መንፈሳዊ ግጥም ብቻ
28K subscribers
167 photos
5 videos
5 files
528 links
በዚህ ቻናል ላይ በየቀኑ ኦርቶዶክሳዊ ግጥሞችን ያገኛሉ
ለአስተያየትና ግጥም እንዲፖሰትላችሁ የምትፈልጉ ለመላክ
@Solasc12
@Solasc13
@Mgetem_group

ኦርቶዶክሳዊ ጥቅሶች ብቻ
@Ortho_quotes
Download Telegram
ሚካኤል አልኩኝ
@Mgetem

የቱ ችግሬ ነው የትኛው ጭንቀቴ
ስምህን ስጠራ የሚቆም ከፊቴ
ሚካኤል ሚካኤል አልኩኝ
ስንቱን አለፍኩኝ

እንኳን መጥቼ ቆሜ ከፊትህ
ደርሰህልኛል ካሳቤ ቀድመህ
ቅዱስ ሚካኤል ልዩ ነው ያንተስ
ልጅህ ቆሜያለው ሆነኝ ሞገስ

ዙርያየ ሰፍረህ ሳትርቅ ከጎኔ
በበረሃው ላይ ሆንከኝ ወገኔ
አንተው ከዋላ አንተው ከፊቴ
አለህ ሚካኤል ለኔ አባቴ

አቅም የለውም ሞት አንተ ፊት
ትቀይራለህ ወደ ሕይወት
በቅድመ እግዚአብሔር ለኔ የምትቆም
በለአም የለም ርቋል መርገም

ወደ እርስቴ የምታደርሰኝ
እውነት ሕይወትን የምትመክረኝ
ብርሃን ሆኗል የኔ ጎዳና
እየመራኸኝ መግበህ መና

http://t.me/Mgetem
http://t.me/Mgetem
http://t.me/Mgetem
❤60🥰21👏10👍9
በገና ከነቦርሳው መግዛት የምትፈልጉ እና መማር የምትፈልጉ በ 0936290305 ላይ ይደውሉ።
❤18
እኔ ማነኝና?
@Mgetem

መላእክት በፊትሽ ፈርተው ከሰገዱ
ኪሩቤል ሱራፌል አንችን ከጋረዱ
እኔ ማነኝ እና ፊትሽ እቆማለሁ
በየትኛው ብዕሬ ስላንች እጽፋለሁ

ገብርኤል ሊያበስርሽ ከፊትሽ መጣና
በፍርሀት ሰገደ ጎንበስ አለና
ከክብሩ በልጦበት የአንች ልዕልና
እሱ እንዲህ ከሆነ አንች ፊት እምቆም
እኔ ማነኝ እና?

ቁጥር አልባ ብራና ባሕር ሙሉ ቀለም
በሊቃናት አባቶች ቢደረስ ቢጻፍም
አንችን የሚገልፅሽ ከቶ አልተገኘም
ብቻ ይበል ትውልድ እፁብ ድንቅ ለዓለም

http://t.me/Mgetem
http://t.me/Mgetem
http://t.me/Mgetem
❤80👍26🥰14👏6🤬3
የሰማዩን ምስክር
@Mgetem

ጨለማን ሰባሪ_ብርሃን ወጥቶብሻል
ሞትን የሚገድል_ትንሳኤን ወልደሻል
ንጽሕ መሶበ ወርቅ_ ድንግል ተብለሻል
ለከበረው ክብርሽ_ስግደት ይገባሻል።

የሰማዩ ምስክር_ የታየው በራማ
በምድራዊው ገነት_ እነሆ ተሰማ
የመልአኩን በስራት_ኤልሳቤጥ ስትደግመው
በሆዷ ያለው ጽንስ_ ደስታ አዘለለው
መጥምቀ መለኮት_ክብሩ ከፍ ያለ ነው።

ለኛ ስለሰጠች _ የሕይወት እንጀራን
ሁሌም ለዘለአለም_ እንወዳታለን
የምስራቋ ደጃፍ_የወለደች ፀሐይ
የኤልሳዕ ማሰሮ_ የበረከት ሲሳይ።

የፍቅር የሰላም _ የምሕረት መገኛ
የምንመካብሽ _ ነይ ነይ ወደ እኛ
ኖርዶስ ቀሲመታት_ በጎ መዓዛ ነሽ
የአማኑኤል ማደሪያ_ የለም የሚመስልሽ።

ጌታዬ ከሰጠኝ_ እናቴ እልሻለው
የመንገድ ስንቄ ነሽ_ እመካብሻለው
ለጠየኩሽ ሁሉ _ መልስ የምትሰጪኝ
እንዳልነዋወጥ_ በዐለቱ ትከይኝ።

በመከራ ጊዜ _ መሸሸጊያ ሆኖን
የመከራን ባሕር_ በፍቅሩ አሻግሮን
እንደበደላችን_ ሳያጠፋን ጌታ
አቆመን በደጁ_ ሞልቶን በእልልታ።

ከኛ የበረታችሁ _ አስቡን በጸሎት
በስጋ ፈተና _ እንዳይገለን ምቾች
በሄድንበት ሁሉ_ እንዲገጥመን ሰላም
ፍፃሜአችን እንዲያምር_አማልጅን ማርያም።

የተሰቀለውን _በገና  አውርዱ
መሰንቆ ክራሩን_ ከበሮ አሰናዱ
መቆሚያ ጽናጽል_ ይታደል ለሁሉም
በያሬድ ውብ ዜማ_በሚያስረሳ ዓለም
ተነሱ እንዘምር_ ለመድኃኒዓለም።

እንዲህ እናምናለን_ እንታመናለን
በተበተንበት በባዕዱ ምድር_ እንመሰክራለን
የሥላሴን ጥበብ_ ትውልድ እንዲረዳ
ይምጣና ይመገብ_ ከእናቱ ጓዳ
ኋላ ለጥያቄ _እነዳይሆን እንግዳ ትጉኃን

በዝማሬው ጣዕም_ተሞልተን ደስታ
በተዋሕዶነቷም _ ነፍሳችን ተጽናንታ
በቃሉ ምስክር _ ቀርቦልን ማዕድ
በወልድ እናት ምልጃ _በሕይወት መንገድ
ከቅድስት ምድራችን _በመጡት
በደጀ ሰላሙ አለን_ ተሰብስበን።

በመረዋ ድምጹ_ በሚስረቀረቀው
ሲሰማ አርነት_ተሰፋን በሚሰብከው
የአባቶችን ምክር_ትዕዛዝ በሚያከብረው
በረጋው አንደበት_ ከቴድሮስ ሰማነው
ኪዳነምሕረት_ በእቅፏ ታኑረው።


ከዕርስታችን ወተን_ ብንኖርም በእሩቅ
መተላለፋችን_ በስሙ እንዲፋቅ
ክብር ሞገስ ሆነን_ ስራው የሚያስደንቅ።

ሀይማኖት ከምግባር_የነፃነት በፍታ
የሚያስተምር  ፍቅር_ ጠዋትና ማታ
የወንጌል አርበኛ_ የሚያስር የሚፈታ
ደጀንን ሸለመን_ የሰራዊት ጌታ።

ለዘመኑ ሕመም_ መድኃኒት ያመርታል
የነፍስ ዶክተር  ነው _ትውልድ ይፈውሳል
ብሉይን  ከሐዲስ _ እያመሳጠረ
ስንቱን ሐሰተኛ_ ከቤት  አባረረ።

በጠላት ተከቦ_ ሲደፈር ተራራው
እንደ ተመረጡት_ በእውነት አብበው
ወንጌልን ተጫምቶ_  በብዕር ይሻገራል
በለበሰው ሞገስ_ ሁሉን ያስደምማል
___

https://t.me/Mgetem
https://t.me/Mgetem
https://t.me/Mgetem
❤110🥰28👍12😢1
ዓለም ላይ ተሁኖ
የምን ፅድቅ ስራ
መዝናናት ነው እንጂ
ዳንኪራ ጭፈራ...
ልሄድ አካባቢ
ሸምገልገል ሲያደርገኝ
ፅድቅም እሰራለሁ
ንስሐ እየገባሁኝ
አለና ተኝቶ በጠዋት ሊነሳ
ለዓለሙ ምኞት ለስጋ እየሳሳ
እንደተኛ ነጋ ዳግም ሳይነሳ ።
✍️ሀብቱ ከእግዚአብሔር

https://t.me/Mgetem
https://t.me/Mgetem
https://t.me/Mgetem
😢51❤38🥰16👍7👏7
የልቤን ሁሉ ለማን ላማክር
Mmezmur
የልቤን ሁሉ ለማን ላማክር | ዘማሪት ፋንቱ ወልዴ
@Mmezmur

የልቤን ሁሉ ለማን ላማክር
እመቤቴ ሆይ ካንቺ በቀር
ለደካማ ሰው መጠጊያ እኮ ነሽ
ሀዘን ጭንቀቴን የምረሳብሽ /2/
አዝ
ቅዱሳን አበው አንቺን መረጡ/2/
ከሲዖል ዓለም ስላመለጡ
ጻድቅ በስራው ያኔ ሲድን/2/
እጠራሻለው ድንግል አንቺን
አዝ
የጭንቄ ደራሽ አክሊሌ ነሽ/2/
ቂም በቀል አያውቅ የዋህ ልብሽ
ልቤ ለፍቅርሽ ሰፊ ስፍራ አለው/2/
ባዘንኩኝ ሰዓት እጠራሻለው
አዝ
ዋሴ ነሽ ለኔ ድንግል እናቴ/2/
ስምሽ ጠበቀኝ ከልጅነቴ
ሁልጊዜ ለኔ በጎ አረግሽልኝ/2/
ምን ልበል ላንቺ ቃላታም የለኝ
አዝ
ላዘንኩኝ ለኔ ደስታዬ ነሽ/2/
ያረጋጋሽኝ ፈጥነሽ ደርሰሽ
ስምሽ ኃጥአንን የሚቀድስ/2/
ከሞት ወደ ሕይወት የሚመልስ

ሼር በማድረግ ለወዳጅ ዘመድዎ ያጋሩ‼️ ተጨማሪ ለማግኘት Join ያድርጉ👇

https://t.me/MMezmur
https://t.me/MMezmur
❤56🥰8👍7👏3
ኃያሉ ጊዮርጊስ
@Mmezmur
ኃያሉ ጊዮርጊስ | ዘማሪ ፍቃዱ አማረ
@Mmezmur

ኮከብ ሲወጣ አየን በልዳ ሠማይ
ሐያሉ ጊዮርጊስ ቆሟል ዘንዶው ላይ
ቤሩታዊት ተነሽ አትሞችም ተጽናኝ
አውሬው ተሸንፏል በአምላክሽ እመኝ
አዝ

ሕዝቡን የሚያስጨንቅ ሠው ገብሩኝ ብሎ
ጊዮርጊስ አደቀቀው በእግሮቹ ሥር ጥሎ
የንጉሡ ልጅ ቤሩት ዕጣው ለአንቺ ሆኗል
ከግንዱ ሊፈታሽ ፈረሰኛው ቆሟል
አዝ

በጣዖታት ምድር አዲስ ጸሐይ ወጣ
በጽድቅ እያበራ ጊዮርጊስ ታጥቆ መጣ
እንግዲህ አፍጵሎን አቴና ሆይ እፈር
ምድሪቱን ይገዛል የአምላካችን ክብር
አዝ

ዱድያኖስ መንግስቱን አልቻለም ሊያጸና
ታላቁ ሠማዕት ቅጥሩን ሠብሯልና
በአነገበው መስቀል አምላኩን ገለጸ
የድል በፍታን ለብሶ ጭፍሮቹን ገሠጸ
አዝ

በይድራስ ተራራ ቅኔን ያስተማረ
ድንቅ ነው አጥንቱ በሐይል የከበረ
ታምራቱ በዝቶ ገድሉን ደመደመ
በጸጋው ቃል ኪዳን ትውልዱን ጠቀመ

ሼር በማድረግ ለወዳጅ ዘመድዎ ያጋሩ‼️ ተጨማሪ ለማግኘት Join ያድርጉ👇👇👇
https://t.me/MMezmur
https://t.me/MMezmur
https://t.me/MMezmur
❤41🥰5
በገና መግዛት እንዲሁም መማር የምትፈልጉ በአካልም እና በonline ለማስተማር ዝግጁ ስልሆንን በ 0936290305 ላይ ይደውሉ ወይም በቴሌግራም ላይ ፃፉልን
❤22
መነነ ዮሐንስ
@Mgetem

የድንግሊቱን ድምፅ ፤
ከእናቱ ማፀህን ፤ ከጠባቡ አልጋው
ዮሐነስ ሲሰማ ፤ ለመውጣት አጓጓው።
ወደ እኔ እንድትመጪ ፤ የጌታዬ እናቱ
እኔ ማነኝ ማለት ፤ ባይችል ባንደበቱ ።
ወቶም ሊቀበላት ፤ ባይታደል እንኳ
የእናቱን ማህፀን ፤ ከውስጥ ሆኖ አንኳኳ።
በእግዚአብሔር መንፈስ ፤ ልቡናው ተቃኝቶ
ደስታውን ለመግለፅ ፤ ባይችል ቃል አውቶ።
በአማናዊት ታቦት ፤ በድንግል ማርያም ፊት
በእናቱ ማህፀን ፤ ዘለለ እንደ ዳዊት።
የድንግሊቱን ድምፅ ፤ ከሰማ ጀምሮ
አስጠላው የአለም ፤ ጩኸት አምባኋሮ።
ተወልዶም አልቆየ ፤ ሌላ አልሰማም ብሎ
መነነ ዮሐንስ ፤ ይህን አለም ጥሎ ።
ዘወትር ሃጢያትን ፤ ለጊዜያዊ ደስታ
እኛም እንደ ውሃ ፤ ጠዋትና ማታ
ከዚህ አለም ጉድጓድ ፤ መቅዳት እንዲበቃን
ድምጿን እንሰማ ዘንድ ፤ ድንግሊቱ ታብቃን።

✍️ አቤል ታደለ

https://t.me/Mgetem
https://t.me/Mgetem
https://t.me/Mgetem
❤77🥰14👍1😭1
ገብረ ሕይወት
@Mgetem

አቡነ ንብሎ ለገብረ ሕይወት፥
እስመ አምጽአ ለነ ትንባሌሁ ሥርየት።
ወንወድሶ በቃለ ማኅሌት፥
እንዘ ንብል ሃሌ ሉያ፥
ሰብአ ግብፅ ወኢትዮጵያ።

ስምዖን ፣ አቅሌስያ በእግዚአብሔር ፊት ፃድቃን፥
ወለዱልን ፀሐይ ብሩህ እም ብሩሃን፥
ግብፅ ብቻ አልበራ ፣ ባሕቢት አል ሐጋራ፥
ናኘ በኢትዮጵያ የትሩፋቱ ጮራ።

ዝቋላ በገድሉ ፣ ምድረ ከብድ በዐፅሙ፥
በተአምራቱም ኃይል ዝጊቲ ገዳሙ፥
በነፍስ ፣ በሥጋ ዳኑ የታመሙ፥
ወውስተ ኩሉ ምድር ወጽአ ነገሮሙ።

እንደ መቶ ሃያው አናብስት አናምርት፥
ከእግረ መቅደስህ አደግሁ ባንተ ትምህርት፥
ዛሬም እልሃለሁ "አቡየ ፣ አቡየ"
"ነዓ አድኅንነኒ ፣ ርድአኒ" ብየ።

ርእሰ ባሕታዊ ገብረ መንፈስ ቅዱስ፥
በትጉኃን ክቡር ፣ በመላእክት ውዱስ፥
በማለድከው ምልጃ ተዘቅዝቀህ ባሕር፥
በኪዳንህ ያመንሁ እኔን አምላክ ይማር።


✍️ከሣቴ ብርሃን
_
https://t.me/Mgetem
https://t.me/Mgetem
https://t.me/Mgetem
❤29👍3
🥀🌹“አንቺ ሱላማጢስ ሆይ፥ ተመለሽ፥ ተመለሽ፤ እናይሽ ዘንድ ተመለሽ፥ ተመለሽ ።” መኃልየ. 7፥1 🥀🌹

እንኳን አደረሳችሁ! ቁስቋም ማርያም

የዩቲዩብ ገጻችንን ሰብስክራይብ በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑን
https://www.youtube.com/@AwdeMihretZetewahdo
❤40🥰11👍2
#እስከዛው_ተኝቼ_ልክረም
@Mgetem

ጌታ ሆይ!
በምድር በዚች ዓለም ላይ - ጥቂት ቀናትን መክረሜ፣
አሳዝኖህ አዝነህልኝ - ከጨመርክልኝ ዕድሜ፣
የአቤሜሌክን እንጂ - የማቱሳላን አልሻም፣
ከ60 ዓመታት እንቅልፍ የ9 ምዕት ኑሮ አልመርጥም፡፡
እንደማቱሳላ ኖሬ - ከድህነት ከምታገል - መከራ ችግርን ከማይ፣
በጎዶሎዋ ምድር - ሳይሞላልኝ ከምሰቃይ፣
60 ዓመት ላንቀላፋ - ዘመነ እንቅልፍ ስጠኝ ከላይ፡፡
ለተዳከመው ገላዬ - ኑሮ ላዛለው አካሌ፣
ልትጨምርልኝ ከዳዳህ - ለዕጣ ፈንታ ለዕድሌ፣
የእንቅልፍ ዕድሜን እንጂ - ቀን አልሻም የመከራ፣
መተኛት እንጂ መቅበዝበዝ -ይቅርብኝ ጌታ አደራ፡፡
እንደ ፃድቁ አቤሜሌክ - ኢትዮጵያዊ ነኝና፣
እንደው የዘር ሆኖብኝ - መተኛት ያምረኛልና፣
እንዳልሠራ እንድጋደም፣
ጥፋቷን መድማቷን ከማይ - የሀገሬን ርሃብ ጥም፣
ሲመቻት ብቻ ቀስቅሰኝ እስከዛው ተኝቼ ልክረም፣
እንዳንቀላፋ እንዳልደክም፣
ዘመነ እንቅልፍን ስጠኝ - ዕድሜ አድለኸኝ ልጋደም፣
መቼስ ስስት አያውቅህም፡፡
©ዘሕሊና
፨፨፨ ፨፨፨ ፨፨፨ ፨፨፨ ፨፨፨ ፨፨፨
(- አቤሜሌክ የኢየሩሳሌምን ጥፋት እንዳያይ 66 ዓመት በተዐምር
እንዲተኛ የተደረገ ኢትዮጵያዊ ነው፡፡ /ትንቢተ ኤርሚያስ/
- ማቱሳላ 969 ዓመታትን የኖረ፣ በዕድሜ የሰውን ዘር ኹሉ የሚበልጥ
ነው፡፡ /ኦሪት ዘፍጥረት/
- የአቤሜሌክ 66 ዓመት መተኛት 60 መባሉ፣ የማቱሳላም 969 ዓመት
ዕድሜ 9 ምዕት/9 መቶ/ መባሉ አጠጋግቶ መቁጠር የአባቶች ልማድ
በመኾኑ ነው - 318ቱን ሊቃውንት ሠለስቱ ምዕት፣ 72ቱን ሊቃናትን
ሰባው ሊቃናት እንዲል፤)
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
t.me/mgetem
t.me/mgetem
t.me/mgetem
❤52
"እነሆም፥ ከዋነኞቹ አለቆች አንዱ ሚካኤል ሊረዳኝ መጣ፤"
ትንቢተ ዳንኤል 10:13


እንኳን ለቅዱስ ሚካኤል ዓመታዊ ክብረ በዓል አደረሳችሁ
የመልአኩ የቅዱስ ሚካኤል ጸሎቱና በረከቱ በእኛ ላይ ለዘለዓለሙ ይደርብን፤ አሜን፡፡

አውደምሕረት ዘተዋሕዶ

የዩቲዩብ ገጻችንን ሰብስክራይብ በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑን 👇
https://www.youtube.com/@AwdeMihretZetewahdo

https://t.me/AwdeMihretZetewahdo
https://t.me/AwdeMihretZetewahdo
❤39
በትሕትናው ልዕልናን ላገኘ፣ ለፍጥረታት ባለው ርኅራኄ የአምላክ እናትን ለሚመስል፣ የተቸገሩትን ፈጥኖ መርዳት ልማዱ ላደረገው፣ የእግዚአብሔር ሠራዊት አለቃ፣ ደግ እና ሰውን ወዳጅ ለሆነው መልአክ ለቅዱስ ሚካኤል ዓመታዊ በዓል እንኳን በሰላም አደረሰን።

ቅዱሳን መላእክት በአንድ ኃጢአተኛ ወደ እግዚአብሔር መመለስ የሚደሰቱትን ያህል፣ ባልተመለሰው ኃጢአተኛ ደግሞ እንዲሁ ያዝናሉ። በአንዱ ኃጢአተኛ መመለስ የተሰማቸውን ደስታ ፈጣሪያቸውን በማመስገን እንደሚገልጹ፣ ባልተመለሰው ኃጥእ የተሰማቸውን ኃዘን ደግሞ አምላካቸውን “ማረው፣ ይቅር በለው” ብለው በመለመን ያሳያሉ። (ያዕ 5፥13) ቅዱስ ሚካኤል አሁን እንዴት እንደ ሆንን አይቶ ይዘንልን፣ አዝኖም ይለምንልን፣ ለምኖም ያስምረን!!!

የዩቲዩብ ገጻችንን ሰብስክራይብ በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑን 👇
https://www.youtube.com/@AwdeMihretZetewahdo

https://t.me/AwdeMihretZetewahdo
https://t.me/AwdeMihretZetewahdo
❤31🥰3👏2
“ጾምን ቀድሱ፥ ጉባኤውንም አውጁ” (ኢዩ.፩፥፲፬)

እንኳን አደረሳችሁ!
መልካም የጾም ወቅት

የዩቲዩብ ገጻችንን ሰብስክራይብ በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑን 👇
https://www.youtube.com/@AwdeMihretZetewahdo

https://t.me/AwdeMihretZetewahdo
https://t.me/AwdeMihretZetewahdo
❤9
ዲ/ን ዳንኤል ክብረት
#ውሸት_እና_ተንኮል
@Mgetem

ውሸትና ተንኮል ጓደኞች ነበሩ፣
እውነትን ለማጥፋት፣እንዲህ ተማከሩ።
እውነት የተባለው፣ይሄ ጠላታችን፣
መጥፋት አለበት፤ጭራሽ ከዓለማችን።
እኛ እየተጠላን፣እሱ እየተወደደ፣
ብዙ ጊዜ አለፈ፣ዘመንም ነጎደ።
የኛ ጊዜ አለፈ፣ዘመንም ነጎደ።
የኛ ብቻ ይሁን፣ መላው ሀገር ምድሩ፣
ውሸትና ተንኮል፣እንዲህ ተማከሩ።
ከዕለታት በአንዱ ቀን፣ተንኮል እያደባ፤
ከውሸት ጋር ሆኖ ከእውነት ቤት ገባ።
እውነት ከጓደኞቹ ሰላምና ፍቅር፣
በድስታ በሀሴት ይጫወቱ ነበር።
ተንኮልም በድንገት፤ እውነትን ተማታ፣
ፍቅርም አዘነ፣ሠላምም ተቆጣ፣
ውሸት ብቅ አለና፣ከተደበቀበት፣
ከተንኮል ጋር ሆኖ፣ እውነትን ገደሉት።
ሰላምእና ፍቅር፣እጅግ እያዘኑ፣
እውነት ተቀበር ከመቃብር ገባ።
ዓለምን የመግዛት፣ብርቱ ዓላማችው
ውሸትና ተንኮል፣ ሞላ የልባቸው።
አንድ ቀን፣ አቶ ውሸት ተነስቶ በጧት፣
የሰፈሩን ሰዎች፣ደስታ ሲመለከት
ተጠራጠረና፣ ወደ ቀብሩ ሮጠ፣
ልክ እንደደረሰ፣ በጣም ደነገጠ።
እውነት ተፈልጎ፣መቃብሩ ሲታይ፣
ምንም ነገር የለም፣አንዳችም የሚታይ።
አወይ ልፋታችን፣ ተንኮል መጥተህ ብታይ፣
እውነት ከቶ አልሞተም፣ዓርጎ ነው ሰማይ።
ወስብሐት ለእግዚአብሔር!

እውነትና ዘይት ምንግዜም ከላይ ናቸው።
∞∞∞∞∞∞∞∞∞∞∞
https://t.me/AwdeMihretZetewahdo
https://t.me/AwdeMihretZetewahdo
❤44👍12👎6🥰3
❗️Ads: ማስታወቂያዎን ትክክለኛው #Target ጋር በቀጥታ ለማድረስ ተቸግረዋል?

በ ትምህርት (Education)፣ መዝናኛ (Entertainment)፣ ቴክኖሎጂ (Technology) እና ቢዝነስ (Business) ዘርፍ ያሉ ኢትዮጵያውያን ተጠቃሚዎችን ማግኘት ይፈልጋሉ? በ TeleAds አማካኝነት በተረጋገጡ ቻናሎች ላይ ማስታወቂያዎን በቀላሉ ያሰሩ።

የቴሌግራም ቻናል ካላችሁ? ቻናላችሁን ዛሬውኑ በማስመዝገብ ከማስታወቂያ አሰሪዎች ጋር ይገናኙ፤ ከቻናላችሁም ገቢ መስራት ጀምሩ።

@teleads_et_bot

https://teleads.tech
❤1