Muhammed Computer Technology (MCT)
38.1K subscribers
527 photos
7 videos
254 files
910 links
🔴አድራሻ:-
✅ ስ.ቁ: 0929273364
✅ ዌብሳይት www.mctplc.com
✅ቴሌግራም አካውንት: https://t.me/mctplc
✅ email: mct16plc@gmail.com
✅ ቲክቶክ አካውንት tiktok.com/@mctplc
Download Telegram
ከኮምፒውተር፣ ከፍላሽ፣ ከExternal Hard Disk በፎልደር ውስጥ ያለን ፋይል እንዴት መደበቅ እንችላለን ከዛስ የደበቅነውን ፎልደርና ፋይል እንዴት እናወጣዋለን?
ምሳሌ: "Documents" የሚል ፎልደር Local Disk C. ቢኖር
✅ Step 1: ከአንድ ላይ Windows key ና R key ይጫኑ ከዛም Run dialog box ይመጣ cmd ብለው ይጻፉና OK ይጫኑ Command Prompt ይመጣላችኋል.
✅ Step 2: ይህንን ይጻፉ attrib +s +h c:\documents ላይ ከዛም Enter ይጫኑ .
አሁን documents የሚለው ፎልደር ከነበረበት ቦታ ይጠፋል ማለት ነው። ይህ ማለት ሙሉበሙሉ ጠፍቷል ማለት አይደለም ተደበቀ እንጅ።
_/_//_/___________
-----ሌላ አማራጭ------
ለምሳሌ ከፍላሽ ዲስክ ወይም ከሀርድዲስክ ያለን መረጃ ለመደበቅ ለምሳሌ ፍላሹ Removable dusk(F) ቢሆን ከኮማንድ ፕሮምፕቱ ላይ F: ብለን ኢተርን እንጫናለን ይህ ማለት ወደ ፍላሽ ዲስክ ገባን ማለት ነው ከፍላሹ ውስጥ documents የሚል ፎደር ቢኖርና መደበቅ ብንፈልግ
✅ attrib +s +h documents ብለን እንጽፋለን ከዛም ኢንተርን እንጫናለን አሁ documents የሚለው ፎልደር ይደበቃል ማለት ነው።
ከፍላሽ ዲስካችን የደበቅነውን documents የሚለውን እንደገና ለማውጣት ብንፈልግ
✅ attrib –s –h documents ጽፈን ኢንተርን እንጫናለን ከዛም ይመለሳል ማለት ነው ከዚህ ላይ የናንተ folder ስም የተለየ ከሆነ documents የሚለውን ብቻ ነው የምትቀይሩት ማለት ነው። ለምሳሌ my secret file የሚል ፎልደር ካላችሁ በ " ማስገባት አለባችሁ ይህም ማለት
✅ ለመደበቅ attrib +s +h "my secret file"
✅ ከተደበቀበት ለማውጣት attrib –s –h "my secret file" የፎልደሩ ስም ከአንድ በላይ word ከሆነ የግድ በ" " ማስገባት አለባችሁ።
_/_//_/___________
አንዳንድ ጊዜ በፍላሽ ዲስክ የያዝነው መረጃ ይደበቅብናል። ከተደበቀበት ሁሉንም ፎልደሮችና ፋይሎችን ለማውጣት ስንፈልግ ከይ በጠቀስኩት አግባብ ለምሳሌ ፍላሽ ዲስካችን Removable Disk(F) ቢሆን ከኮማንድ ፕሮምፕቱ ላይ F: ብለን እንጫንና attrib -s -h /s /d ብለን እንጽግና ኢንተርን እንጫናለን ከዛም ሁሉም የተደበቀው ፋይል ሁሉ ይወጣልናል ማለት ነው። ሞክሩትና እዩት!
ሲሰተም ሪስቶር (System Restore)
ሲስተም ሪስቶር የምንጠቀምበት በኮምፒውተራችን ላይ
ችግሮች(ብልሽት) ሲያጋጥም በጥሩ ሁኔታ በሚሰራበት
ጊዜ በኮምፒውተሩ አውቶማቲካሊ ወይም ማኑዋሊ
በተዘጋጀው ሪስቶር ፖይንት በመጠቀም የነበሩ ወርድ
ዶከመንቶች፣ ፎቶግራፎች፣ ሙዚቃዎች፣ ኢሜል
መልክቶች እንዲሁም የምርጫችን የሆኑ ኢንተርኔት
ዌብሳይቶች፣ ማይ ዶክመንት ውስጥ ያሉ የተለያዩ
ፋይሎችን ሳይጠፉ በነበረበት ፣የምናሰተካክልበት የዊንዶ
ኤክሰፒ፣ 7፣ 8 ቱል ሲሆን ሪሰቶር ስናደርግ
በኮምፒውተራችን ላይ ያሉ ፋይሎች በጭራሽ አያጠፋም
እንዲሁም አይቀይርብንም ነገር ግን ሪስቶር ካደረግንበት
ቀንና ሰዓት ቦሃላ የተጫኑ ሶፍትዌሮች፣ አፕሊኬሽን
ፕሮግራሞች ይጠፋሉ እንደገና መጫን ይኖርብናል ፡፡
ዳታዎች ከኮምፒውተር ላይ መጥፋት ወይም መበላሸት
ምክንያት የሚሆኑት
1. አዲስ ድራይቨር ከተጫነ
2. ዊንዶ ኦፕሬቲንግ ሲስተማችን አብዴት ስናደርግ
3. የተለያዩ አፕልኬሽን ሶፍትዌሮች መጫን
ሲስተም ሪስቶር በቫይረስ የተጠቁና የተበላሹ ፋይሎችን
እና በአድ/ሪሙቭ ፕሮግራም ያስወገድናቸውን
ሶፍትዌሮች ወደነበረበት መመለስ አንችልም አንዲሁም
በቫይረስ የተጠቁ ፋይሎችን አይፀዳም፡፡
Share your knowledge free for millions ያለዎትን
እና ያገኙትን እውቀት በነፃ ለሚሊዎኖች ያካፍሉ/ያድርሱ
❤2
ኮምፒውተር ላይ ልታውቋቸው ግድ ነው ያልናቸውን አቋራጭ የኪቦርድ መንገዶችን (Shortcuts) እናሳውቃችሁ
Ctrl+C እና Ctrl+X
****************************

Ctrl+C የመርጥነውን ጽሁፍ ወይንም ፎልደር ይሁን ፋይል ኮፒ ለማድረግ ይረዳናል። አይ ድግግሞሽ አልፈልግም ቆርጬ (Cut) ነው መውሰድ የምፈልገው ካልን ደሞ Ctrl+Xን መንካት ነው። ከት ካደረግንበት ቦታ ፋይሉን ወይም ጽሁፉን ያጠፋዋል።
ለአፕል ኮምፑተር ተጠቃሚዎች Ctrlን በcommand(cmd) በመተካት መጠቀም ይችላሉ።

Ctrl+V

ይህ አቋራጭ የሚጠቅመን ከላይ ኮፒ ወይም ከት ያደርግነውን በምፈልገው ቦታ ላይ ለማቀመጥ ነው። የንምፈልገው ቦታ ላይ ሄደን Ctrl+V ስንነካ ፋይሉን ያስቀምጥልናል።
ለአፕል ተጥቃሚዎች Cmd+Vን መጠቀም ይችላሉ

Ctrl+F

Ctrl+F በመካት የመፈለጊያ ሳጥን (Search) መክፈት እንችላለን። የህም የፈለግነዉን ጽሁፍ(text) እና ፋይል ለማግኘት ይረዳናል።
ለአፕል ተጠቃዎች Cmd+F በመንካት መጠቀም ይችላሉ።

Alt+Tab

Alt+Tab መጫን በተከፈቱ ፕሮግራሞች መሃል እንደፈለግን እንድቀያይር ያደርገናል። ለምሳሌ በብራውዘር ኢንተርኔት እየተጠቀምን ከነበር እና ወደ መፈትነው ወርድ ፋይል መሄድ ብንፈልግ Alt+Tab በመንካት መለወጥ እንችላለን።
ለአፕል ተጠቃሚዎች cmd+Tab ተጥቀሙ።

Ctrl+Backspace እና Ctrl+Left ወይም Right arrow

Backspace የጽሁፍ ፋይል ላይ አንድ ፊደልን ወይም ምልክትን ለማጥፋት ይጠቅምናል። ነገር ግን Ctrl+Backspace ሁሉንም ነገር አንድ ሳያስቀር ያጠፋልናል።
Ctrlን ተጭነን የግራ(left) እና ቀኝ(Right) ቀስቶችን ስንነካ እንደ ከርሰር ተጥቅመን የምንፈሊገዉን ተከታታይ ፋይል ወይም ጽሁፍ በጅምላ እንድንመርጥ ይረዳናል።

Ctrl+S

ዶክመንቶች ላይ እየሰራን የሰራበውን ቶሎ ሴቭ ማድረግ ቢያስፈልህልገን የምንጠቀመው Ctrl+S ነው። በተለይ እንደኛ አገር ላሉ የመብራት ችግር ላለባቨው አገሮች ዶችመታቭን ሴቭ ሳናደርግ እንዳይጠፋ ፍቱን መፍትሄ ነው።
ለአፕል ተጠቃሚዎች cmd+S ተጠቀሙ።

Ctrl+Home እና Ctrl+End

Ctrl+Home ከርሳችንን ወደ ዶክመንታችም መጅውመሪያ ይመልሰዋል። በተቃራኒው Ctrl+End ደሞ ከርሰራችንን ወደ. ዶክመንታችን መጨረሻ ይወስዋል።

Ctrl+P

ፒሪንት ማድረግ የምንፈልገው ፋይል ወንም ዶቹመንት ካለ Ctrl+P ስንነካ የፕሪንትን መስኮት በመክፈት የፕሪንት አማራጮችን ያሳየናል።
ለአፕል ተጠቃሚዎች cmd+Pን ተጠቀሙ።

PageUp ፣ Spacebar እና Pagedown

ከስሙ መገመት እንደሚቻለው PageUp እና Pagedown ዶክመንታችን ላይ ወደ ቀጣይ ገጽ ወንም ወደ ቀድሞ ገጽ ለመሄድ ይጠቅመናል። የኢንተርኔት ብራውዘር በመጠቀምበት ሰአት ደሞ Spacebar ወይም Shift+Spacebar አንድ ገጽ ለመዝለል ያስችለናል።
✅ ትርጓሜ - ሲ ድራይቭ (ሲ :) ምን ማለት ነው? ሲ ድራይቭ (ሲ :) ኦፐሬቲንግ ሲስተም እና ተዛማጅ የስርዓት ፋይሎችን የያዘ ዋናው የሃርድ ዲስክ ክፋይ ነው ፡፡ በዊንዶውስ ኦፐሬቲንግ ሲስተሞች ውስጥ ሲ ድራይቭ እንደ “C: \” ሆኖ የተወከለው ፣ የድራይቭን root directory የሚወክል የኋላ ኋላ ፡፡
✅ ሲ ድራይቭ እንደ የስርዓቱ ዋና ሃርድ ድራይቭ ተደርጎ የሚወሰድ ሲሆን የስርዓተ ክወናውን ፣ የስርዓት ፋይሎችን እና ሌሎች መተግበሪያዎችን እና ተዛማጅ ፋይሎቻቸውን ለማከማቸት ያገለግላል ፡፡ በኋላ ባለው የዊንዶውስ ስሪት ፣ ሲ-ድራይቭ እንደ ፕራይሜሪ ድራይቭ ወይም Local Disk የሚል ስያሜ የተሰጠው ሲሆን “My Computer” የሚለውን አቃፊ በመክፈት በነባሪነት ማግኘት ይቻላል፡፡
✅ ቴኮፒዲያ ሲ ድራይቭን ያብራራል (ሲ :) ለዲስክ ድራይቮች በ Letter የመሰየሚያ ዘዴው ከ DOS የመጀመሪያ ቀናት ጀምሮ ነበር ፡፡ A እና B የሚሉት ፊደሎች ለፍሎፒ ዲስክ ድራይቮች የተቀመጡ ሲሆኑ ሲ ሲ ደግሞ ኦፐሬቲንግ ሲስተም እና ተዛማጅ የስርዓት ፋይሎች ላለው ለዋናው የሃርድ ዲስክ ክፋይ ተመድቧል ፡፡
✅ የቆዩ የ DOS ስሪቶች ሃርድ ድራይቮችን ከግምት ውስጥ ከመግባትዎ በፊት ለእያንዳንዱ ፍሎፒ ድራይቭ letter ይመድባሉ ፡፡ በዚህ መንገድ ኮምፒዩተሩ ከሁለት በላይ የፍሎፒ ድራይቮች ቢኖሩት ኖሮ ሃርድ ዲስክ ድራይቭ D :, E: ወዘተ ተብሎ ይጠራ ነበር ፡፡ ሆኖም ፣ ከ ‹DOS 5.0› ጀምሮ ድራይቭ ሲ: የፍሎፒ ድራይቮች ብዛት ምንም ይሁን ምን ለመጀመሪያው ሀርድ ዲስክ ተመድቦለታል (የቡት ድራይቭ ወይ A: ወይም C :) ነበር ፡፡
✅ Letter A እና B ለ ፍልፒ ዲስክ ድራይቮች የተያዙ ስለነበሩ አብዛኛው ኮምፒተር ሁለት የተለያዩ የፍሎፒ ድራይቮች ስላለው አንዱ ለ 3 1⁄2 ″ ፍሎፒዎች (A :) እና ሌላኛው ደግሞ ለ 5 1⁄4 ″ ፍሎፒዎች (ቢ :) ፡፡
✅ ሌሎች ፊደላት (ዲ ፣ ኢ ፣ ኤፍ ፣ ወዘተ) ለሌሎች ሃርድ ድራይቮች ፣ ፍላሽ ድራይቮች ወይም ለኦፕቲካል ድራይቮች (ሲዲ ድራይቮች ፣ ዲቪዲ ድራይቮች ፣ ዲስክ አባካሪዎች ፣ የብሉ ሬይ ድራይቮች ፣ ወዘተ) ሊመደቡ ይችላሉ ፡፡ በሌላ አገላለጽ ፊደሎች logical ድራይቭዎችን ለመወሰን ያገለግሉ ነበር ፣ ምንም እንኳን ብዙ ቆየት ብለው physical storage መሣሪያዎችን ለመለየትም ያገለግሉ ነበር ፡፡
✅ ዛሬም ቢሆን ኮምፒተርው ለፍሎፒ ዲስክ ድራይቭ ከአሁን በኋላ በአብዛኞቹ ኮምፒውተሮች ውስጥ ባይገኙም ለ ‹A› እና B ›ድራይቮች መያዙን ይቀጥላል ፡፡
✅ የሃርድ ድራይቭዎ ዓላማ (C: drive) የኮምፒተርዎ ሃርድ ድራይቭ በመባል የሚታወቀው ሲ-ድራይቭ የኮምፒተርዎን ኦፐሬቲንግ ሲስተም (ዊንዶውስ ፣ ማክ ኦኤስ ፣ ሊነክስ ፣ ወዘተ) እንዲሁም የሚጠቀሙባቸውን አፕሊኬሽኖች (ለምሳሌ ማይክሮሶፍት ኦፊስ ፣ አዶቤ ፣ ሞዚላ ፋየርፎክስ) የማከማቸት አስፈላጊ ሥራ አለው ፡፡ ) እና ከበይነመረቡ (Internet) የሚያወርዷቸው ፋይሎች።
✅ በ C: ድራይቭ ላይ ምን አለ? የ “ሲ” ድራይቭ በአሁኑ ጊዜ ለሚሰሩባቸው ፋይሎች እንደ ጊዜያዊ ማከማቻ ቦታ በጥሩ ሁኔታ ጥቅም ላይ ይውላል ፡፡ በ C ላይ መተማመን ለረጅም ጊዜ ማከማቻ ድራይቭ አደገኛ ነው።
❤1
ኮምፒዩተር
ኮምፕዩተር ማለት ማንኛውንም ኢንፎርሜሽን ፕሮሰስ የሚያደርግ ማሽን ነው። ይህንም የሚያደርገው በተርታ የተቀመጡ ትዕዛዞች በመፈጸም ነው። ለብዙ ሰዎች ኮምፒዩተር ሲባል ዐዕምሯቸው ላይ የሚመጣው የግል (ፐርሰናል) ኮምፒዩተር ነው። ነገር ግን ኮምፒዩተር ሲባል በጣም ብዙ ነገሮችን ያጠቃልላል። ላፕቶፕ ፣ ዴስክቶፕ ፣ ማይክሮ-ኮምፒዩተር ፣ ሱፐር-ኮምፒዩተር ፣ ካልኩሌተር ፣ዲጂታል ካሜራ እና ሌሎችንም ያጠቃልላል።
ኮምፒዩተር
ታሪክ
ቀድሞ አስሊ ማለት አንድ በሒሳባዊ ትዕዛዝ የተለያዩ የጥንት መሣሪያዎችን እየተጠቀመ ቁጥሮችን የሚያሰላ ሰው ነበር። እስከ 20ኛው ክፍለ-ዘመን ድረስ የተለያዩ ጠቃሚ መሣሪያዎች ተሰርተዋል። ከዛ በኋላ ትልልቅ ማሸኖች መሠራት ጀመሩ። እነዚህ ማሽኖች ከዛሬው ኮምፒዩተሮች(አስሊዎች) ጋር ሲወዳደሩ በጣም ትልቅና ቀርፋፋ ናቸው።
የኮምፒዩተር ዐይነቶች
ሜን ፍሪም
ሱፐር ኮምፒዩተር
ዎርክ ስቴሽን
ማይክሮ ኮምፒዩተር-(ዴስክቶፕ፣ ላፕቶፕ፣ ፓልምቶፕ)
ሚኒ ኮምፒዩተር
ዋና የኮምፒየተር ዐይነቶች እንደሚከተለው ነው፦
የኮምፕዩተር ክፍሎች
የኮምፕዩተር የውስጥ ክፍሎች የሚከተሉት ናቸው፡-
1. ሞኒተር (የምንሰራውን ነገር እንዲያሳየን፤ምስል፣ጽሑፍ፣ ቪዲዮ ወይም ማንኛውም ነገር ሊሆን ይችላል)
ሞኒተር 14 ኢንች፣ 15 ኢንች፣ ወዘተ. እየተባለ ይገላጻል፡፡
14 ኢንች 15 ኢንች እያልን ስንናገር አለካኩ ከምስል ማሳያው አንድ ጥግ እስከ ሌላኛው ጥግ ያለውን ርቀት በመለካት ነው፡፡(ስዕሉን ይመልከቱ፡፡)
በፊት የነበሩት የላፕቶፕና ዴስክቶፕ ኮምፒዩተሮች ሬሾ (ርዝመት ሲካፈል ለወርድ) 4በ3(በትክክል ሲጻፍ 4:3 ይሆናል) ነበር፡፡
አሁን ደግሞ የቲያትር ሞድ የሚባለው ባለ 16፡9 ሬሾ ወይም ዋይድ ስክሪን (widescreen) በመጠቀም ላይ ናቸው፡፡
2.ማዘርቦርድ(እናት ሰሌዳ)(ሁሉም የኮምፕዩተር ክፍሎች(ዕቃዎች)የሚቀዳጁበት)
3.ሲፒዩ(የኮምፕዩተሩ አእማሮ እንደማለት ነው፡፡ይህ ሲባል ግን ሲፒዩን ከሰው አእምሮ ጋር አንድ ነው ማለት አይደለም፡፡)
4.ሜሞሪ(ማስታወሻ)(የምንሰራውን ስራ ወይም ፋይል በጊዚያዊነት አስቀምጠንበት የምንሰራበት)
ሜሞሪ(ማስታወሻ) በባይት (Bytes) ይለካል፡፡ ከ Bytes ፊት Kilo፣ ማለትም ኪሎባይት (kilobytes)([1,024 ባይቶች ወይም Bytes ማለት ነው፡፡ ] ፣ Mega[1,048,576 ባይቶች ወይም Bytes ] ፣ Giga [1,073,741,824 ባይቶች ወይም Bytes]፣ ወዘተ የሚሉትን ቃላት በመጠቀም ኪሎባይት(kilobyte)፣ ሜጋባይት (megabyte)፣ ጊጋባይት (gigabyte) እያልን የኮምፒዩተር ሜሞሪ መግለፅ እንገልጻለን፡፡
ለምሳሌ 10 MegaBytes ወይም ባጭሩ ሲጸፍ 10MB ይህ ማለት 10,485,760 Bytes ይሆናል ማለት ነው፡፡
5.ኤክስፓንሽ ስሎት
6.የኤሌክትሪክ ሀይል ማቅረቢያ (power supply)
7.የሲዲ ማሰሪያ (cd drive)
8.ሀርድ ዲስክ (የምንሰራውን ወይም የምንጠቀምበትን ፋይል በቋሚነት ለማስቀመጥ)
9. መሎጊያ (ማውስ )
10.የፊደል ገበታ (ኪቦርድ)
ዊኪፒዲያ ላይ ያለውን ምስል ከቁጥሩ ጋር ማነጻጸር ይቻላል፡፡
ኮምፕዩተሮች እንዴት እንደሚሰሩ
ታዋቂ ዋና ዋና የኮምፕዩተር አምራቾች
ታዋቂ የኮምፕዩተር አምራቾች የሚከተሉት ናቸው፡፡ ይህ ማለት ግን እያንዳዱን የኮምፕዩተር ክፍል(ዕቃዎች)ይሠራሉ ማለት አይደለም፡፡
1.አይቢኤም[IBM](አሁን እንኳ የፒሲ ክፍሉን እ.ኤ.አ. በ2004 ለቻይናው ሊኖቮ ሸጦታል)፡፡ አሁን ሜን ፍሬም[Main Frame] ኮምፒዩተር ነው በብዛት የሚያመርቱት/የሚሠሩት፡፡
ድረ ገጽ---[ http://www.ibm.com የአይቢኤም ድረ ገጽ ]
2.ዴል[Dell]
ድረ ገጽ---[ http://www.dell.com የዴል ድረ ገጽ]
በኢትዮጵያ የዴል ወኪል አልታ ኮምፒዩተር ነው፡ ፡አድራሻቸው ቦሌ መንገድ ሸዋ ሱፐርማርኬት ፊትለፊት ኔጃት ኮምፒዩተር ያለበት ፎቅ ላይ ነው፡፡
3.ኤሰር[Acer]
ድረ ገጽ---[ http://www.acer.com የኤሰር ድረ ገጽ]
በኢትዮጵያ የኤሰር ወኪል ኔጃት ኮምፒዩተር ነው፡፡ አድራሻቸው ቦሌ መንገድ ሸዋ ሱፐርማርኬት ፊትለፊት አልታ ኮምፒዩተር ያለበት ፎቅ ላይ ነው፡፡
4.ቶሺባ [Toshiba]
ድረ ገጽ---[ http://www.toshiba.com የቶሺባ ድረ ገጽ]
5. አፕል [Apple]
ድረ ገጽ---[ http://www.apple.com የአፕል ድረ ገጽ]
6.ኤችፒ[HP]
ድረ ገጽ---[ http://www.hp.com የኤችፒ[ድረ ገጽ]
ኮምፕዩተሮችና የዓለም ፊደላት
የመጀመሪያቹ ኮምፕዩተሮች የሚሠሩት በእንግሊዝኛ ፊደል ብቻ ነበር። ቀስ በቀስ ግን የተለያዩ ኣገሮች ሊቃውንት በየራሳቸው ፊደላት እንዲሠሩ ኣደረጉ። ኮምፕዩተር በእያንዳንዱ የግዕዝ ፊደል፣ ኣኃዝና ምልክት እንዲሠራ ለመጀመሪያ ጊዜ የፈጠረው ኢትዮጵያዊው ዶክተር ኣበራ ሞላ ነው። በቅርቡም አያንዳንዱ የግዕዝ ፊደል፣ ኣኃዝና ምልክት ዩኒኮድ የሚባል የዓለም ፊደላት መደብ ውስጥ መግባት ቀጥሏል።
💢ስልካችሁ📲 ላይ #አፕልኬሽን ስትከፍቱ :⬇️⬇️⬇️

✅This Application Stopped Working‼️
✅Crashing‼️
✅Won’t open‼️
✅Won’t respond‼️
✅Isn’t working properly‼️

🔆እያለ ላስቸገራችሁ መፍትሔ⬇️

1⃣.#Restart እና #Update ይሞክሩ፤ እንደዚህ ስታደርጉ በአብዛኛው ጊዜ ይስተካከላል።👍

⚠️ስልካችሁን📲 #Restart አድርጉት።

⚠️Setting➡️ Software Update ውስጥ ገብታችሁ የስልካችሁን📲 Operating System #Update አድርጉ።

⚠️_Playstore ላይ ገብታችሁ አፑን #Update አድርጉት።

2⃣.*Update Google Play Services *

⚠️ስትከፍቱ #Update አድርጉት ይላችኋል።

3⃣. አፑን የማትጠቀሙበት ከሆነ *Setting* ውስጥ ገብታችሁ #Forced\Stop አድርጉት።

⚠️System App ካልሆነ #Uninstall❌ ያድርጉት።

4⃣. Clear App and Cache ይሞክሩ።

⚠️Setting➡️ Manage apps➡️ ያስቸገራችሁን አፕ➡️ Clear Data and Clear Cache.

5⃣. እኔ እንዳየሁት ከሆነ ከላይ በነገርኳችሁ መፍትሔ 95% ስልኮች📲 ይስተካከላሉ👍 ለተቀሩት ስልኮች #Hard_Reset መሞከር ይቻላል።

⚠️ኮፒ ስልኮችንና ብዙ ጊዜ Hard Reset የተደረጉ ስልኮችን አይጨምርም‼️ እነሱ ስልኮች📲 ሌላ ታሪክ ውስጥ ናቸው።😁
✅የሶፍትዌር ችግር ማለት ምን ማለት ነው?
ከሚከተሉት አንደኛው ወይም ሁሉም ችግሮች በአይፎን ወይም የአንድሮይድ ስልክዎ ላይ ተከስተው ያውቃሉ?
⏺ስልክዎ በራሱ ጊዜ እየበራ ይጠፋል፣ ወይም Involuntary Restart ያደርጋል
⏺ ስልኩ ሙሉ በሙሉ አይነሳም Dead Phone ይሆናል
⏺ ከጫኗቸው አፕሊኬሽኖች የተወሰኑቱ ተለይተው ያለመስራት ወይም የመዘግየትና ስታክ የማድረግ ችግር ያሳያሉ
⏺ በአጠቃላይ ስልክዎ እጅግ በጣም ቀርፋፋ ይሆናል ( ⚠️ በእርግጥ አንዳንድ ጊዜ ይህ አይነቱ ችግር በስልካችን ላይ በጣም ብዙ አፕሊኬሽኖችና ዳታዎችን በመያዝ ምክንያት ከሚሞሪ መጣበብም የተነሳ ሊከሰት ይችላል) ወይም
⏺ የአንድሮይድ ወይም የአፕል ሎጎ ላይ Stack ያደርጋል
⏺ ለስልክዎ ያስገቡት የፓተርን ፓስወርድ ጠፍቶዎታል፣ ወይም User Locked ሆኗል ⏺ የኔትወርክ መዘጋት(Carrier Network Locked )፣
⏺ ከሚከተሉት አንደኛውን መልእክት ይሰጥዎታል
📍 SIM not Valid,
📍 Wrong SIM,
📍 Contact SP (Service Provider), 📍 Unknown SIM,
📍Phone Restricted ወዘተ…
እና ሌሎችም እነዚህን የመሳሰሉ ችግሮች በሚከሰቱበት ጊዜ ስልኩ የሶፍትዌር ችግር አለው ማለት ነው፡፡
⏺ በዚህ ጊዜ ከዚህ በታች የሚከተሉት መፍትሄዎች ችግሩን ሙሉ በሙሉ በመቅረፍ እፎይታ ይሰጡዎታል ማለት ነው
⚠️ ማሳሰቢያ፡- ማንኛውንም የሶፍትዌርም ሆነ የሀርድዌር ጥገና ከመከወናችን በፊት data backup ማድረግ ወይም ያሉንን ዳታዎችና መረጃዎች ወደሌላ ሚዲየም (ወደሌላ ፍላሽ ሚሞሪ ወይም ወደ ኮምፒውተር ወይም ወደጎግል ወይም አይክላውድ አካውንት) ማዛወር ይኖርብናል፡፡
⏺ ይህን ማድረግ በጥገናው ሂደት ለሚደርስ የዳታ መጥፋት ሁነኛ መፍትሄ ይሆናል፡፡
📍 ለአንድሮይድ ስልኮች
❗️Hard Reset or Factory Reset ማድረግ Format ማድረግ በዚህም ችግሩ ካልተፈታ
❗️ በ Stock Firmware Flash ማድረግ ❗️ Unlocking,
❗️ Android Rooting ማድረግ (User, Network Provider or Carrier etc… ) እና ሌሎችም
ለአይፎን ስልኮች በቅርብ ጊዜ
❗️ የ iTunes Software Restore ማድረግ ቀደም ብለው በነበሩት የአይፎን ስልኮች ላይ የተለያዩ
❗️ የJailbreaking ሶፍትዌሮች በመጠቀም የኔትወርክ ክልከላውን ሰብሮ ማለፍ እና ሌሎችም በድጋሚ ማንኛውንም የሶፍትዌርም ሆነ የሀርድዌር ጥገና ከመከወናችን በፊት ⚠️ data backup ማድረግ በፍጹም በፍጹም
እንዳይዘነጉ፡፡
👍1
✳️ የዊንዶዉስ-10 ቨርዥን "1809" በሚቀጥለዉ ሳምንት አገልግሎቱ ይቋረጣል

ግዙፉ #የቴክኖሎጂ ኩባንያ ማይክሮሶፍት የዊንዶዉስ-10 የቨርዥን (version-1809) ምርቱ ከሚቀጥለዉ ሳምንት ጀምሮ አገልግሎቱን እንደሚያቋርጥ ገለጸ፡፡
አገልግሎታቸዉ ላበቃ ምርቶች ቴክኒካዊ ድጋፎችን እንደማያቀርብ የገለጸዉ ማይክሮሶፍት ይህን ተከትሎ በሶፍትዌሮቹ ላይ ለሚከሰቱ የሶፍትዌር ክፍተቶች እና ተጋላጭነቶችም ማዘመኛዎችን እንደማያቀርብ እና የደህንነት ጥገናዎችንም እንደማያደርግ አሳውቋል።

የአገልግሎት ጊዜያቸዉ ያበቃ ሶፍትዌሮችን አሁንም ድረስ የሚጠቀሙ ደንበኞች የሲስተሞቻቸዉን ከጉዳት ነፃ እንዲሆኑ እና ከመረጃ ጥቃቶች እንዲጠበቁ በፍጥነት ምርቶቻቸዉን ወደ ቅርብ ጊዜ የዊንዶዉ-10 ቨርዥኖች እንዲያሻሽሉ ማይክሮሶፍት አሳስቧል፡፡
የኢንተርፕራይዝ (Enterprise)፣ የኢዱኬሽን (Education) እና ከኢንተርኔት ጋር የተቆራኙ ቁሶች (IoT Enterprise) ሆነዉ የዊንዶዉስ-10 ቨርዥን 1809 ተጠቃሚዎ አገልግሎቱን እስከ ፈረንጆቹ ግንቦት 11/2021 እንደሚቆይላቸዉ ታዉቋል፡፡
በመሆኑን እርስዎ እየተገለገሉበት ያለዉ ኮምፒዉተር ዊንዶዉስ-10 ቨርዥን 1809 ከሆነ በመጀመሪያ ወደ ዊንዶዉስ-10 ቨርዥን 1903 ካዘመኑ በኋላ ወደ የዊንዶዉስ-10 ቨርዥን 2004 ማሳደግ እና በኮምፒዉተሩ በመተግበር (installed) ይኖርዎታል፡፡
ይህንን የዝመና አማራጭ ማይክሮሶፍት ባያበረታታዉም ተጠቃሚዎች Media Creation Tool ተጠቅመዉ ምርቶቻቸዉን ማዘመን ይችላሉ፡፡
እርስዎ እየተጠቀሙበት ያለዉን የዊንዶዉ ቨርዥን ለማወቅ በመጀመሪያ Start የሚለዉን በመጫን > "Settings" የሚለዉን መምረጥ > ከዚያም "System" ሲስተምን በመጫን > "About" የሚለዉን መምረጥ የኮምፒዉተርዎን ቨርዥን ማወቅ ይችላሉ፡፡ አልያም window + R ተጭነው በሚመጣላቹ ዊንዶውስ ላይ winver ብላቹ enter ስትሉት ያሳያችዋል።
ስሞኑን የለቀቅኳቸው ጥሩና አስተማሪ ቪዲዮዎች አሉ እነሱን እንድታዪቸው ግብዣየ ነው። በተጨማሪም አዳዲስ ቪዲዮችን እየሰራሁ ስለሆነ #Subscribe በማድረግ ምርጥ ምርጥ ትምህርታዊ ቪዲዮዎችን ይከታተሉ!
#ያወቁትን ማሳወቅ ብልህነት ነው!
የ YouTube ቻናል ሊንክ 👇👇👇
https://www.youtube.com/channel/UCZBIP6PqUdmmagdTjbyp_AQ
ሰለ ቴሌግራም ማወቅ ያለባችሁ 10 ወሳኝ ነጋሮች

✔ 1ኛ :- ያለንበትን ቦታ ለጓደኞቻችን መላክ እንችላለን እንዴት መጀመሪያ ቴሌግራም እንከፍታለን ከዛ የምንልከውን ሰዉ እንመርጣለን ከዛ መላክዋን ከፍተን location የምለውን ተጭነን ያለንበትን ቦታ መላክ ይቻላል ::

✔ 2ኛ :- ከኛ ወጪ ማንም ሰው ቴሌግራማችንን ማንም ሰዉ እንደይጠቀም ከፈለግን password ማዘጋጀት ይቻላል እንዴት መጀመሪያ ቴሌግራም እንከፍታለን ከዛ በቴሌግራም ጫፈ ላይ ሦስት መሰመር አለ እሱን አንዴ እንነካለን ከዛ setting የምለውን እንነካለን ከዛ privacy and security የምለውን እንነካለን ከዛ passcode የምለወን እንነካለን ከዛ passcode lock on እናደርጋለን ከዛ የምንፈልገውን password እናስገባለን ::

✔ 3ኛ:- እንዴት ቴሌግራም ብር እንደይበላ ማድረግ ይቻላል
በመጀመሪያ ቴሌግራም እንከፍታለን ከዛ በቴሌግራም ጫፈ ያለውን ሦስቷን መሰመር እንነካለን ከዛ setting ላይ እንገባለን ከዛ data and storage የምለዉን እንነካለን ከዛ
ከዛ when using mobile data -OF-አድርጉት ::

✔4ኛ :- የለክነዉን message ከደረሰ ቦኃላ delete ማድረግ ይቻላል እንዴት መጀመሪያ የለነክነዉን message እንከፍታለን ከዛ ቦታዉ ላይ አጥብቀን እንዛለን ከዛ ከላይ የምለውን Also delete receive የምለውን ራይት እናደርጋለን ከዛ ሁለቱም ጋ delete ይሆናል ::
5ኛ :- እንዴት በአንድ የቴሌግራም አፕሊኬሽን ሁለት account እንጠቀማለን
በመጀመሪያ ቴሌግራም እንከፍታለን ከዛ ከላይ
በቴሌግራሙ ጫፍ ላይ የለወን ሦስት መሰመር እንነካለን ከዛ ይህችን ምልክት ይንኩ ( v ) ከዛ new account ይለናል ከዛ መክፈት

✅6ኛ :- በተላይ ማታ ማታ ስንጠቀም ዓይናችን እንደይጎዳ ቴሌግራማችን በጥቁር መልክ እንድሆን ከፍለግን dark ,, black ,, colour እንድትሆን ከፈለግን ...
በመጀመሪያ ቴሌግራም እንከፍታለን ከዛ የቴሌግራም ጫፈ ላይ የለወን ሦስት መሰመር እንነካለን ከዛ chat setting ላይ ገብተን ከምሰጠን የመልክ ምርጫ የፍለግነዉን እንመርጣለን ::

✔7ኛ :- ቴሌግራም የሉ ፅፎች አልነበብ እየሎት ተቸግረዋል ማለት ፍደሎችሁ አንሰዉ ለዓይን አልተይ ከለ ፍደሎቹሁን ትልቅ ማድረግ ይቻላል እንዴት ?
አዎ በመጀመሪያ ቴሌግራም እንከፍታለን ከዛ በቴሌግራም ጫፍ ላይ ያለውን ሦስት መሰመር እንነካለን ከዛ chat setting ላይ እንገባለን ከዛ message text size የምል አለ እሱን እንነካና የፍለግነዉን ያህል ትልቅ ማድርግየ ይቻላል ::

✔8ኛ:- እንዴት የራሳችንን የቴሌግራም ቻናል መክፈት እንችላለን ?
በመጀመሪያ ቴሌግራም እንከፍታለን
ከዛ በቴሌግራም ጫፈ ላይ ያለውን ሦስት መሰመር እንነካለን ከዛ New channel የምለውን ነክተን create new channel የምለውን እንነካለን ከዛ እኛ ለመክፈት የፍለግነዉን የቻናል ስም እናስገባለን ::

✔9ኛ :- እንዴት የራሳችንን የቴሌግራፍ ጉሩፒ እንከፍታለን ?
በመጀመሪያ ቴሌግራም እንከፍታለን ከዛ ከላይ የለዉን ሦስት መሰመር እንነካለን ከዛ new group የምለውን እንነካለን ከዛ create new groupጠ የምለዉን እንነካለን ከዛ እኛ ለመክፍት የፍለግነዉን የጉሩፒ ስም እናስገባለን ::

✔10ኛ :- እንዴት አድርገን profile photo መቀየር እንችላለን ?
በመጀመሪያ ቴሌግራም እንከፍታለን ከዛ ከላይ ያለዉን ሦስት መሰመር እንነካለን ከዛ setting ላይ እንገባለን ከዛ set profile photo የምለውን በመንካት የፍለግነዉን ፎቶ መቀየር ይቻላል ።
#የመመረቂያ_ጽሁፍ_ሪሰርች_ለሚሰሩ_ለተመራቂ_ተማሪዎች
# ጥሩ_የጥናት_አቀራሪብ_መረጃ
Good research presentation (Defense)
ጥሩ አቀራረብ እንዲያደርጉ የሚረዱዋችሁን አንዳንድ ነጥቦች።
ጥናታዊ ጽሑፍን በጥሩ ሁኔታ ለማቅረብ (good presentation) ከሚረዱ ቁልፍ ነገሮች አንዱ በጥሩ ሁኔታ የተዘጋጀ ኃይል ሰጪ ማብራሪያ ነጥብ (PowerPoint) ነው። እርስዎ # ጥሩ ማብራሪያ ነጥብ (power point) እንዲኖርዎ ደግሞ እነዚህን ይጠቀሙ፦
.
# 1ኛ . ኃይል ሰጪ ማብራሪያ ነጥብ (Powerpoint) ብዙ ስላይድ አይኑረው። በ15 ደቂቃ ለማቅረብ እስከ 15 በዛ ከተባለ ከ20 እስከ 25 ማሳያ (slide) እጅግ በቂ ነው።
«Oral presentation is visual as well as an auditory medium» በቃልዎት የሚያብራሩት ቢሆን የተሻለ ዋጋ ያለው መሆኑን እና የጥናቱ ባለቤት መሆንዎን የሚያረጋህጥ መሆኑን አይርሱ።
.
# 2ኛ . ማሳያ (slide) በብዙ ጽሑፍ የተጠቀጠቀ መሆን የለበትም። ከጽሑፍ ይልቅ ፎቶዎችን፣ ግራፎችንና ሰንጠረዦችን በደምብ ይጠቀሙ። "አንድ ፎቶ ወይም ሰንጠረዥ ከ1000 ቃላት በላይ ገላጭ ነው" የሚለውን አባባል ልብ ይበሉ።
.
# 3ኛ . መብራራት የሚፈልጉ ቃላትን ብቻ በርዕስ መልክ ይጻፉ። ማብራሪያቸውን የግድ ማሳያ (slide) ላይ መፃፍ አይጠበቅብዎትም።
«One of the most common fault or error commited by graduate student is to write every single words and detail full sentences on their slides» ነው የሚለው። Please never crowd each slide !!!
.
# 4ኛ . የሚቀርበው ጥናት እጅግ ሰፊ ይዘት ያለው ቢሆን ለመመጠን ሳይቸገሩ በማሳያ (slide) ላይ ለመዳሰስ ማሳያዎትን (slide) በክፍል በክፍል (part) ይክፈሉት።
....... Introduction (መግቢያ)
....... Main Body (ሃተታ) as Discussion
....... Conclusion ( መደምደሚያ) ያድርጉት።
.
# 5ኛ . ከአንዱ ማሳያ (slide) ወደ ሌላው ሲዘዋወሩ (ሲሸጋገሩ) ጊዜ እንዳይወስድብዎ (እንዳይንቀረፈፍ) Animation ባይጠበሙ ይመረጣል።
.
# 6ኛ . በማሳያዎ (slide) ላይ የሚሰፍሩ ጽሑፎች በትንሹ በ24 መጠን (Font Size) መሆን ይጠበቅባቸዋል።
ከዚያ በታች ከሆኑ ላይታዩ ስለሚችሉ ታዳሚዎትን ያስከፋሉ፣ ሥራዎትን ይደብቃሉ ማለት ነው።
.
# 7ኛ . የጽሑፎቹ ቅርጽ አይነት (Font type) "Time new roman" ቢሆን የተሻለ ነው። ከዚህ ካለፉ ግን Nyala እና Countur ይጠቀሙ።
በተለይ ግን script አይነት ቅርፅ ያለው ጽሑፍ አያድርጉት። የማሳያው ጀርባ ወይም መደብ (Background) ከፊደሎቹ ቀለም (font color) ፍጹም ተቃራኒ ቀለም ያለው መሆን አለበት። ብዙ ጊዜ በነጭ መደብ ላይ ጥቁር ቀለም ያላቸውን ፊደላት (ጽሑፎች) መጠቀም ቢችሉ ይመከራሉ።
.
# 8ኛ . ሙሉ ሃሳብዎን ለመግለፅ ትላልቅ ፊደላትን (Capital letter) ከመጠቀም ይቆጠቡ። ለማንበብና ለመረዳት ቀላሉ ትናንሽ ፊደላትን (Small letters) መጠቀም መሆኑ አይዘንጉ።
.
# 9ኛ . የማሳያ (slide) ጽሑፎች እጅግ ብዙ የቀለም (Font colour) ዝብርቅርቅ የበዛበት ከሆነ አትኩሮትን ግራ ስለሚያጋባ ብዙ ቀለም አይጠቀሙ። ከተቻለ በአንድ አይነት ቀለም ቢሆን ካልሆነ ግን ልዩ ገለጻ የሚፈልጉትን ለማቅለም ሁለት ቀለሞች በቂ ናቸው።
.
# 10ኛ . የ (Spelling of words, gramatical structure of sentences, punctuations… ) ስህተት እንዳይኖርብዎት ቢጠነቀቁ የተሻለ ውጠኣማ ይሆናሉ።
# 11ኛ . አስተያየት (professional recommendation) በሚለው የጥናት ክፍልዎ ውስጥ ከተማሩበት አንጻር ለደረሱባቸው ችግሮች መንገዶችን ለመጠቆም ይሞክሩ ይንጅ "# ድርጅቱ_ይህንን_ችግር_ማስተካከል_አለበት " የሚል ደረቅ ትዕዛዝ ከማስገባት ይቆጠቡ። የሚያስተካክለው እንዴት ባለ ዘዴ፤ መቼ፣ በማን፣ የት፣ ለምን.. እንደሆነ ሙያዊ ድጋፍ መስጠትዎን አይርሱ።
.
# 11ኛ. ያዘጋጁትን ማሳያ (slide) ከማቅረብዎ በፊት ደጋግመው ያንብቡ።
.
አዘጋጁ
~ አለባበሱ ?
~ ከሰላምታ ጀምሮ እስከ ምስጋና ያለው አነጋገሩ ?
~ መጠቀም የሌለበት ቃላት ?
~ የቡድን ሥራ ሲሆንስ ?
~ ጥያቄና መልስ ምን መምሰል አለበት ?
የሚሉትን በቀጣይ ክፍሎች ለመዳሰስ እሞክራለሁ። ለውድ የሀገሬ # የኢትዮጵያ ተመራቂ የኮሌጅና የዩኒቨርሲስቲ ተማሪዎች መልካም የጥናት ማጠቃለያ ጊዜ ይሁንላችሁ።
~~~ {Daniel Shewaatek - ዘጽዮን}
~~~ [Instructor at Ethiopia University]
መልካም ዕድል!!!!!
ምንጭ፦
Introduction to Research Methods - AAU (~~~ {Daniel Shewaatek - ዘጽዮን})
# የተማሩትን_ማስተማር # ያወቁትን_ማሳወቅ # ብልህነት ነው
# ለሰው መልካሙን እንጅ መጥፎውን አትመኝ
# ስለኮምፒውተር ያለዎትን እውቀት ያጎለብታሉ
ይህ የኔ የፌስቡክ ገጽ ነው ስለሆነም ፔጄን ላይ ጠቃሚና ወቅታዊ መረጃዎች ያገኛሉ
ሙሀመድ አሚን በቴሌግራም መከታተል ለምትፈልጉ https://t.me/MuhammedComputerTechnology በዚህ የቴሌግራም ቻናል ብዙ ጠቃሚ መረጃዎችን ታገኛላችሁ
https://m.facebook.com/mameamin.6te.net
ስለዚህ ፔጁን # ላይክ # ሼር በማድረግ ለሌሎች እህት ወንድሞች ጓደኞቻችሁ እንዲደርስ ያድርጉ
# በይበልጥ_ስለኮምፒውተር_ይማራሉ
# ፔጄን_like_share_ያድርጉ_መረጃ_እንዲደርሳችሁ
❤1
ስሞኑን የለቀቅኳቸው ጥሩና አስተማሪ ቪዲዮዎች አሉ እነሱን እንድታዪቸው ግብዣየ ነው። በተጨማሪም አዳዲስ ቪዲዮችን እየሰራሁ ስለሆነ #Subscribe በማድረግ ምርጥ ምርጥ ትምህርታዊ ቪዲዮዎችን ይከታተሉ!
#ያወቁትን ማሳወቅ ብልህነት ነው!
የ YouTube ቻናል ሊንክ 👇👇👇
https://www.youtube.com/channel/UCZBIP6PqUdmmagdTjbyp_AQ
ዲሽ አተካከል ለፍፁም ጀማሪዎችና ለተካኑ ቴክኒሽያን በሙለር IT solution የተዘጋጀ!

✅ በቴሌግራም ቻናል: https://t.me/MuhammedComputerTechnology
https://t.me/MuhammedComputerTechnology
ቴሌግራምዎን hack እንዳይደረግብዎ ይፈልጋሉ❓

✔️መፍትሄውን እነሆ👇👇👇

👉ቴሌግራም ማለት እንደ ማንኛውም የ messaging application ነው ማለትም እንደ⇝whatts app,viber, imo,tango.....etc
👉ቴሌግራም እንደ whatsapp,viber,imo...ሁሉ በቀላሉ በ "sms-based verification process" hack ሊደረግ ይችላል✅

✴️ሌሎችም hack ማድረጊያ አፕሊኬሽኖች አሉ
ማለትም 👉desktop app
👉android app አሉ።
እናም በነዚህ👆 የሀኪንግ አይነቶች አካውንታቹ ሌላ ስልክ ላይ ወይም ሌላ #pc ላይ ሊኖር ይችላል✅

1⃣.በመጀመሪያም ይህ መሆኑን እና አለመሆኑን ለማረጋገጥ አሁን step by step ተከታተሉኝ
💢Telegram⇢seting⇢privecy and security⇢active session 👉 ላይ በመግባት በእናንተ አካውንት የገባ ሰው እንዳለና እንደሌለ ማወቅ ያስችላል።

⚠️Note: እራስዎ በሌላ #አፕ ከገቡም ያመጣልዎታል መርጠው መርጠው ነው።

✴️ ከዛም Terminate all other sessions ክሊክ በሉት፤ ይህ ሚጠቅመው በሌላ ስልክ 📱 የእናንተን #አካውንት የሚጠቀም ሰው ካለ remove ያደርገዋል።

2⃣.Security ደግሞ ለማጠናከር👇

seting⇢privecy and security⇢two step verification⇢set aditional pasword ከዛ የፈለጉትን password *..

⚠️ግን የ #gmail አካውንት ሊኖራቹ ይገባል።

✴️ ይህ👆 ጠንካራ የሚባለው #የቴሌግራም security ነው።

✔️የሚጠቅመው #እንደፌስቡክ ሁላ በሌላ ስልክ📲 ስንገባ password ይጠይቀናል (log in) እያልን ነው የምንገባው ማለት ነው።

✔️ ሌላ ሰው #በsms የተላከውን ኮዳችሁን አግኝቶ እንኳ ቢከፍተው
ወደቴሌግራማችሁ በጭራሽ መግባት አይችልም።

✴️ ማንም ሰው ለመግባት #በኢሜል የሰጣችሁት ኮድ ማወቅ ስለማይችል በጭራሽ❌ መግባት አይችልም፥፥

⚠️የፃፋችሁትን password እንዳትረሱት::


መረጃዎች ቶሎ ቶሎ እንዲደርሳችሁ ቻናላችንን #Mute ያደረጋችሁት #UNMUTE በማድረግ ተባበሩን🙏🙏🙏"

⚠️መረጃዎችን ለወዳጅዎ 👥 ያጋሩ
ለቪዲዮ ኤዲቲንግ የሚያገለግሉ 9 የ አንግሮይድ አፖች

ቪዲዮን ኤዲት ለማድረግ የግድ ኮምፒውተር መጠቀም አይኖርቦትም። ዘመን አፈራሽ የሆኑ ቴክኖሎጂዎች ሞባይል ስልኮን ክኮምፒውተር ባልተናነሰ መልኩ ቪዲዮን ኤዲት አንዲያደርጉ ያስችሎታል። እኛም 10 ለቪዲዮ ኤዲቲንግ ያገለግላሉ ያልናቸውን አፖች የዘን ቀርበናል።

1, FilmoraGo በብዙ ተጠቃሚዎች ዘንድ የተወደደ አስደናቂ የ ዓንድሮኢድ ቪዲዮ ኤዲቲንግ መተግበሪያ ነው። የመቁረጥ ፣ ገጽታዎችን መቀየር ፣ ሙዚቃን የመሳሰሉት ዋና ዋና ተግባራት በቀላሉ ሊከናወኑ ይችላሉ ፡፡ እንዲሁም ለ Youtube ለ Instagram እና ለ Facebook ሚሆኒ ቪዲዮችን መስራት ይችናሉ
የዳውንሎድ ሊንክ: https://play.google.com/store/apps/details?id=com.wondershare.filmorago

2, Adobe Premiere Clip: አዶቤ ፕሪሚየር ክሊፕ ማንኛውንም ቪዲዮ ከእርስዎ የ ስማርት ፎን በፍጥነት እንዲያርትዑ ያስችልዎታል። ለመጠቀም ፈጣን እና አዝናኝ ነው። ስለ ክሊፕ በጣም ጥሩው ባህሪ አውቶማቲክ ቪዲዮ መፍጠር ችሎታ ነው ፣ ማለትም ፣ መተግበሪያው በመረጣቸው ማንኛቸውም ፎቶዎች ወይም ቅንጥቦች አማካኝነት ቪዲዮዎችን በራስ-ሰር ለእርስዎ መፍጠር ይችላል ፡፡
የዳውንሎድ ሊንክ: https://play.google.com/store/apps/details?id=com.adobe.premiereclip

3, VideoShow ብዙ ሽልማቶችን የተቀበለ ሲሆን በነጻ በ Play Store ውስጥ ለሚገኙት ምርጥ የቪዲዮ መተግበሪያዎች አንዱ ነው። VideoShow ለአጠቃቀም ቀላል እና ለአጠቃቀም ቀላል ነው ፡፡ ከዋና ዋና ተግባራት ፊልተሮችን ፣ ሙዚቃዎችን እና የድምፅ ውጤቶችን በመጨመር ወይም ቀጥታ ስርጭትን በማከናወን ቪዲዮዎን ማስዋብ ይችላሉ ፡፡
የዳውንሎድ ሊንክ: https://play.google.com/store/apps/details?id=com.xvideostudio.videoeditor

4, PowerDirector ለአጠቃቀም ቀላል የሆነ የጊዜ መስመር ያለው ሙሉ ለሙሉ የ አንግሮይድ ቪዲዮ ኤዲተር ነው ፣ ግን ከመቆጣጠሪዎች ጋር ለመግባባት የተወሰነ ጊዜ ሊወስድዎት ይችላል። ሆኖም ፣ አንዴ በዚህ መተግበሪያ ኤክስ ኤክስፐርት ከሆኑ ባለሙያዎችን መፍጠር እና በሰከንዶች ጊዜ ውስጥ ምርጥ የሚባሉ ቪዲዮዎችን መስራት ይችላሉ ፡፡ ከቪድዮዎ ውስጥ ለመምረጥ ከ 30 በላይ የተለያዩ የትራንዚሽን ምርጫዎች አሉት ፡፡
የዳውንሎድ ሊንክ: https://play.google.com/store/apps/details?id=com.cyberlink.powerdirector.DRA140225_01
5, KineMaster ከኃይለኛ ባህሪዎች ጋር በጥሩ ሁኔታ ከተሰራ በይነገጽ ጋር በመጣመር KineMaster ለ Android ተስማሚ የቪዲዮ አርት ኤዲቲንግ መሣሪያ ነው። የተለያዩ የሚዲያ ፋይሎችን በቀላሉ ለማስመጣት የ “copy paste” መጠቀም ይችላሉ። ቪዲዮዎችን በፍጥነት ለመፍጠር KineMaster ኤዲቲንግ ሂደት ላይ በይበልጥ ይረዳል። በቪዲዮ መቁረጥ የተለያዩ የሽግግር ዓይነቶችን መጨመር ፣ ወይም የጽሁፎችን ወይም የትርጉም ጽሑፎችን ብሎግ ማስገባት ይችላሉ

የዳውንሎድ ሊንክ: https://play.google.com/store/apps/details?id=com.nexstreaming.app.kinemasterfree

6, Quik እጅግ በጣም ጥሩ ቪዲዮዎችን ለመፍጠር ኩዊክ ሌላ ብልጥ መንገድ ነው ፡፡ ፈጣን እና ነፃ ነው። የራስዎን ታሪኮች በኩዊክ ለማድረግ የራስዎን ተወዳጅ ፎቶዎች ወይም ቪዲዮ ይምረጡ። ስለ ኩዊክ በጣም ጥሩው ነገር አውቶማቲክ የቪዲዮ ፈጠራ ችሎታዎች ይዞ መምጣቱ መሆኑ ነው ፡፡ ቪዲዮዎችን crop ማድረግ ፣ ማሳመሪያዎችን ፣ ጽሑፎችን መጨመር እና ማንኛውንም Audio መምታት በፍጥነት ማመሳሰል ይችላሉ ፡፡
የዳውንሎድ ሊንክ: https://play.google.com/store/apps/details?id=com.stupeflix.replay
7, VivaVideo ብዙ አስደናቂ ባህሪዎች አሉት። መተግበሪያው በቀጥታ ከ አንግሮይድዎ ፕሮፌሽናል-የሚመስሉ ቪዲዮዎችን እንዲፈጥሩ ለማገዝ የታሰበ ነው። ከተለጣፊዎች እስከ ተንቀሣቃሽ ክሊፖች እና የትርጉም ጽሑፎች ከሚገኙ በመቶዎች የሚቆጠሩ ተስማሚ ፊልተሮች መምረጥ ይችላሉ ፡፡ በውስጡ የማይንቀሳቀስ ዘገምተኛ(slow motion) ተንቀሳቃሽ ቪዲዮ ሰሪ እና የተንሸራታች ማሳያ(slideshow maker) ሰሪ አለው።
የዳውንሎድ ሊንክ: https://play.google.com/store/apps/details?id=com.quvideo.xiaoying

8, Funimate video editor በቀላሉ አዝናኝ ቪዲዮዎችን ለመፍጠር ይረዳል። የዕለት ተዕለት አፍታዎችን ወዲያውኑ ወደ የፈጠራ ቪዲዮዎችን መለወጥ እና ለተለያዩ ማህበራዊ ሜዲያ የማጋሪያ አማራጮች አሉት ። አጭር ቪዲዮዎችን ኤዲት ለማድረግ የታቀዱ ከ 1 በላይ የላቁ አማራጮች አሉት ፡፡

የዳውንሎድ ሊንክ: https://play.google.com/store/apps/details?id=com.avcrbt.funimate

9, Magisto መደበኛ የቪዲዮ ኤዲቲንግ ተሞክሮ ለሌላቸው ምርጥ የቪዲዮ ኤዲቲንግ መተግበሪያ ነው። ብዙ ጥረት ሳያደርጉ ምርጥ ቪዲዮን ለመስራት እንዲረዳዎ የቪዲዮ ክሊፕ ፣ ፎቶግራፎችን ፣ audio ፣ ጽሑፎችን ፣ የቪዲዮ ውጤቶችን እና የቪዲዮ ማጣሪያዎችን ይይዛል ፡፡ አንድ ወይም ከዛ በላይ ቪዲዮ ክሊፕ እና ለድምጽ ማጫወቻው አንድ ዘፈን ይምረጡ እና መተግበሪያው በጥቂት ደቂቃዎች ውስጥ አውቶማቲካሊ ቪዲዮ ይፈጥራል።
የዳውንሎድ ሊንክ: https://play.google.com/store/apps/details?id=com.magisto
❤1
#EaseUS_Data_Recovery_Wizard_Pro

#የሚሰጣቸው_ጥቅሞች
#1ኛ_የጠፉ_Permanently_Delete_የተደረጉ_የትኛውንም አይነት መረጃ ከኮምፒውተራችን,ከፍለሻችን,ከHD Recover ማድረግ ያስችለናል።
#2ኛ Formate የተደረጉ የትኛውንም Storage Recover ማድረግ ያስችለናል።
#የተለያዩ_ጥቅሞች_አሉት.....
👍2
ድንገት Delete (Format) ያረግናቸውን
ለምሳሌ :-
▫️ፍይል
▫️ዶክመንትን
▫️ፎቶዎችን
▫️ቪዲዮዎችን
▫️ሌሎችም በድጋሜ ለመመለስ የሚጠቅሙ ምርጥ ሶፍትዌር ለዊንዶውስ ተጠቃሚዎች
#EaseUS_Data_Recovery_Wizard_Pro
👆 ከላይ ያለውን በማውረድ መጠቀም ትችላላችሁ 👆👆
#የሚሰጣቸው_ጥቅሞች
#1ኛ_የጠፉ_Permanently_Delete_የተደረጉ_የትኛውንም አይነት መረጃ ከኮምፒውተራችን,ከፍለሻችን,ከHD Recover ማድረግ ያስችለናል።
#2ኛ Formate የተደረጉ የትኛውንም Storage Recover ማድረግ ያስችለናል።
#የተለያዩ_ጥቅሞች_አሉት.....
አካሄዳችን እየተመቻችሁ ነው?
Anonymous Poll
96%
ተመችቶኛል
4%
አልተመቸኝም