Mosaic Technologies
29 subscribers
11 photos
7 links
Download Telegram
to view and join the conversation
Channel created
Channel photo updated
የሰውን አንጎል ከማሽን ጋር የሚያገናኘው መሣሪያ!

ኤለን መስክ የሰው ልጆች አንጎል ላይ ምርምር በሚያደርገው ኒውራሊንክ በተሰኘው ተቋሙ የሰው ልጆችን አንጎል ከማሽን ጋር ቀጥታ ግንኙነት እንዲኖረው የሚያስችል አሠራርን ሊያሳይ መሆኑ ተነግሯል።

ኤለን የሚያሳየው ሂደት ሰዎች በአዕምሯቸው ስልክ ወይም ኮምፒውተር የሚቆጣጠሩበት ነው። እንደ እርሱ ገለጻ ከሆነ የረዥም ጊዜ እቅዱ ለሰው ልጆች ላቅ ያለ ብቃት መስጠት ነው።

ሰዎች፤ ከሰው ሰራሽ ክህሎት (አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ) ጋር መተሳሰር እንዳለባቸው የሚያምነው ኤለን ይህም ሰው ሰራሽ ክህሎት ከሰው ልጆች በልጦ ሰዎችን እንዳያጠፋ ይረዳል ሲል ያስረዳል።

ተቋሙ እየሠራው ያለው መሣሪያ ከ3,000 በላይ ኤሌክትሮዶች የያዘ፣ ከሰው ልጅ ጸጉር የቀጠነ ገመድ ጋር የተያያዘም ነው። መሣሪያው ከ 1,000 በላይ ኒውሮኖችን ማንቀሳቀስ ይችላል።

አምና ከተቋሙ የወጣ መግለጫ እንደሚጠቁመው በመሣሪያው ኮምፒውተርን በአንጎል መቆጣጠር እንዲቻል ዝንጀሮዎች ላይ ሙከራ ተደርጎበታል።

የፒትስበርግ ዩኒቨርስቲ ተባባሪ ፕሮፌሰር ጄኔፈር ኮሊንገር፤ ኤለን እየሞከረ ያለው ነገር ለሕክምና ቴክኖሎጂ አስተዋጽኦ የሚያበረክት ይሆናል። ሆኖም ግን በቴክኖሎጂ ውጤት ሕክምናን የሚያግዝ መሣሪያ ለመሥራት ጊዜ እንደሚወስድ ይጠቅሳሉ።

መረጃውን ከ#BBC አግኝተነዋል ዝርዝር መረጃዎችን እንዲሁም ስለ አሰራሩ በቅርቡ የምናደርሳችሁ ይሆናል፡፡

ለውጤታማነቶ አብረን እንሥራ!
Mosaic Technologies
🌐 Mosaictech.net
📱 +251 92 089 6435
"ሲም ቦክስ"

ኢትዮጵያ በቴሌኮም ማጭበርበር ጉዳት ከሚደርስባቸው ሀገራት አንዷ ናት። በተለይ ከውጭ ሀገራት የሚደወሉ ስልኮች ሲም ቦክስ በሚባለው በአንድ ጊዜ እስከ 720 የሚደርሱ ሲም ካርዶችን በሚወስደው መሳሪያ አማካኝነት ጉዳቱ ይደርሳል።

ሲም ቦክስ የተባለውን መሳሪያ የሚጠቀሙት እዚሁ ሀገር ውስጥ ያሉ ግለሰቦች ሲሆኑ ከውጭ የሚመጡ ጥሪዎችን ከኢንተርኔት ጋር በማገናኘት በሀገር ውስጥ ቁጥር እንዲደርስ ያደርጋሉ። ይህም ቴሌ ከውጭ ከሚደውሉ ሰዎች ማግኘት የነበረበትን ገቢ በማሳጣት በሀገር ውስጥ መደበኛ ታሪፍ ብቻ ገቢው እንዲወሰን ያደርገዋል።

ከዚህም በተጨማሪ ኢትዮ ቴሌኮም ባልተጠቀመበት ሁኔታ በርካታ ዶላሮችን ይከፍላል። ይህም የውጭ ምንዛሬ ብክነትን ያስከትላል። በተለያዩ አጋጣሚዎች እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ 20 ሚሊዮን የሚጠጉ ሲም ካርዶች የማን እንደሆኑ አይታወቅም። ይህም ጉዳቱን አባብሶታል።

🌐 www.mosaictech.net

@MosaicTechEth
አዲስ የአማርኛ ፕሮግራሚንግ ቋንቋ ፡ ቡና ስክሪፕት!

ቡና ስክሪፕት ፡ አዲስ የአማርኛ ፕሮግራሚንግ ቋንቋ ነው፡፡ ጃቫ ስክሪፕትና(JavaScript) ታይፕ ስክሪፕትን( TypeScript) ሙሉ በሙሉ በአማርኛ ለመጻፍ የሚያስችል አዲስ የፕሮግራሚንግ ቋንቋ ነው፡፡ፕሮግራሞችን በማንኛውም የዓለም ቋንቋ መጻፍ ያስችላል፡፡

በቡና ስክሪፕት ፣ በአማርኛ የጻፈው ፕሮግራም ፣ የትኛውም ኮምፒውተር ላይ ( ዊንዶውስ፣ ማክ፣ ሊነክስ እና የተለያዩ ስልኮች ላይ ) ያለምንም ችግር ይሰራል ( run ያደርጋል) ፡፡

ኮዱን በሚጽፉ ግዜ፣ ስለያንዳንዱ ፈንክሽኖች፣ ሜትዶች፣ እና ወዘተ ሙሉ ድጋፍ እዛው በአማርኛ ያገኛሉ፡፡ ቡና ስክሪፕት የተሰራው ፤ማንኛውንም የፕሮግራሚንግ ቋንቋ በማንኛውም የተፈጥሮ ቋንቋ ለመጻፍ በሚያስችል በአሜሪካ ያምሮዊ ጥበቃ ሂደት( patent pending) ላይ ባለ የፈጠራ ሀሳብ ነው፡፡

ከፍተኛ የፕሮግራሚንግ ጽንሰ ሀሳቦች እንደ object oriented concept( ቁስ መር) ፣ Machine learning ( አውታር ስልጠና) መስራት/ ለመጻፍ ያስችላል፡፡

ምንጭ፡- ze Addis

🌐 http://www.mosaictech.net

@MosaicTechEth
በኢትዮጵያ ትልቅ ጎብኚ ያላቸው ድረ ገጾች፦

1. hulusport.com
2. habeshabets.com
3. axumbet.com
4. betika.et
5. qefira.com
6. ethiojobs.net
7. bet251.net
8. ethiotelecom.et
9. ethiopianairlines.com
10. vamos.bet

Source - SimilarWeb/shegahq

🌐 http://www.mosaictech.net

@MosaicTechEth
የሶሻል ሚዲያ ካለኝ ዌብሳይት ምን ይጠቅመኛል?

ይህ በርካታ ሰዎች የሚያነሱት ጥያቄ ነው፡፡ ይህንን ጥያቄ በሦስት አመክንዮዎች እንመልከታቸው፡፡

1. የድርጅቶን አጠቃላይ ገጽታ ሶሻል ሚዲያ ሊገልጽሎት አይችልም፡፡

ድርጅቶ የሚያመርተው ምርት ወይም የሚሸጠው እቃ አልያም የሚሰጠው አገልግሎት በሶሻል ሚዲያ ሙሉ ለሙሉ ሊገለጽ አይችልም፡፡

የድርጅቶ ቢሮ፣ የድርጅቶ ብራንዲንግና የተሰናሰለው አገልግሎቶን የሚያሳዩት በራሶት ዌብሳይት ነው፡፡

በአጠቃላይ ዌብሳይት ማለት ቢሮ(መሸጫ ቦታዎ) እንደማለት ሲሆን ሶሻል ሚዲያዎ ይህንን ቢሮዎትን ለማስተዋወቅ የሚረዳዎት ነው፡፡

2. ደንበኛዎን (ተገልጋዮን) ይበልጥ የሚያቀርቡበት መንገድ ነው

ደምበኛዎ(ተገልጋዮ) ስለ እርሶ ይበልጥ ማወቅ ካሻው መጀመሪያ እርሶን በየ በይነ መረቡ ላይ ይፈልጎታል፡፡ በቀላሉ የሚያገኞት ከሆነ የተሻለ ተወዳዳሪ ይሆናሉ ማለት ነው፡፡

ደምበኛዎን ተገቢውን መረጃ ከዌብሳይቶ ካገኘ በቀላሉ በአድራሻዎት ያገኞታል፡፡ ይህ ደንበኛዎን(ተገልጋዮን) ይበልጥ ወደ እርሶ ያቀርበዋል፡፡

3. በደንበኛዎ(ተገልጋዮ) የሚያገኙት አምነት ይጨምራል

በሦሻል ሚዲያ በርካታ እርሶን የሚመስል፣ የእርሶን አይነት አገልግሎት የሚሰጥ ብዙ ይገኛል ከእነዚህ ውስጥ ለመመረጥ ዌብሳይቶ የማይተካ ሚና ይጫወታል፡፡ ከሌሎች አንጻር እርሶ ዌብሳይት ስላሎ የተሻለ ምርቶን ያስተዋውቃሉ፡፡ የተሻለ እምነትም በደንበኛዎ ዘንድ ያገኛሉ፡፡

🌐 http://www.mosaictech.net

@MosaicTechEth
Forwarded from Et-Menu