Muhammed Computer Technology (MCT)
38.1K subscribers
527 photos
7 videos
254 files
910 links
🔴አድራሻ:-
✅ ስ.ቁ: 0929273364
✅ ዌብሳይት www.mctplc.com
✅ቴሌግራም አካውንት: https://t.me/mctplc
✅ email: mct16plc@gmail.com
✅ ቲክቶክ አካውንት tiktok.com/@mctplc
Download Telegram
💢ስልክዎ ላይ #Application's ሲጭኑ "There was a Problem Parsing The Package" እያላችሁ ለተቸገራችሁ #መፍትሔ ⬇️⬇️⬇️

1⃣.USB Debugging On አድርጉት።

⚠️Settings➡️ About Phone➡️ Build Number (7ጊዜ ይንኩት)➡️ ወደ Setting ይመለሱና➡️ Developer Options➡️ USB debugging የሚለውን #ON ያድርጉት።

2⃣. የጫኑት Antivirus ወይም Cleaner ካለ ለጊዜው #Disable ያድርጉት።

3⃣. ያለዎት አፕ #Corrupted ወይም Download ተደርጎ ያላለቀ❌ ሊሆን ስለሚችል ከእንደገና Download📥 ያድርጉት።

⚠️አፖችን #ከPlaystore ብቻ ቢያወርዱ📥 ተመራጭ ነው።👍

4⃣. የPlay Storeን Cache Cookies Clear ያድርጉት።

⚠️Settings➡️ Apps➡️ Playstore ➡️ Clear Cache Cookies

5⃣. ሊጭኑት ያሰቡት አፕ ካለዎት Operating System ጋር #Compatible ሳይሆን ሲቀር።

⚠️በተጨማሪም ሌላ የሚፈልገው Hardware Requirements ካለ የአፑን #description በደንብ ያንብቡ።
Šethio_techs
✅RAM
ራም (ራንደም አክሰስ ሜሞሪ) ኮምፒውተር በፍጥነት ኦፕሬቲንግ ሲስተም (ኦኤስ) ፣ Application ፕሮግራሞች እና መረጃዎች በአሁኑ ወቅት በሚቀመጡበት የኮምፒተር መሣሪያ ውስጥ ሃርድዌር ነው ፡፡
#RAM የሚጠቅመው #የተቀሰቀሱ/የተከፈቱ #ፕሮግራሞች #በፍጥነት እንዲሰሩ የሚጠቅም ነው፡፡ የ RAM ተግባር በተለዋጭነቱ ምክንያት ራም ቋሚ መረጃዎችን ማከማቸት አይችልም።
ይህ ሊሆን የሚችለው #ኮምፕዩተሩ እነዚህን የተቀሰቀሱ #ፕሮግራሞች ለጊዜው (ተቀስቅሰው እስካሉ ድረስ) ለምሳሌ #HHD ወይም ከሲዲ ከማንበብ ይልቅ ከራም ላይ ያነባቸዋል፡፡ ይህ ማለት ራም #ጊዚያዊ ፕሮግራም ተሸካሚ ግን በፍጥነት አቅራቢ እንደማለት ነው፡፡ #ለምሳሌ አንድ ተጠቃሚ ኢንተርነት የሚቀዝፍ ከሆነ ቀዛፊውን ከፍቷል፡፡ ሰነድ የሚጽፍ ከሆነ ወርድን ከፍቷል #ፎቶ ወይም ቪዲዮ የሚሰራ ከሆነ የፎቶና ቪዲዮ #ፕሮግራሞች ከፍቷል፡፡ እና እነዚህ ፕሮግራሞች #እስከተከፈቱ ድረስ #ራም ለጊዜው ተሸክሞ ይይዛቸዋል፡፡ ለዚህም ነው ራም ከፍ ባለ ቁጥር #የኮምፕዩተሩም #ፍጥነት የሚጨምረው፡፡ ያው አማካይ አዛዢም እራሱን የቻለ ሚና ቢጫወትም፡፡ #ራም ልክ እንደሌሎቹ ክፍሎች ዋና ቦርድ ቦታ ስላለው እዛ ይሰካል፡፡

✅Hard_disk

#ዳታዎችን በቋሚነት #ለመያዝ ነው፡፡ #የኮምፒውተሩ አሰራር ሂደት(operating system) #የሚጫንበት እና በአግባቡ ኮምፒውተሩ ለተጠቃሚዎች አገልግሎት ምቹ የሚያደርጉትን የአሰራር ሂደት #ፋይሎች(operating system files) የሚቀመጡበት #የኮምፒውተር ክፍል ነው፡፡ áˆˆáˆáˆłáˆŒ የሆነ #ሰነድ ጽፈው ለመያዝ ከፈለጉ የሚይዘው #HHD ላይ ነው፡፡ እንደተለመደው HHD ዋና ቦርድ ላይ የሰካል፡፡ HHD ዳታ ሲያነብና ሲጽፍ #ማግኔታዊ ነው
👍1
ላፕቶፕ ስንገዛ ማወቅ እና ማየት ያለብን ወሳኝ ነጥቦች
1 የመሳሪያ ስርዓት (Operating system)
2 የስክሪን መጠን (Screen Size)
3 ሲፒዩ(CPU)
4 ራም(RAM)
5 የሃርድ ድራይቭ አይነት (Hard Drive Type)
6 የምስል ጥራት (Image Quality)
7 የባትሪ ቆይታ (Battery Life)
8 ብራንድ (Brand)
ኮርi3 ኮርi5 ኮርi7 ምንድናቸው?
በሃገራችን ገበያ አሁን አሁን በርከት ያሉ የላፕቶፕ እና
የኮምፒውተር ሱቆች እየታዩ ይገኛሉ፡፡ለገቢያም የተለያዩ
የላፕቶፕ አይነቶች.በተለያየ ይዘት ይገኛሉ፡፡ እንዚህን
የተለያየ
ይዘት ያላቸውን የላፕቶፕ አይነቶች ለመግዛት በዋናነት
መታየት
ያለበትን ከዚህ በታች በዝርዝር ተቀምጠዋል፡፡
1. የመሳሪያ ስርዓት (platform) Windows, Mac
and
Linux
ለአጠቃቀም ምቹ እንደሆነ የሚነገርለት Windows የብዙ
ሰዎች
ምርጫ ነው፡፡ቀላል፣ ምቹ እና ተለዋዋጭ ነው፤ በዋጋም
ደረጃ
ጥሩ የሚባል ነው፡፡
ማክ( Mac) የአፕል ድርጅት ምርት ሲሆን ለዲዛይን
ተመራጭ
የሆነ
ፕላትፎረም ነው፡፡ለደህንነትም ከWindows እንደሚሻል
ይነገርለታል፡፡
2. የስክሪን መጠን
ወደ ግዢ ከመግባታችን በፊት የምንገዛው ላፕቶፕ ከቦታ
ወደ
ቦታ ይዘን ለመንቀሳቀስ (portable) ምቹ መሆኑን
ማረጋገጥ
ያስፈልጋል፡፡ ላፕቶፖች እንደየስክሪን መጠናቸው
የተከፋፈሉ
ናቸው፡፡
• 11 to 12 inches(27.94cm-30.48cm) ፡በጣም
ቀጭን
እና ቀላሉ የስክሪን ሳይዝ ነው፡፡ ከ1.1ኪሎ እስከ1.5ኪሎ
ይመዝናል፡፡
• 13 to 14 inches (33.02cm- 35.56cm) ፡ይህ
የስክርን
ሳይዝ ያለቸው ላፕቶፖች በጣም ተመጣጣኝ portability
ያላቸው እና በላፕቶፕ ተጠቃሚዎች ተመራጭ ናቸው፡፡
• 15 inches(38.1cm): እውቁ የላፕቶፕ የስክሪን
ሳይዝ
ሲሆን፤ተለቅ ያለ የስክሪን ሳይዝ ከፈለጉ ይህንን እንዲገዙ
እንመክራለን ፡፡
• 17 to 18 inches (43.18cm- 45.72cm)፡
ላፕቶፖን
ይዘው የማይንቀሳቀሱ ከሆነ እና ትልቅ የስክሪን ሳይዝ
ከፈለጉ
ይህንን ይግዙ፡፡ ለጌመሮች እና ትልልቅ የሶፈተዌር
ዲዛይን
ለሚያደርጉ ሰዎች ተመራጭ የሆነ የላፕቶፕ አይነት ነው፡፡
3. ሲፒዩ(CPU)
የኮምፒዉተር አይምሮ በመባል የሚታወቀው ሲፒዩ
(CPU),
ላፕቶፕ ለመግዛት ሁላችንም ማየት ያለብን ዝርዝር ነው፡፡
• AMD A series or Intel Core i3 / i5: በየቀኑ
ለምንጠቀማቸው ስራዎች የሚሆኑ የሲፒዩ አይነቶች
ሲሆኑ Core
i5 ለሶፈትዌር ዴቨሎፕመንት እና አነስተኛ የዲዛይን
ስራዎችን
ለምሳሌ እንደ Photoshop, Archicad, AutoCadን
የመሳሰሉ በጥሩ ሁኔታ እንድንሰራ ይጠቅሙናል፡፡
በተጨማሪም
ግራፊክስ ካርድ ያለውና የሌለው በማለትም ይለያያሉ፡፡
ግራፊክስ
ካርድ ያለቸው የተሻለ የዲዛይን እና አኒሜሽን ስራዎችን
ያከናውኑልናል፡፡ በዋጋውም ተመጣጣኝ ነው፡፡
• Intel Core i7፡ በጣም አስደማሚ የጌም እና
የዲዛይን
እንዲሁም ልዩ የሆኑ የኮምፒውተር ስራችን ለምሳሌ አንደ
ሜትሮሎጂ፤ውስብስብ ስሌቶችን እንድንሰራ የሚረዳን
የላፐቶፕ
አይነት ነው፡፡
4 .ራም(RAM): ለፍጥነት 4ጂቢ እና ከዛ በላይ የሆነ
RAM
እንዲጠቀሙ እንመክሮታለን፡፡ ዋጋቸው አነስ ያሉ
ላፕቶፖች
በ2ጂቢ ይመጣሉ፡፡ የዲዛይን ስራዎችን እና የሶፈትዌር
ዴቨሎፕመንት ስራዎችን ለመስራት 6ጂቢ ራም እና ከዚያ
በላይ
ያለው ላፕቶፕ ቢገዙ ይመረጣል፡፡
5.የሃርድ ድራይቭ አይነት፡ ሁለት አይነት የሃርድ ድራይቭ
አይነቶች ያሉ( HDDrive እና SSDrive) ሲሆን
በሃገራችን
ያልተለመደው SSDrive ከHDDrive የተሻለ የፍጥነት
አቅም
እና ድራይቩ ላይ ያለውን ዳታ በፍጥነት መድረስ እና
መገልበጥ
(copy)ያስችለናል፡፡
6 .የምስል ጥራት፡ የተሻለ ጥራት የተሻለ ምስል
እንድናገኝ
ይረዳናል፡፡ 1366 x 768 ጥሩ የሚባል የምስል ጥራት
ያለው
ሲሆን ከዚህ የተሻለ ወጪ በማውጣት 1920 x 1080
የተሻለ
ምስል ማግኘት እንችላለን፡፡Full HD 1080P በመባልም
ይታወቃል፡፡
7 .የባትሪ ቆይታ፡ አብዛኛው ሃገር ውስጥ የሚገቡት
የላፕቶፕ
አይነቶች 4 ሰዓታት የሚቆዩ ሲሆን ከ6-8 ሰዓታትም
የሚቆዩ
ኦርጅናል ላፕቶፖች አሉ፡፡
8 . ብራንድ፡ የተላያዩ የላፕቶፕ ብራንዶጭ ባሉበት ገቢያ
የተኛውን መግዛት እንዳለብን አስቀድመን ማወቅ አለብን፡፡
• ከጥራት አኳያ ደግሞ APPLEን የሚደርስ የለም፡፡ HP
እና DELLም የተሻሉ ብራንዶች ናቸው
👍2
📶 ዋይ ፋይ ምንድነው?
✅ Wi-Fi እንዴት ይሰራል?
ይህ ቃል ለአብዛኛው ተጠቃሚ፤ ሞያተኛውንም ሲጨምር አጋጥሞናል ከ ኢንተርኔት ጋር እየተለዋወጠ ሲገባ እናየዋለን፡፡ በሞያችንም ለሰዎች ለማስረዳት ስንሞክር አለመግባባት ይከሰታሉ፡፡ እርግጥ ነው ዋይ ፋይ ኢንተርኔት ለማገኘት ይራዳል ነገርግን በራሱ ኢንተርኔት አይደለም፡፡
✅ምንም እንኳን በአይናችን ባናያቸውም የራዲዮ ሞገዶች ሁሌም መረጃዎችን ተሸክመው በዙሪያችን እንዳሉ ይታወቃል፡፡ ከእነዚህ የሬዲዮ ሞገዶች ጥቂቶቹ የWi-Fi ሲግናሎች ናቸው፡፡ Wi-Fi በሚለው ስም ውስጥ የሚገኙ ሆሄያት እንደ አህጽሮተ ቃል የትኛውንም ነገር የማይወክሉ ሲሆን በመነሻነት አንድ ከፍተኛ መጠን ያለውን መረጃ በአጭር ርቀት ውስጥ የራዲዮ ሞገዶችን በመጠቀም ማስተላለፍ የሚችልን ቁስ በቀላሉ ማስታዎስ እንዲቻል ተብሎ የተሰጠ ስያሜ ነው፡፡

✅ እንደ ብሮድካስት ራዲዮና ተንቀሳቃሽ ስልክ ሲግናሎች ሁሉ የWi-Fi ሲግናልም በ19ኛው መቶ ክፍለ ዘመን መገባደጃ አካባቢ የተገኘ ሳይንሳዊ ፈጠራ ነው፡፡ ኤሌክትሮኖች በሽቦ ውስጥ በሚንቀሳቀሱበት ጊዜ በየተወሰኑ ጊዜያት አቅጣጫዎችን ይቀይራሉ፡፡ በሌላ ሽቦ ላይ የሚገኙ ኤሌክትሮኖች ከእነዚህ አቅጣጫ ከሚቀያይሩ ኤልክትሮኖች ጋር ቴሌፋቲክ በሆነ መንገድ የተያያዙ ስለሆኑ መንቀሳቀስ ይጀምራሉ፡፡ ይህ ግኝት መጀመሪያ የታወቀው በ1887 በሄንሪክ ሄርትዝ ነው፡፡

✅ የሚታይ ብርሃንን የያዙ ኤሌክትሮመግነጢሳዊ ህብሮች ከራዲዮ ሞገዶች የተሻለ ከፍተኛ ፍሪኩየንሲን ያመነጫሉ፡፡ የተለመዱት የኤ ኤም ወይም ኤፍ ኤም ራዲዮ እና የቴሌቪዥን ስርጭቶች መረጃን በተከታታይ ሲግናሎች ወይም በአናሎግ ያደርሳሉ፡፡ Wi-Fi መረጃን የሚያሰራጨው እንደ ያልተያያዙ ዋጋዎች የባይናሪ መረጃ ዜሮዎችና አንዶች በዲጂታል መንገድ ነው፡፡ ይህም የሞባይል ቁሶች ከፍተኛ መጠን ያላቸውን እንደ ቪዲዮ፣ ምስል፣ ድምጽ እና የጽሁፍ መልዕክቶችን በቀላሉ እንዲልኩ ያስችላቸዋል፡፡

✅ አንድን መረጃ በዋይ ፋይ ኦንላይን ላይ ስንፈልግ የዋይ ፋይ ቁሳችን የሬዲዮ ሞገዶችን አልፎ ከዋይ ፋዩ መገኛ ነጥብ ጋር ይናበባል፡፡ ይህም በኢንተርኔት ራውተራችን አንቴና አማካኝነት ነው፡፡ ከዚያም በአካባቢው ባሉ የኢንተርኔት ገመዶች አማካኝነት ጥያቄያችን ወደምንፈልገው የመረጃ ቋት ይተላለፋል፡፡ ሂደቱ ሲያልቅም በመጣበት መንገድ ተመልሶ ይመጣል፡፡

✅ በተለያዩ ኩባንዎች የተሰሩ የዋይ ፋይ ቁሶች 802.11 የተሰኘ ተመሳሳይ ስታንዳርድን ስለሚከተሉ እርስ በርሳቸው መናበብ ይችላሉ፡፡ ይህ ስታንዳርድ ዜሮዎችና አንዶች ራዲዮ ሞገድን በመጠቀም እንዴት እንደተወከሉና ቁሶቹ ራሳቸውን እንዴት እንደሚለዩ የሚወስን ነው፡፡ እነዲሁም ደግሞ ኬሪየር ሴንስ መልቲፕል አክሰስ (CSMA) የተሰኘ እንዴትና መቼ መግባባት እንዳለባቸው የሚወስን አሊጎሪዝም ይከተላሉ፡፡ ይህ አሊጎሪዝም የዋይ ፋይ ቁሶችን ስማርት ያደርጋቸዋል፡፡

✅ አንዳንድ ጊዜ ከዋይ ፋይ ጋር በተያያዘ ችግሮች ይገጥሙናል፡፡ ወይም ከዋይ ፋዩ መገኛ ነጥብ ጋር ለመገናኘት እንቸገራለን ይህም የሚሆነው የራዲዮ ሲግናሎች በርቀት ምክንያ ሲደክሙ ነው፡፡ ለምሳሌ ወፍራም ግድግዳ፣ የብረት መከለያዎች አንዲሁም አኳሪየም የራዲዮ ሞገዶችን ሊያደክማቸው ይችላል፡፡

✅ ዋይ ፋይ ይህ ቃል ለአብዛኛው ተጠቃሚ፤ ሞያተኛውንም ሲጨምር አጋጥሞናል ከ
ኢንተርኔት ጋር እየተለዋወጠ ሲገባ እናየዋለን፡፡ በሞያችንም ለሰዎች ለማስረዳት ስንሞክር አለመግባባት ይከሰታሉ፡፡ እርግጥ ነው ዋይ ፋይ ኢንተርኔት ለማገኘት ይራዳል ነገርግን በራሱ ኢንተርኔት አይደለም፡፡

✅ ዋይ ፋይ ገመድ አልባ የኮምፒውተር ግንኙነት መፍጠሪያ ዘዴ ሲሆን ኢንተርኔትን ጨምሮ የተለያዩ መረጃዎችን፣ ፋይሎችን፣ እንዲሁም እቃዎችን (ፕሪንተር፣ እስካነር) በጋራ እንድንጠቀም ይረዳናል፡፡ ይህ ማለት ደግሞ የባለገመድ ግንኙነት (cable Network) ምትክ መሆኑን ያሳያል፡፡
👍1
✍ከ7-12ኛ ክፍል Textbooks, መማሪያ መጽሀፎችን Textbooks በPDF ይፈልጋሉ?
✔️የፈለጉትን መጽሀፍት በPDF በቴሌግራም ቻናላችን ታገኛሉ!
👇👇የቴሌግራም ቻናሉ👇👇👇👇
https://t.me/EthiopiaDigitalLibrary
https://t.me/EthiopiaDigitalLibrary
https://t.me/EthiopiaDigitalLibrary
https://t.me/EthiopiaDigitalLibrary
አሁኑ ይቀላቀሉ!
ምርጥ ምርጥ መጽሀፎችን በስልካችሁ ማግኘት ትችላላችሁ!
የኢትዮጵያ ዲጅታል ላይብረሪ (Ethiopian Digital Library)
👍1
💢የኮምፒውተርዎ 💻 desktop ላይ #አጫጭር ኖቶችን ✍ ማስቀመጥ ከፈለጉ search bar ላይ ይሒዱና sticky notes ብለው #search ያድርጉ።

⚠️ለተማሪዎች 👨‍💻 ካነበቡት ነገር ውስጥ #በጣም አስፈላጊ የሆኑ ነገሮችን ለመያዝ እንዲሁም ለሌሎቻችንም #ስልክ_ቁጥር፤ቀጠሮ እና የመሳሰሉትን ለመያዝ ጠቃሚ 👍 ናት ይሞክሯት።
SHRE SHARE
MuhammedAminWebsite_1_1.0 (1).apk
156.1 KB
ይህች App የኔን ዌብሳይት የምትከፍትላችሁ App ናት ገብታችሁ ጠቃሚ የሆኑ መረጃዎችን ማግኘት ይችላሉ!
ይሞክሯት!
👆👆👆👆👆👆👆👆
✳️ Google ካስጠነቀቃቸው ነገሮች ውስጥ አንዱ እና ዋነኛው የ Google አካውንታቺን ለርጅም ጊዜ ካልተጠቀማቹበት Google ራሱ አካውንቱን ሙሉ ለሙሉ እንደሚሰርዝ (Delete) እንደሚያርገው Google ባለፈው ወር አሳውቋል፡፡

🔻ስለዚህ የ Google አካውነታችሁ እንዳይሰረዝ አካውንታችሁን አሁኑኑ መጠቀም በመጀመር አካውነታችሁን Active እንዲሆን ማድረግ ትችላላችሁ፡፡

🔻አካውነታችሁን Active እንዲሆን የተለያዩ ነገሮች መጠቀም ትችላላችሁ። ለምሳሌ፦ በ Gmail (Email) ከጓደኛቹህ ጋ ማውራት ፤ Google Drive ፤ Google Photo እና የመሳሰሉ የ Google አገልግሎቶችን ሊጠቀሙ ይገባል ብሏል Google፡፡

🔻የ Google አካውንታቸው የተሰረዘባቸው ሰዎች ከዚህ በፊት የተለዋዋጧቸው ኢሜሎችም ሆነ ሌሎች ግላዊ መረጃዎች ሙሉ ለሙሉ እንደሚሰርዝ ጎግል አስጠንቅቋል፡፡

🔻ስለዚህ የ Google አካውነታችሁን ግዜው ሳይደርስ አሁኑኑ መጠቀም ጀምሩ።

✅በ ©Just_Offical የቀረበ።
✅✅ስለ_ኢትዮሳት✅✅

💥ሰሞኑን በተደጋጋሚ ስለ ETHIOSAT ከሚነሱ ጥያቄዎች መካካል ግልፅ መረጃ እንዲኖራችሁ የሚከተሉትን ነገሮች አዘጋጅተናል።

1, ኢትዮሳት ከተቀላቀሉ የሀገር ውስጥ ቻናሎች አብዛኞቹ ከ ጥር 13 ጀምሮ የ ናይል ሳት ስርጭታቸው ያቆማሉ።

⭕️ከጥር 13 ጀምሮ ከናይል ሳት የሚወጡ ቻናሎች ዝርዝር ውስጥ

👉FANA TV
👉WALTA TV
👉ETV
👉Amhara TV
👉Asham TV
👉OBN
👉OBS ይገኙበታል

2, ኢትዮሳት ለመጠቀም የግድ የሰሀኑ አቅጣጫ ከነበረበት በተቃራኒ በስተምስራቅ ዞሮ መስተካከል ይኖርበታል

3, ኢትዮሳት ላይ የገቡ ቻናሎች አብዛኞቹ በHD ስርጭት ስለሚተላለፉ አነርሱን ለማግኘት HD ሪሴቨር ያስፈልጋል።

4, ኢትዮሳት በ SD ይሰራል! ነገር ግን እስካሁን ባለው ሁኔታ በ Sd ሪሴቨር የሚሰሩት ውስን(14) ቻናሎች ብቻ ናቸው።

5, ኢትዮሳት እና ናይል ሳት በ አንድ ሰሀን አይሰሩም ሁለቱንም ለመጠቀም ሁለት ሰሀን ያስፈልጋል።

6, ኢትዮ ሳት የሚገኝበት ሳተላይት NSS 12 57E ሙሉ ኢትዮጵያ ከፍተኛ ሽፋን ስላለው ከ 60CM ዲሽ ጀምሮ ይሰራል።

7, ሪሴቨሮች ላይ ከሚነሱ ጥያቄዎች መካከል በተለይ SUPERMAX 2350 SUPERTECH
በ 11105 H 45000 ላይ ሲግናል ችግር ያመጣል መፍትሄው ሪስቨር መቀየር ነው።

👉 ይህ frequency 11105 H 45000 የገመድ ችግር ካለም የማስቸገር ባህሪ አለው

8, ሪሴቨራቹ ላይ NSS12 የሚል ከሌለ SATELLITE LIST ላይ ADD ማድረግ ወይም አንደኛው ሳተላይት ላይ ፍሪክዌንሲውን መሙላት ይቻላል።

✅ #አዲሱን_የኢትዮ_ሳት - አዲሱን የኢትዮጵያውያን ቻናሎች መገኛ ሳተላይት እንዲሁም ለማንኛውም አይነት የዲሽ ብልሽትም ሆነ አዲስ ዲሽ ለማሰራት ከፈለጉ #በጥራት እና #በዋስትና እንዲሁም #በተመጣጣኝ_ዋጋ እንሰራሎታለን ይደውሉልን።

አድራሻ
💥አጋሮ/ጅማ/
📲 +251938095912
📲 +251941301488

ለማንኛውም ጥያቄ በቴሌግራም @J_Dishbot ይጠቀሙ!!
Copy From Agaro Dish &Technology Info.
❤1👍1
የኢትዮሳት ብቸኛ ጥቅሞች
Ethiosat Exclusive Benefits
➧ሀ/የሳተላይት ክፍያ
የሳተላይት ቻናሎች ክፍያ በሚይዙት ባንድዊድዝ የሚወሰን ቢሆንም ኢትዮሳት ላይ የሚገኙት ቻናሎች ክፍያ ከሌላ ሳተላይት ጋር ሲነፃፀር በግማሽ ይቀንሳሉ። ይህ ደግሞ ሌላ ሳተላይት ላይ በSD ጥራት ያስተላልፉ ከነበረ በHD እንዲያደርጉት እድል ይፈጥርላቸዋል። በተጨማሪም ለሌሎች የፕሮዳክሽን ሥራዎች ትርፍ ይኖራቸዋል።
➧ለ/የቻናሎች ይዘት
በሌሎች ሳተላይቶች የሚገኙ ቻናሎች የአገራቸውን ጥቅም ከማስጠበቃቸው የተነሳ በርካታ ቻናሎች ከፍላጎታችን ውጭ ይገባሉ። በተጨማሪም እያንዳንዱ ተፈላጊ ኢትዮጵያዊ ቻናል የተለያየ ፍርኩየንሲ ያለው ከመሆኑ እንፃር ቻናሎችን ፈልጎ ቅደም ተከተል ለማስያዝ ብዙ ሰዓት ይወስዳል። ኢትዮሳት ላይ ያሉ ፍሪኩየንሲዎች ግን ለጊዜው ከ125 በላይ ናቸው ሰርች በሚደረግበት ሰዓትም የሚገቡት ጠቃሚዎቹና የተመረጡ ኢትዮጵያዊ ቻናሎች ብቻ ናቸው።
➧ሐ/ የቻናሎች ጥራት
እኛ ኢትዮጵያዊያን ጥራት ይገባናል። ስለሆነም ኢትዮሳት ላይ የሚገኙ አብዛኛዎቹ ቻናሎች ከፍተኛ ጥራት ያላቸው (HD) ናቸው። ቁጥራቸው ቀላል የማይባል ሰዎች SD ሪሲቨር ያላቸው መሆኑንም በመገንዘብ ለ6 ወራት የሚቆዩ የተወሰኑ ቻናሎች በSD ይሰራሉ ። ነገር ግን በዘላቂነት ቻናሎቹን በጥራት ለመመልከት HD ሪሲቨር ያስፈልጋል።
➧መ/ በዛፍ እና በግንብ የመከለል ሁኔታ
ይህ ሳተላይት 57°E እንደመሆኑ መጠን ከፊት ለፊት በሚኖር ዛፍ ወይም ግንብ የመከለል ሁኔታው ዝቅተኛ ነው። በተለይ ኮንዶሚኒዬሞች ላይ ሀገርኛ ቻናሎችን ለማግኘት ሲቸገር ለነበረ ሰው ችግሩን ያቃልልለታል። በዛፍ የተከበቡ መኖሪያ ቤቶችም እንዲሁ።
➧ሠ/ ኳስ የማግኘት ሁኔታ
ከዚህ በፊት ብዙ የእግርኳስ ተጠቃሚ ያለው ቫርዚሽ ቲቢ ከኢትዮሳት የሚርቀው 4.5° ስለሆነ ሌላ ተጨማሪ ዲሽ ሳያስፈልግ በቀላሉ አንድ LNB እና ስዊች በመጨመር ተጠቃሚ መሆን ይቻላል። ምናልባት ሌሎች ሳተላይቶች ላይ የማናገኛቸው የፊልም ቻናሎችንም እዚሁ ሳተላይት ላይ እናገኛለን።
➧ረ/ የቀጣይነት ሁኔታ
የዚህ ሳተላይት ባለቤት በቀመጫውን ሉግዘንበርግ ያደረገው SES ካምፓኒ ሲሆን ኢትዮሳት በብቸኛነት የተከራየው ለኢትዮጵያውያን የተዘጋጀ ሳተላይት ነው። ሆኖም የሳተላይቱ "Orbital Position" ኢትዮጵያ አናት ላይ ስለሆነ ኢትዮጵያ የራሷን የኮሙኒኬሽን ሳተላይት ከ3 ዓመት በኋላ ስታመጥቅ 58.3°E ላይ ያርፋል። ስለሆነም ምንም አይነት ተጨማሪ የዲሽ እንቅስቃሴ ሳይደረግ ፍሪኩየንሲ ብቻ በመሙላት ኢትዮጵያዊ ቻናሎችን በቀጣይነት መጠቀም ይቻላል።
➧ሰ/ ፖለቲካዊ እና ሃይማኖታዊ ቻናሎች
በዚህ ሳተላይት የሚተላለፉ ቻናሎች ሐይማኖታዊም ይሁን ፖለቲካዊ ይዘት ይኑራቸው ገደብ የለባቸውም። ነገር ግን ሀገርን አደጋ ላይ ሊጥሉ የሚችሉ ቻናሎች ላይ እንደስከዚህ በፊቱ በ"Jaming" የሚዘጉ ሳይሆኑ ስርዓት ባለው መንገድ ኢትዮሳት ከሳተላይት ካንፓኒው ጋር የሚደራደርባቸው እና ማስተካከያ የሚደረግባቸው ይሆናል። በዚህ በኩል የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት የራሱ የሆነ ድርሻ አለው።
👍3❤1
ልታውቋቸው የሚገቡ Commands እንዴት አድርገን የኮምፒውተራችንን Users ማስተዳደር እንችላለን?
🔶 በመጀመሪያ ደረጃ Command Prompt ወይም CMDን እንከፍታለን።
ለምክፈት በ3 አማርጮች እንጠቀማለን
1ኛ Start-> All Program -> Accessories -> Command Prompt ከዛም Right Click በማድረግ Run as Administrator ብለው ይጫኑ
2ኛ Crtl+R በመጫን CMD ብለው በመጻፍ OKን ይጫኑ
3ኛ start -> Search Box ላይ CMD ወይም Command Prompt ብለው ይፈልጉ።
ከዛም Right Click በማድረግ Run as Administrator ብለው ይጫኑ
ከዛም ከሶስቱ 1ን አማራጭ ተጠቅመው ሲከፍቱት Black Screen ይመጣላችኋል። ከዛም ከታች ከ1-8ኛ ድረስ ያለውን ተግባራቶችን ይሞክሩ።
አዘጋጅ Muhammed Computer Technology
✅ 1ኛ net user ይህ ኮማንድ የሚጠቅመን ከኮምፒውተራችን ያሉንት Users ይዘረዝርልናል። እንዲሁም ከማንኛውም ኮምፒውተር ላይ Administrator የሚል አካውንት አለ እሱ ምን እንደሆነ ከታች መልሱን ያገኛሉ።
✅ 2ኛ net user muhammed /add ይህ ኮማንድ ከኮምፒውተራችን ላይ muhammed የሚባል User Create(እንዲፈጠር ያደርግልናል)
✅ 3ኛ net user muhammed * ይህ ኮማንድ ከላይ ለፈጠራችሁት muhammed ለሚባል User ወይም ከዚህ በፊት ላለ User ለምሳሌ amin የሚባል ቢኖር Muhammed በሚለው ፈንታ amin የሚለውን ስታስገቡ ለUseሩ Password እንድታስገቡ ይጋብዛችኋል። ትኩረት‼️ሁለት ጊዜ password እንድታስገቡ ይጠይቃችኋል ሁለቱም password ተመሳሳይ መሆን አለበት። እንዲሁም ፓስውርድ ስታስገቡ እይታያችሁም ወይም ፓስወርድ ስትጽፉ አይታያችሁም ግን በውስጥ ታዋቂነት እየጻፈ ስለሆነ ግራ እንዳትጋቡ።
ነገርግን ለUseሩ password ነስጠት ባትፈልጉ ዝም ብላችሁ 2 ጊዜ Enterን መጫን ብቻ ነው።
✅ 4ኛ net user muhammed /add * ይህ ኮማንድ የሚያገለግለን አንድን User ከነ password Create(መፍጠር) ብትፈልጉ ይህንን መጠቀም አለባችሁ። ኮማንዱ በመጀመሪያ ደረጃ User create ያደርግና በተመሳሳይ ፓስወርድ እንድታስገቡ ይጋብዛችኋል። password ማስገብት ከፈለጋችሁ አስገቡ ግን password ማስገባት ካልፈለጋችሁ Enterን 2 ጊዜ ይጫኑ።
ይህ ማለት ከላይ ተ.ቁ 2ና 3ን በአንድ ጊዜ ለመስራት ያገለግለናል።
✅ 5ኛ net localgroup Administrators muhammed /add ይህ ኮማንድ ከላይ የፈጠርነው user ምን ጊዜም Standard User ነው የሚሆነው።
በኮምፒውተር ተጠቃሚዎች አይነት Users Type በ3 ይከፈላል 1ኛ Administrator 2ኛ Standard User 3ኛ Gusts ናቸው።
እነዚህ Users ለምሳሌ ከላይ የፈጠርነው User Muhammed የሚባለው ከላይ ባለው ኮማንድ ሲፈጠር Standard User ነው። Standard User ደግሞ በኮምፒውተሩ ላይ ሙሉ የሆነ የመቆጣጠር አቅም የለውም የግድ ምን መሆን አለበት Administrator መሆን አለበት።
ስለዚህ ከላይ ያለውን 5ኛ ተ.ቁን Command መጠቀም ይኖርብናል።
✅ 6ኛ net localgroup Administrators muhammed /del ይህ ኮማንድ በተ.ቁ 5 ላይ muhammed የሚባለውን User ወደ Administratorነት ቀይረነዋል ነገር ግን ወደ Standar User ለመቀየር ከተፈለገ 6ኛውን ኮማንድ መጠቀም አለብን ማለት ነው። ይህም Muhammed የሚባለውን User ከ Administrator Account Type ወደ Standard User Account Type ቀየርነው ማለት ነው።
✅ 7ኛ ከማንኛው ኮምፒውተር ላይ Administrator የሚባል User አለ ይህ User ለአደጋ ጊዜ ተብሎ የተቀመጠ User አለ ይህ User ከኮምፒዩተሩ ተደብቆ ሁኖ ነው ያለው ይህንን User መሉ በሙሉ ከኮምፒውተሩ ማጥፋት አይቻልም ነገርግን ሌሎች የተፈጠሩ User Account ማጥፋት ትቻላል። ለእናንተ የምመክራችሁ User Accountችን ሊጠፋብን ይችላል የሚል ስጋት ካለባችሁ Administrator የሚባለውን User Account Active ማድረግ አለባችሁ አሁን እሱን እናያለን!
🛑 net user Administrator active:yes
ከኮምፒውተሩ የተፈጠረን User Account ሳናጠፋ Inactive ለማድረግ ወይም እንዳይሰራ ለማድረግ ለምሳሌ muhammed የሚለውን እንዳይሰራ ለማድረግ።
🔷 net user muhammed active:no ይህ ኮማንድ muhammed የሚባለው user inactive ሁኗል ማለት ነው። እንደገና ግን Active ለማድረግ ከፈለጋችሁ
🔶 bet user muhammed active:yes የሚለውን ኮማንድ ተጠቀሙ።
✅ 8ኛ ከኮምፒውተሩ ያለውን User Account ሙሉ በሙሉ ለማጥፋት ከፈለጋችሁ ለምሳሌ muhammed የሚባለውን ማጥፈት ብትፈልጉ
🛑 net user muhammed /del
ማስጠንቀቂያ ይህ ኮማንድ ለምሳሌ muhammed የሚባለውን user መረጃ ሙሉ በሙሉ ነው የሚያጠፋው ያ ማለት በውጡ ያስቀመጣቸው Desktop ላይ My Documents ላይ My Music ላይ My Picture ላይ ያስቀመጣቸውን ሙሉ መረጃ ያጠፋብናል ስለዚህ ትኩረት ማድረግ አለባችሁ።
ግን ለትምህርት ለምሳሌ እንደእስካሁኑ muhammed የሚባል User Account ላይ እንደ መለማመጃ ልትጠቀሙበት ትችላላችሁ።
#ይሞክሩት!
ከተመቻችሁ ለሌሎች እንዲደርሳቸው #ሼር ቢያደርጉ ጥሩነት ነው።
👍2
የ10ኛና 11ኛ ክፍል Teacher Guide በPDF ከፈለጋችሁ።
ከታች ባለው ሊንክ ገብታችሁ ማግኘት ትችላላችሁ።
👇👇👇👇👇👇👇👇👇
@EthiopiaDigitalLibrary
@EthiopiaDigitalLibrary
@EthiopiaDigitalLibrary
@EthiopiaDigitalLibrary
✿በተደጋጋሚ በስራ ቃለመጠይቅ/ ኢንተርቪው ጊዜ
የሚጠየቁ ጥያቄዎች✿
ክፍል1
በተደጋጋሚ የሚጠየቁ ወደ 30 የሚደርሱ ጥያቄዎችንና ልታሰጡ የሚገባቸውን ምላሾች እንዲሁም ማድረግ የሚገባችሁን ጥንቃቄ በተመለከተ ለዛሬ 10 ያህሉን ይዘናል ቀሪዎቹን በሌላ ጊዜ የምናቀርብ ይሆናል፡፡
1, እስኪ ስለራስህ ንገረን?
ይህ ጥያቄ እንዲሁ በግርድፉ ሲታይ ቀላል ይመስላል ይሁን
እንጂ ብዙዎች ገና ከጅምሩ ስህተት የሚሰሩበት ነው፡፡ ብዙ
ተጠያቂዎች ለዚህ ጥያቄ መልስ የሚመስላቸው ስለራሳቸው የህይወት ታሪክ ማውራት ነው ፡ ይሁን እንጂ እንዲያ ለማለት ሳይሆን በስራ ህይወት ላይ ስላለህ ማንነት ፡ የስራ ልምድ
ካለህ በዚያኛው የስራ ቦታ ስላስመዘገብካቸውና ስለሰራሀቸው ጥሩ ስራዎች እንዲሁም ጀማሪ ተቀጣሪ ከሆንክ በዩኒቨርሲቲ ቆይታህ ስለነበረህ መልካም እንቅስቃሴ ወይም ስለሰራኸው የመመረቂያ ፕሮጀክት ልታወራ ትችላለህ፡፡ በንግግርህም ወቅት ጠያቂው የመጀመሪያ ምርጫው እንድትሆን ጠቃሚ ነገሮቹ ላይ ትኩረት አድርግ፡፡
2,ስለዚህ የስራ መደብ እንዴት ሰማህ??
ሌላው በተደጋጋሚ የሚጠየቀው ጥያቄ ይሄ ነው ፡ በዚህ ወቅት ማድረግ የሚገባችሁ ነገር በትክክል ስለዚህ የስራ መደብ የሰማችሁበትን ቦታ በግልፅ ተናገሩ ፡ በጋዜጣ ; በማስታወቂያ ቦርድ ; በጓደኛችሁ አልያም በማህበራዊ ድህረ ገፆች ላይ አይቼ አመለከትኩኝ ማለት ትችላላችሁ፡፡
3፡ ስለመስሪያ ቤታችን ምንተውቃለህ?
ይህ ጥያቄ ለጠያቂው የሚሰጠው ትልቅ መልዕክት አለ ፡ በተቻለ መጠን ወዳመለከታችሁበት መስሪያቤት ከመሄዳችሁ በፊት ስለ መስሪያቤቱ በቂ ግንዛቤ ሊኖራችሁ ይገባል ፡ ተልዕኮውን, አላማውን, ራዕዩን በግልፅ ልትረዱ ይገባል
እናንተም በዚሁ መስሪያቤት ተልዕኮ አላማና ራዕይ ውስጥ
ልታበረክቱ ስለምትችሉት ነገር በአጭሩ ተናገሩ፡፡
ያመለከታችሁበት መስሪያ ቤት ድህረገጽ ካለው About
የሚለውን በመጫን መረጃውን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
አልያም በአንዳንዶቹ ዘንድ ገና ወደ ግቢያቸው ስትገቡ ተገቢውን
መረጃ በሆነ ቦርድ ወይም በአንዳች ነገር በግልፅ ተፅፎ ታገኙታላችሁ፡፡
ለዚህ ጥያቄ ተገቢውን ምላሽ መስጠት ለስራው የሰጣችሁትን ትኩረት ያሳያል፡፡
4፡ ለምን እዚህ መቀጠር ፈለክ ?
ብዙውን ግዜ ቀጣሪዎች በቅጥር ወቅት ሊቀጥሩ የሚፈልጉት በተቻለ መጠን ልህቀቱ ጥሩ የሆነውን ሰው ነው እናም ለሚጠየቀው ጥያቄ አሳማኝ መልስ መስጠት አንዱ ማሳያ
ነው፡
★የእናንተ መስሪያ ቤት ትኩረት አድርጎ በሚሰራባቸው ዘርፎች ላይ ብሳተፍ ትልቅ አስተዋፅኦ እንደማበረክት ስላመንኩኝ፡፡
★ መስሪያ ቤቱ ትልቅ እና መልካም እንቅስቃሴዎችን እያስመዘገበ በመሆኑ እኔም የዚህ አካል መሆንን ስለምፈልግ፡፡
★ ያመለከታችሁበት መስሪያ ቤት የሚሰጠውን አገልግሎት በመለየት እንደዚያ አይነት ግልጋሎት የሚሰጡ ቦታዎች ላይ መሆን በህይወታችሁም ላይ እንዲሁም ለህሊነሠችሁ የሚሰጠውን እርካታ ተናገሩ፡፡
5, ለምን አንተን እንቀጥርሀለን?
እንዲህ የሚል ጥያቄ ከተጠየቃችሁ አልፈለጉኝም ማለት
ነው ብላችሁ እንዳትደነግጡ ይልቁን ደስ ሊላችሁ ይገባል ምክንያቱም በጠያቂው ዘንድ ጥሩ ቦታን አግኝታችኋል ማለት ነው ፡ እናም በዚህ ወቅት
★ እናንተን በመቅጠራቸው በመስሪያ ቤቱ ጉዞ ላይ የእናንተን አቅም በመጨመር ተገቢውን አገልግሎት እንደምትሰጡ፡፡
★ በቡድን እንቅስቃሴ ውስጥ የቡድኑን አንድነት በማጠናከር ለመስሪያቤቱ እድገት ጉልህ አስተዋጽኦ እንደምታበረክቱ
ተናገሩ፡፡
እንዲሁም መሰል ምላሾችን አክሉበት
6፡ በሙያህ ጠንካራ ጎኖች አሉኝ ብለህ የምታምናቸው ነገሮች ምንድን ናቸው?
★ ያሉህን እውነተኛ ጥንካሬዎች ተናገር ፡ እንዲኖርህ የምትፈልገውን ሳይሆን ያለህን ነገር፡፡
★ ከምትወዳደርበት የስራ መደብ ጋር ተያያዥነት ያላቸውን
ሙያዊ ጥንካሬዎችን አስቀድም፡፡
7፡ ድክመቶችህ ምን ምን ናቸው?
ሀለሉም ሰው ድክመቶች ቢኖሩበትም ቅሉ በስራ ቃለ
መጠይቅ ወቅት እኒህ እኒህ ድክመቶች አሉብኝ ብሎ መናገር አይመከርም ይልቁን የሚታይ ድክመት አለብኝ ብዬ አላምንም ለዚህም ማስረጃ የሚሆነኝ እኔ ባለብኝ ድክመት ምክንያት ነገሮች
ተበላሽተውበኝ አለማወቃቸው አንዱ ማሳያዬ ነው ብሎ መመለስ ተገቢ ይሆናል፡፡
8፡ በሙያህ ያስመዘገብከው ስኬት ምንድነው?
አሁን ልትቀጠርበት ባለው የሙያ ዘርፍ ቀደም ብለህ ያስመዘገብከውን ውጤት ተናገር ፡ የሰራኸውን ነገር መናገር ጉራ አይደለምና ዘና ብለህ ስላበረከትከው ነገር አውራ ፡
ጀማሪ ተቀጣሪም ከሆነክ መመረቂያህ ተግባራዊ ተደርጎ ተሰርቶ ከሆነ እሱን ጥቀስ፡፡
9፡ ቀደም ብሎ በነበረህ የስራ ወቅት የገጠመህ ግጭት ወይም አለመግባባት ነበር ወይ? ከገጠመህስ እንዴት ፈታኸው?
አስተውል ጠያቂህ ይህን ጥያቄ የጠየቀህ ስለአንተ ጀብድ ወይም ሌላ ለመስማት ሳይሆን፡ ለችግሮች ምላሽ የምትሰጥበትን መንገድ ለማወቅ ነው ፡ እናም ጉዳዩ ገጥሞህ ከሆነ የፈታህበትን መንገድ ጥበብ በተሞላበት መልኩ መልስ፡፡
10: ከአምስት አመት በኃላ እደርስበታለሁ ብለህ የምታስበው ራዕይ ምንድነው? የምር ራዕያችሁ የሆነውን ነገር መናገር ተገቢ ነው ፡ ልትደርሱበት የምትፈልጉበትን ቦታ ግልፅ መሆኑን ሊለካ እና ሊደረስበት የሚችል ነገር ተናገሩ ፡ በዛው መስሪያ ቤት እስከ መጪዎቹ አምስት አመታት የመቆየት ሀሳብ ካላችሁ በዛ
መስሪያቤት የት ቦታመድረስ እንደምትፈልጉ ጭምር ተናገሩ፡
ይህም ከእነርሱ ጋር የረጅም ጊዜ እቅድን አንግባችሁ እንደመጣችሁ እንዲረዱ ያደርጋቸዋል፡ እናም ከሌሎች ተወዳዳሪዎች በተሻለ ትኩረት እንድትስቡ ያደርጋችኃል
ማለት ነው፡፡
እንግዲህ እነኚህንና የመሳሰሉትን ነገሮች ተግባራዊ ማድረግ በቃለመጠይቅ ወቅት የተሻለ ማንነት እንድትላበሱ ያደርጋችኃል ብለን እናስባለን፡፡
ክፍል ሁለት እንሆ!!
➊ 11; ለምን አሁን ያለህበትን ስራ ትለቃለህ? አስተውሉ ለዚህ ጥያቄ በምትመልሱት መልስ ለቀጣሪዎቻችሁ ከአንድ በላይ ትርጓሜን ያሰጣል በመጀመሪያ ደረጃ ቀድሞ ስትሰሩበት የነበረውን መስሪያ ቤት መጥፎነት ለመናገር አትድፈሩ ይልቁን አዲስ ነገር ለማወቅ ፍላጎት እንዳላችሁ ፣ አሁን እየተወዳደራችሁ እንዳላችሁበት አይነት የስራ ዘርፍ ላይ መስራት ህልማችሁ እንደሆነ ፣ ለምሳሌ፦ ያመለከታችሁበት መስሪያ ቤት ለህዝብ አገልገሎት መስጠት ከሆነ ፡ እናንተ በቀጥታ ከህብረተሰቡ ጋር የሚያገናኙ ስራዎች ላይ መስራት እንደምትፈልጉ ይሁን እንጂ ቀድሞ የነበራችሁበት እንዲህ አይነቱን አገለግሎት እንደማይሰጥ ፡ ከዚህም መነሾነት የቀደመውን ስራችሁን ለመተው እንደወሰናችሁ ተናገሩ፡፡
➋ 12 ፦ ምን አይነት የስራ አካባቢ ያስደስትሀል / የስራ መንፈስ / Work environment ?
በዚህ መስሪያ ቤት ከማመልከታችሁ በፊት በዛ ቦታ
ስላለው የስራ መንፈስ በቂ ጥናት እንዳደረጋችሁና እንደተማረካችሁበት በመጥቀስ አሁን እያመለከታችሁ እንዳላችሁበት አይነት የስራ መንፈስን እንደምትመርጡ መናገር ትችላላችሁ፡፡
➌ 13 ፦ ምን አይነት የአመራር ስልትን ትከተላለህ?
ምናልባት አሁን እያመለከታችሁ ያላችሁበት የስራ መደብ
የአመራርነት ላይሆን ይችላል ነገር ግን ቀጣሪዎቻችሁ ይህን
ጥያቄ የሚጠይቋችሁ ከእነርሱ ጋር በምትዘልቁበት ወቅት
ምናልባት በአመራርነት የመስራታችሁ እድል ስላለ ምን
አይነት መሪ እንደሆናቸህ ቀድመው የሚለኩበት ነው፡ ጥሩ መሪ ጠንካራ እና ከነገሮች ጋር ተጣጣፊ መሆን የሚችል ፣ በቡድን ስራ
የሚያምን እና የገዢነት ሳይሆን የመሪነት ስሜት የሚሰማው
አይነት ነው፡፡ እናንተም በእንዲህ አይነት የመሪነት ዘርፍ ውስጥ የምትመደቡ መሆኑን ግለፁ፡፡
➍ 14 ፦ ጓደኞችህ ወይም
በተደጋጋሚ በስራ ቃለመጠይቅ/ ኢንተርቪው ጊዜ
የሚጠየቁ ጥያቄዎች✿
ክፍል 2 ክፍል 1ን ያንብቡ መጀመሪያ
ስለአንተ ምን
ይላሉ?
ይህን ጥያቄ ስትመልሱ ታማኝ ሆናችሁ መልሱ ምክንያቱም
ሁሉን መስፈርት አሟልታችሁ ለቅጥር ብቁ ከሆናችሁ ወደቀድሞ አለቃችሁ ወይም በCV ላይ ወደገለፃችሁት ሰው መደወላቸው ስለማይቀር፡፡ እውነተኛ ጠንካራ ጎናችሁን በተሰጣችሁ ፕሮጀክት ላይ እስከምን ድረስ ገፍታችሁ እንደምትሄዱ ተናገሩ፡፡
➎ 15 ፦ ለምን ይህን ያክል ጊዜ ሳትቀጠር ተቀመጥክ?
ከተመረቃችሁ በኃላ ወይም ከቀድሞ ስራችሁ ከወጣችሁ
በኃላ እስከአሁን ድረስ ( የጊዜ ክፍተት ካለ) ለምን ስራ እንዳልገባችሁና በዚህ ጊዜ ምን ስታደርጉ እንደነበረ ስትናገሩ በተቻለ መጠን ጊዜውን እንዳባከናችሁ አርጎ እንደማይሰማችሁ እና በበጎ ፈቃደኝነትም ይሁን በሌላ መልክ ስታገለግሉ እንደነበረ አልያም ጥቂት ጊዜ እረፍት ማድረግ ፈልጋችሁ እንደነበረ ግለፁ፡፡
➏ 16 ፦ በተቀጠርክ በመጀመሪያዎቹ ሶስት ወራት ውስጥ ምን ትጠብቃለህ?
በተለየ መልኩ የቀጣሪዎችን ትኩረት ለማግኘት ብላችሁ
የማይጨበጠና የማይመስል ነገር አትናገሩ፡ መስሪያ ቤቱን መላመድና በአግባቡ ከስራ ባልደረቦቻችሁ ጋር የቡድን መንፈስን በማምጣት ይህንና ያንን ላበረክት እፈልጋለሁ ማለት ይቻላል፡፡
➐ 17 ፦ ስለ ደመወዝ የምትለው ነገር ምንድነው?
ቅጥሩ ሲወጣ ደመወዝ የተገለፀ ወይም በድርጅቱ ስኬል ከሆነ ይህ ጥያቄ አይነሳም ይሁን እንጂ የደመወዝ ሁኔታ በስምምነት ከሆነ እናንተ ሊከፈላችሁ የሚገባውን ደመወዝ ቀድሞ ያሉ ሰራተኞች ከሚከፈላቸውና እናንተ ካለችሁ የትምህርት ዝግጅት ብሎም የስራ ልምድ አንፃር ይህን ያክል ብላችሁ መደራደር ትችላላችሁ ፡ በርግጥ ቀጣሪዎች ይህን ያክል ልንከፍልህ
እንችላለን ሊሏችሁ ይችላሉ ነገር ግን እናንተ ሊከፈላችሁ ይገባኛል ከምትሉት ጋር መደራደር ይቻላል፡፡
➑ 18 ፦ ከስራ ውጪ ምን ማድረግ ያስደስትሀል? ከስራ ውጪ ብዙጊዜ የምታደርጉትን እውነተኛውን ነገር ተናገሩ ምንም እንኳ አንዳንድ ጊዜ በህብረተሰቡ ዘንድ ቅቡልነት የሌላቸውንና በይፋ የማይነገሩ ባህሪያት ካሏችሁ እነሱን መጥቀስ የእስካሁኑን ጉዞ ውሀ እንዲበላው ሊያስደርግ ስለሚችል ጥንቃቄ አድርጉ፡፡
➒ 19 ፦ እንሰሳ ብትሆን ኖሮ ምን አይነቱን ትመርጥ ነበር?
እንደዚህ አይነት ወጣ ያለ ጥያቄ ለነገሮች ከተለመደው እይታ ውጪ የምትመለከቱበትን መነፅር ለማየት እንጂ ውሻ ወይ ድመት ወይ ደግሞ አንበሳ የሚለውን ለመስማት አይደለም ነገር ግን ለምን ያንን እንደመረጣችሁ የምታስረዱበትን መንገድ
ስለሚመዘን ለምትሰጡት መልስ ምክንያታዊ ሁኑ፡፡
➓ 20 ፦ ጥያቄዎች አሉህ?
የመጨረሻው የሚሆነው ጥያቄ የሆኑባችሁን ነገሮች መጠየቅ ነው ስለሆነም እነዚህን ጥያቄዎች ጠይቃችሁ አመስግኖ መውጣት ነው፡፡
❖ በመጨረሻም ❖
በCV ላይ የፃፋችኃቸው ነገሮችን በአግባቡ ማስተዋል ተገቢ ነው ምክንያቱም አንዳንድ ጊዜ እዛ ላይ ያሉ ነገሮችን ደግመው ስለሚጠይቋችሁ አንድ አይነት ነገር መመለስ መቻል አለባችሁ፡፡
How to write CV
በቀጣሪዎች ዘንድ ተመራጭ CV እንዴት መፃፍ ይቻላል፡፡
CV ማለት የአንድ ሰው የትምህርትና ሌሎች professional ታሪኮቹን በአጭር መልኩ የሚገለፅበት መንገድ ነው፡፡ ብዙ ግዜ ለስራ ማመልከቻነት እንጠቀምበታለን የራሳችንንም ማንነት በጥሩና ቀለል ባለ መልኩ ለማቅረብ ያስችለናል፡፡ ታዲያ በዚህ ወቅት እንዲቀጥሩን ለምንፈልጋቸው ቀጣሪዎች አሰልቺ ያልሆነና ሳቢ የሆነ CV መፃፍ ትልቅ ትኩረት ለማግኘት ያስችለናል፡፡
ታዲያ እንዴት እንዲህ ያለውን CV መፃፍ እንችላለን እና ምን ምን መካተት አለበት የሚለውን እንመልከት፡፡
፩ ከቀድሞ ስራ ጋር የተያያዙ የስራ ልምዶች፡፡
፪ የትምህርት ሁኔታ እና ሌሎች ተዛማጅ ችሎታዎች
፫ አፃፃፋችሁን ለማንበብ እና ለመረዳት ቀለል ባለመልኩ ይሁን
፬ የስራ ልምድ ካላችሁ በቀደመው ስራችሁ ያሳካችኋቸውን ነገሮች ጥቀሱ፡፡ ጀማሪ ከሆናችሁ ደግሞ በነፃ አገልግሎት እንዲሁም በተማራችሁበት የትምህርት ተቋም ስታደርጉ የነበረውን መልካም እንቅስቃሴ ጥቀሱ፡፡
፭ ፊደላት እና ቃላት አጠቃቀም ትኩረት ማድረግ ፡፡
፮ እናንተ በመስሪያ ቤቱ ብትቀጠሩ ልታበረክቱ የምትፈልጉትንና እናንተ በመቀጠራችሁ በመስሪያ ቤቱ
ስኬት ላይ ልትጨምሩ የምትፈልጉትን ጥቀሱ
፯ አድራሻችሁን ስትጠቅሱ የተለያዩ አማራጮችን አስቀምጡ፡ ስልክ ኢሜይል፡፡
፰ ሪፈረንስ ስትጠቅሱ ስለእናንተ በደንብ ሊገልፅ የሚችል ሰው ይሁን፡፡
፱ ከሁለት ገፅ ባይበልጥ መልካም ነው አሰለቺ እንዳይሆን ተጠንቀቁ፡፡
★★★ማድረግ የሌለባችሁ★★★
1 የቃላትና ፊደላት ግድፈት እንዳይኖር ተጠንቀቁ፡፡
2 የማይሰራና የማትገኙበትን አድራሻ አትጠቀሙ፡፡
3 ራሳችሁን ስትገልፁ ግልፅ ያልሆነና የሚያሻማ እንዳይሆን
4 ውሸት!!! ውሸት ወንዝ አያሻግርም በፍፁም አትዋሹ፡፡
እውነተኛው ማንነታችሁን ብቻ ግለፁ፡፡ እስኪ እነዚህን ነገሮች በ CV ዎቻችሁ ላይ አካቷቸው ጥሩ
ነገር እንደሆነ ተስፋ እናደርጋለን፡፡ እናንተ ያወቃችሁትን ሌሎች
ወዳጆቻችሁ እንዲደርሳቸው ሼር ያድርጉ፡፡
🤔1
📺እንዴት የኮምፕይተራችንን ፍጥነት መጨመር እንችላለን❓

የ ኮምፒዩተራቹ operating system window 10 ነው? በምትከፍቱት እና በምትጠቀሙበት ሰአት እየተንቀራፈፈ አማሯችዋል? እንግዲያውስ ፍጥነቱን ሊጨምሩ የሚችሉ ነገሮችን እናያለን።
1⃣. Power option
Start menu ላይ power option ብላቹ ፈልጉ ከሚመጣላቹ window ውስጥ high performance የሚለውን ምረጡ

2⃣.Disable unwanted start up programs
ይሄ ኮምፒዩተራችንን በምንከፍትበት ጊዜ ያለ እኛ ፍቃድ ፕሮግራሞችን እየከፈተ ፍጥነቱን ከሚቀንሱ ነገሮች አንዱ ነው። ይሄን ለመከላከል
Task manager ላይ መግባት (ይሄን ለማግኘት start menu ላይ right click አድርጎ ማግኘት ይቻላል አልያም Ctrl Alt እና delete የሚለውን አንድ ላይ መጫን)
ከሚመጣው window ውስጥ start up ላይ በማድረግ የማትፈልጉትን ፕሮግራሞች disable ማድረግ። እዚህ ጋር impact የሚለው high ከሆነ disable ባታረጉ ይመረጣል።

3⃣.Defragment and optimize drive
Start menu search bar ላይ defragment ብሎ መፈለግ
Window ሲመጣላቹ የምትፈልጉትን driver መርጣቹ optimize ማድረግ

4⃣. Delete unnecessary temporary file
Start menu ላይ right click አድርጎ run የሚለውን መምረጥ አልያም window key እና R ን ከ ኪቦርዳችን ላይ አንድ ላይ መጫን
%temp% ብሎ ጽፎ enter መጫን
የሚመጣላቹ folder ላይ ያሉ ፋይሎችንctrl + A ተጭነን ሁሉንም ሲመርጥልን ማጥፋት
ድጋሚ run ቦክሱን ከፍታቹ temp ብሎ መጻፍ ከሚመጣላቹ folder ውስጥ ያሉ ፋይሎችን ሁሉ ማጥፋት
አሁንም ለ ሶስተኛ ጊዜ run ቦክስ ላይ prefetch ብሎ መጻፍ የሚመጣላቹ folder ውስጥ የሚገኙ ፋይሎችን ማጥፋት።
እነዚህን የምናጠፋበት ምክንያት ጊዜያዊ እና space የያዙ ፋይሎች ስለሆኑ ነው። ምንም አይነት ችግር አያመጡም።

5⃣. Clean up Memory
This pc ውስጥ ገብታቹ የምፈልጉት local ዲስክ ላይ right click በማድረግ property መምረጥ
Disk clean up የምትለውን icon click ማድረግ
የሚመጣውን የ warning box ok ማድረግ
እዚህ ጋ recycle bin ውስጥ ያሉ ፋይሎች ሳይቀሩ ነው የሚጠፉት

6⃣. Reduce run time service
Run box ከፍታቹ msconfig ብሎ መጻፍ
ቀጥሎ ከሚመጣው window service የሚለውን መጫን
በመቀጠል hide all microsoft service የሚለውን tick ማድረግ በመቀጠል disable የምትለዋን icon click ማድረግ

7⃣. Registry tweaks
Run box መክፈት(window key + R)
regedit ብሎ መጻፍ
Hkey -current user
Control panel
Mouse
Mouse hover time
valueን ወደ 10 መቀየር
እዛው folder ላይ desktop መምረጥ
Menu show delay
Valueን ወደ 10 መቀየር

8⃣. visual effects
Start menu ላይ System ብሎ መፈለግ
Advanced system setting መምረጥ
Advance ውስጥ በመግባት setting መምረጥ
Adjust for best performance መምረጥ
ቀጥሎ የምትፈልጉት ነገር ካለ ቲክ በማድረግ መምረጥ
በመጨረሻም ከላይ ያሉትን ከጨረስን በኋላ ኮምፒዩተራችንን Restart ማድረግ
Ethiopian Universities Viewer.apk
13.8 MB
አስደሳች ዜና !! አዲስ ወደ ግቢ ለሚገቡ ተማሪዎች
EthioICT Garage ስለ እያንዳንዱ በኢትዮፒያ ውስጥ ስለሚገኙ የመንግስት ዩኒቨርስቲዎች የተለያየ አይነት መረጃ የምታገኙበትን ይህንን Android Application አበርክቶላቹሀል።ሁላችሁም ይህን Application በመጠቀም ስል ዩኒቨርስቲ እንዲሁም ዩኒቨርስቲው ስለሚገኝበት አከባቢ መረጃ ማግኝት ትችላላቹህ።
ሌሎች ተጨማሪ Apps ማግኘት ከፈለጋችሁ
👇👇👇👇👇👇👇👇👇 https://t.me/joinchat/AAAAAFJQrwyMTOrtWOA52w
👍1
📱ስማርት ስልክ ባትሪ ለረጅም ሰዓት አገልግሎት⏰
✅ Background process ሚያደርጉ አፖችን ማስቆም
✅ የማትጠቀሙባቸውን Apps Uninstalled ማድረግ Apps በበዛ ቁጥር ባትሪ የመጠቀም አቅም ስለሚጨምር።
✅ ስልካችሁን በማይግልበት መልኩ ይጠቀሙ።
✅ የስልኩን Back cover በማውለቅ ይጠቀሙ።
✅ የያልኩ Internal Storage and SD Memory full ማለት የለበትም።
✅ ቪዲዮ ሲመለከቱ Brightness ይቀንሱ።
✅ ባትሪዎን በጣም የሚጠቀሙ አፕ ማወቅ እና እገዳ መጣል ወይም እንዳይሰሩ ማድረግ
👉 🔧Setting-battery
✅ Facebook E-mile. Instagram, Twitter, You tube... ከፍተው አለመተው
✅ Bluetooth, WiFi, GPS... በተርታ ክፍት ሲቀመጡ ስልክዎ ሁሌም Searching process ሲለሚጫወት ባትሪዎን ይጨርስቦታል
✅ ስልክዎን በማይጠቀሙበት ወቅት Ultra Power Save 🔐Øn ማድረግ ስልክዎ ከመደወል እና ሜሴጅ ከመቀበል ሌላ ስራ አይኖረውም ሰለዚህ ባትሪዎን ለረጅም ሰዓት ይጠቀማሉ 👍
✅ Animation app አይጠቀሙ
✅ Screensaver ጥቁር ነገሮችን መጠቀም
✅ Night mode መጠቀም ለምሳሌ የፌስቡክ፣ የቴሌግራም ወደ Night mode መቀየር
✅ የስልክዎ Brightness በዝቅተኛው ደረጃ🔅ማድረግ
🐒Setting 🔄Manage 🔄apps 🔄Process ማይገለገሉትን አፕ Force #stop ማድረግ
✅ ስልካችሁን በማይጠቀሙበት ሰአት Lock ያድርጉት
✅ የስልካችሁን Auto Lock ዝቅተኛውን ያድርጉ።
✅ ስልክዎ ላይ 24ሰዓት ሙጭጭ አይበሉ
✅ ስልክዎን Power off በማድረግ ይቻርጁት።
✅ ቢያንስ በ24 ሰአታት ውስጥ ለ1 ሰአት Off ቢደረግ ይመረጣል ወይም 1 ግዜ off አድርጎ እንደገና ማስነሳት
እነዚህ ተግባራዊ ያድርጉ!
ለተጨማሪ መረጃ
Telegram channel ይቀላቀሉ

@MuhammedComputerTechnology
👍4
~+ አዲስ Smart ሞባይል ስልክ ሲገዙ ማገናዘብ የሚገባዎ 10 ነገሮች ከምሳሌ ጋር ~+
መግዛት ያሰቡት smart ሞባይል ስልክ iPhone ወይም Samsung ወይም ሌላ ሊሆን ይችላል።ማንኛውም smart ሞባይል ስልክ ሲገዙ ስልኩ ቀጥሎ የተዘረዘሩትን 6 መመዘኛዎች ማሟላቱን ማረጋገጥ ያስፈልጋል።
1~ ፕሮሰሰር(Processor)
ብዙ ግዜ ጌም የሚጫወቱ ከሆነ፣ቪድዮ የሚያዩ ከሆነ ወይም የቪድዮ ኤዲቲንግ የሚሰሩ ከሆነ የስልኩ ፕሮሰሰር Qualcom Snapdragon(652/820/821) ቢሆን ይመረጣል።ለመካከለኛ ተጠቃሚ ፕሮሰሰሩ MedaTek ከሆነ በቂ ነው።
2 ~ ካሜራ
ፎቶ የማንሳት ልምድ ያለው ሰው የስልኩ ካሜራ 13mp(Megapixels) በላይ መሆኑን ማረጋገጥ ያስፈልጋል።ለመካከለኛ ተጠቃሚ ግን 8mp በቂ ነው።
3 ~ ባትሪ
ብዙ ሰዓት ቪድዮ ለሚያይ፣ጌም ለሚጫወት ሰው ባትሪው 3500mAh(Miliamp Hour) በላይ መሆኑን ማረጋገጥ ያስፈልጋል። ለመካከለኛ ተጠቃሚ 3000mAh በቂ ነው።
4 ~ ኦፐሬቲንግ ሲስተም(OS)
የተለያዩ ኦፐሬቲንግ ሲስተም(OS) ቨርዥኖች አሉ።ለምሳሌ samsung galaxy ስልኮች ኪትካት፣ሎሊፓፕ፣ማርሽሜሎ...ወዘተ የተባሉ ቨርዥኖች አሉ። ስለዚህ latest ቨርዥን መምረጥ ይመከራል።
5 ~ Storage
ስልኩ በቂ የማጠራቀሚያ አቅም ቢኖረው ይመረጣል። 16GB/32GB/64GB..ከነዚህ ውስጥ መምረጥ ነው። ስልኩ ኤክስተርናል ሜሞሪ(microSD card) የሚቀበል መሆን አለበት።
6 ~ Headphone Jack
HeadPhone 3.5mm audio
jack ቢሆን ይመረጣል።
7 RAM ከተቻለ ከ4GB በላይ ቢሆን ጥሩ ነው ነገርግን ለመካከለኛ ተጠቃሚ 2GB በቂ ነው
8 USB File transfer USB 2.0 በአሁኑ ጊዜ ያለ ስለሆነ ይህ ፖርት ያለው ቢሆ ይነረጣል , USB 3.0 ቢሆን ጥሩ ነው.
9 Physical Size በኢንች ለናንተ የሚቸውንም መምረጥ አለባችሁ በተለይ ለአያያዝ ምቹ መሆኑን አረጋግጡ።
10 የሚቀበለው የሲም ካርድ አይነት መለየት።
ምሳሌ ከታች ያለውን Specification ተመልከቱ።
Dimensions: 75.8 x 164 x 8.9 mm
Weight : 205 g
SoC: MediaTek Helio P35 (MT6765)
CPU : 4x 2.3 GHz ARM Cortex-A53, 4x 1.8 GHz ARM Cortex-A53, Cores : 8
GPU : PowerVR GE8320, 680 MHz
RAM : 3 GB, 4 GB, 6 GB
Storage : 32 GB, 64 GB, 128 GB
Memory cards : microSD, microSDHC, microSDXC
Display : 6.5 in, TFT, 720 x 1560 pixels, 24 bit
Battery : 5000 mAh, Li-Ion
OS: Android 10
Camera : 8000 x 6000 pixels, 1920 x 1080 pixels, 30 fps
SIM card : Nano-SIM
Wi-Fi : a, b, g, n, n 5GHz, ac, Dual band, Wi-Fi Hotspot, Wi-Fi Direct
USB: 2.0, Micro USB
Bluetooth: 5.0
Positioning: GPS, A-GPS, GLONASS, BeiDou
👍2
💠System32 ምንድን ነው?

System32 ፎለደር ሆኖ፣ ከ Windows 2000 ጀምሮ በእያንዳንዱ Windows ቨርዥኖች ላይ ተካቷል። የሚገኘውም በ C:\Windows\System32 ሲሆን እና Windows ስራውን በትክክል እንዲያከናውን የሚያስችሉ ሁሉንም ፋይሎች፤ ፎልደሮችን በውስጡ አካቷል።
System32 በጣም ብዙ ፋይሎችን ነው የያዘው፣ እያንዳዳቸው ምን እንደሚሰሩ ለማየት ይሄን ፎረም ሊንክ ተጭነህ ማየት ትችላለህ፣ Symantec's forums።
በአጠቃላይ የSystem32 ፋይሎች በሁለት መክፈል እንችላለን:

💠DLL(Dynamic Link Library) ፋይሎች:-

የተለያዩ ፕሮግራሞች የ Windows ክፍልን አክሰስ ማድረግ እንዲችሉ መንገዱን ይከፍቱላቸዋል እና በዛው የተሰጣቸውን task ያከናውናሉ። ምሳሌ፣ አንዱ የ DDL ፋይል ኮምፒውተሩ ሙዚቃ እንዲያጫውት ሲያደርግ፣ ሌላኛው ደሞ automatic Windows Updates ይሆናል የሚያከናውነው።
ብዙዎቹ DDL የሚጀምሩት ኮምፒተርህን ስታስነሳው ነው። Windows ያለነርሱ መነሳት አይችልም፣ ለዛ ነው የ DDL errors ማስተካከል እንዲሁ ቀላል የማይሆነው!

💠EXE(Executable) ፋይሎች:-

እነዚህ ፋይሎች፣ የሶፍትዌር መተግበሪያና utilities ችን የያዘ ነው። የተለያዩ ሶፍትዌሮችን፣ እንበልና Chrome ወይም Word ን ስትከፍት በተመሳሳይ የነርሱን Executable ፋይላቸውን ነው የምታስጀምረው። ግን የ System32 EXE ፋይሎች ከዛም በላይ ናቸው፣ ለ Task Manager ወሳኝ የሆነው ስለ winlogon.exe ማንሳት እንችላለን፣ ያለዚህ ፋይል ወደ ኮምፒተርህ sign in ብለህ እራሱ መግባት አትችልም!

💠 System32 ፎልደርን ባጠፋውስ?

ሲጀምር ሲስተሙ እንዲሁ በቀላሉ System32 ን እንድታጠፋ አይፈቅድልህም፣ Administrative privilege ይጠይቃል። Admin ብትሆን እራሱ System32 ፎለደር በአንዴ ማጥፋት አትችልም፣ ምክንያቱም በ System32 ውስጥ የሚገኙ የተለያዩ ፕሮግራሞች በስተዃላ እየሮጡ ስለሆነ። ያለው አማራጭ ፎልደሩ ውስጥ ገብተህ አንድ በአንድ መደለት ነው። ሙሉ ፋይሎችን በዚህ መንገድ ካጠፋሃቸው በዃላ ኮምፒተርህ ያለተለመደ ባህሪ ማሳየት ይጀምራል:
💎 መንቀራፈፍ
💎 መፍዘዝ | መደንዘዝ
💎 በመጨረሻም ከነአካቴው ለምትሰጠው ትዕዛዝ መልስ መስጠት ያቆማል፣ shutdown ብትለው እራሱ ምላሽ የለም። እንደምንም hard shutdown(shutdown በተንን ለተወሰኑ ሰከንዶች በመያዝ) አድርገህ ዘጋኸው፣ ግን እስከ ወዲያኛው ነበር የዘጋኸው(መልሰህ ማስነሳት አትችልም)። System restoreማለትም አትችልም(የቱን ፋይል? system32 ውስጥ ያሉትን ሁሉንም ፋይሎችኮ አጥፍታቸዋል)።

የመጨረሻ መፍትሄ፣ እንደ አዲስ Windows OS መጫን!
👍1
አዳዲስ ለተመራቂና ስራ በ0 አመት እንዲሁም ስራ ለማሻሻል የስራ ማስታወቂያወችን በማይታመን ፍጥነት እጃችሁ ላይ የሚያደርስ ምርጥ Channel
@ethiovacancynet
@ethiovacancynet
@ethiovacancynet
@ethiovacancynet
ቻናለችንን በመቀላቀል ወቅታዊ የስራ ማስታወቂያዊችን ይክታተሉ! እናመሰግናለን።
ሸር በማድረግ ለሌሎች እዲደርስ እናድርግ!