መንፈሳዊ ግጥም ብቻ
27.6K subscribers
173 photos
5 videos
5 files
509 links
በዚህ ቻናል ላይ በየቀኑ ኦርቶዶክሳዊ ግጥሞችን ያገኛሉ
ለአስተያየትና ግጥም እንዲፖሰትላችሁ የምትፈልጉ ለመላክ
@Solasc12
@Solasc13
@Mgetem_group

ኦርቶዶክሳዊ ጥቅሶች ብቻ
@Ortho_quotes
Download Telegram
#ሳልፆም_ሊፈሰክ_ነው
አይ የኔ ነገር!!!
@Mgetem

እርግጥ አልበላሁም ስጋም ሆነ ቅቤ
አልፆም አለኝ እንጂ አመፀኛ ልቤ
ካምናና ካቻምና የዘንድሮ ብሶ
መላ ማንነቴ በሀጢያት ተለውሶ
ስዋሽ ስቀጥፍ
ህግን ስተላለፍ
ስሰድብ ሳደማ
የሰው ስጋ ሳማ
ባይኔ ሳመነዝር
የሰው ሰው ሳማትር
ገላዬን ሳራቁት
አዳምን/ሔዋንን ሳሳስት
ስረሳ ስቃይህን
መስቀል ህማምህን
ያን ሁሉ ግርፋት
ነብሴ ሳያስጨንቃት
አይ እኔ
በሀሰት ስመሰክር
በሀጢያት ስዳክር
ለማይሞላ ኑሮ
ሳልሻል ዘንድሮ
ፆሙ ተጋመሰ
ጊዜው ተጋመሰ
ጌታ ሆይ
አቤቱ አስበኝ
ለንሰሀ አብቃኝ
እስቲ የቀረውን ለበረከት በለው
አመፀኛ ልቤ ፆምህን ይፁመው
"ከደጀ ሰላሙ ከካህኑ እግር ስር
ንስሀዬን ልውሰድ ስለመስቀል ፍቅር"
የንሰሀ ህይወት ይስጠን!
___________________________
@Mgetem
@Mgetem
@Menfesawi_getem_bot
👍42🥰1
❖የሰማዩ ጌታ የአርያም ባለቤት❖
❖የአምላኮች አምላክ የፍጥረታት አባት❖
❖ሀያል ፍቅር ስቦት ከመንበሩ ወርዶ❖️
❖በዛ በበረት በከብቶች ግርግም ️
..ከንፅህት ቅድስት ድንግል ማርያም ተወልዶ❖
❖እኛን ላዳነበት ለብርሃነ ልደቱ❖
❖እንኳን አደረሰን  አደረሳችሁ።❖
-----ከ ሰመረ ፍስሃ---
#መልካም_በአል
🥰1
ውድ የቻናላችን ቤተሰቦች እንኳን ለጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል በሰላም አደረሳችሁ እያልን
የግጥም ችሎታ ያላችሁ ወይም ደግሞ እዚህ ቻናል ላይ ቢለቀቅ ይጠቅማሉ የምትሏቸው ግጥሞች ካላችሁ በመላክ መሳተፍ ትችላላችሁ
#ግጥሞችን_ለመላክ
@Menfesawi_getem_bot ላይ
/start ብላችሁ ብትልኩልን ይደርሱናል
አልያም ደግሞ በአድሚኖቻችን አድራሻ
@bubushu
@kal002 ላይ መላክ ትችላላችሁ
ስለ ተሳትፎአችሁ እናመሠግናለን
👍2👏1
#እነዃት_እናትህ ዮሐ 19:27
(በሰመረ ፍስሃ)

የበዛው በደሌ ሀጢያቴ ለመደምሰስ
ያጣሁት ልጅነት ዳግም ለመመለስ
ፈጣሪ ሆነህ ሳለ እንደ ፍጡር ተቆጠርክ
እውነተኛው አምላክ በሀሰት ከሰሱህ
ጥፋተኛ ብለው መስቀል ላይ ሰቀሉህ::
እኔም ደግነትህ ፍቅርህን ተመልክቼ
እንደ በግ ሲጎትቱህ ስትከተላቸው አይቼ
ችንካሮችህ አይተው አለቀሱ አይኖቼ
እንባዬ እንደ ጅረት ጉንጬ ላዬ ፈሰሰ
ውስጤ ሀዘን ገባው ሆዴም ተላወሰ
አንተ ግን...
የእንግልትህ ብዛት ስቃይ ሳይገድብህ
ርሀቡ ጥማቱ ድካም ሳይዳግትህ
ደጋፊዬ እንድትሆነኝ ለችግሬ መከታ
እንባዬን ተመልክታ ቀኜን እንድታበረታ
መስቀልህ ስር ያለችውን አዛኝቷ አናትህ
ብለህ አስረከብከኝ እነዃት እናትህ::
እኔም ደስ ብሎኝ እናቴ ናት ብዬ
ወደ ቤቴ አስገባኀት ወደ ህይወት ጎጆዬ::
ለኔም መፅናኛዬ አማላጅ እንድትሆነኝ
እነሆ ልጅሽ ብለህ እናትህ ሰጠሀኝ::
__________________________
@Mgetem
@Menfesawi_getem_bot
@kal002
4
Forwarded from ማኔ ጫኔ
✤ ይበዛል✤
ጠይቄ ካደረክልኝ
ሳልጠይቅ የሰጠኸኝ
ይበዛል...
ከተወረወረብኝ ከማየው ጦር
የሰወርኝ ከማላየው ጾር
ይበዛል...
ስምህን ሳልጠራ ከዋልኩበት
ከኔ ያልተለየህበት በምሕረት
በይቅርታ የጠራኽኝ ባባትነት
ይበዛል...
ከኔ ብርታት ቸርነት
ከብዙ በደሌ ይቅርታህ
ከአሸናፊነቴ ድልህ
ይበዛል...
ይበዛል ይበዛል ይበልጣል
እንዲበዛልን መጥተሃል
እንዲበዛልን ሞተሃል።
ከመታሰቢያ መስፍን
@Mgetem
3👍1
፨መኖርን ሳትኖረ፨
ትእዛዙን ሰምተህ
ቃሉን እያወቅኸው
መቼ ታገልክና
ሥጋክን አሸነፍከው
ወድቆ መነሳት
ተሰብሮ መጠገን
ማዕቀሉ ሲያይል
በጌታህ መታመን
በተስፋ ስትወጣ
የመከራን ዳገት
አክሊሉ ይታይህ
የዘላለም ሕይወት
ዓላማ ሳይኖርህ
በልማድ ተጉዘህ
መኖርን ሳትኖር
ለምን ትሞታለህ

ከሱናማዊት
@Mgetem
1
#ሃይማኖት_አንዲት_ናት
@Mgetem

ሀይማኖት አንዲት ናት
አንዲት ናት ሃይማኖት፣ ፃድቃን የሄዱባት ከአበው ያገኘናት።
እማ ተዋህዶ ፈተና ቢበዛ በአውሎ በወጀቡ ክፉውን አንፈራም የመጣ ቢመጣ
መስቀሉ ሃይል ነው አለ በልባችን።
የአንገቴ ማህተም ያሰርኩት ጥቁር ክር፣ ስለ ተዋህዶ ይናገር ይመስክር። እናም አልበጥስም ማህተቤን ካንገቴ፣ ብኩርናዬ እኮ ናት ኦርተዶክስነቴ። የደሙን መሰረት ተዋህዶን ንቄ እንዴት ፍልስፋናን ልመን እውነት ብዬ። የመሰረተውን ማንም ሰው ተነስቶ፣ እንዴት ይታመናል ፍልስፍና ከቶ። እምነቴን ከምክድ ለገንዘብ ለእንጀራ፣ ይቅርብኝ መክበሩ ስሜም አይጠራ። ጓዳዬም ሳይሞላ ኑሮዬም ሳያምር፣ ከአበው መቃብር ላይ ከዋሻው ልቀበር፣ ነፍስ ያስምራልና የቃልኪዳኑ አፈር። በውርደት ከምለብስ የሲኦልን ካባ፣ ሌጦው ይሻለኛል የአባቶቼ ዳባ። ያመንኩት እውነት ነው አልጠራጠርም ፣ እሞታለሁ እንጂ እምነቴን አልክድም። ከሰማዕታቱ ከፃድቃኑ ህይወት ፣ ይሄን ነው የማውቀው ስለ ስሙ መሞት።
✤ ስብሐት ለእግዚአብሔር ✤
____________________________
ኢየሩሳሌም (ተዋህዶ ) ሆይ ብረሳሽ ቀኜ ትርሳኝ!
ከስንታየው
____________________________
@Mgetem
@Mgetem
@Menfesawi_getem_bot
3👍2
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ጥምቀተ ኢየሱስ
(ጥምቀተ ክርስቶስ ) (ጥምቀተ ወልድ)
በድጋሜ የተለጠፈ

የጥምቀቱ ባለቤት የሆናችው በዓለም ያላችው ክርስቲያኖች በሙሉ እንኳን አደረሳችው ሸር በማረግ ለሁሉም አዳርሱ

++በመጋቤ ሐዲስ ሄኖክ ፈንቴ+

ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሰላሳ ዓመት ሲመላው

ዮሐንስ ሰላሳ ዓመት ከስድስት ወር ሲሆነው በዮሐንስ እጅ ሊጠመቅ ከገሊላ ወደ ዮርዳኖስ ሄደ

ለምን ወደዮሐንስ ሄደ ዮሐንስ ወደ ኢየሱስ ለምን አልመጣም ቢሉ ባሪያ በጌታው እጅ ይጠመቃል እንጂ ጌታ በባሪያው እጅ ይጠመቃልን ቢሉ ?

1 ለትህትና

ጌታችን ከሰማየ ሰማያት ወርዶ ሰው የሆነው ለትህትና ነው እንጂ ለልእልና አይደለምና

2 አብነት ለመሆን

ጌታችን ዮሐንስን መጥተህ አጥምቀኝ ቢለው ዛሬ ነገሥታት መኳንንት ሀብታሞች መታችው አጥምቁን ይሉ ነበርና ሂዳችው ተጠመቁ ለማለት

ከሌሎች ወንዞች ለይቶ ጥምቀቱን ለምን በዮርዳኖስ አደረገው ቢሉ?

1 ትንቢቱን ለመፈፀም

ዮርዳኖስ ወደሃላው ተመለሰ ብሎ መዝሙረኛው ዳዊት ስለ ዮርዳኖስ ትንቢት ተናግሮ ነበርና ለመፈፀም ነው

2 የአዳምና የሄዋን የእዳ ደብዳቤአቸውን ለመደምሰስ

ከእለታት አንድ ቀን ዲያብሎስ በአዳምና በሔዋን ላይ የጨለማ መጋረጃ ጋርዶ ድቃይ አጽንቶ ስመ ግብርናታችውን ጽፋችው ብተሰጡኝ ስቃይ አቀልላችዋለው ብሏቸው ስቃዩን ያቀለለልን መስሏቸው

አዳም የዲያብሎስ ባሪያ ነው ሔዋን የዲያብሎስ ባሪያ ናት ብለው ጽፈው ሰጡት።

ያን ተቀብሎ በሁለት እብነ ሩካም ጽፎ አንዱን ሲኦል አንዱን ዮርዳኖስ ጥሎት ነበርና በዮርዳኖስ የተጣለውን በጥምቀቱ ለመደምሰስ ዮርዳኖስን መርጧል።

ሲጠመቅም እንደአምላክነቱ አቅልጦ እንደ ሰውነቱ ረግጦ የእዳ ደብዳቤአቸውን አጥፍቶላቸዋል ።

በሲኦል የጣለውን በዕለተ አ ዓርብ በአካለ ነፍስ ወርዶ ደምስሶታል።

ጌታችን ዮሐንስን አጥምቀቀኝ ሲለው

ሌላውን

በአንተ ስም

በአብ ስም

በመንፈስ ቅዱስ ስም

አጠምቃለው አንተን በማን ስም ላጥምቅህ? አለው።

የቡሩክ አብ ልጁ ብርሃንን የምትገልጥ ይቅር በለን የዓለምን ኀጢአት የሚያስወግደው የእግዚአብሔር በግ እነሆ

ክህነትህ እንደ መልከጼዴቅ ክህነት ለዘለአለም ነው እያልክ አጥምቀኝ አለው።

+የአብ ልጅ መሆኑን

+ብርሃን የሚገልጥ መሆኑን

+ይቅር ባይ መሆኑን

+የዓለምን ኀጢአት የሚያስወግድ የእግዚአብሔር በግ መሆኑን

+ክህነቱ ዘለዓለማዊ መሆኑን እየመሰከረ አጥምቆታል

ጥምቀቱን በውሃ ያደረገው ስለምን ነው ቢሉ?

+ውሃ በዙፋን ካለ ንጉሥ በአደባባይ እስካለ ጽኑስ ለሁሉ የሚገኝ ነው።

+ውሃ ጽንፍ እስከ ጽንፍ ይፈሳል ጥምቀትም ጽንፍ እስከ ጽንፍ ይደርሳልና

+ወሃ ከእድፍ ያነጻል ጥምቀትም ከኀጢአት ያነጻልና

+ወሃ የወሰደው ፍለጋ የለውም በጥምቀትም የተሰረየ ኀጢአት በፍዳ አያስዝምና

,

+ውሃ መልክ ያሳያል መልክ ያለመልማል

ጥምቀትም መልክአ ነፍስ ያሳያል መልክአ ነፍስ ያለመልማልና

+በውሃ የታጠበ ልብስ እየቀደም እየነፃ ኃይል ግዘፍ እየነሳ ይሄዳል

ምእመናንም ተጠምቀው ገድል ትሩፋት ከጊዚ ወደ ጊዜ እየሰሩ እየጨመሩ ይሄዳሉና

+ርብቃ ለይስሐቅ የታጨችው ውሃ ስትቀዳ ነው

ምእመናንም ለክርስቶስ ሙሰሽራነት የሚታጬት በውሃ ተጠምቀው ነውና

+በውሃ ቀድሞ ሰብአ ትካት ሰብኣ ግብጽ ጠፍተው ነበርና ውሃ ለመአት እንጂ ለምህረት አልተፈጠረም ብለውት ነበርና ለመአትም ለምህረትም እንደተፈጠረ ለመግለጽ ከሁሉም ውሃን መርጦ በውሃ ተጠመቀ።

በመአር በወተት በወይን በዘይት ተጠምቆ ቢሆን ኑሮ

ሀብታሞች እንጂ ድሃዎች አያገኙትምና ሁሉ በሚያገኘው በውሃ ተጠመቀ።

ሲጠመቅም መንፈስ ቅዱስ በረግብ አምሰሰልወርዷል።

መንፈስቅዱስን ስለምን ርግብ አለው ቢሉ?

+ርግብ ሀዳጊተ በቀል ናትመንፈስ ቅዱስም ሀዳጌ በቀል ነውና

+ርግብ በኖህ ጊዜ ኀፀ ማየ አይኅ ነትገ ማየ አይኅ ስትል ቆጽለ እፀ ዘይት ይዛ ተገኝታለች መንፈስ ቅዱስም ተስፋ መስቀልን ያበስራልና

+ርግብ ክንፋን ቢመቷት እነረቁላሏን።ቢሰብሩባት ቤታን ካላፈረሱባት ቦተዋን አትለቅም መንፈስ ቅዱስም ኀጢአት ቢሰሩም ለንስሃ ይጠራል እንጂ ፈፅሞ ካልካዱት አይርቅምና ።

ጥምቀቱን በመአልት ያላደረገው በሌሊት ያደረገው ስለምነው ቢሉ?

በመአልት አድርጎት ቢሆን መንፈስ ቅዱስ በቁሙ ርግብ ነው ብለው በተጠራጠሩ ነበና

አሁንስ ርግብ አለመሆኑ በምን ይታወቃል ቢሉ ?ጌታችን የተጠመቀ ከሌሊቱ አስር ሰአት ነው

በአስር ሰአት ወፎች ርግቦች አይበሩም ተሀዋስያን ከቦታቸው አይንቀሳቀሱምና በዚህ ርግብ አለመሆኑ ይታወቃል።

መንፈስ ቅዱስ የወረደው ከውሀው ከወጣ ከዮሀንስ ከተለየ በሇላ ነው

ከውሃው ሳለ ወርዶ ቢሆን ለቀድሶተ ማያት የወረደ ነው ባሉ ነበርና።

ከዮሀንስ ጋራም ሳለ ቢሆን ስለ ክብረ ዮሐንስ የወረደ ነው ባሉ ነበርና ።

ሲወርድም ረቦ ወርዷልቢሉ

አብ ምሉእ ነው

አንተም ምሉእ ነህ

እኔም ምሉእ ነኝ ሲል ነው

አንድም አሰይፎ ወርዷል ቢሉ

የብሉየ መዋእል የአብሕይወት ነኝ

የብሉየ መዋእል የአንተም ህይወት ነኝ

እኔም ብሉየ መዋእል ሕይወት ነኝ ሲል ነው።

ወርዶም ራሱን ቆንጠጥ አድርጎ ይዞታል

አብ አኃዜ ዓለም ነው

አንተም አኀዜ ዓለም ነህ

እኔም አኀዜ ዓለም ነኝ ሲል ነው።

መውረዱ ለአብነት ነው

እናንተም ስትጠመቁ እንደዚህ እወርድላችዋለው ሲል ነው።

ከዚህ በሃላ አብ በደመና ሁኖ የምወደው ልጄ ይህ ነው እርሱን ስሙት ብሎ ልጁ መሆኑን መስክሯል።

ጌታችን ሲጠመቅ አንድነት ሶስትነት ተገልፇል

ወልድ በመጠመቅ

መንፈስ ቅዱስ በርግብ አምሳል በመውረድ

አብ በደመና ሁኖ በመመስከር

አንድ ሲሆኑ ሶስት ሶስት ሲሆኑ አንድ መሆናቸው ተገልጧል ማቴ 3÷13-17።

እውነተኛው ሃይማኖት የትኛው ነው ?

ከተሰኘው ክፍል አንድ መጻፌ ላይና

የማቴዎስ ወንጌል ትርጓሜ ላይ የተወሰደ

መጋቤ ሐዲስ ሄኖክ ፈንቴ

ጥር 8+2010

ዱባይ አላይን ተጻፈ
2👍2
፨እናምናለን በምስጢረ ጥምቀቱ፨
በመጋቤ ምስጢርነቱ
በመንግሥተ ሰማይ በርነቱ
ሰው ካልተወለደ ከውኃና ከመንፈስ
ሕይወት እንደሌለው ርስት እንደማይወርስ
ያመነ የተጠመቀ ይድናል
በጥምቀቱ ልጅነት ያገኛል
ባያምን ባይጠመቅ ከልጅነቱ ይወጣል
ኢጥዮጵያዊው ባኮስ በሐዋርያው በፊሊጶስ
ከነቤተሰቦቹ እስጢፋኖስ
ቅዱስ ጳውሎስ ከደማስቆ መልስ
በጥምቀት ተወልደዋል ከመንፈስ ቅዱስ
ሔዋን በሰማንያ አዳም በአርባ ቀኑ
ገነት እንደገቡ ልጅነት እንዳገኙ
ሴቶች በሰማንያ ወንዶች ደግሞ በአርባ
ልጅነት እንዲያገኝ ተጠምቆ እንዲገባ
እናምናለን በእውነት
ያለጥርጥር በእምነት፡፡
@Mgetem
✤✤✤✤✤✤✞✤✤✤✤✤✤
@MENFESAWItsufoche
✤✤✤✤✤✤✞✤✤✤✤✤✤
👍3
​​#ጨረቃን_ማን_መራው?
@Mgetem
የጨረቃን ያህል አዕምሮ ስታጣ፤
መታደል ሲሳንህ የፀሐይን ዕጣ፤
ውሸት ታውጃለህ
አዲስ ነገር ላታመጣ፤
እውነት ግን ታይታለች
በምሽት ተገልጣ።
ያቺ ውብ ጨረቃ ዮርዳኖስን ሆና፤
በከዋክብት ወረብ
ታጅባ በደመና፤
በዮሐንስ እጅ በዮርዳኖስ ሰማይ፤
ሲጠመቅ አሳየች
መድኃኔዓለም በማይ።
በላይ በሰማያት ተደገመች ቃና፤
ዕፁብ ዕፁብ አልን እኛም አየንና።
አዕምሮ ያለው ሰው
ያልገባውን እውነት፤
በስሜታዊነት የካደውን እምነት፤
የጌታዋን ጥምቀት
ጨረቃ ተረድታ፤
በስቅለቱ ደም የሆነች
ዛሬ ታየች በርታ።
"ይሄን ደማቅ ስዕል
ማን ሳለው ይባላል?
ምድሩን ይልቀቅ ስንል....
#ጨረቃን_ማን_መራው
ሊወርድ ይገባል።"
ብለህ በመናደድ ትናገር ይሆናል።
ግና የዚ ባለቤት........
በሰማይ ጨረቃ በምድር ይቅርና፤
አላየኸው እንጂ በደማቅ ተስሏል ባንተም ልቦና።
ከአምላክ ሰው መሆን በላይ ድንቅ እወነትም ተዓምርም የለም ግን አብዛኞቻችን ይህ ምስጢር ሊገባን አልቻለም አምላክ ምስጢሩን ይግለጥልን
በሄኖክ ክበበው 13/5/2011

በትላንትናው ዕለት ለታየው ድንቅ ተአምር የተገጠመ መንፈሳዊ ስነ-ግጥም

@Mgetem
@Mgetem
@kal002
👍31
Forwarded from 🌻 መንፈሳዊ ሥነ-ጹሑፎች🌻 (Semere Fsiha)
#ኣነ_ክርስቲያን_እየ!
#ወኣነ_ክርስቲያን_ውእቱ!
(ህፃን ቅዱስ ቂርቆስ)

💐🌷🌹🌻🌼🌸🌺
እንኳን ለዓመታዊ በዓል ህፃን ቅዱስ ቂርቆስ ወቅድስት ኢየሉጣ በሰላም አደረሳችሁ አደረሰን!!!
🌺🌸🌼🌻🌹🌷💐

💝💝💝
@MENFESAWItsufoche
💝💝💝
👍1
🌙🌑

፨ሰማይ መሰከረ፨

➴➴➴➴➴➴➴➴➴
@Mgetem
👍1
#ናፈቀኝ ....
ዲ/ን ዳንኤል ክብረት
@Mgetem

የማለዳ ተመስጦ ... ውዳሴ ማርያም መድገሜ
በልጅነት ልመጣልህ .. ጧት ማታ መፍገምገሜ
ዛሬ ግን ናፍቆት ሆነብኝ .. ተዘረረብኝ አቅሜ
እንቅልፌ ሰላም አጣ .... እባብ ሆነብኝ ሕልሜ ።
.
"እግዚኦ" ሲባል ሰምቼ .. ሳልነሳ ከትራሴ
ድንጋጤ ወረረኝ .. ከእግሬ ጥፍር እስከራሴ
ሰዓታቱን እየሰማሁ ... ተቀሰቀሰ መንፈሴ
ትዝዝ አለኝ ማኅሌቱ ... ስትዋብበት ነፍሴ
የእናቴ ስም ናፈቀኝ ...... የሕርያቆስ ቅዳሴ
.
እራሴንም ስላጣሁት ..... ከቤትህ በመራቄ
እንደ ሎጥ ሚስት መሰልኩኝ ፤ አደባባይ ደርቄ
.
የመዝሙረ-ዳዊት ጸሎት .. አነከተኝ በትዝታ
ነፍሴን ስላስጠማኋት ... አነባችብኝ አብዝታ
እሪሪሪ ብላ አለቀሰች ... በስጋ ወንጭፍ ተገዝታ
.
ናፈቀኝ ትምህርቱ ... የቅዱስ ያሬድ ጸጋ
ቁጥር ዜማ መጮሄ .... አንደበቴ እስኪዘጋ
ዛሬ ላለው ማንነቴ .. ምን ይሆን የ'ኔ ዋጋ ??
.
በከበሮ በጽናጽል ... መዘመሩ ማሸብሸቡ
ጃኖ ለብሶ በመሰለፍ ... ማመርገዱ መወረቡ
የትውስታ ስለት ይዘው ፤ ወደ ልቤ ሰርገው ገቡ
.
አምላኬንም ሳመሰግን .. ወደ ሰማይ አንጋጥጬ
እንዲህ ዛሬ ልቀብረው .. በልቤ ውስጥ ረግጬ
አገልግሎቴ ናፈቀኝ ... ከሁሉ በላይ አስበልጬ
ኮርስ ስማር ትዝ አለኝ ... በዛፉ ስር ተቀምጬ
.
አንገቴ ላይ የታሰረው .. ለምን ነበር ማኅተቤ
ዛሬ ለምን አታለልኩት .. በምክንያት ተንተብትቤ ?
.
ምኑ ነው የሆነብኝ .. ለቤተ መቅደስ እንቅፋት ?
ትዳር ለምን መሰለኝ .. ሜዳ ሆኖ ተዳፋት ?
ልቤ ከብዶ እስከመቼ .. እኖራለሁ በጥፋት ?
ነፍሴንስ ምንበወጣት ... በ'ሳት ጅራፍ ላስገርፋት
.
ድጓ ሲሉ ትርጓሜ ... ብዙ ጊዜ ሰምቻለሁ
ድጓ ሲሉ ትርጓሜ ... ብዙ ጊዜ ሰምቻለሁ
ሰው መስዬ ሲመግቡኝ .. ባ'ይኔ ብሌን አይቻለሁ
ታዲያ ግን ምን ዋጋ አለው .. ማንበብ እንደሁ ትቻለሁ
.
እውነት ነው አይካድም .. አውደ ምኅረት መቀመጤ
ወንጌሉንም እየሰማሁ .... ሳላስበው መመሰጤ
ትዝ ይለኛል አጀንዳዬ ... ከንፈሮቼንም መምጠጤ
.
ጽዋ ቢሉ ዝክረ ሰንበት .. እንዳያልፈን ስንጣራ
ዓርብ ጸሎት ስንሰለፍ .. ነጭ ለብሰን በጋራ
ከትንሹም ከትልቁም ... ስለድኅነት ስናወራ
"ጉዞ" ብለን በባዶ እግር .. ሳንደክም በተራራ
ነጭ ለብሰን ጧፍ ይዘን .. እንደ ኮከብ ስናበራ
አዎ! አስታውሳለሁ ... ስልሳ ፍሬ ስናፈራ
.
ጾም ጸሎቱ ትዝ ይለኛል .. በላያችን ስናጌጠው
በስግደት ተሽቀዳድመን ... ሳጥናኤን ስናመልጠው
ብዙ ነበር በንስሐው ... በቁርባኑ የሚገልጠው
.
ጌታ ሆይ!
ተመልሶ ይላክልኝ ... መንፈሳዊ ጀግንነቴ
በመቅደስህ ዋጋ ይክፈል .. የናቡቴ ልጅነቴ
"እሺ" ብሎ እንዳልሰራው .. አይሁንብኝ ማንነቴ
.
ቀራኒዮ አይረሳኝ ... ችንካር ያለው መስቀሉ
በክቡር ደም ተነክሮ .. ቀይ ሆኖ መንቀልቀሉ
.
እመ ብርሐን በልደቷ .. ትመልሰኝ ወደ ጥንቱ
የቅዱሳን ጥበቃቸው .... አይለየኝ በረከቱ
ናፈቀኝ
ሰነፍ ልቤ እየገዛኝ .. በሞት ሰይፍ በጫጨቀኝ
ይቅር በለኝ አምላኬ! ... ከመቅደስህ አታርቀኝ
በግራ መቆም መረረኝ ፤ አሰልፈኝ በልጅህ ቀኝ
አብርሃምን ላክና ... መልስህን ቶሎ አሳውቀኝ
በራሴ አይን ስደናበር.. መታዘብህ አስጨነቀኝ
የምኅረት ቃል አንደበትህ ፤ ፅኑ ፍቅርህ ናፈቀኝ።
___________________________
@Mgetem
@Mgetem
@scgpx
👍74
​​#ሞትሰ
(ከሣቴብርሃን ገብረኢየሱስ)
@Mgetem

ቅዱስ ያሬድ ሊቁ፤
በሕይወት እናት ሞት ታየ መደነቁ::
እንዲህ በሚል ቃሉ፤
”ሞታ ለማርያም የዓፅብ ለኵሉ“::

ሞትስ ፥ጌታም ቀምሷል፤
የጥሉን ግድግዳ ፥ በመስቀል አፍርሷል::
ታዲያ፤
ሞታ ከመ ወልዳ፤
የነፍሳተ ሲኦል ፥ማምለጫ ቀዳዳ፤
የሆነላት ድንግል ፥ እረፍቷ ምን ይደንቅ?

ድንቅስ ፥ ከድንቅም ድንቅ፤
አብዝቶ ሚያስጨንቅ ፥ አልፎም የሚያሳቅቅ፤
የትንሣኤን እናት ፥ ትንሣኤዋን ሲንቅ፤
ሞታ ቀርታለች ሲል ፥ ልሣነ መናፍቅ!!

@Mgetem
@Mgetem
👍2
Forwarded from መንፈሳዊ ግጥም ብቻ (ቦአኔርጌስ ቦት)
​​፨ ሞትሰ ፨
(በከሳቴብርሃን)

ቅዱስ ያሬድ ሊቁ፤
በሕይወት እናት ሞት ታየ መደነቁ::
እንዲህ በሚል ቃሉ፤
”ሞታ ለማርያም የዓፅብ ለኵሉ“::

ሞትስ ፥ጌታም ቀምሷል፤
የጥሉን ግድግዳ ፥ በመስቀል አፍርሷል::
ታዲያ፤
ሞታ ከመ ወልዳ፤
የነፍሳተ ሲኦል ፥ማምለጫ ቀዳዳ፤
የሆነላት ድንግል ፥ እረፍቷ ምን ይደንቅ?

ድንቅስ ፥ ከድንቅም ድንቅ፤
አብዝቶ ሚያስጨንቅ ፥ አልፎም የሚያሳቅቅ፤
የትንሣኤን እናት ፥ ትንሣኤዋን ሲንቅ፤
ሞታ ቀርታለች ሲል ፥ ልሣነ መናፍቅ!!

@mgetem
@mgetem
የሰማዩን ምስክር
🌻🌻🌻🌻🌻🌻

ጨለማን ሰባሪ_ብርሃን ወጥቶብሻል
ሞትን የሚገድል_ትንሳኤን ወልደሻል
ንጽሕ መሶበ ወርቅ_ ድንግል ተብለሻል
ለከበረው ክብርሽ_ስግደት ይገባሻል።

የሰማዩ ምስክር_ የታየው በራማ
በምድራዊው ገነት_ እነሆ ተሰማ
የመልአኩን በስራት_ኤልሳቤጥ ስትደግመው
በሆዷ ያለው ጽንስ_ ደስታ አዘለለው
መጥምቀ መለኮት_ክብሩ ከፍ ያለ ነው።

ለኛ ስለሰጠች _ የሕይወት እንጀራን
ሁሌም ለዘለአለም_ እንወዳታለን
የምስራቋ ደጃፍ_የወለደች ፀሐይ
የኤልሳዕ ማሰሮ_ የበረከት ሲሳይ።

የፍቅር የሰላም _ የምሕረት መገኛ
የምንመካብሽ _ ነይ ነይ ወደ እኛ
ኖርዶስ ቀሲመታት_ በጎ መዓዛ ነሽ
የአማኑኤል ማደሪያ_ የለም የሚመስልሽ።

ጌታዬ ከሰጠኝ_ እናቴ እልሻለው
የመንገድ ስንቄ ነሽ_ እመካብሻለው
ለጠየኩሽ ሁሉ _ መልስ የምትሰጪኝ
እንዳልነዋወጥ_ በዐለቱ ትከይኝ።

በመከራ ጊዜ _ መሸሸጊያ ሆኖን
የመከራን ባሕር_ በፍቅሩ አሻግሮን
እንደበደላችን_ ሳያጠፋን ጌታ
አቆመን በደጁ_ ሞልቶን በእልልታ።

ከኛ የበረታችሁ _ አስቡን በጸሎት
በስጋ ፈተና _ እንዳይገለን ምቾች
በሄድንበት ሁሉ_ እንዲገጥመን ሰላም
ፍፃሜአችን እንዲያምር_አማልጅን ማርያም።

የተሰቀለውን _በገና አውርዱ
መሰንቆ ክራሩን_ ከበሮ አሰናዱ
መቆሚያ ጽናጽል_ ይታደል ለሁሉም
በያሬድ ውብ ዜማ_በሚያስረሳ ዓለም
ተነሱ እንዘምር_ ለመድኃኒዓለም።

እንዲህ እናምናለን_ እንታመናለን
በተበተንበት በባዕዱ ምድር_ እንመሰክራለን
የሥላሴን ጥበብ_ ትውልድ እንዲረዳ
ይምጣና ይመገብ_ ከእናቱ ጓዳ
ኋላ ለጥያቄ _እነዳይሆን እንግዳ ትጉኃን

በዝማሬው ጣዕም_ተሞልተን ደስታ
በተዋሕዶነቷም _ ነፍሳችን ተጽናንታ
በቃሉ ምስክር _ ቀርቦልን ማዕድ
በወልድ እናት ምልጃ _በሕይወት መንገድ
ከቅድስት ምድራችን _በመጡት
በደጀ ሰላሙ አለን_ ተሰብስበን።

በመረዋ ድምጹ_ በሚስረቀረቀው
ሲሰማ አርነት_ተሰፋን በሚሰብከው
የአባቶችን ምክር_ትዕዛዝ በሚያከብረው
በረጋው አንደበት_ ከቴድሮስ ሰማነው
ኪዳነምሕረት_ በእቅፏ ታኑረው።


ከዕርስታችን ወተን_ ብንኖርም በእሩቅ
መተላለፋችን_ በስሙ እንዲፋቅ
ክብር ሞገስ ሆነን_ ስራው የሚያስደንቅ።

ሀይማኖት ከምግባር_የነፃነት በፍታ
የሚያስተምር ፍቅር_ ጠዋትና ማታ
የወንጌል አርበኛ_ የሚያስር የሚፈታ
ደጀንን ሸለመን_ የሰራዊት ጌታ።

ለዘመኑ ሕመም_ መድኃኒት ያመርታል
የነፍስ ዶክተር ነው _ትውልድ ይፈውሳል
ብሉይን ከሐዲስ _ እያመሳጠረ
ስንቱን ሐሰተኛ_ ከቤት አባረረ።

በጠላት ተከቦ_ ሲደፈር ተራራው
እንደ ተመረጡት_ በእውነት አብበው
ወንጌልን ተጫምቶ_ በብዕር ይሻገራል
በለበሰው ሞገስ_ ሁሉን ያስደምማል
___________________________
@Mgetem
@Mgetem
@Scgpx
👍43
#መጎዳቴን_አይቶ
@Mgetem

መጎዳቴን አይቶ
ሊቀይር ታሪኬን
ካለሁበት መጥቶ
ሊሞላው ጓዳዬን
መዳን ትወዳለህ ?
ብሎ ቢጠይቀኝ
የሰለለ አካሌን
በአይኔ እያማተርኩኝ
እወዳለሁ ! አልኩት
መፈወስን ሽቼ
የመጥምቁ አምላክ
መሆኑን ሰምቼ፡፡
የጫማውን ጠፍር
መፍታት የተሳነው
ዛሬ ሽባ እግሮቼን
መፈወስ ተቻለው፡፡
ዳንኩኝ በጸበሉ
በእጁ ተጠምቄ
ለምስክር በቃው
በምልጃው ደምቄ፡፡

ከረዳኢ ሃዱሽ
_______________________
@Mgetem
@Mgetem
@Scgpx
👍51
በምህረቱ መራኝ
ትላንት ነበርኩኝ እያለው የሌለው
እንዳማረ ተክል ፍሬ እንደሌለው
ደስታዬም ነበረ ለሞቴ መንገዱ
ህይወቴም ሚመስሉ አንዳች ያልተጎዱ
እውነታው ባይገባኝ የመኖሬ ምክንያት
እጆቼን ዘረጋው እምባዬም ፈሰሰ
ጉልበቴም ታዘዙ ለዳንስ እንዳልተነሱ
ልሳኔም በቃሉ ይቅርታን ለመነ
የወደቀልኝን እርሱን አገነነ
መውደቄን ተረድቶ የማይለኝ ችላ
አምላከ ብርሃን ህይወቴን አጎላ
በመሃሪነቱ ምህረቱን ሽሮኝ
ለህይወቴ ፍዳ መፍትሄው ሆነኝ
ጥር 23/2011
*በምንቴ/የአብስራ
___________
@Mgetem
1
#ናፈቀኝ ....
ዲ/ን ዳንኤል ክብረት
@Mgetem

የማለዳ ተመስጦ ... ውዳሴ ማርያም መድገሜ
በልጅነት ልመጣልህ .. ጧት ማታ መፍገምገሜ
ዛሬ ግን ናፍቆት ሆነብኝ .. ተዘረረብኝ አቅሜ
እንቅልፌ ሰላም አጣ .... እባብ ሆነብኝ ሕልሜ ።
.
"እግዚኦ" ሲባል ሰምቼ .. ሳልነሳ ከትራሴ
ድንጋጤ ወረረኝ .. ከእግሬ ጥፍር እስከራሴ
ሰዓታቱን እየሰማሁ ... ተቀሰቀሰ መንፈሴ
ትዝዝ አለኝ ማኅሌቱ ... ስትዋብበት ነፍሴ
የእናቴ ስም ናፈቀኝ ...... የሕርያቆስ ቅዳሴ
.
እራሴንም ስላጣሁት ..... ከቤትህ በመራቄ
እንደ ሎጥ ሚስት መሰልኩኝ ፤ አደባባይ ደርቄ
.
የመዝሙረ-ዳዊት ጸሎት .. አነከተኝ በትዝታ
ነፍሴን ስላስጠማኋት ... አነባችብኝ አብዝታ
እሪሪሪ ብላ አለቀሰች ... በስጋ ወንጭፍ ተገዝታ
.
ናፈቀኝ ትምህርቱ ... የቅዱስ ያሬድ ጸጋ
ቁጥር ዜማ መጮሄ .... አንደበቴ እስኪዘጋ
ዛሬ ላለው ማንነቴ .. ምን ይሆን የ'ኔ ዋጋ ??
.
በከበሮ በጽናጽል ... መዘመሩ ማሸብሸቡ
ጃኖ ለብሶ በመሰለፍ ... ማመርገዱ መወረቡ
የትውስታ ስለት ይዘው ፤ ወደ ልቤ ሰርገው ገቡ
.
አምላኬንም ሳመሰግን .. ወደ ሰማይ አንጋጥጬ
እንዲህ ዛሬ ልቀብረው .. በልቤ ውስጥ ረግጬ
አገልግሎቴ ናፈቀኝ ... ከሁሉ በላይ አስበልጬ
ኮርስ ስማር ትዝ አለኝ ... በዛፉ ስር ተቀምጬ
.
አንገቴ ላይ የታሰረው .. ለምን ነበር ማኅተቤ
ዛሬ ለምን አታለልኩት .. በምክንያት ተንተብትቤ ?
.
ምኑ ነው የሆነብኝ .. ለቤተ መቅደስ እንቅፋት ?
ትዳር ለምን መሰለኝ .. ሜዳ ሆኖ ተዳፋት ?
ልቤ ከብዶ እስከመቼ .. እኖራለሁ በጥፋት ?
ነፍሴንስ ምንበወጣት ... በ'ሳት ጅራፍ ላስገርፋት
.
ድጓ ሲሉ ትርጓሜ ... ብዙ ጊዜ ሰምቻለሁ
ድጓ ሲሉ ትርጓሜ ... ብዙ ጊዜ ሰምቻለሁ
ሰው መስዬ ሲመግቡኝ .. ባ'ይኔ ብሌን አይቻለሁ
ታዲያ ግን ምን ዋጋ አለው .. ማንበብ እንደሁ ትቻለሁ
.
እውነት ነው አይካድም .. አውደ ምኅረት መቀመጤ
ወንጌሉንም እየሰማሁ .... ሳላስበው መመሰጤ
ትዝ ይለኛል አጀንዳዬ ... ከንፈሮቼንም መምጠጤ
.
ጽዋ ቢሉ ዝክረ ሰንበት .. እንዳያልፈን ስንጣራ
ዓርብ ጸሎት ስንሰለፍ .. ነጭ ለብሰን በጋራ
ከትንሹም ከትልቁም ... ስለድኅነት ስናወራ
"ጉዞ" ብለን በባዶ እግር .. ሳንደክም በተራራ
ነጭ ለብሰን ጧፍ ይዘን .. እንደ ኮከብ ስናበራ
አዎ! አስታውሳለሁ ... ስልሳ ፍሬ ስናፈራ
.
ጾም ጸሎቱ ትዝ ይለኛል .. በላያችን ስናጌጠው
በስግደት ተሽቀዳድመን ... ሳጥናኤን ስናመልጠው
ብዙ ነበር በንስሐው ... በቁርባኑ የሚገልጠው
.
ጌታ ሆይ!
ተመልሶ ይላክልኝ ... መንፈሳዊ ጀግንነቴ
በመቅደስህ ዋጋ ይክፈል .. የናቡቴ ልጅነቴ
"እሺ" ብሎ እንዳልሰራው .. አይሁንብኝ ማንነቴ
.
ቀራኒዮ አይረሳኝ ... ችንካር ያለው መስቀሉ
በክቡር ደም ተነክሮ .. ቀይ ሆኖ መንቀልቀሉ
.
እመ ብርሐን በልደቷ .. ትመልሰኝ ወደ ጥንቱ
የቅዱሳን ጥበቃቸው .... አይለየኝ በረከቱ
ናፈቀኝ
ሰነፍ ልቤ እየገዛኝ .. በሞት ሰይፍ በጫጨቀኝ
ይቅር በለኝ አምላኬ! ... ከመቅደስህ አታርቀኝ
በግራ መቆም መረረኝ ፤ አሰልፈኝ በልጅህ ቀኝ
አብርሃምን ላክና ... መልስህን ቶሎ አሳውቀኝ
በራሴ አይን ስደናበር.. መታዘብህ አስጨነቀኝ
የምኅረት ቃል አንደበትህ ፤ ፅኑ ፍቅርህ ናፈቀኝ።
#ሙሐዘ ጥበባት ዲ/ን ዳንኤል ክብረት
___________________________
@Mgetem
@Mgetem
@scgpx
👍103🥰1🤬1