♨️አንድ ጊዜ አንድ ወጣት ወደ ቡድሃ ቀርቦ ፦
“በህይወቴ በጣም ተቸግራለሁ፣ እባክህ ከዚህ ችግር ለመውጣት መፍትሄውን ንገረኝ” አለው።
ቡድሃ እንዲህ አለ፡- “አንድ እፍኝ ጨው በአንድ ብርጭቆ ውሃ ውስጥ ጨምረው እና ጠጣው…” ወጣቱም እንዲሁ አደረገ።
"እንዴት ነው ጣዕሙ?" ቡድሃ ጠየቀ።ወጣቱም፦ "በጣም መጥፎ እና በጣም ጨዋማ " አለ ምራቁን እየተፋ።
ቡድሃ ፈገግ አለና “በድጋሚ አንድ እፍኝ ጨው በእጅህ ይዘህ ተከተለኝ"አለው። ሁለቱም ቀስ ብለው ወደፊት መሄድ ጀመሩ እና ጥቂት ርቀት ከተጓዙ በኋላ በጠራ እና ንፁህ በሆነ ውሃ በተሰራ ሀይቅ ፊት ለፊት ቆሙ።
“ና፣ አሁን ይህን ጨው በውሃ ውስጥ አኑረው” በማለት ቡድሃ አዘዘ። ወጣቱም እንዲሁ አደረገ።
"አሁን የዚህን ሀይቅ ውሃ ጠጣ"አለ ቡድሃ። ወጣቱ ውሃ መጠጣት ጀመረ፣ አሁንም ቡድሃ “ጣዕሙ እንዴት እንደሆነ ንገረኝ፣ አሁንም ጨዋማ ሆኖ አገኘኸው?"ብሎ ጠየቀው።
"አይ ይህ ጣፋጭ ነው።በጣም ጥሩ ነው" አለ ወጣቱ
ቡድሃ ከወጣቱ አጠገብ ተቀምጦ እጁን ይዞ፦“የህይወት ችግር ልክ እንደ ጨው ነው፣ ብዙም ያነሰም አይደለም። በህይወት ውስጥ ያለው የችግር መጠን ተመሳሳይ ነው በትክክል ተመሳሳይ ነው።
ነገር ግን ምን ያህል ሀዘኑን ውስጣችንን መራር እንደሚያደርገው በምንቀመጥበት ዕቃ ላይ ይወሰናል።
ስለዚህ ስታዝን ማድረግ የምትችለው ብቸኛው ነገር እራስህን ትልቅ ማድረግ ነው።በብርጭቆ አትቆይ ችግር ህይወትን መራር ያደርገዋልና ፣ሐይቅ ሁን እራስህን ከችግሩ በላይ ጉዝፍ አድርግ።

👍6❤2
አንዲት ወጣት ሴት ሕይወቷ ምን ያህል ከባድ እንደሆነና ተስፋ መቁረጧን ለእናቷ እያማረረች ትነግራታለች።
እናት ልጇን ካዳመጠች በኋላ ምንም ቃል ሳትተነፍስ ወደ ኩሽና ትወሰዳትና ሶስት የብረት ድስቶችን አውጥታ ውሃ ሞላቻቸው። ከዚያም ድስቶቹን የኤሌትሪክ ምድጃ ላይ በመጣድ ውሃው በደንብ እንዲፈላ አደረገች።
በመጀመሪያው ድስት ውስጥ ካሮት ከተተችበት። በሁለተኛው እንቁላል፤ በመጨረሻው ድስት ውስጥ ደግሞ ተቆልቶ የተፈጨ የቡና ዱቄት ጨመረች።
ከ20 ደቂቃ በኋላ ምድጃውን አጠፋችና የተቀቀለውን ካሮት እና እንቁላል አውጥታ በአንድ ሳህን ውስጥ አስገባች። በአንድ ኩባያ ውስጥ ደግሞ የተወሰነውን የፈላ ቡና ስኒ ላይ ከሞላች በኋላ በልጇ ፊት አስቀምጣ ‘’ልጄ ምን ይታይሻል?’’ ስትል ጠየቀች።
ልጅቷም “ካሮት ፣ እንቁላል እና ቡና” ብላ መለሰች ።
እናትየዋ ጎድጓዳ ሳህኑን ወደ ሴት ልጇ ቀረብ አድርጋ ካሮቱን እንድትነካውና ምን እንደሚሰማት ጠየቀች።
ልጅቷም እንዲሁ አደረገች እና " ካሮቱ ይለሰልሳል " ብላ መለሰች።
ልክ እንደ ካሮቱ ሁሉ እንቁላሉን እንድትነካውና መስበር ከቻለች እንድትሰብረው ጠየቀቻት።
ልጅም እንዲሁ በማድረግ እንቁላሉ እንደጠነከረና ሊሰበር እንደማይችል አረጋገጠች።
በመጨረሻ እናት ልጇ አንድ ሲኒ ቡና እንድትጠጣ ጠየቀቻት። ቡናውን ከቀመሰች በኋላ ጥሩ ጣዕም እና መአዛ እንዳለው ነገረቻት።
ከዚያም ልጅቷ እናቷን ተመለከተችና "እናቴ ይህን ሁሉ ያደረግሽው ምን ልታሳይኝ ፈልገሽ ነው??" ብላ ጠየቀቻት።
እናት እንዲህ ስትል ገልጸችላት
“አየሽ ልጄ፤ እነዚህ ሶስት ነገሮች እያንዳንዳቸው ተመሳሳይ ችግር ገጥሟቸው ነበር። ነገር ግን ሶስቱም ለገጠማቸው ነገር የተለያየ ምላሽ ሰጥተዋል።
እንደምታይው ካሮቱ የፈላ ውሃው ውስጥ ከመግባቱ በፊት ጠንካራ ነበር ነገር ግን ከተቀቀለ በኋላ ለስላሳ እና ደካማ ሆነ።
በቀላሉ ተሰባሪ የነበረው እንቁላል ከተቀቀለ በኋላ ጠንካራና ደንዳና ሆነ።
በመጨረሻም ምንም ጣእም ያልነበረው የቡና ፍሬ ከተቆላና ከተፈጨ በኋላ በፈላ ውሃ ላይ ሲጨመር የውሃውን ጣእም ለወጠው።’’
ይህን ካብራራች በኋላ እናት ልጇን እንዲህ ስትል ጠየቀች፡
"አንቺ ከሶስቱ ውስጥ የትኛውን ነሽ? በህይወት ውስጥ ችግር ሲገጥምሽ ምን ምላሽ ትሰጪያለሽ?
እናት ቀጠለች:-
‘’ልጄ፤ ችግር ካጋጠመሽ በኋላ እንደ ካሮቱ ጥንካሬሽን ታጭያለሽ ወይስ እንደ እንቁላል ጠንካራ እና ደንዳና ትሆኛለሽ? እንደ ቡና ከሆንሽ በከፋ ደረጃ ውስጥ ስታልፊ ተሻሽለሽ በዙሪያሽ ያለውን ሁኔታ ወደ ጥሩ መአዛና ጣእም ትቀይሪዋለሽ።’’
ወቅቱ በጣም ጨለማ ሲሆንና ፈተናዎች/ተግዳሮቶች እየበዙ ሲመጡ እራሳችሁን ወደ ሌላ ደረጃ ከፍ ታደርጋላችሁ? መከራን እንዴት ትቋቋማላችሁ?
ካሮት ፣ እንቁላል ወይስ የቡና ፍሬ ነህ/ሽ

❤11👍1
ለፈገግታ 😁😁😁
ማሞ ለብቻው የ70 ዓመት እድሜ ሽማግሌ ነው። አንድ ቀን መንገድ በማቋረጥ ላይ እያለ አንዲት መኪና እያበረረች መጥታ አጠገቡ "ሲጢጢጢጢ" ብላ ትቆማለች።
ሽማግሌው ማሞ ለብቻው በመኪናዋ ከመገጨት ለጥቂት ይተርፋል።
መኪናዋን እየነዳች የነበረችዋ ሴት ሹፌርም በጣም ተናዳ ከመኪናዋ በመውረድ...
ሹፌር:-"ጋሼ ለምንድነው እያዩ የምይሄዱት?" ትለዋለች።
ማሞ ለብቻው:- "ኧረ ልጄ ስህተቱ እኮ ያንቺው ነው።" ብሎ ብእርጋታ ይመልስላታል።
ሹፌር፦"ስሙ አባቴ እኔ መኪና በማሽከርከር የ15 አመት ልምድ ያለኝ ሰው ነኝ! እንዴት ነው ያንቺ ጥፋት ነው የሚለኝ?" ብላ አሁንም በቁጣ ትመልስለታለች።
ማሞ ለብቻው:- ፈገግ እያል "ኧረ የኔ ልጅ እኔም በእግር የመጓዝ የ70 ዓመት ልምድ ያለኝ ሰው ነኝ!!!" 😀😀😛😛😀😀
ብሏት እርፍ!!!

❤21😁4
በዉስጥህ ያለዉን እምቅ አቅም ለማዉጣት ከሚጠቅሙህ ዉስጥ ጥቂቶቹ እንሆ...
1. የሕይወትህን ልጓም ጨብጥ : ለራስህ ደስታና ስኬት አንተ ኃላፊነት አለብህ። ስለዚህ የሕይወትህን ልጓም በመጨበጥ ወደፈለግክበት ቦታ የሚመሩህን ውሳኔዎች በራስህ ውሰድ።
2. ግልጽ ግቦችን አስቀምጥ : ልታሳካው የምትፈልገውን ነገር ለይተህ ግልጽ፣ ሊለካ የሚችል፣ ሊደረስበት የሚችል፣ ተዛማጅነት ያለውና ጊዜ የተቀመጠለት (SMART) ግቦችን አውጣ። ይህ ወደ ግብህ ለመድረስ ይረዳሃል።
3. አስተሳሰብህን ቀይር : ሃሳቦችህና እምነቶችህ እውነታህን ይቀርጻሉ። ስለዚህ የሚገድቡህን እምነቶች ቀይርና ግቦችህን ለማሳካት የሚረዳህን የዕድገት አስተሳሰብ ተጠቀም።
4. የማስፈንጠር ኃይልን ተጠቀም : ግቦችህና ማግኘት የምትፈልጋቸው ውጤቶች አሁን ተሳክተው እንዳለ አድርገህ በአእምሮህ አስፍንጥር። ይህ ትኩረትህን ለመጠበቅና ለመነሳሳት ይረዳሃል።
5. ከፍተኛ እርምጃ ውሰድ : ወደ ግቦችህ ለመድረስ እጅግ ከፍተኛና ወጥ የሆነ እርምጃ ውሰድ። ፍርሃት ወይም እርግጠኛ አለመሆን ወደኋላ እንዳይሉህ ፍቀድ።
6. ስኬትን ምሰል : አንተ ልታሳካው የፈለግከውን ያሳኩ ሰዎችን ፈልግና ከነሱ ተማር። ተመሳሳይ ውጤቶችን ለማግኘት የእነሱን ባህሪና ስልቶች ምሰል።
7. ውድቀትህን ተቀበል : ውድቀት የመማር ሂደት አስፈላጊ አካል ነው። ስለዚህ በመዉደቅ አትፍራ። ይልቁንም፣ ውድቀትን ለመማርና ለማደግ እንደ ዕድል ተጠቀምበት።
8. አመስጋኝነትን አዳብር : ላለህ ነገር ሁሉ አመስጋኝነትን ተለማመድ እና በሕይወትህ ውስጥ ባሉት አዎንታዊ ገጽታዎች ላይ አተኩር። ይህ አዎንታዊ አስተሳሰብህን ለመጠበቅና ብዙ መልካም ነገሮችን ወደ ሕይወትህ ለመሳብ ይረዳሃል።
9. የድርጊት ዕቅድ አውጣ: ግቦችህን ለማሳካት የድርጊት ዕቅድ አዘጋጅ፣ እና ወደ ትናንሽና በቀላሉ ወደሚተዳደሩ ደረጃዎች ከፋፍለው። ይህ በቅድሚያ በሚገባቸው ነገሮች ላይ እንድትደራጅና እንድታተኩር ያግዝሃል።
10. ራስህን ጠብቅ . የአካል፣ ስሜታዊና አእምሯዊ ጤንነትህን ተንከባከብ። በመደበኛነት ስፖርት ስራ፣ ጤናማ አመጋገብ ተመገብ፣ በቂ እንቅልፍ አግኝ፣ እንዲሁም ጉልበትህን ለመሙላትና ተነሳሽነትህን ለመጠበቅ የሚረዱህን የእንክብካቤ ተግባራት ቅድሚያ ስጥ።

❤8
ዲስፕሊን የተሞላበት የማሸነፍ ስልት እንዴት ይሰራል
1. ስትራቴጂ ውስብስብ አይደለም፣ ግን ከባድ ነው።
👍🏿 ስልት ቀላል መርሆዎች ቢኖሩትም፣ በተግባር ላይ ማዋል እና ትክክለኛውን ውሳኔ መስጠት አስቸጋሪ ነው። ትልቁ ፈተና ፅንሰ ሀሳቡ ሳይሆን ትግበራው ነው።
2. ማሸነፍ ማለት ተፎካካሪዎችን ማሸነፍ አይደለም። ዋጋ መፍጠር እና መያዝ ነው።
👍🏿 የስትራቴጂ ዋና ግብ ሌላውን ኩባንያ ማጥፋት ሳይሆን፣ ለደንበኞችዎ ልዩ ዋጋ (Value) መፍጠር እና ያንን ዋጋ ለራስዎ ማስቀረት (መያዝ) ነው።
3. የስትራቴጂው ዋና ይዘት ምን ማድረግ እንደሌለብህ መምረጥ ነው።
👍🏿 ጥሩ ስልት የትኩረት ነጥብን ያሳያል። ሁሉንም ነገር ለማድረግ ከመሞከር ይልቅ፣ ከግብህ የሚያዘናጉህን ነገሮች ሁሉ በግልጽ መተው ነው።
4. ጥሩ ስትራቴጂ አንድ ትልቅ ውሳኔ ብቻ ሳይሆን፣ እርስ በርስ የሚደጋገፉ እና የሚጠናከሩ የተቀናጁ ውሳኔዎች ስብስብ ነው።
👍🏿 ስልት በበርካታ ውሳኔዎች የተገነባ ነው። ለምሳሌ የአገልግሎት ምርጫዎ፣ የዋጋ አወጣጥዎ እና የግብይት ዘዴዎ ሁሉ እርስ በእርስ ተሰናስለውና ተጠናክረው መሥራት አለባቸው።
5. ስልት ስለ ምክንያት እና ውጤት መላምት ነው።
👍🏿 ስልትህ "ይህን (ምክንያት) ብናደርግ፣ ይህ ውጤት (ማሸነፍ) ይከተላል" የሚል አስተሳሰብ ላይ የተመሠረተ ፈተና ነው።
6. ተወዳዳሪ ጥቅም ከሌለ፣ ደንበኞች ምርትዎን ወይም አገልግሎትዎን ከሌሎች እንዲመርጡበት ምንም ምክንያት የለም።
👍🏿 ልዩ የሚያደርግህ ነገር ከሌለህ፣ ደንበኞች ወደ አንተ እንዲመጡ የሚገፋፋ ኃይል የለም። ሁልጊዜ ከሌሎች የተሻለ የሚያደርግህ ነገር ሊኖርህ ይገባል።
7. ታላላቅ ስልቶች ደፋር ናቸው፣ ሆኖም ግን እውነታን ያገናዘቡ ናቸው።
👍🏿 የላቀ ስልት ትልቅ እይታንና ለውጥን ያነሳሳል፣ ግን ሊደረስበት የሚችል እና በተጨባጭ የሚተገበር መሆን አለበት።
8. ስልት ማለት በገበያው ውስጥ ለማሸነፍ የሚደረጉ ልዩ ምርጫዎች ናቸው።
👍🏿 ስልት አጠቃላይ ምኞት አይደለም። በየትኛው ገበያ እንደምትወዳደር፣ ለማን እንደምትሸጥ እና እንዴት እንደምትለያይ በመወሰን ላይ ያተኩራል።
9. ግልጽ ስልት የሌለው ኩባንያ ሁሉንም ነገር ለመሞከር ፈቃደኛ ነው።
👍🏿 ስትራቴጂ አለመኖር ማለት ትኩረት ማጣት ማለት ነው። ግልጽ መመሪያ ከሌለ፣ ድርጅቱ ጉልበቱንና ሀብቱን በማይጠቅሙ አቅጣጫዎች ላይ ሊያባክን ይችላል።
10. ምርጥ ስልቶች የተቀናጁ ፣ ቀጥተኛ እና በድርጅቱ ውስጥ ለሁሉም ሰው በቀላሉ የሚገባቸው ናቸው።
👍🏿 ውጤታማ ስልት የሰነድ ክምር አይደለም። ቀላል፣ ትርጉም ያለው እና በድርጅቱ ውስጥ ያለ እያንዳንዱ ሰራተኛ ሊረዳውና ሊከተለው የሚችል መሆን አለበት።

❤10
5ቱ የህይወት ወርቃማ ህጎች
1. ምላሽዎን በሚቆጣጠሩበት ጊዜ ትንሽ
ምላሽ መስጠትን ይማሩ ማንም ሰው
ሊቆጣጠረዎ አይችልም::
2. እራስህን ከሌሎች ጋር ማወዳደር
አቁም የስኬትህ መለኪያ የራስህ
ግስጋሴ ነው::
3 ሌላ ሳይሆን እራስህን ተቆጣጠር,
ሌሎችን መቆጣጠር ጥንካሬ ነው,
ራስን መቆጣጠር ግን እውነተኛ ሀይል
ነው::
5. ጓደኞችህን በጥንቃቄ ምረጥ, የተሻለ
ሰው ለመሆን ፈጣኑ መንገድ እራስህን
በጥሩ ሰዎች መክበብ ነው::
1. ምላሽዎን በሚቆጣጠሩበት ጊዜ ትንሽ
ምላሽ መስጠትን ይማሩ ማንም ሰው
ሊቆጣጠረዎ አይችልም::
2. እራስህን ከሌሎች ጋር ማወዳደር
አቁም የስኬትህ መለኪያ የራስህ
ግስጋሴ ነው::
3 ሌላ ሳይሆን እራስህን ተቆጣጠር,
ሌሎችን መቆጣጠር ጥንካሬ ነው,
ራስን መቆጣጠር ግን እውነተኛ ሀይል
ነው::
5. ጓደኞችህን በጥንቃቄ ምረጥ, የተሻለ
ሰው ለመሆን ፈጣኑ መንገድ እራስህን
በጥሩ ሰዎች መክበብ ነው::
❤18
"ክብርህን ከእጅህ እንጅ ከሰው አትጠብቅ"
☑ከተሳሳተ ሰው ጋር ሁኖ ብዙ ከመጠቀም ብቸኛ ሁኖ ብዙ መጎዳት ይሻላል::
☑መጥፎ ቃል ተናግሮ ፈጣሪንም ሰውንም ከማሳዘን ዝምታ ይሻላል::
☑በተሳሳተ አቅጣጫ ከመሮጥ ሁኖ በእምነት መጠበቅ ይሻላል::
☑ከተሳሳተ መንጋ ጋር በፍጥነት ከመጓዝ ከትክክለኛ ማንነት ጋር ለብቻ መጓዝ ይሻላል::
☑ህሊን አቆሽሾና ራስን አጥቶ ከሰው ጋር ከመሆን በንጽህና ብቸኛ ሁኖ መኖር ይሻላል::
☑ራስህን ባከበርከው ልክ ነው ሰው የሚአከብርህ ራስህ በሰጠከው ግምት ልክ ነው ሰው የሚገምትክ በፈቃድህ በተገኘክበት ቦታ ነው ሰው ወንበር ስቦ የሚአስቀምጥክ::
☑ስለዚህ በህይወትክ ማንንም አትውቀስ በማንም አትዘን ምንም ላይ አትፍረድ ማንም ሰው ያልሆንከውን ነህ አይልክም
ምን ጊዜም ክብርህን ከእጅህ እንጅ ከሰው አትጠብቅ::
☑ለሰዎች ምናልኩ እንጅ ምን አሉኝ ብለህ አትጨነቅ::
ማስተዋል ጥበብ ነው::

❤13👍4
ስትተወው ለሚቀር አለም እምነትህን አትጣ ከክብርህ አትውረድ
➡ደስታህን በእምነት እንጅ በገንዘብ ለማግኘት አትሞክር እምነት ሲኖር ሁሉን ማግኘት ይቻላልና
➡ንግግርህን አሳንሰህ ተግባር እና ምልከታህን አብዛ እውነተኛ ኃይል ዝምታና ተግባር ውስጥ ነው
➡የወዳጆችህን ክበብ ትንሽ አድርግ ምስጢሮችህን ደግሞ ከዚያ በላይ ጥብቅ አድርግ
➡በሁሉ ነገር አትከራከር ውጤቶችህ ብቻ ይናገሩ
➡ንዴትህን ተቆጣጠር የጠላትህ ምርጥ ሰላይ እርሱ ነውና
➡እነርሱ የሚከተሉት ጥሩ ሰው ሁን እንጅ በፍጹም አታሳድ
➡ደግና ጠንካራ ሁን ነገር ግን በፍጹም ልፍስፍስ አትሁን
➡ትኩረትህን እንደ ገንዘብ በልክ ስጥ ሁሉም ሰው ሊገዛው አይችልምና
➡በጣም አስከፊ ቀንህ ላይ እንኳ እንደ ስኬታማ ሰው ተላበስ
➡ቦታው ያንተ ባይሆንም እንኳ ፈገግታህን ቀንሰህ ግርማ ሞገስክን ጨምረህ የራስህ እንደሆነ አስመስለህ ተራመድ
➡ሳይጠብቁህ ብቅ በል ከዚያም በበለጠ ፍጥነት ከእይታ ስውር በል በዚያ ቅጽበት ብዙ ነገር ታገኛለህና
➡በዝምታ እራስህን ገንባ ድምጽህን ከፍ አድርገህ የምትፎክረው አንድ ጊዜ ብቻ ይሁን
➡ግድ ቢሰጥም ባይሰጥም እንዲገምቱ አድርጋቸው ከግምታቸው ብዙ ጠቃሚ ፍንጭ ታገኛለህና
➡ያደረግከውን በፍጹም አታብራራ ምክንያቱም አድራጊዎች ብዙ አይናገሩም
➡ፈጣን ምላሽ አትስጥ ነገስታትኮ እነሱ እንዲጠብቋቸው ያደርጋሉና
➡እንደ እሳት ተወዳጅ እና አስፈሪ ገጽታ ይኑርህ እንደአስፈላጊነቱ በአንዱ ገጽታህ ለሚወዱህ ማብሰያ ለሚጠሉህ ማቃጠያ ትሆናለህና
➡ሁል ጊዜ ስንፍናህን ወደ ኃይል ለውጥና ታታሪ ሁን
➡ስምህ ከህልውናህ በላይ ክብደት እንዱኖረው አድርግ
➡ስትሄድ ትዝታን ሳይሆን አሻራን ትተህ እለፍ
➡አስታውስ ከአንድ ጊዜ በላይ የተሰራ ስህተት ምርጫ እንጅ ስህተት አይደለምና ለከለፈ ስሀተት ተማርበት እንጅ ስህተትህን አትድገም
ማስተዋል ጥበብ ነው

❤14
አለቃህም አንተም የማትሰሩትን ስራ ቢያዝዝህ ምን ታደርጋለህ
▶ንጉሡ አማካሪዎቹ እና ጥበበኞቹ ስራ ሲፈቱ አየና አንድ ስራ ማሰራት ፈለገ በዚህም ጊዜ ሰበሰባቸውና አንድ ስራ ላዝዛችሁ ነው አላቸው::
▶እነርሱም እሽ ንጉስ ሆይ ምን እንታዘዝ አሉት::
▶ንጉሡም እንደው ምድር ላይ ያሉ ቤቶች እና ቤተ መንግስቶች ሰልችተውኛል እና አንድ ነገር ላማክራችሁ ወደድኩ መቼም እናንተ ጥበበኛ ስለሆናችሁ መላ አታጡም አላቸው::
▶እነሱም እንዴ ንጉሥ ሆይ እርስዎ አዘውን የማንሰራው ምናለ ይዘዙን አሉ::
▶ንጉሡም ድሮምኮ እኮራባችሗለሁ አለና ጥያቄውን ቀጠለ
ሰማይ ላይ ቤት እንዲሰራልኝ እፈልጋለሁ አለ::
▶በዚህን ጊዜ ሁሉም ደነገጡ ሰማይ አይታረስ ንጉሥ አይከሰስ ሆነባቸው ነገሩ አይሆንም እንዳይሉ ጥበበኛ ናቸው ተብሎ ከንጉሡ እኩል እንክብካቤ የሚደረግላቸው አማካሪዎች ናቸው::
▶ንጉሡ ቀጠለ ይህንን ካላደረጋችሁ እናንተ ላይ እርምጃ እወስዳለሁ አላቸው::
▶እነሱም በጣም አሰቡና ስብሰባ ተቀመጡ ምን እናድርግ ይህ ንጉሥ ደግሞ አይራራልንም እያሉ ሁሉም ለየራሳቸው ማሰብ ጀመሩ::
▶ከዚህም በሗላ ከመካከላቸው አንዱ ተነሳና እኔ አንድ ሀሳብ አለኝ አለና ነገራቸው እነሱም በሀሳቡ ተስማምተው ወደ ንጉሱ አቀኑ::
▶ንጉሥ ሆይ ሺ አመት ይንገሱ አለ የተወከለ አባል:: ሰማይ ላይ በጣም የሚአምር ቤት ለመስራት ዲዛይኑን ሰርተን ጨርሰናል ነገር ግን አንድ ችግር ገጠሞናል አላቸው::
▶ንጉሡም ተናገር ምን ቸገራችሁ አለው::
▶ሰማይ ላይ የትኛው ቦታ እንደሚሰራ አላወቅንም ስለዚህ እርስዎ ሄደው ቦታውን መምረጥ ይኖርብዎታል አለው::
▶ንጉሡም ግራ ተጋባና እንዴ እንዴት ነው ሰማይ ላይ ሄጄ የማሳያችሁ ይህ የማይቻል ነው አላቸው::
▶እነሱም ወዲያው በቅጽበት መልስ ሰጡ ትክክል ብለዋል ንጉሥ ሆይ እኛም የማንችለውን ነገር ስለጠየቁን ይህ ሀሳብ መጣልን አሉት::
▶ንጉሡም በመልሳቸው ተደስቶ ይቅር አላቸው::
▶ከዚህ የምንረዳው አንዳንድ ሰዎች ራሳቸው የማይሰሩትን ነገር ማዘዝ የተንኮልና ክፋት ጥግ ነው::
አስቸግሮ ሲመጣ አስቸግሮ መመለስን : በጥያቄ ሲመጣ በጥያቄ መመለስን : በጥበብ ሲመጣ በጥበብ መመለስን : ብልህነትን : አእምሮአችንን ከተጠቀምን ለችግሮች ሁሉ መፍትሔ ቅርብ ይሆናል::

❤12
7ቱ አሉታዊ አስተሳሰቦች
1. ጅምላ ፍረጃ: አንድ ሰው ባጠፋው ጥፋት እርሱ የወጣበትን ቤተሰብ ወይም ማህበረሰብ እንደርሱው በመጥፎ መመልከት::
2. ፖላራይዜሽን: ለምሳሌ አንድን ጠቅላይ ሚኒስቴርን የሚቃወሙ አካላት ምንም ጥሩ ነገር እንደሌለው ሙሉ ለሙሉ መጥላት
እንደዚሁም የሚደግፉት አካላት ምንም ጥፋት እንደሌለው እና ፍጹም መልካም ስራ ብቻ እንዳለው አርጎ መደገፍ ነው
ይህ ዋልታ ረገጥ አስተሳሰብ ነው::
3 የአእምሮ ማጣሪያ: ይህ ደግሞ ለምሳሌ በስብሰባ መካከል ንግግር ስናደርግ አንድ ሰው ረግጦ ቢወጣ
ከስብሰባ መልስ የምናሰላስለው ሲከታተሉን የነበሩትን ብዙዎቹን ሳይሆን ያንን አንድ ግለሰብ ነው::
4 . አዎንታዊ አስተያየቶችን ማጣጣል:
ያለንን ጥሩ ነገር ሲነግሩን ከመቀበል ይልቅ ማጣጣል ነው::
ምሳሌ አንተኮ ጥሩ የትምህርት ደረጃ አለህ ሲሉት አይ ምን ዋጋ አለው ብር እንደሁ ያለው አልተማሩት ጋር ነው ይላል ማለት ነው::
5. ወደ መደምደሚያ መዝለል:
አንድ ግለሰብ ስብሰባ ላይ ንግግር ቢአደርግ እና አንድ ታዳሚ የሰውየውን ሀሳብ የሚቃወም ሀሳብ ቢአቀርብ እና
በአጋጣሚ በሌላ ቀንም እንዱሁ ያው ሰውዬ ተቃራኒ የሚመስል ሀሳብ ቢሰነዝር
በዚህን ጊዜ ሰብሳቢው ይሄ ሰውዬ ይጠላኛል ብሎ ይደመድማል::
6. ማጉላት: ይህ ደግሞ የአንድን ሰው ብዙ ጥሩ ነገሮች ከመናገር ይልቅ አንዷን ጥፋት አጉልቶ ማውጣት ነው::
7. ስሜታዊ አስተሳሰብ: ይህ ደግሞ በስሜት ሆኖ መወሰን ነው
አንዳንድ በስሜት የተወሰኑ ውሳኔዎች ትልቅ ዋጋ የሚአስከፍሉ ናቸው::

👍8❤5
ያለህ ከሌለህ ይበልጣልና ተመስገን በል
☑ጧት ስትነሳ ተመስገን በል ምክንያቱም ሞተህ ልታድር ትችል ነበርና:: ከአልጋህ ስትወርድ ተመስገን በል ምክንያቱም በሆነ ምክንያት የአልጋ ቁራኛ ልትሆን ትችል ነበርና::
☑ከቤት ወጥተህ ስትሄድ ተመስገን በል ምክንያቱም ብዙዎች መውጣት እየፈለጉ ቤት ውለዋልና::
☑ቆመህ በመራመድህ ተመስገን በል ምክንያቱም ብዙ ሰዎች እጅ እግራቸው ተቆርጦ, አይናቸው ጠፍቶ, ብዙ አካላቸው ጎድሎ በየጎዳናው ወድቀዋልና::
☑ሆድህም ምግብ በመቀበሉ ተመስገን በል ምክንያቱም ምግብ ሰጥቶ ሆድ ይነሳልና::
☑እስኪ ከሌለህ ይልቅ ያለህን በረከት ቁጠረው አትጨርሰውም አንተ ያለክን ነገር ብዙዎች የሌላቸው ይመኙታልና ባለህ ነገር አመስግን ደስ ይበልህ::
☑ባለው ያላመሰገነ አይጨመርለትም ይልቁንም ያለውም ይወሰድበታል::

❤15👍6
በሕወትህ በፍጹም መፍቀድ የሌሉብህ ነገሮች
1.በራስህ ሕይወት ውስጥ በተሳፋሪ ወንበር ላይ አትቀመጥ:: ሕይወትህን በራስህ ምራ በእውነት የምትፈልገውን ነገር አድርግ:: ቤተሰብህ ወይንም ማህበረሰቡ በአሽከርካሪ ወንበር ላይ እንዲቀመጡ ከፈቀድክ በደረሱበት መድረሻ ፈጽሞ ደስተኛ አትሆንም::
2. ቀሪ ህይወትህን አብረሀቸው ለማሳለፍ ካላሰብክ ማንም ሰው በፍቅርህ እንዲወድቅ አትፍቀድ::በዚህ አለም ላይ ካሉ ስሜቶች ሁሉ ከባዱ የወደድከውን ሰው ከልብህ ለማውጣት መሞከር ነው::
3. በማንም ሰው ላይ በመልኩ, በዘሩ, በሀይማኖቱ ወይንም ሊቆጣጠራቸው በማይችላቸው ነገሮች ላይ ተመስርተህ አትፍረድ::
4. በፍጹም ሰዎች እንደ አመራጭ እንዲቆጥሩህ አትፍቀድ::
5. የአእምሮ ሰላምክን የሚአውክ ሰው በህይወትህ ውስጥ ቦታ እንዲኖረው አትፍቀድ:: የአእምሮ ሰላምህ ቀዳሚው ትኩረትህ ሊሆን ይገባል::
6. ከአሉታዊ የውስጥ ንግግር ተቆጠብ:: ከራስህ ጋር የምታደርገው ንግግር ከነፍስህ ጋር እንደመነጋገር ይቆጠራል::
7. በሌላ ሰው ህይወት ውስጥ ጣልቃ አትግባ:: ሙሉ ትኩረትህ በራስህ እና በእድገትህ ላይ ይሁን::
8. ያለፉ የህይወት ተሞክሮዎችህ ውብ የሆነው የወደፊት ህይወትህን እንዲአበላሹ አትፍቀድ::
9. ከምትወዳቸው ሰዎች ውጭ በህይወትህ ውስጥ ልታደርገው የምትፈልገውን ነገር ያላደረጉ ሰዎችን ምክር አትስማ::
10. በህልሞችህ ላይ ፈጽሞ ተስፋ አትቁረጥ ጽኑ ከሆንክ እና ጠንክረህ ከሰራህ ህልሞችህን እውን የምታደርግበትን መንገድ ሁሌም ታገኛለህ::

❤12👍8🤔1
ወዳጅ ስታበጅ በችግርህ ወራት አብጅ
➡ ልዝብ አንደበት ወዳጅነትን ያበዛል:: ብዙ ወዳጆች ይኑሩህ ነገር ግን ምክርህን ለሁሉም አትግለጥ::
➡ወዳጅ ስታበጅ በችግርህ ወራት አብጅ
ስለ ማዕድህ የሚወድህ ወዳጅ አለና
ባለጸጋ በሆንክ ጊዜ የሚወድህ አለና
ስልጣን ላይ በወጣህ ጊዜ የሚወድህ አለና::
እነዚህን ሁሉ ፈጥነህም እምነት አትጣልባቸው ወረተኛ ወዳጅ አለና በመከራህ ቀንም ከአንተ ጋር አይታገስም::
በተቸገርክ ጊዜ ይለዩሃል: ይሰወሩብሃል የሚሰድቡህ እና ባላጋራህም ይሆናሉ::
➡እውነተኛ ወዳጅስ በችግርክም በደስታክም ጊዜ ለውጥ የለውም ለደግነቱም ሚዛን የለውም
የታመነ ወዳጅ የሕይወት መድኃኒት ነው::
በችግርህ ጊዜ አብሮህ የሚቆም: መከራህን አብሮ የሚካፈል : ከመከራም የሚአወጣህ ነው::

❤9
የተሰበረ ሁሉ ያበቃለት አይደለም ከበፊቱ የተሻለ የመሆን እድልም አለው
✔በዚህ አለም ላይ ስንኖር በሕይወት ጉዞ ውስጥ ውጣ ውረድ ያለ ነው:: ከመስጠት በሗላ መቀበል አለ:: ከማጣት በሗላም ማግኘት አለ:: ከሀዘን በሗላ መሳቅ አለ:: ከህመም በሗላ መዳን አለ:: ከስራ ማጣት በሗላ መልካም ስራ ማግኘት አለ::
✔ሳትፈተን መልካም ውጤት የለም:: ሳትቸገር ተድላ የለም:: ለመኖር ዋጋ ትከፍላለህ:: ለመኖር ስትል ዝቅ ትላለህ ለመኖር ስትል እንባ ታፈሳለህ:: ለመኖር ስትል ከሀገር ትሰደዳለህ:: ለመኖር ስትል አይቶ እንዳላየ ሰምቶ እንደልሰማ ትሆነለህ:: ለመኖር ስትል አንገት ትደፋለህ::
✔አንድ ቀን ግን ሁሉም ያልፍና ቀና ብለህ ከሰው እኩል ትራመዳለህ:: በዚህ አለም ላይ ምንም ነገር ልታጣ ትችላለህ ነገር ግን ሁሉም የሚተካ ነገር ነው:: በዚህ ውል አልባ እና ውጥንቅጡ በበዛበት አለም በትእግስት ነገሮችን መርምሮ በማስተዋል መኖር የውስጥ ሰላምን ማስጠበቅ እና የህሊና መረጋጋት ማግኘትን የመሰለ ትልቅ ስኬት የለም::
✔የውስጥ መረጋጋትን እና የህሊና ሰላምን ማጣት ግን ትልቁ ውድቀት ነው:: የህሊና ሰላም ማግኘት ህይወትን በተሻለ መንገድ እንድናጣጥም እና ፈተናን በቀላሉ እንድናልፍ ይረዳናል::
✔ስለዚህ ስንኖር ልብሳችን እንዳይቆሽሽ እንደምንጠነቀቀው ሁሉ በበለጠ ደግሞ ህሊናችን እንዳይቆሽሽ መጠንቀቅ አለብን:: አጥንታችን እንዳይሰበር ብቻ ሳይሆን ልባችንም እንዳይሰበር እንጠንቀቅ:: ይህን አስታውሱ የተሰበረ እጅ ባገገመ ጊዜ የበለጠ ጠንካራ ይሆናል የተሰበረ ልብም እንደዛው:: በአግባቡ ያልተጠገነ ስብር ግን ቢሰራም የቁስሉ ጠባሳ ዘወትር እየደማ አንካሳ ሁኖ ይኖራል::

❤11👍5
የስኬት መርሆዎች
፩) የመጀመሪያ ዲግሪ ዐይን መግለጫ መሆኑን እወቅ። በቀጣይ የፈለግኸውን መርጠህና አመራርጠህ የመማር እድል ይኖርሃል።
፪) ለምን እንደምትማር የጠራ ዓላማ ይኑርህ። የትምህርትህ ምክንያቱ ካላሳመነህ ግን በከንቱ ጊዜህን አታባክን።
፫) ለነጥብ ስትል ብዙ ማወቅ ያለብህ ነገር እንዳያመልጥህ። በሥራ ዓለም ላይ ማንም ስንት ነጥብ ይዘህ እንደተመረቅህ ጉዳዩ አይደለም።
፬) በምትማርበት ዘርፍ ማወቅ ያለብህን ዋና ዋና ጉዳዮች ጠንቅቀህ ማወቅ እንዳለብህ እንዳትዘነጋ። ነጥብህ ትልቅ ሆኖ የዘርፍህን ዋና ጉዳዮች ካላወቅህ ፈላጊ አይኖርህም።
፭) ከትምህርትህ በተጨማሪ ተዛማጅ መጽሓፍትን አንብብ። ጋዜጦች እና ዜናዎችን በመከታተል መረጃዎችን መዝግበህ ያዝ።
፮) በትምህርት ቤት ማህበራዊ ጉዳዮች ውስጥ በንቃት ተሳተፍ። በመልካም ጸባይህ ጥሩ ኔትወርክ ገንባ።
፯) ራስን የመግለጽ ችሎታን እና የጠቅላላ ሁኔታዎች ግንዛቤህን አዳብር። ለዚህ ደግሞ ብዙ መጽሓፍትን አንብብ። ጠቃሚ ፖድካስቶችን መርጠህ ተመልከት።
፰) ለእንዳንድ መ/ቤቶች ነጻ አገልግሎት ስጥ። ቢቻልህ መቀጠር በምትፈልግበት መ/ቤት ላይ የመመረቂያ ጽሁፍና ጥናቶች አድርግ።
፱) በማህበራዊ ሚድያዎች ንቁ ተሳትፎ አድርግ። ሰዎች ተወዳጅ፣ ጻፍ፣ አስተያየት ስጥ፣ ጠይቅ።
፲) ገና ሳትመረቅ ኩባንያ መሥርት። ኮሌጅ ውስጥ ትልቅ ገበያ አለ። እነ ፌስቡክ በዶርም ውስጥ መመሥረታቸውን አስታውስ።

❤7
1. ‹‹ እኔ ሃይማኖተኛ ነው የምለው የሌሎችን ስቃይ የሚረዳ ሠውን ነው፡፡ ››
2. ‹‹ በዓለም ላይ እውነተኛው ሠላም እንዲሠፍን ከፈለግን ልጆችን ስለሠላም ማስተማር መጀመር አለብን፡፡ ››
3. ‹‹ ዓለም ላይ ልታየው የምትፈልገውን ለውጥ ሁን፡፡ ››
4. ‹‹ መንፈሳዊ ጥንካሬ ከማይበገር ውስጣዊ ፈቃድ እንጂ ጡንቻን በማሳበጥ አይመጣም፡፡ ››
5. ‹‹ ነፃነት የመሳሳት ነፃነትን ካላካተተ በራሱ ዋጋ የለውም፡፡ ››
6. ‹‹ ማንም ሠው እኔን ከራሴ ፈቃድ ውጪ ሊጎዳኝ አይችልም፡፡ ››
7. ‹‹ ፀሎት ጧቱን መክፈቻ ቁልፍና እና ማታውን ማጥበቂያ ብሎን ነው፡፡ ››
8. ‹‹ ራስህን ለማግኘት ምርጡ መንገድ በአንተ ውስጥ ያለውን የሌሎች ማንነት መጣል ነው፡፡ ››
9. ‹‹ እንዴት ማሠብ እንዳለባቸው የሚያውቁ ሠዎች መምህር አያስፈልጋቸውም፡፡ ››
10. ‹‹ለመሞት ተዘጋጅቻለሁ፣ ለመግደል ግን የምዘጋጅበት ምንም ምክንያት የለም።››
11. ‹‹ መልካም ሠው ሕይወት ላላቸው ነገሮች ሁሉ ወዳጅ ነው፡፡ ››
12. ‹‹ ዓይንን በዓይን የሚለው ህግ መጨረሻው ዓለምን በሙሉ አይነስውር ማድረግ ነው፡፡ ››
13. ‹‹ ደስታ ማለት የምታስበውን ነገር፣ የምትናገረውን ነገርና የምታደርገውን ነገር ከሌሎች ጋር በመስማማትና በመዋሃድ የምታመጣው ሲሆን ነው፡፡ ››
14. ‹‹ ደካሞች ይቅር አይሉም፡፡ ይቅር ማለት ወይም ይቅርታ ማድረግ የጠንካሮች መገለጫ ነው፡፡ ››
15. ‹‹ ራስህን ስለሆንክና ትክክል ስለሆንክ ብዙ ሠዎች በተለይም አላዋቂ የሆኑ ሠዎች ሊቀጡህ ወይም ሊጠሉህ ይፈልጋሉ፡፡ ለትክክለኛነትህ ይቅርታ አታድርግለት፡፡ ትክክል ከሆንክና ትክክል መሆንህን ካወቅክ ለአዕምሮህ ንገረው፡፡ ምንም እንኳን ከታናናሾቹ አንዱ ብትሆንም እውነት አሁንም እውነት ነው፡፡ ››
16. ‹‹ አንድ ግራም ተግባር ከብዙ ቶን ስብከት በላይ ዋጋ አለው፡፡ ››
17. ‹‹በዓለም ላይ የሰውን ስግብግብነት ለማሟላት ሳይሆን ለሰው ልጅ ፍላጎት የሚበቃ በቂ ነገር አለ።››
18. ‹‹ ሠው ማለት የአስተሳሰቦቹ ብዜት ነው፡፡ የሚያስበውን ነውና የሚሆነው፡፡››
19. ‹‹ ያለአንዳች ተግባር የትም መድረስ አትችልም፡፡ ››
20. ‹‹እውነተኛ ሀብት የሆነው የወርቅና የብር ቁርጥራጭ ሳይሆን ጤና ነው።››

❤15
ሕልሜን ላጫውታችሁ
አንድን ሕልም አለምኩ፡፡ አንድን በአለም አቀፍ ደረጃ እጅግ ተፈላጊነት ያለውን ጥበበኛ አዛውንት ያገኘሁት ይመስለኛል፡፡ ይህ ጥበበኛ ሰው ምንም አይነት ጥያቄ ከብዶት አያውም፣ ለማንኛውም አይነት አስቸጋሪ ሁኔታ መፍትሄ በመስጠት የታወቀ ነው፡፡ ለዚህም ነው ሰዎች ቢያንስ ከአንድ አመት በፊት ቀጠሮ በማስያዝ ከአለም ዙሪያ ወደእርሱ የሚመጡት፡፡ ጠቢቡ አስተርጓሚ አያስፈልገውም፡፡ የአለምን ሁሉ ቋንቋ ጥንቅቅ አድርጎ ያውቃል፡፡ ፈገግተኛ፣ የደስ ደስ ያለውና ከአጠገቡ መለየትን የማያስመኝ መረጋጋት ያለው ሰው ነው፡፡ እንዴት እንደሆነ ባላውቀውም ካለምንም ቀጠሮ ለብቻዬ ጠቢቡን የማግኘት እድል ያገኘሁ ይመስለኛል - በሕልሜ፡፡
ሁኔታው ድንገተኛ ስለሆነብኝ ይመስለኛል፣ ምንም እንኳን ጊዜ ቢሰጠኝ ብዙ የምጠይቃቸው ጥያቄዎች ቢኖሩኝም የምለውን አጣሁ፡፡ ሰዎች ከአለም ዙሪያ በብዙ ትግል የሚያገኙትን ይህንን ጠቢብ የማግኘት እድል አግኝቼ ምንም ነገር ሳላገኝ ሄጄ በኋላ እንዳይጸጽተኝ የመጣልኝን ሁሉ ለመጠየቅ ወሰንኩ፡፡ እንዲህ ስል ጠየኩት፣ “ሰዎች ወደአንተ ይዘው ለሚመጡት ጥያቄ በሙሉ ለመፍትሄ የሚሆንን ምክር የመለገስ ጥበብ እንዳለህ ዝናህን ሰምቻለሁ፡፡ እስቲ እስካሁን ድረስ ለመምከር ወይም መፍትሄ ለመስጠት ከባድ ሆኖ ያገኘኸውን ቀንደኛ ሁኔታ ንገረኝ” አልኩት፡፡
አንዴ እኔን፣ አንድ ጊዜ ደግሞ መሬት መሬት ከቃኘ በኋላ፣ እንደገና ወደ እኔ ከዚያም ልክ አንድ አዲስ ሃሳብ ሰማዩ ላይ የሚያነብ እስኪመስልበት ድረስ ወደላይ ከተመለከተ በኋላ እንዲህ አለኝ፡-
“ፈጣሪ አድሎኝ ለብዙ ሰዎች መፍትሄ የሚሆኑ ምክሮች የመለገስ ብቃት አለኝ፡፡ በዚህም ደስተኛ ነኝ፡፡ ምክር ፍለጋ ወደእኔ የሚመጡት በአብዛኛው በወጣትነትና በመካከለኛው የእድሜ ክልል ውስጥ የሚገኙ ሰዎች ናቸው፡፡ እስካሁን ድረስ በሺህ የሚቆጠሩ ሰዎችን አማክሬአለሁ፡፡ እስካሁን የሰጠኸኝ ምክር አልሰራልኝም በማለት የተመለሰ ሰው አላጋጠመኝም፡፡ ይህ የሆነበት ምክንያት ሁለት ነው፡፡ አንደኛው በወጣትና በጎልማሳ እድሜአቸው ላይ የሚገኙት ሰዎች ምክሩን ተግባራዊ አድርገው መፍትሄ በማግኘታቸው ምክንያት ወደ እኔ አይመለሱም፡፡ ከዚህ ለየት የሚለው ሁኔታ ግን እንደ እኔ እድሜያቸው እጅግ የገፋ አዛውንቶች ይዘው የሚመጡት ጥያቄ ነው፡፡ የእነዚህ ሰዎች ጥያቄ በአብዛኛው የጸጸት ጥያቄ ነው፡፡”
ጠቢቡ ንግግሩን ቀጠለ፡- “ያሳለፏቸውን አመታቶቻቸው መቼ መጥተው መቼ እንደሄዱ ማሰብ እስከሚያስቸግራቸው ድረስ ግር የሚላቸው አዛውንት ጥቂት አይደሉም፡፡ አሁን መለስ ብለው ሲያስቡት ሕይወታቸውን ወደማይፈልጉበት አቅጣጫ እንዲሄድ ያደረገውንና አሁን የሚጸጸቱበትን ውጤት ያስከተለባቸውን የመነሻ ችግር በሚገባ ያውቁታል፡፡ በወቅቱ እርምጃ ወስደው ሊያርሟቸው የሚገቡ ቀላል የሚመስሉ ሁኔታዎች ዛሬ ምንም ቢጸጸቱ እንኳን ሊቀለብሱት የማችሉትን ሰበብ አጠራቅሞ አገኙት፡፡”
ጠቢቡ ፍላጎቴን አይቶ የኋላ ኋላ እንዳልጸጸት ምን ማድረግ እንዳለብኝ ምክርን ለገሰኝ፡፡ የሰጠኝ ምክሮች ከብዙ አዛውንት የጸጸት ሁኔታ በመነሳት በብዙ ሰዎች የሚንጸባረቁትን የጸጸት መንስኤዎች በመጭመቅ እንደሆነ ገምቻለሁ፡፡ ወዲያውኑ ከእንቅልፌ ባነንኩኝና ሳልረሳቸው ጠቢቡ በምክሩ የጠቆመኝን የሚከተሉትን መመሪያዎች መዘገብኳቸው፡፡
1. “ሁል ጊዜ አንተው ያመንክበትን ሕይወት መኖርህን እርግጠኛ ሁን፡፡”
2. “ልክህን እወቅ፣ ለስራህና ለሕይወትህ መርህና ገደብ ይኑርህ፡፡”
3. “ማንነትህን፣ ኑሮህንም ሆነ የሰራሃቸውን ስህተቶች አሻሽላቸው እንጂ አትፈርባቸው፡፡”
4. “ከወዳጆችህ ጋር ነጻ የሆነን ግንኙነት መስርት፣ ግልጽነትና የቀረበ ወዳጅነት ቢጎዳህም ከጉዳቱ ጥቅሙ ይበልጣልና በፍጹም አትሽሽ፡፡”
5. በመጨረሻ፣ ሁል ጊዜ ደስተኛ መሆንን ምረጥ፡፡ የሕይወት ቀንደኛ ዓላማዎች ከሚባሉት ውጤቶች መካከል ደስተኛነት አንዱ ነውና፡፡
(“የሕይወት ጸጸቶች” ከተሰኘው የዶ/ር ኢዮብ ማሞ መጽሐፍ የተወሰደ)

❤13👏1
ዝም አትበል!
በመጀመሪያው የክፍል ቀን የ"ህግ መግቢያ" የትምህርት ክፍለ ጊዜ...ፕሮፌሰሩ ወደ ክፍል እንደገቡ በመጀመሪያው ረድፍ የተቀመጠውን ተማሪ ስም ጠየቁ።
"ስምህ ማን ነው?"
"ስሜ ኔልሰን ይባላል መምህር!" አለ
"ከክፍል ውጣና ሂድ!...ወደ ኋላ እንዳትመለስ!" መምህሩ ክፉኛ ጮኹ።
ኔልሰን ግራ ተጋብቶ ነበር።ተነሥቶ በፍጥነት ዕቃውን ሰብስቦ ከክፍሉ ወጣ። ሁሉም ተማሪዎች ቢፈሩም በውስጣቸው ተናደዱ... ግን ማንም አልተናገረም።
"ደህና!... እንጀምር ሕጎች ምንድናቸው?" በማለት አስተማሪው ጠየቁ ።
ተማሪዎቹ አሁንም ፈርተው ነበር፣ ነገር ግን ቀስ በቀስ ለጥያቄው መልስ መስጠት ጀመሩ።
"በማህበረሰባችን ውስጥ ሥርዓት እንዲኖረን የሚያደርግ።"
"አይ!" በማለት ፕሮፌሰሩ መለሱ።
"ስርአት ለማስፈን።"
"አይ!..."
"ስለዚህ የተሳሳቱ ሰዎች ለድርጊታቸው ዋጋ እንዲከፍሉ ለማስቻል።"
"አይ!...የዚህን ጥያቄ መልስ የሚያውቅ አለ? "
"ፍትህ ይከበር ዘንድ።" አንዲት ልጅ በፍርሃት ተናገረች።
በመጨረሻ!...ፍትህ ማለቴ ነው። እና አሁን ፍትህ ምንድን ነው?" ሁሉም በፕሮፌሰሩ መጥፎ አመለካከት መበሳጨት ጀመሩ። ሆኖም መልሱን ቀጠሉ።
"ሰብአዊ መብቶችን ለማስከበር…
እሺ!...ሌላ ምን?"አስተማሪውን ጠየቀ
"መልካሙን ከክፉ ለመለየት ፣ በጎ ለሚሠሩት ዋጋ ለመስጠት…"
"እሺ!... ያ መጥፎ አይደለም፣ ግን ይህን ጥያቄ መልሱ። ኔልሰንን ከክፍል ውስጥ በማባረር ላይ በትክክል እርምጃ ወስጃለሁ?" ሁሉም ዝም አሉ ማንም አልመለሰም።
"አንድ መልስ እፈልጋለሁ!"
"አይ!..." ሁሉም በአንድነት መለሱ።
"ግፍ ሰርቻለሁ ማለት ይቻላል?"
"አዎ!... "
"...እና!... አንዳችሁም ስለእሱ ምንም ያላደረጋችሁት ለምንድ ነው? ህግጋቶች እና ደንቦች ለማስፈጸም ፍላጎት ከሌለን ምን ይጠቅማቸዋል? እያንዳንዳችሁ ኢፍትሃዊነትን በምታዩበት ጊዜ የመናገር ግዴታ አለባችሁ። ሁላችሁም!...ዳግመኛ ዝም አትበሉ! ሂዱ... ኔልሰንን አምጡት! "ሲል ተናገሩ።
መብትና ግዴታችንን በመጠበቅ በደካሞች ላይ የሚደርሰውን ኢፍትሃዊ ድርጊት በመቃወም ክብራችንን እንመልስ።
ክብርም ለድርድር እንደማይቀርብ እንማር።

❤8👍5
#ከማበድህ_በፊት_5_ነገሮችን_አስታውስ!
#የስኬት_አቡጊዳ_መጽሐፍ
#1_ዛሬ_ለራስህ_እረፍት_ስጠው፡፡ ስላስጠቁህ እና ተስፋ እንድትቆርጥ ስላደረጉህ ሰዎች እያሰብክ ከመዋለል ይልቅ ያበረታቱህን ሰዎች በምታደንቅበት እና በምታመስግንበት ጉልበትህ ላይ ትኩረትህን ዳግም አድርግ፡፡ አስታውስ አንዳንድ ሰዎች የሚፈጽሙብህን ክብረ ቢስ ተግባር እና ንግግር መቆጣጠር አትችል ይሆናል፤ ነገር ግን ዛሬ በእነርሱ ላለመረበሽ መወሰን ትችላለህ፡፡
#2_በጫጫታ_ውስጥ_ገብተህ_አትጥፋ
አንዳንድ ጊዜ ልብህ ቀድሞ ያወቀውን ነገር አእምሮህ ለመቀበል ጊዜ ይወስድበታል፡፡ ተንፍስ፡፡ ምስክር እንጂ ዳኛ አትሁን፡፡ የራስህን ድምጽ - የራስህን ነፍስ ለማዳመጥ ለራስህ ቦታ ስጥ፡፡ ብዙ ሰዎች በዓለም ውስጥ ያለውን ጫጫታ በመስማት በሁካታው መሀል ገብተው ይጠፋሉ፡፡
#3_ደግ_ሁን_ግን_እምቢ_ማለትንም_ተማር! ሁልጊዜ በሁሉም ነገር የሚስማማ ሰው ልትሆን አትችልም፡፡ የዚህ አይነት ሰው ከሆንክ የሰዎች መጠቀሚያ ትሆናለህ፡፡ አንዳንድ ጊዜ ወሰን ማስመር አለብህ፡፡ አንዳንድ ጊዜ “አይሆንም” ወይም “እምቢ” ማለት አስፈላጊው የራስ እንክብካቤ ነው፡፡
#4_ሕይወት_ስሜታዊ_ሽክርክሪት_አትሁንብህ
ሕይወት ስሜታዊ ሽክርክሪት ስትሆንብህ ቀለል ያሉ ልማዶችን በመገንባት ራስህን አረጋጋ፡፡ አልጋህን አንጥፍ፡፡ አትክልቶችህን ውኃ አጠጣ፡፡ የራስህን ሳህንና ማንኪያ እጠብ፡፡ ቀላልነት እርጋታን እና ጥበብን ይስባል፡፡
#5_ተይዘህ_አትቅር
ምንም አድርግ ምን ዛሬ ስሜትህን ባበላሸው ትንሽ ነገር ውስጥ ብቻ ተቀርቅረህ ወይም ተይዘህ አትቅር፡፡ ተንፍስ፤ ከፊትህ ላለው ነገርም ምስጋና አድርስ፡፡ አንዳንዶቹ በረከት ናቸው፤ ምንም ነገር ደግሞ ለዘላለም አይቆይም፡፡ ሕይወትን በየእለቱ በሚገጥሙ አሉታዊ ገጠመኞች ላይ ለማባከን በጣም አጭር ናት...
#አዎን_የተሻለ_ማሰብ_ትችላለህ ይህም ማለት ውሎ አድሮ የተሻለ መኖር እንድትችል ሊያደርግህ የሚችለውን ውስጣዊ ጥንካሬህን መክፈት ትችላለህ ማለት ነው፡

👏8❤5👍2🔥1
አንድ ሰው ስኬታማ መሆን እፈልጋለው ምን ላድርግ ብሎ አንድ ታዋቂ ጥበበኛን ይጠይቀዋል። ጥበበኛውም ስኬታማ መሆን ትፈልጋለህ?
ከፈለክ ና ተከተለኝ ብሎ ውሃ ያለበት ቦታ ይወስደውና አንገቱን ይዞ ፊቱን ውሃ ውስጥ ይዘፍቀዋል። ከደቂቃዎች በኋለ ከውሃ ለመውጣት ይፈራገጥ ጀመር። ጥበበኛው ትንሽ ይፈራገጥ ብሎ በማሰብ አለቀቀውም። በመጨረሻም ነብሱ ከመውጣቷ በፊት ይለቀውና ከውሃው ወጥቶ አየር ውስጥ በፍጥነት መተንፈስ ይጀምራል። ውሃ ውስጥ እያለህ ምን ነበር ምትፈልገው? ሲለው
እንዴ ሌላ ምን እፈልጋለው አየር ነዋ፣ መተንፈስ ብቻ። በቃ ስኬትን እንደ አየሩ መፈለግ ከቻልክ ታገኘዋለህ፤ በርታ ብሎት ይሄዳል።
ፅኑ ፍላጎት ፍርሃትንና ድካምን ያስረሳል! ከልብ የመነጨ መሻት ከስሜተዊ የአዕምሮ ክፍል የሚመነጨውን ፍርሃት ይደመስሳል፤ ወኔንም ያላብሳል!!

❤21👍6
አንድ ጊዜ አንድ ሰው በረሃ ውስጥ ጠፋ። ይዞት የነበረው ጥቂት ምግብና ውኃ ወዲያው አለቀበት፤ ላለፉት ሁለት ቀናትም አንዲት ጠብታ ውኃ ሲናፍቅ ቆይቷል።
በልቡ ያውቅ ነበር፣ በሚቀጥሉት ጥቂት ሰዓታት ውስጥ ውኃ ካላገኘ ሞቱ አይቀሬ መሆኑን። ነገር ግን የሆነ ቦታ ላይ፣ አንድ ተአምር እንደሚከሰትና ውኃ እንደሚያገኝ በእግዚአብሔር ላይ እምነት ነበረው። ልክ በዚያን ጊዜ አንዲት ጎጆ አየ። ዓይኖቹን ማመን አልቻለም። ከዚህ በፊት በበረሃማ ነጸብራቅና በቅዠት ተታልሎ ነበር። ነገር ግን ያ ምስኪን ሰው ከማመን ውጪ ሌላ አማራጭ አልነበረውም፤ ይህ የመጨረሻ ተስፋው ነበርና።
በቀሪው ጉልበቱ ወደ ጎጆዋ መጓዝ ጀመረ። እየቀረበ ሲመጣ ተስፋው ጨመረ፤ በዚህ ጊዜ ዕድል ከእርሱ ጋር ነበረች። በእርግጥም ጎጆ ነበረች። ግን ይሄ ምንድን ነው? ጎጆዋ ለዓመታት ማንም ያልደረሰባት ይመስል ባዶ ነበረች። ሰውየው አሁንም ውኃ ለማግኘት ተስፋ በማድረግ ወደ ጎጆዋ ገባ። በውስጥ ያየውን ሲመለከት ዓይኖቹን ማመን አልቻለም።
አንድ የእጅ ፓምፕ ተተክሎ ነበር። ሰውየው በአዲስ ኃይል ተሞላ። ለእያንዳንዷ ጠብታ ውኃ የተጠማው ሰው በፍጥነት የእጅ ፓምፑን መሥራት ጀመረ። ነገር ግን የእጅ ፓምፑ ለዘመናት ደርቆ ነበር። ሰውየው ተስፋ ቆረጠ፤ አሁን ከሞት ሊያድነው የሚችል ምንም ነገር እንደሌለ ተሰማው። ሙሉ በሙሉ ደክሞ ወደቀ።
ልክ በዚያን ጊዜ፣ ከጎጆዋ ጣሪያ ላይ በውኃ የተሞላ አንድ ጠርሙስ ታስሮ አየ። በሆነ መንገድ ወደ እሱ ተንደረደረና ሊከፍተውና ሊጠጣው ሲል፣ በጠርሙሱ ላይ የተለጠፈ አንድ ወረቀት አየ። እንዲህ ይነበባል፦ "ይህን ውኃ የእጅ ፓምፑን ለማስነሳት ተጠቀምበት፣ እናም ጠርሙሱን መልሰህ መሙላትን አትርሳ።"
ይህ እንግዳ ሁኔታ ነበር። ሰውየው ውኃውን መጠጣት እንዳለበት ወይም ፓምፑን ለማስነሳት ወደ ውስጥ መክተት እንዳለበት መወሰን አልቻለም። በአእምሮው ውስጥ ሁሉም ዓይነት ጥያቄዎች ተነሱ፦ ውኃውን ከከተትኩ በኋላ ፓምፑ ባይሠራስ? ማስታወሻው ውሸት ቢሆንስ? የመሬት ውስጥ ውኃውም ደርቆ ቢሆንስ? ነገር ግን ፓምፑ ቢነሳስ? ማስታወሻው እውነት ቢሆንስ? ምን ማድረግ እንዳለበት ሊገባው አልቻለም።
ከዚያም፣ ካሰበ በኋላ ጠርሙሱን ከፍቶ በሚንቀጠቀጡ እጆቹ ውኃውን ወደ ፓምፑ ውስጥ መክተት ጀመረ። ውኃውን ከከተተ በኋላ ወደ እግዚአብሔር ጸለየና ፓምፑን መሥራት ጀመረ። አንድ፣ ሁለት፣ ሦስት... እና ቀዝቃዛ፣ ንጹሕ ውኃ ከእጅ ፓምፑ መፍሰስ ጀመረ! # ተዋነይ - Tewanay
ያ ውኃ ሕይወት ሰጪ ነበር። ሰውየው እስኪረካ ጠጣ፤ ሕይወቱ ተመለሰ። አእምሮው እንደገና መሥራት ጀመረ። ጠርሙሱን እንደገና በውኃ ሞልቶ ከጣሪያው ላይ አሰረው። ይህን ሲያደርግ፣ ከፊት ለፊቱ ሌላ የመስታወት ጠርሙስ አየ። ከፈተውና በውስጡ እርሳስና ከበረሃው መውጫ መንገድ የሚያሳይ ካርታ አገኘ።
ሰውየው መንገዱን በቃሉ ይዞ ካርታ ያለበትን ጠርሙስ ወደነበረበት መለሰው። ከዚህ በኋላ የራሱን የውኃ ጠርሙሶች (አስቀድሞ የነበሩትን) ሞልቶ መሄድ ጀመረ። ጥቂት ርቀት ከተጓዘ በኋላ አንድ ጊዜ ወደ ኋላ ተመለከተና ካሰበ በኋላ ወደ ጎጆዋ ተመልሶ በውኃ በተሞላው ጠርሙስ ላይ የተለጠፈውን ወረቀት አነሳና በላዩ ላይ የሆነ ነገር መጻፍ ጀመረ። እንዲህ ሲል ጻፈ፦ "እመኑኝ፣ ይህ የእጅ ፓምፕ ይሠራል!"
ይህ ታሪክ ስለ ሕይወት ራሱ ነው። በጣም አስቸጋሪ በሆነ ሁኔታ ውስጥ እንኳን ተስፋ መቁረጥ እንደሌለብን ያስተምረናል። የዚህ ታሪክ ምግባራዊ ትምህርትም ታላቅ ነገር ከማግኘታችን በፊት ከእኛ በኩል የሆነ ነገር መስጠት እንዳለብን ነው—ልክ ሰውየው ፓምፑ እንዲሠራ ለማድረግ በእጁ የነበረውን ውኃ በሙሉ እንደከተተው።
ብታዩት፣ በዚህ ታሪክ ውስጥ ያለው ውኃ በሕይወት ውስጥ ያሉትን ጠቃሚ ነገሮች ይወክላል፤ በአይናችን ውስጥ ልዩ ዋጋ ያላቸውን ነገሮች። ለአንዳንዶች ይህ መልእክት እውቀት ሊሆን ይችላል፣ ለሌላው ፍቅር፣ ለሌላ ሰው ደግሞ ገንዘብ ሊሆን ይችላል። ምንም ይሁን ምን፣ እሱን ለማግኘት በመጀመሪያ በድርጊታችን የእጅ ፓምፕ ውስጥ መክተት አለብን፤ በምላሹም ካዋጣችሁት አስተዋጽኦ እጅግ በላቀ መጠን መልሳችሁ ታገኙታላችሁ

❤20