Forwarded from ሙከሚል የንፅፅር ቤተ መጽሐፍ (𓆩𝄽Mukamil𝄽𓆪)
አሰላሙአለይኩም ወራህመቱላሂ ወበረካቱ
እህት ወንድሞች አንድ ነገር ላስቸግራቹ ነው
ለአላህ ብላቹ ተባበሩኝ
አንዲት እህት ስደት ከመጣች ሁለት አመት ሆኗታል ግን በጣም እሚያሳዝነው አሰሪዋ ጠንቋይ ናትና ልጅታን ምንም ነገር እንዳታቅ አድርጋ አፍዝዛታለች እናም ይችህ እህት አላህ ዳኚ ሲላት ዝምብላ ከቤቱ ትወጣለች ከዛም ሲደክማት መንገድ ላይ ቁጭ ትላለች ከዛም አንድ ሱዳናዊ ግለሰብ ያያታል ሲያያት ግን ልጅቷ ላይ ችግር እንዳለ ይረዳና ጠጋ ብሎ ሲጠይቃት ተስፋን የሚያስቆርጡ ንግግሮችን ትመልስለታለች እሱም ችግር እንዳለ ይረዳና ያለውን ገንዘብ ሰጣትና ሪያድ ኢንባሲ ብላ እንድትሳፈር ተባበራት ከዛም ይችህ እህት ወደ ኢንባሲው ከገባች ቦሀላ ፈዛ ቁጭ ባለችበት አንድ ሀበሻዊ ያገኛታል ከዛም እነደመጀመሪያው ገለሰብ ሲጠይቃት ተመሳሳይ መልስ መለሰችለት እና ይችህ እህት ስትጠየቅ ምታቀው ወላሂ ስሟንና የአባቷን ስም ብቻ ነው ምታቀው 2ት አመት ቤተሰብን ሳታወራ ቆይታለች ቤተሰቦቿ ይኑሩ አይኑሩ አንድ ምታቀው ነገር የለም የት እንደነበረችኳን ስንጠይቃት ምታስታውሰው ነገር የለም እና አስብት እናት የልጇን ድምፅ ሀለት አመት ሳትሰማ ሞታለች ብላ ቁርጧን አላውቀች ሁሌ ልባ እንደተጠለጠለ ወላሂ ይከብዳል ልጅቱም እናት አባትን የወንድም እህቶቿን ድምፅ ሳትሰማ ጭራሽ ስማቸውን እስከመርሳት ድርስ እና ውንድምና እህቶች ሼር በማድረግ ተባበሩኝ በዝች ልጅ ቦታ እራሳችንን አስቀምጠን እናስብ
የልጅቷ ስም ሙኒራ አብደላህ ትባላለች
የትወልድ ባታ ጉንችሬ ልዩ ስሙ ኡፍጠሬ ሚባል ቦታ ነው ብላናለች ባረከላሁፊኩም ተባበሩን ወላጆች ልጆቻቹን እያሰባቹ ወደዃላ አትበሉብን
ያገኘ ካለ በዚህ ስልክ ተባበሩን 0550745238
የቻናል ባለቤቶች ተባበሩን

👍13❤7😢1
Forwarded from Pk(ታላቁ አብርሐም) official channel
አፕሊኬሽኑን ለማግኘት
👉 https://t.me/pk_talaku/15
ለመመዝገብ ይህንን ይመልከቱ
👉 https://t.me/pk_talaku/18
የክፍያ አከፋፈል ጋር በተገናኘ ይህንን ተመልከቱ
👉 https://t.me/pk_talaku/25
አፕሊኬሽኑ አልወርድላቹህ ላላቹህ ይህን ይመልከቱ
👉 https://t.me/pk_talaku/48
በPaypal ክፍያ ለምትፈፅሙ ለአንድ መፅሐፍ
👉 https://t.me/pk_talaku/51
ለPaypal ከፋዮች ብዙ ለመግዛት
👉 https://t.me/pk_talaku/52
ማንኛውም ጥያቄ ካላቹህ pkን ለማናገር
👉 t.me/pk_talaku?direct
👉 https://t.me/pk_talaku/15
ለመመዝገብ ይህንን ይመልከቱ
👉 https://t.me/pk_talaku/18
የክፍያ አከፋፈል ጋር በተገናኘ ይህንን ተመልከቱ
👉 https://t.me/pk_talaku/25
አፕሊኬሽኑ አልወርድላቹህ ላላቹህ ይህን ይመልከቱ
👉 https://t.me/pk_talaku/48
በPaypal ክፍያ ለምትፈፅሙ ለአንድ መፅሐፍ
👉 https://t.me/pk_talaku/51
ለPaypal ከፋዮች ብዙ ለመግዛት
👉 https://t.me/pk_talaku/52
ማንኛውም ጥያቄ ካላቹህ pkን ለማናገር
👉 t.me/pk_talaku?direct
👍5❤1🍓1
◆ 1 ሒጃብ :- በእስልምና አስተምህሮ መሠረት ሒጃብ ሴቶችን ከተለያዩ ጥቃቶች ለመከላከል የተደነገገ መሆኑን ሱረቱል አህዛብ በግልፅ ያስቀምጥልናል ።
يَٰٓأَيُّهَا ٱلنَّبِىُّ قُل لِّأَزْوَٰجِكَ وَبَنَاتِكَ وَنِسَآءِ ٱلْمُؤْمِنِينَ يُدْنِينَ عَلَيْهِنَّ مِن جَلَٰبِيبِهِنَّ ۚ ذَٰلِكَ أَدْنَىٰٓ أَن يُعْرَفْنَ فَلَا يُؤْذَيْنَ ۗ وَكَانَ ٱللَّهُ غَفُورًۭا رَّحِيمًۭا
አንተ ነቢዩ ሆይ! ለሚስቶቸህ፣ ለሴቶች ልጆችህም፣ ለምእምናን ሚስቶችም ከመከናነቢያዎቻቸው በላያቸው ላይ እንዲለቁ ንገራቸው፡፡ ይህ እንዲታወቁና (በባለጌዎች) እንዳይደፈሩ ለመኾን በጣም የቀረበ ነው፡፡ አላህም መሓሪ አዛኝ ነው፡፡ [ አል- አህዛብ 59]
◆ 2 አይንን መስበር :- ለወንጀል ሁሉ የመጀመሪያው መንስኤ እይታ እንደመሆኑ መጠን ኢስላም ወንዶችን አይናቸውን መስበር እንዲሁም ዝሙትን አለ መቅረብ እንዳለባቸው ያዛል ።
قُل لِّلْمُؤْمِنِينَ يَغُضُّوا۟ مِنْ أَبْصَٰرِهِمْ وَيَحْفَظُوا۟ فُرُوجَهُمْ ۚ ذَٰلِكَ أَزْكَىٰ لَهُمْ ۗ إِنَّ ٱللَّهَ خَبِيرٌۢ بِمَا يَصْنَعُونَ
ለምእመናን ንገራቸው፡- ዓይኖቻቸውን (ያልተፈቀደን ከማየት) ይከልክሉ፤ ብልቶቻቸውንም ይጠብቁ፤ ይህ ለነሱ የተሻለ ነው፤ አላህ በሚሠሩት ሁሉ ውስጥ ዐዋቂ ነው፡፡ [አን- ኑር 30]
◆ 3 ባዕድ የሆኑ ወንድና ሴት በአንድ ክፍል ውስጥ መገለልን መከልከል :- የአብዛኛው ሴቶች ጥቃት ትኩረት ባልተሰጠው በመጓጓዣዎች እንዲሁም በቤቶች ውስጥ መገለሎች የሚከሰት ሲሆን ኢስላም ይሄንን መስመር ዘግቶታል።
وَلاَ يَدْخُلُ عَلَيْهَا رَجُلٌ إِلاَّ وَمَعَهَا مَحْرَمٌ
" ከርሷ ጋር መሕረም (አብሮ መሆን የተፈቀደለት የቅርብ ዘመድ) ከሌለ በቀር በእርሷ ላይ ባዕድ ወንድ አይገባም " [ ሰሂህ አል-ቡኻሪ 1862]
◆ 4 ሴት ልጅ ረጅም ጉዞን ያለ መሕረም (አብሮ መሆን የተፈቀደለት የቅርብ ዘመድ) ከሌለ ብቻዋን መጓዝን ከልክሏል :- ሴቶች ስደት ላይ እንዲሁም በተለያዩ ጉዞዎች ላይ የሚደርስባቸውን አሰቃቂ ጥቃት ኢስላም አስቀድሞ የዚህንም መንገድ በመዝጋት አብሯት ሚጠብቃት መሕረም ( አብሮ መሆን የተፈቀደለት የቅርብ ዘመድ ) እንዲኖር ያዛል ።
لاَ تُسَافِرِ الْمَرْأَةُ إِلاَّ مَعَ ذِي مَحْرَمٍ
ሴት ከመሕረሟ ( አብሮ መሆን የተፈቀደለት የቅርብ ዘመድ ) ጋር እንጂ አትጓዝ (ጉዞ አታድርግ ) [ሰሂህ አል-ቡኻሪ 1862]
◆5 የአባት ጥበቃ :- ሴት ልጅ ከማግባቷ በፊት በጣም ፈተናዎች ሚበዙባት ግዜ እንደመሆኑ ለሴት ልጆች የተለየ ጥበቃ ስለሚያስፈልጋቸው የአላህ መልዕክተኛ ሰ.ዐ.ወ ሁለት ሴት ልጆችን ጠብቆና ተንከባክቦ ለቁም ነገር ያበቃን አባት እኔና እሱ በጀነት እንዲህ ነን በማለት ጣቶቻቸውን በማጣመር በጀነት ከሳቸው ጋር ቅርብ እንደሚሆን አበስረዋል ።
عَالَ جَارِيَتَيْنِ حَتَّى تَبْلُغَا جَاءَ يَوْمَ الْقِيَامَةِ أَنَا وَهُوَ " . وَضَمَّ أَصَابِعَهُ .
ሁለት ሴት ልጆችን እስኪደርሱ በአግባቡ የተንከባከበና ያሳደገ ሰው ፣ የትንሳኤ ቀን እኔና እርሱ እንደዚህ ነን ( ብለው ጣቶቻቸውን አጣመሩ) [ ሰሂህ ሙስሊም 2631]
© https://t.me/MewedaComp
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
❤25🥰9👍4💯3😇1
Forwarded from عبدالفتاح🖋️ Abdulfetah
የዑመር ኢብኑል ኸጧብ🤎 አገልጋይ የነበረው አስለም እንዲህ ሲል ይተርካል:
በአንድ ሌሊት ከዑመር ኢብኑ አል-ኸጣብ🤎 ጋር የሕዝባቸውን ሁኔታ ለመቃኘት ከመዲና ወጥተን ጋር ወደ ሐረቱ-ዋቂም ወደተባለ ስፍራ አመራን። ሱራር በተባለ ቦታ ስንደርስ በሩቅ እሳት ታየን። ዑመርም «አስለም ሆይ! ብርዱና ሌሊቱ ያስቆማቸው መንገደኞች ይታዩኛል፤ ወደ እነሱ እንሂድ» አሉኝ። በፍጥነት ስንቀርብ አንዲትን እናት ከሕፃናት ልጆቿ ጋር አገኘን፤ እሳቱ ላይ ድስት ተጥዷል፣ ልጆቿም ያለቅሳሉ።
ዑመርም🤎 «አሠላሙ ዐለይኩም ያ አሥሐበድ-ደውእ (የብርሃኑ ባለቤቶች)» አሉ — «የእሳቱ ባለቤቶች» ማለትን ጠልተው ነው።
እሷም «ወዐለይኩም አሠላም» አለች።
ዑመር🤎 «ወደ እናንተ ልቅረብ (ልጠጋ)?» ሲሉ ጠየቁ።
ሴቲቱም «በበጎ ከሆነ ቅረብ፣ ካልሆነ ግን ተወን» አለች።
ቀረብ ብለውም «ምን አጋጠማችሁ?» አሏት።
እሷም «ሌሊቱና ብርዱ ጉዟችንን አሰናከለን» አለች።
ዑመር «እነዚህ ሕፃናት ለምን ያለቅሳሉ?» አሏት።
«በረሃብ ምክንያት ነው» አለች።
«በዚህ ድስት ውስጥ ያለው ምንድን ነው?» ሲሉ ጠየቋት።
«ልጆቹ እስኪተኙ እያፈላሁ የማታልልበት ውኃ ነው፤ አላህ በእኛና በዑመር መካከል ይፍረድ!» አለች።
ዑመርም «አላህ ይዘንልሽ! ዑመር የእናንተን ሁኔታ እንዴት ሊያውቅ ይችላል?» አሏት።
እሷም «የእኛን ጉዳይ ተረክቦ ከዚያ በእኛ ይዘናጋል?» ብላ መለሰች።
በንግግሯ የደነገጡት ዑመር🤎 «ተከተለኝ እንሂድ!» አሉኝ። በፍጥነት ወደ ዱቄት ማከማቻ ቤት (ዳሩድ-ደቂቅ) ሄድን። አንድ የዱቄት ከረጢትና የስጋ ስብ አውጥተው «በጀርባዬ ላይ ጫንልኝ» አሉኝ። እኔም «እኔ ልሸከምልዎ?» ብላቸው «በቂያማ ቀን ወንጀሌን ትሸከምልኛለህ?» አሉኝ በቁጣ። በጀርባቸው ላይ ጫንኩላቸውና በፍጥነት ወደ እናትየው ተመለስን።
ዑመር🤎 የዱቄቱንና የሥቡን ጥቂት ክፍል ድስቱ ውስጥ አድርገው «እኔ አማስልልሻለሁ፤ አንቺ ዱቄቱን ነስንሺልኝ» አሏት። ከድስቱም ሥር እሳቱን እየነፉ ያቀጣጥሉ ጀመር፤ ከዚያም ድስቱን አወረዱት።
ቀጥሎም፡ «የሚበሉበት እቃ አምጪልኝ» አሏት፤ ሰፊ እቃ (ሳህን) አቀበለቻችውና ምግቡን አደረጉላት። ከዚያም ለሴቲቱ፡ «አንቺ መግቢያቸው፤ እኔ ደግሞ አቀዝቅዝላቸዋለሁ» አሏት። እስኪጠግቡ ድረስ ማብላታቸውን አላቆሙም፤ የቀረውንም ምግብ እሷ ዘንድ ትተውላት ተነሱ፤ እኔም አብሬ ተነሣሁ።
ሴቲቱም፡ «አላህ መልካም ምንዳህን ይክፈልህ! ከምእመናን መሪ (ከዑመር) ይልቅ ለዚህ ሥልጣን የተገባኸው አንተ ነበርክ» አለች።
እርሳቸውም፡ «ወደ ምእመናን መሪ ዘንድ በመጣሽ ጊዜ መልካም ነገርን ተናገሪ፤ አላህ ካለ እዚያ ታገኚኛለሽ» አሏት።
ከዚያም ከእሷ ዘወር ብለው ፈቀቅ አሉና በርከክ ብለው ተቀመጡ።
እኔም፡ «ከዚህ ሌላ የምናከናውነው ጉዳይ አለንኮ» አልኳቸው፤ እርሳቸው ግን ምንም አልመለሱልኝም። ህፃናቱ ሲጫወቱና ሲስቁ፣ ከዚያም ተኝተው እስኪረጉ ድረስ ይመለከቷቸው ነበር።
ከዚያም፡ «አስለም ሆይ! ረሀብ አሳድሯቸውና አስለቅሷቸው ነበር፤ ስለዚህ ያየሁትን ደስታና እርጋታ ሳላይ መመለስ አልፈለግኩም ነበር» አሉኝ።» ይለናል አስለም።
በንጋታው እናትየው ወደ መዲና ሄዳ የዑመርን ማረፊያ ጠይቃ ገባች። ያ ማታ የረዳት ሰው አሚሩል ሙእሚኒን ተብሎ ከሶሐቦች መካከል ተቀምጦ ባየች ጊዜ ዑመር መሆኑን አውቃ ስጋት ያዛት።
ዑመርም🤎 «አንቺ እናት ሆይ! ምንም ስጋት አይግባሽ፤ በደልሽን ከአንቺ ልገዛሽ እንጂ ሌላ አይደለም፣ በስንት ልግዛሽ?» አሏት። በአርባ ድርሃም ከተስማሙ በኋላ ለፀሐፊያቸው «በርግጥም ዑመር ከዚች እናት በደሏን በአርባ ድርሃም ገዝቷል» ብለው እንዲጽፍ አዘዙ። ዐሊይንና ዑሥማንን (ረ.ዐ) ምስክር አድርገው ደብዳቤውን ለሶሐቦች በመስጠት « በሞትኩ ጊዜ ይህን ደብዳቤ ከከፈኔ መካከል አድርጋችሁ ቅበሩኝ፤ አላህን በእሱ እንድገናኘው» አሉ።
በአንድ ሌሊት ከዑመር ኢብኑ አል-ኸጣብ
ዑመርም
እሷም «ወዐለይኩም አሠላም» አለች።
ዑመር
ሴቲቱም «በበጎ ከሆነ ቅረብ፣ ካልሆነ ግን ተወን» አለች።
ቀረብ ብለውም «ምን አጋጠማችሁ?» አሏት።
እሷም «ሌሊቱና ብርዱ ጉዟችንን አሰናከለን» አለች።
ዑመር «እነዚህ ሕፃናት ለምን ያለቅሳሉ?» አሏት።
«በረሃብ ምክንያት ነው» አለች።
«በዚህ ድስት ውስጥ ያለው ምንድን ነው?» ሲሉ ጠየቋት።
«ልጆቹ እስኪተኙ እያፈላሁ የማታልልበት ውኃ ነው፤ አላህ በእኛና በዑመር መካከል ይፍረድ!» አለች።
ዑመርም «አላህ ይዘንልሽ! ዑመር የእናንተን ሁኔታ እንዴት ሊያውቅ ይችላል?» አሏት።
እሷም «የእኛን ጉዳይ ተረክቦ ከዚያ በእኛ ይዘናጋል?» ብላ መለሰች።
በንግግሯ የደነገጡት ዑመር
ዑመር
ቀጥሎም፡ «የሚበሉበት እቃ አምጪልኝ» አሏት፤ ሰፊ እቃ (ሳህን) አቀበለቻችውና ምግቡን አደረጉላት። ከዚያም ለሴቲቱ፡ «አንቺ መግቢያቸው፤ እኔ ደግሞ አቀዝቅዝላቸዋለሁ» አሏት። እስኪጠግቡ ድረስ ማብላታቸውን አላቆሙም፤ የቀረውንም ምግብ እሷ ዘንድ ትተውላት ተነሱ፤ እኔም አብሬ ተነሣሁ።
ሴቲቱም፡ «አላህ መልካም ምንዳህን ይክፈልህ! ከምእመናን መሪ (ከዑመር) ይልቅ ለዚህ ሥልጣን የተገባኸው አንተ ነበርክ» አለች።
እርሳቸውም፡ «ወደ ምእመናን መሪ ዘንድ በመጣሽ ጊዜ መልካም ነገርን ተናገሪ፤ አላህ ካለ እዚያ ታገኚኛለሽ» አሏት።
ከዚያም ከእሷ ዘወር ብለው ፈቀቅ አሉና በርከክ ብለው ተቀመጡ።
እኔም፡ «ከዚህ ሌላ የምናከናውነው ጉዳይ አለንኮ» አልኳቸው፤ እርሳቸው ግን ምንም አልመለሱልኝም። ህፃናቱ ሲጫወቱና ሲስቁ፣ ከዚያም ተኝተው እስኪረጉ ድረስ ይመለከቷቸው ነበር።
ከዚያም፡ «አስለም ሆይ! ረሀብ አሳድሯቸውና አስለቅሷቸው ነበር፤ ስለዚህ ያየሁትን ደስታና እርጋታ ሳላይ መመለስ አልፈለግኩም ነበር» አሉኝ።» ይለናል አስለም።
በንጋታው እናትየው ወደ መዲና ሄዳ የዑመርን ማረፊያ ጠይቃ ገባች። ያ ማታ የረዳት ሰው አሚሩል ሙእሚኒን ተብሎ ከሶሐቦች መካከል ተቀምጦ ባየች ጊዜ ዑመር መሆኑን አውቃ ስጋት ያዛት።
ዑመርም
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
❤15👍4😢2
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
❤22👍11🔥3🥰1👌1
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
😁40🤣16👌4❤2
Forwarded from Ilyas's perspective
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
👍14🥰5🔥3👌1💯1
Forwarded from ᏃᗩᏦᏆᖇ’Official Channel” (ᏃᗩᏦᏆᖇ️ ️)
“በሰሞኑ አጀንዳ ውስጥ ተድበስብሰው መታለፍ የሌለባቸው አንዳንድ ጉዳዮች ስላሉ፣ የተወሰነ ሀሳቤን ላስቀምጥ።
◆ በመጀመሪያ፦ አንድ ወንድ ኒቃብ ያልለበሰችን ሴት ማግባቱ በራሱ ሐራም ነው አንልም። ይህ ከግለሰቡ የግል የጋብቻ ምርጫ ጋር የተያያዘ ጉዳይ ነው። አላህ ከፈቀደ ከጋብቻው ቦኋላ በመልካም ምክርና በጥበብ ሊያስተካክላት፣ ወደ ተሻለ ደረጃም እንድትደርስ ሊረዳት ይችላል።
ነገር ግን በዚህ ዙሪያ አንዳንድ ስህተቶች ታይተዋል። ስህተቱ ደግሞ ብዙ ሰዎች አርአያ አድርገው ከሚከተሉት ሰው የተፈጸመ ከሆነ፣ ያ ነገር ስህተት መሆኑን በጥበብና በፍትሕ ለማስረዳት ጥረት ማድረግ አማኝ የሆነ ሰው ሊወጣው የሚገባ ኃላፊነት ነው። ይህ ግን ሰውየውን ማዋረድ ወይም መስደብ ማለት አይደለም፤ ስህተቱን ከሰውየው ለይቶ ማስረዳት ነው።
1. የሴቶች ተገላላጭነትና ተበሩጅ።
የተገላለጡና ያጌጡ ሴቶች በወንዶች ፊት ራሳቸውን በማሳየት በሚዲያ መቅረብ ሸሪዐችን የማይፈቅደው ጉዳይ ነው። አላህም በተከበረው ቃሉ እንዲህ ይላል፦
وَقَرْنَ فِى بُيُوتِكُنَّ وَلَا تَبَرَّجْنَ تَبَرُّجَ ٱلْجَٰهِلِيَّةِ ٱلْأُولَىٰ ۖ وَأَقِمْنَ ٱلصَّلَوٰةَ وَءَاتِينَ ٱلزَّكَوٰةَ وَأَطِعْنَ ٱللَّهَ وَرَسُولَهُۥٓ ۚ إِنَّمَا يُرِيدُ ٱللَّهُ لِيُذْهِبَ عَنكُمُ ٱلرِّجْسَ أَهْلَ ٱلْبَيْتِ وَيُطَهِّرَكُمْ تَطْهِيرًا
“በቤቶቻችሁም ውስጥ እርጉ፤ እንደ ፊተኛይቱ የመሐይምነት ዘመን መገላለጥም በማጌጥ አትገለጡ። ሶላትንም በደንቡ ስገዱ፣ ዘካንም ስጡ፣ አላህንና መልእክተኛውንም ታዘዙ። የነቢዩ ቤተሰቦች ሆይ! አላህ ከእናንተ ላይ እርክሰትን ሊያስወግድና በፍጹም ሊያጠራችሁ ብቻ ይፈልጋል።”
(ሱረቱል አሕዛብ፣ 33፥33)
2. ኢኽቲላጥ።
በሰርግም ይሁን በሌሎች አጋጣሚዎች፣ ከነ-መሸፈናቸውና ከአለባበሳቸው ጋር የማይስማማ ሁኔታ ውስጥ ሴቶችና ወንዶች በአንድ ቦታ መቀላቀል (ኢኽቲላጥ) እንደ አንድ የሸሪዐ ጉዳይ መታየት አለበት። ይህም ፊትናን ሊያስከትል የሚችል ሁኔታ ነው።
ከዑለማዎች መካከል ሸይኽ ኢብኑ ባዝ (ረሒመሁላህ) እንዲህ ብለዋል፦
أما اختلاط الرجال بالنساء في الأعراس أو في غير الأعراس فهذا منكر لا يجوز لما فيه من الفتنة
“ወንዶችና ሴቶች በሰርግም ሆነ ከሰርግ ውጪ መቀላቀላቸው ፊትናን ስለሚያስከትል የማይፈቀድ ሙንከር ነው።”
فتاوى نور على الدرب لسماحة الإمام عبد العزيز بن عبد الله بن باز، الجزء الأول، ص 1574]
3. ኒቃብና ሜካፕ።
ፊትን መሸፈን የኺላፍ ጉዳይ መሆኑን እንደሚታወቀው፣ ፊትን መክፈት ይፈቀዳል በሚሉ ዑለማዎች ዘንድም ቢሆን ሴት ፊቷን ስትገልጥ ራሷን በሜካፕና በማስዋብ የወንዶችን ቀልብ በሚስብ መልኩ መቅረብ የተለየ ጉዳይ ነው። ስለዚህ የኒቃብ ኺላፍን ሰበብ በማድረግ ሜካፕንና ተበሩጅን ማጽደቅ ትክክል አይደለም።
ሸይኽ አሕመድ ኢብኑ የሕያ አን-ነጅሚ (ረሒመሁላህ) እንዲህ ይላሉ፦
خطأ العالم المخالف للشرع ثلمة في الدين، فإن بُيِّنت للناس رُقِعت تلك الثلمة، وإن حاول الآخرون الاعتذار له وتبرير خطئه اتسعت تلك الثلمة، وأثرت فسادًا في الدين.
“የዐሊም ከሸሪዐ ጋር የሚቃረን ስህተት በዲን ላይ ስብራት ነው። ያ ስህተት ለሰዎች ተብራርቶ ከተስተካከለ ስብራቱ ይጠገናል። ነገር ግን ሌሎች ለተሳሳተው ዐሊም ሰበብ ለመደርደርና ስህተቱን ትክክል ለማስመሰል ከሞከሩ፣ ያ ስብራት ይሰፋል፤ በዲን ላይም ጉዳት ያስከትላል።”
[الدرر النجمية]
በመጨረሻም፣ የምንናገረው ሰውን ለማዋረድ ሳይሆን ስህተትን ስህተት ለማለት ነው። አንድ ሰው ብዙ መልካም ሥራዎች ቢኖሩትም፣ ያ እኛን ስህተቱን ስህተት ከማለት አይከለክለንም። በተመሳሳይ መልኩም አንድ ሰው በአንድ ጉዳይ ስህተት ቢሠራ ሌሎቹን መልካም ሥራዎቹን መካድ አይገባም።
እውነትን ከሰው ጋር እንመዝን እንጂ፣ ሰውን በእውነት አንመዝን። የሸሪዐ መለኪያው ሰው ሳይሆን ቁርኣንና ሱና ናቸው።

👌25❤7🥰7🔥4
Forwarded from Esmizo student ☄ (Esmizo)
አሰላም አለይኩም ወራህመቱላሂ ወበረካትሁ
በአረብ ሀገር በሳዉዲ አረብያ የምትኖር እህታችን ሀናን አህመድ በዚሁ የቲክቶክ መድረክ ወንድሞችንና ኡስታዞችን ስታግዝ ስታበረታታና ለበጎ ስራ ስትሽቀዳደም የነበረች መልካም እህታችን ነች። ሆኖም ግን በድንገት ባጋጠማት ከፍተኛ የጤና እክል ምክንያት ሶስት ጊዜ ያህል አባድ የሰርጀሪ ህክምናዎችን ለማድረግ ተገዳለች።
በዚህም ምክንያት ያላትን ጥሪት በሙሉ ለመድኃኒትና ለሕክምና ጨርሳ አሁን ላይ ከባድ የሰው ዕዳ ውስጥ ወድቃ ትገኛለች። ትናንት ካላት ላይ በማካፈልና ሰዎችን በመርዳት የምትታወቀው እህታችን ዛሬ የእኛን እጅና ድጋፍ አጥብቃ ትፈልጋለች።
ከአላህ ቀጥሎ ለእህታችን ሀናን እኛ ከጎኑዋ አለንላት ብለን ካለባት የሕመም ስቃይና የዕዳ ጭንቀት እንድትገላገል በቻልነው አቅም ልንደርስላት ይገባል። ይህ እህታችንን ብቻ ሳይሆን በአረብ ሀገር የሚገኙ እህቶቻችንን ድጋፍ የምናሳይበት ነዉ። የአረብ ሀገር እህቶች እስከዛሬ ለብዙዎች ሲሆኑ አይተናል ዛሬ ለነሱም መሆናችንን እናሳይ ።
ስለሆነም ሁላችሁም ከታች በተቀመጠው የባንክ ሂሳብ ቁጥር አቅማችሁ የፈቀደውን በመለገስ ወይም የተከፈተውን የቴሌግራም ግሩፕ በመቀላቀል ከጎኗ እንድትቆሙ በአላህ ስም ጥሪያችንን እናቀርባለን።
አካውት እህታችንን ለመርዳት
ንግድ ባንክ፡1000586128977
አሚነት ጡሃ ዑመር
የቴሌግራም ግሩፕ https://t.me/+R3jwr9j2xJdkNTI0
በሁሉም በእህት ወንድሞች ቻናሎች የሚለቀቅ

👍8😢5❤1
ሴት እና ሐጢኣት እንዲሁም እድፉ በክርስትና
በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩህሩህ በጣም አዛኝ በሆነው
በክርስትና አስተምህሮ በሴቶች ላይ ለሚደርሱ የባይብልን እውቅና ያገኙ ገደቦችና ጭቆናዎች እንደ ዋና ምክንያት ሚጠቀሰው የሔዋን የመጀመሪያ አበሳ ሲሆን በኦሪት ዘፍጥረት3:6 መሰረት ሔዋን በመጀመሪያ በመታለሏና አዳምን ለውድቀት በመዳረጓ፣ ሴት ልጅ ለሰው ልጅ ጥፋትና መከራ ዋነኛ ምክንያት ተደርጋ ትወሰዳለች ።
1ኛ ወደ ጢሞቴዎስ 2:13-14
••••••••••
¹⁴ ደግሞም የተታለለው አዳም አይደለም፤ የተታለለችውና ኀጢአተኛ የሆነችው ሴቷ ናት።
፨ በቤተክርስቲያን ትልቅ ቦታ የሚሰጠው በላቲን "ሥላሴ" ሚለውን ቃል ለመጀመሪያ ግዜ የተጠቀመው ጥንታዊው የቤተክርስቲያን አባት ተርቱሊያንም ሴት የሃጢኣት መጀመሪያ በመሆኗ ምን ያህል የተዋረደች ፍጥረት እንደሆነች ያስቀምጥልናል።
"You are the devil's gateway: you are the unsealer of that (forbidden) tree: you are the first deserter of the divine law you are she who persuaded him whom the devil was not valiant enough to attack. You destroyed so easily God's image, man. "
" አንቺ የዲያቢሎስ መግቢያ በር ነሽ ፤ የዚያች (የተከለከለች ) ዛፍ ማህተም ከፋች ነሽ ፤ መለኮታዊውን ህግ የመጀመሪያ ተላላፊ ነሽ ፤ ዲያቢሎስ ሊያጠቃው ድፍረት ያጣበትን እርሱን ያሳመንሽው አንቺ ነሽ ። የአምላክን አምሳል ሰውን በቀላሉ አጠፋሽ ።"
[Tertullian, On the Apparel of Women, Book I, Chap. I (ANF, Vol. 4, p. 14]
፨ ነገሩ በወቀሳ አላበቃም ሴቶች ላይ የተጣሉ ገደቦች ና ቅጣቶች ማስተማር ካለመቻል ጀምሮ የሴት ልጅ የምጥ ጭንቀትና ስቃይ በባሏ መገዛትና መሰል በባይብል እውቅና ያገኙ ሴት ላይ የሚደርሱ ጭቆናዎችና የተፈጥሮ ህመሞች ጭምር በሴቷ ሔዋን ጥፋት ምክንያት የመጡ ተገቢ ቅጣቶች ተደርገው ይቆጠራሉ።
ኦሪት ዘፍጥረት 3:16
••••••••••
¹⁶ ሴቲቱንም እንዲህ አላት፤ “በምጥ ጊዜ ጭንቅሽን አበዛለሁ፤ በሥቃይም ትወልጃለሽ፤ ፍላጎትሽም ወደ ባልሽ ይሆናል፤ እርሱም የበላይሽ ይሆናል።”
፨ ጳውሎስም ሴት ማታስተምርበትን ምክንያት ሲገልፅ ቀድማ ሐጢኣተኛ የሆነችው ሴት ናት ይለናል።
1ኛ ወደ ጢሞቴዎስ 2:12-14
••••••••••
¹² ሴት ዝም እንድትል እንጂ እንድታስተምር ወይም በወንድ ላይ ሥልጣን እንዲኖራት አልፈቅድም፤
¹³ ምክንያቱም አዳም ቀድሞ ተፈጥሯል፤ ከዚያም ሔዋን ተፈጠረች።

፨ ዋና ዋና ከሚባሉ ከፍተኛ ተቀባይነት ካላቸው ጥንታዊ የቤተክርስቲያን አባቶች ውስጥ የሆነው ዩሐንስ አፈወርቅም ሴት ማታስተምረው አንዴ አስተምሯ አበላሽታ ነው ይለናል።
The woman taught once, and ruined all.
ሴቲቱ አንድ ጊዜ አስተማረች፤ ሁሉንም ነገር አበላሸች( አጠፋች) ።
[John Chrysostom, Homilies on 1 Timothy, Homily IX (p. 469)]
፨ በጥቅሉ በክርስትና አስተምህሮ ሴት የዲያቢሎስ መግቢያ በር የሐጢኣት መጀመሪያና የሰው ልጆች መጥፊያ ምክንያት ስለሆነች የሚደርሱባት ባይብል ላይ የተጠቀሱ ገደቦችና ጭቆናዎችም ሆነ ተፈጥሮኣዊ ህመሞች ተገቢ ናቸው የሚል እምነት አላቸው ።

👍30❤12🔥5👌4😁2🍓2
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
😁55🤣16😭1
Forwarded from MAHIR | صَوْتُ الْحَقّ
እባብ መርዝ ባይኖረው የሰው ልጅ እንደ ገመድ ይዘልበት ነበር !
fyodor dostoevsky
fyodor dostoevsky
💯35👌16🔥2
መመዝገብ የምትፈልጉ
@Al_Rashid_01 / @Sabi_nizwan / @FatimaMuh1
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
🥰16❤8🤗4🔥3👌3
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
👍18🔥7❤3