Meweda | Comparison
1.9K subscribers
39 photos
15 videos
1 file
41 links
Faith through knowledge

[ እምነትን በእውቀት ]
Download Telegram
በክርስትና የሴት ልጅ መማርና ማስተማር መብትን በተመለከተ ባይብል ላይ የተቀመጡትን ጥቅሶች እኛን አይወክልም ለሚሉ ወገንታት የአባቶች ኢጅማዕ እንዳለው አሳይተን እናባርራለን😌
👍23🔥9😁8
የሴት ልጅ ማስተማር መብት በክርስትና

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩህሩህ በጣም አዛኝ በሆነው

▪️ መፅሐፍ ቅዱስ ሴት ከወንድ ያነሰች በመሆኗ ምክንያት ማስተማር እንደሌለባት የሚያመላክቱ ጥቅሶችን በግልፅ የሚያስቀምጥ ቢሆንም ፣ በዘመናዊ አብያተ ክርስቲያናት እና በተለያዩ የሚዲያ መድረኮች ይህንን መመሪያ «እኛ አይመለከተንም» በሚል ህጉን ሲጥሱ ይስተዋላል ። ይሁን እንጂ ይህ አቋም አብዛኞቹን የቤተክርስቲያን ጥንታዊ አበው አስተምህሮ የማይከተል እንዲሁም የመፅሐፍ ቅዱሱን አውድ ያላገናዘበ የሰዎችን ስሜት ለመጠበቅ ሲባል የተሰጠ ትርጓሜ በመሆኑ የጥንታዊ አበው ንግግሮችን እና የመፅሐፍ ቅዱሱን አውድ ባገናዘበ መልኩ በክርስትና አስተምህሮ ሴቶች የማስተማር ሚና እንደሌላቸው በአላህ ፍቃድ የምናይ ይሆናል።

📗 1ኛ ወደ ጢሞቴዎስ 2:11-12
••••••••••
¹¹ ሴት በጸጥታና በሙሉ መገዛት ትማር።
¹² ሴት ዝም እንድትል እንጂ እንድታስተምር ወይም በወንድ ላይ ሥልጣን እንዲኖራት አልፈቅድም፤

፨ይህንን ጥቅስ በተወሰኑ ሰዎች የተገደበ ነው የሚል ማስተባበያ ቢሰጡም እዛው 1 ኛ ጢሞትዮስ 2:13 ላይ የማታስተምርበትን ምክንያት ሲያስቀምጥ ከኋላ የተፈጠረች መሆኗን በመጥቀስ አለማስተማሯን ከተፈጥሮዋ ጋር ስለሚያቆራኘው ሴቶችን በጠቅላላ እንጂ የአንድን አከባቢን ሴቶች ብቻ ሊወክል አይችልም ።

📗 1ኛ ወደ ጢሞቴዎስ 2:13
••••••••••
¹³ ምክንያቱም አዳም ቀድሞ ተፈጥሯል፤ ከዚያም ሔዋን ተፈጠረች።

፨ በተመሳሳይ መልኩ ወደ  ቆሮንቶስ ሰዎች ላይ ያለውም ጥቅስ ይህንኑ የሚያጠናክር ሆኖ እናገኘዋለን ።

📗1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 14:34-35
••••••••••
³⁴ ሴቶች በጉባኤ ዝም ይበሉ፤ ሕግም እንደሚለው እንዲታዘዙ እንጂ እንዲናገሩ አልተፈቀደላቸውም፤
³⁵ ሴቶች ለማወቅ የሚፈልጉት አንዳንድ ነገር ካለ፣ ባሎቻቸውን በቤት ይጠይቁ፤ ምክንያቱም ሴት በጉባኤ መካከል ብትናገር የሚያሳፍር ነው።

፨ እነዚህ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች ሴቶችን በአጠቃላይ የሚመለከቱ እና የማስተማር ሚናን የሚከለክሉ መሆናቸውን  አብዛኛው የቤተክርስቲያን አበው በአጽንኦት ያስቀምጣሉ።

"It is not permitted to a woman to speak in the church; but neither (is it permitted her) to teach, nor to baptize, nor to offer, nor to claim to herself a lot in any manly function, not to say (in any) sacerdotal office."

"ለሴት በቤተክርስቲያን መናገር የተፈቀደ አይደለም፤ እንዲሁም ማስተማር፣ ማጥመቅ፣ መስዋዕት ማቅረብ ወይም ማንኛውንም የወንድ ተግባር ለራሷ መመደብ፣ በክህነት አገልግሎት ውስጥ መሳተፍም አልተፈቀደላትም።"

📗Tertullian, On the Veiling of Virgins, Chapter IX. In: Ante-Nicene Fathers, Volume IV, p. 33.

"Let the woman learn in silence; that is, let her not speak at all in the church; which rule he has also given in his Epistle to the Corinthians, where he says, It is a shame for women to speak in the church; and the reason is, that the law has made them subject to men."

"ሴት በዝምታ ትማር፤ ይህም ማለት በቤተክርስቲያን ውስጥ በፍጹም አትናገር ማለት ነው፤ ይህንን ደግሞ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች በጻፈው መልእክቱ ላይ እንደ ሕግ ሰጥቶታል፣ በዚያም 'ለሴቶች በቤተክርስቲያን መናገር እፍረት ነው' ይላል፤ ምክንያቱም ሕጉ ለወንዶች ተገዢ እንዲሆኑ አድርጓቸዋልና።"

📗The Homilies of S. John Chrysostom on the Epistles of St. Paul the Apostle to Timothy, Titus, and Philemon  Homily IX

፨እስካሁን ባየናቸው የመፅሐፍ ቅዱስ  ጥቅሶችና የቤተክርስቲያን አበው ትምህርቶች መሠረት  የሴቶች የማስተማር ሚና የተከለከለበት ዋና ምክንያት በአፈጣጠር ቅደም ተከተል እንዲሁም  በወንድ ላይ ባላቸው ተገዢነት ላይ ተመስርቶ በመሆኑ መፅሐፍ ቅዱስም ሆነ የቤተክርስቲያን አባቶች ለሴቶች ያላቸውን የወረደ አመለካከት የሚያሳይ ነው።

© https://t.me/MewedaComp
🔥17❤7👏7👍2
▪️ነገ ከምሽቱ 2:00
🔥29👍19❤8🥰1
"‏ مَنْ نَفَّسَ عَنْ مُؤْمِنٍ كُرْبَةً مِنْ كُرَبِ الدُّنْيَا نَفَّسَ اللَّهُ عَنْهُ كُرْبَةً مِنْ كُرَبِ يَوْمِ الْقِيَامَةِ وَمَنْ يَسَّرَ عَلَى مُعْسِرٍ يَسَّرَ اللَّهُ عَلَيْهِ فِي الدُّنْيَا وَالآخِرَةِ وَمَنْ سَتَرَ مُسْلِمًا سَتَرَهُ اللَّهُ فِي الدُّنْيَا وَالآخِرَةِ وَاللَّهُ فِي عَوْنِ الْعَبْدِ مَا كَانَ الْعَبْدُ فِي عَوْنِ أَخِيهِ"✨

📗 sahih muslim 2699a
🥰17❤10🍓6👌2🕊1🏆1
✍️ እንሆ የክረምት ንጽጽር ኮርስ ምዝገባ ተጀመረ🎉🎉🎉🎉

✸ የ6 ኪሎ ጀመዓ ከኢርሻድ ዕቅበተ-ኢስላም ግሩፕ ጋር በመተባበር ያዘጋጀው ልዩ የንፅፅር ትምህርት ምዝገባ መጀመሩን ሲያበስራቹ በታላቅ ደስታ ነው። ስልጠናው ተማሪዎች በትምህርት ሂደቱ በንጽጽር ዘርፍ ወሳኝ እና አንገብጋቢ የሆኑ ርእሶች ላይ ጥልቅ የሆነ እውቀትን እንዲይዙ፤ ጠቃሚ ልምድ እንዲያካብቱ አቅዶ የተነሳ ትልቅ ፕሮጀክት ነው። የሚሰጠው  በOnline እንደመሆኑ በማንኛውም ቦታ ሆነው መከታተል ይችላሉ።

ከታች በተቀመጠው ማጣሪያ ፎርም ቀድመው በመመዝገብ ቦታዎን ያስጠብቁ።

🔖 መመዝገቢያ ፎርም፦

╰┈➤• የወንዶች መመዝገቢያ

           ∘₊✧──────✧₊∘

╰┈➤• የእህቶች መመዝገቢያ

🪧 ማሳሰቢያ ፦  ማጣሪያው የሚካሄደው ፎርሙ ላይ በሚሞላው መረጃ ስለሆነ ተመዝጋቢዎች በጥንቃቄና በታማኝነት ሊሞሉ ይጠበቃል። 

የ6ኪሎ ጀመዓ ዳዕዋና ቂርዓት ሴክተር
ለማንኛውም ጥያቄ @Valid_Qireat_bot

@AAU6kilojemea
❤11👍7😢3
🔥13👍8❤4
Forwarded from Sαlαh Responds ࿈
🥷

ወንድም ኢምራን ትናንት ማታ 4:00 Live ከፍቶ፣ ሌሊቱን ሙሉ ተቀምጦ፣ ነግቶ አሁንም ሳያቋርጥ እስከ ቀኑ 7:00 ላይቭ ላይ ነው። በጥቅሉ ወደ አራት ሰዎች ሸሀዳ ይዘዋል።

☑️Sαlαh Responds😘

➡️ t.me/mahircomp123
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
👏23👍12❤7🔥6
"وَأَطِيعُوا۟ ٱللَّهَ وَرَسُولَهُۥ وَلَا تَنَٰزَعُوا۟ فَتَفْشَلُوا۟ وَتَذْهَبَ رِيحُكُمْ ۖ وَٱصْبِرُوٓا۟ ۚ إِنَّ ٱللَّهَ مَعَ ٱلصَّٰبِرِينَ"

Al-Anfal [8:46]
❤19🥰6👌3
"حَدَّثَنِي يَحْيَى بْنُ يُوسُفَ، أَخْبَرَنَا أَبُو بَكْرٍ ـ هُوَ ابْنُ عَيَّاشٍ ـ عَنْ أَبِي حَصِينٍ، عَنْ أَبِي صَالِحٍ، عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ ـ رضى الله عنه ـ أَنَّ رَجُلاً، قَالَ لِلنَّبِيِّ صلى الله عليه وسلم أَوْصِنِي‏.‏ قَالَ ‏"‏ لاَ تَغْضَبْ ‏"‌‏.‏ فَرَدَّدَ مِرَارًا، قَالَ ‏"‏ لاَ تَغْضَبْ ‏"‌‏.‏"
  Sahih al-Bukhari, 6116
❤11👌10🥰5🔥1
ታላቁ የቲክቶክ መድረክ ነገ ሰኞ ከምሽቱ 3:00 ላይ ነው!

ስለሙስሊም ተማሪዎች የመብት ጥያቄ ታሪካዊ ዳራ፤ ሕጋዊ መሠረት እና አሁናዊ ሁኔታ ከመፍትሔ ጋር በጥልቀት ይዳሰሳል። የድምፃችን ይሰማው ታጋይ ሙባረክ አደም፤ ጠበቃው ሙስጠፋ ሺፋ፤ የንፅፅር መምህሩ የሕያ ኢብኑ ኑሕ፤ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ሙስሊም ተማሪዎች ሕብረት ፀሐፊው ሁሴን ዩሱፍ በመድረኩ ላይ ሀሳቦቻቸውን ያንፀባርቃል።

፨ ፖስተሩን በስቶሪዎቻችን ላይ እናጋራ፤ ፕሮፋይልም እናድርግ
፨ የዩኒቨርስቲ ጀመዓዎች በቻናሎቻችሁ ላይ አጋሩ
፨ የሀይስኩል ጀመዓዎች መልዕክቱን አድርሱ
፨ በሀገር ውስጥም ሆነ በውጭ ሀገር ያላችሁ ተፅዕኖ ፈጣሪ ስብዕናዎች፤ ኡስታዞች እና ዳዒዎች መልዕክቱን ለሁሉም አድርሱ

ሁሉም ተጋባዥ ነው። አጀንዳው የሁሉም ነውና ሁሉም ይገኝ። ተማሪ፣ የተማሪ ወላጅ፣ መምህር፣ የመንግስት ሰራተኛ ወዘተ ... ማንም እንዳይቀር።

🗓 ቀን፡ ሰኞ፣ ሰኔ 22 (Monday, 29 June)
⏰ ሰዓት፡ ከምሽቱ 03፡00 ሰዓት

እውቀትን መፈለግ መብት ነው፤ እምነትንም በክብር መተግበር እንዲሁ!

የቲክቶክ ገፃችንን Follow በማድረግ ዝግጅቱን ይጠብቁ፦

https://www.tiktok.com/@aaumsu

ጥያቄ አለን _ ፍትሐዊ መልስ እስኪመጣ ! ! !

© aaumsu

@AAU6kilojemea
👍10🔥5❤2
❤1
Meweda | Comparison
Photo
ለወገናችን የተሰጠ ምላሽ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩህሩህ በጣም አዛኝ በሆነው

▪️ወገናችን መልስ ለመስጠት መሞከርህ የሚበረታታ ቢሆንም የሰጠሃቸው ምላሾች ግን የሚጨበጥ ሃሳብ የጎደላቸው ሆነው አግኝቻቸዋለው ይህ እንዳለ ሆኖ ትንሽ መልስ ሚመስል ነገር ያላቸውን ሃሳቦች አሜን ብለው ለሚቀበሉ ወገኖች ሲባል እንያቸው ።

፨ አውግስጢኖስ ላይ ካነሳኸው ሃሳብ ስነሳ    Questions on the Heptateuch፣ መጽሐፍ 1፣ አንቀጽ 153 ላይ ባሰፈረው ሃሳብ፣ ሴቶች ለባሎቻቸው መገዛት ያለባቸው ‘weaker brain’  በመሆናቸው እንደሆነ በግልፅ አስቀምጧል።  የቤተሰብን አስተዳደር ስርዐት ለማስረዳት በሚል ሰበብ ሴቷን የአዕምሮ ጎዶሎ አድርጎ መፈረጁ ተቀባይነት የለውም፤  ምክንያቱም የቤተሰብን አስተዳደራዊ መዋቅር ለማሳየት ወይም ለማስረዳት ሲባል ሴትን እንደ ዝቅተኛ አካል መፈረጅ ወይም ማንነቷን ማሳነስ አግባብነት የለውም።

፨ ቅዱስ አውግስጢኖስ በThe Trinity፣ መጽሐፍ 12፣ ምዕራፍ 7 ላይ ሴትና ወንድ እኩል አዕምሯዊ አቅም አላቸው በማለት ተናግሯል በሚል የቀረበው ሃሳብ፣ ከጽሁፉ ዐውድ  ጋር ፈጽሞ የማይጣጣም በመሆኑ፣ በጥቅሱ ላይ የተሰጠው ትርጓሜ ከእውነታው የራቀ ነው።"

፨ "ፅሁፉ ትኩረቱን ያደረገው  የሰው አዕምሮ የእግዚአብሔር መልክ (Image of God) ሊባል የሚችለው ዘላለማዊ እና መንፈሳዊ እውነታዎች ላይ እንደሆነ እና ፣ ይህ በመንፈሳዊነት የመጠመድ አቅም እና በውስጡ ያለው መለኮታዊ መልክ ለወንዶች ብቻ የተወሰነ ሳይሆን፣ ለሴቶችም ጭምር የተሰጠ መሆኑን የሚያሳይ ፅሁፍ ነው እዛው ከፍ ብለን ስንመለከት የሰው አዕምሮና የእግዝኣብሔር መልክ ሚለውን በዚህ መልኩ ያብራራልናል።

"As we said of the nature of the human mind, that both in the case when as a whole it contemplates the truth it is the image of God; and in the case when anything is divided from it, and diverted in order to the cognition of temporal things; nevertheless on that side on which it beholds and consults truth, here also it is the image of God, but on that side whereby it is directed to the cognition of the lower things, it is not the image of God"

እንደ ተናገርነው ስለ ሰው አእምሮ ተፈጥሮ፣ አእምሮ በአጠቃላይ እውነታን ሲያሰላስል የእግዚአብሔር መልክ ነው፤ እንዲሁም ከእውነታው የተወሰነ ክፍል ተከፍሎ ወደ ጊዜያዊ ነገሮች እውቀት ሲዘነብልም እንኳ፣ እውነታን በሚመለከትበትና በሚያማክርበት በዚያ አቅጣጫ የእግዚአብሔር መልክ ነው። ነገር ግን ወደ ዝቅተኛ ነገሮች እውቀት በሚመራበት በዚያ በኩል የእግዚአብሔር መልክ አይደለም»።

📗 Saint Augustine's "The Trinity" (De Trinitate), Book 12, Chapter 7.

"so that the image of God may remain on that side of the mind of man on which it cleaves to the beholding or the consulting of the eternal reasons of things; and this, it is clear, not men only, but also women have.

ይህም የእግዚአብሔር መልክ በሰው አእምሮ ውስጥ ዘላለማዊ የሆኑ የነገሮችን ምክንያቶች በሚያይበት ወይም በሚያማክርበት ክፍል ውስጥ እንዲኖር ነው። ይህ ደግሞ ወንዶች ብቻ ሳይሆኑ ሴቶችም እንዳሏቸው ግልጽ ነው»።

📗 Saint Augustine's "The Trinity" (De Trinitate), Book 12, Chapter 7.

፨ ከላይ እንደተመለከትነው  ወገናችን ከዐውዱ ውጪ ያመጣው ሀሳብ የሰው አዕምሮ በዘላለማዊና መንፈሳዊ ነገሮች ላይ ሲያተኩር የሚኖረው የእግዝኣብሔር መልክ ለወንዶች ብቻ ሳይሆን ለሴቶችም እንዳላቸው የሚያሳይ ክፍል እንጂ በምድራዊ አስተሳሰብ እኩል የአዕምሮ ብቃት አላቸው የሚለውን የሚያሲዝ ፅሁፍ በፍፁም አይደለም።

፨ አሳ ጎርጓሪ ዘንዶ ያወጣል አሉ  ባይሆን ሴት ብቻዋን ያለ ወንድ የእግዝኣብሔር መልክ ልትባል አትችልም ይለናል ፡)

that the woman together with her own husband is the image of God, so that that whole substance may be one image; but when she is referred separately to her quality of help-meet, which regards the woman herself alone, then she is not the image of God; but as regards the man alone, he is the image of God as fully and completely as when the woman too is joined with him in one.

ሴትየዋ ከራሷ ባል ጋር በአንድነት የእግዚአብሔር መልክ ናት፤ በዚህም አጠቃላይ የሰው ልጅ ባሕርይ አንድ መልክ ሊሆን ይችላል። ነገር ግን ሴትየዋ ለብቻዋ 'ረዳትነት'  ከሚለው ባሕርይዋ ጋር በተያያዘ ስትጠቀስ፣ በዚያ ጊዜ የእግዚአብሔር መልክ አይደለችም። በሌላ በኩል፣ ወንዱ ብቻውን ሲታይ፣ ሴትየዋም ከእርሱ ጋር በአንድነት በተጣመረችበት ጊዜ እንደነበረው ሁሉ፣ ሙሉ እና ፍጹም በሆነ መልኩ የእግዚአብሔር መልክ ነው።"

📗 Saint Augustine's "The Trinity" (De Trinitate), Book 12, Chapter 7.

© https://t.me/MewedaComp
👍14❤5🔥4😁4👎1
❤37🔥10🥰9🤩2👏1
የመጅሊስ አካላት እና የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሰላምና ፀጥታ ኃላፊ የሆነችው ወ/ሮ ሊዲያ ቦታው ድረስ በአካል ተገኝተው፣ የተማሪዎች ጅልባብና ኒቃብ መሬት ተወርውሮ፤ በምትኩ ተማሪዎች  ለብሰውት ሲማሩ በነበሩት ማስክ በልመና መግባት ማለት ..... 💔
💔54😭32❤6🤬6👍2😁2🤯1
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
▪️ቁርዐን ሴትን ልጅ በመምታት ያዛል ??

©  https://t.me/MewedaComp
❤37👏8👍6😁2🔥1
🏷 وَمَنْ سَلَكَ طَرِيقًا يَلْتَمِسُ فِيهِ عِلْمًا سَهَّلَ اللَّهُ لَهُ بِهِ طَرِيقًا إِلَى الْجَنَّةِ وَمَا اجْتَمَعَ قَوْمٌ فِي بَيْتٍ مِنْ بُيُوتِ اللَّهِ يَتْلُونَ كِتَابَ اللَّهِ وَيَتَدَارَسُونَهُ بَيْنَهُمْ إِلاَّ نَزَلَتْ عَلَيْهِمُ السَّكِينَةُ وَغَشِيَتْهُمُ الرَّحْمَةُ وَحَفَّتْهُمُ الْمَلاَئِكَةُ وَذَكَرَهُمُ اللَّهُ فِيمَنْ عِنْدَهُ

[ Sahih Muslim, 2699 a ]
🥰16❤6👍6
🏷 وَمَا زَادَ اللَّهُ عَبْدًا بِعَفْوٍ إِلاَّ عِزًّا وَمَا تَوَاضَعَ أَحَدٌ لِلَّهِ إِلاَّ رَفَعَهُ اللَّهُ ‏
[Sahih Muslim, 2588]
❤14🥰9👍5
🤎✨
🥰24❤8🤩5❤‍🔥2🍓2🤗1
🏷 ሁለት ሴቶች በወሊድ ሰዐት የሚያጋጥማቸው የስነ-ልቦና ሁኔታ ከእምነታቸው አንፃር ሲታይ:

፨ ክርስቲያኗ ሴት በጭንቅ ውስጥ ሆና ወደ መፅሐፏ ስታስብ ...

📔ኦሪት ዘፍጥረት 3:16
••••••••••
¹⁶ ሴቲቱንም እንዲህ አላት፤ “በምጥ ጊዜ ጭንቅሽን አበዛለሁ፤ በሥቃይም ትወልጃለሽ፤ ፍላጎትሽም ወደ ባልሽ ይሆናል፤ እርሱም የበላይሽ ይሆናል።”

፨ ሙስሊሟ እንስት ወደ እምነቷ ስትመለስ በወሊድ ጊዜ የሚሰማትን የ ሞት ስጋት በማርገብ ፣ ብትሞት እንኳን ሰማዕት እንደምትሆን ስለሚነግራት በውስጧ የመረጋጋት ስሜት ይፈጠራል።

[...وَالْمَرْأَةُ تَمُوتُ بِجُمْعٍ شَهِيدٌ ‏]

[...እናም በወሊድ ምክንያት (በፅንስ ወይም በወሊድ ሂደት) የምትሞት ሴት ሰማዕት ናት።'"]

📔Sunan Abi Dawud, 3111

የሴት ልጅን የመውለድ ተፈጥሮአዊ ሂደት በማክበር፣ በዚያ ሂደት ሕይወቷ የሚያልፍ ሴት የሰማዕትነት ደረጃ እንደሚኖራት የደነገገው ብቸኛው እምነት ኢስላም 🤎
❤62👍18🕊6👏4🤝2