አእምሮን ማነፅ 🧠 Mind Programming
229 subscribers
1 photo
3 videos
18 links
Download Telegram
ጠንካራ ስብዕና መገንባት የሚፈልግ ሰው ራሱን አንድ ነገር ማለማመድ አለበት፤ ሰዎች መጥፎ ፊት መጥፎ አስተያየት ቢሰጡት እንኳን ችግራቸው ከኔ ጋር ነው ብሎ ማሰብ የለበትም።

እንደዛ ብሎ የማያስብ ሰው የሚፈልግበት ለመድረስ ማንም አያቆመውም! ምክንያቱም ሰዎች በፈለጉት መንገድ ቢያስቡት፣ ቢንቁት ወይ ቢሰድቡት አይሞቀው አይበርደው ትልቁን ስዕል እያየ ወደ ከፍታው ይገሰግሳል።

https://t.me/MindProgramingPart1 🧠
መቼም የማትረሳውን የህይወት ትምህርት የምትማረው ከትልቁ ስህተትህ ነው፤ ብዙም አትናደድ በቀሪው ዘመንህ እንዳትረሳው የተፈለገ ወሳኝ መልዕክት ስላለ ከዛ ስህተትህ ልብህኝ ከፍተህ ተማርበት።

https://t.me/MindProgramingPart1🧠
እልህ ይዞህ ያውቃል? የሚንቁህና የበታችነት እንዲሰማህ የሚያደርጉህ ሰዎች ህይወትህን የቀን ጨለማ አድርገውት ያውቃሉ አይደል?

እሳትን ስትፈልግ ንብረት ለማውደም ትጠቀምበታለህ ስትፈልግ ደግሞ ምግብ ታበስልበታለህ፤ ታዲያ ለናቁህ ሰዎች ማንነትህን ለማሳየት ጠንክረህ ሰርተህ በስኬትህ የያዘህን እልህ ለምን አትወጣም?! የምድራችን ጣፋጭ በቀል በናቁህ ፊት የሚያስከብር ስኬት መጎናፀፍ ነው!

https://t.me/MindProgramingPart1🧠
😎 'ሁሉም ጥሩ ይሆናል' የሚል ጥቅስ ሰምተን ይሆናል ግን ሁሉን ጥሩ የምናደርገው እኛ ነን፤ ቀንህ ጥሩ እንዲሆን ከፈለክ ከእንቅልፍ እንደተነሳህ እነዚህን 2 ነገሮች ሁሌም አድርጋቸው።

1. ከአልጋህ ሳትወርድ ፈጣሪህን በማመስገን ጀምር ፤ አሁን የሌለህን ሳይሆን በጣም የሚያስደስትህን ከፈጣሪ የተሰጠህን 5 ነገሮች እየጠራህ አመስግን።

2. እህቴ ከእንቅልፍ እንደተነሳሽ አመሰገንሽ አይደል? ከዛ ቀንሽ ያማረ የሚሆነው ምን ብሰሪ የት ብትሄጂ ከማንጋር ብታሳልፊ እንደሆነ በአይምሮሽ ውሎሽን አስቢው፤ ይሄን እንዳደረግሽ ቀንሽን ጀምሪው።

ዛሬ ወይም ነገ ብቻ ሳይሆን ሁሌም አድርገው! አድርጊው! ደስተኛ መሆን የሚፈልግ ሰው ተግባር እንጂ ሁሉም ጥሩ ይሆናል እያለ ደጅ ደጁን አያይም።

https://t.me/MindProgramingPart1🧠
💧 ወዳጄ የምትሰራውን ስራ የምታከብረው ከሆነ እሱም መልሶ ያከብርሀል፤ የምትፈልገው ከፍታ ላይ ያስቀምጥሀል፤ ስትንቀው ደግሞ ህይወትህን አሰልቺ አርጎ ባለህበት ያስቀርሀል።
እህቴ ለስራሽ ለትምህርትሽ የምትሰጪው ቦታ የህይወት መዳረሻሽን ይወስነዋል፤ ስለዚህ በስራዬማ ቀልድ የለም ማለት አለብሽ እንደሱ ካላልሽ እሱም መልሶ በኑሮሽ ላይ ይቀልድብሻል።
ስኬታማ ሰዎች ከኛ የሚለዩት ለሚሰሩት ስራ በሚሰጡት ክብር ነው! ጂም ሮን 'ህልምህን ከእውነቱ ጋር የምታስታርቀው በዲስፕሊን ብቻ ነው' ይለናል።

https://t.me/MindProgramingPart1🧠
🦟 አንዲት ዝንብ ከቤት ለመውጣት ፈልጋ ዝግ ከሆነ መስኮት ጋር ደጋግማ ብትጋጭ ይሳካላታል እንዴ? ወይ ተዓምር ተፈጥሮ መስኮቱን ሰንጥቃው ካሎጣች በስተቀር መውጣት አትችልም፤ ይሄኔ ትንሽ ዞር ዞር ብትል እኮ ክፍት በር ይኖራል እሷ ግን አሁንም እየደጋገመች ከመስኮቱ ጋር ትጋጫለች። ይህቺ ዝንብ ጠንክራ ብትሰራም ጠንክራ ስላላሰበች ከቤት ውስጥ መውጣት አልቻለችም!

ወዳጄ ያንተም ችግር ጠንክሮ ከመስራት ሳይሆን ትክክለኛውንና የምትወደውን ስራ ካለማሰብህ ይሆናል አየለፋህ ምንም ጠብ ያላለወ። እህቴ ጥረትሽን ባደንቅም ለትክክለኛውና ለምትወጂው ሙያ አስበሽ እየለፋሽ ካሎነ እንደ ዝንቧ ከመስኮቱ ጋር እየተጋጨሽ እንደሆነ አስቢ።
(ከዳዊት ድሪምስ 'ትልቅ ህልም አለኝ' መፅሀፍ የተወሰደ ሀሳብ)
https://t.me/MindProgramingPart1🧠
🧣 ስኬታማ የሆነውንም ያልሆነውንም እኩል የሚያመሳስላቸው አንድ ነገር አለ፤ ሁለቱም ተመሳሳይና አሰልቺ ነገር መስራት ይጠላሉ፤ ልዩነታቸው ግን ስኬታማዎቹ እያስጠላቸው እየመረራየው ከባዱን ስራ ይሰሩታል። ሰነፎቹ ደግሞ ሰልችቷቸው ያቆሙታል። ወዳጄ ለውጥ እኮ ከባድ ነው! ቀላል ቢሆንማ ሁሉም ያደርገው ነበር። ጥቂቶች ብቻ በኑሯቸው ደስተኛና ስኬታማ የሚሆኑት ከባዱን ነገር ለመስራት ራሳቸውን ስለሚያሳምኑ ነው። ዳይ ወደ ስራ!

https://t.me/MindProgramingPart1🧠
💪የሚተቹህን የሚንቁህን አጎንብሰህ እለፋቸው፤ የጥረትህ ፅዋ ሞልቶ ስትለወጥ የናቁህን ታስገርማለህ! ስኬት ምን እንደሆነ ታስተምራቸዋለህ!
የምትፈልገውን የምታገኝበት ጊዜ ሩቅ ይመስልሀል እንጂ ቅርብ ነው፤ ልፋትህን ያቆምክ ዕለት ግን ትችታቸውና ንቀታቸው ልክ እንደሆነ እያረጋገጥክ እንደሆነ አስብ!

https://t.me/MindProgramingPart1🧠
🧤በህይወት ውስጥ ከባዱ ነገር መሳሳት አይደለም፤ ለማስተካከል ምንም አለማድረግ ነው። ችግሩ ትላንት የገጠመን አስጠሊታ ነገር አይደለም ግን ካለፈው ምንም አለመማር ነው።
ሁሌም ለምን ተሳሳትኩ ማለት የለብንም፤ ግን ደግሜ እንዳልሳሳት ምን ላድርግ ማለት ነው ያለብን፤ አሁንም ደግመን ብንሳሳት ምን እማርበታለው ማለት ነው ያለብን፤ ለዚች አጭር እድሜማ ስህተት ሰራሁ ብለን አንተክዝም!

https://t.me/MindProgramingPart1🧠
ውሃ በተሞላ ድስት ውስጥ አንዲት እንቁራሪት ብንጨምርና ከዚያም ውሃውን ማፍላት ብንጀምር፤ ውሃው እየፈላ በሄደ ቁጥር እንቁራሪቷም የሰውነት ሙቀቷን ማስተካከል ትጀምራለች፡፡

☞ የውሃው ሙቀት ከፍተኛ እየሆነ ሲሄድ እሷም የሰውነቷን ሙቀት በዛው ልክ ማስተካከሉን ትቀጥላለች፡፡ የውሃው ሙቀት ጨምሮ የመፍላት ነጥብ (boiling point) ላይ ሲደርስ ግን ማስተካከል የማትችልበት ደረጃ ስለደረሰ እሯሷን ለማዳን ከድስቱ ዘላ ለመውጣት ትፈልጋለች ትሞክራለች፤ ግን ዘላ መውጣት አቅም አይኖራትም አትችልም፡፡
ምክንያቱም ያላትን አቅም ሁሉ ሙቀቷን በማስተካከል የውሃውን ቃጠሎ ለመከላከልና ለመላመድ ባደረገችው ተጋድሎ ጨርሳዋለችና፤ ወዲያው ትሞታለች፡፡

እንቁራሪቷን ምን ገደላት?
አብዛኞቻቸችን የፈላ ውሃ እንል ይሆናል፤ እውነታው ግን ይህ አይደለም ፡፡ እንቁራሪቷን የገደላት የፈላው ውሃ ሳይሆን መች መዝለል እንዳለባት የመወሰን አቅም ማጣቷ ነው፡፡

አብዛኞቻችን ከሰዎችም ይሁን ከነገሮች ጋር ያለንን ነገር ለማስተካከልና ለመላመድ እንሞክር ይሆናል፤ ግን እስከ መቼ ማስተካከል እንዳለብንና መች መወሰን እንዳለብን ማወቅ ይሳነናል፡፡
አንዳንዴ ነገሮችን የለመድናቸውና ለኛ የማይጎዱ መስለው ይታዩናል፤
በመጨረሻው ቅፅበት ግን እንዳልለመድናቸው ቢገባንም
ማምለጥና መውጣት የማይቻለን ሰአት ይሆናል፡፡ በጥፋት/ወንጀል/ መንገድ ውስጥም ስንሆን እንዲሁ ነው፤ ትንሹን ወንጀል እንለምደዋለን የሚጎዳን አይመስለንም፤ ደስታ ውስጥ ያለን ይመስለናል፤ ደስታው ሙቀት ይፈጥርልናል፡፡ ሙቀቱ ወደ እሳት የተቀየረ ጊዜ ግን . . .!!!??

ከሙቀቱ መውጣት ካልቻልን ከእሳት እንደማንወጣ እውን ነው!
ሙሉ አቅም ባለን ጊዜ እንዝለል!!!

https://t.me/MindProgramingPart1🧠
🧣ህልምህን ማንም አልሰጠህም ስለዚህ ማንም አይነጥቅህም! ከፈጣሪ የተሰጠህን መርምረህ ማወቅ ብቻ ነው የሚጠበቅብህ፤ ያወክ ዕለት ሌሎች ካንተ ቀድመው ያሳኩበትን መንገድ ትኮርጅና እየወደክ እየተነሳህ ወደ ስኬት ተራራህ ትወጣለህ።

https://t.me/MindProgramingPart1🧠