Malae Woreda Sencie and Information Technology
9 subscribers
5 photos
1 video
2 links
Sencie and Information Technology
Download Telegram
#የዳታ_መቆጣጠሪያ_አፕሊኬሽን_ልጠቁማችሁ

በሞባይል ስልካችን ኢንተርኔት ስንጠቀም የሚያሳስበን ዋናውና ትልቁ ነገር የዓየር ሰዓት(የሞባይል ካርድ) ወጪ ነው፡፡ የሞባይል ካርድ እየሞላን #ፌስቡክ#ዩቲዩብ#ኢንስተግራም#ቴሌግራም እና አንድ አንድ መረጃዎችን ብራውዝ እናደርጋለን፡፡

ነገር ግን ይበቀኛል ብለን የሞላነው የሞባይል ካርድ(በጥቅል መልኩም ይሁን በመደበኛ) ድንገት ሙልጭ ብሎ ያልቅና ያበሳጨናል፡፡

ለምንድን ነው የሞላነው ሞባይል ካርድ ቶሎ የሚያልቅብን?

1ኛ፡- የዓየር ሰዓትና የኢንተርኔት ጥቅል ዋጋ ውድ በመሆኑ፣

2ኛ፡- የኛ የአጠቃቀም ችግር፦

የመጀመሪያው ችግር አሁን ለግዜው ምንም ማድረግ አንችልም፡፡ ሁለተኛው ምክንያት ማለትም የኛ የአጠቃቀም ችግር ግን ማስተካከል ይቻላል፡፡

የአጠቃቀም ችግር ማለት ምን ማለት ነው?

ኢንተርኔት ስንጠቀም ቢያንስ 4 ዓይነት ኮንተንቶችን ብራውዝ እናደርጋለን፡፡ እነሱም:-

#ቪዲዮ#ፎቶ#ሙዚቃ(ድምፅ)፤#ፁሁፍ ሊሆኑ ይችላሉ፡፡እነዚህ ኮንተንቶች ዳታ አጠቃቀማቸው ይለያያል፡፡ ለምሳሌ:- #ቪዲዮና #ፎቶ እኩል ዳታ አይጠቀሙም፡፡

#ቪድዮ የበለጠ ዳታ ይጠቀማል፡፡ ስለዚህ #ቪዲዮ ውድ ነው ማለት ነው፡፡በተመሳሳይ መልኩ በኢንተርኔት #ሙዚቃ ከማዳመጥ እና የተለያዩ #ፁሆፎች ከማንበብ፤ሙዚቃ ማዳማጥ ይበልጥ ሞባይል ካርዳችንን ይበላል፡፡

ስለዚህ ኢንተርኔት ስንጠቀም የሞላነውን ካርድ የሚበሉብን ኮንተንቶች በቅደም ተከተል የሚከተለውን ይመስላሉ፡-

1ኛ፡- #ቪዲዮ
2ኛ፡- #ፎቶ
3ኛ፡- #ፁሁፎች

የሆነ ፁሁፍ ለማንበብ ብለን ሞባይል ካርድ ሞልተን ኢንተርኔት መጠቀም ስንጀምር ፁሁፉን ትተን ቪዲዮ ማየት ከጀመርን(ቪዲዮ ብዙ ይበላል) ካርዱ ሲያልቅ ያሰብነውን ስላላረግን ያበሳጨናል፡፡

ስለዚህ ማቀድ ያስፈልጋል፡፡ ከዚያም ያቀድነውን ማድረግ ያስፈለጋል ማለት ነው፡፡

ሞባይል ካርድ ሞልተን ኢንተርኔት ብራውዝ ስናደርግ ያቀድነውን ለማድረግ ዳታችንን መቆጣጠር ይኖርብናል፡፡ ዳታ መቆጣጠር ማለት ለምሳሌ 1Gb ኢንተርኔት ጥቅል ሞልታችሁ ከሆነ ኢንተርኔት መጠቀም ስትጀምሩ ለምሳሌ ፌስቡክ ብራውዝ አድርጋችሁ ስትጨርሱ ከ1Gb ውስጥ ምን ያህል ቀረኝ የሚለውን መቆጣጠር ማለት ነው፡፡

የሞላችሁት የኢንተርኔት ጥቀል ለመቆጣጠር “Internet Speed Meter Lite” የሚባል አፕሊኬሽን አለ፡፡ ነፃ ነው፡፡ አፕሊኬሽኑን ዳውንሎድ ታደርጉታላችሁ፡፡ ከዚያ ስታስነሱት ዳታችሁን ይቆጣጠርላችኋል ፡፡

ይህ አፕሊኬሽን ፡-

1ኛ፡-ምን ያህል ዳታ እንደተጠቀማችሁ ወይም እየተጠቀማችሁ መሆኑን ይነግራችኋል፣

2ኛ፡-የትኛው አፕሊኬሽን ብዙ ዳታ እየበላባችሁ እንደ ሆነ ይነግራችኋል፡፡..ወዘተ

ስለዚህ በዚህ ዓይነት መልኩ ዳታችሁን እየተቆጣጠራችሁ እና እየቆጠባችሁ በመጠቀም ቢያንስ የሞላችሁትን ሞባይል ካርድ ድንገት ሙልጭ ብሎ ከማለቅ ትድናላችሁ፡፡

የአፕሊኬሽኑ ሊንክ ይሄው፡-
https://play.google.com/store/apps/details?id=com.internet.speed.meter.li

#ሼር_ይደረግ
ምንጭ:- dotcomtvshow
┈┈┈┈••●◉❖◉
☞ እባክዎ! ያነበብነውን፣ የምናቀውን መረጃዎችን ለሌሎች እንዲደርስ በማድረግ መልካም ሀሳብን እናንሸራሽር። ለግዜው አፍልከሽኑን እስከ ምያገኙ ድረስ ከሞባይላች ላይ ያለውን ዳታ ሰቨሩን On ብደረግ ይመከራል።
የዓለማችንን መልክ የቀየሩት 20ዎቹ የምንግዜም ታላላቅ ኢኖቬሽኖች
========================
በሰው ልጆች ረዥም የህይወት ጉዞ ውስጥ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚና እንዲ በቀላሉ የሚገለፅ ጉዳይ አይደለም፡፡ ሰዎች ወደዚች ምድር ከመጡ አንስቶ አካላዊውን ዓለም ለመግራት የሚያስችሉ የተለያዩ ፈጠራዎችንና የኢኖቬሽን ውጤቶች ያለማቋረጥ ሲተገብሩ ቆይተዋል፡፡ እነዚህ መሳሪያዎች አለም አሁን ያላትን መልክ ያጎናፀፏት እና የቀጣዩንም ትውልድ እጣ ፋንታ በበጎም ይሁን በክፉ የመወሰን አቅማቸው በእጅጉ የተጠበቀ ነው፡፡ አለማችን እስካሁን ያየቻቸውን የኢኖቬሽን ውጤቶች ለሰው ልጆች ከሰጡት ግልጋሎት እና በታሪክ ውስጥ ካላቸው የገዘፈ ተጽዕኖ አንፃር የሚከተሉት ኢኖቬሽኖች ከምንግዜም ታላላቆቹ መካከል ይገኙበታል፡፡ በዘመን ቅደም ተከተል እንመልከታቸው፡

1. እሳት (FIRE) - ስለእሳት ስናነሳ ብዙዎች የሚከራከሩበት ጉዳይ ቢኖር እሳት ተፈለሰፈ ከሚባል ይልቅ ተገኝቷል የሚለው ሃሳብ እጅግ ተስማሚ መሆኑን ነው፡፡ ቀደምት የሰው ዘሮች እሳትን እንዴት መፍጠር እና መቆጣጠር እንደሚችሉ ከማወቃቸው በፊት የእሳትን አደጋዎች በየአጋጣሚው ተመልክተው ሊሆን ይችላል፡፡ ነገር ግን የእሳትን ምንነት ከተረዱና የሚሰጣቸውን ጥቅም ካወቁ በኋላ እሳትን እንደ አንድ ትልቅ መገልገያ መጠቀም ጀምረዋል፡፡ አንዳንድ የአርኪዎሎጂ አጥኝዎች እሳት ጥቅም ላይ የዋለው ከ2 ሚሊዮን አመት በፊት ነው ሲሉ ሌሎች ደግሞ 125 ሺ አመታት እንዳስቆጠረ ይገልፃሉ፡፡ ይህ ክርክር ምንም ተባለ ምንም በሰው ልጆች ታሪክ ታላቅ ግኝት የሆነው እሳት ሰዎች ራሳቸውን ከተለያዩ ነገሮች እንዲከላከሉ እና ማብሰል የሚባለውን ትልቅ ክህሎት እንዲረዱ ያስቻል አስገራሚ ግኝት ነው፡፡

2. ተሽከርካሪ ጎማ (WHEEL) - ይህ ፈጠራ የተገኘው በ3500 ዓመተ ዓለም (B.C) በሜሶፖታሚያ የስልጣኔ ዘመን ነበር፡፡ የሜሶፖታሚያ ህዝቦች ይህንን አስገራሚ ፈጠራ የሸክላ ቁሳቁሶችን ለማበጃጀት ሲጠቀሙበት የቆየ ቢሆንም ከሶስትና አራት መቶ አመታት በኋላ ፈጠራው ለሰረገላ ማሽከርከሪያ ጥቅም ላይ ከዋለ በኋላ የመሳሪያው ተፅዕኖ እጅግ እየናኘ ሄዷል፡፡ ተሽከርካሪ ጎማ ለሰው ልጆች የመጓጓዣ እና የንድግ ስርዓት መፈጠር ትልቅ ሚና ያለው ግኝት ነው፡፡

3. ኦፕቲካል ሌንሶች (OPTICAL LENSES) - የሰዎችን የእይታ አቅም ይበልጥ ለመጨመር እንደ ኦፕቲካል ሌንሶች ያሉ አስገራሚ ግኝቶች እጅግ ወሳኝ ነበሩ፡፡ ረዥም የፈጠራ ሂደት የነበራቸው እነዚህ ግኝቶች በጥንቱ የግብፅ እና የሜሶፖታሚያ የስልጣኔ ዘመን እንደበለፀጉ የሚታመን ሲሆን ከግሪክ የተገኙት የብርሃን ንድፈ ሃሳቦች ደግሞ ለግኝቱ እውን መሆን ትልቅ ሚና ነበራቸው፡፡ ኦፕቲካል ሌንሶች እንደቴሊቭዥን፣ ፎቶግራፍ እና ፊልም ያሉ ትልልቅ የሚዲያ ቴክኖሎጂዎች እንዲፈጠሩ መንገድ የጠረጉም ናቸው፡፡

4. ኮምፓስ (COMPASS) - ይህ እንቅስቃሴን ለመምራት የተዘየደው የቴክኖሎጂ ግኝት የሰው ልጆችን የአሰሳ ጥበብና አቅም ወደ አዲስ ምዕራፍ በመወሰድ ተተኪ የማይገኝለት አስገራሚ ግኝት ነው፡፡ የመጀሪያዎቹ ኮምፓሶች በተፈጥሮ የመግነጢሳዊ ይዘት ባላቸው የማዕድን ቁራጮች ወይም (lodestone) አማካኝነት የተሰሩ ሲሆን፤ ከክርስቶስ ልደት በፊት በ 300 እና 200 አመተ አለም አካባቢ በቻይና እንደተሰሩም ይነገራል፡፡

5. ወረቀት (PAPER) - በ100 ዓመተ አለም አካባቢ በቻይና የተፈለሰፈው ይህ ግኘት የሰው ልጆችን የፅህፈት እና ሃሳብን የማጋራት ልምድ በእጅጉ የቀየረ እንደሆነ ይነገርለታል፡፡ ከዚህ ጊዜ በፊት በግብፅ እና በሜክሲኮ የስልጣኔ ዘመናት የተፈለሰፉት እንደ ፓፒረስና አሜት ያሉ የመፃፊያ ቁሶች ለወረቅት መፈጠር አስተዋፅዖ ቢኖራቸውም በቻይና የነበረው ግኝት ግን አሁን ላለው የወረቀት ቴክሎጂ ትልቅ መሰረት የጣለ ነው፡፡
6. ባሩድ (GUNPOWDER) - ከተለያዩ የኬሚካል ንጥረ ነገሮች ተቀይጦ የሚሰራው ይህ ተቀጣጣይ ፈንጂ በ9ኛው ክፍለ ዘመን በቻይና እንደተፈለሰፈ የሚነገር ሲሆን ለዘመናዊው የጦር ቴክኖሎጂ መስፋፋትም ፈር ቀዳጅ የሚባል ነው፡፡ ይህ ግኘት በሰው ልጆች የውጊያ ታሪክ ውስጥ ትልቅ ተፅዕኖ ያሳደረ መሆኑም ይነገርለታል፡፡

7. ማተሚያ (PRINTING PRESS) - እንደአውሮፓውያኑ በ1439 በጀርመናዊው ዮሃንስ ጉተንበርግ የተፈጠረው ይህ መሳሪያ ለሰው ልጆች የአዲስ ህይወት መጀመሪያ ዘመን ተደርጎ በብዙዎች ይወሰዳል፡፡ ይህ አስገራሚ ቴክኖሎጂ በሰዎች እጅ እየተፃፈ የሚሰራጨውን አድካሚ የፅህፈት ስርዓት በሜካናይዝድ ማሽን በመተካት የእውቀት አድማስ በሰዎች ዘንድ በቀላሉ እንዲሰፋፋ እና የሃይማኖት አስተምህሮዎች በአለም ላይ በፍጥነት እንዲናኙ ያስቻለ አስገራሚ ግኘት ነው፡፡

8. ኤሌክትሪክ (ELECTRICITY) - የኤሌክትሪክ ፈጠራ ብዙ ብሩህ አዕምሮዎች ለሺህና ከዚያ በላይ አመታት አስተዋፅዖ ያደረጉበት እፁብ ድንቅ የሆነ የቴክኖሎጂ ግኝት ነው፡፡ በ18ኛው ክፍለ ዘመን የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ቤንጃሚን ፍራንክሊን ስለኤሌክትሪክ የነበረውን የአለም መረዳት አንድ እርምጃ ያራመደ የመሪነት አበርክቶት እንደነበረው የሚገለፅ ሲሆን በምርምር ዘርፍ ደረጃ ለመስኩ የሰጠው ሁለንተናዊ ትኩረት የቴክኖሎጂውን እድገት በእጅጉ አፋጥኖታል፡፡ ከዚህ ሂደት በማስከተል በ1879 የቶማስ ኤዲሰን የብርሃን አምፖል መፈጠር የኤሌክትሪክ ቴክኖሎጂ ይበልጥ ወደሰዎች እንዲቀርብ ያስቻለ ክስተት ነው፡፡ ይህ የምንግዜም ታላቅ ፈጠራ የሰው ልጆችን የህይወት መንገድ እስከወዲያኘው የቀየረ ግሩም ቴክኖሎጂ ነው፡፡

9. የእንፋሎት ሞተር (STEAM ENGINE) - በስኮትላንዳዊው የፈጠራ ባለሙያ ጀምስ ዋት ከ1763 እስከ 1775 ተሰራ የሚባለው የእንፋሎት ሞተር ሌላኛው ለሰው ልጆች ትልቅ መሰረት የጣለ አስደናቂ የፈጠራ ውጤት ነው፡፡ ይህ የቴክኖሎጂ ግኝት በጊዜው ለነበሩት ባቡሮች፣ መርከቦች እና በጠቅላለው ለኢንዱስትሪው አብዮት ዋና የሃይል ምንጭ በመሆን ተከትሎ ለመጣው የሰው ልጅ አብርሆት ታላቅ ውለታ ያደረገ አስገራሚ ፈጠራ ነው፡፡

10. የነዳጅ ሞተር (INTERNAL COMBUSTION ENGINE) - በ19ኛው ክፍለዘመን የተዋወቀው ይህ የቴክኖሎጂ ፈጠራ በመጀመሪያ በቤልጄሚያዊው ኢንጅነር ኢትየን ሌኖየር (በ1859) የተፈጠረ ሲሆን ከጥቂት አመታት በኋላ በጀርመናዊው ኒኮላስ ኦቶ ይበልጥ ሊሻሻል ችሏል፡፡ ይህ አስገራሚ ፈጠራ የኬሚካል ኢነርጂን ወደ ሜካኒካል ኢነርጂ በመቀየር ቀድሞ የእንፋሎት ሞተር ሲሰጥ ግልጋሎት በተሻለ ሁኔታ በመተካት ለዘመናዊ መኪናዎችና አውሮፕላኖች ማገልገል የቻለ አስገራሚ ፈጠራ ነው፡፡

11. ስልክ (TELEPHONE) - የስኮትላንድ ተወላጁ አሌግዛንደር ግርሃም ቤል በሰው ልጆች የመገናኛ ጥበብ ውስጥ ትልቅ አብዮት የፈጠረውን የስልክ ቴክኖሎጂ በራሱ ስም ያስመዘገበ ታላቅ የፈጠራ ባለሙያ ቢሆንም ከሱ ቀደምና እሱ በነበረበት ዘመንም ብዙ የፈጠራ ባለሙያዎች ለቴክኖለጂው ማበብ የራሳቸውን አሻራ ጥለዋል፡፡ አሌግዛንደር ግርሃም ቤል አንደአውሮፓውያኑ በ1876 በኤሌክተሪክ ስልክ የመጀመሪያውን ፓትንት ካገኘ በኋላ የሰው ልጆች እርስ በእርስ የመገናኘት ልምድ እስወዲያኛው ተቀይሯል፡፡

12. ክትባት (VACCINATION) - የክትባት ግኘት ለአንዳንዶች አከራካሪ ፈጠራ ቢሆንም ብዙዎች እንደሚገልፁት ከሆነ ግን በአለም ላይ የተከሰቱ በሽታዎችን በማጥፋት ነው።
የኮምፒዩተር እና ሞባይል ስልክ ላይ የሚጫኑ ጌምዎች እና ቴሌቪዥን የልጆችን የአእምሮ ዕድገት እያቀጨጩ ነው ሲሉ ተመራማሪዎች አስጠነቀቁ።

"በልጆቻችን ላይ እየፈጸምነው ያለው ግፍ ይቅር የማይባል ነው" ይላሉ ሚሸል ደስመርጌት። እኚህ ሰው ፈረንሳዊ ሳይንቲስት ናቸው። ከሰሞኑ ዓለምን እያነጋገሩ ነው።
"በዚህ ዘመን የሚወለዱ ልጆችን ድንዙዝ እያደረግናቸው ነው፤ ይህም የሚሆነው ብዙ ጌሞችን፣ ብዙ የስክሪን ሰዓቶችን ስለፈቀድልናቸው ነው፤ ሳናውቀው ስንፍናን እያወረስናቸው ነው" ይላሉ።

ፕሮፌሰር ሚሸል የኒውሮሳይንስ ሊቅ ናቸው። ዘለግ ላሉ ዓመታት በጉዳዩ ዙርያ ጥናት አድርገው የደረሱበት ሐቅ አንድ ነው። ይህም በዲጂታል ዘመን የተወለዱ ልጆች የአእምሮ ምጥቀት ልኬታቸው (IQ) በሚያስደነግጥ ሁኔታ እያሽቆለቆለ መሆኑን።

ብዙ ወላጆች በተቃራኒው ያስባሉ። ለልጆቻቸው ጌምና ስልክ በገፍ ያቀርቡላቸዋል።

ልጆቻቸው ስልክ ነካክተው በራሳቸው መክፈታቸው የአእምሮ እድገት ልቀት መስሎ ይታያቸዋል።

"ልጄን እኮ…" ብለው ማዳነቅ የሚወዱ ወላጆች ብዙ ናቸው።

ልጆቻቸው ፊልም ተመልከተው መሳቃቸው በራሱ የብልህነታቸው ማሳያ ያደርጉታል።

በመላው ዓለም ልጆች ረዥም ሰዓት በዲጂታል ዓለም ውስጥ ቀልባቸው ይሰወራል። ይህ እንዲሆን የፈቀደው ትውልድ በልጆቹ ላይ ይቅር የማይባል ግፍ ነው እየፈጸመ ያለው ይላሉ ፕሮፌሰር ሚሸል።

የዲጂታል ቁሶች (ስልክ፣ ጌም፣ ቴሌቪዥንና የመሳሰሉት) የልጆችን የአእምሮ ዕድገት እያቀጨጩ ነው ባይ ናቸው ፕሮፌሰሩ።

አሁን የእሳቸው ሐሳብ በሳይንስ ማኅበረሰቡ ዘንድ ከፍተኛ ክርክር ቀስቅሷል።
Forwarded from Tgg
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
በጂንካ የሳኢቴ መምሪያ እና የጂንካ ዩኒቨርሲቲ በቅንጅት ያዘጋጁት የፈጠራ ስራ ኤግዥቢሽን ፕሮግራም
"ዴልታ" የተሰኘው የኮቪድ ዝርያ ኢትዮጵያ ውስጥ ተገኘ።

አደገኛው የኮቪድ ዴልታ ዝርያ ኢትዮጵያ ውስጥ መገኘቱን የጤና ሚኒስቴር ይፋ አደረገ።

የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ በሰጡት መግለጫ “በኢትዮጵያ ባለፉት ሳምንታት በወረርሽኙ የሚያዙ ሰዎች፣ የሚሞቱና ፅኑ ህሙማን ቁጥር በጣም አሻቅቧል” ብለዋል።

አዲሱ ዝርያ ሁሉንም የዕድሜ ክልል የሚያጠቃ፣ ለከባድ ህመምና ሞት የሚዳርግ በተለይም ባልተከተቡ ሰዎች ላይ የሚበረታ ዝርያ መሆኑን ገልፀዋል።

ክትባት በየጤና ተቋማቱ በመገኘት እንዲወስዱ፣ የኮቪድ ፕሮቶኮልን ከሁሉም ተቋማትና ግለሰቦች እንደሚጠበቅም አሳስበዋል።

በኢትዮጵያ ባለፈው ሳምንት ብቻ 8 ሺህ 300 ሰዎች በወረርሽኙ ተይዘዋል።

እስካሁን በአገሪቱ 313 ሺህ ሰዎች በበሽታው ተይዘዋል። ከ4 ሺህ 700 በላይ ሰዎች ደግሞ በወረርሽኙ ሳቢያ ሕይወታቸው አልፏል።

በኮቪድ ወረርሽኝ የመያዝ ምጣኔውም ከ1 በመቶ ወደ 20 በመቶ አሻቅቧል ፤ ባለፈው ሳምንት 118 ሰዎች ሞተዋል። #ENA

@tikvahethiopia
Forwarded from Tgg
በፈጣን ኢንተርኔት ዘገምተኛ አገልግሎት
*************************************
በኢንተርኔት ተጠቃሚዎች ዘንድ በአሰልቺነታቸው ከሚታወቁ ችግሮች መካከል አንደኛው ከፍተኛ የሆነ ፍጥነት ያለው የበይነ መረብ አገልግሎት እየተጠቀምን እንኳን በተግባር ያለው ፍጥነቱ በጣም ዘገምተኛ መሆን ነው፡፡ ለምሳሌ በአውስትራሊያ ካሉ 8.2 ሚሊዮን የመኖሪያና የንግድ ቤቶች ባሳለፍነው ነሀሴ 2021 የተሰበሰበ መረጃ እንደሚያመለክተው 77 በመቶ የሚሆኑ ተጠቃሚዎች በገመድ የሚተላለፍን የበይነ መረብ አገልግሎት የሚጠቀሙ ሲሆን ይህም በሴኮንድ 50 ሜጋ ባይት ማስጠቀም የሚያስችል ነው፡፡

ይህም በቤት ውስጥም ሆነ በስራ ቦታ የተለያዩ ከፍተኛ የኢንተርኔት ፍጥነት የሚፈልጉ አገልግሎቶችን ለማግኘት በቂ እንደሆነ ይታወቃል፡፡ ለምሳሌ አንድ ሰው ኔትፍሊክስን ለመከታተል 12 ሜጋ ባይት የሚደርስ ፍጥነት ያስፈልገዋል፡፡ ለቪዲዮ ኮንፍረንስ ደግሞ ከ2-3 ሜጋ ባይት በሴኮንድ ሲያስፈልገው ለተለያዩ ጌሞች ከ1 ሜጋ ባይት ያነሰ ፍጥነት ያስፈልገዋል፡፡

ይሁን እንጂ 50 ሜጋ ባይት ፍጥነት ያለውን የበይነ መረብ አገልግሎት የሚጠቀም ሰው የቪዲዮዎች መቆራረጥ፣ የምስሎች በፍጥነት አለመክፈት እና መረጃዎችን በፍጥነት የማስተላለፍ ችግር ይገጥመዋል፡፡ ይህ ችግር ማለትም ፈጣን ኢንተርኔት እያለ እንኳን የሚከሰት መቆራረጥ መሰረታዊ ችግሩ የሚመነጨው ከኢንተርኔት ፍጥነት ሳይሆን ከፍጥነት ጋር ከማይያያዙ latency እና loss ከተባሉ ችግሮች ነው፡፡

ሌተንሲ ወይም አንድ መረጃ ከመረጃ ቋት ወደ መገልገያ ቦታችን ለመድረስ የሚጨርስበት ጊዜ የሚመለከት ሲሆን አነስተኛ እና በአመዛኙ ተመጣጠኝ ወይም ወጥ የሆነ እንዲሆን በማድረግ ችግሩን መቅረፍ ይቻላል፡፡ ሁለተኛው ደግሞ ከመረጃ ቋት ወደ ቤታችን ወይም ወደ መገልገያ ኮምፒውተራችን ወይም ስልካችን መረጃ ሲተላለፍ በጉዞ ሂደት የመጥፋት (loss) ወይም መንገድ ላይ የመቅረት ችግር ነው፡፡

ከላይ በተጠቀሰው ቦታ የተሰራው ጥናት እንደሚያመለክተው ሰዎች ለአገልግሎት ከከፈሉት የኢንተርኔት ፍጥነት ውስጥ በብዛት የሚጠቀሙት ከ6 በመቶ የማይበልጠውን ነው፡፡ ከዚህ በተቃራኒው ደግሞ በኦንላን ያለን ቆይታ ካለፈው አመት በ59 በመቶ መጨመሩ ተነግሯል፡፡

ምንጭ techxplore
ተጨማሪ ንባብ https://techxplore.com/news/2021-09-internet-jumpy-high.html
ቴሌግራም ለሳይበር ወንጀለኞች ምቹ እየሆነ መምጣቱን ጥናት አመለከተ፡፡

የመልዕክት መላላኪያ መተግበሪያው ቴሌግራም ለሳይበር ወንጀለኞች እንቅስቃሴ ምቹ እየሆነ መምጣቱ ተገለፀ፡፡

የሳይበር ደህንነት ተቋም የሆነው ሳይበርኢንት እና ፋይናንሺያል ታይምስ በጋራ ባደረጉት ጥናት መተግበሪያው የተመዘበሩ መረጃዎች እና ለጠለፋ (hack) የሚውሉ መጠቀሚያዎችን ለመሸጥና ለመግዛት በሳይበር ወንጀለኞች ዘንድ በከፍተኛ ደረጃ ተመራጭ እየሆነ መምጣቱ ተመላክቷል፡፡

ከዚህ ቀደም ወንጀለኞቹ ለመሰል ተግባራት ዳርክ ዌብ የተባለውን ምስጢራዊ የበይነ መረብ ሥርዓት ይጠቀሙ እንደነበር ፋይናንሺያል ታይምስ ያወጣው ሀተታ ያመላክታል፡፡

ቴሌግራም ለአጠቃቀም ቀላል እና የሚደረግበት ቁጥጥር መላላት ወንጀለኞቹ ወደ መተግበሪያው ፊታቸውን ለማዞራቸው በምክንያትነት ተቀምጧል፡፡

በመቶ ሺዎች የሚጠጉ የተለያዩ ግለሰቦች መጠቀሚያ ኢሜይሎች እና የምስጢር ቁልፎች ወንጀለኞቹ በሚጠቀሙባቸው የመተግበሪያው ቻናሎች እና የቡድን መጠቀሚያዎች (group) ውስጥ ለሽያጭ ሲተዋወቁ መታዘቡን ዘገባው አመላክቷል፡፡

ለክፍያ አገልግሎት የሚውል ካርድ እና የግለሰቦች የባንክ መረጃ እንዲሁም የፓስፖርት ቅጂዎች በመተግበሪያው መጠቀሚዎች ለሽያጭ ከሚቀርቡት መካከል መሆናቸው ተጠቁሟል፡፡ ከነዚህ በተጨማሪም የሰዎችን መረጃ ለመበርበር የሚያገለግሉ ሶፍትዌሮች እና መመሪያዎች በወንጀለኞቹ እንደሚቀርቡ ጥናቱ ታዝቧል፡፡