Mark Tech Info | Mark Technology Information
6.21K subscribers
659 photos
12 videos
42 files
430 links
Buy ads: https://telega.io/c/MarkTechInfo

ለአስተያየት ፣ ጥቆማ ፣ ለማስታወቂያ እና ለጥያቄዎች በዚህ ያናግሩን።
👇👇👇👇👇👇👇👇
@MarkTechInfoBot
Download Telegram
በ2016 ዓ.ም በትግራይ ክልል የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና በሦስት ዙር ይሰጣል።

በ2012 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ተማሪ የነበሩና የመልቀቂያ ፈተናውን ያልወሰዱ 9,514 ተማሪዎች በመጀመሪያ ዙር ፈተናውን ከመስከረም 29/2016 ዓ.ም ጀምሮ እየወሰዱ ይገኛሉ።

በ2012 ዓ.ም የ11ኛ ክፍል ተማሪ ለነበሩ ተማሪዎች በጥር 2016 ዓ.ም የመልቀቂያ ፈተናው ይሰጣል።

በ2012 ዓ.ም የ10ኛ ክፍል ተማሪ ለነበሩ ተማሪዎች በግንቦት 2016 ዓ.ም መጨረሻ መልቀቂያ ፈተናው እንደሚሰጥ የክልሉ ትምህርት ቢሮ ገልጿል።

የ12ኛ ክፍል ፈተና በዚህ ዓመት በሦስት ዙር መሰጠቱ በክልሉ ለአራት ዓመታት የትምህርት ጊዜ ያለፈባቸውን ተማሪዎች ለማካተት በማሰብ መሆኑን የቢሮው ኃላፊ ኪሮስ ጉዕሽ (ዶ/ር) ተናግረዋል፡፡

ለተጨማሪ የ12ኛ ክፍል መረጃዎች 
●▬▬▬▬▬ ๑۩۩๑ ▬▬▬▬▬● 
⭕️ 👉 t.me/grade12results 👈  ⭕️ 
⭕️ 👉 t.me/grade12results 👈  ⭕️ 
⭕️ 👉 t.me/grade12results 👈  ⭕️ 
●▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬●
👍11😢1
#Update

በትግራይ ሲሰጥ የነበረው የ12ኛ ክፍል ሀገራዊ ፈተና ተጠናቀቀ።

የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት በትግራይ ክልል የ12ኛ ክፍል አገራዊ ፈተና በተረጋጋ እና ሰላማዊ በሆነ ሁኔታ ተጠናቋል ሲል አሳውቋል።

በተመሳሳይ የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ትምህርት ቢሮው ፈተናው በተረጋጋ ሁኔታ መጠናቀቁ አሳውቋን።

የቢሮ ሃላፊ ዶ/ር ኪሮስ ጉዑሽ ፤ዥ አገር አቀፍ ፈተናው በተያዘለት ዕቅድ እንዲጠናቀቅ ያደረጋችሁ ከፌደራል እስከ ትምህርት ቤቶች እና ዩንቨርሲቲዎች ያላችሁ ተቋሞች፣ የትምህርት ኣመራሮች እና መምህራን፤ ከፌደራል እስከ ወረዳ ያላችሁ የፀጥታ እና ደህንንት ተቋሞች እና ኣመራሮች፤ ከተለያዩ ኢትዮጵያ ዩንቨርሲቲዎች የተውጣጣችሁ ፈታኞች የላቀ ምስጋናችንን እናቀርባለን "  ብለዋል።

ሃላፊው " ፈተናው በተረጋጋ ሁኔታ እንዲጠናቀቅ  ተፈታኝ  ተማሪዎቻችን ከናንተ የሚጠበቀው ሁሉ ስለደረጋችሁ ለናንተም የላቀ ምስጋና ይገባቹሃል " ሲሉ አክለዋል። 

ከመስከረም 29 እስከ ጥቅምት 02/2016 ዓ/ም  ለአራት ተከታታይ ቀናት በትግራይ ክልል ሲሰጥ የቆየውን የ12 ክፍል አገራዊ ፈተና ከ9,000 በላይ ተማሪዎች መፈተናቸውን የክልሉ ትምህርት ቢሮ መረጃ ያሳያል።

የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት የፈተና ውጤቱን ባጠረ ጊዜ ለማሳወቅ እንደሚሰራ ገልጿል።

የትምህርት ሚኒስቴር ሚንስትር ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ መስከረም 28 /2016 ዓ.ም ለመገናኛ ብዙሃን በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ፤ የትግራይ ተፈታኞቹን ውጤት በአንድ ሳምንት ውስጥ ለማሳወቅ ይሰራል።

የሚያልፉ ተማሪዎች በአገር አቀፍ ደረጃ ውጤታቸው ከተገለጸ ተማሪዎች ጋር አብረው ወደ ዩኒቨርሲቲ እንዲገቡ ለማድረግ ጥረት እንደሚደረግ መግለፃቸው አይዘነጋም።

ለተጨማሪ የ12ኛ ክፍል መረጃዎች 
●▬▬▬▬▬ ๑۩۩๑ ▬▬▬▬▬● 
⭕️ 👉 t.me/grade12results 👈  ⭕️ 
⭕️ 👉 t.me/grade12results 👈  ⭕️ 
⭕️ 👉 t.me/grade12results 👈  ⭕️ 
●▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬●
👍7👌5🤔1
‼️የ6 ተማሪዎች ህይወት አልፏል

በትግራይ የ12ኛ ክፍል ፈተና ጨርሰው ወደ ቤተሰቦቻቸው ሲመለሱ የነበሩ ተማሪዎች በደረሰባቸው የመኪና አደጋ ህይወታቸው አለፈ።

በርካቶችም ቀላል እና ከባድ ጉዳት ደርሶባቸዋል።

በዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ ፈተናቸውን ጨርሰው ወደ ተንቤን እና አካባቢው ሲጓዙ የነበሩ ተማሪዎችን አስፋሮ የነበረ ኣውቶብስ በሀውዜን ወረዳ " ደብረ ሰላም " የሚባል አካባቢ ተገልብጦ የ6 ተማሪዎች ህይወት አልፏል።

በአደጋው ​​ከሞቱት 6 ተማሪዎች በተጨማሪ 53 ተማሪዎች ከባድና ቀላል የአካል ጉዳት እንደደረሰባቸው የሀውዜን መጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል አሳውቋል።

የሀውዜን የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል እና የመጋብ ጤና ጣቢያ የህክምና እና የአምቡላንስ ባለሙያዎች ተጎጂዎች ህክምና እንዲያገኙ ከፍተኛ ጥረት ማድረጋቸው ተነግሯል።

ጉዳት የደረሰባቸው 29 ተማሪዎች በሀውዜን የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል እና መጋብ ጤና ጣቢያ በህክምና ላይ ሲሆኑ ፤ 24ቱ ከባድ ጉዳት የደረሰባቸው ተማሪዎች ወደ አይደር ሪፈራል ሆስፒታል መላካቸውን ከቴሌቪዥን ትግራይ ያገኘነው መረጃ ያሳያል።

ለተጨማሪ የ12ኛ ክፍል መረጃዎች 
●▬▬▬▬▬ ๑۩۩๑ ▬▬▬▬▬● 
⭕️ 👉 t.me/grade12results 👈  ⭕️ 
⭕️ 👉 t.me/grade12results 👈  ⭕️ 
⭕️ 👉 t.me/grade12results 👈  ⭕️ 
●▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬●
👍4😱3👏2
"መንግሥት ወደ ዩኒቨርሲቲ የሚገባውን ተማሪ ቁጥር ሆን ብሎ የመቀነስ ምንም ፍላጎት የለውም።"

-የትምህርት ሚኒስትር ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር)

መንግሥት በትምህርት ዘርፍ እየወሰዳቸው ስላሉ ማሻሻያዎችና የ12ኛ ክፍል ፈተና ውጤትን አስመልክተው የትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) ከብሔራዊ ቴሌቪዥን ጣቢያው ጋር ቆይታ አድርገዋል።

መንግሥት ወደ ዩኒቨርሲቲ የሚገባውን ተማሪ ቁጥር ሆን ብሎ የመቀነስ ምንም ፍላጎት እንደሌለው ሚኒስትሩ ተናግረዋል።

"ችሎታ ያላቸው ተማሪዎች ወደ ዩኒቨርሲቲዎች እንዲገቡ ነው የሚጠበቀው" ያሉት ሚኒስትሩ፤ በዩኒቨርሲቲ ደረጃ መማር የሚችሉ ወጣቶችን ለማፍራት እየተሠራ ነው ብለዋል።

ዩኒቨርሲቲ ለመግባት የሚያስችል አቅም የሌላቸው ተማሪዎች ህብረተሰቡን በማገልገል ራሳቸው የሚጠቀሙባቸው ሌሎች ሥራዎች ላይ የሚሰማሩበት ዕድል መኖሩን ጠቁመዋል። በዚህም የTVET ተቋማትን በማስፋፋት ወጣቶቹ የሚያስፈልጋቸውን ክህሎት እንዲያገኙ የሚደረግ መሆኑን ገልጸዋል።

"በጣም የተወሳሰበና በዕውቀት ላይ የተመሰረተ ዓለም እየተፈጠረ ነው" ያሉት ሚኒስትሩ፤ "ብዙ የተማሩና ብዙ ክህሎት ያላቸው ወጣቶች ቢኖሩ የመንግሥት ፍላጎት ነው" ብለዋል።

"ተማሪዎች እንዲያልፉ ነው የምንፈልገው። ተማሪዎች በመውደቃቸው የሚገኝ ምንም ጥቅም የለም። እየሆነ ያለው ያሳዝናል። ነገር ግን የሰጠናቸው ፈተናዎች ያለብንን የትምህርት ጥራት ጉድለት፣ የበሽታችንን ጥግ አሳይተውናል።"

ለተጨማሪ የ12ኛ ክፍል መረጃዎች 
●▬▬▬▬▬ ๑۩۩๑ ▬▬▬▬▬● 
⭕️ 👉 t.me/grade12results 👈  ⭕️ 
⭕️ 👉 t.me/grade12results 👈  ⭕️ 
⭕️ 👉 t.me/grade12results 👈  ⭕️ 
●▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬●
👏2😱1🕊1
ዘንድሮ ከ100 ሺህ በላይ ተማሪዎች በሬሜዲያል ፕሮግራም እንደሚታቀፉ የትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) ገልጸዋል።

የኢቢሲ ብርቱ ወግ ፕሮግራም እንግዳ የነበሩት ሚኒስትሩ፤ የ2015 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ፈተና ማለፍ ያልቻሉ ተማሪዎች በTVET ተቋማት እንዲሁም በሬሜዲያል ፕሮግራም ተጠቃሚ እንደሚሆኑ ጠቁመዋል።

1,200 በላይ የቴክኒክና ሙያ ትምህርት ስልጠና ተቋማት በሀገሪቱ እንዳሉ የገለጹት ሚኒስትሩ፤ የ12ኛ ክፍል ፈተናን ማለፍ ያልቻሉት ተማሪዎች ወደእነዚህ የስልጠና ተቋማት ገብተው የሚያስፈልጋቸውን ክህሎት እንዲያገኙ ይደረጋል ብለዋል።

በሌላ በኩል ከ100 ሺህ በላይ ተማሪዎች በ2016 ዓ.ም በሬሜዲያል ፕሮግራም የሚታቀፉ መሆናቸውን ተናግረዋል።

እነዚህ ተማሪዎች ወደ ዩኒቨርሲቲ ሲገቡ ብቃት ያላቸው ተማሪዎች እንዲሆኑ የሚያዘጋጃቸውን የማጠናከሪያ ትምህርት ለአንድ ዓመት እንደሚወስዱ ገልጸዋል።

ባለፈው ዓመት በሬሜዲያል ፕሮግራም ታቅፈው የነበሩ ተማሪዎች ላይ በተሠራ የማብቃት ሥራ የመልቀቂያ ፈተና በድጋሜ ከወሰዱ ተማሪዎች 70 ከመቶ የሚሆኑት ማለፋቸውን ሚኒስትሩ አስታውሰዋል።

ለተጨማሪ የ12ኛ ክፍል መረጃዎች 
●▬▬▬▬▬ ๑۩۩๑ ▬▬▬▬▬● 
⭕️ 👉 t.me/grade12results 👈  ⭕️ 
⭕️ 👉 t.me/grade12results 👈  ⭕️ 
⭕️ 👉 t.me/grade12results 👈  ⭕️ 
●▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬●
👍101🤔1
"በ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና የያዝነው አቅጣጫ የሚቀጥል ነው። ወደኋላ የምንመልሰው አይደለም።"

- የትምህርት ሚኒስትር ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር)

የትምህርት ዘርፍ ማሻሻያዎች እና የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተናን አስመልክተው የትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) ከኢቢሲ ጋር ቆይታ አድርገዋል።

መንግሥት በ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ላይ የያዘውን አቅጣጫ አጠናክሮ እንደሚቀጥልበት ሚኒስትሩ ተናግረዋል።

"የመልቀቂያ ፈተና አሰጣጡን የበለጠ ውጤታማ ለማድረግ ይሠራል" ብለዋል።

በዚህም በግንቦት ወር መጨረሻ የሚከናወነው የ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ፈተና ድብልቅ / Hybrid በሆነ መልኩ እንደሚሰጥ ሚኒስትሩ አረጋግጠዋል።

ፈተናው በከፊል በዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ በአካል፥ በከፊል ደግሞ በኦንላይን (በተለይ የኢንተርኔት ችግር ባለባቸው አካባቢዎች) የሚሰጥ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

ደህንነቱ በተጠበቀ መልኩ በቴክኖሎጂ በመታገዝ ፈተናውን መስጠት የመንግሥትን ወጪ ይቀንሳል ያሉት ሚኒስትሩ፤ ይህን ለማሳካት ለፈተናው የሚሆኑ ታብሌቶችን የማሰባሰብ ሥራ መጀመሩን ጠቁመዋል።

የ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ምዝገባም በኦንላይን ይከናወናል ብለዋል።

ለተጨማሪ የ12ኛ ክፍል መረጃዎች 
●▬▬▬▬▬ ๑۩۩๑ ▬▬▬▬▬● 
⭕️ 👉 t.me/grade12results 👈  ⭕️ 
⭕️ 👉 t.me/grade12results 👈  ⭕️ 
⭕️ 👉 t.me/grade12results 👈  ⭕️ 
●▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬●
👍8
‼️ብሔራዊ ፈተና

ባለፉት ሁለት የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተናዎች በሚሊዮን የሚቆጠሩ ተማሪዎች ተፈትነው ያለፉት ግን እጅግ በጣም ጥቂት ናቸው።

ምን የተቀረ ነገር ኖሮ ነው ? የትምህርት ሚኒስትሩ ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ ከሰሞኑን በብሄራዊ ቴሌቪዥን ጣቢያ ቀርበው ማብራሪያ ሰጥታዋል።

ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ ፦

" የፈተናው ክብደ እና ቅለት ከሆነ ምንም የተቀየረ ነገር የለም።

የፈተና አሰጣጥ እና ዝግጅት ሂደት አለ፤ እራሱን የቻለ ሳይንስ አለው በጣም እንዳይከብድም በጣም እንዳይቀልም።

እስከ ዛሬ ሲሰራ ከነበረው ምንም የተለየ ነገር የለም። የተለየው ፈተና አሰጣጡ ነው።

ፈተና አሰጣጡ ያመጣው ለውጥ ምንድነው ከተባለ ፤ ከዚህ በፊት ፈተናዎች በየትምህርት ቤት ነው የሚሰጡት ፈተና መታተም ከጀመረ ጊዜ ጀምሮ ፣ ከወጣ ጊዜ ጀምሮ ፈተናዎቹ ይሰረቃሉ።

ፈተና ሲሰረቅ የነበረው በተደራጀ መልክ ነው በክልሎች ፈታኞች በየክልሉ ሲሄዱ ትልቅ ግብዣ ተደርጎ ጉቦ ተሰጥቷቸው ተማሪዎቹ እንዲኮራረጁ ይደረጋል። ውጤቱ ትርጉም ያለው አልነበረም።

እኔ ትምህርት ሚኒስቴር የመጣሁ ጊዜ በሁለተኛው ሳምንት ፈተና ሰጥተን ነበር በድሮው አሰጣት ፎርማት ያኔ ነው የማለፊያ ውጤት 50 በመቶ ነው ብለን ፖሊሲ ያደረግነው ፣በወቅቱ ፈተና አሰጣጡን አልቀየርንም ነበር ያኔ ያለፈው 48% ነው። አንዳንድ ክልሎች 70-80 በመቶ አሳልፈዋል።

በምንም አይነት የተማሪዎቹ ችሎታና ብቃት አይደለም። ... መሰረቅ መኮረጁን ለማወቅ ዳታውን ከተታትሎ ማግኘት ይቻላል፤ ግልፅ ነው።

ፈተናው እራሱ የተማሪዎች ችሎታና ብቃት መለኪያ አልነበረም። ያንን ነው የቀየርነው። ከምንም በፊት የሰራነው በተማሪዎች ጭንቅላት ውስጥ በስርቆት፣ በማጭበርበር  ፣ ሌላ ሰው በማስፈተን ፣ በመኮረጅ የሚገኝ ትምህርት የለም የሚል ነው። ይሄን አውቀው እንደ ችሎታቸው እንዲያጠኑ ነው ያደረግነው።

የዛ ውጤት፣ እንደ ሀገር ያለንበትን ልክ ነው ያሳወቀን። በዚህም ይሄ ነው የትምህርት ስርዓቱ ካልን በኃላ ሪፎርሞችን በተግባር አውለን አንድ ትውልድ ቢበላሽብን ቀጣዩን እንዴት እናድናለን ብለን ነው እየሰራን ያለነው። "

እንደ ትምህርት ሚኒስቴር መረጃ ፤ በ2014 እና በ2015 በድምሩ 1,741,619 ተማሪዎች የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና ውስደዋል። ከነዚህ ውስጥ ያለፉት በድምሩ 57,301 ተፈታኞች ናቸው።

በዚህ ልክ ተፈታኝ ተማሪዎች መውደቃቸው ዜጎችን ያስደነገጠ ቢሆንም ከነዚህ ተማሪዎች በፊትም ፈተናው አሰጣጡ በዚህ መንገድ ቢሆን ውጤቱ ከዚህ እንደማይለይና የትምህርት ስርዓቱ ውድቀት ከታች ጀምሮ የመጣ እንደሆነ የሚገልጹ በርካቶች ናቸው።

ለዚህ ውድቀት ደግሞ ሁሉም ባለድርሻ ኃላፊነት እንዳለበትና ተማሪዎቹን ከሚያስተምሯቸው መምህራን ብቃት አንስቶ ፣ የትምህርት ቤቶች የጥራት ጉዳይ፣ የግብዓት አቅርቦት ሁሉ ሊፈተሽ የሚገባው እንደሆነ የሚያመላክት መሆኑ ይነሳል።

ለተጨማሪ የ12ኛ ክፍል መረጃዎች 
●▬▬▬▬▬ ๑۩۩๑ ▬▬▬▬▬● 
⭕️ 👉 t.me/grade12results 👈  ⭕️ 
⭕️ 👉 t.me/grade12results 👈  ⭕️ 
⭕️ 👉 t.me/grade12results 👈  ⭕️ 
●▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬●
🕊6👌3👍2😱21
የቅሬታ ምላሽ

በ2015 ት/ት ዘመን የ12ኛ ክፍል ሀገራዊ ፈተና ለይ በአካል በመምጣት ቅሬታ ላቀረባችሁ በስልክ ወይም በአጭር የጽሁፍ መልዕክት ምላሽ ተሰጥቷል። እየተሰጠም ይገኛል።

በበይነ መረብ(Online) ቅሬታ ያቀረባችሁ ምላሹም በበይነ መረብ የተሰጠ በመሆኑ ከዚህ በፊት ውጤት ባያችሁበት መልኩ በድረ ገጽ eaes.et ላይ ምላሹን ማየት የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን።

በቁጥር የተወሰኑ ቅሬታዎች በምላሽ ሂደት ላይ ያሉ በመሆኑ በትዕግስት እንድትጠብቁን እንጠይቃለን።

የት/ት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት

ለተጨማሪ የ12ኛ ክፍል መረጃዎች 
●▬▬▬▬▬ ๑۩۩๑ ▬▬▬▬▬● 
⭕️ 👉 t.me/grade12results 👈  ⭕️ 
⭕️ 👉 t.me/grade12results 👈  ⭕️ 
⭕️ 👉 t.me/grade12results 👈  ⭕️ 
●▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬●
👍1
ተሸለመች👏

የ2015 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ከፍተኛ ውጤት ላስመዝግባለችው ሃናን ናጂ ሙለጌ ድርጅት ባለቤቱ ሀጂ ሙስጠፋ አህመድና betopia ፕሮፐርቲ ባለቤት አቶ ሙኒር በጋራ 200 ሺህ ብር ሽልማት ሰጥተዋታል።

በተጨማሪም የ betopia ፕሮፐርቲው ባለቤት አቶ ሙኒር ትምህርቷን ተምራ ጨርሳ ህዝቧን ማገልገል እስክትጀምር በየ ወሩ 10 ሺህ ብር ደምወዝ ተቆራጭ አድርጎላታል።

ለተጨማሪ የ12ኛ ክፍል መረጃዎች 
●▬▬▬▬▬ ๑۩۩๑ ▬▬▬▬▬● 
⭕️ 👉 t.me/grade12results 👈  ⭕️ 
⭕️ 👉 t.me/grade12results 👈  ⭕️ 
⭕️ 👉 t.me/grade12results 👈  ⭕️ 
●▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬●
👍2
#ጥቆማ

የ12ኛ ክፍል ትምህርታችሁን አጠናቃችሁ በቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሌኒየም ሕክምና ኮሌጅ የሕክምና ትምህርት ለመማር የምትፈልጉ የመመዝገቢያ መስፈርት በቅርቡ ይፋ እንደሚያደርግ ኮሌጁ አሳውቋል፡፡

እስከዛው በትዕግስት እንድትጠብቁ ኮሌጁ ጠይቋል፡፡

ለተጨማሪ የ12ኛ ክፍል መረጃዎች 
●▬▬▬▬▬ ๑۩۩๑ ▬▬▬▬▬● 
⭕️ 👉 t.me/grade12results 👈  ⭕️ 
⭕️ 👉 t.me/grade12results 👈  ⭕️ 
⭕️ 👉 t.me/grade12results 👈  ⭕️ 
●▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬●
👏2👍1
የተማሪዎች ክፍፍል እና መማር የሚችሉት ‼️

ከ50% በላይ ያመጡ ተማሪዎች በሙሉ በባቻቸው ፍሬሽማን ኮርስ ይጀምራል። በቅርቡ ወደ ተመረጡ 15 ዩኒቨርስቲወች ይመደባሉ።

ከ50% በታች ያመጡ ተማሪዎች ሶስት አማራጭ አላቸው

1) መንግስት የሚሰጠውን ሁለተኛ ዕድል /Remedial Program/ በመጠቀም የማካካሻ ትምህርት መውሰድ እና አንድ ባች ዝቅ ብሎ ፍሬሽማን መጀመር።(መቁረጫ ነጥብ ለሚያሟሉ)

💠 ከመንግስት ዩንቨርሲቲ ውጭ በግል ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የማካካሻ ትምህርት ተምረው የድግሪ መማሪያ ውጤት አምጥተው ቀጣይ ድግሪ መማር ይችላሉ።

2) ከቀጣይ ተፈታኞች(2016 ባች) ጋር በግል ድጋሚ መፈተን ይችላሉ

3)ቴክኒክና ሙያ መሰልጠን ይችላሉ። (መቁረጫ ነጥብ በቅርቡ)

💠በመንግስት ስፖንሰርነት ማካካሻ የሚወስዱ #የ100ሺህ ተማሪዎች የመቁረጫ ነጥብ በቅርብ ቀን ይፋ ይደረጋል። 

💠እንድሁም አጠቃላይ በ Remedial ፕሮግራም እና በ ቴክኒክ እና ሙያ የሚያስገባውን መቁረጫ ነጥብ በቅርቡ ይፋ ይሆናል።

ለተጨማሪ የ12ኛ ክፍል መረጃዎች 
●▬▬▬▬▬ ๑۩۩๑ ▬▬▬▬▬● 
⭕️ 👉 t.me/grade12results 👈  ⭕️ 
⭕️ 👉 t.me/grade12results 👈  ⭕️ 
⭕️ 👉 t.me/grade12results 👈  ⭕️ 
●▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬●
👍18🤩1
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
በ12ኛ ክፍል ውጤት “ራቁታችንን ምን እንደምንመስል አይተነዋል” - ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ

የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ፤ የመስሪያ ቤታቸውን የዘንድሮ እቅድ እና የበጀት ዓመቱን የሩብ ዓመት አፈጻጸም ለማቅረብ ዛሬ ረቡዕ በፓርላማ ተገኝተው ነበር። የዛሬውን ስብሰባ በጠራው የተወካዮች ምክር ቤት የሰው ሃብት ልማት፣ ሥራ ስምሪት እና ቴክኖሎጂ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ለሚኒስትሩ ካቀረባቸው ጥያቄዎች መካከል የ12ኛ ክፍል ፈተና ውጤትን የሚመለከት ይገኝበታል።

ከፈተናው ውጤት ጋር በተያያዘ ለቀረበላቸው ጥያቄዎች የሰጡትን ምላሽ መስማት የምትፈልጉ 👇
https://youtu.be/fvT_05aux4o

ለተጨማሪ የ12ኛ ክፍል መረጃዎች 
●▬▬▬▬▬ ๑۩۩๑ ▬▬▬▬▬● 
⭕️ 👉 t.me/grade12results 👈  ⭕️ 
⭕️ 👉 t.me/grade12results 👈  ⭕️ 
⭕️ 👉 t.me/grade12results 👈  ⭕️ 
●▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬●
👍5
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ በዛሬው የፓርላማ ቆይታቸው ስለ ሬሜድያል ከተናገሩት👇

💥አምና በመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች #105,000 የሬሜዲያል ተማሪዎች ትምህርታቸውን ተከታትለዋል፤ #63,033 ተማሪዎች አልፈዋል።

💥አምና በግል ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት #44,500 የሬሜዲያል ተማሪዎች ትምህርታቸውን ተከታትለው፥ #27,587 የሚሆኑት አልፈዋል።

💥በአጠቃላይ #145,500 ተማሪዎች በሬሜዲያል ፕሮግራም ትምህርታቸውን ተከታትለው #90,620 አካባቢ ተማሪዎች ከሬሜዲያል ወደ ፍሬሽማን አልፈዋል።

🛟በዚህ ዓመት ፍሬሽማን የሚኖረው አምና በሬሜዲያል ፕሮግራም ትምህርታቸውን ተከታትለው ያለፉት #90,620 ተማሪዎች እና በ#2015 የኢንትራንስ ፈተና 50% እና ከዚያ በላይ ያመጡት #27,200 ተማሪዎች ናቸው።

💥ዘንድሮ በዩንቨርሲቲዎች(በከፍተኛ የትምህርት ተቋማት) ውስጥ በአጠቃላይ የሚመደቡት #191,509 ተማሪዎች ሲሆኑ ከነዚያ ውስጥ በሬሜዲያል #164,242 ተማሪዎችን ይቀበላሉ።( የመንግስት እና የግል ተቋማት ላይ)

💥የተማሪዎች ምደባን በተመለከተ በምንም አይነት መልኩ አግባብ ያልሆነ በአድሎ ላይ የተመሰረተ ምደባ ሚባል ነገር እንደማይኖር አስረግጠው ተናግረዋል። ብቸኛው ከምደባ አሰራር በተለየ መልኩ የሚስተናገደው የህክምና አስገዳጅ ጉዳይ ሲኖር ብቻ መሆኑን ተናግረዋል።

የፕሮፌሰሩን ሰፋ ያለ ማብራሪያ ያድምጡ👇
https://youtu.be/fvT_05aux4o

ለተጨማሪ የ12ኛ ክፍል መረጃዎች 
●▬▬▬▬▬ ๑۩۩๑ ▬▬▬▬▬● 
⭕️ 👉 t.me/grade12results 👈  ⭕️ 
⭕️ 👉 t.me/grade12results 👈  ⭕️ 
⭕️ 👉 t.me/grade12results 👈  ⭕️ 
●▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬●
👍16
‼️ተጠናቋል

የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ከ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ውጤት ጋር በተያያዘ የተማሪዎች ቅሬታ ማቅረቢያ ጊዜ መጠናቀቁን አረጋግጧል፡፡

በ2015 ትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ሀገራዊ ፈተና ውጤት ላይ በስልክና በአጭር የጽሁፍ መልዕክት ቅሬታ ላቀረቡ ተማሪዎች አገልግሎቱ ባለፉት ቀናት ምላሽ ሲሰጥ መቆየቱን አስታውሷል፡፡

ይሁን እንጂ በተለያዩ አስገዳጅ ምክንያቶች በወቅቱ ቅሬታ ማቅረብ ያልቻሉ ተፈታኞች በአገልግሎቱ ለዚህ ሥራ ለተመደበ ክፍል ማቅረብ የሚችሉ መሆኑን እናሳውቋል፡፡

ለተጨማሪ የ12ኛ ክፍል መረጃዎች 
●▬▬▬▬▬ ๑۩۩๑ ▬▬▬▬▬● 
⭕️ 👉 t.me/grade12results 👈  ⭕️ 
⭕️ 👉 t.me/grade12results 👈  ⭕️ 
⭕️ 👉 t.me/grade12results 👈  ⭕️ 
●▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬●
👍2
የዘንድሮ የዩኒቨርሲቲ የተማሪዎች ምደባ ችሎታና ፍላጎታቸውን መሰረት ባደረገ መልኩ ይከናወናል -ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ

የዘንድሮ የዩኒቨርሲቲ የተማሪዎች ምደባ ችሎታና ፍላጎታቸውን መሰረት ባደረገ መልኩ የሚከናወን እንጂ በማንም ተጽዕኖ የሚቀየር አይደለም ሲሉ የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ገለጹ።
 
በ2014 የትምህርት ዘመን በመንግስትና በግል የሪሚዲያል ፈተና ከወሰዱ 145 ሺህ ተማሪዎች መካከል 90 ሺህ ያህሉ ወደ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መግባት የሚያስችላቸውን ውጤት አስመዝግበዋል።
 
እነዚህ ተማሪዎች በ2015 የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ወስደው የዩኒቨርስቲ መግቢያ ውጤት ካመጡት ከ27 ሺህ በላይ ተማሪዎች ጋር ተደምረው በአጠቃላይ ከ117 ሺህ በላይ ተማሪዎች ወደ ተለያዩ የመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች ይመደባሉ ተብሎ ይጠበቃል።
 
ፕሮፌሰር ብርሃኑ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት በሰጡት ማብራሪያ የዘንድሮ የተማሪዎች ምደባ ችሎታቸውንና ፍላጎታቸውን መሰረት ባደረገ መልኩ በፍትሐዊነት እንደሚከናወን ገልጸዋል።
 
ቀደም ሲል በተማሪዎች ምደባ ላይ ይነሱ የነበሩ ቅሬታዎችን ታሳቢ በማድረግ ክፍተቶች ተለይተው እንዲስተካከሉ መደረጉንም አብራርተዋል።
 
በመሆኑም በከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የትምህርት ጥራትን ለማምጣት ተማሪዎች በችሎታቸውና በፍላጎታቸው መሰረት እንዲመደቡ ይደረጋል ነው ያሉት።
 
የህክምና ክትትል እያደረጉ መሆኑን ትክክለኛ ማስረጃ ከሚያቀርቡ ተማሪዎች ውጪ የዝውውር ጥያቄ ተቀባይነት እንደሌለውም ተናግረዋል።  
 
አንዳንድ ግለሰቦች ምደባ ለማስቀየር ጥያቄ እንደሚያቀርቡ የተናገሩት ፕሮፈሰሩ የተማሪዎቹ ምደባ በማንም ተጽዕኖ ምክንያት ሊቀየር አይችልም ብለዋል።
 
ለተጨማሪ የ12ኛ ክፍል መረጃዎች 
●▬▬▬▬▬ ๑۩۩๑ ▬▬▬▬▬● 
⭕️ 👉 t.me/grade12results 👈  ⭕️ 
⭕️ 👉 t.me/grade12results 👈  ⭕️ 
⭕️ 👉 t.me/grade12results 👈  ⭕️ 
●▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬●
👍7
SCHOLARSHIP

በ2015 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል አገር አቀፍ ፈተና ወስዳችሁ ለትምህርት ሚኒስቴር ተጠሪ በሆኑ የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች በወጪ መጋራት (ስኮላርሽፕ) ለመማር ያለፋችሁና በምደባ ወቅት አዎንታዊ ድጋፍ ለምትሹ ተማሪዎች ማመልከቻችሁን በ https://student.ethernet.edu.et በኩል እስከ ጥቅምት 16/2016 ዓ.ም እንድታመለክቱ ትምህርት ሚኒስቴር አሳውቋል።

ምንም አይነት ማመልከቻ በአካል #የማይቀበል መሆኑን ሚኒስቴሩ አሳስቧል።
 
ለተጨማሪ የ12ኛ ክፍል መረጃዎች 
●▬▬▬▬▬ ๑۩۩๑ ▬▬▬▬▬● 
⭕️ 👉 t.me/grade12results 👈  ⭕️ 
⭕️ 👉 t.me/grade12results 👈  ⭕️ 
⭕️ 👉 t.me/grade12results 👈  ⭕️ 
●▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬●
👍4👌1
‼️በ2015 ሬሚድያል ፈተና ተፈትናችሁ ላለፋችሁ ተማሪዎች!!

" ከግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋም ወደ መንግስት ከፍተኛ ትምህርት ተቋም ተዛውሮ መማር አይቻልም " - ትምህርት ሚኒስቴር

ትምህርት ሚኒስቴር ዛሬ ጥቅምት 9 ቀን 2016 ዓ/ም ለሁሉም የመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች እና የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በፃፈው ደብዳቤ በ2015  ትምህርት ዘመን የሬሜዲያል ትምህርት ተከታትለው 50 በመቶ እና ከዚያ በላይ ያመጡ ተማሪዎች የፍሬሽማን ኮርስ እንዲማሩ መወሰኑን አስታውሷል።

በዚህም መሰረት ተማሪዎች ፦

- ከመንግስት ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ወደ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተዛውሮ መማር እንደሚችሉ፤

- ከአንድ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋም ወደ ሌላ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋም ተዛውሮ መማር እንደሚችሉ፤

- ከግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋም ወደ መንግስት ከፍተኛ ትምህርት ተቋም ተዛውሮ መማር #የማይችሉ መሆኑን ትምህርት ሚኒስቴር አስገንዝቧል። ተማሪዎች ከአንድ ተቋም ወደ ሌላ ተቋም ሄደው መማር የሚፈልጉ ከሆነ መረጃቸው በአግባቡ ተደራጅቶ እንዲሰጣቸው ትምህርት ሚኒስቴር በፃፈው ደብዳቤ አሳስቧል።

ለተጨማሪ የ12ኛ ክፍል መረጃዎች 
●▬▬▬▬▬ ๑۩۩๑ ▬▬▬▬▬● 
⭕️ 👉 t.me/grade12results 👈  ⭕️ 
⭕️ 👉 t.me/grade12results 👈  ⭕️ 
⭕️ 👉 t.me/grade12results 👈  ⭕️ 
●▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬●
👍17🤔4😢4🤯3👏2👌1🕊1
‼️የዩኒቨርስቲ ምደባ

በ2015 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ብሄራዊ ፈተና ወስደው ያለፉ ተማሪዎች የዩኒቨርሲቲ ምደባ አሰራርን አስመልክቶ የተሰጠ ማብራሪያ

የተማሪ ምደባ መስፈርቶች፡-

1.  1000 ለሚሆኑ ከፍተኛ ውጤት ላስመዘገቡ ተማሪዎች፡- የምደባ ስርዓቱ በተፈጥሮም ሆነ በማህበራዊ ሳይንስ መስኮች 1000 ከፍተኛ ውጤት ያስመዘገቡ ተማሪዎችን  በመጀመሪያ የዩኒቨርስቲ እና የትምህርት መስክ ምርጫቸው ምደባ የሚካሄድ ይሆናል።

2. ውጤት፡- የምደባ ስርዓቱ እያንዳንዱ ተማሪ ያስመዘገበውን አጠቃላይ ውጤት በምደባ ስርዓት ሂደት ውስጥ መለያ አድርጎ ይጠቀማል፡፡የተሻለ ውጤት ያስመዘገቡ ተማሪዎች ሌሎች ተፈጻሚ የሚሆኑ ህግና ደንቦችን ባልጣሰ መልኩ ምርጫቸውን በመጠበቅ ረገድ ቅድሚያ ይሰጣቸዋል፡፡

3. የዩኒቨርሲቲ ምርጫ፡- የምደባ ስርዓቱ በተማሪዎች የተመረጡ ዩኒቨርሲቲዎች ያላቸውን የቅበላ አቅም ታሳቢ ያደረገ ነው፡፡ ተማሪዎች 46 ዩኒቨርሲቲዎች ለምርጫ ቀርበውላቸዋል፡፡ መረጃው የተሰበሰበው https://portal.etherenet.edu.et ላይ ነው፡፡

4. በተማሪዎች የተመረጡ ተቋማት ያላቸው የትምህርት ፕሮግራሞች ፡- የምደባ ስርዓቱ በተማሪዎች የተመረጡ የትምህርት ፕሮግራሞች እና የተመረጡት ዩኒቨርሲቲዎች ያላቸውን የትምህርት ፕሮግራም መሰረት ያደረገ እንዲሆን ተደርጓል፡፡

5. ጾታ ፡- በተቋማት የጾታ ተዋጽኦን ለመጠበቅ በሚኖረው የምደባ ስርዓት የጾታ ተዋጽኦና ሚዛን እንዲጠበቅ ተደርጓል፣

ለተጨማሪ የ12ኛ ክፍል መረጃዎች 
●▬▬▬▬▬ ๑۩۩๑ ▬▬▬▬▬● 
⭕️ 👉 t.me/grade12results 👈  ⭕️ 
⭕️ 👉 t.me/grade12results 👈  ⭕️ 
⭕️ 👉 t.me/grade12results 👈  ⭕️ 
●▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬●
👍6🙏21🤔1