ማርመድሕ ሚዲያ - Marmedh Media
6.23K subscribers
461 photos
10 videos
22 files
442 links
ገብተህ የማትወጣ ከሆነ ብቻ JOIN አድርግ! እርግጠኛ ነኝ ትወዱታላችኹ ተቀላቀሉን!
ጥቅሙን ተቀላቅላችኹ ዕዩት፥ በተለይ አጫጭር አነቃቂ ጽሑፎች ይ ማ ር ካ ሉ!
ወቅታዊ ጉዳይ አይታጣበትም... ከገባችኹ ትርፍ አላችኹ!

TIKTok
http://tiktok.com/@mekuriya19
ለሐሳብና አስተያየት
https://t.me/Proud24
Download Telegram
Audio
ግጥምና ዜማ ቸግሯችኹ እንደሆን @Proud24 ላይ አውሩኝ
ማርመድሕ ሚዲያ - Marmedh Media pinned «🔔 #ጾም ለተወሰነ ጊዜ እህል ከመብላትና ውሃ ከመጠጣት መታቀብ ወይም ለተወሰኑ ወራት ከጥሉላት፣ ከሥጋ፣ ከቅቤ፣ ከወተት፣ ከእንቁላል በአጠቃላይ ከእንስሳት ውጤት መከልከል ነው። ... ይህ ብቻ #ጾምን ፍጹም ስለማያደርግ ሕዋሳት ሁሉ በ'የራሳቸው ክፉ ከመሥራት መታቀብ አለባቸው። ... ይኸውም ዓይን ክፉ ከማየት፣ ጆሮ ክፉ ከመስማት፣ አንደበት ክፉ ከመናገር፣ እጅ ክፉ ከመሥራት፣ እግር ወደ ክፉ ቦታ ከመሄድ…»
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
🌿 #ንነጽር_፹፮

አንድ ሰው ዙፋን ላይ ተቀምጦ ካየኸው #ንጉሥ ነው ማለት ነው።
ከግራና ከቀኝ ጦር ይዘው የቆሙ ሰዎች ካየህ የንጉሡ
#ጠባቂዎች ናቸው ማለት ነው።

አየህ! ይህንን ለማወቅ እስኪነገርህ አትጠብቅም፤ ምልክቱን ብቻ በማየት ብዙ ነገርን መለየት ትችላለህ።
ወዳጄ! አንገቱ ላይ ማዕተብ ያለበት ሰው ካየህ ክርስቶሳዊ ነው ማለት ነው። ክርስቶሳዊ ለመባል ክርክቶሳዊ ምልክትን ልትይዝ ይገባሃል።

ይኼውልህ...
"
#ታርጋ_የሌለው_መኪና_በትራፊክ_ፖሊስ ይያዛል" እናማ ክርስቶሳዊ እንሁን🙏

◦◦●●Join us on telegram
@MekuriyaM
🌿 #ንነጽር_፹፯

ለመጀመርያ ጊዜ ስልክ በያዝኩ ሰዓት ለታናናሽ እህቶቼ ስልኩን
#እንደፈለጉ_እንዲያደርጉት_እሰጣቸው_ነበር
ትንሽ ቆየኹና
#ባትሪው_ይፎርጃል_በቃ_በቃ_ማለት_ጀመርኩ
ትንሽ ቆየኹና ደግሞ
#አያይ_አልሰጥም_ስልኩ_ይበላሻል_ብዬ_መከልከል_ጀመርኩ
...
አየህ ወዳጄ! ሰለ አንድ ነገር በጥልቀት ማወቅ ስንጀምር፤ ለነገሩ የነበረን ቦታ ይቀየራል። ሕይወት ደረጃ እንዳላት ሁሉ ውስጠ ሕሊናችንንም እንዲሁ ጀረጃ አላት።
...
ወዳጄ! ትላንት የነበርክበት ደረጃ ላይ ዛሬም አለህ? ወይስ ፈቀቅ ለማለት ተዘጋጅተሃል?


◦◦●●Join us on telegram
@MekuriyaM
#ኧረ ግፍ ነው በደቀ መዛሙርቱ ጭካኔ !

ከመርዓዊ ወጣ ብሎ በሚገኘው ጋፊት ቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያን የሚማሩ ከአስራ ሁለት በላይ የአብነት (የቅኔ ደቀ መዛሙርት) በአረመኒያዊ እና ጭካኔ በተሞላበት ከሌሊቱ ስድስት ሰዓት አከባቢ ከመጠለያቸው ድረስ ገብተው እረሽነዋቸዋል።😥😥😥
ኧረ ፍረድ አምላኬ😭😭😭
<<<ታላቅ ግፍ በጋፊት>>>

ዛሬም እንደተለመደው በአዴት ከተማ በፍልሰታ ደብር ላይ የተፈጸመው የደቀ መዛሙርት ግድያ በብራቃት እና በአካባቢዋ ተጠናክሮ ቀጥሏል❗️ድንቁርናን ያክል ክፉ ጠላት ለመፋለም በመንፈስ ቅዱስ እየተመሩ በመንፈሳዊ አውደ ውጊያ ተቀላቅለው "በእንተ ስማ ለማርያም" እያሉ ከተናካሽ ውሻ እና ከተናዳፊ ረሀብ ጋር እየታገሉ የሚገኙ በሰሜን ጎጃም ሀገረ ስብከት ሥር በሚገኘው በላይ ጋፊት ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን የቅኔ ጉባኤ ደቀ መዛሙርት በመንፈቀ ሌሊት በግፍ ተገድለዋል❗️
⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻
በሀገረ ስብከታችን በቅርቡ ይህ የጥላቻ ድርጊት ሲፈጸም ለ2ተኛ ጊዜ መሆኑ ነው በዛሬው እለት <<<በቁጥር ከ11>>> በላይ የሚሆኑ የቅኔ ደቀ መዛሙርት በላይ ጋፊት ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ብቻ ተሰውተዋል የቀሪዎች አስከሬን በየዱሩ እየተፈለገ ነው ተገለው ተጥለው ከሆነ ባይሆን በክብር ለመቅበር እንዲቻል ታስቦ መሆኑ ነው።
⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻
ልጄ ተምሮ ይመጣል ብላ የምትጠባበቅ የተማሪው እናት መምህር ሳይሆን አስከሬን እንዲደርሳት ተፈርዶባታል ይህንን ሁሉ መከራ ያመጣው ያው ባለማተብ፣ባለፍቅር እና ባለራዕይ መሆን ነው ታዲያ ጥቁር መልበስ እና በጋራ ማዘን በዚህ ጉዳይ አይገባምን
⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻
እነዚህ ደቀ መዛሙርትኮ በቀላሉ የ11 አድባራት መሪዎች ናቸው ተራ ግለሰቦች አይደሉም ይህ ድርጊት ሲፈጸም የ11 አድባራትን ቁልፍ ሰብሮ ዝርፊያ መፈፀም እንደማለት አንደለምን
⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻
ከዚህ ጋር ተያይዞ የደብሩ መሪጌታ የሥጋ ልጅ (የቅኔ ተማሪ) በግፍ የተገደለ ሲሆን የደብሩ ኃላፊ የሆኑትን ቀሲስ ደጋአረገ አሳየን ጨምሮ የደብሩ አገልጋዮች ያልተገባ እንግልት እና ድብደባ እየተፈጸመባቸው መሆኑን ከታማኝ ምንጮች መረዳት ችለናል።

◦◦●●Join us on telegram
@MekuriyaM
❝❞
+ እኔ ግን እኔ አይደለሁም +

አውግስጢኖስ፦ ፈጣሪ የለም ባይ እና በዝሙት የተበላሸ ሕይወት ይኖር የነበረ ሰው ነው:: በቅዱስ አምብሮስ ስብከት ከተመለሰ በኋላ ግን ይህ ሰው ፍጹም በንስሓ ተለውጦ በምንኵስና መንገድ ሔዶ እስከ ጵጵስና ደረሰ:: ይህንን የንስሓ ሕይወት መኖር ከጀመረ በኋላ ቀድሞ በአመንዝራነት ሕይወት ሲኖር ወዳጁ የነበረች አንዲት ሴት መንገድ ላይ ከሩቅ አይታ ተከትላ ጠራችው::

ወደ ቀድሞ ትዝታውና ኃጢአቱ መመለስ ያልፈለገው ይህ አባትም ጥሪዋን እንዳልሰማ ሆኖ በፍጥነት መሔድ ጀመረ::

ይህች ሴትም እየሳቀች :-

አውግስጢኖስ እኔ እኮ ነኝ! ብላ ጮኸች

እርሱም ወደ እርስዋ ዞሮ :- ''እኔ ግን እኔ አይደለሁም'' አላት::

●●◦◦Join us on telegram
@MekuriyaM

❝ ❞
🌿 #ንነጽር_

"ይሰቀል ይሰቀል" ሲሉ ሳንሠማቸው፣
"ይገደል ይገደል" ሲሉም ሳናያቸው፤
         ግና
"አማላጅ አማላጅ" ብለው ሲናገሩ ይኸው አየናቸው፤
       እኛም
ወልደ አብ፣ ወልደ ማርያም አምላክ ነው አልናቸው።

◦◦●●Join us on telegram
      
@MekuriyaM
ውድ ቤተሰቦቼ ለትንሽ ጊዜ ኅብረታችንን ለማጠናከር ስል አንዳንድ ማስታወቅያዎችን ልሠራ ነው። እናንተም left አታድርጉ አደራ! Share እያደረጋችኹ በትንሽ ጊዜ ውስጥ 2k እናድርሰው ተባበሩኝ አኹን 1433 ነን🙏🙏🙏
ማርመድሕ ሚዲያ - Marmedh Media pinned «ውድ ቤተሰቦቼ ለትንሽ ጊዜ ኅብረታችንን ለማጠናከር ስል አንዳንድ ማስታወቅያዎችን ልሠራ ነው። እናንተም left አታድርጉ አደራ! Share እያደረጋችኹ በትንሽ ጊዜ ውስጥ 2k እናድርሰው ተባበሩኝ አኹን 1433 ነን🙏🙏🙏»