".ይህንን አልስማ "
@Mgetem
የኖህ መሸሸጊያ አምሳለ ሐመሩ
የሙሴ ሰገነት የምስጢር ደብሩ
አማሌቅ ሊያጠፋሽ ሲመክር ሲሰማማ
አኔ ልቅደም ካአንቺ ይህንስ አልስማ
...............................ይህንን አልስማ
ክርስቶስ የዘራሽ የስንዴዋ አዝመራ
የማጠፊው መብራት ያለሽ በተራራ
የጴጥሮስ መሠረት አለት ሽልማቱ
አይስማ ጆሮዬ ሲያሳዱሽ በከንቱ
የአትናቴዎስ እርሻ የቄርሎስ ቡቃያ
የዴስቆርዮስ ፍሬ የጽናት ማሳያ
የዮሐንስ ትምህርት አፈ ወርቅነቱ
አልይሽ እናቴ ሲበላሽ እሳቱ
...........................ይህንስ አልስማ
ከ Biruk Asamere
@Mgetem
@Mgetem
@sulamatiz

👍7
#መስከረም_ሲታጠን
(ዲ/ን ሕሊና በለጠ)
@Mgetem
ከብሶት አድማስ ሥር - ከጽልመቱ ማዶ - የብርሃን ጎህ ሲቀድ፣
በሃይማኖት ፍቅር - ሀገር ልቡ ነዶ - ፍርሐት ሲቀረደድ፣
የእማትን ልቅሶ - የአበውን እንባ - የውርዛዌን ወኔ፣
የአንድነትን እርሾ - የአትንኩንን ካባ - የፍትሕን ጠኔ፣
ከእግዚኦታው ማዕድ - ከካህናቱ ዕድ - ይህን ኹሉ ይዞ፣
ዕጣኑ ዐረገ - ወጣ ወደ ሰማይ - ሺ ጸሎት አርግዞ።
በታደለች ሰንበት - ዣን ተከል ሥር ያለው - ወዲህም ከጦሳ፣
በሃይማኖት እሳት - ልቡ የተቃጠለው - የመንፈሱን እንጂ - የምድሩን
ቢረሳ፣
ይግባኙን ወደ ላይ - በእግዚኦታ ሊያደርስ - በአንድነት ሲነሣ፣
ምድር ሰማይ ሆነች - ሰውም መልአክ ሆነ - ግዙፋን ረቀቁ፣
ሰላማዊ ብለው - በሰማያዊ ሰልፍ - ከሰማይ ታረቁ።
በዚህችስ ሰንበት - ግዙፍ አይደለች ምድር - አፈርም የለባት፣
ከኢዮር ከኤረር - ከራማ የተለየ - ምንስ ተሠራባት?
በዚህችስ ሰንበት.....
የመላእክት ሀገር - ኢዮር ኤረርና - ራማ ብቻ አይደሉ፣
ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ - መሐረነ ክርስቶስ - እግዚኦ እያሉ፣
ማዕጠንቱን ይዘው - ጎንደርና ወሎም - ለሦስቱ ሰማያት - ራብዓይ
ሆነው ዋሉ።
እኛስ የምናውቀው - በዕለተ መልአኩ - በ12ኛው ቀን - ኅዳር ሲታጠን
ነው፣
ሀገር መልአክ ኾኖ - በ12ኛ ዓመት (2012) - ወሎና ጎንደር ላይ -
መስክዬን አጠነው።
መስከረም ሲታጠን...
ከልቡና ደጃፍ - ብሔር ሚሉት ዕድፍ፣
በማዕጠንት ምድጃ - ተጠርጎ ሲራገፍ፣
ጎጥ ሚሉት ቆሻሻ - ዘር የሚሉት ትቢያ፣
ነዶ ሲቀጣጠል - በፍቅር ማራገቢያ፤
መስከረም ሲታጠን - ከኦርቶዶክስ አድማስ ሥር፣
የምድሩ ያየሩ - የሲዖሉ ጋኔን - በጢሱ ሲታወር፣
ወዶ የታወረው - የጋኔኑ ቢጤም - ተባሉ ተጣሉን - በትግኃት ሲዘክር፣
ይህን ለመመስከር - አላየሁ አልሰማሁ - ብሎ ሲግደረደር፣
ያደለው ዐይናማ - የመላእክቱን ዐይን - ዐይኑ ያደረገ
ከሰልፈኞቹ ጋር - ያየውን መስክሮ - በክብር ዐረገ።
መስከረም ሲታጠን....
የተስፋ ብርሃን - በአቅሌስያ ደጃፍ - ጭል ጭል እያለ፣
የበሯ ላይ ጽልመት - በአንድነቱ ክንድ - የሚናድ መሰለ።
መስከረም ሲታጠን - የዕጣኑ መዓዛ - ደቡብ ላይም ሔደ፣
ሰሜንና ምሥራቅ - ምዕራብ ላይም ሔደ፣
ለሃይማኖት የመሞት - ሰማዕት የመሆን - ጥብዓት እያወደ።
መስከረም ሲታጠን....
ጥቅምትና ኅዳር - ታኅሣሥና ጥር - መጋቢት ሚያዝያም - ፈክተው
ይውላሉ፣
ቤተ ክርስቲያን ሆይ - ክረምትሽ አለፈ - በጋ ነው እያሉ።
@Mgetem
@Mgetem
@Solasc

👍8❤2
Forwarded from የorthodox መዝሙር ብቻ
ሥላሴን አመስግኑ
ሥላሴን አመስግኑ (፪)
የምድር ፍጥረታት ዘምሩ እልል በሉ
በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ
ምስጋና ይገባል ከምንም በፊት
ዓለማትን ሁሉ ለፈጠረ ጌታ
ምስጋና ይገባል ከጠዋት እስከ ማታ
አዝ = = = = =
ኪሩቤል ሱራፌል የሚያመሰግኑት
መላእክት በሰማይ የሚዘምሩለት
እኛም የአዳም ልጆች እንዘምራለን
በሰማይም በምድር እንጠራሃለን
አዝ = = = = = =
ብራብ በሥላሴ እጠግባለሁኝ
ብጠማም በአምላኬ እረካለሁኝ
ሥላሴ አምባዬ ክብሬ ናቸውና
ሁሌ ይመሩኛል በህይወት ጎዳና
💞 @yeorthodoxmezmur 💟
💘 @yeorthodoxmezmur 💓
💖 @yeorthodoxmezmur 💝
ሥላሴን አመስግኑ (፪)
የምድር ፍጥረታት ዘምሩ እልል በሉ
በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ
ምስጋና ይገባል ከምንም በፊት
ዓለማትን ሁሉ ለፈጠረ ጌታ
ምስጋና ይገባል ከጠዋት እስከ ማታ
አዝ = = = = =
ኪሩቤል ሱራፌል የሚያመሰግኑት
መላእክት በሰማይ የሚዘምሩለት
እኛም የአዳም ልጆች እንዘምራለን
በሰማይም በምድር እንጠራሃለን
አዝ = = = = = =
ብራብ በሥላሴ እጠግባለሁኝ
ብጠማም በአምላኬ እረካለሁኝ
ሥላሴ አምባዬ ክብሬ ናቸውና
ሁሌ ይመሩኛል በህይወት ጎዳና
💞 @yeorthodoxmezmur 💟
💘 @yeorthodoxmezmur 💓
💖 @yeorthodoxmezmur 💝
❤2👍2
Forwarded from የorthodox መዝሙር ብቻ
ብዙ ልጆች አሉት ለስሙ ምስክር
በዙሪያዉ ያሉት አብቅቷል ለክብር
ስለ ፍጹም ምልጃዉ የኔ ግን ይለያል
መልኩ ሚካኤል ስለዉ ደስ ይለኛል
አዝ
ከመላእክት ክብሩ ከፍ ከፍ ብሎ
በአምላክ የተሾመ ዘንዶዉንም ጥሎ
አሳዳጊየ ነዉ ሆኖ እናት አባቴ
ሚካኤል ባለበት ይሸሻል ጠላቴ
አዝ
ከሚታየዉ ሁሉ ልቤ ከሚፈራዉ
ካላየሁት ነገር ጠላት ከሰወረዉ
ያድነኛል ፈጥኖ ከመንገዴ ወቶ
ሚካኤል ሀያሉ ክንፎቹን ዘርግቶ
አዝ
በባህራን ታሪክ በነ ጠናፊኖስ
በአፎሚያ መትረፍ በነዱረታዎስ
በነብዪ ዳንኤል የጭፍን ሰምና
የሚካኤል ስራ ይቀጥላል ገና
አዝ
በጉዞ የረዳችሁ በባህር በየብሱ
ፈጥኖ ደርሶላችሁ እንባን ስታፈሱ
ስለታችሁ ሰምሯል ቁሙ በዝማሬ
በሚካኤል ምልጃ የቆማችሁ ዛሬ
አዝ
ክብር ለሚገባዉ ክብርን እንሰጣለን
ንጉስ ለወደደዉ እንሰግድለታለን
እንኳን ለሚካኤል ለሚቆም ጌታ ፊት
ክብርን እንሰጥ የለ ለምድር ሹማምት
💟 @yeorthodoxmezmur
💖 @yeorthodoxmezmur
💘 @yeorthodoxmezmur
በዙሪያዉ ያሉት አብቅቷል ለክብር
ስለ ፍጹም ምልጃዉ የኔ ግን ይለያል
መልኩ ሚካኤል ስለዉ ደስ ይለኛል
አዝ
ከመላእክት ክብሩ ከፍ ከፍ ብሎ
በአምላክ የተሾመ ዘንዶዉንም ጥሎ
አሳዳጊየ ነዉ ሆኖ እናት አባቴ
ሚካኤል ባለበት ይሸሻል ጠላቴ
አዝ
ከሚታየዉ ሁሉ ልቤ ከሚፈራዉ
ካላየሁት ነገር ጠላት ከሰወረዉ
ያድነኛል ፈጥኖ ከመንገዴ ወቶ
ሚካኤል ሀያሉ ክንፎቹን ዘርግቶ
አዝ
በባህራን ታሪክ በነ ጠናፊኖስ
በአፎሚያ መትረፍ በነዱረታዎስ
በነብዪ ዳንኤል የጭፍን ሰምና
የሚካኤል ስራ ይቀጥላል ገና
አዝ
በጉዞ የረዳችሁ በባህር በየብሱ
ፈጥኖ ደርሶላችሁ እንባን ስታፈሱ
ስለታችሁ ሰምሯል ቁሙ በዝማሬ
በሚካኤል ምልጃ የቆማችሁ ዛሬ
አዝ
ክብር ለሚገባዉ ክብርን እንሰጣለን
ንጉስ ለወደደዉ እንሰግድለታለን
እንኳን ለሚካኤል ለሚቆም ጌታ ፊት
ክብርን እንሰጥ የለ ለምድር ሹማምት
💟 @yeorthodoxmezmur
💖 @yeorthodoxmezmur
💘 @yeorthodoxmezmur
❤3👍2
መራራ ሕይወቴ
መራራ ሕይወቴ ጣፈጠ በማርያም
ማዘን ስደት ይቅር እስከ ዘለዓለም
ተፈውሷልና በእመቤታችን
የመሪባ ውኃ ተባረከልን
በእግዝእትነ ማርያም እንድናለን
አዝ.........
ሀገሪቱ መልካም ኑሮዋ መራራ
በስደት አለቀ ወገኔ በተራ
ሽማግሌ እንዲጦር ህፃናት እንዲያድጉ
ኤልሳዕን የሚተካ አባት ሰው ፈልጉ
ማሰሮ አምጡ ጨውም ጨምራችሁ
ሞት አንዳይነግስ በመካከላችሁ
ማረን እንበል ኤሎሄ ብለን
እንዋደድ እንዲሰምርልን
ትውልድ ሁሉ ብፅዕት የሚሉሽ
ኢትዮጵያን እንባዋን አብሽ
አዝ.........
ታለቅሳለች እና እማማ ኢትዮጵያ
የወላዶች መካን አርገዋት ልጆቿ
ዓለሙም ንብረቱም ሁሉም ያልፋልና
ይበቃናል እንበል በቀና ልቦና
የህፃናት ድምፅ ተሰማ በራማ
ስለሆነች ምድሪቱ አኬልዳማ
የዘገየ ቢመስል እግዚአብሔር
ቀድሞ ይፈርዳል ሳሉ በምድር
የአቤል ደም ፀባኦት ደረሰ
ቃየልስ ወዴት ገሰገሰ
ለአዛኝቷ ሁሉ ይሆናልና
ንገሯት በጽኑ ልመና
አዝ........
አኔ የኬፋ ነኝ የአጵሎስ አትበሉ
የተለያየ መንግስት አይጸናም እንዲሉ
የኢትዮጵያ ልጆች አንድ ነን ሁላችን
ልዩነት እናጥፋ ከመካከላችን
ስንዴ መሃል እንክርዳድ አንዝራ
ተደምስሷል የዲያበሎስ ሴራ
በአስጨናቂዎች እጅ አትጣለን
ፍረድልን እናነባለን
ለልጁ አባት ይገደዋልና
አምላክ ሆይ ተመልከተን ናና
ስለማርያም ብለን ለምነን
አልፈናል ያን ክፉ ዘመን
አዝ...........
ሀገርን አይተውም ያለ አንዳች ጻድቅ
ስውሩም ይታያል አይሆንም ድብቅ
የአባቶቼ እርስት ስሟ ቶኔቶር
ገበዟ ጊዮርጊስ ነው አሥራት የድንግል
ዳሯን እሳት መሃሏን ገነት
ለእኛም ይስጠን ፍቅር አንድነት
የተሰዓቱ ቅዱሳን መሸሻ
ኖላዊ ኄር ጠባቂሽ ነው ጋሻ
ትውልድ ሁሉ ብፅዕት የሚሉሽ
ኢትዮጵያን እንባዋን አብሽ
ትውልድ ሁሉ ብፅዕት የሚሉሽ
ሀገሬን እንባዋን አብሽ
🙏 @yeorthodoxmezmur🙏
🙏 @yeorthodoxmezmur🙏
🙏 @yeorthodoxmezmur🙏
መራራ ሕይወቴ ጣፈጠ በማርያም
ማዘን ስደት ይቅር እስከ ዘለዓለም
ተፈውሷልና በእመቤታችን
የመሪባ ውኃ ተባረከልን
በእግዝእትነ ማርያም እንድናለን
አዝ.........
ሀገሪቱ መልካም ኑሮዋ መራራ
በስደት አለቀ ወገኔ በተራ
ሽማግሌ እንዲጦር ህፃናት እንዲያድጉ
ኤልሳዕን የሚተካ አባት ሰው ፈልጉ
ማሰሮ አምጡ ጨውም ጨምራችሁ
ሞት አንዳይነግስ በመካከላችሁ
ማረን እንበል ኤሎሄ ብለን
እንዋደድ እንዲሰምርልን
ትውልድ ሁሉ ብፅዕት የሚሉሽ
ኢትዮጵያን እንባዋን አብሽ
አዝ.........
ታለቅሳለች እና እማማ ኢትዮጵያ
የወላዶች መካን አርገዋት ልጆቿ
ዓለሙም ንብረቱም ሁሉም ያልፋልና
ይበቃናል እንበል በቀና ልቦና
የህፃናት ድምፅ ተሰማ በራማ
ስለሆነች ምድሪቱ አኬልዳማ
የዘገየ ቢመስል እግዚአብሔር
ቀድሞ ይፈርዳል ሳሉ በምድር
የአቤል ደም ፀባኦት ደረሰ
ቃየልስ ወዴት ገሰገሰ
ለአዛኝቷ ሁሉ ይሆናልና
ንገሯት በጽኑ ልመና
አዝ........
አኔ የኬፋ ነኝ የአጵሎስ አትበሉ
የተለያየ መንግስት አይጸናም እንዲሉ
የኢትዮጵያ ልጆች አንድ ነን ሁላችን
ልዩነት እናጥፋ ከመካከላችን
ስንዴ መሃል እንክርዳድ አንዝራ
ተደምስሷል የዲያበሎስ ሴራ
በአስጨናቂዎች እጅ አትጣለን
ፍረድልን እናነባለን
ለልጁ አባት ይገደዋልና
አምላክ ሆይ ተመልከተን ናና
ስለማርያም ብለን ለምነን
አልፈናል ያን ክፉ ዘመን
አዝ...........
ሀገርን አይተውም ያለ አንዳች ጻድቅ
ስውሩም ይታያል አይሆንም ድብቅ
የአባቶቼ እርስት ስሟ ቶኔቶር
ገበዟ ጊዮርጊስ ነው አሥራት የድንግል
ዳሯን እሳት መሃሏን ገነት
ለእኛም ይስጠን ፍቅር አንድነት
የተሰዓቱ ቅዱሳን መሸሻ
ኖላዊ ኄር ጠባቂሽ ነው ጋሻ
ትውልድ ሁሉ ብፅዕት የሚሉሽ
ኢትዮጵያን እንባዋን አብሽ
ትውልድ ሁሉ ብፅዕት የሚሉሽ
ሀገሬን እንባዋን አብሽ
🙏 @yeorthodoxmezmur🙏
🙏 @yeorthodoxmezmur🙏
🙏 @yeorthodoxmezmur🙏
👍6❤1
#እስከዛው_ተኝቼ_ልክረም
@Mgetem
ጌታ ሆይ!
በምድር በዚች ዓለም ላይ - ጥቂት ቀናትን መክረሜ፣
አሳዝኖህ አዝነህልኝ - ከጨመርክልኝ ዕድሜ፣
የአቤሜሌክን እንጂ - የማቱሳላን አልሻም፣
ከ60 ዓመታት እንቅልፍ የ9 ምዕት ኑሮ አልመርጥም፡፡
እንደማቱሳላ ኖሬ - ከድህነት ከምታገል - መከራ ችግርን ከማይ፣
በጎዶሎዋ ምድር - ሳይሞላልኝ ከምሰቃይ፣
60 ዓመት ላንቀላፋ - ዘመነ እንቅልፍ ስጠኝ ከላይ፡፡
ለተዳከመው ገላዬ - ኑሮ ላዛለው አካሌ፣
ልትጨምርልኝ ከዳዳህ - ለዕጣ ፈንታ ለዕድሌ፣
የእንቅልፍ ዕድሜን እንጂ - ቀን አልሻም የመከራ፣
መተኛት እንጂ መቅበዝበዝ -ይቅርብኝ ጌታ አደራ፡፡
እንደ ፃድቁ አቤሜሌክ - ኢትዮጵያዊ ነኝና፣
እንደው የዘር ሆኖብኝ - መተኛት ያምረኛልና፣
እንዳልሠራ እንድጋደም፣
ጥፋቷን መድማቷን ከማይ - የሀገሬን ርሃብ ጥም፣
ሲመቻት ብቻ ቀስቅሰኝ እስከዛው ተኝቼ ልክረም፣
እንዳንቀላፋ እንዳልደክም፣
ዘመነ እንቅልፍን ስጠኝ - ዕድሜ አድለኸኝ ልጋደም፣
መቼስ ስስት አያውቅህም፡፡
©ዘሕሊና
፨፨፨ ፨፨፨ ፨፨፨ ፨፨፨ ፨፨፨ ፨፨፨
(- አቤሜሌክ የኢየሩሳሌምን ጥፋት እንዳያይ 66 ዓመት በተዐምር
እንዲተኛ የተደረገ ኢትዮጵያዊ ነው፡፡ /ትንቢተ ኤርሚያስ/
- ማቱሳላ 969 ዓመታትን የኖረ፣ በዕድሜ የሰውን ዘር ኹሉ የሚበልጥ
ነው፡፡ /ኦሪት ዘፍጥረት/
- የአቤሜሌክ 66 ዓመት መተኛት 60 መባሉ፣ የማቱሳላም 969 ዓመት
ዕድሜ 9 ምዕት/9 መቶ/ መባሉ አጠጋግቶ መቁጠር የአባቶች ልማድ
በመኾኑ ነው - 318ቱን ሊቃውንት ሠለስቱ ምዕት፣ 72ቱን ሊቃናትን
ሰባው ሊቃናት እንዲል፤)
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
@Mgetem
@Mgetem
@solasc

👍4
Forwarded from Kesatebirhan Ze Tewahdo (Channel Manneger፹)
መስቀል እና ኢትዮጵያ
@boaneerges
መስቀል ማለት የተመሳቀለ ዕፅ/ እንጨት/ ማለት ነው፡፡ መስቀል በብሉይ ኪዳን ላይ/ በኦሪት ህግ/ የእርግማን ምልክት ነበረ፡፡ ‹‹በእንጨት ላይ የተሰቀለ በእግዚእሄር ዘንድ የተረገመ ነው፡፡›› (ዘዳ 21፣23) ክብር ይግባውና ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እስኪሰቀልበት ድረስ የእርግማን ምልክት ተደርጎም ይወሰድ የነበረ ነው፡፡ ከክርስቶስ ስቅለት በኀላ ግን ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በእንጨት/ዕፅ/ ምክንያት ከገባንበት እርግማን በእንጨት ላይ ተሰቅሎ ከእርግማናችን ነፃ አውጥቶናል፡፡ስለዚህ ቅዱስ መስቀል የእርግማን ምልክት መሆኑ ቀርቶ የድኅነት ምልክት ፣የነፃነት አርማ፣ መመኪያችን፣ መዳኛችን፣ ትምክህታችን ሆኗል፡፡
ወደ ርዕሳችን መለስ እንበልና ስለ መስቀልና ኢትዮጵያውያን እንነጋገር፡፡ ለኢትዮጲያውያን ስለ መስቀል መናገር ለቀባሪው ማርዳት ቢሆንብንም ባለን ውስን አቅም ግን አይንን ለመክፈት ልብን ለማንቃት የምትሆን ነገር ለመናገር እንሞክራለን፡፡
በአለም ላይ ለመስቀል ቅርብ ከሆኑት ሀገራት መካከል የግንባር ቀደሙን ቦታ የምትይዘው ኢትዮጵያ ናት፡፡ ምንም እንኳን ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የተሰቀለበትን መስቀል በጊዜው ጠንካራ የአለም መንግስታት የነበሩት ሲከፋፈሉት ለኢትዮጵያውያን ባይደርስም በ15ኛው ክፍለ ዘመን በጻድቁ አፄ ዘርዓ ያዕቆብ የንግስና ዘመን ላይ በግብፅ የነበረው የቀኙ ግማደ መስቀል ወደ ሀገራችን ገብቶ በግሽን አምባሰል ተራራ ላይ ሊቀመጥ ችሏል፡፡ለምን ወደ ሀገራችን ሊገባ ቻለ ለሚለው ሰፊ ማብራሪያ ቢኖረውም እኛ ግን አንድ ነገር ጠቅሰን እንለፍ፡፡ ስለ መስቀሉ ኢትዮጲያ መምጣት ባሰብን ጊዜ ወደ ልባችን ጊዜ አንድ ቃል ሁል ጊዜ ታቃጭላለች ‹‹ መስቀሌን በመስቀለኛ ቦታ ላይ አስቀምጥ›› ለዚህች ቃል ብዙዎቻችን አዲስ አይደለንም፡፡ እስኪ አንድ ጊዜ የአዕምሮአችንን ባቡር እናስነሳና የኢትዮጲያን ትክክለኛ ካርታ አሰሳ እንውጣ ማለቴ ኤርትራ ያልተገነጠለችበትን መሬታችንም ለጂቡቲና ለሱዳንና ያልተሸጡባትን ካርታ ማለቴ ነው፡፡ አገኛቹት? አዎ ምልክቱ ምን ይመስላል? ብዙ አትጠራጠር የመስቀል ቅርፅ ነው ያለው፡፡ ስለዚህ ከላይ ባነበብነው ቃል መሰረት ለቅዱስ መስቀል ትክክለኛ ማረፊያ ማነች? ኢትዮጲያ!!! መስቀለኛው ተራራ ደግሞ ግሽን ላይ ነው፡፡
አሁን ደግሞ ኢትዮጲያ ለመስቀል ያላትን ክብርና ቦታ ለሁለት ከፍለን እንመልከት፡
ዕምነታዊ ክብርና ቦታ
ባህላዊ ክብርና ቦታ
❖ዕምነታዊ ክብርና ቦታ፡ ለስንዱዋ እመቤት ለኢትዮጲያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን መስቀል ማለት የክርስቶስ ምልክት፣ ከሲኦል መከራና ስቃይ የዳነችበት፣ የነፃነት አርማዋና መመኪያዋም ነው፡፡ ለዛም ነው በዕለት ተዕለት አገልግሎቶቿ ላይ መስቀልን በአፏ ትመሰክራለች፣ በወንጌልዋ ትሰብከዋለች፣ በአገልግሎቷ ትይዘዋለች፡፡ ይህም ማለት በመሰረታዊ የሃይማኖት ጸሎቶቿ ውስጥ ‹‹መስቀል ሃይላችን ነው ሃይላችን መስቀል ነው የሚያፀናን መስቀል ነው መስቀል ቤዛችን ነው መስቀል የነፍሳችን መዳኛ ነው አይሁድ ይክዱታል እኛ ግን እናምነዋለን ያመነው እኛም በመስቀሉ እንድናለን ድነናልም›› ብላ ዘወትር የምትጸልየውና የምትመሰክረው፡፡
ያዕቆብ ዘአልበረዲ ሰዎች ወደ ክርስትና ዕምነት አምጥቶ በሚያጠምቅበት ሰዓት ሁለቴ ጥምቀት ስለሌለ የተጠመቁትን ካልተጠመቁት ለመለየት በአንገታቸው ላይ ክር ያስር ነበር፡፡ የትውፊት ሁሉ መገኛ የሆነቸውን የኢትዮጵያ ኦርቶዶከስ ቤተክርስቲያንም የያዕቆብ ዘአልበረዲን ፈለግ በመከተል ልጆቿን ከአሕዛብና ከመናፍቃን ለመለየት በአንገታቸው ላይ የክርስቶስን መስቀል እንዲያስሩ ታስተምራለች፡፡ ቤተ ክርስቲያንም ስታንፅ በጉልላቷ ላይ መስቀልን የምታደርግበትም ምክንያት መስቀል ለቤተክርስቲያኗ አርማና መለያ ስለሆነ ነው፡፡
በቅዳሴዋና በኪዳኗ ላይም መስቀልን ይዛ ስለ ነፃነታችን ትሰብካለች፡፡ ከመስቀሏ በረከትን እንድናገኝ በካህናቷ ታሳልማለች፣ ትባርካለችም፡፡
ከዚህ በተጨማሪም በአደባባይ ወታ ለመስቀሉ መገኘት ዋነኛ ምክንያት የሆነውን የደመራን በዓል በመስከረም 16 ላይ በድምቀት ታከብራለች፡፡ ከ18ቱ የጌታ በዓላትም አንዱ ነው ብላ ታስተምራለች፡፡
❖ባህላዊ ክብርና ቦታ፡ ኢትዮጵያውያንና ለመስቀል ያላቸው ቁርኝነት ጠበቅ ያለ ነው፡፡ ግንኙነታቸው የሚጀምረው ግማደ መስቀሉ ወደ ሀገራችን ከገባበት ዘመንም ይቀድማል፡፡ ለዚህም ማሳያ የሚሆነን በስማቸው፣ በአለባበሳቸው፣ በመሀላቸው፣ በተለያዩ ኪነህንፃዎቻቸው ላይ መጠቀማቸው ነው፡፡
ለምሳሌ በ6ኛው ክፍለ ዘመን በሀገራችን ላይ የነገሰውን አፄ ገብረ መስቀልን ልብ ይሏል፡፡
በ12ኛው ክፍለ ዘመን በኢትዮጲያ ኪነ ህንፃ ላይ ደማቅ አሻራውን ያኖረው ቅዱስ ላሊበላ የገነባቸው 11ዱ አብያተ ክርስቲያናት መመልከት በራሱ ኢትዮጵያና መስቀል ያላቸውን ግንኙነት በሰፊው ያሳያል፡፡ በተለይም የመስቀል ቅርፅ ያለውን ቤተ ጊዮርጊስን ማየት ብቻ በቂ ነው፡፡
የኢትዮጲያውያንን የባህል ልብስ ለተመለከተ ደግሞ ከላይ ከአንገታቸው አካባቢ በክብ ጥለት ይወርድና በእግራቸው ላይ ከፊት ለፊት በኩል መስቀል ከኃላ ደግሞ ጥለት ተደርጎ ይሰራል፡፡ጥለቱ የአለም ምሳሌ ሲሆን መስቀሉ ደግሞ የመንፈሳዊ ህይወት ምሳሌ ነው፡፡ ይህም ማለት ጥለት የሆነውን አለም ወደ ኃላ ትቼ መንፈሳዊነትን ከፊቴ አስቀድሜያለው ማለት ነው፡፡
አብዛኛው የደቡብ ኢትዮጵያ ሕዝቦችም የዘመን መለወጫቸውን የመስቀል በዓል ላይ ተመርኩዘው ማክበራቸውም ለመስቀልና ኢትዮጵያውያን ግንኙነት እንደማሳያ ነው፡፡
በአጠቃላይ መስቀል በኢትዮጵያና በጵያውያን ላይ በእምነታቸው፣ በባህላቸውና በአመለካከታቸው ውስጥ ታላቅ ሚና ያለው ነው፡፡ ሁላችንም
ስንጀምር አብሮን የነበረ እስክንፈፅም የረዳን የአባቶቻችን አምላክ እግዚአብሔር ይክበር ይመስገን፤ የመስቀሉ ፍቅርና በረከት በሁላችን ላይ ይደር፤ አሜን!!!
‹‹ወስበሀት ለእግዚአብሄር፣ ወለወላዲቱ ድንግል፣ ወለመስቀሉ ክቡር››
ተፃፈ በናሆም ግርማ
@Boaneerges
ለአስተያየት እና ጥያቄ
@AskBoaBot

❤4👍4
#ተዋሕዶ
@Mgetem
በመንገድ ላይ ስብከት ያልተገኘች ነበጊታር ፒያኖ በጭፈራ ያልኖረች
ከመፅሀፍ ቅዱሱ አንዱን ያልዘዘለለች
አስቲ ለምሣሌ
የቅዱሣን ፃድቃን ምልጃቸውን ንቀው
ሰማዕታት የሞቱት ለይምሰል ነው ብለው
ዘመናዊ ሀይማኖት ይሻለናል ያሉ
በዘመን አመጣሽ ጌታን ተቀበሉ በአስመሳይ ትህትና ሰውን የሚያታሉ
በአለት ድንጋይ ላይ አሉ የበቀሉ
ሌላም አለ ደግሞ በጨረቃ ያመነ
በጨረቃ ስግደት ልቡ የደነደነ
በየዘመናቱ ሀይማኖት ተነስቶል
ለፅድቅ እና ለእዉነት ማን እንዳንቺ ሆኖል
በዘመን ቅብብል ምንሽ ተቀይሯል
እንደ ተዋህዶ በአምላክ የከበረ አረ የት ይገኛል
አቃጥልናት ያሉ የሉም በምድር ላይ
ተዋህዶ አዲስነሽ ሁል ጊዜ እንደ ሠማይ
ገና ትደምቃለሸ በዓለም አደባባይ
ክብርሽ ክርስቶስ ኤልሻዳይ አዶናይ
©ወልደ ሰንበት

❤1
ውድ ቤተሰቦቻችን እባካችሁ ለሁሉም ይድረስ ይህ መልዕክት አሁን ምንኖርባት ጊዜ ፈተና መከራ ስርማህትነት የተመላች ናትና
ይድረስ ለሁሉም የተማማርናትን የእውነት ቃል እንተግብራት እባካችሁ እንጸልይ እናልቅስ እንመለስ
#እባካችሁ #እንጸልይ #እናልቅስ በእንባ ወደ እርሱ እንመለስ
#አምላክ ይታረቀን ዘንድ
#እንጸልይ
#እናልቅስ
ያወቅናትን ትንሽ እውነት እንኑር አምላክን እንማጸነው
#ስለ ሀገራችን ሰላም
#ስለ ካህናት አባቶቻችን
#ስለ ዲያቆናት ወንድሞቻችን
#ስለ ቅድስት ቤተክርስቲያን
#ስለ ህዝባችን
#ስለ በደላችን
#ስለ በዛው ኃጢአታችን
ስለ ሀገራችን ሰላም እናልቅስ እንጸልይ እንመለስ እባካችሁ አንድ እንሁን አምላክ ይታረቀን ከመሃቱ ይጠብቀን ዘንድ
#እንጸልይ #እናልቅስ
#ውድ ቤተሰቦቼ ስለ እውነት ንጽህት ስለ ሆነች ስለ እመ አምላክ እማጸናችኃለሁኝ
ከአሁኑዋ ሰዓት ጀምሮ እናልቅስ ስለ ሁላችንም ሰላም እባካችሁ እናልቅስ አምላክ ይታረቀን ዘንድ
የበረከት ሀገራችውን ቅዱሳን ያስምሩልን ዘንድ እባካችሁ እንጸልይ
#ስለ አቡነ ተክለሃይማኖት
#ስለ አቡነ ሀብተ ማርያም
#ስለ አቡነ ዜና ማርቆስ
#ስለ አቡነ እስትንፋሰ ክርስቶስ
#ስለ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ
#ስለ አቡነ ገብረ ክርስቶስ
#ስለ አቡነ አረጋዊ
#ስለ አቡነ ተክለ ሐዋርያት
#ስለ አቡነ ክርስቶስ ሞዓ
#ስለ አቡነ አባ ክርስቶስ ቤዛነ ስለ ቃልኪዳን ሀገራቸው ምህረትን ያሰጡን ዘንድ #እንጸልይ #እናልቅስ
#ሼር እናድርግ
ሁሉም ህዝበ ክርስቲያን በአንድነት የቤተክራቲያን ድምጽ እንስማ እንተግብር እንዳን የንስሃ እድሜ ይሰጠን ዘንድ ለማይረባ ከንቱ ሞት አሳልፎ እንዳይሰጠን እንጸልይ እናልቅስ እንመለስ
ሁላችንም በአንድነት በንቃት እንመላለስ እንጠንቀቅ
በእየ ቤተክርስቲያናችን ተሰባስበን ምዕላ እናድርስ ከአባቶቻችን ጋራ በእየ ቤታችን በለቅሶ እንጸልይ እንማጸን እንላለን።
አምላክ ሀገራችንን ይጠብቅ
ይባርክ
ሁላችንንም ለተከበረ ሞት ያብቃን።
ሼር እናድርግ እባካችሁ ሁላችንም ቢያንስ 21 እህት ወንድሞቻችን ይደርሳቸው ዘንድ ሼር እናድርግ
Helansan
https://t.me/joinchat/D81j2AzEDRapYwTb2nWMsQ

👍5👎1
#እስከዛው_ተኝቼ_ልክረም
@Mgetem
ጌታ ሆይ!
በምድር በዚች ዓለም ላይ - ጥቂት ቀናትን መክረሜ፣
አሳዝኖህ አዝነህልኝ - ከጨመርክልኝ ዕድሜ፣
የአቤሜሌክን እንጂ - የማቱሳላን አልሻም፣
ከ60 ዓመታት እንቅልፍ የ9 ምዕት ኑሮ አልመርጥም፡፡
እንደማቱሳላ ኖሬ - ከድህነት ከምታገል - መከራ ችግርን ከማይ፣
በጎዶሎዋ ምድር - ሳይሞላልኝ ከምሰቃይ፣
60 ዓመት ላንቀላፋ - ዘመነ እንቅልፍ ስጠኝ ከላይ፡፡
ለተዳከመው ገላዬ - ኑሮ ላዛለው አካሌ፣
ልትጨምርልኝ ከዳዳህ - ለዕጣ ፈንታ ለዕድሌ፣
የእንቅልፍ ዕድሜን እንጂ - ቀን አልሻም የመከራ፣
መተኛት እንጂ መቅበዝበዝ -ይቅርብኝ ጌታ አደራ፡፡
እንደ ፃድቁ አቤሜሌክ - ኢትዮጵያዊ ነኝና፣
እንደው የዘር ሆኖብኝ - መተኛት ያምረኛልና፣
እንዳልሠራ እንድጋደም፣
ጥፋቷን መድማቷን ከማይ - የሀገሬን ርሃብ ጥም፣
ሲመቻት ብቻ ቀስቅሰኝ እስከዛው ተኝቼ ልክረም፣
እንዳንቀላፋ እንዳልደክም፣
ዘመነ እንቅልፍን ስጠኝ - ዕድሜ አድለኸኝ ልጋደም፣
መቼስ ስስት አያውቅህም፡፡
©ዘሕሊና
፨፨፨ ፨፨፨ ፨፨፨ ፨፨፨ ፨፨፨ ፨፨፨
(- አቤሜሌክ የኢየሩሳሌምን ጥፋት እንዳያይ 66 ዓመት በተዐምር
እንዲተኛ የተደረገ ኢትዮጵያዊ ነው፡፡ /ትንቢተ ኤርሚያስ/
- ማቱሳላ 969 ዓመታትን የኖረ፣ በዕድሜ የሰውን ዘር ኹሉ የሚበልጥ
ነው፡፡ /ኦሪት ዘፍጥረት/
- የአቤሜሌክ 66 ዓመት መተኛት 60 መባሉ፣ የማቱሳላም 969 ዓመት
ዕድሜ 9 ምዕት/9 መቶ/ መባሉ አጠጋግቶ መቁጠር የአባቶች ልማድ
በመኾኑ ነው - 318ቱን ሊቃውንት ሠለስቱ ምዕት፣ 72ቱን ሊቃናትን
ሰባው ሊቃናት እንዲል፤)
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
@Mgetem
@Mgetem
@solasc
@Mgetem
ጌታ ሆይ!
በምድር በዚች ዓለም ላይ - ጥቂት ቀናትን መክረሜ፣
አሳዝኖህ አዝነህልኝ - ከጨመርክልኝ ዕድሜ፣
የአቤሜሌክን እንጂ - የማቱሳላን አልሻም፣
ከ60 ዓመታት እንቅልፍ የ9 ምዕት ኑሮ አልመርጥም፡፡
እንደማቱሳላ ኖሬ - ከድህነት ከምታገል - መከራ ችግርን ከማይ፣
በጎዶሎዋ ምድር - ሳይሞላልኝ ከምሰቃይ፣
60 ዓመት ላንቀላፋ - ዘመነ እንቅልፍ ስጠኝ ከላይ፡፡
ለተዳከመው ገላዬ - ኑሮ ላዛለው አካሌ፣
ልትጨምርልኝ ከዳዳህ - ለዕጣ ፈንታ ለዕድሌ፣
የእንቅልፍ ዕድሜን እንጂ - ቀን አልሻም የመከራ፣
መተኛት እንጂ መቅበዝበዝ -ይቅርብኝ ጌታ አደራ፡፡
እንደ ፃድቁ አቤሜሌክ - ኢትዮጵያዊ ነኝና፣
እንደው የዘር ሆኖብኝ - መተኛት ያምረኛልና፣
እንዳልሠራ እንድጋደም፣
ጥፋቷን መድማቷን ከማይ - የሀገሬን ርሃብ ጥም፣
ሲመቻት ብቻ ቀስቅሰኝ እስከዛው ተኝቼ ልክረም፣
እንዳንቀላፋ እንዳልደክም፣
ዘመነ እንቅልፍን ስጠኝ - ዕድሜ አድለኸኝ ልጋደም፣
መቼስ ስስት አያውቅህም፡፡
©ዘሕሊና
፨፨፨ ፨፨፨ ፨፨፨ ፨፨፨ ፨፨፨ ፨፨፨
(- አቤሜሌክ የኢየሩሳሌምን ጥፋት እንዳያይ 66 ዓመት በተዐምር
እንዲተኛ የተደረገ ኢትዮጵያዊ ነው፡፡ /ትንቢተ ኤርሚያስ/
- ማቱሳላ 969 ዓመታትን የኖረ፣ በዕድሜ የሰውን ዘር ኹሉ የሚበልጥ
ነው፡፡ /ኦሪት ዘፍጥረት/
- የአቤሜሌክ 66 ዓመት መተኛት 60 መባሉ፣ የማቱሳላም 969 ዓመት
ዕድሜ 9 ምዕት/9 መቶ/ መባሉ አጠጋግቶ መቁጠር የአባቶች ልማድ
በመኾኑ ነው - 318ቱን ሊቃውንት ሠለስቱ ምዕት፣ 72ቱን ሊቃናትን
ሰባው ሊቃናት እንዲል፤)
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
@Mgetem
@Mgetem
@solasc
👍5❤4
#ሰማያዊ_ፓርቲን_ይምረጡ
@Mgetem
ምርጫ ደርሷል። ማንን ለመምረጥ አስባችኋል? እኔ “ሰማያዊ ፓርቲ”ን ብያለሁ። ደሞ ሌላ እንዳታስቡ አደራ። “አባ ፣ አባታችን ሆይ በሰማይ የምትኖር” ብለን የምንጠራበትን የልጅነት መንፈስ በጥምቀት የምታድለው ፤ “ሃገራችን በሰማይ ነው” ብለን ምንመካበትን ሰማያዊ ዜግነት ምታጎናጽፈው ፤ ሰማያዊት ኢየሩሳሌም መንግሥተ ሰማያት ምታወርሰውን ሰማያዊ ተቋም “ቅድስት ቤተ ክርስቲያንን” ማለቴ ነው።
የምርጫ ምልክቷ - መስቀል
ማኒፌስቶ - ወንጌል
ጽ/ቤት ቅርንጫፍ - አጥቢያ ቤተ ክርስቲያን በራፍ
የፓርቲው መሥራችና ሊቀመንበር - መድኃኔዓለም (ስሙ ይክበር)
ምክትል - ድንግል
የቦርድ አባላት - ቅዱሳንና ቅዱሳት
፨ ሰማያዊ ፓርቲ ተዋሕዶን ይምረጡ ፤ ጽፈው አጥፈው በልቡና ኮሮጆ ያስቀምጡ!! ፨
___________
📌ሼር

ለካስ ዛሬም አለ
(የኃዘን እንጉርጉሮ)
በዲ/ን ሕሊና በለጠ
@Mgetem
ትዕቢት ያጀገነው
ራሱን መውደዱ ልቡን ያሳበጠው
አምላኩን ለመግደል ሰይፍ የመዠረጠው
እንደ ነዳጅ ረግጦ ሰይጣን 'ሚሾፍረው
የጋኔን መኪና ሄሮድስ የተባለ
144 ሺህ ጠርቶ የገደለ
ለካስ ዛሬም አለ።
ጳውሎስ ቃል ሲያወጣ ጴጥሮስም ሲፈውስ
'ግደል' የሚል ጋኔን ከአንጀቱ ተጣብቆ ክፋቱ 'ሚላወስ
ከነገሥታት መኻል ኔሮን የተባለ ነበረ አንድ ቀውስ።
የስንቱን ከተማ መኖሪያ አቃጠለ
አንዱን በሰይፍ ጣለ
በእንጨት ላይ ዘቅዝቆ አንዱንም ሰቀለ።
ለካስ ንጉሥ ኔሮን ዛሬም ሰይፉን ስሏል
ዘቅዝቆ የመስቀሉ ሥራውም ቀጥሏል
መቅደሱን አቃጥሎ እሳቱንም ሞቋል
እንደ በቆሎ እሸት የሰው አካል ጠብሷል
ለካስ ዛሬም ኖሯል!
በቅድስቲቱ አገር ባገሬ በ'ማማ
ከጥንት ግፍ መኻል ምን አለ ያልተሰማ?
መንኮራኩር ሠርቶ አካል የሚፈጨው
የሰው አካል ገፎ የሚነሰንስ ጨው
ከአንበሳ 'ሚያታግል
በዕብን ወግሮ 'ሚገ'ል
በቁም አሥሮ 'ሚያነድድ
ቆዳ 'ሚቀረድድ
እንደ ጥንቱ ኔሮ
እልፍ ነው ዘንድሮ።
ግራኝ ግብሩ አልሞተም ሕያው ነች ዮዲትም
መቅደስ ሚያነድና ካህንን የሚሰድ አይታጣም የትም።
የነ ሜንዴዝ እሾኽ መቼ ተነቀለ?
ይኸው አመርቅዞ ስንት አማኝ ገደለ።
በአየር ላይ በሮ መርዙን የረጨብን ጥልያን መች ጠፋ
መርዝ የሚያዘንብ ኪይ ቦርድ በዘመኑ አየር ቀጥሏል ቀጠፋ።
እነ ሄሮድስ አሉ
እነ ኔሮን አሉ
እነ ግራኝ አሉ
እነ ዮዲት አሉ
ድምጥያኖስ አለ ዲዮቅልጥያኖስ
የጋኔን ቀኝ እጅ የዲያቢሎስ በርኖስ::
መክስምያኖስ አለ አማኝ እየቀጣ
ቆስጠንጢኖስ 'ሚባል ንጉሥ እስኪመጣ
______
@Mgetem
@Mgetem
(የኃዘን እንጉርጉሮ)
በዲ/ን ሕሊና በለጠ
@Mgetem
ትዕቢት ያጀገነው
ራሱን መውደዱ ልቡን ያሳበጠው
አምላኩን ለመግደል ሰይፍ የመዠረጠው
እንደ ነዳጅ ረግጦ ሰይጣን 'ሚሾፍረው
የጋኔን መኪና ሄሮድስ የተባለ
144 ሺህ ጠርቶ የገደለ
ለካስ ዛሬም አለ።
ጳውሎስ ቃል ሲያወጣ ጴጥሮስም ሲፈውስ
'ግደል' የሚል ጋኔን ከአንጀቱ ተጣብቆ ክፋቱ 'ሚላወስ
ከነገሥታት መኻል ኔሮን የተባለ ነበረ አንድ ቀውስ።
የስንቱን ከተማ መኖሪያ አቃጠለ
አንዱን በሰይፍ ጣለ
በእንጨት ላይ ዘቅዝቆ አንዱንም ሰቀለ።
ለካስ ንጉሥ ኔሮን ዛሬም ሰይፉን ስሏል
ዘቅዝቆ የመስቀሉ ሥራውም ቀጥሏል
መቅደሱን አቃጥሎ እሳቱንም ሞቋል
እንደ በቆሎ እሸት የሰው አካል ጠብሷል
ለካስ ዛሬም ኖሯል!
በቅድስቲቱ አገር ባገሬ በ'ማማ
ከጥንት ግፍ መኻል ምን አለ ያልተሰማ?
መንኮራኩር ሠርቶ አካል የሚፈጨው
የሰው አካል ገፎ የሚነሰንስ ጨው
ከአንበሳ 'ሚያታግል
በዕብን ወግሮ 'ሚገ'ል
በቁም አሥሮ 'ሚያነድድ
ቆዳ 'ሚቀረድድ
እንደ ጥንቱ ኔሮ
እልፍ ነው ዘንድሮ።
ግራኝ ግብሩ አልሞተም ሕያው ነች ዮዲትም
መቅደስ ሚያነድና ካህንን የሚሰድ አይታጣም የትም።
የነ ሜንዴዝ እሾኽ መቼ ተነቀለ?
ይኸው አመርቅዞ ስንት አማኝ ገደለ።
በአየር ላይ በሮ መርዙን የረጨብን ጥልያን መች ጠፋ
መርዝ የሚያዘንብ ኪይ ቦርድ በዘመኑ አየር ቀጥሏል ቀጠፋ።
እነ ሄሮድስ አሉ
እነ ኔሮን አሉ
እነ ግራኝ አሉ
እነ ዮዲት አሉ
ድምጥያኖስ አለ ዲዮቅልጥያኖስ
የጋኔን ቀኝ እጅ የዲያቢሎስ በርኖስ::
መክስምያኖስ አለ አማኝ እየቀጣ
ቆስጠንጢኖስ 'ሚባል ንጉሥ እስኪመጣ
______
@Mgetem
@Mgetem
👍5❤3
#ማስታወቂያ
#አድሚን_ስለሚፈለግ
ውድ የመንፈሳዊ ግጥም ብቻ ቻናላችን ተከታዮች እንደሚታወቀው መንፈሳዊ ግጥም ቻናላችን እስከዛሬ ድረስ ኦርቶዶክሳዊ ግጥሞችን ሲያቀርብላችሁ የነበረ ቻናል ነው።
ነገር ግን በአድሚኖች እጥረት እና ሥራ መደራረብ ምክንያት ባለፉት 2 ወራት ተቀዛቅዞ የቆየ መሆኑን ከእናንተ በሚመጡ አስተያየቶች ለማወቅ ችለናል። ስለሆነም የቻናላችን አድሚን በመሆን ግጥሞችን ማዘጋጀት እና መልቀቅ የምትፈልጉ 2 አድሚኖች(1 ወንድ እና 1 ሴት) ስለምንፈልግ ፍላጎቱ ያላቹ እና ከታች ያሉትን መስርት የምታሟሉ
@Solasc ላይ አናግሩን።
#መስፈርት
1, ኦርቶዶክስ መሆን
2, በሳምንት 2 ግጥም መልቀቅ የሚችል

#ማን_እንዳቺ
@Mgetem
#ማን_እንደ_አንቺ ፈጥኖ ደራሽ
#ሰላማዊት ልብን አዳሽ
አረጋጊ እንባን አባሽ፡፡
ማን እንዳቺ አዛኝቱ
#የአምላክ_እናት ድንግሊቱ
#አማላጅ_ነሽ የፍጥረቱ
ሰውን መላሽ ከስህተቱ፡፡
ማን እንዳቺ የሚየፅናና
የሚያወጣ ከፈተና
ደግፎ ከቅፎ የሚያቀና
#ማን_እንዳቺ አስታራቂ
#ሀጢአተኛን የማትንቂ
#ጆሮ_ዳባን የማታወቂ
መልካም ስራሽ አስደናቂ፡፡
ማን እንደ አንቺ መከለያ
ታማኝ እናት መጠለያ
ቀና መንገድ መታመኛ
የንስሀ በር መግቢያ፡፡
#ማን_እንደ_አንቺ ተቆርቋሪ
#የማታልፊ የሰው ጥሪ
አቤት ብለሽ አናጋሪ
ሰማያዊት ንግሰት የኛ አብሳሪ፡፡
ማን እንዳቺ ለወደቁት
#አዛኝ_አፅናኝ ንፁህ እንቁ
#ሰው_ረስቶአቸው ለተናቁት
#በሀዘን_መከራ ለወደቁት፡፡
#ማን_እንደ_አንቺ የሚረዳ
የመትሞይ የሁሉን ጓዳ
እባክሽ አውጪን ከዓለም ፍዳ
ሁዋላ ጠፍተን እንዳንጎዳ፡፡
ፀበልሽ ፈዋሽ ያለዋጋ
ለእኛ እኮነሽ ባለ አደራ
እባክሽ አውጪን ከሐጢአት ተራ
እንድንኖር ከአንቺ ጋራ፡፡
መን እንደ አንቺ ያለው ለዛ
ንግግር የሚያዋዛ
በረከትን የሚያበዛ፡፡
ማን እንደ አንቺ ልዩ ስጦታ
አምላክ ያደለን የነፍስ እርካታ
ደስ አለን ዛሬ ዲያብሎስ ሲመታ
መግቢያ መውጪያ አጥቶ ሲሄድ በአንድ አፍታ
#ስምሽ_ግሩም_ነው የህይወት ገበታ፡፡
ማን እንደ አንቺ ታምረኛ
የኔ ላሉሽ ምስጢረኛ
አማላጅ ነሽ እውነተኛ
#ዛሬም_እባክሽ_ነይ_ወደኛ ! 🙏
📌ሼር
@Mgetem
@Mgetem
@Solasc
@Mgetem
#ማን_እንደ_አንቺ ፈጥኖ ደራሽ
#ሰላማዊት ልብን አዳሽ
አረጋጊ እንባን አባሽ፡፡
ማን እንዳቺ አዛኝቱ
#የአምላክ_እናት ድንግሊቱ
#አማላጅ_ነሽ የፍጥረቱ
ሰውን መላሽ ከስህተቱ፡፡
ማን እንዳቺ የሚየፅናና
የሚያወጣ ከፈተና
ደግፎ ከቅፎ የሚያቀና
#ማን_እንዳቺ አስታራቂ
#ሀጢአተኛን የማትንቂ
#ጆሮ_ዳባን የማታወቂ
መልካም ስራሽ አስደናቂ፡፡
ማን እንደ አንቺ መከለያ
ታማኝ እናት መጠለያ
ቀና መንገድ መታመኛ
የንስሀ በር መግቢያ፡፡
#ማን_እንደ_አንቺ ተቆርቋሪ
#የማታልፊ የሰው ጥሪ
አቤት ብለሽ አናጋሪ
ሰማያዊት ንግሰት የኛ አብሳሪ፡፡
ማን እንዳቺ ለወደቁት
#አዛኝ_አፅናኝ ንፁህ እንቁ
#ሰው_ረስቶአቸው ለተናቁት
#በሀዘን_መከራ ለወደቁት፡፡
#ማን_እንደ_አንቺ የሚረዳ
የመትሞይ የሁሉን ጓዳ
እባክሽ አውጪን ከዓለም ፍዳ
ሁዋላ ጠፍተን እንዳንጎዳ፡፡
ፀበልሽ ፈዋሽ ያለዋጋ
ለእኛ እኮነሽ ባለ አደራ
እባክሽ አውጪን ከሐጢአት ተራ
እንድንኖር ከአንቺ ጋራ፡፡
መን እንደ አንቺ ያለው ለዛ
ንግግር የሚያዋዛ
በረከትን የሚያበዛ፡፡
ማን እንደ አንቺ ልዩ ስጦታ
አምላክ ያደለን የነፍስ እርካታ
ደስ አለን ዛሬ ዲያብሎስ ሲመታ
መግቢያ መውጪያ አጥቶ ሲሄድ በአንድ አፍታ
#ስምሽ_ግሩም_ነው የህይወት ገበታ፡፡
ማን እንደ አንቺ ታምረኛ
የኔ ላሉሽ ምስጢረኛ
አማላጅ ነሽ እውነተኛ
#ዛሬም_እባክሽ_ነይ_ወደኛ ! 🙏
📌ሼር
@Mgetem
@Mgetem
@Solasc
👍9❤3
#ታሪክህን_እወቅ
@Mgetem
ታሪክህን እወቅ እንዳትሆን መናፈቅ
ትውልዱ ተጠንቀቅ ፈጥነህ እንዳትወድቅ
ምን ያለ ዘመን ነው ዘመነ መቅሰፍት
መለየት ያቃተው እሬት ከፍትፍት
ምን ያለ ዘመን ነው ዘመነ ተልካሻ
መለየት ያቃተው በጎችን ከውሻ
ምን ያለ ዘመን ነው ያረጀ ያፈጀ
ወንድም ከወንድሙ እርስበርስ ያፋጀ
ምን ያለ ዘመን ነው ዘመነ ውጥንቅጥ
የሰውን ልጅ ሁሉ በኃጥያት የሚያጠልቅ
ምን ያለ ዘመን ነው ዘመነ ዘለፋ
ወንድም ለወንድሙ የማይሆነው ተስፋ
ምን አይነት ዘመን ነው ክህደት የበዛበት
የዲያቢሎስ ሥርዓት የተንሰራፋበት
ወገኔ ተው ዕወቅ ተው ዕወቅ
እባክህ ተጠንቀቅ ለራስህም ዕወቅ
ሊቀ ብርሃናት መርቆሬዎስ አረጋ
@Mgetem
@Mgetem
@Yohannes_mariyam
@Mgetem
ታሪክህን እወቅ እንዳትሆን መናፈቅ
ትውልዱ ተጠንቀቅ ፈጥነህ እንዳትወድቅ
ምን ያለ ዘመን ነው ዘመነ መቅሰፍት
መለየት ያቃተው እሬት ከፍትፍት
ምን ያለ ዘመን ነው ዘመነ ተልካሻ
መለየት ያቃተው በጎችን ከውሻ
ምን ያለ ዘመን ነው ያረጀ ያፈጀ
ወንድም ከወንድሙ እርስበርስ ያፋጀ
ምን ያለ ዘመን ነው ዘመነ ውጥንቅጥ
የሰውን ልጅ ሁሉ በኃጥያት የሚያጠልቅ
ምን ያለ ዘመን ነው ዘመነ ዘለፋ
ወንድም ለወንድሙ የማይሆነው ተስፋ
ምን አይነት ዘመን ነው ክህደት የበዛበት
የዲያቢሎስ ሥርዓት የተንሰራፋበት
ወገኔ ተው ዕወቅ ተው ዕወቅ
እባክህ ተጠንቀቅ ለራስህም ዕወቅ
ሊቀ ብርሃናት መርቆሬዎስ አረጋ
@Mgetem
@Mgetem
@Yohannes_mariyam
❤4👍2👎1
#የተማሪ ወዳጅ
@Megtem
የተማሪ ወዳጅ ቢቀር ምን አባቱ
ዱላ ሲያነሱበት ይላል ባዛኝቱ
እንኳን ባዛኝቱ ይበል በሥላሴ
እኔ እወደዋለሁ እስኪ ወጣ ነፍሴ
አንቺ ባለ ጠላ ሁልጊዜ ቅራሪ
እኔስ እሞታለሁ ለዛ ለተማሪ
ገበሬ ቢያገቡት አፈር አፈር ይላል
ነጋዴ ቢያገቡት ቅመም ቅመም ይላል
ወታደር ቢያገቡት ባሩድ ባሩድ ይላል
ከሁሉም ከሁሉም ተማሪ ይሻላል
ቀድሶ ሲወጣ እጣን እጣን ይላል
@Mgetem
@Mgetem
@Yohnnes_mariyam
@Megtem
የተማሪ ወዳጅ ቢቀር ምን አባቱ
ዱላ ሲያነሱበት ይላል ባዛኝቱ
እንኳን ባዛኝቱ ይበል በሥላሴ
እኔ እወደዋለሁ እስኪ ወጣ ነፍሴ
አንቺ ባለ ጠላ ሁልጊዜ ቅራሪ
እኔስ እሞታለሁ ለዛ ለተማሪ
ገበሬ ቢያገቡት አፈር አፈር ይላል
ነጋዴ ቢያገቡት ቅመም ቅመም ይላል
ወታደር ቢያገቡት ባሩድ ባሩድ ይላል
ከሁሉም ከሁሉም ተማሪ ይሻላል
ቀድሶ ሲወጣ እጣን እጣን ይላል
@Mgetem
@Mgetem
@Yohnnes_mariyam
❤3👍3
#አትደንግጡ
@Mgetem
ማዕበል ባነሣ
ወጀብ ቢበረታ
ሁከትና ዋይታ
ቢሆን እንኳን ላፍታ
መታወክ መረበሽ
ከቶ አያስፈልም
ከእርሷ ጋር እያላችሁ
አትደንግጡ አይዟችሁ
መርከቧ ጽኑ ናት
አትሰምጥም አጠፋም
ጌታዋ ትጉህ ነው
ከቶ አያንቀላፋም
ይህች መርከብ ድንቅ ናት
እስኪ እንቀኝላት
አማናዊት መርከብ
#ቤተ-ክርስትያን ናት።
የእምነታችሁን ጽናት
ትዕግሥታችሁን ሊያይ
ተኣምራቱን ሊገልጥ
ማዳኑንም ሊያሳይ
ያንቀላፋ መስሎ
ጸጥ ቢል ባርምሞ
ተስፋችሁ አይጨልም
ዝም አይልም ፈጽሞ።
ምክንያት ሳታበዙ
ሁሌ ብትጸልዩ
አድነን ብላችሁ
በእምነት ብትዘምቱ
ያኔ ይገሠጻል
ማዕበል ነፋሱ
ኑፋቄ ክህደቱ።
መ/ር ኃይለሚካኤል ብርሃኑ
@Mgetem
@Mgetem
@Yohannes_mariyam
@Mgetem
ማዕበል ባነሣ
ወጀብ ቢበረታ
ሁከትና ዋይታ
ቢሆን እንኳን ላፍታ
መታወክ መረበሽ
ከቶ አያስፈልም
ከእርሷ ጋር እያላችሁ
አትደንግጡ አይዟችሁ
መርከቧ ጽኑ ናት
አትሰምጥም አጠፋም
ጌታዋ ትጉህ ነው
ከቶ አያንቀላፋም
ይህች መርከብ ድንቅ ናት
እስኪ እንቀኝላት
አማናዊት መርከብ
#ቤተ-ክርስትያን ናት።
የእምነታችሁን ጽናት
ትዕግሥታችሁን ሊያይ
ተኣምራቱን ሊገልጥ
ማዳኑንም ሊያሳይ
ያንቀላፋ መስሎ
ጸጥ ቢል ባርምሞ
ተስፋችሁ አይጨልም
ዝም አይልም ፈጽሞ።
ምክንያት ሳታበዙ
ሁሌ ብትጸልዩ
አድነን ብላችሁ
በእምነት ብትዘምቱ
ያኔ ይገሠጻል
ማዕበል ነፋሱ
ኑፋቄ ክህደቱ።
መ/ር ኃይለሚካኤል ብርሃኑ
@Mgetem
@Mgetem
@Yohannes_mariyam
👍5
"መሳል መልካም ነው ብረትን ያሰላዋልና፤ መጽሐፍም መልካም ነው ልብን ያበራዋልና፡፡ መጽሐፍ መነጽር ነው፣ ለሚመለከተው ሰው ከሩቅ ያሳያልና"
መጽሐፈ ጨዋታ መንፈሳዊ፡፡
@Mgetem
@Mgetem
@Mgetem_bot
መጽሐፈ ጨዋታ መንፈሳዊ፡፡
@Mgetem
@Mgetem
@Mgetem_bot
👍1