Meweda | Comparison
1.9K subscribers
38 photos
14 videos
1 file
40 links
Faith through knowledge

[ እምነትን በእውቀት ]
Download Telegram
በጣም ያስገረመሽ ምንድነው አትሉኝም እስካሁን ባየናቸው ፅሁፎች አብዛኞቹ ክርስቲያን ሴት ላይ የተጣሉ ገደቦች ምክንያታቸው  የአዕምሮዋ ጉድለት መሆኑ ፡)
🤣57😁6🥴4😭4🔥3😢2
Forwarded from ስለ ቀልባችን
❝አላህን በማያስደስት መንገድ የተጀመረ መጀመሪያ፣ ፍጻሜው ባለቤቱን አያስደስተውም።❞
❤34👍15💯8👏3🍓1
አንደሉስ → የዛሬዋ ስፔን‼
================
(በአውሮፓ እምብርት ያበራችው የኢስላም ፀሐይ እና የጠፋችው ውብ ገፅታ!)
||
✍️ «የአይቤሪያን ልሳነ ምድር ታሪክና ባህል ለመረዳት የሚሞክር ማንም ሰው፣ ያንን 'አስደናቂ የሆነውን ኢስላማዊ ትሩፋት' ከግምት ውስጥ ሳያስገባ ማለፍ አይችልም!» - (ሪቻርድ ፍሌቸር፣ 'ኢስላማዊቷ ስፔን' በተሰኘው መጽሐፉ)


🖊 ዛሬ ስፔን እና ፖርቱጋል ብለን የምንጠራቸው ሀገራት፣ ከአንድ ሺህ ዓመታት በፊት በአውሮፓ የጨለማ ዘመን (Dark Ages) ውስጥ ብቸኛዋ የበራች የብርሃን ደሴት ነበሩ። ስሟ "አንደሉስ" (Al-Andalus) ይባላል። ይህች ምድር ከ711 እ.ኤ.አ
እስከ 1492 እ.ኤ.አ ለስምንት መቶ ዓመታት በእስልምና አስተዳደር ስር የነበረች፣ ዓለም ያየቻት እጅግ
ስልጡን፣ የሳይንስ፣ የፍትሕ እና የመቻቻል ማማ ነበረች።

እስኪ የዚችን የጠፋችና የተረሳች ታሪከኛ ምድር የተወሰኑ ገጽታዎች እንቃኝ፦


1⃣ ታሪካዊው መግቢያ፡ የጧሪቅ ኢብኑ ዚያድ ድል! ⚔️፦

🎀 በ711 እ.ኤ.አ ታላቁ የኡመውያ ኸሊፋ አል-ወሊድ ኢብኑ ዐብዱልመሊክ ባዘዘው መሠረት፣ ጀግናው የጦር አዛዥ ጧሪቅ ኢብኑ ዚያድ 7,000 የሚጠጉ ወታደሮቹን ይዞ ወደ አይቤሪያ ልሳነ-ምድር ተሻገረ። ያ ተሻግሮ ያረፈበት ትልቅ ተራራ እስከ ዛሬ ድረስ በስሙ "ጀበለ-ጥ'ጧሪቅ" (Gibraltar) ተብሎ ይጠራል።

🖊 በዚያን ጊዜ ስፔንን ይገዛ የነበረው ጨቋኙ የቪዚጎዝ (Visigothic) ንጉስ ሮደሪክ (Roderic) ነበር። ጧሪቅ ኢብኑ
ዚያድ በጓዳሌት ጦርነት (Battle of Guadalete) የሮደሪክን ግዙፍ ጦር ድል በማድረግ፣ አብዛኛውን የስፔን እና
የፖርቱጋል ክፍል፣ አልፎም እስከ ደቡብ ፈረንሳይ ድረስ በ7 ዓመታት ውስጥ በኢስላም ጥላ ስር አስገባ። ይህች ምድርም አንደሉስ ተብላ ተሰየመች።



2⃣  ቆርዶባ (Córdoba)፡ የዓለም የዕውቀት ማዕከል! 😀

🎀 አንደሉስ በተለይም በዐብዱ-ር'ረሕማን አድ-ዳኺል (Abd al-Rahman I) እና በኡመውያ ኸሊፋዎች ዘመን፣ የዓለም የዕውቀት፣
የሥልጣኔ እና የንግድ ማዕከል ሆነች። ዋና ከተማዋ ቆርዶባ (قرطبة) በዚያ የጨለማ ዘመን የአውሮፓ ትልቋ ከተማ ነበረች።

  ✅  ከ100,000 በላይ ነዋሪዎች ነበሯት።

✅ መንገዶቿ በሌሊት በመብራት (Oil lanterns) ያበሩ ነበር (በዚያን ጊዜ ለንደን እና ፓሪስ በጭቃ እና በጨለማ የተዋጡ ነበሩ)።

  ✅ በከተማዋ 70 ግዙፍ ቤተ-መጻሕፍት፣ 700 መስጂዶች፣ እና 3,000 የሕዝብ መታጠቢያዎች ነበሩ።
 
✅ ዛሬም ድረስ በአርክቴክቸር ድንቅነቱ የሚነገርለት የቆርዶባ ታላቁ መስጂድ (Mosque-Cathedral of Córdoba) የዚህ ዘመን ትሩፋት ነው።


3⃣ የሳይንስ እና የሕክምና ወርቃማ ዘመን 🔬

🎀 ዛሬ አውሮፓውያን ለደረሱበት የሳይንስ እና የሕዳሴ (Renaissance) ከፍታ፣ መሠረቱን የጣሉት የአንደሉስ ሙስሊም ምሁራን ናቸው።


✅ ሕክምና፡
➡️ አቡ አል-ቃሲም አል-ዘህራዊ የተባለው ሙስሊም ሊቅ፣ ዘመናዊ የቀዶ ጥገና (Surgery) አባት ይባላል። ዛሬ የምንጠቀምባቸውን 200 የሰርጀሪ እቃዎች የፈጠረው እርሱ ነው።
 
✅ አስትሮኖሚና ሒሳብ፡
➡️ አል-ዘርቃሊ (Al-Zarqali)፣ የኮፐርኒከስን ሥራዎች ያስቀደመ ታላቅ የአስትሮኖሚ ሊቅ ነበር። ከ0-9 ያሉት ቁጥሮች (Arabic numerals) ወደ አውሮፓ የገቡት በዚችው በአንደሉስ በኩል ነው።

  ✅ ግብርና (Agronomy)፡
➡️ ሙስሊሞች ዘመናዊ የመስኖ ስርአት (Irrigation)፣ ሸንኮራ አገዳ፣ ሎሚ፣ ሩዝ፣ እና ሮማን (Pomegranate) የመሳሰሉትን ፍራፍሬዎች ለመጀመሪያ ጊዜ ወደ አውሮፓ ያስተዋወቁት በአንደሉስ ነበር።



4⃣ ፍትህ፣ አብሮነት እና መቻቻል (La Convivencia) 🕊️

🎀 በአንደሉስ ዘመን ሙስሊሞች፣ አይሁዶች እና ክርስቲያኖች በአንድነት በሰላም የኖሩበት "ወርቃማው የአብሮነት ዘመን" ነበር። ክርስቲያኖችና አይሁዶች የራሳቸውን ኃይማኖት በነፃነት መተግበር ብቻ ሳይሆን፣ በመንግስት ውስጥ ትልልቅ የሥልጣን ቦታዎች
(አምባሳደር፣ ሐኪም፣ ሚኒስትር) ነበሯቸው። በተለይም አይሁዶች በአውሮፓ ይደርስባቸው ከነበረው ጭፍጨፋ ሸሽተው ሰላም ያገኙት
በኢስላማዊቷ ስፔን (አንደሉስ) ውስጥ ነበር። ይህ ዘመን በታሪክ "Golden age of Jewish culture" ተብሎ
ይጠራል። ዛሬ ግን እነርሱ ታሪካቸውን ረስተው ፍልስጤምን ወረዋል።


5⃣ የአንደሉስ ብርሃን መጥፋት፡ የውድቀት መጀመሪያ (Reconquista) 💔፦

🎀 ከጥንካሬዋ በኋላ አንደሉስ መዳከም ጀመረች። ምክንያቱ ደግሞ የውጭ ጠላት ሳይሆን፣ የሙስሊሙ የውስጥ ሽኩቻ እና መከፋፈል
(Taifas/የአናሳ መንግስታት ዘመን) መምጣቱ ነበር። በ1031 እ.ኤ.አ የቆርዶባ ኸሊፋነት ሲፈርስ፣ አንደሉስ ወደ ትናንሽ እና እርስበርስ ወደሚዋጉ የሙስሊም ግዛቶች ተከፋፈለች።

✒️ ይህንን የሙስሊሙን መከፋፈል የተጠቀሙት የሰሜን ክርስቲያን መንግስታት (ካስቲል፣ አራጎን፣ ሊዮን) በጋራ በመሆን የሪኮንኪስታ
(Reconquista - ዳግም የማስመለስ) ጦርነት ጀመሩ። መጀመሪያ ቶሌዶን (1085)፣ ከዚያም ቆርዶባን (1236) እና ሲቪልን (1248) ተቆጣጠሩ።

✒️ የመጨረሻዋ ምሽግ መውደቅ፡ ግራናዳ (1492)
💾  የመጨረሻዋ የሙስሊሞች ምሽግ የነበረችው ግራናዳ (Granada)፣ ለ250 ዓመታት ታግላ፣ በመጨረሻ ጃንዋሪ 1 ቀን 1492 እ.ኤ.አ በንጉስ ፈርዲናንድ እና ንግስት ኢዛቤላ ጦር ተከበበች። የአንደሉስ የመጨረሻው ሙስሊም መሪ (አቡ ዐብደልሏህ)፣ ያንን ድንቅ የሆነውን የአልሐምብራ ቤተመንግስት (Alhambra Palace) ቁልፍ አስረክቦ፣ ከከተማዋ ሲወጣ፣ ስቅስቅ ብሎ አለቀሰ። ያኔ እናቱ «እንደ ወንድ ተዋግተህ ማቆየት ያቃተህን ሀገር፣ እንደ ሴት አታልቅስላት» ብላዋለች ይባላል።

✒️ ከዚያ በኋላ ስፔንን የተቆጣጠሩት ካቶሊኮች፣ በሙስሊሞች እና አይሁዶች ላይ ታይቶ የማይታወቅ የዘር ማጥፋት (Inquisition) አወጁ። «ወይ ወደ ክርስትና ግቡ፣ ወይ ሀገር ለቃችሁ ውጡ፣ አለበለዚያ ትገደላላችሁ» የሚል አዋጅ ወጣ። በሚሊዮን የሚቆጠሩ
የሙስሊም መጽሐፍት በአደባባይ ተቃጠሉ፤ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ሙስሊሞች (ሞሪስኮስ በመባል የሚታወቁት) ተገድለዋል፤ ከፊሎችም ወደ ሞሮኮ እና አልጄሪያ ተሰደዋል።


⏰ አንደሉስ ዛሬ በካርታ ላይ የለችም። ነገር ግን የተዋበው አርክቴክቸሯ፣ ያስተማረችው የሳይንስ ብርሃን እና የፍትህ ታሪኳ መቼም አይረሳም። የሙስሊሙን ኡማ ትልቅነትም ሆነ መከፋፈል፣ ምን አይነት ውርደትና ውድቀት እንደሚያመጣ የምታስተምር
ሕያው የታሪክ መጽሐፍ ናት!

ታሪክን እንማር፤ ከስህተታችንም እንንቃ!

#HistoryOfIslam #AlAndalus #IslamicSpain #GoldenAge #Cordoba #MuslimHistory
#EthiopianMuslims

(ይህን ማራኪ ታሪካዊ ጽሑፍ ሼር በማድረግ፣ እኛ ሙስሊሞች ምን አይነት የከፍታ ታሪክ እንደነበረን ለትውልዱ እናስታውስ!)

||
t.me/MuradTadesse
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
❤21👍7🔥5
⏺ የእህት አይላ ቻናል ነው ተቀላቀሉ 🤗

https://t.me/muslimah0085
🥰15❤10🔥5👍3
ሩፈይዳ አል-አስለሚያ የሴቶች ቂርአት ማዕከል

🔖 በሥራ ውጥረት፣ በትምህርት ወይም በቤተሰብ ኃላፊነት ምክንያት የጌታሽን ቃል (ቁርአንን) መማር ፈልገሽ ጊዜ አጥተሻል?

"ሩፈይዳ አል-አስለሚያ  የሴቶች ቂርአት ማዕከል ዘመኑ ያፈራውን ቴክኖሎጂ በመጠቀም ርቀትን አቅርቦና ጊዜን ቆጥቦ  ብቃት ባላቸው ሴት ኡስታዛዎች በቤትሽ ሆነሽ ምትማሪበትን እድል አመቻችቶልሻል  ።

የምንሰጣቸው ትምህርቶች እንደየተማሪው ደረጃ

> ለጀማሪዎች ቃዒዳ
> ነዘር (ቁርአንን ጥርት ባለ ተጅዊድ ማንበብ )
> ሂፍዝ
> ተጅዊድን ማስተካከል የሚችሉበት የሃለቃ ቂርአት
> የተጅዊድ ህጎች
> እንዲሁም አጫጭር መሰረታዊ ኩቱቦች

ለመመዝገብ ቻናላችንን ይቀላቀሉ 👇

® https://t.me/Rufeyda123
❤14👍7
▪️የኢርሻድ እቅበተ እምነት መስራች የሆነው ኡስታዛችን ሳላህ  ውይይቱ ከመከናወኑ በፊት  500 k የማስገባት ቻሌንጅ ተጀምሯል ሁላችንም ፕሮፋይል በማረግና ቪዲዮ በመስራት እናሰራጭ ባረከላሁ ፊኩም
🔥25👍11❤6
Forwarded from Sαlαh Responds ࿈ (Sαlαɦ 𝓩αiη⁷)
🕋 ከፍተኛ ላይክ ያገኘ ሰው፣ በነጻ ዑምራ ይሄዳል።

📊 አካውንታችንን ፎሎው የማስደረግ ቻሌንጅ ተጀምሯል። በዚህም መሠረት:-

1- ማንኛውም ሰው እርሱን ፎሎ ማድረግ እንዳለበት የሚገልጽ አጭር ነገር ተናግሮ ቪዲዮ ይሰራል።

2- በቪዲዮው ላይ የእርሱን Profile ፎቶ ተጠቅሞ እና ትክክለኛው አካውንት (197k ፎሎ ያለውን) Mention ያደርጋል።

🎁 በመጨረሻም ቪዲዮው ከፍተኛ Like ያገኘ ማንኛውም ሰው በነጻ ዑምራ ይሄዳል።
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
❤17👍4
የተበረዘው መፅሐፍ የቱ ነው ? ባይብል ወይስ ቁርዐን ? በሚል ውይይት ገብቶ አው መፅሐፍ ቅዱስ ተበርዟል ብሎ የጀመረ ተወያይ 👏😁
🤣25😁6
መፅሐፉ ተበርዟል ዋና ሃሳቡ ግን አልተበረዘም፡) ኧረ ዲያቆን 😄
😁31🤔1😢1
ሰማዕቱ ብራና vs ባይብል :)
😁18
🟠ቁርዐን ጥያቄ ማይነሳበት መሆኑን አስመስክረናል አላሁ አክበር ⚡️⚡️
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
👏38🥰5
አላሁ አክበር 🔥🔥
🔥29
ጉድ! ክርስቲያኖች እያበዱ ነው። 🤭
😁38❤3👍2
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
🟠ለዲያቆን ከጓደኞቹ የተሰጠው አስተያየት :)
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
🤣60😁21👍3
🟠ለሹብሃዎች በቂ ምላሽ በመስጠት የምናውቀው የወንድም ሁሴን ኸድር ቻናል በጣም ወሳኝ ከምላቸው ቻናሎች ውስጥ ነው ተቀላቀሉ  👇

https://t.me/iwnetlehullu1
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
❤13🔥3
🟠ከዚህ በፊት ባየናቸው ፅሁፎች በክርስትና ሴት ልጅ በግልፅ የአዕምሮ ጎዶሎ እንዲሁም የማመዛዘን ችግር ጭምር ያለባት እንደሆነችና በዚህም ምክንያት መመስከር መፍረድ ወጥታ መማርም ሆነ ማስተማር ወዘተ .... እንደማትችል አይተናል ። እስኪ ዛሬ እስልምና ላይ በዚህ ዙሪያ ለሚያነሱት ውሃ የማያነሳ ሙግት መልስ እንስጥ ...
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
🔥15👍2
በሴት ልጅ አዕምሮና ምስክርነት ዙሪያ የሚነሱ ትችቶች

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩህሩህ በጣም አዛኝ በሆነው

🟠የሐዲስን ትክክለኛ ዐውድ ባለመረዳት ከሚሰነዘሩ የተሳሳቱ  ትችቶች ውስጥ ሴት ልጅ የአዕምሮ ጎዶሎ ናት የሚለው ትችት ነው ።  በእስልምና አስተምህሮ ውስጥ "ናቂሳቱ ዐቅል" ሲባል የሚያመለክተው አጠቃላይ የማሰብ ችሎታን ሳይሆን፣  በተፈጥሮ ሂደት ውስጥ ሊከሰት የሚችልን  "የማስታወስ አቅም ድክመት" ነው። ይህም በንግድ ዕዳና  መሰል ወንዶች ሚዘወትሩባቸው ምስክርነቶች  ውስጥ ሊከሰት የሚችለውን የመርሳት እድል ሁለት ሴቶች በማድረግ  ለመከላከል እና ፍትህ እንዳይዛባ የተዘጋጀ የህግ ጥበቃ (Legal safeguard) ነው።

" የሴት ምስክርነት እንደ ግማሽ የወንድ ምስክርነት አይደለምን?’ እኛም ‘አዎን’ አልን። እሳቸውም ‘ይህ የሴት የአእምሮዋ  ጉድለት በመሆኑ ነው’ አሉ።"

📗Sahih al-Bukhari, 2658 

፨ ይህም ምስክርነት የሚገኘው  ሱረቱል በቀራ ሲሆን " አንዲቱ ብትረሳ አንደኛዋ ታስታውሳት ዘንድ ስለሚል የአዕምሮ ጉድለት የሚለው መርሳትን እንደሚወክል መረዳት ይቻላል ።

" ..فَرَجُلٌ وَامْرَأَتَانِ مِمَّن تَرْضَوْنَ مِنَ الشُّهَدَاءِ أَن تَضِلَّ إِحْدَاهُمَا فَتُذَكِّرَ إِحْدَاهُمَا الْأُخْرَىٰ ۚ ..."

​«...ከምስክሮችም የሆኑ አንድ ወንድ እና ሁለት ሴቶች ይሁኑ፤ (ይህም) አንዲቱ ብትረሳ ሌላይቱ ታስታውሳት ዘንድ ነው።»

📗ሱረቱል በቀራ 282

፨ ኢማም አል-ነወዊይ በሰሂህ ሙስሊም ሸርህ ላይ በግልጽ እንዳስቀመጡት፣ ይህ ጉድለት የሚባለው "የመያዝ/የማስታወስ ችሎታ" ጋር የተያያዘ ነው።

قوله : «أما نقصان العقل فشهادة امرأتين تعدل شهادة رجل تنبيه منه على ما وراءه وهو ما نبه الله تعالى عليه في كتابه بقوله تعالى : أن تضل إحداهما فتذكر إحداهما الأخرى أي إنهن قليلات الضبط،

"በአእምሮ መጉደልን በተመለከተ፡ የሁለት ሴቶች ምስክርነት የአንድ ወንድ ምስክርነት ጋር እኩል መሆኑ፣ ከዚህ በስተጀርባ ላለው ነገር ማስታወሻ ነው። ይህም አላህ በቅዱስ ቁርኣኑ ‘ከሁለቱ አንዷ ብትረሳ ሌላኛዋ እንድታስታውሳት’ ብሎ የገለጸው ነው። ይህም ማለት ሴቶች የማስታወስ (የመያዝ) አቅማቸው ደካማ ነው ማለት ነው።"

📗صحيح مسلم بشرح النووي، المجلد الأول، ص 59

፨ ዘመናዊ የሳይንስ ጥናቶች እንዳረጋገጡት፣ እርግዝናና መሰል ነገራቶች በሴቶች አእምሮ ላይ ተፅዕኖ ያሳድራል። ​በተለይ በሦስተኛው የእርግዝና ወር የመስማት #ማስታወስ ችሎታ፣ ትኩረት እና የአፈጻጸም ተግባራት ላይ መጠነኛ መዳከም ሊከሰት እንደሚችል ጥናቶች ያሳያሉ።

The results of this study revealed that the occurrence of mild impairment of auditory memory, attention and executive functions in the third trimester of pregnancy is consistent with the main hypothesis.

የዚህ ጥናት ውጤት እንደሚያሳየው፣ በእርግዝና ሦስተኛው ሶስት ወር ውስጥ የመስማት ችሎታ (auditory memory)፣ ትኩረት እና የአፈጻጸም ተግባራት (executive functions) መጠነኛ መዳከም መከሰቱ ከዋናው ግምት ጋር የሚጣጣም ነው።

📗Ali, S. A., Begum, T., Reza, F., Wan Rosilawati, W. R., & Wan Nor Azlen, W. M. (n.d.). Auditory Cognitive Function Assessment During Pregnancy: An Event-Related Potential and Neuropsychological Study. Chapter 6: Conclusion.

፨ ከንግድና መሰል ጉዳዮች ጋር የተያያዙ ምስክርነቶች ላይ ሴት 2 መሆኗ የተፈለገበት ምክንያት ሴት ልጅ ከንግድና መሰል ነገራቶች የራቀች በመሆኗ ቅድም ያነሳነው  የመርሳት ችግር ሊጎላ ስለሚችል ነው ።

፨ኢማም ኢብኑ ከሲር በታላቁ ተፍሲራቸው ላይ እንደገለጹት፤ 'ሴቶች ሁለት መሆን ያለባቸው በገንዘብ ነክ ንግድና መሰል ጉዳዮች እንደሆነ አስፍረዋል ።

فإن لم يكونا رجلين فرجل وامرأتان، وهذا إنما يكون في الأموال وما يقصد به المال»

"ወንዶች ሁለት ካልሆኑ (በምስክርነት ጊዜ)፣ አንድ ወንድ እና ሁለት ሴቶች ይሁኑ፤ ይህም የሚሆነው በገንዘብ ነክ ጉዳዮች እና ገንዘብን በሚመለከቱ ጉዳዮች ላይ ብቻ ነው"።

📗تفسير القرآن العظيم» للحافظ عماد الدين إسماعيل بن عمر بن كثير  سورة البقرة 282

፨የሴቶች ምስክርነት በሁለት መተካቱ አጠቃላይ አእምሯዊ አቅምን የሚለካ ሳይሆን፣ ከገንዘብ እና ከንግድ ውሎች ጋር በተያያዘ ሴቶች በብዛት ከነዚህ ነገራቶች የራቁ በመሆናቸው  ሊፈጠር የሚችለውን የመርሳት ክፍተት ለመቅረፍ የተቀመጠ ጥንቃቄ የተሞላበት ድንጋጌ ነው።   ከዚህ ውጭ ባሉ ጉዳዮች ማለትም በጡት ማጥባት፣ በሴቶች ተፈጥሮአዊ ክስተቶች እና በሌሎችም የቤት ውስጥ እውነታዎች ሴት ብቻዋን የምትሰጠው ምስክርነት ሙሉ በሙሉ ተቀባይነት እንዳለው 📗ሰሒሕ አል-ቡኻሪ (2659)ን ጨምሮ ሌሎች ማስረጃዎች ያረጋግጣሉ።

© https://t.me/MewedaComp
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
🔥11🥰9❤8👏1