ውሃ በተሞላ ድስት ውስጥ አንዲት እንቁራሪት ብንጨምርና ከዚያም ውሃውን ማፍላት ብንጀምር፤ ውሃው እየፈላ በሄደ ቁጥር እንቁራሪቷም የሰውነት ሙቀቷን ማስተካከል ትጀምራለች፡፡
☞ የውሃው ሙቀት ከፍተኛ እየሆነ ሲሄድ እሷም የሰውነቷን ሙቀት በዛው ልክ ማስተካከሉን ትቀጥላለች፡፡ የውሃው ሙቀት ጨምሮ የመፍላት ነጥብ (boiling point) ላይ ሲደርስ ግን ማስተካከል የማትችልበት ደረጃ ስለደረሰ እሯሷን ለማዳን ከድስቱ ዘላ ለመውጣት ትፈልጋለች ትሞክራለች፤ ግን ዘላ መውጣት አቅም አይኖራትም አትችልም፡፡
ምክንያቱም ያላትን አቅም ሁሉ ሙቀቷን በማስተካከል የውሃውን ቃጠሎ ለመከላከልና ለመላመድ ባደረገችው ተጋድሎ ጨርሳዋለችና፤ ወዲያው ትሞታለች፡፡
እንቁራሪቷን ምን ገደላት?
አብዛኞቻቸችን የፈላ ውሃ እንል ይሆናል፤ እውነታው ግን ይህ አይደለም ፡፡ እንቁራሪቷን የገደላት የፈላው ውሃ ሳይሆን መች መዝለል እንዳለባት የመወሰን አቅም ማጣቷ ነው፡፡
አብዛኞቻችን ከሰዎችም ይሁን ከነገሮች ጋር ያለንን ነገር ለማስተካከልና ለመላመድ እንሞክር ይሆናል፤ ግን እስከ መቼ ማስተካከል እንዳለብንና መች መወሰን እንዳለብን ማወቅ ይሳነናል፡፡
አንዳንዴ ነገሮችን የለመድናቸውና ለኛ የማይጎዱ መስለው ይታዩናል፤
በመጨረሻው ቅፅበት ግን እንዳልለመድናቸው ቢገባንም
ማምለጥና መውጣት የማይቻለን ሰአት ይሆናል፡፡ በጥፋት/ወንጀል/ መንገድ ውስጥም ስንሆን እንዲሁ ነው፤ ትንሹን ወንጀል እንለምደዋለን የሚጎዳን አይመስለንም፤ ደስታ ውስጥ ያለን ይመስለናል፤ ደስታው ሙቀት ይፈጥርልናል፡፡ ሙቀቱ ወደ እሳት የተቀየረ ጊዜ ግን . . .!!!??
ከሙቀቱ መውጣት ካልቻልን ከእሳት እንደማንወጣ እውን ነው!
ሙሉ አቅም ባለን ጊዜ እንዝለል!!!
https://t.me/MindProgramingPart1🧠

🧣ህልምህን ማንም አልሰጠህም ስለዚህ ማንም አይነጥቅህም! ከፈጣሪ የተሰጠህን መርምረህ ማወቅ ብቻ ነው የሚጠበቅብህ፤ ያወክ ዕለት ሌሎች ካንተ ቀድመው ያሳኩበትን መንገድ ትኮርጅና እየወደክ እየተነሳህ ወደ ስኬት ተራራህ ትወጣለህ።
https://t.me/MindProgramingPart1🧠
https://t.me/MindProgramingPart1🧠
🔑ጥግ ድረስ ለመደሰት የምትፈልገው ሁሉ መሳካት የለበትም፤ እንደዛ የሚያስብ ሰው የዋህ ነው። እህቴ ልብሽ በደስታ እንዲሞላ ነገሮች ሁሉ በምትፈልጊው መንገድ መሄድ አይጠበቅባቸውም፤ ለዛሬዋ ቀን ያልረሱም አሉ፤ እድለኛ ነሽ ያለፈውን ማስተካከል ባትችዪ ነገን ማሳመር ተቸይሻለሽ። ከምንም ነገር በላይ አንድ ነገር ማስታወስ አለብን 'እጃችን ላይ ያለው ዛሬ ነው! ዛሬን ከመደሰት ውጪ ሌላ አማራጭ የለንም!'
https://t.me/MindProgramingPart1🧠
https://t.me/MindProgramingPart1🧠
🧤ህይወትህን ከዓላማህ ጋር አጣብቀው፤ ከሰዎች ጋር አይደለም፣ ከሰበሰብከው ሀብት ወይ ከሁኔታዎች ጋር አይደለም፤ ከአላማህ ጋር አጣብቀው! ምክንያቱም ሰዎችና ሁኔታዎች በጊዜ ሂደት ይቀየራሉ እንዳስቀመጥን ላናኛቸው እንችላለን፤ አላማችን ግን ማንም የማይነካው የማይነቀነቅ ግንብ ስለሆነ እሱን ለማሳካት መኖራችን ራሱ ደስታ ይፈጥርልናል።
ጥያቄው "የመኖርህን አላማ ታውቀዋለህ? ታውቂዋለሽ?" ነው። ካላወቅነው ግን ቢያንስ ማሰብ መጀመር አለብን።
https://t.me/MindProgramingPart1🧠
ጥያቄው "የመኖርህን አላማ ታውቀዋለህ? ታውቂዋለሽ?" ነው። ካላወቅነው ግን ቢያንስ ማሰብ መጀመር አለብን።
https://t.me/MindProgramingPart1🧠
💧አንድ ቀን ባለፈ ቁጥር ለፍፃሜ ቀናችን አንድ እርምጃ እየቀረብን ነው፤ አስቡት ቀኑን በጭንቀት ወይ ምንም በማይጠቅመን ካሳለፍነው ደግሞ ደግመን የማናገኘውን ሀብት ሜዳ ላይ እየበተነው ነው። መቼ እንደምናልፍ ስለማናውቅ ለፍፃሜያችን በጣም እየቀረብን እንደሆነ አስበን በሙሉ አቅማችን መስራት፣ ህይወትን ያለጭንቀት ማጣጣም አለብን! ወዳጄ መቼም ይሄን ወርቃማ ጊዜ ማንም ደግሞ አይሰጥህም፤ የዛሬ 50 አመት ወይ አቅም አንሶህ አርጅተሀል ወይ ደግሞ አልፈሀል...ይሄንን አስብና ያኔ እንዳይቆጭህ ማድረግ ያለብህን ሁሉ አድርግ።
https://t.me/MindProgramingPart1🧠
https://t.me/MindProgramingPart1🧠
ሁልጊዜም ስንፍና ሲሰማን 'አይ የኔ ነገር' ብለን ተስፋ ከመቁረጥ ይልቅ፤ በጣም ቀላል ብለን ከምንንቃት ስራ እንጀምር። ለምሳሌ የግድ መፃፍ ያለብን ሪፖርት ወይ ደግሞ የቤት ስራ (Assignment) ቢኖር ወረቀትና እስኪሪቢቶ የምንሰራበት ጠረጴዛ ላይ በማስቀመጥ እንጀምር፣ ከዛ የፈለገ ስንፍና ቢሰማን እንኳን አይምሯችን 'ኸረ ጠረጴዛ ላይ ያስቀመጥከውን ወረቀትና እስኪሪቢቶ ለመቼ ነው? ስራ እንጂ..' እያለ አላስቀምጥ ይለናል፤ ያኔ አንድ የሆነ ሞራል የሚሰጠን ነገር እንዳገኘን ተሰምቶን ስራውን እንጀምራለን። እንጂ ስንፍና የኛ ብቻ የግል ፀባይ እንደሆነ ማሰብ የለብንም የመጠን ልዩነት ነው እንጂ ሁሉም ሰው የሆነ ነገር ለማድረግ ይሰንፋል ወይ እያመነታ ጊዜው ይነጉዳል።
https://t.me/MindProgramingPart1🧠
https://t.me/MindProgramingPart1🧠
እኔኮ ከሰማይ ከፍታ ብታይ ነጥብ እንኳን የማልሸፍን ፍጡር ነኝ! የኔ መኖር የኔ አለመኖር ለዚች ምድር ምንም የሚቀይረው ነገር የለም! የሚል ስሜት የሚሰማህ ከሆነ መሬት የምትባለው ግዙፍ መስላ የምትታየን መኖሪያችን ራሱ ከአጠቃላይ አለም ምን ያህል ትንሽ እንደሆነች ከስዕሉ ማየት በቂ ነው።
በዚህ አለም ስትኖር አመንክም አላመንክም አንተ የምታስፈልጋቸው ብዙ ሰዎች አሉ፤ እህቴ ያንቺ መኖር የሚያስፈልጋቸው ብዙ ሰዎች አሉ፤ ሲከፋን ግን እኔኮ ምንም አልጠቅምም እንልና ራሳችንን አቅልለን እናያለን። ወሳኙ ነገር በብዙ ሰው ተፈላጊ መሆን አይደለም፤ ለምናስፈልጋቸው ጥቂት ሰዎች ብርሀን መሆን ነው! የኛ መኖር ብቻ ለነሱ ብርሀን ነው፤ የኛ መከፋት ማዘንና ተስፋ መቁረጥ ለነሱ ጨለማ ነው።
https://t.me/MindProgramingPart1🧠
በዚህ አለም ስትኖር አመንክም አላመንክም አንተ የምታስፈልጋቸው ብዙ ሰዎች አሉ፤ እህቴ ያንቺ መኖር የሚያስፈልጋቸው ብዙ ሰዎች አሉ፤ ሲከፋን ግን እኔኮ ምንም አልጠቅምም እንልና ራሳችንን አቅልለን እናያለን። ወሳኙ ነገር በብዙ ሰው ተፈላጊ መሆን አይደለም፤ ለምናስፈልጋቸው ጥቂት ሰዎች ብርሀን መሆን ነው! የኛ መኖር ብቻ ለነሱ ብርሀን ነው፤ የኛ መከፋት ማዘንና ተስፋ መቁረጥ ለነሱ ጨለማ ነው።
https://t.me/MindProgramingPart1🧠
💧አንዳንዴ እኮ ምንም ሳይጎድለን ትዕግስት ማጣት ብቻ ባለንበት ያስቀረናል። ይቺ አለም ትንፋሹን ዋጥ አርጎ ለረጅም ጊዜ የቆየ የሚያሸንፍባት መድረክ ናት። ለምሳሌ መዝናናት ፈታ ማለት እያማረህ ግን ቆይ እስኪ ዛሬ ይለፈኝ ማለት ከጀመርክና ያን ጊዜ ለሚጠቅምህ ነገር ከተጠቀምከው አትጠራጠር ትክክለኛው መንገድ ላይ ነህ። ያ ተከታታይ ድራማ ዛሬ ይለፈኝና ስራ ልስራ ማለት ከጀመርሽ ለውጡን በቅርቡ ታዪዋለሽ። ትዕግስት ማለት ገንዘብ አውጥቶ ፈታ ማለት ያምርህና ግን ለምን አንደኛዬን ጥሩ አቅም ሲኖረኝ አልዝናናም ብሎ ወጥሮ መስራት ነው።
https://t.me/MindProgramingPart1🧠
https://t.me/MindProgramingPart1🧠
አመለካከት ቀላል የሚመስል ግን ልዩነት ፈጣሪ ነገር ነው፤ በዚህ አለም ታሪክ የገዘፈ ቦታና ስኬት ላይ የደረሱ ሰዎች ከኛ የተለየ ስጦታ አልተሰጣቸውም ግን ከኛ በተለየ መንገድ ችግሮችን እንደ ጥሩ እድል ይጠቀሙባቸዋል።
ከደሀ ቤተሰብ የተወለዱ ሁለት ሰዎች እንዲህ ሊያስቡ ይችላሉ። አንዱ "በቃ የሆነ ነገር በግሌ እንዳልሰራ ቤተሰቦቼ አቅም ስለሌላቸው ወይ ደግሞ ደህና ዘመድ ስለሌለኝ የትም አልደርስም።"
ሁለተኛው "ከድሀ መወለዴ ችግርን መቋቋም እንድችልና የትኛውንም ፈተና እንዳሸንፍ ጥንካሬ ሆኖኛል" ብሎ ለስኬቱ እንደመሰላል ይጠቀምታል።
አስቡት ሁለቱም የገጠማቸው ተመሳሳይ ችግር ቢሆንም የአመለካከት ልዩነት ግን አንዱን ከፍ አርጎ እላይ ይሰቅለዋል አንዱን ባለበት ያስቀረዋል።