\\ልቤ_ሰላም_አርገልኝ//
ቸር ጠባቂ የሰራዊት ጌታ
ቀና ስል የማይህ በጥዋት በማታ
በረከትህ ብዙ ስጦታህን የማያልቅ
የማይደርቅ ምንጭህ ፍፅም
ክፉ ስራችን አይተህ ሳትፈርድብን
ሳትቆጣን በምህረትህ በቸርነትህን
ከዘመን ዘመን አሻገርከን ተመስገን
የሚደነቅ፦
ብላቴና ሳትል ታላቁን አዛውንት
ቀሳውስቱን ሳትል ታላቁን ሊቃውንት
ሁለን በየፍርዱ ታሰድስተዋለህ
በፀጋህ በፍቅርህ ትባርከዋለህ
እኔም ልመና አለኝ ሳለሁ በመቅደስህ
በወርቁ ማጠኛ በመሰቀሉ እንዳይህ
ልበ ሰላም አርገልኝ ባርከኝ በእጅህ"።
አቤቱ_አምላኬ_ሆይ_የመጠሪያዩን_ዘመን_አላዉቀውምና_ለንሰሐ_ሞት_አበቃኝ_ዘንድ_ቅዱስ_ፍቃድህ_ይሁን_ኣሜን፫
ወስብሓት_ለእግዚአብሔር
ወለወላዲቱ_ድንግል ወለመስቀሉ_ክብር_ይቆየን_አሜን፫
*ከእህተ ማርያም
=====================
@Mgetem
ቸር ጠባቂ የሰራዊት ጌታ
ቀና ስል የማይህ በጥዋት በማታ
በረከትህ ብዙ ስጦታህን የማያልቅ
የማይደርቅ ምንጭህ ፍፅም
ክፉ ስራችን አይተህ ሳትፈርድብን
ሳትቆጣን በምህረትህ በቸርነትህን
ከዘመን ዘመን አሻገርከን ተመስገን
የሚደነቅ፦
ብላቴና ሳትል ታላቁን አዛውንት
ቀሳውስቱን ሳትል ታላቁን ሊቃውንት
ሁለን በየፍርዱ ታሰድስተዋለህ
በፀጋህ በፍቅርህ ትባርከዋለህ
እኔም ልመና አለኝ ሳለሁ በመቅደስህ
በወርቁ ማጠኛ በመሰቀሉ እንዳይህ
ልበ ሰላም አርገልኝ ባርከኝ በእጅህ"።
አቤቱ_አምላኬ_ሆይ_የመጠሪያዩን_ዘመን_አላዉቀውምና_ለንሰሐ_ሞት_አበቃኝ_ዘንድ_ቅዱስ_ፍቃድህ_ይሁን_ኣሜን፫
ወስብሓት_ለእግዚአብሔር
ወለወላዲቱ_ድንግል ወለመስቀሉ_ክብር_ይቆየን_አሜን፫
*ከእህተ ማርያም
=====================
@Mgetem
👍2❤1
#የቱ_ላይ_ነው_ፍቅርህ?
@Mgetem
በጥጋቡ ዘመን አብሬክ ታድሜ
ስጠማ ጠጥቼ ስራብ ተመግቤ
ላልክድህ ምያለው ከቤትህ ላልርቅ
በሰው ፊት መስክሬ ኪዳንህን ልጠብቅ
አሁን ትቼክ ከሄድኩ ቀራንዮ ሳለህ
ብለህ ስጠይቀኝ የቱ ላይ ነው ፍቅርህ
ጌታዬ ጨነቀኝ ምን ልመልስልህ
.
.
.
ዘወትር ስጠራኝ ዘውትር ሳንቀላፋ
ሁሌ ስትፈልገኝ ሁልጊዜ ስጠፋ
አንተ ከእኔ ስርቅ ኃጢአትን ስለምዳት
ሶስት የዶሮ ጬኸት ሲያልፈኝ እንደዘበት
ብለህ ስጠይቀኝ ምኑ ላይ ነው ፍቅርህ
ጌታዬ ጨነቀኝ ምን ልመልስልህ
.
.
ምትህ ሞቴን ሲሽር ስቃይህ ስቃዬን ስደት ስደቴን
የርህራሄ ጥልቀት የፍቅርህ ስፋቱ
ሳይረዳኝ ሲቀር እንዲው እንደከንቱ
ይህን ተገንዝበህ ብለህ ስጠይቀኝ የቱ ላይ ነው ፍቅርህ
ጌታዬ ጨነቀኝ ምን ልመልስልህ
.
.
እንባዬ ሲታበስ ጭንቀቴ ሲፈታ
ፈጥነህ ስደርስልኝ የጠራሁ ለታ
ቀይ ባህር ሲከፈል ፈርኦንም ሰጥሞ ሲቀር
ከበሮ እየመታሁ በደስታ ስዘምር
ቆይቼ -ቆይቼ-ሁሉን እረስቼ
ሃጢአት ውስጥ ገብቼ ጣኦት አረስቼ
ስክድህ ስታየኝ ውሌን በጥሼብህ
ብለህ ስትጠይቀኝ የቱ ላይ ነው ፍቅርህ
ጌታዬ ጨነቀኝ ምን ልመልስልህ።
__________________________
@Mgetem
@Mgetem
@Menfesawi_getem_bot
@Mgetem
በጥጋቡ ዘመን አብሬክ ታድሜ
ስጠማ ጠጥቼ ስራብ ተመግቤ
ላልክድህ ምያለው ከቤትህ ላልርቅ
በሰው ፊት መስክሬ ኪዳንህን ልጠብቅ
አሁን ትቼክ ከሄድኩ ቀራንዮ ሳለህ
ብለህ ስጠይቀኝ የቱ ላይ ነው ፍቅርህ
ጌታዬ ጨነቀኝ ምን ልመልስልህ
.
.
.
ዘወትር ስጠራኝ ዘውትር ሳንቀላፋ
ሁሌ ስትፈልገኝ ሁልጊዜ ስጠፋ
አንተ ከእኔ ስርቅ ኃጢአትን ስለምዳት
ሶስት የዶሮ ጬኸት ሲያልፈኝ እንደዘበት
ብለህ ስጠይቀኝ ምኑ ላይ ነው ፍቅርህ
ጌታዬ ጨነቀኝ ምን ልመልስልህ
.
.
ምትህ ሞቴን ሲሽር ስቃይህ ስቃዬን ስደት ስደቴን
የርህራሄ ጥልቀት የፍቅርህ ስፋቱ
ሳይረዳኝ ሲቀር እንዲው እንደከንቱ
ይህን ተገንዝበህ ብለህ ስጠይቀኝ የቱ ላይ ነው ፍቅርህ
ጌታዬ ጨነቀኝ ምን ልመልስልህ
.
.
እንባዬ ሲታበስ ጭንቀቴ ሲፈታ
ፈጥነህ ስደርስልኝ የጠራሁ ለታ
ቀይ ባህር ሲከፈል ፈርኦንም ሰጥሞ ሲቀር
ከበሮ እየመታሁ በደስታ ስዘምር
ቆይቼ -ቆይቼ-ሁሉን እረስቼ
ሃጢአት ውስጥ ገብቼ ጣኦት አረስቼ
ስክድህ ስታየኝ ውሌን በጥሼብህ
ብለህ ስትጠይቀኝ የቱ ላይ ነው ፍቅርህ
ጌታዬ ጨነቀኝ ምን ልመልስልህ።
__________________________
@Mgetem
@Mgetem
@Menfesawi_getem_bot
👍3
#ነበርኩ_መች_ያድናል
@Mgetem
ሀጢያትን ስትሰራ አምላክን እረስተህ
ቅዱሱን ሰውነት በሀጢያት አርክሰህ
ትእዛዝን ሳትፈጽም መልካምን ሳትሰራ
ዘይት ሳታዘጋጅ መብራትህ ሳይበራ
በተጠራህ ጊዜ መላከሞት ሲመጣ
ለማያልፈው አለም ሲወጣልህ እጣ
ለሚዛን ስትቀርብ አገልጋይ ነበርኩኝ እያልክ መናገሩ
መዝሙር ዘምሬያለው ሄጃለው ከበሩ
ብሎ መከራከር ያኔ መች ይጠቅማል
ይዞ መገኘት ነው ነበርኩ መች ያድናል!!!!
____________________________
@Mgetem
@Mgetem
@Menfesawi_getem_bot
@Mgetem
ሀጢያትን ስትሰራ አምላክን እረስተህ
ቅዱሱን ሰውነት በሀጢያት አርክሰህ
ትእዛዝን ሳትፈጽም መልካምን ሳትሰራ
ዘይት ሳታዘጋጅ መብራትህ ሳይበራ
በተጠራህ ጊዜ መላከሞት ሲመጣ
ለማያልፈው አለም ሲወጣልህ እጣ
ለሚዛን ስትቀርብ አገልጋይ ነበርኩኝ እያልክ መናገሩ
መዝሙር ዘምሬያለው ሄጃለው ከበሩ
ብሎ መከራከር ያኔ መች ይጠቅማል
ይዞ መገኘት ነው ነበርኩ መች ያድናል!!!!
____________________________
@Mgetem
@Mgetem
@Menfesawi_getem_bot
#ስጋ_ነው_ምርኩዜ
@Mgetem
ስጋዬ ወፍሮ አፌ ክፉ ደፍሮ
ሓሰትን መስክሮ እውነት ቅሉን ሽሮ
እውነት ተሸሸጋ ማን እውነት ሊያወጋ
ስለ ክፉ ስጋ።
ስለ ክፉ ስጋ ነፍሴ ስትወጋ
የአንደበቴ ችቦ የአንደበቴ ሰንጋ
ነፍሴ ስትቃትት የስጋ ጦር ወግቷት
ቀንም ሌሊትም ቁስሉ ሲያሰቃያት
ጭንቅ ጥብብ አለች ቀኑ ጨልሞባት
የምታውቀው ቤቷ ተዘግቶባት
ስጋ ሲበድላት በሐዘን በትካዜ
በሐሰት ባለሟል በስጋ ምርኩዜ
እኔንም ተረድታ በእምነት መደብዘዜ
በህይወት ልታልፍ ልትጓዝ በግዜ
ነፍሴ የተዘጋጀች ልታቀርብ ኑዛዜ።
____________________________
@Mgetem
@Mgetem
@Menfesawi_getem_bot
@Mgetem
ስጋዬ ወፍሮ አፌ ክፉ ደፍሮ
ሓሰትን መስክሮ እውነት ቅሉን ሽሮ
እውነት ተሸሸጋ ማን እውነት ሊያወጋ
ስለ ክፉ ስጋ።
ስለ ክፉ ስጋ ነፍሴ ስትወጋ
የአንደበቴ ችቦ የአንደበቴ ሰንጋ
ነፍሴ ስትቃትት የስጋ ጦር ወግቷት
ቀንም ሌሊትም ቁስሉ ሲያሰቃያት
ጭንቅ ጥብብ አለች ቀኑ ጨልሞባት
የምታውቀው ቤቷ ተዘግቶባት
ስጋ ሲበድላት በሐዘን በትካዜ
በሐሰት ባለሟል በስጋ ምርኩዜ
እኔንም ተረድታ በእምነት መደብዘዜ
በህይወት ልታልፍ ልትጓዝ በግዜ
ነፍሴ የተዘጋጀች ልታቀርብ ኑዛዜ።
____________________________
@Mgetem
@Mgetem
@Menfesawi_getem_bot
❤3👍1
እንዴት ተሸነፍን ?
✍ከሣቴብርሃን ገ/ኢየሱስ
እንዴት ተሸነፍን?
ለምን እጅ ሰጠን?
የፈቃድ ምርኮኞች አርጎ ማን ለወጠን?
በሥጋ አበው በመንፈስ ጠላት፤
የኾ’ንባትን ግብር ማን ይሆን ልብ ያላት?
እነሆ ምሥክር. . . . . . ከሕያዋን መዝገብ፤
የደም የአጥንት ጽሕፈት ደምቆ ሚታይ ሳይነትብ፤
ዓድዋ ብራና ተገልጦ ይነበብ!
በእምዬ ምኒልክ እምዬ ምትባል፤
በልቡ የምትሣል፤
የከንፈሩ ውብ ቃል፤
የኪዳን ማሠርያ ኾና የምትማል፤
በምልጃ ጸሎቷ በልመናዋ ኃይል፤
ድል ብታቀዳጀው ይኼ ምን ይገርማል?
ለ’ኛም ደበዘዘች የማንነት ፊደል፤
ድል ማንበብ ተስኖን… በዕውር ለዕውር ምሪት ተያይዘን ገደል፤
ወትሮስ የአሣ ግማት ከጭንቅላቱ አይደል?
እንዴት ተሸነፍን?
ለምን እጅ ሰጠን?
ምክንያቱማ ይኸው፤
ልብ ለሚል ልቡ ለሚሰማ ጆሮው::
ቅድመ ምእተ ዓመት..
ለሃገር ለሃይማኖት ሲሆን የሞት ሽረት፤
ለዚያ የቁርጥ ዕለት..
ምን እንደተሠራ ከታሪክ መመልከት!
የጥይት እሩምታ የሞት ጥላ መሃል ያስቀደሰ ቆሞ፤
በእምነት የተዋጋ ታቦት ተሸክሞ፤
የጠገበን ፋሽስት ድራሹን ያጠፋ በባዶ ሆድ ገጥሞ…
እስከ ሠርክ ጦሞ፤
ያ ነበልባል ትውልድ፤
ልጁ ሆነና አመድ፤
“ጊዮርጊስ ታቦት ከንቱ፤
ቤል ጣዖት ውእቱ፤
ይልቅ ጊዮርጊስ ቢራን ብሉ ጠጡ ተደሰቱ!!”
ብሎ የሚሣለቅ ሲነሣ ዛሬ ላይ፤
ጾም ጸሎት ወዲያልኝ ስግደት ለምኔ ባይ ፤
በሑዳዴ ረቡዕ ጮማ ቆራጭ ጠጅ ጣይ፤
ሲነሣ በዛ ባይ ቅዳሴ ረዘመ፤
ለባሕር ማዶ ኳስ ማኅሌት እየቆመ፤
የድል ምዕራፋችን ያኔ አከተመ::
በጓዳችን ሞልቶ የተረፈን ውሰት፤
ከባሕር ማዶ ጫፍ ያማተርን ዕለት፤
አበው በደማቸው የተጋደሉለት፤
የባህል የታሪክ የሃይማኖት ዓለት፤
በቸልታችን ጎርፍ በክሕደት ዓውሎ፤
እንደሚፈራርስ ከሥር ተመንግሎ፤
እንቅጩን በማወቅ ብንነቃ ቶሎ፤
መች መማረክ ነበር እጅ ወደላይ ብሎ?
በግድ ያልተያዘ በፈቃድ ኮብልሎ፡፡
እንዴት ተሸነፍን?
ለምን እጅ ሰጠን?
በሥጋ የአበው በመንፈስ የጠላት፤
የኾን’ባትን ግብር ማን ይሆን ልብ ያላት?
የጉዞ ሥንቃችን ድንግልን የት ተውናት?
ፈረሰኛው ጊዮርጊስ ታቦቱ እንደትናንት፤
ፊት እየቀደመ ድል ማድረግ ወዴት ናት?
ማን ያዘው ጋሻውን ቅዳሴ ሰዓታት፤
ጾም ጸሎት ስግደቱን ገቢረ ትሩፋት::
እንዴት ተሸነፍን?
ለምን እጅ ሰጠን?
23/06/2009 ዓ.ም
@Mgetem
@Mgetem
@Scgpx
✍ከሣቴብርሃን ገ/ኢየሱስ
እንዴት ተሸነፍን?
ለምን እጅ ሰጠን?
የፈቃድ ምርኮኞች አርጎ ማን ለወጠን?
በሥጋ አበው በመንፈስ ጠላት፤
የኾ’ንባትን ግብር ማን ይሆን ልብ ያላት?
እነሆ ምሥክር. . . . . . ከሕያዋን መዝገብ፤
የደም የአጥንት ጽሕፈት ደምቆ ሚታይ ሳይነትብ፤
ዓድዋ ብራና ተገልጦ ይነበብ!
በእምዬ ምኒልክ እምዬ ምትባል፤
በልቡ የምትሣል፤
የከንፈሩ ውብ ቃል፤
የኪዳን ማሠርያ ኾና የምትማል፤
በምልጃ ጸሎቷ በልመናዋ ኃይል፤
ድል ብታቀዳጀው ይኼ ምን ይገርማል?
ለ’ኛም ደበዘዘች የማንነት ፊደል፤
ድል ማንበብ ተስኖን… በዕውር ለዕውር ምሪት ተያይዘን ገደል፤
ወትሮስ የአሣ ግማት ከጭንቅላቱ አይደል?
እንዴት ተሸነፍን?
ለምን እጅ ሰጠን?
ምክንያቱማ ይኸው፤
ልብ ለሚል ልቡ ለሚሰማ ጆሮው::
ቅድመ ምእተ ዓመት..
ለሃገር ለሃይማኖት ሲሆን የሞት ሽረት፤
ለዚያ የቁርጥ ዕለት..
ምን እንደተሠራ ከታሪክ መመልከት!
የጥይት እሩምታ የሞት ጥላ መሃል ያስቀደሰ ቆሞ፤
በእምነት የተዋጋ ታቦት ተሸክሞ፤
የጠገበን ፋሽስት ድራሹን ያጠፋ በባዶ ሆድ ገጥሞ…
እስከ ሠርክ ጦሞ፤
ያ ነበልባል ትውልድ፤
ልጁ ሆነና አመድ፤
“ጊዮርጊስ ታቦት ከንቱ፤
ቤል ጣዖት ውእቱ፤
ይልቅ ጊዮርጊስ ቢራን ብሉ ጠጡ ተደሰቱ!!”
ብሎ የሚሣለቅ ሲነሣ ዛሬ ላይ፤
ጾም ጸሎት ወዲያልኝ ስግደት ለምኔ ባይ ፤
በሑዳዴ ረቡዕ ጮማ ቆራጭ ጠጅ ጣይ፤
ሲነሣ በዛ ባይ ቅዳሴ ረዘመ፤
ለባሕር ማዶ ኳስ ማኅሌት እየቆመ፤
የድል ምዕራፋችን ያኔ አከተመ::
በጓዳችን ሞልቶ የተረፈን ውሰት፤
ከባሕር ማዶ ጫፍ ያማተርን ዕለት፤
አበው በደማቸው የተጋደሉለት፤
የባህል የታሪክ የሃይማኖት ዓለት፤
በቸልታችን ጎርፍ በክሕደት ዓውሎ፤
እንደሚፈራርስ ከሥር ተመንግሎ፤
እንቅጩን በማወቅ ብንነቃ ቶሎ፤
መች መማረክ ነበር እጅ ወደላይ ብሎ?
በግድ ያልተያዘ በፈቃድ ኮብልሎ፡፡
እንዴት ተሸነፍን?
ለምን እጅ ሰጠን?
በሥጋ የአበው በመንፈስ የጠላት፤
የኾን’ባትን ግብር ማን ይሆን ልብ ያላት?
የጉዞ ሥንቃችን ድንግልን የት ተውናት?
ፈረሰኛው ጊዮርጊስ ታቦቱ እንደትናንት፤
ፊት እየቀደመ ድል ማድረግ ወዴት ናት?
ማን ያዘው ጋሻውን ቅዳሴ ሰዓታት፤
ጾም ጸሎት ስግደቱን ገቢረ ትሩፋት::
እንዴት ተሸነፍን?
ለምን እጅ ሰጠን?
23/06/2009 ዓ.ም
@Mgetem
@Mgetem
@Scgpx
👍6❤3
#ለአባ_የትናንቱ
ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ
ያለ ማወቅ ጽልመት ሀገሩን ሲወርሰው
ማን ነበር ትውልዱን በወንጌል ያረሰው?
አባ ተክለ ሃይማኖት አባ የትናንቱ
ትዝ አለኝ ተጋድሎው ውል አለኝ ሕይወቱ
በቆላ በደጋ የተንከራተትኸው
የሃይማኖትን ተክል ዞረህ የተከልኸው
የኢትዮጵያ ፀሐይ አባ ተክለ አብ
እስቲ መለስ ብዬ ሥራህን ላስብ
የክህደት ጨለማ በአንተ ሲርቅ
የሃይማኖት ብርሃን ሲያንጸባርቅ
በቀንና ሌሊት ከላይ ታች ዞረህ
ሕዝቡን አደረስከው አስተምረህ መክረህ
ስንት ነበር አባ ‹የጉዞ አበልህ›?
ያረፍህበት ስፍራ የተዘጋጀልህ
የት ነበር መኝታው ጎን ማሳረፊያህ?
ንገረኝ እባክህ ማን ነበር የሸኘህ?
እሳት አባቴ ሆይ እኔ አመድ ልጅህ
በዘመኔ ቋንቋ እስኪ ልጠይቅህ?
@Mgetem
@Mgetem
@Menfesawi_getem_bot
ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ
ያለ ማወቅ ጽልመት ሀገሩን ሲወርሰው
ማን ነበር ትውልዱን በወንጌል ያረሰው?
አባ ተክለ ሃይማኖት አባ የትናንቱ
ትዝ አለኝ ተጋድሎው ውል አለኝ ሕይወቱ
በቆላ በደጋ የተንከራተትኸው
የሃይማኖትን ተክል ዞረህ የተከልኸው
የኢትዮጵያ ፀሐይ አባ ተክለ አብ
እስቲ መለስ ብዬ ሥራህን ላስብ
የክህደት ጨለማ በአንተ ሲርቅ
የሃይማኖት ብርሃን ሲያንጸባርቅ
በቀንና ሌሊት ከላይ ታች ዞረህ
ሕዝቡን አደረስከው አስተምረህ መክረህ
ስንት ነበር አባ ‹የጉዞ አበልህ›?
ያረፍህበት ስፍራ የተዘጋጀልህ
የት ነበር መኝታው ጎን ማሳረፊያህ?
ንገረኝ እባክህ ማን ነበር የሸኘህ?
እሳት አባቴ ሆይ እኔ አመድ ልጅህ
በዘመኔ ቋንቋ እስኪ ልጠይቅህ?
@Mgetem
@Mgetem
@Menfesawi_getem_bot
❤2👍1😢1
#እሱ_ነው_እሱ
@Mgetem
ጥንት ያለ የነበረ
ዓለሙን በጥበቡ የመሠረተ
ምድርን በኃይሉ የፈጠረ
ዘመናትን የለካ የቀመረ
ነቢያትን ያናገረ
ኃያል ሱባኤ ያስቀጠረ
ከይስሐቅ ጋር የተሰዋ
እስራኤልን ያከበረ
ከዮናስ ጋር በዓሣ ሆድ
ከዮሴፍ ጋር የታሰረ
እሱ ነው እሱ ለሙሴ
ሕጉን ትእዛዙን ያስተማረ
በተረዳ ሦስትነቱ
በስም በግብሩ በአካላቱ
የሚመለክ በአንድነቱ
በሕልውናው በመለኮቱ
በአገዛዙ በጌትነቱ
እሱ ነው እሱ የጥንት የጠዋቱ
እንዘ አሐዱ ሠለስቱ
በእጹብ ብቻ ይወሰናል
ቀዳማዊ ልደቱ
አይመረመርም ረቂቅ ነው
ዳግማዊ ሰውነቱ
ከወላዲተ-ቃል እናቱ
ግሩም ድንቅ ነው ጥበቡ
ወሰን የለውም ቸርነቱ
ወልደ አብ ወልደ ማርያም
የሰማዩ የመሬቱ
እሱ ነው እሱ አልፋና ዖሜጋ
የሚታዘዙለት መላዕክቱ
የሚታሰብ በቀዳሚ በሳምንቱ
በዘወረደ በቅዳሴው በሰዓታቱ
እሱ ነው እሱ ፍጹም አምላክ ፍጹም ሰው የሆነ
ይጠብቀን በምህረቱ
ስለ እናቱም ከመዓቱ።።።።
___________________________
@Mgetem
@Mgetem
@helansane
@Mgetem
ጥንት ያለ የነበረ
ዓለሙን በጥበቡ የመሠረተ
ምድርን በኃይሉ የፈጠረ
ዘመናትን የለካ የቀመረ
ነቢያትን ያናገረ
ኃያል ሱባኤ ያስቀጠረ
ከይስሐቅ ጋር የተሰዋ
እስራኤልን ያከበረ
ከዮናስ ጋር በዓሣ ሆድ
ከዮሴፍ ጋር የታሰረ
እሱ ነው እሱ ለሙሴ
ሕጉን ትእዛዙን ያስተማረ
በተረዳ ሦስትነቱ
በስም በግብሩ በአካላቱ
የሚመለክ በአንድነቱ
በሕልውናው በመለኮቱ
በአገዛዙ በጌትነቱ
እሱ ነው እሱ የጥንት የጠዋቱ
እንዘ አሐዱ ሠለስቱ
በእጹብ ብቻ ይወሰናል
ቀዳማዊ ልደቱ
አይመረመርም ረቂቅ ነው
ዳግማዊ ሰውነቱ
ከወላዲተ-ቃል እናቱ
ግሩም ድንቅ ነው ጥበቡ
ወሰን የለውም ቸርነቱ
ወልደ አብ ወልደ ማርያም
የሰማዩ የመሬቱ
እሱ ነው እሱ አልፋና ዖሜጋ
የሚታዘዙለት መላዕክቱ
የሚታሰብ በቀዳሚ በሳምንቱ
በዘወረደ በቅዳሴው በሰዓታቱ
እሱ ነው እሱ ፍጹም አምላክ ፍጹም ሰው የሆነ
ይጠብቀን በምህረቱ
ስለ እናቱም ከመዓቱ።።።።
___________________________
@Mgetem
@Mgetem
@helansane
👍3
አዳም ሆይ ንገረኝ
አንተስ አንድ ጊዜ
ትዕዛዝን ተላልፈክ
መለከቱን ሰምተክ
በቃሉ ተመለስክ
እኔስ ስንት ጊዜ
ስንት ጊዜ ወደኩ
ልጅነቴን በእጨት
ሰቅዬ አንጠለጠልኩ
@Mgetem
አንተስ አንድ ጊዜ
ትዕዛዝን ተላልፈክ
መለከቱን ሰምተክ
በቃሉ ተመለስክ
እኔስ ስንት ጊዜ
ስንት ጊዜ ወደኩ
ልጅነቴን በእጨት
ሰቅዬ አንጠለጠልኩ
@Mgetem
❤1
በዜሮ ይባዛል!
ፆም×0=0 ስግደት×0=0
ጸሎት ×0=0
ተግቼ ብጸልይ እጆቼን ዘርግቼ
ቤቴ ባዶ ቢቀር ያለኝን መጽውቼ
ቀኑን ሙሉ ብጾም እስኪቆረጥ አንጀቴ
ዘወትር ብሰግድ እስኪዝል ጉልበቴ
በቀድስ ባስቀድስ በመቅደሱ ግርማ
ብዘምር ባወድስ የሚጣፍጥ ዜማ
ወንጌልን ብሰብክ ምስጢር አመስጥሬ
ብናገር ባስተምር ትርጉሙን ዘርዝሬ
ጥልና ክርክር ካሉ በህይወቴ
ሐሜት ክርክር ካልጠፉ ከቤቴ
በዜሮ ይባዛል ፍቅር በማጣቴ።
ስብሐት ለእግዚአብሔር!
ፆም×ፍቅር= 30 ያማር ፍሬ
ጸሎት×ፍቅር= 60ያማር ፍሬ
ስግደት× ትህትና= 100ያማረ ፍሬ
@Mgetem
ፆም×0=0 ስግደት×0=0
ጸሎት ×0=0
ተግቼ ብጸልይ እጆቼን ዘርግቼ
ቤቴ ባዶ ቢቀር ያለኝን መጽውቼ
ቀኑን ሙሉ ብጾም እስኪቆረጥ አንጀቴ
ዘወትር ብሰግድ እስኪዝል ጉልበቴ
በቀድስ ባስቀድስ በመቅደሱ ግርማ
ብዘምር ባወድስ የሚጣፍጥ ዜማ
ወንጌልን ብሰብክ ምስጢር አመስጥሬ
ብናገር ባስተምር ትርጉሙን ዘርዝሬ
ጥልና ክርክር ካሉ በህይወቴ
ሐሜት ክርክር ካልጠፉ ከቤቴ
በዜሮ ይባዛል ፍቅር በማጣቴ።
ስብሐት ለእግዚአብሔር!
ፆም×ፍቅር= 30 ያማር ፍሬ
ጸሎት×ፍቅር= 60ያማር ፍሬ
ስግደት× ትህትና= 100ያማረ ፍሬ
@Mgetem
👍3❤1
፨ምነው እመብርሃን፨
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
አዬ ምነው እመብርሀን
ኢትዮጵያን ጨከንሽባት
ምነው ቀኝሽን እረሳሻት
እስከመቼ ድረስ እንዲህ መቀነትሽን ታጠብቂባት
ልቦናሽን ታዞሪባት
ፈተናዋን ሰቀቀኗን ጣሯን ይበቃል ሳትያት
አላንቺ እኮ ማንም የላት
አውሮፓ እደሁ ትናጋዋን በፋሺስታዊ ነቀርሳ
ታርሳ ተምሳ በስብሳ
ምድራዊ እባጭ ጫንቃዋን እንደ ኮረብታ ተጭኗት
ቀና ብላ እውነት እንዳታይ አንገቷን ቁልቁል ጠምዝዟት
ነፍሷን ድጦ ያስበረከካት ስልጡን ብኩን መፃጉዕ ናት
እና ፈርቼ እንዳልባክን ሲርቀኝ የሀይልሽ ውጋጋን
አንቺ ካጠገቤ አትራቂ በርታ በይኝ እመብርሀን
ቃልኪዳኔን እንዳልረሳት እንዳልዘነጋት ኢትዮጵያን
አዎን ብቻዬን ነኝ ፈራሁ
እሸሸግበት ጥግ አጣሁ
እምፀናበት ልብ አጣሁ
እማማ ኢትዮጵያን መንፈሴ ተፈትቶ እንዳይክዳት ሰጋሁ
አዋጅ የምስራች ብዬ የትብት ምግቤን ገድፌ
ከእናቴ ማህፀን አልፌ በኢትዮጵያ ማህፀን አርፌ
ካፈሯ አጥንቴን ቀፍፌ ደሜን ከደሟ አጠንፍፌ
ከወዟወዟን ቀፍፌ
በህፃን እግሬ ድኬባት በህልም አክናፌ ከንፌ
እረኝነቴን በሰብሏ በምድሯ ላብ አሳልፌ
ከጫጩት እና ከጥጃ ከግልገል ጋር ተቃቅፌ
በጋው የረኛ አደባባይ ክረምት እንደ ወዙ ፍሳሽ
በገጠር የደመና ዳስ በገደል የሸለቆ አዳራሽ
ከቆቅና ከሚዳቋ ከጅግራ ጠረን ስተሻሽ
በወንዝ አፋፍ ሐረግ ዝላይ መወርወር መንጠልጠል ጢሎሽ
ከፍልፈል ጋር እሩጫ ስገጥም ከቀበሮ ድብብቆሽ
ከራዳ ጫፍ ሳር ለግት ላሜ ትንሽ ግጦሽ
ለጥጃዬ የሌት ግርዶሽ
ለጥማድ በሬዎቼ እራት ለማታቸው ጥቂት ድርቆሽ
ለግልገሌ ከአውሬ ከለል እማሳው ስር ጎጆ መትከል
ለፀሐይ የሾላ ጠለል ለዝናብ የገሳ ጠለል
ውሎ የንብ ቀፎ ማሰስ ያበባ እምቡጥ ሲፈነዳ
የግጦሽ ሳር ሲለመልም ሲሰማሩ ሰደድ ሜዳ
አዝመራው ጣል ከምበል ሲል ከብቱ ለሆራ ሲነዳ
ፈረስ ግልቢያ ስሸመጥጥ ከወፎች ዜማ ስቀዳ
ልቤ በንፋስ ተንሳፎ በዋሽንት ዋይታ ሲከዳ
ያቺን ነው ኢትዮጵያ የምላት
እመብርሀን ምነው እረሳሻት
ያቺን የልጅነት ምስራች የህፃንነት ብስራት
የሳቅ የፍንደቃ ዘመን የምኞት የተስፋ ብፅዓት
ያቺን የልጅነት እናት
አዛኝቱ እንዴት ብለሽ ጥርሶችሽን ትነክሺባት
ስሜን በስምሽ ሰይሜ ባገልግሎትሽ ስዋትት
ከዜማ ቤት ቅኔ ቤት ከድጓ ቤት መጻህፍት
ካንቺ ተቆራኝታ እድሌ ካንቺ ተቆራኝታ ነፍሴ
ከቀፈፋ ደጀ ሰላም ከቤተልሄም ቅዳሴ
አኮ... ቀዶ.. ቀፍፎ .... ዳባ ለብሶ
ቅኔ ዘርፎ .....ግስ ገሶ
መቅደስ አጥኖ ማሕሌት ቆሞ
በልብሰ ተክሕኖ አጊጦ በብር አክሊል ተሸልሞ
እመብርሀን ያንቺ ፅላት ነፍሴ ላይ በሳት ታትሞ
የመናኒው የአባ ተድላ ርድ ሆኜ አብሮኝ ታድሞ
ሕይወቴ እምነትሽን ፀንሶ
ስጋ ፈቃዴ ተድሶ
ለሕንፃሽ መዲና ቆሞ ለክብርሽ ድባብ ምሰሶ
ስሜን በስምሽ ሰይሜ ሆነሽኝ የእምነቴ ፋኖስ
ለዋዜማሽ ግሸን ማርያም ለክብርሽ ደብረ ሊባኖስ
ስሮጥ በወንበሩ አኖርሽኝ በአንበሳው በቅዱስ ማርቆስ
ታዲያን ዛሬ ኢትየጵያ ስትወድቅ ከምትሰጪኝ ለፍርሃት ጦስ
ምነው በእረኝነት እድሜ አይኔን በጓጎጣት የሎስ
የጋኔል ጥምብ አንሳ ከንፎ ወርዶ በጨለማ በርኖስ
እባክሽ እመብርሀን ይብቃሽ እባክሽ ስለ ፍቅሩ ወልዳ
ፅናት ስጪኝ እንድካፈል የእናቴን የኢትዮጵያን ፍዳ
ከነከሳት መርዝ እንድቀምስ ከነደደችበት እቶን
የእሷን ሞት እኔ እንድሞታት ገላዋ ገላዬ እንዲሆን
አዎን ብቻዬን ነኝ ፈራሁ
እምፀናበት ልብ አጣሁ
እሸሸግበት ጥግ አጣሁ
ህፃን ሆኜ የርግብ ጫጩት
አንዳንዴ ራብ ሲያዳክማት
ችጋር ከጎጆዋ ገፍቶ እዛፉ ግርጌ ሲጥላት
እናቷ በርራ ደርሳላት
በአክናፏ ሙቀት ታቅፋት
እፍ እያለች ግንባሯ ላይ ሕይወት ስተነፍስባት
ወዲያው ነፍስ ትዘራለች
ችር.... ብር.... ትር.... እያለች
እባክሽ
* ከ (ሰቆቃው ጴጥሮስ- ሎሬት ፀጋዬ ገ/መድህን )
@Mgetem
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
አዬ ምነው እመብርሀን
ኢትዮጵያን ጨከንሽባት
ምነው ቀኝሽን እረሳሻት
እስከመቼ ድረስ እንዲህ መቀነትሽን ታጠብቂባት
ልቦናሽን ታዞሪባት
ፈተናዋን ሰቀቀኗን ጣሯን ይበቃል ሳትያት
አላንቺ እኮ ማንም የላት
አውሮፓ እደሁ ትናጋዋን በፋሺስታዊ ነቀርሳ
ታርሳ ተምሳ በስብሳ
ምድራዊ እባጭ ጫንቃዋን እንደ ኮረብታ ተጭኗት
ቀና ብላ እውነት እንዳታይ አንገቷን ቁልቁል ጠምዝዟት
ነፍሷን ድጦ ያስበረከካት ስልጡን ብኩን መፃጉዕ ናት
እና ፈርቼ እንዳልባክን ሲርቀኝ የሀይልሽ ውጋጋን
አንቺ ካጠገቤ አትራቂ በርታ በይኝ እመብርሀን
ቃልኪዳኔን እንዳልረሳት እንዳልዘነጋት ኢትዮጵያን
አዎን ብቻዬን ነኝ ፈራሁ
እሸሸግበት ጥግ አጣሁ
እምፀናበት ልብ አጣሁ
እማማ ኢትዮጵያን መንፈሴ ተፈትቶ እንዳይክዳት ሰጋሁ
አዋጅ የምስራች ብዬ የትብት ምግቤን ገድፌ
ከእናቴ ማህፀን አልፌ በኢትዮጵያ ማህፀን አርፌ
ካፈሯ አጥንቴን ቀፍፌ ደሜን ከደሟ አጠንፍፌ
ከወዟወዟን ቀፍፌ
በህፃን እግሬ ድኬባት በህልም አክናፌ ከንፌ
እረኝነቴን በሰብሏ በምድሯ ላብ አሳልፌ
ከጫጩት እና ከጥጃ ከግልገል ጋር ተቃቅፌ
በጋው የረኛ አደባባይ ክረምት እንደ ወዙ ፍሳሽ
በገጠር የደመና ዳስ በገደል የሸለቆ አዳራሽ
ከቆቅና ከሚዳቋ ከጅግራ ጠረን ስተሻሽ
በወንዝ አፋፍ ሐረግ ዝላይ መወርወር መንጠልጠል ጢሎሽ
ከፍልፈል ጋር እሩጫ ስገጥም ከቀበሮ ድብብቆሽ
ከራዳ ጫፍ ሳር ለግት ላሜ ትንሽ ግጦሽ
ለጥጃዬ የሌት ግርዶሽ
ለጥማድ በሬዎቼ እራት ለማታቸው ጥቂት ድርቆሽ
ለግልገሌ ከአውሬ ከለል እማሳው ስር ጎጆ መትከል
ለፀሐይ የሾላ ጠለል ለዝናብ የገሳ ጠለል
ውሎ የንብ ቀፎ ማሰስ ያበባ እምቡጥ ሲፈነዳ
የግጦሽ ሳር ሲለመልም ሲሰማሩ ሰደድ ሜዳ
አዝመራው ጣል ከምበል ሲል ከብቱ ለሆራ ሲነዳ
ፈረስ ግልቢያ ስሸመጥጥ ከወፎች ዜማ ስቀዳ
ልቤ በንፋስ ተንሳፎ በዋሽንት ዋይታ ሲከዳ
ያቺን ነው ኢትዮጵያ የምላት
እመብርሀን ምነው እረሳሻት
ያቺን የልጅነት ምስራች የህፃንነት ብስራት
የሳቅ የፍንደቃ ዘመን የምኞት የተስፋ ብፅዓት
ያቺን የልጅነት እናት
አዛኝቱ እንዴት ብለሽ ጥርሶችሽን ትነክሺባት
ስሜን በስምሽ ሰይሜ ባገልግሎትሽ ስዋትት
ከዜማ ቤት ቅኔ ቤት ከድጓ ቤት መጻህፍት
ካንቺ ተቆራኝታ እድሌ ካንቺ ተቆራኝታ ነፍሴ
ከቀፈፋ ደጀ ሰላም ከቤተልሄም ቅዳሴ
አኮ... ቀዶ.. ቀፍፎ .... ዳባ ለብሶ
ቅኔ ዘርፎ .....ግስ ገሶ
መቅደስ አጥኖ ማሕሌት ቆሞ
በልብሰ ተክሕኖ አጊጦ በብር አክሊል ተሸልሞ
እመብርሀን ያንቺ ፅላት ነፍሴ ላይ በሳት ታትሞ
የመናኒው የአባ ተድላ ርድ ሆኜ አብሮኝ ታድሞ
ሕይወቴ እምነትሽን ፀንሶ
ስጋ ፈቃዴ ተድሶ
ለሕንፃሽ መዲና ቆሞ ለክብርሽ ድባብ ምሰሶ
ስሜን በስምሽ ሰይሜ ሆነሽኝ የእምነቴ ፋኖስ
ለዋዜማሽ ግሸን ማርያም ለክብርሽ ደብረ ሊባኖስ
ስሮጥ በወንበሩ አኖርሽኝ በአንበሳው በቅዱስ ማርቆስ
ታዲያን ዛሬ ኢትየጵያ ስትወድቅ ከምትሰጪኝ ለፍርሃት ጦስ
ምነው በእረኝነት እድሜ አይኔን በጓጎጣት የሎስ
የጋኔል ጥምብ አንሳ ከንፎ ወርዶ በጨለማ በርኖስ
እባክሽ እመብርሀን ይብቃሽ እባክሽ ስለ ፍቅሩ ወልዳ
ፅናት ስጪኝ እንድካፈል የእናቴን የኢትዮጵያን ፍዳ
ከነከሳት መርዝ እንድቀምስ ከነደደችበት እቶን
የእሷን ሞት እኔ እንድሞታት ገላዋ ገላዬ እንዲሆን
አዎን ብቻዬን ነኝ ፈራሁ
እምፀናበት ልብ አጣሁ
እሸሸግበት ጥግ አጣሁ
ህፃን ሆኜ የርግብ ጫጩት
አንዳንዴ ራብ ሲያዳክማት
ችጋር ከጎጆዋ ገፍቶ እዛፉ ግርጌ ሲጥላት
እናቷ በርራ ደርሳላት
በአክናፏ ሙቀት ታቅፋት
እፍ እያለች ግንባሯ ላይ ሕይወት ስተነፍስባት
ወዲያው ነፍስ ትዘራለች
ችር.... ብር.... ትር.... እያለች
እባክሽ
* ከ (ሰቆቃው ጴጥሮስ- ሎሬት ፀጋዬ ገ/መድህን )
@Mgetem
❤2👍1🥰1
፨ ተዘጋችተን እኑር፨
ርቀን ከቆምን ከተዋሕዶ አምባ
ምግባር ጎዶሎ እንዳንሆን ገለባ
ለማይበጀን ዓለም ጭራሽ ለማይረባ
በማይሆንን ሁሉ ስንል ወጣ ገባ
ያቺ ቀን ሳትመጣ ሳናውቅ እንደሌባ
ተዘጋጅተን እንኑር ንስሐም እንግባ።
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
*ከገብረየስ ገቢቶ
@Mgetem
ርቀን ከቆምን ከተዋሕዶ አምባ
ምግባር ጎዶሎ እንዳንሆን ገለባ
ለማይበጀን ዓለም ጭራሽ ለማይረባ
በማይሆንን ሁሉ ስንል ወጣ ገባ
ያቺ ቀን ሳትመጣ ሳናውቅ እንደሌባ
ተዘጋጅተን እንኑር ንስሐም እንግባ።
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
*ከገብረየስ ገቢቶ
@Mgetem
፨ማን ነው አትበሉኝ፨
ማን ነው አትበሉኝ የደማ ላንተ
ማን ነው አትበሉኝ አደኖህ የሞተ
በአብ በወልድ ስም በመንፈስ ቅዱስ
በምድር የመጣ የሰማይ ንጉስ
ከከብቶቹ ጋጥ ውስጥ የተወለደለኝ ከድንግል እናቴ
እኔ ሞቼበት ነው ሊያድን ከሃጥያቴ
ማን ነው አትበሉኝ ደም የደማ ላንተ
ማን ነው አትበሉኝ አድኖህ የሞተ
በወርቅ አክሊል ምትክ እሾህ የለበሰ
እንባዬን ሊያብሰው ደሙን ያፈሰሰ
እኔኑ ሊያድነኝ ሲገርፍ የዋለ እኔ ግን የካድኩት
ለማተብ መኖርን ያስተማረኝ እምነት
ብርክክ የምልለት የንጉሶች ንጉስ
እልል ይባልለት ለኔ ጌታ እየሱስ
ማን ነው አትበሉኝ ደም የደማ ላንተ
ማን ነው አትበሉኝ አድኖህ የሞተ
እንደ ጴጥሮስ ሆኜ ብክደውም ቅሉ
ዶሮ ሳይጮህ ሶስቴ ሳይል አኩሉሉ
እሱ ግን እሱ ነው የይቅርታ ንጉስ
ምህረትን ለመስጠት ማይጠይቅ
እየሱስ ነው ጌታ ፊቱ የሚያበራ
ግርማው የሚያስፈራ
እናም..
ማን ነው አትበሉኝ ደም የደማ ላንተ
ማን ነው አትበሉኝ ሊያድንህ የሞተ።
@Mgetem @Mgetem
ማን ነው አትበሉኝ የደማ ላንተ
ማን ነው አትበሉኝ አደኖህ የሞተ
በአብ በወልድ ስም በመንፈስ ቅዱስ
በምድር የመጣ የሰማይ ንጉስ
ከከብቶቹ ጋጥ ውስጥ የተወለደለኝ ከድንግል እናቴ
እኔ ሞቼበት ነው ሊያድን ከሃጥያቴ
ማን ነው አትበሉኝ ደም የደማ ላንተ
ማን ነው አትበሉኝ አድኖህ የሞተ
በወርቅ አክሊል ምትክ እሾህ የለበሰ
እንባዬን ሊያብሰው ደሙን ያፈሰሰ
እኔኑ ሊያድነኝ ሲገርፍ የዋለ እኔ ግን የካድኩት
ለማተብ መኖርን ያስተማረኝ እምነት
ብርክክ የምልለት የንጉሶች ንጉስ
እልል ይባልለት ለኔ ጌታ እየሱስ
ማን ነው አትበሉኝ ደም የደማ ላንተ
ማን ነው አትበሉኝ አድኖህ የሞተ
እንደ ጴጥሮስ ሆኜ ብክደውም ቅሉ
ዶሮ ሳይጮህ ሶስቴ ሳይል አኩሉሉ
እሱ ግን እሱ ነው የይቅርታ ንጉስ
ምህረትን ለመስጠት ማይጠይቅ
እየሱስ ነው ጌታ ፊቱ የሚያበራ
ግርማው የሚያስፈራ
እናም..
ማን ነው አትበሉኝ ደም የደማ ላንተ
ማን ነው አትበሉኝ ሊያድንህ የሞተ።
@Mgetem @Mgetem
❤4👍1
#መስቀሉ_በፊቴ
@Mgetem
የቀራኒዮ አርማ የፍቅር ሰሌዳ
የሰላም ብራና ቀለሙን የቀዳ
የድህነት ማህደሯ ጠቋሚ መሪዋ
እንቅፋት ነቃፊ አዳኝ ጠባቂዋ
የሰማዩ ንጉስ ስጋው ቆርሶባት
ደሙን አፍስሶ ላቡን ደቅኖባት
የትውልድን አረም ሊነቅል ከስሩ
ባሪያውን መስሎ ወረደ ከክብሩ።
ኤሎሄ ብሎ ጮኸ አምላክ ሆኖ ሳለ
የጠላትን መንግስት ንዶ እየጣለ
ደብዳቤውን ደምስሶ በችንካሩ ፋቀው
የዕዳው ፅሕፈት በደሙ ጠረገው።
በመስቀል የዋለ ጎልጎታ ያደረ
እባቡን ቀጥቅጦ አዳምን የማረ
ሄዋንን ከጭንቀቷ ጎትቶ ያወጣት
ልጆቿን ከሲኦል አትርፎ ከእሳት
በመስቀሉ ገፅ በችንካሩ ጫፍ
በእሾህ አክሊል ብሳት በከሳሾቹ አፍ
መከራው ሲፀና ስቃዩ ሲበረታ
ፊቱን በጥፊ ሶስት ጊዜ ሲመታ
የአምላካችን ፍቅር ከልብ የፈለቀ
ቢሆን ነው እንጂ ይቅርታው የላቀ።
በቃ!
ታዲያ ከመስቀሉ ወዲያ መገለጫ ለእኔ
ከወዴት ይገኛል ማረፊያ ለአይኔ?
ኧረ ከየት ይመጣል ተግዳሮቱን ሚያክል
የዕዳዬን ጣጣ በነፍሱ ሚከፍል።
ትምክህቱ ይራቅ ከጌታዬ መስቀል በቀር
አይኔ ሌላ አያይም ከቀራኒዮ መንደር
የመስቀሉን ፍቅር የሚያደንቀው አለ
ልቤ ላይ ከትሞ ነፍሴ እየነዋለለ።
የክርስቶስ መስቀል በፊቴ ተስሎ
እኔ እንድጠነክር እርሱ ስለኔ ዝሎ
የምሸከመውን እርሱ ተሸክሞ
ለኔ እንዲበራ እርሱ ላይ ጨልሞ
መስቀሉን ደረሰው ፍቅሩን እየፃፈ
የአመፃን ማዕበል በምሕረት ቀዘፈ
ቸርነቱ በዝቶ ቅጣቱ አለፈ።
➴ከእህተ ማርያም
ዛሬ መጋቢት 10 የጌታችንና የመዳኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ቅዱስ መስቀል የተገኘበት ቀን ነው። ቀኑ በጾም ወረ ስለሆነ ወደ መስክርም17 እንዲከበር ተደርጓል ይህም ቁፋሮ የተጀመረበት ቀን ማለት ነው።
____________________________
@Mgetem
@Mgetem
@Menfesawi_getem_bot
@Mgetem
የቀራኒዮ አርማ የፍቅር ሰሌዳ
የሰላም ብራና ቀለሙን የቀዳ
የድህነት ማህደሯ ጠቋሚ መሪዋ
እንቅፋት ነቃፊ አዳኝ ጠባቂዋ
የሰማዩ ንጉስ ስጋው ቆርሶባት
ደሙን አፍስሶ ላቡን ደቅኖባት
የትውልድን አረም ሊነቅል ከስሩ
ባሪያውን መስሎ ወረደ ከክብሩ።
ኤሎሄ ብሎ ጮኸ አምላክ ሆኖ ሳለ
የጠላትን መንግስት ንዶ እየጣለ
ደብዳቤውን ደምስሶ በችንካሩ ፋቀው
የዕዳው ፅሕፈት በደሙ ጠረገው።
በመስቀል የዋለ ጎልጎታ ያደረ
እባቡን ቀጥቅጦ አዳምን የማረ
ሄዋንን ከጭንቀቷ ጎትቶ ያወጣት
ልጆቿን ከሲኦል አትርፎ ከእሳት
በመስቀሉ ገፅ በችንካሩ ጫፍ
በእሾህ አክሊል ብሳት በከሳሾቹ አፍ
መከራው ሲፀና ስቃዩ ሲበረታ
ፊቱን በጥፊ ሶስት ጊዜ ሲመታ
የአምላካችን ፍቅር ከልብ የፈለቀ
ቢሆን ነው እንጂ ይቅርታው የላቀ።
በቃ!
ታዲያ ከመስቀሉ ወዲያ መገለጫ ለእኔ
ከወዴት ይገኛል ማረፊያ ለአይኔ?
ኧረ ከየት ይመጣል ተግዳሮቱን ሚያክል
የዕዳዬን ጣጣ በነፍሱ ሚከፍል።
ትምክህቱ ይራቅ ከጌታዬ መስቀል በቀር
አይኔ ሌላ አያይም ከቀራኒዮ መንደር
የመስቀሉን ፍቅር የሚያደንቀው አለ
ልቤ ላይ ከትሞ ነፍሴ እየነዋለለ።
የክርስቶስ መስቀል በፊቴ ተስሎ
እኔ እንድጠነክር እርሱ ስለኔ ዝሎ
የምሸከመውን እርሱ ተሸክሞ
ለኔ እንዲበራ እርሱ ላይ ጨልሞ
መስቀሉን ደረሰው ፍቅሩን እየፃፈ
የአመፃን ማዕበል በምሕረት ቀዘፈ
ቸርነቱ በዝቶ ቅጣቱ አለፈ።
➴ከእህተ ማርያም
ዛሬ መጋቢት 10 የጌታችንና የመዳኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ቅዱስ መስቀል የተገኘበት ቀን ነው። ቀኑ በጾም ወረ ስለሆነ ወደ መስክርም17 እንዲከበር ተደርጓል ይህም ቁፋሮ የተጀመረበት ቀን ማለት ነው።
____________________________
@Mgetem
@Mgetem
@Menfesawi_getem_bot
👍5❤1
#ሳልፆም_ሊፈሰክ_ነው
@Mgetem
አይ የኔ ነገር !
እርግጥ አልበላሁም #ስጋም ሆነ #ቅቤ
አልፆም አለኝ እንጂ #አመፀኛ_ልቤ
ካምናና ካቻምና #የዘንድሮ_ብሶ
መላ ማንነቴ #በሀጢያት_ተለውሶ
#ስዋሽ_ስቀጥፍ
ህግን ስተላለፍ
ስሰድብ ሳደማ
የሰው ስጋ ሳማ
ባይኔ ሳመነዝር
የሰው ሰው ሳማትር
#ገላዬን_ሳራቁት
አዳምን/ሔዋንን ሳሳስት
ስረሳ ስቃይህን
መስቀል ህማምህን
ያን ሁሉ ግርፋት
ነብሴ ሳያስጨንቃት
#አይ_እኔ
በሀሰት ስመሰክር
በሀጢያት ስዳክር
ለማይሞላ ኑሮ
ሳልሻል ዘንድሮ
ፆሙ ተጋመሰ
ጊዜው ተጋመሰ
#ጌታ_ሆይ
አቤቱ አስበኝ
ለንሰሀ አብቃኝ
#እስቲ_የቀረውን ለበረከት በለው
#አመፀኛ_ልቤ ፆምህን ይፁመው
"ከደጀ ሰላሙ ከካህኑ እግር ስር
ንስሀዬን ልውሰድ ስለመስቀል ፍቅር" 🙏
@Mgetem
@Mgetem
አይ የኔ ነገር !
እርግጥ አልበላሁም #ስጋም ሆነ #ቅቤ
አልፆም አለኝ እንጂ #አመፀኛ_ልቤ
ካምናና ካቻምና #የዘንድሮ_ብሶ
መላ ማንነቴ #በሀጢያት_ተለውሶ
#ስዋሽ_ስቀጥፍ
ህግን ስተላለፍ
ስሰድብ ሳደማ
የሰው ስጋ ሳማ
ባይኔ ሳመነዝር
የሰው ሰው ሳማትር
#ገላዬን_ሳራቁት
አዳምን/ሔዋንን ሳሳስት
ስረሳ ስቃይህን
መስቀል ህማምህን
ያን ሁሉ ግርፋት
ነብሴ ሳያስጨንቃት
#አይ_እኔ
በሀሰት ስመሰክር
በሀጢያት ስዳክር
ለማይሞላ ኑሮ
ሳልሻል ዘንድሮ
ፆሙ ተጋመሰ
ጊዜው ተጋመሰ
#ጌታ_ሆይ
አቤቱ አስበኝ
ለንሰሀ አብቃኝ
#እስቲ_የቀረውን ለበረከት በለው
#አመፀኛ_ልቤ ፆምህን ይፁመው
"ከደጀ ሰላሙ ከካህኑ እግር ስር
ንስሀዬን ልውሰድ ስለመስቀል ፍቅር" 🙏
@Mgetem
❤3👍2
#ሕፃን_መፃጕዕ
(ውርስ ትርጉም)
ከሣቴብርሃን ገብረኢየሱስ
@Mgetem
“ብላቴና” የሚል፤
ከግብሩ የተነሣ የተሰጠው ቅፅል፤
በትርጓሜ ወንጌል የሚነበብ ሰፍሮ፤
መፃጕዕ መፃጕዕ ሕፃነ አእምሮ፤
ጨቅላ ነው ፤ ትክክል!
ምንም ነፍስ የማያውቅ፤
እሳትና ውሃን መለየት የማይችል።
ቢለይማ ኖሮ፤
ከእሳተ መለኮት ፤ እጁን ይልክ ነበር ፤ ለጥፊ ሰንዝሮ ?
......................................................
መነሻ ቅኔ ፦ ዕዝል ጉባዔ ቃና
ዘመሪጌታ ጥበበ ደስታ
.......................................................
መፃጕዕ ለ 38 ዓመት ሲማቅቅበት ከነበረ ደዌው የፈወሰው ክርስቶስን በቤተመቅደስ በጥፊ ስለ መምታቱ መሪጌታ ጥበበ ደስታ የተቀኙትን ቅኔ መነሻ በማድረግ የተገጠመ
ከሣቴብርሃን ገብረኢየሱስ
.......................................................
@Mgetem
@Mgetem
@Scgpx9
(ውርስ ትርጉም)
ከሣቴብርሃን ገብረኢየሱስ
@Mgetem
“ብላቴና” የሚል፤
ከግብሩ የተነሣ የተሰጠው ቅፅል፤
በትርጓሜ ወንጌል የሚነበብ ሰፍሮ፤
መፃጕዕ መፃጕዕ ሕፃነ አእምሮ፤
ጨቅላ ነው ፤ ትክክል!
ምንም ነፍስ የማያውቅ፤
እሳትና ውሃን መለየት የማይችል።
ቢለይማ ኖሮ፤
ከእሳተ መለኮት ፤ እጁን ይልክ ነበር ፤ ለጥፊ ሰንዝሮ ?
......................................................
መነሻ ቅኔ ፦ ዕዝል ጉባዔ ቃና
ዘመሪጌታ ጥበበ ደስታ
ሕፃን ኢያእመሬ ነፍስ ዓዲ፤
አኮኑ ፈነወ እዴሁ መንገለ እሳት ነዳዲ
.......................................................
መፃጕዕ ለ 38 ዓመት ሲማቅቅበት ከነበረ ደዌው የፈወሰው ክርስቶስን በቤተመቅደስ በጥፊ ስለ መምታቱ መሪጌታ ጥበበ ደስታ የተቀኙትን ቅኔ መነሻ በማድረግ የተገጠመ
ከሣቴብርሃን ገብረኢየሱስ
.......................................................
@Mgetem
@Mgetem
@Scgpx9
👍2🥰1
#በኃይማኖት_ስኖር
መጋቤ ሐዲስ ሳሙኤል አያልነህ
@Mgetem
በኃይማኖት ስኖር ከኃጢአት ጠብቀኝ
ኃጢአት ብሰራ ግን ተንሳሒ አድርገኝ
ከኃጢአት ጋር መኖር እንዳልለማመድ
ንፁህ ልብ ስጠኝ ልጓዝ በአንተ መንገድ
ጥቂት ናት እያልኩኝ መስላኝ የማትጎዳ
ኃጢአት ሳጠራቅም በህይወቴ ጓዳ
ንስሐ ገብቼ ሳልወጣ አርነት
እንዳልሞት ታደገኝ በኃጢአት ባርነት።
@Mgetem
@Mgetem
መጋቤ ሐዲስ ሳሙኤል አያልነህ
@Mgetem
በኃይማኖት ስኖር ከኃጢአት ጠብቀኝ
ኃጢአት ብሰራ ግን ተንሳሒ አድርገኝ
ከኃጢአት ጋር መኖር እንዳልለማመድ
ንፁህ ልብ ስጠኝ ልጓዝ በአንተ መንገድ
ጥቂት ናት እያልኩኝ መስላኝ የማትጎዳ
ኃጢአት ሳጠራቅም በህይወቴ ጓዳ
ንስሐ ገብቼ ሳልወጣ አርነት
እንዳልሞት ታደገኝ በኃጢአት ባርነት።
@Mgetem
@Mgetem
👍2
ዲ/ን ዳንኤል ክብረት
#ውሸት_እና_ተንኮል
@Mgetem
ውሸትና ተንኮል ጓደኞች ነበሩ፣
እውነትን ለማጥፋት፣እንዲህ ተማከሩ።
እውነት የተባለው፣ይሄ ጠላታችን፣
መጥፋት አለበት፤ጭራሽ ከዓለማችን።
እኛ እየተጠላን፣እሱ እየተወደደ፣
ብዙ ጊዜ አለፈ፣ዘመንም ነጎደ።
የኛ ጊዜ አለፈ፣ዘመንም ነጎደ።
የኛ ብቻ ይሁን፣ መላው ሀገር ምድሩ፣
ውሸትና ተንኮል፣እንዲህ ተማከሩ።
ከዕለታት በአንዱ ቀን፣ተንኮል እያደባ፤
ከውሸት ጋር ሆኖ ከእውነት ቤት ገባ።
እውነት ከጓደኞቹ ሰላምና ፍቅር፣
በድስታ በሀሴት ይጫወቱ ነበር።
ተንኮልም በድንገት፤ እውነትን ተማታ፣
ፍቅርም አዘነ፣ሠላምም ተቆጣ፣
ውሸት ብቅ አለና፣ከተደበቀበት፣
ከተንኮል ጋር ሆኖ፣ እውነትን ገደሉት።
ሰላምእና ፍቅር፣እጅግ እያዘኑ፣
እውነት ተቀበር ከመቃብር ገባ።
ዓለምን የመግዛት፣ብርቱ ዓላማችው
ውሸትና ተንኮል፣ ሞላ የልባቸው።
አንድ ቀን፣ አቶ ውሸት ተነስቶ በጧት፣
የሰፈሩን ሰዎች፣ደስታ ሲመለከት
ተጠራጠረና፣ ወደ ቀብሩ ሮጠ፣
ልክ እንደደረሰ፣ በጣም ደነገጠ።
እውነት ተፈልጎ፣መቃብሩ ሲታይ፣
ምንም ነገር የለም፣አንዳችም የሚታይ።
አወይ ልፋታችን፣ ተንኮል መጥተህ ብታይ፣
እውነት ከቶ አልሞተም፣ዓርጎ ነው ሰማይ።
ወስብሐት ለእግዚአብሔር!
እውነትና ዘይት ምንግዜም ከላይ ናቸው።
∞∞∞∞∞∞∞∞∞∞∞
@Mgetem
@Mgetem
@Menfesawi_getem_bot
#ውሸት_እና_ተንኮል
@Mgetem
ውሸትና ተንኮል ጓደኞች ነበሩ፣
እውነትን ለማጥፋት፣እንዲህ ተማከሩ።
እውነት የተባለው፣ይሄ ጠላታችን፣
መጥፋት አለበት፤ጭራሽ ከዓለማችን።
እኛ እየተጠላን፣እሱ እየተወደደ፣
ብዙ ጊዜ አለፈ፣ዘመንም ነጎደ።
የኛ ጊዜ አለፈ፣ዘመንም ነጎደ።
የኛ ብቻ ይሁን፣ መላው ሀገር ምድሩ፣
ውሸትና ተንኮል፣እንዲህ ተማከሩ።
ከዕለታት በአንዱ ቀን፣ተንኮል እያደባ፤
ከውሸት ጋር ሆኖ ከእውነት ቤት ገባ።
እውነት ከጓደኞቹ ሰላምና ፍቅር፣
በድስታ በሀሴት ይጫወቱ ነበር።
ተንኮልም በድንገት፤ እውነትን ተማታ፣
ፍቅርም አዘነ፣ሠላምም ተቆጣ፣
ውሸት ብቅ አለና፣ከተደበቀበት፣
ከተንኮል ጋር ሆኖ፣ እውነትን ገደሉት።
ሰላምእና ፍቅር፣እጅግ እያዘኑ፣
እውነት ተቀበር ከመቃብር ገባ።
ዓለምን የመግዛት፣ብርቱ ዓላማችው
ውሸትና ተንኮል፣ ሞላ የልባቸው።
አንድ ቀን፣ አቶ ውሸት ተነስቶ በጧት፣
የሰፈሩን ሰዎች፣ደስታ ሲመለከት
ተጠራጠረና፣ ወደ ቀብሩ ሮጠ፣
ልክ እንደደረሰ፣ በጣም ደነገጠ።
እውነት ተፈልጎ፣መቃብሩ ሲታይ፣
ምንም ነገር የለም፣አንዳችም የሚታይ።
አወይ ልፋታችን፣ ተንኮል መጥተህ ብታይ፣
እውነት ከቶ አልሞተም፣ዓርጎ ነው ሰማይ።
ወስብሐት ለእግዚአብሔር!
እውነትና ዘይት ምንግዜም ከላይ ናቸው።
∞∞∞∞∞∞∞∞∞∞∞
@Mgetem
@Mgetem
@Menfesawi_getem_bot
❤3👍2👎1
Forwarded from Daregot Media
መድኃኔዓለም ወይስ የግል አዳኝ
መዳን እንደ ቀለብ ፤ መዋጀት እንደ እህል፤
በቁና ተሰፍሮ የተሰጠ ይመስል፤
መሲሑን ለብቻ ፤ ኢየሱስን የግል፤
አ’ርገህ ምትቀበል፤
አድራሻህ ከየት ነው ስምህን ማን ልበል?
በእንተዝ ነገር ስምዐ ኮነ መልአክ፤
በጊዜ ልደቱ ወደ እረኞች ሲላክ።
መድኃኒት ክርስቶስ ግርግም መወለዱ ፤ በጨርቅ መጠቅለሉ፤
ለእረኞች በግል የተሰጠ ሳይሆን ለዓለሙ ሁሉ፤
እነሆ ሲታወቅ በምሥራች ቃሉ፤
አልሰማህም አሉ።
ራሱ ባለቤቱ፤
በወንጌል ትምህርቱ፤
“ለድኅነተ ዓለም በመልዕልተ መስቀል
ከምድር ከፍ ብዬ ዕርቃኔን ስሰቀል”
አንድ ሁለት ሰው ሳይሆን “ሁሉን እስባለሁ”
ሲል እየሰማነው፤
ጆሮ ነሳህ ምነው?
ደግሞስ ሳምራዊቷ፤
“ብፍርስንያ” ‘ሚሏት ውሃ ቀጂ ሴቷ፤
ውሃ አጠጭኝ ብሎ ፤ በፍቅር ጎብኝቷት ፤ እሷን ብቻ መርጦ፤
ሕይወት ሆኗት ሲሄድ ታሪኳን ለውጦ፤
አዳኝ ፣ መሲሕ የግል፤
መቼ ሰማን ስትል?
እንስራዋን ጥላ ገሰገሰች እንጂ ሰማርያ መንደር፤
የጠበቅነው አምላክ ተገለጠ ብላ ላ’ለም ልትናገር።
ከዚያማ፤
ድኅነት በሷ ሳይቀር፤
ለሃያ አምስት ምዕት ወገኖቹ መጣ፤
ከዓለት ክርስቶስ ማየ ሕይወት ፈልቆ ሁለት ቀን ተጠጣ።
መጣፍ ባለማወቅ ልቡናህ የሳተ፤
ዝንጕ ‘ምትሆን አንተ፤
“በእውነት ክርስቶስ የዓለም መድኃኒት እንደሆነ አውቀናል።”
ስትል ሰማርያ ፤ በአልሰሜነትህ በጣም ተደንቀናል።
ከእንግዲህስ ስማ የተዋሕዶን አዋጅ፤
“ቤዛ ኵሉ እንጂ ነው ዓለሙን የሚዋጅ፤
የብቻዬም አይደል፤
የብቻህም አይደል፤
ፋሲካን ልታከብር በደመ ክርስቶስ ፤ ነጽታ ምትታጠብ፤
የምድር ሐሴት እንጂ ፤ የምድር ሁሉ ገንዘብ።
እናም፤
“መ ድ ኃ ኔ ዓ ለ ም”
ያለሚለው ቀለም፤
ትድግናውን ገላጭ ምሉዕ ፊደል የለም።”
እያለች ስትጠራው ስማት በየዕለቱ፤
እያት ስታነግሠው በስመ መንግሥቱ፤
በጥንተ ስቅለቱ።
መድኃኔዓለም!
መድኃኔዓለም!
መድኃኔዓለም!
መዳን እንደ ቀለብ ፤ መዋጀት እንደ እህል፤
በቁና ተሰፍሮ የተሰጠ ይመስል፤
መሲሑን ለብቻ ፤ ኢየሱስን የግል፤
አ’ርገህ ምትቀበል፤
አድራሻህ ከየት ነው ስምህን ማን ልበል?
በእንተዝ ነገር ስምዐ ኮነ መልአክ፤
በጊዜ ልደቱ ወደ እረኞች ሲላክ።
መድኃኒት ክርስቶስ ግርግም መወለዱ ፤ በጨርቅ መጠቅለሉ፤
ለእረኞች በግል የተሰጠ ሳይሆን ለዓለሙ ሁሉ፤
እነሆ ሲታወቅ በምሥራች ቃሉ፤
አልሰማህም አሉ።
ራሱ ባለቤቱ፤
በወንጌል ትምህርቱ፤
“ለድኅነተ ዓለም በመልዕልተ መስቀል
ከምድር ከፍ ብዬ ዕርቃኔን ስሰቀል”
አንድ ሁለት ሰው ሳይሆን “ሁሉን እስባለሁ”
ሲል እየሰማነው፤
ጆሮ ነሳህ ምነው?
ደግሞስ ሳምራዊቷ፤
“ብፍርስንያ” ‘ሚሏት ውሃ ቀጂ ሴቷ፤
ውሃ አጠጭኝ ብሎ ፤ በፍቅር ጎብኝቷት ፤ እሷን ብቻ መርጦ፤
ሕይወት ሆኗት ሲሄድ ታሪኳን ለውጦ፤
አዳኝ ፣ መሲሕ የግል፤
መቼ ሰማን ስትል?
እንስራዋን ጥላ ገሰገሰች እንጂ ሰማርያ መንደር፤
የጠበቅነው አምላክ ተገለጠ ብላ ላ’ለም ልትናገር።
ከዚያማ፤
ድኅነት በሷ ሳይቀር፤
ለሃያ አምስት ምዕት ወገኖቹ መጣ፤
ከዓለት ክርስቶስ ማየ ሕይወት ፈልቆ ሁለት ቀን ተጠጣ።
መጣፍ ባለማወቅ ልቡናህ የሳተ፤
ዝንጕ ‘ምትሆን አንተ፤
“በእውነት ክርስቶስ የዓለም መድኃኒት እንደሆነ አውቀናል።”
ስትል ሰማርያ ፤ በአልሰሜነትህ በጣም ተደንቀናል።
ከእንግዲህስ ስማ የተዋሕዶን አዋጅ፤
“ቤዛ ኵሉ እንጂ ነው ዓለሙን የሚዋጅ፤
የብቻዬም አይደል፤
የብቻህም አይደል፤
ፋሲካን ልታከብር በደመ ክርስቶስ ፤ ነጽታ ምትታጠብ፤
የምድር ሐሴት እንጂ ፤ የምድር ሁሉ ገንዘብ።
እናም፤
“መ ድ ኃ ኔ ዓ ለ ም”
ያለሚለው ቀለም፤
ትድግናውን ገላጭ ምሉዕ ፊደል የለም።”
እያለች ስትጠራው ስማት በየዕለቱ፤
እያት ስታነግሠው በስመ መንግሥቱ፤
በጥንተ ስቅለቱ።
መድኃኔዓለም!
መድኃኔዓለም!
መድኃኔዓለም!
❤3👍1