Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
👏38🥰5
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
🤣60😁21👍3
https://t.me/iwnetlehullu1
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
❤13🔥3
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
🔥15👍2
በሴት ልጅ አዕምሮና ምስክርነት ዙሪያ የሚነሱ ትችቶች
በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩህሩህ በጣም አዛኝ በሆነው
🟠 የሐዲስን ትክክለኛ ዐውድ ባለመረዳት ከሚሰነዘሩ የተሳሳቱ ትችቶች ውስጥ ሴት ልጅ የአዕምሮ ጎዶሎ ናት የሚለው ትችት ነው ። በእስልምና አስተምህሮ ውስጥ "ናቂሳቱ ዐቅል" ሲባል የሚያመለክተው አጠቃላይ የማሰብ ችሎታን ሳይሆን፣ በተፈጥሮ ሂደት ውስጥ ሊከሰት የሚችልን "የማስታወስ አቅም ድክመት" ነው። ይህም በንግድ ዕዳና መሰል ወንዶች ሚዘወትሩባቸው ምስክርነቶች ውስጥ ሊከሰት የሚችለውን የመርሳት እድል ሁለት ሴቶች በማድረግ ለመከላከል እና ፍትህ እንዳይዛባ የተዘጋጀ የህግ ጥበቃ (Legal safeguard) ነው።
" የሴት ምስክርነት እንደ ግማሽ የወንድ ምስክርነት አይደለምን?’ እኛም ‘አዎን’ አልን። እሳቸውም ‘ይህ የሴት የአእምሮዋ ጉድለት በመሆኑ ነው’ አሉ።"
📗Sahih al-Bukhari, 2658
፨ ይህም ምስክርነት የሚገኘው ሱረቱል በቀራ ሲሆን " አንዲቱ ብትረሳ አንደኛዋ ታስታውሳት ዘንድ ስለሚል የአዕምሮ ጉድለት የሚለው መርሳትን እንደሚወክል መረዳት ይቻላል ።
" ..فَرَجُلٌ وَامْرَأَتَانِ مِمَّن تَرْضَوْنَ مِنَ الشُّهَدَاءِ أَن تَضِلَّ إِحْدَاهُمَا فَتُذَكِّرَ إِحْدَاهُمَا الْأُخْرَىٰ ۚ ..."
«...ከምስክሮችም የሆኑ አንድ ወንድ እና ሁለት ሴቶች ይሁኑ፤ (ይህም) አንዲቱ ብትረሳ ሌላይቱ ታስታውሳት ዘንድ ነው።»
📗ሱረቱል በቀራ 282
፨ ኢማም አል-ነወዊይ በሰሂህ ሙስሊም ሸርህ ላይ በግልጽ እንዳስቀመጡት፣ ይህ ጉድለት የሚባለው "የመያዝ/የማስታወስ ችሎታ" ጋር የተያያዘ ነው።
قوله : «أما نقصان العقل فشهادة امرأتين تعدل شهادة رجل تنبيه منه على ما وراءه وهو ما نبه الله تعالى عليه في كتابه بقوله تعالى : أن تضل إحداهما فتذكر إحداهما الأخرى أي إنهن قليلات الضبط،
"በአእምሮ መጉደልን በተመለከተ፡ የሁለት ሴቶች ምስክርነት የአንድ ወንድ ምስክርነት ጋር እኩል መሆኑ፣ ከዚህ በስተጀርባ ላለው ነገር ማስታወሻ ነው። ይህም አላህ በቅዱስ ቁርኣኑ ‘ከሁለቱ አንዷ ብትረሳ ሌላኛዋ እንድታስታውሳት’ ብሎ የገለጸው ነው። ይህም ማለት ሴቶች የማስታወስ (የመያዝ) አቅማቸው ደካማ ነው ማለት ነው።"
📗صحيح مسلم بشرح النووي، المجلد الأول، ص 59
፨ ዘመናዊ የሳይንስ ጥናቶች እንዳረጋገጡት፣ እርግዝናና መሰል ነገራቶች በሴቶች አእምሮ ላይ ተፅዕኖ ያሳድራል። በተለይ በሦስተኛው የእርግዝና ወር የመስማት #ማስታወስ ችሎታ፣ ትኩረት እና የአፈጻጸም ተግባራት ላይ መጠነኛ መዳከም ሊከሰት እንደሚችል ጥናቶች ያሳያሉ።
The results of this study revealed that the occurrence of mild impairment of auditory memory, attention and executive functions in the third trimester of pregnancy is consistent with the main hypothesis.
የዚህ ጥናት ውጤት እንደሚያሳየው፣ በእርግዝና ሦስተኛው ሶስት ወር ውስጥ የመስማት ችሎታ (auditory memory)፣ ትኩረት እና የአፈጻጸም ተግባራት (executive functions) መጠነኛ መዳከም መከሰቱ ከዋናው ግምት ጋር የሚጣጣም ነው።
📗Ali, S. A., Begum, T., Reza, F., Wan Rosilawati, W. R., & Wan Nor Azlen, W. M. (n.d.). Auditory Cognitive Function Assessment During Pregnancy: An Event-Related Potential and Neuropsychological Study. Chapter 6: Conclusion.
፨ ከንግድና መሰል ጉዳዮች ጋር የተያያዙ ምስክርነቶች ላይ ሴት 2 መሆኗ የተፈለገበት ምክንያት ሴት ልጅ ከንግድና መሰል ነገራቶች የራቀች በመሆኗ ቅድም ያነሳነው የመርሳት ችግር ሊጎላ ስለሚችል ነው ።
፨ኢማም ኢብኑ ከሲር በታላቁ ተፍሲራቸው ላይ እንደገለጹት፤ 'ሴቶች ሁለት መሆን ያለባቸው በገንዘብ ነክ ንግድና መሰል ጉዳዮች እንደሆነ አስፍረዋል ።
فإن لم يكونا رجلين فرجل وامرأتان، وهذا إنما يكون في الأموال وما يقصد به المال»
"ወንዶች ሁለት ካልሆኑ (በምስክርነት ጊዜ)፣ አንድ ወንድ እና ሁለት ሴቶች ይሁኑ፤ ይህም የሚሆነው በገንዘብ ነክ ጉዳዮች እና ገንዘብን በሚመለከቱ ጉዳዮች ላይ ብቻ ነው"።
📗تفسير القرآن العظيم» للحافظ عماد الدين إسماعيل بن عمر بن كثير سورة البقرة 282
፨የሴቶች ምስክርነት በሁለት መተካቱ አጠቃላይ አእምሯዊ አቅምን የሚለካ ሳይሆን፣ ከገንዘብ እና ከንግድ ውሎች ጋር በተያያዘ ሴቶች በብዛት ከነዚህ ነገራቶች የራቁ በመሆናቸው ሊፈጠር የሚችለውን የመርሳት ክፍተት ለመቅረፍ የተቀመጠ ጥንቃቄ የተሞላበት ድንጋጌ ነው። ከዚህ ውጭ ባሉ ጉዳዮች ማለትም በጡት ማጥባት፣ በሴቶች ተፈጥሮአዊ ክስተቶች እና በሌሎችም የቤት ውስጥ እውነታዎች ሴት ብቻዋን የምትሰጠው ምስክርነት ሙሉ በሙሉ ተቀባይነት እንዳለው 📗ሰሒሕ አል-ቡኻሪ (2659)ን ጨምሮ ሌሎች ማስረጃዎች ያረጋግጣሉ።
© https://t.me/MewedaComp

🔥11🥰9❤8👏1
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
YouTube
ሀሰተኛ ነቢይ? ለስልጣንና ዝና ብለው? ክፍል (2) ግጥም #ፒኬ #ጃህ #ኢምራን #ሳላህ #ወሒድ #ሁሱ #ኢብሮ
📖 Welcome to PK(ታላቁ አብርሐም) – A Journey Through the Abrahamic Faiths 🌟
Step into a space where Islam, Christianity, and Judaism meet in truth, light, and deep reflection. Eshma Ilah is your gateway to exploring divine messages, sacred texts, and the powerful…
Step into a space where Islam, Christianity, and Judaism meet in truth, light, and deep reflection. Eshma Ilah is your gateway to exploring divine messages, sacred texts, and the powerful…
❤7
Forwarded from ሙከሚል የንፅፅር ቤተ መጽሐፍ (𓆩𝄽Mukamil𝄽𓆪)
አሰላሙአለይኩም ወራህመቱላሂ ወበረካቱ
እህት ወንድሞች አንድ ነገር ላስቸግራቹ ነው
ለአላህ ብላቹ ተባበሩኝ
አንዲት እህት ስደት ከመጣች ሁለት አመት ሆኗታል ግን በጣም እሚያሳዝነው አሰሪዋ ጠንቋይ ናትና ልጅታን ምንም ነገር እንዳታቅ አድርጋ አፍዝዛታለች እናም ይችህ እህት አላህ ዳኚ ሲላት ዝምብላ ከቤቱ ትወጣለች ከዛም ሲደክማት መንገድ ላይ ቁጭ ትላለች ከዛም አንድ ሱዳናዊ ግለሰብ ያያታል ሲያያት ግን ልጅቷ ላይ ችግር እንዳለ ይረዳና ጠጋ ብሎ ሲጠይቃት ተስፋን የሚያስቆርጡ ንግግሮችን ትመልስለታለች እሱም ችግር እንዳለ ይረዳና ያለውን ገንዘብ ሰጣትና ሪያድ ኢንባሲ ብላ እንድትሳፈር ተባበራት ከዛም ይችህ እህት ወደ ኢንባሲው ከገባች ቦሀላ ፈዛ ቁጭ ባለችበት አንድ ሀበሻዊ ያገኛታል ከዛም እነደመጀመሪያው ገለሰብ ሲጠይቃት ተመሳሳይ መልስ መለሰችለት እና ይችህ እህት ስትጠየቅ ምታቀው ወላሂ ስሟንና የአባቷን ስም ብቻ ነው ምታቀው 2ት አመት ቤተሰብን ሳታወራ ቆይታለች ቤተሰቦቿ ይኑሩ አይኑሩ አንድ ምታቀው ነገር የለም የት እንደነበረችኳን ስንጠይቃት ምታስታውሰው ነገር የለም እና አስብት እናት የልጇን ድምፅ ሀለት አመት ሳትሰማ ሞታለች ብላ ቁርጧን አላውቀች ሁሌ ልባ እንደተጠለጠለ ወላሂ ይከብዳል ልጅቱም እናት አባትን የወንድም እህቶቿን ድምፅ ሳትሰማ ጭራሽ ስማቸውን እስከመርሳት ድርስ እና ውንድምና እህቶች ሼር በማድረግ ተባበሩኝ በዝች ልጅ ቦታ እራሳችንን አስቀምጠን እናስብ
የልጅቷ ስም ሙኒራ አብደላህ ትባላለች
የትወልድ ባታ ጉንችሬ ልዩ ስሙ ኡፍጠሬ ሚባል ቦታ ነው ብላናለች ባረከላሁፊኩም ተባበሩን ወላጆች ልጆቻቹን እያሰባቹ ወደዃላ አትበሉብን
ያገኘ ካለ በዚህ ስልክ ተባበሩን 0550745238
የቻናል ባለቤቶች ተባበሩን

👍13❤7😢1
Forwarded from Pk(ታላቁ አብርሐም) official channel
አፕሊኬሽኑን ለማግኘት
👉 https://t.me/pk_talaku/15
ለመመዝገብ ይህንን ይመልከቱ
👉 https://t.me/pk_talaku/18
የክፍያ አከፋፈል ጋር በተገናኘ ይህንን ተመልከቱ
👉 https://t.me/pk_talaku/25
አፕሊኬሽኑ አልወርድላቹህ ላላቹህ ይህን ይመልከቱ
👉 https://t.me/pk_talaku/48
በPaypal ክፍያ ለምትፈፅሙ ለአንድ መፅሐፍ
👉 https://t.me/pk_talaku/51
ለPaypal ከፋዮች ብዙ ለመግዛት
👉 https://t.me/pk_talaku/52
ማንኛውም ጥያቄ ካላቹህ pkን ለማናገር
👉 t.me/pk_talaku?direct
👉 https://t.me/pk_talaku/15
ለመመዝገብ ይህንን ይመልከቱ
👉 https://t.me/pk_talaku/18
የክፍያ አከፋፈል ጋር በተገናኘ ይህንን ተመልከቱ
👉 https://t.me/pk_talaku/25
አፕሊኬሽኑ አልወርድላቹህ ላላቹህ ይህን ይመልከቱ
👉 https://t.me/pk_talaku/48
በPaypal ክፍያ ለምትፈፅሙ ለአንድ መፅሐፍ
👉 https://t.me/pk_talaku/51
ለPaypal ከፋዮች ብዙ ለመግዛት
👉 https://t.me/pk_talaku/52
ማንኛውም ጥያቄ ካላቹህ pkን ለማናገር
👉 t.me/pk_talaku?direct
👍5❤1🍓1
◆ 1 ሒጃብ :- በእስልምና አስተምህሮ መሠረት ሒጃብ ሴቶችን ከተለያዩ ጥቃቶች ለመከላከል የተደነገገ መሆኑን ሱረቱል አህዛብ በግልፅ ያስቀምጥልናል ።
يَٰٓأَيُّهَا ٱلنَّبِىُّ قُل لِّأَزْوَٰجِكَ وَبَنَاتِكَ وَنِسَآءِ ٱلْمُؤْمِنِينَ يُدْنِينَ عَلَيْهِنَّ مِن جَلَٰبِيبِهِنَّ ۚ ذَٰلِكَ أَدْنَىٰٓ أَن يُعْرَفْنَ فَلَا يُؤْذَيْنَ ۗ وَكَانَ ٱللَّهُ غَفُورًۭا رَّحِيمًۭا
አንተ ነቢዩ ሆይ! ለሚስቶቸህ፣ ለሴቶች ልጆችህም፣ ለምእምናን ሚስቶችም ከመከናነቢያዎቻቸው በላያቸው ላይ እንዲለቁ ንገራቸው፡፡ ይህ እንዲታወቁና (በባለጌዎች) እንዳይደፈሩ ለመኾን በጣም የቀረበ ነው፡፡ አላህም መሓሪ አዛኝ ነው፡፡ [ አል- አህዛብ 59]
◆ 2 አይንን መስበር :- ለወንጀል ሁሉ የመጀመሪያው መንስኤ እይታ እንደመሆኑ መጠን ኢስላም ወንዶችን አይናቸውን መስበር እንዲሁም ዝሙትን አለ መቅረብ እንዳለባቸው ያዛል ።
قُل لِّلْمُؤْمِنِينَ يَغُضُّوا۟ مِنْ أَبْصَٰرِهِمْ وَيَحْفَظُوا۟ فُرُوجَهُمْ ۚ ذَٰلِكَ أَزْكَىٰ لَهُمْ ۗ إِنَّ ٱللَّهَ خَبِيرٌۢ بِمَا يَصْنَعُونَ
ለምእመናን ንገራቸው፡- ዓይኖቻቸውን (ያልተፈቀደን ከማየት) ይከልክሉ፤ ብልቶቻቸውንም ይጠብቁ፤ ይህ ለነሱ የተሻለ ነው፤ አላህ በሚሠሩት ሁሉ ውስጥ ዐዋቂ ነው፡፡ [አን- ኑር 30]
◆ 3 ባዕድ የሆኑ ወንድና ሴት በአንድ ክፍል ውስጥ መገለልን መከልከል :- የአብዛኛው ሴቶች ጥቃት ትኩረት ባልተሰጠው በመጓጓዣዎች እንዲሁም በቤቶች ውስጥ መገለሎች የሚከሰት ሲሆን ኢስላም ይሄንን መስመር ዘግቶታል።
وَلاَ يَدْخُلُ عَلَيْهَا رَجُلٌ إِلاَّ وَمَعَهَا مَحْرَمٌ
" ከርሷ ጋር መሕረም (አብሮ መሆን የተፈቀደለት የቅርብ ዘመድ) ከሌለ በቀር በእርሷ ላይ ባዕድ ወንድ አይገባም " [ ሰሂህ አል-ቡኻሪ 1862]
◆ 4 ሴት ልጅ ረጅም ጉዞን ያለ መሕረም (አብሮ መሆን የተፈቀደለት የቅርብ ዘመድ) ከሌለ ብቻዋን መጓዝን ከልክሏል :- ሴቶች ስደት ላይ እንዲሁም በተለያዩ ጉዞዎች ላይ የሚደርስባቸውን አሰቃቂ ጥቃት ኢስላም አስቀድሞ የዚህንም መንገድ በመዝጋት አብሯት ሚጠብቃት መሕረም ( አብሮ መሆን የተፈቀደለት የቅርብ ዘመድ ) እንዲኖር ያዛል ።
لاَ تُسَافِرِ الْمَرْأَةُ إِلاَّ مَعَ ذِي مَحْرَمٍ
ሴት ከመሕረሟ ( አብሮ መሆን የተፈቀደለት የቅርብ ዘመድ ) ጋር እንጂ አትጓዝ (ጉዞ አታድርግ ) [ሰሂህ አል-ቡኻሪ 1862]
◆5 የአባት ጥበቃ :- ሴት ልጅ ከማግባቷ በፊት በጣም ፈተናዎች ሚበዙባት ግዜ እንደመሆኑ ለሴት ልጆች የተለየ ጥበቃ ስለሚያስፈልጋቸው የአላህ መልዕክተኛ ሰ.ዐ.ወ ሁለት ሴት ልጆችን ጠብቆና ተንከባክቦ ለቁም ነገር ያበቃን አባት እኔና እሱ በጀነት እንዲህ ነን በማለት ጣቶቻቸውን በማጣመር በጀነት ከሳቸው ጋር ቅርብ እንደሚሆን አበስረዋል ።
عَالَ جَارِيَتَيْنِ حَتَّى تَبْلُغَا جَاءَ يَوْمَ الْقِيَامَةِ أَنَا وَهُوَ " . وَضَمَّ أَصَابِعَهُ .
ሁለት ሴት ልጆችን እስኪደርሱ በአግባቡ የተንከባከበና ያሳደገ ሰው ፣ የትንሳኤ ቀን እኔና እርሱ እንደዚህ ነን ( ብለው ጣቶቻቸውን አጣመሩ) [ ሰሂህ ሙስሊም 2631]
© https://t.me/MewedaComp
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
❤25🥰9👍4💯3😇1
Forwarded from عبدالفتاح🖋️ Abdulfetah
የዑመር ኢብኑል ኸጧብ🤎 አገልጋይ የነበረው አስለም እንዲህ ሲል ይተርካል:
በአንድ ሌሊት ከዑመር ኢብኑ አል-ኸጣብ🤎 ጋር የሕዝባቸውን ሁኔታ ለመቃኘት ከመዲና ወጥተን ጋር ወደ ሐረቱ-ዋቂም ወደተባለ ስፍራ አመራን። ሱራር በተባለ ቦታ ስንደርስ በሩቅ እሳት ታየን። ዑመርም «አስለም ሆይ! ብርዱና ሌሊቱ ያስቆማቸው መንገደኞች ይታዩኛል፤ ወደ እነሱ እንሂድ» አሉኝ። በፍጥነት ስንቀርብ አንዲትን እናት ከሕፃናት ልጆቿ ጋር አገኘን፤ እሳቱ ላይ ድስት ተጥዷል፣ ልጆቿም ያለቅሳሉ።
ዑመርም🤎 «አሠላሙ ዐለይኩም ያ አሥሐበድ-ደውእ (የብርሃኑ ባለቤቶች)» አሉ — «የእሳቱ ባለቤቶች» ማለትን ጠልተው ነው።
እሷም «ወዐለይኩም አሠላም» አለች።
ዑመር🤎 «ወደ እናንተ ልቅረብ (ልጠጋ)?» ሲሉ ጠየቁ።
ሴቲቱም «በበጎ ከሆነ ቅረብ፣ ካልሆነ ግን ተወን» አለች።
ቀረብ ብለውም «ምን አጋጠማችሁ?» አሏት።
እሷም «ሌሊቱና ብርዱ ጉዟችንን አሰናከለን» አለች።
ዑመር «እነዚህ ሕፃናት ለምን ያለቅሳሉ?» አሏት።
«በረሃብ ምክንያት ነው» አለች።
«በዚህ ድስት ውስጥ ያለው ምንድን ነው?» ሲሉ ጠየቋት።
«ልጆቹ እስኪተኙ እያፈላሁ የማታልልበት ውኃ ነው፤ አላህ በእኛና በዑመር መካከል ይፍረድ!» አለች።
ዑመርም «አላህ ይዘንልሽ! ዑመር የእናንተን ሁኔታ እንዴት ሊያውቅ ይችላል?» አሏት።
እሷም «የእኛን ጉዳይ ተረክቦ ከዚያ በእኛ ይዘናጋል?» ብላ መለሰች።
በንግግሯ የደነገጡት ዑመር🤎 «ተከተለኝ እንሂድ!» አሉኝ። በፍጥነት ወደ ዱቄት ማከማቻ ቤት (ዳሩድ-ደቂቅ) ሄድን። አንድ የዱቄት ከረጢትና የስጋ ስብ አውጥተው «በጀርባዬ ላይ ጫንልኝ» አሉኝ። እኔም «እኔ ልሸከምልዎ?» ብላቸው «በቂያማ ቀን ወንጀሌን ትሸከምልኛለህ?» አሉኝ በቁጣ። በጀርባቸው ላይ ጫንኩላቸውና በፍጥነት ወደ እናትየው ተመለስን።
ዑመር🤎 የዱቄቱንና የሥቡን ጥቂት ክፍል ድስቱ ውስጥ አድርገው «እኔ አማስልልሻለሁ፤ አንቺ ዱቄቱን ነስንሺልኝ» አሏት። ከድስቱም ሥር እሳቱን እየነፉ ያቀጣጥሉ ጀመር፤ ከዚያም ድስቱን አወረዱት።
ቀጥሎም፡ «የሚበሉበት እቃ አምጪልኝ» አሏት፤ ሰፊ እቃ (ሳህን) አቀበለቻችውና ምግቡን አደረጉላት። ከዚያም ለሴቲቱ፡ «አንቺ መግቢያቸው፤ እኔ ደግሞ አቀዝቅዝላቸዋለሁ» አሏት። እስኪጠግቡ ድረስ ማብላታቸውን አላቆሙም፤ የቀረውንም ምግብ እሷ ዘንድ ትተውላት ተነሱ፤ እኔም አብሬ ተነሣሁ።
ሴቲቱም፡ «አላህ መልካም ምንዳህን ይክፈልህ! ከምእመናን መሪ (ከዑመር) ይልቅ ለዚህ ሥልጣን የተገባኸው አንተ ነበርክ» አለች።
እርሳቸውም፡ «ወደ ምእመናን መሪ ዘንድ በመጣሽ ጊዜ መልካም ነገርን ተናገሪ፤ አላህ ካለ እዚያ ታገኚኛለሽ» አሏት።
ከዚያም ከእሷ ዘወር ብለው ፈቀቅ አሉና በርከክ ብለው ተቀመጡ።
እኔም፡ «ከዚህ ሌላ የምናከናውነው ጉዳይ አለንኮ» አልኳቸው፤ እርሳቸው ግን ምንም አልመለሱልኝም። ህፃናቱ ሲጫወቱና ሲስቁ፣ ከዚያም ተኝተው እስኪረጉ ድረስ ይመለከቷቸው ነበር።
ከዚያም፡ «አስለም ሆይ! ረሀብ አሳድሯቸውና አስለቅሷቸው ነበር፤ ስለዚህ ያየሁትን ደስታና እርጋታ ሳላይ መመለስ አልፈለግኩም ነበር» አሉኝ።» ይለናል አስለም።
በንጋታው እናትየው ወደ መዲና ሄዳ የዑመርን ማረፊያ ጠይቃ ገባች። ያ ማታ የረዳት ሰው አሚሩል ሙእሚኒን ተብሎ ከሶሐቦች መካከል ተቀምጦ ባየች ጊዜ ዑመር መሆኑን አውቃ ስጋት ያዛት።
ዑመርም🤎 «አንቺ እናት ሆይ! ምንም ስጋት አይግባሽ፤ በደልሽን ከአንቺ ልገዛሽ እንጂ ሌላ አይደለም፣ በስንት ልግዛሽ?» አሏት። በአርባ ድርሃም ከተስማሙ በኋላ ለፀሐፊያቸው «በርግጥም ዑመር ከዚች እናት በደሏን በአርባ ድርሃም ገዝቷል» ብለው እንዲጽፍ አዘዙ። ዐሊይንና ዑሥማንን (ረ.ዐ) ምስክር አድርገው ደብዳቤውን ለሶሐቦች በመስጠት « በሞትኩ ጊዜ ይህን ደብዳቤ ከከፈኔ መካከል አድርጋችሁ ቅበሩኝ፤ አላህን በእሱ እንድገናኘው» አሉ።
በአንድ ሌሊት ከዑመር ኢብኑ አል-ኸጣብ
ዑመርም
እሷም «ወዐለይኩም አሠላም» አለች።
ዑመር
ሴቲቱም «በበጎ ከሆነ ቅረብ፣ ካልሆነ ግን ተወን» አለች።
ቀረብ ብለውም «ምን አጋጠማችሁ?» አሏት።
እሷም «ሌሊቱና ብርዱ ጉዟችንን አሰናከለን» አለች።
ዑመር «እነዚህ ሕፃናት ለምን ያለቅሳሉ?» አሏት።
«በረሃብ ምክንያት ነው» አለች።
«በዚህ ድስት ውስጥ ያለው ምንድን ነው?» ሲሉ ጠየቋት።
«ልጆቹ እስኪተኙ እያፈላሁ የማታልልበት ውኃ ነው፤ አላህ በእኛና በዑመር መካከል ይፍረድ!» አለች።
ዑመርም «አላህ ይዘንልሽ! ዑመር የእናንተን ሁኔታ እንዴት ሊያውቅ ይችላል?» አሏት።
እሷም «የእኛን ጉዳይ ተረክቦ ከዚያ በእኛ ይዘናጋል?» ብላ መለሰች።
በንግግሯ የደነገጡት ዑመር
ዑመር
ቀጥሎም፡ «የሚበሉበት እቃ አምጪልኝ» አሏት፤ ሰፊ እቃ (ሳህን) አቀበለቻችውና ምግቡን አደረጉላት። ከዚያም ለሴቲቱ፡ «አንቺ መግቢያቸው፤ እኔ ደግሞ አቀዝቅዝላቸዋለሁ» አሏት። እስኪጠግቡ ድረስ ማብላታቸውን አላቆሙም፤ የቀረውንም ምግብ እሷ ዘንድ ትተውላት ተነሱ፤ እኔም አብሬ ተነሣሁ።
ሴቲቱም፡ «አላህ መልካም ምንዳህን ይክፈልህ! ከምእመናን መሪ (ከዑመር) ይልቅ ለዚህ ሥልጣን የተገባኸው አንተ ነበርክ» አለች።
እርሳቸውም፡ «ወደ ምእመናን መሪ ዘንድ በመጣሽ ጊዜ መልካም ነገርን ተናገሪ፤ አላህ ካለ እዚያ ታገኚኛለሽ» አሏት።
ከዚያም ከእሷ ዘወር ብለው ፈቀቅ አሉና በርከክ ብለው ተቀመጡ።
እኔም፡ «ከዚህ ሌላ የምናከናውነው ጉዳይ አለንኮ» አልኳቸው፤ እርሳቸው ግን ምንም አልመለሱልኝም። ህፃናቱ ሲጫወቱና ሲስቁ፣ ከዚያም ተኝተው እስኪረጉ ድረስ ይመለከቷቸው ነበር።
ከዚያም፡ «አስለም ሆይ! ረሀብ አሳድሯቸውና አስለቅሷቸው ነበር፤ ስለዚህ ያየሁትን ደስታና እርጋታ ሳላይ መመለስ አልፈለግኩም ነበር» አሉኝ።» ይለናል አስለም።
በንጋታው እናትየው ወደ መዲና ሄዳ የዑመርን ማረፊያ ጠይቃ ገባች። ያ ማታ የረዳት ሰው አሚሩል ሙእሚኒን ተብሎ ከሶሐቦች መካከል ተቀምጦ ባየች ጊዜ ዑመር መሆኑን አውቃ ስጋት ያዛት።
ዑመርም
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
❤15👍4😢2
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
❤22👍11🔥3🥰1👌1
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
😁40🤣16👌4❤2
Forwarded from Ilyas's perspective
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
👍14🥰5🔥3👌1💯1