MS (Multiple Sclerosis) in Ethiopia
194 subscribers
56 photos
8 videos
5 files
19 links
MS is an autoimune ......
Download Telegram
አቡበከር ቃሲም እባላለሁ፣ ከ MS ህመም ጋር ከ 6 አመት በላይ
ኖሬያለሁ፣በበሽታው ምክንያት በ አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የ 3 ኛ
አመት ኤሌክትሪካል ኢንጅነሪንግ ትምህርቴን ማቋረጥን ተገድጃለሁ፤
በሽታው በአፍሪካና በምድር ወገብ ዙሪያ በሚገኙ ሀገራት ላይ
የመከሰቱ እድል አናሳ ነው፤በሽታው ከተከሰተ እንደ አውሮፓዊያን
አቆጣጠር 1868 ጀምሮ በባለሙያዎች ብዙ ጥረት ቢደረግም ፍቱን
መድሀኒቱ አልተገኘለትም ፤ነገርግን ለበሽታው ህክምና የሚውሉ
መድሀኒቶች ይሰጣሉ፤ እኔ እና የማህበሩ አባላት ረጅም ግዜ
ቢፈጅብንም እስከ 38 የሚደርሱ MS ህሙማንን ማግኘት ችለናል ፤
እንዲሁም"የ መልቲፕል ስክሎሮሲስ ህሙማን መርጃ በጎ አድራጎት
ማህበር"ን መስርተናል፤ ከመሰረትንበትም አላማዎች ውሰጥ እነዚህ
ይጠቀሳሉ:―
―ከጤና ባለሙያዎች ጋር በመተባበር ስለ በሽታው ግንዛቤን ማስፋት
፤
―ለ MS ተጠቂዎች የአቅምና የስነ ልቦና ድጋፍ ማድረግ፤
―ከባለሙያዎች ጋር በመተባበር ስለ MS የቆመ የ ፊዝዮቴራፒ
ማዕከልን መክፈት፤እንዲሁም
―ለ MS ህሙማን የህክምና ድጋፍ ማድረግ፤ይገኙበታል።
ነገርግን ለህክምና የሚውሉ መድሀኒቶች ሀገራችን ውስጥ አለመኖሩ
እና ከሌላም ሀገር ለማስመጣት ዋጋቸው ውድ በመሆኑ እኔ እና
ማህበራችን ውስጥ የምንገኝ አባላት በበቂ ሁኔታ ህክምናውን
መከታተል አልቻልንም፣ከህክምናው በተጨማሪ አሰፈላጊ በሆኑ
ጉዳዮች ላይ ትብብራችሁን በትህትና እንጠይቃለን።
://www.facebook.com/MSiEth/
Forwarded from Abubeker Kasim
https://www.focusonability.com.au/FOA/films/2526.html
እባካችሁ ሰዎች በዚህ ሊንክ ገብታችሁ ቮት አርጉኝ የናንተ ድምፅ ለእኔ ትልቅ ሽልማት ያስገኝልኛል ውድድሩ አለም አቀፍ ነው
👍2
Multiple Sclerosis(MS):-

MS ማለት በ central nervous system (የ አንጎል እና የጀርባ አጥንት ቁርኝት) የሚከሰት የበሽታ አይነት ነው። "central nervous system" myelin sheath በተባለ የ ፕሮቲን ውህድ የተሸፈነ ነው (እንደ ኤሌክትሪክ ገመድ)።
   
Multiple Sclerosis (MS), Auto immune disease ሲሆን  ይህ ማለት,የበሽታ ተከላካይ ሀይላችን የራሱን፣ንፁሁን የሰውነታችንን አካል ሲያጠቁ የሚከሰት በሸታ ነው።

በዚህ መልኩ ከአንጎላችን ወደ አካላችን የሚተላለፉ መልእክቶች በአግባቡ አለመድረስ ወይም ሙሉ ለሙሉ  አለመድረስን ያስከትላል።

   የ MS መንስኤ በግልፅ ባይታወቅም የተለያዩ የህክምና ባለሙያዎች ግምታቸውን
_ በዘር
_vit d እጥረት.....ያስቀምጣሉ።

ዋና ዋና የ MS ምልክቶች ውስጥ
_ድካም
_የእይታ ችግር( አንዳንዴም እይታን እስከማጣት ድረስ)
_ የባላንስ ማጣት
_ የመደንዘዝ ስሜት
_ የሰውነት ቅንጅትን ማጣት ...
You can join me by these channels
ዩቱዩብ፦ https://www.youtube.com/channel/UCT4Q0W2JlZBbh75P2Dfa4GA?sub_confirmation=1
ቴሌግራም: - https://t.me/MSiETh
ፌስቡክ:- https://www.facebook.com/profile.php?id=100088483377456
👍3