የዛሬው የ May 26 የእሑድ አገልግሎታችን ይህንን ይመስል ነበር! ስለ ሁሉም ነገር የወለላይቱ እመቤት የድንግል ማርያም ልጅ ኃያሉ መድኃኔ ዓለም ክብር ምስጋና ይድረሰው! አገልግሎቱ ይቀጥላል ...
#_የቅዱስ_ቁርባን_ጸጋ_ለምን_ተሰወረብን?
#_እኛ_ቅዱስ_ቁርባን_ተቀብለናል_ግን_ቁርባኑ_እኛን_አልተቀበለንም!
በቀሲስ ሄኖክ ወልደ-ማርያም
ሼር በማድረግ ለወዳጆ አዳርሱ!
ተወዳጆች ሆይ የቅዱስ ቁርባን ጸጋ ለቅዱሳን፣ በእውነተኛ አባቶች እና በንስሐ ለነጹት ምዕመናን የሚገለጥ ነው፡፡ ምክንያቱም ሰውነታቸው፣ ሕይወታቸው በአምልኮት እና በጾም፣ በጸሎት እና ስግደት የማሸ ስለሆነ፤ ለመንፈስ ቅዱስ እንደ ታጠነ የንብ ቀፎ ነው፡፡
የታጠነ የንብ ቀፎ ንቦች ግር ብለው ከነ አውራው እንደሚገቡ ሁሉ ቅዱሳን መንፈስ ቅዱስ እንደ ንብ ስለሚከባቸው የቅድስ ቁርባን ምስጢር እና ጸጋ ይገለጽላቸዋል፡፡
እኛ ግን ምስጢር የማይገለጽልን፣ ጸጋው ከነፍስ ከሥጋችን የማይዋሃደው፣ ንስሐ ብንገባም ቂም ቋጥረን ፣ የበደለንም ይሁን የበደልነውን ይቅር ሳንል፣ ንስሐ ብንገባም ሐሜት አልተው ብለን፣ የጌታን ቅዱስ ሥጋ በሐሜት ከሰው ሥጋ ጋር ስለምንበላ፤ ጌታ በነጻ የሰጠንን እኛ ለሰዎች ቸርነት ስላላደረግን፣ ቅዱስ ቁርባን ብንቀበልም ቅዱስ ቁርባኑን ነፍስ እና ሥጋችንን አልቀበል ይለናል፡፡
እኛ ቅዱስ ቁርባን በገሃድ ተቀብለን ግን ቅዱስ ቁርባኑ እኛን ላይቀበለን ይችላል፡፡ ትልቁ ጸጋ ማጣት እኛ ቅዱስ ቁርባን ተቀብለን ቅዱስ ቁርባን እኛን ሳይቀበል መቅረቱ ነው፡፡ ይህ ማለት ቅዱስ ሥጋው ከሥጋችን ክብር ደሙ ከደማችን ሳይዋሃድ ሲቀር ማለት ነው፡፡
እስኪ ይህንን እንዲያጠናክርልን ገድለ ቅዱሳንን እንመልከት፡፡ አቡነ እስትንፋሰ ክርስቶስ ጥር 13 ቀን የዓመቱ የእግዚአብሔር አብ በዓል ቀን ከአባቸው ከካህኑ ከመልአከ ምክሩ ጋር ቅዳሴ ገቡ፡፡ ያኔ እድሜያቸው 14 ዓመት ነበር፡፡
ካህኑ መልአከ ምክሩ በቅስና አቡነ እስትንፋሰ ክርስቶስ በዲቁና ቀድሰው በሺዎች የሚቆጠሩ ምዕመናንን ቅዱስ ቁርባን አቀበሏቸው፡፡ የአቡነ እስትንፋሰ ክርስቶስ አባት ካህኑ መልአከ ምክሩ ‹‹ልጄ በዚህች ዕለት ስንት ሰዎች ቆረቡ›› ብለው ጠየቋቸው፡፡
አቡነ እስትንፋሰ ክርስቶስም ‹‹12 ሰዎች ብቻ ቆረቡ፡፡ የቀሩት ሰዎች በድፍረት ስለተቀበሉ በእሳት ሰንሰለት ታስረው በእሳት አለንጋ መላእክት እየገረፏቸው እስከ ቤታቸው አደረሷቸው›› በማለት ለአባታቸው ተናገሩ፡፡
ገድለ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስን ስንመለከት ደግሞ ጻድቁ አንድ ቀን ገቦታ በሚባል ቦታ በአንዲት ቤተ ክርስቲያን ተሰውረው ገብተው በቅዱስ ቁርባን ጊዜ እግዚአብሔር ምስጢር ገለጠላቸው፡፡ በዛን ቀን ሁለት መቶ ሰዎች ቅዳሴ አስቀድሰው ቅዱስ ቁርባን ለመቀበል ተገኝተው ነበር፡፡ ሁለት መቶ ሰዎች ቅዱስ ቁርባን ተቀበሉ፡፡
ከእነሱ ሃይማኖቱ የጸና፣ ምግባሩ የቀና አንድ ሰው ብቻ ቅዱስ ቁርባን ሲቀበል ቅዱስ ሥጋው ከሥጋው ፣ ክቡር ደሙ ከደሙ ጋር ወይም ቅዱስ ቁርባን ሲቀበል መለኮታዊ ጸጋ የተቀበለው አንድ ሰው ብቻ መሆኑን በመንፈስ ቅዱስ ገላጭነት አወቁ፣ አውቀውም ተደነቁ፡፡
አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስም አብሯቸው የነበረውን የእግዚአብሔርን መልአክ ‹‹ሥጋውን ደሙን ያልተቀበሉ እነዚህ ሰዎች ኃጢአታቸው ምንድን ነው›› በማለት ጠየቁት፡፡ መልኩም ‹‹በእግዚአብሐር ዘንድ ኃጢአታቸው ብዙ ነው፡፡ ከእነሱ ውስጥም ወደ ንስሐ ከተመለሰ ከአንድ ሰው በቀር የተረፈ የለም፡፡ እነዚህ ኃጥአን ግን በምድር ላይ በዘመናቸው የሰይጣን ጭፍራ ሆኑ›› ብሎ ነገራቸው፡፡
ወዳጆቼ በሁለቱም ገድለ ቅዱሳን ላይ የተጻፈው ታሪክ አንድ አይነት ነው፡፡ ለሰው እና ለራሳቸው በሚታየው ቅዱስ ቁርባን ተቀብለዋል፡፡ ነገር ግን ቅዱስ ቁርባን ሲቀበሉ መለኮታዊ ጸጋን፣ መለኮታዊ ኃይልን፣ ረድኤተ እግዚአብሔርን፣ ጸጋ መንፈስ ቅዱስን አልተቀበሉም፡፡
እነሱ ቅዱስ ቁርባን ተቀበሉ እንጂ ቅዱስ ቁርባን እነሱን አልተቀበለም፡፡ እውነተኛ ንስሐ ሳንገባ፣ የበደልነውን ሳንክስ፣ የቀማነውን ሳንመልስ፣ የተጣላነውን ሳንታረቅ፣ ይቅርታ ሳናደርግ፣ ሐሜቱን፣ ክፋቱን፣ ምቀንነቱን ወዘተ ሳንተው ቅዱስ ቁርባን ብንቀበል በገድሉ ላይ እንዳሉት ምዕመናን ቅዱስ ቁርባን እኛን ሳይቀበለን ይቀራል፡፡ ዛሬም እየሆነ ያለው ይኸው ነው፡፡ ብዙዎቻችን ቅዱስ ቁርባን እንቀበላለን በበደላችን ምክንያት ቅዱስ ቁርባን እኛን ሳይቀበለን ይቀራል፡፡
ወዳጆቼ አንድ ሰው አሞት ሐኪም ለሕመሙ ፈዋሽ መድኃኒት ያዝለታል፡፡ ሐኪሙ ለታማሚው መድኃኒት ሲያዝለት መድኃኒቱን የሚያረክሰውን፣ እንዳይሠራ የሚያደርገውን የመድኃኒቱን ተጻጻሪ ነገር አብሮ እንዳይወስድ ያስጠነቅቀዋል፡፡
ቸልተኛ እና ግድ የለሽ ታማሚ ከሆነ የመጠጥ ሱስ፣ የሐሽሽ ሹሽ ካለበት መድኃኒቱን ከመውሰዱ ወይም ከወሰደ በኃላ መጠጥ ቢጠጣ፣ ሐሽሽ ቢጠቀም መድኃኒቱ አይሠራም፡፡ ለሕመሙ ፈዋሽ አይሆንም፡፡ የግድ ለመዳን ከፈለገ የመጠጥ እና የሐሽሽ ሱሱን መተው አለበት፡፡ ይህን ሲያደርግ ነው መድኃኒቱ በበሽታው ላይ የበላይ ሆኖ ፈውስ የሚያገኘው፡፡
እኛም ዛሬ የሐሜት፣ የዝሙት፣ የምቀኝነት፣ የስድብ ወዘተ ስሱ ሳንተው ቅዱስ ቁርባን ብንቀበል የቅዱስ ቁርባን መለኮታዊ ኃይል እና ጸጋው ለእኛ አይገለጥም ወይም በእኛ አይገለጥም፡፡
በአጭሩ መለኮታዊ ኃይል አይሆነንም፡፡ እንደ መጠጥ እና ሐሽሽ ሱስ የሆኑብንን ኃጢአት ከሰውነታችን በማስወገድ ቅዱስ ቁርባን የምንቀበል ከሆነ በእውነትም ሰማያዊ ኃይልን እንቀበላለን፡፡
የመቅደሱ አገልጋዮችም የቅዱስ ቁርባን መለኮታዊ ኃይል እና ጸጋው የተሰወረብን የተገለጠ ኃጢአት ወይም የተሰወረ ኃጢአት ስላለብን ነው፡፡ አብረውን ለሚያገለግሉና ለምዕመናኑ በቀላሉ የሚታዩ ለትችት እና ለሐሜት የሚያጋልጡን ኃጢአት የተጋለጥን ስለሆንን የቅዱስ ቁርባን መለኮታዊ ኃይል እና ጸጋው አይገለጥልንም፡፡
ክህነት ላይ ሐሜት፣ ዝሙት፣ ዘረኝነት፣ አድመኝነት፣ ቂመኛነት ወዘተ ተሸክም የቅዱስ ቁርባን መለኮታዊ ኃይል እና ጸጋ መሸከም በፍጹም አንችልም፡፡ ለቅዱስ ቁርባን መለኮታዊ ኃይል እና ጸጋው ከአባቶች እስከ ምዕመናን ተሰውሮብናል፡፡ የቅዱስ ቁርባንን መለኮታዊ ኃይል እና ጸጋ የሚገልጥልን ጸጋ ስለሌለን ቅዱስ ቁርባንን ከቀመበል ባሻገር ለክብሩ እና ስለምናገኘው ክብር አንጨነቅም፡፡
የሰው ልጅ በእግዚአብሔር ቤት እየኖረ እየተመላለሰ ነገር ግን በኃጢአት እየረሰከ ከሄደ የእግዚአብሔር ክብር ይርቀዋል፣ ጸጋው ይሰወርበታል፡፡ አባቶቻችን እግዚአብሔርን እጅጉን ስለሚያከብሩት፣ ስለሚፈሩት፣ ክብሩን እና መለኮታዊ ኃይሉን ስለሚረዱት እግዚአብሔር ደግሞ በአጸፋው ክብሩን ያሳውቃቸዋል፣ ጸጋውን ይሰጣቸዋል፣ ምስጢሩን ይገልጥላቸዋል፡፡
ሌላው የቅዱስ ቁርባን ጸጋው አብሮን እንዳይኖር የሚያደርገው ንስሐ ገብተን ቅዱስ ቁርባን ከተቀበልን በኃላ አንዴ ንስሐዬን ጨርሻለሁ ስለዚህ ንስሐ አያስፈልገኝም ምክንያቱም እኔ ቆራቢ ነኝ ብለን ለራሳችን ትልቅ የጽድቅ ቦታ ሰጥተን ስለምንቆርብ ነው፡፡
በአለፍ ገደም ያማነው፣ ሰውን ያለጥፋቱ የተቆጣነው፣ በሥራችን ያናደድነው፣ የሰደብነው ያሽማጠጥነው ‹‹ይቅር ይበለኝና›› በሚል የሽፋን ሐሜት ያማነውን ንስሐ ስለማንገባበት ነው፡፡
እሺ መቼም ለምደነው ንስሐ አንግባ ግን ቢያንስ ቅዳሴ አልቆ ደርገት ሲወርዱ ሰልፍ ይዘን መሰስ ብለን ቅዱስ ቁርባን ከመቀበላችን በፊት በእግዚኦታ ጊዜ ‹‹አቤቱ በማወቅም ባለማወቅም የሠራሁትን ኃጢአቴን ይቅር በለኝ›› ብለን እዛው ለክርስቶስ ጥቃቅን ነገር ግን ኃጢአት ያለመሰሉንን በደላችንን ጠቅለል አድርገን ስለማንናዘዝ ነው፡፡

አንድ ሰው ከሚፈጽማቸው ኑዛዜዎች አንድ ኃጢአቱን ለጌታ መናዘዝ ነው፡፡ ኃጢአታችንን በጸሎት ሰዓት በቅዳሴ ጊዜ እያስታወስን ብንናዘዝ እኛ ከማናውቀው እና ከምናውቀው እግዚአብሔር ባወቀ ኃጢአታችንን ይቅር ይለናል፡፡
ይህንን እና ሌሎችንም ባልተገበርንበት ሁኔታ የቅዱስ ቁርባን ጸጋ ለእኛ ተነስቶ በበረሃ ላሉት እና ስለ ሀገር ለሚያለቅሱት፣ ለሚያነቡት ቢሰጥ ትክክል ነው፡፡ ገበሬ ማር ለሚሰጡት ንቦች ከቀፎው እንዳይወጡ ወደ ሌላ እንዳይኮበልሉ ለንቦቹ የሚያደርገውን ጥንቃቄ እኛ መለኮታዊ ጸጋ ለሚያሰጠን የዘላለም ሕይወት ለሚያወርሰን ቅዱስ ቁርባን ጸጋው፣ በረከቱ ኃይሉ ሞገሱ ከእኛ እንዳይርቀን ልንጠነቀቅ ይገባናል፡፡
የምንጠነቀቅ እና ቶሎ ቶሎ ንስሐ እየገባን በካህን አፍ ይፍቱኝ እየተባልን ቅዱስ ቁርባን የምንቀበል ከሆነ ጸጋው፣ በረከቱ ኃይሉ ሞገሱ በእኛ ላይ ያድራል፡፡
ወዳጆቼ አንድ ነገር በቦታው ለመግባት ወይም ለመግጠም ልኩ ያስፈልገዋል፡፡ ሁለት ልክ ያልሆኑ ነገሮች ሊገጥሙ አይችልም፡፡ ምሳሌ ለመስጠት ባይመጥንም ለምሳሌ አንድ ብሎን የራሱ የሆነ ግጣም ሲገጥመው ነው ልክ ሆኖ የሚታሰረውና ጠበቅ አድርጎ የሚይዘው፡፡ በአበባላችንስ ድስት ግጣሙን አይደል የምንለው፡፡
ቅዱስ ቁርባንም ጸጋው ከስጋችን እና ከነፍሳች ጋር የሚገጥመው እና ጸጋና በረከት ኃይል የሚሆነው ሰውነታችን በንስሐ ታጥቦ፣ በይቅርታ ተሞርዶ፣ ሲገኝ ነው፡፡ በዚህ ሰውነት ላይ የቅዱስ ቁርባን ጸጋ ያድርበታል፡፡ ይህ ማለት ጸጋው ከነፍስ ከሥጋችን ጋር ይገጥማል ማለት ነው፡፡ ገጠመ ማለት ቅዱስ ቁርባን ትክክለኛውን ቦታ አገኘ ማለት ነው፡፡
በንስሐ ባልታጠበ ግን በኃጢአት ባደፈ ሰውነት ላይ፣ በይቅርታ ባልተስተካከለ ሰውነት ላይ ንጹህ ክብር ቅዱስ የሆነው ቅዱስ ቁርባን ጸጋ እና በረከት ሆኖ ከማደር ይልቅ እዳ በደል ይሆናል፡፡
ዘላለማዊ ገነት እወርስበታለሁ ያልነው ቅዱስ ቁርባን ዘላለማዊ እሳት እንዳይሆንብንና እንዳያመጣብን ከቂም ከበቀል ከዘረኝነት ርቀን በንስሐ ሆነን ብንቀበል ብዙ ጸጋ እናገኝበታለን ከጌታም እንገናኝበታለን፡፡ ቅዱስ ቁርባን ስንቀበል ቅዱስ ቁርባን እኛን እንዲቀበል እንዲሰምርልን መጸለይ አለብን፡፡
ግንቦት 19-9-16 ዓ.ም
እንግሊዝ

በ UK አርብ እና ቅዳሜ May 30 እና Jun 1 የነበረን አገልገሎት እጅጉን ደስ የሚል እና እንደ ክፉዎች ሐሳብ፣ ምቀኝነት ሳይሆን እንደ እግዚአብሔር ቸርነት ተከናውኗል! አገልግሎቱ ይቀጥላል!
"ማዳን የእግዚአብሔር ነው፣ በረከትህም በሕዝብህ ላይ ነው" መዝ 3፥8