EECMY Children Ministry: MY Sunday School
951 subscribers
1.33K photos
15 videos
186 links
MY Sunday School is the official page of EECMY Children Ministry.

Wholistic Growth For Our Children!

Access Sunday School learning materials at www.mysundayschool.org
Download Telegram
የታዳጊ ወጣቶች ስልጠና በሀዋሳ
====
"በሥጋችሁ እግዚአብሔርን አክብሩ " በሚል መሪ ቃል
በማዕከላዊ ደቡብ ኢ/ያ ሲኖዶስ  በልጆች አገልግሎት መምርያ የተዘጋጀ የታዳጊ ወጣቶች ስልጠና ከ ሐምሌ 1-5 - 2016 ዓ.ም ቀኑን ሙሉ ለተከታታይ አምስት ቀናት ዕድሜያቸው  ከ14-17 ዓመት ላሉ ታዳጊ  ወጣቶች በሀዋሳ ታቦር መካነ ኢየሱስ  ግቢ ውስጥ ተዘጋጅቷል። ወላጆች ልጆችን ምሳ በማስያዝ እንድትልኩ የልጆች መምርያ  ያሳስባችኃል: ሁላችሁም ተጋብዛችኃል ተባረኩ።

#EmpoweringGeneration #EECMY #SouthCentralEthiopiaSynod #ChildrenMinistry  #Teenagers #Hawassa
@MYSundaySchool
የኢ/ወ/ቤ/ክ/መካነ ኢየሱስ ካለንደር: ሐምሌ 2016 ዓ.ም

Kaalandarii WKWWMYI, Adoolessa 2016/2024

(Source: EECMY- Yemisrach Dimts Communication Service)

https://t.me/eecmyyouthministry
https://t.me/MYSundaySchool
የኢ/ወ/ቤ/ክ/መካነ ኢየሱስ ካለንደር: ነሐሴ 2016 ዓ.ም

Kaalandarii WKWWMYI, Hagayya 2016/2024

(Source: EECMY- Yemisrach Dimts Communication Service)

https://t.me/eecmyyouthministry
https://t.me/MYSundaySchool
ትውልደ ኢትዮጵያዊው ሄማን በቀለ በታይም መፅሔት የ2024 ምርጥ ልጅ ተባለ
*******

ትውልደ ኢትዮጵያዊው ሄማን በቀለ በታይም መፅሔት የ2024 ምርጥ ልጅ በመባል ተመርጧል።

አዲስ አበባ ኢትዮጵያ ተወልዶ አሜሪካ ነዋሪነቱን ያደረገው ሄማን በቀለ የቆዳ ካንሰር መከላከያ ሳሙና በመፍጠሩ ነው ለዓለም ህዝብ አሳቢ ልብ ያለው ልጅ ለመባል የበቃው።

ሄማን በቀለ ገና የ7 ዓመት ልጅ እያለ ነበር የራሱን የሳይንስ ሙከራዎችን በቤት ውስጥ ማካሄድ የጀመረው። ወላጆቹም ፍላጎቱን በማየት በቅርበት ይከታተሉት ነበር።

በዚህ የጀመረው የሳይንስና የምርምር ፍቅሩ፣ ባሳለፍነው ጥቅምት ወር የ3 ኤም ኩባንያ እና የዲስከቨሪ ትምህርት በፌርፋክስ ካውንቲ ቨርጂኒያ በሚገኘው በውድሰን ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ባዘጋጀው ውድድር ላይ እንዲሳተፍ ምክንያት ሆነው።

የ15 ዓመቱ የ10ኛ ክፍል ተማሪ የሆነው ሄማን የወጣት ሳይንቲስት ውድደሩንም አሸነፈ፤ የ25 ሺህ ዶላር ተሸላሚም ሆነ።

ሄማን ለዚህ ውጤት ያበቃው ሳሙናዎችን እና ኬሚካሎችን በማዋሐድ የቆዳ ካንሰር የሚከላከል ሳሙና ለመፍጠር ሙከራ በማድረጉ ነው።

እንዲህ ዓይነቱ ምርት ወደ ገበያ ለመምጣት ዓመታት ሊወስድ ቢችልም፣ ዛሬም በምርምር ላብራቶሪ ጊዜውን ሚያሳልፈው ታዳጊ አንድ ቀን የእኔ ሳሙና በሌሎች ሰዎች ሕይወት ላይ ቀጥተኛ ተጽዕኖ ሊያሳድር ይችላል ብሎ ያምናል።

ሄማን ለ2024 የታይም የዓመቱ ምርጥ ልጅ ተብሎ እውቅና እንዲያገኝ የረዳው ከራስ ወዳድነት ነፃ የሆነ የፈጠራ ስራው እንደሆነ ተነግሯል።

በ4 ዓመቱ ከቤተሰቦቹ ጋር ወደ አሜሪካ ከማቅናቱ በፊት አዲስ አበባ ውስጥ ኑሮውን አድርጎ የነበረው ሄማን፤ በጠራራማ ፀሐይ ውስጥ የሚሰሩ የጉልበት ሰራተኞችን በየመንገዱ ማየቱ ለቆዳ ካንሰር መድኀኒት ለመፍጠር ምክንያት እንደሆነው ያስታውሳል።

ወላጆቹ እሱን እና እህቶቹን ከቤት ውጭ ብዙ ጊዜ ያለፀሐይ መከላከያ መውጣት የሚያስከትለውን አደጋ ያስረዷቸው ስለነበረ ስለቆዳ ካንሰር ሊያውቅ ችሏል።

ሄማን በኢኮኖሚ ዝቅ ያሉ ሰዎች ከቆዳ ካንሰር እንዴት ነው እራሳቸውን ሚከላከሉት የሚል ጥያቄ በአዕምሮው ይመላለስ ነበር።

በጊዜው ለቆዳ ካንሰር ሕክምና የሚወጣው 40 ሺህ ዶላር የበለጠ ዋጋ ስለሆነ "ዓለም አቀፍ ተጽዕኖ ያለው አንድ ነገር ምንድን ነው፣ ሁሉም ሰው ሊጠቀምበት የሚችል ኢኮኖሚያዊ ጉዳት የሌለው" በማለት ሄማን ማሰቡን ቀጠለ።

“ሁሉም ሰው ማለት ይቻላል ለማፅዳት ሳሙና እና ውኃ ይጠቀማል።ስለዚህ ሳሙና በጣም ጥሩው አማራጭ ሊሆን ይችላል" በሚል ሳሙና ለመስራት ወሰነ።

ሄማን በቀለ ሳሙናውን በመስራት በባልቲሞር በሚገኘው የጆንስ ሆፕኪንስ ብሉምበርግ የህዝብ ጤና ትምህርት ቤት በአይጦች ላይ መሰረታዊ ምርምር ሲያካሂድ ቆይተዋል ።

አሁን ላይ እንስሳትን በተለያዩ የቆዳ ካንሰር መርፌዎች እና በሊፕይድ የታሰረውን ኢሚኪሞድ የተቀላቀለውን ሳሙና በመቀባት ውጤቱ ምን እንደሆነ ለማየት በዝግጅት ላይ ነው።

እሱን ለመፈተሽ እየተዘጋጀ ቢሆንም ሄማን ገና የሚቀረው ረጅም መንገድ እንዳለ ያውቃል፤ ሳሙናን መሞከር ብቻ ሳይሆን የፈጠራ ባለቤትነት እና የኤፍዲኤ የምስክር ወረቀት ማግኘት በአጠቃላይ አሥር ዓመት ሊወስድ ይችላል።

ቤተሰቦቹን በተለይም ወላጆቹን ለስኬቶቹ መንገድ ስለሆኑ ሁሌም የሚያመሰግናቸው ሄማን፤ መምህር የሆኑት እናቱ ሙሉእመቤት እና የአሜሪካ ዓለም አቀፍ ልማት ኤጀንሲ የሰው ሀብት ስፔሻሊስት የሆኑት አባቱ ወንድወሰን፣ለልጆቻቸው ጥሩ ትምህርትና ኑሮ ብዙ ዋጋ ከፍለዋል፤ የሚችሉትን አድርገዋል፤ ሊመሰገኑ ይገባል ብሏል።

"ብዙ ሰዎች ሁሉም ነገር ተከናውኗል አልቋል የሚል አስተሳሰብ አላቸው፤ ነገር ግን አሁን ሁሉም ነገር ገና ነው መስራቴን ቀጥላለሁ ዓለማችንን ለማሻሻል እና የተሻለ ቦታ ለማድረግ አዳዲስ መንገዶችን ማሰቤን አላቆምም" ሲልም ሄማን ለታይም መፅሔት ሀሳቡን አካፍሏል።

(Source: Ethiopian Broadcasting Corporate)
Forwarded from EECMY Youth Ministry
***የወጣቶች የወንጌል ስርጭት እንቅስቃሴ- በሻኪሶ
***Youth Evangelism Movement in EECMY-AGS- Shakiso
===
የኢት./ወ/ቤ/ክ/መካነ ኢየሱስ በአዶላ ገናሌ ሲኖዶስ: ከኦዶ ሻኪሶ ሰበካ ማ/ምዕመናናት የተወጣጡ ወጣቶች እና የወጣቶች አገልግሎት መሪዎች በሻኪሶ ከተማ የተሰጠውን ሁለንተናዊ የወጣቶች አገልግሎት ስልጠና ካጠናቀቁ በኋላ በሻኪሶ ከተማ በመዟዟር ለብዙዎች ወንጌልን መስክረዋል: በዚህም የወንጌል ምስክርነት አገልግሎት ብዙዎች ወንጌልን ሰምተዋል:: ስልጠናውን ሲሰጡ የነበሩት የኢ/ወ/ቤ/ክ/መካነ ኢየሱስ የልጆች እና ወጣቶች አገልግሎት መምሪያ ዳይሬክተር Wondmagegn Udessa Bidire ከወጣቶቹ ጋር በመሆን በወንጌል ምስክርነት አገልግሎት የተሳተፉ ሲሆን: በከተማው አደባባይም ስለ እግዚአብሔር ፍቅር እና የክርስቶስ አዳኝነት ላይ ትኩረት በማድረግ ወንጌል ሰብከዋል:: በቤተክርስቲያኒቱ አቅዳ እየሰራችበት ባለው መሰረት:
ይህ የወንጌል ስርጭት እንቅስቃሴ ተጠናክሮ የሚቀጥል ይሆናል::

''ሰዎች ሁሉ ሊድኑና እውነቱን ወደ ማወቅ ሊደርሱ በሚወድ በእግዚአብሔር በመድኃኒታችን ፊት መልካምና ደስ የሚያሰኝ ይህ ነው።''
1ጢሞቴዎስ 2:3-4
====
====
***Duula Dhuga Ba'umsa Wongeelaa Dargaggootaa, Shaakkisootti
===
WKWWMYI Sinoodoosii Adoolaa Gannaaleetti, dargaggootnii fi qindeessitootni tajaajila dargaggootaa sabakaa Oddoo Shaakkisoo irraa walitta qabamaniif, tajaajila hundagaleessa dargaggootaa magaalaa Shaakkisootti kennamaa ture erga xumuranii booda, magaalaa Shaakkisoo keessa naanna’uun wangeela labsaniiru, namoota hedduuttis Wongeela dhugaa bahaniiru. Leenjicha kennaa kan turan
Daarektarri Qajeelcha Tajaajila Ijoollee fi Dargaggootaa WKWWMYI Wondmagegn Udessa Bidire, dargaggoota waliin ta’uun tajaajila Wongeela dhugaa bahuu irratti hirmaataniiru, addabaabahii magaalaa Shaakkisoottis ergaa Jaalala Waaqayyoo fi Fayyisaa ta'uu Kiristoos irratti xiyyeeffate bu'uura godhachuun Wangeela lallabaniiru. Akkaataa karoora WKWWMYI karoorfattee irratti hojjachaa jirtuu, sochiin labsii Wangeelaa kun cimee kan itti fufu ta'a.
===========
===========

''Kun gaarii dha, fuula Waaqayyo fayyisaa keenya durattis fudhatamaa dha. Waaqayyo, namni hundinuu akka fayyu, dhugaa beekuu biras akka ga'u in fedha.'' 1Xim. 2:3-4

===
👉Youth Evangelism Movement in EECMY- AGS- Shakiso.

''This is good, and pleases God our Savior, who wants all people to be saved and to come to a knowledge of the truth.'' 1Tim. 2:3-4

#EECMY #Mission #Evangelism #Gospel #GreatCommission #Wangeela #ወንጌል
@eecmyyouthministry