Muhammed Computer Technology (MCT)
38.1K subscribers
527 photos
7 videos
254 files
910 links
🔴አድራሻ:-
✅ ስ.ቁ: 0929273364
✅ ዌብሳይት www.mctplc.com
✅ቴሌግራም አካውንት: https://t.me/mctplc
✅ email: mct16plc@gmail.com
✅ ቲክቶክ አካውንት tiktok.com/@mctplc
Download Telegram
✳️ የዊንዶዉስ-10 ቨርዥን "1809" በሚቀጥለዉ ሳምንት አገልግሎቱ ይቋረጣል

ግዙፉ #የቴክኖሎጂ ኩባንያ ማይክሮሶፍት የዊንዶዉስ-10 የቨርዥን (version-1809) ምርቱ ከሚቀጥለዉ ሳምንት ጀምሮ አገልግሎቱን እንደሚያቋርጥ ገለጸ፡፡
አገልግሎታቸዉ ላበቃ ምርቶች ቴክኒካዊ ድጋፎችን እንደማያቀርብ የገለጸዉ ማይክሮሶፍት ይህን ተከትሎ በሶፍትዌሮቹ ላይ ለሚከሰቱ የሶፍትዌር ክፍተቶች እና ተጋላጭነቶችም ማዘመኛዎችን እንደማያቀርብ እና የደህንነት ጥገናዎችንም እንደማያደርግ አሳውቋል።

የአገልግሎት ጊዜያቸዉ ያበቃ ሶፍትዌሮችን አሁንም ድረስ የሚጠቀሙ ደንበኞች የሲስተሞቻቸዉን ከጉዳት ነፃ እንዲሆኑ እና ከመረጃ ጥቃቶች እንዲጠበቁ በፍጥነት ምርቶቻቸዉን ወደ ቅርብ ጊዜ የዊንዶዉ-10 ቨርዥኖች እንዲያሻሽሉ ማይክሮሶፍት አሳስቧል፡፡
የኢንተርፕራይዝ (Enterprise)፣ የኢዱኬሽን (Education) እና ከኢንተርኔት ጋር የተቆራኙ ቁሶች (IoT Enterprise) ሆነዉ የዊንዶዉስ-10 ቨርዥን 1809 ተጠቃሚዎ አገልግሎቱን እስከ ፈረንጆቹ ግንቦት 11/2021 እንደሚቆይላቸዉ ታዉቋል፡፡
በመሆኑን እርስዎ እየተገለገሉበት ያለዉ ኮምፒዉተር ዊንዶዉስ-10 ቨርዥን 1809 ከሆነ በመጀመሪያ ወደ ዊንዶዉስ-10 ቨርዥን 1903 ካዘመኑ በኋላ ወደ የዊንዶዉስ-10 ቨርዥን 2004 ማሳደግ እና በኮምፒዉተሩ በመተግበር (installed) ይኖርዎታል፡፡
ይህንን የዝመና አማራጭ ማይክሮሶፍት ባያበረታታዉም ተጠቃሚዎች Media Creation Tool ተጠቅመዉ ምርቶቻቸዉን ማዘመን ይችላሉ፡፡
እርስዎ እየተጠቀሙበት ያለዉን የዊንዶዉ ቨርዥን ለማወቅ በመጀመሪያ Start የሚለዉን በመጫን > "Settings" የሚለዉን መምረጥ > ከዚያም "System" ሲስተምን በመጫን > "About" የሚለዉን መምረጥ የኮምፒዉተርዎን ቨርዥን ማወቅ ይችላሉ፡፡ አልያም window + R ተጭነው በሚመጣላቹ ዊንዶውስ ላይ winver ብላቹ enter ስትሉት ያሳያችዋል።
ስሞኑን የለቀቅኳቸው ጥሩና አስተማሪ ቪዲዮዎች አሉ እነሱን እንድታዪቸው ግብዣየ ነው። በተጨማሪም አዳዲስ ቪዲዮችን እየሰራሁ ስለሆነ #Subscribe በማድረግ ምርጥ ምርጥ ትምህርታዊ ቪዲዮዎችን ይከታተሉ!
#ያወቁትን ማሳወቅ ብልህነት ነው!
የ YouTube ቻናል ሊንክ 👇👇👇
https://www.youtube.com/channel/UCZBIP6PqUdmmagdTjbyp_AQ
ሰለ ቴሌግራም ማወቅ ያለባችሁ 10 ወሳኝ ነጋሮች

✔ 1ኛ :- ያለንበትን ቦታ ለጓደኞቻችን መላክ እንችላለን እንዴት መጀመሪያ ቴሌግራም እንከፍታለን ከዛ የምንልከውን ሰዉ እንመርጣለን ከዛ መላክዋን ከፍተን location የምለውን ተጭነን ያለንበትን ቦታ መላክ ይቻላል ::

✔ 2ኛ :- ከኛ ወጪ ማንም ሰው ቴሌግራማችንን ማንም ሰዉ እንደይጠቀም ከፈለግን password ማዘጋጀት ይቻላል እንዴት መጀመሪያ ቴሌግራም እንከፍታለን ከዛ በቴሌግራም ጫፈ ላይ ሦስት መሰመር አለ እሱን አንዴ እንነካለን ከዛ setting የምለውን እንነካለን ከዛ privacy and security የምለውን እንነካለን ከዛ passcode የምለወን እንነካለን ከዛ passcode lock on እናደርጋለን ከዛ የምንፈልገውን password እናስገባለን ::

✔ 3ኛ:- እንዴት ቴሌግራም ብር እንደይበላ ማድረግ ይቻላል
በመጀመሪያ ቴሌግራም እንከፍታለን ከዛ በቴሌግራም ጫፈ ያለውን ሦስቷን መሰመር እንነካለን ከዛ setting ላይ እንገባለን ከዛ data and storage የምለዉን እንነካለን ከዛ
ከዛ when using mobile data -OF-አድርጉት ::

✔4ኛ :- የለክነዉን message ከደረሰ ቦኃላ delete ማድረግ ይቻላል እንዴት መጀመሪያ የለነክነዉን message እንከፍታለን ከዛ ቦታዉ ላይ አጥብቀን እንዛለን ከዛ ከላይ የምለውን Also delete receive የምለውን ራይት እናደርጋለን ከዛ ሁለቱም ጋ delete ይሆናል ::
5ኛ :- እንዴት በአንድ የቴሌግራም አፕሊኬሽን ሁለት account እንጠቀማለን
በመጀመሪያ ቴሌግራም እንከፍታለን ከዛ ከላይ
በቴሌግራሙ ጫፍ ላይ የለወን ሦስት መሰመር እንነካለን ከዛ ይህችን ምልክት ይንኩ ( v ) ከዛ new account ይለናል ከዛ መክፈት

✅6ኛ :- በተላይ ማታ ማታ ስንጠቀም ዓይናችን እንደይጎዳ ቴሌግራማችን በጥቁር መልክ እንድሆን ከፍለግን dark ,, black ,, colour እንድትሆን ከፈለግን ...
በመጀመሪያ ቴሌግራም እንከፍታለን ከዛ የቴሌግራም ጫፈ ላይ የለወን ሦስት መሰመር እንነካለን ከዛ chat setting ላይ ገብተን ከምሰጠን የመልክ ምርጫ የፍለግነዉን እንመርጣለን ::

✔7ኛ :- ቴሌግራም የሉ ፅፎች አልነበብ እየሎት ተቸግረዋል ማለት ፍደሎችሁ አንሰዉ ለዓይን አልተይ ከለ ፍደሎቹሁን ትልቅ ማድረግ ይቻላል እንዴት ?
አዎ በመጀመሪያ ቴሌግራም እንከፍታለን ከዛ በቴሌግራም ጫፍ ላይ ያለውን ሦስት መሰመር እንነካለን ከዛ chat setting ላይ እንገባለን ከዛ message text size የምል አለ እሱን እንነካና የፍለግነዉን ያህል ትልቅ ማድርግየ ይቻላል ::

✔8ኛ:- እንዴት የራሳችንን የቴሌግራም ቻናል መክፈት እንችላለን ?
በመጀመሪያ ቴሌግራም እንከፍታለን
ከዛ በቴሌግራም ጫፈ ላይ ያለውን ሦስት መሰመር እንነካለን ከዛ New channel የምለውን ነክተን create new channel የምለውን እንነካለን ከዛ እኛ ለመክፈት የፍለግነዉን የቻናል ስም እናስገባለን ::

✔9ኛ :- እንዴት የራሳችንን የቴሌግራፍ ጉሩፒ እንከፍታለን ?
በመጀመሪያ ቴሌግራም እንከፍታለን ከዛ ከላይ የለዉን ሦስት መሰመር እንነካለን ከዛ new group የምለውን እንነካለን ከዛ create new groupጠ የምለዉን እንነካለን ከዛ እኛ ለመክፍት የፍለግነዉን የጉሩፒ ስም እናስገባለን ::

✔10ኛ :- እንዴት አድርገን profile photo መቀየር እንችላለን ?
በመጀመሪያ ቴሌግራም እንከፍታለን ከዛ ከላይ ያለዉን ሦስት መሰመር እንነካለን ከዛ setting ላይ እንገባለን ከዛ set profile photo የምለውን በመንካት የፍለግነዉን ፎቶ መቀየር ይቻላል ።
#የመመረቂያ_ጽሁፍ_ሪሰርች_ለሚሰሩ_ለተመራቂ_ተማሪዎች
# ጥሩ_የጥናት_አቀራሪብ_መረጃ
Good research presentation (Defense)
ጥሩ አቀራረብ እንዲያደርጉ የሚረዱዋችሁን አንዳንድ ነጥቦች።
ጥናታዊ ጽሑፍን በጥሩ ሁኔታ ለማቅረብ (good presentation) ከሚረዱ ቁልፍ ነገሮች አንዱ በጥሩ ሁኔታ የተዘጋጀ ኃይል ሰጪ ማብራሪያ ነጥብ (PowerPoint) ነው። እርስዎ # ጥሩ ማብራሪያ ነጥብ (power point) እንዲኖርዎ ደግሞ እነዚህን ይጠቀሙ፦
.
# 1ኛ . ኃይል ሰጪ ማብራሪያ ነጥብ (Powerpoint) ብዙ ስላይድ አይኑረው። በ15 ደቂቃ ለማቅረብ እስከ 15 በዛ ከተባለ ከ20 እስከ 25 ማሳያ (slide) እጅግ በቂ ነው።
«Oral presentation is visual as well as an auditory medium» በቃልዎት የሚያብራሩት ቢሆን የተሻለ ዋጋ ያለው መሆኑን እና የጥናቱ ባለቤት መሆንዎን የሚያረጋህጥ መሆኑን አይርሱ።
.
# 2ኛ . ማሳያ (slide) በብዙ ጽሑፍ የተጠቀጠቀ መሆን የለበትም። ከጽሑፍ ይልቅ ፎቶዎችን፣ ግራፎችንና ሰንጠረዦችን በደምብ ይጠቀሙ። "አንድ ፎቶ ወይም ሰንጠረዥ ከ1000 ቃላት በላይ ገላጭ ነው" የሚለውን አባባል ልብ ይበሉ።
.
# 3ኛ . መብራራት የሚፈልጉ ቃላትን ብቻ በርዕስ መልክ ይጻፉ። ማብራሪያቸውን የግድ ማሳያ (slide) ላይ መፃፍ አይጠበቅብዎትም።
«One of the most common fault or error commited by graduate student is to write every single words and detail full sentences on their slides» ነው የሚለው። Please never crowd each slide !!!
.
# 4ኛ . የሚቀርበው ጥናት እጅግ ሰፊ ይዘት ያለው ቢሆን ለመመጠን ሳይቸገሩ በማሳያ (slide) ላይ ለመዳሰስ ማሳያዎትን (slide) በክፍል በክፍል (part) ይክፈሉት።
....... Introduction (መግቢያ)
....... Main Body (ሃተታ) as Discussion
....... Conclusion ( መደምደሚያ) ያድርጉት።
.
# 5ኛ . ከአንዱ ማሳያ (slide) ወደ ሌላው ሲዘዋወሩ (ሲሸጋገሩ) ጊዜ እንዳይወስድብዎ (እንዳይንቀረፈፍ) Animation ባይጠበሙ ይመረጣል።
.
# 6ኛ . በማሳያዎ (slide) ላይ የሚሰፍሩ ጽሑፎች በትንሹ በ24 መጠን (Font Size) መሆን ይጠበቅባቸዋል።
ከዚያ በታች ከሆኑ ላይታዩ ስለሚችሉ ታዳሚዎትን ያስከፋሉ፣ ሥራዎትን ይደብቃሉ ማለት ነው።
.
# 7ኛ . የጽሑፎቹ ቅርጽ አይነት (Font type) "Time new roman" ቢሆን የተሻለ ነው። ከዚህ ካለፉ ግን Nyala እና Countur ይጠቀሙ።
በተለይ ግን script አይነት ቅርፅ ያለው ጽሑፍ አያድርጉት። የማሳያው ጀርባ ወይም መደብ (Background) ከፊደሎቹ ቀለም (font color) ፍጹም ተቃራኒ ቀለም ያለው መሆን አለበት። ብዙ ጊዜ በነጭ መደብ ላይ ጥቁር ቀለም ያላቸውን ፊደላት (ጽሑፎች) መጠቀም ቢችሉ ይመከራሉ።
.
# 8ኛ . ሙሉ ሃሳብዎን ለመግለፅ ትላልቅ ፊደላትን (Capital letter) ከመጠቀም ይቆጠቡ። ለማንበብና ለመረዳት ቀላሉ ትናንሽ ፊደላትን (Small letters) መጠቀም መሆኑ አይዘንጉ።
.
# 9ኛ . የማሳያ (slide) ጽሑፎች እጅግ ብዙ የቀለም (Font colour) ዝብርቅርቅ የበዛበት ከሆነ አትኩሮትን ግራ ስለሚያጋባ ብዙ ቀለም አይጠቀሙ። ከተቻለ በአንድ አይነት ቀለም ቢሆን ካልሆነ ግን ልዩ ገለጻ የሚፈልጉትን ለማቅለም ሁለት ቀለሞች በቂ ናቸው።
.
# 10ኛ . የ (Spelling of words, gramatical structure of sentences, punctuations… ) ስህተት እንዳይኖርብዎት ቢጠነቀቁ የተሻለ ውጠኣማ ይሆናሉ።
# 11ኛ . አስተያየት (professional recommendation) በሚለው የጥናት ክፍልዎ ውስጥ ከተማሩበት አንጻር ለደረሱባቸው ችግሮች መንገዶችን ለመጠቆም ይሞክሩ ይንጅ "# ድርጅቱ_ይህንን_ችግር_ማስተካከል_አለበት " የሚል ደረቅ ትዕዛዝ ከማስገባት ይቆጠቡ። የሚያስተካክለው እንዴት ባለ ዘዴ፤ መቼ፣ በማን፣ የት፣ ለምን.. እንደሆነ ሙያዊ ድጋፍ መስጠትዎን አይርሱ።
.
# 11ኛ. ያዘጋጁትን ማሳያ (slide) ከማቅረብዎ በፊት ደጋግመው ያንብቡ።
.
አዘጋጁ
~ አለባበሱ ?
~ ከሰላምታ ጀምሮ እስከ ምስጋና ያለው አነጋገሩ ?
~ መጠቀም የሌለበት ቃላት ?
~ የቡድን ሥራ ሲሆንስ ?
~ ጥያቄና መልስ ምን መምሰል አለበት ?
የሚሉትን በቀጣይ ክፍሎች ለመዳሰስ እሞክራለሁ። ለውድ የሀገሬ # የኢትዮጵያ ተመራቂ የኮሌጅና የዩኒቨርሲስቲ ተማሪዎች መልካም የጥናት ማጠቃለያ ጊዜ ይሁንላችሁ።
~~~ {Daniel Shewaatek - ዘጽዮን}
~~~ [Instructor at Ethiopia University]
መልካም ዕድል!!!!!
ምንጭ፦
Introduction to Research Methods - AAU (~~~ {Daniel Shewaatek - ዘጽዮን})
# የተማሩትን_ማስተማር # ያወቁትን_ማሳወቅ # ብልህነት ነው
# ለሰው መልካሙን እንጅ መጥፎውን አትመኝ
# ስለኮምፒውተር ያለዎትን እውቀት ያጎለብታሉ
ይህ የኔ የፌስቡክ ገጽ ነው ስለሆነም ፔጄን ላይ ጠቃሚና ወቅታዊ መረጃዎች ያገኛሉ
ሙሀመድ አሚን በቴሌግራም መከታተል ለምትፈልጉ https://t.me/MuhammedComputerTechnology በዚህ የቴሌግራም ቻናል ብዙ ጠቃሚ መረጃዎችን ታገኛላችሁ
https://m.facebook.com/mameamin.6te.net
ስለዚህ ፔጁን # ላይክ # ሼር በማድረግ ለሌሎች እህት ወንድሞች ጓደኞቻችሁ እንዲደርስ ያድርጉ
# በይበልጥ_ስለኮምፒውተር_ይማራሉ
# ፔጄን_like_share_ያድርጉ_መረጃ_እንዲደርሳችሁ
❤1
ስሞኑን የለቀቅኳቸው ጥሩና አስተማሪ ቪዲዮዎች አሉ እነሱን እንድታዪቸው ግብዣየ ነው። በተጨማሪም አዳዲስ ቪዲዮችን እየሰራሁ ስለሆነ #Subscribe በማድረግ ምርጥ ምርጥ ትምህርታዊ ቪዲዮዎችን ይከታተሉ!
#ያወቁትን ማሳወቅ ብልህነት ነው!
የ YouTube ቻናል ሊንክ 👇👇👇
https://www.youtube.com/channel/UCZBIP6PqUdmmagdTjbyp_AQ
ዲሽ አተካከል ለፍፁም ጀማሪዎችና ለተካኑ ቴክኒሽያን በሙለር IT solution የተዘጋጀ!

✅ በቴሌግራም ቻናል: https://t.me/MuhammedComputerTechnology
https://t.me/MuhammedComputerTechnology
ቴሌግራምዎን hack እንዳይደረግብዎ ይፈልጋሉ❓

✔️መፍትሄውን እነሆ👇👇👇

👉ቴሌግራም ማለት እንደ ማንኛውም የ messaging application ነው ማለትም እንደ⇝whatts app,viber, imo,tango.....etc
👉ቴሌግራም እንደ whatsapp,viber,imo...ሁሉ በቀላሉ በ "sms-based verification process" hack ሊደረግ ይችላል✅

✴️ሌሎችም hack ማድረጊያ አፕሊኬሽኖች አሉ
ማለትም 👉desktop app
👉android app አሉ።
እናም በነዚህ👆 የሀኪንግ አይነቶች አካውንታቹ ሌላ ስልክ ላይ ወይም ሌላ #pc ላይ ሊኖር ይችላል✅

1⃣.በመጀመሪያም ይህ መሆኑን እና አለመሆኑን ለማረጋገጥ አሁን step by step ተከታተሉኝ
💢Telegram⇢seting⇢privecy and security⇢active session 👉 ላይ በመግባት በእናንተ አካውንት የገባ ሰው እንዳለና እንደሌለ ማወቅ ያስችላል።

⚠️Note: እራስዎ በሌላ #አፕ ከገቡም ያመጣልዎታል መርጠው መርጠው ነው።

✴️ ከዛም Terminate all other sessions ክሊክ በሉት፤ ይህ ሚጠቅመው በሌላ ስልክ 📱 የእናንተን #አካውንት የሚጠቀም ሰው ካለ remove ያደርገዋል።

2⃣.Security ደግሞ ለማጠናከር👇

seting⇢privecy and security⇢two step verification⇢set aditional pasword ከዛ የፈለጉትን password *..

⚠️ግን የ #gmail አካውንት ሊኖራቹ ይገባል።

✴️ ይህ👆 ጠንካራ የሚባለው #የቴሌግራም security ነው።

✔️የሚጠቅመው #እንደፌስቡክ ሁላ በሌላ ስልክ📲 ስንገባ password ይጠይቀናል (log in) እያልን ነው የምንገባው ማለት ነው።

✔️ ሌላ ሰው #በsms የተላከውን ኮዳችሁን አግኝቶ እንኳ ቢከፍተው
ወደቴሌግራማችሁ በጭራሽ መግባት አይችልም።

✴️ ማንም ሰው ለመግባት #በኢሜል የሰጣችሁት ኮድ ማወቅ ስለማይችል በጭራሽ❌ መግባት አይችልም፥፥

⚠️የፃፋችሁትን password እንዳትረሱት::


መረጃዎች ቶሎ ቶሎ እንዲደርሳችሁ ቻናላችንን #Mute ያደረጋችሁት #UNMUTE በማድረግ ተባበሩን🙏🙏🙏"

⚠️መረጃዎችን ለወዳጅዎ 👥 ያጋሩ
ለቪዲዮ ኤዲቲንግ የሚያገለግሉ 9 የ አንግሮይድ አፖች

ቪዲዮን ኤዲት ለማድረግ የግድ ኮምፒውተር መጠቀም አይኖርቦትም። ዘመን አፈራሽ የሆኑ ቴክኖሎጂዎች ሞባይል ስልኮን ክኮምፒውተር ባልተናነሰ መልኩ ቪዲዮን ኤዲት አንዲያደርጉ ያስችሎታል። እኛም 10 ለቪዲዮ ኤዲቲንግ ያገለግላሉ ያልናቸውን አፖች የዘን ቀርበናል።

1, FilmoraGo በብዙ ተጠቃሚዎች ዘንድ የተወደደ አስደናቂ የ ዓንድሮኢድ ቪዲዮ ኤዲቲንግ መተግበሪያ ነው። የመቁረጥ ፣ ገጽታዎችን መቀየር ፣ ሙዚቃን የመሳሰሉት ዋና ዋና ተግባራት በቀላሉ ሊከናወኑ ይችላሉ ፡፡ እንዲሁም ለ Youtube ለ Instagram እና ለ Facebook ሚሆኒ ቪዲዮችን መስራት ይችናሉ
የዳውንሎድ ሊንክ: https://play.google.com/store/apps/details?id=com.wondershare.filmorago

2, Adobe Premiere Clip: አዶቤ ፕሪሚየር ክሊፕ ማንኛውንም ቪዲዮ ከእርስዎ የ ስማርት ፎን በፍጥነት እንዲያርትዑ ያስችልዎታል። ለመጠቀም ፈጣን እና አዝናኝ ነው። ስለ ክሊፕ በጣም ጥሩው ባህሪ አውቶማቲክ ቪዲዮ መፍጠር ችሎታ ነው ፣ ማለትም ፣ መተግበሪያው በመረጣቸው ማንኛቸውም ፎቶዎች ወይም ቅንጥቦች አማካኝነት ቪዲዮዎችን በራስ-ሰር ለእርስዎ መፍጠር ይችላል ፡፡
የዳውንሎድ ሊንክ: https://play.google.com/store/apps/details?id=com.adobe.premiereclip

3, VideoShow ብዙ ሽልማቶችን የተቀበለ ሲሆን በነጻ በ Play Store ውስጥ ለሚገኙት ምርጥ የቪዲዮ መተግበሪያዎች አንዱ ነው። VideoShow ለአጠቃቀም ቀላል እና ለአጠቃቀም ቀላል ነው ፡፡ ከዋና ዋና ተግባራት ፊልተሮችን ፣ ሙዚቃዎችን እና የድምፅ ውጤቶችን በመጨመር ወይም ቀጥታ ስርጭትን በማከናወን ቪዲዮዎን ማስዋብ ይችላሉ ፡፡
የዳውንሎድ ሊንክ: https://play.google.com/store/apps/details?id=com.xvideostudio.videoeditor

4, PowerDirector ለአጠቃቀም ቀላል የሆነ የጊዜ መስመር ያለው ሙሉ ለሙሉ የ አንግሮይድ ቪዲዮ ኤዲተር ነው ፣ ግን ከመቆጣጠሪዎች ጋር ለመግባባት የተወሰነ ጊዜ ሊወስድዎት ይችላል። ሆኖም ፣ አንዴ በዚህ መተግበሪያ ኤክስ ኤክስፐርት ከሆኑ ባለሙያዎችን መፍጠር እና በሰከንዶች ጊዜ ውስጥ ምርጥ የሚባሉ ቪዲዮዎችን መስራት ይችላሉ ፡፡ ከቪድዮዎ ውስጥ ለመምረጥ ከ 30 በላይ የተለያዩ የትራንዚሽን ምርጫዎች አሉት ፡፡
የዳውንሎድ ሊንክ: https://play.google.com/store/apps/details?id=com.cyberlink.powerdirector.DRA140225_01
5, KineMaster ከኃይለኛ ባህሪዎች ጋር በጥሩ ሁኔታ ከተሰራ በይነገጽ ጋር በመጣመር KineMaster ለ Android ተስማሚ የቪዲዮ አርት ኤዲቲንግ መሣሪያ ነው። የተለያዩ የሚዲያ ፋይሎችን በቀላሉ ለማስመጣት የ “copy paste” መጠቀም ይችላሉ። ቪዲዮዎችን በፍጥነት ለመፍጠር KineMaster ኤዲቲንግ ሂደት ላይ በይበልጥ ይረዳል። በቪዲዮ መቁረጥ የተለያዩ የሽግግር ዓይነቶችን መጨመር ፣ ወይም የጽሁፎችን ወይም የትርጉም ጽሑፎችን ብሎግ ማስገባት ይችላሉ

የዳውንሎድ ሊንክ: https://play.google.com/store/apps/details?id=com.nexstreaming.app.kinemasterfree

6, Quik እጅግ በጣም ጥሩ ቪዲዮዎችን ለመፍጠር ኩዊክ ሌላ ብልጥ መንገድ ነው ፡፡ ፈጣን እና ነፃ ነው። የራስዎን ታሪኮች በኩዊክ ለማድረግ የራስዎን ተወዳጅ ፎቶዎች ወይም ቪዲዮ ይምረጡ። ስለ ኩዊክ በጣም ጥሩው ነገር አውቶማቲክ የቪዲዮ ፈጠራ ችሎታዎች ይዞ መምጣቱ መሆኑ ነው ፡፡ ቪዲዮዎችን crop ማድረግ ፣ ማሳመሪያዎችን ፣ ጽሑፎችን መጨመር እና ማንኛውንም Audio መምታት በፍጥነት ማመሳሰል ይችላሉ ፡፡
የዳውንሎድ ሊንክ: https://play.google.com/store/apps/details?id=com.stupeflix.replay
7, VivaVideo ብዙ አስደናቂ ባህሪዎች አሉት። መተግበሪያው በቀጥታ ከ አንግሮይድዎ ፕሮፌሽናል-የሚመስሉ ቪዲዮዎችን እንዲፈጥሩ ለማገዝ የታሰበ ነው። ከተለጣፊዎች እስከ ተንቀሣቃሽ ክሊፖች እና የትርጉም ጽሑፎች ከሚገኙ በመቶዎች የሚቆጠሩ ተስማሚ ፊልተሮች መምረጥ ይችላሉ ፡፡ በውስጡ የማይንቀሳቀስ ዘገምተኛ(slow motion) ተንቀሳቃሽ ቪዲዮ ሰሪ እና የተንሸራታች ማሳያ(slideshow maker) ሰሪ አለው።
የዳውንሎድ ሊንክ: https://play.google.com/store/apps/details?id=com.quvideo.xiaoying

8, Funimate video editor በቀላሉ አዝናኝ ቪዲዮዎችን ለመፍጠር ይረዳል። የዕለት ተዕለት አፍታዎችን ወዲያውኑ ወደ የፈጠራ ቪዲዮዎችን መለወጥ እና ለተለያዩ ማህበራዊ ሜዲያ የማጋሪያ አማራጮች አሉት ። አጭር ቪዲዮዎችን ኤዲት ለማድረግ የታቀዱ ከ 1 በላይ የላቁ አማራጮች አሉት ፡፡

የዳውንሎድ ሊንክ: https://play.google.com/store/apps/details?id=com.avcrbt.funimate

9, Magisto መደበኛ የቪዲዮ ኤዲቲንግ ተሞክሮ ለሌላቸው ምርጥ የቪዲዮ ኤዲቲንግ መተግበሪያ ነው። ብዙ ጥረት ሳያደርጉ ምርጥ ቪዲዮን ለመስራት እንዲረዳዎ የቪዲዮ ክሊፕ ፣ ፎቶግራፎችን ፣ audio ፣ ጽሑፎችን ፣ የቪዲዮ ውጤቶችን እና የቪዲዮ ማጣሪያዎችን ይይዛል ፡፡ አንድ ወይም ከዛ በላይ ቪዲዮ ክሊፕ እና ለድምጽ ማጫወቻው አንድ ዘፈን ይምረጡ እና መተግበሪያው በጥቂት ደቂቃዎች ውስጥ አውቶማቲካሊ ቪዲዮ ይፈጥራል።
የዳውንሎድ ሊንክ: https://play.google.com/store/apps/details?id=com.magisto
❤1
#EaseUS_Data_Recovery_Wizard_Pro

#የሚሰጣቸው_ጥቅሞች
#1ኛ_የጠፉ_Permanently_Delete_የተደረጉ_የትኛውንም አይነት መረጃ ከኮምፒውተራችን,ከፍለሻችን,ከHD Recover ማድረግ ያስችለናል።
#2ኛ Formate የተደረጉ የትኛውንም Storage Recover ማድረግ ያስችለናል።
#የተለያዩ_ጥቅሞች_አሉት.....
👍2
ድንገት Delete (Format) ያረግናቸውን
ለምሳሌ :-
▫️ፍይል
▫️ዶክመንትን
▫️ፎቶዎችን
▫️ቪዲዮዎችን
▫️ሌሎችም በድጋሜ ለመመለስ የሚጠቅሙ ምርጥ ሶፍትዌር ለዊንዶውስ ተጠቃሚዎች
#EaseUS_Data_Recovery_Wizard_Pro
👆 ከላይ ያለውን በማውረድ መጠቀም ትችላላችሁ 👆👆
#የሚሰጣቸው_ጥቅሞች
#1ኛ_የጠፉ_Permanently_Delete_የተደረጉ_የትኛውንም አይነት መረጃ ከኮምፒውተራችን,ከፍለሻችን,ከHD Recover ማድረግ ያስችለናል።
#2ኛ Formate የተደረጉ የትኛውንም Storage Recover ማድረግ ያስችለናል።
#የተለያዩ_ጥቅሞች_አሉት.....
አካሄዳችን እየተመቻችሁ ነው?
Anonymous Poll
96%
ተመችቶኛል
4%
አልተመቸኝም
🌀ውድ የቻናላችን ተከታታዮች የተለያዩ ኮርሶችን መማር እና ማወቅ ለምትፈልጉ በሙሉ ማለትም ለምሳሌ #Programming , #Web_Development , #Networking እና ሌሎችም...(ከታች ያሉትን ሳይቶች ይጠቀሙ)


1. www.codecademy.com
2. www.lynda.com
3. www.udemy.com
4. www.udacity.com
5. www.coursera.org
6. www.w3schools.com
7. www.thenewboston.org
8. www.programmr.com
9. www.codeavengers.com
10. www.codeschool.com
11. www.learnstreet.com
12. www.teamtreehouse.com
13. www.sqlzoo.net
14. www.codehs.com
15. www.teamtreehouse.com
16. www.html5rocks.com
17. www.codepen.io
18. www.sitepoint.com
19. www.tutorialspoint.com
20. www.javatpoint.com
21. www.cplusplus.com
22. www.learncpp.com
23. www.tutorialspoint.com
24. www.cprogramming.com
25. www.stackoverflow.com
26. www.learncodethehardway.org
27. www.bloc.io
28. www.howtocode.io
29. www.edx.org
30. www.instructables.com
31. www.developer.apple.com
32. www.developer.android.com
33. www.developers.google.com
34. www.developer.mozilla.org
35. www.msdn.microsoft.com
36. www.decompera.com
37. www.www.developphp.com
38. www.quackit.com
39. www.htmlite.com
40. www.siteduzero.com
41. www.dreamincode.net
42. www.phpbuddy.com
43. www.php.net
44. www.microsoftvirtualacademy.com
45. www.professormesser.com

⚠️ " ማወቅ መልካም ነው፤ ያወቁትን ማሳወቅ ደግሞ በጎነት ነው። " [ Share ማድረጎን እንዳይረሱ።]

🔆 መልካም ቀን ይሁንላቹ
VLC ቪዲዮ ማጫወቻ አቋራጭ ቁልፎች (Shortcuts)
ዛሬ ከበርካታ ሚዲያ ማጫዎቻዎች መካከል በአቀራረቡ ተወዳጅነትን ያተረፈዉን ቪ ኤል ሲን(VLC) እንዴት አቋራጭ ቁልፎችን በመጠቀም በቀላሉ መገልገል እንደምንችል እናያለን፡፡
1. Play/pause
 Space bar የተሰኘዉን ቁልፍ በመጠቀም የምናየዉን ቪዲዮ ማቆም ና እንደገና ማጫዎት እንችላለን፡፡
2. Mute audio
 የምናየዉን ቪዲዮ ደምፅ ሚዉት(ለማጥፋት) ‘M’ን በመጫን ማጥፋት ና ደግመን ተጭነን ማብራት እንችላለን፡፡
3. Full screen
 ‘F’ን በመጠቀም በኮምፒዉተራችን ስክሪን ሙሉ ማየት ና ደግመን በመጫን ወደ ነበረበት መመለስ እንችላለን፡፡
4. Change audio track
 አንዳንድ ቪዲዮዎች ከአንድ በላይ የድምፅ (audio track) አማራጭ ሊኖራቸዉ ይችላል፡፡
በዚህ ጊዜ ‘B’ን በመጠቀም መቀያየር እንችላለን፡፡
5. Volume control
 ድምፅ ለመጨመር Ctrl + arrow up
 ድምፅ ለመቀነስ Ctrl + arrow down
6. Video play speed
 የምናየዉን ቪዲዮ ፍጥነት ለመቆጣጠር የሚከተሉትን ቁልፎች መጠቀም እንችላለን፡፡
• + ለመጨመር
• - ለመቀነስ
7. Seeking
 ቪዲዮዉን ለማሳለፍ 3 አይነት መንገዶችን መጠቀም እንችላለን፡፡
I. አጭር ወደ ፊት shift+right arrow (3 sec
II. አጭር ወደ ኋላ shift +left arrow
III. መካከለኛ ወደ ፊት alt +right arrow (10 sec
IV. መካከለኛ ወደ ኋላ alt + left arrow
V. ረጅም ወደ ፊት ctrl + right arrow (1 min
VI. ረጅም ወደ ኋላ ctrl + left arrow
8. Remaining time
 Full screen አርገን ቪዲዮ የምናይ ከሆነ ምን ያክል ሰዓት እንደቀረን አያሳየንም ስለዚህ ‘T’ን በመንካት ማየት እንችላለን
፡፡
9. Subtitles
 የምናየዉ ቪዲዮ subtitle ካለዉ ነገር ግን ፅሁፉ የሚረብሸን ከሆነ ‘V’ን ነክተን ማጥፋት እንዲሁም እንደገና ማምጣት እንችላለን፡፡

10. Record video
 እያየን ያለዉን ቪዲዮ ሪከርድ ማድረግ ብንፈልግ Shift + Rን በመጠቀም መቅዳት እንችላለን፡፡
ይህም cut አርገን ቪዲዮ ለመስራት ያስችለናል፡፡
11. Quit
 ጨርሰንም ሆነ አቋርጠን ቪዲዮዉን ለመዝጋት ከፈለግን ctrl + Q በመጫን መዉጣት እንችላለን፡፡
የሞባይል ስልክን operating System አፕዴት የማድረግ ጠቀሜታው ....
1.በፊት ከነበረው ሶፍትዌር በተጨማሪ አዳዲስ ሶፍትዌሮችና መገልገያዋችን
ያመጣል
2. ሞባይሉ አንዳንድ የሶፍትዌር ችግሮች ካሉበት አፕዴት አድርጎ ሲጨርስ
የነበሩበትን ችግሮች ያስተካክለዋል
3 . ሞባይሉ በፊት ከነበረው ይዘት በተለያዪ ነገሮች ለውጥን ያመጣል
ማስጠንቀቂያ
ሞባይል ስልክ አፕዴት ከማድረጋችን በፊት ሊደረጉ የሚገባቸው ጥንቃቄዋች
- ሞባይሉ ትክክለኛ(Original ) መሆኑን ማረጋገጥ
-ሞባይሉ Root ያልተደረገ መሆን ይኖርበታል
- ሞባይሉ አፕዴት እያደረገ ባትሪ መነቀል የለበትም
- ባትሪ ከ50% በላይ ቻርጅ ሊኖረው ይገባል
በተጨማሪም ሞባይሉን እራሳችን አፕዴት ማድረግ ከፈለግን ጥሩ ፍጥነት ያለው
WiFi internet ብንጠቀም ጥሩ ነው
ሞባይሉ በ WiFi internet አፕዴት ለማድረግ
1. ከ WiFi internet ማገናኘት
2. Settings የሚለውን መክፈት
3. ወደ ታች በመውረድ About መንካት
4. Check for Updates መንካት
5. Update
ዳታ በመጠቀም እንዳትሞክሩት በጣም ብዙ ብር ነው የሚበላችሁ። በWiFi update አድርጉ።
👍2
የቴክኖሎጂይ የቴሌግራም ቻናል ጥቆማ፡-
ሰላም እንዴት ናችሁ፤ዛሬም እንደተለመደዉ አንድ አዲስ የቴክኖሎጅ መረጃ ይዤላችሁ መጥቻለሁ፤
መረጃዉ ለእኔ በጣም ያስደመመኝና የተደሰትኩበት በመሆኑ እናንተም የመረጃዎቹ ተጋሪ ሁኑ እላለሁ፡፡
የምጠቁማችሁ ቻናል Byte Software Development P.L.C ሲሆን በቻናሉ ለተጠቃሚ ህ/ሰብ ዉስብስብ ችግሮችን በቀላል ቴክኖሎጂይ በማንኛዉም ባለሙያ መፍታት የሚያስችሉ ቴክኖሎጂዎችን የምናገኝበት ቻናል ሲሆን የተለያዩ ተቋማት ፕሮግራሞቹን በማሰራት ተግባራዊ አድርገዋቸዉ ከክልል እስከ ወረዳ ባሉ ቢሮዎች፤መምሪያዎችና ጽ/ቤት ይሁንታን እንዳገኙ በተሰጡ የምስክር ወረቀቶችና በተቀመጡ አድራሻዎች ለማረጋገጥ ችያለሁ፡፡
በፕሮግራሞቹ አዘጋጅ ከተዘጋጁት ፕሮግራሞች መካከል፤-
1. የከተሞች መጠጥ ዉሃና ፍሳሽ አገ/ጸ/ቤት(በዝርዝር 12 ፕሮግራሞችን የያዘ)፤
2. የትምህርት ቤት ስራዎችን ለማዘመን የተሰሩ(በዝርዝር 12 ፕሮግራሞችን የያዘ)፤
3. ለተቋራጮች የግንባታ ነጣላ፤የሚያስፈልግ ዕቃ፤የሰዉ ሀይል የሚሰራ፤
4. የመስኖ ዲዛይን መስሪያ፤
5. የመጠጥ ዉሃ ዲዛይን መስሪያ፤
6. የጤና ተቋማት የታካሚዎች ዳታ ቤዝ ወዘተ፡
ሲሆኑ ወደ ቴሌግራም ቻናሉ ከታች ያለዉን ሊንክ https://t.me/joinchat/AAAAAEg5y8d8AYbjgRJJVg
በመጫን ዝርዝር መረጃዎችን ማግግኘት ይችላሉ፡፡የፕሮግራሞቹን ዝርዝር ይዘን በሌላ ጊዜ እንመለሳለን፤
❤1
ሰላም እንዴት ናችሁ? ሰሞኑን በለቀቅኳቸው አስተማሪ ቪዲዮዎች በ10 ቀን ከ 12,500 ደቂቃ በላይ የታየ ሲሆነ ከ550 በላይ ደግሞ Subscribers አፍርቻለሁ። ስለሆነም ለሁላችሁም ምስጋናየ ይድረሳችሁ ብያለሁ። አሁንም ቢሆን ምርጥ የሆኑ ቪዲዮ እያዘጋጅሁ ስለሆነ ከትምህርቱ ተካፋይ ይሁኑ ስል በታላቅ አክብሮት ነው። የ
YouTube ቻናሉን Subscribe ማድረጋችሁን አትርሱ።
#ያወቁትን ማሳወቅ ብልህነት ነው!
የ YouTube ቻናል ሊንክ 👇👇👇
https://www.youtube.com/channel/UCZBIP6PqUdmmagdTjbyp_AQ
✅YouTube channel እንዴት #Subscribe እናደርጋለን?

➡️ስልካችሁ ላይ #Google account (Gmail) ካለ በቀላሉ "Subscribe" የሚለውን #መንካት ማረግ ይችላሉ Facebook ላይ ፎቶ like 👍 እንደማረግ ያህል ቀላል ነው።

➡️ስልካችሁ ላይ Google account (Gmail) የሌለ ደግሞ የGmail Username and password በማስገባት "Subscribe" ማድረግ ትችላላችሁ /ወደፊትም ድንገት ስልካችሁ📲 ቢበላሽ ይጠቅማችኋል።
💻 ኮምፒውተር ላይ በአማርኛ እንዴት እንደሚፃፍ ያውቃሉ?ሲጽፉስ ምን ያህል ይፈጥናሉ?


❖መጀመሪያ Ge'ez 10 Software ያወረዱ እና install ያድርጉት ከዛም አማርኛ መፃፍ ስትፈልጉ power ge'ez status phonetic Unicode Mode (ፎ) ላይ ያድርጉት በ English መፃፍ ስትፈልጉ ደግሞ power ge'ez status English Mode (ኢ) ላይ አድርጉት ከዛም የሚከተሉትን ኣጭር መግላጫ በትክክል ይመልከቱ

◕ሀ➭H_ሁ➭Hu_ሂ➭Hi_ሃ➭Ha_ሄ➭Hy_ህ➭He_ሆ➭Ho

◕ለ➭L_ሉ➭Lu_ሊ➭Li_ላ➭La_ሌ➭Ly_ል➭Le_ሎ➭Lo

❖ሐ➭Shift+h_ሑ➭Shift+hu_ሒ➭Shift+hi_ሓ➭Shift+ha_ሔ➭Shift+hy_ሕ➭Shift+he_ሖ➭Shift+ho

መ➭M_ሙ➭Mu_ሚ➭Mi_ማ➭Ma_ሜ➭My_ም➭Me_ሞ➭Mo

❖ሠ➭Shift+s_ሡ➭Shift+su_ሢ➭Shift+si_ሣ➭Shift+sa_ሤ➭Shift+sy_ሥ➭Shift+se_ሦ➭Shift+so

◕ረ➭R_ሩ➭Ru_ሪ➭Ri_ራ➭Ra_ሬ➭Ry_ር➭Re_ሮ➭Ro

◕ሰ➭S_ሱ➭Su_ሲ➭Si_ሳ➭Sa_ሴ➭Sy_ስ➭Se_ሶ➭So

❖ሸ➭Shift+s_ሹ➭Shift+su_ሺ➭Shift+si_ሻ➭Shift+sa_ሼ➭Shift+sy_ሽ➭Shift+se ሾ➭Shift+so

◕ቀ፡➭Q ቁ፡➭Qu ቂ፡➭Qi ቃ፡➭Qa ቄ፡➭Qy ቅ፡➭Qe ቆ፡➭Qo

◕በ፡➭B ቡ፡➭Bu ቢ፡➭Bi ባ፡➭Ba ቤ፡➭By ብ፡➭Be ቦ፡➭Bo

◕ተ፡➭T ቱ፡➭Tu ቲ፡➭Ti ታ፡➭Ta ቴ፡➭Ty ት፡➭Te ቶ፡➭To

◕ ቸ፡➭C ቹ፡➭Cu ቺ፡➭Ci ቻ፡➭Ca ቼ፡➭Cy ች፡➭Ce ቾ፡➭Co

◕ነ፡➭N ኑ፡➭Nu ኒ፡➭Ni ና፡➭Na ኔ፡➭Ny ን፡➭Ne ኖ፡➭No

❏ኘ፡➭Shift +n ኙ፡➭Shift +nu ኚ➭Shift+ni ኛ፡➭Shift +na ኜ፡➭Shift +ny ኝ፡➭Shift + ne ኞ፡➭Shift +no

◕ከ፡➭Ka ኩ፡➭Ku ኪ፡➭Ki ካ፡➭Ka ኬ፡➭Ky ክ፡➭Ke ኮ፡➭Ko

❖ ኸ ☛capslock + Shift + h
ኹ ☛capslock + Shift + hu
ኺ ☛capslock + Shift + hi
ኻ ☛Capslock + Shift + ha
ኼ ☛Capslock + Shift + hy
ኽ ☛Capslock + Shift + he
ኾ ☛Capslock + Shift + ho

❏ኀ፡➭ Capslock + H ኁ፡➭ Capslock + HU ኂ፡➭Capslock + HI ኃ፡➭Capslock + HA ኄ፡➭Capslock + HY ኅ፡➭Capslock + HE ኆ፡➭Capslock + HO

❏አ፡➭Capslock X ኡ፡➭Xu ኢ፡➭Xi ኣ፡➭Xa ኤ፡➭Xy እ፡➭Xe ኦ፡➭XoDe

❖ዐ፡➭Shift +x ዑ፡➭Shift +xu ዒ➭Shift +xi ዓ፡➭Shift +xa ዔ➭Shift +xy ዕ፡➭Shift +xe ዖ➭Shift +xo

✪ወ፡➭W ዉ፡➭Wu ዊ፡➭Wi ዋ፡➭Wa ዌ፡➭Wy ው፡➭We ዎ፡➭wo

✪ዘ፡➭Z ዙ፡➭Zu ዚ፡➭Zi ዛ፡➭Za ዜ፡➭Zy ዝ፡➭Ze ዞ፡➭Zo

❏ዠ፡➭Shift + Z ዡ፡➭Shift + Zu ዢ፡➭Shift + Zi ዣ፡➭Shift +Zaዤ፡➭Shift + Zy ዥ፡➭Shift +Ze ዦ፡➭Shift + Zo

✪ፈ፡➭F ፉ➭Fu ፊ፡➭Fi ፋ፡➭Fa ፌ፡➭Fy ፍ፡➭Fe ፎ፡➭Fo

✪ ፐ፡➭P ፑ፡➭Pu ፒ፡➭Pi ፓ፡➭Pa ፔ፡➭Py ፕ፡➭Pe ፖ፡➭Po

✪ገ፡➭G ጉ፡➭Gu ጊ፡➭Gi ጋ፡➭Ga ጌ፡➭Gy ግ፡➭Ge ጎ፡➭Go

✪ደ፡➭D ዱ፡➭Du ዲ፡➭Di ዳ፡➭Da ዴ፡➭Dy ድ፡➭ዶ፡Do

❏ጠ፡➭Shift + t ጡ፡➭Shift + tu ጢ፡➭Shift + ti ጣ፡➭Shift+ta ጤ፡➭Shift + ty ጥ፡➭Shift + te ጦ፡➭Shift + to

❏ጨ፡➭Shift +c ጩ፡➭Shift +cu ጪ፡➭Shift +ci ጫ፡➭Shift+caጬ፡➭Shift +cy ጭ፡➭Shift +ce ጮ: ➭Shift +co

❏ጸ፡➭Capslock + t ጹ፡➭Capslock + tu ጺ፡➭Capslock + ti ጻ፡➭Capslock + ta ጼ፡➭Capslock + ty ጽ፡➭Capslock + t ጾ፡➭Capslock + to

❖ ፀ➭☞Capslock+Shift+t
ፁ➭☞Capslock+Shift+tu
ፂ➭☞Capslock + Shift + ti
ፃ➭☞Capslock + Shift + t
ፄ➭☞Capslock + Shift + ty
ፅ➭☞Capslock + Shift + te
ፆ➭☞Capslock + Shift + to

✪ጀ፡➭J ጁ፡➭Gu ጂ፡➭Ji ጃ፡➭Ga ጄ፡➭Gy ጅ፡➭Ge ጆ፡➭Jo

✪ቨ፡➭V ቩ፡➭Vu ቪ፡➭Vi ቫ፡➭Va ቬ፡➭Vy ቭ፡➭Ve ቮ፡➭Vo
▁▁▁▁▁▁▁▁▁▁

ቋ➭Capslock+qwa ቧ➭Capslock+bwa
ቷ➭Capslock+twa
ኟ➭Capslock +Shift+nwa
ቿ➭Capslock+cwa ሟ➭Capslock+mwa
ቷ➭Capslock+twa ጓ➭Capslock gwa
ፏ➭Capslock+fwa ሯ➭Capslock +rwa ዷ➭Capslock+dwa ቯ➭Capslock+vwa ኋ➭Capslock+hwa ዟ➭Capslock+zwa ዧ➭Capslock+Shif+zwa
ኗ➭Capslock+nwa ሏ➭Capslock+lwa
ኳ➭Capslock+kwa ሷ➭Capslock+swa
ጇ➭Capslock+jwa ጧ➭Capslock+twa

ለሌሎች እንዲደርሳቸው #FORWARD ያድርጉ
👏2👍1