Muhammed Computer Technology (MCT)
38.1K subscribers
527 photos
7 videos
254 files
910 links
🔴አድራሻ:-
✅ ስ.ቁ: 0929273364
✅ ዌብሳይት www.mctplc.com
✅ቴሌግራም አካውንት: https://t.me/mctplc
✅ email: mct16plc@gmail.com
✅ ቲክቶክ አካውንት tiktok.com/@mctplc
Download Telegram
All_about_computer 100 Question with answer 👆👆👆
❤1🤔1
All About Computer 100 Question with Answer.pdf
306.9 KB
All about computer 100 Question with answer በPDF
ከላይ 👆👆👆 ያለውን ይጠቀሙ!
Facebook Muhammed Computer Technology
Telegram @MuhammedComputerTechnology Technology
YouTube Muhammed Computer Technology
የጡረታ አበል ስሌት ምሳሌዎች
⏺ 1. ዕድሜ በመድረሱ ለሚጠየቅ የዘለቄታ ጡረታ አበል ስሌት
 ለሲቪል የመንግስት ሠራተኛ
በህግ የተወሰነው የጡረታ መውጫ ዕድሜ በመድረስ ከስራ ለሚሰናበት ሲቪል የመንግስት ሠራተኛ ለመጀመሪያ 10 ዓመት ለፈፀመው አገልግሎት 30% ከ10 ዓመት በላይ ለተፈፀመ ለእያንዳንዱ ዓመት አገልግሎት በ1.25 በማባዛት ከ30% ጋር በመደመር የሚገኘው መቶኛ ውጤት ከመጨረሻዎቹ 36 ወራት አማካይ ደመወዝ ጋር ተባዝቶ የሚሰላ ይሆናል፡፡
ለምሳሌ፡-
የ28 ዓመት አገልግሎት ያለው ሲቪል የመንግስት ሠራተኛ ለመጀመሪያው 10 ዓመት አገልግሎት 30%፣ ከአስር ዓመት በላይ ያለው 18 ዓመት አገልግሎት 18×1.25 = 22.5% ሲሆን በአጠቃላይ 30% + 22.5% = 52.5% ነው፡፡ የመጨረሻዎቹ 36 ወራት አማካይ ደመወዙ 5000.00 ከሆነ የባለመብቱ የዘለቄታ የጡረታ አበል 5,000.00 x 52.5% = 2,625.00 ብር ይሆናል፡፡
 ለመከላከያ ሠራዊትና ፖሊስ አባላት
በህግ የተወሰነው የጡረታ መውጫ ዕድሜ በመድረስ ከስራ ለሚሰናበት የመከላከያ ሠራዊትና የፖሊስ አባል ለመጀመሪያ 10 ዓመት ለፈፀመው አገልግሎት 30% ከ10 ዓመት በላይ ለተፈፀመ ለእያንዳንዱ ዓመት አገልግሎት በ1.65 በማባዛት ከ30% ጋር በመደመር የሚገኘው መቶኛ ውጤት ከመጨረሻዎቹ 36 ወራት አማካይ ደመወዝ ጋር ተባዝቶ የሚሰላ ይሆናል፡፡
ለምሳሌ:-
የ28 ዓመት አገልግሎት ያለው የመከላከያ ሠራዊት ወይም የፖሊስ አባል ለመጀመሪያው 10 ዓመት አግልግሎት 30%፣ከአስር ዓመት በላይ ያለው 18 ዓመት አገልግሎት 18×1.65 = 29.7% ሲሆን በአጠቃላይ 30% + 29.7%= 59.7% ነው፡፡ የመጨረሻዎቹ 36 ወራትአማካይ ደመወዙ 5,000.00 ከሆነ የባለመብቱየዘለቄታ የጡረታ አበል 5,000.00 x 59.7% = 2,985.00 ብር ይሆናል ፡፡
2. በጤና ጉድለት የዘለቄታ ጡረታ አበል ስሌት
ከ10 ዓመትና በላይ አገልግሎ በጤና ጉድለት ምክንያት ከሥራ ለሚሰናበት ስቪል የመንግስት ሰራተኛ ወይም የመከላከያ ሰራዊትና ፖሊስ አባል የጡረታአበል የሚወሰነው በዕድሜ ለጡረታ በመድረስ ምክንያት በሚሰራው የጡረታ አበል ስሌት መሰረት ነው፡፡
ሊድን የማይችል የሥራ ላይ ጉዳት የዘለቄታ ጡረታ አበል
የመንግስት ሠራተኛው ጉዳት ከደረሰበት ቀን በፊት የነበረው የወር ደመወዙ 47 በመቶ በመያዝ ይሰላል፡፡
ለምሳሌ፡-
ሠራተኛው ላይ ጉዳት ከደረሰበት ቀን በፊት ባለው ወር ደመወዙ 4,000.00 ብር ቢሆን 4,000.00 × 47% = 1,880.00 ብር የዘለቄታየጉዳት ጡረታ አበል ያገኛል፡፡
⏺ 1. የዳረጎት (የአንድ ጊዜ) ክፍያ
1.1 የአገልግሎት እና የጤና ጉድለት ዳረጎት
ከ10 ዓመት ያነሰ አገልግሎት የፈጸመ የመንግስት ሠራተኛ ዕድሜው ለጡረታ በመድረሱ ከሥራ ሲሰናበት ወይም ከ10 ዓመት ያነሰ አገልግሎት ፈፅሞ በጤና ጉድለት ምክንያት ለማንኛውም ደመወዝ ለሚያስገኝ ስራ ብቁ ያለመሆኑ በህክምና ቦርድ ተረጋግጦ ከሥራ ከተሰናበተ የአንድ ጊዜ የዳረጎት ክፍያ ያገኛል፡፡
የአንድ ጊዜ የዳረጎት ክፍያ የሚሰላው የመንግስት ሰራተኛው ከሥራ ከተሰናበተበት ወይም ለማንኛውም ሥራ ብቁ ያለመሆኑን የሚገልጽ የህክምና ቦርድ ማስረጃ ከተሰጠበት ወር በፊት ያለው መደበኛ የወር ደመወዝ በአገልግሎት መጠን ተባዝቶ፣ለሲቪል ሰራተኛ በ1.25፣ ለመከላከያ ሠራዊትና ለፖሊስ አባል በ1.65 ታስቦ የአንድ ጊዜ ዳረጎት ይከፈላል፡፡
ምሳሌ 1፡-
አንድ የሲቪል ሠራተኛ አገልግሎቱ 5 ዓመት የሆነ ሠራተኛ ደመወዙ 3,000.00 ቢሆን 3,000.00 X 5 X 1.25 = 18,750.00 የአንድ ጊዜ ዳረጎት አበል ይከፈለዋል፡፡
ምሳሌ 2፡-
አንድ የመከላከያ ሠራዊት ወይም የፖሊስ አባል አገልግሎቱ 5 ዓመት ቢሆንና ደመወዙ 3,000.00 ቢሆን 3,000.00 X 5 X 1.65 = 24,750.00 ብር የአንድ ጊዜ ዳረጎት አበል ይከፈለዋል፡፡
1.2 ሊድን የሚችል የሥራ ላይ ጉዳት ዳረጎት/የአንድ ጊዜ ክፍያ/
የመንግስት ሠራተኛው ጉዳት ከደረሰበት ቀን በፊት ባለው ወር የተከፈለው መደበኛ የወር ደመወዝ መጠን ሲባዛ 5 ሲባዛበ12 ወራት ሲባዛ በ47% ሲባዛ የጉዳት መጠን በመቶኛ ይሆናል፡፡ የጉዳት መጠኑ ከ10 በመቶ በላይ መሆን አለበት፡፡
የሥራ ላይ ጉዳት ስሌት= ደመወዝ X 47% X 5 X 12 X የጉዳት መጠን በመቶኛ ይሆናል፡፡
የጉዳት መጠኑ ከ10 በመቶ በላይ መሆን አለበት፡፡
ለምሳሌ፡-
ሠራተኛው ከጉዳት በፊት የነበረው ደመወዝ 4,000.00 ብር ቢሆን እና የጉዳት መጠኑ 20 በመቶ ከሆነ 4,000.00 × 47% ×5 × 12 × 20%= 22,560.00 ብር የአንድ ጊዜ ክፍያ ያገኛል፡፡
መረጃውን #Share /ሸር/ በማድረግ ለሌሎችም ያካፍሉ።
⏺ በ YouTube channel ጥሩ ጥሩ ትምህርታዊ ቪዲዮችን ይከታተሉ።
የ YouTube ቻናል ሊንክ 👇👇👇
https://www.youtube.com/channel/UCZBIP6PqUdmmagdTjbyp_AQ
ከኮምፒውተር፣ ከፍላሽ፣ ከExternal Hard Disk በፎልደር ውስጥ ያለን ፋይል እንዴት መደበቅ እንችላለን ከዛስ የደበቅነውን ፎልደርና ፋይል እንዴት እናወጣዋለን?
ምሳሌ: "Documents" የሚል ፎልደር Local Disk C. ቢኖር
✅ Step 1: ከአንድ ላይ Windows key ና R key ይጫኑ ከዛም Run dialog box ይመጣ cmd ብለው ይጻፉና OK ይጫኑ Command Prompt ይመጣላችኋል.
✅ Step 2: ይህንን ይጻፉ attrib +s +h c:\documents ላይ ከዛም Enter ይጫኑ .
አሁን documents የሚለው ፎልደር ከነበረበት ቦታ ይጠፋል ማለት ነው። ይህ ማለት ሙሉበሙሉ ጠፍቷል ማለት አይደለም ተደበቀ እንጅ።
_________/_//_/___________
-----ሌላ አማራጭ------
ለምሳሌ ከፍላሽ ዲስክ ወይም ከሀርድዲስክ ያለን መረጃ ለመደበቅ ለምሳሌ ፍላሹ Removable dusk(F) ቢሆን ከኮማንድ ፕሮምፕቱ ላይ F: ብለን ኢተርን እንጫናለን ይህ ማለት ወደ ፍላሽ ዲስክ ገባን ማለት ነው ከፍላሹ ውስጥ documents የሚል ፎደር ቢኖርና መደበቅ ብንፈልግ
✅ attrib +s +h documents ብለን እንጽፋለን ከዛም ኢንተርን እንጫናለን አሁ documents የሚለው ፎልደር ይደበቃል ማለት ነው።
ከፍላሽ ዲስካችን የደበቅነውን documents የሚለውን እንደገና ለማውጣት ብንፈልግ
✅ attrib –s –h documents ጽፈን ኢንተርን እንጫናለን ከዛም ይመለሳል ማለት ነው ከዚህ ላይ የናንተ folder ስም የተለየ ከሆነ documents የሚለውን ብቻ ነው የምትቀይሩት ማለት ነው። ለምሳሌ my secret file የሚል ፎልደር ካላችሁ በ " ማስገባት አለባችሁ ይህም ማለት
✅ ለመደበቅ attrib +s +h "my secret file"
✅ ከተደበቀበት ለማውጣት attrib –s –h "my secret file" የፎልደሩ ስም ከአንድ በላይ word ከሆነ የግድ በ" " ማስገባት አለባችሁ።
_________/_//_/___________
አንዳንድ ጊዜ በፍላሽ ዲስክ የያዝነው መረጃ ይደበቅብናል። ከተደበቀበት ሁሉንም ፎልደሮችና ፋይሎችን ለማውጣት ስንፈልግ ከይ በጠቀስኩት አግባብ ለምሳሌ ፍላሽ ዲስካችን Removable Disk(F) ቢሆን ከኮማንድ ፕሮምፕቱ ላይ F: ብለን እንጫንና attrib -s -h /s /d ብለን እንጽግና ኢንተርን እንጫናለን ከዛም ሁሉም የተደበቀው ፋይል ሁሉ ይወጣልናል ማለት ነው። ሞክሩትና እዩት!
👉 ያወቁትን ማሳወቅ፣ የተማሩትን ማስተማር ብልህነት ነው!
👉 አስተያየት ካላችሁ ጻፉልኝ
👉 ሼር በማድረግ ለምትወዷቸው ጓደኞቻችሁ አጋሯቸው
👉 ፔጁን like ያላደረጋችሁ like አድርጉ ምርጥና ጠቃሚ መረጃወች እንዲደርሳችሁ!
የ Computer System Information ምንድን ነው?
ምስሉን ቢያዩት የተሻለ ነው
1ኛ አማራጭ
Open Start. 1.
Search for msinfo32 and click the top result to open the System Information app.
2. Select the System Summary category from the left navigation pane.
ሰርች ቦክስ ላይ በመግባት System Information የሚለውን ይፈልጉ
2ኛ አማራጭ Windows+R, ስንጫን RUN ይመጣልናል “msinfo32” ብለው ይጻፉ ከዛም Okን ይንኩ።
System Information የሚል ይመጣላችኋል።
ከእነዚህም ውስጥ
✅ OS Name ይህ የሚያሳየን ከኮምፒውተሩ ላይ የተጫነውን Opreating System ምን እንደሆነ ያሳየናል ለምሳሌ Microsoft Windows 7 Home premium
✅ Version የሚለው የኮምፒውተሩ ላይ ዩየተጫነው Opreating System Versionና Service Pack ስንት እንደሆነ ያሳየናል።
✅ OS Manufacturer ይህ የሚያሳየን Opreating System አምራች ድርጅቱ ማን እንደሆነ ያሳየናል።
✅ System Name ይህ የኮምፒውተሩን System Name ያሳየናል። ይህም ስም የሚገኘው ኮምፒውተሩ እንዳዲስ ሲከፈት ወይም ፎርማት ሲደረግ የሚሰጠው ስም ነው።
✅ System Manufacturer የኮምፒውተሩን አምራች ድርጅት ማን እንደሆነ ያሳየናል። ለምሳሌ Dell, Toshiba, HP
✅ System Model ይህ የሚያሳየው የኮምፒውተሩን ሞዴል ምን እንደሆነ ያሳየናል።
✅ System Type ይህ የሚያሳየን ምን አይነት ከሁለት አንዱን ሲሆን 1ኛው X86-based PCና 2ኛው X64-based PC ናቸው ይህ ማለት X86 ከሆነ 32 Bit Opreating system Support የሚያደርግ ሲሆን X64 ማለት ደግሞ 64 Bit Opreating System Support ያደርጋል ማለት ነው።
✅ Processor የኮምፒውተሩን ፕሮሰሲንግ ፍጥነት በኽርትዝ ስንት እንደሆነና ኮር ስንት እንደሆነ የፕሮሰሰሩ አይነትን ያሳየናል።
✅ BIOS version/Date ይህ የሚያሳየን የአምራቹን ድርጅት ስም፣ የVersion ቁጥርና በመቼ ግዜ እንደተመረተ እ.ኤ.አ ያሳየናል።
✅ SMBIOS version ይህ የሚያሳየን System Management BIOS Version በቁጥር ያሳየናል።
✅ Windows Directory ይህ የሚያሳየን Windows የተጫነበትን Path ያሳየናል።
✅ System Directory ይህ የኮምፒውተሩን ሲስተም32 System32 የተጫነበትን Path ያሳየናል።
✅ Boot Device የኮምፒውተሩን Boot Device ቦታን ያመላክታል።
✅ User name ይህ የተጠቃሚው Userን ያሳየናል።
✅ Time Zone ይህ ከኮምፒውተሩ ላይ የተሞላውን Time Zome ያሳየናል።
✅ Install Physical Memory(RAM) ከኮምፒውተሩ ላይ ያለው RAM ምን ያክል Size እንደሆነ ያስየናል።
✅ physical available memory ኮምፒውተሩ loading Opreating system ሜሞሪ የያዘውን ሳይጨምር ቀሪው ሜሞሪን ያመላክታል። ምን ግዜም ይቀንሳል ግን መጠኑ ይለያያል እንጅ።
✅ Total Virtual memory ምናባዊ ሜሞሪ ሲባል ኮምፒተርን physical memory እጥረቶችን ለማካካስ የሚያስችል ነው።
The main difference between physical and virtual memory is that the physical memory refers to the actual RAM of the system that stores the currently executing programs, but the virtual memory is a memory management technique that allows the users to execute programs larger than the actual physical memory.
እስኪ የእሶን ኮምፒውተር በዚህ መሰረት ስለኮምፒውተርዎ መረጃ ይወቁ!
ከተመቻችሁ #ሼር እርሶ ምክንያት ይሁኑ ሰዊች እንዲያውቁ!
Muhammed Computer Technology (MCT) pinned «5 ምርጥ አለምአቀፍ ነፃ የትምህርት ዕድል ማግኛ ድህረ ገፆች(Websites) ☞ 1 - StudentScholarships.org 2 - collegeboard.org 3 - StudentScholarships.org 4 - ScholarshipExperts.com 5 - SuperCollege.com መልካም እድል ስለኮምፒውተርና ቴክኖሎጅ ያለዎትን እውቀት ያሳድጉ በተጨማሪም በቴሌግራሜ ቻናል ምርጥ ምርጥ ስለኮምፒውተር የምለቃቸውን…»
​​✳️ ውድ ቤተሰቦቻችን ዛሬ የዘመናችን አስደናቂ ፈጠራዎች ከሆኑት መሀል ዛሬ ስለ ሜሞሪ ካርድ ወይም SD CARD በጥቂቱ መረጃ ልንሰጣችሁ አስበናል።

◽️ ይህች SD Card የምንላት መሳሪያ ኤሌክትሮኒክ የመረጃ ማከማቻ ስትሆን ዲጅታል ኢንፎርሜሽኖችን ለማስቀመጥ ወይም Store ለማድረግ ያገለግላል፡፡ ይቺ ዳታ ማከማቻ በዲጅታል ካሜራዎች፣ በተንቀሳቃሽ ስልኮች፣ በላፕቶፖችና በኮንፒውተሮች፣ በታብሌቶች ፣በmp3 ማጫዋቻዎችና በቪድዮ ጌም ኮንስሎች ትገኛለች፡፡

◽️ የሚሞሪ ካርድ በመጀመሪያ ወደ አለም ብቅ ያለው በፈረንጆቹ አቆጣጠር በ1995 ሲሆን ይሄውም PC Card (PCMAIA) የሚል ስያሜ ነበራቸው፡፡ እነዚህ የመጀመሪያዎቹ ሚሞሪዎች አሁን በስፋት ተሰራጭተው ከሚገኙ ሚሞሪዎች በመጠን ከፍ ያሉ ሲሆን መረጃ የመያዝ አቅማቸውም በጣም አነስተኛ ነበር፡፡

◽️ በአሁኑ ወቅት እነዚህ ቀደምት ሚሞሪዎች በስፋት እያገለገሉ ያሉት በእንዱስትሪያል አፕልኬሽኖችና እንደ ሞደም ያሉ ኤሌክትሪካል ዲቫይሶችን ለማገናኘት ብቻ ነው፡፡ አብዛሃኞቹ ሚሞሪ ካርዶች መረጃዎችን እንደገና መላልሶ ማጥፋትና መጫን የሚያስችሉ ሲሆን መረጃዎችንም የሚይዙት ያለምንም ፓዎር ነው፡፡

◽️ ከአመታት በኋላ መሻሻሎችን በማሳየት የተላየዩ ሚሞሪዎች ገበያውን መቀላቀል ጀመሩ በተለይ ከመጀመሪያዎቹ PC Card በመጠን አነስ ያሉና መረጃ የመያዝ አቀማቸው ከፍ ያሉ በመሆናቸው ተቀባይነት ለማገኘት ብዙ ጊዜ አልፈጀባቸውም፡፡ ከነዚህም ውስጥም Compact Flash, Smart Media, እና Miniature Card ይገኝበታል፡፡

◽️ በ2001 (እ.ኤ.አ) Smart Media ሚሞሪ ካርድ 50% የዲጅታል ካሜራ ገበያውን ተቆጣጥሮ ነበር፡፡ Compact Flash, የተባለው የሚሞሪ ካርድ አይነት ደግሞ በአብዛኛው የፕሮፌሽናል ዲጅታል ካሜራዎች ላይ ነግሶ ነበር፡፡ እነዚህ የሚሞሪ ካርድ አይነቶች ተፈላጊነታቸው ጥያቄ ውስጥ የገባው በ2010 (እ.ኤ.አ) Micro SD ሚሞሪ ካርዶች መምጣታቸውን ተከትሎ ሲሆን በብዙ የሞባይል ብራንዶች ላይ እና ታብሌቶች ላይ በመገጠም ተፈላጊነታቸው በጣም ሊንር ችሏል፡፡

◽️ እስከ 2010 (እ.ኤ.አ) የሶኒ ካምፓኒ ለምርቶቹ ሚሞሪ እስቲክን ብቻ ይጠቀም ነበር በተመሳሳይ ታዋቂው የዲጅታል ካሜራዎች አምራች Olympus ኩባንያ XD CARD ብቻ የሚጠቀሙ ካሜራዎችን ያመርት የነበረ ሲሆን በኋላ ላይ ግን ሶኒም ሆነ ኦሎምፐስ በምርቶቻቸው ላይ SD MEMORY CARD እንደተጨማሪ የሚያስገቡ ካሜራዎችን ማምረት ግድ ብሏቸዋል፡፡

◽️ አሁን ላይ በብዛት የምንጠቀምባቸው Micro SD ሚሞሪ ካርድ 1.4 mm ቲክነስ ያላቸው ሲሆን በቅርቡ ይፋ በተደረገው መረጃ መሰረት እስከ 1 TB ወይም 1000 GB መረጃን የመሸከም አቅም እንዲኖራቸው ተደርጎ ለመስራት ተችሏል፡፡ ልብ በሉ የመጀመሪያዎቹ ሚሞሪ ካርዶች መረጃ የመሸከም አቅም 32 MB ነበረ ይህ ማለት ከ30 ፎቶዎች በላይ የመያዝ አቅሙ ያልነበረው ነው፡፡ ለ25 አመታት የፍላሽ ስቶሬጅ (Flash Storage) ገበያውን እየመራ ያለው San የተባለው እውቅ ካንፓኒ አሁን ላይ ባለው ቴክኖሎጂ 128 GB SDXC Memory Card (1.4 mm) ማምረቱን ያስታወቀ ሲሆን መረጃን በስሌት ለማስርዳት ያህል አዲሱ ሜሞሪ፡-
🔺16 ሰዓት HD ቪድዮዎች
🔺7500 ሙዚቃዎችን
🔺3200 ፎቶዎችን
🔺ከ125 በላይ አፕልኬሽኖችንም በዛች ጉደኛ SDXC ሚሞሪ ካርድ (1.4mm) ከላይ የተጠቀሱትን ሚዲያ ፋይሎች በሙሉ በአንድ ላይ ማስቀመጥ ተችሏል ይለናል፡፡

ŠHabeshan_Techs
ኮምፒውተራችንን #Rufes_software ተጠቅመን እንዴት #Format አድርገን Window መጫን እንችላለን?

አስፈላጊ ነገሮች
1. #Flash_disk: 4GB ወይም ከዚያ በላይ
2. #operating_system(Os) setup: windows xp 7, 8 or 10 iso IMG💿
3.Format የሚደረገው #ኮምፒውተር

ማሳሰቢያ:
👍ይህን ስራ ለማጠናቀቅ ወደ 40 ደቂቃ ሊቆይ ይችላል::

የአሰራር ቅደም ተከተል
1. በመጀመሪያ Rufus Software ከሌላችሁ Download አድርጉ....

2. በመቀጠል ሶፍትዌሩን ሳትጭኑ ራይት ክሊክን በመጫን ''run as admin"የሚለውን ይምረጡ...

3. ከዛ የተዘጋጀውን Flash Disk ኮምፒተሩ(rufes ካለበት) ላይ እንሰካለን። ፕሮግራሙ ከተከፈተ በኋላ ፍላሽ ዲስኩን device የሚለውን menu ተጭነን እንመርጠዋለን...

4. ከዚህ በኋላ iso image የሚለው ቦታ ሄደን የተዘጋጀውን የ windows soft ኮፒ አስገብተን drive letter እንመርጣለን...

5. ይህን ስናደርግ ፕሮግራሙ ራሱ ሁሉን ነገር ስለሚያዘጋጅ ሌላ የምናስተካክለው ነገር የለም ማለት ነው...

6. ከዛ start የሚለውን በተን ስንጫን ፍላሽ ላይ ያለ ማንኛውም ዳታ ይጠፋል ብሎ ማስጠንቀቂያ ይሰጠናል...

7. የምንፈልግው መረጃ ፍላሽ ላይ ካለ ባክአፕ ማድረግ አለብን።
እሱን ካረጋገጥን በኋላ ok እንለዋለን...

8. በመጨረሻ ፕሮግራሙ የ window setup ን ወደ ፍላሽ ዲስኩ ኮፒ በማድረግ ስራውን መስራት ይጀምራል....

9. ፕሮግራሙ ኮፒ አድርጎ ሲጨርስ exit አድርጎ መውጣት....

👍አሁን ፍላሽ ዲስኩን ተጠቅመን እንዴት ፎርማት እንደምንችል እናያለን

1. Format የሚደረገውን ኮምፒውተር shut down ያድርጉ...

2. ያዘጋጀነውን ፍላሽ ዲስክ አስገብተው turn on ያድርጉ.....

3 : F2 ወይም F12 ን (እንደ ኮምፒውተሩ ሞዴል ይለያያል) ከዛም USB Drive የሚለውን ይምረጡ።

4. Windows load ያደርጋል " install windows " የሚለው ሲመጣልዎ የሚፈልጉትን ቋንቋ እና ሌሎች ዝርዝሮችን ይሙሉ ከዛም next ን ክሊክ ያድርጉ....

5. "Please read the license terms" የሚለው ሲመጣልዎ
"I accept the license terms" የሚለውን ክሊክ ያድርጉ...

6. "Which type of installation do you want?" ሲልዎት Custom የሚለውን ይምረጡ...

7. "Where do you want to install Windows?" የሚለው ፔጅ ላይ "Drive options" የሚለውን ክሊክ...

8. ፎርማት ማድረግ የሚፈልጉትን "partition" ይምረጡና "format" ላይ ክሊክ ያድርጉ...

9. ፎርማት አድርገው ሲጨርሱ "next" ላይ ክሊክ ያድርጉ...

10. ከዛ በመቀጠል ትዕዛዙን (instruction) በመከተል window install ያድርጉ...እዚህ ላይ ስለሚዘገይ በትዕግስት ይጠብቁ...

11. Window install አድርጎ ሲጨርስ የሚፈልጉትን application software ይጫኑበት::
💢ስልክዎ ላይ #Application's ሲጭኑ "There was a Problem Parsing The Package" እያላችሁ ለተቸገራችሁ #መፍትሔ ⬇️⬇️⬇️

1⃣.USB Debugging On አድርጉት።

⚠️Settings➡️ About Phone➡️ Build Number (7ጊዜ ይንኩት)➡️ ወደ Setting ይመለሱና➡️ Developer Options➡️ USB debugging የሚለውን #ON ያድርጉት።

2⃣. የጫኑት Antivirus ወይም Cleaner ካለ ለጊዜው #Disable ያድርጉት።

3⃣. ያለዎት አፕ #Corrupted ወይም Download ተደርጎ ያላለቀ❌ ሊሆን ስለሚችል ከእንደገና Download📥 ያድርጉት።

⚠️አፖችን #ከPlaystore ብቻ ቢያወርዱ📥 ተመራጭ ነው።👍

4⃣. የPlay Storeን Cache Cookies Clear ያድርጉት።

⚠️Settings➡️ Apps➡️ Playstore ➡️ Clear Cache Cookies

5⃣. ሊጭኑት ያሰቡት አፕ ካለዎት Operating System ጋር #Compatible ሳይሆን ሲቀር።

⚠️በተጨማሪም ሌላ የሚፈልገው Hardware Requirements ካለ የአፑን #description በደንብ ያንብቡ።
Šethio_techs
✅RAM
ራም (ራንደም አክሰስ ሜሞሪ) ኮምፒውተር በፍጥነት ኦፕሬቲንግ ሲስተም (ኦኤስ) ፣ Application ፕሮግራሞች እና መረጃዎች በአሁኑ ወቅት በሚቀመጡበት የኮምፒተር መሣሪያ ውስጥ ሃርድዌር ነው ፡፡
#RAM የሚጠቅመው #የተቀሰቀሱ/የተከፈቱ #ፕሮግራሞች #በፍጥነት እንዲሰሩ የሚጠቅም ነው፡፡ የ RAM ተግባር በተለዋጭነቱ ምክንያት ራም ቋሚ መረጃዎችን ማከማቸት አይችልም።
ይህ ሊሆን የሚችለው #ኮምፕዩተሩ እነዚህን የተቀሰቀሱ #ፕሮግራሞች ለጊዜው (ተቀስቅሰው እስካሉ ድረስ) ለምሳሌ #HHD ወይም ከሲዲ ከማንበብ ይልቅ ከራም ላይ ያነባቸዋል፡፡ ይህ ማለት ራም #ጊዚያዊ ፕሮግራም ተሸካሚ ግን በፍጥነት አቅራቢ እንደማለት ነው፡፡ #ለምሳሌ አንድ ተጠቃሚ ኢንተርነት የሚቀዝፍ ከሆነ ቀዛፊውን ከፍቷል፡፡ ሰነድ የሚጽፍ ከሆነ ወርድን ከፍቷል #ፎቶ ወይም ቪዲዮ የሚሰራ ከሆነ የፎቶና ቪዲዮ #ፕሮግራሞች ከፍቷል፡፡ እና እነዚህ ፕሮግራሞች #እስከተከፈቱ ድረስ #ራም ለጊዜው ተሸክሞ ይይዛቸዋል፡፡ ለዚህም ነው ራም ከፍ ባለ ቁጥር #የኮምፕዩተሩም #ፍጥነት የሚጨምረው፡፡ ያው አማካይ አዛዢም እራሱን የቻለ ሚና ቢጫወትም፡፡ #ራም ልክ እንደሌሎቹ ክፍሎች ዋና ቦርድ ቦታ ስላለው እዛ ይሰካል፡፡

✅Hard_disk

#ዳታዎችን በቋሚነት #ለመያዝ ነው፡፡ #የኮምፒውተሩ አሰራር ሂደት(operating system) #የሚጫንበት እና በአግባቡ ኮምፒውተሩ ለተጠቃሚዎች አገልግሎት ምቹ የሚያደርጉትን የአሰራር ሂደት #ፋይሎች(operating system files) የሚቀመጡበት #የኮምፒውተር ክፍል ነው፡፡ áˆˆáˆáˆłáˆŒ የሆነ #ሰነድ ጽፈው ለመያዝ ከፈለጉ የሚይዘው #HHD ላይ ነው፡፡ እንደተለመደው HHD ዋና ቦርድ ላይ የሰካል፡፡ HHD ዳታ ሲያነብና ሲጽፍ #ማግኔታዊ ነው
👍1
ላፕቶፕ ስንገዛ ማወቅ እና ማየት ያለብን ወሳኝ ነጥቦች
1 የመሳሪያ ስርዓት (Operating system)
2 የስክሪን መጠን (Screen Size)
3 ሲፒዩ(CPU)
4 ራም(RAM)
5 የሃርድ ድራይቭ አይነት (Hard Drive Type)
6 የምስል ጥራት (Image Quality)
7 የባትሪ ቆይታ (Battery Life)
8 ብራንድ (Brand)
ኮርi3 ኮርi5 ኮርi7 ምንድናቸው?
በሃገራችን ገበያ አሁን አሁን በርከት ያሉ የላፕቶፕ እና
የኮምፒውተር ሱቆች እየታዩ ይገኛሉ፡፡ለገቢያም የተለያዩ
የላፕቶፕ አይነቶች.በተለያየ ይዘት ይገኛሉ፡፡ እንዚህን
የተለያየ
ይዘት ያላቸውን የላፕቶፕ አይነቶች ለመግዛት በዋናነት
መታየት
ያለበትን ከዚህ በታች በዝርዝር ተቀምጠዋል፡፡
1. የመሳሪያ ስርዓት (platform) Windows, Mac
and
Linux
ለአጠቃቀም ምቹ እንደሆነ የሚነገርለት Windows የብዙ
ሰዎች
ምርጫ ነው፡፡ቀላል፣ ምቹ እና ተለዋዋጭ ነው፤ በዋጋም
ደረጃ
ጥሩ የሚባል ነው፡፡
ማክ( Mac) የአፕል ድርጅት ምርት ሲሆን ለዲዛይን
ተመራጭ
የሆነ
ፕላትፎረም ነው፡፡ለደህንነትም ከWindows እንደሚሻል
ይነገርለታል፡፡
2. የስክሪን መጠን
ወደ ግዢ ከመግባታችን በፊት የምንገዛው ላፕቶፕ ከቦታ
ወደ
ቦታ ይዘን ለመንቀሳቀስ (portable) ምቹ መሆኑን
ማረጋገጥ
ያስፈልጋል፡፡ ላፕቶፖች እንደየስክሪን መጠናቸው
የተከፋፈሉ
ናቸው፡፡
• 11 to 12 inches(27.94cm-30.48cm) ፡በጣም
ቀጭን
እና ቀላሉ የስክሪን ሳይዝ ነው፡፡ ከ1.1ኪሎ እስከ1.5ኪሎ
ይመዝናል፡፡
• 13 to 14 inches (33.02cm- 35.56cm) ፡ይህ
የስክርን
ሳይዝ ያለቸው ላፕቶፖች በጣም ተመጣጣኝ portability
ያላቸው እና በላፕቶፕ ተጠቃሚዎች ተመራጭ ናቸው፡፡
• 15 inches(38.1cm): እውቁ የላፕቶፕ የስክሪን
ሳይዝ
ሲሆን፤ተለቅ ያለ የስክሪን ሳይዝ ከፈለጉ ይህንን እንዲገዙ
እንመክራለን ፡፡
• 17 to 18 inches (43.18cm- 45.72cm)፡
ላፕቶፖን
ይዘው የማይንቀሳቀሱ ከሆነ እና ትልቅ የስክሪን ሳይዝ
ከፈለጉ
ይህንን ይግዙ፡፡ ለጌመሮች እና ትልልቅ የሶፈተዌር
ዲዛይን
ለሚያደርጉ ሰዎች ተመራጭ የሆነ የላፕቶፕ አይነት ነው፡፡
3. ሲፒዩ(CPU)
የኮምፒዉተር አይምሮ በመባል የሚታወቀው ሲፒዩ
(CPU),
ላፕቶፕ ለመግዛት ሁላችንም ማየት ያለብን ዝርዝር ነው፡፡
• AMD A series or Intel Core i3 / i5: በየቀኑ
ለምንጠቀማቸው ስራዎች የሚሆኑ የሲፒዩ አይነቶች
ሲሆኑ Core
i5 ለሶፈትዌር ዴቨሎፕመንት እና አነስተኛ የዲዛይን
ስራዎችን
ለምሳሌ እንደ Photoshop, Archicad, AutoCadን
የመሳሰሉ በጥሩ ሁኔታ እንድንሰራ ይጠቅሙናል፡፡
በተጨማሪም
ግራፊክስ ካርድ ያለውና የሌለው በማለትም ይለያያሉ፡፡
ግራፊክስ
ካርድ ያለቸው የተሻለ የዲዛይን እና አኒሜሽን ስራዎችን
ያከናውኑልናል፡፡ በዋጋውም ተመጣጣኝ ነው፡፡
• Intel Core i7፡ በጣም አስደማሚ የጌም እና
የዲዛይን
እንዲሁም ልዩ የሆኑ የኮምፒውተር ስራችን ለምሳሌ አንደ
ሜትሮሎጂ፤ውስብስብ ስሌቶችን እንድንሰራ የሚረዳን
የላፐቶፕ
አይነት ነው፡፡
4 .ራም(RAM): ለፍጥነት 4ጂቢ እና ከዛ በላይ የሆነ
RAM
እንዲጠቀሙ እንመክሮታለን፡፡ ዋጋቸው አነስ ያሉ
ላፕቶፖች
በ2ጂቢ ይመጣሉ፡፡ የዲዛይን ስራዎችን እና የሶፈትዌር
ዴቨሎፕመንት ስራዎችን ለመስራት 6ጂቢ ራም እና ከዚያ
በላይ
ያለው ላፕቶፕ ቢገዙ ይመረጣል፡፡
5.የሃርድ ድራይቭ አይነት፡ ሁለት አይነት የሃርድ ድራይቭ
አይነቶች ያሉ( HDDrive እና SSDrive) ሲሆን
በሃገራችን
ያልተለመደው SSDrive ከHDDrive የተሻለ የፍጥነት
አቅም
እና ድራይቩ ላይ ያለውን ዳታ በፍጥነት መድረስ እና
መገልበጥ
(copy)ያስችለናል፡፡
6 .የምስል ጥራት፡ የተሻለ ጥራት የተሻለ ምስል
እንድናገኝ
ይረዳናል፡፡ 1366 x 768 ጥሩ የሚባል የምስል ጥራት
ያለው
ሲሆን ከዚህ የተሻለ ወጪ በማውጣት 1920 x 1080
የተሻለ
ምስል ማግኘት እንችላለን፡፡Full HD 1080P በመባልም
ይታወቃል፡፡
7 .የባትሪ ቆይታ፡ አብዛኛው ሃገር ውስጥ የሚገቡት
የላፕቶፕ
አይነቶች 4 ሰዓታት የሚቆዩ ሲሆን ከ6-8 ሰዓታትም
የሚቆዩ
ኦርጅናል ላፕቶፖች አሉ፡፡
8 . ብራንድ፡ የተላያዩ የላፕቶፕ ብራንዶጭ ባሉበት ገቢያ
የተኛውን መግዛት እንዳለብን አስቀድመን ማወቅ አለብን፡፡
• ከጥራት አኳያ ደግሞ APPLEን የሚደርስ የለም፡፡ HP
እና DELLም የተሻሉ ብራንዶች ናቸው
👍2
📶 ዋይ ፋይ ምንድነው?
✅ Wi-Fi እንዴት ይሰራል?
ይህ ቃል ለአብዛኛው ተጠቃሚ፤ ሞያተኛውንም ሲጨምር አጋጥሞናል ከ ኢንተርኔት ጋር እየተለዋወጠ ሲገባ እናየዋለን፡፡ በሞያችንም ለሰዎች ለማስረዳት ስንሞክር አለመግባባት ይከሰታሉ፡፡ እርግጥ ነው ዋይ ፋይ ኢንተርኔት ለማገኘት ይራዳል ነገርግን በራሱ ኢንተርኔት አይደለም፡፡
✅ምንም እንኳን በአይናችን ባናያቸውም የራዲዮ ሞገዶች ሁሌም መረጃዎችን ተሸክመው በዙሪያችን እንዳሉ ይታወቃል፡፡ ከእነዚህ የሬዲዮ ሞገዶች ጥቂቶቹ የWi-Fi ሲግናሎች ናቸው፡፡ Wi-Fi በሚለው ስም ውስጥ የሚገኙ ሆሄያት እንደ አህጽሮተ ቃል የትኛውንም ነገር የማይወክሉ ሲሆን በመነሻነት አንድ ከፍተኛ መጠን ያለውን መረጃ በአጭር ርቀት ውስጥ የራዲዮ ሞገዶችን በመጠቀም ማስተላለፍ የሚችልን ቁስ በቀላሉ ማስታዎስ እንዲቻል ተብሎ የተሰጠ ስያሜ ነው፡፡

✅ እንደ ብሮድካስት ራዲዮና ተንቀሳቃሽ ስልክ ሲግናሎች ሁሉ የWi-Fi ሲግናልም በ19ኛው መቶ ክፍለ ዘመን መገባደጃ አካባቢ የተገኘ ሳይንሳዊ ፈጠራ ነው፡፡ ኤሌክትሮኖች በሽቦ ውስጥ በሚንቀሳቀሱበት ጊዜ በየተወሰኑ ጊዜያት አቅጣጫዎችን ይቀይራሉ፡፡ በሌላ ሽቦ ላይ የሚገኙ ኤሌክትሮኖች ከእነዚህ አቅጣጫ ከሚቀያይሩ ኤልክትሮኖች ጋር ቴሌፋቲክ በሆነ መንገድ የተያያዙ ስለሆኑ መንቀሳቀስ ይጀምራሉ፡፡ ይህ ግኝት መጀመሪያ የታወቀው በ1887 በሄንሪክ ሄርትዝ ነው፡፡

✅ የሚታይ ብርሃንን የያዙ ኤሌክትሮመግነጢሳዊ ህብሮች ከራዲዮ ሞገዶች የተሻለ ከፍተኛ ፍሪኩየንሲን ያመነጫሉ፡፡ የተለመዱት የኤ ኤም ወይም ኤፍ ኤም ራዲዮ እና የቴሌቪዥን ስርጭቶች መረጃን በተከታታይ ሲግናሎች ወይም በአናሎግ ያደርሳሉ፡፡ Wi-Fi መረጃን የሚያሰራጨው እንደ ያልተያያዙ ዋጋዎች የባይናሪ መረጃ ዜሮዎችና አንዶች በዲጂታል መንገድ ነው፡፡ ይህም የሞባይል ቁሶች ከፍተኛ መጠን ያላቸውን እንደ ቪዲዮ፣ ምስል፣ ድምጽ እና የጽሁፍ መልዕክቶችን በቀላሉ እንዲልኩ ያስችላቸዋል፡፡

✅ አንድን መረጃ በዋይ ፋይ ኦንላይን ላይ ስንፈልግ የዋይ ፋይ ቁሳችን የሬዲዮ ሞገዶችን አልፎ ከዋይ ፋዩ መገኛ ነጥብ ጋር ይናበባል፡፡ ይህም በኢንተርኔት ራውተራችን አንቴና አማካኝነት ነው፡፡ ከዚያም በአካባቢው ባሉ የኢንተርኔት ገመዶች አማካኝነት ጥያቄያችን ወደምንፈልገው የመረጃ ቋት ይተላለፋል፡፡ ሂደቱ ሲያልቅም በመጣበት መንገድ ተመልሶ ይመጣል፡፡

✅ በተለያዩ ኩባንዎች የተሰሩ የዋይ ፋይ ቁሶች 802.11 የተሰኘ ተመሳሳይ ስታንዳርድን ስለሚከተሉ እርስ በርሳቸው መናበብ ይችላሉ፡፡ ይህ ስታንዳርድ ዜሮዎችና አንዶች ራዲዮ ሞገድን በመጠቀም እንዴት እንደተወከሉና ቁሶቹ ራሳቸውን እንዴት እንደሚለዩ የሚወስን ነው፡፡ እነዲሁም ደግሞ ኬሪየር ሴንስ መልቲፕል አክሰስ (CSMA) የተሰኘ እንዴትና መቼ መግባባት እንዳለባቸው የሚወስን አሊጎሪዝም ይከተላሉ፡፡ ይህ አሊጎሪዝም የዋይ ፋይ ቁሶችን ስማርት ያደርጋቸዋል፡፡

✅ አንዳንድ ጊዜ ከዋይ ፋይ ጋር በተያያዘ ችግሮች ይገጥሙናል፡፡ ወይም ከዋይ ፋዩ መገኛ ነጥብ ጋር ለመገናኘት እንቸገራለን ይህም የሚሆነው የራዲዮ ሲግናሎች በርቀት ምክንያ ሲደክሙ ነው፡፡ ለምሳሌ ወፍራም ግድግዳ፣ የብረት መከለያዎች አንዲሁም አኳሪየም የራዲዮ ሞገዶችን ሊያደክማቸው ይችላል፡፡

✅ ዋይ ፋይ ይህ ቃል ለአብዛኛው ተጠቃሚ፤ ሞያተኛውንም ሲጨምር አጋጥሞናል ከ
ኢንተርኔት ጋር እየተለዋወጠ ሲገባ እናየዋለን፡፡ በሞያችንም ለሰዎች ለማስረዳት ስንሞክር አለመግባባት ይከሰታሉ፡፡ እርግጥ ነው ዋይ ፋይ ኢንተርኔት ለማገኘት ይራዳል ነገርግን በራሱ ኢንተርኔት አይደለም፡፡

✅ ዋይ ፋይ ገመድ አልባ የኮምፒውተር ግንኙነት መፍጠሪያ ዘዴ ሲሆን ኢንተርኔትን ጨምሮ የተለያዩ መረጃዎችን፣ ፋይሎችን፣ እንዲሁም እቃዎችን (ፕሪንተር፣ እስካነር) በጋራ እንድንጠቀም ይረዳናል፡፡ ይህ ማለት ደግሞ የባለገመድ ግንኙነት (cable Network) ምትክ መሆኑን ያሳያል፡፡
👍1
✍ከ7-12ኛ ክፍል Textbooks, መማሪያ መጽሀፎችን Textbooks በPDF ይፈልጋሉ?
✔️የፈለጉትን መጽሀፍት በPDF በቴሌግራም ቻናላችን ታገኛሉ!
👇👇የቴሌግራም ቻናሉ👇👇👇👇
https://t.me/EthiopiaDigitalLibrary
https://t.me/EthiopiaDigitalLibrary
https://t.me/EthiopiaDigitalLibrary
https://t.me/EthiopiaDigitalLibrary
አሁኑ ይቀላቀሉ!
ምርጥ ምርጥ መጽሀፎችን በስልካችሁ ማግኘት ትችላላችሁ!
የኢትዮጵያ ዲጅታል ላይብረሪ (Ethiopian Digital Library)
👍1
💢የኮምፒውተርዎ 💻 desktop ላይ #አጫጭር ኖቶችን ✍ ማስቀመጥ ከፈለጉ search bar ላይ ይሒዱና sticky notes ብለው #search ያድርጉ።

⚠️ለተማሪዎች 👨‍💻 ካነበቡት ነገር ውስጥ #በጣም አስፈላጊ የሆኑ ነገሮችን ለመያዝ እንዲሁም ለሌሎቻችንም #ስልክ_ቁጥር፤ቀጠሮ እና የመሳሰሉትን ለመያዝ ጠቃሚ 👍 ናት ይሞክሯት።
SHRE SHARE
MuhammedAminWebsite_1_1.0 (1).apk
156.1 KB
ይህች App የኔን ዌብሳይት የምትከፍትላችሁ App ናት ገብታችሁ ጠቃሚ የሆኑ መረጃዎችን ማግኘት ይችላሉ!
ይሞክሯት!
👆👆👆👆👆👆👆👆
✳️ Google ካስጠነቀቃቸው ነገሮች ውስጥ አንዱ እና ዋነኛው የ Google አካውንታቺን ለርጅም ጊዜ ካልተጠቀማቹበት Google ራሱ አካውንቱን ሙሉ ለሙሉ እንደሚሰርዝ (Delete) እንደሚያርገው Google ባለፈው ወር አሳውቋል፡፡

🔻ስለዚህ የ Google አካውነታችሁ እንዳይሰረዝ አካውንታችሁን አሁኑኑ መጠቀም በመጀመር አካውነታችሁን Active እንዲሆን ማድረግ ትችላላችሁ፡፡

🔻አካውነታችሁን Active እንዲሆን የተለያዩ ነገሮች መጠቀም ትችላላችሁ። ለምሳሌ፦ በ Gmail (Email) ከጓደኛቹህ ጋ ማውራት ፤ Google Drive ፤ Google Photo እና የመሳሰሉ የ Google አገልግሎቶችን ሊጠቀሙ ይገባል ብሏል Google፡፡

🔻የ Google አካውንታቸው የተሰረዘባቸው ሰዎች ከዚህ በፊት የተለዋዋጧቸው ኢሜሎችም ሆነ ሌሎች ግላዊ መረጃዎች ሙሉ ለሙሉ እንደሚሰርዝ ጎግል አስጠንቅቋል፡፡

🔻ስለዚህ የ Google አካውነታችሁን ግዜው ሳይደርስ አሁኑኑ መጠቀም ጀምሩ።

✅በ ©Just_Offical የቀረበ።
✅✅ስለ_ኢትዮሳት✅✅

💥ሰሞኑን በተደጋጋሚ ስለ ETHIOSAT ከሚነሱ ጥያቄዎች መካካል ግልፅ መረጃ እንዲኖራችሁ የሚከተሉትን ነገሮች አዘጋጅተናል።

1, ኢትዮሳት ከተቀላቀሉ የሀገር ውስጥ ቻናሎች አብዛኞቹ ከ ጥር 13 ጀምሮ የ ናይል ሳት ስርጭታቸው ያቆማሉ።

⭕️ከጥር 13 ጀምሮ ከናይል ሳት የሚወጡ ቻናሎች ዝርዝር ውስጥ

👉FANA TV
👉WALTA TV
👉ETV
👉Amhara TV
👉Asham TV
👉OBN
👉OBS ይገኙበታል

2, ኢትዮሳት ለመጠቀም የግድ የሰሀኑ አቅጣጫ ከነበረበት በተቃራኒ በስተምስራቅ ዞሮ መስተካከል ይኖርበታል

3, ኢትዮሳት ላይ የገቡ ቻናሎች አብዛኞቹ በHD ስርጭት ስለሚተላለፉ አነርሱን ለማግኘት HD ሪሴቨር ያስፈልጋል።

4, ኢትዮሳት በ SD ይሰራል! ነገር ግን እስካሁን ባለው ሁኔታ በ Sd ሪሴቨር የሚሰሩት ውስን(14) ቻናሎች ብቻ ናቸው።

5, ኢትዮሳት እና ናይል ሳት በ አንድ ሰሀን አይሰሩም ሁለቱንም ለመጠቀም ሁለት ሰሀን ያስፈልጋል።

6, ኢትዮ ሳት የሚገኝበት ሳተላይት NSS 12 57E ሙሉ ኢትዮጵያ ከፍተኛ ሽፋን ስላለው ከ 60CM ዲሽ ጀምሮ ይሰራል።

7, ሪሴቨሮች ላይ ከሚነሱ ጥያቄዎች መካከል በተለይ SUPERMAX 2350 SUPERTECH
በ 11105 H 45000 ላይ ሲግናል ችግር ያመጣል መፍትሄው ሪስቨር መቀየር ነው።

👉 ይህ frequency 11105 H 45000 የገመድ ችግር ካለም የማስቸገር ባህሪ አለው

8, ሪሴቨራቹ ላይ NSS12 የሚል ከሌለ SATELLITE LIST ላይ ADD ማድረግ ወይም አንደኛው ሳተላይት ላይ ፍሪክዌንሲውን መሙላት ይቻላል።

✅ #አዲሱን_የኢትዮ_ሳት - አዲሱን የኢትዮጵያውያን ቻናሎች መገኛ ሳተላይት እንዲሁም ለማንኛውም አይነት የዲሽ ብልሽትም ሆነ አዲስ ዲሽ ለማሰራት ከፈለጉ #በጥራት እና #በዋስትና እንዲሁም #በተመጣጣኝ_ዋጋ እንሰራሎታለን ይደውሉልን።

አድራሻ
💥አጋሮ/ጅማ/
📲 +251938095912
📲 +251941301488

ለማንኛውም ጥያቄ በቴሌግራም @J_Dishbot ይጠቀሙ!!
Copy From Agaro Dish &Technology Info.
❤1👍1
የኢትዮሳት ብቸኛ ጥቅሞች
Ethiosat Exclusive Benefits
➧ሀ/የሳተላይት ክፍያ
የሳተላይት ቻናሎች ክፍያ በሚይዙት ባንድዊድዝ የሚወሰን ቢሆንም ኢትዮሳት ላይ የሚገኙት ቻናሎች ክፍያ ከሌላ ሳተላይት ጋር ሲነፃፀር በግማሽ ይቀንሳሉ። ይህ ደግሞ ሌላ ሳተላይት ላይ በSD ጥራት ያስተላልፉ ከነበረ በHD እንዲያደርጉት እድል ይፈጥርላቸዋል። በተጨማሪም ለሌሎች የፕሮዳክሽን ሥራዎች ትርፍ ይኖራቸዋል።
➧ለ/የቻናሎች ይዘት
በሌሎች ሳተላይቶች የሚገኙ ቻናሎች የአገራቸውን ጥቅም ከማስጠበቃቸው የተነሳ በርካታ ቻናሎች ከፍላጎታችን ውጭ ይገባሉ። በተጨማሪም እያንዳንዱ ተፈላጊ ኢትዮጵያዊ ቻናል የተለያየ ፍርኩየንሲ ያለው ከመሆኑ እንፃር ቻናሎችን ፈልጎ ቅደም ተከተል ለማስያዝ ብዙ ሰዓት ይወስዳል። ኢትዮሳት ላይ ያሉ ፍሪኩየንሲዎች ግን ለጊዜው ከ125 በላይ ናቸው ሰርች በሚደረግበት ሰዓትም የሚገቡት ጠቃሚዎቹና የተመረጡ ኢትዮጵያዊ ቻናሎች ብቻ ናቸው።
➧ሐ/ የቻናሎች ጥራት
እኛ ኢትዮጵያዊያን ጥራት ይገባናል። ስለሆነም ኢትዮሳት ላይ የሚገኙ አብዛኛዎቹ ቻናሎች ከፍተኛ ጥራት ያላቸው (HD) ናቸው። ቁጥራቸው ቀላል የማይባል ሰዎች SD ሪሲቨር ያላቸው መሆኑንም በመገንዘብ ለ6 ወራት የሚቆዩ የተወሰኑ ቻናሎች በSD ይሰራሉ ። ነገር ግን በዘላቂነት ቻናሎቹን በጥራት ለመመልከት HD ሪሲቨር ያስፈልጋል።
➧መ/ በዛፍ እና በግንብ የመከለል ሁኔታ
ይህ ሳተላይት 57°E እንደመሆኑ መጠን ከፊት ለፊት በሚኖር ዛፍ ወይም ግንብ የመከለል ሁኔታው ዝቅተኛ ነው። በተለይ ኮንዶሚኒዬሞች ላይ ሀገርኛ ቻናሎችን ለማግኘት ሲቸገር ለነበረ ሰው ችግሩን ያቃልልለታል። በዛፍ የተከበቡ መኖሪያ ቤቶችም እንዲሁ።
➧ሠ/ ኳስ የማግኘት ሁኔታ
ከዚህ በፊት ብዙ የእግርኳስ ተጠቃሚ ያለው ቫርዚሽ ቲቢ ከኢትዮሳት የሚርቀው 4.5° ስለሆነ ሌላ ተጨማሪ ዲሽ ሳያስፈልግ በቀላሉ አንድ LNB እና ስዊች በመጨመር ተጠቃሚ መሆን ይቻላል። ምናልባት ሌሎች ሳተላይቶች ላይ የማናገኛቸው የፊልም ቻናሎችንም እዚሁ ሳተላይት ላይ እናገኛለን።
➧ረ/ የቀጣይነት ሁኔታ
የዚህ ሳተላይት ባለቤት በቀመጫውን ሉግዘንበርግ ያደረገው SES ካምፓኒ ሲሆን ኢትዮሳት በብቸኛነት የተከራየው ለኢትዮጵያውያን የተዘጋጀ ሳተላይት ነው። ሆኖም የሳተላይቱ "Orbital Position" ኢትዮጵያ አናት ላይ ስለሆነ ኢትዮጵያ የራሷን የኮሙኒኬሽን ሳተላይት ከ3 ዓመት በኋላ ስታመጥቅ 58.3°E ላይ ያርፋል። ስለሆነም ምንም አይነት ተጨማሪ የዲሽ እንቅስቃሴ ሳይደረግ ፍሪኩየንሲ ብቻ በመሙላት ኢትዮጵያዊ ቻናሎችን በቀጣይነት መጠቀም ይቻላል።
➧ሰ/ ፖለቲካዊ እና ሃይማኖታዊ ቻናሎች
በዚህ ሳተላይት የሚተላለፉ ቻናሎች ሐይማኖታዊም ይሁን ፖለቲካዊ ይዘት ይኑራቸው ገደብ የለባቸውም። ነገር ግን ሀገርን አደጋ ላይ ሊጥሉ የሚችሉ ቻናሎች ላይ እንደስከዚህ በፊቱ በ"Jaming" የሚዘጉ ሳይሆኑ ስርዓት ባለው መንገድ ኢትዮሳት ከሳተላይት ካንፓኒው ጋር የሚደራደርባቸው እና ማስተካከያ የሚደረግባቸው ይሆናል። በዚህ በኩል የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት የራሱ የሆነ ድርሻ አለው።
👍3❤1
ልታውቋቸው የሚገቡ Commands እንዴት አድርገን የኮምፒውተራችንን Users ማስተዳደር እንችላለን?
🔶 በመጀመሪያ ደረጃ Command Prompt ወይም CMDን እንከፍታለን።
ለምክፈት በ3 አማርጮች እንጠቀማለን
1ኛ Start-> All Program -> Accessories -> Command Prompt ከዛም Right Click በማድረግ Run as Administrator ብለው ይጫኑ
2ኛ Crtl+R በመጫን CMD ብለው በመጻፍ OKን ይጫኑ
3ኛ start -> Search Box ላይ CMD ወይም Command Prompt ብለው ይፈልጉ።
ከዛም Right Click በማድረግ Run as Administrator ብለው ይጫኑ
ከዛም ከሶስቱ 1ን አማራጭ ተጠቅመው ሲከፍቱት Black Screen ይመጣላችኋል። ከዛም ከታች ከ1-8ኛ ድረስ ያለውን ተግባራቶችን ይሞክሩ።
አዘጋጅ Muhammed Computer Technology
✅ 1ኛ net user ይህ ኮማንድ የሚጠቅመን ከኮምፒውተራችን ያሉንት Users ይዘረዝርልናል። እንዲሁም ከማንኛውም ኮምፒውተር ላይ Administrator የሚል አካውንት አለ እሱ ምን እንደሆነ ከታች መልሱን ያገኛሉ።
✅ 2ኛ net user muhammed /add ይህ ኮማንድ ከኮምፒውተራችን ላይ muhammed የሚባል User Create(እንዲፈጠር ያደርግልናል)
✅ 3ኛ net user muhammed * ይህ ኮማንድ ከላይ ለፈጠራችሁት muhammed ለሚባል User ወይም ከዚህ በፊት ላለ User ለምሳሌ amin የሚባል ቢኖር Muhammed በሚለው ፈንታ amin የሚለውን ስታስገቡ ለUseሩ Password እንድታስገቡ ይጋብዛችኋል። ትኩረት‼️ሁለት ጊዜ password እንድታስገቡ ይጠይቃችኋል ሁለቱም password ተመሳሳይ መሆን አለበት። እንዲሁም ፓስውርድ ስታስገቡ እይታያችሁም ወይም ፓስወርድ ስትጽፉ አይታያችሁም ግን በውስጥ ታዋቂነት እየጻፈ ስለሆነ ግራ እንዳትጋቡ።
ነገርግን ለUseሩ password ነስጠት ባትፈልጉ ዝም ብላችሁ 2 ጊዜ Enterን መጫን ብቻ ነው።
✅ 4ኛ net user muhammed /add * ይህ ኮማንድ የሚያገለግለን አንድን User ከነ password Create(መፍጠር) ብትፈልጉ ይህንን መጠቀም አለባችሁ። ኮማንዱ በመጀመሪያ ደረጃ User create ያደርግና በተመሳሳይ ፓስወርድ እንድታስገቡ ይጋብዛችኋል። password ማስገብት ከፈለጋችሁ አስገቡ ግን password ማስገባት ካልፈለጋችሁ Enterን 2 ጊዜ ይጫኑ።
ይህ ማለት ከላይ ተ.ቁ 2ና 3ን በአንድ ጊዜ ለመስራት ያገለግለናል።
✅ 5ኛ net localgroup Administrators muhammed /add ይህ ኮማንድ ከላይ የፈጠርነው user ምን ጊዜም Standard User ነው የሚሆነው።
በኮምፒውተር ተጠቃሚዎች አይነት Users Type በ3 ይከፈላል 1ኛ Administrator 2ኛ Standard User 3ኛ Gusts ናቸው።
እነዚህ Users ለምሳሌ ከላይ የፈጠርነው User Muhammed የሚባለው ከላይ ባለው ኮማንድ ሲፈጠር Standard User ነው። Standard User ደግሞ በኮምፒውተሩ ላይ ሙሉ የሆነ የመቆጣጠር አቅም የለውም የግድ ምን መሆን አለበት Administrator መሆን አለበት።
ስለዚህ ከላይ ያለውን 5ኛ ተ.ቁን Command መጠቀም ይኖርብናል።
✅ 6ኛ net localgroup Administrators muhammed /del ይህ ኮማንድ በተ.ቁ 5 ላይ muhammed የሚባለውን User ወደ Administratorነት ቀይረነዋል ነገር ግን ወደ Standar User ለመቀየር ከተፈለገ 6ኛውን ኮማንድ መጠቀም አለብን ማለት ነው። ይህም Muhammed የሚባለውን User ከ Administrator Account Type ወደ Standard User Account Type ቀየርነው ማለት ነው።
✅ 7ኛ ከማንኛው ኮምፒውተር ላይ Administrator የሚባል User አለ ይህ User ለአደጋ ጊዜ ተብሎ የተቀመጠ User አለ ይህ User ከኮምፒዩተሩ ተደብቆ ሁኖ ነው ያለው ይህንን User መሉ በሙሉ ከኮምፒውተሩ ማጥፋት አይቻልም ነገርግን ሌሎች የተፈጠሩ User Account ማጥፋት ትቻላል። ለእናንተ የምመክራችሁ User Accountችን ሊጠፋብን ይችላል የሚል ስጋት ካለባችሁ Administrator የሚባለውን User Account Active ማድረግ አለባችሁ አሁን እሱን እናያለን!
🛑 net user Administrator active:yes
ከኮምፒውተሩ የተፈጠረን User Account ሳናጠፋ Inactive ለማድረግ ወይም እንዳይሰራ ለማድረግ ለምሳሌ muhammed የሚለውን እንዳይሰራ ለማድረግ።
🔷 net user muhammed active:no ይህ ኮማንድ muhammed የሚባለው user inactive ሁኗል ማለት ነው። እንደገና ግን Active ለማድረግ ከፈለጋችሁ
🔶 bet user muhammed active:yes የሚለውን ኮማንድ ተጠቀሙ።
✅ 8ኛ ከኮምፒውተሩ ያለውን User Account ሙሉ በሙሉ ለማጥፋት ከፈለጋችሁ ለምሳሌ muhammed የሚባለውን ማጥፈት ብትፈልጉ
🛑 net user muhammed /del
ማስጠንቀቂያ ይህ ኮማንድ ለምሳሌ muhammed የሚባለውን user መረጃ ሙሉ በሙሉ ነው የሚያጠፋው ያ ማለት በውጡ ያስቀመጣቸው Desktop ላይ My Documents ላይ My Music ላይ My Picture ላይ ያስቀመጣቸውን ሙሉ መረጃ ያጠፋብናል ስለዚህ ትኩረት ማድረግ አለባችሁ።
ግን ለትምህርት ለምሳሌ እንደእስካሁኑ muhammed የሚባል User Account ላይ እንደ መለማመጃ ልትጠቀሙበት ትችላላችሁ።
#ይሞክሩት!
ከተመቻችሁ ለሌሎች እንዲደርሳቸው #ሼር ቢያደርጉ ጥሩነት ነው።
👍2