Forwarded from Fentaw
የዳግማዊ ምኒልክ ህክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ የ2018 በጀት ዓመት እቅድ አፈጻጸም ግምገማና የ2019 በጀት ዓመት እቅድ ትውውቅ መድረክ በድምቀት አካሄደ!
የዳግማዊ ምኒልክ ህክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ የ2018 ዓ/ም በጀት ዓመት እቅድ አፈጻጸም ለመገምገም እና የ2019 በጀት ዓመት እቅድ ለማስተዋወቅ ያዘጋጀው ዓመታዊ መድረክ ዛሬ ማለትም ነሃሴ 26-12-2018 ዓ/ም ተካሄደ። መድረኩ የኮሌጁን አጠቃላይ የስራ ቁመና ከማሳደግ ባለፈ የሰራተኞችን ተሳትፎ እና የባለቤትነት ስሜት ያጠናከረ ነበር።
መርሃ ግብሩን በንግግር የከፈቱት የኮሌጁ ቺፍ ኤክስኪዩቲቭ ዳይሬክተር አቶ አለሙ ዳንኤል ሲሆኑ፣ መድረኩ የቀጣዩን ዓመት አቅጣጫዎች የሚወስን ምዕራፍ መሆኑን አንስተዋል። ለዚህም ተሳታፊዎች አጀንዳዎችን በጥሞና በመከታተል ገንቢ ሃሳቦችን፣ ጥያቄዎችን እና የማዳበሪያ አስተያየቶችን በመስጠት እቅዱን በባለቤትነት በመውሰድ በትጋት መፈጸም አስፈላጊ መሆኑን አስታውሰዋል።
የኮሌጁ የቺፍ ኤክስኪዩቲቭ ዳይሬክተር አማካሪ አቶ ጥበቡ ቸርነት የ2018 ዓ/ም በጀት ዓመት እቅድ አፈጻጸም በሰፊው ያነሱ ሲሆን በዚህም መሰረት በመር ማስተማር፣ በጥናትና ምርምር ፣ በማህበረስብ አቀፍ አገልግሎት፡ በአስተዳደራዊና በገፅታ ግንባታ ከፍተኛ ስራዎች የተሰሩበት አመት እነደሆን በሪፖረቱ በሰፊው አንስተዋል፡፡ በተጨማሪም ኮሌጁ ባጋጠሙ ተግዳሮቶችና የተወሰዱ የመፍትሔ እርምጃዎችን በሰፊው በማቅረብ አጠቃላይ በኮሌጁ የተመዘገቡት አበረታች ውጤቶች የተቋሙ ሠራተኞች የጋራ ርብርብ ውጤት መሆኑን ተጠቁሟል።
የኮሌጁ እቅድ፣ በጀት ክትትልና ግምገማ ዳይሬክተር ወ/ሮ ቆንጅት ሃይለየሱስ የ2019 በጀት ዓመት እቅድን ይፋ አድርገዋል። እቅዱ ዋና ትኩረቱን የመማር ማስተማር፣ የጥናትና ምርምር ስራዎችን በስፋት ማጠናከር፣ ህብረተሰብ አቀፍ የማህበረሰብ አገልግሎት ተደራሽነትን ማስፋት፣ እንዲሁም የአስተዳደር ዘርፍ አሰራሮችን በቴክኖሎጂና በብቃት ማዘመን ላይ በማተኮር በሰፊው ተመላክቷል።
በቀረቡት ሪፖርቶች እና እቅዶች ዙሪያ ከተሳታፊዎች ለተነሱ ጥያቄዎች እና አስተያየቶች የማኔጅመንት አባላት በየዘርፋቸው ሰፋ ያለ ማብራሪያና ምላሽ የሰጡ ሲሆን፡ ይህም ለ2019 በጀት ዓመት እቅድ በላቀ ደረጃ ለመፈፀም እንደ መስፈንጠሪያ እንደሚሆን ይጠበቃል፡፡
የዕለቱ መርሃ ግብር ሲጠናቀቅም በኮሌጁ ለረጅም ዓመታት በታማኝነት ያገለገሉ እና በጡረታ የተገለሉ የቀድሞ ሰራተኞች እውቅናና ምስክር ወረቀት የተሰጠ ሲሆን ከዚህም በተጨማሪ በበጀት ዓመቱ የላቀ የስራ አፈጻጸም ላስመዘገቡ የአካዳሚክ እና የአስተዳደር ሰራተኞች የምስጋና እና የእውቅና ሰርተፍኬት ተበርክቶላቸዋል።
በመጨረሻም የኮሌጁ ቺፍ ኤክስኪዩቲቭ ዳይሬክተር አቶ አለሙ ዳንኤል በመዝጊያ ንግግራቸው ለኮሌጁ ሰራተኞች ምስጋና በማቅረብ፣ ኮሌጁን በሁለተናዊ ለውጥ መገንባት የሚቻለው በሰራተኛው ጠንካራ ተሳትፎ መሆኑን ገልጸው፤ ማኔጅመንቱ ለዚህ አላማ ስኬት ሁልጊዜም ቁርጠኛ በመሆን እንደሚሰራ በማረጋገጥ መርሃ ግብሩ ተጠናቋል።

❤3
Forwarded from Fentaw
Forwarded from Fentaw
Forwarded from Fentaw