Forwarded from Addis Ababa Health Bureau / አዲስ አበባ ጤና ቢሮ / AACAHB /
❤1👍1

የዳግማዊ ምኒልክ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ የጥናትና ምርምር ስራዎችን አስመልክቶ ሲምፖዚየም አካሂዷል።
አ/አ/ጤና ቢሮ የካቲት 19 ቀን 2018 ዓ.ም
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮ ስር የሚገኘው የዳግማዊ ምኒሊክ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ብቁ የጤና ባለሞያዎችን በማፍራት ለጤናው ዘርፍ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እያበረከተ ሲሆን ከዚህ ባለፈም የማህበረሰቡን ችግሮች ላይ ጥናት እና ምርምር በማድረግ ሳይንሳዊ በሆነ መንገድ በመፍታት ትኩረት አድርጎ እየሰራ ይገኛል ።
ኮሌጁ በተለይም በ2017 ዓ.ም የተከናወኑ የጥናትና ምርምር ስራዎችን አስመልክቶ የኮሌጁ አመራሮች ፣ ተመራማሪዎች ፣ የጤና ባለሞያዎች በአዲስ አበባ ከተማ ከሚገኙ የጤና ተቋማት እና ባለድርሻ አካላት በተገኙበት ሲምፖዚየም አካሂዷል።
የሲምፖዚየሙን ዓለማ በማስመልከት ገለፃ ያደረጉት የኮሌጁ የጥናትና የማህበራዊ አገልግሎት ቺፍ ዳይሬክተር ዶክተር ፍቅር ወልደስላሴ ሲምፖዚየሙ ኮሌጁ ምርምርን፣ ፈጠራን እና የማህበረሰብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ያለውን ጠንካራ ቁርጠኝነት የሚያሳይ ነው ብለዋል።
ምርምር ለአካዳሚክ እድገት ብቻ ሳይሆን ማስረጃ ለማመንጨት ችግሮችን ለመፍታት እና ለህብረተሰብ ብሎም ለሃገር የሚሰጠውን አገልግሎት ጥራት ለማሻሻል የሚያስችል መሆኑንም ገልፀዋል።
የጥናትና ምርምር ስራ የኮሌጁ የመማር ማስተማር ስራ አንዱ አካል እና የስራ ባህል በማድረግ እየተሰራ እና የማህበረሰቡን የጤና ችግሮች በጥናትና ምርምር ለመፍታት አቅሙን እያሳደገ ነው ብለዋል።
የሚሰሩ የጥናትና ምርምር ተግባራት ጥንካሬዎችን አጠናክሮ በማስቀጠል የማህበረሰቡን የጤና ችግሮች ለመለየትና ለመፍታት እያደረገ ላለው ሚና አቅሙን ይበልጥ ለማሳደግ ይሰራል ብለዋል።
ሲምፖዚየሙ በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ የቀዳማይ ልጅነት ዕድገት ልማት ፕሮግራም፣ የወጣቶች የተዋልዶ ጤና ግንዛቤና ተደራሽነት ፣ የህብረተሰቡ በጤና ተቋማት አገልግሎቶች ላይ ያለው እርካታ ያተኮሩ ጥናትና ምርምሮች ቀርበዋል።
በተለይም በጤና ተቋማት ያለው የተገልጋዮች እርካታ ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮ ጋር በትብብር መሰራቱ በማህበረሰቡ ላይ ተጨባጭ ውጤት ለማስመዝገብ ያለው ፋይዳ ጉልህ በመሆኑ ጥናትና ምርምር መደረጉ ተገልጿል።
በቢሮው ስር በሚገኙ ሆስፒታሎች በተለይም የስኳርና ደም ግፊትን ጨምሮ ሌሎች ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎች ላይ የተገልጋዮች ክትትል እና ህክምና እንዲሁም የድንገተኛ ህክምና አሰጣጥ ላይ የተካሄዱ ጥናትና ምርምሮች እና የታየ መሻሻሎች ቀርበዋል።
እንደ ሀገር ኤች አይ ቪ ከእናት ወደ ልጅ የመተላለፍ መጠንን እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር በ2030 ከ5 በመቶ በታች ለማድረስ የተያዘውን ዕቅድ በከተማዋ አስቀድሞ ማሳካት መቻሉ በተሰሩት ጥናትና ምርምሮች ላይ ቀርቧል።
የዳግማዊ ምኒልክ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ቺፍ ኤክስኪዩቲቭ ዳይሬክተር አቶ አለሙ ዳንኤል ኮሌጁ የማህበረሰቡን የጤና ችግሮች በጥናትና ምርምር በመለየት እና በመፍታት ትልቅ አስተዋፅኦ እያበረከተ ነው ብለዋል።
የዳግማዊ ምኒልክ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ከተመሰረተበት ከ1941 ዓ.ም ጀምሮ በጤናው ዘርፍ ብቁ ባለሞያዎችን በማፍራት ከአዲስ አበባ ከተማ ባለፈ እንደ ሃገር ለዘርፉ ትልቅ አስተዋጽኦ እያበረከተ እንደሚገኝ አቶ አለሙ ዳንኤል ገልጸዋል፡፡
ኮሌጁ ከመማር ማስተማር ባለፈ በጥናትና ምርምር ስራዎች የህብረተሰቡን ችግሮች ሳይንሳዊ በሆነ መንገድ በመለየት እና በመፍታት የድርሻውን እየተወጣ እንደሚገኝም ዳይሬክተሩ አለሙ ዳንኤል ተናግረዋል።
በ2017 ዓ.ም በኮሌጁ ተመራማሪዎች ከህብረተሰቡ እና ከከተማዋ ባለፈ ለሃገር የፖሊሲ ግብዓት ፋይዳ ያላቸው 22 ጥናቶች መካሄድ መቻላቸውንም አለሙ ዳንኤል ገልፀዋል።
በተያዘው 2018 ዓ.ም 36 ጥናቶች በመካሄድ ላይ መሆናቸውን እና ጥናቶቹ የሚጠበቀውን ውጤት እንዲያስመዘግቡ በትኩረት እየተሰራ ነው ብለዋል።
የኮሌጁ ቺፍ አካዳሚክ ዳይሬክተር ዶክተር ደረጄ ደርበው የተካሄዱ እና እየተካሄዱ የሚገኙ የጥናትና ምርምር ስራዎችን ይበልጥ ውጤታማ በማድረግ ሲምፖዚየሙን ወደ ጥናትና ምርምር ኮንፈረንስ ለማሳደግ በትኩረት እንደሚሰራ ገልፀዋል።

❤6👍1
Forwarded from Fentaw
የዳግማዊ ምኒልክ ሕክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ የግማሽ ዓመት የሥራ አፈጻጸም ግምገማ መርሃ ግብር የማኔጅመንት አባላትና ሠራተኞች በተገኙበት በተሳካ ሁኔታ አከናውኗል።
ፕሮግራሙን በይፋ የከፈቱት የኮሌጁ ችፍ አስተዳደርና ልማት ዳይሬከተር አቶ ዱሬሳ ሙላቱ ሲሆኑ ለተሳታፊዎች የእነኳን ደህና መጣችሁ መልዕከት አስተላልፈው ተቋማዊ አሰራርን የበለጠ ለማጠናከርና ያለተሰሩ ስራዎችን ለመለየት የመድረኩን አስፈላጊነት እና ያለውን ጠቀሜታ በአጽንኦት ገልፀዋል። አክለውም ቀጣይነት ያለው ግምገማና ክትትል ሁሉን ዓቀፍ ተቋማዊ ለውጥ የሚኖረውን ሚና በማንሳት የመድረኩን አስፈላጊነት በድጋሜ አመልክተዋል።
ሪፖረቱን ያቀረቡት የኮሌጁ አቅድና በጀት ክትትልና ግምገማ ዳይሬከተር የሆኑት ቆንጅት ሀይለየሱስ በስድስት ወር የስራ አፈጻጸምን ሰፋ ያለ ሪፖርት አቅርበዋል። ሪፖረቱ በዋናነት በመማር ማስተማር ሂደት የተሰሩ ስራዎች፣ የጥናትና ምርምር ፣ የማህበረሰብ አገልግሎት ብሎም በአስተዳደር አርፉ ላይ የተከናወኑ አንኳር ተግባራትን በሰፊው የዳሰሰ ሲሆን ሁሉም የአስተዳደርና የአካዳሚክ መርሃ ግብሮች ላይ የታቀዱ ተግባራት ክንውንን በተሳካ ሁኔታ ማጠናቀቁን አመልክቷል።
በበጀት አመቱም በመማር ማሰተማሩ የተሰሩ ተግባራት ማለትም የማስተማሪያ ቁሳቁሶች ግዥ፡ የተማሪዎች የትምህርት ድጋፍ፡ የጤና ትምህርት ዘርፎችን በዕወቀት፣ ክህሎት እና በአመለካከት ብቁና ተወዳዳረ የጤና ባለሙያ በማፍራትና ድጋፍ ላይ የተሰሩ ስራዎች ተመልክቷል ፣ በዚህም ረገድ ኮለጁን ብቁና ተዎዳዳሪ ለማድረግ የተሰሩ ስራዎች አበረታች መሆናቸው የተነሳ ሲሆን በማህበረስብ ዐቀፍ አገልግሎት ደግሞ ከበፊት የተሻለ ሰው ተኮር ስራዎችና በማሀበረሰቡ ውስጥ ቸግሮችን በመለየትና መፈትሄ በመሰጠትም ሰፊ ስራዎች የተሰሩበት የግማሽ ዓመት ምሆኑ ተጠቁሟል፡፡በተጨማሪም ኮሌጁ በማህበረሰብ አቀፍ የጤና ግንዛቤ ማስጨበጫ ስራዎች ላይ በንቃት በመሳተፍ ለማህበራዊ ኃላፊነት እና ለህዝብ ጤና አገልግሎት ያለውን ማሳየቱ በሪፖረቱ ተመላክቷል።
በአስተዳደር ዘርፉ ደግሞ የማሪያ ክፈሎችንና ቤተ-መፅሃፍትን በማዘምን፡ ለመምህራን ስልጠና በማመቻቸት፡ ጉልህ ስራዎች መሰራታቸውን ሪፖረቱ በሰፊው ዳሷል፡፤ ከዚህም በተጨማሪ፣ ተማሪዎቹን በተግባር ብቁ ለማደረግ ከፍተኛ መዋዕለ ንዋይ በማውጣት የሰርቶ ማሳያ ክፈሎችን በማዘመን ከፍተኛ ስራዎች መሰራታቸውም ተነስተዋል፤፤ በጥናትና ምርም ዘረፍ የተሻለ አፈፃፀም የታየ ሲሆን ለዚህም መገለጫ ኮሌጁ የጥናትና ምርምር ሲምፖዚየም በማደረግ ቸግር ፈች ለሆኑ ጥናትና ምርምር ውጤቶች ይፋ መድረጋቸው ተብራርቷል፡፡
በሪፖርቱ ላይ ለተነሱ ሁሉም ጥያቄዎች የማኔጅመንት ዓባለት በየዘርፋቸው ሰፋ ያለ ምላሽና ማብራሪያ የሰጡ ሲሆን በመጨረሻም በግማሽ ዓመቱ ከፍተኛ የስራ አፈፃፀም ላስመዘገቡ የአካዳሚክ እና የአስተዳደር ሰራተኞች፣ የምስጋና እና የእውቅና ሰርተፊኬት ተበርክቶላቸዋል፡፡
በመጨረሻም የኮሌጁ ችፍ ኤክስኪዩቲቭ ደይሬከተር አቶ አለሙ ዳንኤል የመዝጊያ ንግግር ያደረጉ ሲሆን ለሰራተኞች ምስጋና በማቅረብ ኮሌጁን በሁለነተናዊ ለውጥ ለመገንባት በሚደረገው ርብርብ የሰራተኛው ሚና ደማቅ መሆኑን በመግለፅ በዚህ ረገድ በቀጣይነት ለሚሰሩ ስረዎች ማኔጅመንቱ ቁርጠኛ መሆኑን ጠቁመው፡ በቀናኤነት ለሚጠየቁ አስተዳደረዊም ሆነ አካዳሚያዊ ጥያቄዎችን ለማሰተናገድ ሁሌም ኮሌጁ ዝገጁ መሆኑን አረጋግጠው፡፡ ሁሉም የኮሌጁ ሰራተኞች በሁለተኛው ግማሽ በጀት አመት ሃላፊነትን እና ሙያዊነትን እንዲጠብቁ አበረታቷል፡፡.

❤5
Forwarded from Fentaw
❤1
Forwarded from Fentaw
Forwarded from Fentaw
Forwarded from Fentaw
Forwarded from Fentaw