EECMY Children Ministry: MY Sunday School
951 subscribers
1.33K photos
15 videos
186 links
MY Sunday School is the official page of EECMY Children Ministry.

Wholistic Growth For Our Children!

Access Sunday School learning materials at www.mysundayschool.org
Download Telegram
Forwarded from EECMY Youth Ministry
*የድንበር ዘለል አገልግሎት ሚስዮናዊ ምደባና የሽኝት መርሃግብር ተካሄደ *

የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን መካነ ኢየሱስ በውጪና በአገር ውስጥ የምስራቹን ይዘው የሚሄዱ ጥሪ ያላቸውን አገልጋዮችን በመመልመል፣ በማሰልጠን እያሰማራች ትገኛለች፡፡
በማዕከላዊ ደቡብ ኢትዮጵያ ሲኖዶስ ስር የምትገኘው የሐዋሳ ቤቴል ማኅበረ ምዕመናንም የድንበር ዘለል አገልግሎት ሚስዮናዊ ደበላ ቦቴን ከነቤተሰቡ ወደ ምስራቅ አፍሪካ ለመላክ የምደባና ሽኝት መርኃግብር አድርጋለች፡፡
በዕለቱም: ከቤተክርስቲያኒቱ ዋና ጽ/ቤት: ከዓለም አቀፍ ሚስዮን ማኅበር ቦርድ: የተለያዩ አብያተ ክርስቲያናት ተወካዮች እና መሪዎች እንዲሁም የሲኖዶስ መሪዎች እና የሐዋሳ ከተማ ማኅበረ ምእመናናት መሪዎች ተገኝተዋል:: በዕለቱም የቤተክርስቲያኒቱ ተባባሪ ጠቅላይ ፀሐፊና የዓለም አቀፍ ሚስዮን ማኅበር ቦርድ ሰብሳቢ ቄስ ፈቃዱ ቤኛ መልዕክት ያስተላለፉ ሲሆን የምደባና የሽኝት ሥነ ሥርዓቱ በሚስዮን ማኅበሩ ዳይሬክተር ቄስ ጥላዬ ከበደ መሪነት ተከናውኗል፡፡
በቀጣይም ይህን ታላቁን የወንጌል ተልዕኮ ከግብ ለማድረስ በፀሎት፣በገንዘብ በተለያዩ መንገዶች ድጋፍ እንዲደረግ ጥሪ ቀርቧል::
(Source: EECMY- International Mission Society)
***
''በወንጌልም ማኅበረተኛ እሆን ዘንድ ስለ ወንጌል ሁሉን አደርጋለሁ።'' 1ቆሮንቶስ 9:23

ስለ ሁሉ እግዚአብሔርን እያመሰገናችሁ
በጸሎት፣ በምክር ፣ በድጋፍ ከአለምአቀፍ የሚስዮን ማህበር አገልግሎት ጎን እንድትቆሙ በጌታ ፍቅር ጥሪ እናቀርባለን።

EECMY-IMS

1000008166432 CBE/ EECMY-IMS
2600280004746 BIRHAN BANK /EECMY-IMS
01320008596702AWASH/ EECMY-IMS

@eecmyyouthministry
*የታዳጊ ወጣቶች አውደ ርዕይ ተካሄደ*

በኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተክርስቲያን መካነ ኢየሱስ የመካኒሳ ማህበረ ምዕመናን በወጣቶች አገልግሎት ስር በሚገኘው የታዳጊ ወጣቶች የተዘጋጀ አውደ ርዕይ/ኤግዚቢሽን ተካሄደ::  የኤግዚቢሽኑ ዋና አላማ ታዳጊዎች ባለፈው አመት የተማሩትን ትምህርት በራሳቸው የፈጠራ መንገድ ለማሳየት ነው። በዚህ ዝግጅት ላይ ከ85 በላይ ታዳጊዎች በ5 የተለያዩ ቡድኖች የተሳተፉ ሲሆን: እያንዳንዱ ቡድን ስለ ፕሮጀክታቸው የፈጠራ ጥበብ ስራዎችን አሳይተው ለጎብኝወች ገለጻ አድርገዋል።
የቤተክርስቲያኒቱ የልጆች እና ወጣቶች አገልግሎት መምርያ ዳይሬክተር ወንድማገኝ ኡዴሳ በኤግዚቢሽኑ ተገኝተው ከጎበኙ በኋላ: የመካኒሳ ማ/ም ወጣት መሪዎችንም ስለ መልካም ስራቸው አበረታተው:  ስራቸው ለሌሎችም መልካም ምሳሌ መሆኑን ገልጸዋል::

#EECMY #Teenager #Ministry #Mekanisa #Congregation
https://t.me/MYSundaySchool
የታዳጊ ወጣቶች ስልጠና በሀዋሳ
====
"በሥጋችሁ እግዚአብሔርን አክብሩ " በሚል መሪ ቃል
በማዕከላዊ ደቡብ ኢ/ያ ሲኖዶስ  በልጆች አገልግሎት መምርያ የተዘጋጀ የታዳጊ ወጣቶች ስልጠና ከ ሐምሌ 1-5 - 2016 ዓ.ም ቀኑን ሙሉ ለተከታታይ አምስት ቀናት ዕድሜያቸው  ከ14-17 ዓመት ላሉ ታዳጊ  ወጣቶች በሀዋሳ ታቦር መካነ ኢየሱስ  ግቢ ውስጥ ተዘጋጅቷል። ወላጆች ልጆችን ምሳ በማስያዝ እንድትልኩ የልጆች መምርያ  ያሳስባችኃል: ሁላችሁም ተጋብዛችኃል ተባረኩ።

#EmpoweringGeneration #EECMY #SouthCentralEthiopiaSynod #ChildrenMinistry  #Teenagers #Hawassa
@MYSundaySchool
የኢ/ወ/ቤ/ክ/መካነ ኢየሱስ ካለንደር: ሐምሌ 2016 ዓ.ም

Kaalandarii WKWWMYI, Adoolessa 2016/2024

(Source: EECMY- Yemisrach Dimts Communication Service)

https://t.me/eecmyyouthministry
https://t.me/MYSundaySchool
የኢ/ወ/ቤ/ክ/መካነ ኢየሱስ ካለንደር: ነሐሴ 2016 ዓ.ም

Kaalandarii WKWWMYI, Hagayya 2016/2024

(Source: EECMY- Yemisrach Dimts Communication Service)

https://t.me/eecmyyouthministry
https://t.me/MYSundaySchool
ትውልደ ኢትዮጵያዊው ሄማን በቀለ በታይም መፅሔት የ2024 ምርጥ ልጅ ተባለ
*******

ትውልደ ኢትዮጵያዊው ሄማን በቀለ በታይም መፅሔት የ2024 ምርጥ ልጅ በመባል ተመርጧል።

አዲስ አበባ ኢትዮጵያ ተወልዶ አሜሪካ ነዋሪነቱን ያደረገው ሄማን በቀለ የቆዳ ካንሰር መከላከያ ሳሙና በመፍጠሩ ነው ለዓለም ህዝብ አሳቢ ልብ ያለው ልጅ ለመባል የበቃው።

ሄማን በቀለ ገና የ7 ዓመት ልጅ እያለ ነበር የራሱን የሳይንስ ሙከራዎችን በቤት ውስጥ ማካሄድ የጀመረው። ወላጆቹም ፍላጎቱን በማየት በቅርበት ይከታተሉት ነበር።

በዚህ የጀመረው የሳይንስና የምርምር ፍቅሩ፣ ባሳለፍነው ጥቅምት ወር የ3 ኤም ኩባንያ እና የዲስከቨሪ ትምህርት በፌርፋክስ ካውንቲ ቨርጂኒያ በሚገኘው በውድሰን ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ባዘጋጀው ውድድር ላይ እንዲሳተፍ ምክንያት ሆነው።

የ15 ዓመቱ የ10ኛ ክፍል ተማሪ የሆነው ሄማን የወጣት ሳይንቲስት ውድደሩንም አሸነፈ፤ የ25 ሺህ ዶላር ተሸላሚም ሆነ።

ሄማን ለዚህ ውጤት ያበቃው ሳሙናዎችን እና ኬሚካሎችን በማዋሐድ የቆዳ ካንሰር የሚከላከል ሳሙና ለመፍጠር ሙከራ በማድረጉ ነው።

እንዲህ ዓይነቱ ምርት ወደ ገበያ ለመምጣት ዓመታት ሊወስድ ቢችልም፣ ዛሬም በምርምር ላብራቶሪ ጊዜውን ሚያሳልፈው ታዳጊ አንድ ቀን የእኔ ሳሙና በሌሎች ሰዎች ሕይወት ላይ ቀጥተኛ ተጽዕኖ ሊያሳድር ይችላል ብሎ ያምናል።

ሄማን ለ2024 የታይም የዓመቱ ምርጥ ልጅ ተብሎ እውቅና እንዲያገኝ የረዳው ከራስ ወዳድነት ነፃ የሆነ የፈጠራ ስራው እንደሆነ ተነግሯል።

በ4 ዓመቱ ከቤተሰቦቹ ጋር ወደ አሜሪካ ከማቅናቱ በፊት አዲስ አበባ ውስጥ ኑሮውን አድርጎ የነበረው ሄማን፤ በጠራራማ ፀሐይ ውስጥ የሚሰሩ የጉልበት ሰራተኞችን በየመንገዱ ማየቱ ለቆዳ ካንሰር መድኀኒት ለመፍጠር ምክንያት እንደሆነው ያስታውሳል።

ወላጆቹ እሱን እና እህቶቹን ከቤት ውጭ ብዙ ጊዜ ያለፀሐይ መከላከያ መውጣት የሚያስከትለውን አደጋ ያስረዷቸው ስለነበረ ስለቆዳ ካንሰር ሊያውቅ ችሏል።

ሄማን በኢኮኖሚ ዝቅ ያሉ ሰዎች ከቆዳ ካንሰር እንዴት ነው እራሳቸውን ሚከላከሉት የሚል ጥያቄ በአዕምሮው ይመላለስ ነበር።

በጊዜው ለቆዳ ካንሰር ሕክምና የሚወጣው 40 ሺህ ዶላር የበለጠ ዋጋ ስለሆነ "ዓለም አቀፍ ተጽዕኖ ያለው አንድ ነገር ምንድን ነው፣ ሁሉም ሰው ሊጠቀምበት የሚችል ኢኮኖሚያዊ ጉዳት የሌለው" በማለት ሄማን ማሰቡን ቀጠለ።

“ሁሉም ሰው ማለት ይቻላል ለማፅዳት ሳሙና እና ውኃ ይጠቀማል።ስለዚህ ሳሙና በጣም ጥሩው አማራጭ ሊሆን ይችላል" በሚል ሳሙና ለመስራት ወሰነ።

ሄማን በቀለ ሳሙናውን በመስራት በባልቲሞር በሚገኘው የጆንስ ሆፕኪንስ ብሉምበርግ የህዝብ ጤና ትምህርት ቤት በአይጦች ላይ መሰረታዊ ምርምር ሲያካሂድ ቆይተዋል ።

አሁን ላይ እንስሳትን በተለያዩ የቆዳ ካንሰር መርፌዎች እና በሊፕይድ የታሰረውን ኢሚኪሞድ የተቀላቀለውን ሳሙና በመቀባት ውጤቱ ምን እንደሆነ ለማየት በዝግጅት ላይ ነው።

እሱን ለመፈተሽ እየተዘጋጀ ቢሆንም ሄማን ገና የሚቀረው ረጅም መንገድ እንዳለ ያውቃል፤ ሳሙናን መሞከር ብቻ ሳይሆን የፈጠራ ባለቤትነት እና የኤፍዲኤ የምስክር ወረቀት ማግኘት በአጠቃላይ አሥር ዓመት ሊወስድ ይችላል።

ቤተሰቦቹን በተለይም ወላጆቹን ለስኬቶቹ መንገድ ስለሆኑ ሁሌም የሚያመሰግናቸው ሄማን፤ መምህር የሆኑት እናቱ ሙሉእመቤት እና የአሜሪካ ዓለም አቀፍ ልማት ኤጀንሲ የሰው ሀብት ስፔሻሊስት የሆኑት አባቱ ወንድወሰን፣ለልጆቻቸው ጥሩ ትምህርትና ኑሮ ብዙ ዋጋ ከፍለዋል፤ የሚችሉትን አድርገዋል፤ ሊመሰገኑ ይገባል ብሏል።

"ብዙ ሰዎች ሁሉም ነገር ተከናውኗል አልቋል የሚል አስተሳሰብ አላቸው፤ ነገር ግን አሁን ሁሉም ነገር ገና ነው መስራቴን ቀጥላለሁ ዓለማችንን ለማሻሻል እና የተሻለ ቦታ ለማድረግ አዳዲስ መንገዶችን ማሰቤን አላቆምም" ሲልም ሄማን ለታይም መፅሔት ሀሳቡን አካፍሏል።

(Source: Ethiopian Broadcasting Corporate)