መንፈሳዊ ግጥም ብቻ
27.6K subscribers
173 photos
5 videos
5 files
509 links
በዚህ ቻናል ላይ በየቀኑ ኦርቶዶክሳዊ ግጥሞችን ያገኛሉ
ለአስተያየትና ግጥም እንዲፖሰትላችሁ የምትፈልጉ ለመላክ
@Solasc12
@Solasc13
@Mgetem_group

ኦርቶዶክሳዊ ጥቅሶች ብቻ
@Ortho_quotes
Download Telegram
📌መልሱ በትክክል ተመልሷል፡፡
መልሱም👇👇👇
_____________________________
ትንቢተ ኢሳያስ ምዕራፍ 60 ÷ 14  የናቁሽ ሁሉ ወደ እግርሽ ጫማ ይሰግዳሉ  ።

_____________________________
የመጀመሪያ መላሻችን
መቅደስ [ID 666969877 ] ስትሆን የተሳተፋችሁ በሙሉ ቃለሕይወት ያሰማልን ተሳትፏችሁ ይቀጥል እናመሠግናለን፡፡
ለአስተያየት እንዲሁም ጥቆማና ግጥም ለመላክ
@Menfesawi_getem_bot
ወይም
@Sol_sc
@Kal002
ላይ ይጠቀሙ
👍1
#ልዩ_ነው_ሕይወቱ
@Mgetetm

በማህፀን ሳለ
ለአምላኩ የሰገደ
በናዝራዊነቱ
ምድር በዳ ያደገ
የብሉይ መደምደሚያ
የሃዲስ ኪዳን መግቢያ
የእውነት ምስክር
ነብይ ሐዋርያ
ደሃውን ሳይንቀው
ንጉሱን ሳይፈራ
ለሕገ እግዚአብሔር ቀንቶ
እውነቱን የዘራ
ልዩ ነው ሕይወቱ
እፁብ እፁብ ድንቅ
የዘካርያስ ልጅ
ዩሐንስ መጥመቅ፡፡
_______________________________
🔔ጥያቄ
ከጌታ እና ከመጥመቀ መለኮት ቅዱስ ዩሐንስ ማን ነው ቀድሞ የተወለደው? በስንት ቀን፣ወር፣ዓመት?መጽሐፍ ቅዱስን መሰረት አድርጎ ቀድሞ ለመለስ ሽልማት አለው? የተዋህዶ ልጆች ተሳተፉ!
➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴
በረከቱን የሚወስደው ማነው የታደለነው
የሚወስደው ማነውየታደለነው/2/
መልሱን 👇
@Menfesawi_getem_Bot
ላይ ይላኩልን
_______________________________
@Mgetem
@Mgetem
2👍1
Forwarded from ማኔ ጫኔ
Forwarded from ማኔ ጫኔ
#Share_Share_Share
ታላቅ መንፈሳዊ የበረከት ጉዞ ወደ ክርስቶስ ሠምራ
📗አዘጋጅ
📗በአሰላ ደ/መ/መ/ዓለም ካቴድራል ሰ/ት/ቤት የ2ኛ ደረጃ እና የመሰናዶ ተማሪዎች ግቢ ጉባኤ
📗እሑድ ኅዳር 30
📗ከጠዋቱ 12 ሰዓት ጀምሮ በደብሩ ንዋያተ ቅዱሳት መሸጫ ፊት ለፊት በመገኘት የጉዞው በረከት ተካፋይ ይሆ
የሞከር ሰው እንኳን አልነበረም ሰለሆነም ሰዓቱ ትክክለኛው ምላሽ የሚሰጥበት ጊዜ ነው 📌
ዩሐንስ በወርሃ ጥቅምት ተጸነሰ በወረሃ መጋቢት በእለተ እሁድ ተወለደ።
ጌታችን በወርሃ መጋቢት ተጸነሰ
በታህሳስ 29 ተወለደ።
ስለዚህ መጥመቀ መለኮት ቅዱስ ዩሐንስ ጌታችን መድሃኒታችን እየሱስ ክርስቶስን በ6 ወር ይበልጠዋል።
ማስረጃ➴ ሉቃ፡1፥36 ፣ ሉቃ፡1፥36

📍📍📍📍📍📍📍📍
@Mgetem @Mgetem
👍1
''የሞት ሞት''
➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴
@Mgetem @Mgetem
🇪🇹 ኢትዮጵያ ሆይ ለምኚ🇪🇹
እጆችሽን ዘርጊ ወደ አምላክሽ
ወደ ውድ ጌታሽ ሁሌ እንዲጠብቅሽ
እናቴ ሆይ አፍሪ መልካም ልጆችን
ጡትሽን ጠብቶ አድጎ እሚጦርሽን
መልካም ዘር ዘርቶ
መልካም ፍሬ የሚያፈራልሽን
ፀልይ ወደ አምላክሽ
ሁሌም መልካም እንዲያሳይሽ
እጆችሽን ዘርጊ
ሁሉን እንዲሰማሽ
እናቶች ተጡረው
እንዲያብብ ቤትሽ
አባቶችም አምረው
እንድትታይ ደምቀሽ
ሁሌም መልካም ሆኖ
እንዲታይም ክብርሽ
ለንጉሱ ጌታ ለአንድዬ እናት ነግረሽ
ሀገረ እርስትሽን እኔን ጎብኝኝ ብለሽ
ለምኛት እናቱን እርቅ እንድታሰጥሽ
የህይማኖት አርማ
የክርስትና መግለጫ
አንቺ እማማ ለምኚ ከጌታ
ሁሌ ሃይማኖታችን
እንድትታይ በርታ
አቡዬን ተክልዬን
ይዘሽ በአንድነት
ተነሽ በግርማ
ሁልጊዜ ለጸሎት
ልጆችሽን ይዘሽ
ቀን ቀን በህብረት
ከፀሎት በኋላ
ምህረቱን እያሰብሽ
ስማኝ ብለሽ ጩሂ
በሲቃ ተሞልተሽ
መከራውን ሁሉ
ከአንቺ እንዲያርቅልሽ፡፡

📌📌📌📌📌📌📌📌
@Mgetem @Mgetem
👍64
''መልካም ነገር ነበር''
➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴
@Mgetem @Mgetem
👍3
ማን ይሆን?

በሃይማኖትዓይን ያየ
ከትንቢቱ ጋር ያስተያየ
አዝመራ ጠፍቶ በቡቃያ
እሕል ሲጠፋ በገበያ
ረኃብ ሲነግስ ጦም ማደሩ
የሞት ዜና ሲተላለፍ በሀገሩ
እስቲ ማን አውቋል ትንቢቱን
የፍጻሜ ምልክቱን
ነቅተን ባንሆን እንድንነቃ
ለእውነተኛ ንስሃ እንድንበቃ
ዝሙት ርኩሰት መዳራቱ
መጠጣት መስከር ጥል ማንሳቱ
ሟርት ቁጣ አድመኝነቱ
ማጨስ መቃም መደነሱ
በየጎዳናው መልከስከሱ
የማይረባ ጣኦት ማምለኩ
ለቃልቻ ለጠንቋ መንበርከኩ
ሁሉ ቀርቶ የስጋ ፈቃድ
በቃለ እግዚአብሄር እንድነሄድ
ፍቅር ደስታ ሰላም ትዕግስት
እምነት ተስፋ ራስን መግዛት
ሆኖ የእኛ ባህሪአችን መለያችን
ፀንተን ነቅተን በተዋህዶ እምነታችን እንነሳ በጉዞአችን።

✦✦✦✦✦✦✦✦✦✦✦
@Mgetem @Mgetem
6
☞ቶማስ ዘመርዓስ
የደም ዋጋ ያምላክ ጥሪ፣
ከንቱ ሆነሽ እንዳትቀሪ፣
የኖረልሽ ያቆዬሽን፣
መልሽልን መርዓስን፣
ባርኮን ይሂድ እባክሽን።
ስሚኝማ ተዋህዶ ላንቺ ነዉ የማወጋ፣
መዓልቱ አልቆ ልሊቱ እስከሚነጋ፣
ታሪክሽን ለፃፈዉ ለከፈለልሽ የደም ዋጋ።
የእሳተ ክፋይ ያንደበት ፍም፣
መርዓስ ጠበብት ማይጠፋ ስም።
መርዓስ•••••••
የኑፋቄ ህንፃ ደርማሽ፣
በወንጌል ልብን አረስራሽ።
መብረቀ-ሰማይ የአንደበት ቃል፣
የመናፍቃን ሽንፈት ድምፀተ-ደወል።
አዳም አዳም ወዴት ነህ የሚል ጥሪ፣
መርዓስ የትኅትና ዳራ ለምዕመኖቹ ነዋሪ።
የአንፆኪያ፣ቁስጥንጥንያ፣እስክንድርያና ሮሜ፣
የንስጥሮስ የውግዘት ራስ ምታት የተዋህዶ ልምላሜ።
ወየው ለአረማውያን ወየው ለከኀዲወቹ፣
ክቡር ገላህን ላጨሱት ለጨካኝ ግፈኞቹ።
የግፍ ግፍ ለሰሩብህ ገላህን እየሸለቱ፣
አፅቅህን እየቆረጡ በስምህ ለተዛበቱ።
ለ 22 ዓመት የጣር ኑሮ ሰቆቃ፣
በግፍ በበደል ጉርናት በነፍስ ሲቃ፣
መርቅያንና ሲሞን መስርይ ምን አሉ፣
ኢቦኒስት ዶሴቶቹ በጭንቀት ሲያቃጭሉ፣
አረማውያን መርገምቶች ለጣኦት ያቃጠሉህ፣
ያኔ ኒቅያ ስትሔድ መርዓስ ሆይ ምን አሉህ ?
መርዓስ••••
ኧረ የመከራህ መግለጫ ተገድፎ ጠፋኝ፣
ኅሊናዬ ወደ ውስጥ እየደማ ጤናየን እየነሳኝ።
የበረሃው ፍሬ የነጎድጓድ ድምጽ እሩምታ፣
ዲያብሎስ ራሙኤልን በቃል ግዝት ሚረታ።
የቆስጠንጢኖስ ቡራኬ መክፈቻ፣
የጉባዔው ያንድነት ልብ መቀነቻ።
እንቆጳዝዮን የታጋሾች አፍላጋት ጥበበኛ፣
የጽኑነት ተምሳሌት ያንድነት መመዘኛ።
መርዓስ የኃይማኖት እንቁ ፍሬ፣
የሳቶሪኖስ ኒቆላዎስ መቅጫ በርበሬ።
የእምነታችን ጨው ማጣፈጫ፣
የውጉዛን መለያያ ማዳመጫ።
መርዓስ•••••••
የተዋኅዶ ወጋገን የኒቅያ ኤጲስ ቆጶስ፣
ዛሬም ዳግም ፈጥነህ ድረስ፣
ባርከንና እንደድሮው እንቀደስ።

በእሸቴ በቀለ
✦✦✦✦✦✦✦✦✦✦✦✦
@Mgetem @Mgetem
4
፨ጋብቻ ክቡር ነው፨
ጋብቻ ክቡር ነው ከሁሉ የበለጠ
ከአምላ ለሰው ልጆች ከጥንት የተሰጠ
መረዳጃ እንዲሆን ጋብቻን ገለጠ
ብቸኝነትንም በትዳር ለወጠ፡፡
ገና ሰው ሲፈጠር ጥንት ከመጀመሪያ
አንድ ለአንድ ነው ለፍጥረት መመሪያ
ኋላም በሥጋዊ ተአምር መጀመሪያ
ጋብቻን በማክበር ሆነልን አርአያ
ሰርግ ቤት በመግባት ከእናቱ ጋራ
በድንግል ልመና ታላቅ ስራን ሰራ
ውሃ የነበረ ጋብቻ ተንቆ
ወይን ጠጅ አረገው ሰውን አስደንቆ
አባት ሌለው ልጅ እንዳይሆን ትውልዱ
እናቱን የማያወቅ እንዳይሆን በግዱ
ምንም ላልታደሰ ለዚህ ትውልድ እጣ
ከበሽታ መውደቅ በማውቀው ጣጣ
በዚህ መች አለቀ ጋብቻን ለናቀ
ማንም እየናቀው ሰውነቱ አለቀ
እለተ ሞቱንም በቅርቡ ጠበቀ
ከመጣው በሽታ እንዲሰውረን
ሁለት ከመሆን አንድ በመሆን
ይሻለን ነበረ መኖር ተባብረን
በዚህ መጥፎ ሕይወት ያለን በጠቅላላ
በንስሃ እናምልጥ በእሳት ሳንበላ
እራሳችን ድነን ሌላውን እናድን
እራስን በመግዛት በአንድ መወሰን
ይኸው ስለሆነ ፍቱን መድኃኒቱ
ሌላ ለመፈለግ አንድከም በከንቱ
ለዚህ የበቃችሁ እንኳን ደስ አላችሁ
በሃሳብ መንገድ ላይ በጉዞ ያላችሁ
እናትና ልጇ በአንድነት ይርዱአችሁ፡፡
@Mgetem @Mgetem
👍61🥰1
* ደስ የሚያሰኝ መስዋዕት*

ሕይወትን መጥኖ ርምጃን ወስኖ
ሕሊናን ሰብስቦ ከሰውም ሰው ሆኖ
ማንነትን አውቆ ራስን መርምሮ
ክህሎት እውቀትን በግብር ሰውሮ
ማን እንደኔ ምሁር ማን እንደኔ አገልጋይ
የቃላት እንቅፋት ትውልድ አሰናካይ
ቁጣን አስወግዶ ተስተካክሎ ቆሞ
ፈራጅ ተችነቱን ታርሞና አርሞ ፡፡
መንገዱ እንኳን ቢሆን አባጣ ጎርባጣ
እነዚህን አልፎ ተራራ የወጣ
በፍቅር በርኅራኄ ራሱን የመገበ
ደስ የሚያሰኝ መስዋዕት ለአምላክ ያቀረበ፡፡

✧✧✧✧✧✧✧✧✧✧✧✧✧
@Mgetem @Mgetem
1
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
👍1
💗እናቴ ስማፀን በስምሽ💗

ድንግል ማርያም ብዬ ስማፀን በስምሽ
በቅድመ እግዚአብሔር ልመናዬን አድርሽ
እኔ ደካማ ነን ኃጢአቴ የበዛ
እኔ ጎስቋላ ነኝ በደሌ የበዛ
ጊዜዬን ያባከንኩ በዋዛ ፈዛዛ
ጊዜዬን ያባከንኩ በከንቱ በዋዛ
እመብርሃን ስልሽ ፈጥነሽ ድረሽልኝ
ልመናዬን ሰምተሽ ቆመሽ ለምኝልኝ
ኃጢአቴ ቢበዛም ይዣለው አንችን
አስምረሻልና በላዔ ሰብን
አንገቴን ቢያስደፋኝ በዝቶብኝ ኃጢአቴ
ምልጃሽን ፈለኩኝ ድንግል ሆይ እናቴ
ያን ክፉ ጨለማ እንዳላይ አደራ
ድንግል ሆይ ከልይኝ ከዲያብሎስ ጭፍራ
እመብርሃን እያልኩ ቆሜ ከደጅሽ
በብርሃን እጆችሽ እንባዬን አብሽ
አለም አታላይ ነች ወደሷ ተሳብኩኝ
ታማልጅኝ ብዬ አንቺኑ ተራብኩኝ

ከእህተ ማርያም
➣➣➣➣➣➣➣➣➣➣➣➣➣
@Mgetem @Mgetem
7👍3🥰2🤬1
""""======ቅድስት እናት ===""""""
""""==="""""
ይቺ ቅድስት እናት _ ቃልን ወሰነችው
በከብቶቹ ግርግም_ ወልዳ ታቀፈችው
በመጠቅለያም_ጠቀለለችው።

ለደቱንም ዘር_ አልቀደመውም
የዳዊት ሥር ነው_መድኃኒአለም
በመወለዱም ድንግልናዋን_አልለወጠውም
የተዘጋች ደጃፍ_እናታችን ማርያም።

ቃል ከአብ _ ያለ ድካም ወጣ
የአዳም ልደቱ_ ደረሰለት ዕጣ
ከድንግልም ያለ _ሕማም ተወለደ
በእውነተኛው ብርሃን_ከሳሽ ተሰደደ።

ምጥ ሳያገኛት_ተሰማ እልልታ
ሰበአ ሰገል መጡ_ሊሰግዱ ለጌታ
እረኞች _ ዘመሩ ተሞልተው ደስታ።

ለአምላክነቱ አመጡለት _ዕጣን
ለንጉሥነቱ _ አቀረቡ ወርቁን
መድኃኒት ነውና _ ገለጡት ትንቢቱን
እነሆ አየነው_ ምስዋዕት ከርቤውን።

ግርማ ያለሽ_ድንግል የአሮን በትር
እናደንቅሻለን _ የሁላችን ክብር
ገናንነትሽን _ልንዘረዝር
በያሬድ ውብ ዜማ_ በዳዊት መዝሙር
ቆመናል ከደጅሽ_ ልንደረድር።

እንደ መልአኩ ገብርኤል_ ከላይ እንደመጣው
ልናመሰግንሽ _ ማርያም ግድ ነው
የባሕሪያችን መዳን_ካንቺ ተገኘልን
በማሕጸንሽ ፍሬ_ሞት ተቀበረልን።

እንደ ሠርግ _ቤት ጉድፍ የሌለብሽ
መንፈስ ቅዱስ _ ያደረብሽ
የልዑል ኃይልም ማርያም ጸለለበሽ ።

ዘለአለም ነዋሪ_የነገስታት ንጉስ
ከኃጢአት ያዳነን_ ይመስገን ኢየሱስ
የልባችን ሰላም_ፍቅርህ በኛ ይንገስ።

ከአብ የተወለደ _ከአለም በፊት የነበረ
አንዱ ቃል እራሱን ( ባሕሪዩን) ሰወረ
እንደምን ይረቃል_የሰማዩ ምስጢር
የሱ ያደረገን_ ይመስገን እግዚአብሔር።

የኪዳን ጽላት_ያለብሽ
የተሰወረ መና_የተሸከምሽ
የወርቅ መሶብ_ የምንልሽ
ደብተራ ድንኳን _አንቺ ነሽ
የጥበብን ወንጌል_ በክንድሽ የታቀፍሽ
አሳስቢ ድንግል ሆይ_ ለመሃሪው ልጅሽ
እናምናለንና _ ሁሉ እንደሚቻልሽ
="""""ቅድስት እናት="""""""""
እህተ ማርያም
@Mgetem @Mgetem
📌📌📌📌📌📌📌📌📌
@MENFESAWItsufoche
👍72🥰1
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#የአፎምያ_አጽናኝ
@Mgetem

ከቀደመው መንገድ ከላይ በተሰጠን
ዕድሳት በማያውቅ በማይሻርው ዘመን
በድንቅ ምስክሮች ብርሃን በሆኑን
እንድንጓዝ ሁሌም የአፎምያ አጽናኝ
ጠላት ቀስቱን ሰብቆ ሊያጠፋን ሲመጣ
እንደ ቋጥኝ ከቦን የዚህ አለም ጣጣ
በከንቱ ስንሮጥ ኋላ እንዳንቀጣ
አማልደን መላኩ የነፍሳችን ዕጣ
የሁሉንም ጸሎት ከአምላክ የምታደርስ
ፍቅር እና ርህራሄ በሰው የምታለብስ
ልክ እንደ ትላንቱ ዛሬም ፈጥነህ ድረስ
በአንደበትህ ፍሬ ውስጣችን ይታደስ
የዳንኤል አጽናኝ የአፎምያ ረዳት
በህይወት የቀየርክ የባህራንን ጽሕፈት
በለአምን የታደክ ከእርግማን መቅጸፍት
እኛንም ጠብቀን ከምናየው መአት
የምጽአት ዋዜማ ለመሆኑ ምስክር
በመጽሐፍ ያለው ቃሉ ሲተገበር
መተማመን ጠፍቶ ሲቀወቅዝ ፍቅር
በወንጌሉ አንድምታ ልባችን ይታጠር
ይቅርታ ምህርቱ ይምጣልን የእግዚአብሔር
እረኛ እንደሌለው ሲጨነቅ ትውልዱ
ተመሳስሎ ቆሞ ሲያስት በመንገዱ
ግራ በመጋት ስንቶቹ ተጎዱ
በየዋህነታቸው አብረው ተሰደዱ
ዘንዶ አፉን ከፍቶ ነፍሳት እንዳይወጥ
የተዋህዶን መዝገብ እውነቱን ለመግለጥ
የቆመውን ሁሉ በአውደ ምህረቱ
ያበረታን አምላክ እሰከ ምጽአቱ።
_____________________________
እንኳን ለሊቀመላአኩ ለቅዱስ ሚካኤል ወርሃዊ ክብር በዓል በሰላም አደርሳቹ አደረሰን የመላአኩ ረድኤት እና ምልጃው አይለየን አሜን!
_____________________________
@Mgetem
@Mgetem
@Menfesawi_getem_bot
👍42👏1
#ስውር_ቅኔ
@Mgetem

የቤተ ክርስትያን ደጅ ዕለት ተለት ስሜ
በፆም በፀሎት በስግደት ደክሜ
አምላኬን ለመንኩት
የሚያስፈልገኝን ዘርዝሬ ነገርኩት
የሚያስፈልገኝ ነገር ቢዘገይ ጊዜ
ነፈከኝ ብዬ በምሬት አንካሴ
ፈጣሪን ወጋሁት
ልቡን አደማሁት
በስርዓት አጥ ምሬቴ
በአጉል እምነቴ
ልቡ ስለቆሰለ
በደመና መሀል ጌታዬ እንዲህ አለ
‹‹ ሁሉን የማቀው እኔ ሆኘ ሳለ
ነፈከኝ ለማለት ምነው ልቦናህ ቸኮለ
ዘርዝረህ የላከውን የልመና ፀሎት
ይመለከት ዘንድ ዐይኔ ተተከለ
የምትፈልገው እንጅ የሚያስፈልግህ አንድም እንደሌሌ
የታዘበው እጄ የጠየከኝን ከማድረግ ተከለከለ
ግና ልጄ አዕምሮህ በደንብ ካሰተዋለ
ባለማድረግ ውስጥም ታላቅ ማድረግ አለ>>
ዳንኤል ከበደ

@Mgetem
@Mgetem
@Menfesawi_getem_bot
ግጥሞቻችሁን ላኩልን
3👍1🥰1
#አፈረሰበት_እቅዱን
@Mgetem

የሰው ዘር ቀዳሚ ጠላት
ለዓለም የሐሰት አባት
የአዳምን ኃጢአት መስራች
በሰዎች ውድቀት ተደሳች
የሐዘን ቤቶችን ለመስራት
ተኝቶ አያውቅም በእውነት
በደምና እንባ እያራሰ
በሰው አጥንት እየማሰ
የሞትን መሰረት በመጣል
የኃጢአት ምሰሶ በመትከል
እጅግ ብዙ ዘመናት ትግሏል
የሞቱን መውጊያ ለመንቀል
ምክንያተ ድኂን ናት ድንግል
የአዳምን እዳ ለማስወገድ
ሥጋን ለበሰ እግዚአብሔር ወልድ
አማኑኤል ሰው በመሆን
ክፉ ተግባሩን የሰይጣንን
አፈረሰበት ዕቅዱን፡፡
____________________________
@Mgetem
@Mgetem
@bubushu
👍2