[[ተምሳሌቶችሺን ሰለፎችሺን አስታዉሺ]]
6.64K subscribers
1.21K photos
661 videos
99 files
3.87K links
وَأَعْظَمُ مَا أَمَرَ اللَّهُ بِهِ التَّوْحِيدُ، وَهُوَ : إِفْرَادُ اللَّهِ بِالْعِبَادَةِ. وَأَعْظَمُ مَا نَهَى عَنْهُ الشِّركُ، وَهُوَ: دَعْوَةُ غَيْرِهِ مَعَهُ،
https://t.me/LetusfearAllah ጆይን በሉ
Download Telegram
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
الإستقامة لمن لا يعرف قيمتها :
لا خوف، لا حزن وموعد مع الجنة،
اللهم ارزقنا الإستقامة وثبتنا حتى نلقاك ..

•  القارئ:- عبدالله القرافي
🌟ፓስፖርት ለማውጣት ወይም ለማሳደስ የቀጠሮ መጥፋት ተቸግረዋል? እንግዲያውስ እኛ ጋር መፍትሄ አለ! ባሉበት ሆነው ያነጋግሩን፤ በታማኝነት እናገለግልዎታለን።

የምንሰጣቸው አገልግሎቶች፦
🚀 1. አስቸኳይ ፓስፖርት ለማውጣት
2. አዲስ ፓስፖርት ለማውጣት
🔄 3. ጊዜው ያለፈበትን ለማሳደስ (Renewal)
🔍 4. የጠፋብዎትን በምትክ ለማውጣት
🛠️ 5. ሌሎች ተያያዥ የፓስፖርት አገልግሎቶች

📞 በስልክ መስመሮቻችን ይደውሉልን፦
📱 09 55 55 76 77
📱 09 33 79 84 42

🌐 በሶሻል ሚዲያ ያግኙን፦
🔹 ቴሌግራም፦ https://t.me/mame8442
🔹 ዋትስአፕ፦ https://wa.me/qr/K7XXZ55DSMVYF1
🔹 ኢሞ፦ https://imo.onelink.me/7QOl/iso
🔹 ፌስቡክ፦ https://www.facebook.com/share/1C2fFtwN7d/

📢 ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት ግሩፖቻችንን ይቀላቀሉ፦
የቴሌግራም ግሩፕ፦ https://t.me/mame_online_service1
የፌስቡክ ግሩፕ፦ https://facebook.com/groups/711263511881888/

ጥራትና ታማኝነት መለያችን ነው! 🤝
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
🔹 ዑዝር ቢል'ጀህል [ክፍል 🌱🌱]

ስለ ዑዝር ቢል'ጀህል ከዚህ ቀደም በመልተቃ የቴሌግራም ግሩፕ በወንድም አቡ ዒምራን የተሰጡ ሙሐደራዎች የድምፅ ቅጅ በተሻለ ጥራት ተዛጋጅቶ በ youtube ቀርቧል። እነሆ ዛሬ ክፍል አንድን አጋራናቹህ በአላህ ፍቃድ ቀጣይ ሙሓደራዎችን በሂደት እንለቃለን።

ለመቀላቀል ⬇️⬇️⬇️
😎 youtube.com/watch?v=-SwNfSuHdf0&feature=shared
=
የቴሌግራም ቻናል
😎 https://t.me/d_fewaid
😎 https://t.me/d_fewaid
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
⚠️ ለ"online ኡስታዝ" ተብዬዎች የተላለፈ ከባድ ማስጠንቀቂያ!

ይህ በዲን ስም ለሚነግዱ፣ አደራ ለሚበሉና እህቶችን ለሚያውኩ "በሚዲያ ቁረአን እናቀራለን ለሚሉ ኡስታዞች" የተሰጠ ጠንካራ ማሳሰቢያ! —**

ቁርአን የልባችን ብርሃን፣ የነፍሳችን ምግብ እና የቂያማ ቀን አማላጃችን ነው። ይህንን ታላቅ የአላህ ቃል ማስተማር የነቢያት ቅርስ እንጂ የገንዘብ ማጋቢያ ወጥመድ አይደለም። ሆኖም ግን በቅርብ ጊዜ በሚዲያ ላይ "ኡስታዝ" የሚለውን ክቡር ስም ተገን አድርገው፣ የእህቶቻችንን አደራ የሚበሉና የዲን ንግድ ውስጥ የገቡ ጥቂት ግለሰቦች የብዙ እህቶቻችንን ህይወት እያመሰቃቀሉ ይገኛሉ።

ዛሬ የምናነሳው ጉዳይ የብዙ እህቶቻችንን ልብ የሰበረ፣ የእምነት ጥንካሬያቸውን የፈተነና በዝምታ የታለፈ ትልቅ ጠባሳ ነው። ቁርአን መቅራትና ማቅራት የነቢያት ታላቅ ቅርስ እንጂ፣ የሰው ኪስ ማድረቂያ ወይም የሴቶች መጀንጀኛ ድልድይ አይደለም። ሆኖም ግን፣ "ኡስታዝ" የሚለውን ክቡር ስም ተገን አድርገው፣ በአላህ ቃል ስም የሚነግዱ ጥቂት ግለሰቦች የኡማውን ክብር እያቆሸሹ ይገኛሉ።

📍 ለእነዚህ "ኡስታዞች" የቀረበ ግልጽ መልፅክት!

1. "ታማኝነት" (አማና) የት ሄደ?
አንዲት እህታችን ቁርአን ልቅራ ብላ ከፊታችሁ ስትቀመጥ፣ እናንተ በስልካችሁ ቻት የምታደርጉ፣ የት ላይ እንደደረሰች የማታውቁ፣ ስህተቷን ሳታርሙ "ማሻአላህ" እያላችሁ የምታሳልፉ ሰዎች ሆይ— አላህን አትፈሩም? ይህቺ እህት ቁርአን መማር የፈለገችው ከአላህ ጋር ለመገናኘት ነው፤ እናንተ ግን በዝንታችሁና በቸልተኝነታችሁ በአላህና በእሷ መካከል ግርዶሽ ሆናችኋል።

2. የድሆችን እና የቤተሰብን ሀቅ አትብሉ!
ብዙዎቹ እህቶቻችን ቤተሰቦቻቸው በረሃብ እየተሰቃዩ፣ ካለቻቸው ጥቂት የቀን ገቢ ላይ ቀንሰው ነው ለእናንተ ክፍያ የሚከፍሉት። የአራት እና የአምስት ወር ክፍያ ቀድማችሁ ተቀብላችሁ፣ ግማሽ ሱራ ሳታቀሩ "በቃሽ" ብላችሁ የምታባርሩ ሰዎች— ይህ የምትበሉት ብር ለእናንተም ሆነ ለቤተሰባችሁ "ሀራም" (የእሳት ሲሳይ) እንጂ በረካ አይሆንም። ስራውን በአግባቡ ሳትሰሩ የምትቀበሉት እያንዳንዱ ሳንቲም በቂያማ ቀን ይጠየቅባችኋል።

3. "ኡስታዝነት" የሴቶች መጀንጀኛ ዘዴ አይደለም!
በዲን ስም ተሸሽጋችሁ፣ በውስጥ መስመር (Inbox) እየገባችሁ የተማሪዎቻችሁን ስነ-ልቦና የምትሰርቁ፣ ከአላማቸው የምታዘናጉና ክብራቸውን የምትነኩ ግለሰቦች ሆይ— የቁርአን መምህርነት ስም አይገባችሁም! እናንተ የዲን ተኩላዎች እንጂ መሪዎች አይደላችሁም። የሙስሊም ሴቶች ክብር የአላህ አደራ መሆኑን አትርሱ።

💡 ተማሪ እህቶቻችን ምን ማድረግ አለባቸው?

እህቴ ሆይ! በአላህ መንገድ ላይ የሚደርስብሽ መከራ ሁሉ ምንዳ አለው። ነገር ግን አትታለዪ፦

ይህ በደል የብዙዎች መሆኑን እንረዳለን፤ ነገር ግን ዝምታው ሊበቃ ይገባል። ብራችሁንም ጊዜያችሁንም እንዳትበዘበዙ የሚከተሉትን ጥንቃቄዎች አድርጉ፦

*   🚩 ሴት መምህራንን (ኡስታዛቶችን) ፈልጉ፦ ከወንድ ጋር ከመቀራት ይልቅ እውቀቱና ተቅዋው ያላቸውን ሴት መምህራን መፈለግ ለዲናችሁም ለክብራችሁም አስተማማኝ ነው።
*   🚩 ለክፍያ አትቸኩሉ፦ ምንም አይነት አስተማማኝ ማስረጃ ሳይኖራችሁ የብዙ ወር ክፍያ በአንዴ አትክፈሉ። ጥራቱን እያያችሁ በየወሩ ክፈሉ።
*   🚩 ድምፃችሁን አውጡ፦ በደል ሲደርስባችሁ ዝም አትበሉ። ለሌሎች እህቶች ንገሩ፣ አጋልጡ። ዝምታችሁ ሌላ እህት ለተመሳሳይ በደል እንድትዳረግ በር ይከፍታል።
*   🚩 የታወቁ መርከዞችን ምረጡ፦ በግለሰብ ደረጃ "አቀራለሁ" ከሚሉ ይልቅ ተጠያቂነትና ክትትል ባለባቸው ታዋቂ የኦንላይን መርከዞች መመዝገብ ብክነትን ይቀንሳል።


#### ⚠️ ከጉዳዩ በስተጀርባ ያሉ ተጨማሪ አደጋዎች

ይህ ችግር ከገንዘብ ብክነት ባለፈ የሚከተሉትን አደጋዎች ይዞ መጥቷል፦
*   የእምነት መላላት፦ እህቶች በእነዚህ ሰዎች ምክንያት መላውን የሃይማኖት መምህራን በጥርጣሬ እንዲያዩና ከዲን ትምህርት እንዲርቁ ያደርጋል።
*   የቁርአን ስርአት መበላሸት፦ ስህተት ሳይታረም "ማሻአላህ" እየተባለ የሚታለፍ ከሆነ፣ ትውልዱ ቁርአንን በተሳሳተ መረጃና አቀራር እንዲይዝ ያደርጋል።
*   የዳዕዋው ዘርፍ መርከስ፦ በዲን ስም የሚነግዱ ሰዎች በበዙ ቁጥር፣ እውነተኛዎቹና አላህን የሚፈሩ ኡስታዞች ስማቸው አብሮ እንዲጠፋ ያደርጋል።

📢 የመጨረሻ መልዕክት!

እውነተኛ አላህን የሚፈሩ፣ ሌት ተቀን የሚያቀሩ፣ የሰውን ገንዘብ የማይመኙ ምርጥ ኡስታዞች አሉን፤ አላህ ያብዛቸው፣ ይጠብቃቸውም። ነገር ግን እነዚህን ጥቂት በዝባዦች ማጋለጥና መገሰጽ የሁላችንም ግዴታ ነው።

አንቺ የተበደልሽ እህቴ ሆይ! አላህ ላወጣሽው ወጪና ለደከምሽው ድካም ምንዳሽን ይክፈልሽ። በእነዚህ መጥፎ ሰዎች ምክንያት የቁርአንን መንገድ እንዳትተዪው፤ አላህ የተሻለ መምህር ይወፍቅሻል።

"እናንተ ያመናችሁ ሆይ! አላህን ፍሩ፤ ከእውነተኞቹም ጋር ሁኑ።" (አል-ተውባህ፡ 119)
t.me/Abu_hibetillah_Asselfiy
t.me/Abu_hibetillah_Asselfiy
👍1
[[ተምሳሌቶችሺን ሰለፎችሺን አስታዉሺ]] pinned «⚠️ ለ"online ኡስታዝ" ተብዬዎች የተላለፈ ከባድ ማስጠንቀቂያ! ይህ በዲን ስም ለሚነግዱ፣ አደራ ለሚበሉና እህቶችን ለሚያውኩ "በሚዲያ ቁረአን እናቀራለን ለሚሉ ኡስታዞች" የተሰጠ ጠንካራ ማሳሰቢያ! —** ቁርአን የልባችን ብርሃን፣ የነፍሳችን ምግብ እና የቂያማ ቀን አማላጃችን ነው። ይህንን ታላቅ የአላህ ቃል ማስተማር የነቢያት ቅርስ እንጂ የገንዘብ ማጋቢያ ወጥመድ አይደለም። ሆኖም ግን በቅርብ…»
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
🔔ልዩ የሙሓደራ እና የንያ ፕሮግራም


ለወሎ ዩኒቨርሲቲ ጢጣ ጤና ካምፓስ ለሚገኙ ሙስሊም ተማሪዎች ከ 2017 ጀምሮ እየሰሩት ያለዉን መስጅድ ከረመዳን በፊት በጋራ እንጨርስ

በፕሮግራሙ ተጋባዥ እንግዶች :-
  ↶↶↶↶↶↶↶↶↶↶

🎙ኡስታዝ አብዱረዛቅ ባጅ

🎙ኡስታዝ አቡ ሀሳን

🎙ወንድም አቡ  ሂበቲላህ


የፕሮግራሙ መሪ :
🎙ኡስታዝ ኡስማን አቡ አመቲረህማን

┌─────────┐
📆│ ቅዳሜ ማታ
╰─────────╯


⏰️🇪🇹☞በኢቲዮ 3:00
⏰️🇸🇦☞በሳኡዲ 9:00
⏰️🇦🇪☞በዱባይ 10:00


https://t.me/alruqyehsheriyeh
ትዳሬ ለምን ዘገየ!?

➡️አውቃለሁ፤ አንዳንድ ጊዜ የጥበቃው ሰዓት ሲረዝም፣ በዙሪያሽ ያሉ እኩዮችሽ የራሳቸውን ጎጆ ሲቀልሱ ስታይ፣ ልብሽ ውስጥ የሚፈጠረውን ስሜት አላህ ያውቃል። ነገር ግን አንድ ነገር ልንገርሽ፤ የዘገየው ነገር ሁሉ የቀረ አይደለም፤ የዘገየው አላህ ባንቺ ልክ፣ ለልብሽ በሚመጥንና ለአኺራሽ በሚበጅ መልኩ እያሰናዳው ስለሆነ ነው።

ይፍጠንም ይዘግይ፤ እርግጠኛ ነኝ ያሰብሽው ዓይነት፣ በሱጁድ ወርደሽ ያለቀስሽለት ዓይነት፣ «ጌታዬ ሆይ እንዲህ ያለውን ስጠኝ» ብለሽ የተመኘሽው ዓይነት አጋር አላህ ይሰጥሻል። የጌታሽ ካዝና አይጎድልም፤ ጊዜው ሲደርስ "ሁን" ይለዋል፤ ይሆናል።

ውድ እህቴ... ዐይንሽን ከአላህ ላይ አትንቀይ። የልብሽን መልሕቅ በረብሽ ላይ ጣይው።  የዘገየው ባንቺ ላይ ካለው ክፋት ሳይሆን፣ ለአንቺ ካለው የእዝነት ጥበብ የተነሳ ነው። ስለዚህ መልካም ጥርጣሬሽን ንፋስ አይግባው። «ለምን ዘገየ?» የሚለው የሸይጧን ሹክሹክታ ኢማንሽን፣ ተወኩልሽንና ያቂንሽን  እንዲፈታተነው አትፍቀጂ።

ያ የለመንሽው ዱዓ አየር ላይ አልቀረም፤ አላህ እየሰማሽ ነው።  አሁንም በፊት እንደምታስቢው፣ በፊት እንደምትመኚው አድርገሽ አስቢ። ተስፋሽን አዳብሪ። አላህ ነገ በተባረከ ትዳር፣ የዲን መሰረት ባለው ቤተሰብ፣ በሱና በደመቀች ጎጆ እንደሚክስሽ አስቢ።

የአላህ ውሳኔ ሁሌም ከምኞታችን በላይ ውብ ነው። ትዕግስትሽ ጣፋጭ ነው፤ ፍሬውም ያማረ ይሆናል። አንቺ ብቻ ከደጃፉ አትጥፊ፤ ዱዓሽን አታቋርጪ። ያሰብሽውን፣ የተመኘሽውን፣ ለዱኒያም ለአኺራሽም የሚሆነውን የልብ ወዳጅ አላህ በቅርቡ ያምጣልሽ።

አላህ የልብሽን መሻት ያሳካ፤ ሷሊህ የሆኑ ልጆች አባት ከሆነ ምርጥ ባሪያው ጋር ያጣምርሽ። አሚን!

🖋ወንድምሽ አቡ ሱፍያን
t.me/AbuSufiyan_Albenan
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
👍4
☹️🙁☹️😣😝☹️☹️😣
✔️የአረብኛ እና የእንግሊዝኛ ቋንቋ
      ትምህርት  ለመማር ፍላጎት ላላችሁ

ኢህሳን የonline የቋንቋ ት/ቤት 
ውድድር ስላዘጋጁ ገብታችሁ መወዳደር ትችላላችሁ

የውድድሩ ማብራሪያ ⭐️
t.me/Ihsan_language/223
t.me/Ihsan_language/223
😣☹️🙁☹️🙁😶‍🌫️😣🥳
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
Forwarded from Abu Zekeriya #1
ኢናሊላሒ ወኢና ኢለሂ ራጂኡን

በቅርቡ ማንነቱ ባልታወቀ ሰው ተገድላ ወደ አኼራ የሄደችው እሕታችን ዙልፋ ናስር  ወንድም የሆነው በደረሰበት ሕመም ምክንያት እሱም ወደ ማይቀረው አለም ሔዶዋል
በእህቱ መሞት ብዙ የተሰቃየው እና በሐዘን የተጎዳው ወንድማችን በደረሰበት የእህቱ መሞት ዜና የሐዘን ዜና ስቃይ በጣም በመጎዳቱ የተነሳ በሕመም ተዳርጎ መሞቱን ነው ዛሬ የደረሰኝ

መረጃውን ዛሬ አንድ መንድማችን ነው ደውሎ ያሳወቀኝ

ሟች ወንድማችን የእሕቱን ስራ ለማስቀጠል እቅስቃሴ ላይ የነበረ ወንድማችን ነበር የአላህ ውሳኔ ሆኖ አጀል ቀድማዋለች

ለ 2ቱም ወንድም እና እህት በድዓ አግዧቸው


ወንድማቹህ አቡ ዘከሪያ
https://t.me/Abuzekeriya01