Meናgn
33 subscribers
5 photos
Devotion
Download Telegram
Channel photo updated
ለምንድን ነው ቤተሰብ ወይም ወዳጅ ሲሞት የሆነ ክፍላችህን አብሮ ሚሞት።
Channel name was changed to «Meናgn»
የሕይወት ዛፍን ውሃ አናጠጣ
ብዙ ሰወች ስለራሳቸው የማያውቁት ፀባይ በብዙ ምክንያት ሊገለጥ ይችላል ከዛም ውስጥ አንዱ በሀዘን ነው። ሀዘን በኛ ላይ የሚፈጥረው ተፅዕኖ የሚወሰነው በሞት ያጣነው ሰው ጋር ያለን ቅርበት ወይም በኛ ማንነት ላይ ባለው ድርሻ ነው።

ምክንያቱም ሕይወት እንደ አንድ ታላቅ ዛፍ ነው ቤተሰብ እንደ ስር፣ ጓደኞች አንደ ቅርንጫፍ ፣ ወዳጆች አንደ ፍሬ ፣ ልጆች አንደ አበባ ናቸው።
ይህም ማለት "እኔ" ብለን ምንጠራው ማንነት የዚህ ሁሉ ውጤት ነው። የነዚህ ህብረት ነው ሕይወታችን ሙሉ፣ ጠንካራ፣ ውብ አና አላማ እንዲኖረው የሚያረጉት።

ሀዘን ስለሚያሳድረው ተፅዕኖ ስሜታችውን በግጥም ከገሉፁ ገጣሚዎች የተወሰኑትን እንይ።

ጋሽ ፀጋዬ ገብረመድህን ከመጠን ያለፈ ሀዘን ሊያመጣ የሚችለውን የመንፈስ ስብራት በሚገባ ስለተረዳ ይመስለኛል
"የት አባቱ ሞትም ይሙት" በሚለው ግጥሙ ላይ

"... አባካቹህ ዘመዶቸ ስሞት ሞትም አብሮኝ ይሙት
በሳቅ በደስታ ግደሉት በሀሴት በእልልታ ውገሩት
አባካቹህ ወገኖቼ ለሞት የልብ ልብ አትስጡት..."

በማለት ፍልስፍናዊ ምክሩን አስነብቦናል።
በእውቀቱ ስዩም ልክ አንደ ጋሽ ፀጋዬ ሞትን የልብልብ ላለመስጠት አስቦ ሞት የማይቀር ነገር መሆኑን በሚገባ የተረዳ ቢሆንም አህቱ ለመውለድ ሆስፒታል ገብታ በቃሬዛ ወደቤት ስትመለስ የተሰማውን ሀዘን "በሞቷ ፊትለፊት" በተሰኘው ግጥሙ ላይ

"... ምን አሽዋ ቢያልቡ ንፋስ ቢጋልቡ
ደመናውን ጠርበው ሃውልት ቢያስገነቡ
ሞት አና ክስመት ነው የተፈጥሮ ግቡ ብዬ አንዳልጽናና ሃሳብ ሁሉ መና ምክር ሁሉ ኦና
እንባን አይገድብም የሰው ፍልስፍና..."

በማለት ከበድ ያለ ሀዘን ሲገጥመን የሰው ፍልስፍና እና ምክር ከዘናችን በቀላሉ ሊያፅናናን አንደማይችል ተናግሯል።

ጠንከር ያለ ሀዘን ስለ ሞት አና አጠቃላይ ስለ ዓለም ያለንን አመለካከት የመቀየር አቅም አለው። በተለይም የፈጣሪን ህልውና ጥያቄ ውስጥ ጥሎብን ሊያልፍ ይችላል።

አፄ ቴውድሮስ ታላቆን የኢትዮጵያ አንድነት ለመመለስ ጎጃምን ለማስገበር ባደረጉት ጦርነት ባሏ በጦርነቱ ላይ የሞተባት፣ ከዛም ወንድሟን አና አባቷን በስቅላት ፍርድ ያጣችው ወ/ሮ ምንትዋብ የደረሰባትን ከባድ ሀዘን

" ... ጠጂም አያምረኝም ድሮ ጠጥቻለሁ
ስጋም አያምረኝም ቋንጣ ሰቅያለሁ
ቢሻኝ ከወንድሜ ካባቴ እበላለሁ... "

በማለት የቤተሰቦችዋ ሞት ምን ያህል አንደጎዳት ከገለፀች በሁላ አንዲህ በማለት ንጉሱን ተሳደበች

"ሽ ብረት ከግራው ሽ ብረት ከቀኙ ፣
ሽ ፈረስ ከሁላው ሽ ፈረስ ከፊቱ
አሄን ሳታይ ሞተች ኮሶ ሻጭ እናቱ
አንድ አግር በርበሬ መንቀል ተስኗቹህ
አቃጥሎ ለብልቦ ፈጅቶ ይግደላቹህ...

ንጉሡ እሂን ስድብ ሲሰማ ሊገላት አንደሚችል ታውቃለች ቢሆንም ግን የሀዘኗ ጥልቀት ስለሞት ያላትን አመለካከት አንዴት አንደቀየረው በሚከተለው ግጥሟ ላይ

እሂንን ሲሰማ ያጓራል አመሉ
ማናት ቢላቹህ ምንትዋብ ናት በሉ

በማለት ሞትን አንዴት ቀድማ አንደገደለችው እናያለን።

ታላቁ ደራሲ Dostoevsky "The Brothers Karamazov"
መፀሐፉ ላይ መሰረታዊ የሆነ ጥያቄን ያነሳል መከራ አና ሀዘን በህፃናት ላይ ለምን ኖረ በማለት?
በ ሀልዎተ ፈጣሪ የሚያምኑ ሰወች "ፈጣሪ የራሱ እቅድ አለው፣ የሱን አቅድ እኛ መረዳት አንችልም" ይላሉ።
ኢ-አማኞች ግን "የህፃን መከራን የሚጠይቅ እቅደ እንዴት ሊኖር ይችላል?" የሚል ሃሳብ አንስተው ይሞግታሉ።
የሁለቱንም ሃሳብ በደንብ ተረድታቹህ መገላገል የምትችሉ ሰዎች ካላቹህ ገላግሏቸው።

እንደ Dostoevsky አመለካከት አንደዚህ ያሉ ሃዘን አና መከራወች በእርጋታ አና በጥንቃቄ ካየናቸው ወደ መንፈሳዊ እድገት አና ወደ ፈጣሪ ያቀርበናል ብሎ ያስባል።

ባለቅኔ ሙሉጌታ ተስፋዬ (አያ ሙሌ) አመለካከት ግን ብዙም ተቀባይነት ያለው አይመስልም። አያ ሙሌ የእርዳታ ድርጅት ውስጥ በሚሰራበት ወቅት ወሎ ውስጥ ህፃናቶች በርሃብ ሲሞቱና ሲሰቃዩ ሲያይ Dostoevsky አንዳለው ወደ ፈጣሪ ሊቀርበው ይቅርና በፈጣሪ ህልውና ላይ ጥያቄ እንዲፈጠርበት አርጉታል።

አያ ሙሌ "አውነት ከመምበርህ የለህማ" በሚለው ግጥሙ ላይ

ናዳ አንደሚጥል ጭላዳ... ድርቅ ሲሳለቅብን
እየናደ አያነደደ... የጎመራ ድኝ ሲለቅብን
እያየህ ዝም ካልክማ
እውነት... እውነት ከመንበርህ የለህማ ጀንበር ትንታጎአን እረጭታ... ሰብ አለሙን ስትፈጀው
አብ ወልዳ ቃልህ ካልበጀን
ድርሳን ትንቢትህ ካልዋጀን
አንተስ ምንህ መለኮት... አኔስ ለምን ያንተ ባርያ
ሆዴን ሁዳዴን ላምልክ አንጅ ትንሣኤ አንደሌለው እሪያ
ያንተን ጉድማ አየሁት
ያንተን ገድልማ ለየሁት
ማረኝ ሲሉት የሚመራ... የማይታደግ አላመልክም
ወትሮም የተማረ ቄስ አንጅ... የሰው ልጅ መላክ አይልክም

በማለት እውን ፈጣሪ ቢኖር ያለምንም ጥፋታቸው ህፃናቶች በድርቅና በቸነፈር ሲሰቃዩና ሲሞቱ እያየ ዝም አይልም ነበር በማለት ለጊዜው ቢሆንም ጠንከር ያሉ ኃይለቃሎችን እየተጠቀመ የፈጣሪን አለመኖር ፣ ቢኖርም አንደዚህ አይነት አምላክ አላመልክም ይል ነበር።
በሀዘን ግዜ እና በቀብር ስነስርዓት ላይ ኃይለቃሎችን አየተጠቀሙ ፈጣሪን መዳፈር በታሪክ አንደነበር ሽብሩ ተድላ "ከጉሬዛም ማርያም እስከ አዲስ አበባ" በተሰኘው መፅሐፉ ላይ በስፋት አስነብቦናል።
ሀዘንን በማባባስ ወዳልተፈለገ ከፈጣሪ ጋር ፀብ ውስጥ ከሚያስገቡን ነገሮች ውስጥ አንዱና ዋነኛው ፀፀት ነው። ከቤተሰቦቻችንና ከዎዳጆቻችን ጋር ብዙ ጥሩ ግዜያትን ሳናሳልፍ የሞት መላአክ ከቀደመን በሀዘናችን ላይ ሌላ ፀፀት ተጨምሮበት ከፈጣሪ ጋር ሆነ ከራሳችን ጋር ያልተገባ ፀብ ውስጥ እንገባለን።

መናኙም አለ "በጃችን ያለው የሕይወት ዛፍ በውሃ እጥረት ከመድረቁ በፊት ለቤተሰቦቻችን እና ለወዳጆቻችን በቂ ግዜን ፣ ፍቅርን ፣ አንክብካቤን በመስጠት የሕይወትን ዛፍ ውሃ እናጠጣ"


Walk in faith and love until next post, stay blessed.
የሐምሌ አፈር ብሶት

My friend is a good farmer and we often talk about farming. coz Agriculture is my DESIRED work. I love the idea of growing food and working with nature. But in reality, I spend my days with computers, working with 0s and 1s.

Anyway, he always tells me how fertilizer is taking over the land and making the soil weak. I talked about this with another friend, and he told me how fertilizer started... I forgot the full story but it was funny because it was initially invented for bombs. and today I wanted to know when it started in Ethiopia.
I'm not talking about when bombs started! 😂"

It started in the 1950s but it spread everywhere in the ‘90s around the time we were born. At first farmers thought it was good. It made crops grow fast and big. But over time, the land changed. The soil lost its natural power.
What was once a help has become a completely dependent. We have a nice and beautifully

I see life in the same way. We chase desire thinking they will make us happy. At first, they do. But soon, we need more and more. Just like the soil, our hearts become weak. We keep chasing, but we are never happy.

Holy scriptures tell us that humans were created last, after everything else. This means we shouldn’t chase after everything in the world but should instead take care of what has already been given to us.


"ያሳደኩት ውሻ ነከሰኝ
ያነደድኩት እሳት ጠበሰኝ"

Until next post, stay blessed.
የሰው ልጅ ሕይወት በምን ዋጋ ይለካል?

በተጠናቀቀ ስኬት፣ በተሟሉ ህልሞች፣ ወይስ በማያቋርጥ እራስን ፈለጋ ውስጥ?
ድግስ 11:45 ላይ

አንዳንዴ ጥልቀት ያለውን ነገር ለመረዳት በማንችልበት ዕድሜ ላይ፣ የበሰሉ ሰዎች የሚናገሩትን ጥልቅ ሃሳብ በስህተት እንደ ቀልድ እንረዳዋለን ወይም ሳንገነዘበው አናልፋለን። አንዳንድ ሀሳቦች ግን ጊዜ ጠብቀው ነገሮችን ማስተዋል ስንጀምር ከዚህ በፊት 'ተራ ነው' ብለን ያልፍንቸው ንግግሮች ሙሉ አቅማቸውን ይዘው አንዳዲስ ሊሞግተን ይከሰታሉ።

በ 18 አመቴ ላይ ይመስለኛል ብዙ ሞያዎች ያሉት አንድ ጓደኛዬ ጋር ሬድፎክስ የተባለ ሆቴል ለሥራ ሄድን። ሥራችን ከጨረስን በኋላ የሆቴሉ ባለቤት በግድግዳ ላይ አንድ ትልቅና የሚያምር ሰዓት እንድንስቅልለት ጠየቀን። ሰዓቱ የማይሰራ ነበር ግን ከባዶ ቦታ ይሻላል ብለን ከሰቀልንለት በሁላ...

ጓደኛዬ:- 'እንዴት አየህው?' ሲል ጠየቀ።
ባለቤቱም:- 'በጣም ውብ ነው… ግን…' በማለት ተናገረ።

ምንሊል ይሆን ብዬ ስጠባበቅ... ችግር ብሎ ያነሳው ሰዓቱ 12:00 ላይ መሆኑን ነው።
ባለቤቱም:- '11:45 ላይ አርገው ሕይወት ሁልግዜም እሩብ ጉዳይ ለ 12:00 ነው ማንም ሙሉ የሆነለት የለም' አለ። በግዜው ምንም አዚህግባ የሚባል ንግግር ሁኖ አላገኘሁትም ብቻ ሩብ ጉዳይ አርገንለት ወጣን።

ሰሞኑን ከብዙ ዓመታት በሁላ እንደቀልድ የሰማሁት ንግግር እንዳዲስ ሙሉ አቅሙን ይዞ ሊሞግተኝ ተከስቷል።

እውን 12:00 ሰዓት የሞላለት ሰው ይኖር?
ሰው 100% ተሳክቶለታል ምንለውስ በምን መስፈርት ተለክቶ ነው?

አብዛኞቻችን ሙሉ የሆነ ሕይወት አንዲኖረን ነው ፍላጎታችን እንከን የሌለው ጕደኝነት፣ ቅዱስ የሆነ ትዳር፣ ከሃሳብና ጭንቀት ነፃ የሆነ ሂዎት፣ የሚገርም ማንነት አንዲኖረን ነው ድካማችን ነገር
ግን ገአዱ ዓለም አንደዛ አይደለም ሚሰራ።

ፍፁም የሆነ የተሳካ ሕይወት የለም፣ የማይጨበጥ ሕልም ነው።
ምን ያህል የተሳካልን፣ የተወደድን፣ የበቃን ቢመስለንም አንድ ባዶ ገፅ፣ የጎደሉ ፊደሎች ይኖራሉ። የምንፈልገው ስራ ከጭንቀት ጋር፣ የምንወደው ቤተሰብ ከስጋት ጋር፣ አኛም ስህተትን አንሰራለን።
የራሳችን ሆነ የሰውን መስቀል መሸከማችን የማይቀር ነገር ነው።

አኛም የሰውችን ሕይወት እያየን እንከን የሌለበት የተሳካ ሕይወት ነው ሚኖሩት ምንለው በኛ ወይም በማህበረሰቡ እይታ (Social validation) በተቀመጡ መስፈረቶች እየዳኘን፣ ስኬታማ ሕይወት እንላለን አንጅ ለነሱ ግን በተቃራኒው ነው።

ገጣሚው አያ ሙሌ:- "ጥበበኛውን አለማወቅ ገደለው"
ብሎ በሰየመው ግጥሙ መግቢያው ላይ...

"መስፍን ነበረ
በቀለም ምትሀት የሰከረ
ውበትን በስእል... እውነትን በቃል የመሰከረ
በሙዚቃ ቋንቋ የቀዘፈ
በዋለ ባደረ መጠን... አንደ ሰማአት ገድሉ
የገዘፈ
አጥቢያ በዘለቀ
ጀንበር በጠለቀ...
ለኛ ይበቃል ስንለው.... ለራሱም ሳይበቃ
<አለቀ>  

በዚህ ግጥም ላይ አያሙሌ እንደገለፀው ማህበረሰቡ እይታ የበቃ ነው ብለን የምናስበው ሰው ለራሱ ሳይበቃ ያልፋል።

የተሳካ ሙሉ ሂወት ብሎ ነገር የለም እሱ ከንቱ ህልም ነው።
ስኬትም ቢሆን ወደ ሌላ የስኬት መንገድ የሚወስደን እንጅ ብቻውን የሚቆም ነገር አይደለም።

ገጣሚ አና ሙዚቀኛ Leonard Cohen "Anthem" በሚለው ሙዚቃው ላይ አንዲህ ባጭሩ ገልፆታል...

"There is a crack in everything,
that is how the light gets in"

በሕይወት ውስጥ የሚገጥሙን ተግዳሮቶች ለስኬት፣ ለጥበብ፣ ሕልሞቻችን ለማሳካት እና አጠቃላይ አዎንታዊ ለውጥ አንድናመጣ የሚረዱን የሕይወት ድግሶች ናቸው።

በገነት ውስጥ እንኳ ፍጹምነት አልነበረም። አዳምና ሄዋንን ተመልከቱ ችግር፣ ህመም ወይም መከራ በሌለበት በገነት ውስጥ ይኖሩ ነበር። ሁሉም ነገር አላቸው ነገር ግን አንድ ዛፍ እርም ነበረ። ፍጹም በሚመስል ሕይወት ውስጥ እንኳ ገደብ ነበረ።

የሕይወት ውበት ያለው 11:45 ላይ እንጅ በፍፁምነት ላይ አይደለም። አበው "ፈጣሪ ሳይደግስ አይጣላም" እንደሚሉት እያንዳንዱ ጉድለት አዲስ ተስፋን የሚከፍት መስኮት ወይም ፈጣሪ ወዳዘጋጀልን ድግስ የሚያደርሰን መንገድ ነው።

ስለዚህ ሕይወት ሙሉ ምትሆነው...
በጉድለት ውስጥ ነው።

"መልካም ጎዶሎነት"
ምግብ ወይም ህይወት? የፋሲካው በግ ድምፅ


ከአንድ ትንሽ በረት ውስጥ 11:45 ላይ በሰላም ነው የተወለድኩ። 
አንዳንዶች "ንፁህ" ብለው ይጠሩኛል ፤ አብዛኛዎቹ ግን "ጤና-አዳም" ነው የሚሉኝ።  

   ለሁለት መንፈቅ ያህል እንደ ማንኛውም ሕጻን በእናቴ እጅ በፍቅር አደኩ። ከዛም እስከ ዛሬዋ ቀን ድረስ ከአባቴ ጋር ቆንጆ ጊዜን ለብቻችን አሳለፍን።  

    ዛሬ ግን… እራሴን ከገበያ መሃል አገኘሁት። የማላቃቸው ሰውች ቀረቡኝ እጃቸውንም በእኔ ላይ ጭነው ያዙኝ፣ አነሱኝም ክብደቴን ገመቱ.. ወደዱት፣ ላቴን አዩ እንከን የላቸውም፣ ጥርሶቸ "ንፁህ ናቸው" ሊወስዱኝ ተስማሙ... ከሁሉም በጎች ለይተው እኔን ለመስዋእትነት መረጡኝ። 
   
   ምንም ጥፋት አላጠፋሁም፣
   የበረት አጥር አልዘለልኩም፣
   ማንንም ሰው አልተዋጋሁም... አልበደልኩም። 
 
    ሆኖም ግን ያበሉኝ፣ ያጠጡኝ፣ የተንከባከቡኝ ቤተሰቦቸ ካዱኝ
እግሮቸን በገመድ አስረው ለባለጊዜ አሳልፈው ሸጡኝ።  

ሊገሉኝ አንደሚወስዱኝ አውቃለሁ ሁኖም ግን አላለቀስኩም ፣ ብዙም አላዘንኩም ፣ ለማምለጥም አልሞከርኩም ፤ በፍቃደኝነት ሄድኩላቸው ምክንያቱም መጨረሻችን እንዲህ አንደሚሆን አባቴ ነግሮኝ ነበር።  

"በግ" የሚል ስያሚ ተሰጦን፣
ያለ ኃጢያታችን እንድንሞት ነው የተፈጠርን።

ሰወች ያለኔ ስጋ
በፆም፣ በፀሎት፣ በስግደት የወደቀ ስጋቸው አይጠገንም ፤
ያለኔ ደም ጉሮሮቸው አይርስም። 

   እኛም እንደነሱ ቤተሰብ ያለን፣ ፍቅር እና ደስታን የምንሻ አንደሆንን ያውቃሉ ነገር ግን ነገ "ፋሲካ" የሚሉት በዓል ነው... የድህነት ቀናቸው ማለት ነው ለራሳቸው ደስታ ነው የኛን ደስታ የምነሱን።

 አንዴት ግን ሰወች ከሞት ወደ ህይዎት የመጡበት ቀን  ለማክበር...
ሌሎች ፍጥረታትን ከህይዎት ወደ ሞት የሚልኩበት ቀን ሊሆን ቻለ።

 በየበዓሉ እኔን የሚመስሉ እልፍ አእላፍ በጎች ይሰዋሉ... ድምጽ የሌላቸው ንጹሃን በጠረጴዛ ላይ፣ ከሳህን በላይ ይቀራሉ።

ሁሌም በእያንዳንዱ በግ መስዋእትነት ውስጥ የማይነገር ሐዘን አለ። የኔ ታሪክ ግን ስለ ምግብ ብቻ አይደለም።

በሰላም ነው የተወለድኩት
በደም ነው የተመለስኩት
The thumb gave us power but now it takes it back with every swipe
አውራ-ጣት

  በአብዛኛው ሃይማኖቶች ውስጥ ከሚገኙት ተመሳሳይ መሠረታዊ ነገሮች ውስጥ ሰይጣን፣ ነብስ፣ እና የአለም አስተዳደር ለሰው ልጅ የመፈቀዱ ጉዳይ ነው። በቅርቡ ስለ ነብስ በሰፌው እመለሰላሁ ፤ ዛሬ ስለ ሰው ልጅ አስተዳደር እናውራ።

    ፈጣሪ ሰውን እንዲያሰተዳደር በፈጠረን ጊዜ፣ ከሌሎች ፍጥረታት በላይ የሚያስቀምጠንን አካላዊ ግዙፍነት አልሰጠንም። በማሽተት ከውሻ፣ በማየት ከንስር፣ በመስማት ከሌሊት ወፍ በላይ አልነበርንም። በርግጥ አብዛኛውችን በማሰብ እና በአመክንዮ እንበልጣቸዋለን።

   የዓለም ስልጣኔ ቀይረዋል ተብለው ከሚነሱት ነገሮች በዋነኝነት የሚጠቀሱት እሳት እና ቋንቋ ናቸው ። ብዙም ካልተወራላቸው ግን ለዓለም ስልጣኔ ግንባታ ትልቁን ድርሻ ከወሰዱት አንዱ አውራ-ጣት ነዉ።

     አዎ ትንሹ የጃችን እጣት ከሌሎች አጠር ወፈርና ገንጠል ብሎ ያለው ግን ተአምር ለመስራር ከተመረጡት ዋነኛ መሳርያውች ውስጥ አንደኛው ነዉ ብለው ብዙወች ያምናሉ።

"The hand of man has become the perfect instrument for grasping, owing in part to the great freedom of movement in the thumb…”
Charles Darwin,

   አውራ-ጣት ከጃችን ላይ ያለው አቀማመጥ (Biological structure) የፈጣሪ ጥበብ ማሳያ እና ለሰው ልጆች ከተሰጡን የፈጣሪ ስጦታወች ዋነኛው አንደሆነ ብዙወቹ ይገልፃሉ።

    በእውነቱ አባቶቻችን የዚህን ጣት ኃይል በግልፅ ሚስጥሩ ተገልፆላቸው ይመስለኛል.. እንደ አእምሮ፣ ልብ፣ ኩላሊት እና አይን ባሉበት የሰውነት ክፍሎች ይህን ትንሽ ጣት መርጠው አውራ ብለው የገዢነት ስም የሰጡት።

"In the absence of any other proof, the thumb alone would convince me of God’s existence."
Isaac newton, እንደተናገረው ይገመታል።

   ይህ ጣት ብቸኛ አይደለም፤ ነገር ግን ከሌሎች ጣቶች ጋር በመስራት፣ የሰው ልጅን ከሌሎች ፍጥረታት የላቀ የሚያደርገው የብልህነት ምልክት ነው።  የተለያዩ መሳርያወችን እንድንጠቀም የዋሻ ፁሁፎችን እና ሰእላትን አንድናስቀምጥ ሃሳቦቻችን ወይም ፈጠራን ለመተግበር የምንጠቀምበት ትልቁ መሳሪያችን ነዉ ።

  ፈጣሪ በትንሽ ነገሮች ታላቅ ነገር መሥራት የሚችል አምላክ እንደሆነ ይህ ጣት ያሳያል። እሱ ከብዛት ይልቅ ጥራትን፣ ከኃይል ይልቅ ብልህነትን የሚያስቀድም አምላክ ነው። ለዚህም ማሳያ የሚሆነን፣
 
ጎልያድን በሳምሶን እንዲሸነፍ ባደረገው ነበር... ዳዊትን ትቶ፣
ለሙሴ የኖህ መርከብን በሰጠው ነበር... በትሩን ትቶ፣
ልጁን...

   ይህ የፈጠራወች ሁሉ ጌታ የነበረው መሳሪያችን ዛሬ...
    ፈጣሪነቱን ረስቶ፣
    ኃላፊነቱን ዘንግቶ፣
    አገልግሎቱን ችላ ብሎ
የእስክሪን ባርያ ሁኖ እያየነው እንገኛለን።

   የሰው ልጅ ታሪክ ሁሉ በአውራ ጣቱ ዙሪያ የተሽከረከረ ነው። አሁን? ይህ ጣት የሚሰራው ዋናው ስራ የእስክሪን መንካት ብቻ ሆኗል። ይህን በዘመናችን ፈልስፍና ከተመለከትን፣ አውራ ጣታችን የፈጣሪን ብልህነት ከሚያሳይበት ይልቅ የቴክኖሎጂ ባርነት ምልክት ሆኗል።  

ቁጭ ብለን ማሰብ፤ ወይም ከቤተሰቦቻችን ጋር መጫወት ሲገባን አውራ-ጣታችን vedio scroll ሲያረግ ይውላል፤
የቤተሰቦቻችን እና የጉደኞቻችን እጅ ይዘን ከነሱጋ በአካል አብሮ መዋል ሲገባን አውራጣታችን remot ይዞ ይውላል፤
እግር ኳስ መጫወት ሲገባን... ሶፋላይ ተቀምጠን እግር ኳስ ስናይ፣ PlayStation ስንጭዋት አንውላለን። 

  በሌላ አነጋገር፣ አውራ ጣታችን ነፃነታችንን አጥፍቶ ዘመናዊ ባርነትን ፈጥሯል። ፈጣሪ የሰጠንን ይህን ኃይል በአግባቡ የምንጠቀምበት ዕድል እየቀነሰ መጥቷል።  ጣታችን የሚያደርገው ነገር ሰው እንድንሆን ወይም ሮቦት እንድንሆን የሚወስነው ባለ-ግዜ ሁኗል።


አውራ-ጣት ፈጣሪ ያጎናፀፍን መሳሪያ ነች፤ መሳሪያውን በመጠቀም መገንባት ወይም ማፍረስ የተሰጠው ለኛ ነው።
የሰዉነታችን ጥላ ክፉላችን ዉስጥ ሲጠፉ ወይም ስናጣዉ… ክፍሉ ብርሃኑን አጣ ነው የምንለዉ ወይስ ሁልጊዜ ልናየዉ ያልቻልነውን ነገር ገለጠልን?
SHADOW

Sometimes I wonder when a shadow drifts away, does the room lose its light? At first, it might feel like something’s missing, like a part of the world has dimmed. But the truth is, the light was never really gone. It was there all along just waiting for me to notice it.

Shadows have a way of hiding things. They hide little truths, quiet moments, and the simple beauty that surrounds us every day. And when the shadows finally leave, it’s like seeing for the first time what was always in front of us.

Darkness doesn’t take anything away. it teaches us where to look. It reminds us to pay attention, to pause, and to appreciate what we might have overlooked. And sometimes, the lessons we only see in the absence of light turn out to be ones that matter the most.
ጥበብ መንፈሳዊ
“ሙሴ ፈጣሪውን ፈጠረ?”

ስነ-ጥበብ በኢትዮጵያ ከዘመናት በላይ ሕይወት ያለው ትውፊት ነው። ከዚህም ውስጥ ቅኔ ለኢትዮጵያ ልዩ ስፈራ አለው። የላቀ እውቀትን የሚያሳይ፣ ህብረተሰብን የሚያነቃቃ፣ እውነትን የሚጠብቅ የሕይወት ፈልስፈናዊ መንገድ ነው።

አበው ሰለ ቅኔ እንዲህ ይላሉ፦

“ስነ-ግጥም ወይም ቅኔ የስነ-ፅሁፍ ወይም ስነ-ጥበብ፤ የፈጠራ ሁሉ የደም ጠብታ ነው።”

ይህ የስነ-ጽሁፍ ሥርዓት በአመክንዮ ማብራሪያ ሊገለፁ የማይችሉ ጥልቅ ፍልስፈናዊ ሀሳቦችን የሚያቀርብልን ምስጢራዊ ፈረሰኛችን ነው።

ስለ ቅኔ ሸገር ሸልፍ ላይ የሰማሁትን አንድ ታሪክ ልንገራቹህ።

አንድ የቅኔ ተማሪ ወደ የኔታው ቀርቦ እንዲህ አለው፦
«ቅድም የዘረፉትን ቅኔ ሰምቻለሁ፤ በውነቱ ይበል የሚያሰኝ የሚያስገርም ቅኔ ነው!» አለ።

የኔታም በስጨት ብሎ አንዲህ መለሱለት፦
«አንተማ ከሰማህኝ ምኑን ተቀኘሁት?»

ጥሩ ቅኔ ሁልጊዜ ሁለት ሃሳቦችን ይይዛል፦ ግልጽ የሆነ መለእክትና የተደበቀ ምስጢር። የቅኔው ሀያልነት የሚለካው የቅኔው ምስጢር በቀላሉ ካልታወቀ ነው።

ለዚህም ነው ሊቃውንት ለዘመናት በዚህ ሚስጥራዊ ጥበብ ነገስታትን ሲገስፁ፣ ፈጣሪን ሲሞግቱ ፣ እውነትን እና የህይወትንም ምስጢር ሲመረምሩ የኖሩት።

እምነት ያለዉ ወይም አማኝ የሆነ ሰው በእምነቱ በኩል የሚመጡ ሀሳቦች አሜን ብሎ የመቀበል ዝንባሌ ይታያል። በቅኔ ውስጥ ግን አሜን ብለን ከተቀበልናቸው ሀሳቦች ጀርባ ያለዉን እውነት ይጠይቃል ይመረምራልም።

ለዚህም ማሳያ እንዲሆነን በፈጣሪ መኖር አብዝተው ከሚያምኑ የቤተክርስቲያን አገልጋዬች የተዘረፏየተወሰኑ ቅኔወችን እናንሳ።

*"ሰዎች የወለዳችሁትን ልጃችሁን አትመኑ፣*
*የወለደች ማርያም እናትን፤
*የወለደችው ልጇ ገላቷልና።"*"

በዚህ ቅኔ ላይ ሞት ለሰው ሁሉ እኩል የተሰጠ መሆኑንና በዚህ ፍርድ ውስጥ ያለውን የፈጣሪ ፍትሀዊነት ከዘመኑን ከሃዲ ትውልድ ጋር አያይዘው አንዲህ ተቀኝተዋል። ሁኖም ግን በሌላ ቅኔ አለቃ ገብረሃና የፈጣሪን የሞት ፍርድ ቅጣት በመጠየቅ (በመቃወም) በሚከተለው ቅኔ ፈጣሪውን አንዲህ ሞግቶታል፦

አንተ ጠላቶቻቹህን ውደዱ ትላለህ
አንተ ደሞ ጠላቶችህን ታጠፉለህ
ስለዚህ ምንድን ነህ… አንተ።

በማለት እኔ ክርስቶስን እንደምመስል እናንተም እኔን ምሰሉ እንዳለው ዻውሎስ፤ እኛም አንተን ለመምሰል ትእዛዝህን ስንፈፅም አንተግን የራስህን ትእዛዝ አትፈፅምም ሲል በቅኔ ፈጣረውን ሲሞግት እናየለን።

ሚስጢር?

አንዳንድ ቅኔወች ወ‍ስብስብ እና ሚስጥራዊ ከመሆናቸው የተነሳ ትርኀሜቸው አሻሚ እንደሆነ ዘመናትን ሊያስቆጥሩ ይችላል። ምክንያቱም ቅኔወች ጥልቅ የሆኑ ስሜታዊ እና መንፈሳዊ ጥያቂወችን በአጭር ፈልስፈና ስለሚቀርቡ ነው።

ገጣሚው በውቀቱ ስዩም ሲናገር፣ *"ቅኔ ምናባዊ መገለጥ እና ያልተንዛዛ ፍልስፍና ነው"* ይላል።

ዘመንን ካስቆጠሩ ትርጎሜቸው እስካሁን አሻሚ ሁኖ ከሚያከራክሩ ቅኔወች ውስጥ ዋነኛው የቅኔው ሊቁ ተዋነይ ስለ ፈጣሪ የተቀኘው ነው።

“የአምን ወይገኒ ኵሉ ዓለም በዘፈጠረ ለሊሁ
ካልኣን እንዘ ይትኤዘዙ ይሰግዱ ቅድሜሁ
ለጠይቆ ዝኒ ነገር ከመ እስራኤል ይፍርሁ
ሙሴ ፈጠረ ፈጣሪሁ፣ ወፈጣሪ ፈጠረ ኪያሁ።”

(ትርጉም)

“ዓለም ሁሉ ራሱ በፈጠረው ያምናል፤ ይገዛልም
ሌሎች እየታዘዙ በፊቱ ይሰግዳሉ
ይህንን ነገር በመረዳት እስራኤል እንዲፈሩት
ሙሴ ፈጣሪውን ፈጠረ
ፈጣሪም እሱን መልሶ ፈጠረው።”

ሊቃውንትም ይህ የተዋነይ ቅኔ ፈጣሪ መኖሩን የሚገልፅ ነዉ ብለዉ የቅኔውን ትርጎሚ ቢያስቀምጡም፤
በሌላ በኩል ግን እግዜር የሙሴ ፈጠራ ነው የሚሉም አሉ። እንዲያውም በዚህ ቅኔ “እግዜርን የሙሴ እጅ ሥራ አድርጎ መግለጡ ብቻ ሳይሆን፣ የፈጠረበት መነሻ የማስገበር ፍላጎት መሆኑን አስቀምጧል” ሲል በዉቀቱ ስዪም ይህ ቅኔ ተዋነይ በፈጣሪ ላለማመኑ የሰጠው ምክንያት ነው በማለት አንድምታ መፅሄት ላይ በሰፊው አብራርቷል።

ቅኔ ሚስጥሩ የሚፈታ ወይም የማይፈታ (እስካሁን ያልተፈታ) ተብለዉ ይጠቀሳሉ። የ‍ተዋነይን ቅኔ ቤተክርስቲያን ሚስጥሩ ይፈታል የፈጣሪ መኖርን የሚገልፅ ነዉ ሲሉ ፤ ኢ-አማኞች በተመሳሳይ ሚስጥሩ ግልፅ ነው የፈጣሪን አለመኖር የሚያሳይ ነው ይላሉ።

ምናልባት ይህ ምስጢር እስካሁን አልተፈታም ብላቹህ እንዴት ትፈቱት ይሆን? ተመራመሩበት።

ለስንብት ይችን ቅኔ ጀባ ልበላቹህ

“አባ ግራኝ ሞተ የሆዴ ወዳጅ
የሚያበላኝ ስጋ የሚያጠጣኝ ጠጅ"

Until next post, stay BLESSED.



“Tat Tvam Asi”
Have you ever wondered where a single drop of water travels, how it falls from the sky as rain, gathers in rivers, seeps into the earth, evaporates, rises again as a cloud, and begins its journey again and again?
When a child knows something they shouldn’t know. My grandmother taps her head and says, “This child has been here before.”
she maybe right. Sometimes you meet someone and your spirit says, “Ah, there you are” It’s not your first meeting, your souls have known each other from another time.

It’s a little like the water we drink. The same water has flowed through rivers, evaporated into clouds, and fallen as rain for generations an endless journey that quietly connects the present to the past. Every drop carries a story of where it has been.

Perhaps our lives move in a similar way. Our experiences, our connections, and even our selves carry echoes of what came before, shaping what comes next. In Indian philosophy, this is called samsara the cycle reincarnation - birth, life, death, and rebirth. Like water, our souls keep flowing, returning, and touching the lives of those who come after us.

Every life is a lesson. Some souls are still learning, others are almost done slowly gathering wisdom from each lifetime before finally finding rest.

Imagine one soul who was first a quiet monk, then a busy imam, and now an atheist making jokes about both. Life really played with him, looks like samsara has a sense of humor. but maybe we are all a little like him:

believing one day,
doubting the next,
laughing about it later.

You know that feeling?
When you look at someone and for just a second, it feels like you have known them forever.
It’s like your soul recognizes theirs.

I look at my friends, and I can see their old souls hiding inside them. they look ordinary, but inside they are from other lives.

One of them is like Tesla riding a lion - smart, full of energy, always curious. No plate in the room survives when he is around. he eats like he’s saving energy for his next life.

Another one? Definitely Leonardo da Vinci on an owl - full of ideas, always observing, experimenting with life is mysteries since teenage.

And then there is him - Galileo Galile on a wise wolf - sharp, thinking ten steps ahead, sometimes even telling the stars to keep quiet during his cosmic meetings.

Augustine on a clever fox - spiritual, wise, and independent. He avoids poetry because rhymes are too risky, so he just writes however he feels.

Indiana Jones on an eagle - creative, bold and fast. He loves studying the world so much, when he saw the cafes map hanging upside down, he got so annoyed he walked out and skipped breakfast.

And finally, Atman on a Dove - she sees how Maya tricks everyone, but stays completely above it.
She drinks water, closes her eyes like she is tasting truth and says, “What an amazing coffee.”
Then she smiles because she knows the difference, but chooses peace.

And thinking about them, I realize it’s the same for all of us. Everyone we meet carries little pieces of their past lives the laughter, the curiosity, the quiet wisdom we can sometimes feel without knowing why. maybe we have all lived other lives, worn different faces, learned the same lessons again and again until we finally get them right.

Sometimes you feel it like a secret wink from the universe saying, “Hey, you and me… we’ve done this before.” Maybe it’s déjà vu, or maybe our souls just remembering.

Life isn’t about being perfect it’s about learning.
We’re all souls figuring things out.

So don’t judge too fast karma has a funny way of flipping the script. All you meat lovers might come back as sheep, and I might return as an onion… or maybe a chicken. Who knows? Samsara loves surprises and karma’s got jokes too.
ከጥላው ወደ አካሉ (ባለ-ሀገር)

ከእግር ጉዞ ወደ ነፍስ ጉዞ፦ የሁለት ሺህ ዓመታት የነፍስ ስደት

​ኑ፣ ወደ አያቶቻችሁ ቀየ አብረን አንሰደድ...

​ሰዎች ስለ "የጊዜ ጉዞ" (Time Travel) ሲያወሩ እንደ ተረት ሊቆጥሩት ይችላሉ፤ እኔ ግን ያንን ድንቅ ጉዞ በተግባር አይቸዋለሁ። በመኪና ተጉዤ፣ ከዚያም ለሁለት ሰዓት ያህል በዱር በገደሉ በእግሬ ስጓዝ አንድ እውነት ተረዳሁ። ያ የሁለት ሰዓት የእግር ጉዞ ወደ ሌላ "ቦታ" ብቻ ሳይሆን፣ ወደ ሌላ "ዘመን" የተሻገርኩበት የነፍስ ቀጭን መንገድ ነበር። በእያንዳንዱ እርምጃዬ ከዘመኑ ጫጫታ እየራኩ፣ ወደ ሁለት ሺህ ዓመታት የጥንት ማንነቴ የተመለስኩ መሰለኝ።

​እኛ ዛሬ የምንኖረው ስልጣኔ በረቀቀበት፣ የሰው ልጅ በቴክኖሎጂ አብዝቶ በተቀራረበበት፣ ነገር ግን እኛ ከራሳችን ጋር በእጅግ በተራራቅንበት ዓለም ውስጥ ነው። በየቀኑ በስልኮቻችን የሚፈሰው የማያቋርጥ መረጃ "ሕይወት" እየመሰለን፣ ከእውነተኛው ማንነታችን አርቆ በባዕድ ምድር አሳደደን።

​ነገር ግን እውነተኛዋ ሕይወት ያቺ ጫጫታ የማይደርስባት፣ በአያቶቻችን መንደር ውስጥ የምትገኘው ቅዱስ ጸጥታ ነች።

በአያቴ መንደር የምናቅፈው፣ የምናሸተውና የምንዳስሰው ነገር ሁሉ "ዋናውን አካል" እንጂ ጥላውን አይደለም። የዳሰስነው ድንጋይ የራሱ ታሪክ አለው፤ ያቀፍነው እንስሳ የራሱ ሙቀት አለው። እዚያ መኖር ማለት ከፍጥረት ጋር ፊት ለፊት መተያየት ነው።

በአያቴ መንደር ውስጥ ሥልጣኔ "የለም" ብሎ የሚጠቀሱት ነገሮች ዝርዝር ማለቂያ የለውም። ንፁህ የመጠጥ ውሃ የለም፣ የኤሌክትሪክ ብርሃን የለም፣ ኢንተርኔትና ኔትወርክ የሚባል የዓለም ሰንሰለት የለም፤ ቴሌቪዥን፣ ሬዲዮ፣ መኪና፣ ብስክሌት፣ አልፎ ተርፎም ሆስፒታል ሆነ ጤና ጣቢያ የለም። ከተማ ውስጥ ለኖርን ሰዎች ይህ "ባዶነት" ሊመስለን ይችላል።

በከተማው ሕይወት ግን፣ በዙሪያችን ሁሉም አለን ግን ያሉት ነገሮች ሁሉ ሰው ሰራሽ "ጥላዎች" ናቸው። ከስልካችን ስክሪን ጀምሮ እስከ ቴሌቪዥኑ፣ ከምንመገበው እስከምንኖርበት የስሚንቶ እስር ቤት ሁሉም ነገር የሰው ልጅ እውቀቱን ተጠቅሞ የፈጠራቸው ግዑዝ ምስሎች ናቸው። እራሳችንን በሰው ሰራሽ ዓለም ሰንሰለት አስረን፣ የእውነተኛውን ሕይወት መዓዛና የነፍስን ድንግል እስትንፋስ ረስተነዋል።
ያለ ስልካችን ባዶ ነን፣ ያለ መብራት ጨለማ ይውጠናል፣ ያለ (GPS) መዳረሻችን አናቀውም፣ ያለ ቧንቧ ምን ልንጠጣ? በቃ ምናለፋን ያለ ነዳጅ ምንም መሆናችን እያየነው ነዉ።

ከአያቴ መንደር ሁሉም ነገር በፈጣሪ እጅ ነዉ ሁሉም ህያው ነው፦

​የሚበሉት፦ ከምድር ማህፀን የወጣ እንጂ በፋብሪካ ያልተፈጠረ፤
​የሚጠጡት፦ ከምድር ማህፀን የፈለቀ ምንጭ እንጂ በቧንቧ ያልታነቀ፤
​የሚኖሩበት፦ ከአፈር፣ ከሳር፣ ከእንጨትና ከእበት ተባብሮ የተሰራ፤
​ማረፊያቸው፦ ከእንጨትና ከከብት ቆዳ (አጎዛ) የተበጀ፤
​ጽዋቸው፦ የከብት ቀንድ (ዋንጫ)፤
​መንገዳችን፦ በእግርና በፈረስ።
መዳኒታችን፦ ሳር-ቅጠሉ...

እኛ ሁሉን ነገር ኑሮን ሁሉን መረጃ ሰብስበን ሕይወትን ስናጣ፣ እነሱ ግን ምንም መረጃ ሳይኖራቸው ሕይወትን በሙላት ይኖሯታል።

​ ሁለቱ "እኔዎች" (self vs Self)

​ትንሹ 'እኔ' (The Small 's' self)

ይህች ትንሿ "እኔ" ከሸክላ የተሰራች፣ በከተማው ጫጫታ የተመረዘች ጊዜያዊ ማንነቴ ነች። እሷ የውጫዊው ዓለም ነጸብራቅ ናት፤ ስሟ፣ ክብሯ፣ ማዕረጓና በሙሉ የዚሁ ትንሿ ማንነት ውጤት ነው።

ይህች ትንሿ "እኔ" በሀሳቦች፣ በትውስታዎችና በማህበራዊ ሚዲያዎች የተገነባች፣ በሁኔታዎች የምትዋዥቅ የማንነት ጥላ ነች። ወደ ገጠሩ ስጠጋ ከተማ ውስጥ ደክሜ የገነባሁት ይህ "እኔ" ብዬ ምጠው ማንነት እንደ ማለዳ ጭጋግ እየተበተነ መጣ። በመጀመሪያ ኢንተርኔቱ ተቋረጠ... የዲጂታል ሰንሰለቴ ተበጠሰ። ከዚያ ኔትወርኩ ጠፋ... የሰው ድምጽ ጸጥ አለ። በመጨረሻም ያ የኑሮ ትውስታ ከውስጤ ተነነ። ይህ የሰው ሰራሽ ማንነት መፍረስ ይባላል።

ከተማ ውስጥ ስንኖር፣ ይህች "እኔ" ራሷን እንደ ዓለሙ ማእከል ትቆጥራለች።
​ኢንተርኔቱ ሲቋረጥ፣ ኔትወርኩ ሲጠፋና የሰው ድምጽ ሲርቅ ግን፣ ይህች የሸክላ ማንነት የምትቆምበት መሬት አጣች።

​ታላቁ 'እኔ' (The Capital 'S' Self)

ታላቁ "እኔ" ደግሞ ትንሹን 'እኔ' የሚመለከተውና የሚታዘበው ንጹህ ንቃተ-ህሊና ነው። እሱ እንደ ቁስ የሚጨበጥ ሳይሆን፣ በውስጣችን ያለ ሁለንተናዊ ብርሃን ነው።
ይች ማንነት እንደ ከተማው ሕይወት ከሰው የሚመጣ የድጅታል ማረጋገጫ "👍" አትሻም፣ ሙላቷ በውስጧ ነዉ። ሀሳቦች ይመጣሉ ይሄዳሉ ፣ ስሜቶች ይነሳሉ ይወድቃሉ፤ ትልቁ 'Self' ግን እነዚህን ሁሉ የሚያስተናግድ፣ የማይለወጥና ዘላለማዊ የሆነ የውስጥ መሰረት ነው።

​በአያቴ ባህላዊ ቤት ውስጥ፣ ከሃያ በላይ ከሚሆኑ የተለያዩ የቤት እንስሳት ጋር በአንድ ጣራ ስር ስናድር፤ እነሱ ከታች በረታቸው ላይ፣ እኛ ደግሞ በቆጥ ላይ በአንድ ክፍል ሆነን በጨለማው ውስጥ ስንተነፍስ ያ የእንስሳቱ የዝግታ ትንፋሽ ወደ ሌላ ዘመን ወሰደኝ።
​በዚያ ጸጥታ ውስጥ የእነሱን የትንፋሽ ሙቀት ስሰማ፣ ልቤ ከሁለት ሺህ ዓመት በፊት ወደነበረው በረት ተጓዘ። የቤተልሔሙ በረት ትንፋሽ ዛሬም በአያቴ ቤት ውስጥ የሚደገም መሰለኝ። በዚያ ቅጽበት፣ ሰውና ተፈጥሮ የሚለያዩበት መስመር ጠፋ። ሁላችንም አንድ አይነት ትንፋሽ፣ አንድ አይነት ውበት እንጋራ ነበር፤ ልክ ፍጥረት ሁሉ በአንድነት እንደሚተነፍስ።

​ያቺ ጫጫታ የምትወደው "ትንሿ ማንነቴ" ድምፅዋን አጠፋች፤ ያቺ ታላቋ "እውነተኛ ነፍሴ" ግን እንደ ፋኖስ ታበራ ነበር።

​ ከውስን ቀን የነፍስ ፋታ በኋላ፣ ዳግም ወደ ከተማዋ የሲሚንቶ እቅፍ ተመልሼ ዳርቻው ወደማይታወቅ የከተማው ጩኸት ስገባ፣ በውስጤ አንድ አስገራሚ ድራማ ተከፈተ።

​"ስማ... ሰማህ?" አሉኝ ጉደኞቸ።
"ምን?" አልኩኝ፣ ከውስጤ ገና ያልጠፋውን የመንደሩን የዝምታ መዓዛ ይዤ።
"ከተማዋን ጥለህ በወጣህበት ቀን ጀምሮ ታላቅ ጦርነት ተቀሰቀሰ! ዓለም በድንጋጤ ማዕበል እየተናወጠች ነው..."

ያቺ በአያቴ መንደር የአፈር ጠረንና የእንስሳቱ እስትንፋስ ፊት አፏን ዘግታ፣ አንገቷን ደፍታ የነበረችው ትንሿ 'self' ያቺ "እኔ" የምላት የሀሳብ ክምር በድል አድራጊነት ሳቅዋን አቀለጠችው። አቧራዋን አራግፋ፣ ያንን ምስኪንና ጭል..ጭል የሚለውን የውስጥ ፋኖሴን (Self) አጥፍታ መድረኩን በባለቤትነት ተረከበችው።

​"እንኳን ደህና መጣህ!" አለችኝ። ይህች ከተማ የእሷ ግዛት ናት፤ ጭንቀቱ፣ ውጥረቱና ጫጫታው ለእሷ እንደ ድግስ ምግብ ናቸው።

​የሚገርመው ነገር፣ self ልጓሙን እንደተረከበች ወዲያውኑ በማላውቀው፣ በማይመለከተኝና በማይጠቅመኝ የርቀት ሀገራት ጦርነት ውስጥ እራሴን አገኘሁት። በማናውቀው ጉዳይ፣ ባልበላነው ዕዳ፣ በማናውቃቸው ሰዎች ጦርነት ውስጥ የሰውን መስቀል ተሸክመን በጭንቀት እንገላታለን። የሰው ልጅ ትልቁ በሽታው ይሄ ነው፦ በአካሉ ካለበት ቦታ ይልቅ፣ ባልተገኘበት የሀሳብ እስር ቤት ውስጥ መሰቃየት ይቀለዋል።

​ለምን እንዲህ እንሰቃያለን?
ምክንያቱም ሕይወታችንን አሳልፈን የሰጠነው "ለፈጣሪዎች" እጅ ስለሆነ ነው።
የምንበላው፣ የምንሰማውና የምናስበው ሁሉ በሰው እጅ በተሰሩ ናቸው። እኛ ነጻ አይደለንም፤ ከዓለሙ ጋር "አንድ" ሆነናል ስንል፣ የዓለሙን ውጥረትና ጦርነትም አብረን ተጋርተናል። በሁለት ራቅ ያሉ ሀገራት መካከል ግጭት ሲነሳ፣ እዚህ እኛ ጋር ሁሉም ነገር ይቆማል። ይህ አላስፈላጊ ጥገኝነት ነጻነታችንን ነጥቆናል። ዛሬ ሀገራት "ነጻ ነን" ቢሉም፣ ነፍሳቸው ግን በሌሎች እጅ ነው ያለችው።
የከተማው ሕይወት የተቀረጸው እኛን ጥገኛ ለማድረግ ነው።

​በአያቴ መንደር ግን እውነት ሌላ ነች። እዚያ ያሉት ቅዱሳን ገበሬዎች ሕይወታቸውን በሰው ሰራሽ "ፈጣሪዎች" እጅ አልጣሉም፤ ይልቁንም ሕይወታቸውን የሰጡት ለእውነተኛው ፈጣሪ ለፈጣሪ ብቻ ነው። እነሱ ከዓለም ጫጫታ የተገነጠሉ ብቸኛ ነጻና ህያው ሰዎች ናቸው...
​የሚበሉት ከምድራቸው ያመረቱትን ነው፤ የሚጠጡት በገዛ እጃቸው ያዘጋጁትን ጠላ ነው፤ የሚጓዙት በታማኝ ፈረሶቻቸው ነው። እነሱ አጽናፈ-ዓለሙ የሰጣቸውን ድንግል ጸጋ እንጂ፣ ሰው የፈጠረለትን ሰው ሰራሽ ዓለም አይሹም።
​ይህ ነው እውነተኛው "ባለ-ሀገርነት"። በአያቴ መንደር ነጻነት ማለት ሉዓላዊነት ብቻ ሳይሆን፣ ከማንም ዕዳና ጫና ተለይቶ በራስ መሬት፣ በራስ ምርትና በፈጣሪ ጥበቃ ስር መኖር ነው። እኛ ከተማ ውስጥ የዓለምን መስቀል ተሸክመን ስንሰቃይ፣ እነሱ ግን በገዛ መንደራቸው ውስጥ የራሳቸውን መንግሥት መስርተው በሰላም ዝም ብለው ይኖራሉ።

​የመዝጊያ ቅኔ፦ የዝምታ ጥሪ

​እውነት እውነት እላችኋለሁ፤ በጊዜ ጉዞ ካላመናችሁ ከአያቶቻችሁ፣ ግፋ ቢል ከቅድመ አያቶቻችሁ መንደር ጎራ በሉ። የከተማው ጩኸት ነፍሳችንን እንዳይነጥቃት፣ የሰው ሰራሹ ዓለም ከእውነተኛው ህልውናችን እንዳያርቀን፣
ኑ... በዚያ በአያቴ ቤት በረት ውስጥ እንዳገኘሁት ቅዱስ ጸጥታ፣
እኛም ለአፍታ በግጥም እንዲህ እንበል፦
​
​አብረን ዝም እንበል፤

ከሰው መንጋ እንገንጠል፤
ለአንድ አፍታ እንኳ እንገለል፤
በእፎይታ ጥላ እንጠለል፤
ዝም ብለን አብረን... ዝም እንበል!

​(ጋሽ ፀጋዬ ገብረመድህን)
ጽድቅ እና ኩነኔ ቢኖርም ባይኖርም
​ከክፋት ደግነት ሳይሻል አይቀርም