ🙏
ስለኮምፒውተርና ቴክኖሎጅ ያለዎትን እውቀት ያሳድጉ በተጨማሪም በቴሌግራሜ ቻናል ምርጥ ምርጥ ስለኮምፒውተር የምለቃቸውን መረጃዎችን ለመከታተል እንዲያመችዎ ይህንን ይጫኑ https://t.me/MuhammedComputerTechnology በቴሌግራም መከታተል ትችላላችሁ
ሼር ማድረጋችሁን አትርሱ በፍጥነት መረጃ እንዲደርሳችሁ
Like & share this page
#ሼር_ያድርጉ
#ፔጄን_ላይክ ማድረግዎን አይርሱ
👍1
Muhammed Computer Technology (MCT) pinned «በኮምፒውተራችሁ ላይ ቢጫ ፎልደር ማየት ሰልችቶችሁል? የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ተከታዮች በየቤታችሁ፣ በስራ ቦታ፣ በት/ቤ እንደሁም በተለያዮ ቦታዎች የምትጠቀሙበት ኮምፒውተር ሁሉንም ፎልደሮች የሚያሳያችሁ በዲፎልት በቢጫ ከለር በመሆኑ የምትፈልጉትን ፋይል በፍጥነት ላለማግኘት ስንተቻችሁን አበሳጭቶችሁል? ሁሌ አንድ አይነት ከለር ማየት ሰልችቶችሁል? ማክሮሶፍት ዊንዶ የምንጠቀምባቸውን በሁሉም ቨርዥን ኦፕሬቲንግ…»
ሪሞት ዴስክቶፕ ኮኔክሽን (Remote Desktop Connection)
ሪሞት ዴስክቶፕ ኮኔክሽን (Remote Desktop Connection) ማለት በአንድ አይነት ኔትወርክ ላይ የሆኑ ኮምፒውተርችን ወይም በኢንተርኔት የተያያዙ ኮምፒውተሮችን ከርቀት ሆኖ ከአንድ ኮምፒውተር ላይ ለመቆጣጠር የምንጠቀምበት የዊንዶ ኦፕሬቲንግ ሲስተም ላይ የምናገኘው ፕሮግራም ሲሆን ባለገመድና ገመድ አልባ ኔትወርክ ላይ እንጠቀምበታለን::
አንድ ሲስተም አድሚኒስትሬተር ሪሞትሊ ሆኖ ሌላ ኮምፒውተር ላይ በሪሞት ዴስክቶፕ በመግባት(በመጠቀም) ፋይሎችን ማዘዋወር፣ ዳውንሎድ ማድረግ፣ ሶፍትዌሮች ሲበላሹ ማስተካከል፣ ኢንስቶል(መጫን)ና ሶፍትዌሮችን ማጥፋት ይችላል፡፡ፕሮግራሙን ለመጠቀም በኔትወርኩ ውስጥ ያሉ ኮምፒውተሮች መከፈት ይኖርባቸዋል እንዲሁም ኔትወርክ ኮኔክሽን(ግንኙነት) መኖር አለበት በተጨማሪ ሪሞት ዴስክቶፕ ፕሮግራም በእያንዳንዱ ኮምፒውተር ላይ መከፈትና ኔትወርክ አክሰስ መፈቀድ ይኖርበታል ይሄን ለማድረግ የአድሚኒስትሬተር አካውንት ተጠቃሚ መሆን ይኖርበታል
ሪሞት ዴስክቶፕ ለመክፈት የምንከተለው ሂደት
1. ማይኮምፒውተር ላይ ራይት ክሊክ ፕሮፐርቲ
2. ሪሞት ዴስክቶፕ (Remote Desktop) ታብ
3. Allows users to connect remotely to this computer የሚለውን ሳጥን እንምረጥ
4. ሪሞትሊ ይህን ኮምፒውተር የሚጠቀሙትን ዩዘሮች(ተጠቃሚዎች) ሴሌክት ሪሞት ዩዘር የሚለውን ቁልፍ በመጫን በኔትወርካችን ውስጥ ያሉ ዩዘሮችን እንምረጥ
5. ኦኬ
ማስታወሻ
ሪሞት ዩዘር ተጠቃሚዎችን መምረጥ የግድ አስፈላጊ አይደለም በፈላጎታችን ለሴኩሪቲ የምነመርጠው ነው
ሪሞት ዴስክቶፕ ለመጠቀም የምንከተለው ሂደት(ስቴፕ)
1. ስታርት - ራን
2. በራን ሳጥን ላይ mstsc ብለን ኦኬ
ወይም
1. ስታርት
2. ኦል ፕሮግራምስ
3. አክሰሰሪስ
4. ኮምኒኬሽን
5. ሪሞት ዴስክቶፕ ኮኔክሽን
Share your knowledge free for millions ያለዎትን እና ያገኙትን እውቀት በነፃ ለሚሊዎኖች ያካፍሉ/ያድርሱ
#የተማሩትን_ማስተማር #ያወቁትን_ማሳወቅ #ብልህነት ነው
#ለሰው መልካሙን እንጅ መጥፎውን አትመኝ🙏
ስለኮምፒውተርና ቴክኖሎጅ ያለዎትን እውቀት ያሳድጉ በተጨማሪም በቴሌግራሜ ቻናል ምርጥ ምርጥ ስለኮምፒውተር የምለቃቸውን መረጃዎችን ለመከታተል እንዲያመችዎ ይህንን ይጫኑ https://t.me/MuhammedComputerTechnology በቴሌግራም መከታተል ትችላላችሁ
ሼር ማድረጋችሁን አትርሱ በፍጥነት መረጃ እንዲደርሳችሁ
Like & share this page
#ሼር_ያድርጉ
#ፔጄን_ላይክ ማድረግዎን አይርሱ
Muhammed Computer Technology (MCT) pinned «ሪሞት ዴስክቶፕ ኮኔክሽን (Remote Desktop Connection) ሪሞት ዴስክቶፕ ኮኔክሽን (Remote Desktop Connection) ማለት በአንድ አይነት ኔትወርክ ላይ የሆኑ ኮምፒውተርችን ወይም በኢንተርኔት የተያያዙ ኮምፒውተሮችን ከርቀት ሆኖ ከአንድ ኮምፒውተር ላይ ለመቆጣጠር የምንጠቀምበት የዊንዶ ኦፕሬቲንግ ሲስተም ላይ የምናገኘው ፕሮግራም ሲሆን ባለገመድና ገመድ አልባ ኔትወርክ ላይ እንጠቀምበታለን::…»
SD ሚሞሪ ካርድ
Secure Digital Card (SD card) ...በጣም የተለመደው የሚሞሪ አይነት ሲሆን በብዙ የዲጂታል ካሜራዎች ላይ የሚሰራ ነው፡፡ ኤስዲ ሚሞሪ ካርድ በአንድ አይነት የቅርጽ መጠን በ3 አይነት የመያዝ መጠን ተሰርቶ እናገኘዋለን፡፡
• በSD/ሴኪውር ዲጂታል ካርድ እስከ 2 ጊጋ ባይት ድረስ የመያዝ መጠን አለው
• በSDHC(ሴኪውር ዲጂታል ሃይ ካፓሲቲ ካርድ የመጨረሻ የመያዝ መጠኑ 32 ጂቢ ተደርጎ የተሰራ ነው፡፡
• በSDXC(ሴኪውር ዲጂታል ኤክስቴንድድ ካርድ) በጣም ከፍተኛ የመያዝ መጠን እና በፈጣን ፕሮሰሲን 2ቴራ ባይት ድረስ የመያዝ አቅም ኖሮት የተሰራ ነው፡፡
#የተማሩትን_ማስተማር #ያወቁትን_ማሳወቅ #ብልህነት ነው
#ለሰው መልካሙን እንጅ መጥፎውን አትመኝ🙏
ስለኮምፒውተርና ቴክኖሎጅ ያለዎትን እውቀት ያሳድጉ በተጨማሪም በቴሌግራሜ ቻናል ምርጥ ምርጥ ስለኮምፒውተር የምለቃቸውን መረጃዎችን ለመከታተል እንዲያመችዎ ይህንን ይጫኑ https://t.me/MuhammedComputerTechnology በቴሌግራም መከታተል ትችላላችሁ
ሼር ማድረጋችሁን አትርሱ በፍጥነት መረጃ እንዲደርሳችሁ
Like & share this page
#ሼር_ያድርጉ
#ፔጄን_ላይክ ማድረግዎን አይርሱ
❤2👍1
ብሎክ ቼይን ምንድነው? ቢትኮይንስ?
ብሎክቼን በሚሊየን የሚቆጠሩ የኮምፒውተር መረጃዎችን ባልተማከለ መልኩ የሚመዘግብ የብሎክ ጥርቅም የሖነ ቴክኖሎጂ ነው፡፡ ይኸ ቴክኖሎጂ በባንኮች እጅ የሚገኘውን እና በመንግሥታት ግምጃ ቤት ቁጥጥር የሚደረግበትን የገንዘብ ዝውውርና የመረጃ ፍሰት ያልተማከለ ለማድረግ እቅድ አለው። ከዚህ በተጨማሪ ከገንዘብ ዝውውር እስከ የመሬት ባለቤትነት ምዝገባ ያሉ ሥራዎችን ሊከወንበት እንደሚችል ተስፋ የተጣለበት ቴክኖሎጂ ነው፡፡ የማይሳሳት፣ የማይሰረዝ እና የማይጭበረበር በሶስተኛ ወገን ጣልቃ ገብነት የማይዘረፍ የአሰራር ሥርዓት ያለው ቴክኖሎጂ ነው፡፡ በተለይ በአፍሪካ ምድር አጨቃጫቂና የግጭት መንስኤ የሆነውን የመሬት አስተዳደርን በመመዝገብ ችግሩን ይፈታል ተብሎ ይታመንበታል፡፡ ይህ በብሎክ ቼይን ቴክኖሎጂ የተመዘገበ የመሬት አስተዳደር ስርዓት ደግሞ በሁሉም ኮምፒውተሮች ተመዝግቦ ስለሚገኝ በኃላፊዎችና በሰራተኞች ከሚደርስበት መጭበርበርና ከሶስተኛ ወገን ስርቆት ይገጥመዋል ተብሎ የማይሰጋበት ከስርቆት የፀዳ ያደርገዋል፡፡
ለምሳሌ በብሎክቼይን የተመዘገበ አንድ መሬት በሙስና ለሌላ ሰው ቢተላለፍ መረጃው ኮፒ ሆኖ በአለም ላይ ባሉ ኮምፒውተሮች ስለሚቀመጥ የትም ቦታ ላይ ይህ ስራ እንደተሰራ ስለሚነግረን ሙሰኞችን ለመቆጣጠር ያስችላል፡፡ ከአፍሪካ ውስጥ ሩዋንዳ ወደዚህ ቴክኖሎጂ በመግባት የመሬት አያያዝን ለማዘመን በቴክኖሎጂው ባለሙያዎች ጋር ስምምነት ተፈራርማ እንቅስቃሴ ማድረግ ጀምራለች፡፡
ኢትዮጵያ ደግሞ የብሎክቼን ቴክኖሎጂን ለማስተዋወቅ ለመጀመሪያ ጊዜ ሴቶች ብቻ የተሳተፉበትን ቡድን እያሰለጠነች ትገኛለች፡፡ ይህም ኤሌክትሮኒክስ የገንዘብ ዝውውር ስርዓት ውስጥ ዲጂታላይዝ የሆነ ስርዓትን ለመፍጠር የምታደርገውን ጥረት የሚደግፍ ነው፡፡
ብሎክ ቼይን የተሳካና ግልፅ የሖነ ምርጫም ለማካሄድ ጥቅም ላይ ይውላል፡፡ ለዲጂታል መታወቂያ፤ የማንፈልጋቸውን መረጃዎች ሙሉ ለሙሉ ለመሸጥ፤ የቅጅ መብትን ለማስጠበቅ፤ ለቤቶች አስተደዳር፤ የእቃ ዝውውርን ለማከናወን፤ ለግብር መክፈያ፤ ለህክምና ስራ (የታካሚዎችን መረጃ ለመያዝ እና ለመሳሰሉት)፤ ለህገወጥ የመሳሪያ ዝውውር ቁጥጥር፤ እና ለመሳሰሉት ጥቅም ላይ የሚውል ቴክኖሎጂ ነው፡፡
ቴክኖሎጂው ክሪፕቶከረንሲ የተባለ ምናባዊ መገበያያ ይጠቀማል። ቢትኮይን ሌላው የክሪፕቶከረንሲ አይነት ነው። ከቢትኮይን በተጨማሪ በርካታ ብሎክ ቼይን የሚጠቀሙ ረቂቅ ገንዘቦች እየተፈጠሩ ነው፡፡ ኢቲሪየም፤ ኢቲሪየም ካሽ፤ ዳሽ፤ ዚካሽ የመሳሰሉ የብሎክቼይን ውጤት የሖኑ ረቂቅ ገንዘቦች ናቸው፡፡
ቢትኮይን (አዲሱ ገንዘብ) ምንድነው?
ቢትኮይን ከፍተኛ ዋጋ ያለው የብሎክ ቼይን ቴክኖሎጂ ነው፡፡ ቢትኮይን በፈረንጆች 2008 ሳቶሺ ናከሞሮ በተባለ ግልሰብ የተፈጠረ ምናባዊ የመገበያያ ገንዘብ ነው፡፡
ይህ አዲስ ዋጋ ያለው ገንዘብ አለም አሁን እየተጠቀመባቸው ካሉ ገንዘቦች ሁሉ በምንዛሬ ከፍተኛ ዋጋ ያለው ረቂቅ ገንዘብ ነው፡፡ የቴኖክሎጂ ባለሙያዎችን እስከ ዛሬ ሲያስጨንቃቸው የነበረው ጉዳይ አንድን እቃ ቅጂው እጃቸው ላይ ሳይኖር ለሌላ ሰው እንዴት ማስተላለፍ ይቻላል? የሚለው ነው፡፡ ለምሳሌ 50 ብርን ለአንድ ሰው በዲጂታል መንገድ ለመላክ ኮፒው ላኪው ጋር አለመቅረቱ ምንም ማረጋገጫ የለም፡፡
ይህ ጉዳይ ክሪፕቶግራፈሮች ለረጅም ጊዜ ሲቸገሩበት የነበረው ጉዳይ ነው፡፡ ክሪፕቶ ከረንሲ ይህንን ችግር የፈታ አዲሱ ቴክሎጂ ነው፡፡
በተለመደው አሰራር የሀገራት የገንዘብ ዝውውር መንግስት እና ባንኮች የሚቆጣጠሩት ነው፡፡ ቢትኮይን የተባለው ገንዘብ ግን ዝውውሩን የሚቆጣጠረው ባለቤቱ ሲሆን የዝውውሩ ህጋዊነት ማረጋገጫ ደግሞ ሁሉም የቢትኮይን ተጠቃሚዎች ናቸው፡፡ ሰዎች በአለም ላይ ካሉ ከሚፈልጉት ሰው ጋር በየትኛውም ቦታ ሆነው ሶስተኛ ወገን ወይም ባንክ ሳያስፈልግ የሚገበያዩበት ቴክኖሎጂ ነው፡፡ ማንም ሊቆጣጠረው እና ሊያጭበረብረው አይችልም፡፡ መንግስታትም ቢሆኑ፡፡ ቁጥጥሩ በሁሉም ግልሰቦች እጅ ሆኖ በሁሉም የቢትኮይን ረቂቅ ገንዘብ ተጠቃሚ ኮምፒውተሮች ላይ መረጃዎቹ ሰፍረው ይገኛሉ፡፡
ለምሳሌ አንድ ሰው የቢትኮይን ተጠቃሚ ሲሆን ልክ እንደ ጂ-ሜል እና ፌስ ቡክ የመለያ ስም አውጥቶ የሚስጥር ቁልፍ መርጦ መጠቀሚያ ይከፍታል፡፡ የሚስጥር ቁጥሩ በጣም ጠንካራ በመሆኑ የመሰረቅ አደጋ አይገጥመውም፡፡ ከዚያ ከፈለገው ሰው ጋር ቢትኮይን መላላክ ይችላል፡፡ ያ የተላላከው የገንዘብ ዝውውር በአለም ላይ ባሉ ኮምፒውተሮች ቅጂው ይቀመጣል፡፡ እነዚህ ሁለት ሰዎች ቢከዳዱ እንኳ አለም ላይ ባሉ ኮምፒውተሮች ዝውውሩ ተመዝግቦ በቅጂ መልክ ስለሚቀመጥ እውነቱን ማወቅ ይቻላል፡፡
በቀላል ምሳሌ እንየው፡፡ ለምሳሌ አንድ ሰው ጫማ መግዛት ቢፈልግ እና ባንክ ቤት ገንዘብ ለማውጣት ቢሄድ ባንክ ቤቱ ሰውየው በስሙ ገንዘብ መኖርና አለመኖሩን አረጋግጦ ገንዘብ ይሰጠዋል፡፡ ሰውየው ገንዘብ እንዳለውና እንደሌለው የሚያውቀው ባንኩ ብቻ ነው፡፡ እሱን ካረጋገጠ በኋላ ገንዘቡን ይሰጠውና የሚፈልገውን መግዛት ይችላል፡፡
ሰውየው በክፍያ ካርድ ቢሆን መግዛት የሚፈልገው እና ካርዱን ለባለሱቁ ሰጥቶ የጫማ መግዣውን ቢያስቆርጥ፤ ሰውየው ገንዘብ እንዳለውና እንደሌለው የሚቆጣጠረው በተመሳሳይ ሶስተኛ ወገን የሆነው ባንኩ ነው፡፡
ወደ ቢትኮይን እንምጣ፡፡ የቢትኮይን መጠቀሚያ ያለው ሰው እቃ ገዝቶ የመገበያያ ገንዘብ ወይም ቢትኮይን እንዳለውና እንደሌለው የሚቆጣጠሩት አለም ላይ ያሉ ሰዎች ናቸው፡፡ ቢትኮይን የሚተላለፍለት ሰው ቢትኮይን አለው ወይ ብሎ ሲጠይቅ አለም ላይ ያሉ ኮምፒውተሮች በቂ ቢትኮይን ካለው ‹‹አዎ›› ከሌለው ደግሞ ‹‹የለውም›› ብለው ማረጋገጫ ይሰጡታል፡፡ ክፍያው ከተፈፀመ በኋላ ደግሞ ቅጂው በመላው አለም ላይ ባሉ ኮምፒውተሮች ተሰራጭቶ ይቀመጣል፡፡
እና በስሜ የተመዘገበ ቢትኮይን ለህዝብ ግልፅ ከሆነ ምኑን ሚስጥር ሆነ?
አይደለም፡፡ ክፍያው ሲፈፀም ግልባጩ አልያም ቅጂው የሚቀመጠው በሚስጥራዊ ስም ነው፡፡ እንጂ በተገልጋዩ የመጠሪያ ስም አይደለም፡፡ ከመጀመሪያው የቢትኮይን አካውንት ሲከፈት ሚስጥራዊ ኮድ አብሮ ይፀድቃል፡፡ ያ ምስጢራዊ መጠቀሚያ ማንም የማይከፍተውና ሊያጭበረብረው የሚችል አይደለም፡፡ የመገበያያ ገንዘቡ ለዚያ ነው ረቂቅ አንዳንዶችም ምናባዊ የሚሉት፡፡
ምንዛሬውስ?
የቢትኮይን ዋጋ በየጊዜው ይጨምራል፡፡ የተወሰነ መዋዠቅም ያጋጥመዋል፡፡ ለምሳሌ ግንቦት 2010 ላይ የ1 ቢትኮይን ዋጋ 0.01 ዶላር ነበር፡፡ ታህሳስ 2017 የ1 ቢትኮይን ዋጋ 19ሺ 783 ዶላር ደረሰ፡፡ ይህንን ፅሁፍ በምናዘጋጀበት ጊዜ ደግሞ ዋጋው ወደ 3ሺ972 ዶላር ወርዷል፡፡
ቢትኮይን የተፈጠረበት ምክንያት የወረቀት ገንዘብ በየጊዜው እየታተመ ስለሚሄድና ስለማያልቅ የገንዘብ የመግዛት አቅም እያሽቆለቆለ በመሄዱ የተነሳ ነው፡፡ ቢት ኮይን ግን የዚህ ስጋት የለበትም፡፡ በአለም ላይ የተፈጠሩ ቢትኮይኖች 21ሚሊየን ብቻ ናቸው፡፡ እነዚህ ቢትኮይኖች 122 አመት እንዲያገለግሉ ተደርጎ የተቀመረ ስሌት ነው፡፡ በየጊዜው የመታም እጣ ፈንታ የማያሰጋው ስለሆነ የመግዛት አቅሙ ይወርዳል ተብሎ አይታስብም፡፡
ቢትኮይን በማንኛውም ኮምፒውተር ማዘዋወር ይቻላል?
ይቻል ነበር፡፡ አሁን ግን የቢትኮይን ዝውውር እያደገ ሲመጣ መደበኛ ኮምፒውተሮች መቃጠል ስለጀመሩ የተሻለ ኮምፒውተርን መጠየቅ ጀምሯል፡፡ አሁን ይህን የቢትኮይን ዝውውር ለመፈፀምና ቢትኮይን ለማግኘት የ500 መደበኛ ኮምፒውተር አቅም ያላቸው ሱፐር ኮምፒውተሮች
ላጊ ሆኗል፡፡ እነዚህ ኮምፒውተሮች ለቢት ኮይን ማግኛ ሆነዋል፡፡
ቢትኮይን የሚነሳበት ተቃውሞ አለ?
አዎ፡፡ ለቢትኮይን ዝውውር ጥቅም ላይ የሚውሉ ኮምፒውተሮች በጣም ከፍተኛ ሃይል ይፈልጋሉ፡፡ ከመንግስት እና ባንክ ቁጥጥር ውጪ ስለሚንቀሳቀስና ተቋማዊ አለመሆኑ የህጋዊነት ጥያቄ በተደጋጋሚ ይነሳበታል፡፡ መንግስታት የገንዘብ ዝውውር እገዳ ለመጣል ቢፈልጉ ይህ አስቸጋሪ ይሆንባቸዋል፡፡
ቢትኮይንን የሚጠቀሙ ሀገራት አሉ?
አሜሪካ፤ ካናዳ፤ ፊንላንድና ቤልጂየም በተለያየ መልኩ ቢትኮይንን የተቀበሉት ሲሆን ቻይና፤ ሩስያ፤ ቬትናምና ቦሊቪያ ደግሞ እገዳ የጣሉ ሀገራት ናቸው፡፡
ምንጭ ministry of innovation and technology
#የተማሩትን_ማስተማር #ያወቁትን_ማሳወቅ #ብልህነት ነው
#ለሰው መልካሙን እንጅ መጥፎውን አትመኝ🙏
ስለኮምፒውተርና ቴክኖሎጅ ያለዎትን እውቀት ያሳድጉ በተጨማሪም በቴሌግራሜ ቻናል ምርጥ ምርጥ ስለኮምፒውተር የምለቃቸውን መረጃዎችን ለመከታተል እንዲያመችዎ ይህንን ይጫኑ https://t.me/MuhammedComputerTechnology በቴሌግራም መከታተል ትችላላችሁ
ሼር ማድረጋችሁን አትርሱ በፍጥነት መረጃ እንዲደርሳችሁ
Like & share this page
#ሼር_ያድርጉ
#ፔጄን_ላይክ ማድረግዎን አይርሱ
Muhammed Computer Technology (MCT) pinned «ብሎክ ቼይን ምንድነው? ቢትኮይንስ? ብሎክቼን በሚሊየን የሚቆጠሩ የኮምፒውተር መረጃዎችን ባልተማከለ መልኩ የሚመዘግብ የብሎክ ጥርቅም የሖነ ቴክኖሎጂ ነው፡፡ ይኸ ቴክኖሎጂ በባንኮች እጅ የሚገኘውን እና በመንግሥታት ግምጃ ቤት ቁጥጥር የሚደረግበትን የገንዘብ ዝውውርና የመረጃ ፍሰት ያልተማከለ ለማድረግ እቅድ አለው። ከዚህ በተጨማሪ ከገንዘብ ዝውውር እስከ የመሬት ባለቤትነት ምዝገባ ያሉ ሥራዎችን ሊከወንበት…»