Muhammed Computer Technology (MCT)
38.1K subscribers
527 photos
7 videos
254 files
910 links
🔴አድራሻ:-
✅ ስ.ቁ: 0929273364
✅ ዌብሳይት www.mctplc.com
✅ቴሌግራም አካውንት: https://t.me/mctplc
✅ email: mct16plc@gmail.com
✅ ቲክቶክ አካውንት tiktok.com/@mctplc
Download Telegram
150 በላይ ልብወለድ በPDF ተጭነዋል?
✔️የፈለጉትን መጽሀፍት በPDF በቴሌግራም ቻናላችን ታገኛሉ!
👇👇የቴሌግራም ቻናሉ👇👇👇👇
@EthiopiaDigitalLibrary
አሁኑ ይቀላቀሉ!
✳️ ቴክኖሎጂያዊ እውነታዎች፡

✅ የመጀመሪያው እ.ኤ.አ. በ 1971 የተፈጠረው የኮምፒዩተር ቫይረስ “CREEPER” ተብሎ ይጠራ ነበር።

✅ አፕል እ.ኤ.አ. በ2014 የሚያስገባው ገቢ ሩብ ከጎግል ፌስቡክ እና አማዞን ተደምረው ከሚያገኙት ገቢ ጋር እኩል ነበር።

✅ HP ፣ Google ፣ Microsoft እና Apple የአይቲ ኩባንያዎች ከመሆናቸው ውጭ አንድ የሚያመሳስላቸው ነገር ሁሉም የተጀመሩት በጋራጅ ውስጥ ነበር።

✅ የጆሮ ማዳመጫ ወይም Earphone ለአንድ ሰዓት ብቻ ማድረግ በጆሮዎ ውስጥ የሚገኙትን ባክቴሪያዎች በ700 እጥፍ ሊጨምር ይችላል።

✅ ከAndroid 1.0 እና 1.1 በስተቀር ሌሎች ሁሉም የAndroid ስሪቶች ጥቂቶችን ለመጥቀስ እንደ ጄሊ ቢን ፣ አይስክሬም ሳንድዊች ፣ ማር ማርብ በመሳሰሉ ጣፋጭ ምግቦች የተሰየሙ ናቸው።
✅ Internet ለአንድ ቀን ቢዘጋ 196 ቢሊዮን ኢሜሎች ፣ 3 ቢሊዮን የጉግል ፍለጋዎች ፣ 12 ቢሊዮን የፌስቡክ እና የዩቲዩብ ቪዲዮ ዕይታዎች እና 500 ሚሊዮን ትዊቶች ሳይላኩ ይቀራሉ።
ምርጥ የኔትወርክ፣ የዳታቤዝ፣ 12ኛ ክፍል ሞዴል ፈተና፣ የ12ኛ ክፍል የዩኒቨርስቲ መግቢያ ፈተና፣ ከ8-12ኛ ክፍል ፈተናዎች፣ ለህግ ተማሪዎች የህግ Dictionary እንዲሁም150 በላይ ልብወለድ በPDF ተጭነዋል?
✔️የፈለጉትን መጽሀፍት በPDF በቴሌግራም ቻናላችን ታገኛሉ!
👇👇የቴሌግራም ቻናሉ👇👇👇👇
@EthiopiaDigitalLibrary
አሁኑ ይቀላቀሉ!
ወደ EthioTele በ 994 ከደንበኞች በተደጋጋሚ የሚነሱ ጥያቄዎችና መልሶቻቸው
1.ጂ.ኤስ.ኤም ምንድን ነው?
ጂ.ኤስ.ኤም ሲተነተን ግሩፕ ስፔሻል ሞባይል ማለት ነው፡፡ አሁን ግን ጂ.ኤስ.ኤም ግሎባል ሲስተም ፎር ሞባይል በሚለው እየተተካ መጥቷል፡፡ ጂ.ኤስ.ኤም በሜጋ ሄርዝ ራዲዮ ፍርኬንሲ ባንድ የሚሰራ በአሁኑ ወቀት በስፋት አገልግሎት ላይ የዋለ የተንቀሳቃሽ መገናኛ አገልግሎት ዓይነት ነው፡፡
2.የጥሪ ክፍያው ምን ያህል ነው?
አገር ውስጥ ከሞበይል ወደ ሞባይል ስልክ፣ከሞባይል ወደ መደበኛ ስልክ፣ከመደበኛ ወደ ሞባይል ስልክ ለሚደረጉ የወጪ ጥሪዎች በደቂቃ ቫትን ጨምሮ 0.83 2 ሳንቲም ይከፍላሉ፡፡ ጥሪን ሲቀበሉ ምን አይነት ክፍያ አይጠየቁም፡፡
3.ተንቀሳቃሽ ስልኬ የት የት ነው የሚሰራው?
ተንቀሳቃሽ ስልክዎ በየትኛውም የኢትዮ ቴሌኮም የሞባይል አገልግሎት ባለበት ቦታ ይሰራል፡፡ የሮሚንግ አገልግሎት ካለዎት ደግሞ የሮሚንግ አገልግሎት በተፈቀደበት ቦታ ጭምር ይሰራል፡፡
4.ሮሚንግ ምንድን ነው?
ሮሚንግ የሞባይል አገልግሎት አንዱ አካል ሲሆን የሞባይል ስልክዎን ከኢትዮጵያ ዉጪ መጠቀም ያስችልዎታል፡፡
5.ኢንተርናሽናል ሮሚንግ ማግኘት እችላለሁን?
ኢትዮ ቴሌኮም ከ 143 በላይ አገሮች ጋር የኢንተርናሽናል ሮሚንግ ስምምነት አለው፡፡ የሮሚንግ አገልግሎት ለመግኘት ብር 5000 በቅድሚያ ተቀማጭ ያደርጋሉ፡፡ ለበለጠ መረጃ ወደ ጥሪ ማዕከላችን 994 ይደውሉ፡፡
6.ቪኤምኤስ VMS ምንድን ነው?
የድምፅ መልክት አገልግሎት (ቪኤምኤስ) የእርስዎ ደንበኞች እርስዎ በተለያዩ ምክንያቶች በስልክዎ መገኘት በማይችሉበት ወቅት ለምሳሌ ሌላ ጥሪ በማስተላለፍ ላይ ከሆኑ፤መመለስ በማይችሉብት፤ ስልክዎ ዝግ በሚሆንበት፤ ከአገልግሎት መስጫ ክልል ዉጪ በሚሆኑበት ወዘተ መልዕክት እንዲያስቀምጥልዎ የሚያስችል አገልግሎት ነው፡፡ እነዚህን መልዕክቶች በተመችዎ ጊዜ በራስዎ ወይም በሌላ ሞባይል በመጠቀም ማዳመጥ ይችላሉ፡፡ የድምፅ መልዕክት ሳጥን እስከመጨረሻ የመያዝ አቅሙ ድረስ መልክት ማስቀመጥ ይቻላል፡፡
7.የድምፅ መልክት አገልግሎት (ቪኤምኤስ) ክፍያ ምን ያህል ነው?
መልክት በድምፅ መቀበያ ሳጥን መቀበል ምንም አያስከፍልም፡፡ ከድምፅ መቀበያ ሳጥኑ መልዕክቱን መስማት በወጪ ጥሪ ሂሳብ እኩል ያስከፍላል፡፡
8.የድምፅ መልክት አገልግሎት (ቪኤምኤስ) እንዴት ማግኘት እችላለሁ?
በአቅራቢያዎት የሚገኘውን የደንበኞች አገልግሎት መስጫ ማዕከላችንን ወይንም የድጋፍ መስጫ መስመራችንን 994 ላይ ይደውሉ፡፡
9.ሒሳብ መክፈያ ጊዜዬ በምን ያህል ጊዜ ይሆን?
ለማናቸውም የኢትዮ ተንቀሳቃሽ አገልግሎቶች የሒሳብ መክፈያ ጊዜ በአንድ ወር ልዩነት ይሆናል፡፡
10.ረዘም ላለ ጊዜ አገር ዉሰጥ በማልኖርበት ወቀት እንዴት ወርሃዊ ክፍያዬን መክፈል እችላለሁ?
ቀድሞ በተጠቀሙት ልክ በቀጣይነት የሚወራረድ ቅድመ ክፍያ መክፈል ይችላሉ፡፡
11.ከተጠቀምኩት ዉጪ ክፍያ ቢመጣብኝ/ ሒሳብን በተመለከተ ቅሬታ ቢኖርብኝ ማንን ማናገር እችላለሁ?
በአቅራቢያዎት ለሚገኘው የኢትዮ ቴሌኮም ቢሮ ደብዳቤ በመፃፍ እና የተጋነነውን ሒሳብ በማያያዝ ለሽያጭ ማዕከሉ ሀላፊ ያሰረኩቡና በቀጠሮዎ መሠረት ይመለሱ፡፡
12.ስልኬ ሲጠፋ ወይም ሲም ካርዴ ቢጠፋ ምን ማድረግ አለብኝ?
ወዲያዉኑ መስመሩን ለማዘጋት ወደ ደንበኞች የአገልግሎት ማዕከል 994 በመደውል ያዘጉ/ወይም ከዚህ ቀደም ለዚህ አገልግሎት በአጭር መልዕክት ከጥሪ ማዕከላችን የተላከሎትን ቁጥር የሚያስታውሱ ከሆነ 980 ይደውሉ፡፡
ከአቅራቢያዎ ከሚገኛ የሽያጭ ማዕከል 15 ብር በመክፍል ምትክ ያገኛሉ፡፡
13.የፒን /የደንበኛው የግል የሚስጥር ቁጥር ምንድን ነው?
የሲም ካርዱ ፐርሰናል አይደንቲፊኬሸን ነምበር (ፒን) ባለ አራት ዲጅት የሚስጥር ቁልፍ ሲሆን ሲም ካርዱን ለማስጀመር ይጠቅማል፡፡ የቀፎዎን መመርያ በመከተል ፒኑን መቀየር ይችላሉ፡፡
14.ፒዩኬ ቁጥር ምንድን ነው?
ፒዩኬ ቁጥር ትክክል ያልሆነ ፒን ሶስት ጊዜ በሚያስገቡበት ወቅት ትክከለኛ የስልኩ ባለቤት መሆኖውን ላማረጋገጥ የሚጠየቅ ቁጥር ነው፡፡ በተጨማሪም ስልኮዎን ለማዘጋት በሚፈልጉበት ወቅት ፒዩኬ ቁጥር ይጠየቃሉ፡፡
ፒ.ዩ.ኬ ቁጥርዎን ለማግኘት ወደ ድጋፍ መስጫ መስመሩ በመደወል ማንነትዎን እና የሲም ካርዱን ቁጥር (ሲም ካርዱ ላይ ያለውን ባለ 19 ዲጂት ቁጥር) መጥቀስ ይኖርብዎታል፡፡ ስልክዎ ሙሉ ለሙሉ ከጥቅም ዉጪ እንዳይሆን የተሳሳተ ፒዩኬ ከዘጠኝ ጊዜ በላይ እንዳይሞክሩ ይጠንቀቁ፡፡
15.ስልኬ ከጥቅም ዉጪ ከሆነ ምን ማድረግ እችላለሁ?
ከጥቅም ዉጪ የሆነ ሲም ካርድ ምትክ ብር 15 (ዋጋው ሊቀየር ይችላል) በመክፈል ከደንበኛ የአገልግሎት መስጫ ማዕከል መውሰድ ይችላሉ፡፡
16.ጥሪ ማድረግ ካልቻልኩኝ ምን ማድረግ እችላለሁ?
ከአገልግሎት መስጫ ክልል ዉጪ ወይም ኔትዎረኩ ደካማ በሆነበት ቦታ ሆነው ሊሆኑ ይችላል፡፡ የኔትዎረክ ጥንካሬ ጠቋሚ ምልክቶቹ ይህን ሊያሳዩ ይችላል፡፡ እባክዎ አጠገብዎ ወዳለ የተሻለ የኔትዎረክ ጥንካሬ ወዳለው ቦታ ፈቀቅ ይበሉ፡፡
17.ቀፎዬ የኢትዮ ኔትዎረክን ማግኘት ካልቻለ ምን ማድረግ አለብኝ?
ሲም ካርዱ ከጥቅም ዉጪ ሆናል ወይም በትክክል አላስገቡትም፡፡ እባክዎ በትክክል ያስገቡ፡፡
18.ቀፎዬ በትክክል መስራት ካልቻለ ምን ማድረግ አለብኝ?
የሞባይሎ ባትሪ አልቆ ሊሆን ይችላል፡፡ ባትሪዎን ይሙሉ ወይም ይቀይሩት እንደ የአስፈላጊነቱ፡፡
19.የድጋፍ መስጫ ቁጥሩ ስንት ነው?
የኢትዮ ድጋፍ መስጫ ቁጥር 994 የጥሪ ማዕከል ሲሆን በቀን 24 ሰአት በአመት 365 ቀናት አገልግሎት ይሰጣል፡፡
ሰላም እንዴት ናችሁ? ሰሞኑን ይዤላችሁ የምቀርበው የ Payroll በExcel እንዴት እንደሚሰራ ጥርት ባለ አቀራረብ ይዤላችሁ እቀርባለሁ። ስሞኑን የለቀቅኳቸው ጥሩና አስተማሪ ቪዲዮዎች አሉ እነሱን እንድታዪቸው ግብዣየ ነው። በተጨማሪም #Subscribe በማድረህ ምርጥ ምርጥ ትምህርታዊ ቪዲዮዎችን ይከታተሉ!
#አላህ ወቅታዊ የሀገራችንን ችግር እንዲያስወግድልን ዱአየ ነው።
#ያወቁትን ማሳወቅ ብልህነት ነው!
#ሼር በማድረግ ለሌሎች ይድረስ!
የ YouTube ቻናል ሊንክ 👇👇👇
https://www.youtube.com/channel/UCZBIP6PqUdmmagdTjbyp_AQ
ከኮምፒውተራችን Local Disc(C)ውስጥ System32 የሚል ፎልደር አለ❗️
💠System32 ምንድን ነው?

System32 ፎለደር ሆኖ፣ ከ Windows 2000 ጀምሮ በእያንዳንዱ Windows ቨርዥኖች ላይ ተካቷል። የሚገኘውም በ C:\Windows\System32 ሲሆን እና Windows ስራውን በትክክል እንዲያከናውን የሚያስችሉ ሁሉንም ፋይሎች፤ ፎልደሮችን በውስጡ አካቷል።
System32 በጣም ብዙ ፋይሎችን ነው የያዘው፣ እያንዳዳቸው ምን እንደሚሰሩ ለማየት ይሄን ፎረም ሊንክ ተጭነህ ማየት ትችላለህ፣ Symantec's forums።
በአጠቃላይ የSystem32 ፋይሎች በሁለት መክፈል እንችላለን:

💠DLL(Dynamic Link Library) ፋይሎች:-

የተለያዩ ፕሮግራሞች የ Windows ክፍልን አክሰስ ማድረግ እንዲችሉ መንገዱን ይከፍቱላቸዋል እና በዛው የተሰጣቸውን task ያከናውናሉ። ምሳሌ፣ አንዱ የ DDL ፋይል ኮምፒውተሩ ሙዚቃ እንዲያጫውት ሲያደርግ፣ ሌላኛው ደሞ automatic Windows Updates ይሆናል የሚያከናውነው።
ብዙዎቹ DDL የሚጀምሩት ኮምፒተርህን ስታስነሳው ነው። Windows ያለነርሱ መነሳት አይችልም፣ ለዛ ነው የ DDL errors ማስተካከል እንዲሁ ቀላል የማይሆነው!

💠EXE(Executable) ፋይሎች:-

እነዚህ ፋይሎች፣ የሶፍትዌር መተግበሪያና utilities ችን የያዘ ነው። የተለያዩ ሶፍትዌሮችን፣ እንበልና Chrome ወይም Word ን ስትከፍት በተመሳሳይ የነርሱን Executable ፋይላቸውን ነው የምታስጀምረው። ግን የ System32 EXE ፋይሎች ከዛም በላይ ናቸው፣ ለ Task Manager ወሳኝ የሆነው ስለ winlogon.exe ማንሳት እንችላለን፣ ያለዚህ ፋይል ወደ ኮምፒተርህ sign in ብለህ እራሱ መግባት አትችልም!

💠 System32 ፎልደርን ባጠፋውስ?

ሲጀምር ሲስተሙ እንዲሁ በቀላሉ System32 ን እንድታጠፋ አይፈቅድልህም፣ Administrative privilege ይጠይቃል። Admin ብትሆን እራሱ System32 ፎለደር በአንዴ ማጥፋት አትችልም፣ ምክንያቱም በ System32 ውስጥ የሚገኙ የተለያዩ ፕሮግራሞች በስተዃላ እየሮጡ ስለሆነ። ያለው አማራጭ ፎልደሩ ውስጥ ገብተህ አንድ በአንድ መደለት ነው። ሙሉ ፋይሎችን በዚህ መንገድ ካጠፋሃቸው በዃላ ኮምፒተርህ ያለተለመደ ባህሪ ማሳየት ይጀምራል:
💎 መንቀራፈፍ
💎 መፍዘዝ | መደንዘዝ
💎 በመጨረሻም ከነአካቴው ለምትሰጠው ትዕዛዝ መልስ መስጠት ያቆማል፣ shutdown ብትለው እራሱ ምላሽ የለም። እንደምንም hard shutdown(shutdown በተንን ለተወሰኑ ሰከንዶች በመያዝ) አድርገህ ዘጋኸው፣ ግን እስከ ወዲያኛው ነበር የዘጋኸው(መልሰህ ማስነሳት አትችልም)። System restoreማለትም አትችልም(የቱን ፋይል? system32 ውስጥ ያሉትን ሁሉንም ፋይሎችኮ አጥፍታቸዋል)።

የመጨረሻ መፍትሄ፣ እንደ አዲስ Windows OS መጫን!
​​✳️ Cloud Storage ምድን ነው?

◽️ ክላውድ ስቶሬጅ የምንለው በኮምፒውተር ወይም በሞባይል ስልክዎት የትኛውም ክፍል ላይ የተቀመጠ ፋይልና ዳታ በሌላ ድርጅት በተዘጋጀ የዳታ ማስቀመጫ ላይ የኢንተርኔት ግንኙነትን በመጠቀም የምናስቀምጥበት ነው፡፡

◽️ በአሁን ሰዓት ይሄን አገልግሎት የተለያዮ ድርጅቶች እየሰጡ ሲሆን በዋናነት Microsoft, Google, and Amazon ትልቁን ቦታ በመያዝ የሚጠቀሱ ሲሆኑ ፋይሎችን እና ዶክመንቶችን ለማስቀመጫ ድርጅቶቹ ለመጠቀሚያ የሚያስፈልግ ስም እና የይለፍ ቃል በማዘጋጀት የተወሰኑ ፋይሎችን በነፃ እንዲሁም በክፍያ እንድናስቀምጥ ያደርጋል፡፡

◽️ መጠባበቂያ ፋይሎችን እና ዶክመንቶችን ክላውድ ስቶሬጂ አገልግሎትን መጠቀም ፍላጎት እየጨመረ የመጣ እና የተለያዮ ጥቅሞች ሲኖሩት ከነዚህም ውስጥ ፋይሎች ጥብቅ በሆነ ቦታ መቀመጣቸው፣ የምናስቀምጠውን ፋይል ከየትኛውም ቦታና በማንኛውም ኮምፒውተር ላይ ሆነን መጠቀም እንችላለን እንዲሁም የግል ፋይሎቻችን የተቀመጠበት ኮምፒውተር ቢሰረቅ፣ ቢበላሽ ወይም በእሳት ቢቃጠል ካስቀመጥንበት ድርጂት ፋይሎቹን ካለምንም ችግር እናገኛለን፡፡

◽️ ባክአፕ ክላውድ በመጠቀም ፋይል እና ዳታ ስናስቀምጥ ኮምፒውተራችን የተገናኘበት የኢንተርኔት ግንኙነት ፍጥነት የሚወስነው ይሆናል ትልቅ መጠን ያላቸውን ፋይሎች ለማስቀመጥ ቀናትን ሊፈጅ የሚችል ሲሆን አገልግሎቱን ለመስጠት Amazon S3፣ Google Mozy እና Microsoft Sky Drive የሚሉ ሶፍትዌሮችን አዘጋጅተዋል፡፡

◽️ ማክሮሶፍት ድርጅት ላይ ለማስቀመጥ Sky Driveን በመጠቀም እስከ 25 GB በነፃ ማንኛውም ሰው ማስቀመጥ የሚችል ሲሆን ባጠቃላይ በነፃ ከሰጠን በላይ ለማስቀመጥ ክፍያ የሚያስፈልግ በመሆኑ ክፍያው የሚወሰነው እንደምናስቀምጠው ዳታ መጠን፣ አገልግሎቱን እንደተጠቀምነው ብዛት እንዲሁም የፋይሎቹ ቁጥር ነው፡፡ 

◽️ በተጨማሪም Google ድርጅት ላይ ለማስቀመጥ Google Driveን በመጠቀም እስከ 15 GB በነፃ ማንኛውም ሰው ከስልክዎ ላይ ያሉትን ፎቶና የመሳሰሉት መረጃዎች ማስቀመጥ የሚችል ሲሆን ባጠቃላይ በነፃ ከሰጠን ስቶሬጅ በላይ ለማስቀመጥ ክፍያ የሚያስፈልግ በመሆኑ ክፍያው የሚወሰነው እንደምናስቀምጠው ዳታ መጠን፣ አገልግሎቱን እንደተጠቀምነው ብዛት እንዲሁም የፋይሎቹ ቁጥር ነው፡፡

ስሞኑን የለቀቅኳቸው ጥሩና አስተማሪ ቪዲዮዎች አሉ እነሱን እንድታዪቸው ግብዣየ ነው። በተጨማሪም #Subscribe በማድረህ ምርጥ ምርጥ ትምህርታዊ ቪዲዮዎችን ይከታተሉ!
#ያወቁትን ማሳወቅ ብልህነት ነው!
የ YouTube ቻናል ሊንክ 👇👇👇
https://www.youtube.com/channel/UCZBIP6PqUdmmagdTjbyp_AQ
✳️ስልካቹን Factory rest ከማድረጋቹ በፊት ማድረግ ያለባቹ ነገር

ስልኩ የራሳቹ ከሆነ እና የራሳቹን Email አድሬስ ያስገባቹበት ከሆነ rest ካደረጋቹት በሁዋላ ስትጠቀሙበት የነበረውን email እንድታስገቡ ስለሚጠይቃቹ password እና email መርሳት የለባቹም
ነገር ግን ከሰው ላይ ገዝታቹት ከሆነ እና የገባበትን email ካላወቃቹት ግን ፓተርኑን ወይም የስልኩን ፓስወርድ የምታውቁት ከሆነ ይህንን ነገር ማጥፋት አለባቹ
መጀመሪያ ላይ Setting
👇
About Phone
👇
Software information
👇
Build Number የሚለውን ሶስት ግዜ ስትነኩት
👇
Developer Option ON ይሆናል

ከዛ ወደ setting ትመለሱና developer option ገብታቹ
OME Unlock የሚለውን ታበሩትና ከዛ FactoryRest ማድረግ ትችላላቹ ምንም Email አይጠይቃቹም ማለት ነው።
❤1😁1
በኮምፒውተራችን አዲስ ዊንዶው ምርት ከጫንን በኋላ እንዴት ደህንነቱን አስተማማኝ እናደርጋለን?

አዲስ ዊንዶውስ ምርቶችን /Windows/ (7፣ 8፣10) ወይም ሌላ ኦፕሬቲንግ ሲስተም ከጫንን በኋላ ደህንነቱ የተጠበቀ ለማድረግና ለማሻሻል ከዚህ በታች የተቀመጡትን የደህንነት እርምጃዎች መተግበር ይመከራል፡፡
1. የዊንዶው ስርዓትን ማዘመን/up to date/ የቅርብ ጊዜ የደህንነት ማዘመኛዎች እና መጠገኛዎችን /updates and patches/ መጫን፡፡
2. ሶፍትዌሮችን ማዘመን /Update software/ ፕሮግራሞች እና መተግበሪያዎች ሁሉም ዓይነት የቅርብ ጊዜ ማዘመኛዎች እና የደህንነት መጠገኛዎች መኖራቸውን ማረጋገጥ ያስፈልጋል፡፡ የታወቁ ሶፍትዌሮች እንደ ጃቫ ፣ አዶቤ ፍላሽ ፣ አዶቤ ሾክዌቭ ፣ አዶቤ አክሮባት ሪደር የመሳሰሉት ጊዜ ያለፈባቸው ከሆኑ በአጥፊ ተልእኮ ላይ የተሰማሩ ተዋንያን ሚስጥራዊ የሆኑ መረጃዎች በቀላሉ ለመድረስ ያስችላቸዋል።
3. መልሶ ማግኛ ስርዓት መፍጠር/Create a restore point/ ለዊንዶው ኦፕሬቲንግ ሲስተሞች(OS) የደህንነት ማዘመኛዎች ከተጫነ ቀጣዩ እርምጃ በዊንዶውስ ውስጥ ወደ ነበረበት የመመለሻ ቦታ መፍጠር ነው። በኮምፒተር ላይ ችግርን ሊያስከትሉ የሚችሉ ወይም ስርዓቱ ላይ ማንኛቸውም ለውጦች ከማድረግዎ በፊት የመልሶ ማግኛ አማራጭን ተግባራዊ ማድረግ ይመከራል።
4. ፀረ-ቫይረስ መጫን Install antivirus product - አስተማማኝ የደህንነት መፍትሔ የሚሰጥ ማለትም ሪልታይም ቅኝት ፣ ራስ-ሰር ዝመና (Automatic update) እና ፋየርዎል ማካተት አለበት
5. ለባለብዙ ደረጃ የጥቃት መከላከያ ንቁ የደህንነት መፍትሄን መጫን/Install a proactive security solution for multi-layered protection
6. የምትክ ስርዓት መፍጠር /Back up your system/
7. መደበኛ አካውንት መጠቀም/ Use a standard user account/
8. የተጠቃሚ መለያ ቁጥጥርዎን ንቁ ማድረግ/Keep your User Account Control enabled/ - የተጠቃሚ መለያ ቁጥጥር በኦፕሬቲንግ ሲስተም ላይ ያልተፈቀዱ ለውጦችን እንዳይኖሩ ያግዛል።
ስሞኑን የለቀቅኳቸው ጥሩና አስተማሪ ቪዲዮዎች አሉ እነሱን እንድታዪቸው ግብዣየ ነው። በተጨማሪም #Subscribe በማድረህ ምርጥ ምርጥ ትምህርታዊ ቪዲዮዎችን ይከታተሉ!
#ያወቁትን ማሳወቅ ብልህነት ነው!
የ YouTube ቻናል ሊንክ 👇👇👇
https://www.youtube.com/channel/UCZBIP6PqUdmmagdTjbyp_AQ
በኮምፒውተራችን ላይ hidden የሆኑ ፉይሎች ለማግኘት እንዳስቀመጥናቸው እርግጠኛ የሆናቸው
ፋይሎችእና ፎልደሮች ተደብቀው ነገር ግን ከእይታችን ሊሰወሩ ይችላሉ፡፡ ይህ በሚያጋጥመን ጊዜ ኮምፒውተራችን እንዲያሳየን የሚደርገውን ቅንብር በማስተካከል እንድንመለከት ያስችለናል ፡፡ ከዚህ ቀጥሎ በቅደም ተከተል የተቀመጡትንመንገዶች በመከተል የኮምፒውተርዎን ቅንብር ያስተካክሉ፡ –
1. Start የሚለው ምልክት በመጀመርሪያ እንመርጣለን
2 በመቀጠል ኮንትሮል ፓናል (control panel)
3. ከሚቀርቡለን ምርጫ ውስጥ Appearance and
Personalizationየሚለው ላይ ክሊክ እናደርጋለን
4. ቪው (view) የሚለውን እንጫናለን ከዚያ አድቫንስድ
ሴቲንግ (advancing setting) እናገኛለን
5. በመጨረሻም Show hidden files, folders, anddrives ክሊክ ካደረግን በኋላ ok የሚለውን መርጠን እናጠናቅቃለን፡፡ Or
start >run >cmd> f:attrib -r -s -h /s /d we can use this
ስሞኑን የለቀቅኳቸው ጥሩና አስተማሪ ቪዲዮዎች አሉ እነሱን እንድታዪቸው ግብዣየ ነው። በተጨማሪም #Subscribe በማድረህ ምርጥ ምርጥ ትምህርታዊ ቪዲዮዎችን ይከታተሉ!
#አላህ ወቅታዊ የሀገራችንን ችግር እንዲያስወግድልን ዱአየ ነው።
#ያወቁትን ማሳወቅ ብልህነት ነው!
የ YouTube ቻናል ሊንክ 👇👇👇
https://www.youtube.com/channel/UCZBIP6PqUdmmagdTjbyp_AQ
◄◄ሼር▻▻ይደረግ ብዙ ማወቅ የሚፈልጉ
#ወንድም #እህቶች አሉን!
#የተማሩትን_ማስተማር #ያወቁትን_ማሳወቅ #ብልህነት ነው
በዚህ የቴሌግራም ቻናል
https://t.me/MuhammedComputerTechnology
ጥሩ ጥሩ ስለኮምፒውተርና ቴክኖሎጅ መረጃዎች እና እውቀቶች ይለቀቃሉ ያለዎትን እውቀት ያሳድጋሉ
በቴሌግራም ቻናሌ በመግባት ብዙ መረጃዎችን ማግኜት ትችላላችሁ።
ከኮምፒውተር፣ ከፍላሽ፣ ከExternal Hard Disk በፎልደር ውስጥ ያለን ፋይል እንዴት መደበቅ እንችላለን ከዛስ የደበቅነውን ፎልደርና ፋይል እንዴት እናወጣዋለን?
ምሳሌ: "Documents" የሚል ፎልደር Local Disk C. ቢኖር
✅ Step 1: ከአንድ ላይ Windows key ና R key ይጫኑ ከዛም Run dialog box ይመጣ cmd ብለው ይጻፉና OK ይጫኑ Command Prompt ይመጣላችኋል.
✅ Step 2: ይህንን ይጻፉ attrib +s +h c:\documents ላይ ከዛም Enter ይጫኑ .
አሁን documents የሚለው ፎልደር ከነበረበት ቦታ ይጠፋል ማለት ነው። ይህ ማለት ሙሉበሙሉ ጠፍቷል ማለት አይደለም ተደበቀ እንጅ።
_/_//_/___________
-----ሌላ አማራጭ------
ለምሳሌ ከፍላሽ ዲስክ ወይም ከሀርድዲስክ ያለን መረጃ ለመደበቅ ለምሳሌ ፍላሹ Removable dusk(F) ቢሆን ከኮማንድ ፕሮምፕቱ ላይ F: ብለን ኢተርን እንጫናለን ይህ ማለት ወደ ፍላሽ ዲስክ ገባን ማለት ነው ከፍላሹ ውስጥ documents የሚል ፎደር ቢኖርና መደበቅ ብንፈልግ
✅ attrib +s +h documents ብለን እንጽፋለን ከዛም ኢንተርን እንጫናለን አሁ documents የሚለው ፎልደር ይደበቃል ማለት ነው።
ከፍላሽ ዲስካችን የደበቅነውን documents የሚለውን እንደገና ለማውጣት ብንፈልግ
✅ attrib –s –h documents ጽፈን ኢንተርን እንጫናለን ከዛም ይመለሳል ማለት ነው ከዚህ ላይ የናንተ folder ስም የተለየ ከሆነ documents የሚለውን ብቻ ነው የምትቀይሩት ማለት ነው። ለምሳሌ my secret file የሚል ፎልደር ካላችሁ በ " ማስገባት አለባችሁ ይህም ማለት
✅ ለመደበቅ attrib +s +h "my secret file"
✅ ከተደበቀበት ለማውጣት attrib –s –h "my secret file" የፎልደሩ ስም ከአንድ በላይ word ከሆነ የግድ በ" " ማስገባት አለባችሁ።
_/_//_/___________
አንዳንድ ጊዜ በፍላሽ ዲስክ የያዝነው መረጃ ይደበቅብናል። ከተደበቀበት ሁሉንም ፎልደሮችና ፋይሎችን ለማውጣት ስንፈልግ ከይ በጠቀስኩት አግባብ ለምሳሌ ፍላሽ ዲስካችን Removable Disk(F) ቢሆን ከኮማንድ ፕሮምፕቱ ላይ F: ብለን እንጫንና attrib -s -h /s /d ብለን እንጽግና ኢንተርን እንጫናለን ከዛም ሁሉም የተደበቀው ፋይል ሁሉ ይወጣልናል ማለት ነው። ሞክሩትና እዩት!
ሲሰተም ሪስቶር (System Restore)
ሲስተም ሪስቶር የምንጠቀምበት በኮምፒውተራችን ላይ
ችግሮች(ብልሽት) ሲያጋጥም በጥሩ ሁኔታ በሚሰራበት
ጊዜ በኮምፒውተሩ አውቶማቲካሊ ወይም ማኑዋሊ
በተዘጋጀው ሪስቶር ፖይንት በመጠቀም የነበሩ ወርድ
ዶከመንቶች፣ ፎቶግራፎች፣ ሙዚቃዎች፣ ኢሜል
መልክቶች እንዲሁም የምርጫችን የሆኑ ኢንተርኔት
ዌብሳይቶች፣ ማይ ዶክመንት ውስጥ ያሉ የተለያዩ
ፋይሎችን ሳይጠፉ በነበረበት ፣የምናሰተካክልበት የዊንዶ
ኤክሰፒ፣ 7፣ 8 ቱል ሲሆን ሪሰቶር ስናደርግ
በኮምፒውተራችን ላይ ያሉ ፋይሎች በጭራሽ አያጠፋም
እንዲሁም አይቀይርብንም ነገር ግን ሪስቶር ካደረግንበት
ቀንና ሰዓት ቦሃላ የተጫኑ ሶፍትዌሮች፣ አፕሊኬሽን
ፕሮግራሞች ይጠፋሉ እንደገና መጫን ይኖርብናል ፡፡
ዳታዎች ከኮምፒውተር ላይ መጥፋት ወይም መበላሸት
ምክንያት የሚሆኑት
1. አዲስ ድራይቨር ከተጫነ
2. ዊንዶ ኦፕሬቲንግ ሲስተማችን አብዴት ስናደርግ
3. የተለያዩ አፕልኬሽን ሶፍትዌሮች መጫን
ሲስተም ሪስቶር በቫይረስ የተጠቁና የተበላሹ ፋይሎችን
እና በአድ/ሪሙቭ ፕሮግራም ያስወገድናቸውን
ሶፍትዌሮች ወደነበረበት መመለስ አንችልም አንዲሁም
በቫይረስ የተጠቁ ፋይሎችን አይፀዳም፡፡
Share your knowledge free for millions ያለዎትን
እና ያገኙትን እውቀት በነፃ ለሚሊዎኖች ያካፍሉ/ያድርሱ
❤2
ኮምፒውተር ላይ ልታውቋቸው ግድ ነው ያልናቸውን አቋራጭ የኪቦርድ መንገዶችን (Shortcuts) እናሳውቃችሁ
Ctrl+C እና Ctrl+X
****************************

Ctrl+C የመርጥነውን ጽሁፍ ወይንም ፎልደር ይሁን ፋይል ኮፒ ለማድረግ ይረዳናል። አይ ድግግሞሽ አልፈልግም ቆርጬ (Cut) ነው መውሰድ የምፈልገው ካልን ደሞ Ctrl+Xን መንካት ነው። ከት ካደረግንበት ቦታ ፋይሉን ወይም ጽሁፉን ያጠፋዋል።
ለአፕል ኮምፑተር ተጠቃሚዎች Ctrlን በcommand(cmd) በመተካት መጠቀም ይችላሉ።

Ctrl+V

ይህ አቋራጭ የሚጠቅመን ከላይ ኮፒ ወይም ከት ያደርግነውን በምፈልገው ቦታ ላይ ለማቀመጥ ነው። የንምፈልገው ቦታ ላይ ሄደን Ctrl+V ስንነካ ፋይሉን ያስቀምጥልናል።
ለአፕል ተጥቃሚዎች Cmd+Vን መጠቀም ይችላሉ

Ctrl+F

Ctrl+F በመካት የመፈለጊያ ሳጥን (Search) መክፈት እንችላለን። የህም የፈለግነዉን ጽሁፍ(text) እና ፋይል ለማግኘት ይረዳናል።
ለአፕል ተጠቃዎች Cmd+F በመንካት መጠቀም ይችላሉ።

Alt+Tab

Alt+Tab መጫን በተከፈቱ ፕሮግራሞች መሃል እንደፈለግን እንድቀያይር ያደርገናል። ለምሳሌ በብራውዘር ኢንተርኔት እየተጠቀምን ከነበር እና ወደ መፈትነው ወርድ ፋይል መሄድ ብንፈልግ Alt+Tab በመንካት መለወጥ እንችላለን።
ለአፕል ተጠቃሚዎች cmd+Tab ተጥቀሙ።

Ctrl+Backspace እና Ctrl+Left ወይም Right arrow

Backspace የጽሁፍ ፋይል ላይ አንድ ፊደልን ወይም ምልክትን ለማጥፋት ይጠቅምናል። ነገር ግን Ctrl+Backspace ሁሉንም ነገር አንድ ሳያስቀር ያጠፋልናል።
Ctrlን ተጭነን የግራ(left) እና ቀኝ(Right) ቀስቶችን ስንነካ እንደ ከርሰር ተጥቅመን የምንፈሊገዉን ተከታታይ ፋይል ወይም ጽሁፍ በጅምላ እንድንመርጥ ይረዳናል።

Ctrl+S

ዶክመንቶች ላይ እየሰራን የሰራበውን ቶሎ ሴቭ ማድረግ ቢያስፈልህልገን የምንጠቀመው Ctrl+S ነው። በተለይ እንደኛ አገር ላሉ የመብራት ችግር ላለባቨው አገሮች ዶችመታቭን ሴቭ ሳናደርግ እንዳይጠፋ ፍቱን መፍትሄ ነው።
ለአፕል ተጠቃሚዎች cmd+S ተጠቀሙ።

Ctrl+Home እና Ctrl+End

Ctrl+Home ከርሳችንን ወደ ዶክመንታችም መጅውመሪያ ይመልሰዋል። በተቃራኒው Ctrl+End ደሞ ከርሰራችንን ወደ. ዶክመንታችን መጨረሻ ይወስዋል።

Ctrl+P

ፒሪንት ማድረግ የምንፈልገው ፋይል ወንም ዶቹመንት ካለ Ctrl+P ስንነካ የፕሪንትን መስኮት በመክፈት የፕሪንት አማራጮችን ያሳየናል።
ለአፕል ተጠቃሚዎች cmd+Pን ተጠቀሙ።

PageUp ፣ Spacebar እና Pagedown

ከስሙ መገመት እንደሚቻለው PageUp እና Pagedown ዶክመንታችን ላይ ወደ ቀጣይ ገጽ ወንም ወደ ቀድሞ ገጽ ለመሄድ ይጠቅመናል። የኢንተርኔት ብራውዘር በመጠቀምበት ሰአት ደሞ Spacebar ወይም Shift+Spacebar አንድ ገጽ ለመዝለል ያስችለናል።
✅ ትርጓሜ - ሲ ድራይቭ (ሲ :) ምን ማለት ነው? ሲ ድራይቭ (ሲ :) ኦፐሬቲንግ ሲስተም እና ተዛማጅ የስርዓት ፋይሎችን የያዘ ዋናው የሃርድ ዲስክ ክፋይ ነው ፡፡ በዊንዶውስ ኦፐሬቲንግ ሲስተሞች ውስጥ ሲ ድራይቭ እንደ “C: \” ሆኖ የተወከለው ፣ የድራይቭን root directory የሚወክል የኋላ ኋላ ፡፡
✅ ሲ ድራይቭ እንደ የስርዓቱ ዋና ሃርድ ድራይቭ ተደርጎ የሚወሰድ ሲሆን የስርዓተ ክወናውን ፣ የስርዓት ፋይሎችን እና ሌሎች መተግበሪያዎችን እና ተዛማጅ ፋይሎቻቸውን ለማከማቸት ያገለግላል ፡፡ በኋላ ባለው የዊንዶውስ ስሪት ፣ ሲ-ድራይቭ እንደ ፕራይሜሪ ድራይቭ ወይም Local Disk የሚል ስያሜ የተሰጠው ሲሆን “My Computer” የሚለውን አቃፊ በመክፈት በነባሪነት ማግኘት ይቻላል፡፡
✅ ቴኮፒዲያ ሲ ድራይቭን ያብራራል (ሲ :) ለዲስክ ድራይቮች በ Letter የመሰየሚያ ዘዴው ከ DOS የመጀመሪያ ቀናት ጀምሮ ነበር ፡፡ A እና B የሚሉት ፊደሎች ለፍሎፒ ዲስክ ድራይቮች የተቀመጡ ሲሆኑ ሲ ሲ ደግሞ ኦፐሬቲንግ ሲስተም እና ተዛማጅ የስርዓት ፋይሎች ላለው ለዋናው የሃርድ ዲስክ ክፋይ ተመድቧል ፡፡
✅ የቆዩ የ DOS ስሪቶች ሃርድ ድራይቮችን ከግምት ውስጥ ከመግባትዎ በፊት ለእያንዳንዱ ፍሎፒ ድራይቭ letter ይመድባሉ ፡፡ በዚህ መንገድ ኮምፒዩተሩ ከሁለት በላይ የፍሎፒ ድራይቮች ቢኖሩት ኖሮ ሃርድ ዲስክ ድራይቭ D :, E: ወዘተ ተብሎ ይጠራ ነበር ፡፡ ሆኖም ፣ ከ ‹DOS 5.0› ጀምሮ ድራይቭ ሲ: የፍሎፒ ድራይቮች ብዛት ምንም ይሁን ምን ለመጀመሪያው ሀርድ ዲስክ ተመድቦለታል (የቡት ድራይቭ ወይ A: ወይም C :) ነበር ፡፡
✅ Letter A እና B ለ ፍልፒ ዲስክ ድራይቮች የተያዙ ስለነበሩ አብዛኛው ኮምፒተር ሁለት የተለያዩ የፍሎፒ ድራይቮች ስላለው አንዱ ለ 3 1⁄2 ″ ፍሎፒዎች (A :) እና ሌላኛው ደግሞ ለ 5 1⁄4 ″ ፍሎፒዎች (ቢ :) ፡፡
✅ ሌሎች ፊደላት (ዲ ፣ ኢ ፣ ኤፍ ፣ ወዘተ) ለሌሎች ሃርድ ድራይቮች ፣ ፍላሽ ድራይቮች ወይም ለኦፕቲካል ድራይቮች (ሲዲ ድራይቮች ፣ ዲቪዲ ድራይቮች ፣ ዲስክ አባካሪዎች ፣ የብሉ ሬይ ድራይቮች ፣ ወዘተ) ሊመደቡ ይችላሉ ፡፡ በሌላ አገላለጽ ፊደሎች logical ድራይቭዎችን ለመወሰን ያገለግሉ ነበር ፣ ምንም እንኳን ብዙ ቆየት ብለው physical storage መሣሪያዎችን ለመለየትም ያገለግሉ ነበር ፡፡
✅ ዛሬም ቢሆን ኮምፒተርው ለፍሎፒ ዲስክ ድራይቭ ከአሁን በኋላ በአብዛኞቹ ኮምፒውተሮች ውስጥ ባይገኙም ለ ‹A› እና B ›ድራይቮች መያዙን ይቀጥላል ፡፡
✅ የሃርድ ድራይቭዎ ዓላማ (C: drive) የኮምፒተርዎ ሃርድ ድራይቭ በመባል የሚታወቀው ሲ-ድራይቭ የኮምፒተርዎን ኦፐሬቲንግ ሲስተም (ዊንዶውስ ፣ ማክ ኦኤስ ፣ ሊነክስ ፣ ወዘተ) እንዲሁም የሚጠቀሙባቸውን አፕሊኬሽኖች (ለምሳሌ ማይክሮሶፍት ኦፊስ ፣ አዶቤ ፣ ሞዚላ ፋየርፎክስ) የማከማቸት አስፈላጊ ሥራ አለው ፡፡ ) እና ከበይነመረቡ (Internet) የሚያወርዷቸው ፋይሎች።
✅ በ C: ድራይቭ ላይ ምን አለ? የ “ሲ” ድራይቭ በአሁኑ ጊዜ ለሚሰሩባቸው ፋይሎች እንደ ጊዜያዊ ማከማቻ ቦታ በጥሩ ሁኔታ ጥቅም ላይ ይውላል ፡፡ በ C ላይ መተማመን ለረጅም ጊዜ ማከማቻ ድራይቭ አደገኛ ነው።
❤1
ኮምፒዩተር
ኮምፕዩተር ማለት ማንኛውንም ኢንፎርሜሽን ፕሮሰስ የሚያደርግ ማሽን ነው። ይህንም የሚያደርገው በተርታ የተቀመጡ ትዕዛዞች በመፈጸም ነው። ለብዙ ሰዎች ኮምፒዩተር ሲባል ዐዕምሯቸው ላይ የሚመጣው የግል (ፐርሰናል) ኮምፒዩተር ነው። ነገር ግን ኮምፒዩተር ሲባል በጣም ብዙ ነገሮችን ያጠቃልላል። ላፕቶፕ ፣ ዴስክቶፕ ፣ ማይክሮ-ኮምፒዩተር ፣ ሱፐር-ኮምፒዩተር ፣ ካልኩሌተር ፣ዲጂታል ካሜራ እና ሌሎችንም ያጠቃልላል።
ኮምፒዩተር
ታሪክ
ቀድሞ አስሊ ማለት አንድ በሒሳባዊ ትዕዛዝ የተለያዩ የጥንት መሣሪያዎችን እየተጠቀመ ቁጥሮችን የሚያሰላ ሰው ነበር። እስከ 20ኛው ክፍለ-ዘመን ድረስ የተለያዩ ጠቃሚ መሣሪያዎች ተሰርተዋል። ከዛ በኋላ ትልልቅ ማሸኖች መሠራት ጀመሩ። እነዚህ ማሽኖች ከዛሬው ኮምፒዩተሮች(አስሊዎች) ጋር ሲወዳደሩ በጣም ትልቅና ቀርፋፋ ናቸው።
የኮምፒዩተር ዐይነቶች
ሜን ፍሪም
ሱፐር ኮምፒዩተር
ዎርክ ስቴሽን
ማይክሮ ኮምፒዩተር-(ዴስክቶፕ፣ ላፕቶፕ፣ ፓልምቶፕ)
ሚኒ ኮምፒዩተር
ዋና የኮምፒየተር ዐይነቶች እንደሚከተለው ነው፦
የኮምፕዩተር ክፍሎች
የኮምፕዩተር የውስጥ ክፍሎች የሚከተሉት ናቸው፡-
1. ሞኒተር (የምንሰራውን ነገር እንዲያሳየን፤ምስል፣ጽሑፍ፣ ቪዲዮ ወይም ማንኛውም ነገር ሊሆን ይችላል)
ሞኒተር 14 ኢንች፣ 15 ኢንች፣ ወዘተ. እየተባለ ይገላጻል፡፡
14 ኢንች 15 ኢንች እያልን ስንናገር አለካኩ ከምስል ማሳያው አንድ ጥግ እስከ ሌላኛው ጥግ ያለውን ርቀት በመለካት ነው፡፡(ስዕሉን ይመልከቱ፡፡)
በፊት የነበሩት የላፕቶፕና ዴስክቶፕ ኮምፒዩተሮች ሬሾ (ርዝመት ሲካፈል ለወርድ) 4በ3(በትክክል ሲጻፍ 4:3 ይሆናል) ነበር፡፡
አሁን ደግሞ የቲያትር ሞድ የሚባለው ባለ 16፡9 ሬሾ ወይም ዋይድ ስክሪን (widescreen) በመጠቀም ላይ ናቸው፡፡
2.ማዘርቦርድ(እናት ሰሌዳ)(ሁሉም የኮምፕዩተር ክፍሎች(ዕቃዎች)የሚቀዳጁበት)
3.ሲፒዩ(የኮምፕዩተሩ አእማሮ እንደማለት ነው፡፡ይህ ሲባል ግን ሲፒዩን ከሰው አእምሮ ጋር አንድ ነው ማለት አይደለም፡፡)
4.ሜሞሪ(ማስታወሻ)(የምንሰራውን ስራ ወይም ፋይል በጊዚያዊነት አስቀምጠንበት የምንሰራበት)
ሜሞሪ(ማስታወሻ) በባይት (Bytes) ይለካል፡፡ ከ Bytes ፊት Kilo፣ ማለትም ኪሎባይት (kilobytes)([1,024 ባይቶች ወይም Bytes ማለት ነው፡፡ ] ፣ Mega[1,048,576 ባይቶች ወይም Bytes ] ፣ Giga [1,073,741,824 ባይቶች ወይም Bytes]፣ ወዘተ የሚሉትን ቃላት በመጠቀም ኪሎባይት(kilobyte)፣ ሜጋባይት (megabyte)፣ ጊጋባይት (gigabyte) እያልን የኮምፒዩተር ሜሞሪ መግለፅ እንገልጻለን፡፡
ለምሳሌ 10 MegaBytes ወይም ባጭሩ ሲጸፍ 10MB ይህ ማለት 10,485,760 Bytes ይሆናል ማለት ነው፡፡
5.ኤክስፓንሽ ስሎት
6.የኤሌክትሪክ ሀይል ማቅረቢያ (power supply)
7.የሲዲ ማሰሪያ (cd drive)
8.ሀርድ ዲስክ (የምንሰራውን ወይም የምንጠቀምበትን ፋይል በቋሚነት ለማስቀመጥ)
9. መሎጊያ (ማውስ )
10.የፊደል ገበታ (ኪቦርድ)
ዊኪፒዲያ ላይ ያለውን ምስል ከቁጥሩ ጋር ማነጻጸር ይቻላል፡፡
ኮምፕዩተሮች እንዴት እንደሚሰሩ
ታዋቂ ዋና ዋና የኮምፕዩተር አምራቾች
ታዋቂ የኮምፕዩተር አምራቾች የሚከተሉት ናቸው፡፡ ይህ ማለት ግን እያንዳዱን የኮምፕዩተር ክፍል(ዕቃዎች)ይሠራሉ ማለት አይደለም፡፡
1.አይቢኤም[IBM](አሁን እንኳ የፒሲ ክፍሉን እ.ኤ.አ. በ2004 ለቻይናው ሊኖቮ ሸጦታል)፡፡ አሁን ሜን ፍሬም[Main Frame] ኮምፒዩተር ነው በብዛት የሚያመርቱት/የሚሠሩት፡፡
ድረ ገጽ---[ http://www.ibm.com የአይቢኤም ድረ ገጽ ]
2.ዴል[Dell]
ድረ ገጽ---[ http://www.dell.com የዴል ድረ ገጽ]
በኢትዮጵያ የዴል ወኪል አልታ ኮምፒዩተር ነው፡ ፡አድራሻቸው ቦሌ መንገድ ሸዋ ሱፐርማርኬት ፊትለፊት ኔጃት ኮምፒዩተር ያለበት ፎቅ ላይ ነው፡፡
3.ኤሰር[Acer]
ድረ ገጽ---[ http://www.acer.com የኤሰር ድረ ገጽ]
በኢትዮጵያ የኤሰር ወኪል ኔጃት ኮምፒዩተር ነው፡፡ አድራሻቸው ቦሌ መንገድ ሸዋ ሱፐርማርኬት ፊትለፊት አልታ ኮምፒዩተር ያለበት ፎቅ ላይ ነው፡፡
4.ቶሺባ [Toshiba]
ድረ ገጽ---[ http://www.toshiba.com የቶሺባ ድረ ገጽ]
5. አፕል [Apple]
ድረ ገጽ---[ http://www.apple.com የአፕል ድረ ገጽ]
6.ኤችፒ[HP]
ድረ ገጽ---[ http://www.hp.com የኤችፒ[ድረ ገጽ]
ኮምፕዩተሮችና የዓለም ፊደላት
የመጀመሪያቹ ኮምፕዩተሮች የሚሠሩት በእንግሊዝኛ ፊደል ብቻ ነበር። ቀስ በቀስ ግን የተለያዩ ኣገሮች ሊቃውንት በየራሳቸው ፊደላት እንዲሠሩ ኣደረጉ። ኮምፕዩተር በእያንዳንዱ የግዕዝ ፊደል፣ ኣኃዝና ምልክት እንዲሠራ ለመጀመሪያ ጊዜ የፈጠረው ኢትዮጵያዊው ዶክተር ኣበራ ሞላ ነው። በቅርቡም አያንዳንዱ የግዕዝ ፊደል፣ ኣኃዝና ምልክት ዩኒኮድ የሚባል የዓለም ፊደላት መደብ ውስጥ መግባት ቀጥሏል።
💢ስልካችሁ📲 ላይ #አፕልኬሽን ስትከፍቱ :⬇️⬇️⬇️

✅This Application Stopped Working‼️
✅Crashing‼️
✅Won’t open‼️
✅Won’t respond‼️
✅Isn’t working properly‼️

🔆እያለ ላስቸገራችሁ መፍትሔ⬇️

1⃣.#Restart እና #Update ይሞክሩ፤ እንደዚህ ስታደርጉ በአብዛኛው ጊዜ ይስተካከላል።👍

⚠️ስልካችሁን📲 #Restart አድርጉት።

⚠️Setting➡️ Software Update ውስጥ ገብታችሁ የስልካችሁን📲 Operating System #Update አድርጉ።

⚠️_Playstore ላይ ገብታችሁ አፑን #Update አድርጉት።

2⃣.*Update Google Play Services *

⚠️ስትከፍቱ #Update አድርጉት ይላችኋል።

3⃣. አፑን የማትጠቀሙበት ከሆነ *Setting* ውስጥ ገብታችሁ #Forced\Stop አድርጉት።

⚠️System App ካልሆነ #Uninstall❌ ያድርጉት።

4⃣. Clear App and Cache ይሞክሩ።

⚠️Setting➡️ Manage apps➡️ ያስቸገራችሁን አፕ➡️ Clear Data and Clear Cache.

5⃣. እኔ እንዳየሁት ከሆነ ከላይ በነገርኳችሁ መፍትሔ 95% ስልኮች📲 ይስተካከላሉ👍 ለተቀሩት ስልኮች #Hard_Reset መሞከር ይቻላል።

⚠️ኮፒ ስልኮችንና ብዙ ጊዜ Hard Reset የተደረጉ ስልኮችን አይጨምርም‼️ እነሱ ስልኮች📲 ሌላ ታሪክ ውስጥ ናቸው።😁
✅የሶፍትዌር ችግር ማለት ምን ማለት ነው?
ከሚከተሉት አንደኛው ወይም ሁሉም ችግሮች በአይፎን ወይም የአንድሮይድ ስልክዎ ላይ ተከስተው ያውቃሉ?
⏺ስልክዎ በራሱ ጊዜ እየበራ ይጠፋል፣ ወይም Involuntary Restart ያደርጋል
⏺ ስልኩ ሙሉ በሙሉ አይነሳም Dead Phone ይሆናል
⏺ ከጫኗቸው አፕሊኬሽኖች የተወሰኑቱ ተለይተው ያለመስራት ወይም የመዘግየትና ስታክ የማድረግ ችግር ያሳያሉ
⏺ በአጠቃላይ ስልክዎ እጅግ በጣም ቀርፋፋ ይሆናል ( ⚠️ በእርግጥ አንዳንድ ጊዜ ይህ አይነቱ ችግር በስልካችን ላይ በጣም ብዙ አፕሊኬሽኖችና ዳታዎችን በመያዝ ምክንያት ከሚሞሪ መጣበብም የተነሳ ሊከሰት ይችላል) ወይም
⏺ የአንድሮይድ ወይም የአፕል ሎጎ ላይ Stack ያደርጋል
⏺ ለስልክዎ ያስገቡት የፓተርን ፓስወርድ ጠፍቶዎታል፣ ወይም User Locked ሆኗል ⏺ የኔትወርክ መዘጋት(Carrier Network Locked )፣
⏺ ከሚከተሉት አንደኛውን መልእክት ይሰጥዎታል
📍 SIM not Valid,
📍 Wrong SIM,
📍 Contact SP (Service Provider), 📍 Unknown SIM,
📍Phone Restricted ወዘተ…
እና ሌሎችም እነዚህን የመሳሰሉ ችግሮች በሚከሰቱበት ጊዜ ስልኩ የሶፍትዌር ችግር አለው ማለት ነው፡፡
⏺ በዚህ ጊዜ ከዚህ በታች የሚከተሉት መፍትሄዎች ችግሩን ሙሉ በሙሉ በመቅረፍ እፎይታ ይሰጡዎታል ማለት ነው
⚠️ ማሳሰቢያ፡- ማንኛውንም የሶፍትዌርም ሆነ የሀርድዌር ጥገና ከመከወናችን በፊት data backup ማድረግ ወይም ያሉንን ዳታዎችና መረጃዎች ወደሌላ ሚዲየም (ወደሌላ ፍላሽ ሚሞሪ ወይም ወደ ኮምፒውተር ወይም ወደጎግል ወይም አይክላውድ አካውንት) ማዛወር ይኖርብናል፡፡
⏺ ይህን ማድረግ በጥገናው ሂደት ለሚደርስ የዳታ መጥፋት ሁነኛ መፍትሄ ይሆናል፡፡
📍 ለአንድሮይድ ስልኮች
❗️Hard Reset or Factory Reset ማድረግ Format ማድረግ በዚህም ችግሩ ካልተፈታ
❗️ በ Stock Firmware Flash ማድረግ ❗️ Unlocking,
❗️ Android Rooting ማድረግ (User, Network Provider or Carrier etc… ) እና ሌሎችም
ለአይፎን ስልኮች በቅርብ ጊዜ
❗️ የ iTunes Software Restore ማድረግ ቀደም ብለው በነበሩት የአይፎን ስልኮች ላይ የተለያዩ
❗️ የJailbreaking ሶፍትዌሮች በመጠቀም የኔትወርክ ክልከላውን ሰብሮ ማለፍ እና ሌሎችም በድጋሚ ማንኛውንም የሶፍትዌርም ሆነ የሀርድዌር ጥገና ከመከወናችን በፊት ⚠️ data backup ማድረግ በፍጹም በፍጹም
እንዳይዘነጉ፡፡
👍1
✳️ የዊንዶዉስ-10 ቨርዥን "1809" በሚቀጥለዉ ሳምንት አገልግሎቱ ይቋረጣል

ግዙፉ #የቴክኖሎጂ ኩባንያ ማይክሮሶፍት የዊንዶዉስ-10 የቨርዥን (version-1809) ምርቱ ከሚቀጥለዉ ሳምንት ጀምሮ አገልግሎቱን እንደሚያቋርጥ ገለጸ፡፡
አገልግሎታቸዉ ላበቃ ምርቶች ቴክኒካዊ ድጋፎችን እንደማያቀርብ የገለጸዉ ማይክሮሶፍት ይህን ተከትሎ በሶፍትዌሮቹ ላይ ለሚከሰቱ የሶፍትዌር ክፍተቶች እና ተጋላጭነቶችም ማዘመኛዎችን እንደማያቀርብ እና የደህንነት ጥገናዎችንም እንደማያደርግ አሳውቋል።

የአገልግሎት ጊዜያቸዉ ያበቃ ሶፍትዌሮችን አሁንም ድረስ የሚጠቀሙ ደንበኞች የሲስተሞቻቸዉን ከጉዳት ነፃ እንዲሆኑ እና ከመረጃ ጥቃቶች እንዲጠበቁ በፍጥነት ምርቶቻቸዉን ወደ ቅርብ ጊዜ የዊንዶዉ-10 ቨርዥኖች እንዲያሻሽሉ ማይክሮሶፍት አሳስቧል፡፡
የኢንተርፕራይዝ (Enterprise)፣ የኢዱኬሽን (Education) እና ከኢንተርኔት ጋር የተቆራኙ ቁሶች (IoT Enterprise) ሆነዉ የዊንዶዉስ-10 ቨርዥን 1809 ተጠቃሚዎ አገልግሎቱን እስከ ፈረንጆቹ ግንቦት 11/2021 እንደሚቆይላቸዉ ታዉቋል፡፡
በመሆኑን እርስዎ እየተገለገሉበት ያለዉ ኮምፒዉተር ዊንዶዉስ-10 ቨርዥን 1809 ከሆነ በመጀመሪያ ወደ ዊንዶዉስ-10 ቨርዥን 1903 ካዘመኑ በኋላ ወደ የዊንዶዉስ-10 ቨርዥን 2004 ማሳደግ እና በኮምፒዉተሩ በመተግበር (installed) ይኖርዎታል፡፡
ይህንን የዝመና አማራጭ ማይክሮሶፍት ባያበረታታዉም ተጠቃሚዎች Media Creation Tool ተጠቅመዉ ምርቶቻቸዉን ማዘመን ይችላሉ፡፡
እርስዎ እየተጠቀሙበት ያለዉን የዊንዶዉ ቨርዥን ለማወቅ በመጀመሪያ Start የሚለዉን በመጫን > "Settings" የሚለዉን መምረጥ > ከዚያም "System" ሲስተምን በመጫን > "About" የሚለዉን መምረጥ የኮምፒዉተርዎን ቨርዥን ማወቅ ይችላሉ፡፡ አልያም window + R ተጭነው በሚመጣላቹ ዊንዶውስ ላይ winver ብላቹ enter ስትሉት ያሳያችዋል።
ስሞኑን የለቀቅኳቸው ጥሩና አስተማሪ ቪዲዮዎች አሉ እነሱን እንድታዪቸው ግብዣየ ነው። በተጨማሪም አዳዲስ ቪዲዮችን እየሰራሁ ስለሆነ #Subscribe በማድረግ ምርጥ ምርጥ ትምህርታዊ ቪዲዮዎችን ይከታተሉ!
#ያወቁትን ማሳወቅ ብልህነት ነው!
የ YouTube ቻናል ሊንክ 👇👇👇
https://www.youtube.com/channel/UCZBIP6PqUdmmagdTjbyp_AQ
ሰለ ቴሌግራም ማወቅ ያለባችሁ 10 ወሳኝ ነጋሮች

✔ 1ኛ :- ያለንበትን ቦታ ለጓደኞቻችን መላክ እንችላለን እንዴት መጀመሪያ ቴሌግራም እንከፍታለን ከዛ የምንልከውን ሰዉ እንመርጣለን ከዛ መላክዋን ከፍተን location የምለውን ተጭነን ያለንበትን ቦታ መላክ ይቻላል ::

✔ 2ኛ :- ከኛ ወጪ ማንም ሰው ቴሌግራማችንን ማንም ሰዉ እንደይጠቀም ከፈለግን password ማዘጋጀት ይቻላል እንዴት መጀመሪያ ቴሌግራም እንከፍታለን ከዛ በቴሌግራም ጫፈ ላይ ሦስት መሰመር አለ እሱን አንዴ እንነካለን ከዛ setting የምለውን እንነካለን ከዛ privacy and security የምለውን እንነካለን ከዛ passcode የምለወን እንነካለን ከዛ passcode lock on እናደርጋለን ከዛ የምንፈልገውን password እናስገባለን ::

✔ 3ኛ:- እንዴት ቴሌግራም ብር እንደይበላ ማድረግ ይቻላል
በመጀመሪያ ቴሌግራም እንከፍታለን ከዛ በቴሌግራም ጫፈ ያለውን ሦስቷን መሰመር እንነካለን ከዛ setting ላይ እንገባለን ከዛ data and storage የምለዉን እንነካለን ከዛ
ከዛ when using mobile data -OF-አድርጉት ::

✔4ኛ :- የለክነዉን message ከደረሰ ቦኃላ delete ማድረግ ይቻላል እንዴት መጀመሪያ የለነክነዉን message እንከፍታለን ከዛ ቦታዉ ላይ አጥብቀን እንዛለን ከዛ ከላይ የምለውን Also delete receive የምለውን ራይት እናደርጋለን ከዛ ሁለቱም ጋ delete ይሆናል ::
5ኛ :- እንዴት በአንድ የቴሌግራም አፕሊኬሽን ሁለት account እንጠቀማለን
በመጀመሪያ ቴሌግራም እንከፍታለን ከዛ ከላይ
በቴሌግራሙ ጫፍ ላይ የለወን ሦስት መሰመር እንነካለን ከዛ ይህችን ምልክት ይንኩ ( v ) ከዛ new account ይለናል ከዛ መክፈት

✅6ኛ :- በተላይ ማታ ማታ ስንጠቀም ዓይናችን እንደይጎዳ ቴሌግራማችን በጥቁር መልክ እንድሆን ከፍለግን dark ,, black ,, colour እንድትሆን ከፈለግን ...
በመጀመሪያ ቴሌግራም እንከፍታለን ከዛ የቴሌግራም ጫፈ ላይ የለወን ሦስት መሰመር እንነካለን ከዛ chat setting ላይ ገብተን ከምሰጠን የመልክ ምርጫ የፍለግነዉን እንመርጣለን ::

✔7ኛ :- ቴሌግራም የሉ ፅፎች አልነበብ እየሎት ተቸግረዋል ማለት ፍደሎችሁ አንሰዉ ለዓይን አልተይ ከለ ፍደሎቹሁን ትልቅ ማድረግ ይቻላል እንዴት ?
አዎ በመጀመሪያ ቴሌግራም እንከፍታለን ከዛ በቴሌግራም ጫፍ ላይ ያለውን ሦስት መሰመር እንነካለን ከዛ chat setting ላይ እንገባለን ከዛ message text size የምል አለ እሱን እንነካና የፍለግነዉን ያህል ትልቅ ማድርግየ ይቻላል ::

✔8ኛ:- እንዴት የራሳችንን የቴሌግራም ቻናል መክፈት እንችላለን ?
በመጀመሪያ ቴሌግራም እንከፍታለን
ከዛ በቴሌግራም ጫፈ ላይ ያለውን ሦስት መሰመር እንነካለን ከዛ New channel የምለውን ነክተን create new channel የምለውን እንነካለን ከዛ እኛ ለመክፈት የፍለግነዉን የቻናል ስም እናስገባለን ::

✔9ኛ :- እንዴት የራሳችንን የቴሌግራፍ ጉሩፒ እንከፍታለን ?
በመጀመሪያ ቴሌግራም እንከፍታለን ከዛ ከላይ የለዉን ሦስት መሰመር እንነካለን ከዛ new group የምለውን እንነካለን ከዛ create new groupጠ የምለዉን እንነካለን ከዛ እኛ ለመክፍት የፍለግነዉን የጉሩፒ ስም እናስገባለን ::

✔10ኛ :- እንዴት አድርገን profile photo መቀየር እንችላለን ?
በመጀመሪያ ቴሌግራም እንከፍታለን ከዛ ከላይ ያለዉን ሦስት መሰመር እንነካለን ከዛ setting ላይ እንገባለን ከዛ set profile photo የምለውን በመንካት የፍለግነዉን ፎቶ መቀየር ይቻላል ።