መንፈሳዊ ግጥም ብቻ
27.6K subscribers
173 photos
5 videos
5 files
509 links
በዚህ ቻናል ላይ በየቀኑ ኦርቶዶክሳዊ ግጥሞችን ያገኛሉ
ለአስተያየትና ግጥም እንዲፖሰትላችሁ የምትፈልጉ ለመላክ
@Solasc12
@Solasc13
@Mgetem_group

ኦርቶዶክሳዊ ጥቅሶች ብቻ
@Ortho_quotes
Download Telegram
፨ ተዘጋችተን እኑር፨
ርቀን ከቆምን ከተዋሕዶ አምባ
ምግባር ጎዶሎ እንዳንሆን ገለባ
ለማይበጀን ዓለም ጭራሽ ለማይረባ
በማይሆንን ሁሉ ስንል ወጣ ገባ
ያቺ ቀን ሳትመጣ ሳናውቅ እንደሌባ
ተዘጋጅተን እንኑር ንስሐም እንግባ።
ወስብሐት ለእግዚአብሔር

*ከገብረየስ ገቢቶ
@Mgetem
፨ማን ነው አትበሉኝ፨
ማን ነው አትበሉኝ የደማ ላንተ
ማን ነው አትበሉኝ አደኖህ የሞተ
በአብ በወልድ ስም በመንፈስ ቅዱስ
በምድር የመጣ የሰማይ ንጉስ
ከከብቶቹ ጋጥ ውስጥ የተወለደለኝ ከድንግል እናቴ
እኔ ሞቼበት ነው ሊያድን ከሃጥያቴ
ማን ነው አትበሉኝ ደም የደማ ላንተ
ማን ነው አትበሉኝ አድኖህ የሞተ
በወርቅ አክሊል ምትክ እሾህ የለበሰ
እንባዬን ሊያብሰው ደሙን ያፈሰሰ
እኔኑ ሊያድነኝ ሲገርፍ የዋለ እኔ ግን የካድኩት
ለማተብ መኖርን ያስተማረኝ እምነት
ብርክክ የምልለት የንጉሶች ንጉስ
እልል ይባልለት ለኔ ጌታ እየሱስ
ማን ነው አትበሉኝ ደም የደማ ላንተ
ማን ነው አትበሉኝ አድኖህ የሞተ
እንደ ጴጥሮስ ሆኜ ብክደውም ቅሉ
ዶሮ ሳይጮህ ሶስቴ ሳይል አኩሉሉ
እሱ ግን እሱ ነው የይቅርታ ንጉስ
ምህረትን ለመስጠት ማይጠይቅ
እየሱስ ነው ጌታ ፊቱ የሚያበራ
ግርማው የሚያስፈራ
እናም..
ማን ነው አትበሉኝ ደም የደማ ላንተ
ማን ነው አትበሉኝ ሊያድንህ የሞተ።

@Mgetem @Mgetem
4👍1
#መስቀሉ_በፊቴ
@Mgetem

የቀራኒዮ አርማ የፍቅር ሰሌዳ
የሰላም ብራና ቀለሙን የቀዳ
የድህነት ማህደሯ ጠቋሚ መሪዋ
እንቅፋት ነቃፊ አዳኝ ጠባቂዋ
የሰማዩ ንጉስ ስጋው ቆርሶባት
ደሙን አፍስሶ ላቡን ደቅኖባት
የትውልድን አረም ሊነቅል ከስሩ
ባሪያውን መስሎ ወረደ ከክብሩ።
ኤሎሄ ብሎ ጮኸ አምላክ ሆኖ ሳለ
የጠላትን መንግስት ንዶ እየጣለ
ደብዳቤውን ደምስሶ በችንካሩ ፋቀው
የዕዳው ፅሕፈት በደሙ ጠረገው።
በመስቀል የዋለ ጎልጎታ ያደረ
እባቡን ቀጥቅጦ አዳምን የማረ
ሄዋንን ከጭንቀቷ ጎትቶ ያወጣት
ልጆቿን ከሲኦል አትርፎ ከእሳት
በመስቀሉ ገፅ በችንካሩ ጫፍ
በእሾህ አክሊል ብሳት በከሳሾቹ አፍ
መከራው ሲፀና ስቃዩ ሲበረታ
ፊቱን በጥፊ ሶስት ጊዜ ሲመታ
የአምላካችን ፍቅር ከልብ የፈለቀ
ቢሆን ነው እንጂ ይቅርታው የላቀ።
በቃ!
ታዲያ ከመስቀሉ ወዲያ መገለጫ ለእኔ
ከወዴት ይገኛል ማረፊያ ለአይኔ?
ኧረ ከየት ይመጣል ተግዳሮቱን ሚያክል
የዕዳዬን ጣጣ በነፍሱ ሚከፍል።
ትምክህቱ ይራቅ ከጌታዬ መስቀል በቀር
አይኔ ሌላ አያይም ከቀራኒዮ መንደር
የመስቀሉን ፍቅር የሚያደንቀው አለ
ልቤ ላይ ከትሞ ነፍሴ እየነዋለለ።
የክርስቶስ መስቀል በፊቴ ተስሎ
እኔ እንድጠነክር እርሱ ስለኔ ዝሎ
የምሸከመውን እርሱ ተሸክሞ
ለኔ እንዲበራ እርሱ ላይ ጨልሞ
መስቀሉን ደረሰው ፍቅሩን እየፃፈ
የአመፃን ማዕበል በምሕረት ቀዘፈ
ቸርነቱ በዝቶ ቅጣቱ አለፈ።
➴ከእህተ ማርያም
ዛሬ መጋቢት 10 የጌታችንና የመዳኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ቅዱስ መስቀል የተገኘበት ቀን ነው። ቀኑ በጾም ወረ ስለሆነ ወደ መስክርም17 እንዲከበር ተደርጓል ይህም ቁፋሮ የተጀመረበት ቀን ማለት ነው።
____________________________
@Mgetem
@Mgetem
@Menfesawi_getem_bot
👍51
 #ሳልፆም_ሊፈሰክ_ነው
@Mgetem
አይ የኔ ነገር !


እርግጥ አልበላሁም #ስጋም ሆነ #ቅቤ
አልፆም አለኝ እንጂ #አመፀኛ_ልቤ
ካምናና ካቻምና #የዘንድሮ_ብሶ
መላ ማንነቴ #በሀጢያት_ተለውሶ
#ስዋሽ_ስቀጥፍ
ህግን ስተላለፍ
ስሰድብ ሳደማ
የሰው ስጋ ሳማ
ባይኔ ሳመነዝር
የሰው ሰው ሳማትር
#ገላዬን_ሳራቁት
አዳምን/ሔዋንን ሳሳስት
ስረሳ ስቃይህን
መስቀል ህማምህን
ያን ሁሉ ግርፋት
ነብሴ ሳያስጨንቃት
#አይ_እኔ
በሀሰት ስመሰክር
በሀጢያት ስዳክር
ለማይሞላ ኑሮ
ሳልሻል ዘንድሮ
ፆሙ ተጋመሰ
ጊዜው ተጋመሰ
#ጌታ_ሆይ
አቤቱ አስበኝ
ለንሰሀ አብቃኝ
#እስቲ_የቀረውን ለበረከት በለው
#አመፀኛ_ልቤ ፆምህን ይፁመው
"ከደጀ ሰላሙ ከካህኑ እግር ስር
ንስሀዬን ልውሰድ ስለመስቀል ፍቅር" 🙏
@Mgetem
3👍2
​​​​​​​​#ሕፃን_መፃጕዕ
(ውርስ ትርጉም)
ከሣቴብርሃን ገብረኢየሱስ
@Mgetem

“ብላቴና” የሚል፤
ከግብሩ የተነሣ የተሰጠው ቅፅል፤
በትርጓሜ ወንጌል የሚነበብ ሰፍሮ፤
መፃጕዕ መፃጕዕ ሕፃነ አእምሮ፤
ጨቅላ ነው ፤ ትክክል!
ምንም ነፍስ የማያውቅ፤
እሳትና ውሃን መለየት የማይችል።

ቢለይማ ኖሮ፤
ከእሳተ መለኮት ፤ እጁን ይልክ ነበር ፤ ለጥፊ ሰንዝሮ ?
......................................................
መነሻ ቅኔ ፦ ዕዝል ጉባዔ ቃና
ዘመሪጌታ ጥበበ ደስታ

 ሕፃን ኢያእመሬ ነፍስ ዓዲ፤ 
አኮኑ ፈነወ እዴሁ መንገለ እሳት ነዳዲ

.......................................................
መፃጕዕ ለ 38 ዓመት ሲማቅቅበት ከነበረ ደዌው የፈወሰው ክርስቶስን በቤተመቅደስ በጥፊ ስለ መምታቱ መሪጌታ ጥበበ ደስታ የተቀኙትን ቅኔ መነሻ በማድረግ የተገጠመ
ከሣቴብርሃን ገብረኢየሱስ
.......................................................
@Mgetem
@Mgetem
@Scgpx9
👍2🥰1
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#በኃይማኖት_ስኖር
መጋቤ ሐዲስ ሳሙኤል አያልነህ
@Mgetem

በኃይማኖት ስኖር ከኃጢአት ጠብቀኝ
ኃጢአት ብሰራ ግን ተንሳሒ አድርገኝ
ከኃጢአት ጋር መኖር እንዳልለማመድ
ንፁህ ልብ ስጠኝ ልጓዝ በአንተ መንገድ
ጥቂት ናት እያልኩኝ መስላኝ የማትጎዳ
ኃጢአት ሳጠራቅም በህይወቴ ጓዳ
ንስሐ ገብቼ ሳልወጣ አርነት
እንዳልሞት ታደገኝ በኃጢአት ባርነት።
@Mgetem
@Mgetem
👍2
ዲ/ን ዳንኤል ክብረት
#ውሸት_እና_ተንኮል
@Mgetem

ውሸትና ተንኮል ጓደኞች ነበሩ፣
እውነትን ለማጥፋት፣እንዲህ ተማከሩ።
እውነት የተባለው፣ይሄ ጠላታችን፣
መጥፋት አለበት፤ጭራሽ ከዓለማችን።
እኛ እየተጠላን፣እሱ እየተወደደ፣
ብዙ ጊዜ አለፈ፣ዘመንም ነጎደ።
የኛ ጊዜ አለፈ፣ዘመንም ነጎደ።
የኛ ብቻ ይሁን፣ መላው ሀገር ምድሩ፣
ውሸትና ተንኮል፣እንዲህ ተማከሩ።
ከዕለታት በአንዱ ቀን፣ተንኮል እያደባ፤
ከውሸት ጋር ሆኖ ከእውነት ቤት ገባ።
እውነት ከጓደኞቹ ሰላምና ፍቅር፣
በድስታ በሀሴት ይጫወቱ ነበር።
ተንኮልም በድንገት፤ እውነትን ተማታ፣
ፍቅርም አዘነ፣ሠላምም ተቆጣ፣
ውሸት ብቅ አለና፣ከተደበቀበት፣
ከተንኮል ጋር ሆኖ፣ እውነትን ገደሉት።
ሰላምእና ፍቅር፣እጅግ እያዘኑ፣
እውነት ተቀበር ከመቃብር ገባ።
ዓለምን የመግዛት፣ብርቱ ዓላማችው
ውሸትና ተንኮል፣ ሞላ የልባቸው።
አንድ ቀን፣ አቶ ውሸት ተነስቶ በጧት፣
የሰፈሩን ሰዎች፣ደስታ ሲመለከት
ተጠራጠረና፣ ወደ ቀብሩ ሮጠ፣
ልክ እንደደረሰ፣ በጣም ደነገጠ።
እውነት ተፈልጎ፣መቃብሩ ሲታይ፣
ምንም ነገር የለም፣አንዳችም የሚታይ።
አወይ ልፋታችን፣ ተንኮል መጥተህ ብታይ፣
እውነት ከቶ አልሞተም፣ዓርጎ ነው ሰማይ።
ወስብሐት ለእግዚአብሔር!

እውነትና ዘይት ምንግዜም ከላይ ናቸው።
∞∞∞∞∞∞∞∞∞∞∞
@Mgetem
@Mgetem
@Menfesawi_getem_bot
3👍2👎1
Forwarded from Daregot Media
መድኃኔዓለም ወይስ የግል አዳኝ


መዳን እንደ ቀለብ ፤ መዋጀት እንደ እህል፤
በቁና ተሰፍሮ የተሰጠ ይመስል፤
መሲሑን ለብቻ ፤ ኢየሱስን የግል፤
አ’ርገህ ምትቀበል፤
አድራሻህ ከየት ነው ስምህን ማን ልበል?

በእንተዝ ነገር ስምዐ ኮነ መልአክ፤
በጊዜ ልደቱ ወደ እረኞች ሲላክ።
መድኃኒት ክርስቶስ ግርግም መወለዱ ፤ በጨርቅ መጠቅለሉ፤
ለእረኞች በግል የተሰጠ ሳይሆን ለዓለሙ ሁሉ፤
እነሆ ሲታወቅ በምሥራች ቃሉ፤
አልሰማህም አሉ።

ራሱ ባለቤቱ፤
በወንጌል ትምህርቱ፤
“ለድኅነተ ዓለም በመልዕልተ መስቀል
ከምድር ከፍ ብዬ ዕርቃኔን ስሰቀል”
አንድ ሁለት ሰው ሳይሆን “ሁሉን እስባለሁ”
ሲል እየሰማነው፤
ጆሮ ነሳህ ምነው?

ደግሞስ ሳምራዊቷ፤
“ብፍርስንያ” ‘ሚሏት ውሃ ቀጂ ሴቷ፤
ውሃ አጠጭኝ ብሎ ፤ በፍቅር ጎብኝቷት ፤ እሷን ብቻ መርጦ፤
ሕይወት ሆኗት ሲሄድ ታሪኳን ለውጦ፤
አዳኝ ፣ መሲሕ የግል፤
መቼ ሰማን ስትል?
እንስራዋን ጥላ ገሰገሰች እንጂ ሰማርያ መንደር፤
የጠበቅነው አምላክ ተገለጠ ብላ ላ’ለም ልትናገር።
ከዚያማ፤
ድኅነት በሷ ሳይቀር፤
ለሃያ አምስት ምዕት ወገኖቹ መጣ፤
ከዓለት ክርስቶስ ማየ ሕይወት ፈልቆ ሁለት ቀን ተጠጣ።

መጣፍ ባለማወቅ ልቡናህ የሳተ፤
ዝንጕ ‘ምትሆን አንተ፤
“በእውነት ክርስቶስ የዓለም መድኃኒት እንደሆነ አውቀናል።”
ስትል ሰማርያ ፤ በአልሰሜነትህ በጣም ተደንቀናል።

ከእንግዲህስ ስማ የተዋሕዶን አዋጅ፤

“ቤዛ ኵሉ እንጂ ነው ዓለሙን የሚዋጅ፤
የብቻዬም አይደል፤
የብቻህም አይደል፤
ፋሲካን ልታከብር በደመ ክርስቶስ ፤ ነጽታ ምትታጠብ፤
የምድር ሐሴት እንጂ ፤ የምድር ሁሉ ገንዘብ።
እናም፤
“መ ድ ኃ ኔ ዓ ለ ም”
ያለሚለው ቀለም፤
ትድግናውን ገላጭ ምሉዕ ፊደል የለም።”

እያለች ስትጠራው ስማት በየዕለቱ፤
እያት ስታነግሠው በስመ መንግሥቱ፤
በጥንተ ስቅለቱ።

መድኃኔዓለም!
መድኃኔዓለም!
መድኃኔዓለም!
3👍1
#ጠላት_ለምን_ከፋው
@Mgetem

እኔው ጎንበስ ብዬ እኔው ቀና ላልኩት
እኔው አመስግኜ እኔው ለሰገድኩት
ጠላት ምን ተነካ የሚያረው በቅናት
እመቤቴ ብዬ እኔው ለወደድኳት
ያንድዬ እናት ብዬ እኔው ላወደስኳት
ብወድቅ ብነሳ እኔው ካልደከመኝ
ሳወድሳት ባድር እኔን ካልሰለቼኝ
ስማፀናት ብውል እኔው ካልታከተኝ
ጠላት ምን አገባው አትስገድ የሚለኝ
ፃድቃንን አይቼ እኔ ብማፀናት
ገብርኤልን አይቼ እኔ ባወድሳት
ሰማዕታትን አይቼ እኔ ብሞትላት
አምላክን አይቼ እኔ እርሷን ብመርጣት
ልጄ ስላለችኝ እናቴ ስላልኳት
ጠላት ለምን ከፋው እኔ እርሷን ብወዳት።
#ከክብሪት_ተፈራ
@@@@@@@@@@@@@@
@Mgetem
@Mgetem
🥰3
#ገድፍሃል
@Mgetem

አንደበትህ ክዶህ ሀሰት ከለመደ
መልካሙን ናቅ አርጎ ሴራ ከወደደ
እንደ አምሳል መሰረት ቀረ ሰው መሆንህ
አምላክም አይኖርም ሳይጣን ነው ከጎንህ
በህይዎት እየኖርክ ከሆንክ አሜኬላ
እኔ ሰው ነኝ እያልክ ልብህ ሰው ከጠላ
በእምነቱ ፀንተህ ወስጋ ከደሙ
አልገለጽ ካለህ የህይወት ትረጉሙ
እውነቱን ተቀበል
ጾምህን ገድፍሃል
ለምን! ማለት ጥሩ ለምን ይመስልሃል?
ውሰጥ ተመርዞ
ልብህ ቂም አርግዞ
ላይሰምር ሱባኤ
ልብ ሳይኖር ጉባኤ
ገደብ የለሽ ምኞት
ከአንገት በላይ ፀሎት
በላይኛው አለም ወንዝ አያሻግርም
እዚ እንደለመደከው ማጭበርበር አይኖርም።

@Mgetem
@Mgetem
👍3
​​#የቆምኩኝ_ሲመስለኝ
@Mgetem

ማዘያው ከጠፋ #የህፃን_አንቀልባ
መልካሙ ተጣሞ #ካጨድን_ገለባ
አፅናኙ ተክዞ መፅናናትን ካጣ
የቆመ የሚመስለው ጎብጦብን ከመጣ
ረሀብ አጠውልጎት  ህፃን ካለቀሰ
ጻድቅ መላ ጠፍቶት #ሰይጣን_ከቀየሰ


#ብርታት_አጎንብሶ ድካም ፀንቶ እግሩ
ይሁዳና ዴማስ ጽድቅ ከመከሩ
ሳዖልና ኬፋ ደግ ካልተስማሙ
አቤቱ ለባሪያህ #መንገዱን_አብራለት
ማየትና መስማት ካንተ ይሁንለት።

#ፈትልን_የሚፈትል ተራቁቶ ካደረ
#ውለታ_የበዛለት በሳቅ ካልዘመረ
በብዙ የተሾመ ጥቂት ካልታመነ
ልብን አሳራፊው ልቡ ከጨከነ
#ሰባኪ_እየካደ ዓለሙ ካመነ

አማኙ ሲታበይ #ቀራጭ_አጐንብሶ
የጽድቁን አዝመራ ከወሰደ አፍሶ
#አቤቱ_ለባሪያህ አይነ ልቡን አብራ
የቆምኩኝ ሲመስለኝ እንዳልወድቅ አደራ።

#ሥራዬ_የሞት ነው ጽድቄ የመርገም ጨርቅ
#አቤቱ_አድነኝ በድካሜ ሳትፈርድ
ብርታትህ ያቁመኝ አንተን እንድመስል
#ማስተዋሌን_አድስ ያለማመኔን ቃል፡፡

ΠΠΠΠΠΠΠΠΠΠΠΠΠΠΠΠΠΠΠ
@Mgetem
@Mgetem
@Menfesawi_getem_bot
​​#መዝሙር_አለቀሰ 💧
@Mgetem

የያሬድ ዝማሬ የአዘማመር ስልቱ
የበገናው ቃና መሠንቆ ቅኝቱ
የከበሮው ውበት የዋሽንት ፍሰቱ
ነበረ ተፈጥሮአቸው ስብሐትን ሊዘሩ
ነበር ተፈጥሮአቸው ስርዓትን ሊያከብሩ
መንፈስን አድሰው ውበትና ሊደምሩ
ስንዱዋ እመቤት ቤተክርስቲያን ቅድስት
ሁሉን አስተማረች እንዳለ በስርዓት
ዛሬማ አፍ የፈታ ሁሉ እያንጎራጎረ
ቀኖና ትውፊቱን እየሸረሸረ
የመዝሙር ስርዓቱ ስልቱ ተቀየረ
መዝሙር ዜማ ሳይሆን ጩኸት ሆኖ ቀረ
ለነፍስ ተትቶ ለስጋ እያደረ
ሳኦልም ከደዌው እንዳልተፈወሰ
ወይኒውም በመዝሙር እንዳልፈራረሰ
መዝሙር ቅዱሳንን እንዳላወደሰ
ዜማን ሀዘን ገባው መዝሙር አለቀሰ
ንጉስ ገ/መስቀል ከግሩ ጦር ሰክቶ
በፍፁም ተመስጦ አለምን እረስቶ
እንዳልነበር ሁሉ ፀጋችን ምግባችን
መዝሙር አንገት ደፋ ከመላዕክት በላይ አዋቂዎች ሆነን
ሰይጠፋ መዝሙሩ እስከነ ስረዓቱ
ፈር እየለቀቀ ዘማሪ ነኝ አለ ሁሉም በየቤቱ
በጠፋበት ሁሉ ተጥሶ መክሊቱ
መዝሙር አለቀሰ ተገፎ ውበቱ
መዝሙር አለቀሰ ተጥሶ ስርዓቱ።
🕓🕓🕓🕓🕔🕓🕓🕓🕔🕓🕔🕔
@Mgetem
@Mgetem
👍31
​​#አቃጥሏት_ግዴለም
@Mgetem
🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥
ቤተ ክርስቲያክርስቲያን ቅድስት እመ ኵሉ፣
የወንጌል ማኅደር የጸናብሽ ቃሉ፣
ስብከትሽ ሰላም ነው ለዓለም በሙሉ፤
አፅራረ ሰላም ግን አንቺን ይጠላሉ፤
ተልእኮሽ ፈውስ ነው ለታመሙ ኹሉ፤
መዳን የማይወዱ ከአንቺ ይሸሻሉ፤
ጭራሽ ሊያሳድዱሽ ይመካከራሉ፤
አጥፍቶ ጠፊዎች ሊያጠፉሽ ይሻሉ።

የጥፋት ልዑካን ለጽድቅ ያልታደሉ፣
ሕንፃሽን በእሳት አቃጠሉት አሉ፤
ጣሪያ ግድግዳዉን አፈረሱት አሉ፤
ባያውቁት ነው እንጂ ቢጠፋቸው ውሉ፣
በአንቺ እሳትነት አብረው ይጨሳሉ፤
በማገዱት እንጨት ኋላ ይነዳሉ፤
ዛሬ እንዳፈረሱሽ ነገ ይፈርሳሉ፤
በሠፈሩት መጠን ዋጋን ያገኛሉ።

አህዛብ ግብዞች ሆይ የሰይጣን ፈረሱ፣
ደስ ካሰኛችሁ እሳት መለኮሱ፣
አቃጥሏት ግዴለም ጣሪያዋን አፍርሱ፤
ግድግዳ ወለሉን ብሎኬቱን አንሡ፤
ለጊዜውም ቢኾን ቅፅሮቿን ደምስሱ፤
ልጆቿን በሙሉ ደም ዕንባ አስለቅሱ።

ነገር ግን ጌታዋ ሲቆጣ ንጉሡ፣
መቃጠላችሁን ፈጽሞ እንዳትረሱ፤
ጽዋ ተርታችሁን ዘወትር አስታውሱ፡፡

ጌታ ችሎ ችሎ መዓቱን ሲያመጣ፣
ቅፅሩን ለማስከበር ሲፈርድ በቁጣ፣
በተራ መንደድ ነው የኹላችሁ ዕጣ፡፡

እስከዚያው ድረስ ግን እስኪመጣ ጌታ፣
የዓለምን መድኀኒት የሕዝብን አለኝታ፣
ቤተ ክርስቲያንን አፍርሷት በአንድ አፍታ፤
አቃጥሏት ግዴለም አንድዷት በተርታ፡፡

እርሷ በትረ ወንጌል የሾለ ብረቱ፣
ብትቆሙ ደፍራችሁ በኃያል ስለቱ፣
ደዌው ለእናንተ ነው ሕመሙ ጉዳቱ።

ጣሪያና ግድግዳው አካሏ ቢደማ፣
ብትነድ ብትቃጠል በክፉዎች ፊርማ፣
መቅደስ ማኅሌቱ ቢመስልም ባድማ፣
አትፈርስም በፍጹም በግብዞች ዐድማ፤
እሳት የሚያነዳት አይደለችም እማ፤
በክርስቶስ ፍቅር ተቃጥላለች ቀድማ፡፡

ቤተ ክርስቲያን ይቺ ምድራዊቷ፣
መለኮት እሳት ነው ጥንትም መሠረቷ፣
የክርስቶስ ደም ነው እስትንፋስ ሕይወቷ፣
አቃጥሏታልና ክርስቶስ እሳቷ፣
አጽንቷታልና አምላክ ባለቤቷ፣
በፍጹም አትፈርስም ጽኑ ነው ዐለቷ፤
በጠላት ዘመቻ አይኾንም ኅልፈቷ፡፡

ወስብሐት ለእግዚአብሔር!
→→→→→→→→→→→→→→

መርከቧን የሚያውክ ንፋስ መቷል
አድነን ክርስቶስ ተጨንቀናል
አድነን ክርስቶስ ተማጽነናል 🙏

ቅድስት ቤተክርስቲያናችንን እግዚአብሔር አምላክ ይጠብቅልን
ሀገራችን ኢትዮጵያን ሰላም ያድርግልን አሜን!!!፫
→→→→→→→→→→→→→→
@Mgetem
@Mgetem
@Menfesawi_getem_bot
👍6🥰1
#ሳይፀልዩ_ማደር
@Mgetem

የተራበ ነብር ከሩቅ ተመልክታ
ሚዳቋ ፀለየች....
"አውጣኝ አውጣኝ" አለች ለፈጠራት ጌታ
ነብሩም ተርቦ
ወደ አምላኩ ቀርቦ
ሚዳቆዋን አይቶ - አንጀቱ ከሆዱ እንደጠጣበቀ
ፈቅዶ እንዲሰጠው - አምላኩን ጠየቀ

የሁለቱን ማብላት - የሁላችን ሰሪ
ፀሎታቸውንም - ሰማቸው ፈጣሪ
አምላክም በድምፁ - ሚዳቆዋን አላት
"እሩጠሽ አምልጪ - ከበረታ ጠላት"

ነብሩንም አለው - "እሩጥ ተከተላት
ምግብህ አርገህ ብላት
ሚዳቆዋ ስትሮጥ
ከነብር ለማምለጥ
ነብሩም ሲከተላት
ሆዱን ሊሞላባት

ቋጥኙን ስትዘል እግሯ ተስፈንጥሮ
ሆዱን ብትረግጠው የተኛው ከርከሮ
ከእንቅልፉ ሲነቃ ልክ ሲደነብር
ጉሮሮውን ያዘው የፀለየው ነብር

አውጣኝ ያለው_ወቶ - አብላኝ ያለው በላ
ሳይፀልይ ያደረው - ከርከሮ ተበላ 🙏
💠💠💠💠💠💠💠💠💠💠💠💠
@Mgetem
@Mgetem
👍62
​​#ይቅርታ_አድርጉልኝ
@Mgetem

#ትናንት_ለበደለን ፡ አምና ላስቀየመን
#ቅሬታን_አጥፍተን ፡ በደል መቁጠር ትተን
የንስሀን ጊዜ ፡ ጨምሮ ሊሰጠን
ይቅርታ እንድናደርግ፡ #ጷጉሜ_ተለገሰን  ።

 ፈንድቆ ለመኖር ፡ እንደ ጨቅላ ህፃን
በሰላም ይፈታ ፡ የቂም ቋጠራችን
ይቅር እንባባል ፡ #አንዳችን_ለአንዳችን
ለዚህ ነው የተሰጠን ፡ #ጷጉሜ_ድልድያችን

እስካሁን ላረኩት ፡ በደል በናንተ ላይ
ይቅርታ አድርጉልኝ ፦

ይቅርታ የሚያደርግ ፡ #ነውና_አስተዋይ
#ለጥሩም_ለመጥፎም ፡ ፍርድ አለ ከሰማይ
ግን እስካለን ድረስ ፡  በጥፉት ምድር ላይ
ለገዛ ጥቅሜ ስል  ፡ ለሰራሁት ጉዳይ
እያወኩኝ ሳላውቅ ፡ እያየሁኝ ሳላይ
ለበደሌ ሁሉ ፡ በሞት ሳንለያይ
#ይቅርታ_አድርጉኝ

ሰው ከአባቱ ገዳይ ፡ ይታረቅ የለም ወይ። 🙏
@Mgetem
@Mgetem
👍3
#ኒቆዲሞስ ዩሐ 3÷2
@Mgetem

ፈሪሳዊው እውቅ መምህር
ሊቅ አልነበርክ ያገር ክብር?
የምርጥ ምርጥ ከእውቅም እውቅ
ነበርክ እኮ የአይሁድ ሊቅ

ግና ሕግ አዋቂ ነህ መባሉ
መምህር ነው ቢልህ ሁሉ
የውስጥህን ስቃይ ገልጠህ
ሚዛን ባይደፋ እውቀትህ
የሰው ሙገሳ ድለላ
ውስጥ ባዶህን ባይሞላ
አስገራሚው ድብቅ ጉዞህ
ከቀን ለሊት አስመርጦህ
ወደ ጌታ መገስገስህ
ሊቅ ስትባል መጠየቅህ
ሕይወት አሲዞ መለሰህ።
______________________
@Mgetem
@Mgetem
@Menfesawi_getem_bot
👍1
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#አህያዋ
@Mgetem

ከእንስሳት ተለይታ
ልትቆም በሰው ተርታ
ሊቀመጥባት ጌታዋ
ሊታወቅላት ዋጋዋ
ላይጠፋባት አደራዋ
ሰው የማገልገል ስራዋ
ሲመጣላት ፈጣሪዋ
ደስ አላት አህያዋ
ሲቀመጥባት በጀርባዋ።
ውርንጭላነቷ ቀርቶ
የታሰረችበት ገመድ ተፈቶ
መናቅ መሰደቧ ጠፍቶ
የዋሁ የጺዮን ልጅ ትህትናን ተመልቶ
አስገባት ከተማ በህዝቡ ፊት መርቶ።
አፋቸው ተለጉሞ
ሃሳባቸው ከፍቶ ጠሞ
አዋቂ ነን ባዮቹ
የአይሁድ ካህናት ግብዞቹ
ዝም ቢሉ ለምስጋና
ለመራቸው በደመና
ለመገባቸው ከሰማይ መና
መመስገኑ መቼ ቀረና
እየተባለ ሆሳእና።
በሴቶች በወንዶቹ
በአዛውንት በልጆቹ
በህጻናት ጡት ጠቢዎቹ።
የዘኪዮስ ምኞት
መቼ ተረሳ በእጥረቱ
ዛፍ ላይ ብቻ በመታየቱ
አለቀረም ፍላጎቱ
ለመዘመር መጓጓቱ
ገብቶለታል ወደ ቤቱ
የጺዮን ልጅ ያትሁቱ
ሊበላ አብሮት ከፍትፍቱ።
መቅደስ ገብቶ ዞሮ ሲቃኝ
ሲመለከት ጊዜ አባካኝ
ጽሎት ትቶ ሲቸረችር
ከሌባ ጋር ሲደራደር
አልቻለም ስለ ቤቱ
ሲያቃጥለው ቅንአቱ
ጅራፍ ሰራ ለትምህርቱ
ቤቱን ሊያጠራ ከጠላቱ።
________________
@Mgetem
@Mgetem
@Menfesawi_getem_bot
👍32
Track 1
Unknown artist
የመዝሙር ግብዣ
🎶🎶🎶🎶🎶🎶🎶🎶🎶🎶
#ዘማሪ =ቴዎድሮስ ዮሴፍ
#ርዕስ =መስቀል ላይ ያየሁት ፍቅር
#አልበም =ቁ.9 የንሰሀ
@Mgetem
@Mgetem
👍1