ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ-Orthodox Tewahido
1.07K subscribers
1 file
Wele come to this channel
Download Telegram
🌿🌿🌿 #ሆሳዕና 🌿🌿🌿
በዕለተ ሆሳዕና እስራኤላውያን ለምን የዘንባባ ዝንጣፊ ፤ የቴምር ዛፍ ዝንጣፊ እና የወይራ ዛፍ ዝንጣፊ ይዘው ዘመሩ? (ማቴ. 21÷1-17፣ ማር. 11÷ 1-10፣ ሉቃ. 19÷29-38፣ ዮሐ. 12÷12-15

የዘንባባ ዝንጣፊ፡-
☞ይስሃቅ በተወለደ ጊዜ አብርሃም ደስ ብሎት ዘንባባ ይዞ እግዚአብሄርን አመስግኖበታል የደስታ መግለጫ በመሆኑ አነተ ደሰታ የምታስገኝ ሃዘናችንንም የምታርቅ አምላክ ነህ ሲሉ ነው፡፡
☞ ዘንባባ ደርቆ እንደገና ህይወት ይዘራል የደረቀ ሕይወታችንን የምታለመልም አምላክ ነህ ሲሉ ነው
☞ ዘንባባ የሰላም ምልክት ነው የሰላም አምልክ ነህ ሲሉ ነው
☞ ዘንባባ እሾሃማ ነው አንተ ህያው አሸናፊ አምላክ ነህ ሲሉ ነው
☞ ዘንባባ እሳት አይበላውም ለብልቦ ይተወዋል እንጅ ጌታም አንተ ባህርይህ የማይመረመር ነው ሲሉ ነው
☞ ዘንባባ የነፃነት ምልክት ነው ከባርነት ነፃ የምታወጣን አንተነህ ሲሉ ነው አኛም ይህን በማሰብ ዘንባባ ይዘን ሆሳእና በአርያም እያልን እለቱን እናስባለን፡፡

የቴምር ዛፍ ዝንጣፊ፡-
☞ የቴምር ዛፍ ፍሬ ጣፋጭ ነው፦ በሃጥያት የመረረውን ሂወታችን የምታጣፍጥልን አምላክ ነህ ሲሉ ነው።
☞ የቴምር ፍሬ የሚገኘው ከዛፉ ከፍታ ላይ ነው አንተ አምላካችን ልዑለ ባህሪ ነህ ከፍ ከፍ ያልክ አምላክ ነህ ሲሉ ነው።
☞ የቴምር ዛፍ ፍሬ በውስጡ ያለው ፍሬ አንድ ነው አንድ አካል አንድ ባህሪ ነህ ሲሉ ነው።
☞ የቴምር ፍሬ በእሾህ የተከበበ ነው ይህም የአንት ባህሪ የማይመረመር በእሳት የተከበበ ነው ሲሉ ነው።

የወይራ ዛፍ ዝንጣፊ፡-
☞ የወይራ ቅጠል የሰላም ማብሰሪያ ነው ሰላማችንን የምታበስርልን የምታስገኝልን አንተ ነህ ሲሉ ነው፡፡
☞ የወይራ ቅጠል ከእንጨት ሁሉ ጽኑ ነው አንተም ጽኑ ሃያል አምላክ ነህ ሲሉ ነው።
☞ ወይራ ለመብራት ያገለግላል ፍሬው ዘይት ያወጣል ከወይራ የሚገኝ ዘይት ጨለማን አሸንፎ ብርሃን እንደሚሰጥ ሁሉ አንተም ጨለማ ህይወታችንን የምታስወግድልን አምላክ ነህ ሲሉ ነው።
☞ በኦሪት ግዜ የወይራ ዘይት ለመስዋአትነት ይቀርብ ነበር አንተም እንደ ዘይቱ ለመተላለፋችን መስዋዕት ሆነህ የምትቀርብ አምላክ ነህ ሲሉ ነው። በመስቀል ላይ መስዋዕት ሆኗልና።

​​⛪️✨⛪️✨ ሆሣዕና ✨⛪️✨⛪️

1⃣🌿ሆሣዕና ማለት ምን ማለት ነው?
#መልስ🌿✍ሆሣዕና ማለት፦ የዕብራይስጥ ቃል ሲሆን ትርጉሙ ‹‹እባክህ አሁን አድን አሁን ባርከን›› ማለት ነው፡፡ በሰሙነ ሕማማት ጸሎተ ፍትሐት ጸሎተ አስተስርዮ ስለማይፈጸም ጸሎተ ፍትሃትና አስተስርዮ የሚደረገው በዚሁ ዕለት ነው።
2⃣🌿 በሆሣዕና ዕለት በእጃችን እደ ቀለበት ማሠራችን የምን ምሳሌ ነው?
#መልስ🌿1.ጌታ ለአዳም የሰጠው ቃል ኪዳን ለማስታወስ፦ ከልጅ ልጅህ ተወልጄ አድንሃለሁ ያለውን የተስፋ ቃል ለማስታወስ።
2. ጌታ ለእመቤታችን የገባላትን ቃል ኪዳን ተምሳሌት ነው።
3. ጌታ ለእስራኤላውያን የሰጣቸው ቃል ኪዳን ተምሳሌት ነው።
4. ጌታ ለአዳም ከሰይጣን ግዛት ነጻ እንዳወጣው ሁሉ እኛም ከሰይጣን ግዛት ከመከራ ሥጋ ከመከራ ነፍስ ከክፋት ከኃጢአት አውጣን ማረን ለንስሐ ሞት አብቃን ከቤትህ አትለየን እንደ ቸርነትህ ይቅር በለን ስንል ለጌታ ዳግም ላናጠፋ ቃል የምንገባበት ነው።
3⃣🌿 ጌታችን በዕለተ ሆሣዕና ለምን በፈረስ ላይ አልተቀመጠም?
#መልስ🌿ትንቢቱንና ምሳሌውን ለመፈጸም ነው፡፡ " አንቺ የጽዮን ልጅ ሆይ፥ እጅግ ደስ ይበልሽ፤ አንቺ የኢየሩሳሌም ልጅ ሆይ፥ እልል በዪ፤ እነሆ፥ ንጉሥሽ ጻድቅና አዳኝ ነው፤ ትሑትም ሆኖ በአህያም፥ በአህያይቱ ግልገል በውርጫይቱ ላይ ተቀምጦ ወደ አንቺ ይመጣል።" ዘካ. 9፥9

🌿በአህያ መቀመጡ፦
•ትህትናን ለማስተማር
•የሰላም ዘመን ነው ሲል
•ለፈለጉኝ ሁሉ የቅርብ አምላክ ነኝ ሲል በንጽህና በየዋህነት ለሚኖሩ ምዕመናን አድሬባቸው እኖራለሁ ሲል።
•አህያዎች ትሁታን ናቸው ረጋ ብለው ነው የሚሄዱት፤ በቀላሉ ትወጣበታለህ፤ በቀላሉ ትይዘዋለህ፤ እንደፈለክም ታዘዋለህ፤
4⃣🌿ጌታችን ወደ ኢየሩሳሌም ሲገባ ዘንባባ የመነጠፉ ምሥጢር የምን ምሳሌ ነው?
#መልስ🌿 1. ዘንባባ፡- ይስሐቅ በተወለደ ጊዜ ደስ ብሎት አብርሃም ዘንባባ ይዞ እግዚአብሔር አመስግኗል።
2. ዘንባባ ደርቆ እንደገና ሕይወት ይዘራል፤ የደረቀ የምታለመልም አምላክ ነህ ሲሉ ነው።
3. ዘንባባ የሰላም ምልክት ነው፤ የሰላም አምላክ ነህ ሲሉ ነው።
4. ዘንባባ የደስታ መግለጫ ነው፤ አንተ ደስ የምታሰኝ ሃዘናችንም የምታርቅልን አምላክ ነህ ሲሉ ነው።
5. ዘንባባ እሾሃማ ነው፤ አንተ ሕያው አሸናፊ አምላክ ነህ ሲሉ ነው።
6. ዘንባባ እሳት አይበላውም ለብልቦ ይተወዋል እንጂ። ጌታም አንተ ባህሪህን የማይመረመር ነው ሲሉ ነው።
5⃣🌿 ሕዝቡ ከልብሳቸው ሌላ ስንት ዓይነት ቅጠል አነጠፉለት ምን ና ምን?
#መልስ🌿 ልብሳቸውን ማንጠፋቸው፦ ለክብሩ መግለጫ ነው።
ሌሎችም ሦስት ዓይነት ቅጠል አነጠፉለት ዘንባባ፤ የቴመር ዛፍ፤ የወይራ ዛፍ አነጠፉለት።
6⃣🌿 ትልቅዋ አህያ በምን ትመሰላለች ውርንጭላዋስ?
#መልስ🌿 ትልቅዋ አህያ የኦሪት ምሳሌ ናት።
1. ትልቅዋ አህያ ሸክም የለመደች ናት ሕገ ኦሪትም የተለመደች ሕግ ናትና።
2. የእስራኤል ምሳሌ ነው፦ ትልቅዋ አህያ ሸክም እንደለመደች ሁሉ እስራኤልም ሕግ ለመፈጸም በሕግ ለመራመድ የለመዱ ናቸው።
3. የአዳም ምሳሌ ነው፦ አዳም ሸክም የበዛበት ነበርና፤
🌿✍ውርንጭላዋ
1. በሕገ ወንጌል ትመሰላለች፦ ምክንያቱም ወንጌል ኢየሱስ ክርስቶስ የመሠረታት የሠራት አዲስዋ ሕግ ናትና።
2. በአህዛብ ትመሰላለች፦ ትንሽዋ አህያ ሸክም የለመደች አይደለችም እንዲሁም አህዛብም ሕግህን የመቀበል የለመደ አይደሉም። ለሕግህ አዲስ ናቸውና።
3. የእመቤታችን ምሳሌ ናት፦ የዓለም ሸክም አቅልላለችና በእመቤታችን ትመሰላለች። እመቤታችን ድኅነተ ምክንያታችን ጌታን የተሸከመች ንጽህት እንከን የሌላት እናት ናትና።
7⃣🌿 አንቺ የኢየሩሳሌም ልጅ ሆይ፥ እጅግ ደስ ይበልሽ አንቺ የኢየሩሳሌም ልጅ ሆይ እልል በይ ንጉሥሽ በአህያ ግልገል ተቀምጦ ወደ አንቺ ይመጣል የሚለው ኃይለ ቃል በየትኛው የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ይገኛል???
#መልስ🌿 ዘካ. 9፥9
8⃣🌿 ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ብዙ ያልታሠሩ አህዮች እያሉ ለምን የታሠሩትን መረጠ?
#መልስ🌿✍አህዮቹ የታሠሩት ሌባ ሰርቆ ነው ያሠራቸው። ወንበዴ ሰርቆ ነው ያሠራቸው አህዮቹ ለጌታ ውለታ ሠርተዋል። ጌታ ሲወለድ አሙቀውታልና ለጌታ ውለታ ልንመልስ ያልቻልነው እኛ ሰዎች ብቻ ነን። የታሠሩት እዲፈቱ የመረጠበት ምሥጥር፦ እኔ ከኃጢአታችሁ ልፈታችሁ የመጣሁ ነኝ ሲል ነው። ወንበዴው አህዮቹን ሰርቆ በመንደር እንዳሠራቸው ዲያብሎስም ለሰው ልጅ በኃጢአት ሰንሰለት ከሲዖል መንደር አስሯቸው ነበርና። ሐዋርያቱ ሲልካቸው ምን ታደርጋላችሁ የሚላችሁ ሰው ቢኖር ጌታቸው ይሻቸዋል በልዋቸው አላቸው። የፈጠራቸው እሱ ነውና።

🌿🌿🌿🌿🌿🌱🌿🌿🌿🌿🌿መልካም የሆሳዕና በዓል ይሁንልን።
ሆሳዕና በኣርያም!
ለመላው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነት ተከታዮች ፆሙን በሰላም አስፈፅሞ እንኳን ለብርሃነ ትንሣኤ በሰላም አደረሳችሁ ።
መከራው ክርስትናየን አጣፈጠው
ስደቱ ማህተቤን አጠበቀው
.
.
.
.
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
እንዴት ቆያችሁን ቤተሰቦቻችን በቅርቡ ወደ መደበኛ መርሃ ግብራችን እንመለሳለን እስከዚያ በመምህር ዘመድኩን በቀለ በኩል በረኸኞች ያስተላለፉትን መልዕክት እነሆ።

አንዘናጋ ንስሃ እንግባ
እንጹም
እንፀልይ
እንስገድ
ቅዱስ ስጋውን ክቡር ደሙን እንቀበል
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አማላክ አሜን!!

የጌታችን ጥምቀት

እንኳን ለብርሃነ ጥምቀቱ በሰላም አደረሳችሁ።

ጥምቀት ማለት ቃላዊ ፍቺው መነከር ፣ መዘፈቅ ፣ ውኃ ውስጥ ገብቶ መውጣት ፣ ብቅ ጥልቅ ማለት ሲሆን በምሥጢራዊ ትርጉሙ ግን ከአብራከ መንፈስ ቅዱስ ከማሕጸነ ዮርዳኖስ ከእግዚአብሔር በመወለድ የቅድስት ሥላሴን ልጅነት ማግኘት ማለት ነው። ጌታችን ለኒቆዲሞስ ባስተማረው ትምህርት "ሰው ዳግመኛ ከውኃ እና ከመንፈስ ካልተወለደ በቀር የእግዚአብሔርን መንግሥት አይወርስም።" በማለት ጥምቀት ዳግመኛ የምንወለድበትና የጸጋ ልጅነት የምናገኝበት ርስቱን የምንወርስበት መሆኑን ነገረን። ዮሐ 3፡5

አንድም ጥምቀት ከክርስቶስ ጋር በሞቱ መተባበር ከእርሱ ጋር አብሮ መሞት መቀበርና መነሳት በአዲስ ሕይወት መመላለስ ማለት ነው። ለዚህም ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ በሮሜ መልእክቱ በጥምቀት ከእርሱ ሞትና ትንሳኤ ጋር የምንተባበር መሆኑን ሲነግረን "እንግዲህ ክርስቶስ በአብ ክብር ከሙታን እንደ ተነሣ እንዲሁ እኛም በአዲስ ሕይወት እንድንመላለስ፥ ከሞቱ ጋር አንድ እንሆን ዘንድ በጥምቀት ከእርሱ ጋር ተቀበርን። ሞቱንም በሚመስል ሞት ከእርሱ ጋር ከተባበርን ትንሣኤውን በሚመስል ትንሣኤ ደግሞ ከእርሱ ጋር እንተባበራለን፤" ሮሜ 6:4-5

ወደ ጌታችን ጥምቀት ስንመጣ እርሱ እከብር አይል ክቡር እቀደስ አይል በባሕርይው ቅዱስ የሆነ አምላክ በጸጋ ያይደለ የባሕርይ የአብ አንድያ ልጁ ሲሆን ስለምን ተጠመቀ ብንል

1ኛ ለብዙ ዘመናት ተሰውሮ የነበረውን ነገረ ሥላሴ በገሐድ በግልጽ ያሳውቅ ያስረዳ ዘንድ ነው። ነገረ ሥላሴ በምሳሌ እና በምሥጢር ካልሆነ በቀር በብሉይ በገሐድ ተገልጦ አናየውም። የእግዚአብሔርን የአካል ሦስትነት በጎላ በተረዳ ያየነው በጌታችን ጥምቀት በባሕረ ዮርዳኖስ ነው። እግዚአብሔር አብ በደመና "እርሱን ስሙት" እያለ ሲመሰክር እግዚአብሔር ወልድ በተለየ አካሉ ሲጠመቅ እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ በርግብ አምሳል ሲወርድ ታይተዋል። ማቴ 3:13-17

2ኛ የእኛን ጥምቀት ይባርክልን ዘንድ ነው። ክርስቶስ ከገሊላ ወደ ግብጽ በመሰደዱ የሰማእታት የክርቲያኖችን ስደት ባርኮ ቀድሶ ሲሰጥ ነው። ቁጭ ብሎ ከሊቃውንት እግር ሥር የተማረው የመማርን አገልግሎት ለኛ ለምዕመናን ይባርክልን ዘንድ ነው። የጾመውም ጾማችንን ባርኮ ቀድሶ ይሰጠን ዘንድ ነው። እንዲሁም የተጠመቀው የኛን የክርስቲያኖችን ጥምቀት ይባርክልን ዘንድ ነው።

3ኛ ለኛ አርአያ አብነት ይሆነን ዘንድ ነው። ጌታችን ወደ ዮሐንስ ሄዶ በባርያው እጅ በመጠመቁ ትሕትናን ከእርሱ እንማራለን። እርሱን አርአያ አብነት አድርገን እኛም ወደ ካህናት ወደ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ሄደን እንጠመቃለን። ይህንንም አብነት አድርገው ታቦታቱ ከመንበራቸው ወደ ባሕረ ጥምቀት በመውረድ ጎዳናውንም እየባረኩ ወደ መንበረ ክብራቸው ይመለሳሉ። አንድም መጠመቅ እንደሚገባን እንማር ዘንድ እርሱ ተጠምቆ አሳይቶናል። ጾሞ ጹሙ ፣ ይቅር ብሎ ይቅር በሉ ፣ ትእዛዛትንም ፈጽሞ ትእዛዛትን ፈጽሙ እንዳለን እንዲሁ ተጠምቆም እንጠመቅ ዘንድ አርአያ አብነት ሆነን።

የበዓሉን ዓላማ ተረድተን የዲያቢሎስን ሥራ ድል የምንነሳበት ለክብረ ሰብዕ የምንቆምበትና ከበጎ ነገር ጋር ብቻ የምንተባበርበት ይሆን ዘንድ ምኞታችንን እየገለጽን ቸሩ አምላካችን ለሀገራችን ኢትዮጽያ ጽኑ ሰላምን

አቤቱ የፍቅርና ቸርነት አምላክ ለእኛ ለልጆችህ ተወልደህ እንዳዳንከን ለሀገራችን እና ለሕዝቦቿ ሰላም እና አንድነትን አውርድልን። በዓሉን ስናከብር ላዘኑ መጽናናትን፣ ለታመሙ ምህረትን ለተቸገሩ በረከትን፣ ሰላም ላጡ ሰላምን ያድልልን።
ይቆየን!