Forwarded from Amhara Prosperity Party/APP2
ድጎማን በተመለከተ
👉60 ቢሊዮን ብር ለሴፍትኔት
👉84 ቢሊዮን ብር ለማዳበሪያ
👉140 ቢሊዮን ብር ለነዳጅ
👉160 ቢሊዮን ብር ለደምዝ
በድምሩ 440 ቢሊዮን ብር መንግስት ድጎማ አድርጓል።
#amharaprosperityparty

የፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት ላይ የተቀመጡ ዋነኞቹ ጉዳዮች ምንድን ናቸው:-
👉ህወሃት ያካሄደው ምርጫ ህጋዊ ምርጫ ባለመሆኑ መሰረዝ
👉በትግራይ ክልል ህጋዊ ባለሆነ ምርጫ የተቋቋመው የክልሉ አስተዳደርና ምክር ቤት እንዲፈርስ
👉ከሁሉም ወገን የተወጣጣ ጊዜያዊ አስተዳደር ማቋቋም
👉 በህዝብ የተመረጠውን የፌደራል መንግስት ስርዓት ማክበር
👉በክልሉ ታጥቀው ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ሃይሎች ትጥቅ መፍታትና በተሃድሶ ወደ መደበኛ ህይወታቸው መመለስ
👉የተቋረጡ አገልግሎቶችን ወደ ስራ ማስመለስ
👉ከቀያቸው የተፈናቀሉ ዜጎችን መመለስ
👉 የትኛውም የውጭ ግንኙነት የማከናወን ስልጣን ያለው የፌደራል መንግስቱ ብቻ መሆኑን ማክበር የሚሉት ናቸው።

❤1
Forwarded from Amhara Prosperity Party/APP2
ቀይ ባህርን በተመለከተ
የቀይ ባህር ጉዳይ ህጋዊ፣ ታሪካዊ፣ መልከዓ ምድራዊና ኢኮኖሚያዊ ጥያቄ ነው ብለን እናምናለን። ይህንን በተረጋጋ መንገድ ማየት ያስፈልጋል። ኢትዮጵያን የቀይ ባህር የማጣት ውሳኔ ማን ወሰነ ብለን ስንፈልግ ተቋማት አልገቡበትም። ይህን የሚያህል የህልውና ጉዳይ ማን እንደወሰነ መጠየቅ ተገቢ ነው። ኢትዮጵያ ተዘግቶባት መኖር አትችልም። ለጎረቤቶቻችን መናገር የምንፈልገው ኢትዮጵያ ስታደግ ለቀጣናውም ልማት ምንጭ ትሆናለች። የምንፈልገው በትብብር ማደግ ነው።

❤2
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስትና በአማራ ፋኖ ሕዝባዊ ድርጅት መካከል የዘላቂ ሰላም ስምምነት ተፈረመ
***
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት እና በአማራ ፋኖ ሕዝባዊ ድርጅት (አፋሕድ) መካከል የዘላቂ ሰላም ስምምነት ተፈርሟል፡፡
ስምምነቱን የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አረጋ ከበደ እና የአማራ ፋኖ ሕዝባዊ ድርጅትን (አፋሕድ) በመወከል ካፒቴን ማስረሻ ሰጤ ተፈራርመዋል።
ውይይቱ እና ድርድሩ በአፍሪካ ሕብረት እና በኢጋድ አደራዳሪነት ሲካሄድ ነው የቆየው።
ርዕሰ መስተዳድሩ አረጋ ከበደ በአስተላለፉት መልዕክት፣ ዛሬ ለክልላችን ሕዝብ የመጀመሪያው ትልቅ የሰላም ኩነት የተካሄደበት ቀን ነው ብለዋል።
ከግጭት አሸናፊም ተሸናፊም የለም፣ ከሰላም ሁሉም ያተርፋል፣ ስምምነቱ ለሰላም ወዳድ ሕዝባችን ትልቅ እፎይታን ይሰጣል ነው ያሉት፡፡
የሕዝብና የመንግስትን ጥሪ ተቀብለው ዘላቂ ሰላም ለማስፈን ለመጡ ወንድሞቻችን እንደ መንግስት አድናቆትና ክብር አለኝ ብለዋል፡፡
የአማራ ፋኖ ሕዝባዊ ድርጅትን (አፋሕድ) በመወከል ስምምነቱን የተፈራረሙት ካፒቴን ማስረሻ ሰጤ በበኩላቸው፣ ማንኛውም ግጭት በመጨረሻ የሚፈታው በውይይትና በድርድር ነው ብለዋል።
ችግሮችና የሀሳብ ልዩነትን በንግግር መፍታት ፖለቲካዊ ሽንፈት ሳይሆን ጥበብና ብልጠት መሆኑን ገልጸው፣ ችግሮችን ለመፍታት ከኢትዮጵያ ታሪካዊ ጠላቶች ጋር ማበር ተገቢ አለመሆኑን አስገንዝበዋል፡፡
የአፍሪካ ሕብረት ኮሚሽን ምክትል ሊቀመንበር አምባሳደር ሰልማ ማሊካ አዳዲ በበኩላቸው፣ ስምምነቱ የሀገሪቱን ቀጣይ መዳረሻ የሚያቃና ነው ብለዋል።
በወንደሰን አፈወርቅ

❤7
እስከመቼ ነው ?
በወቅቱ ጎንደር ከተማ እኖር ነበር። በወርሐ ጥር 2018 ዓ.ም ወደ ባሕር ዳር የሚያስሄድ አንድ ጠንካራ ማኅበራዊ ጉዳይ ገጥሞኛል። ነገር ግን የመንገዱ ጉዳይ ዳገት ኾኖብኛል። በአውሮፕላን መጓዝን እንደ አማራጭ ለመጠቀም ባስብም ከጎንደር ባሕር ዳር በቀኑ በረራ አይደረግም። በአዲስ አበባ ዞሮ ለመሄድ ደግሞ የሚቻል አልኾነም። በዚህ መካከል የምሄድበት ማኅበራዊ ጉዳይ ሊያልፈኝ ኾነ።
አሁን በየብስ ትራንስፖርት መጓዝ ግዴታ ኾነብኝ። በአማራ ክልል ግጭት ከተፈጠረ ጀምሮ መንገዶች ሁሉ አስተማማኝ አይደሉም። ይህ ደግሞ ታላቅ ስጋት ነው።
ስለ ምን ቢሉ መንገድ ላይ እገታ እና ዘረፋ አለና። ብታገት በእኔ ላይ ከሚደርሰው ችግር ባለፈ ለቤተሰብ እዳ መኾንን ፈራሁ። እኔም በታጣቂዎች ተይዤ ዋጋ መክፈል የለብኝም።
ኾኖም መሄዴ ግድ ኾነብኝ። ረቡዕ ማለዳ አዘዞ መናኽሪያ ተገኝሁ። መናኽሪያ እንደተለመደው በተጓዦች ተጨናንቃለች። መኪና ውስጥ ገብቸ ተቀመጥኩኝ፤ ቀስ በቀስ መኪናው በተጓዦች ተሞላ።
ከመናኽሪያ ወጥተን ጉዞ ተጀመረ። ጠዳ ከተማን ካለፍን በኋላ የታጣቂ ኃይሎችን በመስጋት ሁሉም ስልኩን እና የእጅ ሰዓቱን መደበቅ ጀመረ። ስጋት፣ ጭንቀት እና ፍርሃት በሁሉም ልቦና ውስጥ አደረ። አሽከርካሪው ከባሕር ዳር ጎንደር የሚመጡ አሽከርካሪዎችን በመስኮት በኩል "መንገድ ሰላም ነው" እያለ ይጠይቃል። ሰላም ነው አይዟችሁ የሚል ምላሽም ሲሰጡትም ሰማሁ።
በዚህ መልስ እኔን ጨምሮ ሁሉም መንገደኞች በመጠኑ መረጋጋት አሳየን። በዚህ ጊዜ ነበር ከጎኔ ከተቀመጠው ወጣት ጋር ማውራት የጀመርነው። ጥቁር የሀዘን ኮፊያን አድርጓል።
ሰላምታ ተለዋወጥን። ምን አጋጥሞህ ነው ጥቁር የለበስከው ? አልኩት። በሃዘን ውስጥ ኾኖ እናቱን በሞት እንዳጣ ነገረኝ። ታመው ነበር? ቀብረህ እየተመለስከ ነው? ጥያቄዬን አከታተልኩበት።
የገጠመውን ያጫውተኝ ጀመር። እናቱን ለማስታመም ከባሕር ዳር ወደ ጎንደር በሚጓዝበት ወቅት በአጋጣሚ ከታጣቂዎች እጅ ወደቀ። መታወቂያው ሲታይ የመንግሥት ሠራተኛ በመኾኑ ከመኪና እንዲወርድ ተደረገ። ታጣቂዎችን እናቱን ለማስታመም እየሄደ መኾኑን እየነገረ ቢማጸናቸውም ሊራሩለት እንዳልፈቀዱ ነገረኝ። አግተው ወደ ጫካ በመውሰድ ለቤተሰቡ ደውለው አንድ ሚሊዮን ብር እንዲከፍሉ ጠየቁ። ገንዘቡ ካልተከፈለ ቀጥሎ የሚመጣው ሞት ነው።
አንድ ሳምንት ከታጣቂዎች ጋር በፍርሃት እና በጭንቀት ቆየ። ከማኅበረሰቡ ተለምኖ አንድ ሚሊዮን ብር ለታጣቂዎች ከተከፈለ በኃላ ተለቀቀ።
እናቱን ለማየት፣ አግኝቶ ለማስታመም ቸኩሏል። ዳሩ ያሰበው አልኾነም። ወደ እናቱ ቤት ሲደርስ እናት ልጇን ለሦስት ዓመታት ማየት እንደተመኘች፤ አቅፋ መሳም የልጅነት ጠረኑን ማሽተት እንደናፈቀች በሞት ተለይታ ነበር። በዚህም ምክንያት ሀዘኑ ከባድ እንደኾነ ዓይኖቹ እንባ እያቀረሩ ነገረኝ።
እናቱን ባለማስታመሙ፤ ወደ ሕክምና ባለማድረሱ፤ የእናቱ እቅፍ፤ የእናቱ ጉርሻ እንደናፈቀው፤ እሷን መጦር ውለታዋን በእንክብካቤ ለመመለስ እንደደረሰላት ሳይነግራት፤ የልጇን የድካሟን ፍሬ፣ ወግ፤ ማዕረግ ሳታይ በሞት በመለየቷ የእግር እሳት ኾኖ እየለበለበው መኾኑን በሃዘን ስሜት ነገረኝ።
ሰላም ቢኾን ኖሮ እናቱ ከመሞቷ በፊት ሊደርስ ይችል ነበር። ይህ አለመኾኑ ልቡን ሰብሮታል። የገጠመው ነገር የማይፋቅ የአዕምሮ ቁስል እንደኾነበትም አነሳልኝ። እርሱ ይሄን ታሪክ እየነገረኝ ዛሬስ መንገድ ላይ እንታገት ይኾን ወይስ ? በሰላም እንደርሳለን ? የሚለው ሃሳብ ሰቅዞ ይዞኛል። ልቤ በጭንቀት ተወጠረች።
እርሱስ በታገተበት መንገድ ድጋሜ መምጣት ምን የሚሉት ነው ? ተስፋ መቁረጥ ? አማራጭ ማጣት ወይስ ምንም አያመጡም የሚል ድፍረት ? በዚህ መንገድ ድጋሜ የመጣሁት የሀዘን ልብስ ስለለበስኩ ሲያዩኝ ልባቸው ይራራል በሚል እምነት ነው። ነገር ግን አሁንም ዋስትና የለኝም። ድጋሜ እንደማልታገት ግን ተስፋ አደርጋለሁ አለኝ።
አስተሳዝነው ዘንድ አቅም አጣሁ። ዝም ማለትን መረጥኩ። በክልሉ ውስጥ ባለው ግጭት ስንቶች እናታቸውን ሳያዩ ተነጠቁ ? ለአጋቾች መክፈል ያልቻሉ ስንቶች ተገደሉ? ስንቶች ሃብት ንብረታቸውን በታጣቂዎች ተዘረፉ? ቤት ይቁጠረው።
ወደ ራሴ ሃሳብ ተመለስኩኝ እኔስ በየብስ ጉዞ ማድረጌ ምን ፈተና ላይ ይጥለኝ ይኾን? እያልኩ ከውስጤ ጋር እየተወያየሁ ጉዞየን ቀጠልኩ። በአጋጣሚ በዕለቱ የሀገር መከላከያ ሠራዊት ከጎንደር ባሕር ዳር አሰሳ እያደረገ በመኾኑ በሰላም ባሕር ዳር መግባት ቻልን። ልጁን ተሰናብቸ ወደ ማረፊያየ አቀናሁ።
የመጣነውን መንገድ አሰብኩ። መቼ ነው ይህ እገታ፣ ዘረፋ እና ግድያ የሚቆመው? ሹፌሮች በነጻነት የትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጡበት፤ ነጋዴዎች ሸቀጥ ከቦታ ቦታ በነጻነት የሚያጓጉዙበት፤ ልጅ እናቱን በሰላም የሚጠይቅበት፤ እናትም ከዚህ ጭንቀት የምትገላገለው መቼ ይሆን? የሚሉ ጥያቄዎች አዕምሮየ ውስጥ ያለ እረፍት ተመላለሱ።
ያለ ሰላም ሁሉም ነገር ከንቱ ነው። ለሰላም በጋራ ካልሠራን ችግሩ ተራ እየጠበቀ በየቤታችን ይገባል። ሀዘኑም ለሁላችንም ይዳረሳል። ለሰላም በጋራ እንነሳ። በጋራ እንሥራ።
"ጊዜ ይፍታው" አይሠራም። ሰላም የሁሉም ነገር መሠረት በመኾኑ ለሰላም እንትጋ። የንጹሐን መንገላታት እና መታገት ይብቃ። ልጅ ከወላጆቹ፣ ወላጆችም ከልጆቻቸው ጋር በሰላም ይገናኙ።
ሰላም ለሁሉም!

👍3
ትናንት፣ ዛሬና ነገ
በሀገራችን ውስጥ በሚዛን ሊያዝ የሚገባው ሌላው ነገር በትናንት፣ በዛሬ እና በነገ መካከል ያለው ምልከታ ነው፡፡ ትናንትን ፈፅሞ የመቀደስም ሆነ ትናንትን ፈፅሞ የማርከስ ጉዞ ሀገርን ያለ ወረት ያስቀራል። ዛሬንና ነገን ማቃለልም ሆነ ዛሬና ነገን የሁሉም ነገር መጀመሪያ ማድረግ ሀገርን ያለ መነሻ ያስቀራል፡፡ ብልፅግና ትናንት ከዛሬና ከነገ ጋር በሚዛን የሚታይበትን መርሕ ይከተላል፡፡
• ከትናንቱ መልካሙን መውሰድ፤ እንከኑን ማረም
• ዛሬን፣ በትናንት መልካም መሠረት ላይ ገንብቶ በሚገባ መጠቀም
• ለነገ ተግባብቶ ወረት ማቆየት
ኢትዮጵያን ወደ ተምሳሌት ሀገር!
ብልፅግናን ይምረጡ!

የሀሳብ የበላይነት እንዲዳብር ፣ ኋላቀር የፓለቲካ ባህል እንዲከስም ብልፅግናን ይምረጡ
ፓርቲያችን ብልፅግና የሀሳብ የበላይነት እንዲዳብር፣ኋላቀር የፖለቲካ ባህል እንዲከስም፣ በኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ አዲስ ምዕራፍ የከፈተ ፣ ከአግላይነት ወደ አካታችነት የቀየረ ሀገርን በልውጥ ጎዳ ያፀና ፓርቲ ነው።
ፖሊሲዎች እና ውሳኔዎች በስሜት ሳይሆን በዕውቀት ላይ የተመሰረተ፣የፖለቲካ ፓርቲዎች የሚወዳደሩት በገንዘብ ወይም በብሔር ሳይሆን በተሻለ አማራጭ ሀሳብ እንዲቀርቡ የተሻለ ምህዳር መፍጠር የቻለ፣ሀሳቦች የሁሉንም ዜጎች ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ እንዲሆኑ ያደረገ ፓርቲ ነው።
ፓርቲያችን ብልፅግና የሀሳብ የበላይነት ያረጋገጠ የሰለጠነ ማህበረሰብ መፍጠር የቻለ ፣ ኋላቀር የፖለቲካ ባህልን በመቅበር ለትውልድ የምትተርፍ፣ የበለፀገች እና የተረጋጋች ኢትዮጵያን ለመገንባት በሀሳብ መሞገት እና የተሻለ አማራጭ ይዞ መቅረብ የቻለ ፓርቲ ነው።
ኢትዮጵያን ወደ ተምሳሌት ሀገር!
#ብልፅግናን_ይምረጡ
#ምርጫ_2018

👍2

#southwollozoneprosperity

👍1
የመጋቢት ፍሬ የደቡብ ወሎ ዞን አስተዳደር ቢሮ
👍6❤1
የመጋቢት ወር ፍሬ ለጋምቦ ወረዳ አስተዳደር ህንፃ!!
👍3❤1💯1
#ተመዝግበዋል?
የ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ሂደት በንቃት እየተከናወነ ይገኛል። የሀገርን ተስፋ ለማለምለም እና የዲሞክራሲ ስርዓትን ለመገንባት የመራጭነት ካርድ መውሰድ የመጀመሪያው እና ወሳኝ እርምጃ ነው።
ታዲያ እርስዎ ለሀገርዎ ድምጽ ለመሆን ተመዝግበዋል?
የዜግነት ግዴታዎን ለመወጣት እና የወደፊት እጣ ፈንታዎን ለመወሰን ዛሬውኑ በአቅራቢያዎ በሚገኝ የምርጫ ጣቢያ በመገኘት ይመዝገቡ። የእርስዎ ድምጽ ለሀገር ግንባታ ወሳኝ ነው!
#7ኛውጠቅላላምርጫ #የዜግነትግዴታ #ተመዝግበዋል #ኢትዮጵያ

❤1👍1
ለመላው ክርስትና ዕምነት ተከታይ፦
እንኳን ለብረሃነ ትንሳኤ በዓል በሰላም አደረሳችሁ አደረሰን!
በዓሉ የሰላም የፍቅርና የመከባበር እንዲሆን መለካም ምኞቴን እየገለጽኩ፡
ዘመን ተሻጋሪ የመልካም ትውልድ ተምሳሌት መሆን በሚያስችል የበዓል አከባበር ዘይቤ
እንደተለመደው ፍፁም ሰላማዊና ሃሴት የበዛበት በዓል ለማሳለፍ ሁሉም የበኩሉ ድርሻና ሃላፊነት ያለበት መሆኑን ተረድቶ ላካባቢው ዙሪያ መለስ ሰላምና ደህንነት በንቃት መጠበቅ አስፈላጊ መሆኑ ይታሰብ ።
አቶ አልየ ይመር፦
የለጋምቦ ወረዳ አስተዳዳሪ
ሚያዚያ/5018 ዓ.ም

👍3❤1
ለመላው ክርስትና ዕምነት ተከታይ በሙሉ እንኳን ለብረሀነ ተንሳኤው በሰላም አደረሳችሁ!!
በኣሉ የሰላም የጤና የፍቅርና ያብሮነት እንድሆን ምኞቴ ነው።
እንደሚታወቀው ታላላቅ ሃይማኖታዊ በኣሎች በመጡ ጊዜ ያንዱ ዕምነት ተከታይ ለሌላው እምነት ተከታይ ለበዓሉ ስኬታማነት ምቹ መደላድል በመፍጠር አብሮነቱን የሚገልፅበት እንዲሁም ማህበራዊ መስተጋብሩን የሚያንሼራሽርበት ታላቅ እሴት ባለቤት መሆናችን ልዩ መገላጭን ነውና!
በድጋሜ መልካም የፋሲካ በዓል ይሁንላችሁ!!
አቶ አበባው ሙህየ ፦
በብልፅግና ፓርቲ የለጋምቦ ወረዳ ቅ/ጽ/ቤት ሃላፊ

👍5❤1