መንፈሳዊ ግጥም ብቻ
27.6K subscribers
173 photos
5 videos
5 files
509 links
በዚህ ቻናል ላይ በየቀኑ ኦርቶዶክሳዊ ግጥሞችን ያገኛሉ
ለአስተያየትና ግጥም እንዲፖሰትላችሁ የምትፈልጉ ለመላክ
@Solasc12
@Solasc13
@Mgetem_group

ኦርቶዶክሳዊ ጥቅሶች ብቻ
@Ortho_quotes
Download Telegram
" አዕሩግ አመ በከዩ ብካየ
ረከቡ ወለተ ዘታሥተሰሪ ጌጋየ
ለወንጌላውያን ኩልነ ዘኮነተነ ምጉያየ
ኢያቄም ወሀና ወለዱ ሰማየ
ሰማዮሙኒ አሥረቀት ፀሐየ
ምስራቀ ምስራቃት ሙፃዕ ፀሐይ
እግዝእትየ ዘመና ሙዳይ
ተወልደት ዮም ዳግሚት ሰማይ "
አረጋውያኑ ― በእጅጉ ቢያለቅሱ፣
በደል በምታርቅ ― በሴት ልጅ ተካሱ፤
ለወንጌልም ልጆች ― መሸሻቸው ካለም ፣
ሰማይን ወለዱ ― ሃናና ኢያቄም ፣
ሰማይዋም (ሰማዯም) ፀሐይን ― አውጥታለች ለዓለም፤
የምሥራቃት ምሥራቅ ― መውጫዋ ለፀሐይ ፣
የፍጥረት እመቤት ― የመናዋ ሙዳይ ፣
ዛሬ ተወለደች ― ዳግማዊቷ ሰማይ ።
2👍2
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
👍3
#እድሜ_ለንስሃ
@Mgetem

ያማረ ያጌጠ አዲስ ቤት ሰርቼ
እስክመለስ ድረስ አደራ ሰጥቼ
ሰፈሩን መንደሩን ቀየውንም ትቼ
ብዙ ዓመታትን ኖሬ ከዛ ሀገር ወጥቼ
አሁን ተመልሼ ስጎበኘው ቤቴን
አይኔን ማመን አቅቶኝ በእጄ ይዤ አፌን
እንዲጠብቅልኝ አደራ ይልኩት ሰው
እሳት ሲያነድበት ሲያጨስበት ኖሮ
ጣሪያውም ጠልሽቶ ግርግዳውም ጦቅሮ
ተረጋግጦ ሳየው ውስጡ ተሰባብሮ
እራሴን ታዘብኩት አዝኜ ከውስጤ
ድሮም!በሰው ተማምኜ ትቼው መቀመጤ
እንግዲ ፍረዱኝ!እስክመለስ ድረስ
ያደፈውን ዘመን በጊዜው እስካድስ
ጣርያ ግርግዳውን ወለሉን አፅደቶ
ያፈራርሰውን ካልጠበቀኝ ሰርቶ
እፋረደዋለው ህግ በፊት አቁሜ
ግን እስከዛው ድረስ
ሰጥቼዋለሁኝ ጥቂት ቀሪ እድሜ።
__________________________
@Mgetem
@Mgetem
@Menfesawi_getem_bot
👍3
ተናፋቂው ግንቦት 11 እየደረሰ ነው!

መቼም “ግንቦት 11 ደግሞ ምን አለ?” ብለው እንደማይጠይቁ እምነታችን ነው!

ባሕረ ጥበባት ቅዱስ ያሬድ - ብርሃናችን እና ጌጣችን ሊቁ ቅዱስ ያሬድ የተሠወረበት ዕለት እኮ ነው፡፡

አምላካችንን - ምክንያተ ድኂን እመቤታችንን - ቅዱሳን መላዕክትን - የምንወዳቸውን ቅዱሳንን - የምንጠለልባት ቤተክርስቲያንን የምናመሰግነው እኮ እርሱ ባቀበለን ዜማ ነው፡፡ መቅረት አይቻልም!

ደግሞ ዕለቱ እሑድ ቀን ነው፡፡ ከአኹኑ ቀጠሮዎን ከወዳጆችዎ ጋር በደብረ ይባቤ ቅዱስ ያሬድ ያድርጉ!

በቡድን እና በኅብረት ከዋዜማው ጀምሮ በማኅሌቱ ለመሳተፍ ለሚመጡ ልዩ አቀባበል እናደርጋለን፡፡

ሊቁ አባታችን ዓለም ዛሬ ላይ የሚያደንቃቸውን ዓለማውያን ሞዛርት እና ቬትሆቨን በ1250 ዓመታት ይቀድማቸዋል፡፡ ዓለም በነዚኽ ሰዎች ቤተመጻሕፍት - አደባባይ - መንገድ እና ትምህርት ቤት ሰይማ እስካሁን እንደታላቅ ቅርስ ስትዘክር አለች፡፡

ቅዱስ ያሬድ ግን ሰማያዊውን የመላእክት እንጀራ አሻግሮልን ልናመሰግነው አልቻልንም፡፡ በአዲስ አበባ እንኳን በስሙ መታሰቢያ ያለው ቤተክርስቲያን አንድ ብቻ ነው፡፡

መላዋ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን በቅዱስ ያሬድ ማኅሌት አምላኳን የምታመሰግን ናት፡፡ ጌጧ ለኾነው ለቅዱስ ያሬድ ግን በዓመታዊ መታሰቢያው ዕለት እንኳን አስባው ማኅሌት አትቆምለትም፡፡

በሌላው ዓለም ቢኾን ስንት ነገር በስሙ ተከናውኖ እና ተሰይሞ ነበር፡፡ አይ ቅዱስ ያሬድ! የአንተን ፈለግ ተከትለን ሰማያዊውን ሥራ መሥራት ቀርቶ አምላክ የመረጠህን አንተን እንኳን በወጉ ማክበር አልቻልንም፡፡

ቅዱስ ኤፍሬምን ከሶርያ - አባ ሕርያቆስን ከብህንሳ አምጥታ ምስጋናዬ በቅዱስ ያሬድ ዜማ ይኹንልኝ ያለችኽ እመ አምላክ በእኛ “የበሉበትን ወጭት ሰባሪነት” እንዴት ታዝንብን ይኾን!?

ለኢትዮጵያ እኮ ነፍሷ ነህ ቅዱስ ያሬድ - ጣዕሟ እኮ ነህ - አላወቀችኽም እንጂ!
____________________
አድራሻ፡ ጎተራ ከአጎና ሲኒማ ወደ መስቀል ፍላወር በሚወስደው መንገድ
#Share #share
1
#ይህን_እናውቃለን
@Mgetem

ዳግም ለመወለድ እንደማትመጣ
ደግሞም እናምናለን!
ስለ ኖኅ ኪዳንህ ምድርን በእሳት እንደማትቀጣ
በቃ እንጨፍራለን!
እንሰየጥናለን!ለመጨረሻ ፍርድ ዳግም እስክትመጣ።
አሁን በዚህ ሰዓት!?
ልምጣ ብትል በየት!?
መልካም ሥራን ሳይሆን ክፋትን አጥብቀን
የምህረት መንገድህን ዘግተናል አርቀን
በትዕቢት አንደበት!
ንስሐ አያሻንም ጻድቃን ነን ብለናል
አሁን በግብራችን ሰይጣንን መስለናል።
ዳግም ብትመጣም
ባስቀመጥኸን ምድር ከቶ አታገኘንም
መናፍስት ሆነናል ሥጋ እንኳን የለንም
አንተ ፍቅር ስቦህ የለበስኽው ሥጋ
በምን እንደሁ እንጃ ተወስዷል ከእኛ ጋ
አሁን በተለምዶ ሥጋ የምንለው
አጥንት የሸፈነ <የኃጢአት ክምር> ነው።
∅∅∅∅∅∅∅∅∅∅∅∅∅∅
@Mgetem
@Mgetem
@Menfesawi_getem_bot
👍21
#ከሳሽ_ዕድፉን_ሳያይ
@Mgetem
 
ስታመነዝር አገኘናት፣
ብለው አካልበዋት፣
ከጌታ ፊት እያቻኮሉ፣
ከእግሩ ሥር አምጥተዋት ጣሉ፡፡

ምን ትላለህ ? ስለዚች ሴት፣
ይዘናታል በማመንዘር ኃጢአት፣
ሙሴ እንደው በሕጉ፣
ብሎናል ወግራችሁ ግደሉ፣
አንተስ ምን ትላለህ ?
ይሰማ እስኪ ፍርድህ … ?

ይላሉ ከሳሾች ….
ወንዱን አስመልጠው ፣ ሴቷን አሳዳጆች፤
እውነት አንሻፋፊ ፣ ግማሽ ምስክሮች፤

ኢየሱስ መለሰ ….
ጐንበስ ብሎ ከምድር ፣ አንዳች እየጻፈ፤
ከʻናንተ መካከል ፣ ነውሯ ያላገኘው፤
ድንጋይን ከሯሷ ፣ አሁኑ ይጫነው፤
ብሎ ሳያበቃ ፣ ቀና ሲል ካለበት፤
ከʻርሷ በቀር የለም ፣ ከተከሳሿ ሴት ፤
ለካስ ሁሉም ጥሎ ፣ ከዚያ ሥፍራ የጠፋው፤
ከʻርሷ ጋር ተጋድሞ ፣ ዕድፉን ባያየው ነው፡፡

ያመነች ግን እርሷ ፣ ተከናወነላት ፤

መንገዷን ቀየረች ፣ ከሞት ወደ ሕይወት፡፡ 🙏
__________________________
@Mgetem
@Mgetem
@Menfesawi_getem_bot
👍31
#ዳግም_ልደት
@Mgetem

እሳት ወይስ ውሀ
ሀዘን ወይ ፍስሀ

አንዱን የግድ ምረጥ
ልብህ ባንዱ ይቁረጥ
ወይ ብረድ ወይ ተኩስ ፡በመሀል አትልፋ
ለብ ብለህ ካፉ ላይ፡ ውጭ እንዳትተፋ

ጨለማ ወይ ብርሀን
አንዱን ምረጥ ዝገን
ሞት ወይስ ህይወት
ሀሰት ወይስ እውነት
መዝሙር ወይስ ኮንሰርት
(አንዱን የግድ ምረጥ...)

ጣዖት ወይስ ታቦት
ሲዖል ወይስ ገነት

ይሄኔ አስተውለህ
አስበህ መርምረህ
ካላወክ ጠየቀህ
በውነት በቅንነት ፡ በበጎ ህሊና
አንዱን ምረጥና ፡ በንፁህ ልቦና
ተወለድ ወንድሜ ዳግም እንደገና ፡፡
🔸🔹🔸🔹🔸🔹🔸🔹🔸🔹🔸🔹
🔹🔸🔹🔸🔹🔸🔹🔸🔹🔸🔹🔸
@Mgetem
@Mgetem
@Menfesawi_getem_bot
🔸🔹🔸🔹🔸🔹🔸🔹🔸🔹🔸🔹
🔹🔸🔹🔸🔹🔸🔹🔸🔹🔸🔹🔸
1👍1
#አገልግሎትና_መኪና
ከሕሊና በለጠ ዘኖኅተ ብርሃን

በአገልግሎት ጋሪ በልኡክ መኪና
ነዳጁ #ፍቅር ነው ፍሬኑ #ትሕትና
መኪና በመንገድ ፍሬን ከሌለው፣
አገልጋይም እንዲሁ ትሕትና ካነሰው፣
መፃኢ ዕጣቸው መጋጨት ብቻ ነው።
ነዳጅና ፍቅርም ይመሳሰላሉ፣
ፍቅር ይኽኛውን ነዳጅም ያኛውን ያንቀሳቅሳሉ።
#ተስፋ መስታወት ነው #ትውፊት ስፖኪዮ፣
#እምነት ደግሞ መሪው የአቅጣጫ መለዮ፤
በእምነት መሪነት በተስፋ መስታወት ወደፊት እያሉ፣
በአዕምሮ ማኅደር በትውፊት 'ሚታዩ ኋላዎችም አሉ።
'ሚንቀሳቀሱበት 'ሚሽከረከሩበት #ትግኃት ይባላል የመኪናው ጎማ፣
#ትግኃት ቅንዓትም ጡሩምባው 'ጲጵ' የሚያደርጉበት ከሃይማኖት መንገድ ዞር እንዲል ጠማማ።
ከእነዚህ ዕቃዎች አንዱ ከጎደለ ወይ ከተጣመመ ወይም ከተበሳ፣
መኪናው አሮጌ ይባላል ከርካሳ።
ጥገናና ሰርቪስ መለዋወጫ ዕቃ ለሚያስፈልገው ሰው፣
መካኒኩ ካህን ፣ ላቫጆው ንስሐ ፣ ጋራጁ መቅደስ ነው።
ሕግ አስከባሪዎች ፖሊሶችስ ካሉ፣
ሥርዐት ቀኖና ተብለው 'ሚጠሩ ትራፊኮች አሉ።
በሃይማኖት መንገድ ሲወጡ ሲወርዱ፣
መጠመቅ ብቻ ነው የመንጃ ፈቃዱ።
መልካም መንገድ!
__________________________
@Mgetem
@Mgetem
@AskBoaBot
👍21
#እንጠይቅ_ተዓምሯን
@Mgetem

፦ዮሐ ፦2 ፥1-11
፦ሉቃ ፦1 ፥ --

እንጠይቅ ስለሷ እውነታው ያልገባችሁ
ከምትናገሩ እንደመጣላችሁ
አበዉን እንጠይቅ ይንገሩን ባካችሁ ።

ብዙ አባቶች አሉ የለበሱ ፍቅሯን እነሱን እንጠይቅ የንገሩን ታምሯን ።

ታምራቱዋን ያየው የተደረገለት
ዶኪማስ ይመስክር ይናገር ስለ እውነት ፦

በዛ በሰረጉ ቤት ቃና ዘገሊላ
ሰርገኛዉ ታድሞ ሲጠጣ ሲበላ ፦

ድንገት በመሀከል ወይኑ በመጥፋቱ
ዶኪማስ ተጨንቆ ሲርድ ሰዉነቱ
የነበረው ደስታ ሁሉም ሲሆን ከንቱ
መቋቋም አቅቶት ሲዝል ጉልበቱ
ተዋረድኩኝ ብሎ ሲታየዉ ሽንፈቱ
እማምላክ አንብባ ጭንቀቱን ከፊቱ ።
እሩህሩህ ናትና እናቴ አዛኚቱ

የዶኪማስ ጭንቀት ሀዘኑ እንዲፈታ
ድንግል ልታማልድ ሄደች ወደ ጌታ
ተዓምር የሚያደርግ ስላላት ቃልኪዳን
"ወይንኪ ዓልቦሙ "አለችው ልጇን ።

ልጇም ሰማና የናቱን ልመና
ውሃውን ቀየረዉ ወደ ወይን ቃና ።

ትናገር ኤልሳቤጥ ትመስክር ታምሯን
የሰላምታዋን ቃል ስትሰማዉ ድምጿን
በምንፈስ ተሞልታ ለክብሯ መስገዷን
በማሕፀኗ ያለዉን ፅንስ ማዘለሏን ።
ልቧ ሀሴት አርጎ መጮኋን በደስታ
ፅንሱም እደዘለለ በድንግል ሰላምታ ።

ምድራዉያንን እኛን ወክላ
ለክብሯ ሰገደች "ሰላም ለኪ "ብላ
ሰማያዉያንን ሁሉ ወክሎ
ገብረኤል አበሰራት" ሰላም ለኪ "ብሎ

ታደያ በኛም ዘመን አሁን ባለንበት
የድንግል ተዓምር በሚገለጥበት
ዓለም በምልጃዋ ድህነት ባገኝበት
ታድያ ለምን ካዱ ጠፋባቸው እውነት ።

አይናቸው እያየ ገድል ታምራቷን
ጆሮአቸውም ሰምቶ ሙታን ማስነሳቱዋን
ታድያ ለምን ይሆን ሰው ናት ማልታቸዉ
ስላልተፃፈ እንጂ ፍቅሯ በልባቸው ።

ከዚህ ሓጥያት ለመዉጣት ለመቅመስ ፍቅሯን
እንጠይቅ ስለሷ ይንገሩን ታምሯን ።
እውነትን ተማሩ ግቡ ወደ በረቱ
የእውነት አማላጅ ናት ድንግል አዛኚቱ ።

ያለዉ ተሾመ
[][][][][][][][][][][][][][][][][][][][][][][][][][][]
@Mgetem
@Mgetem
@Menfesawi_getem_bot
👍73
#የአምላኬ ስራ እንጂ
🔖🔖🔖🔖🔖🔖🔖


እሲቲ ለአንድ አፍታ ስሙኝ ወገኖቼ
አሁን የምታዩኝ እንደዚ ፈክቼ
ደስታዬ ወሰን አጥቶ ከመጠን በላይ
የምረቃ ቆቡን ድፍቼ የምታይ
በጥናት ተግቼ እንቅልፌን አጥቼ
ፕሮጀክት አሳይመንት ሁሉንም ሰርቼ
ከቶ አንዳይመስላቹ የቆምኩኝ በደስታ
ያበቃኝ እሱ ነው የጌቶቹ ጌታ።
እናም እወቁልኝ የስኬቴን ምስጢር
የመቆሜን ነገር እንደዚህ በክብር
የኔ ስራ አይደለም በአንዳቸውም ቦታ
የአምላኬ ስራ እንጂ ያቆመኝ ከፍታ።
➴ ከቃልኪዳን ተፈራ
2👍2
#እውነት_አለቀሰች
@Mgetem

ልብ ያለህ አስተውል ጆሮ ያለህ ስማ
እግርህ እንዳይገባ ከክህደት ከተማ።
የያዝከውን አጽና ልብህ አይጨነቅ
ለጥያቄህ መልስም ሊቃውንትን ጠይቅ።
ለእውነት የቆመ ሃይማኖቱን የሚያውቅ
ንባብ ትርጓሜን ጠንቅቆ የሚዘልቅ
ተናገር ዩሐንስ አንተ ልሳነ ወርቅ።
ቄርሎስን ጠይቀው የተዋህዶን ምስጢር
የክርስቶስ ነገር እንዴት እንደነበር
ከብሉይ ከሐዲስ በማቀነባበር
እንዳመሰጠረው በብዙ ምስክር።
ነቢዩ ኢሳያስ ብርሃነ ዓለም ጳውሎስ
መዝሙረኛው ዳዊት ሐዋርያው ሉቃስ
አባ ዝክረ ማርያም ወአባ ጴጥሮስ
የስነ ዘፍጥረት ሊቅ ኤጲፋኒዮስ
ዝም አትበል ተናገር ቅዱስ ሳዊሮስ
በሥጋው ማክበሩን አምላክ ክርስቶስ።
ጊዮርጊስ ተናገር አንተ የጥዋት ጮራ
ክርስቶስ መሲሕም ተብሎ እንደሚጠራ።
ወልድ ቅብዕ በማለት ክህደት አስተማሩ
የሥግው ቃል ነገር መች ገባቸው ዳሩ
የተዋሕዶ ምስጢር ሳይገባቸው ቅሉ
ሃይማኖት ከምስጢር ይደባልቃሉ።
ክርስቶስ በሥጋ እንደሞተ ሲያውቁ
በሥጋስ መክበሩን እንዴት አላወቁ
ሊቃውንት እያሉ ለምን አይጠይቁ
በተዋሕዶ ከበረ ብለው ሲናገሩ
ለዚህ ብሂላቸው የታል ምስክሩ።
ግብርን በማፋለስ አንድ ገጽ ካለው ከሰባልዮስ
አንድነትን ትቶ ሁለት አካል ካለው ከእርጉም ንስጥሮስ
መንፈስ ቅዱስ ሕጸፅ ካለው ከመቅዶንዮስ
ወልድ ፍጡር ካለው ከእርጉም ከአርዮስ
የዚህ ክህደቱ በምንም አያንስ።
ፈላጊዋ ጠፍቶ እውነት አለቀሰች
ግብራቸው ተቃርኖ ሀሰት ጥላት ሄደች።
ዳሩ ግን ወገኔ ይህ ክህደት ነውና
ቀኑ ሳይመሽብህ መንገድህን አቅና
እውነትን ከፈለክ ታገኛለህና
እረፍት ስላላት የህይወት ጎዳና
የያዝከውን ይዘህ በሃይማኖት ጽና።
___________________________
@Mgetem
@Mgetem
@Menfesawi_getem_bot
👍124🤬1
#ያኔ_እመረቃለሁ
@Mgetem

ሀሁ ABCD ፊደላት ቆጥሬ
ጥበብን ለመማር መፃሕፍት ደርድሬ
ሀገሬን ወገኔን እናቴን ለመርዳት
ድንቁርናን ጥዬ ከችግር ለመውጣት
ጋራውን ስወጣ ቁልቁለት ወርጄ
ከአንድ ወደ ሌላ ማለፍ ተላምጄ
ነገን ለማሸነፍ እቅድ እነድፋአለሁ
ተስፋ ስንቅ ሆኖልኝ እሩቅ አልማለሁ፡፡
ደግሞ
መቼነው የማያት ያቺን የብርሃን ቀን?
ነፃ ምወጣባት ከቴንሽን ሰቀቀን
መች ትሆን እያልኩኝ አማትሬ ሳያት
ያቺን የቀናት ቀን እንዲሁ ስናፍቃት
ቀናት ተሰብስበው ወራት አቀናጁ
ወራትም አብረው አመታት አበጁ
የዘመን ባለቤት ጊዜያት አቀዳጅቶ
ጉዞና መንገዴን ጥርጊያዬን አቅንቶ
በጊዜው ውብ አርጎ ሁሉን አስተካክሎ
የምርቃቴን ቀን ለገሰኝ በቶሎ፡፡

የእናት የአባቴ ህልም የተስፋ ቀናቸው
የብርሃን ቀን መጣች ሀሴት ልትሞላቸው
የምመረቅባት....የልፋት ካባዬን የምደርብባት
ራዕይ ዓላማዬ ግብ የሚመታባት፡፡
ነገ!
ሀገሬን ወገኔን የምጠቅም ዜጋ
ለእውነት ለቅንነት ጦር ይዜ ምዋጋ
የማይነቃነቅ ብርቱ ትውልድ ሆኜ
ለጥፋት የማልቆም የማልቀር ባክኜ
አንድነት ሰላምን ፍቅርን ተነቅሼ
የዳዊትን ትምክህት የምጓዝ ለብሼ
እንድሆን ብሩህ ትውልድ ሥላሴ ድረሱ
መላ ማንነቴን ህይወቴን ቀድሱ፡፡
የአብርሃምን ቤት እንደባረካችሁ
ትውልዱንም ታላቅ እንዳደረጋችሁ
ብርቱ መጠለያ ዋስ ድጋፍ ሁኑልኝ
ዓጋዕዝተ ዓለም ቀኔን መርቁልኝ፡፡

እንደ ያዕቆብ ሌሊት ይባረክ ህይወቴ
ሙሉ ሀሴት ይሁን የምርቃት ለቴ፡፡
ባላቅን ልካችሁ
ሰዓታት ዕለታት ቀኔን መርቁልኝ
በጴጥሮስ መክፈቻ
የገዛ ሀጥያቴን አጥባችሁ አጥሩልኝ፡፡
መልአከ ምክራችሁን ወደኔ ላኩልኝ
ዲግሪዬን በትንፋሹ እንዲቀድስልኝ
አብሳሪውን መልአክ ጠርታችሁ ላኩልኝ
የምስራች ነግሮ ደስታ እንዲበዛልኝ፡፡
ጆሮዬ ይሰማው የድንግል ሰላምታ
ይታጠፍ ጉልበቴ ይስገድ ለአንተ ጌታ
ጉዞዬን በሙሉ ባንተ ላይ ስጥለው
መቻል እስቂያቅተኝ ያኔ እመረቃለሁ፡፡

___________________________

ለ2011ዓ.ም የተዋህዶ ልጆች በሙሉ እንኳን ለመርቃ ቀናቹ አደረሳቹ እንላለን።

ገጣሚ ረዳኢ ሃዱሽ
___________________________
@Mgetem
@Mgetem
@Menfesawi_getem_bot
👍82
​​❗️ታላቅ መንፈሳዊ ጉባኤ
➤በአሰላ ደብረ መድኃኒት መድኃኔዓለም ካቴድራል
➤ከሐምሌ 5 ( ከአርብ) አስከ ሐምሌ 7 (እሁድ)
ሁላችሁም ተጋብዛችኋል
#Share ሼር ያድርጉት
​​❗️ታላቅ መንፈሳዊ ጉባኤ
➤በአሰላ ደብረ መድኃኒት መድኃኔዓለም ካቴድራል
➤ከሐምሌ 5 ( ከአርብ) አስከ ሐምሌ 7 (እሁድ)
ሁላችሁም ተጋብዛችኋል
#Share ሼር ያድርጉት
#የአምላክ_መገኛ
@Mgetem

አንድ እለት አንድ ወጣት
አንድን የበቁ አባት
በማለት ጠየቀ በጣም ፈልጋለሁ አምላኬን ለማየት
ከልብህ ከፈለክ አምላክን ለማግኘት
ልምራህ ወዳለበት ተነስ ተከተለኝ
ታዲያ ግን አደራ ልመለስ አትበለኝ
አምላክን ለማየት ከልብህ ከፈለግክ
እርሱ ወዳለበት ስንሄድ ታየዋለክ
ካሉት በኋላማ ተነሱ በአንድነት ወደ አምላክ ሊሄዱ
ከጠበቀው በላይ ሩቅ ሲሆንበት ወጣቱ መንገዱ
እስኬት ነዉ ምንሄደው አምላክ የት ነው ያለው
እርሱ አምላክ ሳለ በዚህ በበረሃ ለምን ነው ሚኖረው
እኔ ግን አባቴ ልሞት ነው ደክሞኛል
ከምነግሮት በላይ ጉሮሮዬ ደርቋል
አባቴ ይንገሩኝ አምላክ የት ይገኛል
እኔስ ሄድኩ እንበል እርሱ ግን ያውቀኛል
አሁን ተቃርበናል ልንደርስ ነው አምላክ ጋ
እዚሁ ጠብቀኝ እኔ ግን ልሄድ ነው ሚጠጣ ፍለጋ
አሉትና እኚያ አባት ፈጥነው ተራመዱ
ወጣቱም በድካም ተንጋሎ አያቸው በፍጥነት ሲሄዱ
እራሱን ጠየቀ እጅጉን ተገርሞ
እኚህ አባት ጥንካሬያቸውን ኬት አመጡት ደግሞ
እኚያ አባት ሄደው ትንሽ እንደቆዩ
ወጣቱ ዞረበት ምድርና ሰማዩ
አምላኬን ሳላየው ልሞት ይሆን እንዴ
ምነው ግን ቢያቆየኝ እስካገኘው አንዴ
ብሎ ሳይጨርሰው እዚያው ራሱን ሳተ ተንጋሎ ሜዳ ላይ
ልክ እንደ ነቃ ዙሪያ ገባውን ሲያይ
እኚያ አባት ተቀምጠው ይፀልዩ ነበር
እሱም ቀና ብሎ የሚፀልዩትን ይሰማቸው ጀመር
ይስሙኝማ አባቴ
አምላኬን አየሁት ለዚያውም ሁለቴ
ወዴት አገኘኸው እንዴትስ ለየኸው
ባገኘኸው ጊዜስ ምንድን ነበር ያልከው
እኔ ወጣት ሆኜ በድካም ስሰቃይ
እርሶ ግን ሸምግለው ጥንካሬዎትን ሳይ
ያን ጊዜ አየሁት አምላኬን በእርሶ ላይ
ውሃ ጠምቶኝ ደክሞኝ ህሊናዬን ስቼ
ስነቃ ለየሁት ፀሎቶን ሰምቼ
በል አድምጠኝ ልጄ ታዲያ አሁንስ ገባህ
አምላክ ሁሌም አለ በዙሪያ በደጅህ
ይገለፅልህ ዘንድ
የትም ሳትሰደድ
በተስፋ ጠብቀው ልቦናህን ከፍተህ
ይህንን ስትፈፅም ያኔ ታየዋለህ

➴በሰላማዊት ጌቱ
___________________________
@mgetem
@Mgetem
@Kal002
👍5
​​የእሳት ትንታግ ፍንጣሪ
የድል ዜማ ወገን አኩሪ
የክብር ጥግ ማማ
የደስታ ውበት ቄጤማ
የመስቀሉን ሀይል ከግሽን የጠበሉን በረከት ዘግና
ይኸው አየኋት በለንደን የእሳት ልጅ እሳት ሆና
የደም አዙሪት ምሬቱ
የእሳት ትግል ሽረቱ
እየፈላባት አሞቷ እየታገላት ሲቃ
ታቦቷን ከራሷ ሳይሆን ከደረቷ ላይ ደብቃ
ተሻገረችው ያን ጉድ አስለቀሰችን ነፍርቃ
ጀመረች አግዢኝ ብላ
ድንግልን በደረቷ አዝላ
ታሪክ ናት ይህች ማሪያም ለተማፀናት በብርቱ
ልጇን ላመነ በልቡ ፍቅሯን ላሰረ በአንገቱ
ረሳችውና ድካሟን የልፋት ውጤት ወርቋን
ከፍ አደረገች በሥዕሏ የድንግልን ማሪያምን ስሟን
ግሸን ሆነች አሉ ለንደን ተቀይራ
መሰረተ ሕይወት ድንግል ተዘምራ
እምነት ከጉያ ውስጥ ድንገት ፈለቀና
ሃሌ ሃሌ ሆነ ድካም ተረሳና
የእኛ እርግብ አማኝቷ
የኢትዮጵያ ልጅ መሰረቷ
ቢላላባት ያሰረችው ቢበጣጠስ መቀነቷ
ተወራርዳ አሸነፈች በጌታ እናት በአዛኚቷ

በቀሲስ ማሞ በዕለቱ የተፃፈ

@Mgetem
@Mgetem
@Bahraan
👍21
#የታወረ_ትውልድ
@Mgetem

ከእናቱ አፈንግጦ እምነት ወዲያ ብሎ በአለም የታለለ
በዚህ በእኔ ዘመን ልበ ስውር ወጣት እጂግ ብዙ አለ
ዶግማና ቀኖና መፈፀም ሲያቅተው በስጋው ሲታለል
ይችን ቅድስት እምነት መፍትሄ ነው ብሎ ትታደስ ይላታል
የመለውጥ ትርጉም ጠንቅቆ ያልገባው ልበ ስውር ጓዴ
በኃጢያት ያደፈ እሱነቱን ይዞ ትታደስ ይለኛል ያላረጀ ነገር ይታደሳል እንዴ?
እነዲዎስቆሮስ ፂም የተነጩላት የፀናች ሀይማኖት
ቆዳቸው እንደ ድንች በአህዛብ ጭካኔ ያኔ የተላጡላት
በሚያስፈራ እሳት ነጎድጓድ በላበት
ለኛ ያቆዩልን ህይወትን ሰውተው
ተዋህዶ እምነቴ ምኗ ነው ያረጀው
በሀጥያት አረንቋ የተቆሳቆለ እርሱ ተቀምጦ
ፍርሀት እንኳን አያውቅ ትታደስ ይለኛል ካፉ ቃል አውጥቶ
መላ በሉት'ማ ምከሩት ይህን ስው
የመታደስ ትርጉም ምን አልባት ቢገባው!!!የናቁሽ ሁሉ ወደ እግርሽ ጫማ ይበረከካሉ
ያከበሩሽም የከበሩ ናቸው
ማሪያምን የጠላ የለውም ከለላ
@Mgetem
@Mgetem
👍1
ውድ የመንፈሳዊ ግጥም ብቻ ቻናላችን ተከታታዮች አብራችሁን ስለሆናችሁ እናመሰግናለን፡፡ 🙏🙏
🖼አዲስ ፕሮፋይል....
#Profile_design Credit to
Sc graphics 📩 @Scgpx