Muhammed Computer Technology (MCT)
38K subscribers
527 photos
7 videos
254 files
910 links
🔴አድራሻ:-
✅ ስ.ቁ: 0929273364
✅ ዌብሳይት www.mctplc.com
✅ቴሌግራም አካውንት: https://t.me/mctplc
✅ email: mct16plc@gmail.com
✅ ቲክቶክ አካውንት tiktok.com/@mctplc
Download Telegram
እየተዝናኑ ይማሩ, እራሶን ይጠይቁ ምርጥ የኮምፒውተር ነክ ፈተናዎች አሁን ፈተና 8 ደርሰናል እያንዳንዳቸው ፈተና 10ጥያቄዎችን ይዟል።
ወደፈተና ልክፍሉ ይግቡ ከአውነት ይጠቀማሉ!
👇👇👇👇👇👇
@mame_tech_QA
@mame_tech_QA
@mame_tech_QA
@mame_tech_QA
#የኔትዎርክ_የትውስትድ_ፔር_ገመድ_ኬበል_ከለር_ኮዶች !
ትውስትድ ፔር ገመድ ለኔትዎርክ ስንጠቀምበት ኮምፒውተሮችንና ዲቫይሶችን ለማገናኘት ያሉትን ገመዶች ቀለማት በመደርደር በአለም አቀፍ የተሰጠውን የአደራደር ተራ ከ1 እስከ 8 በማስቀመጥ ወደ አርጃ(RJ)45 ዲቫይስ ውስጥ እናስገባለን በመቀጠልም ለኔትዎርክ ዝርጋ ከሚያስፈልጉት ዋናው እቃ ውስጥ ክሊገፐርን በመጠቀም አርጃ(RJ)45 ዲቫይስ እንጨፈልቃለን ይህን ከማድረጋችን በፌት በአለም አቀፍ ደረጃ የተሰጣቸውን የቀለም አደረራደረር አይነት የሚጠቀሙትን መለየት ያስፈልጋል እነዚህን እንደሚከተልው እናያለን፡፡
በቲውስድ ፔር ገመድ ውስጥ ያለው አንሽድድ ቲውስትድ ፔር ገመድ በ568A ና 568B እንከፍለዋለን ይን ገመድ ያሉትን ስምንት(8) ገመዶች ውስጥ ካሉት ቀለማት ከዚህ በታች ባለው መሰረት እንደረድራቸዋለን
በ568B
1. ነጭና ኦሬንጂ (ብርቱካናማ)
2. ኦሬንጂ(ብርቱካናማ)
3. ነጭና አረንጔዴ
4. ስሚያዊ
5. ነጭና ስሚያዊ
6. አረንጔዴ
7. ነጭና ቡናማ
8. ቡናማ ናቸው
በ568A
1. ነጭና አረንጔዴ
2. አረንጔዴ
3. ነጭና ኦሬንጂ (ብርቱካናማ)
4. ስሚያዊ
5. ነጭና ስሚያዊ
6. ኦሬንጂ(ብርቱካናማ)
7. ነጭና ቡናማ
8. ቡናማ ናቸው
ቀጥታ & በማጣመር ዲቫይሶችን ማገናኘት
ኮምፒውተሮችንና ዲቫይሶችን ለማገናኘት ገመዶች ቀለማት በመደርደር በኔትዎርካችን ላይ የምንጠቀማቸውን ዲቫይሶች ስትሬት (ቀጭታ)ና ክሮስኦቨር በማለት እንለያለን
ቀጥታ የምንጠቀመው በሁለቱም(2) ጫፍ ላይ አርጃ (RJ)45 ላይ የምናስገባው ለሚከተሉት ዲቫይሶች ነው
ስዊች ከራውተር ጋር ስናገናኝ
ኮምፒውተር ከስዊች
ኮምፒውተር ከሃብ ጋር ብቻ ናቸው
ይህም ማለት በA ወይም በB አደራደረ ብቻ በሁለቱም ጫፍ በመጠቀም ነው
ክሮስ አቨር(በማጣመር)የምንለው በአንድ ጫፍ
በB በሌላኛው ሳይድ በA በመስራት ስንጠቀም ነው
ይህም አደራደር የሚጠቀሙት የሚከተሉት ዲቫይሶች
ናቸው፡፡
ስዊች ከስዊች
ስዊች ከሃብ
ሀብ ከሃብ
ራውተር ከራውተር
ኮምፒውተር ከኮምፒውተር
ኮምፒውተር ከራውተር ናቸው
ብዙ #መማር የሚፈልጉ ሰዎች ስላሉ እባክዎ #ሼር ያድርጉት...
#የተማሩትን_ማስተማር #ያወቁትን_ማሳወቅ #ብልህነት ነው
#ለሰው መልካሙን እንጅ መጥፎውን አትመኝ
ስለኮምፒውተርና ቴክኖሎጅ ያለዎትን እውቀት ያሳድጉ በተጨማሪም በቴሌግራሜ ቻናል ምርጥ ምርጥ ስለኮምፒውተር የምለቃቸውን መረጃዎችን ለመከታተል እንዲያመችዎ ይህንን ይጫኑ https://t.me/MuhammedComputerTechnology በቴሌግራም መከታተል ትችላላችሁ
ሼር ማድረጋችሁን አትርሱ በፍጥነት መረጃ እንዲደርሳችሁ
Like & share this page
#ሼር_ያድርጉ
#ፔጄን_ላይክ ማድረግዎን አይርሱ
✅ Cisco Packet Tracer በሲስኮ ሲስተም የተፈጠረ አውታረ መረብ/የኔትወርክ መሳሪያ ነው፡፡ ለኔትወርክ ሰርቲፊኬቶች ስልጠና የሚጠቅም ሶፍትዌር በመሆኑ በPacket Tracer ተማሪዎች ያልተገደበ የቁጥር መሳሪያዎችን አውታረመረብ/ የኔትወርክ እቃዎችን ልክ እንደ እውነተኛ ዲቫይሶቹ በመሆኑ የሙከራ ስልጠናዎችን እና ችግሮችን ለመማር ያስችላቸዋል፡፡
የመሳሪያው ዓላማ የተማሪዎችን የኔትዎርክ መሰረታዊ መርሆችን ለመማር ልዩ ክህሎቶችን ለማዳበር የተሰራ ሲሆን እንደ ራውተር ፣ስዊች እና የተለያዩ የኔትወርክ ዲቫይሶችን የያዘ ነው፡፡
✅ Cisco Packet Tracer ሲሲኮ ፓኬት መከታተያ ተማሪዎች በኔትወርክ ባህሪ ላይ እንዲሞክሩ እና “ምን ቢሆን” ጥያቄዎችን እንዲጠይቁ የሚያስችል ኃይለኛ የአውታረ መረብ የማስመሰል ፕሮግራም ነው ፡፡ የፓኬት ትራከር የኔትዎርኪንግ አካዳሚ አጠቃላይ የመማር ልምድ ዋና አካል እንደመሆን መጠን ፣ ምስላዊነትን ማሳየት ፣ መጻፍ ፣ ግምገማ እና የትብብር ችሎታዎችን ያቀርባል እንዲሁም ውስብስብ የቴክኖሎጂ ፅንሰ ሀሳቦችን ማስተማር እና መማርን ያመቻቻል ፡፡
✅ ሲሲኮ ፓኬት መከታተያ 64-ቢት በክፍል ውስጥ አካላዊ መሣሪያዎችን የሚጨምር ሲሆን ተማሪዎች በማያልቅ ያልተገደበ ቁጥር ያላቸው አውታረመረብ እንዲፈጥሩ ፣ ልምድን ፣ ግኝትን እና መላ ፍለጋን ያበረታታል ፡፡ በማስመሰል ላይ የተመሠረተ የመማሪያ አካባቢ ተማሪዎች በ 21 ኛው ክፍለ ዘመን እንደ ውሳኔ አሰጣጥ ፣ ፈጠራ እና ሂሳዊ አስተሳሰብ እና ችግር ፈቺ ያሉ ችሎታዎችን እንዲያዳብሩ ይረዳቸዋል ፡፡ ፓኬት ትራከር የኔትወርክ አካዳሚ ሥርዓተ-ትምህርትን ያሟላ ሲሆን መምህራን ውስብስብ ቴክኒካዊ ፅንሰ ሀሳቦችን እና የኔትወርክ ሲስተም ዲዛይንን በቀላሉ እንዲያስተምሩ እና እንዲያሳዩ ያስችላቸዋል ፡፡
✅ የሲሲኮ ፓኬት መከታተያ የሚከተሉትን ፕሮቶኮሎች ይደግፋል-
🔶 Application
FTP, SMTP, POP3, HTTP, TFTP, Telnet, SSH, DNS, DHCP, NTP, SNMP, AAA, ISR VOIP, SCCP config and calls ISR to command support, Call Manager Express.
🔶 Transport
TCP and UDP, TCP Nagle Algorithm & IP Fragmentation, RTP.
🔶 Network
BGP, IPv4, ICMP, ARP, IPv6, ICMPv6, IPSec, RIPv1/ v2/ng, Multi-Area OSPF, EIGRP, Static Routing, Route Redistribution, Multilayer Switching, L3 QoS, NAT, CBAL, Zone-based policy firewall and Intrusion Protection System on the ISR, GRE VPN, IPSec VPN.
🔶 Network Access Interface
Ethernet (802.3), 802.11, HDLC, Frame Relay, PPP, PPPoE, STP, RSTP, VTP, DTP, CDP, 802.1q, PAgP, L2 QoS, SLARP, Simple WEP, WPA, EAP.
Cisco Packet Tracer የተለያዩ ስሪት ያለው ሲሆን 7.3 አሁን ያለው ነው ለዊንዶ፣ ላይኑክስ እና ማክ ኦፕሬቲንግ ሲስተም ተጠቃሚዎች እንደፍላጎታችሁ መጫን ትችላላችሁ። ጎግል ላይ Cisco Packet Tracer version 7.3 ብላችሁ ሰርች በማድረግና በማውረድ መጠቀም ትችላላችሁ።
🔶 ሶፍትዌሩን ማውረድ ለምትፈል 👇👇👇
https://www.filehorse.com/download-cisco-packet-tracer-64/
ካይዘን ምንድነው?
ካይዘን የጃፓን የአሰራር ፍልስፍና ሆኖ
የአሰራር ልምዶችን፣ ብቃትን ወዘተ
በቀጣይነት ለማሻሻል የሚያስችል የአሰራር
ፍልስፍና ነው፡፡
ካይዘን - “የተሻለ ለውጥ”
· ካይዘን የደንበኛን ፍላጎት ሙሉ በሙሉ ለማርካትና የምርትና ምርታማነት ማሻሻያ መንገድ ሆኖ የአገልግሎት አሰጣጥ ስርዓት ጥራትን ለማሻሻል ተከታታይ የሆነና የማያቋርጥ የፍልስፍና ሂደት ነው:፡
·ካይዘን በምርት ሂደት ውስጥ የሚታዩ
ብክነቶችን በማስወገድ ወይም በመቀነስ
ያለንን ሀብት በቁጠባና እና አዋጭ በሆነ
መንገድ ለመጠቀም በማስቻል ቀጣይና
የማያቋርጥ የምርት ጥራትና
ምርታማነትን ለማሳደግ የሚያስችል
አሰራር ነው፡፡
· ካይዘን ብክነትን በማስወገድ
ጥራት፣ ወጪና
የማስረከቢያጊዜያችንን በማሻሻል
ቁልፍ አስተዋጽኦ ያደርጋል፡፡
· ካይዘን የደንበኛን ፍላጎት ሙሉ በሙሉ ለማርካትና የምርትና ምርታማነት ማሻሻያ መንገድ ሆኖ የአገልግሎት አሰጣጥ ስርዓት ጥራትን ለማሻሻል ተከታታይ የሆነና የማያቋርጥ የፍልስፍና ሂደት ነው
· ካይዘን ተከታታይ የሆነ የብቃት ዕድገት የሚያመጣ ስርዓት ሲሆን በተለይም በትኩረት ችግሮችን ከምንጫቸው እየለየና ምላሽ እየሰጠ የሚሄድ የለውጥ ስርዓት ነው፡፡
የካይዘን አስፈላጊነትና ጠቀሜታው
በምርት ሆነ በአገልሎት አሰጣጥ ወቅት ብክነትንና አላስፈላጊ ወጪዎችን በመቀነስ፤ ሐብትን ከፍ የሚያደርግ ነው
ምቹ የስራ አካባቢን ይፈጥራል
የደንበኛ እርካታን ያሳድጋል
የድርጅቱን የተቋሙን ዘለቄታነት ያረጋግጣል
የማምረቻ ቦታችንን በአግባ እንድንጠቀም ይረዳናል
ተከታታይ የሆነ ፈጣን ለውጦችን ያስገኛል
ተወዳዳሪነታችን እንዲጨምር ያደርጋል
የስራ እድል ይፈጥራል፤ የሐገርን ገቢ ያሻሽላል
በምርት መምረት/ አገልግሎት አሰጣጥ ወቅት እሴት የሚጨምሩ አሰራሮችን ያሻሽላል፡፡
የመረጃ ግንኙነትን በማጠናከር የአመራሩንና የሰራተኛውን ግንኙነት ያጠናክራል


የካዘን ባህሪያት
የካዘን ባህሪያት
1. ቀጣይነት ያለው መሻሻል
የካይዘን ትግበራ ያልተካሄደባቸው ቢዝነሶች ፤አምራች ድርጅቶች ምርትና ማሻሻያ
ቢኖራቸውም ቀጣይነት የለውም፡፡ በካይዘን የአመራር ፍልስፍና የታጀበ አሰራርን የሚያራምድ ድርጅት/ተቋም/ የምርት ጥራቱ፣ ምርታማነቱና አገልግሎት አሰጣጡ ቀጣይና በማያቋርጥ ተከታታይ መሻሻል ሂደት ውስጥ ያልፋል፡፡
2. ሁሉንም የሚያሳትፍ መሆኑ
ካይዘን ተግባራዊ በሚሆንበት ድርጅት (ተቋም) ሁሉም ሰራተኛ ከማኔጅምንቱ እስከ ታች
ሰራተኛ መሳተፍ ይኖርበታል፡፡ የሁሉም ሰራተኞች ተሳትፎ ካልታከለበት ካይዘን
ተግባራዊ ሊሆን አይችልም፡፡ በካይዘን አተገባበር የማሻሻያ ሃሳብ ከከፍተኛ አመራር ደረጃ ወደ
ታች የሚመጣ ሳይሆን በዝቅተኛ እርከን ከሚገኙ ሰራተኞች በማመንጨት ወደ ከፍተኛ
አመራሩ የሚቀርብ ይሆናል፡:በመሆኑም የተጠናከረ የግንኙነትና ሃሳብን በነፃነት
የማቅረቢያ ስርዓትን መዘርጋት ያስፈልጋል፡፡
3. ብዙ ወጪ የማይጠይቅ መሆኑ
· ያለምንም ወጪ ወይም በትንሽ
ወጪ ካይዘንን መተግበር ይቻላል፡፡
· 5ቱ ማዎችን በማስቀደም ሌሎች
የካይዘን መሳሪያዎችን ለመተግበር
የሚያስፈልገው የመዋዕለ ንዋይ ፍሰት
እጅግ አነስተኛ ነው፡፡
· የካይዘንን ትግበራ ፅንሰ ሃሳብ ከግምት ውስጥ ያላስገባ የመዋዕለ-ንዋይ ፍሰት ብክነትን ያስከትላል
4. በሁሉም የዘርፍ ዓይነቶች የሚተገበር መሆኑ
በፋብሪካ፤በኢንተርፕራይዞች፤በህብረት ሰራ ማህበራት፤አገልግሎት ሰጪ ድርጅቶች፤በቢሮ፤በቤት፤
በቦርሳችንና በኪሳችንም ሳይቀር ካይዘን ሊተገበር ይገባል፡፡
5. ትንንሽ መሻሻሎች ድምር መሆኑ
ካይዘን በራሱ ትልቅ ውጤትን ለማምጣት ይችላል በማለት የሚተገበር ሳይሆን በሚገኙ ጥቃቅን መሻሻሎች ጥርቅም ውጤት የሚፈልገውን ግዙፍ ለውጥ የሚያመጣ የአመራር ፍልስፍና ነው፡፡
ካይዘን የትንንሽ መሻሻሎች ድምር ነው፡፡

የካይዘን ችግር አፈታት ዘዴ
ካይዘን እንደ ሌሎች የለውጥ መሳሪያዎች አንድ ጊዜ ተተግብሮ የሚቆም ሳይሆን ሁል ጊዜ ሁሉም ቦታ ሊተገበር የሚችል የስራ አመራር ፍልስፍና ነው፡፡
· ማቀድ(ማ)
· መስራት(መ)
· አፈጻጸምን መፈተሽና ማስተካከል(መፈ)
· የተስተካከለውን ሃሳብ መተግበር(መተ)
ካይዘን እንደ ሌሎች የለውጥ መሳሪያዎች አንድ ጊዜ ተተግብሮ የሚቆም ሳይሆን ሁል ጊዜ ሁሉም ቦታ ሊተገበር የሚችል የስራ አመራር ፍልስፍና ነው፡፡
· ማቀድ(ማ)
· መስራት(መ)
· አፈጻጸምን መፈተሽና ማስተካከል(መፈ)
· የተስተካከለውን ሃሳብ መተግበር(መተ)
ካይዘንን ለመተግበር ሚያስችሉ መሰረታዊ/አስፈላጊ አጀንዳዎች
የስራ ዕቅድ፡- የአጭርና የረጅም ጊዜ የምርት ወይም የአገልግሎት መስጠት ዕቅድ ለማዘጋጀትና ለመምራትም ሆነ አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችል የአመራር ችሎታ ነው፡፡
ወጪዎችን መመዝገብና የስራ መረጃዎችን መያዝ፡-
በካይዘን ትግበራ የአንድን ነጠላ ምርት ወጪ መረጃ በጣም ወሳኙና አስፈላጊ ነው፡፡ይህ ወቅታዊ የሆኑ የምርት ወይም የአገልግሎት ወጪን ለመተንተን ብቻ ሳይሆን በካይዘን ትግበራ ወቅት ለማሻሻል ከምናስቀምጠው ግብና የሚገኘውን ውጤት ከምርት ወይም ከአገልግሎት ወጪ አንፃር ለመለካት ያስችላል፡፡ በተጨማሪ የተለያዩ የስራ መረጃዎች በጣም አስፈላጊ ናቸው፡፡የስራ መረጃዎች ከተለያዩ የስራ አመላካቾች ጋር የሚገናኙና ለምርት፤ለአገልግሎት ጥራት፤ለምርት ማስረከቢያ ጊዜ፤ለስራ ላይ ደህንነትና ምርት ለማምረት ወይም አገልግሎት ለመስጠት የሚፈጅበትን ሰዓት፤የተፈጠሩ የምርት ግድፈቶች፤ የአገልግሎት ቅሬታዎችና የመሳሰሉትን ያካትታል፡፡
እምነትና ኃላፊነትን መስጠት፡- ካይዘን በከፍተኛ አመራር፤ በመካከለኛ አመራርና ለስራው ቅርብ በሆኑ ሰራተኞች ቅንጅት የሚተገበር ነው፡፡ ስለዚህ እምነትና ኃላፊነትን መስጠት የካይዘን አመራር ፍልስፍና ሲሆን፤
· ሰራተኞች በስራ ቦታቸው ላይ ያላቸውን ተነሳሽነት መደገፍ
· አስፈላጊውን ኃላፊነት ለአመራር/ሱፐርቫይዘሮች መስጠት
· ለሰራተኞች የስልጠና ዕድል ማመቻቸትና ሰራተኛን ማመን ያስፈልጋል
የካይዘን ህግ/ደንብ
· ለደንበኛ ትኩረት መስጠቱ፤
· ቀጣይና የማያቋርጥ መሻሻል ማምጣቱ፤
· ችግሮችን የሚያሳውቅ መሆኑ፤
· የስራ ቡድኖችን ሚፈጥር መሆኑ
· የተለያየ ዕውቀት ያላቸውን ቡድኖች ውስጥሚካተት መሆኑ፤
· ትክክለኛ ሂደትን የሚከተል መሆኑ፤
· ራስን መግዛት ማሳደጉ፤
· እያንዳንዱ ሰራተኛ መረጃ እንዲያገኝ ማድረጉ
· እያንዳንዱ ሰራተኛ አስፈላጊውን ስልጠና እንዲያገኝ የሚያደርግ መሆኑ
ካይዘን ለመተግበር ምን ያስፈልጋል
· የካይዘን ዕውቀት
· ቀና አስተሳሰብ
· የሁሉም ተሳትፎ
· ፍላጎትና ድጋፍ
· ስለ ካይዘን ማስተማርና መማር
· ካይዘን በቀጣይነት መተግበር
ሊተኮርባቸው የሚገባቸው ጉዳዮች
ጥራት
ጥራት ማለት አንድን ምርት ወይም አገልግሎት ለመጠቀም ተስማሚ ሆኖ ሲቀርብ ነው፡፡ ምርቱ ወይም አገልግሎቱ የደንበኛን አጠቃላይ ፍላጎት ማሟላት የሚኖርበት ሲሆን የጥራት ቁጥጥርና የደንበኛ ቅሬታ የአንድን ምርት ወይም አገልግሎት ጥራት የሚወስኑ ናቸው፡፡
2. ወጪ
ወጪ ማለት አንድን ምርት ለማምረት ወይም አገልግሎት ለመስጠት የምናወጣው የግብዓት፤ሰው ኃይል፤የመሳሪያና ሌሎች ወጪዎች ማለት ነው፡፡ የአንድ ዕቃ ዋጋ የሚወሰነው በወጪ መርህ ሳይሆን በገበያ ፍላጎት መሆን ይኖርበታል፡፡
በተለምዶአዊ ወይም በወጪ መርህ ዋጋ የሚወሰነው ፡- ዋጋ = ወጪ + ትርፍ
በገበያ መርህ ወይም በካይዘን ዋጋ የሚወሰነው ፡- ትርፍ = ዋጋ - ወጪ ነው፡፡
3. ምርታማነት
ምርታማነት ማለት አንድን ምርት ለማምረት ወይም አገልግሎት ለመስጠት
ሚያስፈልጉትን እንደ ግብዓት፤የሰው ኃይል፤መሳሪያና ሌሎች ወጪዎች
👍1
መጠን በዝቅተኛ ወጪ ከፍተኛ ምርት ወይም አገልግሎት ማግኘት ነው፡
የማቅረቢያ ጊዜ
የማቅረቢያ ጊዜ ማለት አንድን ምርት አምርቶ ለደንበኛ ማስረከብ የሚቻልበት
ጊዜ ነው፡፡
የስራ ቦታ ደህንነት
ምርት ወይም አገልግሎት በሚሰጥበት አካባቢ የሠራተኛውን ደህንነት
የሚጎዱትን ዕቃዎች ወይም አሰራሮች ማስተካከል ነው፡፡
የስራ ተነሳሽነት
ሰራተኛው ከዚህ በፊት ከነበረው ሁኔታ በተለየ ምርትን በጥራት በማምረት
ወይም አገልግሎትን በተሸለ መንገድ ለመስጠት ሲነሳ ነው፡፡
አካባቢያችን - የውሃ አጠቃቀም፣ የአየር መበከል፣
የድምጽ ሁኔታ፣ተረፈ ምርት……


እሴት የሚጨምርና የማይጨምር ስራ
1. እሴት የሚጨምር ስራ
· ደንበኛው በምርቱ ላይ እሴት እንደተጨመረ ሲያድርበት
· የምርቱ ዋጋ ወይም እሴት ሲጨምር
· እሴት ሲጨምር ሶስት ዳይሜንሽን አለው ፡፡እነሱም
- የሰው ኃይል፤መሳሪያ
- መረጃ
- ግብዓት ናቸው
2. እሴት የማይጨምር
እሴት የማይቸምሩ ስራዎች ብክነቶች ናቸው፡፡ስለሆነም ለምርት፤ለአገልግሎት ወይም ለሁለቱም ሂደት ምንም አስተዋጽዖ ስለሌላቸው መወገድ አለባቸው፡፡
እሴት የማይጨምሩ ስራዎችን በማስወገድና በመቀነስ እንዲሁም እሴት ያላቸውን ስራዎች ከፍ በማድረግ ብክነትን ማሻሻል ይቻላል፡፡
ሰባቱ የችግር አፈታት ዘዴዎች
1) የጋራ ግንዛቤ ማግኘት
ከማንኛውም ቦታ ማንኛውንም ነጥብ በማንሳት፤ አንቀሳቃሾች ለምን? ወይም ትክክል ነውን? የሚለውን ማሰብ አለባቸው፡፡ ይህ ለካይዘን ተግባራት የመጀመሪያው ቁልፍ ነው፡፡
2) ነባራዊ ሁኔታን መረዳት
ለማንኛውም ችግር፣ የቻሉትን ያህል መረጃዎችን በማሰባሰብ ትክክለኛ የሆኑ መንስኤዎች መለየት፡፡
3) በአሃዛዊ መረጃዎች ማጣራት
አሃዛዊ መረጃዎችን የመሰብሰብ እና የመመደብ ሥራ የዋና ተግባራችን አካል መሆን አለበት፤ ምን እቃ? የምን ማሽን?፣ ማ?፣ መቼ? እና እንዴት? የሚሉት መረጃዎች የሚሞሉበት የማረጋገጫ ቅጽ ማዘጋጀት፡፡ እነዚህን መረጃዎች በመከፋፈል በቁጥር በመመደብ የችግሩ መንስኤ በቀላሉ እንዲለይ ማስቻል፡፡
4) ዕቅዳችንን ማረጋገጥ
የተግባሮቻችን ትኩረት በሚገባ ግልጽ ማድረግ፡፡
5) መደገፍ
የሌሎች ሰዎች ድጋፍን ማበረታታት፤ ብዙ ሃሳቦች ከተለያዩ አቅጣጫ እንዲፈልቁ ማድረግ፡፡
6) የሌሎችን ሃሳብ መቀበል
የማነቃቂያ ሃሳቦችን በመጠቀም ብዙ አማራጭ ሃሳቦች እና የመፍትሄ አማራጮች ማስገኘት አለበት፡፡
7) ማስቀጠል/ማዝለቅ
ውጤቱን ካረጋገጥን ብኋላ፣ ደረጃ በማውጣት የማረጋገጫ ስርዓት በመዘርጋት ችግሩ እንዳይደገም መከላከል አለብን፡፡
1. እሴት የሚጨምር ስራ
· ደንበኛው በምርቱ ላይ እሴት እንደተጨመረ ሲያድርበት
· የምርቱ ዋጋ ወይም እሴት ሲጨምር
· እሴት ሲጨምር ሶስት ዳይሜንሽን አለው ፡፡እነሱም
- የሰው ኃይል፤መሳሪያ
- መረጃ
- ግብዓት ናቸው
2. እሴት የማይጨምር
እሴት የማይቸምሩ ስራዎች ብክነቶች ናቸው፡፡ስለሆነም ለምርት፤ለአገልግሎት ወይም ለሁለቱም ሂደት ምንም አስተዋጽዖ ስለሌላቸው መወገድ አለባቸው፡፡
እሴት የማይጨምሩ ስራዎችን በማስወገድና በመቀነስ እንዲሁም እሴት ያላቸውን ስራዎች ከፍ በማድረግ ብክነትን ማሻሻል ይቻላል፡፡
ሰባቱ የችግር አፈታት ዘዴዎች
1) የጋራ ግንዛቤ ማግኘት
ከማንኛውም ቦታ ማንኛውንም ነጥብ በማንሳት፤ አንቀሳቃሾች ለምን? ወይም ትክክል ነውን? የሚለውን ማሰብ አለባቸው፡፡ ይህ ለካይዘን ተግባራት የመጀመሪያው ቁልፍ ነው፡፡
2) ነባራዊ ሁኔታን መረዳት
ለማንኛውም ችግር፣ የቻሉትን ያህል መረጃዎችን በማሰባሰብ ትክክለኛ የሆኑ መንስኤዎች መለየት፡፡
3) በአሃዛዊ መረጃዎች ማጣራት
አሃዛዊ መረጃዎችን የመሰብሰብ እና የመመደብ ሥራ የዋና ተግባራችን አካል መሆን አለበት፤ ምን እቃ? የምን ማሽን?፣ ማ?፣ መቼ? እና እንዴት? የሚሉት መረጃዎች የሚሞሉበት የማረጋገጫ ቅጽ ማዘጋጀት፡፡ እነዚህን መረጃዎች በመከፋፈል በቁጥር በመመደብ የችግሩ መንስኤ በቀላሉ እንዲለይ ማስቻል፡፡
4) ዕቅዳችንን ማረጋገጥ
የተግባሮቻችን ትኩረት በሚገባ ግልጽ ማድረግ፡፡
5) መደገፍ
የሌሎች ሰዎች ድጋፍን ማበረታታት፤ ብዙ ሃሳቦች ከተለያዩ አቅጣጫ እንዲፈልቁ ማድረግ፡፡
6) የሌሎችን ሃሳብ መቀበል
የማነቃቂያ ሃሳቦችን በመጠቀም ብዙ አማራጭ ሃሳቦች እና የመፍትሄ አማራጮች ማስገኘት አለበት፡፡
7) ማስቀጠል/ማዝለቅ
ውጤቱን ካረጋገጥን ብኋላ፣ ደረጃ በማውጣት የማረጋገጫ ስርዓት በመዘርጋት ችግሩ እንዳይደገም መከላከል አለብን፡፡
👍4
ላፕቶፓችን ላይ ያለውን ኢንተርኔት እንዴት ያለምንም ሶፍት ዌር በሞባይላችን
መጠቀም እንችላለን?
1. cmdን በአንሜኒስትሬተር ያሩጡት (right click በማድረግ run as
administrator የሚለውን መጫን)
2. ላፕቶፓችን ኔትዎርክ ሼር ለማድረግ ብቁ መሆኑን ለማረጋገጥ:netsh
wlan show drivers የሚለውን ጽፎ ከሚመጣልን ዝርዝር ውስጥ Hosted
network supported :Yes ይህ ከመጣ ላፕቶፓችን ይችላል ማለት ነው
3. በመቀጠል ይህንን ኮማንድ ማስገባት: netsh wlan set hostednetwork mode=allow ssid=Hotspotname key=password
ማሳሰቢያ: SSID የሚለውን በፈለግነው ስም መቀየር እንችላለን: KEY የሚለው የዋይ ፋይ ፓስዎርዳችን ስለሆነ የምንፈልገውን መስጠት እንችላለን
4. በመቀጠል የኔት ዎርክ አዳፕተራችንን በመክፈት እና እሱላይ right click
በማድረግ : Allow other network users to connect through this
computer's internet connection የሚለውን እንመርጥያ ከስር ካለው ሊስት ውስጥ የፈጠርነውን የዋየርለስ ኔትዎርክ እንመርጥለታለን። ከዛም OK በለን እንወጣለን
5. በመጭረሻ ወደ CMD ተመልሰን:
ለማስጀመር netsh wlan start hostednetwork የሚለውን ኮማንድ
እናስገባለን ለማቆም netsh wlan stop hostednetwork የሚለውን እናስገባለን
6. አሁን ሞባይላችንን wifi ከፍትን SSID ላይ ያስገባነውን የኔትዎርክ ስም
መርጠን ለሚለው KEY ላይ ያስገባነውን በመስጠት መጠቀም መጀመር እንችላለን።
ቫይረስ /Virus/  የኮምፒውተር ቫይረስ እራሱን ሌሎች ፋይሎች ላይ በማጣበቅ የሚያባዛ እና ተላላፊ ማልዌር ነው፡፡ ቫይረስ እራሱን ከተለያዩ ሶፍትዌሮች ጋር ባማጠባቅ እንደ ወርድ ዶኩሜንት ሊሆን ይችላል እኛ ፐሮገራሞቹን ስንከፍት እሱም አብሮ በመቀስቀስ የሚራባ ነው፡፡ በተጨማሪም ኔትዎርክ እና አንተርኔትንም ጨምሮ ማለት ነው፤ በፈላሽ ዲስክ፤ሜሞሪ ካርደ እና ሲዲዎችን በመጠቀም ይተላለፋል፡፡
ቫይረስ እንደሌሎቹ ማዌሮችን ኮምውተራችን በመበከል ኮምውተራችን ፍጥነቱን ይቀንሳል፤ ዳታ ያጠፋል ዋይንም ይሰርቃል፡፡ ከበድ ያሉ ቫይረሶች የክፒውተራችንን ሃረድዋር ጭምር ሊጎዱ ይችላሉ፡፡ ለምሳሌ ሃረድ ዲስክን በመጉዳት ኦፐሬቲንግ ሲይሰተማችን ክራሽ እነዲዲርግ ያደርጋሉ፡፡ 
⭕️ ወርም/Worm/ 
ወርሞች በአብዛኛው ተንሰራፍተው የሚገኙ ማዌሮች ናቸው፡፡ በኔትዎርክ አማካኝነት እራሳቸውን ችለው የኦፐሬቲንግ ሲይስተማችንን ድክመት በመጠቀም የሚባዙ ናቸው፡፡ ብዙ ጊዜ ኔትዎርክን በማጨናነቅ የእንተርኔት ፍጥነት ይቀንሳሉ ፤ የኮምፒውተራችን ፕሮሰሰር በአላስፋለጊ ትዛዞች በማጨናነቅ ኮምውተራችን ቀርፋፋ ያደርጋሉ፡፡
ከቫይረስ ጋር የሚለያቸው ወርሞች የሰዎችን ድጋፍ ሳያስፈልጋቸው እራሳቸውን ማባዛት ከመቻላቸው በላይ በኢሜሎች አታች ተደርገው ወደ ኮምፒውተራችን ሊገብ ይችላሉ፡፡ ቫይረስ ግን ለመባዛት የግድ እኛ የተበከለውን ፍላሽ ዲስክ መክፈት ይንም የተበከለ ወርድ ፋይል መክፈት ይኖርብናል፡፡ 
በማልዌር የተጠቁ ኮምፒውተሮች የሚያሳያቸው ምልክቶች 
ማልዌሮች የሚያደርሱት ጉዳት እና ምልክት እንደ ማልዌሩ አይነት፤እንደ ኮምፒውተሩ አይነት እና እነደ ሚጠቀመው የ ኦፐሬቲንግ ሲሰይሰም ቢለያይም አብዛኛው ጊዜ ግን አንድ ኮምፒውተር በማልዌር ሲጠቃ ከስር የተገለጹትን ምልክቶች ያሳያል
⭕️ የኮምፒውተር ፍጥነት መቀነስ 
የኢንተረኔት ፍጥነት መቀነስ ( የኢንተርኔ ፍጥነት የቀነሰው ከ ኢንተርኔ አገልግሎት ከሰጠን አካል አለመሆኑን እረግጠኛ መሆን የኖርብናል) 
 â­•️ የዌብ ብራውሰራችን ማዝገም 
ከእኛ እውቅና ውጪ በተለያየ ስም የተፈጠሩ ፈይሎች ወይን የተደበቁ ፋይሎች 
⭕️ የማናውቀው አይኮን ዴስክቶፓችን ላይ ሲገኝ 
⭕️ ፕሮገራሞች ካለእኛ ትዛዝ ሲከፈቱ ወይንም ሲዘጉ 
⭕️ áŠĽáŠ› ያላክነው ኢሜይል ተልኮ ከሆነ 
⭕️ ፌስቡክ ላይ እኛ ፖስት ያላደረግነው እና ካልታወቀ ምንጭ በእኛ ስም ፖስት የሚደረግ ከሆነ 
⭕️ የዴስክቶፕ ከለር መዛባት 
⭕️ አንዳድ ፕሮገራሞች አልከፍት ማለት በተለይ ታስክ ማናጀር አልከፈት ካለ ኮምፒውተራችን በማልዌር ተጠቅቶ ሊሆን ሰለሚችል ከተች የተገለጹትን መፍትሄዎች መተግበር ያስፈልጋል
🛑 እርምጃዎች እና ጥንቃቄዎች 
ማልዌሮች ኮምፒውተራችንን በመበከል አደጋ ከማድረሳቸው በፊት አስፈላጊውን ጥንቃቄ በማድረግ የሚፈጠረውን ችግር በከፍተኛ መልኩ መቀነስ ይቻላል፡፡ አንዴ ገብተው ጉዳት ካደረሱ በኋላ ግን ወደኋላ መመለሾ በጣም አዳጋች ነው የሚሆነው ስለዚህ ቅድመ ጥንቃቅ ማድረገ የተሸለ አማራጭ ነው፡፡ 
🛑 ምንጊዜም አንቲቫይረስ መጠቀም 
🛑 የምንጠቀምባቸው አንቲቫይረሶች ተአማኝነት ያላቸው መሆኑን ማረጋገጥ ይኖርብናል 
🛑 በተቻለን መጠን አንቲቪረሳቻንን አፕቱዴት ማድረግ 
🛑 á‰€áˆ‹áˆ የሆኑ በነጻ ዶወንሎደ አድርገን የምንጠቀምባቸው አንቲቫይረሶቸ 
1️⃣ McCaffe 
2️⃣ Avira 
3️⃣ Microsoft Security Essential 
4️⃣ Avast
🛑ዳውንሎድ የምናደርገው ሶፍትዌር በተለይ ቶረንት ፋይሎችን ከመክፈታችን በፊት ስካን ማድረግ ከማናውቀው አካል በኢሜላችን የሚላኩ የተላያዩ ዳውንሎድ ሊንኮችን ከመክፈት መቆጠብ ፤በተወሰነ ጊዜ ልዩነት ኮምፒውተራችንን ፉል ስካን ማድረግ፡፡
▻▻▻▻▻◈◈◈◄◄◄▻▻▻◈◈◈◄◄◄◄◄
የኮምፒውተር ቫይረስ /Malware/ ምንድነው ?
🔆 Malware áˆšáˆˆá‹ ቃል የመጣው Malicious Software የሚለውን ሁለት ቃል እንድላይ በመጭመቅ ነው፡፡ ቀጥታ ትርጉሙም ጎጂ ሶፍትዌር ማለት ነው፡፡ 
ማልዌር ወይም በተለምዶ እኛ ቫይረስ የምንለው በኮምፒውተር ቋንቋ የተፃፈ ኮድ/ሶፍትዌር ሲሆን ከእኛ እውቅና ውጪ ኮምፒውተራችን ላይ ተጭኖ ከፍላጎታችን በተጣፃረረ መንገድ የሚሰራ ነው፡፡ ማልዌር የኮምፒወተራችንን አስራር ያውካል ፤ያንቀራፍፋል፤ ዳታ የጠፋል ወይንም ይደብቃል፤ መረጃ ይሰርቃል ባጠቃላይ ኮምፒውተራችን ከእኛ እውቅና ውጪ ስርአቱን በማዛባት ጉዳት ያደርሳል፡፡ 
ማልዌር ሰፋ ያለ እና የጅምላ ስያሜ ነው ፡፡ ከማዌር አይነቶች ውስጥ ጥቂቶቹን አናያለን፡፡ 
1️⃣ አድዌር /Adware: Advertising-supported Software/ 
ይህ ማልዌር ከተላያየ ዌብሳይቶች ጋር አብሮ የሚመጣ ሲሆን ከእኛ ፍቃድ ውጭ ማስታወቂያዎችን ሚያሰራጭ ነው፡፡ ጥሩ ምሳሌ የሚሆነን እንዳን የዳውንሎደ ዌብሳይቶችን ስንጠቀም ከእኛ ፍላጎት ውጪ በአዲስ ታብ ወይንም አዲስ ዊንዶው ያለፈላጎታችን ማስታወቂያ ሚከፈትበት ነው፡፡አኝህ የሚከፈቱ ማስታወቂያዎች መንም እንኳን ለዌብሳይቱ የገቢ ምንጭ ቢሆኑም አንዳነድ ጊዜ ግን ማዌልሮችን ያስተላልፋሉ፡፡
አንዳንድ ነፃ ሶፈተዌር ስንጭን ደግሞ አብረው በግዴታ ወይንም በተጠቃሙው ቸልተኝነት ህጋዊ ሶፍትዌር መስለው ይጫናሉ፡፡ ታዲያ በምን መልክ ነው ኮምፒውተራችን የሚጎዱት?
የኢንተርኔት ብራውሰራችን (ሞዚላ ፋየር ፎክስ፣ኦፔራ፤ኢንተርኔት ኤክስፕሎረር) አላስፈላጊ ጫና በማሳደር የኢነተሬን ፍጥነት ይቀንሳሉ 
ስለምንጎበኛቸው ዌብሰይ መረጃ ላመረታቸው አካል ይልካሉ
 áŠ¨ááˆ‹áŒŽá‰łá‰˝áŠ• ውጪ በግዴታ የማንፈልገውን ማስታወቂያ ያሳዩናል (ወሲብ ነክ ሊሆኑ ይችላሉ)
2️⃣ ራንሰምዌር /Ransomware : Ransom Software/ 
ራንሰም ዌር ቀጥታ ትርጉሙ አጋች ሶፍትዌር ማለት ነው፡፡ ኮምፒውተራችንን በማገት ለማስለቀቅ ክፍያ የሚጠይቅ ነው፡፡ 
ለምሳሌ ወርድ ዶክመንቶችን ብቻ ‘ኢንክርይፕት’ (ዳታ መቆለፊያ መንገድ ነው) በማድረግ ለመክፈት ገንዘብ ይጠይቃል ወይንም ደግም ጭራሽ ኮምፒውተሩን በመቆለፍ ወይንም በማገት ክፍያ የሚጠይቅ ነው፡፡ ይህ ማልዌር አንዴ ኮምፒውተራችን ካገታ በኋላ እንደነበረ ለመመለሾ በጣም አዳጋች ሊሆን ይችላል፡፡ 
3️⃣ ሩትኪት /Rootkit/ áˆŠá‰ľáŠŞá‰ľ የሚባሉት ማልዌሮች የኮምፒውተራችን ዋናው መቆጣጠሪያ ክፍልን በማጥቃት ኮምፒወታረችን የሚቆጣጠሩ ናቸው፡፡ አንዴ ከተጫኑ በኋላ ያመረታቸው አካል ከርቀት ሆኖ በኢንቴርኔት አማከኝነት ኮምፒውተራችን መቆጣጠር ያስችለዋል ማለት ነው፡፡ የማልዌሩ ባለቤት ከእኛ እውቅና ውጪ ሴቲንጎችን ከርቀት ማሻሻል፤ ዳታ መስረቅ፤ ማጥፋት ክፍ ሲልም ካለበት ቦታ ሆኖ በእኛ ኮምፒውተር አማካኝነት የተለያዩ ወንጀሎችን መፈፀም ይችላል፡፡ ከአሰራራቸው ረቂቅነት የተነሳ ሩትኪቶችን ማደን ካበድ ነው፡፡
4️⃣ ስፓይዌር /Spyware: Spying Software/ 
ስፓይዌሮች በዋናነት ተግባራቸው ኮምፒውተራችንን እንቅስቃሴ ልቅም አድረገው በመሰለል ለባለቤታቸው መላክ ነው፡፡ የሚልኩት መረጃ እንደ ስፓይዌሩ አይነት ቢለያይም የምንጎበኘውን ዌብሳይት፤የምንጠቀመውን ብራውሰር; ኦፐሬቲንገግ ሲስተም ምን እንደሆነ፤ ውቤሳይቶች ላይ የምንሞላውን ፎርሞች ኢሜል እና ፓስዎረድን ጨምሮ የምንጽፈውን ፊደላት ሳይቀር መዝግበው ይልካሉ፡፡ 
5️⃣ ትሮጃን /Trojan Horse/ 
ትሮጃኖች ብዙ ጊዜ ህጋዊ ሶፈትዌሮች መስለው የሚጫኑ ናቸው ፤አንዳነዴም እኛ እራሳችን ቀጥታ ዳውንሎደ አድርገን የምንጭናቸው ናቸው፡፡ተግባራቸው ከ ስፓይዌር እና ሩትኪት ጋር ተመሳሳይ ሲሆን
ሚለያቸው ኮምፒውተራችንን የሚበክሉበት መንገድ ነው ፡፡
ምንጭ ከተለያዩ ዌብሳይቶች
እየተዝናኑ ይማሩ, እራሶን ይጠይቁ ምርጥ የኮምፒውተር ነክ ፈተናዎች አሁን ፈተና 9 ደርሰናል እያንዳንዳቸው ፈተና 10ጥያቄዎችን ይዟል።
ወደፈተና ልክፍሉ ይግቡ ከአውነት ይጠቀማሉ!
👇👇👇👇👇👇
@mame_tech_QA
@mame_tech_QA
@mame_tech_QA
@mame_tech_QA
ፍላሽ ዲስክ ከኮምፒውተራችን ጋር ተጠቅመን ከጨረስን በኋላ eject ማድረጋችን ምንድን ነው ጥቅሙ? አስበውት ያውቃሉ እስኪ ሀሳባችሁን አጋሩኝ?
✅ ፍላሽ፣ External Hard Disk፣ እንዲሁም CD/DVD ከኮምፒውተራችን ሰክተን ተጠቅመን ስንጨርስ በቀጥታ የሚታየን ነገር ቢኖር በቶሎ ፍላሹን፣ External Hard Disk መልቀል ወይም CD/DVD ከሆነ ደግሞ ሲዲው እንዲወጣ መጫን ነው።
✅ ነገር ግን አብዛኛዎቻችን ፍላሼ፣ External ሀርዲ ዲስኬ፣ የምጠቀምበት ሲዲ አልሰራልኝ አለ? ኮራፕት አደረገብኝ፣ ፍላሽ ዲስኬ Write Protected ሆነብኝ፣ ፍላሽ ዲስኬ ከነጭራሹ ከኮምፒውተሬ ጋ ብሰካው እይሰራም፣ ፍላሽ ዲስኬን ከኮምፒውተሩ ጋ ስሰካው ድምጽ ያሰማኛ ግን My computer ጋ ስሄድ የለም የሚል በብዛት የሚነሳ ጥያቄ ነው። ለዚህ ሁሉ ችግር ተጠያቂዎቹ እኛው ነን።
✅ቅድመ ጥንቃቄ ማድረግ አለባችሁ።
በመጀመሪያ ደረጃ ፍላሽ ዲስክ፣ External ሀርድ ዲስክ፣ ሲዲ/ዲቪዲ ወደ ኮምፒውተር ስብሰካና ስናስገባ ኮምፕዩተሩ Read/ Write process ያደርጋል። ይህ ማለት ስራ እየሰራ ነው ማለት ነው።
✅ ፍላሽ ዲስክ፣ External ሀርድ ዲስክ፣ ሲዲ/ዲቪዲ ወደ ኮምፒውተር ሰክተንና አስገብተን ፋይል ለምሳሌ ከኮምፒውተር ወደ ፍላሽ፣ ከፍላሽ ወደ ኮምፒውተር, ከExternal Hard Disk ወደ ኮምፒውተር .......... መረጃ ስናገላብጥ አሁን ሁሉም ስራ ላይ ናቸው ማለት ነው። ስለሆነም መረጃ እያላላክን ሳለ ከተሰካበት ብንነቅለው። ከገባበት ብባወጣው። ስራውን ሳይጨርስ አቋረጥነው ማለት ነው። በዚህ አጋጣሚ የመበላሸት አጋጣሚው በጣም ሰፊ ነው በተለይ ደግሞ ለExternal Hard Diskና CD/DVD እንዲሁም ፍላሽ ዲስኮች።
✅ ፍላሽ ዲስክ፣ External ሀርድ ዲስክ፣ ሲዲ/ዲቪዲ ከኮምፒውተር ጋ ተሰክተው እያለ ዝም ብለን የምነቅለው ከሆነ ይህም የመበላሽት አጋጣሚው በጣም ሰፊ ነው።
✅ ስለሆነም ማንኛውንም ከኮምፒውተር ጋ የሚሰኩ Storage Device በጥንቃቄ በሚከተለው ፕሮሰስ ፍላሽ ዲስክ፣ External ሀርድ ዲስክ፣ ሲዲ/ዲቪዲ ከኮምፒውተራችን ሳንነቅለው በፊት Eject ማድረግ አለባችሁ።
✅ Start -> All Program -> Computer or This PC -> ወደ ፍላሻችን ወይም External Hard Disk..... በመሄድ Right click በማድረግ Eject የሚለውን ይጫኑ። ከዛም ቢያንስ ለ5 ሰከንድ ይጠብቁ በቅድሚያ ግን ከፍላሽ ዲሳክችን....... የተከፈተ ማንኛውንም ፕሮግራም መዝጋት አስፈላጊ ነው።
ከላይ ያለውን ምስሉን ይመልከቱ!⁉️
✅ Eject ጥቅም ከኮምፒውተር ጋ የተሰካን ማንኛውንም ነገር ግንኙነቱን ያቋርጣል ማለት ነው። እንደገና ግንኙነቱ እንዲቀጥል ከፈለጋችሁ እንደአዲስ በመንቀል መሰካት ያስፈልጋል።
✅ይህ ተግባር የሁልጊዜ ስራችንና ተግባራችን ይሁን።
✅ ከተመቻችሁ ለሌሎች ሰዎች እንዲደርሳቸው #ሼር ይደረግ!
✅ ለፔጁ አዲስ የሆናችሁ ሰዎች #Like #shear ይደረግ።
👍4
ፋይል ወደ ፈላሽ ስንልክ "The Disk Is Write-Protected" እያለ አይቀበልም?
ፎርማት ለማድረግ ስንሞክር "the disk is write protected" እያለ ፎረማት አልሆንም ይላል?
በቅድሚያ ግን ምስሉን ይመልከቱ!
ሁለት መንገዶችን እጠቁማለሁ የቀለለውን ተጠቀሙ
1.
Windows Key + R በጋራ እንጫን በRun ሳጥን ላይ regedit ጽፈንEnter በማለት Registry Editor እንክፈት
2. HKEY_LOCAL_MACHINE\SYSTEM\Curr
entControlSet\Control
3.
በግራ በኩል ባለው ክፍል ላይ right click Control key and select New -> Key. Name the new sub-key so created as StorageDevicePolicies.
Now come to the right pane of this sub-keyi.e. StorageDevicePolicies, right click and select New -> DWORDValue. Name the newly created DWORD as WriteProtect.
In some cases, you might find that this DWORD under the sub-key already exists and the DWORD has a Value set to 1. Double click on the DWORD to modify its Value data
4.
በሳጥኑ ላይ Value data የሚለው ላይ 0 የነበረውን ወደ 1 በመቀየር OKወይም
Command Prompt
1. Command Prompt
2. diskpart
3. list disk
4. select disk #(ፍላሽ ያለበትን ቁጥር እንፃፍ) ኢንተር
5. attributes disk clear readonly ኢንተር6. Command Prompt እንዝጋ
Share your knowledge free for thousands Teach your self and teach your brother
👍1
ምን ይባላል? ጥቅሙስ?
✅ #ፕሮግራሚንግ ላንጉጅ ምንድን ነው?
(what is programming language)?
መጀመርያ programming language የሚለው ነገር ከማየታችን በፊት #ፕሮግራም ምንድን ነው(what is program) የሚለውን እንመልከት #ፕሮግራም ማለት በአጭሩ አንድን ነገር ለመሥራት ወይም ውጤት(output)ለማግኘት በቅድሚያ የምንፅፋቸው ነገሮች ሥብሥብ ፕሮግራም ይባላል።
ለምሣሌ ካርድ ለመሙላት *805*....# call እንደምንለው ማለት ነው ፤ከዛ ያሥገባነው ቁጥር ትክክል ከሆነ Dear Customer, your prepaid account has been recharged succesfully የሚል text ይደርሠናል ማለት ነው። ቁጥሩን ግን በምታስገቡበት ጊዜ መሰላል ብትረሱ አልያም የኮከብ ምልክት ወይም ደግሞ ከምትሞሉት የካርድ ቁጥር አንድ ዲጂት ቢጎድል ሲስተሙ አይሰራም።
ልክ እንደዚው ፕሮግራማችንም ትክክል ከሆነ ውጤት(output) እናገኛለን ካልሆነ ደግሞ ሥህተት የሆነ ውጤት እናገኛለን ወይም ስህተት ነው ይላል ማለት ነው።
ለምሣሌ ፦ከታች ያለውን C++ ፕሮግራም እንመልከት
#include <iostream>;
using namespace std;
int main( )
{
cout<<" Hello, World "<<endl;
return 0;
}
output : Hello, World
ይህ ከላይ በ እንግሊዘኛ የተፃፋው ምሣሌ" Hello, World " የሚለውን ፅሁፍ screenu ላይ ያሣየናል ሥለዚህ ይህንን ነገር ፕሮግራም እንለዋለን ማለት ነው። ከላይ ባለው ፕሮግራም ላይ የመጀመሪያዎቹ ሁለት መስመሮች ማንኛውም የ C++ code በምትሰሩበት ጊዜ የምትጠቀሟቸው ሲሆን የምታስገቡትን ኮድ ኮምፓይለራቹህ እንዲረዳው የሚረዱ መቅረት የሌለባቸው ነገሮች ናቸው።
ከላይ ያለውን ፕሮግራም run በምታደርጉበት ወቅት ኮምፒውተራቹው ላይ HI ATC የሚል out put ይመጣላቹሃል cout<< ____ ; ተብሎ የሚገባ ማንኛውም አይነት data ፕሮግራሙን ጨርሳቹህ run ስታደርጉ ኮምፒውተራቹህ ላይ ይወጣል ማለት ነው int main( ) የሚለው የምታስገቡት ነገር በሙሉ integer መሆኑን ለኮምፓይለሩ ያሳውቀዋል
The syntax for preprocessor directive statement is
#include <headerfilename.h>
The .h extension tells the compiler that the file is a header file. The preprocessor directive
statement instructs the compiler to bring all the contents of the header file to our program.
Some of the header files that we are going to use are:
iostream.h: - contains standard input and output functions.Some of the functions defined ( እኛ ለምሳሌነት የተጠቀምነው የheader type ነው ሌሎችም ግን እሉ ለምሳሌ math.h የሚባል የሂደር አይነት አለ ጥቅሙም የምንሰራው ፕሮግራም ላይ Mathematical formula och like cosine, sine, tangent, quadratic equation...ወዘተ ሲኖሩ ይህንን እንጠቀማለን ለምሳሌ ካልኩሌተር መስራት ብትፈልጉ # include <math.h> የሚል መግቢያ መጠቀም ይኖርባቹሃል
Here are:
Cin>>: is a standard input function that accepts input from the user. Syntax:
For single input
Cin>>var1; // var ማለት ማንኛውም የምታስገቡት ነገር ማለት ነው
For multiple inputs
Cin>>var1>>var2>>var3; // የምታስገቧቸው inputs
Cin will take value from the keyboard and store it in the memory. Thus the cin statement needs a variable that is a reserved memory place holder.
Cout<<: standard output function that displays its content to the Screen.Syntax:
For single output
Cout<<Var1;
For multiple outputs
Cout<<var1<<”, “<<var2<<” and “<<var3;
<<endl: standard output function that displays a new line character
⏺ ፕሮግራሚንግ ላንጉጅ ምንድን ነው ፦
ፕሮግራሚንግ ላንጉጅ ማለት የራሡ የሆነ የአፃፃፍ ህግ ያለው ሆኖ የምንጽፋቸው ችሮግራሞች የሚያሥተዳድር ማለት ነው።
✅ sorce code እኛየፃፍነው ፕሮግራም
✅ machine language ኮምፒውተር የሚረዳበት ቋንቋ ማለት ነው።
🛑 syntax(ሣይንታክሥ)
ከላይ ለመጥቀሥ እንደ ሞከርኩት ፕሮግራሚንግ ላንጉጅ ማለት የራሡ የሆነ የአፃፃፍ ህግ አለው ይህ የአፃፃፍ ህግ ሣይንታክሥ(syntax)ይባላል።
Like አማርኛ ላይ ሠዋሠው እንግሊዝኛ ላይ ደግሞ ግራመር እንደምንለው ማለት ነው። #ለምሣሌ ይህን ፕሮግራም እንመልከት እዚህ ላይ የተፃፋው እያንዳንዱ ነገር syntax መሠረት ያደረገ ነው።
#include <iostream>
using namespace std;
int main( )
{
cout<<" hello world"<<endl;
return 0;
}
ለምሣሌ አንድን አረፍተ ነገር ፅፈን ሥንጨርሥ ለአማርኛ አራት ነጥብ ፤ለእንግሊዝኛ አንድ ነጥብ(full stop)&ለ ፕሮግራሚንግ ላንጉጅ ደግሞ" ; " እንጠቀማለን ነገር ግን ሁሉም ፕሮግራሚንግ ላንጉጅ ማለት ሣይሆን C++ ጨምሮ አብዛኞቹ " ; "ይጠቀማሉ።
ሥለ #ፕሮግራሚንግ ላንጉጅ(ቋንቋ) ይህን ያህል ካወራን በመቀጠል ዋና ዋና የሚባሉትን እንጥቀስ በአሁኑ ሠአት በአለማችን ላይ ብዙ አይነት እና ጥቅም ያላቸው ፕሮግራሚንግ ላንጉጅዎች አሉ ከነርሡም መካከል በዋናነት የሚጠቀሡት የሚከተሉት ናቸው
✅ JS(javascript)
✅ C
✅ phyton
✅ C++
✅ Go(Go lang)
✅ C#
✅ Java
✅ CSS
✅ Php
✅ html etc...
ለዛሬ እዚህ ላይ ይብቃን በቀጣይ ስለእያንዳንዱ ፕሮግራሚግ ቋንቋ በጥልቀት እያየን እንሄዳለ።
◄◄ሼር▻▻ይደረግ ብዙ ማወቅ የሚፈልጉ
#ወንድም #እህቶች አሉን!
#የተማሩትን_ማስተማር #ያወቁትን_ማሳወቅ #ብልህነት ነው
በዚህ የቴሌግራም ቻናል
https://t.me/MuhammedComputerTechnology
ጥሩ ጥሩ ስለኮምፒውተርና ቴክኖሎጅ መረጃዎች እና እውቀቶች ይለቀቃሉ ያለዎትን እውቀት ያሳድጋሉ
በቴሌግራም ቻናሌ በመግባት ብዙ መረጃዎችን ማግኜት ትችላላችሁ።
ማንኛውንም ሶፍትዌር የምታገኙበት ምርጥ ዌብሳይት!
👇👇👇👇👇👇
www.getintopc.com
ይሞክሩት❤❤❤
Forwarded from Quality ButtonSCAM
ማንኛውንም አይነት የኮምፒውተር ለመግዛትና ለመሸጥ የሚያመች ምርጥ ገጽ!
💻 አዳዲስና ያገለገሉ ላፕቶፕ ኮምፒውተር
🖥 አዳዲስና ያገለገሉ ደስክቶፕ ኮምፒውተር ⌨️ ኪቦርዶችን
🖱ማውዞችን
🖨 ፕሪንተሮችንና ፎቶኮፒዎችን በአንድ ቦታ ያገኛሉ።
የካይዘን ስራ አመራር ፍልስፍና ምንነት
✅ ካይዘን የሚለው ቃል የጃፓን ቃል ሆኖ ካይ ማለት ለውጥ ሲሆን ዘን ማለት ደግሞ የተሻለ ማለት ነው፣

✅ ቀጣይነት ያለው የተሻለ ለውጥ ማለት እንደሆነ ትርጓሜው ያመላክታል፣

✅ የካይዘን ስራ አመራር ፍልስፍና ትኩረት የሚሰጠው ነባራዊ ሁኔታን በመረዳትና የስራ አካባቢን በማሻሻል ላይ ነው፣

✅ ዋና የለውጥ ተዋናይ አድርጎ የሚወስደውም የሰው ኃይሉን በተለይም ፈጻሚውን ነው፣

✅ የካይዘን የለውጥ መርሆ አንድም ቀን ቢሆን ያለ ለውጥ ማለፍ የለበትም የሚል ነው፣

✅ የካይዘን የለውጥ ቡድን የማያቋርጥ የጥራት መሻሻልን ማዕከል ያደረገና ከታች ጀምሮ ያለውን ሰራተኛ የሚያቅፍ ቡድን ነው፣

✅ የየካይዘን የለውጥ ቡድን ፍልስፍና የሚመነጨው ከአሳታፊነት እና ሰብዓዊ ተኮር ከሆነ አመራር /Participative and Human Oriented Management/ ሲሆን የዚህ አመራር ፍልስፍና ለሰዎችና ለፍላጐታቸው ትኩረት የሚሰጥ ነው፣

ለዚህም ምክንያቱ ሰዎች የአንድ ተቋም ከፍተኛው ሀብት ናቸው ተብሎ ስለሚታመን ነው፣
ሰዎች ለተቋማቸው ትርጉም ያለው አስተዋጽኦ ሊያበረክቱ የሚችሉት በተለመደው ድርጅታዊ መዋቅር የሰው ኃይል አሰላለፍ የተዋረድ አሠራር ላይ በተመሠረተ የሥራ ትዕዛዝ በመስጠትና በመቀበል አመራር ብቻ ሳይሆን በሥራ ቦታ ላይ እንደ አንድ የሥራ ክፍል ቡድን እና ግለሰብ ስለሚሰጡት አገልግሎት እና ስለአሠራራቸው የተሻለ ሀሣብ እንዲያመነጩ፣ እንዲመክሩ፣ እንዲተገብሩ፣ ለውጣቸውን እንዲያዩ፣ ከለውጡም እንዲቋደሱ የሚያስችል የሥራ አካባቢ ሲፈጠርላቸው ነው፣

የካይዘን ልማት ቡድኖች ለውጥ እንዲያመጡ ከሚያስችሏቸው ዘዴዎች መካከል የሚከተሉት በመሠረታዊነት ይጠቀሳሉ፤

🔷 የሠራተኞችን የችግሮች/ማነቆዎች የማቃለልና የመፍታት አቅማቸውን ማሳደግ፣

🔷 የጋራ ብልጽግና ወይንም ዕድገት መርህን መከተል፣

🔷 ቀና አስተሳሰብን መፍጠርና ማስረጽ፣

🔷 የሥራ ላይ ሥነ ምግባርን መገንባት፣

🔷 የደንበኞችን ፍላጐት ማዕከል ያደረገ አሠራርን በመከተል፣ የሥራ ፍላጐትን ማነሳሳት፣

✅ ለሥራ ከፍተኛ መበረታታትን መፍጠር፣

✅ የግል ኃላፊነትን በአግባቡ የመገንዘብና የመወጣት ስሜትን መፍጠር፣

✅ እያንዳንዱ ሠራተኛ ከሥራ ክፍልና ከተቋም ባሻገር የህብረተሰብ ዕድገትን ማምጣት አስተዋጽኦ እንዳለው ማስገንዘብ ናቸው፡፡

⏺⏺⏺ጠቀሜታ⏺⏺⏺
✅ ሠራተኛውንና የሥራ አመራሩን ያቀራርባል፣
✅በሠራተኞች መካከል የሥራ ትብብርን ይፈጥራል፣
✅ የሥራ ዕርካታን ያስገኛል፣
✅ ለሥራ ያነቃቃል፣
✅ በራስ መተማመንን ይፈጥራል፣
✅ መሪዎችን ለማፍራት ይረዳል፣
✅ ተተኪዎችን ለማፍራት ይረዳል፣
✅ የሥራ ፈጠራን ያበረታታል፣
👍4❤1
Chose your favorite
1. Computer Hardware
2. Computer Networking
3. Computer Software
4. Cloud computing
5. Cyber Security and Ethical Hacking
6. Data Science and Data Analysis
7. Programming Language
8. Mobile Application Development
9. Operating system
10. Web Development
11. Web Designing
12. Graphics design
13. Network Analytics and testing
14. Robotics
15. Artificial intelligence
16. Computer Operator
17. Computer Administrator
18. DBMS (DataBase management system)
19. Video Game Designer
20. Computer Architecture and Engineering
21. Cryptography
22. Research and development
23. Software Engineering
24. Game development